You are on page 1of 19

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ

የማህበራዊ ሳይንስ እና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ


የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል
ለሁለተኛ ዲግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ ትልመ ጥናት
ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ለማሻሻል ያለው ተጽዕኖ በቴፒ
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሰባተኛ ክፍል ተተኳሪነት

አዜብ ጌታቸው

አማካሪ
ደጀኔ አካዩ (ዶ/ር)
የካቲት 2016 ዓ.ም
ምዕራፍ አንድ፤ መግቢያ

1.1 የጥናቱ ዳራ

 ከአራቱ የቋንቋ ክሂሎች አንዱ መፃፍ ሲሆን ለሀሳብ ማስተላለፊያነት የሚያገለግል

ነው፡፡ ለሰው ልጆች የሚሰጠው ጥቅም ከፍ ያለ ሲሆን በዋናነት ዕውቀት

የሚቀሰምበትና የሚተላለፍበት፣ ታሪክ የሚመዘገብበትና ከዘመን ወደ ዘመን

የሚሸጋገርበት ድልድይ ሆኖ ያገለግላል::

 Brown (2004) የመፃፍ ትምህርት የፊደላትን ቅርፅ ከማስለየት ጀምሮ

ተማሪዎች ቃላትን፣ አረፍተ ነገሮችን እና አንቀፆችን ከዚያም ሲያልፍ አንድ

የተሟላ ፅሁፉን መፃፍ የሚችሉበትን ክሂል እንዲያገኙ በየደረጃው ይቀርባል፡፡


የቀጠለ...

 ተማሪዎች በሚጽፉበት ጊዜ ሃሳባቸውን በተሻለ መንገድ ለመግለጽ ይፈልጋሉ፡፡

በጽሁፍ የሚያስተላልፉትን መልእክት ደጋግመው ያስባሉ ፣ይመረምራሉ ፣እግረ

መንገዳቸውንም ስለድርጊትና ቃላት ግንኙነት ይማራሉ፡፡ የመጻፍ ትምህርት

የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆን አለበት፡፡

 ተማሪዎች ስለማያውቁት ነገር እንዲጽፉ ማድረግ መጻፍን እጅግ አስቸጋሪ

ተግባር አድርገው እንዲያስቡት ያደርጋቸዋል፡፡ ተማሪዎች ስለሚፈልጉት ርእስ

በራሳቸው ቃላትና የአገላለጽ ችሎታ ተጠቅመው እየጻፉ መለማመድ አለባቸው

(በድሉ ፣ 1996) ፡፡
1.2 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት
 መጻፍ ከአፍልቆት ክሂል አንዱ ሲሆን ተማሪዎች በውስጣቸው ያለውን ሃሳብ ፣
ስሜታቸውን ፣ፍላጎታቸውን በአጠቃላይ የህይወት ተሞክሮና ነባራዊ ሁኔታዎችን
ወዘተ እንዲገልጡ እና የተለያዩ ልምምዶችን እንዲያከናውኑ የሚጠይቅ ክሂል
በመሆኑ የመጻፍ ክሂላቸውን ለማሻሻል ብዙጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ምክንያቱም በክሂሉ ውስጥ የሚገኙት አላባውያን ማለትም ይዘት ፣አደረጃጀት፣
ቃላት ፣ የቋንቋ አጠቃቀም እና የአጻጻፍ ስርአት በተግባር ተኮር መለማመድ
ስላለባቸው ነው(Nunan፣ 1991)፡፡
 ስለሆነም ተማሪዎች ክሂሉን ለማዳበር ትኩረት ሰጥተው ሰፊ ልምምድና ብዙ
ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡
የቀጠለ…

 የመጻፍ ክሂል ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት፡፡ የመጻፍ ክሂል ሃሳብን ለመለዋወጥ

አዳዲስ እውቀትን ለማግኘትና ልምድን ለማዳበር እንዲሁም ሃሳብን ለመግለጽ

ወይም አንድን የምርምር ውጤት መዝግቦ ለሌላ ትውልድ ለማቆየት ፣በማህበረሰቡ

ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ሆኖ ለመገኘትና አልፎም በተማረ ማህበረሰብ ውስጥ የተለያዩ

ተግባራትን ለማከናወን ትልቅ ሚናን ይጫወታል፡፡

 በተጨማሪም ተማሪዎች የሚማሯቸውን የተለያዩ የቀለም ትምህርቶች በተሳካ

ሁኔታ እንዲከታተሉ ከማስቻሉም በላይ ወደፊት ለሚጠብቋቸው ሙያዎች የስራ

መስኮች ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው (Chen ፣1994)፡፡


የቀጠለ...

 ማረው (1996) በመጻፍ ትምህርት ሂደት በተማሪዎች ላይ የሚከሰቱ ችግሮች

ክህሎት ማነስ እና ሃሳብን በተገቢው መንገድ ማደራጀት ያለመቻል ናቸው በማለት

ይገልጻሉ፡፡

 አጥኝዋ በመምህርነት የሙያ ቆይታዋ ስታስተምራቸው የነበሩ የሰባተኛ ክፍል

ተማሪዎች አብዛኞቹ የመጻፍ ክሂል ችግር የሚታይባቸው መሆኑ ማለትም

የሚሰጣቸውን ተግባራት በአግባቡ መጻፍ አለመቻላቸው እና በትምህርት ቤት

ውስጥ የግል ማመልከቻ ለመጻፍ የመምህራንን እርዳታ መጠየቃቸው ይህንን ጥናት

እንድታካሂድ አነሳስቷታል፡፡
1.3 የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄዎች
ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አውድ ውስጥ
የተማሪዎችን የመጻፍ ችሎታን ከማሻሻል አኳያ የራሱ ሚና ይኖረው ይሆን? የሚለውን
ጥያቄ ለመመለስ አጥኝዋ ጥናቱን ለማድረግ ተነስታለች፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን
ጥያቄዎች ለመመለስ ጥረት ታደርጋለች፡፡
 ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ለማሻሻል
ያለው ጥቅም ምንድ ነው?
 ተግባር ተኮር የማስተማሪያ ዘዴ የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች መጻፍ
ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ምንድን ነው?
1.4 የጥናቱ አብይ አላማ
የጥናቱ ዋናው አላማ ተግባር ተኮር የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን
የመጻፍ ክሂልን ለማሻሻል ያለውን ሚና መመርመር ሲሆን ይህንንም ለማሳካት ከታች
የተዘረዘሩት ንዑሳን አላማዎች ይኖሩታል፡፡

1.5. የጥናቱ ዝርዝር አላማዎች

 ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ለማሻሻል


ያለው ጥቅም ምን እንደሆነ መፈተሽ፡፡

 ተግባር ተኮር የማስተማሪያ ዘዴ የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ


ተማሪዎች መጻፍ ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ መመርመር፡፡
1.6 የጥናቱ ጠቀሜታ
ይህ ጥናት ተጠንቶ ሲያበቃ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሎ
ይታሰባል፡፡

 የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴን ተጠቅመው


ተማሪዎቻቸውን ቢያስተምሩ የመጻፍ ክሂልን ለማሻሻል ጥቆማ ሊሰጣቸው
ይችላል፡፡

 ከዚህ ጥናት የሚገኘውን ውጤት መሰረት በማድረግ የትምህርት መርጃ መሳሪያ


አዘጋጆች ለመርሃ ትምህርት፣ ለመማሪያ መጸሀፍት አዘጋጆች፣ ለስርአተ ትምህርት
ባለሙያዎች በተግባር ተኮር የማስተማሪያ ዘዴ ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲያዘጋጁ
አመቺ ሁኔታ ሊፈጥርላቸው ይችላል፡፡
የቀጠለ...
 ከዚህ ጥናት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥናቶች ለማጥናት የሚፈልጉ አጥኚዎች ይህ

ጥናት በመነሻ ሀሳብነት ግብአት ሆኖ ሊያገለግላቸው ይችላል፡፡

1.7 የጥናቱ ወሰን


ይህ ጥናት የሚካሄደው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት
በሸካ ዞን በቴፒ ከተማ ከሚገኙ ሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ
በሆነው በቴፒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፡፡ በ2016 ዓ.ም ሰባተኛ ክፍል
ከሚማሩ ተማሪዎች ናሙና በመውሰድ ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ
የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ለማሻሻል ያለው ተጽዕኖን መመርመር ላይ የሚወሰን
ይሆናል፡፡
ምዕራፍ ሦስት፤ የጥናቱ ዘዴ
3.1. የጥናቱ ዲዛይን (ንድፍ)
የዚህ ትልመ ጥናት ዋነኛ አላማ ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴ የተማሪዎች የመጻፍ

ክሂል ላይ ያለውን ተጽእኖ መፈተሽ ሲሆን ይህንንም ከግብ ለማድረስ ጥናቱ መረጃ

መሰብሰብና መተንተንን ስለሚያካትት መጠናዊ የምርምር ሂደትን የሚከተል ነው፡፡

ጥናቱን ለማካሄድ ፍትነታዊ የምርምር ስልትን በመጠቀም በተመረጠው ክፍል እድል ሰጭ

ናሙናን በመከተል ተጠኝዎችን በቀላል እጣ ንሞና ይለያሉ፡፡ አንዱን ክፍል የቁጥጥር ቡድን

ሁለተኛውን ሙከራዊ ቡድን በማለት በእጣ እንዲለዩ


የቀጠለ...
ከተደረገ በኋላ የቁጥጥር ቡድኑ በመምህር መር ማስተማሪያ ዘዴ እንዲሁም ሙከራዊ
ቡድኑ በተግባር ተኮር የማስተማሪያ ዘዴ ትምህርታቸውን ለስድስት ሳምንታት
እንዲከታተሉ በማድረግ በሁለቱ ቡድኖች መካከል የታየውን ለውጥ በማወዳደርና
ያላቸውን የባህሪ መመሳሰል እና መለያየት ለማጥናት አጥኝዋ አቅዳለች፡፡

3.2. የናሙና አወሳሰድ

3.2.1. የትምህርት ቤት ናሙና አመራረጥ


በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በሸካ ዞን ካሉ ሁለት ወረዳዎች የኪ ወረዳ
ቴፒ ከተማ አስተዳደርን እንዲሁም በከተማው ከሚገኙ ሶስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
ቴፒ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በእድል ሰጪ የናሙና ዘዴ ተመርጧል፡፡
3.2.2 የክፍል ደረጃ ናሙና አመራረጥ
• ይህ ትልመ ጥናት ትኩረት ያደረገው በቴፒ ሙሉ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
ሲሆን በ2016 ዓ.ም በትምህርት ቤቱ ከሚማሩት ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል
ካሉ ተማሪዎች ውስጥ የሰባተኛ ክፍል በእድል ሰጪ የናሙና ዘዴ ተመርጧል፡፡

• ተማሪዎቹ በሰባት ክፍሎች የተከፋፈሉ በመሆኑ በቀላል እጣ ንሞና ሁለቱን ክፍል


በመውሰድ የአንዱን ክፍል ተማሪዎች የሙከራ ቡድን እንዲሁም ሁለተኛውን
የቁጥጥር ቡድን በማድረግ ጥናቱን ለመስራት አጥኝዋ አቅዳለች፡፡ (የክፍሎቹ ብዛት
ከትምህርት ቤቱ አስተዳደር የተገኘ ነው፡፡)
3.2.3 የመምህራን ናሙና አመራረጥ
 በትምህርት ቤቱ ሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርትን የሚያስተምሩት ሁለት
ሴት መምህራን ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ በአንድ መምህርት የሚማሩ ሁለት ክፍሎች
በአላማዊ የናሙና አመራረጥ ስልት አጥኝዋ ለመምረጥ አቅዳለች ምክንያቱም
ከመምራን ችሎታ መለያየት አንጻር ልዩነት እንዳይፈጠር በማሰብ ነው፡፡

 ፈተናውን እና የትምህርቱን ይዘት ለመገምገም ደግሞ ሁለት የሁለተኛ ዲግሪ


የአማርኛ ቋንቋ በተማሩ መምህራን በአላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ለመምረጥ
አጥኝዋ አቅዳለች፡፡
3.3 የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ
ለዚህ ጥናት ለመረጃ መሰብሰቢያነት ያገለግላል በማለት የታቀደው ፈተና ነው፡፡

3.3.1. ፈተና
ለጥናቱ ዋነኛ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሆኖ የሚያገለግለው ፈተና ነው፡፡
ፈተናውም ለሁለት ጊዜ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህም የቅድመ ፈተና እና የድህረ ፈተና ሲሆን
ቅድመ ፈተናው የሙከራ ትምህርቱ ከመከናወኑ በፊት ለሁለቱም ቡድኖች ማለትም
የሙከራ ቡድን እና የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች ተመጣጣኝ የመጻፍ ክሂል አላቸው
ወይም የላቸውም የሚለውን ለመለየት ነው፡፡
የቀጠለ…
 ሁለተኛ የሚሰጠው ፈተና ድህረ ፈተና ሲሆን ተጠኝ ተማሪዎች በታቀደላቸው
ክፍለ ጊዜ መጨረሻ ላይ የሚሰጣቸው ሲሆን ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ
ዘዴ በሙከራ ቡድን ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ላይ ያሳደረውን ተጽእኖ
ለመገምገም ነው፡፡

 ቅድመና ድህረ ፈተናዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ሆነው ተመሳሳይ የአጠያየቅ ስልትን


የተከተሉ እንዲሆኑና በመማሪያ መጽሃፋቸው ከተማሩት የመጻፍ ክሂል ይዘቶችን
ተከትሎ በአጥኝዋ ተዘጋጅቶ በክፍሉ መምህራን እንዲፈተኑ ይደረጋል፡፡ የቅድመ
እና ድህረ ፈተና የአስተማማኝነት ደረጃውን ለመለካት በspss ለመፈተሽ አጥኝዋ
አቅዳለች፡፡
3.4 የመረጃ አተናተን
 የዚህ ጥናት መረጃዎች የሚሰበሰቡት በፈተና ሲሆን በሙከራና በቁጥጥር ቡድኑ

ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እያንዳንዳቸው በቅድመ ትምህርት እና ድህረ ትምህርት

ባስመዘገቧቸው ውጤቶች የሚሰበሰቡ የፈተና መረጃዎችን በሁለቱ ቡድኖች

አማካይ ውጤቶች ነው፡፡ መደበኛ ልይይት እንዲሁም በነጻ ናሙና ቲ ቴስት

ተተንትኖ ይቀርባል፡፡

 የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ በመደበኛ ክፍለ ጊዜያቸው የሚማሩ ሲሆን ሁለቱም

ክፍል በአንድ መምህር ለስድስት ሳምንት እንዲማሩ ይደረጋል፡፡


የቀጠለ...
 የቁጥጥር ቡድኑ በመማሪያ መጸሀፉ ላይ ያለውን መደበኛውን
ትምህርት የሚማሩ ሲሆን የሙከራ ቡድኑ ደግሞ የመማሪያ

መጸሀፉን በማገናዘብ ለተግባር ተኮር ማስተማሪያ ዘዴ የሚሆኑ

ተግባራትን በማዘጋጀት የሙከራ ጥናቱን ሂደት ተግባር ላይ ለማዋል

በአጥኝዋ ይዘጋጃል፡፡

 ሁለተኛ ዲግሪ በተማሩ በተመረጡ መምህራን የሚገመገም

ይሆናል፡፡
አመሰግናለሁ

You might also like