Professional Documents
Culture Documents
ዮጊት
ዮጊት
አዲስአበባ, ኢትዮጵያ
ታህሳስ/2015 ዓ.ም
ምስጋና
በመጀመሪያ የትምህርት/ቤት መሻሻል/ም/ር/መ/ር አሰፉ ክብረት በስልጠናና በአስፈላጊ ቁሳቁሶች ድጋፍ ላደረጉልን ልባዊ ምስጋናችንን
እናቀርባለን፡፡
ማውጫገ ገፅ
ምዕራፍ አንድ
መግቢያ…………………………………………………………………….…………………..1
1.2. የጥናቱ ዳራ………………………………………………………………………………2
1.3.የጥናቱ መንሥኤ………………………………………………………………………….3
1.4. የጥናቱ ዓላማ…………………………………………………………………………….3
1.4.1. አጠቃላይ ዓላማ………………………………………………………………………..3
1.4.2. ዝርዝር ዓላማ…..…………….………………………………………………………..3
1.5. የጥናቱጠቀሜታ…………………………………………………………………………3
1.6. የችግሩማላምት…………………………………………………………………….……4
1.7. የጥናቱወሰን……………………………………………………………………………..4
ምዕራፍ ሁለት፡ ተዛማጅ ጽሁፍ
1.2 የጥናቱ ዳራ
በሥነ-ምግባር ትምህርት ተማሪዎች በምዕራፍ አንድ ግብረ-ገብ በተለያየ ጊዜ ተምረዋል የተለያዩ ፅሁፎች በርዕሱ ዙሪያ
ተፅፈዋል፡፡
ዑራኤል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛደረጃ ትምህርት ቤትበቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01
በ 1963 ዓ.ም. የተመሰረተነው፡ሰፊ ግቢናማራኪ ውብ ንፁህ አየር የሚነፍስበት ለመማር ማስተማርናለንባብ ምቹ ሲሆን
ተማሪዎች የክፍል የመጫወቻ ሜዳ የተለያዩ የት/ት ቢሮዎች ሲገኙ እንዲሁም የአስተዳደር ቢሮ በፎቆች ላይ የተለያየ
አገልግሎት በመስጠት ይገኛል የቅድመ መደበኛ መማሪያናመጫወቻም ይገኛሉ የተለያዩ ለመማር ማስተማር አገልግሎት
ደጋፊዎች በሙሉይገኛሉ፡፡
1.5.የጥናቱ ጠቀሜታ
ይህ ጥናት ለተማሪዎች ለመምህራን ለወላጅ በጣም ጠቀሜታ አለው ። ምክንያቱም ተማሪዎች ካለባቸዉ ችግር ተሻሽለዉ ማየት
ለሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ማለትም በቅድሚያ ለራሱ ከዚያም ለቤተሰብ ,ለወገን ብሎም ለሀገር እድገት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
1.6.የችግሩ መላምት
ለዚህ ጥናት ምክንያት ይሆናሉ ተብሎ በአጠኚዎቹ የታሰበ መላምት
ሀ. ተማሪዎች የመጡበት አመጣጥ (አስተዳደግ)
ለ. ለትምህርቱ ብዙ ቦታ ባለመስጠት
ሐ. ከአሣዳጊ ወይም ከወላጆቻቸው ምክር ማጣት
መ.የመምህሩ የማስተማሪያው ሥነ-ዘዴው ግልጽ አለመሆን
ሠ. የጓደኛ አላስፈላጊ ምክሮችን በመቀበል
ረ. መጤ ባህሎች ኢትዮጵያዊነትን የማያሳዩ ዘመናዊ ለመሆን ከመፈለግ
ሰ. በእኛ ወግ የተነወሩ ፊልሞችን በመመልከት
1.7. የጥናቱ ወሰን(scope of the research)
ይህ ጥናት ና ምርምር በ 8 ኛሀ በሁለት ወንድ ተማሪዎች በ 2015 የዑራኤል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሥነ-ምግባር ችግር
ያለባቸው ተማሪዎችን ነው፡፡
ውስንነት
ይህን ተግባራዊ ጥናት ና ምርምር ስንሰራ
መምህራን ቶሎ መገናኘት አለመቻል
በክፍለ ጊዜ አለመቻቸት
የተለያዩ መረጃዎችን ለመሰብበሰብ ናለመገናኘት ካለን ጊዜ እጥረት
እንዲሁም መፃህፍቶችን በሰፊው ያለማግኘት ለዚህ ጥናት ችግሮች ነበሩ፡፡
ምዕራፍ ሁለት
2. የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ
የዚህ ተግባራዊጥ ናትናምርምር መረጃዎች የተሰበሰቡት ለጥናቱ ከተወሰኑት ዋነኛ ተተኳሪዎች ማለትም በናሙናነት
ከተመረጡት የስነ-ምግባር ችግር ካለባቸው ተማሪዎች ከተማሪ ወላጆች እናመምህራን በፅሁፍ መጠይቅ የተሰበሰበ
መረጃ ነው፡፡
2.1. መረጃዎቹ የተተነተኑበት መንገድ
የተግባራዊ ጥናት አድራጊው ከተማሪዎች ከተማሪ ወላጅና ከመምህራን በፅሁፍ መጠይቅ የተሰበሰበውን በግልፅ
በማሣየት በሚያመች መልኩ ቁጥሮቹን በመጠቀም ለመተንተን ተሞክሯል፡፡
ምዕራፍ ሦስት
3.1 ለመምህራን የተዘጋጁ መጠይቂች ናምላሾች
የዑራኤል መ/ደ/ት/ቤት የሚያስተምሩ መምህራንና 8 ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የተጠየቁ መጠይቆች ናምላሾች
3. የተማሪዎችን ሥነ-ምግባር ችግር ለመፍታት በይበልጥ መወሰድ ያለበት እርምጃ ምንድን ነው?አማራጮች፡
ሀ. የወላጅ ድጋፍ መጠንከር አለበት
ለ. የት/ቤቱ ደንብ በግልፅ ማስረዳት
ሐ. የመምህራን ምክር የጎላ መሆን አለበት
4. ተማሪዎችን በስነ-ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ከተማሪዎች ከመምህራን እና ከወላጆች ምን ይጠበቃሉ ይላሉ በዝርዝር
ይፃፉ::
ከመምህራን የሚጠበቀው
ከወላጅ ጋር ቀጣይነት ያለው ምክክር ማድረግ
ተማሪዎች በስነ-ምግባር ለውጥ ሲያሳዩ ማበረታታት
መምህሩ ተማሪዎቹን እንደልጁ መቁጠር ናበማቅረብ መምከር
መምህራን ለተማሪዎች አርአያ መሆን
ከተማሪዎች የሚጠበቀው
በክፍል ውስጥ ከመረበሽ ይልቅ መምህሩን መከታተል
ተማሪዎች ለጓደኛቸው ታማኝ ግልፅ መሆን
የስነበ-ዜጋ ና የስነ-ምግባር ት/ት ለቁጥር ሳይሆን የባህሪይ ለውጥ ለማምጣት መስራት
ከወላጆችየሚጠበቀው
የልጆችን ውሎ መከታተል
ስለልጆቻቸው ውጤት መከታተል ና የሚሰጣቸው መልመጃዎች እንዲሰሩት ማድረግ
2.የስነ-ዜጋ ና ስነ-ምግባር ት/ት ከሌሎች የት/ት አይቶች ጋር ሲነጻጸር ያንተ(ቺ) ውጤት ምን ይመስላል፡፡
አማራጮች ወንድ በፐርሰንት ሴት በፐርሰንት ድምር በፐርሰንት
ሀ. ከፍተኛ 2 40% 3 60% 5 100
ለ. መካከለኛ - - - - - -
ሐ. ዝቅተኛ - - - - - -
በተራ ቁጥር 2 ዝቅተኛነው ካልክ(ሽ) ምክንያቱን ይፃፉ
ለሚለው አንድም ተማሪ ዝቅተኛ ነውያለ የለም፡፡
5. ተማሪዎች የስነ-ምግባር ችግር እንዳይታይባቸው ከተማሪዎች ከመምህራን እና ከወላጆች (ከአሳዳጊዎች) ምን
ይጠበቃል ትላለህ(ሽ)
በስነ-ምግባር የታነፀ ዜጋን ለማፍራት ከመምህሩ የሚጠበቀው
ከወላጆች ጋር የልጆቻቸውን ውሎ እንዲከታተሉ መነጋገር
የግብረ ገብ ት/ት በአግባቡ ማስተማር
ተማሪዎች ታዛዥ እና ታማኝ እንዲሆኑ መምከር
የችግሩ ባለቤት ከሆኑት ተማሪዎች ጋር ተከታታይነት ያለው ውይይት ማድረግ
ከተማሪዎች ምን ይጠበቃል
የስነ-ዜጋ ና የስነ-ምግባር ት/ትን ለማርክ ብቻ ሳይሆን የስነ-ምግባር ባህሪያትን ተረድተው
ታማኝ
ታዛዥ እና
ቅን መሆን
የስነ-ምግባር መርሆችን ጠንቅቆ ማወቅና መተግበር
ማንኛዉንም ማህበረሰብ ማክበር
ከወላጆች የሚጠበቀው
ውሏቸውን መከታተል
የት/ት ግብአቶችን ማሟላት
የሚሰጣቸውን የቤት ስራዎች እንዲሰሩ መከታተል
ስለልጆቻቸው ከመምህራን ጋር መወያየት
ሀ. አዎ 2 3 5
ለ. አልተወያየውም 2 2 4
በተራ ቁጥር 1 አልተወያየሁም ለሚለውመጠይቅ ምክንያቱን በዝርዝር ይፃፉ ለሚለው
ካለብን የጊዜ እጥረት የተነሳ ነው ያሉት 3 ወላጆች እንዲሁም
1 ወላጅ ልጄ በቤቴ ውስጥ ጨዋ ስለሆነ ያንን ባህሪ ት/ቤት ውስጥም የሚተገበር መስሎ ስለታየኝ ነው ብለዋል፡፡
2. እርሶ ለተማሪው(ዋ) የት/ት ግብአት አሟልተውለታል(ላታል)
አማራጮች ወ በፐርሰንት ሴ በፐርሰንት ድምር በፐርሰንት
ሀ. አዎ 4 3 7
ለ. አላሟላሁም - - - - - -
በተራ ቁጥር 2 አላሟላሁም ካሉ ምክንያቱን በዝርዝር ይፃፉ ለሚለው ማንም የለም
3. በት/ቤት አካባቢ አዋኪ ነገሮች አለ ይላሉ
አማራጮች ወ በፐርሰንት ሴ በፐርሰንት ድምር በፐርሰንት
ሀ. አዎን 1 1
ለ. የለም 4 2 6
ሐ. ካለይጠቀስ
በተራ ቁጥር 3 ካለ ይጠቀስ ለሚለው
ከአንድ ወላጅ የተሰጠ ምላሽ በት/ቤቱ አዋኪ ነገሮች የሉም ነገርግን ተማሪዎች ከት/ቤቱ ሲወጡ የተለያዩ ሱቆች ስላሉ
ተማሪዎች በሱስ የተበርዙ ሰዎችን ባህሪ ና መጥፎ ነገር ይጋራሉ ብለዋል፡፡
ከተማሪ የሚጠበቀው
ታማኝ ቅን ታዛዥ መሆን
መምህራን የሚሏቸውን በአግባቡ መስማት ና መተግበር
የስነ-ምግባር ት/ትን ለቁጥር ሳይሆን ለተሻለ ባህሪ መጠቀም
በቤት ውስጥ እርስ በርስ መከባበር
ምዕራፍ አራት
4.1 በችግሩ የተነሱ ነጥቦች
ሀ. አንዳንድ ወላጅ/አሳዳጊ የልጆቹን ባህሪ በደንብ አለመረዳታቸው
ለ. ወላጆች ተማሪዎቹን በት/ት ላይ በሚገባ አለመረዳት
ሐ. ወላጅ ልጆቹን በት/ትም ሆነ በሥነ-ምግባር አለማነፅ ሁሉንም መምህር ላይ ብቻ
በመጣል ችግሮቹ በክፍል እንዲታዩ አድረጓል፡፡
መ. በክፍል ውስጥ ፀጥታ እንዲከበር ሁሉንም ተማሪ የሚገዛ ደንብ ከተማሪዎች
ጋር ተመካክሮ በጋራ ማውጣት
የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች
ሀ. ለተማሪዎች መልካም ስነ-ምግባር ግንባታ ለጤናማ የት/ት ክትትል ውጤት ከወላጆች
እኩል የተፈለገውን ያህል አልተገኘም ስለዚህ ወላጆች ለመማር ማስተማሩ ሂደት
ስኬታማነት የቅርብ ክትትል ቢያደርጉ
ለ. አንድ ተማሪ ወይም ተማሪዎች የሥነ-ምግባር ችግር ቢፈጥር (ሩ) ችግር ፈጣሪዎችን
ለይቶ እርማት መስጠት ናማስተማር እንጂ ሁሉንም ተማሪዎች በጠቅላላ አለመቆጣት
ወይም አለመቅጣት ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል
ሐ. የተማሪዎች የስነ-ምግባር ችግር ጉዳዩ የአንድ ወገን ሥራ ብቻ ባለመሆኑ
የሚመለከታቸው ሁሉ በጋራ በመሆን ችግሩ የሚቃለልበት መንገድ ቢፈለግ ትኩረት ቢሰጥበት
መ. በክፍል ውስጥ ፀጥታ እንዲከበር ሁሉንም ተማሪ የሚገዛ ደንብ ከተማሪዎች ጋር
ተመካክሮ በጋራ በማውጣት በሚታይ ቦታ በትልልቁ በመፃፍ መለጠፍ ቢቻል እና ደንቡን
የተላለፈ ተማሪ በቂ ቅጣት መስጠት ነው፡፡
ማጣቀጫ
ከሥነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ማሰልጠኛ ሞጁል የፌደራል ሥነ-ምግባር ናየፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሚያዚያ 2008
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠ/ማ/ጉ/ቢሮ ካዘጋጀው ሞጁል ላይ ስለ ሥነ-ምግባር 2009 ዓ.ም. የተወሰደ