You are on page 1of 15

ክፍል 5

የተቋማት ጤና አጠባበቅ ፓኬጅ


5.1. በትምህርት ቤት የንፅህና አጠባበቅ

ሀ/ የመማሪያ ክፍሎች ሁኔታ


•ህንፃው ያልተሰነጣጠቀና አደጋ የማያደርስ መሆን አለበት
•ክፍሎች በቂና ንፁህ አየር፣ የተፈጥሮ ብርሃን የማያስገቡ መስኮቶች
ሊኖሩት ይገባል
•መስኮቶች ሁልጊዜ መከፈት ይኖርባቸዋል
•ወለሉም ሆነ ግድግዳው በቀላሉ ሊፀዳ የሚችልና ንፅህናው የተጠበቀ
መሆን አለበት
ለ/ የንፁህ ውኃ አቅርቦት

 ውሃው የታከመና በየወቅቱ በላብራቶሪ የሚመረመር


 ተማሪዎችና መምህራን በራሳቸው ንፅህናው የተጠበቀ ውሃ
መጠጫ መጠቀም አለባቸው
 ውሃው የሚሰራና ሁል ጊዜ ክፍት መሆን አለበት
 በተማሪዎች ቁጥር በቂ መጠን ያለው ውሃ እና አመች ቦታ ላይ
የመቅጃ ቦታ ሊዘጋጅ ይገባል
 አንድ የውሃ ቧምቧ/ፎሴት ለ100 ተማሪዎች ያገለግላል በሚል
ስሌት መዘጋጀቱን ማረጋገጥ
ሐ/ መፀዳጃ ቤት

 የመፀዳጃ ቤቱ ከመማሪያ ክፍሎች ቢያንስ 30 ሜትር ርቀት ላይ


መሠራቱንና የነፋስ አቅጣጫ የተከተለ መሆኑን
 ለሴቶች የተለየ ንፅህናው የተጠበቀ መጸዳጃ ቤት መኖር እንዳለበት
 ስለ መፀዳጃ ቤቱ ንፅህና አጠባበቅ (ወለሉንና ግድግዳውን በወቅቱ
ተከታትለው ማፅዳታቸውን)
መፀዳጃ ቤት የቀጠለ . . .

 መፀዳጃ ቤቱ በማንኛውም ወቅት ለተጠቃሚዎች ክፍት መሆን


አለበት
 አንድ መቀመጫ ለሴት ተማሪዎች አንድ ለ35፤ ለወንድ
ተማሪዎች አንድ ለ100 አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል በሚል ታስቦ
መዘጋጀቱን ማረጋገጥ
 ንፅህናው የተጠበቀ የእጅ መታጠቢያ (ሳሙና፣ኦሞ ወይም አመድ)
ከመፀዳጃ ቤቱ አጠገብ መኖር እንዳለበት
 በእጅ መታጠቢያው ውስጥ ውኃ በየጊዜው እንዲሞላ
መ/ መሠረታዊ የግል ንጽህና

 ከእጅ መታጠቢያ እና ውሃ መጠጫ አካባቢዎች የፍሳሽ ማስረጊያ


ጉድጓድ እንዲዘጋጅ ማድረግ
 የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃው (ማስረጊያ) በአግባቡ ጥቅም ላይ
መዋሉን መከታተልና የአጠቃቀም ችግር ካለ ማስተማር
 ለደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ (ማቃጠያ) የሚውል ጉድጓድ
መዘጋጀቱንና እየተጠቀሙበት መሆኑን ማረጋገጥ
የቀጠለ መሠረታዊ የግል ንጽህና. . .

 በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ቅርጫት


እንዲኖር (እንዲጠቀሙ) ማስተማር
 የተሰበሰበውን ቆሻሻ በተገቢው በታ በጥንቃቄ መቃጠል ማስወገድ
እንደሚገባ ማስገንዘብ
 በየሳምንቱ በፕሮግራም የተያዘ የግቢ ፅዳት ዘመቻ እንዲኖር
ማስተማርና ተግባራዊነቱንም መከታተል
ሠ/ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር

 ለመምህራንና ለተማሪዎች በዋና ዋና ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ


በሽታዎች ላይ ማስተማር
 በትምህርት ቤት ውስጥ ተላላፊ በሽታና ሌሎች የጤና ችግሮች
ያጋጠማቸውን ተማሪዎች ማከምና ስለ መተላለፊያና መከላከያ
መንገዶቹ ትምህርት መስጠት
 በትምህርት ቤት ውስጥ የትራኮማ መከላከልና መቆጣጠር
ሥራዎችን ማከናወን
5.3. የጤና ኬላ ንፅህና አጠባበቅ

 ሁል ጊዜ ንፅህናው የተጠበቀ፣ሽታ የሌለው፣ እቃዎቹ በአግባቡ የተቀመጡ እና


በንጽህና የተያዙ ሊሆኑ ይገባል
 ንፅህናው የተጠበቀና ሁል ጊዜ ለአገልግሎት ክፍት የሆነ መፀዳጃ ቤት መኖር
አለበት
 የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ወይም ማቃጠያ (Incinerator) ሊኖረው ይገባል፡፡
 የእንግዴ ልጅ መቅበሪያ ጉድጓድ (placenta pit) ሊኖረው ይገባል
 የቧንቧ ውኃ ከሌለ ከንፁህ ቦታ የተቀዳ እና በንፁህ እቃ የተቀመጠ የውኃ
አቅርቦት እንዲኖር ማድረግ፡፡
 የቧንቧ ውኃ አቅርቦት ማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ የዝናብ ውሃን በንፁህ
እቃ በማጠራቀም አክሞ መጠቀም ይገባል፡፡
ለ/ ከጤና ኬላ የሚወጡ ቆሻሻዎች ከሚያስከተሉት ጉዳት አንፃር

• ጉዳት የማያስከትሉ /Non infectious wastes/፡- ከደምና ሰውነት ፈሳሽ


ጋር ንክኪ የሌላቸው
• ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ /Infectious non- sharp clinical wastes/፡-
በምርመራ የምንጠቀምባቸውን፣ በህክምና ወቅትና በወሊድ ጊዜ ከሰውነት
አካላት የሚወጡ የሰውነት ፈሳሾችን
• ስለታማ ነገሮች/Sharp materials/፡- እነዚህ በሰውነት ላይ መቆረጥን
ወይም መወጋት የሚያስከትሉና ከህመምተኛው ወደ ጤነኛ ሰው በሽታን
በቀላሉ ሊያስተላልፉ የሚችሉ ናቸው፡፡
ከጤና ኬላ የሚወጡ ቆሻሻዎች ከሚያስከተሉት ጉዳት አንፃር….

• በወሊድ ጊዜ የሚወገዱ የሰውነት አካላት /Anatomical wastes and


Placenta/፡-እነዚህ ቆሻሻዎች የሰው አካል በመሆናቸው ስነ
ምግባር በተሞላበትና የአካባቢውን ወግ በጠበቀ መልኩ በጥናቃቄ
መወገድ አለባቸው

• መድኃኒቶችና ሪኤጅንቶች/Pharmaceutical wastes/፡-


የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችና ህክምና
መገልገያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡.
ሐ/ የቆሻሻ አሰባሰብ፣ አያያዝና አወጋገድ
 የሚመረተውን የቆሻሻ መጠን መቀነስ (Waste minimization)፡-

 ቆሻሻዎችን መለየት እና ማጠራቀም (segregation and Storage) ፡-

 በየክፍሉ እንደ ቆሻሻው አይነት የተለያዩ ማጠራቀሚያዎች


እንዲኖሩ ማድረግ
 ሌላ ሰው ቀለሙን አይቶ ሊረዳው እንዲችል እንዲሁም ጽሁፍ
እንዲኖረው ማድረግ
 በተለያዩ ማጠራቀሚያዎች የተሰበሰበውን ቆሻሻ ቶሎ ማስወገድ
በጤና ኬላ ውስጥ ለቆሻሻ ማጠራቀሚያነት የምንጠቀምባቸው እቃዎች
ቀለም የሚከተሉት ናቸው፡፡
4. የኃይማኖት ተቋማት የቆሻሻ አወጋገድ
• ንፁህ ውኃ፣መፀዳጃ ቤት፣የእጅ መታጠቢያ፣ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ
ማስወገጃ ሊኖረው ይገባል፡፡
• የቆሻሻ ማስወገጃ ዘዴዎች እንዲኖሩ ሰፊ እና ተከታታይ ትምህርት
መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ሁ!!
ግና ለ
መ ሰ

You might also like