You are on page 1of 1

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በአንቀፀ ብፁዓን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና አቡነ ሐብተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፍሬ ቅዱሳን ሰንበት ትምህርት ቤት የቀዳማይ ኮርሰኞች የትምህርተ
ሃይማኖት ማጠቃለያ ፈተና።
ስም--------------------------------------------------------- ቀን------------------- ፊርማ---------------- የተሰጠው ደቂቃ፡- 45

ትዕዛዝ ፩- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል የሆኑትን እውነት ስህተት የሆኑትን ደግሞ ሀሰት በማለት መልሱ።
---------- 1. ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን ስንል የክርስቶስን መነሳት ማለት ነው የሚለው በደንብ የገልፀዋል፡፡
---------- 2. ቁርባን ነብስ የተዋሐደው የክርስቶስ ስጋና ደም ነው፡፡
---------- 3. ክርስቶስ ሲራብ በስጋው ሙት ሲያስነሳ በመለኮቱ ነው፡፡
---------- 4. የምንጠመቀው ከክርስቶስ ከጎኑ በፈሰሰው ውሃ ስለሆነ ከወልድ ነው ምንወለደው፡፡
---------- 5. ጥምቀት ከሚደጋገሙ ምስጢራት አንዱ ነው፡፡
---------- 6. ቁርባን ከ ስንዴ እና ከወይን ስለሚዘጋጅ ምሳሌ ወይም ማስታወሻ ነው ልንል እንችላለን፡፡
---------- 7. ሥላሴ ስንል ሦስት አካል ሦስት መለኮት ማለታችን ነው፡፡
ትዕዛዝ ፪- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክለኛ የሆነውን በመምረጥ ይመልሱ።
-----8. ለቁርባን ከሚደረጉ ዝግጅቶች መካከል ያልሆነው?
ሀ/ ልብስ ማንፃት ለ/ ሰውነትን ንፁ ማድረግ
ሐ/ ሀእና ለ መ/ መልስ የለም
-----9. በፍጹም ተዋሐዶ ሰው ሆነ ስንል የቱን አይወክልም
ሀ/ ያለ መቀላቀል ለ/ ያለ መለወጥ ሐ/ ያለ ተላጽቆ መ/ መልስ የለም
-----10. ለምን ሰው ሆነ
ሀ/ የአዳምን ያተፈረደበትን ሞት ለመሻር ለ/ ሐዲስ ተፈጥሮ ለመስጠት ሐ/ ከዳቢሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት
መ/ አባታዊ ፍቅሩን ለመግለጥ ሠ/ ሁሉም መልስ ነው፡፡
ትዕዛዝ ፫- የሚከተሉትን ጥያቄዎች በአጭሩ ተገቢውን መልስ በፅሁፍ ስጡ።
11. የጥምቀት ምሳሌዋችን ጥቀስ፡፡
12. ለትንሳኤ ማስረጃ አንድ ጥቅስ፡፡
13. ምስጥረ ሥላሴ ለምን ምስጥር ተባለ፡፡
14. የሥላሴን ሦስትነት አብራሩ፡፡
15. ኩነት ከሌሎቹ በምን ይለያል፡፡
16. ድሕነት ማለት ምን ማለት ነው፡፡
17. ለትንሳኤ ማስረጃችን ማን ነው፡፡
18. የሰውን ልጅ የሚያድነው ምን መሆን አለበት፡፡
19. ስለ ጥምቀት ሚያስረዳ አንድ ጥቅስ፡፡
20. ሥላሴን ሚያስረዳ አንድ ጥቅስ፡፡
21. የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ስም ማን ነው፡፡
22. ቅዱስ ቁርባን ለምን ቅዱስ እንለዋለን፡፡
23. ለቁርባን ማስረጃ አንድ ጥቅስ፡፡
24. ተዋሕዶ ማለት ምን ማለት ነው፡፡

You might also like