You are on page 1of 10

1.

መግቢያ
1.2. የጥናቱ ዳራ

ይህ ጥናትና ምርምር የተካሄደው በረጲ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ትመረህርት ቤትየ 5 ኛ”D” ክፍል 5

ወንድ ተማሪዎች ካላቸው የባህርይ ችግር መነሻ በማድግ ነው እነዚህ ተማሪዎች በክፍልም ሆነ በትምህርት

ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ያለባቸው የባህሪይ ችግር ለማሸሻል ታስቦ ነው እነዚህ ወንድ ተማርዎች ያለባቸው

የባህሪይ ችግር ባጭሩ ካለተፈታ ለክፍል ተማርዎችም ሆነ ለመምህራን በመማር ማስተማሩ ስራ ላይ

አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥር ስለሆነ ችግሩን ለመፍታት ፤ከተማሪዎች ፤ከተማሪወላጆች እናከመምህራን ጋር

በመሆን የመፍትሄ ሀሳብ ለማፈላለግና ችግሩን ለመቅረፍ የበኩላችንን ድጋፍና ክትትል እናደርጋል፡፡

1.3. የጥናቱ አላማ

በረጲ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 5 ኛ”D” ክፍል 5 ወንድ ተማሪዎች የባህሪይ ችግር

መንስኤውን ለመረዳትና መፍትሄ ለመስጠት አላማዎችን ነድፊያለሁ

1.በ 5 ኛ” D ክፍል ያሉ 5 ወንድ ተማሪዎች የባህሪይ ችግር መንስኤለመረዳት

2.ችግራቸውን መነሻ በማድረግ የተሻለ ባህሪይ እንድኖራቸው ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ

1.4 በ የጥናቱ መሪ ጥያቄዎች

1
እነዚህ ጥያቄዎች ችግሩን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋጽ ኦአላቸው

1በ5ኛ”D

ክፍል ያሉ 5 ወንድ ተማሪዎች ለባህሪያቸው መበላሸት ምክኒያት የቤተሰብ ክትትል ማነስ ይሆን

2.ከትምህርት ቤት ውጭም ሆነ ከትምህርት ቤት ውስጥ ያላቸው የጋደኛ ተጽእኖ ይሆን

3.የተማሪዎች የትምህርት ፍላጎት ያለመኖር ይሆን

የቃላት ትርጉም

የባህሪይ ችግር ማለት በክፍል ውስጥም ሆነ ከክፍል ውጭ አላስፈላጊ የሆኑ የመማር ማስተማር ስራን

የሚያደናቅፉ ስነምግባር ማሳየት ማልት ነው

2. ምዕራፍ ሁለት

2.1. የተዛማጅ ፁሑፍ ቅንብር (Review of related literature)

2
የተማሪዎች ባህሪይ ብዙ አይነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የዚህ ጥናትና ምርምር ትኩረትም በአሁኑ ሰዓት

በተማሪዎች ላይ ያለው የባህራይ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ የዚህን ችግር ለመፍታት አስፈላጊ

ነው፡፡ የተለያዩ ምሁራን የፃፏቸው መፅሐፍትና ያደረጓቸው ጥናቶችን በመዳሰስ አሰፈላጊ የተዛማጅ ፁሑፍ

ቅኝት ተደርጎአል፡፡ ይሔም እንደሚከተለው በአጭሩ ቀርቧል፡፡

2.2. የተማሪ ባህሪይ ንድፍ ሃሳብ

ይህ የተማሪዎች ባህሪይ ንድፈ ሃሳብ ባህሪይ ብለን የምንጠራው ስነምግባር ማለት ሲሆን የአንድ ሰው

ጥሩነት ወይም መጥፎነትን የሚነገረን ተግባር ነው፡፡ የባህሪይ ችግር ማለት በክፍል ውስጥና ውጭ የመማር

ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ማለት ነው፡፡ የባህሪ ችግር መኖር የመማር ማስተማር ሂደትን የሚጎዳ ነው

(ኤልሳቤጥ 1982 እናቦርች 1988)፡ይህ ሁኔታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ አሉታዊ ተፅዕኖ

እንዳለው ብዙዎቹ ካመኑበት ቆይቷል (Du,plesis1988 and odharo1996) ::

3. ምዕራፍ ሶስት

3.1. የጥናቱ ስነ ዘዴ

3
ይህ ጥናትና ምርምር በረጲ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 5 ኛ ”D ክፍል 5 ወንድ

ተማሪዎች የባህሪይ ችግር ላይ ሲሆን የእነዚህ ተማሪዎች የባህሪይ ችግር መንስኤዎችን ለመለየት ከተማሪ

ወላጆችና ከራሳቸው ከተማሪዎች ጋር በመወያየት እንዲሁም የክፍል አለቆችን በማነጋገር መፍትሄ በመፈለግ

የተሻለ ስነምግባር እንድኖራቸው በማድረግ በክፍል ውስጥ የተሻለ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍተርና

ለአጋር መምህራን ጥያቄዎችን በማዘጋጀት ፤በመተንተን ፤ተሻለ መሸሻል እንዲኖር አደርጋለሁ

3.2. የናሙና አመራርጥ ዘዴዎች

ይህ ጥናትና ምርምር የተካሄደው በረጲ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በሚገኙ በ 5 ኛ” D

ክፍል ውሰጥ 5 ወንድ ተማሪዎች በሚያሳዪት የባህሪይ ችግር ላይ በማተኮር ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክኒያት

እነዚህ ተማሪዎች በረጲ አፀደህፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ትመረህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ

ስለያደርጉ ነው፡፡ ለጥናቱ የሚያስፈልጉ ተሳታፊዎች የክፍል አለቆች የተመረጡት የናሙና አወሳሰድ ዘዴ

በቀጥታ ተሳትፎ አመራርጥ ዘዴ ነው፡፡ መ/ራን በተመለከተ 4 መ/ራን በተጠኝ ክፍል ገብተው ስለሚያስተምሩ

በቀጥታ ተሳታፊ ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ 3 የተማሪ ወላጆችን በምቾት የናሙና አመራረጥ

ዘዴ በመምረጥ ተሳታፊ እንድሆኑ ተደርጓል፡፡

የጥናቱ ተሳታፊዎች

4
ተ.ቁ የጥናቱ ተሳታፊዎች ወ ሴ ድ ምርመራ

1 መምህራን 4 4

2 የተማሪዎች ወላጆች 1 2 3

3 የክፍል አለቆች 1 2 3

4 ጠቅላላ ድምር 6 4 10

ሰንጠረዥ 1.የፁሑፍ ቃለ መጠየቅ የተሳተፉ የጥናት ተሳታፊዎች

የጥናት ተሳታፊዎች ወ ሴ ድ ምርመራ

መምህራን 4 4

የክፍል አለቆች 1 2 3

ጠ/ድ 5 2 7

ሰንጠረዥ 2.በዉይይቱ ተሳተፉ ተሳታፊዎች


5
ተሳታፊዎች ወ ሴ ድ ምርመራ

የተማሪዎች 2 1 3

ወላጆች

ጠ/ድ 2 1 3

3.3. መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች

ለጥናቱ አሰፈላጊ የሆነውን መረጃ ለመሠብሠብ ሶስት የመረጃ መሠብሰቢያ መሣሪያዎችን

ተጠቅመናል፡፡ እነሱም፡

1.ምልከታ በማድረግ (Observation)

2.የፁሑፍ መጠየቅ

3.ውይይት

1. በምልከታ፡ በዚህ የተሰበሰቡ የምልከታ መስፈርቶች የተማሪዎችን የባህሪይ ችግር አመላካች

መሆናቸውን የጥናት ምርምር ልምድ ባላቸው ሁለት የትምህርት ቤቱ መ/ራን ተገምግሞ አስፈላጊ

አስተያየት

1.የመማሪያቁሳቁስ ማሟላት በተመለከተ

2. በክፍል ውስጥ ያላቸው የትምህርት ክትትል በተመለከተ

3. ከክፍል የመውጣት ሁኔታ በተመለከተ

4. የደንብ ልብስ አለባበስ በተመለከተ ምልከታ በማድረግ ለመለየት ተችሏል፡፡

2.የፁሑፍ መጠየቅ ፡ ይህ መጠየቅ የተዘጋጀው የተማሪዎቹን ባህሪይ በተመለከተ የተሻለ ግንዛቤ እንድኖር

ተደርጎ ነው፡፡ በዚህ መሠረት የፁፍ መጠይቅ በናሙናነት በተመረጠ ክፍል ለሚያሥተምሩ መ/ራን ለክፍል

አለቆች ተሰጥቶ ፊት ለፊት እንድሞሉ በማድረግ አሰፈላጊ መረጃ ተሰብስቧል፡፡

3. ውይይት ፡ የተማሪ ወላጅ በመጥራት ስለተማሪዎች ባህሪይ በመወያየት በቀረቡት ሃሳቦች ላይ

መረጃ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

6
3.4. የመረጃ ትንተና

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ፡- በጥናቱ የታቀፉትን ተማሪዎች የባህሪ ችግር ምን ያህል እንደተለወጡ እና በአሁኑ

ሰዓት የመማር ማስተማር ሂደት ያመጡትን የባህሪ ለዉጥ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ነዉ፡፡

ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ በምልከታ ናበፅሁፍ መጠየቅ እና በዉይይት የተሰበሰቡትን መረጃዎች ትርጉም

በሚሰጥ ሁኔታ ተደራጅተዉ ከቀረቡ በኀላ ከተፈለገዉ ጥናቱ ዓላማ አኳ ያ ምን ዉጤት እንደሚያሳዩ

ተተንትነዉ ቀርበዋል፡፡ በምልከታ ወቅት የተፈለጉትን የተማሪ ባህሪያት በተፈለገዉ መጠን አጥጋቢ ሁኔታ

መታየታቸዉን ለማመላከ ትሬቲንግስኬል (rating scale) ነዉ ጥቅም ላይ የዋለዉ፡፡ በዚህ ስኬል ተፈለገዉን

የተማሪዎች የባህሪ ችግር መኖር ለማረጋገጥ አዎ ፤አይደለም እና እርግጠኛ አየደለሁም የሚል እንዲያመላክት

ተደርጎ ተዘጋጅቷል፡፡

ይሄዉም 1. አዎ

2. አይደለም

3. እርግጠኛ አይደለሁም

በዚህም መሰረት ለጥናቱ በናሙናነት የተካተቱ 5 ወንድ ተማሪዎች የምልከታ ዉጤት አማካኝ ነጥብ

ተወስዶ አብዛኛዎቹ የምልከታ ዉጤት አማናከኝ ከ 3 በላይ ሆኖ ከተገኘ የተፈለገዉ የተማሪ ባህሪ

መስተካከል አለመቻሉን ያመለክታል፡፡ በአንፃሩ በአማካኝ ከ 3 በታች ሆኖ ከተገኘ ተማሪዎች ለተፈለገዉ

የባህሪችግር መሻሻል እንዳላቸዉ ያመለክታል፡፡

7
ጥያቄዎች 1 % 2 % 3 %

የመ.ብ የመ.ብ የመ.ብ

የተማሪዎች ለትምህርት 4 40 6 60

ያላቸው ፍላጎት አነስተኛ

ሆኖ ይሆን?

ለባህሪያቸው መበላሸት 5 50 5 50

የወላጆች ክትትል ማነሰ

ይሆን

ለባህሪያቸው መበላሸት 5 50 5 50

ምክኒያት የጓደኛ ተፅዕኖ

ይሆን ?

ጠ/ድ 50 50

ከላይ ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለዉ ለተማሪዎች የባህሪይ ችግር የቀረቡላቸዉ ጥያቄዎች የወላጅ

ክትትል ማነስ 50% ፤ የጓደኛ ተጽዕኖ 50% እና ለትምህርት ያላቸዉ ፍላጎት 40% በመሆን ያመለክታል

በማለት መልሰዋል፡፡ ከተሰጠዉ ምላሽ መረዳት እንደሚቻለዉ በተማሪዎች ላይ የባህሪ ችግር እንደነበረ

ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

4.1 በጥናቱ የተደረሰበት ድምዳሜ

በዚህ ጥናት ናምርምር የተለዩ እነዚህ ሶስት ወንድ ተማሪዎች በተደረገላቸዉ ክትትል ናድጋፍ የነበረባቸዉ

የባህሪይ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻ ለመምጣቱን ከክፍል አለቆች ናከሚያስተምሯቸዉ መምህራን

ከራሳቸዉ ድንገተኛ ምልከታ ለመረዳት ችያለሁ፡፡

8
5.1 ማጠቃለያና መደምደሚያ ,

ይህ ጥናት የሚካሄደዉ በረጲ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ትምህርት ቤት በ 5 ኛ D ” ክፍል ዉስጥ

ተማሪዎች የባህሪ ችግር ምክኒያቶች በመፈለግ መፍትሄ ለማምታት ሲሆን በተለያዩ የመረጃ መሰብሰቢያ

መሳሪያ ተሰብስበዉ የተገኙ ግብዓቶች እንደሚከተለዉ ቀርቧል፡፡

1. ተማሪዎቹ ለትምህርት ያላቸዉ አመለካከት ዝቅተኛ መሆኑ ፤

2. ተማሪዎቹ ትምህርት ቤትን ለጊዜ ማሳለፊያነት የሚጠቀሙበት መሆኑ፤

3. ቤተሰብ ክትትልና ድጋፍ አነስተኛ መሆኑ፤

5.2. መደምደሚያ

ከላይ የተዘረዘሩት ግኝቶች እንደሚያሳየን በ 5 ኛ“ D ክፍል ዉስጥ ወንድ ተማሪዎች የባህሪ ችግር

እንዲኖርባቸዉ የሚያደርጋቸዉ ለትምህርት የሚሰጡት ትኩረት፤ የቤተሰብ ክትትልና ድጋፈፍ ዝቅተኛ መሆኑ

ነዉ፡፡ ስለሆነም እነዚህን ችግሮች አስወግዶ ተማሪዎች ባህሪያቸዉን ለማሻሻል አጥኚዉ የሚከተሉትን

የመፍትሄ የድርጊት ተግባራት አከናዉነዋል፡፡

5.3. የመፍትሄ ተግባራት

1. ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸዉን ግንዛቤ እንዲጨምር ከሁሉም መምህራን እዛ ክፍል ከሚገቡት ጋር

ለመስረሰት ተሞክሩዋል፤

2. ወላጆች ለልጆቻቸዉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ክትትልና ድጋፍ እንዲያደርጉ በተለያ የጊዜ በአካልና በስልክ

እዛክፍል ከሚገቡት መምህራን ጋር ለመስረሰት ተሞክሩዋል፤

3 . እነዚህ ተማሪዎች ትምረታቸዉን እነዲወዱ በግላቸዉ በተለያየ ጊዚያት በማስተምረው የትምህርት

ዓይነት ለመርዳት ሞክሪያለዉ

ከላይ የተዘረዘሩት የመፍትሄ ተግባራት ተግባራዊ በመሆናቸዉ በኣብዛኛዉ ላይ የሚታየዉ የባህሪይ ችግር

በመጠኑ ዉጤት የተሻሉ እንደሆነ የሚል የአጥኚዉ ድምዳሜ ላይ ደርሱዋል፡፡

9
ዋቢ መጻህፍት

- ትምህርት ሚኒስትር መጽሄተ ምርምር 1995 ቁጥር 2 አዲስአበባ

- ሞርጋንና ሌሎቹ 1986 ኢጁኬሽናልሳየኮሎጂ ( Educational Psychology)

- አሊይመር 1992 መጥሄተ ምርምር ከገፅ 1 የተወሰደ

10

You might also like