You are on page 1of 5

1.

የቅድመ መደበኛ ትምህርት የመምህሩ መምሪያ


2. ስርዓተ ትምህርት

3. የተከታታይ ምዘና ሂደት የግንዛቤ መስጫ

እንደ ቅድስት ሃና መዋዕለ ህፃናት ትምህርት ቤት መምህራን ለምታስተምሩበት ትምህርት የመምህሩ አጋዥ
መጽሐፍት በየደረጃዉ መለትም

1. 3-4 ዓመት
2. 4-5 ዓመት
3. 5-6 ዓመት
በየደረጃዉ የተቀመጠዉን እንደየ ክፍል ደረጃችሁ እያንዳንዱን የትምህርት አቀራረብ ከጭብጥ አንፃር
መገምገም አለበት፡፡ ሲገመገምም በእያንዳንዱ ጭብጥ ከልጆች እድሜ አንፃር የሚከብድና በጣም
የቀለለ ወይም በእድሜያቸዉ ሊመጥናቸዉ የማይችለዉን በሚገባ በመለየት በየገጹና በየጭብጡ
መገምገም ነዉ፡፡

የግምገማዉ ሂደት አገማገም


 ጭብጥ 1
ለተገቢዉ እድገትና የአካል ጥንካሬ ተገቢዉን እንክብካቤ ማድረግ

በዚህ ጭብጥ ህፃናት

1. የስሜት ህዋሳቸዉን በአግባቡ መጠቀም አለባቸዉ


2. የአካል ክፍሎቻቸዉን በመለየት በጥንቃቄ መያዝ
3. ጤናቸዉን መጠበቅ አለባቸዉ
4. በአጠቃላይ የአካል ደህንነታቸዉን መጠበቅን ማወቅ እንዳለባቸዉ ያስተማራል

ከዚህም አንፃር ችግር ካለበት መለየትና ማየት ያስፈልጋል፡፡

ጭብጥ 2 እና 5
ተቀባይነት ባለዉ መልኩ ከሌሎች ጋር ግንኙነት መፍጠር እና ከአካባቢ ጋር በሚፈጠር መስተጋብር አካባቢን
ማጥናትና በአግባቡ ማጣጣም

በነዚህ ጭብጦች

1. አካባቢያቸዉን መፈተሸና ማጥናት


2. በአካባቢያቸዉ ያሉ ሰዎችን ማወቅና ፍላጎታቸዉን መረዳት
3. ሌሎችን መንከባከብና ያላቸዉን ማካፈል
4. በአጠቃላይ አካባቢያቸዉንና በአካባቢያቸዉ ዙሪያ ያለዉን ነባራዊ ነገር በመፈተሸ መረዳት ይችላሉ
ከዚህ አንፃር ችግር ያለበትን መለየትና ማዉጣት

ጭብጥ 3 እና 4

ቋንቋን በአግባቡ መጠቀምና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ዉስጥ የሂሳብ ስሌትና እንቅስቃሴ መጠቀም

1. መረጃዎችን በአግባቡ በመሰብሰብ መጠቀም


2. የእንቅስቃሴን ፅንስ ሀሳብ ተረድተዉ መናገር
3. ምናብንና ፈጠራን በመጠቀም ሀሳብን መግለጽ
4. የተለያዩ መፅሀፍትን በማገላበጥ የደስታ ስሜትን መፍጠር
5. የቁሳቁሶችና ባህሪ በመፈተሸ መግለፅንና መረዳት መቻል
6. የጊዜና የቦታን ፅንሰ ሀሳብ መረዳት መቻል

ከላይ በተዘረዘሩት ጭብጦች በመታገዝና በሚገባ በማየት ከልጆች አቅም አንፃር

 የቃላት ችግር
 የመረጃ መሳሪያ አጠቃቀም ችግር
 ከልጆች እድሜ አንፃር
 በአካባቢ ሊገኝ የማይችልና በምናብ የተጠቀሰ ካለ
ይህን የመሳሰለና በመገምገም ወቅት በሚነሱ ሀሳቦች ላይ በመወያየት መለየት፡፡

መልካም ግምገማ
ተከታታይ ምዘና

ተከታታይ ምዘና ከጭብጥ አንፃር የሚገመገም ሲሆን በየእለቱ የልጆችን እንቅስቃሴ በማየት መከታተያ ቅፅ
ላይ መያዝ

1. በኮሙኒኬሽን ቡክ የልጆችን ችግር ለወላጅ በማሳወቅ አብሮ መስራት

2. ዉጤት ትንተናን እጅግ በጣም ጥሩ ፤ በጣም ጥሩ ፤ጥሩ እና ደካማ በማለት መተንተንና በደካሞች ላይ
መስራት
3. ሪፓርት ካርድ ላይ A,B,C በማለት ዉጤት መስጠት
4. በማርክ ማጠራቀሚያ ላይ ግን
 የክፍልና የቤት ስራ 5
 የክፍል ተሳትፎ 5
 የክፍል ሙከራ 10
 የእጅ ጽሑፍ 5
 ከሌሎች ጋር ያለዉ ቅልጥፍና 5
 ሙከራ /ቴስት/ 10
 የሚድ ፈተና 20
 አጠቃላይ ፈተና 40
 በአጠቃላይ ከ 100/ከመቶ ያመጡትን ዉጤት A,B,C ቀይሮ ሪፓርት ካርድ ላይ በመሙላት
ልጆችን ተወዳዳሪ እንጂ የሚለይ ዉጤት እንዲሆን መሰራት አለበት፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫዉን የመሰዱ መምህራን

You might also like