You are on page 1of 2

1: ሥነ- ፍጥረት ስንል ምን ማለታችን ነው ?

ሀ/ የፍጥረት መበጀት ለ/ የፍጥረት አይነት ሐ/ ፍጡር መ/ አዳም

2: እግዚአብሔር አምላክ በነቢብ (በመናገር) ከፈጠራቸው ፍጥረት መሀከል -------ነው?

ሀ/ብርሃን ለ/ ጠፈር ሐ/ ጨለማ መ/ሀ እና ለ

3: ከመላዕክት ግብራቸው መሀከል

ሀ/ መላዕክት ሰውን ይረዳሉ ለ/ መላዕክት ንሰሐ በሚገባ ሰው ደስ ይሰኛሉ

ሐ/ መላዕክት ለሰው ይማልዳሉ መ/ ሁሉም

4: በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይን እና ምድርን ፈጠረ :- ይህ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል በየትኛው ክፍል ይገኛል?

ሀ/ ዘፍ 1÷1 ለ/ ዘፍ 2÷1 ሐ/ ዮሐንስ ወንጌል 1÷1 መ/ ሀ እና ለ

5: አርብ ማለት :- በሚስጢራዊ አፈታቱ

ሀ/ የፍጥረት መካተቻ ለ/ የመና መካተቻ ሐ/ የሥራ መካተቻ መ/ ሁሉም

6: ሰው ከፍጥረት ሁሉ የከበረ ነው ምንለው ------- ምክንያት ነው ፡፡

ሀ/ ፍጥረት ከተፈጠሩ በሀላ በመፈጠሩ

ለ/ በምድር ላይ የተፈጠሩ ፍጥረታትን ገዢ ስለሆነ

ሐ/ በእግዚአብሔር አርያና አምሳል በመፈጠሩ


መ/ ሁሉም

7: እግዚአብሔር አምላክ በገቢር (በመስራት ) የፈጠረው ፍጥረት ----- ነው

ሀ/ ሰው ለ/ መላዕክት ሐ/ ጨለማ መ/ከዋክብት

8: እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረትን ---- መንገድ ፈጠረ

ሀ/ በ 3 ለ/ በ 2 ሐ/ በ 5 መ/ በ 7

9: በስነፍጥረት አቆጣጠር ረብዕ ስንተኛ ቀን ናት?

ሀ/ 2 ኛ ቀን ለ/ 4 ኛ ቀን ሐ/ 3 ኛ ቀን መ/ 5 ኛ ቀን

10: መላዕክ ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ/ መልዕክተኛ ለ/ አለቃ ሐ / ሹም መ/ ሁሉም

11: የመላዕክት ባሕሪያት መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?

ሀ/ መላዕክት በፍጥረታቸው ረቂቃን ናቸው ስጋና አጥንት የላቸውም ፡፡

ለ/ ቁጥራቸው በአሀዝ ( በቁጥር ) አይወሰንም

ሐ/ መላዕክት ንሰሀ በሚገቡ ደስ ይሰኛሉ

መ/ ሀ እና ለ

You might also like