You are on page 1of 20

የትምህርት ቤት ጤና ተግባቦት

አተገባበር መመሪያ
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

መግቢያ
የልጅነት ወቅት ለተለያዩ ባህሪያት መሰረት የሚጣልበት ወሳኝ ጊዜ ነው። በጤና
ዙሪያ ትምሕርት ቤቶች ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች ልጆች ጤናን ለማሻሻል የሚረዱ
ልማዶችን እንዲያዳብሩና በተዘዋዋሪ ላሉበት ማህበረሰብ የጤና መረጃ እንዲያደረሱ
ያስችሏቸዋል። በአጠቃላይ የትምሕርት ቤት የጤና ተግባቦት ሥራዎች:-
* በመከላከል ላይ ያተኮራሉ
* ዘላቂ የሆን የባህሪ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋሉ
* በትምህርትም ሆነ በጤና ረገድ ጠቃሚ ለውጥ ያስገኛሉ
* ወጭን ይቆጥባሉ (ፕሮግራሙን ከመተግበር አንፃር)

በትምሕርት ቤቶች ውስጥ የሚሠሩ የጤና ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ


በትምህርት ቤቶች ባለቤትነት እና መሪነት ብሎም በወላጅ ተወካዮች፣ በመምህራንና
በተማሪዎች ተሳትፎ መታገዝ አለባቸው። በተጨማሪም ትምሕርት ቤቶች ከጤና
ኤክስቴንሽን ሠራተኞችና ከሌሎች የጤና አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ያላቸውን
ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊ ነው። የጤና እንቅስቃሴዎችን በማስተባበሩ በኩል
የወረዳ ትምህርት እና ጤና ፅ/ቤቶችም ትልቅ ድርሻ አላቸው።

ይህ መመሪያ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁለተኛው ትምህርት ሳይክል


ማለትም ከ5ኛ-8ኛ ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችንና የቤተሰቦቻቸውን ጤና የሚያሻሽሉ
ሥራዎችን በቀላሉ ለማከናወን ይረዳል። በዚህ ደረጃ ያሉ ታዳጊዎች የጤና
መልዕክቶችን ከራሳቸው አልፈው ለቤተሰባቸውና ለማህበረሰቡ ማዳረስ መቻላቸው
እንዲሁም ከመደበኛው ትምህርት ውጪ ባሉ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ በጤና
ክበባት፣ በዘመቻዎች) ያላቸው ተሳትፎ ለጤና ተግባቦት ሥራዎች ምቹ ሁኔታን
ይፈጥራል።

3
የትምሕርት ቤት ጤና ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

ይህንን መመሪያ መምህራን፣ የጤና ክበባት አስተባባሪዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን


ባለሙያዎች፣ የወረዳ ፅ/ቤት ባለሙያዎች እና ሌሎች የጤና ጉዳዮችን በትምሕርት
ቤቶች በማዳረስ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎች ሊጠቀሙበት ይችላሉ። መመሪያው
ተማሪዎች እና የትምህርት ቤት ማህበረሰቡ (መምህራን፣ ቅጥር ሰራተኞች)
ጤናን መሰረት ያደረጉ ልምዶች እንዲያዳብሩ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት
ይደግፋል። የመመሪያው ዓላማዎች መምህራን፣ የክበባት መሪዎችና የጤና ሠራተኞች
የሚከተሉትን ተግባራት እንዲያከናውኑ ማገዝ ነው።

* ተማሪዎችና አጠቃላይ የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ከጤና ጋር ተያያዥ


የሆኑ አዎንታዊ ባህሪያትን እንዲተገብሩ ማበረታታት
* ለተማሪ ቤተሰቦችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በተማሪዎች
አማካኝነት በጤና ዙርያ ጠቃሚ መረጃ ማስተላለፍ
* በጤና ዙሪያ የሚሠሩ ተግባራት ሳይቋረጡ እንዲቀጥሉ ለማስቻል
የወረዳ ት/ቢሮ፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ የወላጅ ተወካዮችንና
የሌሎች ባለድርሻ አካላትን አቅም መገንባት

እነዚህን ዓላማዎች ለማሳካት ይህ መመሪያ በውስጡ የሚከተሉትን ርዕሰ ጉዳዮች


አካቶ ይዟል።
* የትምሕርት ቤት ጤና ሥራዎች ጠቀሜታ
* በትምህርት ቤቶች ትኩረት የሚሹ የጤና ጉዳዮች
* ስኬታማ የትምህርት ቤት ጤና ፕሮግራሞች መገለጫ ባህሪያት
* የትምህርት ቤት ጤና እንክብካቤ ፕሮግራሞችን መቅረፅና መተግበር
* ጤና ነክ ዝግጅቶች/ክብረበዓላት
* የተሟላ የትምህርት ቤት ጤና ፕሮግራም

4
የትምሕርት ቤት ጤና ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

የትምህርት ቤት ጤና ሥራዎች ጠቀሜታ


ለታዳጊ ልጆች፡- ልጆች የተሟላ እድገት እንዲኖራቸው የአካላዊ፤ ስነልቦናዊ እና
ማህበራዊ ደህንነታቸው ተጠብቆ ማደግ አለባቸው። ስለጤና አጠባበቅ ጥሩ መሰረት
ያላቸው ልጆች፤ አዋቂ በሚሆኑ ጊዜ ጤናማ ኑሮ መምራት ይችላሉ። ለልጆቻቸውም
መልካም የጤና ጥበቃ ልምዶችን ያወርሳሉ፡፡

ትምህርት ቤቶች፡ ተማሪዎች ጤናቸው ሲሻሻል ትምሕርት የመቀበል


አቅማቸው ይዳብራል። በመሆኑም በትምሕርት ቤት ውስጥ የሚሠሩ የጤና
ሥራዎች ለመማር ማስተማሩ ሂደት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። እነዚህ ሥራዎች
በተጨማሪም ትምህርት ቤቱንና መምህራንን ከወላጆችና በአጠቃላይ ከማህበረሰቡ
ጋር ያቀራርባሉ።

ለወላጆች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ፡- በትምሕርት ቤት ውስጥ


የሚተገበሩ የጤና ሥራዎች ወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ስለጤና ጠለቅ ያለ
እውቀት እንዲኖራቸው፣ በጤና ዙርያ አዳዲስ መረጃ እንዲያገኙ እና በልጆቻቸው
የመማማር ሂደት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያግዟቸዋል።

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እና መደበኛ የጤና ክብካቤ


ሰጪዎች፦ ህብረተሰቡን ያሳተፉ ስራዎችን ከመተግበር አንፃር መደበኛ
የጤና እንክብካቤ ሰጪዎች ከትምህርት ቤቶች ጋር በጥምረት መስራታቸው
አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅና የማህበረሰቡን ጤና ለማሻሻል የሚያግዝ ዕድል
ይፈጥርላቸዋል።

5
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

በትምህርት ቤቶች ትኩረት የሚሹ የጤና ጉዳዮች


በግለሰብ እና በማህበረሰብ ውስጥ የባህሪ ለውጥን ማምጣት የጤና ተግባራት ዋነኛ
ትኩረት ነው። ስለዚህ ትምህርት ቤቶች ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ተማሪዎች
እንዲረዱ እና አንዲተገብሩ ማስቻል አለባቸው። ይህንንም ስኬታማ ለማድረግ
የጤና ተግባቦት ሥራዎች እድሜን እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን ያገናዘቡ መሆን
አለባቸው። ከዚህም አኳያ በትምህርት ቤቶች ትኩረት ከሚሹ የጤና ጉዳዮች
መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ።

ስርዓተ ምግብ፦ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት በቂ እና የተመጣጠነ


ምግብ ባለማግኘታቸው ምክንያት ለምግብ እጥረት ይዳረጋሉ። ይህ ደግሞ የልጆቹን
አካላዊ እና አዕምራዊ እድገት ስለሚገታ ትምህርት የመቀበል አቅማቸውን እና
ፍላጎታቸውን በእጅጉ ይቀንሰዋል። አንጀትን የሚያጠቁ ወይም በደም ውስጥ ያሉ
ጥገኛ ተህዋስያን በእነዚህ ልጆች ለሚከሰት የምግብ ዕጥረት አንድ መንስኤ ናቸው።
በመሆኑም በስርዓተ ምግብ ዙሪያ የትምሕርት ቤት የጤና ተግባራት የሚከተሉትን
ታሳቢ ማድረግ አለባቸው።

* ስለስርዓተ ምግብ ዕውቀት እና ጠቃሚ መረጃ እንዲኖራቸው ማድረግ


* ተማሪዎች ስለ ሀይልና ሙቀት ሠጪ፣ የሰውነት ገንቢ እና በሽታ
ተከላካይ ምግቦች ጥቅም አውቀው የተመጣጠነ ምግብ እንዲመገቡ
ማበረታታት
* ስለተመጣጠነ ምግብ እና ጠቀሜታው ከቤተሰብ ጋር በግልፅ
እንዲወያዩ ማስቻል ልጆች የቤተሰቦቻቸው አመጋገብ ሁኔታ
የተስተካከለ እንዲሆን የራሳቸውን አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ማስቻል
* ምግብን በንፅህና መያዝ ስላለው ጠቀሜታ ማስተማርና በትምሕርት
ቤትም ሆነ በቤታቸው የምግብን ንፅሕና እንዲጠብቁ ማስቻል
* በምግብ እጥረት ምክንያት የሚታዩ ምልክቶችን እና ስሜቶችን
እንዲገነዘቡ ማድረግ

6
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

የውሃ አያያዝ፤ የግል እና የአካባቢ ንፅህና፦ ልጆች ንፅህናን


ባለመጠበቅ ምክንያት እንደ ተቅማጥ እና ትራኮማ ላሉ ተላላፊ በሽታዎች እጅጉን
ተጋላጭ ናቸው። እጆቻቸውንና ፊታቸውን በአግባቡ አለመታጠብ፣ መፀዳጃ ቤቶችን
በአግባቡ አለመጠቀም እንዲሁም አካባቢን በንፅህና አለመያዝ የተማሪዎችን ብሎም
አጠቃላይ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ጤና ያውካል። ከዚህም በተጨማሪ ሴት
ተማሪዎች የወር አበባ ንፅሕና በአግባቡ መጠበቅ ሳይችሉ ሲቀሩ በራስ የመተማመን
ችሎታቸው ያንሳል፣ ትምሕርታቸውንም ለመከታተል አዳጋች ይሆንባቸዋል።
ስለዚህም የትምሕርት ቤት የጤና ሥራዎች የሚከተሉትን ነጥቦች ሊያሟሉ ይገባል።

* ተማሪዎች እጃቸውንና ፊታቸውን በሳሙና በደንብ መታጠብ


ልምድ እንዲያደርጉ ማገዝ
* ተማሪዎች ለቤተሰቦቻቸው እና ለማህበረሰቡ ስለ እጅ መታጠብ፣
ስለ መፀዳጃ ቤት መጠቀምና ስለሌሎች አካባቢን በንፅህና መያዝ
አስፈላጊነት እንዲያስተምሩና እንዲያበረታቱ ማስቻል
* የመፀዳጃ ስፍራዎችንም ሆነ ቁሳቁሶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ
ማድረግ
* በውሃ አያያዝ በግልና አካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ዙርያ
ከቤተሰባቸው ጋር ውይይት እንዲያደርጉ ማበረታታት
* ሴት ተማሪዎች የወር አበባ ንፅሕናን በቀላሉ ለመጠበቅ
የሚያስችላቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ መርዳት
ወባ፦ የወባ በሽታ ወባ በሚበዛበት የሀገራችን ክፍል የሚኖሩ በርካታ ተማሪዎችን
እና ቤተሰቦቻቸውን ያጠቃል። ወባን ለመከላከል በትምሕርት ቤቶች ውስጥ
የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልጋል።
* ተማሪዎች ስለወባ እውቀት እና አጠቃላይ መረጃ እንዲኖራቸው
ማድረግ

7
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

* ወባን ለመከላከል ስለምንጠቀምባቸው መንገዶች በተለይም


በመድሀኒት ስለተነከረ አጎበር አጠቃቀም ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
ስለአጠቃቀሙም ቤተሰቦቻቸውን እና የአካባቢው ነዋሪዎችን
ማሳወቅ
* ስለወባ ምልክቶች እና ህክምናውን የት እና እንዴት ማግኝት
እንደሚቻል ማሳወቅ
* ከቤተሰባቸው ወይንም ከአካባቢው ነዋሪ የትኛው አባል ለወባ
በሽታ ይበልጥ ተጋላጭ እንደሆነ ማስገንዘብ (ለምሳሌ ነብሰ ጡር
ሴቶች እና ከ 5ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊ ህፃናት)

ቲቢ (ሳንባ ነቀርሳ)፦ በቲቢ ዙርያ የሚከወኑ ተግባራት የሚከተሉትን


ማካተት ይኖርበታል።

* የቲቢ መከላከያ መንገዶች ተማሪዎች እንዲያውቁ ማድረግ


* ቲቢን ለመከላከል በክፍል ውስጥ እስከተቻለ ድረስ መስኮት
እንዲከፈት ማድረግ
* የቲቢን ምልክቶች ተማሪዎች እንዲያውቁ ማድረግና ምልክቶቹ
በእነሱም ሆነ በቤተሰባቸው ላይ ከተከሰቱ ህክምና እንዲያገኙ
ማበረታታት
* ከቤተሰቦቻቸው ጋር ስለ ቲቢ እንዲነጋገሩ እና በግልፅ እንዲወያዩ
ያስችላቸዋል።

8
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

ስኬታማ የትምህርት ቤት ጤና ፕሮግራሞች


መገለጫ ባህሪያት

የተለያዩ ተደጋጋፊ የባሕሪ ለውጥ ስትራቴጂዎችን መተግበር፡


የጤና ርዕሰ ጉዳዮችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ተማሪዎች እንዲረዱ እና የባህሪ
ለውጥ እንዲያመጡ ለማስቻል የተለያዩ ስልቶችን ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል።
ስለዚህም የትምህርት ቤት የጤና እንቅስቃሴዎችን የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች
ከሚያከናውኑት ስራ ጋር ማስተሳሰር እና ተማሪዎችን በሚጠቅም መልኩ ከባለድርሻ
አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ከስርዓተ ምግብ ጋር ተዛማጅ
የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ የግብርናው ዘርፍ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ማመቻቸት፤
በውሃ አያያዝ እና በግልና አካባቢ ንፅህና ጥበቃ ዙርያ ትምሕርት ቤቱ ከውሃ ዘርፍ
ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠናክር ማድረግና የመሳሰሉ አካሄዶች አስፈላጊ ናቸው።

ተማሪዎች ራሳቸው ተለውጠው ህብረተሰቡን እንዲለውጡ


ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፡- የተቀናጀ የትምህርት ቤት የጤና ስትራቴጂ
ትኩረቱ የተማሪዎችን የትምህርት እና የጤና ፍላጎት ከማሟላት አልፎ ተማሪዎቹ
በትምህርት ቤት እና በማህበረሰቡ ውስጥ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ የሚሳተፉበትን
ዕድል ማመቻቸት ነው። ተማሪዎች ጠቃሚ የጤና መልዕክት ወደህብረተሰቡ
እንዲያደርሱ ማስቻል በጎ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሆነ እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል።
በተጨማሪም ተማሪዎች ጤናን ያገናዘበ ባህሪን ይዘው ማደጋቸው በቀጣይም
ቤተሰብ በሚመሰርቱ ጊዜ ይህ ልምድ የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል።

9
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

ተማሪዎችን የሚመለከቱ የጤና ጉዳዮችን ለይቶ መፍትሔ


ማስቀመጥና ለጤና ችግር አጋላጭ ሁኔታዎችን መቅረፍ
የትምህርት ቤት ደንቦችን፣ ፓሊሲዎችን፣ ፕሮግራሞችን በማሻሻልና ተግባራዊ
በማድረግ ተማሪዎችን ለጤና ችግር እና ትምህረት ማቋረጥ ከሚዳርጉ ሁኔታዎች
መከላከል ይቻላል። ለምሳሌ፦ በትምህርት ቤት ግቢ አካባቢ የሚከፈቱ የአልኮልና
አደንዛዥ ዕፅ መሸጫ ሱቆች ካሉ ከአካባቢው ለማስነሳት ከወረዳ/ቀበሌ አስተዳደር
ጋር በትብብር መስራት።

የትምህርት ቤት ማህበረሰብን እና ባለድርሻ አካላትን አቅም


መገንባት
መምህራንና ሌሎች የባለድርሻ አካላት መሻሻል የሚሹ ጉዳዮችን ነጥለው
እንዲያውቁ፤ ከመልካም ተሞክሮዎች ልምድ እንዲቀስሙ፤ ለችግሮቻቸው መፍትሄ
እንዲያበጁ እንዲሁም አዳዲስ ስትራቴጂዎችን ለመተግበር የሚያስችላቸውን
ክህሎት ሊያዳብሩ ይገባል። ዘላቂ የሆነ ለውጥ እንዲኖር እነዚህ አካላት ጠቃሚ
የጤና መረጃዎችን በተመለከተ በራሳቸው ባህል እና ሀይማኖት የተቃኝ ማህበራዊ
እና የባህሪ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስልቶች እንዲነድፉ ብሎም ተግባራዊ
ማድረግ አለባቸው።

ውጤታማ የትምህርት ቤት ጤና ግብረ ኃይል ማቋቋምና


ማጠናከር መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና የክበባት መሪዎችን በአባልነት የያዘ
የጤና ግብረ ኃይል የጤና ስራዎች ቀጣይ ሆነው እንዲከናወኑ ትልቅ ጠቀሜታ
አለው። ከ18 ዓመት በታች ባሉ ተማሪዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ለሚሠራ ሥራ
የቤተሰብን ፈቃድ ለማግኘት ሲባል የወላጅና መምህር ህብረትን ታሳቢ ማድረግ
ያስፈልጋል። በዚህ ግብረ ኃይል ውስጥ ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን በማድረስና
አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ የመደበኛ ጤና እንክብካቤ ሰጪ ዳይሬክተር
የሚኖረው/ራት ሚና መዘንጋት የለበትም።

10
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

የትምህርት ቤት ጤና ተግባቦት አተገባበር


ደረጃ 1፦ የትምህርት ቤቱን አስተዳደር ድጋፍ ማግኘት
በትምሕርት ቤቶች ምንም አይነት እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት የትምሕርት ቤቱ
አስተዳደር እና የወረዳው ትምህርት ቢሮ በሥራው አስፈላጊነት አምነው ተገቢውን
ድጋፍ መስጠት አለባቸው። እነዚህ አካላት በሚከተለው መልኩ ድጋፍ ሊያደርጉ
ይችላሉ።
* ት/ቤቱ ወይንም የወረዳው ትምሕርት ፅ/ቤት የጤናን ጉዳይ
በተቋማቸው ራዕይ ወይንም ተልዕኮ ውስጥ ማካተት (አንድን
ወረዳ ሞዴል ወረዳ ሊያሰኘው ከሚችሉት መስፈርቶች አንዱ
በስሩ ያሉ ት/ቤቶች 100% የጤናን ጉዳይ ያካተቱ መሆናቸው)
* የት/ቤት ጤና ጉዳዮችን የሚከታተል ሰው መመደብ
* አስፈላጊ ግብዓቶችን መመደብ
* ጤናን ጠብቆ መኖር ያለውን ጠቀሜታ ለተማሪዎች፣ ለትምህርት
ቤቱ ቅጥር ሰራተኞች እንዲሁም ለወላጆች ማሳወቅ

የትምሕርት ቤቱ አስተዳደርና የወረዳው ፅ/ቤት እነዚህን ድጋፎች እንዲያደርጉ


ተከታታይ ስብሰባዎችን ማካሄድ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ስብሰባዎች
ከማድረግ በፊት መዘጋጀትና ዋና ዋና ማሳመኛ ነጥቦችን ይዞ መግባት ያስፈልጋል።

ደረጃ 2፦ የጤና ግብረ ሀይል በትምህርት ቤት ማቋቋም


የት/ቤት ጤና ግብረ ሀይል የትምህርት ቤት ጤና እና ተያያዥ ጉዳዮች አተገባበራቸውን
የሚከታተል ቡድን ነው። ግብረ ሀይሉ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚሹ የት/ቤት ጤና
ጉዳዮችን በቅደም ተከተል ያስቀምጣል፤ የትምህርት ቤቱ ጤና አስተባባሪ ሊከውናቸው
የሚገቡ ዝርዝር ተግባራትን ያቅዳል። ከዚህም በተጨማሪ አጋር ድርጅቶች፤ የጤና
ኤክስቴንሽን ሰራተኞች እንዲሁም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና እንክብካቤ ሰጪዎች
በትምሕርት ቤቱ ውስጥ ለሚሠራው የጤና ሥራ እገዛ እንዲያደርጉ ይቀሰቅሳል።

11
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

የጤና ግብረ ሀይሉ ከታች ከተዘረዘሩት አካላት መካከል ቢያንስ አንድ ተወካይ
ሊኖራቸው ይገባል
* የትምህርት ቤት አመራር
* መምህራን
* የክበብ መሪዎች/ተጠሪዎች
* የወላጅ መምህር ህብረት
* ተማሪዎች
* ጤና ባለሙያዎች
* በተማሪዎች ጤና እና ደህንነት ጉዳዮች ዙርያ ተሳትፎ የሚያደርጉ
የማህበረሰብ አባላት

በተጨማሪ የትምህርት ቤት ጤና ተጠሪ/አስተባባሪ የሚሆን ሰው መመደብ (ምክትል


ርዕሰ መምህር ሊሆኑ ይችላሉ)። የትምህርት ቤት ጤና ተጠሪው/አስተባባሪው የጤና
ግብረ ኃይሉን ያጠናክራል፣ የጤና ስራዎችን ያስተባብራል እንዲሁም በት/ቤት የጤና
ጉዳዮች ውስጥ የተካተቱ ክንዋኔዎችን ያዘጋጃል፣ ስኬታማ እና በደንብ የተደራጀ
የትምህርት ቤት ጤና መዋቅር (ለምሳሌ መመሪያዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ለተለያየ
ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚሆኑ ግብዓቶች) እንዲኖር ይሰራል።

ደረጃ 3፦ የሥራ ዕቅድ ማዘጋጀትና መተግበር


የጤና ግብረ ኃይሉ ግልፅ የሆነ የሥራ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባት ይኖርበታል።
የሚዘጋጀው የጤና ሥራዎች ዕቅድ ከትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ዕቅድ ጋር አብሮ ሊሄድ
የሚችል መሆን አለበት። የሥራ ዕቅዱን ከማዘጋጀት በፊት ተሳታፊዎች በትምሕርት
ቤትና በአካባቢው ስላሉ የጤና እክሎችና ፕሮግራሞች በሚከተለው መልኩ መረጃ
ማሰባሰብ ይኖርባቸዋል።እና ትምህረት ማቋረጥ ከሚዳርጉ ሁኔታዎች መከላከል እና
መታደግ ይቻላል፡፡

12
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

* ጤናን በተመለከተ ት/ቤቱ ምን አይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው?


* ውጤታማው አካሄድ ምን ነበር? ከገጠሙ ችግሮች የተገኙ
መልካም ተሞክሮዎች ምን ነበሩ?
* ተማሪዎች/የት/ቤት ማህበረሰብ/አጠቃላይ ማህበረሰብ ላይ
አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ ያሉት የጤና ጠንቆች የትኞቹ ናቸው?
* ከውሀ እና ንፅህና አጠባበቅ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጉዳዮች
* ወባ
* የአመጋገብ ስርዓት
* ቲቢ (ሳንባ ነቀርሳ)
* ሌላ ካለ
* ለእነዚህ የጤና ችግሮች የሚያጋልጡ መንስኤዎች ምንድን ናቸው?
* የትኛው የጤና ችግር በቀዳሚነት ይታይ? የትኛውስ ይቀጥል?
* በዚህ ረገድ ያሉት መልካም አጋጣሚዎች ምንድን ናቸው?
* ፕሮግራሙን ሊደግፉ የሚችሉ ባለድርሻ አካላት እና አጋር
ድርጅቶች እነማን ናቸው?

ሥራዎችን መከታተል፣ መገምገም እና መልሶ ማቀድ


ሥራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን በየጊዜው ማየት እና የሚፈለገው ውጤት መምጣቱን
በመገምገም በሥራው ሂደት ውስጥ አስፈላጊውን ማሻሻያ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም
በጎ ለውጦችን አጠናክሮ ለመቀጠልና በሂደቱ የሚያጋጥሙ መሰናክሎችን ለይቶ
መፍትሔ ለመስጠት ያስችላል።

13
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

ጤና ነክ ዝግጅቶች/የጤና ቀን
በጤና ዙርያ ሁለት አይነት ዝግጅቶች ሊዘጋጁ ይችላሉ፤ አንደኛው ዝግጅት የትምህርት
ማህበረሰቡን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሰፊውን ማህበረሰብ ያካተተ
ነው። የእነዚህ ዝግጅቶች ዋነኛ ዓላማ ጤናን የሚያበረታቱ ባህሪዎችን ለማስፋፋት
ነው።

እነዚህ ዝግጅቶች ሲዘጋጁ ትምህርት ቤቶች፡-


* የዝግጅት ቀናትን ቀደም ብለው ማስተዋወቅ
* የልጆችን እድሜ ያገናዘበ መልዕክቶችን መቅረፅ
* እነዚህ ዝግጅቶች በደንብ ታቅደው በተሳካ መልኩ እንዲከናወኑ
እና የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ ሲባል ከፕሮራም ፈፃሚ
አካላት ጋር በጋራ መስራት አለባቸው።

የጤና ዝግጅቶች በትምህረት ቤቶች በሚከናወኑ ጊዜ የትምህርት ቤት ክበባት ዝግጅቱ


በተሳካ ሁኔታ በማከናወኑ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አላቸው። የጤና ዝግጅቶች
በሚሰናዱበት ጊዜ ከዝግጅቱ በፊት እና በኋላ ለትምህርት ቤቶች የቴክኒክ ድጋፍ
ማድረግ አስፈላጊ ነው።

14
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

በጤና ክብረ በዓላት ላይ በትምህረት ቤት ውስጥ ሊዳሰሱ ከሚችሉ


ጉዳዮች ለምሳሌ ያህል
የጤና ጉዳይ የጤና ቀናት
ጥገኛ ተዋህስያንን የማስወገድ ዘመቻ
ሥርዓተ ምግብ የምግብ ዝግጅት ሰርቶ ማሳያ (በአካባቢው በተገኙ የምግብ
አይነቶችን በመጠቀም)
የእጅ መታጠብ ቀን
የውሃ አያያዝ፤ የንጹህ ምግብ ቀን
የግል እና የመጸዳጃ ቤት ቀን (በተለይም ውጪ መፀዳዳት በሚበዛባቸው
የአካባቢ ንፅህና አካባቢዎች)
የአካባቢ ፅዳት ቀን/ዘመቻ
የዓለም ወባ ቀን
ወባ የአጎበር አጠቃቀም እና አሠቃቀልን ሰርቶ ማሳያ
የአካባቢ ንፅህናን ለመጠበቅ (ኩሬዎችን የማዳረቅ ስራ)
የወጣቶች ስነ የልጃገረዶች ቀን
ተዋልዶ ጤና የዓለም የሴቶች ቀን
ቲቢ የዓለም ቲቢ ቀን

የትምህርት ክበባት ድርሻ


የጤና ተግባራትን በጥምረት ለማቀድ ይረዳ ዘንድ መምህራን እንዲሁም የክበባት
መሪዎች በጤና ጉዳዮች ዙርያ ስለሚኖራቸው የስራ ድርሻ እና የትግበራ ስልቶች
መነጋገር እና መወያየት አለባቸው። በተጨማሪም ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር፤
ከት/ቤቱ ጤና ግብረ ኃይል፤ ከፕሮግራም ፈፃሚ አካላት፤ ጤና ኤክስቴንሽን
ሰራተኞች እንዲሁም ከመደበኛ የጤና ክብካቤ ሰጪዎች ምን አይነት ድጋፍ
እንደሚያስፈልጋቸው ለይተው እና ቀድመው ማወቅ አለባቸው።

15
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

የጤና ክበባት ተማሪዎችን በሰፊው ለማንቀሳቀስ፤ የጤና ውይይጥች ለምሳሌ በ 1


ለ 5 አደረጃጀት ውስጥ እንዲዳሰሱ፤ አልባሌ ወግ እና ልማዶች ብሎም የተሳሳቱ
አመለካከቶች እንዲቀየሩ፤ ጠቃሚ የጤና መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዲሁም ተቀባይነት
ያላቸው የጤና መገለጫ ባህርያት ልምድ ሆነው እንዲቀሩ ተልቅ እገዛ ያደርጋሉ።

ሚኒ ሚድያ፤ የአርት እና የስነ-ፅሁፍ ክበባት እያዝናኑ የሚያስተምሩ ክንውኖችን


በማዘጋጀት በኩል አስተዋፅ ያበረክታሉ። ክበባቱ በሚያዘጋጁት የጤና መሰናዶ ላይ
የሚተላለፈው መልዕክት ይዘት ከራሳቸው ቢመጣና በራሳቸው ቢዘጋጅ የተሻለ
ይሆናል።

ይሁን እንጂ የሚተላለፉት የጤና መልዕክቶች ትክክለኛ ስለመሆናቸው እና አሉታዊ


ሳይሆን ገንቢ ሀሳቦች ስለመነገራቸው እርግጠኛ ለመሆን መልዕክቶቹ ከመተላለፋቸው
በፊት የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች፤ መደበኛ ጤና ክብካቤ ሰጪዎች ወይንም
ፕሮግራም ፈፃሚ አካላትን ቅድመ ይሁንታ ማግኘት አለባቸው። የሚተላለፉት
መልዕክቶች ይዘት የጤና አገልግሎት ፍላጎትን ከፍ ማድረግ የሚያስችሉ፤ ሰዎች
ጤናን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ዘይቤን እንዲከተሉ የሚያግዙ እንዲሁም ተማሪዎች
በቀረቡት የጤና ጉዳዮች ዙርያ ከቤተሰቦቻቸው እና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር እንዲወያዩ
የሚያስችሉ መሆን አለባቸው።

የተሟላ የትምህርት ቤት ጤና ፕሮግራም


በዚህ መመሪያ ውስጥ ያሉት የትምሕርት ቤት ጤና ተግባቦት ሥራዎችን ከአጠቃላዩ
የትምሕርት ቤት የጤና ፕሮግራም ተለይተው የሚተገበሩ አይደሉም። የትምሕርት
ቤት ጤና ተግባቦት ሥራዎች አስፈላጊ ቢሆኑም ብቻቸውን የሚፈለገውን ለውጥ
አያመጡም። በመሆኑም የጤና ተግባቦቶቹ በሚተገበሩበት ወቅት የሚከተሉትን
አብሮ ማስኬድ ያስፈልጋል።

16
የትምሕርት ቤትየትምህርት
ጤና ተግባቦት
ቤትአተገባበር
ጤና ተግባቦት
መመሪያ

1. የትምህርት ቤት ጤና ዝግጅቶችን ከጤና አገልግሎት ጋር


ማስተሳሰር ፡- በትምህርት ቤት ውስጥ የሚሰናዱ የጤና ዝግጅቶች ተማሪዎች፣
ቤተሰቦቻቸውና አጠቃላይ ማህበረሰቡ በጤና ተቋማት ለሚሰጡት አገልግሎቶችን
እንዲጠቀሙ ማበረታታት ያስፈልጋል።

2. ምቹ የሆነ የትምህርት ቤት አካባቢ መፍጠር፡- ትምህርት ቤቶች


የጤና ስራዎችን ለማናወን የሚያስችል ንፁህ፣ ጤናማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ
እንዲሁም አመቺ ከባቢ መፍጠር አለባቸው። በተለይም የጤና ክብረ በዓላት
በሚዘጋጁበት ወቅት የአካባቢው ሰዎች ፕሮግራሙን ለመታደም ስለሚመጡ
የንፅህና መጠበቂያ ስፍራዎችን እና የውሀ አቅርቦት እንዲሁም የመፀዳጃ ስፍራ
ማቅረብ አለባቸው። የጤና ተግባራት በትምህርት ቤት ሲዘጋጁ የተለያዩ
አገልግሎቶችን ለማከናወን እንዲሁም የጤና ምርመራ አገልግሎት ለመስጠት
የሚያስችል በቂ ቦታ ማዘጋጀትም ያስፈልጋል።

3. ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ግንኙነት መፍጠር: በትምህርት


ቤቶች፣ በወላጆች፣ በማህበረሰቡ፣ በድርጅት እንዲሁም በባድርሻ አካላት መሀከል
የጠበቀ ግንኙነት እና ትስስር ሊኖር ይገባል። ይህም ተማሪዎች በበጎ ፈቃደኝነት
ለማህበረሰቡ በጎ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ እድል ይፈጥርላቸዋል፣ በቤተሰብ እና
በማህበረሰቡ አባላት መሀከል ውይይት እንዲኖር ያበረታታል፣ እንዲሁም የጤና
እንቅስቃሴዎችን ከማህበረሰቡ ጋር ማስተሳሰር ተግባራቱ ቀጣይነት እንዲኖራቸው
ያደርጋል።

4. የጤናን ጠቀሜታ የሚያሳውቁ ክበባትን ማጠናከር፡ እነዚህ


ክበባት ተማሪዎች እድሜያቸውን ያገናዘበ የጤና መረጃ እንዲያገኙ እና ተገቢውን
የባህሪ ለውጥ እንዲያመጡ ያግዛሉ። በትምህርት ቤት የሚዘጋጁ የጤና ተግባራት

17
የትምህርት ቤት
የትምሕርት ቤት ጤና
ጤና ተግባቦት
ተግባቦት አተገባበር መመሪያ

ተማሪዎች ስለጤና ጉዳዮች የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዲሁም እድሜያቸውን እና


የእድገት ደረጃቸውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የጤና መልዕክቶችን በማድረስ በግለሰብ፤
በቤተሰብ እንዲሁም በማህበረሰብ ደረጃ ለውጥ እንዲያመጡ ለማድረግ የተዘጋጁ
ናቸው።

18
This guideline is made possible by the generous support of the American people through the United States Agency for Inter-
national Development (USAID). The contents are the responsibility of Johns Hopkins Center for Communication Programs
Ethiopia and do not necessarily reflect the views of USAID or the United States Government.

Federal Democratic Republic of Ethiopia


Ministry of Health

You might also like