Professional Documents
Culture Documents
Kintarot
Kintarot
ውድ የሳይቴክ ቤተሰቦች… በመልዕክት መቀበያችን በተደጋጋሚ ስለ ኪንታሮት መረጃ ይዘንላችሁ እንድንመጣ በጠየቃችሁን መሰረት እነሆ ጊዜው ደርሶ ዛሬ
ይዘንላችሁ መጥተናል፡፡ ይህ መረጃ በዚህ ችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች ይደርስ ዘንድ በቅድሚያ ሼር ብታደርጉትና ወደ ንባብ ብትገቡ ደስ ይለናል፡፡ መልካም ንባብ…
የቂጥ ኪንታሮት ሠገራን በምናስወገድ ጊዜ ከማማጥ ወይንም በእርግዝና ጊዜ በሚከሰት የደም ስሮች ላይ የሚገኝ ግፊት ምክንያት የሚመጣ ሲሆን በሁለት መልኩ
ይከፈላል፡፡
1) ውስጣዊ ኪንታሮት (internal hemorrhoid) በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኝ
2) ውጫዊ ኪንታሮት (external hemorrhoid) በላይኛው ቆዳ ላይ የሚገኝ
ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰት ሲሆን በተለይ ዕድሜያቸው 50 ዓመት የሞላቸው ሰዎች ላይ በስፋት (ግማሽ በሚሆን ደረጃ) የኪንታሮት ምልክቶች እንደሚያዩ
ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ በቤት ውስጥ ሕክምና እና የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ በማድረግ ይድናሉ፡፡
✔ የኪንታሮት ምልክቶች
• ሕመም የሌለው ከፊንጢጣ የሚፈስ ደም
• በሰገራ መውጫ አካባቢ ማሳከክ
• ሕመም ወይንም አለመመቸት
• በፊንጢጣ አካባቢ እብጠት ናቸዉ፡፡
ወይም
--------------------------------------------
ምንጭ - ማህደረ ጤና እና ዶ/ር ሆነልያት