You are on page 1of 1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በአንቀፀ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ ሐብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤት የቀዳማይ ኮርሰኞች የክርስቲያናዊ ሥነምግባር
ማጠቃለያ ፈተና።
ስም--------------------------------------------------------- ቀን----------------------- ፊርማ---------------------- የተሰጠው ደቂቃ፡- 50
ትዕዛዝ ፩- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆኑትን እውነት ስህተት የሆኑትን ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ። (1 ነጥብ)
----------------1/ የሥነምግባር ትምህርታችን ላይ የተፈጥሮ አጠባበቅ እና የአየር ብክለት እንዲነሳ ወይም እንዲወሳ ግድ የሆነው ምንጩ መንፈሳዊ ህይወት ስለሆነ ነው።
----------------2/ የክርስቲያናዊ ሥነምግባር ትምህርት አላማው በጎ እንድኖን ብቻ ነው።
----------------3/ የቅዳሴ ህይወትን መኖር የሚለው ሃሳብ ለባልንጀራህ እስከ መሞት እራስን አሳልፎ መስጠትን ያካትታል።
ትዕዛዝ ፪- የሚከተሉትን ጥያቄዎች በ 'ሀ' ውስጥ ያሉትን ከ 'ለ' ጋር አዛምዱ። (1 ነጥብ)
ሀ ለ
-----1/ "እያንዳንዱን ጥቃቅን ፍጥረታት ስታዮ ክርስቶስን እንድታዩ እጠብቃለሁ።" ሀ/ አቡነ ሺኖዳ
-----2/ "የጸሎት አላማው ጸሎቱን መዋሐድ እንጂ መጨረስ አይደለም።" ለ/ ቅዱስ ማሪሳቅ
-----3/ "ንግግር የዚህ ዓለም አካል ነው፤ ዝምታ ደግሞ የሚመጣው ዓለም ምስጢር ነው።" ሐ/ ቅዱስ ባስሊዮስ
-----4/ "ኃጢአት ማድረግ ማለት በክርስቶስ ላይ አንድ ሚስማር/ አንድ ችንካር መምታት ማለት ነው።"
-----5/ "የጸሎት ሁሉ ቁንጮ በዝምታ እግዚአብሔር ፊት በፍርሃት መቆም ነው።"
ትዕዛዝ ፫- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክለኛ የሆነውን በመምረጥ ይመልሱ። (1.5 ነጥብ)
-----1/ እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ስላረፈ ይህንን ቀን ቀደሰው………………….
ሀ/ ቀዳሚውን ሰንበት ለ/ የመጀመሪያውን ቀን ሐ/ እሁድን ዕለት መ/ አርብ ዕለትን
-----2/ ከሚከተሉት ውስጥ "በከንቱ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት" የሚለውን አይመለከትም
ሀ/ በዓለማዊ ዘፈን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለ/ ያለምክንያት መጥራት ሐ/ በአምልኮተ እግዚአብሔር መ/ በአምልኮተ ጣዖት ሠ/ በሐሳዊ ትንቢት
-----3/ ይህ ሕግ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ከእግዚአብሔር ያገኘው ሕግ ነው
ሀ/ የቤተመንግስት ሕግ ለ/ የፍታብሔር ሕግ ሐ/ ኢ.ጽሑፋዊ ሕግ መ/ የቤተክህነት ሕግ
----- 4/ ጌታችን ትምህርቱን (አንቀጸ ብፁዓንን) ለምን በተራራ ላይ አስተማረ
ሀ/ የቀድሞ ህግ በተራራ ስለተሰጠ ያንን ሕግ የሰጠሁት እኔ ነኝ ሲል ለ/ የክብሩን ነገር ሊገልጽ
ሐ/ ተራራ ከፍ እንዲል እነሱም ልባቸው ከፍ እንዲል በምድራዊ ነገር እንዳይታለሉ መ/ ሁሉም ሠ/ መልስ የለም
-----5/ የብፁዓን አዋጆች ብዛት ሲዘረዘር ስንት ናቸው። ሀ/ ስድስት ለ/ አሥር ሐ/ ሦስት መ/ ዘጠኝ
-----6/ "የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መጽናናትን ያገኛሉ" (ማቴ 5፡4) የሚለው ምን ለማለት ነው?
ሀ/ ስለ ኀጢዓት እያሰቡ ማዘን ለ/ ስለ ባልንጀራ ኀጢዓት እያሰቡ ማዘን ሐ/ በሥጋ ስለሞተ ሰው እያሰቡ ማዘን
መ/ ስለ ምድራዊ ሀብትና ስልጣን መጥፋት ማዘን ሠ/ ሀ ና ለ ረ/ ሁሉም
-----7/ ከሰይጣን ፈተና ለመውጣትና ድል ለመንሳት ማድረግ የማይገባን የቱ ነው።
ሀ/ ዘወትር ተግቶ ከልብ መጸለይ ለ/ ለፈቃደ እግዚአብሔር መገዛት ሐ/ ሥጋዊ ፍላጎታችንን መጠበቅ፣ ለእርሱ መገዛት
ሐ/ ነቅቶ፣ ተግቶና፣ ታጥቆ መቆም(1ጴጥ 5:7) መ/ ልማዳዊ፣ ስሜታዊ ኀጢዓትን ማጎልበት ሠ/ ሐ ና መ ረ/ሁሉም
-----8/ …………………… ሰዎችን የሚመለከቱ የጽድቅ ሥራዎች ናቸው፡፡
ሀ/ ጥበብ፣ ንቃት፣ ትህትና፣ ትዕግስተኝነት ለ/ ገርነት (ደግነት)፣ አስተዋይነት፣ ጽጉዕነት (ጽናት) ሐ/ ሰላማዊነት፣ ልግስና፣ እውነተኛነት መ/ ልበ ሰፊነት፣ ደስተኛነት፣
ታማኝነት ሠ/ ጨዋነት፣ ህዳጌ በቀል (ይቅርባይነት) ፣ አማኝነት ረ/ መ ና ሠ ሰ/ሁሉም ሸ/ ሀ ና ሐ
-----9/ አታመንዝር የሚለው ሕግ የተሰጠበት ዓላማ ነው
ሀ/ በዋጋ ስለተገዛን፣ በሥጋችን እግዚአብሔርን ማክበር ስላለብን ለ/ አመንዝራነት እንሰሳዊ ፀባይ ስለሆነ ሐ/ አዕምሯችን እንድንጠብቅ
መ/ አመንዝራነት ደስ ስለሚል ሠ/ መልሱ የለም ረ/ ከ "መ" በቀር ሁሉም
-----10/ "ጌታችን ነፍሳትን የሚሰርቁትን ሌቦች ይላቸዋል" (ዮሐ 10) ለመሆኑ እንዴት ይሰርቃሉ?
ሀ/ በኑፋቄ፣ በሐሰት ትምህርትና ትንቢት ለ/ ወደ ኀጢዓት መንደር ወደ ሞት መንደር በመውሰድ ሐ/ አለማዊ ትምህርትን በማስተማር መ/ ሀ ና ለ ሠ/ ሁሉም
-----11/ ……………………….. ከስድስቱ ህግጋተ ወንጌል አይመደብም
ሀ/ በዓይን ያየ የተመኘም አመነዘረ ለ/ ወንድሙን ጨርቃም ብሎ የተሳደበ ይፈረድበታል ሐ/ ታምሜ ጎበኛችሁኝ መ/ ተርቤ አበላችሁኝ
ሠ/ ሁሉም ረ/ ሀ ና ለ ሰ/ ሐ ና መ
-----12/ አንቀጸ ብፁአን የተባለውን ትምህርት ማን አስተማረ ይህ ትምህርት ………………. በሚል ስያሜም ይጠራል
ሀ/ ኢየሱስ፣ ህገ ኦሪት ለ/ ጳውሎስ፣ የተራራው ስብከት ሐ/ ክርስቶስ፣ አንቀጸ ወንጌል መ/ ኢየሱስ፣ የተራራው ስብከት
ሠ/ ጴጥሮስ፣ አንቀጸ ብፁዓን
-----13/ "በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው" ማለት ምን ማለት ነው?
ሀ/ በትህትና የሚኖሩ ለ/ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ሐ/ በአለማዊ እውቀት ደካማ የሆኑ መ/ እራሳቸውን ያዋረዱ
ሠ/ ሀ ና መ ረ/ ሁሉም
ትዕዛዝ ፬- የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ ተገቢውን መልስ በፅሁፍ ስጡ። (2.5 ነጥብ)
1. ሥነፍጥረታት የተፈጠሩት ለአንክሮ ለተዘክሮ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው?
2. ስንት አይነት የግል ፀሎት አለ? ዘርዝራቹ አብራሩ።
3. 6ቱ ቃላተ ወንጌል የሚባሉትን ከነ ጥቅሶቻቸው ዘርዝሩ።
4. ከተራራው ስብከት ወይም ከብፁዓን አዋጆች ውስጥ ቢያንስ 5 ጥቀሱ።
5. የዝምታ እና የአርምሞ ልዩነታቸውን አብራሩ።
6. የማህበር ጸሎት ጥቅሞች ምን ምንድን ናቸው።
7. ኢየሱስ ክርስቶስ የት ነው የሚገኘው? ለምንድነውስ የማንቀበለው?
8. 10ቱን ትዕዛዛት ዘርዝረህ ፃፍ?
9. ፀሎተ ኢየሱስ ወይም ፀሎተ ልቦና የምንለው የቱን ፀሎት ነው?
ትዕዛዝ ፭- ጉርሻ
1. ከ 22ቱ የእግዚአብሔር ኅቡዕ ስሞች (22ቱ አሌፋት) ቢያንስ 7ቱን ጥቀሱ። (3 ነጥብ)
2. ከአጠቃላይ የክርስቲያናዊ ሥነምግባር ትምህርታቹ የተረዳችሁትን በ አንድ ዓ.ነገር አስቀምጡ፡፡ (1 ነጥብ)

You might also like