You are on page 1of 23

በበሰኔ ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በ 2016 ዓ.ም ከሚማሩት ህጻናት አንድ ወንድ እና


ሁለት ሴት በጠዋት ቀድመው ሲመጡና በሽኝት ሰዓት ብቻቸውን ሲቀሩ
የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ የተደረገ ጥናት፡፡
አዘጋጆች መምህራን ስም ፡- የመለያ ቁጥር 1 ኛ. መ/ርት
ስህነ አለሙ ገ/መድህን 14/ 2141
2 ኛ. መ/ርት ብስራት ኪሮስ 14/ 2113
3 ኛ. መ/ርት ገነት ሐሰን 14/ 2116
4 ኛ. መ/ርት ብዙአየሁ በሪሁን 14/ 2114
5 ኛ. መ/ርት ሐብታም ፀጋዬ 14/ 2117
6 ኛ. መ/ርት ዘውድነሽ እንድሪስ 14/ 2153
7 ኛ. መ/ርት ይርበብ ደገፋይ 14/ 2151
8 ኛ. መ/ርት ቤተልሄም በዛብህ 14/ 2112
ለደብረ ብርሃን መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ሙያ ትምህርት ክፍል
ለድርጊት ምርምር (PPED 232) የተዘጋጀ የተግባር ስራ በክፍል 23 የሚገኙ
የቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራ የተጠና ድርጊታዊ ምርምር ነው ፡፡
ታህሳስ 20 /2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ምስጋና፡-
በቅድሚያ በነገሮች ሁሉ ለረዳን እና ላሳካልን ለልዑል እግዚያብሔርን ክብር
ምስጋ ይገባል፡፡ በመቀጠል ይህንን ጥናት ስናደርግ ለስራው የሚሆን መረጃ ለተባበሩን
የትምህርት ቤቱ፣ ማህበረሰብ፣ የወላጅ ኮሚቴ እንዲሁም የትምህርት ቤቱ
አስተዳደር ለአቶ አመሐ አበበ ፣ በዚህ መጠይቁ ለተባበሩን ለኬጂ ርዕሰ መምህር
ወ/ሪት አበበች መለሰ መረጃ በማሟላት ስላደረጉልኝ እጅግ ምስጋናዬን
አቀርባለሁ በተጨማሪም በቋንቋ ትምህርት ክፍል አባል መምህራንን
በመረጃ ማጠናከር በሙያዊ እገዛቸው ላደረጉልኝ ምስጋናዬን አቀርባለሁ
ይህ እድል ለሰጠን ለትምህርት ቤቱም ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡

ማውጫ ገፅ
ምእራፍ አንድ
መግቢያ

የጥናቱ ዳራ
የጥናቱ ችግር ማብራርያ

የምርምሩ አላማ
የምርምሩ (የጥናቱ) ዝርዝር ዓላማዎች----------------

የጥናቱ አስፈላጊነት (አሳሳቢነት)-------------------------

የጥናቱ የቱኩረት ነጥብ-----------------------------------


ምእራፍ ሁለት

የጥናቱ ዘዴ -----------------------------------------------
የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች -----------------
ጥናቱ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች----------------------

ጥናቱን ለማድረግ የሚያጋጥሙ ችግሮች-------------


የተዛማጅ ፅሁፎች ቅኝት-------------------------------

የመረጃ ምንጮችን መተንተን ---------------------------

ከመረጃ ምንጭ የተገኘ ምላሽ ---------------------------


ምእራፍ ሶስት

የመፍትሄ ሀሳቦች አተገባበር


የጥናቱ አበይት ግኝቶች ውጤት-----------------------
የጥናቱ የማጠቃለያ ሪፓርት-------------------------
የመፍትሄ ሀሳቦች አተገባበራቸው---------------------
ለጥናቱ የተመደበ በጀት---------------------------------

ምእራፍ አንድ

መግቢያ
የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ጋር ሲያደርግ የነበረው መስተጋብር በወቅቱ ለመኖር
የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሁሉ ማግኘት እንዲችል ረድቶታል፡፡ ይህ ማለት
የሰው ልጅ በራሱና በአካባቢው መካከል ያለውን የእውቀት ክፍተት
ለመሙላት ሲታገል የነበረ መሆኑን ያሳያል፡፡አሁንም በመታገል ላይ ይገኛል፡፡
በንፋስ ስልክ ላፍቶ የሚገኘ

በሰኔ ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት በአለው ራዕይና ተልእኮ መሰረት
ህጻናትን በአራቱም የመዳበር አቅጣጫዎች እነሱም በአካል ፣ በአእምሮ፣
በማህበራዊ እና በስሜት ለማዳበር ባአለው ተነሳሽነት መሰረት የህጻናቱን
ለመንከባከብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ውሎ መሰረት በማድረግ በቅድመ
አንደኛ ደረጃ ትምህር ቤት ሕጻናት ላይ የሚደርሱትን ሁነቶች በማጤን
ሕጻናት በጠዋት ሲመጡ እና በሽኝት ሰዓት ብቻቸውን ሲሆኑ
የሚገጥማቸውን ችግር በመገንዘብ ይሄንን ጥናትና ምርምር ለማድረግ
ተነሳስተናል፡፡

1.1 የጥናቱ ዳራ መነሻ


በንፋስ ስልክ ላፍቶ ልዩ ስሙ ሳሪስ በሚገኘ በሰኔ ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት ውስጥ ከሚማሩት ህጻናት ውስጥ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት ሕጻናት
የሚደርስባቸውን የተለያዩ ተጽዕኖች ለመቅረፍ ነው፡፡ ይህ ማለት ሕጻናት ጠዋት
ከአንድ ሰዓት ከሰላሳ በፊት ቀድመው ሲመጡ አብዛኛው ተማሪ ስለማይመጣና
ሁሉም የግቢው ሰራተኞች ሊገቡ ስለማይችሉ ህጻናቱ ለብቻቸው በሚሆኑበት
ግዜ የሚሰማቸውን ስሜት መረበሽ፤ ብቸኝነትና ፍራቻ በተጨማሪም ሕጻናት
በሚሸኙት ግዜ ወላጅ በሰዓቱ መጥቶ ካልወሰዳቸው የተለያዩ የሞራል፣ የአዕምሮ፣
የአካል ጉዳት እና ጥቃት እንዳይደርስባቸው ነው፡፡ አካባቢው ለመኪና አደጋ
ተጋላጭ በመሆኑ ችግሩን
ቢቀጥል ጉዳቱን የከፋ ያደርገዋል በማለት ጥናቱን ለመጀመር ተወሰነ ፡፡ ከዚህ
በፊት ትምህርት ቤት ውስጥ በዚህ ርህስ የተጠና ጥናት እንደሌለ ፋይል
ምልከታ(ፍተሻ) ላይ ተመልክተናል፡፡

1.2 የጥናቱ ችግር ማብራርያ

ይህ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ያሥቀመጠው መላምት ሕጻናት በማንኛውም


ግዜ ብቻቸውን ሲሆኑ የሚገጥማቸው ችግር የመረበሽ ፣ የማልቀስ፣ መጫወቻ
ላይ በመንጠል መውደቅ፣ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማቸው ከግቢ መውጣት፣ለመኪና
አደጋ እና በተጨማሪም ጾታዊ ጥቃት የሚጎዳቸውን ነገሮች በመንካት ወደ አፍ
በመክተት ከፍተኛ አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል ተብሎ ይታሰባል፡፡

የጥናቱ አስፈላጊነት (አሳሳቢነት)

ሕፃናቱ የሚመጡበት ሰዓት ከአንድ ከሰላሳ በፊት ስለሆነ በግቢ ውስጥ የጥነቃ
ሰራተኛ ብቻ በመኖራቸው ልጆቹን በመጫወቻ ላይ በመንጠልጠል የአካል ጉዳት
መድረስ እና ከግቢ ውጭ ለመውጣት መሞከር ሕፃናቱ ለከፋ ጉዳት መጋለጣቸው
አይቀሬ ነው፡፡ በሽኝት ሰዓት ደግሞ ሁሉም መምህር ሆነ ሞግዚት በስራ እየደከመ ውሎ
ወደ ቤቱ ገብቶ ሌላ ሀላፊነት የሚወጣበትን ሰዓት የወላጅ መዘግየት ልጆቹን ቶሎ
አለመረከብ ችግር ነዉ፡፡ ይህ ችግር በጊዜ መፍትሄ ካላገኘ ሕፃናቱን ለከፋ ጉዳት
ይዳርጋል፡፡
1.3 ጥናቱ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች

ይህ ጥናት የሚመልሰው ጥያቄ ሕጻናት ጠዋት ቀድመው ለምን እንደሚመጡና

በሽኝት ሰዓት ለምን ዘግይተው እንደሚሄዱ ለማወቅ ያሥችላል ፡፡ በተጨማሪም

ህጻናት በጠዋት በመምጣታቸውና በመዘግየታቸው ምክንያት የሚደርስባቸውን

ተጽዕኖምን እንደሆነ ለማወቅ ያሥችላል፡፡

ጥያቄ ብዛት 5 ናቸው፡፡

መጠይቅ 1. በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ህጻናት ጠዋት ቀድመው


በሚመጡበትና በሚሸኙበት ጊዜ በቶሎ የማይሄዱ ህጻናት አሉ? በተደጋጋሚ ነው ?
ወይስ አይደለም ? አዎ -------- አይደለም -------

መጠይቅ 2 . ህጻናቶች ጠዋት ያለ ሰዓት ቀድመው ሲመጡና በሽኝት ሰአት ወላጆች


ቶሎ የማይወስድባውቸን ምክንያቶች ምንድን ናቸው ?
መጠይቅ 3 . ህጻናቶች ጠዋት ቀድመው በመምጣታቸው እና በሽኝት ሰአት ቶሎ ባለ
መወሰዳቸው የሚገጥማችው ችግሮች ምንድን ናቸው?

መጠይቅ 4 . ችግሩን ካዩ(ካወቁ) ለመፍታት ሙከራ አድርገዋል? አዎ -----------------


አይደለም---------------------

መጠይቅ 5 . ለሚፈጠሩ ችግሮች ምን ዓይነት የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባሉ?

1.4 የምርምሩ አላማ


ጠዋት ቀድመው የሚመጡና በሽኝት የሚዘገዩ ህጻናት ከችግሩ በመነሳት
የመፍትሄ ሃሳብ ለመፈለግ ነው፡፡ይህ ጥናት ለማድረግ ከመምህራን እና
ከሞግዚቶች ጋር በመሆን ውስጣዊና ውጫዊ የሆኑ ሁኔታዎችን በመፈተሽ
ለችግሩ የሚሆን የመፍትሄ ሃሳብ ለመፈለግ ለማመቻቸት ነው፡፡

የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች

ሀ- ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ የሆኑ አዉንታዊ የትምህርት ቤትና አካባቢን


መፍጠር፡፡

ለ-በመምህር፣ በሞግዚቶች እና በወላጆች ላይ ንቃተ-ህሊና ለመፍጠር፡፡

ሐ- ህፃናቱ ስሜታቸው ሳይረበሽ ቀኑን እንዲወሉ ለማድረግ ፡፡

መ- ለሚደርስባቸው አካላዊ ሆነ ስነልቦና ጉዳት ፈጣን ምላሽ ለመፈለግ፡፡

ሠ-በልጅነት ጊዜ ለወደፊት እድገት ወሳኝ ጊዜ መሆኑን ለሚመለከተው ሁሉ


ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠር፡፡

ረ- በትምህርት ቤት ግቢ ለሕፃናት የሚደረጉትን ድጋፍ እና እንክብካቤ ለህብረተሰቡ


ማሳወቅ፡፡

ምዕራፍ ሁለት
የጥናቱ ዘዴ

የጥናቱ አካላይ

የጥናቱ የቱኩረት ያደረገው የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች ህጻናት ሲሆኑ


በግቢ ውስጥ ብቻቸውን ሲሆኑ ከሚሰማቸው የፍርሃት ስሜት መረበሽ እና
ከሚደርስባቸው ልዩ ልዩ አደጋዎች (ተግዳሮቶችን) ለይቶ የመፍትሄ ሐሳብ
ለመሰንዘር ነው፡፡

ወሳኝ ናሙና የጥናቱ ተሳታፊዎች

አጥኚዎች መጠይቆችን በማዘጋጀት ለተጠኚዉ ቅርበት ላላቸው ሰዎች


ለሚመለከታቸው ለተማሪ ወላጆች፤መምህራን ከሞግዚቶችና የጥበቃ ሰራተኛ
መጠይቁን በማስሞላት መረጃን ይሰበስባል በተደጋጋሚ ከተያዘ መረጃ የሚፈለጉ
ግብዓቶችን ይወስዳል፡፡

የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች(ዘዴዎች)

ይህ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በአሁኑ ወቅት ከሚስተዋለው ችግር በመነሳት የችግሩ


መነሻ ሊሆን ይችላል ተብሎ በአጥኚው የቀረበውን መላምት በመጠይቆች(ቃለ
መጠይቅ) በማረጋገጥ ገላጭ የሆነ መረጃን ማሰባሰብና መፍትሄ ሀሳብ በማፈላለግ
ይካሄዳል፡፡

የተዛማጅ ጽሁፎች ቅኝት


ለህጻናት እንክብካቤና ጥበቃ ሃላፊነት የአለባቸው ተቋሞችና አገልግሎት
ሰጪ ድርጅቶች በህጸናት ጉዳይ ስልጣን በአላቸው አካላት የወጡ ደረጃዎች
ማሟላታቸውን በተለይም አደጋን በመከላከል በጠየና አጠባበቅ ክትትል ረገድ
መሰረት መፈጸማቸው የኮንቬንሽኑ አባል አገሮች ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

/የህጻናት መብት ኮንቬንሽን፤ክፍል 1 ገጽ 9/

ህጻናት በአካልና በአእምሮ ያልጎለመሱ በመሆናቸው ምክንያት


የጤንነታቸውን እና አካላቸውን አእምሮአቸውን እንዱሁም በግብረ-ገብ እና
ማህበራዊ እድገታቸውን በተመለከተ ልዩ አንክብካቤ የሚሹና እንዲሁም
ክብራቸውን ደህንነታቸውን እና ነጻነታቸውነ መሰረት የአደረገ የህግ ጥበቃ
እንዲደረግላቸው አስፈላጊ መሆኑን መገንዘብ፡፡

/የአፍሪካ ህጻናት መብቶችን ደህንነት ምዕራፍ አንድ ገጽ 3/


ህጻናት በወላጆቻቸው ወይም በአሳደጊዎቻቸው ወይም በሌሎች ሰዎች ቁጥጥር
ስር በሚገኙበት ግዜ ማንኛውም አይነት በአካላቸው ወይም በአእምሮአቸው
ጉዳት የሚያመጣ ለጉዳት ወይም ጉስቁልና የሚዳርግ አያያዝ በቸልታ መጣል
ወይም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ ማስገደድ ጭምር እንዳይፈጸምባቸው
ተገቢውን የህግ የአስተዳደር እርምጃ ይወሰዳሉ፡፡

/የአፍሪካ ህጻናት ደህንነት ምዕራፍ አንድ ገጽ 4/

ወላጆች ወይም ህጋዊ አሳዳሪዎች በህጻኑ ላይ ተመጣጣኝ ቁጥጥር


ማድረግ ያላቸው መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ህጻን በግል ህይወቱ
ወይም በቤተሰቡ ቤት ውስጥ የሚደረጉ ህገወት ጣልቃ ገብነትና ከሚሰነዘሩ
ጥቃቶች የመጠበቅ መብት አለው፡፡ ህጻኑ ከነዚህ ጣልቃ ገብነቶችና ጥቃቶች
እንዲጠበቅ ህጋዊ ከለላ የማግኘት መብት አለው፡፡

/የአፍሪካ ደህንነት ምዕራፍ አንድ ገጽ 4/


‹‹
የልጆች ደህንነታቸው የተጠበቀና እየተወደዱ መሆናቸዉን ከተሰማቸው
አእምሮቸውን በማነሳሳት በጨዋታ እና በትብብር ላይ ልዩ ይሆናሉ፡፡ የሚፈሩ እና
የማይፈለጉ የመሆን ስሜት ከተሰማቸዉ የፍርሐት እና የመጨነቅ ስሜት በመቆጣጠር
የበታችነት እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል፡፡›

ሲሉ ዶ/ር ቤሰቫልንደር ኮልክ ጽፈዋ

መረጃ ምንጮችን መተንተን


የመረጃ ምንጭ ተሳታፊዎች
ከወላጅ ለልጆች ሁለንተናዊ እድገት መሰረት የሚጥሉ ብርሃኖች ናችው ፡፡
ከመምህራን ፡- ከወላጅ በመቀጠል ልጆች ሁለንተናዊ እድገት በመከታተል፣
እንዲመሯቸው እና እንዲረዷችው ሞዴል በመሆን ለህጻኑ መምህር ተነባቢ
መፅሐፍ ናቸዉ፡፡
ከሞግዚት፡-ለልጆች ቀጣይ እድገት እና ለዉጥ ጤናማና ውጤታማ እንዲሆኑ
የዕለት ከዕለት ተግባራትን ሕፃናትን የሚያግዝ ቀኝ እጆች ናቸው፡፡
ጥበቃ፡-አካባቢን በመመልከት ለመማር ማስተማሩ በሰላም እንዲካሄድ ያደርጋሉ፡፡

ከወላጅ ከመምህራን ከሞግዚት ጥበቃ


ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ
4 6 10 - 2 2 - 4 4 2 - 2

ከመረጃ ምንጭ የተገኘ ምላሽ

መጠይቅ 1. በቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ህጻናት ጠዋት ቀድመው


በሚመጡበትና በሚሸኙበት ጊዜ በቶሎ የማይሄዱ ህጻናት አሉ? በተደጋጋሚ ነው?
ወይስ አይደለም?
አዎ --------------- አይደለም -----------------

ከወላጅ ከመምህር ከሞግዚት ጥበቃ

አዎ አይደለም አዎ አይደለም አዎ አይደለም አዎ አይደለም


7 3 2 4 2
መጠይቅ አንድ መሰረት መጠይቁን ከተጠየቁት አስር ወላጆች መካከከል 70%
የሚሆኑት መላሾች ቀድመው የሚመጡና ዘግይተው የሚሸኙ ሕጻናት መኖራቸውን
ግንዛቤው ያላቸው ሲሆን 30% የሚሆኑት መላሾች ግንቤው የሌላቸው ናቸው፡፡
በተመሳሳይም ከጥበቃ፣ መምህራንና ሞግዚቶች 100% ግንዘቤው ያላቸው ናቸው፡፡

መጠይቅ 2 . ህጻናቶች ጠዋት ያለ ሰዓት ቀድመው ሲመጡና በሽኝት ሰአት ወላጆች

ቶሎ የማይወስድባቸውን ምክንያቶች ምንድን ናቸው ? ተብሎ ለተጠየቀ ጥያቄ

ከወላጅ፣ጥበቃ፣ ከመምህር እና ከሞግዚቶች የተሰጡት ምላሾች ፡-

ከወላጅ መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት

በተሰበሰበው መረጃ መሰረት በመጠይቅ ሁለት ላይ ህጻናት በሰዓቱ አለ

መውሰድና ጠዋት ከ 1፡30 በፊት የሚያመጡበትን ምክንያት ይሆናል ብለው

ወላጆች ያስቀመጡአቸው ምክንያቶች እንደሚከተሉት የናቸው፡-

 የስራ ሁኔታ (የወላጆች ስራ ባህሪ)

 የስራ ሰአት

 የስራ ቦታ ርቀት

 በቸልተኝነት እና ግዴለሽ መሆን

በማንኛውም ሰአት ትምህርት ቤቱ መቀበል እና መሸኘት አለበት ብሎ ማመን


! ሀላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በትምህርት ቤቱ ላይ መጣል፡፡

አንዳንድ ወላጆች ቶሎ በመምጣት ህጻናትን ማንወስደው በር ላይ ሁሉም


ወላጆች በአንድ ሰዓት ለመውሰድ ስለሚመጡ ያለውን መጨናነቅ በመፍራት
ነው የሚል አስተያየት አስቀምጠዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዲወስዱና
እንዲመልሱ ሃላፊነት ያለባቸው / የተሰጣቸው /አካላት ቀድመው እና ዘግይተው
የመምጣት ችግር ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ጥበቃ መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት

የወላጆች የስራ ቦታ ርቀት እና የትራንስፖርት ከረፈደ ያለ መጨናነቅ ለማስቀረት


ይመስለናል ብለዋል፡፡

መምህራን መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት

እዚህ መጠይቅ ላይ ከመምህራን የተገኘው ምላሽ አንዳንድ ወላጆች በገቢ


ማነስ በኑሮ ዉድ መሆን ትርፍ ስራ በመስራት ምክንያት ያረፍዳሉ ወይንም
ቀድመው ያለሰአት ያመጣሉ ሌላው የተሰጠው አስተያየት በስራ ጫና እና ድካም
ከሰአት ለመውሰድ ሰአቱን የመዘንጋት ችግር ወላጆች ሊያጋጥማቸው ይችላል
ብለዋል፡፡

ከሞግዚት መጠይቅ በተመለከተ የተመለሰ አስተያየት

ልጆቹን የሚያመጣ እና የሚወስድ ሰው ባለመኖሩ በስራ ምክንያት


ወላጆች ቀርተው የመጡና ለመመለስ ችግር አለ ብለዋል፡፡የመንግስት ትምህርት
ቤት በመሆኑ በየትኛውም ስዓት መውሰድ እና ማመላለስ እንችላለን በሚል
የተሳሳተ አመለካከት በመያዝ የመግቢያ እና የመውጫ ስዓትን ያለማወቅ እና
ያለማክበር ነው ብለዋል፡፡

ከላይ ከተሰጠው ምላሽ አንጻር መጥይቅ ሁለትን ጠቅለል አድርገን ስናየው ህፃናት ይህ
ችግር የሚገጥማቸው በቤተሰብ የኑሮ ሁኔታ፣ የስራቸው ባህሪ ፣ቸልተኝነት ወይም
ግዴለሽ መሆን እና ሀላፊነትን ካለመወጣት የመጣ መሆኑን ከተጠያቂዎች ምላሽ
ተገኝታል ፡፡
መጠይቅ 3 ህጻናቶች ጠዋት ቀድመው በመምጣታቸው እና በሽኝት ሰአት ቶሎ ባለ
መወሰዳቸው የሚገጥማችው ችግሮች ምንድን ናቸው?

ተብሎ ለተጠየቀ ጥያቄ ከወላጆች ፣ጥበቃ፣ ከመምህራን እና ከሞግዚት የተሰጠ


ምላሽ ስንመለከት፡-

በወላጆች መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት ፡- ህፃናት ቶሎ በመምጣታቸው እና


በስዓታቸው ባለ መወሰዳቸው የሚደርስባቸው ችግር በተባለው በተጠየቁት
የሰጡት መልስ፡- ፍርሃትና ትካዜን ይፈጥርባቸዋል፡፡

በልጆቹ ላይ የብቸኝነት ስሜት ይፈጥራል፣ማዘን፣መተከዝ፣በራስመተማ


መንማጣት፣ ያለመፈግ እና ባለቤት የማጣት ስሜት ይፈጥርባቸውል፡፡

የበታችነት ስሜት ግራ እንዲጋቡ ያደርጋል ከልክ በላይ እንዲደክሙ ያደርጋል ፡፡


የስነ- ልንቦና ጫና ይፈጥረል፡፡
ትምህርት ቤቱን እንዲጠሉ ያደርጋል፡፡
ጥበቃ መጠይቅ በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት
የእኛ የስራ መወጫ ሰአት ስለሆነ ተቀያሪ እስኪ መጣ ህጻኑን ብመለከት እንኳን
የብቸኝነት የሰማዋል አልቅሶ ከግቢ የመውጣት ሙከራ እና መጫወቻ ላይ
ተንጠልጥሎ መውደቅ አጋጥሞናል ያውቃል ብለዋል፡፡

ከመምህራን መጠይቅ በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት


 ፆታዊ ጥቃት ሊጋለጡ ይችላሉ፤
የመፍራትና የብቸኝነት ስሜት በስፋት ይታይባቸዋል፤
ለተለያዩ አካላዊ ጉዳት ተጋላጭ ይሆናሉ፤
በሚደርስባቸው ችግር ምክንያት ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ፤
ፍርሃት ይነግስባቸዋል፤
በራሳቸው እንዳይተማመኑ ይሆናሉ፤
የተጠሉ ይመስላቸዋል፤
ከሞግዚት መጠይቅ በተመለከተ የተሰጠ አስተያየት
ከልክ በላይ መጨነቅና ማልቀስ፤
ለአደጋ የተጋለጡ ይሆናሉ፤
በራስ መተማመን ይጠፋል፤
ይረበሻሉ፣ይጨነቃሉ እንዲሁም ያለቅሳሉ፤
ከትምህርት ቤት ግቢ መውጣት መጥፋት ፤
በአካል ደግሞ መውደቅ እና መሰበር ይደርስባቸዋል፡፡
ጠቅለል አድርገን ስናየው በዚህ መጠይቅ አስተያየት እንዲሰጡ ከተጋበዙ
ከጥበቅ፣መምህራን፣ወላጆች እና ሞግዚቶች የተገኘው ግኝት ልጆች በጠዋት
በመምጣት እና ማታ ቶሎ ባለመወሰዳቸው የመፍራት፤ የብቸኝነት ስሜት
በስፋት ይታይባቸዋል፤በሚደርስባቸው ችግር ምክንያት ጭንቀት ውስጥ
ይገባሉ፤ፍርሃት ይነግስባቸዋል፤በራሳቸው እንዳይተማመኑ ይሆናሉ፤የተጠሉ
ይመስላቸዋል ፡፡ይህ በመሆኑ በሕፃናቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሥነ ልቦና ጫና
ከማድረሱም በበላይ በትምህርት አቀባበላቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሣድራል፡፡

በተጨማሪም ለከፋ ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ በመሆኑ ለተለያዩ አካላዊ


ጉዳት ተጋላጭ መሆን፤ጾታዊ ጥቃት ሰለባ መሆን፤የጠለያየ ጉዳ የሚያደርሱ
ነገሮችን በመነካካት በህይወታቸው ላይ አደጋ ለሚፈጥሩ ነገሮች ተጋላጭ
ይሆናሉ፡፡

መጠይቅ 4 ችግሩን ካዩ(ካወቁ)ጀምሮ ለመፍታት ሙከራ አድርገዋል ?

አዎ --------- አይደለም-------

ከወላጅ ከመምህር ከሞግዚት ጥበቃ

አዎ አይደለም አዎ አይደለም አዎ አይደለም አዎ አይደለም


7 3 2 4 2
ወላጆች መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት ፡- ይህንን ችግር ለመፍታት
አብዛኛው ወላጅ በተቻለ መጠን ለልጆቹ ቶሎ ለመድረ እና ጠዋትም በስዓቱ
ለመድረስ ጥረት እንደሚያደርጉ ሀሳብ ሰተዋል ሃሳብ ከሰጡት አስር ወላጆች
ውስጥ ሶስት የሚሆኑት ልጆቻችንን በፈለጉት ስዓት ወደ ትምህርት ቤት
የሚያመጡ እና የሚወስዱ ናቸው፡፡ በመልካም ፍቃደኝነት ለቅሶ ወይም
ማህበራዊ ጉዳይ ሲያጋጥም ልጆቹን ከእኛ ልጅ ጋር እንወስዳለን ብለዋል ፡፡

ጥበቃ መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት ፡-ይህን ችግር ለመፍታት እናቱን የኑሮ


ጫና በማየት ብቻ በቂ ነው፡፡ተተኪ ጥበቃ እስኪ መጣ በአጠገቤ አስቀምጣለሁ
መምህርም ሰአቱ ደርሶ ይመጣሉ ለነሱ እሰጣለሁ ብለዋል፡፡

ከመምህራን መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት ፡-


ለዚህ መጠይቅ መምህራን ምንም እንኳን ጠዋት ቀድመው ቢያመጡ ከስዓትም
ዘግይተው ቢወስዱ እንደ መምህር በየግዜው ከወላጆች ጋር ተነጋግረናል፡፡
በተቻለ መጠን እንደ መምህር በጠዋት በመገኘት ልጆቹን መቀበል እና ማቆየት
ከስዓት ልጆቻቸው መጥተው እንዲወስዱ በስልክ በማስጠራት ስራ ሰርተናል የሚል
አስተያየት አስቀምጠዋል፡፡

ሞግዚቶች መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት፡-

እንደ ሞግዚት ለዚህ ችግር የወሰዱት መፍትሄ ቀድሞ መገኘት ከስዓት በስዓቱ
መጥተው እንዲወስዱ ማድረግ በተጨማሪም ህፃናቱን ቤታቸው ድረስ የማድረስ
ስራም ተሰርቷል የሚል አስተያየት ተሰቷል፡፡
ይህ መጠይቅ ሲጠቃለል አብዛኛው ወላጅ የልጁን መግቢያ እና መውጫ ስዓት
አክብሮ በመምጣት በመምህራን ፣ በሞግዚቶች እና በአጠቃላይ በትምህርት ቤቱ ላይ
የመደርሰውን የህፃናት በጠዋት መምጣትና ዘግይቶ የመውሰድ ችግር ጫና ለመፍታት
የራሰን ጥረት የሚያደርግ ነው፡፡
ይህን መጠይቅ አስተያየት ከሰጡት አስር ሰዎች ውስጥም ሰባቱ 70% ይህንን
ያደርጋሉ ነገር ግን ሶስቱ አስተያየት ሰጡት 30% የሚሆኑት ደግሞ ችግሩን ለመፍታት
ሙከራ ያላደረጉት ናቸው፡፡
እንደ አንድ መጠይቅ ላይ ችግሩን የሚያውቁ ቢሆኑም የልጆቻቸው ችግር ግን
መፈታት ያለባቸው እነርሱ ሚናቸውን ጭምር አያውቁም ቢያውቁም ለመፍታት
ጥረት አያደርጉም፡፡
እንደ መምህራን እንደ ሞግዚትም ሲታይም ያለውን ችግር በአግባቡ ተለይቷል
በተቻለ መጠን ችግሩን ለመፍታት የራሳቸውን ሃላፊነት ተወጥተዋል፡፡ ከሃላፊነት
የዘለለ ህፃናቱን ቤታቸው ድረስ መውሰድ በማቆየት፣ለወላጆች ስልክ ደውሎ በመንገር
ሲመጡ በማቀበል እና በመኖሪያ ቤት ድረስ ልጆቹን ተቀባይ ካለ በማድረስ ተችሏል፡፡

መጠይቅ 5 . ለሚፈጠሩ ችግሮች ምን ዓይነት የመፍትሄ ሃሳብ ያቀርባሉ ?

ወላጆች መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት ፡- ቀድሞ በመምጣታቸው እና ዘግይቶ


በሚወሰዱበት ግዜ የሚፈጠሩ ችግሮችን መውሰድ አለባቸው የተባለ የመፍትሄ
ሀሳቦች ወላጆች በየእለቱ ያለባቸውን ችግር ለትምህርት ቤቱ ማስረዳት፤አስፈላጊውን
ውይይት ማድረግ፤ በስዓቱ መስጠት እና ቀድሞ በመገኘት ልጆቹን መረከብ፤
በኮሚኒኬሽን ደብተር፤በስልክ፤ በቴሌግራም ቻናል መጠቀም ቢቻል፤ የተለየ ስዓት
ጥበቃ ቢደረግ ለሁሉም ወላጅ የመግቢያ እና የመውጫ ስዓት ህገ ደንብ ላይ
መወያየት፤ጠንከር ያለ መመሪያ መስጠት ወላጅም የችግሩ ባለቤትም መፍትሄ
መስጠት የሚችል ቢሆን፤

ጥበቃ መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት፡-እኔ መፍትሄ ባገኝ ጥሩ ነበር እናቱ ስትሄድ


ያለቀሰ ልጅ ማባበል እንዳያለቅስ ማድረግ እንኳን አልቻልንም ብለዋል፤ የኑሮ ጫና
ሆኖባት ነው እንጂ ልጇን በዚህ ብርድ ጥላ አትሄድም የሚል አስተያየት ሰተዋል፡፡

ከመምህራን መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት፡- ከወላጅ ጋር መነጋገር በመግባባት


ችግሮቻቸዉ ላይ በመመካከር መፍትሄ ላይ መድረስ ቢቻል የሚል አስተያየት ሰተዋል፡፡
ከሞግዚት መጠይቅ በተመለከተ አስተያየት፡- ችግሩ እንዳይደርስ ቀድሞ በመነጋገር
የተለየ ችግር ያጋጠማቸውን ወላጆች ለትምህርት ቤቱ አስቀድሞ ማሳወቅ
እንዲችሉ ማሳሰብ፡፡

ይህ መጠይቅ ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ እንደመፍትሄ

ሐሳብ የተቀመተው የወላጆች እና ትምህርት ቤቱ ማህበረስብ

የተበቀ ግንኑነት መፍጠር፡፡ በተደጋጋሚ ችግሩን ሚፈጥሩ

ወላጆችን ለብቻቸው በመጥራት ማነጋገር፡፡ ወላጆች ያለባቸውን የኑሮ ሁኔታ


ልጆቻው ላይ ተፅዕኖ በሚያደርስ መልኩ ካለው መፍታት እንዲችሉ መግባባት እና
ከባለድርሻ አካል ሙያዊ ድጋፍ መጠየቅ፡፡ ለህፃናት ተማሪዎች በተቻለ መጠን
በአቅራቢያቸው ባለ ትምህርት ቤት የመማር እድል እንዲያገኙ ማድረግ፡፡

ለትብብሮ ብድጋሚ አመሰግናለሁ!!!


ምዕራፍ ሶስት

የጥናቱ ዉጤት የመፍትሄ ሃሳቦች አተገባበራቸው

 ከመምህሮች እና ከሞግዚቶች ጋር በመወያየት ለትምህርት ቤቱ ቅርብ የሆነ


በትብብር በበጎ ፍቃደኝነት ፕሮግራም በማዉጣት ቀድሞ በመገኘት ልጆቹን
በመረከብ ወላጆችን ማገዝ ያጋጠማቸውን ችግሮች በጋራ መፍታት፡፡

ለወላጆች ቀድመው ሲመጡ የሚገጥማቸውን ችግሮች ማስገንዘብ፡፡

ሌላ ልጆቹን በዛች ሰዓት የሚተባበር ጎረቤት ወይም ዘመድ መፈለግ፡፡

በአቅራቢያቸው ሕፃኑም ሆነ ወላጅ የሚታወቅ ሰው ሐላፊነት

የሚሰማው ጠዋት ሲመጡ እና በሽኝት ሰአት በክፍያ

ማመላለስ፡፡

ከወላጅ( አሳዲዎች ) የሚጠበቀው

 ወላጅ በየጊዜዉ ልጆች የደረሱበትን ምን እንደገጠማቸው ለማወቅ ከመምራን

ጋር ፊት ለፊት ወይም ስልክ በመጠቀም መከታተልና ለማወቅ መጣር፤

 ከመምህሩ የሚሰጠውን ምክሮች በጥሞና ማዳመጥና በትክክል መስራት


መተግበር፤

ከመምህራን የሚጠበቀዉ
• መምህር ባጋጠመ እክል ሁሉ ችግር ፈቺ እና ማህበረሰቡን የሚያገለግል መሆኑን

ሁሌ ማሰብ ፤

• ከወላጅ ጋር ቀጣይነት ያለዉ ምክክር ማድረግ፤


• ለሕፃናቱ በተግባር የተደገፈ ትምህርት መስጠት ራሳቸውን ከአደጋ

ለመጠነቅ(ለመከላከል)ግንዛቤ መፍጠር፤

የመፍትሄ ሃሳቦች አተገባበራቸው የጥናቱ በአግባቡ ለማካሄድ ይመች ዘንድ


የጊዜ ድልድል መስራት ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ለሚከተለው ተግባራት እና
የተመደበላቸውን ጊዜያት እንደሚከተለው ተገልፃል፡፡
ተ.ቁ የሚከናወኑት ተግባራት የመከወኛ የግዜ ድልድል

ጥቅም ህዳር ታህሳስ



1. የሚጠና ችግር መለየት 
2. ችግሩ የደረሰበት ህፃን 
መለየት
3. ቃለ መጠይቅ ማካሄድ  
4. ከጥናቱ አካላ ጋር መወያየት   

5. የድርጊት ምርምሩን ወደ 
ፅሁፍ መቀየር
ለጥናቱ የተመደበ ባጀት

ጥናቱ የተመደበ በጀት ማለት ጥናቱን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ወጪዎች


በሚከተለው መንገድ ታቅዳል፡፡

ተ.ቁ የሚፈለጉት ቁሳቁስ የሚፈለግ ምርመራ


የገንዘብ
መጠን
1. ወረቀት እና እስኪቢርቶ 100 ብር እንደ አስፈላጊነቱ
ሊጨምር ይችላል፡፡
2. የትራንስፖርት 240 ብር እንደ አስፈላጊነቱ
ሊጨምር ይችላል፡፡
3. የሞባይል ካርድ 200 ብር እንደ አስፈላጊነቱ
ሊጨምር ይችላል፡፡
4. ለማፃፍያ፣ ለኮፕ እና ለመጠለዝ 1,300 ብር እንደ አስፈላጊነቱ
ሊጨምር ይችላል፡፡
5. ጠቅላላ ድምር 1,840 ብር

የጥናቱ የተገኙ ለዉጦች

ህጻናት ጠዋት ቀድመው ሲመጡ እና በሽኝት ሰዓት ወላጅ ሲቆይባችው


በሚደርስባቸውን ተጽእኖ ለመቅረፍ የአጼ ቴዎድሮስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ
መምህራን ችግሩን በትኩረት በማጤን ሁኔታው ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመሰጠት
የችግሩን ባለቤቶች በቅርብ በማወያየት ችግሩ የት እንዳለ በተደረገው ጥረት በቅድመ
አንደኛ ትምህርት ቤት ውስጥ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ህጻናትን ችግር በመውሰድ
የህጻናቱን ችግር በቅርብ በማጤን ከሕጻናቱ ሁኔታ በመገንዘብ ይህንን ችግር
ለመቅረፍ ይህንን ጥናትና ምርምር አድረገናል፡፡
በዚህ ጥናት የአገኘነው መረጃ መሰረት ከወላጅ፣ በመምህር እና ከሞግዚት
በተጨማሪም ከህጻናት ጋር በመነጋገር የህጻናቶቹን ችግር በመረዳት ሕጻናት በማለዳ
ጠዋት ከ 1፡30 በፊት ግቢ ሲመጡ እና በሽኝት ሰአት ለብቻቸው ሲቀሩ
የሚደርስባቸውን ስሜታዊ፣ አካለዊ ፣ ማህበራዊ እና የሞራል ጉዳቶችን ለመቀነስ
ችግሩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እና ከሌሎች ወላጆች መረጃን በመሰብሰብ
ከትምህርት ቤት ማህበረሰብ እና ከመምህራን በአገኘነው መረጃ መሰረት ከላይ
የተጠቀሱትን የህጻናት ጉዳቶችን በአመዛኙ በቤተሰብ ሁኔታ በቤተሰብ የስራ ሰዓት
አለመጣጣም የአካባቢ ርቀት የቤተሰብ ብቻ ልጅን ማሳደግ በተጨማሪም
የቤተሰብ ቸልተኝነት መሆኑን በአደረግነው ጥናት ተረድተናል፡፡
የዚህ ጥናት አላማ የህጻናትን ችግር ለመቅረፍ መጠን የተጠቀሱትን ህጻናት
ቤተሰብ በማወያየት ችግሩን እንደ ችግሩ ሁኔታ በመመልከት የህጻናቱን ወላጅን በግል
በማነጋገር የችግራቸውን መፍትሄ በጋራ በመፈለግ ጠዋት ከ 1፡30 ቀድመው
የሚመጡ ህጻናትን ችግር ለመቅረፍ የህጻቱ ወላጆችን በመጥራት ችግሩን በመረዳት
ህጻናት ሊደርሰባቸው የሚችለውን ጉዳት በግልጽ በመንገር ለወላጆች በማስረዳት
ህጻናት በሰዓት እና በግዜ መምጣት እና መሄድ እንዳለባቸው በመነጋገር በዚህም
ወላጅ ህጻናትን ብቻቸውን ጥሎ መሄድ እንደሌለባቸው ህጻናቱን ለሞግዚት ወይንም
ለመምህርት ሰተው መሄድ እንዳለባቸው በመነጋገር ችግሩን ለመቅረፍ ችለናል፡፡
በቀጣይ የተመለከትነው ህጻናት በሚሸኙበት ጊዜ በቶሎ እና በሰዓቱ የማይሄዱ
ህጻናትን በተመለከተ የህጻናቱን የቤተሰብ ሁኔታ በማጥናት ህጻኑን ሁኔታ
በመመለከት የህጻኑን ቤተሰብ ወይም አሳዳጊ በመጥራት በመወያየት በስራ ምክንያት
የሚቆዩትን ህጻናት ሁኔታ ወላጅ ወይንም አሳዳጊ በግዜና በሰዓቱ እንዲመጣ
በተጨማሪም በእናት ብቻ የምታድገው ህጻን ደግሞ የተወሰነ ግዜ ሞግዚቶች እና
መምህራን የራሳቸውን እገዛ ቢያደርጉም ችግሩ ሊቀረፍ ባለመቻሉ የህጻንዋን እናት
በግለጽ ስለ ህጻንዋ ሁኔታ ማሰብ እንዳለባት ካልሆነም በቤትዋ አካባቢ ህጻንዋን
እንድታስተምራት በመንገር ሀሳባችንን አካፍለን ነገር ግን የህጻንዋ ወላጅ ህጻንዋን
የምታመላልስ ሰው በመቅጠር በአሁኑ ሰዓት ህጻንዋ በግዜ እና በሰአቱ እየሄደች
ትገኛለች፡፡
በመጨረሻም የተመለከትነው ህጻን በቤተሰብ ቸልተኝነት ምክንያት በሰዓቱ የማሄድ
ህጻን ሲሆን ይሄ ህጻን በሰዓቱ እና በግዜ መሄድ እንዳለነት ህጻኑ ብቻውን ብዙ ጉዳቶች
ሊያጋጥሙት እንደሚችሉ ቤተሰብ ሀላፊነት መውሰድ እንዳለበት በግልጽ በመንገር
ችግሩን ለመቅረፍ ችለናል፡፡

የጥናቱ የማጠቃለያ ሪፖርት


ይህ ጥናትና ምርምር በአደረግነው ዳሰሳ መሰረት ህጻናት በሚሸኙበትና ጠዋት
አስቀድመው ሲመጡ የሚገጥማቸውን ተጽእኖ እና ተግዳሮት ለመቀነስ
በአደረግነው ጥረት ከችግሩ አካላት ህጻናትን ከሚንከባከቡ ሰዎች ከመምህራን
ከሞግዚቶች በአገኘነው ሃሳብ መሰረት በቅድሚያ የህጻናትን ሽኝትና ጠዋት ሲመጡ
ያሉትን ሁኔታዎች በዝርዝር በመግለፅ የህጻናት ቤተሰብ በጠዋት ስራ መሄድና ህጻናት
በሚሸኙበት ሰዓት ቶሎ አለመምጣት ፣ የአካባቢ ርቀት ፣ ህጻናትን የሚያመላልሱ
ቤተሰቦች አዛውንቶች እና አረጋውያን በመሆናቸው በተጨማሪም ህጻናቱን
ለመውሰድ የተላኩ ሰዎች ግዴታቸውን ባግባቡ ባለመወጣት እና አንዳንድቸልተኛ
ቤተሰብ ስለሆኑ ይህ ጥናትና ምርምር እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሀሳቦች የተለያዩ
አካላትን ያካተተ ሲሆን የህፃን ችግር በሰኔ ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት
ቤት ወንድ አንድ ሴት ሁለት ህጻናት ላይ በአደረግነው ጥናት ለችግሩ መንስኤ ነው
ብለን የወሰድነውን መፍትሄ ወላጆች ቀድመው በጠዋት ከ 1፡30 በፊት ህጻናትን
ጥለው የሚሄዱት የራሳቸውን ስራ እንጂ የህጻናቱን ችግር ያለማሰብ በመሆኑና
የህጻናቱ መኖራያ ቤት እና የትምህርት ቤቱ መራራቅ በተጨማሪም ህጻናትን
የሚያመላልሱት አካላት አቅም ማነስ እና ቸልተኛ መሆን ሌላ ህጻናትን
የሚያሳድጉት አካላት ብቸኛ መሆን ማለትም በእናት ወይም በአባት ብቻ ጋር አብሮ
መኖር ሲሆን ለህጻናቱ ችግሩ የከፋ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከላይ የተጠቀሱትን
ችግሮች በማጤን በሰኔ ዘጠኝ ቅድመ አንደኛ መምህራን ህጻናትን በአራቱም የመዳበር
አቅጣጫ እነሱም በአካል፣ በአእምሮ፣ በማህበራዊ እና በስሜት የማዳበር ባለው
አላማ መሰረት የህጻናትን ችግር ተገንዝቦ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር
የችግሩን አካላት በቅርብ በማወያየት በህፃናት ላይ የሚደርሰውን ችግር ለመቅረፍ
ችለናል፡፡ ነገር ግን በህፃናቱ ላይ የሚደርሱ አልፎ አልፎ ይህ ችግር ቢከሰት የተቋሙ
ጥበቃ መምህራን እና ሞግዚቶች ህፃናት ሳይረበሹ እና ሳያለቅሱ ለወላጅ ለማቆየ
የራሳቸውን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ናቸው፡፡

ጥናቱን ለማድረግ የሚያጋጥሙ ችግሮች


ይህን ጥናት ለመስራት የሚያጋጥሙን ችግሮች ለጥናቱ ገንቢ ሃሳብ አለመስጠት
፤መረጃን በትክል አለማካፈል፤የጥናቱን ሃሳብ አለመረዳት፤መጠይቆቹን በአግባቡ
አለመሙላ መጠራጠር እና የወላጆች ፍቃደኛ አለመሆን ናቸው፡፡

አስተያየት

የህፃናትን በተመለከተ የነገ ተስፋ በመሆናቸው ማህበረሰቡ፣መምህራን፣

ሞግዚቶች እና ወላጆች የሚመለከተው የመንግስት አካል የግድ ሀላፊነቱን መወጣት

አለበት፡፡ ከወላጅ ጋር ጥሩ ግንኙነት በመፍጠርም በመመካከር የህፃናትን ደህንነት

እንክብካቤን ማሻሻል እና መለወጥ ይቻላል፡፡

ዋቢ መፅሀፍት
የህጻናት መብት ኮንቬንሽን፤ክፍል 1 ገጽ 9

የአፍሪካ ህጻናት መብቶችን ደህንነት ምዕራፍ ገጽ 3 እና 4


የአፍሪካ ደህንነት ምዕራፍ ገጽ 4
ዶ/ር ቤሰቫልንደር ኮልክ ጽፈዋ

You might also like