You are on page 1of 2

በስመ አብ ወወልድ ወመንፍስ ቅድስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሙሉ ስም ---------------------------
የመስንቆ ተማሪዎች መመዘኛ ፈተና (50)
ክፍል አንድ ፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ፡፡
1…………………… መሰንቆ ከክር የዜማ መሳሪያ ይመደባል፡፡.
2 ………………….. የምንሰማው ድምፅ ሁሉ ዜማ ነው፡፡
3 ………………….. መሰንቆ የሃይማኖት ምሳሌ ናት ሲባል ያልተጠመቀ
ሰው መምታት ስለማይችል ነው፡፡
4 ……………………ዳያቶኒክ እስኬል 5 የድምፅ ደረጃ ያለው ነው፡፡
5……………………. Do Re በእንግሊዘኛው C እና B ማለት ነው፡፡
6 …………………..ትዝታ ቅኝት ከተፈጥሮ ድምፅ 4 ኛ እና 7 ኛ ድምፅ በመግደፍ
ይገኛል፡፡
ክፍል ሁለት ፡- ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. ከሚከተሉት ውስጥ የቱ ነው ትክክል
ሀ. E # አንጂ b የለውም ሐ. B b እንጂ # የለውም
ለ. ከ E እስከ A ሲላካ 3 Tone ነው መ. B ተነስተን አንድ ቶን ስነሂድ D አናገኛልን፡፡
2. ልዩ የሆነው የቱ ነው፡፡
ሀ. ከ E እስከ G# ለ ከ B እስከ C# ሐ ከ A# እስከ D መ ከ F እስከ A
3. ለምስጋና የማይውል ለሐጢያት፣ ለዝሙት፣ ለጣዎት ማምለኪያ የሚውል የዜማ አይነት የቱ ነው
ሀ.) መንፈሳዊ ዜማ ለ) የአዕዋፍ ዜማ ሐ) አላማዊ ዜማ መ) ባህላዊ ዜማ
4. መሰንቆ በእጣን መታሸቱ የምን ምሳሌ ነው፡፡
ሀ ) የጌታችን ለ) የነገረ ተዋህዶ ሐ) የእመቤታችን መ) የቅዱሳን
5. በዜማ ድምፆች መካከል ያለው ርቀት በምን ይለካል፡፡
ሀ ) በስኬል ለ) በቶን ሐ) በቅኝት መ) በሜጀር
ክፍል ሦስት፡- ሀ ስር ያሉትን ከለ ስር አዛምድ
ሀ ለ
1. ….መሰንቆ ሀ ) የደብረ ሲና
2. ….መቃኛ ለ) የድንግል ማርያም
3. … በርኩማ ሐ) የፃድቃን ምሳሌ
4. …ጭራ መ) የኖህ ቃል ኪዳን
5. …እጣን ሠ) የልዑል እግዚአብሔር
6. …የድምፅ ሳጥን ረ) የእመቤታችን (የሀይማኖት)
7. …መገዝጋዣ (ቦ) ሰ) የአንዲት ሃይማኖት
ሸ) የጥምቀት
ቀ) የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ
ክፍል አራት፡ ትክክለኛውን መልስ ስጡ(
1. መሰንቆ በምን በምን ይመሰላል አብራሩ
2. መሰረታዊ የዜማ ድምፆች የሚባሉ ስንት ናቸው
3. ቅኝቶች(ሜዠር) ለመጨመር ወይም ለመቀነስ የምንጠቀምባቸውን ጠቃሚ ምልክቶች ፃፉ
4. ዋና ዋና የኢትዮጵያ ቅኝቶች የሚባሉት ስንት ናቸው እነሱስ
5. የትዝታ ቅኝት ልኬት ፃፉ
6. ሜዥር ዳኛቶኒክ እስኪል ኢንተርቫል (ቀመር ) ፃፉ
7. ቅኝቶች እርስ በርሳቸው በምን በምን ይለያያሉ፡፡
8. መስንቆ በመጽሀፍ ቅዱስ የት ቦታ ይገኛል፡፡
9. ፔንታቶኒክ ስኬል ማለት ምን ማለት ነው፡፡
10. ድምጽ መሰንቆ ላይ ወደታች ስወርድ ምን ይሆናል
ቦነስ
1. በሜዠር ዲያቶኒክ ስኬል ደርድሩ
ሀ )F#
ለ )Bb
ሐ )D
2. በትዝታ ሜዠር ቅኝት መሰረት ስሩ
ሀ ) Eb
ለ )A#
ሐ )B
3. በአንቺሆዬ ቅኝት መሰረት ስሩ
ሀ )Gb
ለ )C#
ሐ )F

You might also like