You are on page 1of 4

የጤና ወግ

የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ካንሰሮች አንዱ ነው። በአለም አቀፍ ሁኔታ በሴቶች
ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች የጡት ካንሰር በ 1 ኛ ደረጃ ይቀመጣል።

የጡት ሴሎች (ህዋሶች ) ከተለመደው ወጣ ባለ እና ጤናማ ባልሆነ መልኩ ሲያድጉ እና ሲባዙ


ይፈጠራል ።

የጡት ካንሰር በአብዛኛው የሚከሰተው በሴቶች ቢሆንም በወንዶች ላይም ሊከሰት ይችላል።

1. የጡት ካንሰር አጋላጭ ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?

የጡት ካንሰር በቅርብ ቤተሰብ መኖር


ለራዲዬሽን (ጨረር ) መጋለጥ
ሲጋራ ማጨስ
አልኮል መጠጣት
ከፍተኛ ውፍረት
ለኤስትሮጅን ሆርሞን ለረጅም ጊዜ ተጋላጭ መሆን – ማለትም
-የወር አበባ በልጅነት መጀመር ( ከ12 አመት በታች ) እና እስከ ረጅም እድሜ መቆየት ( ከ
55 አመት በላይ)
-ከማረጥ በኋላ የሆርሞን እንክብሎችን መውሰድ
-ልጅ አለመውለድ ወይም የመጀመሪያ እርግዝና ከ30 አመት በኋላ መሆን

2. የጡት ካንሰርን ለመከላከል ምን ማድረግ ይቻላል?

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ


ክብደትን መቆጣጠር
የከብት ስጋ አለማዘውተር
ሲጋራን አለማጨስ

3. የጡት ካንሰር ምልክቶች ምንድን ናቸው

የጡት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል እብጠት


የጡት ቆዳ መሰርጎድ
የጡት ጫፍ ወደውስጥ መገልበጥ
በብብት ስር የንፍፊት እብጠት
የጡት ፈሳሽ (ከወተት ውጪ)

4. በጡቴ ላይ ያሉ ለውጦችን ለማወቅ ምን ማድረግ አለብኝ ?

ራስን በራስ ጡትን በመዳሰስ እብጠት መኖር አለመኖሩን መመርመር


Adver tisement

ልብ በይ

ጡት ላይ እብጠት ካለ ህመም ባይኖረውም እንኳን ሃኪም ማየት ያስፈልጋል።


ይህ በህክምና ተቋማት በህክምና ባለሞያዎች የሚደረግ ምርመራን ስለማይተካ ቅድመ
ምርመራዎችን በእጅ የሚዳሰስ እብጠት ባይኖርም እንኳን ማድረግ ያስፈልጋል ።( በእጅ
በመዳሰስ ለመለየት የማይቻል እብጠት እና ጤናማ ያልሆነ እድገት ሊኖር ስለሚችል)

5. የጡት ካንሰር ምርመራ አለው?

አዎ ። የጡት ካንሰር ካንሰር መኖር አለመኖሩን ለማወቅ፣ ካለም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለማግኘት
የሚያስችሉ ምርመራዎች አሉ።

6. የጡት ካንሰር መፈተሻ ምርመራዎች ምንድን ናቸው ?

ማሞግራፊ

ከአርባ አመት በላይ ያሉ ሴቶች በየአመቱ የማሞግራፊ ምርመራ ማድረግ አለባቸው

እንደየአስፈላጊነቱ ሌሎች ምርመራዎችም ሊደረጉ ይችላሉ።

7. የጡት ካንሰር ህክምና አለው?

አዎ። የህክምናው አይነት እንደ ካንሰሩ አይነት ይወሰናል

በዶ/ር ማህሌት አለማየሁ


ትዊተር: @MahletAlemayeh7
ምንጭ: https://www.cancer.gov/types/breast/patient/breast-screening-
pdq

Advertisements

REPORT THIS AD

Fitsum T. Hailemariam February 19, 2020 የሴቶች ጤና


#Breastcancer, #evidencebasedmedicine, #womenhealth, #yetenaweg,
Ethiopia
Published by Fitsum T. Hailemariam
Transplant Nephrologist at Thomas Jefferson University Hospital View
more posts

የጤና ወግ, Blog at WordPress.com.

You might also like