You are on page 1of 78

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

ሂዩማኒቲስ ፋካሊቲ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች)ና ስነጽሁፍ አማርኛ ትምህርት ክፍል

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር


የአንብቦ መረዳት ችሎታን የማጎልበት ሚና፤በደጋ ዳሞት ወረዳ ፈረስቤት
አጠቃላይ 2 ኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ ትምህርትቤት በዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎች ተተኳሪነት

በዘበናይ ደምሴ

ነሃሴ፣ 2011 ዓ.ም


ባህርዳር

በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የአንብቦ መረዳት


ችሎታን የማጎልበት ሚና፤ በደጋዳሞት ወረዳ ፈረስቤትአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ
ትምህርት መሠናዶ ትምህርትቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

~0~
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

ሂዩማኒቲስ ፋካሊቲ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች)ና ስነጽሁፍ አማርኛ ትምህርት ክፍል

ድህረ ምረቃ መርሃ-ግብር

ለአማርኛ ማስተማር ማስተርስ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ

በዘበናይ ደምሴ

አማካሪ
ዶ/ር ማረው ዓለሙ

ነሐሴ፣ 2011 ዓ.ም

ባህርዳር

~1~
ምስጋና
በቅድሚያ ይህ ጥናት ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ምንም መሰልቸት በቅንነት
ድጋፋቸው ሳይለየኝ ከዚህ ደረጃ እንድደርስ ለረዱኝ አማካሪዬ ማረው አለሙ (ዶ/ር) ከልብ የመነጨ ከፍተኛ
ምስጋና አቀርባለሁ፡፡

በመቀጠልም በመረጃ መሰብሰብ ሂደት ያለምንም መሰላቸት ቅንነት በተላበሰ ሁኔታ ለረዱኝ፣መረጃ በመስጠት
ለተባበሩኝና ለደገፉኝ በፈረስ ቤት አጠቃላይ ሁለተኛና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርትቤት በመማር
ላይ ያሉ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችና ፈተና በመፈተንና አስተያየት በመስጠት ለተባበሩኝ የትምህርትቤቱ
የቋንቋ መምህራን ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ፡፡

እንዲሁም ገንቢ አስተያየት በመስጠትና ጽሁፌን በኮንፒውተር በጥራት በማተም በተፈለገው ጊዜ


ላደረሱልኝና ትክክለኛ ቅርጽ በማስያዝ ሁልጊዜ ያለመታከት ድጋፍና እገዛ ላደረጉልኝ ለወንድሜ ለአቶ ድልነሳ
ደምሴና ለባለቤቴ ለአቶ ደመላሽ አንዷለም በእግዚያብሄር ስም ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ፡፡

በመጨረሻም ትምህርቴን በንቃት እንድከታተል ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ከጎኔ ሁና ቤተሰቤን በመደገፍና


በመንከባከብ ላገዘችኝ እህቴ ለወ/ሮ አቻምየለሽ ተድላ ልባዊ ምስጋናየ የላቀ ነው፡፡

~i~
የይዘት ማዉጫ
ይዘት ገጽ
ምስጋና..................................................................................................................................................i
የይዘት ማዉጫ......................................................................................................................................ii
አህጽሮተጥናት.......................................................................................................................................iv
ምዕራፍ አንድ፤ መግቢያ..............................................................................................................................1
1.1 የጥናቱ ዳራ...................................................................................................................................1
1.2 የጥናቱ መነሻ ችግር..........................................................................................................................4
1.3 የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄ....................................................................................................................7
1.4. የጥናቱ አላማ...............................................................................................................................7
1.5. የጥናቱ አስፈላጊነት.........................................................................................................................8
1.6. የጥናቱ ወሰን................................................................................................................................8
1.7 የጥናቱ ውስንነት.............................................................................................................................9
1.8 ቁልፍ ቃላት ብያኔ...........................................................................................................................9
ምዕራፍ ሁለት፤ የተዛማጅ ድርሳናት ክለሳ........................................................................................................10
2.1. የገፀባህርይተኮር ዘዴ የንድፈ ሃሳብ ቅኝት.......................................................................................10
2.2. በገጸባህርይተኮር ዘዴ የማንበብ ክሒልን የማስተማር ጠቀሜታ.................................................................12
2.3. በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ የማንበብ ክሂልን የማስተማር አቀራረብ................................................14
2.4. በገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ የተደረጉ ተዛማጅ ጥናቶች ክለሳ.............................................................17
ምዕራፍ ሦስት፤ የአጠናን ዘዴ......................................................................................................................20
3.1 የአጠናን ስልት.............................................................................................................................20
3.2 የጥናቱ ተሳታፊዎች...................................................................................................................20
3.3 የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ.............................................................................................................21
3.4 የማስተማሪያ ቴክስት ዝግጅት......................................................................................................22
3.5 የአጠናን ሒደት.........................................................................................................................24
3.6 የመረጃ አተናተን ዘዴ..................................................................................................................25
ምዕራፍ አራት:- የጥናቱ ውጤት ትንተናና ማብራሪያ..................................................................................26
4.1 የውጤት ትንተና...........................................................................................................................26
4.2 የውጤት ማብራሪያ.......................................................................................................................30
ምዕራፍ አምስት፡- ማጠቃለያ፣መደምደሚያና መፍትሄ................................................................................32
5.1 ማጠቃለያ..................................................................................................................................32

~ ii ~
5.2 መደምደሚያ...............................................................................................................................33
5.3 መፍትሔ...................................................................................................................................33
ዋቢዎች..............................................................................................................................................35
አባሪዎች.............................................................................................................................................39
አባሪ ሀ. የቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና..........................................................................................39
አባሪ ለ. የድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና...........................................................................................45
አባሪ ሐ. በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ ለማስተማር የቀረቡ ቴክስቶች.........................................................52
አባሪ መ. ልዩ ልዩ ሰንጠረዦች.................................................................................................................80

~ iii ~
አህጽሮተጥናት
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን
ለማጎልበት ያለውን አስተዋጾ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ሙከራዊ ምርምር ስልትን ተከትሎ የተሰራና
በአይነቱ ደግሞ መጠናዊ ምርምር ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋዳሞት
ወረዳ በፈረስቤት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርትቤት በ 2011 ዓመተ
ምህረት ትምህርታቸውን በ 39 ክፍሎች ተመድበው በመከታተል ላይ ከሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች
መካከል በእድል ሰጭ ናሙና የተወሰኑት የዘጠነኛ ምድብ 2 ክፍል ተማሪዎች የሙከራ እና የዘጠነኛ ምድብ 28
ክፍል ተማሪዎች የቁጥጥር ቡድን በመሆን ነው፡፡ የተጠኝ ቡድን ተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ዳራ
ለማወቅ በቅድሚያ ቅድመ ትምህርት ፈተና ተሰጥቷል፡፡ የተገኘው ውጤትም ተመጣጣኝ የአንብቦ መረዳት
ችሎታ እንዳላቸው ያመለክታል፡፡ በመቀጠልም የጥናቱ ተሳታፊዎች የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ
በተዘጋጀው ቴክስት በተቃራኒ ፈረቃቸው በሳምንት ሁለት ቀን ለአራት ሳምንት ያህል እንዲማሩ ተደርጓል፡፡
ለጥናቱ የተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና ነው፡፡ በሂደቱም ቅድመትምህርት ፈተናና
ድህረትምህርት ፈተና ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በዚህም መሰረት በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት የተገኙት
የፈተና ውጤቶች በገላጭ ስታትስቲክስ በአማካይ፣ መደበኛ ልይይት፤ በነጻ ናሙና ቲ-ቴስትና በዳግም ልኬት
ቲ-ቴስት ቀመር ተሰልቷል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረት የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና
አማካይ ውጤት በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት በስታትስቲክስ (p=.001) በመሆን ጉልህ ልዩነት (p < 0.05) ታይቷል፡፡
ይህም በስነጽሁፍ ቴክስት፤ ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን እንደሚያጎለብት
አመላክቷል፡፡ እንዲሁም በሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል
በዳግም ልኬት ቲ-ቴስት በስታትስቲክስ ጉልህ ልዩነት (p < 0.05) ታይቷል፡፡ በዚህም በስነጽሁፍ ቴክስት
ገጸባህርይ ተኮር የማስተማር ዘዴ ለውጥ እንዳመጣ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ የጥናቱ ውጤትና ማብራሪያ
እንደሚያሳየው በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ
ለማጎልበት ጉልህ ሚና አለው፡፡ ይህም በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር
የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት አዎንታዊ ሚና አለውየሚልነው፡፡

~ iv ~
ምዕራፍ አንድ፤ መግቢያ
1.1 የጥናቱ ዳራ

ስነጽሁፍ ቋንቋን ለማስተማር ከፍተኛ ሚና ቢኖረውም በዓለም የቋንቋ ትምህርት ታሪክ ስነጽሑፍን
መጠቀም የተጀመረውና በሰፊው እየታወቀ የመጣው እ.አ.አ ከ 1950 ዎቹ ወዲህ ነው (ብራምፊት፣
1986)፡፡ ይሁንእንጅ ካርተርና ሎንግ (1991) እንደሚያስረዱትም በቋንቋና ስነጽሑፍ መካከል ያለው
ግንኙነት በውል እየታወቀ የመጣው እ.አ.አ ከ 1980 ዎቹ በኋላ ነው፡፡

መምህራን ስነጽሑፍን በቋንቋ ትምህርት ውስጥ ለማካተት በርካታ ምክንያቶች አሏቸው፡፡ ሳግ (1975)፣
ብራምፊትና ካርተር (1986) ስነጽሑፍ ተማሪዎች በቀጥታ በተግባር የሚማሩበት እንደሆነ በጥናት
መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡ ካርተርና ሎንግ (1991) እንደገለጹት መምህራን ስነጽሁፍን ለቋንቋ ማስተማሪያነት
የሚጠቀሙበት ምክንያት ሶስቱን ሞዴሎች ለማሳየት አመች ስለሆነ ነው ፡፡ እነሱም የመጀመሪያው ባህል
ተኮር ሞዴል ሲሆን ስለሞዴሉ ስኮት (1964) ሲገልጹ ስነጽሁፍ ባህላዊ አመለካከት እንዲኖር ከሚያደርጉ
መንገዶች ውስጥ ዋነኛው ነው ፡፡ ስኮት ጨምረውም የማህበረሰቡን ባህል ለማወቅ ስነጽሁፍ በጣም
ጠቃሚ መሆኑን አጠንክረው ሲገልጹ ስነጽሁፍ የታሪካዊና ማህበራዊ ዳራ ምንጭ ስለሆነና እደጥበብን
ለማቅረብ እንደወካይ ተደርጎ ስለሚወሰድ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደላዛር (1993) አገላለጽ የስነጽሑፍ
ይዘቶች ተማሪዎች ከታላሚው ባህል ጋር የበለጠ ትስስር እንዲኖራቸው ያስችላሉ፡፡

ሁለተኛው ቋንቋ ተኮር ሞዴል ነው፡፡ አገልግሎቱም ተማሪዎች በስነጽሁፍ ውስጥ ያሉ ገጸባህርያትን የቋንቋ
አጠቃቀም ተረድተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው፡፡ ስነጽሁፋዊ ስራዎች አንድን የተወሰነ ስነልሳናዊ ይዘት
ወይም ስነምዕላድ ለማወቅ ያስችላሉ፡፡ የቋንቋ ሞዴሉ ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥ ቃላትን ለማስፋት፣
የማንበብ ችሎታን ለማሻሻል፣ የጽሁፍን ሀሳብና አገባባዊ ፍቺን ለመረዳት ክህሎትን ለመጨመር ብሎም
ለተለያዩ ቋንቋነክ ትምህርቶች ተጋልጦ እንዲኖር ለማድረግ ያስችላል፡፡

ሶስተኛው ሰብዕና ግንባታ ሞዴል ሲሆን ሰብዕና ግንባታ ሞዴል በስነጽሁፍ ትምህርት ውስጥ የበለጠ
ተማሪተኮር አቀራረብ እንዲኖር ያስችላል፡፡ ዋና ትኩረቱም ስነጽሁፍን እንደመነሻ በመጠቀም ለመማር፣
ባህልን ለማወቅ፣ ተማሪዎችን ለመከታተልና ለመመዘን እንዲሁም ስነጽሁፍ ውስጥ ስለሚገኙ ይዘቶች
ለመወያየት ነው፡፡

በቋንቋ ትምህርት ሂደት ስነጽሑፍን እንደማስተማሪያ መሳሪያ መጠቀም የሚያስፈልግበት ዋናው


ምክንያት በተመረጡ የፈጠራ ስራዎች አማካይነት የተለያዩ የቋንቋ ክህሎቶችን በማስተማር
የተማሪዎችን በክሂሎች የመጠቀም ብቃት ከፍ ለማድረግ ነው፡፡ ስነጽሑፍ የቋንቋ አጠቃቀም

~1~
እውቀትን ያዳብራል፡፡ በትምህርት ሂደትም የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ይቀሰቅሳል፡፡ በሚመረጡ
ጽሑፎች ውስጥ ከሚገኙ ጭብጦች፣ ገፀባህርያት፣ መቼትና ሴራ በመነሳት የቋንቋ ክሂልንና
ሰዋሰውን ለማስተማር ስነጽሁፍ ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡ በአጠቃላይ ስነጽሁፍን በቋንቋ ትምህርት
ውስጥ ማካተት ለተማሪዎች ጠቅላላ እውቀት፣ አእምሯዊ ብስለት፣ ማህበራዊና ስነምግባራዊ
እድገት ያለው አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው (ሂል፣1986) ፡፡

ላዛር (1993)፣ በድሉ (1996) እና ፈቃደ (1991) በስነፅሁፋዊ ስራዎች ቋንቋን ማስተማር የቋንቋ
ክሂሎችን ለማዳበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው በአፅንኦት ገልፀዋል፡፡

በተማሪዎች መካከል የሚደረግ ስነጽሑፋዊ ውይይት ተማሪዎችን ስለሚስብ


የተሳታፊነታቸውን ደረጃ ከፍ ያደርጋል፤ ተማሪዎች ድራማዎችን ሲሰሩ፣ ግጥሞችንና
አጫጭር ታሪኮችን ሲያነቡ የመናገርና የማንበብ ክሂላቸው ይዳብራል፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ
ስነፅሁፍ በባህርይው ሳቢ ስለሆነ ተማሪዎች በስነፅሁፍ ስራ ላይ ተመስርተው ክሂሎችን
ለማዳበር በሚከናወኑ ልምምዶች ላይ ለመሳተፍ በአብዛኛው ውጫዊ ግፊት አይፈልጉም፤
ስለስነፅሁፍ መናገር ይፈልጋሉ፤ስነፅሁፍ መፃፍ ይፈልጋሉ፤ስነፅሁፍ ማዳመጥ ይፈልጋሉ
(በድሉ፣1996 ፡ 7)፡፡

ሂል (1986) ስነጽሁፋዊ ስራዎችን ለቋንቋ ትምህርት ማስተማሪያነት መጠቀም ያለውን


ስነትምህርታዊ ፋይዳ ሲያስረዱ፤ ስነጽሑፍ አውድ ከሳች መሆኑን፣ ተግባቦት አጎልባች መሆኑንና
ተነሳሽነት ፈጣሪ መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡

እንደላዘር (1993) አገላለጽም ሥነፅሁፋዊ የፈጠራ ስራዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ስሜቶች መገለጫ
በመሆናቸው፣ አንባቢን ወይም አድማጭን ግላዊ መልስ እንዲሰጥ የሚያነሳሱ የቋንቋ አጠቃቀም
ስልት ያላቸው በመሆናቸው፣ የዓለምን አስደናቂ ስሜት፣ አስፈሪነት፣ ራዕይ፣ ገፅታን በቃላት
የሚቀርፁ በመሆናቸውና በርካታ ሰዎችን በአንድ ላይ በማገናኘት አስተያየታቸውን፣ ሀሳባቸውን፣
ግንዛቤያቸውን ለመረዳት የሚያስችሉ መሳሪያዎች በመሆናቸው የቋንቋ ትምህርቱን ማራኪና
ተወዳጅ የማድረግ አቅም አላቸው፡፡

ስነፅሁፍን ለቋንቋ ማስተማሪያነት በክፍል ውስጥ ስንጠቀም የቋንቋ ትምህርቱን ለመረዳት ቀላልና
አዕምሮን የሚቀርፅ ከማድረጉም በላይ የቋንቋ ክሂሎችን እርስ በእርስ ለማቀናጀት ይረዳል፡፡ የቃላት
እውቀት ማግኘትንም ያፋጥናል፡፡ እንዲሁም ራስን ለማረም፣የንባብና የፅህፈት ልምምድ ለማድረግ
ዕድል ይሰጣል ፡፡

ስነፅሁፍ የስነልሳናዊ እውቀትን ጥቅምና አጠቃቀምን ያብራራል ተማሪዎች ከስነፅሁፋዊ ስራዎች


ጋር የሚኖራቸውን መስተጋብርም ያሳድጋል፡፡ ስሜታቸውን ይቀሰቅሳል፣ በመጨረሻም የማንበብ
ችሎታቸውን ይጨምራል (ማኬይ፣1986)፡፡

~2~
ፓርኪንስን እና ሬይድቶማስ (2000) ስለስነጽሁፍ አስፈላጊነት ሲያብራሩ ፋይዳውን ከባህል
ማበልጸጊያነቱ፣ ከአንጻራዊ ታማኒነቱ፣ ተጨባጭነቱ፣ ከቋንቋ ናሙናነቱ፣ ከተግባራዊ አስተዋሽነቱ፣ ከቋንቋ
ለመዳ ፍላጎት አነሳሽነቱና መልመጃዎችን ለማዘጋጀት ካለው አመችነት አንጻር ዘርዝረው የቋንቋ ለመዳ
ካለስነጽሑፍ ምልዑ እንደማይሆን ገልጸዋል፡፡

ስነጽሁፍ የተማሪዎችን የስነጽሁፍ ችሎታና በራስ መተማመን የሚያጎለብት ነው (አልከድር፣


2005)፡፡ ስነጽሁፍ ከሌሎች የትምህርት አይነቶች የሚለየው ለግላዊ ተሳትፎ እድል ከመስጠቱ
የተነሳ የውስጥ ተነሳሽነትን የሚፈጥር እንጅ በውጭ ምክንያቶች ላይ የማይመሰረት በመሆኑ ነው፡፡

ኮሊና ስላተር (1990) በስነጽሑፍ ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን ቀልብና ስሜት እየሳበ የተራክቦን ደረጃ
ከፍ እንደሚያደርግ ያስረዳሉ፡፡ ቱርከር (1991) ደግሞ የቋንቋን ትምህርት በድግግሞሽ፤ ከተማሪው የዕለት
ተእለት ኑሮጋር ባልተዛመዱና ሽምደዳን በሚጋብዙ የማስተማሪያ ዘዴዎች ማቅረብ የተማሪዎችን
የፈጠራ ችሎታ የሚጎዳና ቋንቋውን በሚገባ እንዳይለምዱት እንቅፋት እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡

ከቀረበው ማብራሪያ መረዳት የሚቻለው ስነፅሁፋዊ ስራዎቹን ለቋንቋ ትምህርት ማስተማሪያነት


የመጠቀም መሠረታዊ ዓላማ የተማሪዎችን አጠቃላይ የቋንቋ ችሎታና ልዩ ልዩ የክሂል
ዘርፎቻቸውን ለማዳበር ነው፡፡ በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር በተማሪዎቹ የመማር
ሒደት ላይ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡

በሚዛናዊነት ባህላዊና ዘመናዊውን አቀራረብ አጣጥመው ቱርከር (1991) ባቀረቡት ጥናት አማራጭ
የለመዳ ስልቶችን አዝናኝና ቅደም ተከተላዊ ደረጃዎችን እንደሚከተለው ያቀርባሉ፡፡ የመግቢያ ጽንሰሐሳብ
የያዘ የጨዋታ ምንባብ፣ የፈጠራ አጻጻፍ፣ ተግባር ተኮር መልመጃ፣ የተዘጋጁትን ጨዋታዎችና ስነጽሑፋዊ
ጽሑፎችን ባነበቡ ቁጥር ምእናባዊ ምስል በአእምሯቸው በመሳል ስለገጸባህሪያቱ ግንዛቤ መውሰድ
ይጀምራሉ፡፡ በዚህም የተሳታፊነት ፍላጎታቸው እየጨመረ ይሔዳል፡፡ ይህ ልምምድ በስነጽሑፍ
የሚያገኟቸውን ገጸባህርያት ጸባይ በመረዳት ቋንቋውን በተሻለ ሁኔታ ለምደው እንዲግባቡ ያስችላቸዋል፡፡
በተለይም ከጥቂት አስርተ ዓመታት ወዲህ ገጸባህርያትን በማስተዋወቅ ለክፍል ውስጥ የቋንቋ ትምህርት
ስነጽሑፍ ለማስተማሪያነት በሚሰጡት አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ ስለመጠቀም የሚሰጡት አማራጮች
እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ሂል (1986)፣ ቱርከር (1991) ስነጽሑፋዊ ገለጻዎች ተማሪዎቹ የገጸባህርያትን
ጸባዮች እንዲለዩና በአንዳንድ ዝርዝር ባህሪያቸው እንዲሳቡ ስለሚያደርግ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያግዛል፡፡
ከዚህም የሚጠየቁ ጥያቄዎች የፈጠራ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩና የጽሑፉን ይዘትና ሚስጥር እንዲረዱ
ያደርጋሉ፡፡

ተማሪዎች ልቦለዶችን አንብበው የገጸባህርይውን ሁለንተናዊ ማንነት በሚመለከት ያገኙትን የተለያየ


መረጃ እያቀናጁ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን ማዳበር ይችላሉ፡፡ መምህራን ልቦለዶችን በመጠቀም

~3~
የተለያዩ ቋንቋ ነክ መልመጃዎችን ማዘጋጀት ይችላሉ፡፡ ከእነዚህም ገጸባህርያቱን መረዳት አንዱ መንገድ
ሲሆን የገጸባህርይውን አለባበስ፣ አነጋገር፣ አስተሳሰብ የሚገልጹ ዝርዝሮችን እንዲያዘጋጁ በማድረግ
የሚከናወን ነው (ሂል፣1986)፡፡

1.2 የጥናቱ መነሻ ችግር


የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማና ብቁ እንዲሆኑ ከሚያስፈልጓቸው
ክሂሎች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በመሆኑም ከሌሎች ክሂሎች ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል (ሃይላንድ፣ 1990)፡፡

የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተማሪዎች ለየክፍል ደረጃው የሚዘጋጁትን ምንባቦች ያለምንም


ችግር አንብበው ሐሳቡን መረዳት፣ መተርጎምና ማብራራት መቻልን አጠቃሎ የያዘ ችሎታ
ነው (በድሉ፣1988)፡፡

ማንበብ የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ ለማዳበር ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ በመሆኑም የተማሪዎችን


የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማዳበር ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች ለትምህርቱ አጋዥ
ከሆኑ ከተለያዩ መጣጥፎች ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ በኩል ማንበብ ትልቅ ሚና ስላለው ነው፡፡ ሀይላንድ
(1990)፣ግርሀም (1887) እና ፑርህማዲ (2012) እንደሚያስረዱት የማንበብ ክሒል ከሌሎች ችሎታዎች
ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡ በእርግጥ በትምህርት አለም የሚኖሩ ሰዎች በየጊዜው ከሚነበቡ ነገሮች ጋር
ይገናኛሉ፡፡ ይሁን እንጅ የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለመመዘን መረጃ ሊገኝባቸው ከሚችሉ
የተለያዩ ፅሁፎች ሀሳብ የሚወሰድበት መንገድ የሚፈለገውን እውቀት ለመገብየት ያስችላቸዋል ብሎ
ለመናገር ያዳግታል፡፡

በተለይ በአሁኑ ወቅት ተማሪዎች በእጃቸው በሚገኙ ስልኮች ‹‹የፌስቡክ›› ተንቀሳቃሽና


የማይንቀሳቀሱ ምስሎችን፤ የቴሌቪዥን ፊልሞችና ፕሮግራሞችን ረጅም ጊዜ ሰጥተው
ስለሚመለከቱ ምንባብ አንብበው ሊተላለፍ የተፈለገውን ጭብጥ የመረዳት ፍላጎታቸው
እየቀነሰ መጥቷል (ፓለኒ፣ 2012) ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ዝቅተኛ ሊሆን የቻለበት ምክንያት
በክፍል ውስጥ የተማሪዎችን የማንበብ ችሎታ ማሻሻልን ማዕከል ያደረገ ትምህርት ዕጦት
መኖር ነው ሲሉ ሉሚኪዮንጋ (2012) ማዳሪጋ አረቢያ እና ኢስቲባሊዝ (2010)ን ዋቢ
በማድረግ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሉሚኪዮንጋ (2012) የተጠቀሱት ዲቻንት(1991) ሲገልጹ
በትምህርት ቤት ውስጥ የማንበብ ዋናው ጠቀሜታ ተማሪዎቹ ቃላቱን ማንበብ እንዲማሩ

~4~
እንጅ የቃላቱን ትርጓሜ እንዲረዱ አይደለም፡፡ ስለዚህ ተማሪዎቹ ቃላትን ብቻ እንዲጠሩ
የሚደረጉ ከሆነ የጠሯቸውን ቃላት ፍቺ ሲጠየቁ መመለስ አይችሉም፡፡ ይህ ደግሞ
የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ወደ ፊት እንዳይራመድ ያደርገዋል፡፡

በአብዛኛው ተማሪዎች ከማንበብ ጋር ሳይተዋወቁ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ሳይኖራቸው


ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡ ስለሆነም የአብዛኞቹ ተማሪዎች
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጥሩ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ስለሌላቸው
የሚያነቡትን ምንባብ በሰፊው እንዳይመለከቱ አድርጓቸዋል፡፡ በተጨማሪም በትምህርት
ውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አሳድሯል (ኮንሌይ፣ 1992)፡፡

በተመሳሳይ አትኪንስና ሌሎች (1996) በርካታ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የዳበረ
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ስለሌላቸው የሚያነቡትን ምንባብ በሰፊው እንዳይመለከቱና
በትምህርት ውጤታቸው ላይም አሉታዊ ተጽእኖ እንዳሳደረ ያስገነዝባሉ፡፡

ቢንትዝ (1997) በአንብቦ መረዳት ዙሪያ ከ 100 በላይ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ የሚያስተምሩ
መምህራንን ጠይቀው በሰበሰቡት መረጃ መሰረትም ሁሉም መምህራን የተማሪዎቻቸው
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያልዳበረ መሆኑን በጥናታቸው አመላክተዋል፡፡

ስነጽሑፍ በቋንቋ ትምህርት ውስጥ የሚያበረክተውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አስመልክቶ በርካታ ምሁራን
አስተያየቶችን ቢሰነዝሩም አሁን ባለው የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ውስጥ ስነጽሁፍ ይህ
ነው ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ድርሻ የለውም፡፡ ከ 1966 ዓ/ም በኋላ ሀገሪቱ የተከተለችው ፍልስፍና ነጸብራቅ የነበረው
ስርዓተ ትምህርት የቋንቋ ማስተማሪያ መጽሐፍት ከየትምህርት አይነቱ የተውጣጡ ደረቅ እውነታዎችን የያዙ
ምንባቦች የታጨቁባቸው መድብሎች አድርጓቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታ ለቋንቋ ትምህርት እውነተኛ አውድ ከማሳጣቱም
በላይ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና ፍላጎት በእጅጉ ጎድቶታል (በድሉ፣1996)፡፡

በርካታ የሐገር ውስጥ ጥናቶችም የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያልዳበረ መሆኑን
ጠቁመዋል፡፡ ለምሳሌ ተሾመ (1997) በከንባታ ጠንባሮ ዞን የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ የ 10 ኛ
ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ
ጠቁመዋል፡፡ የተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ዝቅተኛ የመሆን ምክንያትም የአንብቦ
መረዳት ትምህርት አሰጣጥ ችግር መሆኑን ከጥናቱ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም
መሰረት (2007) በአንካሻ ወረዳ በሚገኙ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ 9 ኛ ክፍል
~5~
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማንበብ ክሒል ትምህርት አቀራረብ ቅኝት በሚለው
ጥናታቸው የደረሱበት ድምዳሜ መምህራን ለማንበብ ክሒል የሚሰጡት ትኩረት ዝቅተኛ
እንደሆነ፤ የማንበብ ክሒልን በመተግበር ሂደት ተጽእኖ አድራጊ ጉዳዮች እንዳሉ
አመላክተዋል፡፡ እንዲሁም ታፈረ (2000) በዳንግላ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የማንበብ ዳራና አንብቦ የመረዳት ችሎታ በሚለው ጥናታቸው
የተማሪዎች የማንበብ ክሒል በዝቅተኛ ደረጃ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ እነዚህ ጥናቶች ችግሩ
መኖሩን አረጋገጡ እንጅ ለችግሩ መፍትሄ አላስቀመጡም በመሆኑም መፍትሄ ለመፈለግ
ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ጥናቱ ተከናውኗል፡፡

ደበበ (1999) በበኩላቸው ማንበብ አእምሮን ለማስፋት እውቀትን ለማዳበር ብሎም ብቁ


ዜጋ ለመሆን ስለሚረዳ ማንበብን መለማመዱ አስፈላጊ ነው በማለት ይመክራሉ፡፡ ይህ
ምክር ለተማሪዎቻችን እጅግ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ የማንበብ ተግባራትን ተግተው
መለማመድ እንዳለባቸው እንዲገነዘቡና አስፈላጊውን እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለባቸው
በስልጠና ማገዙ ተገቢ እንደሆነም አክለው ይመክራሉ፡፡

ይህ ጥናት በፈረስቤት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ


ትምህርትቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤
በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የአንብቦ መረዳት ችሎታን የማጎልበት ሚና
የፈተሸ ነው፡፡ አጥኚዋ በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ለማጥናት የተነሳችበት ምክንያት ከምሁራን
ሐሳብ በተጨማሪ በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ተማሪዎችን የማንበብ ክሒል በተደጋጋሚ
ስታስተምር ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን በሚሰሩበት ጊዜ ችግር ሲገጥማቸው
አስተውላለች፡፡ ችግሩም አንድን ምንባብ ካነበቡ በኋላ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን
አለመመለስ፣ ከምንባቡ ለወጡ የቃል ጥያቄዎች ምላሽ አለመስጠት፣ ለሚሰጧቸው
መልሶች ምክንያታዊ አለመሆን፣ የነገሮችን አንድነትና ልዩነት አለመለየት፣ ከምንባቡ
የወጡና የተፋለሱ ዓ/ነገሮችን አለማደራጀት፣ የምንባቡን ዋና ሐሳብ አለመለየት፣ ምንባቡ
ውስጥ ስላሉ አንዳንድ ሐሳቦች ማብራሪያ አለመስጠት፣ ምንባቡን አለመጨረስና አስቀድሞ
የምንባቡን የገጽ ብዛት መቁጠር ይጠቀሳሉ፡፡ ስለዚህ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍ

~6~
ቴክስት ገጸባህርይተኮር በማስተማር ተማሪዎች የሚኖራቸውን የአንብቦ መረዳት ችሎታ
ለመፈተሽ ጥናት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

1.3 የጥናቱ መሰረታዊ ጥያቄ


ይህ ጥናት በዋናነት የሚከተለውን መሰረታዊ ጥያቄ ይመልሳል፡፡
 በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር
የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያጎለብታል?

1.4. የጥናቱ አላማ


የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደጋ ዳሞት ወረዳ በፈረስ ቤት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት
መሰናዶ ትምህርትቤት በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍ
ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የአንብቦ መረዳት ችሎታን በማጎልበት ረገድ የሚኖረውን ሚና መፈተሽ
ነው፡፡

1.5. የጥናቱ አስፈላጊነት

የዚህ ጥናት ውጤት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ሊኖሩት ይችላል፡፡


 መምህራን በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍቴክስት ገጸባህርይተኮር በማስተማር ማንበብን
እንዲያለማምዱ ግንዛቤ ይፈጥራል፡፡
 መማሪያ መጽሐፍት አዘጋጆች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር
ማስተማር ማንበብን ማለማመድ የሚያስችሉ ተግባራትን እንዲያካትቱ ያግዛል፡፡
 ወደፊት ለሚደረጉ ጥናቶች እንደመነሻ በመሆን ያገለግላል፡፡

1.6. የጥናቱ ወሰን


ይህ ጥናት የተካሄደው በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋዳሞት ወረዳ ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች ውስጥ በፈረስቤት አጠቃላይ 2 ኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርትቤት ነው፡፡ በጥናቱ
ተሳታፊ የሆኑት ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ በ 2011 ዓመተ ምህረት በመማር ላይ ከሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎች ውስጥ በእድል ሰጭ ናሙና የዘጠነኛ ምድብ 2 ክፍል ተማሪዎችን የሙከራ ና የዘጠነኛ ምድብ 28
ክፍል ተማሪዎችን የቁጥጥር አድርጎ በመውሰድ ነው፡፡ ጥናቱ በዚህ ትምህርት ቤት ሊዎሰን የቻለበት ምክንያት
አጥኝዋ የምትሰራበት ትምህርት ቤት በመሆኑና ጥናቱን ለማካሄድ አመች በመሆኑ ነው፡፡

~7~
ጥናቱ በዋናነት የሚያተኩረው በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ ነው፡፡ በመሆኑም
ተማሪዎች ከልብወለዱ በተወሰደው ምንባብ ውስጥ ስለተካተቱ ገጸባህርያት ሙሉ እይታ እንዲኖራቸው
በገጸባህርይው በጥበቡና በታሪኩ መዋቅር መካከል ያለውን ዝምድና መተንተንና የገጸባህርያትን መልክ፣ተክለ
ሰውነት፣ባህርይና አመለካከት መለየት ናቸው፡፡ ኪታብ (2013)፣ዳውዴና ክሊፓን(2010) እንደሚገልጹት
በገጸባህሪያት ተኮር ማስተማር ተማሪዎች ገጸባህሪት ምን አሰቡ? ምን ተሰማቸው? ምንስ ሰሩ? አንድን ነገር
ለምን በዚህ መንገድ ሰሩ? የሚሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ ምንባቡን በጥልቀት እንዲመረምሩና አስተያት
በመጻፍ፣ በመናገርና በድራማ መልክ እንዲገልጹ የሚደረግ ሂደት ነው፡፡ ይህም የምንባቡን መልክት ለመረዳት
ከፍተኛ አስተዋጾ አለው፡፡

በጥናቱ ውስጥ የተካተቱት ተላውጦዎች ገጸባህርይ ተኮር የማስተማር ዘዴ በነጻ ተላውጦነት አንብቦ የመረዳት
ችሎታ ደግሞ በጥገኛ ተላውጦነት ተመድበዋል፡፡

1.7 የጥናቱ ውስንነት


ጥናቱ ሙከራዊ በመሆኑ በአንድ ነጻተላውጦና በአንድ ጥገኛተላውጦ ላይ ብቻ ትኩረት በማድረጉ ሌሎች ተጽኖ
አምጭ ነገሮችን አከቶ ባለማየቱ፤ የአንብቦ መረዳት ችሎታ መለኪያ ፈተናው ሁሉንም የፈተና አይነቶች
ባለማካተቱና በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ የተጠኑ ቀደምት ጥናቶች ባለመገኘታቸው ጥናቱ ውስንነት ይታይበታል፡፡

1.8 ቁልፍ ቃላት ብያኔ


አንብቦ የመረዳት ችሎታ፡-በአንብቦ የመረዳት ፈተና የሚረጋገጥ ሲሆን በጽሁፍ የሰፈረን ሀሳብ አንብቦ
ሊተላለፍ የተፈለገውን መልክት መረዳት፣ መተርጎም፣ ማብራራት ነው፡፡
በገፀባህርይተኮር ማስተማር፡- ስለገጸባህርያቱ ተገቢ መረጃዎችን በመሰብሰብ ገጸባህርያቱ ከጭብጡና
ከመዋቅሩ ጋር ያላቸውን ትስስር ማሳየትና የገጸባህርያቱን የቋንቋ
አጠቃቀም እንደ አውድ መጠቀም ነው፡፡
ቴክስት፡- ከአንድ ስነጽሁፍ የተቀነበበ (የተወሰደ) ጽሁፍ ነው፡፡ መምህራን ስለአንድ ነገር ለማሳወቅ፣ለማስተማር
የሚያዘጋጁት ወይም የሚጽፉት ቅንጫቢ ጽሁፍ ነው፡፡

~8~
ምዕራፍ ሁለት፤ የተዛማጅ ድርሳናት ክለሳ

2.1. የገፀባህርይተኮር ዘዴ የንድፈ ሃሳብ ቅኝት

ገጸባህርይተኮር ትምህርት በባህላዊ የቋንቋ ማስተማር በመጽሐፍ ተገድቦ በመምህር ገለጻና ንግግር ተወስኖ
ቆይቷል፡፡ ይህም ተማሪው በሽምደዳና ፈተና ተኮር በሆነ ግብታዊ ስራ ያለ በቂ እውቀትና በራስ መተማመን
ይገበይ የነበረው የቋንቋ ክሒል ለመዳ ሒደት ሲሆን ስነጽሑፍን በመጠቀም ገጸባህርያት ተኮር ትምህርት
መስጠት ለተማሪው ተነሳሽነትና ተራክቦ ሰፊ እድል በማስገኘቱ ባህላዊውን የቋንቋ ለመዳ ሒደት ከነግምገማ
ስልቱ አስወግዶታል፡፡ በመሆኑም የስነጽሑፍ ከፍተኛ ግላዊነት የምንለው እንደ አንዳንድ የትምህርት ዘርፎች
በውጭ ተጽእኖ የሚመሰረት ሳይሆን በውስጥ ፋላጎትና ዝንባሌ ላይ ስለሚገነባ ገጸባህርይተኮር ትምህርት
ለተማሪዎች የተሳትፎ እድሎችን በስፋት በማመቻቸት ረገድ ተመራጭ መሆኑ ግልጽ ነው (አልከድር
2005፣ ክሩዝ 2010)፡፡

በተለያዩ የቋንቋ ማስተማሪያ ስነዘዴዎች ስነጽሁፍ አንዱ የቋንቋ ማስተማሪያ ሊሆን የቻለበት
ምክንያት ስነጽሁፍና ቋንቋ የጠበቀ ቁርኝት ስላላቸው ነው፡፡ ስነጽሁፍ የሚገለጸው በቋንቋ ሲሆን
ቋንቋ ለስነጽሁፍ እንደማዕዘን ድንጋይ የሚቆጠር ነው፡፡ ያለቋንቋ ስነጽሁፍ የማይታሰብ እንደሆነ ሁሉ
ስነጽሁፍም በበኩሉ ለቋንቋ እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል (ብሩፊትና ካርተር፣1986)፡፡ ስለዚህ
ስነጽሁፍን እንደቋንቋ ማስተማሪያ መሳሪያ መጠቀም ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው በቴክስቱ ላይ
በሰፈረው ጉዳይ ሲከራከሩና ሲወያዩ በመካከላቸው ተግባቦት ሊፈጠር ይችላል (ማክሬ፣1991)፡፡
በተጨማሪም (ላዛር፣1993)፡፡ የስነጽሁፍ ቴክስትን ለቋንቋ ማስተማሪያነት መጠቀም የቋንቋን
ትምህርት ተግባራት አጓጊና ተወዳጅ እንዲሆን በማድረግ አራቱን የቋንቋ ክሂሎች ተማሪዎች
እንዲያጎለብቱ ማድረግ ነው በማለት ያብራራሉ፡፡

ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎችን አንብበው የተፈለገውን ሀሳብ (መልክት) ለማግኘት ሲጠያየቁና ሲወያዩ
የቃላት ሀብታቸው ይዳብራል፤የአስተሳሰብ አድማሳቸው ይሰፋል፡፡ አንድን የተጻፈ ጽሁፍ አንብበው
በሌላ መንገድ መግለጽ ይለማመዳሉ፡፡ በዚህ ሂደት አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው ይጎለብታል፤ በቴክስቱ
ውስጥ ከሚገኙ ጭብጦች፣ገጸባህርያት፣መቸት ወዘተ በመነሳት የተለያዩ የአንብቦ መረዳት መልመጃዎች
ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ስነጽሁፍ ቋንቋን ለማስተማር ጠቃሚ መሳሪያ ነው የሚባለው
(ሂል፣1986)፡፡

~9~
ገጸባህርያት ተኮር ማስተማር የምንለው ስለገጸባህርያት ተገቢ መረጃዎችን በመሰብሰብ ገጸባህሪያቱ
ከጭብጡና ከመዋቅሩ ጋር ያላቸውን ትስስር ማሳየትና የገጸባህርያቱን የቋንቋ አጠቃቀም እንደ አውድ
መጠቀምን ነው (ሂል፣1986)፡፡ ቶም (2008) ደግሞ ተማሪዎች ከገጸባህርያትጋር በሚኖራቸው ስሜታዊ
መቀራረብ በጽሁፍ ወይንም በንግግር የሚያቀርቡበት መንገድ ነው በማለት ሐሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

በገጸባህርያት ተኮር ማስተማር ተማሪዎች በልብ ወለድ ታሪክ የተሳተፉ ገጸባህርያትን ዝርዝር በመያዝ ገላጭ
ቃላትን በመመዝገብ ስለ ገጸባህርያቱ ሙሉ እይታ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው፡፡ በመቀጠል ገጸባህርያቱን
የሚመለከቱ ነገሮች ማለትም ውጫዊ ማንነታቸውንም ሆነ የውስጥ አስተሳሰቦቻቸውን በጽሑፍ፣ በንግግርና
በድራማ እንዲገልጹ የሚደረግበት መንገድ ነው (ሂል፣ 1986)፡፡

ኪታብ (2013)፤ ዳዎዴና ክሌፓን (2010) እንደሚገልጹት በገጸባህርያት ተኮር ማስተማር ተማሪዎች
ገጸባህርያት ምን አሰቡ? ምን ተሰማቸው? ምንስ ሰሩ? አንድን ነገር ለምን በዚህ መንገድ ሰሩ? የሚሉ
ጥያቄዎችን ለመመለስ አስተያየት በመጻፍ፣ በመናገርና በድራማ መልክ እንዲገልጹ የሚደረግ ሒደት ነው
ይላሉ፡፡

ገፀ ባህርያት ተኮር ማስተማር የልቦለድ ገጸባህርይ የአካልና የማንነት ገለጻ ከታሪኩ ሁነቶች ጋር
ያለውን መያያዝ በማስረዳት ይጀምራል፡፡ በመቀጠልም የቋንቋ አጠቃቀሙ ጠንከር ያለ ቢሆን
እንኳ ተማሪዎቹ ቀስ እያሉ የገፀባህርይውን ፍላጎትና ስነልቦና እንዲረዱ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም
በገፀባህርይው በጥበቡና በታሪኩ መዋቅር መካከል ያለውን ዝምድና መተንተን ይችላሉ (ሂል፣
1986)፡፡

ፍራንሲስኮ (2003) ሲገልጹ በገጸባህርያት ተኮር ማስተማር ተማሪዎች የራሳቸውን ሐሳብ


በንግግር የሚገልጹበትን ዘዴ ያስተምራል፡፡ ከዚያም ስለገጸባህርያት አካላዊና ባህሪያዊ መረጃ
በመሰብሰብ የገጸባህርይውን የቋንቋ አጠቃቀም ቋንቋን ለማስተማር እንደአውድ
መጠቀምንም ይጨምራል፡፡

2.2. በገጸባህርይተኮር ዘዴ የማንበብ ክሒልን የማስተማር ጠቀሜታ


በስነጽሁፍ አማካኝነት ቋንቋ ለማስተማር በሚደረገው ጥረት የፈጠራ ስራዎች (ስነጽሁፎች) ስለሚኖራቸው
ሚና ሂል (1986)፣ኮሊና ስላተር (1987)፣ላዛር (1993) በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ይስማማሉ፡፡ የፈጠራ ስራዎች
በቋንቋ ትምህርት ሂደት ውስጥ ተማሪዎችን ያነቃቃሉ፤ምናባዊ ሀይል ስላላቸው የተማሪዎችን ልብ
በመስቀልና በመመሰጥ ትምህርቱን እንዲከታተሉ ያደርጋሉ፤ለምሳሌ ተማሪዎች በልብ ወለዱ ውስጥ
የሚያገኙትን ገጸባህርይ ከራሳቸው ህይዎት ጋር ወይም ከሚያውቁት ከሌላ ሰው ህይወት ጋር ሊመሳሰል

~ 10 ~
ስለሚችል ተሞክሯቸውን በመጠቀም በንግግርም ሆነ በጽሁፍ ሊገልጹት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ስነጽሁፋዊ
ቴክስቶች አዕምሮን የማደስና በመንፈስ ሀሴትን የመናኘት ባህርይ ስላላቸው ተማሪዎች ደስ እያላቸው
የቋንቋውን ትምህርት እንዲከታተሉ ያደርጋቸዋል፡፡

ማሊ (2001) ስነጽሁፋዊ አቀራረቦች ተማሪዎች የገጸባህርያትን ጸባዮች እንዲለዩና በአንዳንድ ባህርያቸው


እንዲሳቡ ስለሚያደርጓቸው ንቁ ተሳታፊነታቸውን ይጨምራል፡፡ ይህም በተግባራዊ ውጤቱ በራስ
መስራትን፣የፈጠራ ችሎታ ማዳበርን እንዲያጎለብቱና የጽሁፉን ሚስጥር እንዲረዱ በማድረግ አንብቦ
የመረዳት ክሂላቸውን ወደላቀ ደረጃ ያሸጋግራል፡፡

በልብወለዶችና በሚና ነጠቃ አቀራረቦች ገጸባህርያትን እንደእውን ሰው በመቁጠር የመጠቀሙ አሰራር


የተለመደ ከመሆኑም በላይ አቀራረቡ በመግቢያዎቻቸው ላይ የተገለጹትን ገጸባህርያት በትረካው ሂደት ውስጥ
ጠለቅ ብለው እንዲገነዘቡና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛል፡፡ የተማሪዎቹ አረዳድ በበረታ
ቁጥር ጠለቅ ያሉና የተዎሳሰቡ የገጸባህርያትን ግንኙነቶች ተንትኖ ማዕከላዊ መልክታቸውን ለመረዳትና
የቋንቋውን ሰዋሰዋዊ አጠቃቀም ከገጸባህርይው ጋር በማገናኘት ለመገንዘብ ያስችላል (ሂል፣1986)፡፡ የስነጽሁፍ
ቴክስቶች የማንበብ ክሂልን ያጎለብታሉ፡፡ ምክንያቱም ምንባባት ትንተና በአንባቢውና በጽሁፉ መካከል
የሚደረግ መስተጋብር ስለሚፈልጉ ነው፡፡ ስነጽሁፍን ማንበብ ለተዝናኖትና መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል፡፡
ስነጽሁፋዊ ቴክስቶች የቋንቋን ትምህርት በማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጾ አላቸው (ሸንግ፣2006)፡፡

አንድን የስነጽሁፍ ቴክስት በማንበብ ተማሪዎች ለተለያዩ የዓረፍተነገር ቅርጾችና ተግባራት እንደዚሁም
ለተለያዩ የቋንቋ አጠቃቀም ቅርጾች እንዲጋለጡ እድል ይሰጣል፡፡ በአጠቃላይ ተማሪዎች የስነጽሁፍ
ቴክስቶችን ሲያነቡ ስለሚያዝናናቸው እንዲመሰጡና በምንባብ ሂደት እንዲዘልቁ በማድረግ አንብቦ
የመረዳት ችሎታቸው ከዕለት ወደዕለት እንዲጎለብት ያደርጋል (ኮሊና ስላተር፣1987)፡፡

አንብቦ መረዳትን ለማስተማር አንዳንድ ታሪኮችንና ቃላትን ከተለያዩ ነገሮችና ጊዜያት ጋር በማዛመድ የአንብቦ መረዳት
ችሎታን ለማሳደግ ይቻላል፡፡ በተለይ በአንድ ጽሑፍ ወይም ታሪክ ውስጥ ያሉ ገጸባህርያትንና ድርጊቶችን በአእምሯቸው
እንዲስሉ ማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ የክፍል መምህራኑ ይህንን ስልት ተማሪዎች እንዲያውቁት
ማድረጋቸው በሚያነቡበት ጊዜ የገጸባህርያቱን ወይም የታሪኩን ምንነትና እንዴትነት በማዛመድ እንዳይረሱት
ያደርጋቸዋል፡፡ የጽሁፉን ታሪክና አላባዊያን በአእምሮ መሳል በቋንቋ መማር በተለይም ደግሞ አንብቦ የመረዳት ችሎታን
በማጎልበት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት (ብሎክ፣ 1997) ያስረዳሉ፡፡ አያይዘውም በመማር ማስተማር ሂደት
ተማሪዎች ምስል ከሳች የሆኑ ታሪኮችን ስሞችንና ቃላትን እንዲያውቁና እነዚህን ሲያነቡ በአእምሯቸው ምን ምስል
እንደተቀረጸ እንዲናገሩና እንዲያስረዱ በማድረግ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን ማጎልበትና ምእናባዊ እይታቸውን
ማሳደግ ከክፍል መምህራኑ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

~ 11 ~
ሂል (1986) ተማሪዎች በሚያነቧቸው ጽሁፎች ውስጥ የሚገኙ ገጸባህርያት ምን አይነት የሰውነት አቋም እንዳላቸውና
የገጸባህሪያቱ ሐሳብ ስሜትና ድርጊት ምን እንደሚመስል ምናባዊ ስእል በአእምሯቸው ይይዛሉ በማለት ሐሳባቸውን
ሰንዝረዋል፡፡

ተማሪዎች የገጸ ባህሪያቱን አስተሳሰብ ፍቅርና ጥላቻቸውን፤ሀዘንና ደስታቸውን በመረዳት ሲያነቡ


ያስተዋሉትን እንዲያቀርቡ በሚደረግበት ሂደት አንብቦ የመረዳት ክሒላቸውን እንዲያሻሽሉ ይረዳቸዋል
(ፍራንሲስኮ፣ 2003) ፡፡

ቱርከር (1991) በገጸባህርያት ተኮር ማስተማር የተማሪውን ሀሳብ የመተንተን ክህሎት ያሳድጋል፡፡ ጠለቅ ያለ
መረጃ ለማግኘትም በጥሞና የማንበብ ልምድን ያጎለብታል፡፡ ይህም እማሬያዊና ፍካሬያዊ ትርጉም ያላቸውን
ቃላት ከአውዱ አንጻር ለመለየትና የባህላዊ እሴቶችን ፋይዳ ከትውልዶችና ከዘመናት አሻራዎች አንጻር ለይቶ
ለመተንተን ያስችላል፡፡

በገጸባህርያትተኮር ቋንቋን ማስተማር የልቦለድ ገጸባህርያትን ዳራ ከታሪኩ ሁነቶች ጋር ያለውን ቁርኝት


በማስረዳት ይጀምራል፡፡ በልምምድ ሂደቶችም ውስብስብና ጠንከር ያሉ ሀሳቦችን ማለትም የገጸባህርያትን
ፍላጎትና ስነልቦና እንዲረዱ ማስቻልን ያበረታታል፡፡ ከዚህም በገጸባህሪያቱ፣በጭብጡና በታሪኩ መዋቅር
መካከል ያለውን ዝምድና ለመተንተን የሚያስችል ፋይዳ ይኖረዋል (ሂል፣1986)፡፡

ስሚዝና ጀፈር (2010) በገጸባህርያትተኮር የማስተማር ጠቀሜታን ሲገልጹ በተማሪዎች አእምሮ እንዲሰርጹ
የተፈለጉ መልካም ስነምግባር ያላቸውን ገጸባህርያት መርጦ ለቋንቋ መልመጃው የክፍል ትምህርት ማበርከት
በተማሪው ላይ በጎ ተጽእኖ በማሳደር እግረ መንገዳቸውን በስነምግባር እየታነጹ እንዲያድጉ ያደርጋል፡፡

ካልቨርት (2004) እንደሚያስረዱት የአንድን ገጸባህርይ ታሪክ እስከተወሰነ ደረጃ ቀለል ባለ አቀራረብ ዘርዝሮ
የሚስብ ልብ አንጠልጣይ ደረጃ ላይ ቆም በማድረግ ተማሪዎቹ የገዛ ልምዳቸውን የተፈጥሮ እምቅ
ችሎታቸውንና ምናባዊ ግምቶቻቸውን በስራ በማዋል ቀጣዩን ሂደት እንዲገልጹ በመምህር ቢጋበዙ ያለ
አንዳች ማስገደድ በመሳተፍ አንብቦ የመረዳት ክህሎታቸውን ማሳደግ ይችላሉ፡፡

2.3. በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ የማንበብ ክሂልን የማስተማር አቀራረብ


ስነጽሁፍ ለትምህርት አላማ እንደመማሪያ ምንጭና እንደትምህርት ዘርፍ ሊቀርብ እንደሚችል (ቬራ፣1991)
፣ካርተርና ሎንግ (1991) ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ጥናት ተግባራዊ የሚሆነው ልብወለድን እንደ መማሪያ ምንጭ
በመጠቀም ቋንቋን ማስተማር ነው፡፡

በቋንቋ ትምህርት ሂደት ስነጽሁፍን እንደመሳሪያነት መጠቀም ዋና ትኩረቱ በተመረጡ የፈጠራ ስራዎች
አማካኝነት የተለያዩ የቋንቋ ክሂሎችን (ማዳመጥ፣መናገር፣ማንበብ፣መጻፍ) ማስተማር ላይ ነው፡፡ ቋንቋን

~ 12 ~
በስነጽሁፍ ማስተማር የቋንቋ አጠቃቀም እውቀት (ክህሎት) ለማዳበር ይጠቅማል፡፡ በትምህርት ሂደትም
የተማሪዎችን የመማር ፍላጎት ያነቃቃል፡፡ በቴክስቱ ውስጥ ከሚገኙ ጭብጦች፣ገጸባህርያት፣መቸት ወዘተ
በመነሳት ሃሳባቸውን በጽሁፍ ወይም በንግግር መግለጽ ይችላሉ፡፡

ሂል (1986) የሚያስረዱት ተማሪዎች በገጸባህርያትተኮር የማስተማር ዘዴ ማንበብን ሲማሩ ስለገጸባህርያቱ


መረጃዎችን ሰብስበው በአዕምሯቸው በመያዝ አንብቦ የመረዳት ልምዳቸውን ማዳበር እንዲችሉ
የገጸባህርያቱን ሁለንተናዊ ማንነት ጠንቅቆ ለመረዳት ከዚህ ቀጥሎ በተዘረዘሩት መንገዶች መጠቀም
አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ እነሱም፡-የገጸባህርያትን ውጫዊ ሁኔታ፣ቁመና፣መልክ፣አለባበስ፣የሰውነት አቋም
የሚገልጹ ቃላትን በመጻፍ መያዝ፤ገጸባህርያቱ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚያከናውኑትን ጉዳይ መቼ? ለምን?
የሚሉትን መለየት፤ከማህበረሰቡ ያፈነገጠውን የገጸባህርያት ባህርይ ወይም አመል ማውጣት፤ከማህበረሰቡጋር
ያለውን ግንኙነት፣የሚጋሯቸውን ጸባዮች መለየት ሲሆኑ ከነዚህ ዝርዝር ጉዳዮች አንጻር ገጸባህርያትን
ሲያስሱና ሲተነትኑ የአንብቦ መረዳት ክሂልን ለማጎልበት ያግዛል፡፡

የስነጽሁፍ ቴክስት ለቋንቋ ማስተማሪያነት ሲውል ሶስት የአቀራረብ የሂደት ደረጃዎችን ሊከተል ይገባል፡፡
የመጀመሪያው ከስራው ጋር መተዋወቅ ነው፡፡ ሁለተኛው ደረጃ የስነጽሁፍ ቴክስቱን በማንበብ የመረዳትና
በጥልቀት የማወቅ ሲሆን፣ ሶስተኛው ቴክስቱን የመተንተንና ትርጓሜ የመስጠት ተግባራት የሚከናወንበት ነው
(ኡር፣ 1991)ና (ኮሊና ስላተር፣1987)፡፡

ሒል (1986)፣ላዛር (1993)፣ በድሉ (1996) ና ብሎክ (1997) ፣ ማረው (2003) እንደሚያስረዱት የስነጽሁፍ
ቴክስት ለቋንቋ ማስተማሪያነት ሲውል አተገባበሩ ቅድመ ንባብ፣የንባብ ጊዜና ድህረ ንባብ ደረጃ ብሎ
በመከፋፈል በየደረጃው ተገቢውን የአተገባበር ብልሀቶች ተግባራዊ ማድረግ ጠቃሚ ይሆናል፡፡

ቅድመ ንባብ ተግባራትን አስመልክተው በድሉ (1996) እንደገለጹት ተማሪዎች ለሚያነቡት ጽሁፍ ምክንያት
እንዲኖራቸውና ፍላጎት እንዲያሳዩ የሚረዱ ተግባራት በቅድመ ንባብ ጊዜ የሚከናወኑት ሲሆኑ እነሱም
አዳዲስ ቃላትን ማብራራት ፣ምንባቡን ማስተዋወቅና መሪ ጥያቄዎችን ማቅረብ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ተማሪዎች የምንባቡን ታሪካዊና ባህላዊ ዳራ እንዲያዉቁ፣ በአካባቢያቸው የቤተ መፅሐፍት አገልግሎት የሚያገኙ
ከሆነ ስለልቦለድ ምንነትና ታሪክ እንዲያነቡና በሚያነቡበት ወቅት ስለሚያነቡት ልብወለድ አስቀድመዉ እንዲተነብዩ
ማድረግ፣ ቀጥሎ የመፅሐፉን ሽፋን ስዕል፣ርዕስ ተመልክተዉ በዉስጥ ገፆች ስለሚወራዉ ነገር እንዲገምቱ ማነሳሳት፣ስለርዕሱ
እንዲወያዩ ማድረግ፣ ከታሪኩ አንድ አንቀፅ በማስነበብ ጠቅለል ያለ ትንበያ ማሰጠት፣ተዘዉትረዉ የማይነገሩ
(የማያውቋቸዉ) ቃላት ካሉ መምረጥና ፍቺ እንዲሰጡ ማድረግ፣ ጭብጡ ላይ የሚያተኩሩ ጥያቄዎችን በመስጠት ከራሳቸዉ
ጋር እያዛመዱ እንዲወያዩ በማድረግ ፍላጎታቸዉን ማነሳሳት ተገቢ ነው (ላዛር፣1993)፡፡

~ 13 ~
የንባብ ጊዜ ክንውንን በተመለከተ ብሎክ (1997) እንደሚያስረዱት በንባብ ጊዜ ጥያቄ
መጠየቅ፣መገመት፣መተንበይ ፣ማብራራት፣መተርጎም፣ምስል መፍጠርና ማጠቃለልን የመሳሰሉ የአንብቦ
መረዳት ብልሀቶችን ተማሪዎች ሊለማመዱ ይገባል፡፡ እንደብሎክ ማብራሪያ ተማሪዎች በንባብ ሂደታቸው
ስለሚያነቡት ጉዳይ በራሳቸውም ሆነ አንዳቸው ለሌላው ጥያቄዎችን መጠየቅን፣ ከአነበቡት መረጃ በመነሳት
ያላነበቡትን ቀጣይክፍል ሀሳብ ወይም ድርጊት ምን ሊሆን እንደሚችል መገመትን፣ ከቀረበው አንድ ፍንጭ
በመነሳት የአዳዲስ ቃላት ትርጉም መረዳትና በቴክስቱ የተሰጠን መረጃ በመገምገም ውሳኔና ማጠቃለያ ላይ
የመድረስ ብልሀቶችን በመለማመድ ክሂሉን ማዳበር አለባቸው፡፡ ዋና ገፀባህሪዉን ወስደዉ ባህሪዉን ባንድ ቃል
እንዲገልፁ፣ገፀባህሪያት ካላቸዉ ባህሪ አንፃር በደረጃ እንዲለዩአቸዉ በማድረግ፡፡ ማለትም ክፉ'ደግ'ቁጡ…
እያሉ፡፡ የተለያዩ ገፀባህሪያትን ባህሪ ወስደዉ እኔ ብሆን እያሉ እንዲፅፉና እንዲናገሩ በማድረግ ገፀባህርይውን
እንዲረዱ መርዳት ይቻላል፡፡

እንደብሎክ አገላለጽ እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ለምሳሌ የቀረበውን ቴክስት ታሪክ አንብቦ ምክንያታዊ
በሆነ መልኩ ማብራራት፣በቴክስቱ ውስጥ የተገኘውን መረጃ ከራስ የህይወት ዳራ እውቀት ጋር በማያያዝ
አማራጭ የትርጓሜ ውሳኔ መስጠትን ማዳበር ይገባል፡፡ በቴክስቱ ውስጥ የቀረቡትን ገጸባህርያት፣ድርጊቶችና
ክስተቶች ምስል እየፈጠሩ ለመረዳት መሞከርና ከአረፍተነገር እስከ ሙሉ ቴክስቱ በየደረጃው ማጠቃለያ
እየሰጡ መሄድም አንብቦ ለመረዳት የሚያስችሉ በመሆናቸው በልምምድ ማዳበር ይገባቸዋል፡፡

በድህረ ንባብ ደረጃ የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ የሚያዳብሩ ተማሪ ተኮር የማስተማሪያ ዘዴን የተከተሉ
እንደሁኔታው በግል፣በጥንድና በቡድን የሚከናወኑ የተለያዩ የስነጽሁፍ ተግባራትን እንዲለማመዱ ማድረግ
ያስፈልጋል (ኮሊና ስላተር፣1987)፡፡ ሒል (1986) ና ላዛር (1993) ይህንን ሃሳብ በመደገፍ እንደሚያስረዱት
በድህረንባብ ደረጃ በተለያዩ ስነጽሁፍ ቅርጾች የተለያዩ ተግባራትን በማደራጀት የተማሪዎችን የቋንቋ ክሂሎች
ማዳበር ይቻላል፡፡ በማለት ይገልጻሉ፡፡

ይህ የንባብ ክፍል የክፍል መምህሩ ተማሪዎች የቀረበውን ምንባብና ታሪክ መረዳታቸውን የሚያረጋግጥበት
ሲሆን በዋናነት ተማሪዎች የታሪኩን ዋና ጭብጥ እንዲያወጡ (እንዲተረጉሙ) ለመርዳት ከምንባቡ
የተገነዘቡትን አጠቃላይ ሃሳብ እንዲገልፁ ማበረታታት፤ በአዳዲስ ቃላት፣አባባሎችና አገላለፆች ዙሪያ ዉይይት
እንዲያደርጉ ማገዝ፡፡ ለምሳሌ የተለየና ተምሳሌታዊ አገላለፅ ያላቸዉን ቃላት እንዲያወጡ ማድረግና ዘይቤአዊ
ትርጉማቸዉን መጠየቅ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተማሪዎች ራሳቸዉን በታሪኩ ዉስጥ በማድረግ የዕለት
ማስታዎሻን በመጠቀም የታሪኩን ሁኔታ እንዲገልፁ ማድረግና ታሪኩ በአንደኛ መደብ ከተተረከ ምንባቡ ዉስጥ
ባለ መረጃ መሰረት ግልፅ የገፀባህርይ ገለፃ እንዲያደርጉ ማለማመድ የትረካ አንፃሩን እንዲረዱት ያግዛል፡፡

ተማሪዎች ያነበቡትን ነገር ተረድተው ዉይይት እንዲያደርጉ ለመርዳት ያነበቡትን ታሪክ መሰረት አድርገዉ
ስለአፃፃፉ፣ስለገጸባህረያት ሁኔታ እንዲወያዩ፣ በፅሁፉ ዉስጥ የተገለፀዉ ሃሳብ በዕዉኑ ዓለም ያለዉን እሴት

~ 14 ~
በተመለከተ ዉይይት ወይም ክርክር እንዲያደርጉ፣ የተፈፀሙ ዋና ዋና ድርጊቶችን ቅደም ተከተል ጠብቀዉ
እንዲገልጹ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ድህረ ንባብ ተግባራት ተማሪዎች ከምንባቡ ያገኟቸውን መረጃዎች
ለማስተሳሰርና ለማዋሃድ የሚያስችሉ ክንዋኔዎችና ተግባራት ናቸው፡፡ ከተግባሮቹም መካከልጥያቄ
መጠየቅ፣ውይይት ማካሄድ፣ጽህፈት፣ትወና፣ስዕል፣ሙዚቃና ዳንስ ይገኙበታል፡፡ የተነበበውን ምንባብ መሰረት
በማድረግ የተዘጋጁ ጥያቄዎችን ያካትታል፡፡ ጥያቄዎቹም የቃላትን ፍች ከመጠየቅ እስከ ምንባቡ ፍሬ ሀሳብና
የጽሀፊውን አመለካከት መጠየቅ ይደርሳሉ (ማረው፣ 2003)፡፡

2.4. በገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ላይ የተደረጉ ተዛማጅ ጥናቶች ክለሳ


ኪታብና ሰይዳራዚ (2013) በጋራ አጭር ልቦለድንና ስነጽሁፍን መሰረት በማድረግ ቋንቋን ማስተማር በሚለው
ጥናታቸው ላይ የሌሎችን አጥኚዎች የጥናት ውጤቶችን ሳግ (1987)፣ ኦቢዴት(1997)፣ ኩስቶዲናና ሱቶን
(1998)፣ ና ሞርዶች (2002)ን ዋቢ በማድረግና በራሳቸው የጥናት ውጤትም አጭር ልብወለድም ይሁን
ስነጽሁፍን መሰረት በማድረግ ቋንቋን ስናስተምር ተማሪዎች ጠያቂ እንዲሆኑ፣ ለነገሮች ትርጉም እንዲሰጡ፣
ሐሳቦችን እንዲያዋህዱ፣ ቋንቋውን መገንዘብ እንዲችሉ ብሎም ተመራማሪ እንዲሆኑ፣ አራቱን የቋንቋ
ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጋሉ፡፡ በተለይ በእርሳቸው የጥናት ግኝት ስነጽሁፍን መሰረት በማድረግ
ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ እንደሚያጎለብት ገልጸዋል፡፡

ሳንዚ (2012) ቋንቋን በስነጽሁፍ አማካኝነት ማስተማር በሚለው ጥናት ስነጽሁፍን ለቋንቋ ማስተማሪያነት
መጠቀም የተማሪዎችን የቋንቋ ክህሎት ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይገልጻሉ፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች
አጭር ልብወለዶችን፣ ድራማዎችን፣ ግጥሞችን ሲያነቡ ቋንቋውን እንዲለምዱ ይገፋፋቸዋል፤ በዚህም
የቃላት ሐብታቸው ይጨምራል፤ የማንበብ ልምድ እንዲያዳብሩ እንዲሁም የማንበብ ብልሐት እንዲማሩበት
ያደርጋል፡፡

ወርቁ (2000) ሳሊህ (1989)ን ዋቢ በማድረግ በስነጽሁፍና በቋንቋ ትምህርት መካከል ያለውን ተዛምዶ
በጥናት ለማረጋገጥ በ 118 ተማሪዎች ላይ ባደረገው ምርምር ስነጽሁፍ የቋንቋ ክሂሎችን ብቻ ሳይሆን
የስነጽሁፍና የሰዋሰው እውቀትንም ማዳበር የሚያስችል መሳሪያ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ይህ የሚያሳየው
ተማሪዎች በስነጽሁፉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ገጸባህርያትን ድርጊትና አመለካከት በትኩረት በመከታተል
በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልክት መረዳት ይችላሉ፤አንብቦ የመረዳት ክሂላቸውንም
ያጎለብታሉ፡፡

የመግቢያ ጽንሰ ሃሳብ የያዘ የጨዋታ ምንባብ፣የፈጠራ አጻጻፍ፣ተግባር ተኮር መልመጃ፣የተዘጋጁትን


ጨዋታዎችና ስነጽሁፋዊ ጽሁፎችን ባነበቡ ቁጥር ምናባዊ ምስል በአዕምሯቸው በመሳል ስለገጸባህርያቱ
ግንዛቤ መውሰድ ይጀምራሉ፡፡ በዚህም የተሳታፊነት ፍላጎታቸውና አንብቦ የመረዳት ችሎታቸው እየጨመረ

~ 15 ~
ይሄዳል፡፡ ይህ ልምምድ በስነጽሁፍ የሚያገኟቸውን ገጸባህርያት ጸባይ በመረዳት ቋንቋን በተሻለ ሁኔታ
ለምደው እንዲግባቡ ያስችላቸዋል በማለት (ቱርከር ፣1991) ባህላዊና ዘመናዊውን አቀራረብ አጣጥመው
ባቀረቡት ጥናት ይገልጻሉ፡፡

በጀማሪ ደረጃና በመለስተኛ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስነጽሁፋዊ ቴክስቶችን፣ መጣጥፎችንና
መዝሙሮችን ለቋንቋ ማስተማሪያ በማቅረብ ባደረገችው ጥናት ስነጽሁፋዊ ቴክስቶችን ለማስተማሪያነት
ማቅረብ ለተማሪዎችም ሆነ ለመምህራን ደስታን በመፍጠር ለመማር የሚያነሳሳ ከመሆኑም በላይ የመተንተን
ክህሎትን የሚያሳድግ መሆኑን (ቫርኬይ፣1995) በፓኪስታን፣ታይዋን፣ኢኳዶርና አሜሪካ ያደረገችውን ጥናት
ዋቢ በማድረግ ወርቁ (2000) ገልጿል ፡፡

ፉአድ (2008) ስነጽሁፍን በመጠቀም እንግሊዘኛ ቋንቋ በማስተማር የንባብ ክሂልን የማጎልበት ሚና በሚል
ርዕስ ባቀረበው ጥናት ስነጽሁፍን በመጠቀም ቋንቋን ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ
እንደሚያጎለብት አመላክቷል፡፡

ስነጽሁፍ ግላዊና ማህበራዊ ህይወትንና ባህልን የሚነካ ጉዳይ ስለሆነ ተማሪዎችን በማነሳሳት ተሳትፎን
የማሳደግና አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማጎልበት አቅም ያለው በመሆኑ ለቋንቋ ማስተማሪያነት አስፈላጊ
እንደሆነ የተለያዩ ጸሃፍት (ሒል 1986፣ኮሊና ስላተር 1987፣በድሉ 1996) ይገልጻሉ፡፡

ዘመንፈስ (1991) በስነጽሁፍ አማካኝነት የአማርኛ ቋንቋን በማስተማር የአጭር ልብወለድ ሚና በሚል ርዕስ
የተጠና ጥናት ነው፡፡ የጥናቱ ዋና ትኩረት በአጭር ልብወለድ አማርኛ ቋንቋን ማስተማር አባይትና ንኡሳን
ክሂሎችን ለማዳበር ያለውን አስተዋጾ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በጥብቅና የሙከራ ሁለት ቡድኖች
ላይ ነው፡፡ በሁለቱ ቡድኖች መካከል ቅድመፈተና ተሰጥቶ ልዩነት አልታየም፤ ነገር ግን በተለያዩ ዘዴዎች
ትምህርት ተሰጥቷቸው ሲፈተኑ ልዩነት መታየቱ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም በአጭር ልብወለድ የተማሩት
በተለመደው ዘዴ ከተማሩት ቡድኖች የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገቡ የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ ውጤቱም
የስነጽሁፍ ቴክስትን በመጠቀም ቋንቋን ማስተማር ውጤታማ እንደሚያደርግ ያመለከተ ነው፡፡ ፈጠራዊ ዘዴን
ተጠቅሞ በስነጽሁፍ አማካኝነት ቋንቋን ማስተማር ክሂሎችን በማጎልበት ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
በተጨማሪም ተማሪዎች እራሳቸውን ችለው እንዲማሩና እርስ በእርስ የመተጋገዝ ባህል እንዲያዳብሩ
ለማድረግ ይረዳል፡፡

እንዳልክ (2010) ባቀረበው ጥናት በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሁፍ ቴክስት ይዘትተኮር የማስተማር ዘዴ
ማስተማር የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያጎለበተ መሆኑን አመላክቷል፡፡ አንብቦ መረዳት ችሎታ
ላይ መሻሻል የታየው ለይዘትተኮር ዘዴ ማስተማሪያነት የቀረቡ ቴክስቶች መቸት፣ሴራ፣ገጸባህርያት
አቀራረብን መሰረት ያደረጉ እና በጽሁፍ ውስጥ ያለ መረጃ መረዳትን የሚያስችሉ በመሆናቸው ነው፡፡

~ 16 ~
እነዚህ ጥናቶች ትኩረት ያደረጉት በስነጽሁፍ ቴክስት ቋንቋን ማስተማር አንብቦ ለመረዳት ችሎታ ከፍተኛ
አስተዋጾ እንዳለው ቢሆንም በስነጽሁፍ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ገጸባህርያትን ድርጊትና አመለካከት በትኩረት
በመከታተልና ምናባዊ ምስል በአዕምሯቸው በመሳል በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገውን መልክት
መረዳት እንደሚችሉ ይህም የተሳታፊነት ፍላጎታቸው እንደሚጨምረውና ግላዊና ማህበራዊ ህይወትንና
ባህልን እንዲያውቁ በተጨማሪም የገጸባህርያትን የቋንቋ አጠቃቀም ተረድተው ተግባራዊ እንዲያደርጉ
ማስቻሉ ከዚህ ጥናት ጋር አንድ ያደርገዋል፡፡

~ 17 ~
ምዕራፍ ሦስት፤ የአጠናን ዘዴ
3.1 የአጠናን ስልት
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የማንበብ
ክሂልን ለማዳበር ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ መጠናዊ ምርምር በመሆኑ ከፊል ሙከራዊ ስልትን
ተከትሎ የተከናወነ ነው፡፡ በሂደቱም ቅድመትምህርት ፈተናና ድህረትምህርት ፈተና ተግባራዊ ተደርጓል፡፡

ንድፉ ባለ ሁለት ቡድን ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ሙከራን የተከተለ ሲሆን ሁለቱ ቡድኖች ማለትም የሙከራውና
የቁጥጥሩም ቡድን በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት ተመሳሳይ የአንብቦ መረዳት ፈተናዎችን በተመሳሳይ ጊዜ እንዲፈተኑ
ተደርጓል፡፡ ቅድመ ትምህርት ፈተናው የሁለቱንም (የሙከራና የቁጥጥር) ቡድኖች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተመጣጣኝነት
ለማረጋገጥ ያገለገለ ሲሆን ድህረትምህርት ፈተናው በተጽኖ ፈጣሪው ማለትም በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍ
ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማረውን የሙከራ ቡድኑንና በስነጽሁፍ ቴክስት በተለመደው የአንብቦ መረዳት
ማስተማሪያ ዘዴ የተማረውን የቁጥጥር ቡድኑን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማነጻጸር አገልግሏል፡፡

3.2 የጥናቱ ተሳታፊዎች


ጥናቱ የተካሄደው በአማራ ክልል፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ ከሚገኙሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች መካከል
የፈረስቤት አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርት ቤት በአመች ንሞና አመራረጥ ዘዴ
ተመርጧል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አጥኚዋ ለብዙ አመታት ያስተማረችበትና አሁንም እየሰራችበት ያለ ትምህርትቤት
ስለሆነና ጥናቱን ለማጥናት ወደ ሌሎች ትምህርት ቤቶች በምትሄድበት ጊዜ የትራንስፖርት አገልግሎት በፈለገችበት ጊዜ
ማግኘት ስለማትችል ብቻዋን ለመሄድ ከምትሰራበትና ከምትኖርበት ቦታ ርቀት ስላላቸው በእግር ተንቀሳቅሶ ለመስራት
አስቸጋሪ ስለሚሆን የሚባክነውን ገንዘብ፣ ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ፣እንዲሁም አስተማማኝነት ያለው መረጃ ለማግኘት
የተሻለ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡

የጥናቱ ተሳታፊዎች በ 2011 ዓ.ም በፈረስቤት አጠቃላይ ሁለተኛና የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርት
ቤት በመማር ላይ ከሚገኙ አራት የክፍል ደረጃ ተማሪዎች መካከል የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ይህ
የክፍል ደረጃ ለጥናቱ የተመረጠበት ምክንያት የ 10 ኛና 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ትኩረታቸውን ሁሉ ለሐገር
አቀፍ ፈተናዎች ብቻ ይሰጣሉ ተብሎ ስለታሰበና የ 9 ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች
በእድሚያቸውም ሆነ በንባብ ተጋልጧቸው አነስተኛ በመሆናቸው የአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ ነው
ተብሎ በመታሰቡ፤ እንዲሁም፣ አጥኚዋ በተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ስታስተምር በሁሉም ክፍሎች የአንብቦ
መረዳት ችግር ያስተዋለች ቢሆንም በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ግን ጎልቶ በመታየቱ ነው፡፡ ይህ በመሆኑም
የክፍል ደረጃው አላማ ተኮር ንሞና ዘዴን በመጠቀም ተመርጧል፡፡

~ 18 ~
የጥናቱ አካላዮች በ 2011 ዓ.ም በመማር ላይ የሚገኙ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዘጠነኛ ክፍል 1536
ተማሪዎች በ 39 የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ይማራሉ፡፡ እያንዳንዱ ክፍል በአማካኝ 40 ተማሪዎች ይዟል፡፡
ተማሪዎችም በት/ቤቱ አሰራር መሰረት የ 8 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መሰረት በማድረግ በችሎታ
ስብጥር የተመደቡ ናቸው፡፡ ይሁንና ሁሉንም ተማሪዎች በጥናቱ ተሳታፊ ለማድረግ ከጊዜ፣ ከገንዘብና ከሰው
ሐይል አንጻር አስቸጋሪ ስለሚሆን በጥናቱ ተሳታፊ ለማድረግ ቀላል የእጣ ማውጣት ንሞና ዘዴ በመጠቀም
የዘጠነኛ ምድብ 2 እና ምድብ 28 ክፍል ተማሪዎች የጥናቱ ተሳታፊዎች ሆነው ተመርጠዋል፡፡

በእጣ ከተመረጡ ሁለት ክፍሎች ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች በጠቅላይ ንሞና ዘዴ ተካተዋል፡፡ ሁሉም
የተካተቱት በክፍል ውስጥ የተመደቡት በችሎታ ስብጥር በመሆኑና ሙሉ መረጃ ለመስጠት ስለሚያስችሉ
ነው፡፡

ክፍሎቹን የሙከራና የቁጥጥር ብሎ ለመለየት የቅድመትምህርት ፈተናውን መጀመሪያ ላይ በመስጠት ከቀላል


እድል ሰጭ ንሞና ዘዴ ውስጥ እጣ የማውጣት ዘዴን በመጠቀም ዘጠነኛ ምድብ 2 የሙከራ ቡድን እንዲሁም
ዘጠነኛ ምድብ 28 የቁጥጥር ቡድን ሆነው ተመርጠዋል፡፡

3.3 የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ


የጥናቱ ዋና አላማ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የአንብቦ
መረዳት ችሎታን የማጎልበት ሚና መመርመር ነው፡፡ ይህንን አላማ ግምት ውስጥ በማስገባት የጥናቱን መረጃ
ለመሰብሰብ በተግባር ላይ የዋለው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ ፈተና ነው፡፡

መረጃን ለመሰብሰብ ከሚያግዙ በርካታ ዘዴዎች መካከል ፈተናዎች ጉልህ ድርሻ ይዘው ይገኛሉ፡፡ ፈተናዎች
በተለያዩ መልኮች ተዘጋጅተውና በጥንቃቄ ተቀናጅተው አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ ያስችላሉ፡፡

ፈተና ማለት የተወሰኑ ጥያቄዎች ተዘጋጅተው ወጥነት ባለው መንገድ የተፈታኞችን አእምሯዊ ወይም
ስነባህርያዊ ሁኔታ አስመልክቶ መረጃ ለመሰብሰብ የሚረዳ መለኪያ ነው፡፡ እዚህ ላይ ወጥነት ሲባል ፈተናው
ለጥናቱ ተሳታፊዎች የሚሰጠው በተመሳሳይ ሁኔታ ማለትም በተመሳሳይ የጊዜ ገደብ፣በተመሳሳይ
የአፈታተንና የአስተራረም መንገድ፣ ተመሳሳይ የመልስ አሰጣጥ መልክ፣ መመሪያና ከተቻለም በተመሳሳይ
ፈታኝ ወይም ተቀራራቢ የአፈታተን ብቃት ባላቸው ሰዎች የሚካሄድ መሆኑን ለማመልከት ነው
(ያለው፣1998)፡፡

በዚህ ጥናት የአንብቦ መረዳት ፈተና የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ በመሆን የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት
ችሎታ ለመለካት አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ ፈተናውም በአጥኝዋ ተዘጋጅቶ በአማርኛ ቋንቋ መምህራንና
በአጥኝዋ አማካሪ ተገምግሞና የማሻሻያ ሃሳብ ተደርጎበት እንደገና ተዘጋጅቷል፡፡ ለአንብቦ መረዳት ፈተና

~ 19 ~
የተዘጋጀው ምንባብ ሲመረጥና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መለኪያ ጥያቄዎች ሲዘጋጁ የክፍል ደረጃውንና
ስርዓተትምህርቱን መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ይህ ፈተና ቅድመትምህርት ፈተና እና ድህረትምህርት ፈተናን አካቶ የያዘ ነው፡፡ ቅድመ ትምህርት ፈተናው
ተማሪዎቹ በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ከመማራቸው በፊት የነበራቸውን የአንብቦ
መረዳት ችሎታ ለመለካት ያገለገለ ሲሆን ድህረ ትምህርት ፈተናው ደግሞ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ማስተማር ከተማሩ በኋላ ያላቸውን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለመለካት
ተግባር ላይ ውሏል፡፡ እንዲሁም አስተማማኝነቱን ለማረጋገጥ ለሌሎች ከጥናቱ አካላይ ውጭ ከሆኑ ሰላሳ
ሰባት ክፍሎች ውስጥ ቀላል የእጣ ንሞና ዘዴ በመጠቀም ሁለት ክፍሎች ምድብ 17 እና ምድብ 24
ተመርጠዋል፡፡ ከነዚህ ክፍሎች ውስጥ እንደገና አስር አስር ተማሪዎች በቀላል የእጣ ማውጣት ንሞና ዘዴ
በመምረጥና ፈተናውን በመፈተን አስተማማኝነቱ በእኩል ከፋይ ዘዴ ተሰልቶ 0.793 በመሆን ከ 0.7 በላይ
ጉልህ ልዩነት በማሳየቱ አስተማማኝነቱ ተረጋግጧል፡፡

3.4 የማስተማሪያ ቴክስት ዝግጅት


ላዛር (1993) እና በድሉ (1996) እንደሚያስረዱት ለአንብቦ መረዳት የሚሆኑ ምንባቦች ሲመረጡ
የተማሪዎችን እድሜ፣ አእምሯዊ ብስለት፣ ፍላጎት፣ ስነጽሁፋዊ ዳህራዊ እውቀት ያገናዘበ ማህበራዊ፣ ባህላዊ፣
ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ያገናዘበ፣የተማሪዎችን የእውቀት ደረጃ የሚመጥን፣የምንባቦች የክብደት ደረጃ
የተመጠነ ከመርሀ ትምህርቱ ጋር ያለው ተዛምዶ የምንባቦች ሳቢነት የሚሉትን ነጥቦች ያካተተ መሆን አለበት
በማለት ይገልጻሉ፡፡ ከዚህ በተያያዘም ማድሰን (1983) ለአንብቦ መረዳት የሚመረጡ ምንባቦች የደራሲውን
አመለካከት ከራሳቸው ጋር ለማገናዘብ የሚረዱ አንድን ነገር በጥልቀት እንዲመረምሩ እንዲገመግሙ የሚያግዝ
ጅምር ሀሳቦችን ለመቋጨት ፍላጎት የሚያሳድሩ፣ በከባድ ቃላት ያልተሞሉ ለቀጣይ ተግባራት ቀስቃሽ ሊሆኑ
ይገባል በማለት ይገልጻሉ፡፡

ይህን መስፈርት መሰረት በማድረግ ማህበራዊ፣ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ እውቀትን ለመስጠት ብሎም


ተማሪዎች አንድን ነገር በጥልቀት እንዲገመግሙ ጅምር ሐሳብ እንዲጨርሱ የሚያደርጉና የማንበብ ፍላጎት
የሚያሳድሩ ምንባቦች ተመርጠዋል፡፡

ተማሪዎች የቅድመትምህርት ፈተናውን ከተፈተኑ በኋላ ለሙከራ ቡድኑ በስነጽሑፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር
የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ክሒላቸውን ለማጎልበት የማስተማሪያ ቴክስቶች በአጥኚዋ ተዘጋጅተዋል፡፡
ቴክስቶቹ ከረጅምና ከአጭር ልቦለዶች እንዲሁም ከቀድሞው የዘጠነኛ ክፍል መማሪያ መጽሃፍ ተቀንጭበው
የተወሰዱ ሲሆን የ 9 ኛ ክፍል መማሪያ መጽሐፉን የተማሪዎችን የክፍል ደረጃና ግንዛቤ መሰረት ባደረገ መልኩ
ተዘጋጅተዋል፡፡ ሁሉም የአንብቦ መረዳት ክሂልን ለማስተማር የተዘጋጁ መልመጃዎችንና ተግባራትን ይዘዋል፡፡

~ 20 ~
ቴክስቶቹ ለሙከራና ለቁጥጥር ቡድኑ በትምህርትነት ከመቅረባቸው በፊት በአጥኚዋ አማካሪና ሁለተኛ ዲግሪ
ባላቸው የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል እሱን ተከትሎም ማሻሻያ ተደርጎባቸው
በተማሪዎቹ ልክ ተባዝተው ለእያንዳንዱ ተማሪ ተሰጥቷል፡፡ ጥናቱን ከግብ ለማድረስም በተቃራኒ ፈረቃ
በሳምንት ሁለት ቀናት (ሰኞና ሐሙስ) በቀን ለ 40 ደቂቃ ለአንድወር በአጥኚዋ ትመምህርቱ ተሰጥቷል፡፡
የተዘጋጀው ቴክስት ተማሪዎች አንብበው የተረዱትን ሃሳብ ምላሽ የሚሰጡበትና የአንብቦ መረዳት
ክሂላቸውን የሚያጎለብቱበትን ተግባራት የያዘ ሲሆን የማንበብ ተግባራትን ቅድመንባብ፣ በንባብጊዚና
በድህረንባብ በማስታዎስ የሚመለሱ ጥያቄዎች፣ እውነት/ሃሰት ጥያቄዎች፣ የተገነዘቡትን በጽሁፍ
የሚገልጹባቸው ጥያቄዎች፣ የምርጫ ጥያቄዎች፣ አውድን በመጠቀም ፍችን እንዲሰጡና አንብቦ የመረዳት
ተግባራትን ለማከናዎን የሚያስችሉ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡

3.5 የአጠናን ሒደት


ጥናቱ ለተከታታይ ወራት የተሰራ ሲሆን ለትምህርትቤት አመራሮች፣ ለተጠኝ ተማሪዎችና ዘጠነኛ ክፍል
አማርኛ ቋንቋን ለሚያስተምሩ መምህራን የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ በሁሉም ክፍሎች ያልዳበረ
እንደሆነ፣ የአንብቦ መረዳት ችግር በይበልጥ በዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ጎልቶ እንደሚታይ፣ ጥናቱ ለምን
ዓላማ እንደሚውልና ችግሩን ለመቅረፍ ደግሞ ሙከራዊ ጥናት እንደሚያስፈልግ በአጥኚዋ መጋቢት 12/2011
ቀን ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ ተማሪዎችም ለመማር ፈቃደኛ መሆናቸውን ተጠይቀው ፈቃደኛነታቸውን ገልጸዋል፡፡

ስለገጸባህርይተኮር ማስተማር የተሻለ ግንዛቤ ያላት አጥኚዋ ስለሆነችና በትምህርትቤቱ ውስጥ ከሚገኙ
መምህራን መካከል በማስተማር ልምድም ቢሆን ከአጥኚዋ የተሻለ ሰው ባለመኖሩ የተነሳ ትምህርቱ በአጥኚዋ
እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

ለሙከራና ለቁጥጥር ቡድኑ ትምህርቱ ከመሰጠቱ በፊት ለመረጃ መሰብሰቢያ የሚሆኑ ሁለት ምንባቦች
ለቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተናዎች በአጥኚዋ ተዘጋጁ፡፡ እነዚህ ምንባቦች
በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ከመሰጠታቸው በፊት በአጥኚዋ አማካሪና
በአማርኛ ቋንቋ መምህራን ተመጣጣኝነታቸው ተገምግሞ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡ የፈተናዎቹ
አስተማማኝነትም በእኩል ከፋይ ዘዴ ተረጋግጧል፡፡

የቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና መጋቢት 23/2011 ዓ.ም ተሰጥቷል፡፡ ፈተናውን ሁለት የአማርኛ
ቋንቋ መምህራን (አንዱ መምህር የሙከራ ቡድኑን ሁለተኛው ደግሞ የቁጥጥር ቡድኑን) እንዲፈትኑ
ተደርጓል፡፡ አጥኚዋ ተማሪዎች በሚፈተኑበት ጊዜ ምልከታ በማድረግ ፈተናውን ያለምንም ችግር እንዲፈተኑ
ሁኔታዎችን አመቻችታለች፡፡

~ 21 ~
የቅድመትምህርት ፈተናው ካበቃ በኋላ የመልስ ወረቀቶችን በአግባቡ በማሰባሰብና በማደራጀት እንዲሁም
በማረም ውጤቱ በሰንጠረዥ ተመዝግቦ ተቀምጧል፡፡ ከዚያም አጥኚዋ የጥናቱን ተሳታፊዎች ለማስተማር
ከአጭርና ረጅም ልቦለዶች ቅንጫቢ በመውሰድ ምንባቦችን አዘጋጅታለች፡፡ ሁሉም ምንባቦች በሳምንት
የሁለት ቀን ተግባር ያላቸውና በቀን ለአርባ ደቂቃ መሰጠት የሚችሉ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡

የተዘጋጁትን የማስተማሪያ ቴክስቶች ለሙከራና ለቁጥጥር ቡድኖች በተቃራኒ ፈረቃ በተለያየ ክፍል እንዲማሩ
ተደርጓል፡፡ አንደኛውን (የቁጥጥር ቡድኑን) በስነጽሁፍ ቴክስት በተለመደው የማንበብ ክሒል ማስተማሪያ ዘዴ
በመጠቀምና ሁለተኛውን (የሙከራ ቡድኑን) ደግሞ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሑፍቴክስት
ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡

የሙከራ ቡድኑ ገጸባህርይና ጭብጡን፣ ገጸባህርይና መዋቅሩን በማገናዘብ ዋና ሐሳቡን መለየት፣


በገጸባህርይው፣ በጥበቡና በታሪኩ መዋቅር መካከል ያለውን ዝምድና መተንተን እንዲችሉ፣ የገጸባህርይውን
አለባበስ፣ አነጋገር፣ አስተሳሰብ የሚገልጹ ዝርዝሮችን እንዲያዘጋጁ በማድረግ ዋና ሐሳቡን በመለየት የአንብቦ
መረዳት ጥያቄዎችን እንዴት መስራት እንዳለባቸው ልዩ እገዛ እየተደረገላቸው ከመጋቢት 26/2011 ዓ/ም እስከ
ግንቦት 02/2011 ዓ/ም ለአንድ ወር ያህል ትምህርቱን እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም የተማሪዎችን
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለመለካት የድህረ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ግንቦት 08/2011 ዓ/ም
ተሰጥቷል፡፡ የአንብቦ መረዳት ፈተናው ለሁለቱም ቡድኖች በሁለት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን እንዲፈተኑ
ተደርጓል፡፡ ፈተናዎችም በአግባቡ ታርመውና ተደራጅተው ለትንተና በሚመች መንገድ ቀርበዋል፡፡

3.6 የመረጃ አተናተን ዘዴ


ከጥናቱ ተተኳሪዎች በፈተና የተሰበሰቡት መረጃዎች ከመተንተናቸው በፊት መልሶቹ ትክክለኛ በሆነ መንገድ
መሞላታቸው ተረጋግጧል፡፡ መረጃው ለትንተና በሚያመች መልኩ ኮድ ተደርጎ በውጤት መመዝገቢያ
ሰንጠረዥ ሰፍሯል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ የጥናቱን አላማ ማሳካት ይችል ዘንድ መጠናዊ ስልትን በመጠቀም
ተተንትኗል፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ ማስተማር የተማሪዎችን
አንብቦ የመረዳት ችሎታ ማጎልበት መቻል-አለ መቻሉን ለመለካት በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት
በአንብቦ መረዳት ፈተና የተሰበሰበው መረጃ በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ በመደበኛ ልይይት)፣ የጉልህነት
ደረጃውን ለማወቅ በነጻ ናሙና ቲ- ቴስትና በዳግም ልኬት ቲ-ቴስት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የሙከራና የቁጥጥር
ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና ውጤት በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልቶ
በሰንጠረዥ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ የሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና
ውጤት እንዲሁም የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና ውጤት ደግሞ
ለየብቻቸው ተነጻጽረው በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይና በመደበኛ ልይይት)፣ የጉልህነት ደረጃውን ለማወቅ
በዳግም ልኬት ቲ- ቴስት ተሰልቷል፡፡

~ 22 ~
ምዕራፍ አራት:- የጥናቱ ውጤት ትንተናና ማብራሪያ

4.1 የውጤት ትንተና


ጥናቱ አላማ አድርጎ የተነሳው በስነጽሁፍ ቴክሰት ገጸባህርይተኮር ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት
ችሎታ ለማጎልበት የሚኖረውን አስተዋጾ መመርመር ነው፡፡ ይህን ለማሳካት በፈተና በተሰበሰበው መረጃ
በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይ ተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የአንብቦ
መረዳት ችሎታ ምን ያህል ያጎለብታል? የሚለውን መሰረታዊ የምርምሩ ጥያቄ ለመመለስ የመረጃው ውጤት
በገላጭ ስታትስቲክስ በአማካይ፣በመደበኛ ልይይት፣በነጻ ናሙና ቲ- ቴስትና በዳግም ልኬት ቲ-ቴስት
ተተንትኗል፡፡ ውጤቱም ቀጥሎ በቀረቡት ሰንጠረዦች ቀርቧል፡፡

የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመ ትምህርትና ድህረ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ንጽጽር በነጻ
ናሙና ቲ-ቴስት

ሠንጠረዥ 4. 1፡- የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ዉጤት ንጽጽር በነጻ
ናሙና ቲ- ቴስት

ቡድን ናሙና አማካይ መደበኛ የቲ ዋጋ የነፃነት ደረጃ የጉልህነት


ልይይት ደረጃ
የሙከራ 40 17.1 3.225 .028 80 .978
የቁጥጥር 42 17.119 3.006
P< 0.05
ከላይ ያለው ሰንጠረዥ የሚያሳየው በሙከራና በቁጥጥር ቡድኑ ቅድመ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
ውጤት ያለውን ልዩነት በአማካይ፣በመደበኛ ልይይትና የልዩነታቸውን የጉልህነት ደረጃ በነጻ ናሙና ቲ- ቴስት
ስሌት ነው፡፡

በሰንጠረዡ ከሰፈረው ገላጭ ስታትስቲክስ መረዳት እንደሚቻለው የሙከራ ቡድኑ ቅድመ ትምህርት ፈተና
አማካይ ውጤት (አማካይ=17.1)፣ከቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት
(አማካይ=17.119) በ (አማካይ=0.019) አንሶ ይታያል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ያስመዘገቡት ውጤት ከአማካይ
ውጤቱ በአማካይ ያለው ልዩነት ሲታይ የሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=3.226)
ከቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=3.006) በ (0.22) በልጦ ተገኝቷል፡፡ ይህም
የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤት ከሙከራ ቡድኑ የቅድመትምህርት ፈተና ውጤት ከአማካይ
በአማካይ ያለው ርቀት የጠበበ መሆኑን ያመለክታል፡፡

~ 23 ~
በዚሁ ሰንጠረዥ እንደታየው የተሳታፊ ተማሪዎች ማለትም የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመ ትምህርት
ፈተና አማካይ ውጤት ልዩነት ይታይበታል፡፡ በዚህም የተነሳ ልዩነቱ ጉልህ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ
መረጃው በነጻ ናሙና ቲ- ቴስት ተሰልቶ (t(80)=.028, p=.978) ሆኗል፡፡ ይህም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ
ልዩነት የሌለ መሆኑን ያሳያል፡፡

የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና ውጤት በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ስሌት ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 4. 2፡- የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ድህረ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ዉጤት ንጽጽር በነጻ
ናሙና ቲ- ቴስት

ቡድን ናሙና አማካይ መደበኛ የቲ ዋጋ የነፃነት ደረጃ የጉልህነት


ልይይት ደረጃ
የሙከራ 40 23.95 2.511 10.354 80 .001
የቁጥጥር 42 17.76 2.895
P<0.05

ሰንጠረዥ 4.2 በሙከራና በቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት መካከል ያለውን
ልዩነት በገላጭ ስታትስቲክስ (በአማካይ፣በመደበኛ ልይይት)ና የልዩነታቸውን የጉልህነት ደረጃ በነጻ ናሙና ቲ-
ቴስት ያሳያል፡፡ ከሰንጠረዡ ገላጭ ስታትስቲክስ መረጃ መረዳት እንደሚቻለው የሙከራ ቡድኑ ድህረትምህርት
የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤት (አማካይ=23.95)፣ ከቁጥጥር ቡድኑ አማካይ ውጤት
(አማካይ=17.76) በ(6.19) በልጦ ይታያል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ያስመዘገቡት ውጤት ከአማካይ ውጤቱ
በአማካይ ያለው ልዩነት ሲታይ የሙከራ ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=2.511) ከቁጥጥር
ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=2.895) በ(0.384)አንሶ ተገኝቷል፡፡ ይህ የሙከራ ቡድኑ
በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ተማሪዎች ከተማሩ በኋላ የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት
ችሎታ ፈተና ውጤት ከአማካይ ውጤት በአማካይ ያለው ርቀት የጠበበ መሆኑን ያሳያል፡፡

ሰንጠረዥ 4.2 እንደሚያሳየው የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት
በአማካይ የሰፋ ልዩነት ይታይበታል፡፡ ልዩነቱ ጉልህ መሆንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ መረጃው በነጻ ናሙና ቲ-
ቴስት ሲሰላ (t(80)=10.354, p=.001) ነው፡፡የጉልህነት ደረጃው ከመቁረጫ ነጥቡ (p < 0.05) ያሳየ ሲሆን የቲ-
ዋጋ ከቲ-የሰንጠረዥ ዋጋ በልጦ ተገኝቷል፡፡ ይህም በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ ልዩነት ያለ መሆኑን
ያመለክታል፡፡

የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና ውጤት እንዲሁም የሙከራ ቡድኑ
ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና ውጤት ንጽጽር በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት

~ 24 ~
ሠንጠረዥ 4. 3፡- የቁጥጥር ቡድን ቅድመ ትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረ ትምህርት ፈተና ዉጤት ንጽጽር በዳግም
ልኬት ናሙና ቲ- ቴስት

የቁጥጥር ቡድን ናሙና አማካይ መደበኛ የቲ ዋጋ የነፃነት የጉልህነት


ልይይት ደረጃ ደረጃ
ቅድመ ትምህርት ፈተና ውጤት 42 17.119 3.00 1.182 41 .066
ድህረ ትምህርት ፈተና ውጤት 17.761 2.89
P<0.05

ከላይ ከሰንጠረዡ እንደሚታየው የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
ውጤት ያለውን ልዩነት ለማነጻጸር በአማካይ፣ በመደበኛ ልይይትና የልዩነታቸውን የጉልህነት ደረጃ በዳግም
ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ስሌት ነው፡፡ በሰንጠረዡ ከሰፈረው ገላጭ ስታትስቲክስ መረዳት እንደሚቻለው
የቁጥጥር ቡድኑ ድህረ ትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤት (አማካይ=17.761)
ከቅድመትምህርት ፈተናው አማካይ ውጤት (አማካይ=17.119) በ (0.642) በልጦ ይገኛል፡፡ የጥናቱ
ተሳታፊዎች ያስመዘገቡት ውጤት ከአማካይ ውጤቱ በአማካይ ያለው ልዩነት ሲታይ የቁጥጥር ቡድኑ የድህረ
ትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=2.89) ከቅድመትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=3.00) በ (0.11)
አንሶ ይገኛል፡፡ በዚህ ሰንጠረዥ እንደተመለከተው የቁጥጥር ቡድኑ ድህረ ትምህርትና ቅድመትምህርት ፈተና
ውጤት መካከል ያለው ልዩነት የጎላ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥም መረጃው በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት
ሲሰላ (t)41=1.182, p=.066) ሆኖ በመገኘቱ የቁጥጥር ቡድኑ በቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ፈተናዎች
መካከል ጉልህ ልዩነት የሌለው መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ይህም የቁጥጥር ቡድኑ የድህረትምህርት ፈተና
ውጤት ከቅድመትምህርት ፈተና ውጤት ጋር ያለው ልዩነት ተቀራራቢ መሆኑን ያሳያል፡፡ ማለትም
እንደልዩነት አይቆጠርም፡፡

የሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና ድህረትምህርት ፈተና ውጤት ንጽጽር በዳግም ልኬት ናሙና
ቲ-ቴስት ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 4. 4፡- የሙከራ ቡድን ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ዉጤት ንጽጽር
በዳግም ልኬት ቲ-ቴስት

የሙከራ ቡድን ናሙና አማካይ መደበኛ የቲ ዋጋ የነፃነት የጉልህነት


ልይይት ደረጃ ደረጃ
ቅድመ ትምህርት ፈተና ውጤት 17.1 3.225 10.787 39 .001
ድህረ ትምህርት ፈተና ውጤት 40 23.95 2.511
P<0.05

~ 25 ~
በሰንጠረዥ 4.4 እንደሚታየው የሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
ውጤት ያለውን ልዩነት ለማነጻጸር በገላጭ ስታትስቲክስ በአማካኝ መደበኛ ልይይትና የልዩነታቸውን
የጉልህነት ደረጃ በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ስሌት ነው፡፡ ከሰንጠረዡ ገላጭ ስታትስቲክስ መረዳት
እንደሚቻለው የሙከራ ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና አማካይውጤት (አማካይ=23.95) ከቅድመትምህርት
ፈተናው አማካይ ውጤት (አማካይ=17.1) በ(6.85) በልጦ ይገኛል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች ያስመዘገቡት ውጤት
ከአማካይ ውጤቱ በአማካይ ያለው ልዩነት ሲታይ የሙከራ ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት
(sd=2.511) ከሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና መደበኛ ልይይት (sd=3.225) በ (0.714) አንሶ ይገኛል፡፡
ከሰንጠረዡ እንደሚታየው የሙከራ ቡድኑ የድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ከቅድመ ትምህርት ፈተና
በአማካይ ውጤት ሰፊ ልዩነት ታይቶበታል፡፡ በመሆኑም ልዩነቱ ጉልህ መሆንና አለመሆኑን ለማረጋገጥ መረጃው
በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ስሌት ሲሰላ (t(39)=10.787, p=.001) ሆኗል፡፡ ይህም በቅድመትምህርትና
ድህረትምህርት ፈተናዎች መካከል ጉልህ ልዩነት ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይህም የሙከራ ቡድኑ በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ ተማሪዎች ከተማሩ በኋላ
የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ፈተና ውጤት የተሻሻለ መሆኑን ያሳያል፡፡

የትንተናውን ውጤት መሰረት በማድረግ ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን


የአንብቦ መረዳት ችሎታ ያጎለብት ይሆን? የሚለው መሰረታዊ ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ አግኝቷል፡፡
ምክንያቱም የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ በቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ጉልህ ልዩነት
አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን በድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት በሁለቱ ቡድኖች መካከል ጉልህ
የሆነ ልዩነት ታይቷል፡፡ ማለትም በሙከራ ቡድኑ የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል
ታይቷል፡፡

4.2 የውጤት ማብራሪያ


በውጤት ትንተናው የታየው በስነጽሁፍ ቴክስት፤ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የአንብቦ
መረዳት ችሎታ ለማጎልበት የሚኖረውን አስተዋጾ መመርመር ነው፡፡ ስለሆነም በአንብቦ መረዳት ፈተና
የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ ስታትስቲክስ ተተንትነው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የሙከራ ቡድኑና የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት ፈተና ውጤትና የሙከራ ቡድኑና የቁጥጥር ቡድኑ
ድህረትምህርት ፈተና ውጤት በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት ሰሌት ፡፡

በመጀመሪያ የታየው የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ንጽጽር
ነው፡፡ በዚህ ንጽጽርም የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ በቅድመትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት (በሰንጠረዥ 4.1)
በጣም ተቀራራቢ ሆኖ ስለተገኘና ጉልህ ልዩነት የማይታይበት በመሆኑ ሁለቱም ቡድኖች ተቀራራቢ የሆነ

~ 26 ~
ውጤት ማስመዝገባቸውን ለማየት ተችሏል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት በሁለቱም ቡድኖች መካከል ምንም
አይነት የማስተማር ልዩነት ሳይፈጠር በመቅረቱ ነው፡፡

በሰንጠረዥ 4.2 የሙከራና የቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ንጽጽር
እንደሚያመለክተው በሁለቱ ቡድኖች መካከል ባለው የፈተና ውጤት ከፍተኛ የሆነ ልዩነት እንዳለ የቀረበው
የስታትስቲክስ ስሌት ያመለክታል፡፡ የሙከራ ቡድኑ በስነጽሁፍ ቴክሰት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ
በመማሩ በስነጽሁፍ ቴክስት በተለመደው የአንብቦ መረዳት ማስተማሪያ ዘዴ ሲማር ከቆየው ከቁጥጥር ቡድኑ
የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ውጤቱም ሂል (1986)፣ ቱርከር (1991)፣ ካልቨርት (2004)፣ ቶም
(2008) ከገለጹት በገጸባህሪያትተኮር የማስተማር ዘዴ ቋንቋን ማስተማር ውጤታማ ነው ከሚለው ሃሳብ ጋር
ተስማሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በመቀጠል የታየው በሰንጠረዥ 4.3 የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት
ፈተና ውጤት፤በሰንጠረዥ 4.4 ደግሞ የሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት
ፈተና ውጤቶች ለየብቻ በዳግም ልኬት ናሙና ቲ-ቴስት ተነጻጽረው ቀርበዋል፡፡ የቁጥጥር ቡድኑ
ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ልዩነቱ ተቀራራቢ ሲሆን የሙከራ ቡድኑ
ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት ከቅድመትምህርት ፈተና ውጤት በአማካይ በልጦ ተገኝቷል፡፡
በልጦ የተገኘው የድህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት በስታትስቲክስ ጉልህ (p < 0.05) ሆኖ መገኘቱ
ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታን ያሻሻለ መሆኑን አመላክቷል፡፡

በጥናቱ ውጤት መሰረት አንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ መሻሻል የታየው ለገጸባህርይተኮር ዘዴማስተማሪያነት
የቀረቡ ቴክስቶች የገጸባህርያትን እንቅስቃሴ ፣መልክ፣ተክለሰውነት፣ባህርይና አመለካከት በትኩረት እንዲገነዘቡ
የሚያደርጉና በጽሁፍ ውስጥ ያለን መረጃ መረዳት የሚያስችሉ በመሆናቸው ተማሪዎችን ለዚህ ውጤት
አብቅቷቸዋል ለማለት ያስችላል፡፡

ጠቅለል ባለ መልኩ የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያመለክተው በስነጽሁፍ ቴክስተ ገጸባህርይ ተኮር የማስተማር
ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት ጉልህ ሚና አለው፡፡ ይህም በሙከራና በቁጥጥር ቡድኑ
ድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤትና በሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት
የአንብቦ መረዳት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል በስታትስቲክስ ጉልህ ልዩነት ታይቷል፡፡ ስለዚህ ይህ ጥናት
በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይ ተኮር የማስተማር ዘዴ አንብቦ የመረዳት ችሎታን ለማሻሻል አዎንታዊ ምላሽ
አለው የሚል አንድምታ ይኖረዋል፡፡ ለዚህም የሙከራ ቡድኑ ብቻ የድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
አማካይ ውጤት በስታትስቲክስ ጉልህ ሆኖ መታየቱ አስረጅ ነው፡፡

~ 27 ~
ምዕራፍ አምስት፡- ማጠቃለያ፣መደምደሚያና መፍትሄ

5.1 ማጠቃለያ
የጥናቱ ዋና አላማ በስነጽሁፍ ቴክስት፤ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ
በማጎልበት ረገድ የሚኖረውን አስተዋጾ መመርመር ሲሆን በጥናቱም ምላሽ ሊሰጥበት የታለመው መሰረታዊ
ጥያቄ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን የአንብቦ
መረዳት ችሎታ ምን ያህል ያጎለብታል? የሚል ነው፡፡

በጥናቱ የተሳተፉትም በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን በደጋ ዳሞት ወረዳ በፈረስ ቤት አጠቃላይ ሁለተኛና
የከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርትቤት በ 2011 ዓመተ ምህረት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ያሉ
የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዚህ የክፍል ደረጃ ከሚገኙ 39 የመማሪያ ክፍሎች መካከል በእድል ሰጭ
ናሙና የተመረጡት የዘጠነኛ ምድብ 2 ክፍል ተማሪዎች የሙከራ የዘጠነኛ ምድብ 28 ክፍል ተማሪዎች የቁጥጥር
ሲሆኑ የጥናቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያም ፈተና ነው፡፡

የክፍል ደረጃውንና መርሃ ትምህርቱን መሰረት ያደረገ በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር አቀራረብ ላይ ያተኮረ
ቴክስት የተዘጋጀ ሲሆን ከልብ ወለዱ በተወሰደው ምንባብ ውስጥ የተካተቱ ገጸባህርያት ምን አሰቡ? ምን
ተሰማቸው? ምን ሰሩ? አንድን ነገር ለምን በዚህ መንገድ ሰሩ? በማለት የምንባቡን መልክት ለመተንተን
የሚያስችሉ እንዲሁም የገጸባህርያትን መልክ፣ተክለሰውነት፣ባህርይና አመለካከት መለየት የሚያስችሉ ቴክስቶች
ተዘጋጅተው ስራላይ ውለዋል፡፡

የጥናቱ ተሳታፊዎችም በተዘጋጀላቸው ቴክስት ከመማራቸው በፊት ቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
በትምህርትቤቱ የቋንቋ መምህራንና በጥናቱ አማካሪ ማስተካከያ ታክሎበትና የጥናቱ ተሳታፊ ባልሆኑ 20
ተማሪዎች ላይ በሙከራ ጥናት ተፈትሾ አስተማማኝ ሆኖ በመገኘቱ የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ
ለመለካት ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በመቀጠልም ለማስተማሪያነት በተዘጋጀው ቴክስት ለአራት ሳምንት ከተማሩ በኋላ
ከቅድመትምህርት ፈተና ጋር ተመሳሳይ የሆነ የድህረትምህርት ፈተና ተግባራዊ በማድረግ ለጥናቱ የሚፈለገው
መረጃ ተሰብስቧል፡፡

በፈተና አማካኝነት የተሰበሰበውን መረጃ መሰረት በማድረግ ስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ
የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት ያለው አሰተዋጾ ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ መረጃው
በአማካይ፣በመደበኛ ልይይት፣ በነጻ ናሙና ቲ- ቴስትና በዳግም ልኬት ቲ- ቴስት ተተንትኗል፡፡ በዚህም በሙከራ
ቡድኑ ድህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤትና በቁጥጥር ቡድኑ ድህረትምህርት አማካይ ውጤት መካከልና
በሙከራ ቡድኑ ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ፈተና አማካይ ውጤት መካከል በስታቲስቲክስ (p< 0.05)

~ 28 ~
ጉልህ ልዩነት በመታየቱና የቲ-ዋጋ ከ ቲ-የሰንጠረዥ ዋጋ በልጦ በመገኘቱ ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የአንብቦ
መረዳት ችሎታን እንደሚያጎለብት ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ የጥናቱ ትንተና ውጤት የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለማጎልበት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴን
መሰረት ያደረገ ቢሆንና ለተማሪዎች የሚቀርቡ ቴክስቶችም የገጸባህርይተኮር አቀራረብን መሰረት አድርገው
ቢዘጋጁ የተሻለ ውጤት ሊገኝ እንደሚችል ጥናቱ ያመላክታል፡፡

5.2 መደምደሚያ
የጥናቱን ውጤትና ማብራሪያ መሰረት በማድረግ የሚከተለው መደምደሚያ ተሰጥቷል፡፡ በስነጸሁፍ
ቴክስት፤ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማጎልበት ጉልህ ሚና አለው፡፡
ይህም በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን
ለማጎልበት አዎንታዊ ሚና አለው የሚል ነው፡፡

5.3 መፍትሔ
በጥናቱ የተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማጎልበት የሚከተሉት የመፍትሄ ሃሳቦች ተጠቁመዋል፡፡

1. የቋንቋ መማሪያ መጽሃፍትን የሚያዘጋጁ ባለሙያዎች ስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር አቀራረብን መሰረት
አድርገው ቴክስቶችን ቢያዘጋጁ፡፡
2. መምህራን በስነጽሁፍ ቴክስት፤ ገጸባህርይተኮር የማስተማሪያ ዘዴ ለአንብቦ መረዳት ችሎታ መጎልበት
ያለውን አስተዋጾ በመገንዘብ በገጸባህርይተኮር የማስተማሪያ ዘዴ ቢያስተምሩ፤ ተማሪዎችም በሚያነቡበት
ጊዜ የገጸባህርያትን እንቅስቃሴና አመለካከት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥተው ቢያነቡ፡፡
3. ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴን ለአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያነት በመጠቀም ረገድ ለአማርኛ ቋንቋ
መምህራን ስልጠና ቢሰጥ፡፡
4. በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ በተማሪዎች መማሪያ
መጽሃፍ ውስጥ በምን ያህል መጠን መዘጋጀት እንዳለበት ቀጣይ ጥናት በስፋት ቢካሄድ የተሻለ ሆኖ ሊተገበር
ይችላል፡፡

~ 29 ~
ዋቢዎች
ሀዲስ አለማየሁ፡፡ (1958)፡፡ፍቅር እስከመቃብር፡፡ አዲስ አበባ፤ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት፡፡

መሰረት ሀሰን፡፡ (2007)፡፡ በአንካሻ ወረዳ በሚገኙ አጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማንበብ ክሒል
ትምህርት አቀራረብ ቅኝት፡፡ ባህር ዳር ዩዩኒቨርሲቲ( ያልታተመ)፡፡

ማረው ዓለሙ፡፡(1998)፡፡ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ፡፡ አዲስ አበባ፤ብርሐንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፡፡

በዓሉ ግርማ፡፡ (1962)፡፡ ከአድማስ ባሻገር፡፡ አዲስ አበባ፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡

በድሉ ዋቅጅራ፡፡ (1988)፡፡ ተሳታፊነት፣ ጭምትነት ሰብዕና አይነት ከድርሰት መጻፍና አንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ፡፡ አዲስ አበባ
ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ትምህርት ቤት ( ያልታተመ)፡፡

በድሉ ዋቅጅራ፡፡ (1996)፡፡ በስነ ጽሁፍ ቋንቋን ማስተማር፡፡ አዲስ አበባ፤ንግድ ማተሚያ ድርጅት.

ተሾመ ፎርሲዶ፡፡ (1997)፡፡ ከንባታና ጠንባሮ ዞን የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስረኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ አንብቦ መረዳት
ችሎታና የማንበብ ፍጥነት፡፡ ለድህረ ምረቃ ቴሲስ፣ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ያልታተመ).

ታደሰ ሊበን፡፡ (1952)፡፡ ሌላው መንገድ፡፡ አዲስ አበባ፤ ንግድ ማተሚያ ቤት.

ታፈረ ወርቁ፡፡ (2000)፡፡ በዳንግላ ከፍተኛ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የማንበብ ዳራና የአንብቦ መረዳት ችሎታ፡፡ ባር ዳር
ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ ጸሁፍ (ያልታተመ)፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር፡፡ (1997)፡፡ ዘጠነኛ ክፍል የተማሪው መጽሐፍ፡፡ አዲስ አበባ፤ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት፡፡

እንዳልክ ፀጋው፡፡ (2010)፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሁፍ ቴክስት ይዘት ተኮር የማስተማር ዘዴ አንብቦ መረዳትንና የማንበብ
ተነሳሽነትን ለማጎልበት ያለው አስተዋጽኦ፡፡ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ( ያልታተመ)፡፡

ወርቁ አለሙ፡፡ (2000)፡፡ የስነ-ጽሁፍ ለአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያነት አተገባበር፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ( ያልታተመ)

ዘመንፈስ ባራኪ፡፡ (1991)፡፡ በስነ-ጽሁፍ አማካኝነት አማርኛ ቋንቋን በማስተማር የአጭር ልቦለድ ሚና፡፡ አድስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ያለው እንዳወቀ፡፡ (1998)፡፡ የምርምር መሰረታዊ መርሆዎችና አተገባበር፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ 3 ኛ እትም፡፡

ደረጀ በቀለ፡፡ (1988)፡፡ ህያው ፍቅር፡፡ አዲስ አበባ፤ ሜጋ ኪነ ጥበባት ማእከል፡፡

ደበበ ሀይለጊዮርጊስ፡፡ (1999)፡፡ ቅድመ ኮሌጅ አማርኛ፡፡ አዲስ አበባ፤ አስቴር ነጋ አሳታሚ ድርጅት፡፡

ፈቃደ አዘዘ፡፡ (1991)፡፡ አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አላማዎች ስለ መማሪያ መጽሐፍትና ስነ ጽሁፍ
ሚና በቋንቋ ትምህርት ከ 1944- 1983 ለቋንቋ ጥናት ተቋም 9 ኛ ዓመታዊ ሴሚናር የቀረበ፤ አ.አ.ዩ.፡፡

ፈቃደ አዘዘ፡፡ (1991)፡፡ የስነቃል መመሪያ፡፡ አዲስ አበባ፤ አልፋ አሳታሚዎች፡፡

Abebe, B. (2017). the effect of short stories on students reading comprehension skills. bahirdar university.

Alkedir, M. (2005). The Role of Literature in Promoting University Self Reliance . Alquads open university.

Atkins.Jone,Hilom Bente Yirga and Nuru Mohamed. (1996). In skills Development Methdology. Addis Abeba:
Addis Abeba printing Press.

~ 30 ~
Bintiz, W. (1997). Exploring Reading Night Mares of Middle and Secondary School. Teacher's Jornal of
Adolescent and Adult literary 411, 23-24.

Bloc, C. (1997). In Teaching the Language Art expanding Thinking Through Student Center Instruction. Bosten:
Allyn and Bacon.

Brumfit. (1986). Literature and Language Teaching. Oxford: Oxford University Press.

Brumfit,C & Carter, R.A. (1986). In literature and language teaching. Oxford: Oxford University Press.

Brumfit,c.j.& r.a.carter. (2000). literature and language teaching. oxfored: oxfored university press.

Calvert, L. (2004). A Teaching Guide to theSignet Classics. edition of Charles Dikness great expectation.
pengun group USA.

Carter,R and Long, M. (1991). Teaching Literature. Harlow,UK: Longman.

Colie,J and Slater,S. (1990). literature in language classroom: A resource book of ideas and Activates. Campige
university press.

Collien,J & Slater,S. (1987). Literature in Language Class Room. Cambredge University Press.

Conely, M. (1992). in Content Reading Instruction Communication Approch. Mc Graw-Hill inc.

Cruh, J. (2010). The role of Literature and Cuiture in English Language teaching. Retrieved from hiip://
www.relinegustica,oza.uam.ma/no 007/no07 artog.htm/.

DowdayJ.K and Kaplan,S. (2010). Teaching in drama in class room. Fransisco D.A: Roterdam sense publisher.

FuadHarunOsman. (2008). The practice of Employing Literary Texts in EFL learning & its role in Fostering
Reading Skill. Bahir dar university.

Gladys, I. (2011). Instructional Stratgies in Primery Schools in Ibadan Worth Local Government Area: an
Emprical Investigation of the Effect on Children Basic Reading and Comprehension Skill . African
Jornal of Education Technology (Volume number One, 1-14.

Graham. (1987). Contention of Meaningt Reading and The Reac. English Teaching Forume, 78-99.

Hill, J. (1986). Using Literature in Language Teaching. London: Macmillan Publishers Ltd.

Hyland, K. (1990). Purposes and Strategy Teaching Extensive Reading Skills. English Teachinf Forum XXVIII (2),
14-17.

Khatib. (2013). English Language Teaacher Motivation in Srilanka Public Scools. Jornal of Language Teaching
Research Vol 4, no 1, 1769-1798.

Kitab, M. (2013). Short Story Based Laguage Class room? International Jornal of Basic Scince and Educational
Technology.

Lazar, G. (1993). Literature and Language Teaching. Cambridge: Cambridge University Press.
~ 31 ~
Long, C. (1991). Teaching Literature. London: Rutiedje.

long, carter ronaled and mich ael . n. (1991). teaching literature. london: Rutl edje.

Lumquinga, P. (2012). The Use of Graphic Organizers to Improve Reading Comprehension Skills With Students
of 1-2 Intensive Course ot Espe. Unpublished Master Thsis, Sangolq Ui Ecuador.

Macky.S. (1986). "Literature in Language Class room" Literature and Language Teaching. Hong Kond:
Educational Law- Peiced Book Scheme with Oxford University Press.

Maclory, S. (1983). The Language Teacher 37.5.

maclory, simon babby tarra. (2013). the language teacher 37.5.

Madson, M. (1983). Teachique in Testing. New York: Oxford University Press.

Mally, A. (2010). Literature & Language Class Room .R.Carter & D.Nunan.

mcrae, j. (1991). lierature with a small 1 . basing stoke: MEP macmillan.

Palani, K. (2012). Promising Reading Habits and Creating Literate Social. International Reference Research
Journal Vol.III Issue 2(1), PP91.

Parkinson,B and Reid Thomas,H. (2000). Teaching literatrure in a second language. Edinbergh: Edinbergh
university press.

Pavey, J. (1972). Litrature in TESL Programs, Language and Culture. New York: Mc.Graw HILL.

Poorahmadi, M. (2012). Investigating the Efficiency of Task Based Instruction in Improving Reading
Comprehension Ability . Islamic Azad University.

Sage, G. (1975). In Incorporating literature in ESL Instruction . UpperSaddle River: NJ: Prentice Hall.

Santhi, T. (2012). Teaching language through literature. journal of English & literature (JEL) Vol.2 issue2.

Scott, C. (1964). Literature and the ESL Program. The Modern Language Jornal 48, 489-493.

shang, h. (2006). content based instruction in the EFL literature curiculum . the internate TESL jornal
vol.xii,No11 http// llitesu.org/techniques/ shange cvl,htm/.

Smith,M and Jffey,D. (2010). Fresh Task on Teaching Literary Elements.

Thom, N. (2008). Using Literary texts in Language Teaching . VNU Jornal of Scince Foregn Language V.24, 120.

Turker, F. (1991). Using Literture in language teaching. hacettp University dergessis say, 6/299-305.

Ur.p. (1991). A Course in Language Teaching . Cambrige: Cambrige University Press.

Vera, J. (1991). Literature as Study & Resource, The purpose of English Literature teaching at University Level.
Revista Aliclntrna English Malaysia University.

~ 32 ~
~ 33 ~
አባሪዎች

አባሪ ሀ. የቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና


በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤ በስነጽሁፍ ቴክሰተ ገጸባህርይተኮር ዘዴ ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታን
የማጎልበት ሚና በሚል ርዕስ ለተካሄደው ምርምር መረጃ እንዲያስገኝ ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ
የአማርኛ ቋንቋ ቅድመትምህርት ፈተና ከ ( 30 %)

መለያ ቁጥር---------------ክፍል---------------ሴክሽን---------------------

የፈተናው መነሻ ስዓት 3፡00

ለፈተናው የተሰጠው ጊዜ 1፡30

አጠቃላይ መመሪያ

ይህ ፈተና የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለመለካት የቀረበ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በቀረበው የምንባብ ሀሳብ
መሰረት የሚመለሱ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡ምንባቡን በጥንቃቄ በማንበብ ለያንዳንዱ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ
በመምረጥ መልስ መስጫ ወረቀት ላይ አስፍሩ፡፡

ምንባብ

ሐይለማርያም ብርሐን የሌለበት ቤት ደስ ስለማይለው እንግዳ ቤት ውስጥ የነበሩትን መብራቶች ሁሉ አብርቷል፡፡ ግድግዳው
ላይ ያለው ስእልም ሆነ ምንጣፍ ሶፋዎቹና የመስኮት መጋረጃዎቹ በብርሐን አማካኝነት ህያው ሆነዋል፡፡ መብራቶቹ የእሱንም
ሁኔታ ጭምር አጉልተው ያሳያሉ፡፡

ጽልመት የመሰለው ጸጉሩ አድጎ ጎፍሯል፡፡ የሶስት ወይም የአራት ቀን እድሜ ያለው ጺሙ፣ ጉንጮቹና አራት ማእዘን አገጩ
ላይ ሲታይ አጥንት ላይ የሚተራመስ ጉንዳን ይመስላል፡፡ ጠይም ፊቱ ላይ ስጋ አይታይም ጉንጮቹ ላይ ያሉት አጥንቶች
እንደአለት ቆመው ሰው ላይ ያፈጣሉ፡፡ ድፍጥፍጥ ብሎ ወርዶ ቀዳዳዎቹ ሰፋፊ የሆኑትን አፍንጫውን እንደወናፍ ዝቅ እያደረገ
ወፍራም ከንፈሮቹን ገጥሞ ከማንበብ ብዛት የተነሳ ደካክመው የቀሉትን መካከለኛ አይኖቹን ውልብልብ እያደረገ ያነባል፡፡

ሐይለማርያም መጽሐፍ ከእጁ ወይም ከኪሱ አይገኝም ማለት ዘበት ነው፡፡ ከመጽሐፍ ጋር አብሮ ውሎ አድሮ አብሮ ከእንቅልፉ
ይነሳል፡፡ በቀኝ እጁ መጽሐፍ ይዞ እንደሆነ ከግራ እጁ የተቀጣጠለ ሲጃራ ይታጣል ብሎ የሚወራረድ የለም፡፡ የተቀጣጠለ ሲጃራ
የተዘረጋ መጽሐፍና አንድ ብርጭቆ ውስኪ የልብ ጓደኞቼ ናቸው፣ ከእነርሱ ጋር ስሆን እዝናናለሁ ይላል፡፡

ሐይለማርያም የሚጠላው ነገር ቢኖር ሐሳቡን የሚገታ ደንቃራ ሲመጣበት በመሆኑ የአበራ ታላቅ ወንድም አቶ አባተ ወርቁ
ሲገቡ በፈገግታ አልተቀበላቸውም ፡፡ ‹‹ አበራ የለም እንዴ ?›› ብለው ኮስተር ባለ ድምጽ ጠየቁት፡፡ ጎሪጥ አይኖቻቸው ያረፉት
በውስኪ ብርጭቆ ላይ ነው፡፡ እድሜ ባያበልዛቸውና ቅንድቦቻቸው ባይረግፉ አይኖቻቸው ያበራን ውብ አይኖች ይመስላሉ፡፡
የኑሮ ትግል ባያስከስላቸው እንደወንድማቸው የቀይ ዳማ ናቸው፡፡ ከቦርጫቸው ይሁን ከአለባበሳቸው አጭር መስለው

~ 34 ~
ይታያሉ፡፡ የለበሱት ከታች ካኪ ሱሪ፣ ከላይ ጥቁር የሱፍ ኮት ነው፡፡ በዚያ ላይ ቀጭን በጥቁር ጥለት የታጠረች ኩታ ደርበዋል፡፡
ነጭ ኩታዋና ጥቁር ጥለቱ ሽበት ጣል ጣል ካለበት ጠጉራቸው ጋር በአንድነት ሲታዩ አንድ አይነት ህብረ ቀለም ይፈጥራሉ፡፡
ፊታቸው ላይ ጎልተው በሚታዩት መስመሮች ላይ ከእድሜ የቀሰሙት እውቀት ተጽፎ ይነበባል፡፡ እንደአበራ ፊት ወጣትነት
ብቻ ያለበት ባዶ ፊት አይደለም፡፡ እነዚያ መስመሮችና እነዚያ እሳታቸው ጠፍቶ ረመጣቸው ብቻ የቀሩ አይኖች ስላሳለፉት
ደስታም ሆነ ሐዘን በዝምታ ያንጎራጉራሉ፡፡

ሐይለማርያም ትኩር ብሎ ፊትለፊት ሰው የመመልከት ልምድ አለው፡፡ ሰው ፊት ላይ ብልጭ ድርግም የሚለው ፈገግታ
ከውስጥ መንጭቶ ወጥቶ የሚነበበው ሐዘንና ደስታ ዘመን እያለፈ ሲሄድ ተጽፈው የሚቀሩት መስመሮች እንደ ጥሩ መጽሐፍ
ያስደስቱታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሰዎችን ፊት ትኩር ብሎ በተመሰጠ አእምሮ ሲመለከት የሚሉትን ሳይሰማ የሚቀርበት ጊዜ
አለ፡፡ በአገኙት ቁጥር በቁጣ ደማቸው የሚለወጥበት ምክንያት ሊገባው አልቻለም፡፡

ዝምታ ቤቱን ዋጠው የአቶ አባተ ዝምታ ይሁን ወይም የአየሩ ቅዝቃዜ ሐይለማርያምን ብርድ ተሰማው፡፡ ረጃጅም
ቅልጥሞቹን ሰብስቦ እንደግመሮ ዝንጀሮ እጆች ከጉልበት በታች የሚውሉትን እጆቹን አጣምሮ ቁጭ ካለበት ሶፋ ላይ
ተመቻችቶ ተቀመጠ፡፡ ሐይለማርያም የሚለውን ነገር ለመፈለግ የአእምሮውን ጓዳ ሲፈትሽ አቶ አባተ የተሰጡትን ውስኪ
እፉት ብለው ካጣጣሙ በኋላ ቀድመውት ከአበራ ጋር ከተዋወቃችሁ ስንት ዘመን ይሆናል ብለው ጎሪጥ አይኖቻቸውን ጣራው
ላይ አሳርፈው ኮስተር ባለ ድምጽ ጠየቁት፡፡ ዱብዳ ነበር፡፡ ለምን ይህን ጥያቄ እንዳቀረቡለት ወይም ጥያቄው ምን አቅጣጫ
እንደሚይዝ ባይገባውም ዘመኑን ለማስታወስ ሲያሰላስል አበራ ከዚህ ቀደም ወንድሜ በኔና ባንተ ጓደኝነት በጣም ይቀናል፤
አጥፊየ አንተ ነህ ብሎ ስለሚያምን ሁለተኛ አንተን እንዳላይ ባገኘኝ ቁጥር ይመክረኛል፡፡ ብሎ የነገረው ትዝ አለውና የጎፈረ
ጸጉሩ ውስጥ ከፍሎ ወደኋላ ካበጠረው በኋላ ሲጃራ አውጥቶ አቀጣጠለ ጉረሮውን አሰላና በግምት ሀያ አመት ይሆናል አላቸው
፡፡

(ምንጭ፡- በአሉ ግርማ (1962) ከአድማስ ባሻገር ለፈተና እንዲመች ሆኖ ተሻሽሎ የተወሰደ )

መመሪያ ፡- ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ
ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. አቶ አባተና ወንድማቸው የሚመሳሰሉት በምንድን ነው?
ሀ. በጉስቁልናቸው ለ. በአለባበሳቸው ሐ. መጠጥ በመውደዳቸው መ. በመልካቸው

2. ሐይለማሪያም ዱብዳ የሆነበት ነገር ምንድን ነው?


ሀ. የአቶ አባተ መምጣት ለ. የአቶ አባተ ጥያቄ ሐ. የአበራ መቅረት
መ. የአቶ አባተና የአበራ መተዋወቀ

3. ከግመሮ ዝንጀሮ እጆች ጋር የተወዳደረው ምንድን ነው?


ሀ.የሐይለማሪያም እረጃጅም ቅልጥሞች ለ.የአቶ አባተ ቁመና
ሐ.የአቶ አባተ ረጃጅም እግሮች መ.የሐይለማሪያም እጆች
4. ከሚከተሉት ውስጥ የሐይለማሪያም ልዩ ባህሪ የሆነው የቱ ነው?

~ 35 ~
ሀ.ጨለማ ክፍል መውደዱ ለ.ብርሀን የሌለበት ቤት መጥላቱ
ሐ.ሰውን በትኩረት መመልከት አለመውደዱ መ.የንባብ ፍቅር አለመኖሩ

5. ከእድሜ የቀሰሙት እውቀት ተጽፎ ይነበባል የተባለው ምን ላይ ነው?


ሀ.ሐይለማሪያም ከሚያነበው መጽሃፍ ላይ ለ.ወረቀት ላይ
ሐ.በሚያደርጉት ንግግር ላይ መ.ፊት ላይ በሚታዩ መስመሮች ላይ
6. መጽሃፍ ከእጁ ወይም ከኪሱ አይለይም የተባለ ከማን ነው?
ሀ.ከአበራ ለ.ከሐይለማሪያም
ሐ.ከአቶ አባተ መ.ከአቶ ወርቁ
7. አቶ አባተ ወርቁ ከሐይለማሪያም ቤት እንደገቡ ዓይኖቻቸው ያረፉት ምንላይ ነበር?
ሀ. በሚያነበው መጽሃፍ ላይ ለ. በውስኪ ብርጭቆ ላይ

ሐ. በተቀጣጠለው ሲጃራ ላይ መ. በተደረደሩት ወንበሮች ላይ

8. ‹‹ስላሳለፉት ደስታም ሆነ ሃዘን በዝምታ ያንጎራጉራሉ ››የተባሉት ምኖች ናቸው?


ሀ.የሐይለማሪያም ጓደኞች ለ.የአቶ አባተ የፊት ገጽታዎች ሐ.ሐይለማሪያም
የሚያነባቸው መጽሃፎች መ. አቶ አባተ ግንባር ላይ የሚታዩ መስመሮች
9. ‹‹ህያው ሆነዋል›› የተባሉት ምኖች ናቸው?
ሀ. ሰዎች ለ. ሶፋዎችና የመስኮት መጋረጃዎች ሐ ግድግዳው መ. ጣራው

10. ጠይም ፊቱ ላይ ስጋ አይታይም ሲል ምን ማለቱ ነው?


ሀ. በጣም የከሳ ነው ለ. በጣም ጥቁር ነው
ሐ. ፊቱ በጸጉር የተሸፈነ ነው መ. በጣም ቆንጆ ነው
11. የሐይለማርያምን ሁኔታ አጉልተው ያሳያሉ የተባሉት -------------- ናቸው፡፡
ሀ. ምንጣፎች ለ. የመስኮት መጋረጃዎች ሐ. መብራቶች መ.መጽኀፎች
12. አጥንት ላይ በሚተራመስ ጉንዳን የተመሰለው ነገር ------------------- ነው፡፡
ሀ.ጽልመት የመሰለው ጸጉሩ ለ. ጺሙ ሐ. አገጩ መ.ያደገው ጸጉሩ
13. በአንቀጽ ሁለት ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ----------- ነው፡፡
ሀ. የሐይለማርያም አካልና ቁመና በጣም ያማረ እንደሆነ
ለ. የሐይለማርያም የኑሮ ሁኔታ የተመቻቸ መሆኑን
ሐ. የሐይለማርያም አካላዊ ሁኔታ በጣም የተጎሳቆለ መሆኑን
መ. ሐይለማርያም በአነጋገሩ ውብና ማራኪ መሆኑን
14. ሐይለማሪያምን የሚያዝናኑት ነገሮች በቅደም ተከተል የትኞቹ ናቸው?

~ 36 ~
ሀ.ውስኪ፣የተቀጣጠለ ሲጃራና መጽሃፍ ለ. መጽሃፍ፣የተቀጣጠለ ሲጃራና ውስኪ
ሐ.የተቀጣጠለ ሲጃራ፣መጽሃፍና ውስኪ መ. ውስኪና መጽሃፍ
15. አቶ አባተ ወርቁ ወደቤት ሲገባ ሐይለማሪያም በፈገግታ ያልተቀበለበት ምክንያት ምን ነበር?
ሀ. ሀሳቡን ስለሚቀበለው ለ.ጥያቄ ስለሚያበዛበት
ሐ.ሀሳቡን ስለሚገታበት መ.ዝምተኛ ስለሆነ
16. ‹‹ደንቃራ››ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ.አመለካከቱ ጥሩ የሆነ ለ.የማይገባው ሐ.የሚያብራራ መ. መሰናክል
17. የአቶ አባተን አለባበስ አንድ አይነት ህብረ ቀለም እንዲፈጥሩ ያደረጉት------ናቸው፡፡
ሀ. የለበሱት ካኪ ሱሪ ለ. የደረቡት ሱፍ ኮት
ሐ. ነጭ ጥቁር ጥለት ኩታቸው መ. ሸሚዛቸው
18. ከሚከተሉት ውስጥ ስለሐይለማሪያምና ስለአቶአባተ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ.ሁለቱም በጣም የሚዋደዱና የሚግባቡ ሰዎች መሆናቸው
ለ.ሁለቱም ሰዎችን ትኩር ብለው የመመልከት ባህሪ አላቸው
ሐ.ሁለቱም ተግባብተውና ተከባብረው የማይኖሩ ናቸው
መ.ሁለቱም በእድሜ ወጣቶች ናቸው
19. የአንቀጽ አንድ ዝርዝር ሃሳብ የሆነው --------ነው፡፡
ሀ. የሐይለማሪያም ገጽታ በጣም የከሳ መሆኑን መግለጹ
ለ. ሐይለማሪያም ብርሃን የሌለበትን ቦታ እንደማይወድ መግለጹ
ሐ. ሐይለማሪያም መጽሃፍ እንደሚወድ መግለጹ
መ. ሀይለማሪያም የአበራ ጓደኛ መሆኑን መግለጹ
20. የሐይለማሪያም አይኖች የቀሉበት ምክንያት ምንድን ነው ?
ሀ.ከመጠጥ ብዛት ለ.ከማንበብ ብዛት ሐ.ሲጃራ ስለሚጠቀም መ.ሁሉም
21. ከመጽሃፍ ጋርውሎ አድሮ ከእንቅልፉ ይነሳል ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ብዙ ጊዜ ያነባል ማለት ነው ለ. መጽሃፉን እንደ ተራስ ይጠቀምበታል ማለት ነው ሐ . ብዙ
ጊዜ ይተኛል ማለት ነው መ. ማንበብ አይወድም ማለት ነው
22. ሐይለማሪያምንና አቶ አባተን የሚያመሳስላቸው ነገር ምንድን ነው ?
ሀ.ሁለቱም በኑሯቸው ደስተኛ አለመሆናቸው ለ.ሁለቱም ጥሩ ባህሪ ያላቸው መሆናቸው ሐ.ሁለቱም
የአበራ ወንድሞች መሆናቸው መ.ሁለቱም አንባቢ መሆናቸው
23. ‹‹እንደአለት ቁመው ሰውላይ ያፈጣሉ››የተባሉት ነገሮች ምንድን ናቸው ?
ሀ.የአቶ አባተ የእግር አጥንቶች ለ .የሐይለማሪያም የጉንጭ አጥንቶች ሐ.መስኮቶች
መ.የቤቱ መጋረጃዎች

~ 37 ~
24. ባገኙት ቁጥር በቁጣ ደማቸው የሚለወጥበት ምክንያት ሊገባው አልቻለም የተባለው ማን ነው ? ሀ.አበራ
ለ.አቶ አባተ ሐ.ሐይለማሪያም መ.ሁሉም
25. ሐይለማሪያም የአዕምሮውን ጓዳ እንዲፈትሽ የተገደደበት ምክንያት ምን ነበር ?
ሀ.ጉልበቱን አጣምሮ መቀመጡ ለ .ቤቱ በዝምታ ስለተዋጠ መፍትሄ ለመፈለግ ሐ.አበራ
የቀረበትን ምክንያት አለማወቁ መ.ለአየሩ ቅዝቃዜ መንስኤ ለመፈለግ
26. አቶ አባተ የሐይለማርያምንና የአበራን የጓደኝነት ዘመን ማወቅ የፈለጉበት ምክንያት ምን ነበር ? ሀ.ጥሩ ጓደኛ
መሆናቸውን ለማወቅ ለ .አበራ አጥፊየ ይሆናል ብለው ስለሚገምቱ ሐ.አበራን ሊጎዳው ይችላል ብለው
ስለሚያስቡ መ.እንደወንድሙ ስለሚያስበው
27. የአቶ አበራን ቁመት አጭር የሚያስመስላቸው ---------ነው፡፡

ሀ.ሽበት ጣልጣል ያደረገው ጸጉራቸው ለ. አለባበሳቸው


. ሐ. ቀይ ዳማ መልካቸው መ.ወጣትነታቸው

28. ሐይለማሪያም ብርሃን የሌለበት ቤት ደስ ስለማይለው የወሰደው እርምጃ ምንድን ነው?


ሀ.ሻማ ማብራት ለ.በክፍሉ ውስጥ የነበሩትን መብራቶች በሙሉ ማብራት
ሐ.ብርሃን ወዳለበት ክፍል መሄድ መ.መስኮትና በር መክፈት

29. አቶአባተ አበራን ከሐይለማሪያምጋር ያለህን ጓደኝነት አቋርጥ የሚሉት ለምን ነበር ? ሀ.ሐይለማሪያም
በባህርይው የተመሰገነ ባለመሆኑ ለ.ሐይለማሪያም የንባብ ፍቅር ስለሌለው
ሐ.በጓደኝነታቸው ስለሚቀና መ.አበራ ሐይለማሪያምን በእውቀት ስለሚበልጠው

30. በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው መልዕክት-----------ነው፡፡


ሀ. ስለአበራናሐይለማሪያም ጥብቅ ጓደኝነት ለ. ስለአቶአበራና ሐይለማሪያም አለመግባባት ሐ. ስለሐይለማሪያም
የኑሮ ሁኔታ መ. ስለሐይለማሪያም አንባቢነት

~ 38 ~
አባሪ ለ. የድህረትምህርት የአንብቦ መረዳት ፈተና
በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት፤በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታን የማጎልበት
ሚና በሚል ርዕስ ለተካሄደው ምርምር መረጃ እንዲያስገኝ ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀ የአማርኛ ቋንቋ
ድህረትምህርት ፈተና ከ(30)፡፡

መለኛ ቁጥር--------------------ክፍል----------------------ሴክሽን---------------------

የፈተናው መነሻ ስዓት፡-3፡00

ለፈተናው የተሰጠው ጊዜ፡-1፡30

አጠቃላይ መመሪያ

ይህ ፈተና የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለመለካት የቀረበ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በቀረበው የምንባብ ሀሳብ
መሰረት የሚመለሱ ሆነው ተዘጋጅተዋል፡፡ ምንባቡን በጥንቃቄ በማንበብ ለያንዳንዱ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ
በመምረጥ መልስ መስጫ ወረቀት ላይ አስፍሩ፡፡

ምንባብ
አብነት በአባቷ መኪና ወደ ስራ ስትሄድ ልቧ እንደሰጋ ነበረች፡፡ ትላንት ምሽት አባቷ መኝታቤት ድረስ መጥተው ‹‹ነገ
የምንነጋገረው ብርቱ ጉዳይ አለ›› ብለዋታል፡፡
መሀል ፒያሳ ከሚገኘው ትልቅ ህንጻ ስር ደርሰው መኪናይቱ ስትቆም አባቷ ፈጥነው በመውረድ ወደ መግቢያው በር
እየተጣደፉ አመሩ፡፡ አብነት ቦርሳዋን አንግታ እጅጌ ጉርድ ሸሚዟን እያስተካከለች ተከተለቻቸው፡፡
ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ ቀና ብላ አንደኛው ፎቅ ላይ በጥቁር መስታወት ላይ በወርቃማ ቀለም የተጻፈውን
ማስታወቂያ ተመለከተች፤ ‹‹አብነት አስመጭና ላኪ ድርጅት››ይላል፡፡ እንደወትሮው የኩራት ስሜት አልተሰማትም፡፡
ሃሳቧ ሁሉ ዛሬ ከአባቷ ጋር በሚፈጠረው ውዝግብ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡
ቢሮዋ በር ላይ ጸሐፊዋ ቅድስት በፈገግታ ተቀብላ አስገባቻት፡፡ ጠበብ ያለችው ቢሮዋ በቆዳ የተለበጠ መጠነኛ
ጠረጴዛና ወንበሮች፣የፋይል ካቢኔትና የመጻህፍት መደርደሪያ ይዛለች፡፡ ስትገባ ቀዝቃዛ አየርና ኦናኦና የሚል ሽታ
ተቀበላት፤በመስኮቱ ዘልቃ የምትገባው የጥዋት ጸሀይ ገና ሙቀቷን በመርጨት ለቢሮዋ ድምቀትንና ሙቀትን
አልቸረቻትም፡፡ አብነት ቦርሳዋን ከጠረጴዛዋ ላይ አስቀምጣ የማሞቂያውን ሶኬት ተከለችና ሻይ አዝዛ ተቀመጠች፡፡
የአብነት መደበኛ ተግባር የድርጅቱን ሂሳብ መከወን ነው፡፡ ትልቁን መዝገብ ጠረጴዛው ላይ ዘርግታ በማቀፊያ
ካከማቸቻቸው ሰነዶች ላይ የወጭና የገቢውን ሂሳብ መመዝገብ ጀመረች፡፡ የምትሰራው ሂሳብ የተጭበረበረ መሆኑን
ስለምታውቅ በዚያ ቢሮ ውስጥ የምታሳልፈው ጊዜ ሁሌም ይቆጫታል፡፡ እርሷ የምትሰራው ሂሳብ ብዙውን ጊዜ
የሚያሳየው መጠነኛ ትርፍ፣አንዳንድ ጊዜም ኪሳራ ሲሆን፣የድርጅቱ ገቢ ግን ቁጥር ስፍር እንደሌለው ታውቃለች፡፡

~ 39 ~
አባቷን ስለዚህ ጉዳይ ጠይቃ የተሰጣት መልስ ‹‹አንድ ቀን ትረጅዋለሽ›› የሚል ነበር፡፡ ያ‹‹ቀን››ግን እጅግ ስለራቀባት
የተጭበረበረ ሂሳብ ስታገላብጥ የምታቃጥለው ጊዜ ያንገበግባታል፡፡
የዘረጋችውን መዝገብ በንዴት አጥፋ እጆቿን አጣምራ ተቀመጠች፡፡ ጠረጴዛዋ ላይ ያለው ካላንደር ሜይዴይን
አስታወሳት፡፡ ሜይደይም ቻርሊን፤ቻርሊም ዛሬ ከአባቷ ጋር የምታደርገውን ውዝግብ፡፡ በሜይዴይ ሰልፍ ላይ
ከተካፈለች ወዲህ አባቷ አነጋግረዋት አያውቁም፡፡ ፊታቸውን በጥላቻ እንዳጠቆሩባት ነበሩ፡፡
ስለአባቷ ጭካኔ እንድታስብ የሚያደርጋት አንድ ድርጊት ምን ጊዜም ከህሌናዋ አይጠፋም፡፡
ከሁለት አመታት በፊት፣በድርጅቱ ውስጥ ስራዋን የጀመረች ሰሞን ነው፡፡ አባቷ ቢሮ ውስጥ ተቀምጣ ስለሂሳብ መዝገብ
አያያዝ ስትወያይ፣ የቢሮው በር ተንኳኩቶ አንድ ጎስቋላ ሰው ይገባል፡፡ የለበሰው ሰማያዊ ቱታ እላዩ ላይ ነትቧል፤
ጫማወቹ ተበጣጥሰዋል፤ በተገለጠው ደረቱ ላይ አጥንቶቹ ፈጥጠዋል፡፡ ረዘም ያለ ከሲታ ፊቱ ላይ አይኖቹ በስጋትና
በጥርጣሬ ይቁለጨለጫሉ፡፡ በራ ጭንቅላቱ ላይ ደግሞ የደም ስሮቹ ትር ትር ትር ሲሉ ይታያሉ፡፡
አብነት ድንግር ብሏት አንዴ አባቷን፤ መልሳ ጎስቋላውን ሰው ስትመለከት ቆየች፡፡ አባቷ ሰውየውን በዝምታ
ከተመለከቱት በኋላ ‹‹ከዚህ በፊት ውሳኔየን አሳውቄሀለሁ አላሳወቅኩህም?›› ሲሉ ተቆጥተው ጠየቁት፡፡
ሰውየው እያጎነበሰ ‹‹ጌታየ…›› ከማለቱ የጀመረውን ሳያስጨርሱት ‹‹የጠየኩህ አጭር ጥያቄ ነው፡፡ አጭር መልስ ብቻ
ስጠኝ?›› ሲሉ አፈጠጡበት፡፡
‹‹አሳውቀውኛል ጌታየ…!›› አለ በመርበትበት፡፡ ‹‹ታዲያስ አስራ አምስት ዓመት ሙሉ ድርጅቱ ውስጥ ስትሰራ፣ አንድ
ቀን እንኳን ለቃሌ ሳልታመን፣ የተናገርሁትን ሳልፈጽም የቀረሁበት ጊዜ አለ?›› ሲሉ ግንባራቸውን ቋጥረው ጠየቁት፡፡
‹‹የለም ጌታየ!››
‹‹እንግዲያ፣ ከስራ ካሰናበትሁህ በኋላ ምን ልትፈጥር መጣህ?! ማሰብና መጨነቅ የነበረብህ እኮ የድርጅቱን አስር ብር
እንኳን የማያወጣ እቃ ለመስረቅ እጆችህን ስትዘረጋ ነበር፡፡ በታታሪና በቅን ሰራተኛነትህ ያላደረኩልህ ነገር አልነበረም፡፡
አስረኛ ክፍል ድረስ ልዩ ወጭ እየሰጠሁ አስተምሬሀለሁ፤ ቤተሰቦችህን እንደቤተሰቤ ቆጥሬ ረድቻቸዋለሁ፡፡ አንተ ግን
አስር ብር ለማያወጣ ንብረት ታማኝነትህን አጎደልክ፡፡ አሁን ልወቅስህ አልፈልግም፤ ሁሉን ነገር ጨርሰናል›› አሉና
ተሸከርካሪ ወንበራቸውን አዙረው ጀርባቸውን ሰጡት፡፡
ሰውየው እንዳቀረቀረ ‹‹ጌታየ ጥፋተኛ ነኝ!›› አለ፡፡ ‹‹ጥፋተኛነትህን ያወቅከው ዛሬ በመሆኑ በራስህ ልታዝን ይገባል፡፡
ጥፋት ከፈጸሙ በኋላ በጥፋታቸው የሚያዝኑ የዋሆች ናቸው፡፡ የሰው ልጅ አእምሮ የተሰጠው ክፉውን ከደጉ አመዛዝኖ
እንዲለይበት አይደለም?! ወዳጀ፤ በእኔ ህይወት እና በድርጅቴ ውስጥ ለየዋሆች የሚሆን ቦታ የለም!›› አሉት
ፊታቸውን እንዳዞሩ፡፡
‹‹ጌታየ ምህረት ያድርጉልኝ?!›› አለ ሰውየው እንባ እየተናነቀው፡፡ አልመለሱለትም ‹‹ ሚስቴ ወልዳ አራስ ቤት ነች፤
ሶስቱ ልጆቼ የሚልሱት የሚቀምሱት ርጋፊ ዱቄት እንኳ የላቸውም፡፡ አይነስውር እናቴ ዛሬ ጠዋት ጠኔ ይዟት
ከተኛችበት የቦንዳ አልጋ ላይ አልተነሳችም፡፡ እኔም እራሴ እህል ከቀመስኩ ዛሬ ሶስተኛ ቀኔ ነው… . ስድስት ወር ሙሉ
ያለስራ……›› ንግግሩን ሳይጨርስ እንባ ቀደመው፡፡

~ 40 ~
አብነት እንባዋን እየታገለች አቀረቀረች አባቷ ግን ጀርባቸውን ሳያዞሩ ‹‹እኔ መንገሻ ከደሙ ንጹህ ነኝ፡፡ መሳሳት
አልነበረብህም፣ ከተሳሳትክ ደግሞ የስህተትህን ዋጋ በጸጋ መቀበል አለብህ፡፡ አሁን ስራ ስለያዝኩ ቢሮየን ለቀህ
ውጣልኝ!›› አሉት በቁጣ፡፡
ሰውየው ፈዞ ባዶ ስሜት ባዘሉ አይኖቹ ጀርባቸውን ሲመለከት ከቆየ በኋላ እንባውን እያባበሰ የቢሮውን በር ከፍቶ
ወጣ፡፡
አብነት ራሷን መቆጣጠር አልቻለችም ‹‹ አባባ! ይህንን ምስኪን ይቅርታ አድርገህለት የነዚያን ሁሉ ምስኪን ፍጥረታት
ህይወት ብታድንስ?!›› እያለች ማልቀስ ጀመረች፡፡
አባቷም ፊታቸውን ወደ እርሷ መልሰው፣ ‹‹ይቅርታን ማድረግ የሚችል ሩህሩህ ልብ ቢኖረኝ ኖሮ ዛሬ ከደረስኩበት
መድረስ ባልቻልኩም ነበር፡፡›› አሏት ሀዘን፣ ቅሬታና ድል አድራጊነት በተሞላበት ትንሽ ፈገግታ፡፡
አብነት በፍጥነት ወጥታ ደረጃውን እየተንደረደረች በመውረድ ሰውየውን ህንጻው መውጫ በር ላይ አስቆመችው፡፡
ተስፋና ጥርጣሬ በተደባለቀባቸው አይኖቹ እየተመለከታት ኪሶቿን ሁሉ እያገላበጠች መፈተሸ ጀመረች ኪሷ ውስጥ
ያገኘችው ግን አንዲት የተጣጠፈች ብር እና ሃያ ሳንቲሞች ብቻ ነበር፡፡ ቦርሳዋን ቢሮ ትታዋለች፡፡
ምን እንደምትሰጠው ጨንቋት ስታስብ የሃያ አንደኛውን አመት ልደቷን ስታከብር ከቤተሰቦቿ የተበረከተላትን የወርቅ
አምባር እጇላይ ተመለከተችው፡፡ አሰበች፡፡ ምርጫ አልነበራትም፡፡ ሳታመነታ አምባሯን አውልቃ ሰጠችው፡፡ ‹‹ይህን
ሸጠህ ቤተሰቦችህን መግባቸው ስራ እስክታገኝ ድረስ ምናልባት አትራቡም ይሆናል፡፡››
‹‹ደህና ሁን!›› ብላው ፎቁን መውጣት ስትጀምር ተከትሎ አስቆማትና ‹‹እመቤት፤ አንችን የማመሰግንበት አንደበት
የለኝም፡፡ ምን እንደምናገር እንኳን አላውቅም….. እግዚአብሔርን የምለምነው ሰው ሆኜ ውለታሽን የምመልስበትን
ቀን እንዲሰጠኝ ብቻ ነው፡፡›› አላት ሳግ ከሚያፍነው ልሳኑ ጋር እየታገለ፡፡

ምንጭ፡-ደረጀ በቀለ (1988) ህያው ፍቅር፡፡ ለፈተና እንዲመች ተሻሽሎ የቀረበ፡፡

መመሪያ፡-ለሚከተሉት ጥያቄዎች በምንባቡ መሰርት ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡


1. ከሚከተሉት ውስጥ አብነት ቢሮ ውስጥ የማይገኝ የቱ ነው?
ሀ.በቆዳ የተለበጠ ጠረጴዛ ለ.የፋይል ካቢኔት ሐ.የመጽሃፍ መደርደሪያ መ.ሶፋ ወንበር
2. የአብነት መደበኛ ስራ ምንድን ነው?
ሀ. የድርጅቱን ገቢ ማሳደግ ለ. የድርጅቱን ሂሳብ በትክክል መስራት
ሐ. ሂሳቡን በማስተካከል ትርፉን መጠነኛ ማድረግ መ. ድርጅቱን ከክስረት ማዳን
3. ቢሮ አንኳኩቶ የገባውን ሰው በትክክል የማይገልጸው የቱ ነው?
ሀ.ጫማዎቹ ተበጣጥሰዋል ለ. ረዘም ባለ ጠይም ፊቱ ላይ ውበት ይነበባል
ሐ.በተገለጠው ደረቱ ላይ አጥንቶቹ ፈጥጠዋል መ. በራ ጭንቅላቱ ላይ የደምስሮቹ ትርትር ሲሉይታያሉ
4. በእኔ ህይወትና በድርጅቴ ውስጥ ለየዋሆች የሚሆን ቦታ የለም በማለት የተናገረ ማን ነው?

~ 41 ~
ሀ.አቶ ቻርሊን ለ.አብነት ሐ.አቶ መንገሻ መ.የድርጅቱ ዘበኛ
5. ቢሮ ውስጥ ገብቶ ይቅርታ እንዲያደርጉለት ሃላፊውን የጠየቀው ሰውዬ ከስራ የተባረረው በምን ምክንያት ነው?
ሀ. በስርቆት ወንጀል ለ. ተገቢ የሆነ የስራ ልምድ ስለሌለው
ሐ. የስራ ችሎታ ስለሌለው መ. ታታሪና ቅን ስላልሆነ

~ 42 ~
6. ይቅርታ ማድረግ የሚችል ሩህሩህ ልብ ቢኖረኝ ኖሮ ዛሬ ከደረስሁበት መድረስ አልችልም ነበር ማለቱ ምንን
ያሳያል?
ሀ. በጥረቱ ያፈራው ሃብት ንብረት መሆኑን ለ. ከቤተሰቦቹ በውርስ ያገኘው መሆኑን
ሐ. በህገወጥ መንገድ ያገኘው ሃብት መሆኑን መ. በእውቀቱ ያፈራው ሃብት መሆኑን
7. አብነት ደረጃውን ወርዳ ሰውየውን ያሥቆመችው ለምን ነበር?
ሀ. አባቷ ይቅርታእንዳደረጉለት ለመግለጽ ለ. አባቷ የላኩትን ገንዘብ ለመስጠት
ሐ. ያላትን የወርቅ አንባር ለመስጠት መ. ሁለተኛ ቢሮ እንዳይመጣ ለማስጠንቀቅ
8. ጠረጴዛላይ ያለው ካላንደር አብነትን በቅደም ተከተል ምን ምን እንድታስታውስ አደረጋት?
ሀ.ሜይደይን--ቻርሊን--ከአባቷጋር የምታደርገውን ውይይት
ለ.ከአባቷጋር የምታደርገውን ውይይት--ቻርሊን--ሜይደይን
ሐ.ቻርሊን--ሜይደይን--ከአባቷጋር የምታደርገውን ውይይት
መ.ሜይደይን--ከአባቷጋር የምታደርገውን ውይይት--ቻርሊን
9. ሰውየውን ተሰናብታ ደረጃውን መውጣት ስትጀምር ተከትሎ ያስቆማት ለምን ነበር?
ሀ. ስጦታውን ለመመለስ ለ. ከድርጅቱ ውስጥ እንድታስቀጥረው ለመማጸን
ሐ. ስጦታውን ስለሰጠችው ለማመስገን መ. እንደሚወዳት ለመግለጽ
10. አብነትን አባቷ አነጋግረዋት አያውቁም የተባለው ከመቼ ጀምሮ ነው?
ሀ. ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ ለ. ከሜይደይ ሰልፍ ጀምሮ
ሐ. በድርጅቱ ውስጥ ስራ ከጀመረች ጀምሮ መ. የወርቅ አምባሯን ከሰጠች ጀምሮ
11. ከስራ የተባረረው ሰውየ የሚያስተዳድራቸው የቤተሰብ አባላት ስንት ናቸው?
ሀ. ሰባት ለ. ስድስት ሐ. አምስት መ. አራት
12. የድርጅቱ ሒሳብ በትክክል አለመሰራቱ ይበልጥ የሚጎዳው የትኛውን ነው?
ሀ. ድርጅቱን ለ. መንግስትን ሐ. ቤተሰቡን መ. የድርጅቱን ሰራተኞች
13. አብነት ‹‹አብነት አስመጭና ላኪ ድርጅት›› የሚለውን ስታነብ እንደወትሮው ኩራት ያልተሰማት ለምንድን ነው?
ሀ. ሀሳቧ ሁሉ ከአባቷ ጋር በሚፈጠረው ውዝግብ ላይ ስለነበረ
ለ. ሀሳቧ ከስራ ከተሰናበተው ሰውየ ላይ ስለነበር
ሐ. የድርጅታቸው ክስረት ስላሳሰባት
መ. ሻይ ሳትጠጣ ከቤት ስለወጣች
14. የድርጅቱ ገቢ ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ ከሚለው ውስጥ የተሰመረበት አውዳዊ ፍቺ ------------- ነው፡፡
ሀ. በጣም ትንሽ ለ. የተመጠነ ሐ. በርካታ መ. ኢምንት
15. አብነት የዘረጋችውን መዝገብ በንዴት አጥፋ እጆቿን አጣምራ የተቀመጠችው ለምንድን ነው?
ሀ. ጠረጴዛው ላይ ያለውን ካሌንደር ለመመልከት ለ. የተጭበረበረ ሒሳብ መስራቷ ስላናደዳት

~ 43 ~
ሐ. የድርጅቱ ገቢ አጥጋቢ ባለመሆኑ መ. በድንገት ቻርሊን ስላስታወሰች
16. የአብነት አባት በአብነት ላይ ፊታቸውን ያጠቆሩበት ጉዳይ ምን ነበር?
ሀ. ስራዋን ባለማክበሯ ለ. ከስራ ለተሰናበተው ሰውየ ስጦታ ስለሰጠች
ሐ. በሜይደይ ሰልፍ ላይ ስለተሳተፈች መ. የድርጅቱን ሒሳብ በትክክል ስላልሰራች
17. ለአብነት እጅግ በጣም የራቀባት ቀን የትኛው ነው?
ሀ. ሜይደይ የሚከበርበት ቀን ለ. ስለድርጅታቸው ትክክለኛ አሰራር የምታውቅበት ቀን
ሐ. ስራ የምትለቅበት ቀን መ. ከቻርሊ ጋር የምትገናኝበት ቀን
18. ከስራ የተባረረው ሰውየ ይቅርታ ለመጠየቅ ቢሮ ውስጥ ሲገባ አብነት ምን እያደረገች ነበር?
ሀ. ከአባቷ ጋር ስለድርጅቱ ሒሳብ አያያዝ እየተነጋገረች
ለ. በጠረጴዛው ላይ የሚገኘውን የጊዜ ሰሌዳ እየተመለከተች
ሐ. የድርጅቱን የሒሳብ መዝገብ እያገላበጠች
መ. የማሞቂያውን ሶኬት ሰክታ ሻይ እያዘዘች
19. ከስራ የተባረረው ሰውየ ይቅርታ ለመጠየቅ የመጣው ያለ ስራ ምን ያህል ወራትን ካሳለፈ በኋላ ነው?
ሀ.አራት ለ. አምስት ሐ. ስድስት መ. ሰባት
20. ከስራ የተሰናበተው ሰው አብነትን ያመሰገነበት መንፈስ ምንድን ነው?
ሀ. እውነተኛ ለ. ሽሙጥ ሐ. ቁጭት መ. በተስፋ
21. አብነት ከአባቷ የምትለየው በምንድን ነው?
ሀ. በአስተሳሰቧ ለ. በመልኳ ሐ. በድርጅት ባለቤትነቷ መ. በስራ ወዳድነቷ
22. ከስራ የተባረረው ሰውየ በድርጅቱ ውስጥ ለስንት ዓመት ሰርቷል?
ሀ. ለ 15 ለ. ለ 14 ሐ. ለ 13 መ.ለ 20
23. አብነት በስራዋ የማትደሰተው ለምንድን ነው?
ሀ. በቂ ደመወዝ ስለማይከፈላት ለ. ስራው አሰልቺ ስለሆነ
ሐ. የምትሰራው ሂሳብ የተጭበረበረ በመሆኑ መ. ድርጅቱ ትርፍ ባለማሳየቱ

~ 44 ~
24. አብነት እጅግ ስቅስቅ ብላ እንድታለቅስ ያደረጋት ጉዳይ ምን ነበር?
ሀ. ከጓደኛዋ መለየት ለ. የአባቷ የጭካኔ ተግባር ሐ. የችግር መደራረብ መ. የስራ ጫና
25. አብነት የምትሰራው ሂሳብ ብዙውን ጊዜ የሚያሳየው------------ነው፡፡
ሀ.ኪሳራ ለ.መጠነኛ ትርፍ ሐ.ከፍተኛ ትርፍ መ.ከፍተኛ ኪሳራ
26. አብነት ወደቢሮ ስትሄድ የሰጋችበት ምክንያት ምን ነበር?
ሀ. ስዓት አሳልፋ በመግባቷ ለ. የተደራረበ የስራ ጫና በመኖሩ
ሐ. የድርጅቱን አትራፊነት ባለማወቋ መ. ከአባቷ ጋርየምትነጋገርበትን ርዕሰጉዳይ ባለማወቋ
27. አብነት 21 ኛ ዓመት ልደቷን ስታከብር ከቤተሰቦቿ የተበረከተላት ምን ነበር?
ሀ. የወርቅ ሀብል ለ. የወርቅ አንባር ሐ. የምትሰራበትን ድርጅት መ. ሙሉ ልብስ
28. የአቶ መንገሻ ድርጅት የሚገኘው የት ሰፈር ነው ?
ሀ. መርካቶ ለ. ጉለሌ ሐ. ፒያሳ መ. ጎተራ
29. አብነት ከስራ ለተባረረው ሰውየ ልትረዳው ፈልጋ ኪሷ ውስጥ ስትገባ ያገኘችው ምንድን ነው?
ሀ. አንድ ብር ከሃያ ለ. አስር ብር ሐ. ሁለት ብር ከሃምሳ መ. መቶ ብር
30. ከአብነት ህሌና የማይጠፋውና ስለአባቷ ጭካኔ እንድታስብ የሚያደርጋት ጉዳይ የተከሰተው መቸ ነው?
ሀ. ከሁለት ዓመት በፊት ለ. በሁለት ወራት ውስጥ
ሐ. ከሳምንት በፊት መ. ከቀናት በፊት

~ 45 ~
አባሪ ሐ. በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር ዘዴ ለማስተማር የቀረቡ ቴክስቶች
በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በስነጽሁፍ ቴክስት ገጸባህርይተኮር የማስተማር ዘዴ የአንብቦ መረዳት ችሎታን
ለማጎልበት ያለውን አስተዋጽኦ ለማወቅ ለሚሰራ የምርምር ጥያቄ ገጸባህርይተኮር ዘዴን ተጠቅሞ ለማስተማር
የተዘጋጀ የማስተማሪያ ቴክስት

የትምህርት ክፍለ ጊዜያት፡- ሰኞና ሐሙስ /በቀን ለ 40 ደቂቃ/

የመማሪያ ክፍል፡- የቲቶሪያል መስጫ ክፍል

ጠቅላላ የትምህርቱ ስዓት፡- 5፡20

ክፍለ ትምህርት አንድ


የትምህርት ርዕሶች፡
-የጽሁፉን ፍሬ ሃሳብ ተረድተው በራሳቸው አባባል መግለጽ

-ገጸባህሪያቱ ከጭብጡና ከመዋቅሩ ጋር ያላቸውን ትስስር መለየት

-ገጸባህርያቱን በማወዳደር የሃሳባቸውን አንድነትና ልዩነት መለየት

-ስለገጸባህርያት ተገቢ መረጃዎችን መሰብሰብ

-ለአዳዲስ ቃላትና ሐረጋት አውዳዊ ፍች መስጠት

ትምህርቱ የሚወስደው ጊዜ ፡- 1፡20

የትምህርቱ ዓላማ፡- ከዚህ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-

-የጽሁፉን ፍሬ ሃሳብ ተረድተው በራሳቸው አባባል ይገልጻሉ

-ምንባቡ ውስጥ ያሉ ገጸባህርያት ከጭብጡና ከመዋቅሩ ጋር ያላቸውን ትስስር ይገልጻሉ

-ገጸባህሪያትን በማወዳደር የሃሳባቸውን አንድነትና ልዩነት ይገልጻሉ

-ስለገጸባህርያቱ ተገቢ መረጃዎችን ይሰበስባሉ

-ከምንባቡ ለወጡ አዳዲስ ቃላትና ሃረጋት አውዳዊ ፍች ይሰጣሉ

~ 46 ~
ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች
1. ጋብቻ ምንድን ነው?

2. ጋብቻ በተጋቢዎች ፈቃደኝነት ላይ ካልተመሰረተ ምን ችግር የሚፈጠር ይመስላችኋል?

2. ስልጣንና ጋብቻ በዘር ሀረግ ቢሆን ኑሮ ምን ሊፈጠር ይችል ነበር?

ምንባብ
በዛብህ በባሉ ሳመንት ለፊትአውራሪ መሸሻ እጅግ ባለሟል ሆኖ ሳይለይ ሰነበተ፡፡ ከባሉ ውጭ ወደተማሪ ቤቱ
ለመመለስ ሲሰናበት፡-

‹‹ ግርግር ሆነና ለብቻ ተገናኝተን አላነጋገርሁህም አገርህ ወዴት ነው?›› አሉት ፊትአውራሪ፡፡

‹‹ አገሬ ማንኩሳ ነው ጌታየ››አለ በዛብህ፡፡

‹‹ እዚህ አያሌ ለመቆየት ታስባለህ?››

‹‹ እኔ አንድ አመት ለመቆየት አስባለሁ ነገርግን ፈጻሚው እግዚአብሄር ነው፡፡››

‹‹ እዚህ በምትቆይበት ጊዜ ቤታችን ቤትህ ነው፤አትለየን እንዳትሰቀቅ እንኩዋን ላንተ ላንዱ ለብዙ እንሆናለን፡፡››
አሉ ፊታውራሪ መሸሻ ረዥም ጢማቸውን በግራ እጃቸው ወደታች እየላጉ፡፡ በዛብህ እጅ ነስቶ ስለሽልማቱና
ስለመስተንግዶውም አመስግኖ ወደተማሪ ቤቱ ሄደ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ለፊታውራሪ መሸሻና ለወይዘሮ ጥሩአይነት
ለቤተሰቡም በሙሉ ቤተኛ ሆነ፡፡ ለምሳ ባይሆን ለራት ለራት ባይሆን ለምሳ ከፊትአውራሪ መሸሻ ቤት አይጠፋም
አንዳንድ ጊዜም ሳይመጣ ውሎ ያደረ እንደሆን እንደወለዱት ልጅ ተጨንቀው እተማሪ ቤቱ ድረስ ጠያቂ ይልኩ
ነበር፡፡

ፊታውራሪ መሸሻ በባላባትነታቸው እጅግ የሚኮሩ መኮነን ነበሩ፡፡ ከትግሬ፣ከሽዋ፣ከጎንደር ነገስታት ጋር ያላቸውን
ዝምድና ቁጭ ብለው እንደውዳሴ ማርያም መድገም የጀመሩ እንደሆነ ሰሚ የሚሰለቸው አይመስላቸውም፡፡
እሳቸው እንደሚተርኩት የሆነ እንደሆነ በትግሬም ሆነ በሽዋ ወይም በጎንደር መንገስ ቢቀርባቸው እንኩዋ ቀጥሎ
ያለው ቦታ ለሌላ መሰጠቱን እንደየግፍግፍ ይቆጥሩት ነበር፡፡ ነገርግን ምን ይደረጋል በድል እንጂ በትግል የማይገኝ
ነገር! ‹‹እኔ መሸሻ፣ እኔ የደፋር ጌታ በዘር ይሁን በሙያ እንኩዋን የሚበልጠኝ የሚተካከለኝ እንደሌለ ማንም
ያውቃል፡፡ ዳሩ ምንይሆናል! ሰው በዘሩና በጋሻው የሚመረጥበት ጊዜ አልፎ እነሆ እንደኛ ያለን ሰዎች እዚህ በባላገር
ከገበሮችና ከበሮች ጋር ተሰማርተናል!›› ብለው እንደመቆጣት ሲሉ አሽቃባጮቻቸው ‹‹ግዴለም ጌቶች ጊዜ
ያልፋል፤ እንዲህ እንደሆን አንቀርም፡፡›› ይሉዋቸውና ወዲያው ይጽናናሉ፡፡

~ 47 ~
ዘር በመቁጠር ምሽታቸው፤ ወይዘሮ ጥሩአይነትም ከባላቸው ምንም ያክል አይሰንፉም ነበር፡፡ ፊታውራሪ መሸሻና
ወይዘሮ ጥሩአይነት ሰብለወንጌል የምትባል አንዲት ሴት ልጅ ብቻ ነበረቻቸው፡፡

ሰብለወንጌል ሳትረዝም ሳታጥር፣ ሳትቀጥን ሳትወፍር በመጠኑ የተሰራች ውበት ከደምግባት ተባብረው ያስጌጡዋት
እጅግ ያማረባት ልጅ ነበረች፡፡ ከዚህም በላይ ጠባይና ትህትና በሰፊው የታደለች ስለነበረችና በባህርይ ትምክህት
የምትጠላ፣ ከወላጆችዋ ፈጽማ የተለየች ነበረች፡፡

ሰብለወንጌል በአስራ አራት አመትዋ በመኩዋንንት ልጆች ወግ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያም፣ መልከማሪያም፣ መልከ
እየሱስና መልከ ጊዮርጊስ አወቀች፡፡ ከወይዘሮ ጥሩአይነትም ኩራታቸውንና ግብዝነታቸውን ብቻ ለሳቸው ትታ
የቤት ባልትናቸውንና ሌላ መልካም ሙያቸውን ሁሉ ጠንቅቃ ስለተማረች ይህ ይቀራታል የማትባል ሙሉ ነበረች፡፡
ስለዚህ በዲማና ባካባቢው የሚያዉቁዋት ወይም ወሬዋን የሰሙ መኩዋንንት ሁሉ ገና አስራ አንድ አመት ሲሆናት
ጀምረው ልጆች የነበሩዋቸው ለልጆቻቸው፣ ልጆች ያልነበሩዋቸው ለዘመዶቻቸው ደጅ ይጠኑ ነበር፡፡ ነገር ግን
ወላጆችዋ እንደእሾህ አጥር ዙሪያዋን ከበው እየተከላከሉ ውበትዋ የጠራቸው ጎበዛዝት ሁሉ ጎምዥተው ዳርዳር
ሲዞሩ ያች ያማረች፣ የጋመረች የገነት ፍሬ የመበያዋ ወራት አለፈ፡፡

*ተማሪዎች ንባባችሁን ገታ አድርጋችሁ እስካሁን ካነበባችሁት ምንባብ ምን እንደተረዳችሁ ለክፍል


ጓደኞቻችሁ ግለጹ?

*የሰብለወንጌል እጣፋንታ ምን የሚሆን ይመስላችኋል?


ፊታውራሪ መሸሻና ምሽታቸው ወይዘሮ ጥሩአይነት በዘር ያክለናል፣ ይመስለናል የማይሉት ሰው ልጃቸውን ለጋብቻ
ሲጠይቅ እንኩዋንስ ሊሰጡ መጠየቃቸውን እንደ ብርቱ ውርደት እየቆጠሩት እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡

‹‹ ወየው ጉድ! ጆሮ አልሰማም አይልምኮ እናንተ?›› ይላሉ ፊታውራሪ መሸሻ ከውጭ ሲገቡ፡፡

‹‹ ዛሬ ደግሞ ምን ሰሙ ጌታየ?›› ይላሉ ባለቤታቸው ወይዘሮ ጥሩአይነት፡፡

‹‹ ቀኛዝማች እገሌ ሰብለወንጌልን ለልጁ ለመነኝ››

‹‹ ቀኛዝማች እገሌ የማን ልጅ ነው?››

‹‹ አባቱን እንኩዋን እኔ እሱም አያውቀው፡፡››

‹‹ ትልቅ ድፍረት!›› ይላሉ ወይዘሮ ጥሩአይነት፡፡

‹‹ ግራዝማች እገሌ ልጅህን ስጠኝ አለኝኮ ጥሩ››

~ 48 ~
‹‹ የማን ልጅ ነው ጌታየ?››

‹‹ አባቱ ሰው አይደለም ገበሬ ነው፡፡››

‹‹ ይህን ሳልሰማ በሞትሁ!››

‹‹ ፊታውራሪ እገሌ ልጄን ለልጁ ለመነኝ››

‹‹ የማን ልጅ ነው?››

‹‹ አባቱ መጫኛ ነካሽ ነጋዴ ነበር፡፡››

‹‹ ምነው ከምታሰድበን ባልተወለደች፡፡››

‹‹ ባላምበራስ እገሌ ልጅህን ስጠኝ ብሎ አማላጅ ላከብኝኮ ሀ . . ሀ . . ሀ . ወይ ጊዜ !››

‹‹ የማን ልጅ ነው?››

‹‹ አባቱ ብዙ ላም የነበረው ባለጌ ባላገር ነበር እሱ ሲሞት ላሙን ሁሉ አውርሶት ሞተ፡፡ አሁን አገዋቱን በፋጋ
እዬጠጣ ሆዱ ሲነፋ ጊዜ ከሰው እኩል የሆነ መስሎት ይሄዋ የኛን ልጅ ይለምን ጀመር!››

‹‹ ይበለን፤ ኧረ ይበለን ሲያንሰን ነው፤ ሲያንሰን ነው፤ ለቀን ሰው ወዳለበት እንዳንሄድ እንደ ታሰርን ሁሉ
ይህን አገር መልቀቅ አቅቶን የባላገር መጫወቻ ሆን፡፡›› ይላሉ ወይዘሮ ጥሩዓነት እንባ እዬተናነቃቸው

‹‹አይ ያንች ነገር ሰው ወዳለበት የምትይ ዛሬ የሰው ምርት አልቆ ግርዱ በቀረበት ዘመን ምን ሰው አለ? የትም
ብትሄጂ ቢበዛ አባት እንጂ አያት ያለው ሰው ይገኝ መሰለሽ?››
‹‹እንዴት?››

‹‹እንዴትማ እንደምታውቂው አንዱ እህሉን፣ አንዱ ጥጡን፣ አንዱ ቅቤውን፣ አንዱ ቆዳውን ሸጦ ጉቦ እየሰጠ
ባላምበራስ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ፊታውራሪ ይባልና ልጁ የባላምባራስ እገሌ፣ የግራዝማች እገሌ፣ የቀኛዝማች
እገሌ፣ የፊታውራሪ እገሌ ልጅ ይባላል፡፡ የሳውቅዮሽ የጨዋታ ቀኛዝማች ግራዝማች! እዚህኮ እኛ ግቢ የነሰጠኝና
የነአረሩ ልጆች ፊታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ግራዝማች እየተባባልን እንጫወት እንደሚሉት ያለ ነው!፡፡ ከአጥንትና
ከደም ያልተወረሰ በጥጥና በቆዳ የተገዛ ፊታውራሪነት፣ ቀኛዝማችነት፡፡ ሆሆ! ኧረ ምን ዘመን መጣብን? ይሄውልሽ
የነዚህ ልጆች ናቸው የኛን ልጅ ለማግባት የሚጠይቁ! እንዲህ ያሉት ልጆች እድሜ ለቆዳ፣ እድሜ ለጥጥ
አባቶቻቸው ግራዝማች፣ ቀኛዝማች እንዳንዶችም እንደኛ ፊታውራሪ ተብለውላቸዋል፤ አያት ግን የላቸውም፡፡
ታዲያ ለነዚህ ልጄን ልስጥ? የእሌኒን፣ የገላውዴዎስን፣ የሱስንዮስን ልጅ የገበሬ ነጋዴ ልስጥ? እነሱ ባያዩ፣ ባይሰሙ
አጥንታቸው አይከሰኝም? አይወቅሰኝም?›› ይላሉ ፊታውራሪ መሸሻ በቁጣ ደማቸው ፈልቶ ራሳቸውን እየነቀነቁ፡፡

~ 49 ~
‹‹ እርስዎም ልስጥ ቢሉ እኔን መቃብር ሳይጫነኝ ልጀ አጥንተ ሰባራ አታገባም! እንዲያውም አላቻዋ አግብታ ዘር
ከምታበላሽ የሚያክላት የሚመስላት አጥታ ሳታገባ ቀረች ብትባል ክብርዋን ይጨምረዋል እንጂ አይቀንሰውም፡፡››

ምንጭ፡- ሐዲስ አለማየሁ (1958፡ 83-87) ፍቅር እስከ መቃብር

መመሪያ አንድ፣ ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ
ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክል ከሆነ እውነት ስህተት ከሆነ ደግሞ ሐሰት በማለት መልሱ፡፡
1. እኔን መቃብር ሳይጫነኝ ልጀ አጥንተ ሰባራ አታገባም በማለት የተናገሩት ወይዘሮ ጥሩአይነት ናቸው፡፡
2. ፊት አውራሪ መሸሻ በባላባትነታቸው እጅግ የሚኮሩ መኮነን ነበሩ፡፡
3. ይህንን አገር መልቀቅ አቅቶን የባላገር መጫወቻ ሆን ያለች ሰብለወንጌል ናት፡፡
4. ለምሳ ባይሆን ለራት ለራት ባይሆን ለምሳ ከፊት አውራሪ መሸሻ ቤት አይጠፋም የተባለው በዛብህ ነው፡፡
5.ሰብለ ወንጌል ከወይዘሮ ጥሩአይነት የወረሰችው ኩራታቸውንና ግብዝነታቸውን ነው፡፡
መመሪያ ሁለት፡- ለሚከተሉት ከምንባቡ ለወጡ ቃላት አውዳዊ ፍች ከሰጣችሁ በኋላ ዓ/ነገር ስሩባቸው፡፡
1. አያሌ
2. ግብዝ
3. ትምክት
4. ጎመዠ
5. ፋጋ
መመሪያ ሶስት ፡-በሚከተሉት ከምንባቡ የወጡ ጥያቄዎች ላይ በቡድን ተወያዩ፡፡
1. እንደምንባቡ ያጋመረችና ያማረች የገነት ፍሬ ሲል ምን ማለቱ ነው?
2. እንደ ፊታውራሪ መሸሻ አስተሳሰብ በባላገር ከገበሮችና ከበሮች ጋር ተሰማርተው የሚኖሩበት ምክንያት
ምንድን ነው?
3. ወይዘሮ ጥሩአይነትና ፊታውራሪ መሸሻ የሚመሳሰሉት በምንድን ነው? የሚለያዩትስ?
4. ሰብለዎንጌል ከቤተሰቦቿ የምትለየው በምንድን ነው?

መመሪያ አራት፡- ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ
የምንባቡን ሃሳብ መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. ፊታውራሪ መሸሻ እጅግ የሚኮሩት በምንድን ነው?
ሀ. በሐብታቸው ለ. በባላባትነታቸው ሐ. በሐገራቸው መ. በልጃቸው
2. ሳትረዝም ሳታጥር፣ ሳትቀጥን ሳትወፍር በመጠኑ የተሰራች ውበት ከደምግባት ተባብረው ያስጌጡዋት ማንን
ነው ?

~ 50 ~
ሀ. ወይዘሮ ጥሩአይነትን ለ ሰብለወንጌልን ሐ. ሐብትሽን መ. አረሩን
3. ሰብለወንጌል በመኳንንት ልጆች ወግ ውዳሴ ማርያምና መልከጊዮርጊስ ያወቀች በስንት አመቷ ነው? ሀ.
በአስራ ሶስት ለ. በአስራ አንድ ሐ. በአስራ ሁለት መ. በአስራ አራት
4. ፊታውራሪ መሸሻና ወይዘሮ ጥሩአይነት ልጃቸውን ለጋብቻ ሲጠየቁ እንደውርደት ቆጥረው እጅግ የሚያዝኑት
ማን ሲጠይቃቸው ነው? ሀ. በእድሜ አቻዋ ያልሆነ ሰው ለ. በዘር ያክለናል ብለው የማይሉት ሰው ሐ.
ሐብት የሌለው ሰው መ. መልከ ጥፉ የሆነ ሰው
5. በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ምንድን ነው?
ሀ. ጋብቻ በዘር ሀረግ መሆን እንዳለበት ለ. ያላቻ ጋብቻ መቆም እንዳለበት ሐ. ሰዎች የፈለጉትን
ማግባት እንዳለባቸው መ. ጋብቻ በተጋቢዎች ፍላጎት እንደሚዎሰን
6. ፊታውራሪ መሸሻ ‹‹እንኩዋን የሚበልጠኝ የሚተካከለኝ የለም›› ያሉት በምንድን ነው? ሀ. በሀብት
ለ. በዘር ሐ. በመልክ መ. በእድሜ
7. ሰብለወንጌልን ገና በአስራ አንድ ዓመቷ ጀምረው ልጆች የነበሩዋቸው ለልጆቻቸው ያልነበሩዋቸው ደግሞ
ለዘመዶቻቸው ደጅ ይጠኑ የነበረው ለምንድን ነው ?
ሀ. ሰብለም እንደወይዘሮ ጥሩአይነት ኩሩ ስለነበረች
ለ. ሰብለ እጅግ ውብ ስለነበረችና በትህትና የታደለች ስለነበረች
ሐ. ሰብለ የተማረችና እጅግም ባለሙያ የነበረች ስለነበረ
መ. ለና ሐ መልስ ናቸው
8. ፊታውራሪ መሸሻ ‹‹ቢበዛ አባት እንጂ አያት ያለው ባላምበራስ፣ ግራዝማች፣ ቀኛዝማች፣ ፊታውራሪ
አይገኝም›› ያሉበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. አብዛኞቹ ማረጉን ያገኙት በጉቦ ስለሆነ ለ. አብዛኞቹ ማረጉን ያገኙት በዘር ሀረግ ስለሆነ ሐ.
አብዛኞቹ ማረጉን የሚያገኙት በጦርነት ስለሆነ መ. አብዛኘኞቹ ማረጉን ያገኙት በእድሜ ስለሆነ
9. ፊታውራሪ መሸሻ ምን አይነት ሰው ናቸው?
ሀ.ውሐ ቀጠነ ብለው የማይከራከሩ ለ. ከእኔ በላይ ሰው የለም ብለው የሚያስቡ ሐ. በትህትና
የተሞሉ ቅን ሰው መ. ሰርተው የሚያሰሩ በሰው ዘንድ የሚወደዱ
10. እንደ ምንባቡ ከሚከተሉት አንዱ ትክክል አይደለም፡፡
ሀ. አጥንተ ሰባራ አግብቶ ዘር ከማበላሸት ይልቅስ የሚያክለው አጥቶ ቀረ መባል የተሻለ ክብር አለው፡፡
ለ. የዘመኑ መሳፍንት በአብዛኛው ስልጣን የያዙት በጉቦ ነው፡፡
ሐ. ወይዘሮ ጥሩአይነት የፊታውራሪ መሸሻን ያህል ሐረግ የመምዘዝ ፍላጎት የላቸውም፡፡
መ. በዛብህ ከበዓሉ በኋላ የነፊታውራሪ መሸሻና ወይዘሮ ጥሩአይነት ቤተኛ ሆኖ ነበር፡፡

~ 51 ~
መመሪያ አምስት፡-ለሚከተሉት ጥያቄዎች በጽሁፍ መልስ ስጡ፡፡
1. ተገቢ መረጃዎችን በመሰብሰብ የሰብለወንጌልን ተክለሰውነት ግለጹ?
2. ከምንባቡ የተረዳችሁትን መልክት ባጭሩ ግለጹ?
3. የፊት አውራሪ መሸሻ አመለካከት ተገቢነው? ወይስ አይደለም? ለምን?

የትምህርቱ መርጃ መሳሪያ፡- ፍቅር እስከ መቃብር


ግምገማ፡- የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን መልስ መገምገም
-የግል ስራዎችን ማረም
-የቡድን ስራዎችን መገምገም

ክፍለ ትምህርት ሁለት


የትምህርት ርዕስ፡- - ስለገጸባህርያት እንቅስቃሴና አመለካከት በአዕምሮ ምስል መፍጠር

- የገጸባህርያትን መልክ፣ጸባይና ባህርይ መለየት

- ያነበቡትን ምንባብ ጭብጥ በአጭሩ መግለጽ


- - ለቃላት አውዳዊ ፍች መስጠት

ለትምህርቱ የተሰጠው ጊዜ፡- 1፡20

የትምህርቱ ዓላማ፡- ከዚህ ክፍለጊዜ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-

-ስለገጸባህርያት እንቅስቃሴና አመለካከት በአዕምሯቸው የሚፈጠረውን ምስልይገልጻሉ፡፡

-የገጸባህርያትን መልክ፣ጸባይና ባህርይ ይለያሉ፡

-ያነበቡትን ምንባብ ጭብጥ በአጭሩ ይገልጻሉ፡፡

-ለቃላት አውዳዊ ፍች ይሰጣሉ፡፡

~ 52 ~
ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች
1. እውነት ተደብቆ የሚቀር ይመስላችኋል?
2. በጣም የምትወዱት ጓደኛችሁ ዋሽቷችሁ ብታገኙት ምን ታደርጋላችሁ?
3. በጓደኛሞች መካከል በግልጽ መነጋገር ከሌለ ምን ሊፈጠር የሚችል ይመስላችኋል?
ምንባብ
በጣም ቆንጆ ነበረች፡፡ ሰዎች ስለአይኖቿ፣ስለጥርሶቿ፣ስለከንፈሮቿ፣ስለባቶቿ፣ስለዳሌዋ፣በጠቅላላው ስለደም ግባቷ
ይነጋገሩበት ነበር፡፡ እድሜዋ አስራ ስምንት ዓመት፣ቁመቷ ደልዳላ ነበር፡፡ ልብሶቿ ደግሞ በከፍተኛ ሞዴል የሚሰፉ
ነበሩ፡፡ ስሟም አልማዝ ደምሴ ይባል ነበር፡፡
አባትየው አቶ ደምሴ አበበ፣ጠይም ደግሞም በጣም ወፍራም ሰውነታቸው ከብዷቸው፣ሲተነፍሱ ኩንታል ተጭና
አቀበት እንደምትወጣ አህያ የሚያቃስቱ ላባቸው ደግሞ እንዲሁ ከሜዳ ደርሶ በአንድ በኩል ቢሉት በአንድ
እያመለጠ የሚጎርፍባቸው ሰው ነበሩ፡፡ አቶ ደምሴ ሞልቶ የተረፋቸው ጌታ ነበሩ፤ በማነኛውም ስዓት እያቃሰቱ
ከየትኛውም ኪስ ሲገቡ እጃቸው መዞት የሚወጣው ገንዘብ የአስር የሃምሳ ደግሞም የመቶብር ኖት ብቻ ነበር፡፡
አልማዝ ሃያ ብር ስትጠይቅ የምትሰጠው ሃምሳ፣ስልሳአምስት ስትጠይቅ መቶብር ነበር፡፡
የታሪካችን አንዱ ሌላው ጎልማሳ አድማሱ አየለ ግን ከትምህርት ቤት ስራ ሊይዝ በወጣበት ጊዜ ወር እስኪደርስ
የሚጠጋበት የወላጆቹ ፍቅርና የዘመድ ቤት አልነበረውም፡፡
አባቱ አቶ አየለ የሞቱት እሱ ገና የአራት ዓመት ህጻን ሳለ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ አድማሱ እንዲህ ቀላል ልጅ አልነበረም
እርግጥ ከትምህርት ቤት ሲወጣ ኑሮ ጭንቅ ሁኖበት ነበር፡፡ግን እያደር ሁሉንም በቶሎ ተላመደው፡፡ ስራ በያዘ
በሁለት ዓመቱ ጥርሱን ነክሶ ገንዘብ በመቆጠብ ቤትና መኪና ገዛ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ በስራውና በግብረገብነቱ
በአላፊዎች ዘንድ በጣም የተመሰገነና ሁልጊዜም ለከፍተኛ ደረጃ የሚታጭ ነበር፡፡
ለአንድ መልከ መልካም ኑሮውእንደዚህ ለተቃናለት ጎልማሳ ደግሞ የስመለከተው ደጉ ነገር በልጅነት በህግ አግብቶ
ወንድም ወይም እህት ከአብራኩ ማድረስ ነበር፡፡ አድማሱ አንድ ቀን ከስራው በአስራ ሁለት ስዓት ወጥቶ በመኪናው
ወደቤቱ ሲሄድ አልማዝን ከራስ መኮነን ድልድይ ወደሳባ ደረጃ ስታቋርጥ አገኛት፡፡ በአንድ ጊዜም ልቡ ስንጥቅ
አለበት፡፡ ደም ግባቷና አቋምዋ ማረከው፡፡ መኪናውን ወደ አንድ ጥግ ቦታ አቁሞ ቤቷን የዚያኑ እለት ኋላ ኋላዋ
ተከትሎ ሂዶ አየው፡፡ ማታውንም የፍቅር ደብዳቤ ጽፎ አድሮ ጧት ከቤቷ ስትወጣ ተጠባብቆ ሰጣት፡፡ በወርም
ውስጥ የከንፈር ዎዳጆችም ሆኑ፡፡ ወደሽርሽር ቦታዎች በየሳምንቱ ይዟት ይሄድ፣ደግሞም ብዙ ለመታሰቢያ የሚሆኑ
ነገሮች ይገዛላት ጀመር፡፡ አገባታለሁ ብሎ በቆረጠም ጊዜ ለወዳጆቹ ሁሉ ያስተዋውቃት ደግሞም ስለሷበሰፊው
ያወራላቸው ጀመር፡፡ ነገር ግን አንድአንድ በጣም ወዳጆቹ የሆኑ ሰዎች አድማሱ ከአልማዝ ጋር በመተዋወቁ
አልተደሰቱም ነበር፡፡ ምክንያቱም በጣም ቀረብ ብለው የሚያውቋት ሰዎች በአልማዝ ላይ ብዙ ነውር ነገር ያወሩባት
ነበር፡፡ መጥፎ ልጅ ነች ከየግብዣው አትታጣም ብዙ የከንፈር ወዳጆች አሏት፡፡ እሷ ግን ከሁሉም አብልጣ
የምትወደው ተሰማ የሚባለውን ልጅ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ይህንኑ ለአድማሱ አምጥተው ይነግሩት ነበር፡፡ ከነዚህም

~ 53 ~
ሰዎች መሀል አንዱ ደበበ የተባለው የአድማሱ የቅርብ ጓደኛው ነበር፡፡ አንድ ቀን ሁለቱ አድማሱና ደበበ ከቤት ቁጭ
ብለው ሲጨዋወቱ ከጭዋታ የተነሳ ደበበ ብድግ አድርጎ ፡-
‹‹አድማሱ ስማኝ ይች ልጅ ትቅርብህ፡፡ እርግጥ ነው ቆንጆ ናት፡፡አባቷም ሀብታም ናቸው፡፡ነገር ግን እሷ
የምታመጣልህ ሀብት ደግሞ መልኳም ቢሆን ምንም አያደርግልህም፡፡ ነግሬሀለሁ ኋላ ትጸጸታለህ፡፡ እሷ ለራሷ
በጣም የምትወደው ተሰማ የተባለ የከንፍር ወዳጅ አላት አሉ፡፡››አለው፡፡
አድማሱ መጀመሪያ ዝም ብሎ ደበበን ሲያዳምጠው ቆይቶ በኋላ እሱም በበኩሉ ብድግ ብሎ እየተንጎራደደ‹‹ሀሰት
ነው ደበበ አትስማ፣የሰው ወሬ ነው እሷ የምትወደው እኔን ብቻ ነው፡፡ ደግሞም መጀመሪያውኑ እንደተዋወቅን
ጊዜያት ሌላ የጠየቃት ወይም እሷ የምትወደው ልጅ ድንገት እንዳለ ብየ ጠይቄያታለሁ፡፡ነገር ግን አንድም ሰው
የለኝም ብላኛለች፡፡››አለው፡፡
ደበበም ባለመስማማት አኳኋን እራሱን እያከከ ‹‹እሷ ምኗሞኝነውና አለኝ ትልሃለች››አለው፡፡‹‹በግድ አልያዝኋት
ለምን አትለኝም ደግሞም እውነቱን ባትነግረኝም እሱን እግዚአብሄር ይወቀው፡፡ እኔ ግን የምወዳትን ለጋብቻም
የማስባትን ልጅ የምትነግረኝን ሁሉ ማመን አለብኝ፡፡››
‹‹እንግዲህ አንተ!እሷፈጽማ ከቃሌ ወጥታ አታውቅም፡፡ ደግሞም አትወጣም፣ተሰማ የሚባልም የከንፈር ወዳጅ
ውሸት ነው የላትም …አይደለም የምትለው››ብሎ ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ፡፡››
‹‹እሽ፡፡ እሱ እንዳልክ ይሁን፡፡ ነገር ግን እኔ አንድ ነገር እንድታደርግልኝ ብጠይቅህ ለኔ ስትል
ታደርግልኛለህ?››አድማሱም አይሆንም በማለት ሊያስቀይመው ስላልፈለገ የጠየቀውን ነገር ሊፈጽም ‹‹እሽ
አደርጋለሁ››አለው፡፡
‹‹የፊታችን ቅዳሜ የነአልማዝ ትምህርት ቤት የዳንስ ቀን ነው፡፡ የሚደረገውም በእቴጌ ሆቴል ነው፡፡››
አድማሱ ተገርሞ፡-‹‹አወ ነግራኛለች፡፡ግን አንተ እንዴት አወቅህ? ››ብሎ ጠየቀው፡፡
‹‹ግድ የለህም እሱን፡፡የነገረችህ እዚያ አብራችሁ እንድትሄዱ ነው?››
‹‹አዎን ብቻ እኔ ገና አልቆረጥሁም፡፡››
‹‹ደግ እንግዲያውስ አትሂድ፡፡ እሷንም አትሂጅ በላት፡፡››
‹‹ለምን?››
ልነግርህ አይደለም፡፡ እሷን አትሂጅ ካልሀት በኋላ አንተ ማታውኑ እቴጌ ሆቴል ሄደህ እበሩ አጠገብ ተደብቀህ
ጠብቃት፡፡ምን አለ በለኝ አድማሱ ሀሰት ቢሆን፡፡እሷን እዚያው ተሰማ ከሚባለው ልጅ ጋር ስትገባ ታገኛታለህ፡፡

*ደበበ አድማሱን ይህንን ያህል የሚወተውተው ለምን ይመሰስላችኋል?


*አድማሱ የደበበን ሃሳብ ተቀብሎ እቴጌ ሆቴል ሂዶ ተደብቆ ማየት አለበት ብላችሁ ታምናላችሁ?ለምን?
*አድማሱ አልማዝን ከተሰማ ጋር ቢያገኛት ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?
*ከቀሪው የምንባብ ክፍል ምን ትጠብቃላችሁ?

~ 54 ~
አድማሱ በዚህ ጊዜ ደበበ አልማዝ ላይ ስላለው ዝቅተኛ ግምት በጣም አዘነ፡፡ ሆኖም ቃል ገብቶለት ነበርና እንዳለው
አደረገ፡፡ አልማዝ ግን ከዚያሁሉአዳራሹ በየደቂቃው በበሩ እየተቀበለ ከሚያስገባው አጀብ ከአንዱም ዘንድ
አልነበረችም፡፡ከምሽቱ አራት ስዓት ሲሆን የደስታው ተካፋይዎች መምጣትን ፈጽመው እንዳቆሙ አድማሱ
ተነስቶወደቤቱ ሄደ፡፡ደበበንም ሰምቶአልማዝን በመጠርጠሩ ሌሊቱን በሞላ ሲያዝን አደረ፡፡ በበነጋው ጥዋት አድማሱ
ከመኝታው ሳይነሳ በር ተንኳኳ ያንኳኳውም ደበበ ነበረ፡፡ እንደገባም አድማሱን፡-
‹‹ታዲያስ!ትላንት ማታ ሂደህ ነበር ወይ!››ብሎ ጠየቀው፡፡
አድማሱም ረጋ ብሎ፡-‹‹አዎ ሂጀነበር፤ነገር ግን አንተ እንዳልከው አልማዝ እዚያ አልመጣችም››አለው፡፡
ደበበ ግን በማንጓጠጥ አኳኋን አፉን ገጥሞ አፍንጫውን ነፋ አድርጎ ‹‹አልማዝ ትላንትና ማታ እዚያ ነበረች
አለው፡፡››
አድማሱ በዚህ ጊዜ ደሙ ፈላ፡፡ ያንቀጠቅጠውም ጀመር፡፡
‹‹ውሸታም ነህ!፡፡እኔ ይህንኑ ፈርቼ ከምሽቱ እስከ አራት ስዓት ተሩብ እዚያው ነበረሁ፡፡ እንግዲህ አጭሩን ልንገርህ
ስማ፡፡ አልማዝ አንተ እንደምታስባት አይደለችም ደግሞም እዚያ አልነበረችም››አለው፡፡
‹‹ነበረች አልሁህ፡፡››
‹‹አድማሱም እንደዚያው አይኖቹ በንዴት ደም እንደለበሱ ሆኖ፡፡››
‹‹ዝም በለኝ አንተ ሰው፡፡ በቅቶኛል የአንተ ንግግር፡፡››አለው፡፡
ደበበ ግን ምንም ቅር ሳይሰኝ ቀጠል አድርጎ፡-
‹‹ሦስት ስዓት ከሩብ ላይ አንዲት ሴት ልጅ ረዥም የተንዘረፈፈና ኩፍ ያለቀሚስ ለብሳ ጥቁር የጌጥ ባርኔጣ አድርጋ
ፊቷን ከባርኔጣው ዙሪያ በተዘረፈፈው ጥቁር ዓይነእርግብ ሸፍና የአንድ ጥቁር ሱፍ ከላይ እስከታች የለበሰ ረዘም ያለ
መልከ ቀና ወጣት ክንድ እቅፍ ስትገባ አላየህም?››ብሎ ጠየቀው፡፡
አድማሱም ይችን ደበበ የገለጻትን ልጅ አይቷት ነበር፡፡ማየቱን ሊገልጽለት ፊቱን መለስ አደረገ፡፡
‹‹ይኸውልህ እሷልጅ አልማዝ ነበረች፡፡እኔም ይኸው ይፈጠራል ብየ በማሰብ ከአዳራሹውስጥ ገብቼተደብቄ
እጠባበቅ ነበር፡፡አይነእርግቡንና ቆቡን ስታነሳ ለየኋት፡፡ክንዱንም ያቀፈችው ልጅ ተሰማ የተባለው ነው፡፡››
አድማሱ ምንም ሳይል ወደ በሩ ተነስቶሄዶ መዚጊያውን ከፍቶ ደበበን ‹‹ከቤቴ ውጣልኝ ይህንን ጊዜ
የምትተበትበው ማን ያውቃል ከኔጋር አጣልተህ አንተ ልታገባት አቅደህ ይሆናል፡፡››አለው፡፡
‹‹እኔ!››
‹‹አዎ አንተ፡፡››
‹‹አድማሱ እንደዚህ አልክ!››
‹‹አዎ አለኩ፡፡››

~ 55 ~
ከዚያ በኋላ አድማሱና ደበበ ተቆራረጡ፡፡ የሰርጉ ዝግጅት በሁለቱም ቤት ተጧጡፎ ቀጥሎ ሳለ አልማዝ አንድቀን
ጧት እቤቷ ከማድቤት ወደአዳራሽ ስታልፍ አደናቅፏት ወድቃ በጣም ታመመች፡፡ ሀኪም ቤት ቢወስዷት ትርፍ
አንጀት ነው ተባለ፡፡ በዚህ ጊዜ ለሰርጋቸው የቀረው ሃያ አንድ ቀን ብቻ ነበር፡፡ነገርግን የግድ ከሰርጋቸው በፊት
አልማዝ ሆዷን የምትቀደድ ሆነች፣እሷም በጣም ፈርታ ነበር፡፡ አድማሱም አይዞሽ አትፍሪ ቀላልነው፡፡ እሩቅ ሳትሄጅ
እኔ እራሴ የዛሬ ስድስት ዓመት ተቀድጀ ነበር እይው ጤናማ ሁኘእስካሁን አለሁ፡፡ እርግጥ እንደተቀደድሽ ለሃያና
ለሰላሳ ደቂቃዎች ያህል እራስሽን ሳታውቂ ትቃዣለሽ፡፡ እኔ ለምሳሌ በተቀደድሁበት ጊዜ ከትምህርት ቤታችን
አንደኛ ቡድን ኳስ ተጫዋቾች አንዱ ነበርኩ፡፡ ልቀደድ በተኛሁበት ሳምንት ታዲያ የኛ ቡድንና የአንድ ሌላ ትምህርት
ቤት አንደኛ ቡድን የመጨረሻ የብር ዋንጫ ሽልማት ግጥሚያ ነበር፡፡ ሰሞኑን ከተጫዋቾች ጓደኞቸ መሃል ጥቂቶቹ
ሀኪም ቤት ድረስ እየመጡ በእንዴት ያለ ዝግጅት መግጠም እንዳለባቸው እንነጋገር ነበር፡፡ እኔም መሰንበቻውን
ሁሉእንዳንሸነፍ በጣም ሳስብ ነበር፡፡ የተቀደድሁ እለት ታዲያ እየጮህኩ‹‹መሸነፍ የለብንም!መሸነፍ የለብንም!
ዋንጫው ከእኛ እጅመውጣት የለበትም!››አልሁኝ አሉ፡፡
አልማዝም የምትቀደድበት ቀን ደረሰ፡፡ ኦፕራሲዎኑም የአርባ ደቂቃ ጊዜ ወሰደ፡፡ አድማሱም በዚህ ጊዜ ጨንቆት
ወዲያና ወዲህ እየተንቆራረጠ ይጸልይ ነበር፡፡ ከመቀደጃውም ቤት ወደክፍሏ መለሷት፡፡አድማሱም እስክትነቃለት
ድረስ ከእናትና ከአባቷጋር ክፍሏ ውስጥ ገብቶብቻውን ወዲያና ወዲህ ሲቆራጠጥ ቆየ፡፡ ከሃያ ደቂቃ በኋለም
አልማዝ ተንቀሳቀሰች፡፡ አድማሱም የደስታ እንባ አንቆት አልጋው ስር ሂዶ ተንበረከከ፡፡ ቀጥሎም ከአልማዝ ድምጽ
ወጣ፡፡
ተሰማ!…ተሰማ!…ተሰምዬ!
ምንጭ፡-(ታደሰ ሊበን፣1952፣ሌላው መንገድ፣ገጽ 15-31) ለማስተማሪያ እንዲመች ተሸሽሎ የተወሰደ፡፡

መመሪያ አንድ፡- ቀጥሎ የቀረቡ ጥያቄዎችን በምንባቡ መሰረት ትክክል ከሆኑ እውነት ትክክል ካልሆኑ ደግሞ ሐሰት
በማለት መልሱ፡፡
1. ደበበ አድማሱ አልማዝን እንዲተዋት የሚወተውተው እሱ ሊያገባት ስለፈለገ ነው፡፡
2. አልማዝ ፈጽሞ ተሰማ የሚባል ልጅ አታውቅም ብሎ መደምደም ይቻላል፡፡
3. አድማሱ ደበበ ‹‹የምልህን አድርግልኝ›› ሲለው እሽ ያለው በነገሩ አምኖበት ሳይሆን ማስቀየም ስላልፈለገ
ነው፡፡
4. ለአድማሱ አልማዝ ትቅርብህ ብሎ አስተያየት የሰጠ ደበበ ብቻ ነበር፡፡
5. አድማሱ አልማዝን ከማደንዘዣ እስከምትነቃ ይጠብቅ የነበር ከጓደኞቹ ጋር በመሆን ነው፡፡

መመሪያ ሁለት፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት በቃል ትክክለኛውን መልስ ስጡ፡፡

1. አልማዝ አድማሱን የተዋወቀችው በስንት አመቷ ነው?

~ 56 ~
2. አድማሱና ደበበ የሚጨቃጨቁት በምን ምክንያት ነበር?
3. የአልማዝ ቀዶ ጥገና ምን ያህል ጊዜ የፈጀ ነበር?
4. አድማሱ አልማዝን ለመጀመሪያ ጊዜ ያያት የት ነበር?
5. የአድማሱና የደበበ ጓደንነት የተጀመረው ከየት ነው?
6. አድማሱና አልማዝ የከንፈር ወዳጅ ለመሆን የፈጀባቸው ጊዜ ምን ያህል ነበር?
7. አልማዝ የታመመችው ምን ነበር?
8. የነአልማዝ ትምህርት ቤት የዳንስ ቀን የተከበረው የት ነበር?

መመሪያ ሶስት፡- ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ
ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. ‹‹ሰዎች ይነጋገሩበት ነበር›› የተባለው በምኗ ነው?
ሀ.በባህሪዋ ለ.በትምህርቷ ሐ.በቁንጅናዋ መ.በህመሟ
2. አድማሱና ደበበ የተቆራረጡት በምን ምክንያት ነው?
ሀ.ደበበ አድማሱን በመዋሸቱ ለ.አድማሱ ደበበን ሚስጥር በመደበቁ
ሐ.ደበበ ለአድማሱ አልማዝ እንደማትሆነው በመግለጹ መ.ደበበ ራስ ወዳድ በመሆኑ
3. የአድማሱ አባት አቶ አየለ የሞቱት አድማሱ የስንት ዓመት ህጻን እያለ ነበር?
ሀ.የአስር ዓመት ለ.የአራት ዓመት ሐ.የስምንት ዓመት መ.የስድስት ዓመት
4. ተጭና አቀበት ከምትወጣ አህያ ጋር የተወዳደረው ማን ነው?
ሀ.አድማሱ ለ.አቶ ደምሴ ሐ.ደበበ መ.ተሰማ
5. በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው መልክት ምንድን ነው? ሀ.ጓደኛ በትዳር ውስጥ ጣልቃ መግባት
እንደሌለበት ለ.ትዳር ለመመስረት መጠናናት እንደሚያስፈልግ ሐ.የፍቅር ጓደኛ የሚለውን ሁሉ ማመን
ተገቢ መሆኑን መ.ሰዎችን መጠራጠር ተገቢ አለመሆኑን
6. አድማሱ ቤትና መኪና የገዛ ስራ በያዘ በስንት ዓመቱ ነው? ሀ.በአምስት ለ.በአስር ሐ.በአራት መ.በሁለት
7. አድማሱ ለአልማዝ የፍቅር ደብዳቤ የሰጣት በአያት በስንተኛ ቀኑ ነበር? ሀ.በወሩ ለ.በዓመቱ
ሐ.በሳምንቱ መ.በማግስቱ
8. አድማሱ ከአልማዝ ጋር በመተዋወቁ የአድማሱ ጓደኞች ያልተደሰቱበት ምክንያት ምን ነበር?
ሀ.አልማዝ በትምህርቷ ጎበዝ ስላልነበረች ለ.አልማዝ የሀብታም ልጅ ስላልነበረች
ሐ.አልማዝ ቆንጆ ልጅ ስላልነበረች መ.አልማዝ በባህሪዋ ምስጉን ስላልነበረች
9. በደበበ አባባል አልማዝ ከተሰማ ጋር ወደ እቴጌ ሆቴል የገባችው በስንት ስዓት ነበር?
ሀ. በሦስት ስዓት ከሩብ ለ. አራት ስዓት ከሩብ
ሐ.ሁለት ስዓት ተኩል መ. በአንድ ስዓት ተኩል
~ 57 ~
10. አልማዝና አድማሱ በትዳር እንደማይቀጥሉ የሚያመላክተው አንቀጽ የቱ ነው?
ሀ.የመጀመሪያው ለ.የሶስተኛው ሐ.የመጨረሻው መ.ስድስተኛው

መመሪያ አራት፡-ለሚከተሉት ከምንባቡ ለወጡ ቃላት አውዳዊ ፍች ስጡ፡፡


1.አብራክ
2.መታሰቢ
3.ደሙ ፈላ
4.ዓይነ እርግብ
5.ጥርሱን ነክሶ
መመሪያ አምስት፡-ለሚከተሉት ጥያቄዎች በጽሁፍ መልስ ስጡ፡፡
1. ስለአልማዝ ተገቢ መረጃዎችን በመሰብሰብ ውስጣዊና ውጫዊ ማንነቷን ግለጹ፡፡
2. እንደደበበ አይነት ጓደኛ እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ? ለምን?
3. እናንተ አድማሱን ብትሆኑ ምን ታደርጋላችሁ?

መርጃ መሳሪያ፡- ሌላው መንገድ

ግምገማ ፡-የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎችን መልስ መገምገም

- የግል ስራቸውን ማረም

ክፍለ ትምህርት ሶስት


የትምህርት ርዕስ፡-የምንባቡን ፍሬ ሃሳብ በአጭሩ በግለጽ
-ስለገጸባህርያቱ በአዕመሯቸው ምስል ይፈጥራሉ
-የገጸባህርያትን እንቅስቃሴና አመለካከት መለየት
-የገጸባህርያትን የአካልና የማንነት ገለጻ ከታሪኩ ሁነቶች ጋር ያለውን መያዝ መለየት
-ያነበቡትን ልቦለድ ታሪክ በጊዜና በቦታ ቅደምተከተል ማቅረብ
-ለቃላት አውዳዊ ፍች መስጠት
ለትምህርቱ የተሰጠው ጊዜ ፡- 1፡20
የትምህርቱ አላማ ፡-ከዚህ ክፍለጊዜ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
-የምንባቡን ፍሬ ሃሳብ በአጭሩ ይገልጻሉ
-ስለገጸባህርያቱ በአዕምሯቸው የተፈጠረውን ምስል ይገልጻሉ

~ 58 ~
-የገጸባህርያትን እንቅስቃሴና አመለካከት ይለያሉ
-የገጸባህርያትን የአካልናየማንነት ገለጻ ከታሪኩ ሁነቶች ጋር ያለውን ትስስር ያስረዳሉ
--ያነበቡትን ልቦለድ ታሪክ በጊዜና በቦታ ቅደም ተከተል ያቀርባሉ፡፡
-ለቃላት አውዳዊ ፍች ይሰጣሉ፡፡

ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች

1. ባህል ምንድን ነው?


2. በአካባቢያችሁ ያሉ ጠቃሚና ጎጅ ባህሎች ምን ምን ናቸው?
3. ጋብቻ በተጋቢዎች ፈቃደኝነት ላይ ካልተመሰረተ ምን የሚፈጠር ይመስላችኋል?
4. የምታውቁትን አንድ ብሔረሰብ የጋብቻ ባህል ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ?
አንቻቦ
በዐይነ ሕሌናው አያት-ጋንዘርን፡፡ አስር አመት ያህል በእድሜ ይበልጣታል፡፡ በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ከብቶቻቸውን ጨሌ
ሲያግጡ፣ እዚያው ከብት ከሚጠብቁበት ስፍራ ላምም ሆነ ፍየል አልበው በአንድ ጮጮ ወተት ጠጥተዋል፡፡ እንደ
አብዛኞቹ የሙርሲ ልጃገረዶች ረዘም፣ፈርጠም ያላለች፣ከንፈሯደም እንደቋጠረ ስጋ ያላበጠ፣ ጥርሷ ከንፈሯን
አልፎ ያላገጠጠ በጥቁር አካሏ ላይ በስሱ የሚፍለቀለቅ በረዶ መሳይ ጥርስ ያላት ዐይናማ ልጅ ነበረች፣ ያኔ
ሲያውቃት፡፡ አሁን አስራ ስድስት አመቷ ነው፡፡ የባህል እዳ ሆኖባት ‹‹የበለጠ እንድታምር››፣ ለቤተሰቦቿ ብዙ ጥሎሽ
እንድታስገኝ እንደእናቶቿ ወግ ከንፈሯን ክብ ከተተለተለች ሁለት አመት አልፏታል፡፡
‹‹ሰው ሰራሽ ውበት የሚያስፈልገው ለመልከ ጥፉዎች ነው፡፡ መልከቀናዎቹን መልከጥፉ ለምን እናደርጋለን የጋዘር
እናት? …››ብሎ የጋዘርን ከንፈር ለመተልተል የተዘጋጀው ስለት ሲፋጭ እንደዋዛ የጠየቀው ትዝ አለው፡፡
‹‹የአያት የቅድመ-አያት ልማዳችንን አስቀሩ በለና! ይኸው ነው የቀረህ፡፡››
የጋዘር እናት ትንታግ ምላስ እንዴት እንደገረፈው፣ ጎሪጥ ዐይናቸው እንዴት እንደገረመመው ታወሰው፡፡ ጋዘር፣
ለእርድ እንደቀረበ ፍየል ስለት ከቧት፣ አንዱ እጇን፣ ሌላው እግሯን በገመድ አስሮ፣ ጉልበት ያለው ተመርጦ እራሷን
በግድ ጠፍሮ፣ የታችኛው ከንፈሯ ግማሽ ክብ በመስመር ሲተለተል የፈሰሰው ደም በሰቀቀን ታወሰው፡፡ ጋዘር ስለት
ሲያርፍባት እንደታረደ ከብት የጮኸችው ተሰምቶት ከሃሳቡ ባነነ፡፡
‹‹መልካም ልማድ እንጅ ጎጅና ክፉ ልማድ እንዴት ይወረሳል? አያት ያጠፋውን አባት እያለማ፣ አባት ያበላሸውን
ልጅ እያሻሻል ሲገኝ ይመስለኛል በጎው ነገር››አለ አንቻቦ፣ እንባ የቋጠሩ ዐይኖቹን ወደ ጠራው ሰማይ ወርውሮ፡፡
በውስጡ አፍኖ ይዞት የነበረው ፍቅር የጠፋው ያንጊዜ ነው፤ ከንፈሯ በስለት ተተልትሎ እንደጎርፍ የወረደው ደም
ከተንጋለለችበት ላይ ሲረጋ-ነቃ፡፡
አባቱ ጋዘርን ለልጃቸው ሚስትነት ጠይቀው ተፈቅዶላቸዋል፡፡ የከንፈሯ መተልተል የሚያስከትለውን ጥሎሽም
ለመክፈል ተስማምተዋል፡፡ ጋዘር ‹‹ከንፈሯን ተተለተለች፤ክብ ሸክላ በከንፈሯ ወጠረች፤ቀለበት ትልትል ከንፈሯን
በጭንቅላቷ አጠለቀች››የማለትን ‹‹የምስራች›› ሲሰሙ በባህላቸውና በልማዳቸው መሰረት ወይፈን አርደው
ወዳጅ ዘመድ ጋብዘው ሸለሉ፤ ፎከሩ፡፡

~ 59 ~
በድግሱ ቀን ‹‹ከደም ጋር የተቀላቀለውን ፈርስ አምጡና ይታጠብ! ለሶስት ጉልቻ ልትበቃ ነውና እንደአባቶቻችን
ወግ ጎንበስ ብለህ ታጠብ!›› ብለው ልጅ የመዳር ወግ ደርሷቸው ሁለመናቸው ፈክቶ አንቻቦን አዘዙት፡፡

1. ከአነበባችሁት ምንባብ ምን ተረዳችሁ?


2. ቀጥሎ ምን ሊፈጠር ይችላል ብላችሁ ትገምታላችሁ?
3. አንቻቦ ጥያቄውን የሚቀበል ይመስላችኋል?

እሱ ግን የአባቱን ቀርቶ የዚያን ሁሉ ሰው ጉርጥርጥ ዐይን ከቁም ነገር አልቆጠረውም፡፡


‹‹አንተን እኮ ነው!›› አሉት አባቱ አፋቸው ተያይዞ፡፡
በንዴት ‹‹ ኧረ አንድ በለኝ ጎሳ!›› ብለው እዚያ የተሰበሰበውን ትንሹንም ትልቁንም ተማጸኑ፡፡ የጎሳውን
ልማድ እንዲፈጽም የሚያደርግ ግን አልተገኘም፡፡
‹‹አልቀበለውም! ›› በማለት አንቻቦ ፈርጠም ብሎ ምላሽ ሰጠ- ለአባቱ፡፡
‹‹ምኑን ነው የማትቀበለው?›› ቁጣቸውን ደብቀው በለዘበ አንደበት ጠየቁት አባቱ፡፡
በደምና በፈርስ መታጠቡንም ሆነ የመረጣችሁልኝን ጋብቻ አልቀበለውም፡፡››
ቁጣቸው አገረሸባቸው፡፡ ከውስጣቸው የሚወጣው ነበልባል አንቻቦን ሳይሆን እሳቸውን መልሶ ሲገርፋቸው
ተሰማቸው፡፡
‹‹ሰድበኸኛል! አዋርደኸኛል! አይማረኝ! አልምርህም!›› የሰራ አካላቸው ተንዘፈዘፈ፡፡
‹‹የማልፈልገውን ጋብቻ አልቀበልም ማለት ስድብ አይደለም! ››
‹‹ እንዴት?››
‹‹እኔ የምፈልገው ውበትን ነው፡፡ ያልተበላሸ ውበት! የፈለኩትን ውበት አጥፍታችሁ የጠላሁትን እንድወድ
ልታስገድዱኝ አትችሉም፡፡›› ከወትሮው ኮስተር ብሎ ለአባቱ ብቻ ሳይሆን እዚያ ለተሰበሰቡት የጎሳው አባላት
ተናገረ፡፡
‹‹አሁን ሌላ የምጠይቅህ የለኝም፡፡ ያስቀየምኩትን የልጅትን ቤተሰብ ብቻ ካስልኝ፡፡ ያስቆጠርኩትን ጥሎሽ እጥፍ
አድርገህ ለመክፈል ቃል ግባልኝ፡፡››
‹‹ያልበላሁትን እዳ ለመክፈል የምገባው ቃል የለኝም!›› አባቱ ይህንን ምላሹን ሲሰሙ ከግርግሩ ቀለበት እመር
ብለው በመስፈንጠር ወደኋላ አፈገፈጉ፡፡ የአብራካቸውን ክፋይ ወሰኑበት እንደ ህጻን ልጅ አቅፈው ሲያዘናፍሉት
የነበረውን ጠመንጃ አቀባብለው ምላጩን ሳቡ፡፡ ጋዘር በማይታመን ፍጥነት ተወርውራ አፈሙዙን ስትመታው
ጥይቱ ኢላማውን ስቶ ባረቀ፡፡
በዚህ አጭር ጊዜ የደረሰበትን የህይወት ውጣውረድ አስታውሶ ‹‹ጊዜው እንዴት ይነጉዳል?›› አለ አንቻቦ ከኦሞ
ወንዝ ዳርቻ ተቀምጦ የማታ ፀሐይ የሚሞቀውን አዞ እያስተዋለ፡፡
(ምንጭ ፡- የቀድሞው አማርኛ 9 ኛ ክፍል (1997) የመማሪያ መጽሐፍ)

~ 60 ~
መመሪያ አንድ፡- የሚከተሉት ከምንባቡ የወጡ ጥያቄዎች ናቸው በቡድን ተወያይታችሁ ተገቢ መልስ ስጡ፡፡

1. ጥይቱ ዒላማውን ስቶ እንዲባርቅ ያደረገችው ማን ናት? ለምን?


2. መልካም ልማድ እንጅ ጎጅና ክፉ ልማድ መወረስ የለበትም በሚለው ሃሳብ የሚስማሙት እነማን ናቸው?
የማይስማሙትስ?
3. የአያት የቅድመ አያት ልማዳችንን አስቀሩ በለና በማለት የተናገሩት የጋዘር እናት ሀሳብ ተቀባይነት አለው
ብላችሁ ታምናላችሁ? ለምን?
4. የአንቻቦን ትዝታ የቀሰቀሰው ምንድን ነው?
5. ያልበላሁትነ እዳ ለመክፈል የምገባው ቃል የለኝም ያለበት ምክንያት ምንድን ነው?
መመሪያ ሁለት፡ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና በማንበብ
ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. .የአንቻቦን አባት በደስታ ያስፈነጠዘው ጉዳይ ምንድን ነው?
ሀ. ወንድ ልጅ መውለዱ ለ. ልጅ የመዳር ወግ ስለደረሰው
ሐ. ልጁ ደም በተቀላቀለበት ፈርስ መታጠቡ መ. ወዳጅ ዘመድ ጠርቶ መጋበዙ
2. ጋዘር ከንሯን የተተለተለችበት ትክክለኛ ምክንያት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የበለጠ እንድታምር ለ. ለቤተሰቦቿ ብዙ ጥሎሽ እንድታስገኝ
ሐ. ሰው ሰራሽ ውበት አስፈላጊ በመሆኑ መ. የአያት የቅድመአያት ልማድ ላለማስቀረት
3. የጋዘር እናት ትንታግ ምላስ የገረፈው ማንን ነው?
ሀ. አንቻቦን ለ. የአንቻቦን አባት ሐ. የጎሳውን አባላት መ. የጋዘርን አባት
4. አንቻቦ ጋብቻውን አልቀበለውም ያለበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. የአባቱን ትዛዝ ላለመፈጸም ለ. ጋዘር ቆንጆ ስላልሆነች
ሐ. ልማዱን ስለሚቃወም መ. ባለጌ ስለሆነ
5.የአንቻቦ አባት ‹‹ሰድበኸኛል! አዋርደኸኛል! አይማረኝ! አልምርህም!›› ያሉበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ.ልጃቸው በሰው መሐል ስለሰደባቸ ለ. የማፈልገውን ጋብቻ አልቀበልም ስላለ
ሐ. ልጃቸው በፈርስና በደም ስለታጠበ መ. ልጃቸው የማህበረሰቡን ወግና ባህል ስለጣሰ
5. የተቆጠረውን ጥሎሽ እጥፍ አድርጎ እንዲከፍል የተጠየቀው ማን ነው?
ሀ. የጋዘር አባት ለ. የአንቻቦ አባት ሐ. ጋዘር መ. አንቻቦ
6. የአንቻቦን አባትና የጋዘርን እናት አንድ የሚያደርጋቸው ምንድን ነው?
ሀ. ልጅ የመዳር ወግ ስለደረሳቸው ለ. ሁለቱም የልማዱ ተገዥ መሆናቸው ሐ. ሁለቱም
ሐብታም መሆናቸው መ.ሁለቱም ወንድ ልጅ ስላላቸው
7. ጋዘር ከንፈሯን የተተለተለችው በስንት አመቷ ነው?
ሀ. በአስራ ስድስት ለ በአስራ አራት ሐ. በሃያ ስድስት መ. በአስር

~ 61 ~
8. ለሶስት ጉልቻ ልትበቃ ነው የሚለው ዓ/ነገር ምንን ይገልጻል?
ሀ. ትዳር ልትመሰርት ነው ለ. በደምና በፈርስ ልትታጠብ ነው
ሐ. ከንፈሯ ሊተለተል ነው መ. ልጅ ልትወልድ ነው
9. የአብራካቸውን ክፋይ ወሰኑበት ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ሊድሩት ወሰኑ ለ. ሊገድሉት ወሰኑ
ሐ. በደም ሊያጥቡት ወሰኑ መ. ያልበላውን እዳ ሊያስከፍሉት ወሰኑ

መመሪያ ሶስት፡- ለሚከተሉት ከምንባቡ ለወጡ ቃላት አውዳዊ ፍች ስጡ፡፡

1. የአብራክ ክፋይ

2. ውርስ
3. ትንታግ
4. ውበት
5. ጮጮ

መመሪያ አራት፡- የሚከተሉት ከምንባቡ የወጡ ጥያቄዎች ናቸው ለያንዳንዱ ጥያቄ አራት አራት ምርጫዎች
ቀርበዋል ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡
1. .አንቻቦ ‹‹እኔ የምፈልገው ውበት ነው ያልተበላሸ ውበት››ያለበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. ጋዘር ውበት ስለሌላት ለ. የጋዘር ውበት በልማዱ ምክንያት ስለጨመረ
ሐ. ጋዘር ከንፈሯ በመተልተሉ ውበቷ ስለተበላሸ መ. በደም መታጠብ ውበትን ስለሚቀንስ
2. የአንቻቦ እድሜ ስንት ነው?
ሀ. አስራ ስድስት ለ. ሃያ ስድስት ሐ. ሰላሳ ስድስት መ. ሃያ አራት
3. አንቻቦ በውስጡ አፍኖ ይዞት የነበረው ፍቅር የጠፋው በምን ምክንያት ነው?
ሀ. ከንፈሯ በስለት ተተልትሎ ደም እንደ ጎርፍ ሲወርድ በማየቱ
ለ. ጋዘር ለእርድ እንደቀረበ ፍየል ስለት ከቧት በማየቱ
ሐ. እጅ እና እግሯን በገመድ ስትታሰር በማየቱ
መ. ከንፈሯ ግማሽ ክብ በመስመር ተተልትሎ በማየቱ
4. በምንባቡ መሰረት የእናት ወግ የተባለው ምንድን ነው?
ሀ. ባል ማግባት ለ. ልጅ መውለድ ሐ. ከንፈር መተልተል መ. ጥሎሽ ማስጣል

~ 62 ~
5. ጋዘርና አንቻቦ በኦሞ ወንዝ ዳርቻ ከሰሯቸው ስራዎች ውስጥ አንቻቦ የሚያስታውሰው የቱን ነው?
ሀ. የወንዙን አካባቢ እየተዘዋወሩ መጎብኘታቸውን
ለ. ላምም ሆነ ፍየል አልበው በአንድ ጮጮ ቀተት መጠጣታቸውን
ሐ. ከንፈሯን በግማሽ ክብ መተልተሏን
መ. አንቻቦን ለመግደል አባቱ ሲተኩስ አፈሙዙን በመምታት ኢላማ ማሳቷን
6. ጋዘር ከንፈሯን በምትተለተልበት ወቅት ጉልበት ያላቸው ሰዎች ተመርጠው ያከናወኑት ተግባር
ምንድን ነው?
ሀ. ሁለቱን እጆቿን መያዝ ለ. ስለቶችን ማቀራረብ
ሐ. እግሯን በገመድ ማሰር መ. እራሷን በግድ ጠፍሮ መያዝ
7. ጋዘር ‹‹ከንፈሯን ተተለተለች፤ክብ ሸክላ በከንፈሯ ወጠረች፤ቀለበት ትልትል ከንፈሯን በጭንቅላቷ
አጠለቀች››የማለትን ‹‹የምስራች›› ሲሰሙ በሚለው አገላለጽ ውስጥ የምስራች የሚለው በጥቅስ ምልክት
ውስጥ የተቀመጠበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. ፀሐፊው ያልተስማማበት መሆኑን ለመግለጽ
ለ. አንባቢያን ትኩረት ሰጥተው እንዲያነቡት ለማሳሰብ
ሐ. ቃሉ ለአንባቢ ያልተለመደ መሆኑን ለመግለጽ
መ. ከሌላ ሰው የተወሰደ ሐሳብ መሆኑን ለማሳየት
8. በምንባቡ ውስጥ ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት ምንድን ነው?
ሀ. አያት ቅድመአያት ያቆዩንን ልማድ ማስቀጠል የልጆች ተግባር እንደሆነ
ለ. አያት ወይም አባት ያበላሸውን ልጅ ማስተካከል እንዳለበት
ሐ. የተፈጥሮ ውበት ብቻ በቂ እንዳልሆነ
መ. ጋብቻ በቤተሰብ ፈቃድ ብቻ መመስረት እንዳለበት
9. በአይነ ህሌናው አያት ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. አሰተዋላት ለ. አስታወሳት ሐ. በአይኑ ገረፋት መ. ተመለከታት
10. አንቻቦ ጋዘርን በስንት ዓመት ይበልጣታል? ሀ.በአስር ለ.በአምስት ሐ.በሁለት መ.በአስራአምስት
መመሪያ አምስት፡-የሚከተሉትን የተፋለሱ ዓረፍተ ነገሮች በድርጊት ቅደም ተከተል አስተካክላችሁ አስቀምጡ፡፡
1. ጋዘር ከንፈሯን ተተለተለች፡፡
2. የአንቻቦ አባት ወይፈን አርደው ወዳጅ ዘመድ ጋበዙ፡፡
3. ጥይቱ ዒላማውን ስቶ ባረቀ፡፡
4. ጋዘር የጠመንጃውን አፈሙዝ መታችው፡
5. አንቻቦ ደም በተቀላቀለበት ፈርስ እንዲታጠብ ታዘዘ፡፡
6. የአንቻቦ አባት ጠመንጃ ተኮሱ፡፡

~ 63 ~
7. አንቻቦ ጋብቻውን እንደማይቀበል ገለጸ፡፡
መመሪያ ስድስት፡-የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጽሁፍ መልሱ፡፡
1. የአንቻቦንና የጋዘርን ውስጣዊና ውጫዊ ማንነት ከታሪኩ ሁነቶች ጋር በማያያዝ አቅርቡ?
2. ከአንቻቦና ከአባቱ አመለካከት የማንን ትደግፋላችሁ? ለምን?

የትምህርቱ መርጃ መሳሪያ፡-የቀድሞው አማርኛ ዘጠነኛ ክፍል መጽሃፍ


ግምገማ፡-የአንብቦ መረዳት የቃል ጥያቄዎችን መልስ መገምገም
- የቡድን ውይይታቸውን መገምገም
-የግል ስራቸውን ማረም

~ 64 ~
ክፍለ ትምህርትአራት
የትምህርቱ ርዕስ፡- የምንባቡን ፍሬ ሀሳብ በራሳቸው መንገድ በንግግር መግለጽ
የገጸባህርትን የአካልና የማንነት ገለጻ ከታሪኩ ሁነቶች ጋር በማያያዝ መግለጽ
ለቃላት እማሬአዊና ፍካሬአዊ ፍች መስጠት
ለትምህርቱ የተሰጠው ጊዜ 1፡20
የትምህርቱ ዓላማ፡- ከዚህ ክፍለጊዜ ትምህርት በኋላ ተማሪዎች፡-
-የምንባቡን ፍሬ ሃሳብ በራሳቸው መንገድ በንግግር ይገልጻሉ፡፡
-የገጸባህርያትንየአካልና የማንነት ገለጻ ከታሪኩ ሁነቶች ጋርበማያያዝ ይገልጻሉ፡፡
-ለቃላት እማሬአዊና ፍካሬአዊ ፍች ይሰጣሉ፡፡

ቅድመ ንባብ ጥያቄዎች


1. ወላጆች ስለምን ማውራት ያስደስታቸዋል?ለምን?
2. ህጻናት ትምህርት የሚጀምሩት ከየትና ከማን ነው?
3. ህጻናት ከማህበረሰቡ ባህል ውጭ የሆኑ ድርጊቶች ሲፈጽሙ ተመልክታችኋል? ምን?
4. ህጻናት መጥፎ ባህሪ እንዲኖራቸው ከሚያደርጉ ድርጊቶቻችን/አስተምሮዎቻችን/ ውስጥ እናንተ
የምታውቋቸውን ጥቀሱ?

ተማሪው
ወዳጀ አባቴ መሪ ጌታ መድሎት፣ወርቄ የተሰኘ ብላቴና አለው፡፡ ታዲያ እኔ በየሰንበቱ ልጠይቀው በሄድሁ ቁጥር
ወሬው በመላ ከወርቄ ፈቀቅ አይልም፡፡

አሁን ባለፈው እሁድ ሰላምታየን አስቀድሜ ወደ ጎጆው ገብቼ ብዙም አልቆየሁ፡፡ ያጣድፈኝ ጀመር፡፡

‹‹ብርቱነህ? የኑሮህ ይዞታስ?››

‹‹ጥሩ ነው!››

‹‹እጮኛ አበጀህ?››

‹‹የለም ገና ነኝ››

‹‹አብጅ እንጂ፡፡ አንዲቱን ፈልግና አግባት…አግብተህ ውለድ…››ዝም ብየ እሰማዋለሁ፡፡

‹‹…እውነት እልሀለሁ …መውለድን የሚያህል ጸጋ የለም…አሁን ወርቄን ተመውለዴ በፊት የነበረው ህይወቴ
ህይወት ነው?›› ከጥቂት እረፍት በኋላ፡፡

~ 65 ~
‹‹ሰማኸኝ- ወይ?››

‹‹እ››

‹‹ወርቄ አራት ዓመት ተመንፈቅ እንደሞላው ነግሬሀለሁ? የኔ ነገር አልነገርሁህም ለካ! አሁን የመማሪያ ጊዜው
ነው፤መምህሩ እኔው ነኝ፡፡ እሱም የዋዛ እንዳይመስልህ፡፡ አስቀድሜ ምን እንዳስተማርሁት ታውቃለህ?››

‹‹ፊደል ነው?››

‹‹የለም ስነ መግባር ነው፡፡ ከስነምግባር ክፍሎችስ አስቀድሜ ምን እንደማስተምረው ነግሬሀለሁ?››

‹‹የለም አልነገርኸኝም፡፡››

‹‹ልግስናን ነው፡፡ በየሳምንቱ እሁድ ማለዳ ወደ ደብር ይዤው እሄድና ሳንቲሜን ተኪሴ እየመዠረጥሁ በመደዳ
ለተኮለኮሉት ነዳያን እመጸውታለሁ፡፡ እንግዲህ ይህንን ሳደርግ እሱ አጠገቤ ቆሞ ያየኛል፤ሌጣ ብራና ማለት አይደል!
…እኔ በጎነትን እየጻፍሁበት ነው፡፡ አይደለም እንዴ?››

‹‹ነው!››

‹‹አየህ ሁላችንም እንዲህ ማድረግ ይገባናል:: ይህን ታደረግን የሚፈቃቀር ትውለድ እናፈራለን፡፡ አይደለም ወይ?››

‹‹ኸረ ጥርጥር የለውም!››

‹‹እኮ!…ለዚያነው ወርቄ ለነዳያን ስመጸውት አጠገቤ ቆሞ እንዲያየኝ የማደርገው…ታዲያ እሱ ይጠይቀኛል፡፡ ምን


ብሎአትለኝም!››

‹‹ምን ብሎ?››

‹‹ ‹ለምንድን ነው ሳንቲም የምትሰጣቸው አብዬ?›ይለኛል፡፡ ‹ያጡትን ነገር እንዲሸምቱበት ነዋ እለዋለሁ፡፡ አንተ


ብቻ ነህ የምትሰጣቸው?›ብሎ ሲለኝ የለም ሌሎች ደጋግ ሰዎችም ይሰጧቸዋል እለዋለሁ፡፡ አንገቱን ደፍቶ
በተመስጦ ያሰላስላል፡፡ አይገርምም?››

*እስካሁን ካነበባችሁት የጽሁፍ ክፍል ምን ተረዳችሁ?


*አባቱ ይህንን ተግባር ለህጻን ልጁ ማሳየቱ ተገቢ ነው ትላላችሁ? ለምን?
*ወርቄ አባቱ እንዳሰቡት በስነመግባር የታነጸ ልጅ የሚሆን ይመስላችኋል? ለምን?

‹‹ይገርማል!››ያለፍላጎቴ የተከፈተውን አፌን በመዳፌ እየተመተመኩ ሰማሁት፡፡

~ 66 ~
‹‹ያስተምሮየን ውጤት በቅርቡ ታያለህ››ሲል አከለ፡፡ ብዙ ባልቆይ ጥሩ ነበር፡፡ግን ቆየሁ፡፡ ሲመሽ ብላቴናው ወርቄ
ብጣሪ እንዳየች ድንቢጥ ሲበር መካከላችን ተገኘ፡፡

‹‹ደህና ነህ ወይ ወርቄ?››አልሁት፣አቧራ የለበሰ ጉንጩን በከንፈሬ እየነካካሁ፡፡››

‹‹ደህናነኝ!አንተስ ደህናነህ?››

‹‹ደህናነኝ!››

‹‹ቤትህ ደህና ናት?››

‹‹ደህና ናት፡፡››

‹‹እህትህስ ደህና ናት?››

‹‹ድህናናት ወርቄ››ተንጠራራሁ፡፡

‹‹አንተስ ደህና ነህ?››

‹‹ልቤ እንዳይፈርስ ሰግቸ ትንፋሸን ቆጠብሁ፡፡ አባትየው በፍቅር ዓይን ይከታተለዋል፡፡

‹‹ጋሽዬ ንጅ!››አለኝ ቀጠለና

‹‹አቤት!››

‹‹እንትን!››

ቅቤ ተቀብቶ ለጋ ቅል የመሰለውን ጠጉር አልባ ራሱን እያከከ አቀረቀረ፡፡

‹‹ምን?››

‹‹እስቲ ሳንቲም ስጠኝ?››

‹‹ሳንቲም ምን ያደርግልሀል?››

‹‹…ኧረግ ያጣሁትን ነገር እሸምትበታለሁ እንጂ!ሌላ ምን አረገዋለሁ? ዛሬ ብዙ ሰዎችን ብጠይቃቸው ደጋጎች


ሰጡኝ፡፡ አንዳንዶቹግን ወግድ አንተ አባት አሰዳቢ አሉኝ፡፡ በል አንተ ስጠኝ አያ!››ትንሽ መዳፉን ወደኔ ዘረጋ፡፡

ሳቄን በከንፈሬ አስሬ ወደመሪጌታ ተመለከትሁ፡፡ ፈገግታው ፊቱላይ የለም፡፡ ገጹ አመዳይ የወረሰው ቅጠል
በመምሰል ላይ ነበር፡፡

~ 67 ~
ምንጭ ፡- (የቀድሞው አማርኛ 9 ኛ ክፍልየተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ) (1997)

መመሪያ አንድ፡-ለሚከተሉትጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት በቃል መልስ ስጡ፡፡


1. አንዳንዶች ወግድ አንተ አባት አሰዳቢ ያሉበት ምክንያት ምንድን ነው?
2. ወርቄ ሳንቲም ምን ያደርግልሀል ሲባል የሰጠው መልስ ምን የሚል ነበር?
3. መርጌታ መድሎት ለወርቄ ትምህርት የሰጡበት መንገድ ተገቢ ነበር? ለምን?
4. የመሪ ጌታ ፍላጎት ተሳክቷል ትላላችሁ ለምን?
5. መርጌታ መድሎት ፈገግታው ከፊቱ ላይ የጠፋው በምን ምክንያት ነው?

መመሪያ ሁለት፡-ለሚከተሉት ቃላት በምንባቡ መሰረት አውዳዊ ፍች ስጡ፡፡


1. ነዳያን 2. ስነምግባር
3. ብላቴና 4. ተመስጦ
5. ብጣሪ 6. መመዥረጥ

መመሪያ ሶስት፡- ቀጥሎ ከምንባቡ የወጡ የአንብቦ መረዳት ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ጥያቄዎችን በጥሞና
በማንበብ ምንባቡን መሰረት በማድረግ ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1. መርጌታ መድሎት ስንት ልጅ አላቸው? ሀ.አንድ ለ.ሁለት ሀ.ሦስት መ.አራት


2. መሪጌታ መድሎት ‹‹አንዲቱን ፈልግና አግባት…አግብተህ ውለድ…››ያሉበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ.የሚስትን አስፈላጊነት ለመግለጽ ለ.የልጅን አስፈላጊነት ለመግለጽ

ሐ.የትዳርን ውስብስብነት ለመግለጽ መ.የብቸኝነት ህይወት አስከፊ መሆኑን ለመግለጽ

3. ወርቄ የስንት ዓመት ህጻን ነበር? ሀ.የስድስት ለ.የስምንት ሐ.የአራት መ.የአስር


4. ወርቄ በመጀመሪያ ጊዜ የተማረው ምን ነበር?

ሀ.ፊደል ለ.ንግግር ሐ.ጽህፈት መ.ስነመግባር

5. መርጌታ መድሎት ወርቄን የሚያስተምሩት መቸ መቸ ነው?

ሀ.ሰኞ ለ.እሁድ ሐ.ሀሙስ መ.ሁልጊዜ

6. ወርቄ መሪጌታ መድሎትን የሚጠይቃቸው ምን ብሎ ነበር?

ሀ.ለምንድን ነው ሳንቲም የምትሰጣቸው ለ.ለምንድን ነው ቤተክርስቲያን የምንሄድ

ሐ.ለምንድን ነው ትምህርት ቤት የማልሄድ መ.ለምንድን ነው ይህንን ምታሳየኝ

~ 68 ~
7. አንገቱን ደፍቶ በተመስጦ ያሰላስላል፡፡የተባለ ማን ነው?

ሀ.መሪጌታ መድሎት ለ.ተራኪው ሐ.ወርቄ መ.የኔ ቢጤው

8. ‹‹ያስተምሮዬን ውጤት በቅርቡ ታያለህ ››ያሉት ወርቄ ምን ሆኖ ያየዋል ብሎ በማሰብ ነው?

ሀ.በስነምግባር የታነጸ ለ.መግባረ ብልሹ ሐ.አዋቂ መ.ነዳያን

መመሪያ አራት፡-ምንባቡን መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቃል መልሱ፡፡


1. ተራኪው ልቤ እንዳይፈርስ ሰገቸ ትንፋሸን ቆጠብሁ ያለው በምን ምክንያት ነው?
2. በታሪኩ ውስጥ ከሌጣ ብራና ጋር የተነጻጸረው ምን ነበር?
3. ተራኪው በመጨረሻላይ ሳቁ የመጣበት ለምን ነበር?
4. በታሪኩ ውስጥ አመዳይ የወረሰው ቅጠል የተነጻጸረው ከምን ጋር ነበር?
5. መሪ ጌታ ተራኪውን ምን ሲሉ መክረውት ነበር? አስረዱ፡፡
6. በታሪኩ ውስጥ ከድንቢጥ ወፍ ጋር የተነጻጸረው ማን ነበር?
7. ብዙ ባልቆይ ጥሩ ነበር ያለበት ምክንያት ምን ነበር?

መመሪያ አምስት ፡-የሚከተሉት ዓ/ነገሮች በያዙት ሃሳብ ላይ በቡድን ተወያዩ፡፡


1. ፊቱ አመዳይ የወረሰው ቅጠል መሰለ ሲል ምን ማለቱ ነው?
2. ህጻን ሌጣ ብራና ማለት ነው? በማለት የገለጹበት ምክንያት ምንድን ነው?
3. ያስተምህሮየን ውጤት በቅርቡ ታያለህ ሲል ምን ማለቱ ነው?
4. የምንባቡ ዋና መልክት ምንድን ነው?

መመሪያ ስድስት፡- በሚከተለው ቃል እማሪያዊና ፍካሪያዊ ፍቹን የሚያሣዩ ዓረፍተ ነገሮች ስሩ፡፡
1. ድንቢጥ
2. ብጣሪ

መርጃ መሳሪያ፡- የቀድሞው ዘጠነኛ ክፍልየአማርኛ መማሪያ መጽሃፍ


ግምገማ ፡- የአንብቦ መረዳት የቃል ጥያቄዎችን መልስ መገምገም
- የግል ስራቸውን መልስ ማረም
- የቡድን ውይይታቸውን መልስ መገምገም

~ 69 ~
አባሪ መ. ልዩ ልዩ ሰንጠረዦች
ሰኝጠረዥ 1፡- የሙከራ ቡድኑ ቅድመና ድህረ ትምህርት ፈተና ውጤት /ከ 30%/

ተ.ቁ ቅድመ ትምህርት አንብቦ ድህረ ትምህርት አንብቦ


የመረዳት ፈተና ውጤት የመረዳት ፈተና ውጤት
1 16 24
2 24 27
3 20 21
4 17 25
5 21 24
6 18 21
7 19 24
8 17 29
9 15 22
10 12 24
11 21 24
12 18 23
13 16 24
14 12 22
15 14 25
16 16 24
17 12 25
18 13 24
19 18 24
20 15 23
21 20 19
22 14 22
23 16 27
24 15 29
25 14 24
26 17 19
27 21 25
28 21 24
29 15 27
30 19 23
31 15 20
32 18 22
33 24 23
34 15 19
35 14 27
36 20 28
37 16 24
38 23 25

~ 70 ~
39 19 27
40 14 25

ሰኝጠረዥ 2፡- የቁጥጥር ቡድኑ ቅድመና ድህረ ትምህርት ፈተና ውጤት /ከ 30%/

ተ.ቁ ቅድመ ትምህርት አንብቦ ድህረ ትምህርት አንብቦ


የመረዳት ፈተና ውጤት የመረዳት ፈተና ውጤት
1 15 19
2 16 15
3 18 15
4 17 21
5 19 16
6 18 18
7 17 17
8 19 17
9 16 21
10 16 15
11 15 23
12 18 19
13 17 21
14 18 14
15 17 18
16 13 21
17 20 20
18 16 21
19 15 12
20 14 15
21 16 16
22 17 20
23 18 21
24 24 23
25 17 13
26 14 12
27 21 20
28 17 15
29 21 16
30 21 21
31 20 19
32 18 18
33 14 14
34 27 20
35 18 19
36 13 20
37 12 15

~ 71 ~
38 14 18
39 16 15
40 19 17
41 12 19
42 16 17

~ 72 ~

You might also like