You are on page 1of 61

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ

አምላክ አሜን

በአ\ኅ\ደ\ም\ሰ\ት\ቤት ውስጥ በህፃናት

ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር
ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው
በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ህፃናት
ክፍል አባላት ዙሪያ የተደረገ ጥናት

በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰንበት ትምህርት

ቤት፳፯ኛ ዙር ኮርሰኞች የመመረቂያ ጥናት
1
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

አዘጋጆች፡-

1. ዳግም መለስ ንጉሴ

2. ናትናኤል ዮናስ እዮብ

3. ባምላክ ሀይሌ ታምራት

4. ዮሴፍ ሰለሞን ካሣ

5. ፍቃዱ ጥሩነህ አባተ

6. ብፅአት ብዙነህ በልሁ

7. ቅድስት ደጀኔ ሞላ

8. ስንታየው ግርማ በቀለ

9. ባንቺአምላክ ናፍቆት ውቡ

10. ሶስና ደምሰው ተስፋዬ

11. ትብለፅ ወርቁ ገብረወልድ

12. ፍሬህይወት ጌታቸው አዳነ

13. አለም ተክላይ ገብኪዳን

አማካሪ ፡- አብርሃም አበበ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

2
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

መቅድም (Preliminaries)
የሰው ልጆች በምድር ላይ ስንኖር ትውልድ ትውልድን እየተካ ዛሬ ላለንበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ሆኖም የማንኛውም
ሰው ትልቅ ወይንም አዋቂ ከመባሉ በፊት ያሳለፈው የእድሜ ዘመን ልጅነት ወይም ህፃንነት ነው፤ በሕይወት
ጉዞኣቸው ውስጥ የሚኖራቸው መልካምና መጥፎ ልማድ፤ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁበትና መሰረት
የሚጥሉበት ወቅት የልጅነት ግዜ ነው፡፡ ጥሩ ስነ ምግባር እና ብሩህ አእምሮ በልጅነቱ የያዘ ለኋላ አወንታዊ
አስተዋጽኦ ይኖረዋል፤ በአንጻሩ ደግሞ መጥፎ ጥሩ ስነ ምግባር እና ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ በልጅነቱ የያዘ ለኋላ
አሉታዊ የሆነ ተጽእኖ ያድርበታል ::

ሕፃናት የሰው ልጅ ሲፈጠር በስጋ ከሚወክሏቸው አራቱ ባህርያተ ስጋ መካከል በሆነው በነፋስ ይወከላሉ፤ ነፋስ
ያገኘውን ተራርጎ ይወስዳል በዚህ ይመጣል በዚያ ይመጣል ለማለትም ያስቸግራል፤ ቅዱስ ዩሐንስ በወንጌልም
እንዲህ ሲል ይጠቅሰዋል ‹‹ነፋስ ወደ ወደደው ይነፍሳልና ድምፁንም ትሰማለህ ነገር ግን ከየት እንደሚመጣ ወዴት
እንደሚሄድ አታውቅም›› ዮሐ 3 -8 ህፃናትም አንድ ቦታ ወስነው መቆየት አይወዱም፤ ደስ ወዳሰኛቸው ቦታ
ሲሄዱና ሲስቁ ሲጫወቱ እናያቸዋለን፡፡

በሌላ በኩል ነፋስ ያገኘውን ጠራርጎ ይሰበስባል ኃይሉ ሲጠነክር ደክሞ እስከ ጥፋት ሊደርስ ይችላል፡፡ ይህ
የሕፃንነት ዘመን ልጆች ከቤታቸው ከአካባቢያቸው በሚኖራቸው ግንኙነት ከሚያዩአቸው እና ከሚሰሟቸው
ነገሮች አኳያ በለጋ አእምሮአቸው እምብዛም ማመዛዘን ሳይችሉ ነገር ግን ከባድ ሆነ ስነ ምግባር ጉድለት ወደ
ህይወታቸው የሚንሰራራበት ዘመን ነው፡፡ ስድብን፤ ዘረኝነት እና ጥላቻን ውሸት፤ ታላላቆችን አለማክበር
የመሳሰሉትን እኩይ ባህርያትን የሚማሩበት ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ጥሩ እና መልካም የሆነ ስነምግባርን
የሚለማመዱበት ዘመንም ይሆናል፡፡
የደብራችን የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ህጻናት ክፍል
አባላት ላይ በየጊዜው እየታየ ባለው የስነ ምግባር ግድፈት ያላቸውን የአገልግሎት መንፈስ የሚቀንስ፣ የሚያዝል
እንዲሁም ከ አገልግሎት እስከ መጥፋት የሚያደርስ ተግዳሮት ይገጥማቸዋል፡፡ ይህም ጠንካራ የሆነ ቁጥጥር
ማነስ፣ የሥነ ልቡና ግንባታ ባለመኖራቸው፣ በሰንበት ት/ቤት ውስጥ እና ውጪ የሚኖረው ተጽእኖ፣ የቤተሰብ ፣
የማህበረሰብ፣ የአቻ ግፊት ወዘተረፈ… ተግዳሮት አስተዋጽኦ ይኾንባቸዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

3
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

በዚህ ጥናታዊ ጽሑፍ በአ/ኅ/ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት እያገለገሉ በሚገኙ ያሉ
የህፃናት ስነምግባር ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸውን ለማሳየት ተሞክሯል፡፡

ምስጋና (Acknowledgement)
በቅድሚያ ኀጢአታችንና ስንፍናችንን ሳያስብ፤ በጎዶሏችን ሁሉ እሞላ ሥራችን በሰላም አስዠምሮ በሰላም
ላስፈጸመን ሰማይ ዙፋኑ ምድር የእግሩ መረገጫ ለኾነችው ለመሐሪው አምላካችን ለልዑል እግዚአብሐየር ክብር፤
ምስጋና አምልኮ ውዳሴ ለርሱ ይኹን::

ምክንያተ ድኅነት ዘወትር ስለልጆቿ የምትለምን በስራችን ሁሉ በምልጃዋ ያልተለያችን የአምላክ ማደርያ
ቅድስት ቅዱሳን ንጽሕተ ንጹሐን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይኹን፤

ረድኤቱ ጠብቆ በምልጃው ደግፎ ለዚች ሰዓት ላደረሰን ዘወትር ከፊታች የሚቀድምልን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ
ሚካኤል ምስጋና ይኹን፡፡ በቃልኪዳናቸው ጠብቀው፤

በደማቸው አፅንተው እውቀትንና ጥበብን ላስቀመጡል በምልጃቸው ለረዱን ቅዱሳን ሁሉ ምስጋና ይሁን፤

በመንገዳችን ሁሉ ለክርስቶስ ሙሽራው የሆነች የጥበብ መፍለቂያ የወንጌል መሰረት የጽድቅ ግምጃ ቤት
እንደማርና ወተት እውቀትን የሰጠችን ለእናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምስጋና ይኹን

ሳይሰለቹ ሳይታክቱ ለረዱንና ለእያንዳንዱ ጥያቄዎቻችንን መልስ ለሰጡን፤ ጊዜያቸውን ሰውተው በቃለ መተይቅ
በቡድን ውይይትና በጽሑፍ መጠይቅ ለተሳተፉ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት ዲ\ን ዳንኤል መኮንን ዲ\ን
ቃልኪዳን ደምሴ፣ ኢዮብ ዳንኤል ፣ ብንያም ወርቁ እግዚአብሔር አምላካችን አባታችን ረድኤቱን ያብዛልን፡፡

ግብአት የሚኾኑ ጽፎችን በመጠቆም ሐሳብና አስተያየት በመስጠት ከፍተኛ ትብብርን በማድረግ በምክሩ
ያልተለየን ወንድማችን ሐብተሥላሴ ሁንዴ ልዩ የሆነ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፤ ፈጣሪ ጥበብና ፀጋን
ያብዛልን በቤቱ በረድኤትና በረከት ያፅናልን::

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

4
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

በሐሳብ እና በምክር ላልተለየን ለወንድማችን አብርሃም አበበ እግዚአብሔር በቤቱ የሚጽናልን፤ በረከት ረድኤቱን
ያጎናጽፍልን፡፡

1.1.1 የጥናታዊ ጽሑፍ መነሻ ዐሳብ (Background of the study) 11

1.1.2 ጥናቱ የተሰራበት ቦታ (background of the organization) 12

1.4.1 አጠቃላይ ዓላማ (General objective) 15

1.4.2 ዝርዝር ዓላማ (Specific objective) 16

2.1.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ህፃናት አስተዳደግ 20

3.1.1 የጥናቱ ስልት (Research methodology) 20

3.1.2 የጥናቱ ስልተ-ቅየሳ (Research design) 21

3.1.3 የመረጃ ምንጭ (Source of data) 21

3.1.4 የናሙና አወሳሰድ ስልት (sampling method) 21

3.1.5 የመረጃ ምንጭ አካላይ (population) 21

3.1.6 የመረጃ ናሙና አወሳሰድ ስልት (Sampling Size) 22

3.1.7 ጥናቱ የሚዳስሳቸው ቦታዎች (Sample Location) 22

3.2.1 በጽሑፍ መጠይቅ (questionnaire) 22

3.2.2 መዛግብት 22

3.2.3 ቃለ መጠይቅ 22

3.3.1 የመረጃ መተንተኛ (Data Analysis and Interpretation) 23

ለተወካዮች 24

ለህጻናት 29

የወላጆች 35

ሀ. የወላጆች አስተዋፅኦ 46

ለ. የሰንበት ት\ቤት አስተዋፅኦ 47

ሐ. ከማህበረሰቡ የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በብቃት ማለፍ ይጠበቅብናል 50

የጽሑፍ መጠይቅ 51

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

5
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

የጽሑፍ መጠይቅአባሪ (APPENDIX) ሐ 55

ማውጫ 2

ሰንጠረዥ 1 ፡ ተወካዮች እና መምህራን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ያገለገሊበትን ዘመን ለማወቅ ባዘጋጀነው

ጥያቄ

ሰንጠረዥ 2፡ ምላሽ ሰጪዎች በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ ስለማግኘታቸው ተጠይቅው የሰጡት

ምላሽ

ሰንጠረዥ 3 ፡ ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን እንደሚመስል ተጠይቀው የሰጡት

ምላሽ

ሰንጠረዥ 4 ፡ ተወካዮች ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ምን ያክል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 5 ፡ ለህጻናቱ ሥለሚሰጣቸው ትምህርት ተጥይቀው የሰጡት ምላሽ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

6
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 6 ፡ተወካዮች ለህጻናት አርአያ መሆን ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 7 ፡ምላሽ ሰጪዎች ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ እንደሚረዷቸው

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 8 ፡ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስዱ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 9 ፡ ህፃናት ሰ/ት/ቤት ከመጡ ጀምሮ አወንታዊ የሆነ የስነምግባር ለውጥ እሚያሳዩ እንደሆነ ለማወቅ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 1. ህጻናቱ በዙፘቸው ካሉ ሰዎች ማንን እንደሚቀርቡ ለማወቅ የጠየቅነው ጥያቄ

ሰንጠረዥ 2. ልጆች ትርፍ ጊዜያቸውን ምን በማድረግ እንደሚያሳልፉ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 3. ትምህርት ቤት ውስጥ አብረቸው የሚሆኑት ጓደኞቻቸው የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

እንደሆኑ

ሰንጠረዥ 4. በትምህርተ ቤታቸው አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም ቦታዎች

እንዳሉ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ሰንጠረዥ 5.ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻቸው እንደሚያስተምሩ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ሰንጠረዥ 6. በህጻናት ክፍል ውስጥ ስትገለግሉ ያጋጠማቸው ችግር እዳለ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

7
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 7. ስንበት ትምህርት ቤት ያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን ያቆሙ ጓደኞች እንዳላቸው ተጠይቀው የሰጡት

ምላሽ ፡

ሰንጠረዥ 8.ሰንበት ትምህርት ቤት መማራቸው ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው ረድቷቸው እንደሆነ ተጠይቀው

የሰጡት ምላሽ ፡

ሰንጠረዥ 9.መንፈሳዊ መጽሃፎችን እንደሚያነቡ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ሰንጠረዥ 1 ፡ ልጆች በቀን ምጸሃፍ ምን ያክል ሰዓት እንዲያነቡ እንደሚያረጉ መምዘኛ

ሰንጠረዥ 2 ፡ ከልጆች ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች እንደሚወያዩ መመዘኛ

ሰንጠረዥ 3 ፡ ልጆች ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ የሚደረግን ክትትል ምምዘኛ

ሰንጠረዥ 4 ፡ ልጆቻቸውን በሃይማኖት ስነምግባር አሳድገው እንደሆነ ጠይቀን የተሰጠን ምላሽ

ሰንጠረዥ 5 ፡ ልጆቻቸውን ከስንበት ትምህርት ቤት ውጪ ካሉ የማህበረሰብ ክፍል ጋር ምን አይነት ግንኚነት

እንዳላቸው ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ሰንጠረዥ 6 ፡ ልጆቻቸው ስንበት ትምህርት ቤት መማሩ\ሯ አለማዊ ህይወታቸው ላይ ያለው አትወአጽኦ ምን

እንደሚመስል ያሳያል

ሰንጠረዥ 7 ፡ ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት እንደሚረይቁ ጠይቀን ያግውኘነው

ምላሽ

ሰንጠረዥ 8 ፡ የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ አስተዋጽአ እንዳለው ተጠይቀው የሰጡት

ምላሽ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

8
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 9 ፡ለልጆቻቸው በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ምን እንደሚመስል ተጠይቀው የሰጡት

ምላሽ

አጠቃሎ (Abstract)
በአጠቃላይ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድረል ሰንበት ትምህርት ቤት የህፃናቱ ስነ-ምግባር
ከቀን ወደ ቀን እየተዳከመና አስጊ የሚባል ሁኔታ ላይ እየደረሰ ይገኛል፡፡ የዚኽ ጥናት ዓላማ በአፍሪካ ኅብረት ደብረ
ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴራል ሰንበት ትምህርት ቤት ሕፃናት ክፍል ያሉ አገልጋዮች የስነ ምግባር ሁኔታዎች
መገምገምና የተሻለ የሚሆንባቸውን መንገዶችን ለመፍጠር እና ሰንበት ትምህርት ቤቷ ብቁ የሆኑ ኦርቶዶክሳዊ
ስነ ምግባር ላቸውን ህፃናት የማፍራት ደረጃ እንድትደርስ ለማስቻል ነው፡፡ ጥናቱ ያጠኑት አባላት በቀለም
ትምህርታቸውም ኾነ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ለጥናታዊ ጽሑፍ ዐዲስ መኾናቸው ተግዳሮት ኾኖባቸዋል፤
ቢኾንም ለጥናቱ እንዲያማክረን የተመደበልንን አማካሪ ድጋፍ በሚገባ በማግኘታችን አገልግሎታችን
አልተስተጓጎለም፡፡ የተሰበሰበውን መረጃ በጥልቀት መርምሮና አብራርቶ ለማሳየት ማብራሪያ ተኮር
(Descriptive Research Design)፡፡ የጥናቱ የመረጃ ምንጭ በይበልጥ የመዠመሪያ ደረጃ (ቀዳማይ) የመረጃ
መሰብሰቢያ መንገድ (Primary Data source) የኾኑ የጽሑፍ መጠይቅ፣ ቃለ መጠይቅ እና የቡድን ውይይት
እንዲኹም እንደአስፈላጊነቱ የኹለተኛ ደረጃ (ድኀራዊ) የመረጃ መሰብሰቢያ መንገድ (Secondary Data
source) የኾኑ ድኅረ ገጽ፣ መዛግብት ማገላበጥ፣ ጥናታዊ ጽሑፎች በጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በአጠቃላይ ሁኔታም
ለዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ 150 ሰዎችን በናሙናነት ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ
ሚካኤል ካቴድረል ሰንበት ትምህርት ቤት ህፃናት ላይ ወላጆችና ሰንበት ትምህርተ ቤት እንዲሁም ማህበረሰቡም
የየራሳቸው የሆነ አስተዋጽኦ አላቸው ከልጅነት እንዴት ተቃንተው እና በስነምግባር ታንጸው ማደግ እንደሚችሉ
የወላጆች እንክብካቤ እና ድጋፍ በማጠናከር በሰንበት ት\ቤት ተግባር ተኮር የሆነ ትምህርቶችን በመስጠት ንቁ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

9
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ዜጋን በማፍራት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ ሲኖረው በህጻናት በኩል ደግሞ ራስን ከማህበረሰቡ አሉታዊ ተጽእኖ
በመጠበቅ ለቤት ክርስቲያን እና ለሃገር የሚተርፍ ትውልድ መሆን ይቻላል።

ምሕጻረ ቃላት (Abbreviation and

Acronyms)
✔ አ/ኅ/ደ/ም/ ቅዱስ ሚካኤል ካ/ሰ/ት/ ቤት----- የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
ሰንበት ትምህርት ቤት
✔ ዓ.ም ……………….. ዓመተ ምሕረት

✔ እ.ኤ …………….. እንደ ኤሮፓውያን

✔ ዲ/ን ……………… ዲያቆን

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

10
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ምዕራፍ አንድ

1. የጥናታዊ ጽሑፍ ዳራ (Background)

1.1.1 የጥናታዊ ጽሑፍ መነሻ ዐሳብ (Background of the study)

እ.ኤ. ዘመን አቆጣጠር መስከረም 2 ቀን 1990 ጀምሮ ተግባራዊ እየሆነ ባለው የሕፃናት መብቶች ስምምነት መሠረትም እንደ
ሀገሩ ሕግ ከዚህ ባነሰ ዕድሜ ለአካለ መጠን ካልደረሱ በቀር ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች ዕድሜም የሆነ ሁሉ ሕፃን ነው::

ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው ታላላቅ አባቶች መካከል አባታችን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቀዳማዊ እንደገለጹት
ሕፃናት የሚባሉት እስከ አሥራ ስምንት ዓመት ዕድሜ ድረስ ያሉት በመሉ እንደሆኑ “ርትዕት ሃይማኖት” በሚል መጽሐፍ
ተጠቅሷል፡፡ በሀገራችን

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

11
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

የአንድ ልጅ ባህሪ ተለዋዋጭ ሲሆን በሳይንሳዊ ፣ በማህበራዊ እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ ጥገኛ ነው። ልጁ
ካደገበት ዓለም ጋር መላመድን ሲማር የሚያገኛቸውን ትልልቅ ሰዎች የሚያበሳጩ ወይም የሚያሳፍሩ አንዳንድ
ባሕርያትን ያዳብራል። አዋቂዎች ብዙውን ጊዜ እንዲህ ዓይነቱን ባሕርይ እንደ ችግር ባሕርይ አድርገው
ይለምናሉ።ሥነ ምግባር ማለት ደግነት፣ በጎነት፣ መልካም ጠባይ ማለት ሲሆን ክርስቲያን የሚለው ቃል
ሲጨመርበት ደግሞ የተሟላና የተለየ ያደርገዋል፡፡ መልካም ጠባይ ማንም ሰው ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን
የተሟላ ዘላቂና የሁል ጊዜ ሆኖም ለሰማያዊ መንግሥት የሚያበቃው በክርስትና እምነት ሲኖሩ ነው፡፡

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በሕገ ልቦና ሕገ ልቦና ማለት እግዚአብሔር አምላክ በልቦናቸው ሕግ እየደነገገላቸው
ምንም የተጻፈ ሕግ ያልኖራቸው ወይም በቃል ሳይነግሯቸው መልካም የሆነውን በልቦናቸው አውቀው የሚሠሩት
ሕግ ነው፡፡ ይህ ሕግ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ያለው 2256 ድረስ ነው፡፡ በሕገ ልቦና የነበሩ አባቶች መልካም
ሥራ ይሠሩ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ጻድቁ አብርሃም ከመልካም ሥራዎቹን ውስጥ ቤቱ
እንግዶችን እየተቀበለ በፍጹም ትሕትና እግራቸው እያጠበ ምግብን መጠጡን እያቀረበ ያስተናግድ እንደ ነበር
ተገልፃል፡፡ ‹‹ እግራችሁን የምትታጠቡበት ውኃ እስካመጣላችሁ ድረስ በዚህ ጥላ ሥር እርፍ በሉ . . . ጥቂት
ምግብ ይምጣላችሁ እንዳስተናግዳቸሁ ፍቀድልኝ›› ዘፍ. 18፥4

በአሁኑ ሰዓት ሕፃናት ከክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ይልቅ አለማዊ ጥፋት እየታየባቸው ሁኖ ይገኛል በምእራባውያን አኗኗር
በመነጠቅ ስለማንነታቸው፣ስለ ሃይማኖታቸው፣ ለሀገራቸው ያላቸው አመለካከትና ክብር፣ ዕውቀት እተመናመነ ሁኖ
እናገኘዋለን፡፡

በህፃናቱ ስነምግባር ለውጥ ላይ ከተለያዩ ቦታዎች የመሚመጡና በተለያየ ጊዜ የሚፈጠሩ ተጽእኖዎች ከፍተና ሚና
ይጫወታሉ፡፡ ከነዚህም መካከል ወላጆችና ሰንበት ት\ቤት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ ።

ወላጆች/አሳዳጊዎች/

የወላጆች የመጀመሪያው መምህራን እናትና አባት ናቸው፡፡ ልጆቻቸውን ከመውለድ እና መሰረታዊ ፍላጎቶችን
እያሟሉ ከማሳደግ ባሻገር ለመንፈሳቸውና ስጋቸው ሊጠቅሟቸው የሚችሉ የስነ- ምግባር ትምህርቶችን እለት
ተእለት በማስተማር ረገድ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅኦ አላቸው፡፡

ሰንበት ትምህርት ቤት

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

12
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሕፃናትን በምግባር ኮትኩቶና በትምሕርተ ሃይማኖት ቀርጾ ለማውጣት ሰንበት ት/ቤቶች ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን እየተስተዋለ ያለው ከ ሰንበት ት\ቤት የሚገባውን ውጤት ግን እየመጣ አይደለም
ይህንንም ደግሞ በግልፅ ማየት ይቻላል ከሰንበት ት\ቤት ወጥተዋል የሚባሉት ያሬዳዊ ዝማሬን እየገለበጡ የቤተ
ክርስቲያኗን ህግና ስርዓት እየሸረሸሩ እንደሆነ ይስተዋላል በህፃናት ረገድም እንዲሁ መልካም ምግባር ያላቸውን
ማየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው ማለት እንችላለን፡፡

1.1.2 ጥናቱ የተሰራበት ቦታ (background of the organization)

የአፍሪካ ኀብረት ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት እንደ ሰንበት
ት/ቤት ተዋቅሮ ከመመስረቱ በፊት ወንድሞችና እህቶች በወቅቱ የወኅኒ ቤቱ ግቢ ውስጥ መግባት ስለማይቻል
ከቅፅረ ቤተክርሰቲያኑ ውጪ በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አካባቢ ተሰብስበው መዝሙሮችን በማጥናት
ለጥምቀት በዓል ታቦት ያጅቡ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በ 1983 ዓ.ም ነሐሴ ወር የደብረ ምህረት ቅዱስ
ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ተቀብሎ በሰ/ት/ቤት ደረጃ ተዋቅሮ ተመሰረተ፡፡በመዋቅሩም
አባላቱን በዕድሜ ደረጃ በመክፈል በዕለተ ሰንበት መርሃግብር በማዘጋጀት አባላቱን ለዕድሜያቸው በሚመጠን
መልኩ ቃለ እግዚአብሔርን ማስተማር ጀመረ፡፡

እንዲህ ባለመልኩ በወኅኒ ቤቱ ቅጽር ግቢ ውስጥ አገልግሎቱ እየተሰጠ በ 1986 ዓ.ም ክረምት ላይ ከወኅኒ ቤቱ
ሐላፊዎች በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት ወደ ወኅኒ ቤቱ ግቢ ውስጥ መግባት እንደማይቻል ተገለጸ፡፡ ይህም በወቅቱ
ለነበሩ ምዕመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት መራራ መርዶ ነበር፡፡ በዚህም ለሰንበት ት/ቤቱ አባላት
“የሰንበት ትምህርት ቤታ የስደት ዘመን” የተሰኘ አሰቸጋሪ የአገልግሎት ወቅት ተጀመረ፡፡

ከዚህ በኃላ የሰንበት ትምህርት ቤታ አገልግሎት እንዳይታጎል በወቅቱ በነበሩ አባላት ከደብሩ አስተዳደርና
ምዕመናን ጋር በመተባበር አማራጮችን መፈለግ ያዙ፡፡ በዚህም መሰረት በአቅራቢያው የነበረውን የመሰረት
ሕይወት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በማሰፈቀድ ለሁለት ሣምንት ያህል በትምህርት ቤቱ መማሪያ
ክፍሎች ውስጥ ጉባኤ ሲደረግ ቆየ፡፡ ከዚህም በኃላ ከወኅኒ ቤቱ ቅጽር ግቢ ውጪ (በወኅኒ ቤቱ እስረኞች
ለመጠየቅ ለሚመጡ ሰዎች ወደ ውስጥ እስኪ ገቡ ድረስ በተዘጋጀ መጠለያ ውስጥ) አገልግሎቱ ቀጠለ፡፡

ይህ መጠለያ ጣርያ እንጂ ግድግዳ የሌለው መቀመጫው ከእንጨት የተሰራ ነበር ፡፡ ያም ሆኖ ሳምንታዊውን ጉባኤ
ለማካሄድ በመጠለያው መጠቀም የሚቻለው የታራሚዎቹ ጎብኝዎች ጉብኝታቸውን ጨርሰው ሲሄዱ ከቀኑ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

13
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

9፡00 ሰዓት በኃላ ባለው ጊዜ ውስጥ የወጣቶችና የህፃናት ሁለት ጉባኤያት አለባቸው፡፡ እነዚህን ጉባኤያት በተለያየ
ሰዓት ለማካኤድ ያለው የቀኑ ቀሪ ጊዜ በቂ ስለማይሆን ሁለት የተለያዩ ጉባኤያት በአንድ ቦታ በተመሳሳይ ሰዓት
ማካኤድ ግድ ሆነ፡፡ ይህም መጠለያውን መሃል ላይ በጆንያ በመጋረድ የላይኛውን ክፍል ሕፃናት በታችኛው ክፍል
ደግሞ ወጣቶች ተሰባስበው ቃል እግዚአብሔርን መማር በዝማሬ ማመስገን የራሱ የሆኑ የድምጽ መረባበሸ ነበር፡፡
የድምጽ ችግሩን ለመቅረፍ የትምህርት ፣ የሥነ - ፅሑፍና የመዝሙር መርሃ ግብሮች በሁለቱም ጉባኤያት ላይ
በተመሳሳይ ሰዓት እንዲካሄድ ተደረገ፡፡ በዚህም በተጨማሪ ቀደም ብሎ እንደተገለፀው መጠለያው ጣርያ እንጂ
ግድግዳ የሌለው በመሆኑ በበጋ ወራት ነፋስና ፀሐይ፤ በክረምት ደግሞ በነፋስ እየተገፋ የሚገባው ወጨፎ እና
ከታች የሚገባው የጎርፍ ውሃ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ይህ ጥረት የበጋውን ፀሐይና ነፋስ በከፊል ቢቀንሰውም
የወጨፎውንና የጎርፉ ችግር ለመቅረፍ እጅግ አስቸጋሪ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በዝናብና በጎርፍ ምክንያት አባላቱ
በጉባኤው ከመታደም እንዳለቀሩና የሰንበት ትምህርት ቤቱም ሳምንታዊ ጉባኤ ለአንድም ቀን እንዳልታጎለ
በወቅቱ የነበሩ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ያስታውሳሉ፡፡

ስደቱ በዚህ አላበቃም በመጠለያው ይደረግ የነበረውን ጉባኤ ከየካቲት በ 1988 ዓ.ም ጀምሮ ማካሄድ
እንደማይቻል አሁንም ከወኃኒ ቤቱ ኃላፊዎች ትዕዛዝ ተላለፈና ሌላ የስደት ምዕራፍ ተጀመረ፡፡ የመማሪያ ቦታ
ሲፈለግ ቆይቶ ቀድሞ በመጠለያው ውስጥ አገልግሎት ሲካኤድ በነበረበት ወቅት ወ/ሮ ንጋታ ብርሃኔ የተባሉ እናት
ግቢያቸውን ለመዝሙር ማጥኛ ፈቅደው ነበርና የመኖሪያ ግቢያቸው ውስጥ ዳስ ተጥሎ ከመዝሙር ባሻገር
ሳምንታዊ ጉባኤ መካሄድ ተጀመረ፡፡ በ 1989 ዓ.ም እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ አሁን ወዳለንበት ቦታ በመምጣት
አገልግሎቱ በቆርቆሮ አዳራሸ ውስጥ እስካሁን ድረስ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

የሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልግሎት ለአገልግሎት በሚመች መልኩ በሥራ አመራርና በሥራ አስፈፃሚ አባላት
የተዋቀረ ሲሆን ቀድሞ ከነበረው የአገልግሎት ዘርፍ ጊዜውን እና የአገልግሎት ስፋት ባገናዘበ መልኩ በአስር
ክፍላት ተዋቅረዋል፡፡ ይህም በሥራ አመራር ሦስት ክፍላት ሲሆኑ እነሱም ሕፃናትና ማዕከላውያን አሰልጣኝ፤
ሐዋርያዊ አገልግሎትና የሰው ኃይልና ንብረት አሰተዳዳሪ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በሥራ አስፈፃሚ ሰባት ክፍላት
ይገኛሉ ፤ እነርሱም መዝሙር ክፍል ፣ ኪነ - ጥበብ ክፍል፣ ትምህርት ክፍል፣ ግንኙነትና አባላት እንክብካቤ ክፍል፣
ጉባኤ አስተባባሪ ክፍል፣ ልማትና በጎ አድራጎትና ሚድያ ክፍል ናቸው፡፡

ከነዚህ ክፍላት መካከል ግንኙነትና አባላት እንክብካቤ ክፍል አንዱ ሲሆን በውስጡ ከያዛቸው ንዑስ ክፍላት መካከል
ውስጥ ውጭ ግንኙነት ንዑስ ክፍል አንዱና ዋናው ክፍል ሲሆን በውስጡም የተማሪዎች ህብረት ይገኛል፡፡ ይህ
የተማሪዎች ህብረት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለህብረቱም ይሁን ለደብራችን በመንፈሳዊና በአለማዊ
እውቀታቸው ልዩ ልዩ አገልግሎት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ ከከፍተኛ ተቋማት ሲመለሱ ጉባኤ በማዘጋጀት፤

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

14
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሕፃናትና ማዕከላውያን አለማዊውን ትምህርት በማሰጠናት ፣ በተለያዩ ክፍላት በመግባት እስከሚሄዱ ድረስ
ያገለግላሉ፡፡ (ምንጭ) በቃለ መጠይቅ የተገኘና ከሰ/ት/ቤታ ማዕደር የተወሰደ፣2008.2010 ዓ.ም

1.2 የጥናታዊ ጽሑፉ የችግር ምንነትና ሐተታ

(Statement of the problem)

ከሰንበት ትምህርት ቤታችን አገልጋዮች ፣ ከተማሪዎች እንዲሁም ከወላጆች ጋር ባደረግነው ውይይት

፣በትምህርት ሰአታቸው ላይ ተገኝተን እንደተመለከትነው ፣ በተለያዩ ጊዜያት በቤት ክርስትያን ውስጥ
በምናሳልፍበት ውቅት እንዳየንው ፣ በቤታችን እንዲሁም በአካባቢያችን ውስጥ እንደታዘብነው ልጆች
ኦርቶዶክሳዊ ይሆነ ስብእና ትላብሰው እያደጉ እንዳለሆነ ተመልክተናል ። ለዚህም ወላጆችን ፣ የሰንበት ትምህርት
ቤትን እና ማህበረሰቡን ዋና ምክንያቶች አድርገን አስቀምተናል ። በዚኽ ጥናት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን
ተገልጸዋል፤ በጥናቱ ፍጻሜም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፤ በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት የመፍትሔ ሐሳብ ይቀርባል፡፡
ለኦርቶዶክሳዊ የህጻናት አስተዳደግ የመጀመሪያው ትግዳሮት የሆነው በቤት ውስጥ ያለው የወላጆች አያያዝ
ሲሆን ሁለተኛው ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ በህፃናት ስነምግባር ላይ ያለውን ችግሮች ነው ሶስተኛው
ማህበረሰቡ በህፃናቱ ስነምግባር ላይ ያላቸው ሚና ነው በዚኽ ጥናት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ተገልጸዋል፤ በጥናቱ
ፍጻሜም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፤ በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት የመፍትሔ ሐሳብ ይቀርባል፡፡

1.3 የጥናታዊ ጽሑፉ ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic Research

Question)

በጥናታዊ ጽሑፉ ለመመለስ የታሰቡት የጥናትና ምርምር ቁልፍ ጥያቄዎች (Basic Research Question) የሚከተሉት

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

15
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ናቸው፡፡

● በቤት ውስጥ ያለው የወላጆች አያያዝ በህጻናቱ ስነምግባር ላይ ያለው ሚና ምንድን ነው?
● ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ በህፃናት ስነምግባር ላይ ምን አይነት ተጽእኖ አላቸው?
● ህፃናቱ ከማህበረሰቡ የሚቀባሏቸው ነገሮች በስነ ምግባራቸው ላይ በምን መልኩ ተግዳሮት ይሆንባቸዋል

1.4 የጥናታዊ ጽሑፉ ዓላማ (Objective of the study)

1.4.1 አጠቃላይ ዓላማ (General objective)

በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ህፃናት ክፍል አገልግሎት ላይ
ያሉ ህፃናትን በኦርቶዶክሳዊ ሥነ- ምግባር ማነጽ

1.4.2 ዝርዝር ዓላማ (Specific objective)

✔ የህጻናቱን ስነ ምግባር የተሻለ ለማድረግ በቤት ውስጥ ያለውን የወላጆች ምን አይነት መሆን እንዳለበት መግለጽ ፣

✔ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ በህፃናት አያያዝ ላይ ያለውን ችግር በመቅረፍ ዘላቂ የሆነ ለውጥ ሊያስከትል የሚችል
መፍትሄ ማቅረብ።

✔ ህጻናቱ ከማህበረሰቡ የሚመጣባቸወን ተጽእኖ እንዴት መቋቋም እና ማለፍ እንደሚችሉ መንገድ እናሳያለን ፣

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

16
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

1.5 የጥናታዊ ጽሑፉ ጠቀሜታ (significance of the

study)
ሀ. ለሰንበት ትምህርት ቤታችን

✔ መልካም ምግባር ያላቸውን ህጻናት የሚያፈሩበትን መንገዶች ያገኙበታል

ለ. ለህጻናቱ

✔ ከቤተሰብ እና ከሰንበት ት/ቤት ጋር ጠንካራና ግልጽ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያስችላቸዋል

✔ ጥሩ ስነምግባር እንዲኖራቸው ይረዳል
ሐ. ወደፊት በዚህ ርእሰ ጉዳይ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ

ቤተ ክርስቲያናችን እንዲኹም ከቤተ ክርስቲያናችን ውጪ ሆነው በተቀራራቢ ርእስ ጥናት ለማድረግ ለሚነሱ
ሰዎች እንደ መነሻ ወይንም ማጣቀሻ ይሆናቸዋል

መ. ለወላጆች

ልጆቻቸውን በጥሩ ስነ ምግባር እንዲያሳድጉ ይረዳል

ከልጆቻቸው ጋር ጤናማ የሆነ ግንኙነት እንዲኖራቸው ያግዛል

. ለጥናቱ አዘጋጆች

ይኼን ጥናት በማድረጋቸው የዚኽ ጥናት ተሳታፊዎች ከአምላክ የሚገኝ በረከት፣ የዕውቀት ሽግግር፣ የልምድ
እንዲኹ የመመረቂያ ነጥብ ያገኛሉ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

17
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

1.6 የጥናቱ ድንበር ወሰን (scope/ delimitation of

the study)
ይኼ ጥናት የተደረገው በደብራችን በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት
ቤት ህፃናት ክፍል ውስጥ በማገልገል ላይ ያሉ ዕድሜያቸው ከ 14 ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን መነሻ ያደረገ ነው።

1.7 የጥናቱ ተግዳሮትና ውሱንነት (limitation of the

study)
በዚህ ጥናት ውስጥ ከፍ ያለ ችግር የሚባለው በዚህ ርዕስ ዙሪያ የተሰራ ጥናት አለማግኘታችን ዋነኛው ሲሆን
ለጥናቱ ሰፋ አድርገን ለመስራት አልቻልንም፡፡

✔ በዚህ ርዕስ ዙሪያ የተሰራ ጥናት ባናገኝም መጽሐፍትን በማንበብ ፣ መጣጥፍቶችን በማሰባሰብ እንዲሁም
ከዚህ ርዕስ ጋር ተያያዥነት ይኖራቸዋል ያልናቸውን ጥናቶች አሰባስበናል ።
✔ ህጻናትን በተፈለገው መጠን ማግኘት አለመቻላችን የጥናቱን ናሙና የተሟላ ለማድርግ ተግዳሮት
ቢሆንብንም በአካል ልናገኛቸው የቻልናቸውን ለምሰብሰብ ሞክረናል
✔ በዚህ ጥናት ዙሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን ለመስራት የእውቀት እና ተደራሽነት አናሳ መሆን
ተግዳሮት ቢሆንብንም ፤ ጥናቱ በሚደረግባቸው አካላት ዙሪያ አነስተኛ ለውጥ ለማምጣት መምህራንን
በመጠየቅ መድረስ የምንችለው ያክል ተጉዘናል ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

18
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

1.5 የጥናታዊ ጽሑፉ አደረጃጀት (Organization

of the paper)
ይኽን ጥናታዊ ጽሑፍ በአምስት ምእራፍ/ክፍሎች/ አደራጅተን አቅርበናል፡፡ በምእራፍ አንድ መግቢያ፣በምእራፍ
ሁለት ተዛማጅ ጽሑፎችን ዳሰሳ፣ በምእራፍ ሦስት የጥናትና ምርምር አካሔድ ስልት፣ በምእራፍ አራት የጥናትና
ምርምር ትንተናና ፍቺ እንዲሁም በምእራፍ አምስት የጥናትና ምርምሩን መደምደሚያ እንዲሁም መፍትሔ
ሀሳቦችን ይዟዋል፡፡

1.6 የቃላት ፍቺ (Definition of Term)

ህፃን ፡- ማለት የአይን አምሮት የልብ ምኞት የሆነ፤ አራስ፤ ጨቅላ፤ ለጋ፤ ቀንበጥ፤ ጡት የሚጠባ ልጅ ፤
ለማይጠባም ናገራል ትረጓሜው የሚያድግ ማለት ነው እርሱም ወንዱን አበባ ሴቱን እማ ይላል፡፡ ( አለቃ ደስታ
ተክለ ወልድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት)
ኦርቶዶክስ ከግሪክኛ ቃላት «ኦርቶ» (የቀና፣ ርቱዕ፣ ትክክለኛ) እና «ዶክስ» (ትምህርት) የመጣ ቃል ነው፤ ቀጥተኛ የቀና
ትክክለኛ ትምህርተ የሚል ትርጉም አለው
እድገት፡- ውስጣዊ ችሎታ ለማዳበር, የተሻለ ፈተናዎችን ለመፈለግ, እና አዳዲስ ተሞክሮዎችን
በራስ-አስተሳሰብ ውስጥ ለማዋሃድ ማለት ነው
አስተዳደግ፡- አንድን ሰው ተቀባይነት ያለው የማህበረሰብ አባል እንዲሆን የማሳደግ፤ የገንቢ እና የስልጠና ሂደት
ማለት ነው

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

19
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሥነ ምግባር፡-ማለት የሰዎችን ተግባር በመጥፎነትና በጥሩነት መክፈል እንደሚቻልና፣ ይህ

ክፍፍል ሥርዓታዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ጥናት የሚያደርግ የፍልስፍና ክፍል ነው። የትኞቹ የሰው ልጅ
ተግባራት እኩይ ሊባሉ ይችላሉ? የትኞቹስ ሰናይ ሊባሉ ይችላሉ? ሥርቆት እኩይ ከተባለ፣ መግደል እንዲሁ እኩይ
ከተባለ፣ አንድ ሰው እህል ሰርቆ የተራበን ሰው እንዳይሞት ቢከላከል፣ ይህ ድርጊት እኩይ ነው ወይንስ ሰናይ? የቱ
መሆኑን መለየት ካልተቻለ፣ በርግጥ አንድ ወጥ የሥነ ምግባር ሥርዓት መገንባት ይቻላልን? ወይንስ ማናቸውም
የሥነ ምግባር ፍልስፍና በዘፈቀደ የተመረጠ ነው? እነዚህንና መሰል የሰው ልጅ ስለ ምግባሩ
የሚሰጠውን ዋጋ የሚያጠና ክፍል ሥነ ምግባር ይባላል።

ክርስቲያን፡- ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን

ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡
ሥነ፡- ማለት ሠናየ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ማማር' መዋብ ማለት ነው፡፡

ምግባር፡- ማለት ገብረ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም ተግባር ክንውን ማለት ነው፡፡

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፡- ማለት የክርስቲያን መልካም ሥራ ያማረ ተግባር የተዋበ ክንውን ወይም
በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና አዳኝነት ያመነ ሰው የሚሠራው መልካም/ያማረ ተግባር ማለት ነው፡፡
ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፡- በምድር እያለን ሰማያዊ ኑሮ ኖረን ለሰማያዊ መንግሥት የምንበቃበት ሕይወት ነው፡፡

ሰውን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን ማስደሰት ነውና፡፡ በመሆኑም ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በሚከተሉት ሕግጋት ሊለካ
ይችላል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

20
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ምእራፍ ሁለት

2.1 የተዛማጅ ጽሑፍ ዳሰሳ (Literature

review)
ማንም ወላጅ ቢሆን ልጁ ምግበረ ብልሹ ሆኖ ማየት አይፈልግም፡፡ ልጆቹ በመልካም ምግባር አድገው ለቁም ነገር
ሲበቁ ማየት ለወላጆች ስኬት ነው፡፡ ሰው የሚማረው ከቤት ጀምሮ በሰፈር ውስጥ፤ በትምህርተ ቤትና ማህበረሰቡ
ውስጥ ከሚያያቸውና ከሚሰማቸው ነገሮች ቢሆን ልጅን ግብረ ገብ አድርጎ የማሳደግ ድርሻ በዋናኝነት የወላጆች
ነው
(ሙሉጌታ አለባቸው. www.Ethiopress.gov.net)

ክርስያናዊ የልጆች አስተዳደግ በልጆች ላይ መንፈሳዊና ግብረ ገባዊ መሰረት ይጥላል ዘመናዊ ትምህርት
ደግሞአእምሮአቸው እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡ ዘመናዊ ትምህር ብቻውን ለልጆች ለመንፈሳዊና ስነ ምግባራዊ
እድገታቸው ይበቃቸዋል ብለን ማሰብ የለብንም፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች በዘመናዊ ትምህር በጣም
የተማሩ ሆነው እያለ ነገር ግን በህይወታቸው ጥሩ ስነ ምግባር የሌላቸው መንፈሳዊነት የማይታይባቸውና
አጠቃላይ ስብእናቸውና የሚናገሯቸው ቃላት እንዲሁም ለሰዎች ያላቸው ዐመለካከት ሻካራና የማይመች የሆኑ
ሰዎች አሉ በሌላ መልኩ ደግሞ ዘመናዊ የሚባለውን ነገር ምንም ያልተማሩ በገጠር ውስጥ የሚኖሩ ነገር ግን
የሚገርሚ, ስራዎችን የሚሰሩ በጣም ጥሩ ስነ ምግባር ያላቸው የሚናገሯቸው ቃላትና አጠቃላይ አመለካከታቸው
አስገራሚና ፍጹም መንፈሳዊ የሆኑ ሰዎች አሉ
(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ እና የልጆች አስተዳደግ ፡ ወይዘሮ ዘውዴ ገብረ እግዚያብሄር)

2.1.1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ህፃናት አስተዳደግ

‹‹ከሕፃንነትህ ጀምረህ ያልተመከርህ በእርጅናህ ጊዜ እንዴት ብልህ ትሆናለህ›› ሲራ 25-2
‹‹ያልተገራ ፈረስገርጋሪ ይሆናል፤ ያልተማረ ልጅም አውታታ ሆኖ ያድጋል›› ሲራ 30-2

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

21
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

‹‹ አባቶች ሆይ፤ ልኮቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጓቸው፡፡›› 1ኛ ቆሮ 14-35

<< ልጆች ቢኖሩህ ምከራቸው ከህጣንነታቸው ጀምረህ ሰቢረ ክሳድ አስተምራቸው›› ሲራ 7-5

‹‹ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍራን ያፈራል፡፡ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት ፤
ክፉ ዛፍም መልካም ዘፍን ማፍራት አይችልም›› ማቴ 7-17

ምእራፍ ሦስት

3.1 የጥናቱ አካሔድና ስልት (Research design and

methodology)
በአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ተወካዮች
እንዲሁም ወላጆች በልጆቹ ሰነምግባር ላይ ባላቸው ተጽእኖ ዙርያ የመሉትን መጠይቅ ላይ የተመሥርቶ የተዘጋጀ
ትንተና፡፡

3.1.1 የጥናቱ ስልት (Research methodology)

የጥናታዊ ጽሑፉን ርእሰ ጉዳይ ገጽታ አጉላቶ በማሳያት የተሰበሰበውን መረጃ በጥልቀት መርምሮና አብራርቶ
በማሳየት ገለጻ ተኮር (Descriptive Research) በጥቅም ላይ ውሏል፡፡

3.1.2 የጥናቱ ስልተ-ቅየሳ (Research design)

በዚኽ ጥናት ውስጥ ሁለት አይነት የጥናት ስትራቴጂ ማለትም ስሌታዊ / መጠናዊ (quantitative) እና ዓይነታዊ
/ገለጻ (qualitative) ወይም ጥምር (mixed methods) በጥቅም ላይ ውሏል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

22
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

3.1.3 የመረጃ ምንጭ (Source of data)

ስለ መረጃ ምንጮች በምንመለከትበት ጊዜ ሁለት አይነት መረጃ ምንጮች አሉ፡፡እነሱም

1.ቀጥተኛ (Primary)

2.በተዘዋዋሪ (Secondary)

● ቀጥተኛ (Primary) ፡- የመረጃ ምንጭ የምንለው መረጃን ስናሰባስብ በቀጥተኛ ከአንድ ሰው የምናገኘው
ሲሆን እኛም ይህንን የመረጃ ምንጭ በመጠቀም መረጃዎችን ማግገኝት ችለናል፡፡ ከላይ እነደተገለጸው
በጽሑፍ መጠየቅ በመበተን እና ቃለ መጠይቅ በማድረግ መረጃን ሰብስበናል፡፡
● በተዘዋዋሪ (Secondary) ፡- የመረጃ ምንጭ የምንለው መረጃን ከተለያዩ ነገሮች የምናገኘው ሲሆን
ለምሳሌ ፡- የድረ ገጽ ፤ ከዚ በፊት የነበረ ወይም የተሰራ ጥናታዊ ጽሑፍ ካለ ፤ ከነሱ የምናገኘው መረጃ
በተዘዋዋሪ የተገኙ መረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በፊት የተሰሩ ጥናታዊ ጽሑፍ ባናገኝም ግን ከድረ ገጽ ላይ
ያገኘናቸው የተለያዩ መረጃዎች አሉ ፤ እነዚህን መረጃዎች አንደ Secondary መረጃ አድርገን መጠቀም
ችለናል፡፡

3.1.4 የናሙና አወሳሰድ ስልት (sampling method)

የናሙና አወሳሰድ ስልት ዕድል ከልካይ (Non probability Sampling) ነው፡፡ ዕድል ከልካይ (Non probability
Sampling) መረጃ ለማግኘት በትክክል ይጠቅማሉ ተብለው የታመነባቸውን ለመምረጥ ዒላማ ናሙና
(purposive sampling technique) አጥኚዎቹ ተጠቅመዋል፡፡

3.1.5 የመረጃ ምንጭ አካላይ (population)

በሰንበት ትምህርት ቤታችን ህፃናት ክፍል ውስጥ ከመቶ በላይ ህጻናት አባላት እንዳሉ ይታመናል፡፡ በተቻለ መጠን
በኣማካይ ሁሉንም ህፃናት ለማካተት ይሞከራል ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

23
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

3.1.6 የመረጃ ናሙና አወሳሰድ ስልት (Sampling Size)

ይህን ጥናት በምናደርግበት ጊዜ የተጠቀምናቸው የናሙና አካላት / ህፃናት ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ስለሆነ የናሙና
ፎርሙላ ለመጠቀም አዳጋች ሆናል ስለሆነም የተመረጡ አካላትን በቁጥር ወስነን አስቀምጠናል በዚህም መሰረት
17 የህፃናት ተወካዮች፤ 75 ህፃናት አገልጋዮች እና 35 የህፃናት ወላጆችን አካተናል

3.1.7 ጥናቱ የሚዳስሳቸው ቦታዎች (Sample Location)

ጥናቱ በደብራችን ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ህጻናትን ፣ የህጻናት ወላጆችን ፣ ተወካዮችን እና የሰንበት
ትምህርት ቤቱን አባላት ብቻ ያካተተ ነው ።

3.2 የመረጃ የማሰባሰቢያ ዘዴ (Instrument of data

collection)

3.2.1 በጽሑፍ መጠይቅ (questionnaire)

በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ያግዛሉ ያልናቸውን አካላት በመምረጥ በጽሁፍ ጥያቄ ተጠቀይዋል ።

3.2.2 መዛግብት
የተለያዩ መጻሕፍት፣ ጥናታዊ ጽሑፍ፣ መጽሔት በማንበብ መረጃ ተሰብስበዋል፡፡

3.2.3 ቃለ መጠይቅ
የዚኽ ጥናት አዘጋጆች ከሰበሰቧቸው መረጃዎች በተጨማሪ ሥራ አመራሮች እንዲኹም በቀላሉ ያላገኙትን
የመፍትሔ ሐሳች የተሻለ እውቀት እንዳላቸው ከሚታመንባቸው አባላት ለማግኘት ብለው ቃለ-መጠይቅ
አድርገዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

24
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

3.3 የመረጃ መተንተኛ መንገዶች

(Method of Data Analysis and
pretation)

3.3.1 የመረጃ መተንተኛ (Data Analysis and Interpretation)

ያገኘናቸውን መረጃዎች በተለያዩ መንገዶች ለመተንትን ችለናል፡፡ ከነዛ መካከል የተጠቀምናቸው የመረጃ
መተንተኛ ዘዴዎች ውስጥ በሰንጠረዥ ሲሆን በዛ ውስጥ በጽሑፍ መጠየቅ የሰበሰብናቸውን እና ቃለ መጠይቅ
አርገን ያገኘናቸውን መረጃዎች በድግግሞሽ (frequency) እና በመቶኛ (percent) አድርገን ገልጸናል ፤
በተጨማሪም በነዚህ መንገዶች ያገኘናቸውን መረጃ ያላቸውን ውጤት መግለጥ ችለናል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

25
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ምእራፍ አራት

4.1 የጥናቱ ትንተና እናፍቺ (Data Analysis and

interpretation)
በደብራችን በአ/ኅ/ደ/ም/ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ፣ ወላጆች እና ህጻናት
ለጥናቱ ተመርጠው ከመሉት የጽሑፍ መጠይቅ የተዘጋጀ ትንተና፡፡

ለተወካዮች
የምላሽ ሰጪዎች ጾታ ድግግሞሽ በመቶኛ
Frequency Percent

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

26
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ወንድ 8 47.06
ለመጠይቁ ምላ
ሴት 9 52.94
የሰጡ
ድምር 17 100

በትክክል ያልተመላ መጠይቅ - -

ሰንጠረዥ 1 ፡ ተወካዮች እና መምህራን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ያገለገሉበትን ዘመን ለማወቅ ባዘጋጀነው ጥያቄ
(ከፍተኛ መጠነኛ አነስተኛ ) የሰጡት ምላሽ

በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ምን ያክል ጊዜ አገልግለዋል ድግግሞሽ በመቶኛ

Frequency Percent

ከፍተኛ ( ከ3 ዓመት በላይ) 8 47.1

መጠነኛ ( ከ1 - 3 ዓመት ) 6 35.29

ለመጠይቁ
አነስተኛ (ከ1 ዓመት በታች) 2 11.76
ምላሽ የሰጡ
የለም - -

ያልተመለሰ 1 5.88

ድምር 17 100
ተወካዮች እና መምህራን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ያገለገሉበትን ዘመን ለማወቅ ባዘጋጀነው መጠይቅ 47.17 %
ከፍተኛ 35.29% መጠነኛ እንዲሁም 11.76% አነስተኛ ናቸው ። ከምላሻቸው ተወካዮች እና መምህራን
በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ማገልገላቸውን ያሳያል።

ሰንጠረዥ 2፡ ምላሽ ሰጪዎች በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ ስለማግኘታቸው ተጠይቅው የሰጡት ምላሽ

ስለህጻናት አያይዝ በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ አሎትድግግሞሽ በመቶኛ

Frequency Percent

ለመጠይቁ ከፍተኛ 1 5.88

ምላሽ የሰጡ መጠነኛ 4 23.53

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

27
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

አነስተኛ 6 35.29

የለም 6 35.29

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ተወካዮች በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ ስለማግኘታቸው ተጠይቅው እመለሱት 5.88% ከፍተኛ
23.53% መጠነኛ ነው ። ነገር ግን በአብዛኛው (70.58%) አነስተኛ እና ምንም ስልጠና አለማግኘታቸውን
ተመልክተናል።

ሰንጠረዥ 3 ፡ ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን እንደሚመስል ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ድግግሞሽ በመቶኛ

ይመስላል Frequency Percent

ከፍተኛ - -

መጠነኛ 7 41.17
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 7 41.17
የሰጡ
የለም 3 17.65

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን እንደሚመስል ተጠይቀው 41.17% መጠነኛ 41.17%
አነስተኛ 17.65% ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል ። ባገኘነው ምላሽ መሰረት በወላጆች እና
በተወካዮች መካከል ያለው ግንኙነት የላላ መሆኑን እንመለከታለን ።

ሰንጠረዥ 4 ፡ ተወካዮች ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ምን ያክል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ምን ያክል ድግግሞሽ በመቶኛ

ተግባራዊ ያረጉታል Frequency Percent

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

28
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ከፍተኛ 1 5.88

መጠነኛ 6 35.29
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 8 47.1
የሰጡ
የለም 1 5.88

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ተወካዮች ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ምን ያክል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተጠይቀው 5.88%
ከፍተኛ 35.29% መጠነኛ 47.1% አነስተኛ እንዲሁም 5.88 % ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት
ምንም ተግባራዊ እንደማያደርጉ ገልጸዋል

ሰንጠረዥ 5 ፡ ለህጻናቱ ሥለሚሰጣቸው ትምህርት ተጥይቀው የሰጡት ምላሽ

ህጻናቱ የሚማሩት ትምህርት ለእድሜያቸው የሚመጥን ነው ድግግሞሽ በመቶኛ

ብለው ያምናሉ Frequency Percent

ከፍተኛ 2 11.76

መጠነኛ 10 58.82
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 5 29.4
የሰጡ
የለም - -

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ህጻናቱ የሚማሩት ትምህርት ለእድሜያቸው የሚመጥን መሆኑን ጠይቀን የተመለሰው 11.76% ከፍተኛ
58.82% መጠነኛ 29.4% አነስተኛ ነው ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

29
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 6 ፡ተወካዮች ለህጻናት አርአያ መሆን ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

በአሁን ሰአት የሚገኙ የህጻናት ተወካዮች ለህጻናት አርአያ ድግግሞሽ በመቶኛ

መሆን ይችላሉ በለው ያስባሉ Frequency Percent

ከፍተኛ 1 5.88

መጠነኛ 10 58.82
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 5 29.4
የሰጡ
የለም 1 5.88

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ተወካዮች ለህጻናት አርአያ መሆን ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ 5.88%ከፍተኛ 58.82% መጠነኛ 29.4%
አነስተኛ 5.88% ደግሞ አራያ መሆን እንደማይችሉ ገልጸዋል።

ሰንጠረዥ 7 ፡ምላሽ ሰጪዎች ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ እንደሚረዷቸው
ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ ድግግሞሽ በመቶኛ

ይረዷቸዋል Frequency Percent

ከፍተኛ 1 5.88

መጠነኛ 5 29.4
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 9 52.9
የሰጡ
የለም 1 5.88

ያልተመለሰ 1 5.88

ድምር 17 100
ምላሽ ሰጪዎች ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ እንደሚረዷቸው ተጠይቀው
የሰጡት ምላሽ 5.88% ከፍተኛ 29.4% መጠነኛ 52.9% አነስተኛ 5.88% ደግሞ ምንም እንደማይረዷቸው
ይገልጻል

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

30
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 8 ፡ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን

እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢውን እርምጃ
እንደሚወስዱ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ
ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸውድግግሞሽ በመቶኛ
ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ Frequency Percent

ከፍተኛ 6 35.29

መጠነኛ 7 41.17
ለመጠይቁ ምላ
አነስተኛ 3 17.65
የሰጡ
የለም 1 5.88

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስዱ ተጠይቀው
የሰጡት ምላሽ 35.29% ከፍተኛ 41.17% መጠነኛ 17.65% አነስተኛ እንዲሁም 5.88% ምንም አይነት
እርምጃ እንደማይወስዱባቸው ገልጸዋል ።

ሰንጠረዥ 9 ፡ ህፃናት ሰ/ት/ቤት ከመጡ ጀምሮ አወንታዊ የሆነ የስነምግባር ለውጥ እሚያሳዩ እንደሆነ ለማወቅ
ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ህፃናት ሰ/ት/ቤት ከመጡ ጀምሮ አወንታዊ የሆነ የስነምግባር ድግግሞሽ በመቶኛ

ለውጥ ያሳያሉ ብለው ያምናሉ Frequency Percent

ከፍተኛ 7 41.17

ለመጠይቁ ምላ መጠነኛ 7 41.17

የሰጡ አነስተኛ 3 17.65

የለም - -

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

31
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ያልተመለሰ - -

ድምር 17 100
ህፃናት ሰ/ት/ቤት ከመጡ ጀምሮ አወንታዊ የሆነ የስነምግባር ለውጥ እሚያሳዩ እንደሆነ ለማወቅ ተጠይቀው
የሰጡት ምላሽ 41.17% ከፍተኛ 41.17% መጠነኛ እንዲሁም 17.65% አነስተኛ ነው።

ለህጻናት
የምላሽ ሰጪዎች ጾታ ድግግሞሽ በመቶኛ
Frequency Percent

ወንድ 34 41.33
ለመጠይቁ ምላ
ሴት 41 54.67
የሰጡ
ድምር 75 100

በትክክል ያልተመላ መጠይቅ - -

ጠቅላላ መጠይቁን ለመምላት የተቀበሉ 75 100

ሰንጠረዥ 1. ህጻናቱ በዙፘቸው ካሉ ሰዎች ማንን እንደሚቀርቡ ለማወቅ የጠየቅነው ጥያቄ

ከቤት ውጪ የሚያጋጥሙሽን\ህን ለማን ድግግሞሽ በመቶኛ

ይናገራሉ Frequency Percent

ለእናት\ለአባት 29 38.66
ለመጠይቁ
ለወንድም/ለእህት 11 14.67
ምላሽ የሰጡ
ለጓደኛ 14 18.67

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

32
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ለማንም 18 24

ከአንድ በላይ የመለሱ 3 4

ድምር 75 100
ሀጻናቱ ከቤት ውጪ የሚያጋጥሙሽን\ህን ለማን እነደሚናገሩ ተጠይቀው 38.66% ለእናት\ለአባት 14.67%
ለወንድም/ለእህት 18.67% ለጓደኛ እንዲሁም 24% ለማንም እንደማይናገሩ ገልጸዋል ። ይህም በአካባቢያቸው
ካሉ ሰዎች ለ እንደሚቀርቡ እና ከሌላው በተሻለ ተጸኖ እንደሚኖርባችው ተረድተናል ።

ሰንጠረዥ 2. ልጆች ትርፍ ጊዜያቸውን ምን በማድረግ እንደሚያሳልፉ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ድግግሞሽ በመቶኛ
ትርፍ ጊዜያችሁንምን በማድረግ
Frequency Percent
ታሳልፋላችሁ

መጽሃፍ በማንበብ 16 21.33

ቤተ ክርስትያን በመሄድ 27 36

ለመጠይቁ
ምላሽ የሰጡ በጨዋታ አልትጠቀሰም 9 12

አልትጠቀሰም 8 10.67

ከአንድ በላይ የመለሱ 15 20

ድምር 75 100
ልጆች ትርፍ ጊዜያቸውን ምን በማድረግ እንደሚያሳልፉ ተጠይቀው % መጽሃፍ % በማንበብ % ቤተ
ክርስትያን በመሄድ % በጨዋታ በማለት መልሰዋል ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

33
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 3. ትምህርት ቤት ውስጥ አብረቸው የሚሆኑት ጓደኞቻቸው የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

እንደሆኑ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፲፭

ድግግሞሽ በመቶኛ
ትምህርት ቤት ውስጥ አብራችሁ
Frequency Percent
የምትሆኗቸው ጓደኞቻችሁ የሰንበት
ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው

አዎ 30 40

ለመጠይቁ በከፊል 39 52
ምላሽ የሰጡ ምንም 6 8

ከአንድ በላይ የመለሱ - -

ድምር 75 100
ትምህርት ቤት ውስጥ አብረቸው የሚሆኑት ጓደኞቻቸው የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሆኑ
ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ % አዎ % በከፊል % ሁሉም ጉደኞቻቸው የሰንብት ትምህርት ቤት ተማሪዎች
እንዳልሆኑ ተናግረዋል ።

ሰንጠረዥ 4. በትምህርተ ቤታቸው አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም ቦታዎች
እንዳሉ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ

ድግግሞሽ በመቶኛ
በትምህርተ ቤታችሁ አቅራቢያ የህፃናቱን
Frequency Percent
ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም
ቦታዎች አሉ

ለመጠይቁ አዎ 30 40

ምላሽ የሰጡ በከፊል 18 24

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

34
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ምንም 24 32

ምንም ያልመለሱ 3 4

ድምር 75 100
በትምህርተ ቤታቸው አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም ቦታዎች እንዳሉ
ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ 40% አሉ 24% በከፊል 32% ምንም አይነት የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ
ቤቶች ወይንም ቦታዎች አለመኖራቸውን እንዱሁም 4% ምንም አልመለሱም።

ሰንጠረዥ 5.ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻቸው እንደሚያስተምሩ

ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ድግግሞሽ በመቶኛ
ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው
Frequency Percent
ትምህርት ለወላጆቻችሁ ታስተምራላችሁ

አዎ 20 26.67

ለመጠይቁ በከፊል 24 32
ምላሽ የሰጡ ምንም 27 36

ምንም ያልመለሱ 4 5.33

ድምር 75 100
ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻቸው እንደሚያስተምሩ ተጠይቀው የሰጡት
ምላሽ 26.67 % አዎ 32 % በከፊል 36 % ምንም 5.33 % ምንም ያልመለሱ::

ሰንጠረዥ 6. በህጻናት ክፍል ውስጥ ስትገለግሉ ያጋጠማቸው ችግር እዳለ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

35
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

በህጻናት ክፍል ውስጥ ስታገለግሉ ድግግሞሽ በመቶኛ

ያጋጠማችሁ ችግር አለ ወይ Frequency Percent
(በባህርያችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር)

አዎ 25 33.33

ለመጠይቁ በከፊል 24 32
ምላሽ የሰጡ ምንም 19 25.33

ምንም ያልመለሱ 7 9.33

ድምር 75 100
በህጻናት ክፍል ውስጥ ስታገለግሉ (በባህርያችሁ ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር) ያጋጠማቸው ችግር እዳለ ተጠይቀው
የሰጡት ምላሽ 33.33 % አዎ 32 % በከፊል 25.33 % ምንም 9.33 % ምንም ያልመለሱ ።

ሰንጠረዥ 7. ስንበት ትምህርት ቤት ያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን ያቆሙ ጓደኞች እንዳላቸው ተጠይቀው የሰጡት
ምላሽ ፡

ድግግሞሽ በመቶኛ
ስንበት ትምህርት ቤት ያገለግሉ የነበሩ አሁን
Frequency Percent
ግን ያቆሙ ጓደኞች አሏችሁ

አዎ 52 69.33

ለመጠይቁ በከፊል 6 8
ምላሽ የሰጡ ምንም 13 13.33

ምንም ያልመለሱ 4 5.33

ድምር 75 100
ስንበት ትምህርት ቤት ያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን ያቆሙ ጓደኞች እንዳላቸው ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ
69.33% አዎ 8 % በከፊል 13.33% ምንም 5.33% ምንም ያልመለሱ ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

36
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ሰንጠረዥ 8.ሰንበት ትምህርት ቤት መማራቸው ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው ረድቷቸው እንደሆነ ተጠይቀው

የሰጡት ምላሽ ፡

ድግግሞሽ በመቶኛ
ሰንበት ትምህርት ቤት በመማር\ሽ ጥሩ ስነ
Frequency Percent
ምግባር እንዲኖረኝ ረድቶኛል በለህ\ሽ
ታስባልህ\ታስቢያለሽ

አዎ 72 96

ለመጠይቁ በከፊል 3 4
ምላሽ የሰጡ ምንም - -

ምንም ያልመለሱ - -

ድምር 75 100
ሰንበት ትምህርት ቤት መማራቸው ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው ረድቷቸው እንደሆነ ተጠይቀው የሰጡት
ምላሽ 96% አዎ 4% በከፊል ነው።

ሰንጠረዥ 9.መንፈሳዊ መጽሃፎችን እንደሚያነቡ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ድግግሞሽ በመቶኛ
መንፈሳዊ መጽሃፎችን ታነባለህ\ታነቢያለሽ
Frequency Percent

አዎ 27 36

ለመጠይቁ በከፊል 33 44
ምላሽ የሰጡ ምንም 15 20

ምንም ያልመለሱ - -

ድምር 75 100
መንፈሳዊ መጽሃፎችን እንደሚያነቡ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ 36% አዎ 44% በከፊል 20% ምንም ነው።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

37
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

የወላጆች

ሰንጠረዥ 1 ፡ ልጆች በቀን ምጸሃፍ ምን ያክል ሰዓት እንዲያነቡ እንደሚያረጉ መምዘኛ

ልጆችዎ በቀን ምጸሃፍ ምን ያክል ሰዓት እንዲያነቡ ያረጋሉ ድግግሞሽ በመቶኛ

Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ 13 37.14

ዝቅተኛ 17 48.57
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 3 8.57
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ - -

ያልተመለሰ 2 5.72

ድምር 35 100
37.14% በጣም ዝቅተኛ 48.57% ዝቅተኛ 8.57% በከፍተኛ መጠን ልጆች በቀን ምጸሃፍ ምን ያክል ሰዓት
እንዲያነቡ ያድርጋሉ።

ሰንጠረዥ 2 ፡ ከልጆች ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች እንደሚወያዩ መመዘኛ

ከልጆችዎ ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ይወያያሉ ድግግሞሽ በመቶኛ
Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ 14 40

ዝቅተኛ 12 34.29
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 6 17.14
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 3 8.57

ያልተመለሰ - -

ድምር 35 100

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

38
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

40% በጣም ዝቅተኛ 34.29% ዝቅተኛ 17.14% ከፍተኛ 8.57% በጣም በከፍተኛ መጠን ከልጆች ጋር በቤት
ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ይወያያሉ።

ሰንጠረዥ 3 ፡ ልጆች ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ የሚደረግን ክትትል ምምዘኛ

ልጆችዎ ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ ክትትል ድግግሞሽ በመቶኛ

ያደርጋሉ Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ 8 22.86

ዝቅተኛ 13 37.14
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 10 28.57
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 4 11.43

ያልተመለሰ - -

ድምር 35 100
ልጆች ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ % በጣም ዝቅተኛ 37.14% ዝቅተኛ 28.57% ከፍተኛ 11.43%
ወላጆች በጣም ከፍተኛ ክትትል ያደርጋሉ።

ሰንጠረዥ 4 ፡ ልጆቻቸውን በሃይማኖት ስነምግባር አሳድገው እንደሆነ ጠይቀን የተሰጠን ምላሽ

ልጆችዎን በሃይማኖት ስነምግባር አሳድጌያለሁ ብለው ያምናሉድግግሞሽ በመቶኛ

Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ 6 17.14

ለመጠይቁ ምላ ዝቅተኛ 14 40

የሰጡ ከፍተኛ 13 37.14

በጣም ከፍተኛ 2 5.72

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

39
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ያልተመለሰ - -

ድምር 35 100
ልጆቻቸውን በሃይማኖት ስነምግባር አሳድገው እንደሆነ ጠይቀን የተሰጠን ምላሽ 17.14% በጣም ዝቅተኛ 40%
ዝቅተኛ 37.14% ከፍተኛ 5.72% በደንብ አሳምኛለሁ።

ሰንጠረዥ 5 ፡ ልጆቻቸውን ከስንበት ትምህርት ቤት ውጪ ካሉ የማህበረሰብ ክፍል ጋር ምን አይነት ግንኙነት

እንዳላቸው ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ ፡

ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ውጪ ካሉ የማህበረሰብ ክፍል ድግግሞሽ በመቶኛ

ጋር ምን አይነት ግንኚነት አላቸው Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ - -

ዝቅተኛ 7 20
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 22 62.86
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 6 17.14

ያልተመለሰ - -

ድምር 35 100
ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ውጪ ካሉ የማህበረሰብ ክፍል ጋር ምን አይነት ግንኚነት እንዳላቸው ተጠይቀው
የሰጡት ምላሽ 20% ዝቅተኛ 62.86% ከፍተኛ 17.14% በጣም ከፍተኛ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሰንጠረዥ 6 ፡ ልጆቻቸው ስንበት ትምህርት ቤት መማሩ\ሯ አለማዊ ህይወታቸው ላይ ያለው አትወአጽኦ ምን

እንደሚመስል ያሳያል

ልጅዎ ስንበት ትምህርት ቤት መማሩ\ሯ አለማዊ ህይወታቸው ድግግሞሽ በመቶኛ

ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅእኖ ይኖረዋል Frequency Percent

ለመጠይቁ ምላ በጣም ዝቅተኛ 21 60

የሰጡ ዝቅተኛ 13 37.14

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

40
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ከፍተኛ - -

በጣም ከፍተኛ - -

ያልተመለሰ 1 2.86

ድምር 35 100
ልጅዎ ስንበት ትምህርት ቤት መማሩ\ሯ አለማዊ ህይወታቸው ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅእኖ ምን እንደሚመስል
ተጠይቀው 60% በጣም ዝቅተኛ 37.14% ዝቅተኛ 2.86 % ወላጆች አልመለሱም።

ሰንጠረዥ 7 ፡ ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት እንደሚረይቁ ጠይቀን

ያግውኘነው ምላሽ

ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህር ድግግሞሽ በመቶኛ

ይጠይቃሉ Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ 11 31.43

ዝቅተኛ 9 25.71
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 12 34.29
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 3 8.57

ያልተመለሰ - -

ድምር 35 100
ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት እንደሚረይቁ ጠይቀን ያግውኘነው ምላሽ
31.43% በጣም ዝቅተኛ 25.71% ዝቅተኛ 34.29% ከፍተኛ 8.57% ወላጆች ልጆቻቸው የሚማሩትን
ትምህርት በድንብ እንደሚቆጣጠሩ ገልጸዋል።

ሰንጠረዥ 8 ፡ የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ አስተዋጽአ እንዳለው ተጠይቀው የሰጡት
ምላሽ

የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ ድግግሞሽ በመቶኛ

አስተዋጽአ አለው ብለው ያምናሉ Frequency Percent

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

41
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

በጣም ዝቅተኛ 2 5.71

ዝቅተኛ 8 22.86
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 12 34.29
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 10 28.57

ያልተመለሰ 3 8.57

ድምር 35 100
የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ አስተዋጽአ እንዳለው ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ 5.71%
በጣም ዝቅተኛ 22.86% ዝቅተኛ 34.29% ከፍተኛ 28.57% በጣም ከፍተኛ 8.57% ወላጆች መልስ
አልሰጡም።

ሰንጠረዥ 9 ፡ለልጆቻቸው በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ምን እንደሚመስል ተጠይቀው

የሰጡት ምላሽ

ለልጅዎ በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ምን ድግግሞሽ በመቶኛ

ይመስላል Frequency Percent

በጣም ዝቅተኛ - -

ዝቅተኛ 9 25.71
ለመጠይቁ ምላ
ከፍተኛ 13 37.14
የሰጡ
በጣም ከፍተኛ 11 31.43

ያልተመለሰ 2 5.72

ድምር 35 100
ለልጅዎ በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ምን እንደሚመስል ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ
25.71% ዝቅተኛ 37.14% ከፍተኛ 31.43% በጣም ከፍተኛ ነው ።

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

42
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ቃለ መጠይቅ
በቃለ መጠይቅ ያሳተፍናቸው አባላት በህፃናት ክፍሉ ለረጅም ጊዜ ሲያገለገሉ የነበሩ በማገልገል ላይ ያሉ፤ በሰንበት
ት/ቤት ውስጥም ረጅም ቆይታ የነበራቸው ሲሆኑ በአገልግሎት ጊዜያቸውም በስነ ምግባር ረገድ
የተመሰከረላቸው እና ለህፃናቱ አርአያመሆን የቻሉ ተወካዮችን ነው

የህፃናትን ስነ ምግባር ላይ ተግዳሮት የሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው፤ የተሻለ ለማድረግ እና አመርቂ ውጤት
ለማምጣትስ ከባለ ድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የሰጡንን ምላሽ አስቀምጠናል

በህፃናቱ ስነ- ምግባር ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ከሚያሳድሩ ምክንያቶች መካከል

ዲ/ን ቃልኪዳን

ተግባር ተኮር የሆነ ትምህርት የመስጠት ልምድ ዝቅተኛ መሆን

የተወካዮች ልምድ አናሳ መሆን

ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ሁኔታ መከታተል አለመቻል

የሰ/ት/ቤት እና የወላጆች ግንኙነት አለመጠናከር

ዲ/ን ዳንኤል መኮንን

የተወካዮች አርኣያነት ማነስ

ተወካዮች ከህፃናት ጋር ያለው ግንኙነት አለመመጣጠን

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

43
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

የአገልግሎት ቸልተኝነት

ኢዮብ ዳንኤል

የወላጆች ለልጆቻቸው ትኩረት አለመስጠት

ተወካዮች ከወላጆች እና ከት/ቤት መምህራን ጋር አለመነጋገር

የተወካዮች ቁጥር እና ልምድ አናሳ መሆን

ተግባራዊ የሆነ ት/ት አለመኖር

በሰ/ት/ቤቱ ደረጃ ለህፃናት የሚሰጠው ትኩረት ከንግግር ያለፈ አለመሆን

የህጻናት ስነ ምግባር የተሻለ ለማድረግ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ የተስጡት ምላሾች

ዲ\ን ቃልኪዳን

የምንሰጣቸውን ትምህርቶች ተግባር ተኮር ማድረግ

ተወካዮች ህጻናቱን በእኩል አይን መመልከት አለባቸው

ተወካዮች እርስ በእርስ መግባባት አለባቸው

ተወካዮች ብቁ የሆነ ስልጠና ቢወስዱ የተሻለ ይሆናል

ወላጆች ስለልጆቻቸው ሁኔታ መከታተል አለባቸው

ዲ/ን ዳንኤል መኮንን

ተወካዮች ለህጻናቱ የስነምግባር አርአያ መሆን አለባቸው

የተወካዮች ቀረቤታ ከህፃናት ጋር በልክ መሆን መቻል አለበት

የመንፈሳዊነት አስተሳሰብ በተወካዮች ቢጀምር

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

44
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ኢዮብ ዳንኤል

ወላጆች ለልጆቻቸው ትኩረት መስጠት አለባቸው

ተወካዮች ከወላጆች እና ከት/ቤት መምህራን ጋር መነጋገር እና ስለህጻናቱ መጠየቅ ይገባቸዋል

የተወካዮች ቁጥር ለህጻናቱ ተመጣጣኝ እና ልምዳቸው ደግሞ ጠንካራ መሆን አለበት

የሚሰጠው የስነምግባር ት/ት ተግባራዊ መሆን አለበት

በሰ/ት/ቤቱ ደረጃ ለህፃናት የሚሰጠው ትኩረት ከንግግር አልፎ በተግባር ቢገለጽ

ምእራፍ ዐምስት

5. ውጤት እና የመፍትሔ ሐሳብ (conclusion

and recommendation)

5.1. መደምደሚያ (Conclusion)

ከአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት የህጻናት ክፍል ተወካዮች ( አሁን ላይ
እሚያገለግሉ እንዲሁም ከአሁን በፊት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ) ከህጻናቱ ወላጆች እንዲሁም ከራሳቸው ከህጻናቱ ተሰበሰበ
የጽሑፍ መጠይቅ እና ቃለመጠይቅ መሠረት የሚከተለው የመደምደሚያ ሐሳብ ላይ ተደርሷል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

45
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

1. የሚከተሉት ጥያቄዎች የወላጆች አያያዝን ለመመዘን ከወጡ መጠይቆች ከምላሾችም መልሶች

የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ወላጆች ልጆቻቸውን መጽሃፍ በደንብ እንዲያንቡ አያደርጉም
● ልጆቻቸው ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ የሚያደርጉት ክትትል ዝቅተኛ ነው
● ወላጆች ልጅቻቸው ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት ይጠይቃሉ
● ለልጆቻቸው በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ከፍተኛ ነው

ወላጆች ልጆቻቸውን መጽሃፍ በደንብ እንዲያንቡ አለማድረጋቸው እና ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ

የሚያደርጉት ክትትል ዝቅተኛ መሆኑ የህጻናት ሰነምግባር እንዲሻሻል ባይረዳቸውም ፤ ወላጆች ልጅቻቸው
ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት መጠየቃቸው እና በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል
እና ቁጥጥር ከፍተኛ መሆኑ የህጻናት ሰነምግባር ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጽኦ አለው።

2. የሚከተሉት ጥያቄዎች የወላጆች እና የልጆቻቸውን ግንኙነት ለመመዘን ከወጡ መጠይቆች ከምላሾችም

መልሶች የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች አይወያዩም
● ህጻናቱ በዙፘቸው ካሉ ሰዎች ወላጆቻቸውን ይቀርባሉ
● ህጻናቱ ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻቸው አያስተምሩም
● የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽአ አለው

ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች አለመወያየታቸው እና ስንበት ትምህርት ቤት

ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻቸው አለማስተማራቸው የህጻናቱ ስነምግባር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ
አለው።

3. የሚከተሉት ጥያቄዎች የተወካዮች ከልጆች እና ከልጆች ወላጆች ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለመመዘን

ከወጡ መጠይቆች ከምላሾችም መልሶች የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ተወካዮች ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ አይረዷቸውም

● ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት አነስተኛ ነው

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

46
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ተወካዮች ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ አለመርዳታቸው ተወካዮች ከህጻናቱ ጋር
ጥሩ የሆነ ግንኙነት እንደሌላቸው ያስረዳል ፤ ይህ እና ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው የላላ ግንኙነት ህጻናቱ ላይ
እየታየ ላለው ክፍተት የራሱ አስተዋጽኦ አለው።

4. የሚከተሉት ጥያቄዎች የተወካዮች ልምድ እውቀት እና ትምህርት አሰጣጥ ለመመዘን ከወጡ መጠይቆች
ከምላሾችም መልሶች የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ተወካዮች እና መምህራን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል

● ተወካዮች በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ አላገኙም

● ህጻናቱ የሚማሩት ትምህርት በመጠነኛ መልኩ ለእድሜያቸው የሚመጥን ነው

ተወካዮች እና መምህራን በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ማገልገላቸው ፣ አንዲሁም ለህጻናት እድሜ
የሚመጥን ትምህርት ማስተማራቸው ለህጻናቱ ስነምግባር ጠቃሚ ቢሆንም በስልጠና ያልተደገፈ መሆኑ ግን
የራሱ አሉታዊ ተጽዕኖ አለው።

5. የሚከተሉት ጥያቄዎች የተወካዮች ስነምግባር ለህጻናት አርዓያ መሆን እንደሚችሉ ለመመዘን ከወጡ
መጠይቆች ከምላሾችም መልሶች የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ተወካዮች ለህጻናት በመጠነኛ መልኩ አርአያ መሆን ይችላሉ

● ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢውን እርምጃ ይወስዳሉ

ተወካዮች ህጻናት ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢውን እርምጃ መውሰዳቸው
ሃላፊነታቸውን እነደተወጡ ያሳየናል ይህም ህጻናቱ ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው ይረዳል ።

6. የሚከተሉት ጥያቄዎች የማህበረሰቡን ተጽዕኖ ለመመዘን ከወጡ መጠይቆች ከምላሾችም መልሶች

የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ልጆች ከማህበረሰቡ ጋር ከፍተኛ ግንኙነት አላቸው

● ትምህርት ቤት ውስጥ አብረቸው የሚሆኑት ጓደኞቻቸው በከፊል የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

ናቸው
● በትምህርተ ቤታቸው አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም ቦታዎች አሉ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

47
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ትምህርት ቤት ውስጥ አብረዋቸው የሚሆኑት ጓደኞቻቸው በከፊል ብቻ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች

መሆን እና በትምህርተ ቤታቸው አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶች ወይንም ቦታዎች መኖር
የህጻናቱ ሰነምግባር ላይ ተጽዕኖ አልው ልጆቹ ከማህበረሰቡ ጋረ ያለው ጥብቅ ግንኙነት ደግሞ ይህን ተጽእኖ
ያብሰዋል ።
7. የሚከተሉት ጥያቄዎች የህጻናቱን ባህሪያት እና ነባራዊ ሁኔታዎች ለመመዘን ከወጡ መጠይቆች
ከምላሾችም መልሶች የሚከተለውን የመደምደሚያ ሐሳብ ቀርቧል
● ልጆች ትርፍ ጊዜያቸውን ቤተ ክርስትያን በመሄድ ያሳልፋሉ

● ልጆች በህጻናት ክፍል ሲያገለግሉ ችግር አጋጥሟቻዋል

● ህጻናቱ ሰንበት ትምህርት ቤት መማራቸው ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖራቸው ረድቷቸዋል
● ልጆች በከፊል መንፈሳዊ ምጽሃፎችን ያነባሉ
● ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ተግባራዊ አያደርጉም

ህጻናቱ ትርፍ ጊዜያቸውን ቤተ ክርስትያን በመሄድ ማሳለፋቸው ፣ ሰንበት ትምህርት ቤት መማራቸው ፣

በከፊልም ቢሆን መንፈሳዊ ምጽሃፎችን ማንበባቸው ጥሩ ነገር ቢሆንም ፤ በህጻናት ክፍል ሲያገለግሉ
የሚያጋጥማቸው ችግሮች እና የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ተግባራዊ አለማድረጋችው በጸባያቸው ላይ
አሉታዊ ተጽዕኖ ያደርግባቸዋል ።

5.2 የመፍትሔ ሐሳብ (Recommendation)

ካገኘነው ማጠቃለያ መነሻ በማድረግ የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድረል ሰንበት
ትምህርት ቤት ህፃናት ክፍል አባላት እና ሰንበት ትምህርት ቤት የሚከተሉትን የመፍትሔ ሐሳብ ተረድተው
በመተግበር በእግዚአብሔር ቸርነት መልካም ምግባር ያላቸውን ኦርቶዶክሳዊ ሕፃናትን ማፍራት ይቻላል ብለን
እናምናለን ።

ሀ. የወላጆች አስተዋፅኦ
1. ከልጆቻቸው ጋር ግልፅ የሆነ ግንኙነት በመመስረት

❖ የቤት ስራዎችን በጋራ መስራት

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

48
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

❖ ስለሚገጥሟቸው ችግሮች እንደ ጓደኛ ማውራት

❖ ከጓደኞች እና ከቤተሠብ አባላት ጋር ማስተዋወቅ
❖ አብረዋቸው ከሚውሉ ጓደኞች ጋር መተዋወቅ እና መቀራረብ
❖ በእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው እርዳታ ያስፈልጋቸው እንደሆነ መጠየቅ

2. ስለ ልጆቻቸው መንፈሳዊ እና አለማዊ ህይወት መከታተል ትልቅ የሆነ ጥቅም አለው

❖ ልጆቻቸው የት እንደሚውሉ ማወቅ

❖ ልጆቻቸው አብረዋቸው የሚውሏቸው ጓደኞች ጠባይ ማጣራትና ማወቅ

❖ ወደ ቤተ ክርስቲያን እዲሄዱ መገፋፋት፤ ሲመለሱም ስለ ተማሩት ትምህርተ መጠየቅ

❖ ልጆች በሚማሩበት አካባቢና በሚኖሩበት መንደር ውስጥ ስሊገኙ አሉታዊ ቤቶች ማወቅና ህፃናቱ እንዳይሄዱ
ማስጠንቀቅ
1. ቁማር ቤቶች
2. ጫት ቤቶችና ሽሻ ቤቶች

3. በልጆች ፊት የሚናገሩትን ቃላት መመጠን

❖ በእናትና አባት መሐከል ማንኛውንም ግጭቶች ቢፈጠሩ ህፃናት እንዳይሰሙ መጠንቀቅ
❖ ከህፃናቱ አእምሮ በላይ የሆኑ ቃላቶችንን በንግግር መሀል አለመጠቀም
❖ ህፃናት በሚያጠፉ ጊዜ አእምሮአቸውን የሚነካ ኃይለ ቃላትን አለመጠቀም
● ከሌሎች ልጆች ጋር በማነፃፀርና በማወዳደር መናገር
● አዕምሮ የሚነኩ ስድቦችን መሳደብ
❖ ስለ ሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር አለመናገር

❖ ስለሚያስተምሯቸው መምህራን መጥፎ አለማውራት

❖ በቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ በማሳለፍ የቤተሠብ ጊዜን አለማባከን

❖ በውሸት ልጆች ፊት አለመማል

4. ከሰ\ት\ቤት ጋር ጠንካራ የሆነ ግንኙነት መፍጠር

❖ ስለ ህፃናቱ ባህርይ ከተወካዮች ጋር መወያየት
❖ የወላጆች ኮሚቴ አባል በመሆን በንቃት መሳተፍ
❖ በሰ/ት/ቤት ውስጥ ለሚገጥሟቸው ችግሮች ከቅርብ መምህራኖቻቸው ጋር መወያየት

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

49
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

❖ ሰ/ት/ቤቱ በሚያዘጋጀው ወላጆችን የሚያሳትፉ ጉባኤዎች እና የውይይት መድረኮች ላይ መሳተፍ

ለ. የሰንበት ት\ቤት አስተዋፅኦ

1. ግብረ ገብ ትምህርቶችን በመደበኛነት መስጠት
❖ ከመደበኛ የትምህርት መርሐ ግብር በተጨማሪ የግብረ ገብ ትምህርቶችን በየጊዜው ማስተማር
❖ የተማሩትን ትምህርት ወደ ተግባር ለመቀየር እንዲችሉ ማድረግ
❖ እርስ በእርስ መከባበር እና መረዳዳት የእለት ተእለት ተግባራቸው እንዲሆን ማስተማር
❖ አርአያ የሚሆኑ ቅዱሳንን ታሪክ መንገርና ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዎችን በመጋበዝ ልምድ እንዲካፍሉ
ማድረግ
❖ በሰንበት ት/ቤት ውስጥ የሚወጡ ህግና ስርዓቶች ተፈፃሚነታቸውን ማረጋገጥ

2. በተወካዮች እና በህፃናት መካከል ጤናማ ግንኙነት ማጠናከር

❖ ሕፃናትን በእኩል አይን ማየት፡- ሰላምታ አሰጣጣችን፤ ፈገግታን ማሳየት፤ ማናገር ወዘተ..
❖ ለህፃናት ተገቢ የሆነ ቀረቤታ ማድረግ፡-
● አወኩሽ ናኩሽ እንዳይመጣ መጠንቀቅ
● አላስፈላጊ ቃላትን መነጋገር እና የግል ገመናን ለህፃናት አለመናገር
● ሕፃናቱ አላስፈላጊ የሆነ አመለካከት ለተወካዮች እንዳይኖራቸቸው መጠንቀቅ

❖ በተወካዮች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በህፃናት ፊት አለማውራት

❖ በተለያዩ የደስታ እና የሀዘን ገጠመኞች ላይ ለህጻናት የሚደረጉትን ነገሮች ተመሳሳይ ማድረግ

3. ወደ ህፃናት ክፍል ለሚመጡ ተወካዮች በቂ የሆነ ስልጠና መስጠት

❖ ስለ ህፃናቱ ባህርይ እና ጠባይ በቂ የሆነ እውቀት እዲያገኙ ማስቻል

❖ ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው የስልጠና መድረኮችን ማዘጋጀት

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

50
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

❖ ተተኪ የሚሆኑ የህፃት ተወካዮችን የማፍራት ስራዎችን መስራት

❖ ወደ ህፃናት ክፍል ለሚመደቡ ተወካዮች መስፈርቶችን ማዘጋጀት

● በአገልግሎት የቆዩበት ጊዜ በጣም ወሳኝነት አለው
● ከህፃናት ጋር የመላመድ ችሎታ ሊኖራቸው ይገባል
● በስነ ምግባር ለህፃናቱ አርአያ ስለመሆናቸው የተመሰከረላቸው አገልጋዮችን መምረጥ
● እድሜያቸው ለህፃናት ተወካይነት በቂ ሊሆን ይገባል

4. ለህፃናት አርአያ መሆን መቻል አለብን

ህፃናት የሚመስሉት የሚያዩትን ነው ለዚህ ደግሞ ተወካዮች የራሳቸው የሆነ አስተዋፅኦ አላቸው
❖ በአለባበስ፤ በአነጋገር፤ በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎቻቸው አብረዋቸው ለሚውሉ ህፃናት ምሳሌ መሆን
❖ ለህፃናት የምንናገረቸውና አድርጉ የምንላቸውን ትእዘዞች በሙሉ ፈፅመን ማሳየት መቻል አለብን
➢ ጥፍርን መቆረጥ
➢ ነጠላ በአግባቡ መልበስ
➢ ንጽህናን መጠበቅ
➢ ፀጉር አለማሳደግ ስርአተ ቤተክርስቲያን እና የሰ/ት/ቤቱን ህገ ደንብ መፈጸም
❖ ሰዓትን በአግባቡ በመጠቀም መንፈሳዊ ህይወታቸው ላይ ፍሬን ማፍራት
5. የህጻናት ክፍሉን አሰራር ማጠናከር

ለህፃናት ክፍል በዚህ ጽሁፍ ላይ ለጠቀስናቸው ችግሮች በተዘዋዋሪ መፍትሔ ሊሰጥ

ይችላል ብለን እናስባለን፡፡ ይህም ማለት

❖ የስራ አመራሩ ለህጻናቱ ይሆናሉ የሚላቸውን ተወካዮች መምረጥ
● ከእድሜ
● ከስነምግባር
● ከአገልግሎት ቆይታ/ልምድ
● ለህጻናት ካላቸው ቀረቤታ

❖ የተመረጡት ተወካዮች የቆይታ ጊዜ በስራ አመራሩ ቆይታ መወስን

● እያንዳንዳቸው የህጻናቱን ባህርይ በደንብ ለመረዳትና ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላቸዋል
● በጣም ከመላመድ የሚመጣን አላስፈላጊ የሆነ ቅርርብን ለመቆጣጠር ያስችላል

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

51
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

● በአገልግሎት ብዛት መሰላቸትን ይቀንሳል (በህጻናቱም በተወካዮችም)

❖ ራሱን የቻለ የስነ ምግባር ኮሚቴ ማዋቀር
● በህጻናት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት ያግዛል
● አለመግባባቶችን ለመቅረፍ ያስችላል
● በተወካዮች ላይ ያሉ ችግሮችን በውይይት ለምፍታት ይረዳል

6. ከህፃናት ወላጆች ጋር የሚኖረንን ግንኙነት ማጠናከር

የወላጆች ኮሚቴን ማጠናከር እና ቋሚ የሆነ የግንኙነት መድረክ ማዘጋጀት

❖ የወላጆች ጉዞ ማዘጋጀት

❖ ህፃናት ክፍሉ ሊሰራቸው ስላሰበውና እየሰራቸው ባሉ ጉዳዮች ላይ ከወላጆች ጋር መወያየት እና የጋራ እቅድ
ማውጣት

❖ ከወላጆች ጋር በየጊዜው የሚገናኙባቸውን መንገዶች ማመቻቸት

■ የግንኙነት ደብተር ማዘጋጀትና ሐሳቦችን መለዋወጥ

❖ ህፃናቱ የሚማሯቸውን ትምህርቶች ለወላጆች ማስተማር፡- በጋራ የሚሰሯቸውን ጥያቄዎች መስጠት

ሐ. ከማህበረሰቡ የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች በብቃት ማለፍ ይጠበቅብናል

1. ቅድሚያ ወደ ችግር ሊወስዱን የሚችሉ የአቻ ግፊቶችን ማሸነፍ ከህፃናቱ ይጠበቃል

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

52
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

❖ ክፉ ጓደኛ መጥፎ ምክር ይመክራል፣ አይዋደድም፣ ጥል ያበዛል፡፡ እናንተም ከእንደዚህ ዓይነት ልጆች
ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፍ፣ ምስጢር ማውራት፣ ለብቻ መገናኘት የለባችሁም፡፡
❖ በአካባቢያችን ያሉትን ሰዎች ኹሉ መተዋወቅና መግባባት መቻል የምስጢር ባልንጀራ፣
ችግሮቻችንን ልናካፍላቸው የሚገባቸው በጥንቃቄ መምረጥ
❖ አብረዋቸው ሊውሉ የሚገቡ ጓደኞችን መለየት\ በእምነት ከሚመስሉን ጋር መሆን
❖ ጠንካራ ወደ ተሻለ የሚመራን ባልንጀራ እንደምንፈልገው ኹሉ እያንዳንዱ ተማሪ ጠንካራ
በመኾን ለሌሎች ተማሪዎች በትምህርት፣ በማኀበራዊ ሕይወት፣ በመንፈሳዊነት ጠንካራና ደጋፊ
መኾን መቻል አለበት፣
❖ መዝናናት ማብዛት እንደፍትወት ያሉ ችግሮችን ያመጣብናልና በመዝናናት ስም ብዙ ጊዜን
አለመስጠት፣

2. በአካባቢያችን ከሚገኙ አሉታዊ ተጽእኖ ሊፈጥሩ ከሚችሉ ቦታዎች መራቅ

❖ ማኅበራዊ ትስስር፡- ለትምህርት፣ አእምሯችንን ለማፍታታት፣ መረጃ ለማግኘት በሚል

ለአጠቃቀማችን ገደብ ማበጀት፤ ስንጠቀም የምንፈልገውን እንዳገኘን ማቋረጥ ይገባል
❖ ሱስና ሱሰኝነትን ከሚያበረታቱ ቦታዎች ርቀትን መጠበቅ
❖ ከትምህርት ቤት አልያም ከ ሰንበት ት/ቤት ውጪ ያለ ታላላቆቻችን እውቅናና ፍቃድ ውጪ አለመሔድ
❖ በጫወታና፣ ከሰዎች ጋር ለመኾን የምናጠፋውን ጊዜ መጠንቀቅ
❖ ጊዜያችንን እጅግ ለሚሻሙ ነገሮች እድል አለመስጠት፣

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

53
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

አባሪ (APPENDIX)
አባሪ (APPENDIX) ሀ

የጽሑፍ መጠይቅ

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ውድ የህፃናት ወላጆች፤ በወጣት የመርሓ ግብር ሥልጠና ወስደው በሚመረቁ
አባላት በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ ስለሚስተዋለው የህፃናት ስነ ምግባር ዙሪያ ለመመዘን የተዘጋጀ ጥናት ነው፡፡

ማንነትዎን መግለጽ አይጠበቅብዎም፣ እባክዎን ትክክለኛ ውጤትና የመፍትሔ ሐሳብ ላይ እንድንደርስ በሚገባ አንብበው
በመረዳት የርሶን ተመክሮ ያካፍሉን፤ ከአራቱ ደረጃዎች ባንዱ ምልክት ያኑሩ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

ጾታ፡ ወንድ ሴት

ተ.ቁ ጥያቄዎች ከፍተኛ መጠነኛ አነስተኛ የለም

1
ልጆችዎ በቀን መጸሐፍ ምን ያክል ሰዓት እንዲያነቡ ያረጋሉ

2
ከልጆችዎ ጋር በቤት ውስጥ ስለመንፈሳዊ ነገሮች ይወያያሉ

3
ልጆችዎ ከሰንበት ትምህርት ቤት እንድዳይቀሩ ክትትል ያደርጋሉ

4
ልጆችዎን በሃይማኖት ስነምግባር አሳድጌያለሁ ብለው ያምናሉ

5 ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ውጪ ካሉ የማህበረሰብ ክፍል ጋር ምን አይነት

ግንኚነት አላቸው

6 ልጅዎ ስንበት ትምህርት ቤት መማሩ\ሯ አለማዊ ህይወታቸው ላይ አሉታዊ የሆነ

ተፅእኖ ይኖረዋል

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

54
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

7
ልጅዎ ከስንበት ትምህርት ቤት ሲመለሱ ስለተማሩት ትምህርት ይጠይቃሉ

8 የወላጆች የኢኮኖሚ እጥረት በህፃናት ስነ ምግባር ላይ አስተዋጽአ አለው ብለው

ያምናሉ

9
ለልጅዎ በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ክትትል እና ቁጥጥር ምን ይመስላል

አባሪ (APPENDIX) ለ
የጽሑፍ መጠይቅ

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን አባላት፤ በወጣት የመርሓ ግብር ሥልጠና ወስደው
በሚመረቁ አባላት በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ ስለሚስተዋለው የህፃናት ስነ ምግባር ዙሪያ ለመመዘን የተዘጋጀ
ጥናት ነው፡፡

ማንነትዎን መግለጽ አይጠበቅብዎም፣ እባክዎን ትክክለኛ ውጤትና የመፍትሔ ሐሳብ ላይ እንድንደርስ በሚገባ አንብበው
በመረዳት የርሶን ተመክሮ ያካፍሉን፤ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

ጾታ፡ ወንድ ሴት

ለእናት\ለአለወንድም\ለእ ለጓደኛ ለማንም

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

55
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ት ት

ከቤት ውጪ የሚያጋጥሙሽን\ህን ለማን ይናገራሉ

ቤተ ክርስትያን
መጽሃፍ በማንበብ በመሄድ በጨዋታ አልትጠቀሰም

ትርፍ ጊዜያችሁንምን በማድረግ ታሳልፋላችሁ

ተ.ቁ አዎ በከፊል ምንም

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

56
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

1 ትምህርት ቤት ውስጥ አብራችሁ የምትሆኗቸው ጓደኞቻችሁ የሰንበት

ትምህርት ቤት ተማሪዎች ናቸው

2 በትምህርተ ቤታችሁ አቅራቢያ የህፃናቱን ምግባር ሊያበላሹ የሚችሉ ቤቶ

ወይንም ቦታዎች አሉ

3 ስንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚማሩትንው ትምህርት ለወላጆቻችሁ

ታስተምራላችሁ

4 በህጻናት ክፍል ውስጥ ስትገለግሉ ያጋጠማችሁ ችግር አለ ወይ

5 ስንበት ትምህርት ቤት ያገለግሉ የነበሩ አሁን ግን ያቆሙ ጓደኞች አሏችሁ

6 ሰንበት ትምህርት ቤት በመማርህ\ሽ ጥሩ ስነ ምግባር እንዲኖረኝ ረድቶኛል

በለህ\ሽ ታስባልህ\ታስቢያለሽ

7 መንፈሳዊ መጽሃፎችን ታነባለህ\ታነቢያለሽ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

57
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

አባሪ (APPENDIX) ሐ
የጽሑፍ መጠይቅአባሪ (APPENDIX) ሐ
የጽሑፍ መጠይቅ

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን ውድ የሰንበት ትምህርት ቤታችን ተወካዮች ፤ በወጣት የመርሓ ግብር ሥልጠና
ወስደው በሚመረቁ አባላት በሰንበት ትምህርት ቤታችን ውስጥ ስለሚስተዋለው የህፃናት ስነ ምግባር ዙሪያ ለመመዘን
የተዘጋጀ ጥናት ነው፡፡

ማንነትዎን መግለጽ አይጠበቅብዎም፣ እባክዎን ትክክለኛ ውጤትና የመፍትሔ ሐሳብ ላይ እንድንደርስ በሚገባ አንብበው
በመረዳት የርሶን ተመክሮ ያካፍሉን፤ ከአራቱ ደረጃዎች ባንዱ ምልክት ያኑሩ በቅድሚያ እናመሰግናለን፡፡

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

58
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ጾታ፡ ወንድ ሴት

ጥያቄዎች ከፍተኛ መጠነኛ አነስተኛ የለም

1. በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ምን ያክል ጊዜ አገልግለዋል ›3 ዓመት 1-3 ዓመት ‹1 ዓመት -

2. ስለህጻናት አያይዝ በቂ የሆነ በስልጠና የትተደገፈ ልምድ አሎት

3. ተወካዮች ከህጻናቱ ወላጆች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል

4. ህጻናቱ የሚማሩትን የስነምግባር ትምህርት ምን ያክል ተግባራዊ

ያረጉታል

5. ህጻናቱ የሚማሩት ትምህርት ለእድሜያቸው የሚመጥን ነው ብለው

ያምናሉ

6. በአሁን ሰአት የሚገኙ የህጻናት ተወካዮች ለህጻናት አርአያ መሆን ይችላ

በለው ያስባሉ

ህጻናት ያለባቸውን መንፈሳዊና አለማዊ ችግሮችን እንዲፈቱ ይረዷቸዋ

7.

ከቤተክርስቲያን ቅጥር ውጪ ህፃናትን እልባሌ ቦታ ቢያገኟቸው ተገቢው

እርምጃ
ይወስዳሉ
ህፃናት ሰ/ት/ቤት ከመጡ ጀምሮ አወንታዊ የሆነ የስነምግባር ለውጥ
ያሳያሉ ብለው ያምናሉ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

59
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

ቃለ መጠይቅ
የህፃናትን ስነ ምግባር ላይ ተግዳሮት የሆኑ ነገሮች ምንድን ናቸው፤ የተሻለ ለማድረግ እና አመርቂ ውጤት
ለማምጣትስ ከባለ ድርሻ አካላት ምን ይጠበቃል

የዋቢ መጻሕፍትና መጣጥፎች ዝርዝር (Reference)

➢ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፣ 1980 ዓ.ም ፣አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

60
በህፃናት ላይ እየታዩ ያሉ የስነ-ምግባር ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው

➢ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የልጆች አስተዳደግ ፡ ዳዊት ደስታ ፣ 2010 ዓ.ም ፣አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ልጆቻችንን እንዴት እናሳድግ ፡ አቤል ሰለሞን ፣ 2005 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ የህፃናት ወጣቶችና ቤተሰብ ደህንነት ድርጅት የህፃናት መብቶች ኮንቬሽን 1996 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
➢ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ እና የልጆች አስተዳደግ ፡ ወ/ሮ ዘውዴ ገ/ እግዚአብሔር ፣ 2004 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
➢ የህጻናት አገልግሎት ክፍል መግለጫ ፡ በአ\ህ\ደ\ም\ሰ\ት\ቤት የህጻናት ክፍል ፣ ህዳር 2013 ዓ.ም ፣ አዲስ
አበባ ኢትዮጵያ
➢ በቤተክርስቲያን በህጻናት አስተዳደግ የሚታዩ ችግሮች የወላጆች እና የሰንበት ት\ቤት ድርሻ ፡ ዳዊት ደስታ
፣ 2005 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ እና የልጆች አስተዳደግ ፡ ቀሲስ ይግዛው መኮንን ፣ 2005 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ትንሿ ቤተ ክርስትያን ፡ ገብረ እግዚያብሄር ኪደ አባይ ፣ 2013 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ሃይማኖትን ለህጻናት ማን ያስተምር ፡ ዲያቆን ደረጀ ፣ 2004 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ የህጻናት መማርያ መጽሐፍ ፡ በሃብተስላሴ ሁንዴ ፣ ያልታተመ ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ክርስቲያናዊ የህጻናትት አስተዳደግ ፡ ዲ\ን ወንድወሰን ሶርሳ ፣ 1995 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
➢ ምክር ወተግሳጽ ዘማር ይስሓቅ ፡ ዲ\ን ሞገስ አብርሃም ፣ 2013 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የአፍሪካ ኅብረት ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካትድራል ሰ/ት/ቤት ፳፯ኛ ዙር ኮርስኞች ፳፻፲፭ ዓ.ም

61

You might also like