Professional Documents
Culture Documents
Amharic - Inclusive Response To COVID-19 at The Household Level - 10920
Amharic - Inclusive Response To COVID-19 at The Household Level - 10920
ፕሮጀከት (ኮዋሽ)
አዲስ አበባ
አካል ጉዳተኛ (በተለይም ሩቅ በሆኑ ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩት) በጣም ተጋላጭ የሆኑ እና ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ
ምለሽ ለመስጠት/ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የሚረሱ/የሚዘነጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ በማህበረሰብ
ደረጃ፣ በትምህርት ቤቶች እና በጤና ተቋማት አካባቢ የሚከናወኑ ተግባራት አካታች (አካል ጉዳተኞችን ግምት ውስጥ
ያስገቡ) እየሆኑ እየመጡ ቢሆንም በቤተሰብ ደረጃም ሊሰሩ የሚገቡ ብዙ ተግባራት ያስፈልጋሉ፡፡ አብዛኞቹ አካል ጉዳተኛ
የሆኑ ልጆች ትምህርት ቤት የማይሄዱ/ከትምህርት የተገለሉ እና በቤት ውስጥ የተቀመጡ ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ አጭር
ማስታወሻ በቤተሰብ ደረጃ ሊከናወኑ ስለሚገባቸው ተግባራት እና የማህበረሰቡ አባላት በቤተሰብ ደረጃ የኮሮና ቫይረስን
ስርጭት እና በቫይረሱ መያዝን ለመቀነስ እንዲሁም የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት በቫይረሱ ከተያዙ ምን ማድረግ
እንዳለብን የሚጠቁም ነው፡፡
አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የኮዋሽ ፕሮጀክት ትኩረት የሚያደርግባቸው ዋናዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡
- አካል ጉዳተኞች የሉበትን እውነታ (ያለባቸው የአካል ጉዳት አይቶችን) መሰረት ባደረገ መልኩ
መልእክቶች/መረጃዎች እና የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ተቋማት ላይ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
- የውሃ ንጽህናና ሀይጅን አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለአካል ጉዳተኞች አካል ጉዳት አልባ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች
እኩል ተደራሽ እንዲሆኑና እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ፡፡
- አካል ጉዳተኞች ተገማች ከሆኑ ጎጂ ስጋቶች ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ ናቸው፡፡
አካል ጉዳተኞች በሚከተሉት ምክንያቶች ለኮሮና ቫይረስ በጣም ተጋልጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡:
- የተወሰኑት አካል ጉዳተኞች በኮሮና ቫይረስ ቢያዙ ለከፋ ህመም የመጋለጥ ከፍተኛ አስጊ ሁኔታ ላይ ስለሚገኙ፡፡
ለዚህም ምንክያቹ ስር የሰደደ ጉዳት መኖር ወይም የደከመ በሽታን የመከላከል አቅም መኖር ይገኙበታል፡፡
- የተወሰኑ አካል ጉዳት አይነቶች አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ አስቸጋሪ ስለሚሆኑ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በቤተሰብ አባል
ወይም በሌሎች ተንከባካቢዎች እገዛ የሚንቀሳቀሱትን የአካል ጉዳተኞች ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም አንዳንድ
የአዕምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች የአካላዊ ርቀትን አስፈላጊነት ላይረዱ ይችላሉ፡፡
- እንዳንድ አካል ጉዳተኞች መሰረታዊ የግል ንጽህናን ለመጠበቅ ያለመቻል ተግዳሮቶች ሲኖርባቸው፤ አንዳንዶች
ደግሞ የፊት ጭምብል/ማስክን በአግባቡ የመጠቀም ተግዳሮቶች ሊኖሩባቸው ይችላሉ፡፡
- አብዛኘውን ጊዜ በገጠር አካካቢ ለሚኖሩ ቤተሰቦች የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ተቋማት የእንቅስቃሴ ወይም
የእይታ ችግር ላለባቸው ሰዎች ተደራሽ አይሆኑም፤ በዚህም ምክንያት አስፈላጊውን የግል ንጽህና ለመጠበቅ
አለመቻል ናቸው፡
2
-
የኮሮና ቫረስን ስርጭት ለመግታት በቤተሰብ ደረጃ የሚከተሉት ሶስት ተግባራት መከናወን አለባቸው፡፡
በጣም አስፈላጊ የሆኑት መረጃዎች ስለጤና እና የግል ንጽህና አጠባበቅ፣ በቫይረሱ የመያዝ እድልን/አደጋን ስለመቀነስ፣
ወይም የበሽታውን ስርጭተት ለመግታት በማህበረሰቡ አካባቢ የተጣሉ እገዳዎች ካሉ (ለምሳሌ፣ ስብሰባን አለማድረግ
ወይም ጎረቤት ለጎረቤት በአካል አለመቀራረብ/አለመገናኘት) የመሳሰሉት ናቸው፡፡ እነዚህ መረጃዎች ለማህበረሰቡ በወረዳ
እና በቀበሌ ባለሙያዎች፣ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ጣቢያና በጤና ኬላ ባለሙያዎች እና በጤና ኤክስቴንሽን
ሰራተኞች መሰራጨት/መሠጠት አለባቸው፡፡ መረጃው በአካል ጉዳተኛው ተንከባካቢ ወይም ረዳት ቀጥታ ሊሰጥም
ይችላል ምክንቱም ግለሰቡ ካለበት የአካል ጉዳት አንጻር አግባብበት ያለውን መረጃ የመስጠት ዘዴ ስለሚያውቅ እና
በቀላሉ ሊግባቡ ስለሚችሉ ነው፡፡ በአካባቢው የሚገኙ ከሆነም የአካል ጉዳተኛ ማህበራት በተለይም የመስማት፣ የእይታ
እና የአዕምሮ ጉዳት ላለባቸው አባሎቻቸው አስፈላጊውን መረጃ ቀጥታ መስጠት ይችላሉ፡፡
ቫይረሱን በተመለከተ ቁልፍ የሆኑ መልእክቶች እና እንዴት መከላከል እንድምችል የሚያሳዩ ምስሎች በእዝል
1 ላይ ቀርቧል፡፡
3
አንደማንኛውም የማህበረሰብ ክፍል አካል ጉዳተኞችም ከሌሎች ሰዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡
አንዳንድ አካል ጉዳተኞች በእያንዳንዱ የህይወት አንቅስቃሴያቸው ረዳቶች ስለሚስፈልጋቸው አካላዊ ርቀትን መጠበቅ
አይችሉም፡፡ በገጠር አካባቢ የቤተሰብ አባላት አስፈላጊ በሚሆንበት ጌዜ አካል ጉዳተኞችን ማገዝ የተለመደ ነው፡፡ በተቻለ
መጠን የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ እገዛውን እንዲያደርጉ ማድረግ እና እገዛውን በሚያደርጉበት ወቅትም
ማስክ/ጭምብል እንዲጠቀሙ ቢደረግ ጥሩ ነው፡፡ በየአካባቢው የማህበረሰብም ስብሰባዎች መደረግ አይኖርባቸውም፡፡
ትምህርት ቤቶች ከተከፈቱና ልጅዎን ለቫይረሱ ሊያጋልጡ የሚችሉ (ለምሳሌ አስም/ለመተንፈስ የሚያስቸግር በሽታ)
ወይም ሌሎች የቫይረሱ ምልክቶች ያልታየባቸው አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት
መሄድ አለባቸው፡፡ ልጅዎ የግል ንጽህናን በጥሩ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚቸገር ወይም አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ የሚቸገር
ከሆነ የቤተሰቡ አባል/ተንከባካቢ/መምህር ልጆን በትምህርት ቤት ውስጥ መርዳት አለባቸው፡፡ ይህ የማይቻል ከሆነ፣
ልጅዎ በቤት ውስጥ በወንድሞቹ እና በእህቶቹ እንዲታገዝ መደረግ አለበት፡፡
የቤተሰብ አባልም ሆነ ሌሎች የአካል ጉዳተኛው ረዳቶች ቫይረሱን በመፍራት ለአካል ጉዳተኛው የሚያደርጉትን
አገዛ ማቆም የለባቸውም ምክንያቱም ይህ ድርጊት በአካል ጉዳተኛው ህይወት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ
ስለሚኖረው ነው፡፡ ነገር ግን የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ የተለያዩ የጥንቃቄ እርምጃዎች መወሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
ከእርምጃዎቹ ዋና ዋናዎቹም፡-
- በተቻለ መጠን የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ እገዛ/እርዳታ እንዲያደርጉ፣
- እገዛ/እርዳታ/ የሚያደርጉ ሰዎች ከሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች/ሰዎች አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቁ እና
እንዲጠነቀቁ፣ እጆቻቸውን በመታጠብ የግል ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ፣ እና በተቻለ መጠን ማስክ/ጭምብል
እንዲጠቀሙ፣
- እገዛ/እርዳታ የሚያደርጉ ሰዎች በአካባቢው ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች መገኘት አይኖርባቸውም
(ለምሳሌ ቤተ ክርስቲያን፣ መስጊድ)፡፡ እገዛ/እርዳታ የሚያደርገው ግለሰብ ተማሪ ከሆነ ትምህርት ቤት መሄዱን
ሳያቆም አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ በትምህርት ቤት ባለበት ወቅት የእጅ ማታጠብን እንደሁም ሌሎች የግል
ንጽህናዎችን መጠበቅ አለበት፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት፣ የአካል ጉዳተኛው የቤተሰብ አባል ወይም ረዳት ለአካል ጉዳተኛው የሚከተሉትን
አገዛዎች ማድረግ አለበት፡፡ አካል ጉዳተኛው፡-
- የመከላከል ተግባራትን አንደ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና የግል ንጽህናን መጠበቅ የመሳሰሉትን
እንዲጠቀም/ተግባራዊ እንዲያደርግ ማገዝ፣
- አንዳንድ የበሽታውን/የኮሮና ቫይረስ/ምልክቶች ካሳየ የምርመራ እና የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ማገዝ፣
- ግለሰቡ ስለበሽታው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንዲረዳ ማገዝ (ለምሳሌ በእዝል 1 ላይ የታዩት)፣
- አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት የተለመደውን የህክምና ድጋፍ/አገልግሎት እንዲያገኙ ማገዝ፣
- ለራሱ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የመመገቢያ እቃዎች እንዲኖሩት፣ እንዲሁም የመኝታ ልብሶችን እና ሌሎች
ልብሶችን ለብቻቸው በማጠብ ማገዝ፣
- አካላዊ እና አዕምሮአዊ ጤንነቱ እንዲጠበቅ እንዲሁም ደስተኛ እንዲሆን እና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማው
ማገዝ ናቸው፡፡
በተቻለ መጠን፣ በአካባቢው እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቀት (ለምሳሌ ሱቆች ወይም የውሃ ተቋም በሚሄዱበት ወቅት)
የፊት ማስክ/ጭምብል መጠቀም አለባቸው፡፡ አንዳንድ አካል ጉዳተኞች ካለባቸው የአካላዊ፣ የጤንነት እና ባህሪያዊ
ምክንያቶች አንጻር ማስኮችን በአግባቡ ማድረግ አይችሉም፡፡ እነዚህ አካል ጉዳተኞች ከእነሱ ጋር ከሚኖሩ የቤተሰብ
አባሎቻቸው ውጭ ካሉ ሰዎች አካላዊ ርቀቶቻቸውን መጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው/ይኖርባቸዋል፡፡
መላ ቤተሰቡን በተለይም አካል ጉዳተኛ የቤተሰብ አባላትን ከበሽታው እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል የሚያሳዩ
መሰረታዊ ሂደቶች ስዕላዊ በሆነ መልኩ በእዝል 1 ላይ ይታያሉ፡፡
4
3. ለዓይነ ስውራን እና የእንቅስቃሴ ችርግ ላለባቸው የአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆኑ የውሃ፣ ንጽህና ሀይጅን
አገልግሎትና ተቋማት (ንጽህና መጠበቂያ፣ ለመታጠቢያ አገልግሎት፣ለመጠጥ አገልግሎት) - እዝል 3
አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ከበሽታው እንዲከላከሉ/እንዲጠብቁ እና የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ማንኛውም በቤት
ውስጥ የሚገኝ የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን አገልግሎት መስጫ ተቋማት (የመጠጥ ውሃ፣ የእጅ መታጠቢያ፣ የገላ መታጠቢያ
እና መጸዳጃ ቤት) ተደራሽ መሆን አለባቸው፣ በተቻለ መጠንም ካለ ሌሎች ረዳት በራሳቸው ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ
መሆን አለባቸው፡፡ ለወረርሽኙ ምላሽ ለመስጠት በምናስብበት ወቅት ይህ ጉዳይ አስፈላጊ የሚሆነው ለግለሰቦች ብቻ
ሳይሆን ለሁሉም ቤተሰብ እና ለአካባቢው ማህበረሰብም ጭምር ነው፡፡
ተደራሽነት ማለት አንድን የአገልግሎት ሰጪ ተቋም ለመጠቀም መምረጥ፣ መቅርብ/መድረስ ወይም መጠቀም ነው፡፡
የእንቅስቃሴ ውስንነት ላለባቸው ሰዎች ፍላጎታቸው እንደየአካል ጉዳቱ ዓይነት ይወሰናል (የእጅ፣ የእግር፣ የጀርባ ወዘተ.)፡
፡ በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ቤተሰብ በቤተሰብ ደረጃ ያለውን የመጸዳጃ ቤት እንደየ ግለሰቡ የአካል ጉዳት ሁኔታ
ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡ ነግር ግን፣ በጣም አስፈላጊው ጉዳይ መጸዳጃ ቤቱ/እጅ መታጠቢያው/የመጠጥ ውሃ አገልግሎት
መስጪያዎች ከቤቱ መራቅ የለባቸውም፣ ወደ አገልግሎት መስጫ ተቋሞቹ የሚወስደው መንገድ የተስተካከለ፣
እንዲሁም አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ ለመጠቀም ቀላል እና ምቹ መሆን አለበት፡፡ አስፈላጊ ከሆነ፣ ለምሳሌ መንሸራተቻ
/ramp/፣ የእጅ ድጋፍ /hand rails/፣ በቀላሉ የሚከፈትና የሚዘጋ በር /easy to operate door/ ፣ በጣም ክፍም ሆነ ዝቅ
ያላሉ የውሃ መዝጊያና መክፈቻ ፎሴቶች /taps that not too high or low/፣ ከፍ ያለ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ /raised
seat in the latrine/ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ለአይነ ስውራን/የእይታ መጠናቸው በጣም ለቀነሰ ሰዎች መሪ ገመድ /guiding
rope/ ወይም ሌሎች አጋዥ ምልክቶች መጠቀም በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ለእጅ መታጠቢያ የሚያገለግሉ ቁሶች እንደ
ሳሙና፣ የእጅ እጣቢ ውሃ ማጠራቀሚያ ባሊ ወዘተ… አይነ ስውራኑ በቀላሉ ሊያገኟቸው እና መጠቀም እንዲችሉ
በመጸዳጃ ቤቱ አቅራቢያ መቀመጥ አለባቸው፡፡
ሁሉም ቤተሰቦች ለሴቶች እና ለልጅ አገረዶች የወር አበባ ንጽህና አጠባበቅ ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡ በተቻለ መጠን
በቂ የሆኑ የወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ቁሶች በቤት ውስጥ መቀመጥ አለባቸው (ይህም የሚሆነው አስፈላጊ በሚሆንበት
ወቅት ይህን ፍለጋ ወደማህበረሰቡ ላለመሄድ/ላለመቀላቀል ነው) ፡፡ በተጨማሪም የወር አባባ ንጽህናን በሚጠብቁበት
ወቅት ውሃ እና ሳሙና በመጸዳጃ ቤቱ ውስጥ መኖራቸው መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች አካል ጉዳተኛ ለሆኑ
ሴቶች እና ልጃገረዶችም በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡
ተደራሽ ለሆኑ የተለያዩ የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ምስሎች በእዝል 2 ይመልከቱ
ግለሰሱ የኮሮና ቫይረስ ምልክሎችን ካሳየ ወይም መተንፈሽ ችግር ካጋጠመው፣ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማድረግ በጣም
አስፈላጊ ነው፡፡ ምልክቶቹ (በእዝል1 ላይ እንደታዩት) ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይ ናቸው፣ ነገር ግን ከጉንፋን በተለየ ሁኔታ
የኮሮና ቫይረስ ምልክት የሆነው የማሽተት እና የመቅመስ አቅም መቀነስ ነው፡፡
የወረዳ እና የቀበሌ ባለሙያዎች እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማህበረሰቡ በኮሮና ቫይረስ የመያዝ ጥርጣሬ
ሲኖራቸው ምን ማድረግ አንዳለባቸው ለማህበረሰቡ ማስረዳት/ማስገንዘብ አለባቸው፡፡ ማሰገንዘብ ካለባቸው ነገሮች
በቅርባቸው ካለው የጤና ጣቢያ መሄድ አለባቸውን፣ በጤና ጣቢያውስ የመመርመሪያ መሳሪያ አለን፣ ወይስ ለምርመራ
ወደ ሆስፒታል መሄድ አለባቸውን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ያካትታል፡፡ እንዲሁም በቅርብ የሚነገኘው የለይቶ ማቆያ ወይም
የማገገሚያ ቦታ የት እንደሆነ እና አካል ጉዳተኞች በዚህ ማእከል ውስጥ እንዴት መግባት እንደሚችሉ (ተደራሽነት እና
የአካል ጉዳተኛው ረዳት እንዴት ሊያስታምመዉ እንደሚችል) ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ የሚገባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች
ናቸው፡፡ ወደ ጤና ጣቢያ በሚሄዱበት ወቅት የህዝብ ማመላለሻ ዘዴን አለመጠቀም እና ማስክ መጠቀም ይኖርባቸዋል፡
፡ አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት አካል ጉዳተኞቹ ከቤተሰብ አባላት ወይም ከረዳቶቻቸው ጋር መሄድ ይኖርባቸዋል በዚህም
ወቅት የህዝብ ማመለለሻ ዘዴን አለመጠቀም፣ ከሌሎች ሰዎች አካላዊ ርቀታቸውን መጠበቅ እና ማስክ/ጭምብል
5
ማድረግ የመሳሰሉት ጥንቃቄዎች መደረግ አለባቸው፡፡ የበሽታው ምልከቶቸ ከታዩነባቸው አካል ጉዳተኞች
እንደማንኛውም ሰው መመርመር አለባቸው፡፡
መመርመር የማይቻል ከሆነ፣ ግለሰቡ ላይ የታዩት ምልክቶች ቀላል ከሆኑ ወይም ግለሰቡ ተመርምሮ ቫይረሱ ከተገኘበት፣
ሁሉም የቤተሰቡ አባላት በአካባቢው ከሚገኙ ሌሎች ማህበረሰቦች እራሳቸውን በመለየት በሽታው እንዳይሰራጭ
ማድረግ አለባቸው፡፡ የምርመራው ውጤት እስኪደረስ ድረስም (አባዛኛው ጊዜ የተወሰኑ ቀናትን ስለሚወሰወድ)
ለጥንቃቄ ሲባል ቤተሰቡ ራሱን በመለየት ውጤቱን መጠበቅ አለበት፡፡
አንድ የቤተሰቡ አባል በኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ካሳየ/ከተጠቃ ምልክቶቹ ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉ ድረስ ሁሉም የዚህ
ቤተሰብ አባላት ከሌሎች የማህበረሰቡ አባላት አካላዊ ርቀታቸውን በበቂ ሁኔታ በመጠበቅ አለባቸው፡፡
በቤተሰብ ውስጥ የተከሰተ ኮሮና ቫይረስ ህመምን አካታች በሆነ መልኩ ለማስተዳደር/ለመቆጣጠር አስፈላጊ
የሆኑ መሰረታዊ ጥንቃቄዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
አካል ጉዳተኛ አባል ያለው የቤተሰብ አባል በኮሮና ቫይረስ ህመም ቢታመም፤ በቤት ውስጥ መቆየት አለበት፡፡
በዚህ ወቅት ታማሚው ግለሰብ፡-
• በተቻለ መጠን በቤት ውስጥ ከሚኖሩ ሰዎች በመራቅ በእንድ ክፍል ውስጥ ይቆዩ፡፡ የክፍሉንም በር ይዝጉት፡፡
• 1 ወይም 2 ሰዎች ብቻ ታማሚውን እንዲንከባከቡ ማድረግ፡፡ እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን በአካባቢው ካሉ ሌሎች
ማህበረሰቦች እንዲለዩ መምከር፡፡
• የሚቻል ከሆነ ንጽህ አየር ክፍሉ ውስጥ እንዲገባ መስኮቶችን መክፈት፡፡
• ከታማሚው ውጭ ሌላ ሰው በክፍሉ ውስጥ ካለ/ከገባ የፊት መሸፈኛ ማስክ/ጭምብል ያድርጉ፡፡
ተንከባካቢዎቻቸውም ማስክ ማድረግ አለባቸው፡፡
• 65 ዓመት እና ከዛ በላይ እድሜ ካላቸው ወይም ከታመሙ ሰዎች (በሌሎች በሽታዎችም ቢሆን) ይራቁ፡፡
6
የአካል ጉዳተኛው አስታማሚ/ተንከባካቢ ወይም ረዳት የሚከተሉትን ማድረግ አለበት፡-
• ታማሚው በቂ እርፍት ማግኘቱን፣ ብዙ ውሃ መጠጣቱን እና የተመጣጠነ ምግብ መመገቡን ማረጋገጥ፡፡
• እጅዎትን በተደጋጋሚ በውሃና በሳሙና ይታጠቡ፣ በተለይም ከሰዎች ጋር ከተገናኙ በኋላ፣ ምግብ ከማዘጋት
በፊት፣ እያዘጋጁ እያሉ እና ካዘጋጁ በኋላ፣ ምግብ ከመመገብዎ በፊት ወይም ታማሚውን ከመመገብዎ በፊት፣
መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ፣ ወይም ታማሚውን መጸዳጃ ቤት እንዲጠቀም ካገዙ በኋላ፡፡
• ብዙ ጊዜ በሰዎች የሚነካኩ እቃዎችን ጨምሮ፣ ቤቱን በተደጋጋሚ በውሃ እና በሳሙና ማጠብ፡፡
• በተቻለ መጠን ከታማሚው ጋር አንድ ክፍል በሚሆኑበት ወቅት ወይም በሚንከባከቡበት ወቅት
ማስክ/ጭምብል ያድርጉ፡፡ ማስኩን አንድ ጊዜ ካደረጉ/ካጠለቁ በኋላ በእጅዎ አይነካኩት፡፡
• ለታማሚው ብቻ የሚያገለግሉ የመመገቢያ ሳህኖች እና ኩባያዎች፣ ፎጣዎች እና ብርድ ልብሶች ይዘጋጁ፡፡
የጥርስ ቡርሾች፣ ፎጣዎች፣ ኩባያዎች እና የመመገቢያ ሳህኖች ቤተሰቡ በጋራ መጠቀም አይኖርበትም፡፡
በታማሚው ሰው አገልግሎት ላይ የዋሉ ልብሶች ለብቻቸው በሞቀ ውሃና በሳሙና መታጠብ አለባቸው፡፡
በኮሮና ቫይረስ ለተጠረጠሩ ወይም እንዳለባቸው የተረጋገጡ
የዓለም ጤና
ሰዎችን የቤት ወስጥ እንክብካቤ
ድርጅት
ራስዎን እና ቤተስብዎን ይንከባከቡ!
7
እዝል 1. ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ቀላል በሆኑ ቋንቋዎች እና ምስሎች የተዘጋጁ መረጃዎች
8
አካል ጉዳተኞች እና በእድሜ የገፉ ሰዎች በየቀኑ እንክብካቤ እና እገዛ ሊያስፈልጋቸው ስለሚችል በዚህም ምክንያት አካል
ጉዳት አልባ እነደሆኑት ሰዎች አካላዊ ርቀትን መጠበቅ አይችሉም ይሆናል፡፡ ለአካል ጉዳተኞቹ እንክብካቤ የሚደርጉት
ሰዎች ከተጎጂዎቹ ጋር በቂ ጊዜ እንዲያሳልፉ አስፈላጊ ቢሆንም በተመሳሳይ ሁኔታ ራሳቸውን ከሌሎች
የማህበረሰብ ክፍሎችም መለየት አለባቸው፡፡
ሎሎቹ ምልክቶች፤ ንፍጥ፣ የጡንቻ ህመም፣ የመገጣጠሚያ ህመም፣ ተቅማጥ፣ ማቅለሽለሽ/ማስታወክ፣ ምግብ
ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
9
የቫይረሱን ሰርጭት ለመግታት ሁላችንም ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ 5 ጉዳዮች፡-
ገዶች፡- እጅዎን በተደጋጋሚ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ወይም የአልኮል
ይዘት ባለው የእጅ መጸጽጃ ኬሚካል ማጽዳት፡፡
በሚስሉ ወይም በሚያስነጥሱበት ወቅት አፍና አፍንጫዎትን በለስላሳ
ወረቀት /soft paper/ ወይም በክርንዎት ይሸፍኑ፡፡
ትዎ አይውጡ፡፡
ፊትዎን፣ አፍንጫዎን፣ አፍዎን እና አይንዎን ከመነካካት ይቆጠቡ፡፡
“እጅ ለእጅም አይጨባበጡ፡፡
ትዎ አይውጡ፡፡
የጤንነት ስሜት የማይሰማዎት ከሆነ ከቤትዎ አይውጡ፡፡
“
አካላዊ
“ ርቀት መጠበቅን ተግባራዊ ያድርጉ፤ ይህም ከሌሎች ሰዎች
ቢያንስ 2 ሜትር መራቅን ይይዛል፡፡
10
ራሰዎን እና ሌሎችን በኮረና ቫይረስ ከመታመም ይጠብቁ፡፡
እንሰሳትን፣ ምግባቸውን እና
አይነምድራቸውን ከነካኩ በኋላ፡፡
•
ቫይረሱ በተለያዩ ገጾች እና ቁሶች ላይ ስለሚኖር መኖሪያ ቤቱን ማጽዳት አስፈላጊ ነው፡፡ በተደጋጋሚ የሚነካኩ ገጾቻን
እና ቁሶችን ለምሳሌ ጠረጴዛዎችን፣ ወንበሮችን እና የምግብ ማብሰያ ቦታዎችን ማጠብ እና ማጽዳት፡፡
11
በሚስሉ ወይም በሚያስነጥሱበት ወቅት አፍና አፍንጫዎትን ይሽፍኑ፡፡
በሚስሉ ወይም በሚያስነጥሱበት ወቅት አፍና አፍንጫዎን ይሽፍኑ፡፡ በሚስሉ ወይም በሚያስነጥሱበት ወቅት ለስላሳ
ወረቀት /soft paper/ ይጠቀሙ፣ ወረቀቱንም የቆሻሻ ማጠራቀሚ እቃ ውስጥ ይጨምሩት፡፡ በሚስሉ ወይም
በሚያስነጥሱበት ወቅት ለስላሳ ወረቀት /soft paper/ ከሌለዎት ክርንዎትን በማጠፍ ይጠቀሙ፡፡ እጅዎትን በውሃና
በሳሙና መታጠብ ካልቻሉ እጅ ማጽጃ ኬሚካል /sanitiser/ ይጠቀሙ፡፡ ኬሚካሉም ቢያንስ 60 በመቶ የአልኮል ይዘት
ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህንንም ለማወቅ በማጽጃ ኬሚካል መያዣው እቃ ላይ የተጸፈውን መረጃ ማንበብ ያስፈልግል፡፡
12
እዝል 2 በቤተሰብ ደረጃ ተደራሽ የሚሆኑ የውሃ፣ ንጽህናና ሀይጅን ተቋማት
በቤተሰብ ደረጃ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች እና ሌሎች የመጠጥ ውሃ እና ንጽህና አገልግሎት መስጫ ተቋማት
በተቻለ መጠን ለተጠቃሚዎቹ ቅርብ መሆን አለባቸው፡፡ በዋነኝነት የቤተሰብ ንጽህና አገልግሎት መስጫ ተቋማት
ከመኖሪያ ቤት ከ 15 ሜትር በላይ በሆነ ርቀት መሰራት የለባቸውም፡፡
የተሸከርካሪ ወንበር መንሸራተቻ /Ramps/፤ የተሸከርካሪ ወንበር ለሚጠቀሙ ሰዎች ብቻ ሳይሆን ክራንች
ለሚጠቀሙ፣ ሌሎች የእንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ወይም ለዓይነ ሰውራን ለሆኑ ሰዎችም ነው፡፡ በቂ ቦታ ካለ እና አስፈላጊ
ከሆነ የእጅ መደገፊያ ያለው መንሸራተቻ ቢሰራ ጥሩ ነው፡፡ መንሸራተቻው በጣም ተዳፋታማ መሆን የለበትም፡፡ ይህም
ማለት በ 1ሜትር የመንሸራተቻ ዝርመት ውስጥ ከፍታው ከ10 ሳንቲ ሜትር መብለጥ የለበትም፡፡ ተሸከርካሪ ወንበር
በቀላሉ መጻዳጃ ቤቱ ክፍል ውስጥ ለመግባት እነዲችል ወደ መጸዳጃ ቤቱ መግቢያ በር ፊት ለፊት ከ 100-120 ሳንቲ
ሜትር ስፋት ያለው ቦታ መኖርም አለበት፡፡ መንሸራተቻው በተለይም ውሃ ሲነካው እንዳያዳልጥ በጣም መለስለስ
የለበትም፡፡ መንሸራተቻውን በአካባቢ በሚገኙ ቅሶችም ለምሳሌ ከእንጨት፣ ከቀርቀሃ፣ ከድንጋይ እና በስሚንቶ መሰራት
ይችላል፡፡ መንሸራተቻው እንዲሁም ተንቀሳቃሽ (ሳያስፈልግ ሊነሳ የሚችል) ሊሆንም ይችላል፡፡
13
2. መጸዳጃ ቤት
የመጸዳጃ ቤቱ ውስጥ፤ መጸዳጃ ቤት ላይ ሲቀመጡ ለመደገፍ እና ሚዛናቸውን ለመጠበቅ እንዲችሉ ከ 70-90 ሳንቲ
ሜትር ከፍታ ያለው ጠንካራ የሆነ የእጅ መደገፊያ (ከብረት፣ ከእንጨት ወይም ከቀርቀሃ የተሰራ) ከመጸዳጃ ቤቱ ወለል
ወይም ግድግዳ ላይ መያያዝ/መገጠም አለበት፡፡ መደገፊያው ከመጸዳጃ ቤቱ መቀመጫ ጎን ወይም ፊት ለፊት መሰራት
እዳለበት የሚወሰነው እንደኣካል ጉዳተኛው ሁኔታና ፍላጎት መሆን አለበት፡፡ አይነ ስውራን የመጸዳጃ ቤቱን መቀመጫ
በቀላሉ እንዲያገኙት አንዳንድ መጠቆሚያ ዘዴዎችን (ለምሳሌ በግድግዳው ላይ መጸዳጃ ቤቱን አቅጠጫ በድምጽ
የሚገልጽ ቴክኖሎጂ ወይም በመጸዳጃ ቤቱ ወለል ላይ የተለየ ድምጽ የሚሰጥ ምልክት ማድረግ) ይቻላል፡፡
የበር እጀታ እና የበር አዘጋግ ሁኔታ፤ ማንኛውም የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ በተለይም ሴቶች እና ልጃገረዶች በመጸዳጃ
ቤቱ ወስጥ በነጻነትና በምቾት መጠቀም አለባቸው፡፡ በአነስተኛ ወጪ የሚሰሩ የበር እጀታዎች እንዱ ከእንጨት የሚሰራ
እና ከወለሉ ከ 90-120 ሳንቲ ማትር ባለው የበሩ ክፍታ ላይ ሊሰራ ይችላል፡፡ በሩም ሙሉ በሙሉ ወደውጭ የሚከፈት
እና ለተሸከርካሪ ወንበር ተጠቃሚዎች፣ ለክራንች ተጠቃሚዎች ወይም አቅም ላነሳቸው ሰዎች በቀላሉ ለመዝጋትም ሆነ
ለመክፈት እንዲያመች በውጭ እና በውስጥ በኩል መያዣ/እጀታ ሊኖረው ይገባል፡፡
የክፍሉ መጠን፤ አስፈላጊ ከሆነ ተሸከርካሪ ወንበር በቀላሉ መዞር እንዲችል መጸዳጃ ቤቱ ስፋት ከ120-150 ሳንቲ ሜትር
ዲያሜትር ያለው ቦታ እና ተሸከርካሪ ወንበሩን መጸዳጃ ቤቱ ውስጥ በአግባቡ ለማስቀመጥ ከመጸዳጃ ቤት መቀመጫው
እስከ ክፍሉ ግድግዳ ቢያነስ 80 ሳንቲ ሜትር ያላነሰ ከፍተት ያለው ቦታ ሊኖረው ይገባል፡፡ ለጊዜው በቤተሰቡ ውስጥ
የተሸከርካሪ ወንበር ተጠቃሚ ከሌለ፣ በመጸዳጃ ቤቱ ክፍል ውስጥ ምን ያህል ቦታ እንደሚያስፈልግ ለማወቅ
የሚከተለውን ዘዴ መጠቀም ይቻላል፡፡ መሬት ላይ ያለውን ቦታ በድንጋይ ወይም በእንጨት ምልክት ማድረግ ከዚያም
የተለያዩ ተጠቃሚዎች የተደረገው ምልክት ውስጥ እየገቡ በመንቀሳቀስ እና መጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ እንዲቀመጡ
በማሰብ በቂ ቦታ መሆኑን መሞከር እና አስፈላጊ በሚሆንበት ወቅት የቦታውን ስፋት ማስተካከል /ማስፋት ወይም
ማጥበብ/፡፡ ክራንች ወይም ረዳት/አጋዥ ለሚያስፈልጋቸው የአካል ጉዳተኞች እንዲያገለግል ክፍሉ ተጨማሪ ስፋት
እንዲኖረው ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ የክፍሉ ከፍታ ሁሉም የቤተሰብ አባላት (አካል ጉዳተኛም ሆነ ጉዳት አልባ)
በቀላሉ ሊገቡበት እና በአግባቡ ሊጠቀሙበት የሚችል መሆን አለበት፡፡
14
የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ፤ የመጸዳጃ ቤት መቀመጫ ላይ
መቀመጥ ለሚቸገሩ፣ ለነፍሰ ጡሮች፣ ለአረጋውያን እና
ለአካል ጉዳተኞች አመቺ መሆን ይኖርበታል፡፡ መቀመጫው
በቦታው ላይ በቋሚነት የሚቀመጥ ወይም ሌሎች
ቤተሰቦች እንዲጠቀሙበት ሲፈለግ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቃሽ
መሆን ይችላል፡፡
3. የመጠጥ ውሃ
በጀሪካን የተጠራቀመ ውሃን መጠቀም ለማይችሉ አካል ጉዳተኞች የቤተሰብ መጠጥ ውሃን በተለያዩ የውሃ
ማጠራቀሚያዎች ለምሳሌ በደንብ በሚከደን፣ ፎሴት በተገጠመለት እና አካል ጉዳተኛው (አቅሙ ደከም ላለ፣ ሚዛኑን
መጠበቅ ለሚቸገር፣ በአንድ እጁን ብቻ ለሚጠቀም ወዘተ…) በቀላሉ እና በራሱ ሊጠቀምበት በሚችል ባልዲ ውስጥ
ማጠራቀም ይቻላል፡፡
4. እጅ እና ገላ መታጠብ
እጅ መታጠብ፤ ከመሬት በላይ በተለያየ ከፍታ (እንደ አስፈላጊነቱ ከ50 እስከ 90 ሳንቲ ሜትር) የተዘጋጁ የእጅ መታጠቢያ
ከውሃና ሳሙና ጋር በግቢው ውስጥ እና በመጸዳጃ ቤቱ አቅራቢያ መዘጋጀት አለበት፡፡ አቅሙ ደከም ላለ ወይም በአንድ
እጅ ብቻ ለሚጠቀም ሰው ትናንሽ ጀሪካኖች ወይም የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ለእጅ መታጠቢያነት መጠቀም ተመራጭ
ናቸው፡፡ የእጅ መታጠቢያው አካባቢ እንዳይጨቀይ እና እናዳያዳልጥ የእጅ እጣቢ ውሃውን ለመያዝ በእጅ መታጠቢያው
አካባቢ ጠጠር መበተን ወይም ባሊ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
15
የተለያዩ የእጅ መታጠቢያ አማራጮችን ከመሬት ባላይ የሚኖራቸውን ከፍታ በማስተካከል ወይም የሰው
መቀመጫ በማዘጋጀት ተደራሽ ማድረግ ይቻላል (ምስሉን እንደሚከተለው ይመልከቱ)፡፡
16