You are on page 1of 128

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የማኅበራዊ ሳይንስና ሥነሰብዕ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች) እና ስነፅሁፍ-አማርኛ ትምህርት ክፍል

ድህረምረቃ መርሃግብር

ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት


ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ

ልዑል በቃሉ

ሰኔ፣ 2012 ዓ.ም.

ጎንደር
ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል
ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የማኀበራዊ ሳይንስና ስነሰብዕ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች) እና ስነፅሁፍ-አማርኛ ትምህርት ክፍል

የድኀረምረቃ መርሐግብር

በተግባራዊ ስነ ልሣን አማርኛን ለማስተማር የማስተርስ ዲግሪ የቀረበ ማሟያ ጥናት

ልዑል በቃሉ

የጥናቱ አማካሪ

አገኘሁ ተስፋ (PhD)

ሰኔ፣ 2012 ዓ.ም.

ጎንደር
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የማኀበራዊ ሳይንስና ስነሰብዕ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች) እና ስነፅሁፍ-አማርኛ ትምህርት ክፍል

የድኀረምረቃ መርሐግብር

ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል
ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ በሚል ርዕስ በተግባራዊ ሥነልሳን አማርኛን ለማስተማር
የማስተርስ ዲግሪ ማሟያ በልዑል በቃሉ የቀረበው ይህ ጥናት የዩኒቨርሲቲውን የጥራትና
የወጥነት መስፈርት ስለማሟላቱ በፈታኞች ተረጋግጦ ተፈርሟል፡፡

የፈተና ቦርድ አባላት

አማካሪ ------------------------------------------ ፊርማ ---------------------- ቀን --------------------

ፈታኝ ------------------------------------------- ፊርማ ----------------------- ቀን --------------------

ፈታኝ -------------------------------------------- ፊርማ ----------------------- ቀን --------------------


ማረጋገጫ

ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል
ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ በሚል ርዕስ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ማህበራዊ ሳይንስና
ስነሰብዕ ኮሌጅ የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች) እና ሥነጽሑፍ-አማርኛ ትምህርት ክፍል በተግባራዊ
ስነልሳን አማርኛን ለማስተማር ለኤም.ኤ ዲግሪ ማሟያ ያቀረብኩት ይህ ጥናት ከዚህ በፊት
በማንኛውም አካል ያልተሠራ የራሴ ወጥ ሥራ መሆኑንና የተጠቀምኩባቸው ድርሳናትም
በትክክል ዋቢዎች የተደረጉና ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የጥናቱ ህጋዊ የባለቤትነት መብት ያለው
መሆኑን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

ስም --------------------------------------------------------------

ፊርማ -----------------------------------------------------------

ቀን ---------------------------------------------------------------

i
ምስጋና

በመጀመሪያ ደረጃ ይህ ጥናት ተጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ ያለምንም እንከን የተለያዩ


ተግባራትን ከቦታ ቦታ እየተዘዋወርኩ እንዳከናውን ላደረገኝ ለቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም
ልጅ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይገባዋል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ይህ ጥናት ተጀምሮ
እከሚጠናቀቅ ድረስ በአካልም ሆነ በስልክ እንዲሁም በኢሜል የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ
ጥናቱ አሁን ባለበት ደረጃ እንዲደርስ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋፅኦ ያበረከቱልኝን
የቀለም አባቴ ዶ/ር አገኘሁ ተስፋን ከልብ አመሰግናለሁ፡፡ በሶስተኛ ደረጃ ጥናቱ የተሳካ
እንዲሆን በሁሉም ነግር ከምትችለው በላይ ለአደረገችልኝ ውዷ ባለቤቴ ወ/ሮ እቴነሽ ጫኔ እና
ስስቴ ለሆኑት የመንፈስ ልጆቼ ቃለአብ ልዑልና ሀሴት ልዑል ምስጋናዬ ከልብ ነው፡፡
በአራተኛ ደረጃ በሀሳብና በገንዘብ ላቅ ያለ ድጋፋቸውን ለቸሩኝ ቤተሰቦቼ ለአባቴ ለአቶ በቃሉ
ዘሪሁን፣ ለዕናቴ ለወ/ሮ ይደነቅ ልመንህ፣ ለወንድሞቼ ለሞላ በቃሉ፣ ፍስሃ በቃሉ፣ ስለሺ
በቃሉና ተመስገን በቃሉ እንዲሁም ለእህቶቼ ውባለም በቃሉ፣ ጥሩነሽ በቃሉ፣ መልካም
በቃሉና የልፍኝ በቃሉ ምስጋናዬ ከልብ የመነጨ ነው፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆነ መረጃ
በመስጠት ለተባበሩኝ በአዲስ አበባ የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት እና የደጃዝማች
ባልቻ አባነፍሶ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ሰራተኞች እንዲሁም የምፈልገውን መረጃ
እንደልቤ ግቢ እየገባሁና እየወጣሁ እንድሰራ ለፈቀደልኝ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምስጋናዬ
የላቀ ነው፡፡ በመጨረሻም ያለውን እውቀት በማካፈል ከጎኔ ላልተለየው ውድ ጓደኛዬ አብርሃም
ዘሪሁን የከበረ ምስጋናዬን ከልብ አቀርባለሁ፡፡

ii
የይዘት ማውጫ

አርዕስት ገፅ
ማረጋገጫ ........................................................................................................................... i
ምስጋና.............................................................................................................................. ii
የይዘት ማውጫ ................................................................................................................. iii
የሰንጠረዥ ማውጫ .......................................................................................................... vi
አህፅሮተ ጥናት.................................................................................................................vii
ምዕራፍ አንድ፤ መግቢያ .................................................................................................... 1
1.1. የጥናቱ ዳራ ............................................................................................................ 1
1.2. የጥናቱ መነሻ ችግር................................................................................................ 9
1.3. የጥናቱ ዓላማ ....................................................................................................... 12
1.4. የጥናቱ ጠቀሜታ .................................................................................................. 13
1.5. የጥናቱ ወሰን........................................................................................................ 14
1.6 የጥናቱ ውስንነት ................................................................................................... 15
1.7. የጥናቱ ቁልፍ ቃላት እና ሃረጋት .......................................................................... 15
ምዕራፍ ሁለት፤ ክለሳ ድርሳናት ....................................................................................... 17
2.1. የቋንቋ ፈተና ምንነት ............................................................................................ 17
2.2. የቋንቋ ፈተና ዓላማ .............................................................................................. 19
2.3. የቋንቋ ፈተና አይነቶች .......................................................................................... 20
2.3.1. የቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና ....................................................................... 21
2.3.2. የደረጃ መለኪያ ፈተና ..................................................................................... 22
2.3.3. የጥንካሬና ድክመት መለኪያ ፈተና .................................................................. 22
2.3.4. የችሎታ መለኪያ ፈተና .................................................................................. 23
2.4. የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርት ዝምድና .......................................................... 26
2.5. የቋንቋ ፈተና የይዘት ተገቢነት ............................................................................... 30

iii
2.6. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ምንነት......................................................................... 32
2.6.1. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት አስፈላጊነት ............................................................ 33
2.6.2. የመማሪያ መፃህፍት ባህርያት ......................................................................... 35
2.7. የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ...................................................................................... 36
2.7.1. የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች ..................................................................... 37
2.7.2. የንግግር ክሂል ንዑሳን ይዘቶች ........................................................................ 38
2.7.3. የንባብ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች ........................................................................... 40
2.7.4 የፅህፈት ክሂል ንዑሳን ይዘቶች......................................................................... 41
2.7.5. የሰዋስው ችሎታ ንዑሳን ይዘቶች ..................................................................... 43
2.8. የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት ....................................................................................... 44
ምዕራፍ ሶስት፤ የአጠናን ዘዴ ........................................................................................... 50
3.1. የምርምሩ ንድፍ ................................................................................................... 50
3.2. የመረጃ ምንጮች .................................................................................................. 50
3.3. የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ .................................................................................. 51
3.4. የመረጃ አተናተን ዘዴ ........................................................................................... 52
ምዕራፍ አራት፣ የመረጃ ትንተናና የውጤት ማብራሪያ ...................................................... 55
4.1. የመረጃ ትንተና..................................................................................................... 55
4.2. የውጤት ማብራሪያ............................................................................................... 64
ምዕራፍ አምስት፤ ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና አስተያየት ................................................... 68
5.1. ማጠቃለያ ............................................................................................................. 68
5.2. መደምደሚያ ......................................................................................................... 70
5.3. አስተያየት ............................................................................................................ 71
ዋቢዎች .......................................................................................................................... 73
አባሪዎች ......................................................................................................................... 80
አባሪ አንድ፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን ........................................................................................................ 80
አባሪ ሁለት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የመናገር ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን ........................................................................................................ 81
አባሪ ሶስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የማንበብ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን..................................................................................................... 82

iv
አባሪ አራት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የመፃፍ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን..................................................................................................... 83
አባሪ አምስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የሰዋስው ዘርፍ ንዑሳን
ይዘቶች የድግግሞሽ መጠን ........................................................................................ 85
አባሪ ስድስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የስነፅሁፍ ዘርፍ ንዑሳን
ይዘቶች የድግግሞሽ መጠን ........................................................................................ 88
አባሪ ሰባት፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2009 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና
................................................................................................................................ 89
አባሪ ስምንት፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2010 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል
ፈተና ........................................................................................................................ 99
አባሪ ዘጠኝ፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2011 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና
.............................................................................................................................. 109

v
የሰንጠረዥ ማውጫ
ሰንጠረዥ 4.1.1. በሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱና በሞዴል ፈተዎቹ
የተካተቱ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ............................................................................ 58
ሰንጠረዥ 4.1.2. የእያንዳንዱ ዓመት ሞዴል ፈተናዎች መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ
ደረጃ መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን.............................................. 60
ሰንጠረዥ 4.1.3. የሶስቱ ዓመት ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ
ደረጃ መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን.............................................. 62

vi
አህፅሮተ ጥናት

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ የጥናቱን ዋና አላማ ከግብ
ለማድረስ አጥኝው ገላጭ ንድፍን የተጠቀመ ሲሆን መረጃ የሰበሰበው ደግሞ በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት
ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደበት ክፍለ ከተማ በአመቺ የናሙና አመራረጥ ስልት የተመረጠ ሲሆን የክፍል
ደረጃው በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልትና ሞዴል ፈተናዎቹ ደግሞ በጠቅላይ የናሙና
አመራረጥ ስልት አማካኝነት ተመርጠው ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት
ከተሰበሰቡ በኋላ መጠናዊ በአይነታዊ በተደገፈ ቅይጥ የመረጃ መተንተኛ ስልት አማካኝነት ትንተናው
ተካሂዷል፡፡ የጥናቱ ግኝትም በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች የተካተቱ ይዘቶች ከቋንቋ
ትምህርት ክሂላት ውስጥ መናገርን፣ ማንባብንና መፃፍን እንዲሁም፣ ሁለቱን የእውቀት ዘርፎች
ማለትም ሰዋስውንና ስነፅሁፍን የተመለከቱ ናቸው፡፡ የማዳመጥን ክሂል የተመለከተ አንድም ጥያቄ
ቦሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ውስጥ አልተካተተም፡፡ በመሆኑም የቋንቋ ትምህርት
ንዑሳን ይዘቶች ተገቢ ውክልና እንዳላገኙ ማወቅ ተችሏል፡፡ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል
ፈተናዎች በተናጠል ከሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን
በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቶ አዎንታዊና በጣም ከፍተኛ ሲሆን የ2011
ዓ.ም ሞዴል ፈተና በ(r=0.925, p=0.008) ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፡፡ የ2010 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና
(r=0.915, p=0.010) እና 2009 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና (r=0.859, p=0.028) ደግሞ በቅደም ተከተል
ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጡ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል
ፈተናዎች በጥቅል ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር ያላቸው የዝምድና መጠንም በፒርሰን ፕሮዳክት
ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቶ በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909, p=0.012) የግንኙነት መጠን
በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡ ሞዴል
ፈተናዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ሲታዩ ደግሞ በ2010 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ
ፈተና ሙሉ ለሙሉ የችሎታ መለኪያ ፈተና ሲሆን፣ በአንፃሩ የ2009 እና የ2011 ዓ.ም ሞዴል
ፈተናዎች ይዘት ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ዝርዝር ይዘቶች እና
ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ ዝምድና የሌላቸው በመሆናቸው ሁሉም የችሎታ
መለኪያ ፈተናዎች ናቸው ብሎ መደምደም እንደማይቻል የጥናቱ ውጤት አመላክቷል፡፡ በጥናቱ ግኝት
ላይ በመመስረት የመፍትሄ ሃሳቦች የተጠቆሙ ሲሆን መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜ
የችሎታ መለኪያ ፈተናን ታሳቢ እያደረጉ ቢያዘጋጁ፣ የፈተና ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላትም
መምህራን በሚያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ውስጥ ምን ምን ይዘቶች እንደተካተቱና
ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የይዘት ዝምድና ምን እንደሚመስል በመፈተሽ አላስፈላጊ ጥያቄዎች
እንዳይካተቱ የማድረግና ለአዘጋጅ መማህራኑም ስለሞዴል ፈተና አዘገጃጀት በየጊዜው ስልጠናዎችን
እያዘጋጁ የሚሰጡበት ሁኔታ ቢመቻች የሚል አስተያየት ተጠቁሟል፡፡

vii
ምዕራፍ አንድ፤ መግቢያ

1.1. የጥናቱ ዳራ

አለም እና ፅጌ (1997) እንደሚያስረዱት የቋንቋ ትምህርት ዋና ዓላማ አራቱን ክሂሎች


ማለትም ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍን ማዳበርና ሁለቱን የዕውቀት ዘርፎች ማለትም
የስነፅሁፍና የስነ ልሳን (ሰዋሰው) ችሎታን ማበልፀግ ነው፡፡ በመሆኑም የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርትም እነዚህን ዓላማዎች እውን ለማድረግ ይቻል ዘንድ ታስቦ በትምህርት ዓይነትነት
እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ክሂሎቹና የዕውቀት ዘርፎቹ በክፍል ውስጥ እንዴት መተግበር
እንዳለባቸው ተወስኖ እና መርሃ ትምህርት ተዘጋጅቶላቸው በቅንጅት እና በተናጠል ይሰጣሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ Brown (1980) የቋንቋ ትምህርት ዓላማ ተማሪዎች በሚማሩት ትምህርት
የባህርይ ለውጥ እንዲያመጡ ማድረግ ነው፡፡ ይህ የባህርይ ለውጥ መምጣት አለመምጣቱ
በዋናነት የሚረጋገጠው ደግሞ በፈተና በመሆኑ ማስተማሩና መፈተኑ የትምህርቱ አካል ሆነው
ሳይነጣጠሉ ይከናወናሉ በማለት ይገልፃሉ፡፡

ቋንቋን የመፈተን ሂደት ደግሞ ያለፈባቸው ሶስት ተከታታይ ታሪካዊ ደረጃዎች እንዳሉት Wier
(1990) እና Baker (1989) ይገልጻሉ፡፡ የመጀመሪያው ዘመን ቅድመ ሳይንስ የሚባለው የፈተና
ዘመን ሲሆን ለረጅም ጊዜ ያገለገለና ከሰዋስው ወትርጉም የማስተማሪያ ዘዴ ተነስቶ እስከ
ሁለተኛው የአለም ጦርነት ጊዜ ድረስ አገለግሎት ላይ መዋል የቻለ ነው፡፡ በዚህ ዘመን በነበሩ
መምኃራን የሚዘጋጀው የቋንቋ ፈተና ግልጽነት የጎደለው በተለይም ከአስተማማኝነትና
ከትክክለኛነት አንጻር ጥያቄዎች የሚነሱበት ነበር፡፡

ሁለተኛው ዘመን የሳይኮሜትሪክ መዋቅራዊያን የቋንቋ ፈተና ዘመን የሚባለው ሲሆን እሰከ
20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ተግባር ላይ ሊውል ችሏል፡፡ ዘመኑ የቋንቋ ፈተናዎች

1
ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይንሳዊ ወደሆነው መርህ የተሸጋገሩበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን
ከመዋቅራዊያን እይታ የቋንቋ ክሂሎችን እየነጣጠሉ መፈተን፣ ከሳይኮሜትሪክ ደግሞ ዝግና
አስተማማኝ የፈተና ዘዴዎች የመነጩበትና የፈተና መርሆዎችም ተግባር ላይ የዋሉበት ሲሆን
ዝግጅቱም በሰለጠኑ ባለሙያዎች ይካሄድ እንደነበረ Baker (1989)፤ Wier (1990) እና
Brawn (1994) ይገልጻሉ፡፡

ሦስተኛው ዘመን ውህዳዊ የቋንቋ ፈተና ስልት የሚባለው ሲሆን በዚህ ዘመን የተለያዩ
የስነልሳን፣ የስነልቦናና የማህበራዊ ዘርፍ ባለሙያዎች በፈተና ሂደቱ ላይ የራሳቸውን
አስተዋጽኦ ያበረከቱበት ወቅት ነው፡፡ በመዋቅራዊያን ዘመን ይተገበር የነበረው የቋንቋ ክሂሎችን
ነጣጥሎ የመፈተኑ ሂደት ቀርቶ ክሂሎችን ውህዳዊ በሆነ መንገድ ባንድ ጊዜ ለመመዘን ጥረት
የተደረገበት ዘመንም ነው፡፡

Heaton (1988) በበኩላቸው ይህን የWier (1990) አከፋፈል ከፍ ያደርጉትና ተግባቦታዊ ዘዴ


የአፈታተን ስልትን አራተኛ አድርገው ያቀርቡታል፡፡ ይህ የቋንቋ ፈተና ከተግባቦታዊ የቋንቋ
ማስተማር ስልት ጋር አብሮ ተያይዞ የመጣ ስልት እንደሆነና መሰረታዊ ዓላማው የቋንቋ ፈተና
የተማሪዎችን የተግባቦት ችሎታ በሚያሳድግና በሚያጎለብት መንገድ መቅረብ አለበት የሚል
እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ Heaton (1988) ሆኑ Wier (1990) እንደሚስማሙበት ግን በእነዚህ
ጊዚያት ሁሉ የቋንቋ ፈተና ያለፈበት ሂደት ከቋንቋ ትምህርት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንደሆነ
ሁሉ አሁንም በተግባር ላይ እየዋለ ያለው ተግባቦታዊ የማስተማር ስልት በፈተናው ላይ
ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

Giri (2010) እና Alderson, Clapham and Wall (1995) እንደሚገልጹት ተግባቦታዊ የቋንቋ
ፈተና ለሁለቱም ማለትም ለብቃትና ለተግባር እኩል ትኩረት መሰጠት አለበት የሚለውን
ሃሳብ ይዞ ከ1990ዎቹ ወዲህ የተዋወቀ ስልት ነው፡፡ በዚህ ሂደት በቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ
ሁለቱ ነገሮች መመዘን አለባቸው፡፡ የመጀመሪያው ተማሪዎች ስለቋንቋው ቅርጽና አጠቃቀም
ያላቸውን እውቀት የሚመለከት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያላቸውን ይህን እውቀት ትርጉም

2
ባለው መንገድ ማሳየት መቻላቸውን የሚመለከት ነው፡፡ በተግባቦታዊ ፈተና ሂደት የሚዘጋጁት
ፈተናዎች ተፈታኞች በዕውኑ አለም ከሚጠቀሙበት የቋንቋ አጠቃቀም ጋር የተዛመዱ
ተግባራትን ማካተት አለባቸው፡፡ Hughes (1989) እንደሚያብራሩትም የቋንቋ ትምህርትና
ፈተና ካላቸው ጥብቅ ግንኙነት አንጻር አብረው የሚሄዱ ናቸው፡፡ በመማር ማስተማሩ ሂደት
የሚደረጉ ክንውኖች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በፈተና ላይ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ በተመሳሳይም
ፈተና በክፍል ውስጥ የሚከናወነውን ትግበራ የመቆጣጠር ሃይል አለው፤ ስለዚህ በሁለቱ
መካከል ያለው ግንኙነት ጥብቅ ነው፡፡

የአፈታተን ሂደቱ ምንም እንኳን የቋንቋን ትምህርት አራት መሰረታዊ ክሒሎችና ሁለት
የዕውቀት ዘርፎች መሰረት አድርጎ የሚከናወን ቢሆንም እንደፈተናዎቹ አይነትና ይዘት
የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ Bachman (1990)፣ Heaton (1990) እና Weir (1990) በርካታ
የፈተና አይነቶች ከመኖራቸው አንፃር አላማቸውም እንዲሁ የትየለሌ ነው በማለት ዋና ዋና
በማለት የገለጿቸው የቋንቋ ትምህርት ዓላማዎች፡- የተማሪዎችን አጠቃላይ የቋንቋ ችሎታ
በመለካት ለእነሱ የሚመጥነውን ቀጣይ የጥናት መስክ ማመላከት፣ ተማሪዎች ለተወሰኑ
ጊዜያት የተማሩትን ትምህርት ምን ያህል እንደጨበጡ ማረጋገጥ፣ የተማሪዎችን ድክመትና
ጥንካሬ ማሳየት፣ ተማሪዎችን መደገፍና ማነቃቃት፣ የመምህራንን የማስተማር ተግባር
ውጤታማነት ማሳየት፣ በቋንቋ ትምህርት ፕሮግራሙ ላይ ማሻሻያና ማስተካከያ ለማድረግ
የሚያስችል መረጃ መሥጠት፣ የትምህርቱ ዓላማዎች በተማሪዎች ዘንድ ምን ያህል ተግባራዊ
እንደሆኑ ማመላከት ወዘተ ናቸው፡፡

ፈተና የአንድን ሰው ተሰጥኦ፣ እውቀት ወይም ብቃት በአንድ በተወሰነ የቋንቋ አገልግሎት
ለመለካት የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡፡ የሚሰጥበት ዋና ዓላማም መረጃ በመሰብሰብ ችግርን
ለመለየት ነው፡፡ ፈተና ውሳኔ ለመስጠት፣ ነገሮችን ለመለካት፣ ተማሪዎችን ለማበረታታት፣
የመርሃ ትምህርቱን ጥንካሬና ድክመት ለመለየት እና በመማር ማስተማሩ ሂደት አስቸጋሪ
ሁኔታዎችን ለመገምገም ያስችላል፡፡ በመሆኑም በመማር ማስተማር ተግባር ውስጥ ስለ
ተማሪዎች የመማር ሂደትና ውጤት ለተለያዩ አካላት መረጃ በመስጠት ያገለግላል፡፡

3
Harrison (1983)፣ Alderson እና ሌሎች (1995) የተባሉት ምሁራን ስለፈተና ሲገልፁ
ተማሪዎች በተማሩት ትምህርት ዙሪያ የተገነዘቡትን ለመለካት፣ ከአንድ የክፍል ደረጃ ወደ
ቀጣዩ የክፍል ደረጃ የሚሸጋገሩበትን ሁኔታ ለመወሰን፣ ለአንድ ስራ ብቁ የሆነን ሰው ለይቶ
ለመምረጥ እና አንድ ሰው ያለውን የዕውቀት ደረጃ ለመመዘን የሚያገለግል መሳሪያ ነው
ይላሉ፡፡ Brown (1994)፣ Heaton (1975) እና Bachman (1990)ንም እንዲሁ ፈተና
በተወሰነ የትምህርት ደረጃ ለተወሰነ ዓላማ የቀረበ ትምህርትን መሰረት በማድረግ ተማሪዎች
ትምህርቱን ምን ያህል እንደተረዱት ለመገንዘብ የሚረዳና ተናጠላዊ ችሎታቸውን ሚዛናዊ
በሆነ መንገድ ለመገምገም የሚያስችል መሳሪያ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ከነዚህ ምሁራን ገለፃ መረዳት የምንችለው መሰረታዊ ጉዳይ ፈተና ተማሪዎች በተወሰነ የክፍል
ደረጃ የሚጠበቅባቸውን የዕውቀት፣ የክህሎትና የባህርይ ለውጦች ማምጣት አለማምጣታቸውን
ለማወቅ የሚረዳና በዚህ መነሻነትም ለቀጣዩ ደረጃ መመጠን አለመመጠናቸውን ለመወሰን
የሚያስችል መረጃ የሚሰጥ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም አንድ ሰው ያለውን እውቀት
በመለካት ለተወሰነ ተግባር ብቁ መሆን አለመሆኑን ለመለየት በመመዘኛ መሳሪያነት
ያገለግላል፡፡

ፈተና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለመደገፍ እንደ ግብዓት ሆኖ ከማገልገሉም በተጨማሪ


ተማሪዎች በየትኛው የትምህርት ይዘትና በምን ያህል ደረጃ ጥንካሬ እንዳላቸው እና ድክመት
እንዳለባቸው በመለየት ለበለጠ ውጤት እንዲነሳሱ የሚያተጋ ሲሆን መምህራኑም የማስተማር
ስልታቸውን የውጤታማነት ደረጃ እንዲፈትሹ ያስችላቸዋል፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ባለድርሻ
አካላት የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚደግፉ አጋዥ ተግባራትን ለማከናወን እንዲችሉ
የሚያደርግ መረጃ ያገኙበታል፡፡ በቋንቋ ትምህርት ረገድም በክፍል ውስጥ ተግባራዊ
የተደረጉትን የታላሚውን ቋንቋ የመማር ማስተማር ክንውን ሂደቶችንም ሆነ ውጤታቸውን
አስመልክቶ እንዲሁም በቀጣይ ለሚወሰዱ እርምጃዎች የሚያግዙ መረጃዎች ከሚገኙባቸው
መንገዶች አንዱ የቋንቋ ትምህርት ፈተና ነው፡፡

4
Hughes (1989) እና Ur (1996) እንደሚገልፁት በቋንቋ ትምህርት ታሪክ የቋንቋ ትምህርት
ፈተና ረጅም እድሜ ያስቆጠረና ዛሬም ድረስ እየተሰራበት ያለ፣ የተማሪዎችን እውቀትና
ችሎታ፣ ጥንካሬና ድክመት እንዲሁም ፍላጎታቸውንም ሆነ የየዕለት ለውጣቸውን ለማወቅና
ቀጣይ ተግባራትን ለመከወን የሚያስችሉ መረጃዎችን በማሰባሰብ ውሳኔዎችን ለመስጠት
የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡

ከልሂቃኑ ሀሳብ መረዳት የሚቻለው የቋንቋ ትምህርት ፈተናዎች አንድ ሰው በቋንቋ ክሂሎችም
ሆነ በዕውቀት ዘርፎች ረገድ ያለውን ችሎታ ገምግሞ ለመረዳት የሚያስችሉና ለውሳኔ
የሚያበቁ መረጃዎችን ማግኛ መሳሪያዎች መሆናቸውን ነው፡፡ ፈተናዎቹ ተማሪዎች በታላሚው
ቋንቋ የመማር ማስተማር ሂደት በተማሯቸው የክሂልና የዕውቀት ዘርፎች ላይ በመመስረት
የሚቀርቡ ናቸው፡፡ በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ በቋንቋ ትምህርት ሂደት ውስጥ ያሉና ያለፉ
ተማሪዎችን የቋንቋ ትምህርት ክህሎት፣ የስነልሳን እና የስነ-ፅሁፍ እውቀት ለመለካት በየእለቱ
ከምንጠቀምባቸው የክፍልና የቤት ስራዎች ውስጥ የሚጠቀሱ መመዘኛዎች ናቸው፡፡ እንደ
ፈተናዎቹ ዓላማም በቅድመ-መማር፣ በመማር ወቅት እና በድህረ-መማር ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
የዚህ ጥናት ትኩረትም በአንድ መርሃ ግብር መጨረሻ ላይ የሚቀርቡ የሞዴል ፈተናዎች
በመሆናቸው በባህርያቸው በድህረ-መማር የሚሰጡ ናቸው፡፡

ከሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተና በፊት የሚሰጡ የቋንቋ ትምህርት ልዩ ልዩ ምዘናዎች


(ፈተናዎች) በዋነኛነት የመማር ማስተማሩን ሂደት ለመደገፍ ያለሙና የማስተማር ሂደቱ አካል
ተደርገው የሚታሰቡ ሲሆን፣ የማጠናቀቂያ ፈተናዎች ግን ተማሪዎች የታላሚውን ቋንቋ
ትምህርት ይዘቶች ምን ያህል እንደተረዱ ለመገምገምና ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚሰጡ ናቸው፡፡

Ur (1996) ፈተና ከትምህርቱ በተጓዳኝ ለትምህርቱ ትኩረት እንዲኖር ታስቦ የሚሰጥ ከሆነ
የመማር ማስተማሩ ሂደት አካል ተደርጎ እንደሚቆጠር፣ በአንፃሩ የመማር ማስተማሩ ሂደት
ከተጠናቀቀ በኋላ የሚሰጥ ከሆነ ደግሞ በተማሪው ላይ የመጣውን የክህሎት፣ የአመለካከትና
የአሰራር ለውጥ ለመመዘን ታስቦ የሚሰጥ እንጂ የሂደቱ አካል ተደርጎ እንደማይታሰብ

5
በመግለፅ ከላይ ያለውን ሀሳብ የሚያጠናክር ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ፈተናዎቹ ከመማር
ማስተማር ጎን ለጎንም ሆነ ትምህርቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ቢሰጡም ተማሪዎች የተማሩትን
ትምህርትና ለክፍል ደረጃው ይመጥናል ተብሎ የተዘጋጀውን መማሪያ መፅሃፍ መሰረት
አድርገው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡

ቋንቋን ማስተማርና ቋንቋን መፈተን እርስ በርስ የተቆራኙና የማይለያዩ ተግባራት እንደሆኑ
Woodford (1980) እና Heaton (1975) ያስረዳሉ፡፡ Madsen (1983)፣ Bertrand እና
Sebula (1980) እንዲሁም Brown (1980) ፈተና የተማሪዎችን እድገት በየጊዜው
ለመከታተልና ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የመማር ማስተማሩ አካል ነው ሲሉት Agarwal
(1996)፣ Taiwo (1995) እና Heaton (1990) ደግሞ ፈተና ተማሪዎችን ለማበረታታት፣
እድገትና መሻሻላቸውን ለመከታተል፣ የመማር ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ ሃሳብ ለመስጠት፣
ስርዓተ ትምህርቱን ለማሻሻልና በአጠቃላይ የመማር ማስተማሩ ሂደት የተሳካ እንዲሆን
የማድረግ ዓላማ ይዞ ከመካሄዱ አንፃር ከማስተማር ተግባርም ተለይቶ እንደማይታይ
ይገልፃሉ፡፡ ስለሆነም ቋንቋን ማስተማርም ሆነ መፈተን የማይነጣጠሉ ከመሆናቸው አንፃር
ሁለቱም በተገቢው መንገድ ሊከወኑ ይገባል፡፡ በወጉ የተዘጋጀ ፈተና በመማር ማስተማሩ ሂደት
አወንታዊ ሚና ሲኖረው፤ ይህ ካልሆነ ግን ውጤቱ የተዛባ ስለሚሆን በርካታ ችግሮችን
ያስከትላል (Gottfredson, 2004):: በመሆኑም ይህ ጥናትም ታላሚ ያደረገውን የአስረኛ ክፍል
የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ቁመና በመፈተሽ ጠንካራ ጎኑ እንዲቀጥል ድክመት ካለው ደግሞ
ለወደፊት እንዲስተካከል የማድረግ ዓላማን ይዞ የተነሳ ነው፡፡

የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርት ተደጋጋፊና የማይነጣጠሉ የቋንቋ መማር ማሰተማር


ተግባራት በመሆናቸው በመካከላቸው ጥብቅ ትስስር ሊኖር እንደሚገባ ይታመናል፡፡ የቋንቋ
ትምህርት በሚሰጥበት የቋንቋ ፈተና መሰጠቱ ግድ ሲሆን ጥሩ የሚባል ፈተናም የትምህርቱን
ሂደት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በማመላከት ለመማር ማስተማሩ ስኬታማነት አዎንታዊ
አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ Heaton (1975) የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርትን ዝምድና
ሲገልፁ በቋንቋ መማር ማስተማር ሂደት ማስተማር እና መፈተን አንደኛው ከሌላኛው
ተነጥለው የሚሰጡ እንዳልሆኑና ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው የቋንቋ መማር ማስተማር ተግባር

6
አካላት እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡ በተመሳሳይ Balker (1989) እንደገለፁት ፈተና በቋንቋ
ትምህርት ሂደት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት
ቤት አስተዳደር አካላት መረጃን፣ ማነቃቂያንና ማረጋገጫን ስለሚፈልጉና ይህንንም የሚያገኙት
ከፈተና ስለሆነ ነው፡፡ የቋንቋ ትምህርት ፈተናዎች በቅድመ መማር፣ በመማር ሂደት እና
በድህረ መማር ጊዜያት ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች በተማሩት ትምህርት ላይ መሰረት
አድርገው የሚሰጡት ፈተናዎች ግን በአብዛኛው በድህረ መማር ጊዜ የሚሰጡ ናቸው፡፡
በመሆኑም ይህ የፈተና አይነት ተማሪዎች ከተማሩት የቋንቋ ትምህርት ጋር ያለው ዝምድና
ጥብቅ ሊሆን ግድ ይላል፡፡ በዚህ ረገድ ጥቅም ላይ የሚውለው የፈተና ዓይነት ደግሞ ከችሎታ
መለኪያ ፈተና ይመደባል፡፡

Alderson (1999)፣ Hughes (2003) እና Madson (1983) እንደሚገልፁት በተለያዩ የመስኩ


ልሂቃን የሚጠቀሱት የፈተና አይነቶች የችሎታ መለኪያ ፈተና፣ የብቃት መለኪያ ፈተና፣
የጥንካሬ እና ድክመት መለኪያ ፈተና እና የቅድመ እና ድህረ ችሎታ መለኪያ ፈተና ናቸው፡፡
ከነዚህ የፈተና አይነቶች መካከል የዚህ ጥናት ትኩረት የችሎታ መለኪያ ፈተና ሲሆን አንድ
የትምህርት መርሃ-ግብር ከተጠናቀቀ በኋላ በዓመቱ አጋማሽ ወይም መጨረሻ ላይ የሚቀርብ
የፈተና አይነት ነው፡፡ የችሎታ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች ከተማሩት ትምህርት ውስጥ ምን
ያህሉን ጨብጠውታል? ምን ያህሉንስ በተግባር ማሳየት ችለዋል? ከታቀደውና ከተማሩት
ትምህርት ውስጥ ምን ያህሉ ግቡን መቷል? የሚሉትን ፍሬ ነገሮች ለማወቅ የሚያስችሉ
መረጃዎችን ለማግኘት ከሚሰጡ ፈተናዎች አንዱ ነው፡፡ ፈተናው ተማሪዎች አንድን የተወሰነ
ትምህርት ከተማሩ በኋላ የሚቀርብ ሲሆን የሚካተቱት ጥያቄዎችም ከመርሃ ትምህርቱና
ከመጽሃፉ ላይ ተመስርተው የሚዘጋጁና ከመማር ማስተማሩ ሂደት ጋርም ጥብቅ ቁርኝት
ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ይህን የፈተና አይነት Alderson እና ሌሎች (1995) ሲገልፁ የችሎታ መለኪያ ፈተና
ለትምህርት የቀረበውን መርሃ ትምህርት ወይም መማሪያ መፅሃፉን መሰረት አድርጎ
የሚዘጋጅና በትምህርት መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ላይ የሚሰጥ የፈተና አይነት ነው ይላሉ፡፡

7
ከሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች አስቀድሞ ከሚሰጡ የችሎታ መለኪያ
ፈተናዎች መካከል ደግሞ የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው የሞዴል ፈተና አንዱ ነው፡፡

የአስረኛ ክፍል ሞዴል ፈተናዎች እንደ ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናዎች ተማሪዎችን
ወደቀጣዩ የክፍል ደረጃ እንዲዛወሩ አልያም የመዛወር እድላቸው ባለመሳካቱ ሌላ የትምህርት
አማራጭ እንዲፈልጉ ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ ለመስጠት አይረዱም፡፡ ነገር ግን ምን ያህል
እንዳወቁና ምን እንደቀራቸው ራሳቸውን ገምግመው የማጠናቀቂያ ፈተናቸውን ከመውሰዳቸው
በፊት ባላቸው ጊዜ እንዲዘጋጁ በማትጋት ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው ሲሆኑ ለተማሪዎች
የጊዜ አጠቃቀምንና የመልስ አጠቋቆርን እንዲለማመዱ ያግዟቸዋል፡፡

በችሎታ መለኪያ ፈተና ስር የሚመደበው የሞዴል ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
ከየትምህርት ቤቶች የተውጣጡ መምህራን ክፍለ ከተማ ላይ በመሰባሰብ የሚያዘጋጁት ነው፡፡
ዓላማውም ተማሪዎች እንዲማሩት የቀረበላቸውን የትምህርት ይዘት ምን ያህል እንደተረዱት
መገምገምና ለቀጣይ ፈተና እንዲዘጋጁ ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ሞዴል ፈተናዎች በመርሃ
ትምህርቱ ወይም በመማሪያ መፅሃፉ በሰፈሩ የትምህርት ይዘቶች ላይ መመስረት አለባቸው፡፡
የትምህርት ይዘቶቹ በመርሃ-ትምህርቱ በጥቅል የሚቀመጡ ሲሆን፣ በጥቅል የተቀመጡት
ይዘቶች ደግሞ ዕለት ከዕለት ተግባራዊ በሚሆኑበት መልኩ በዝርዝር ለተማሪዎች የሚደርሱት
በመማሪያ መፅሃፋቸው በኩል ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ለዚህ ጥናት በተመረጠው ክፍለ ከተማ
ሲሰጡ የነበሩት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ለዘጠነኛ እና ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች
የተዘጋጁትን የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መማሪያ መፃህፍት ይዘት እና ለመፃህፍቱ መዘጋጀት
ምክንያት የሆኑትን የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች መሰረት አድርገው የተዘጋጁ መሆናቸውን
አጥኚው ማረጋገጥ ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲገመግሙ፣
እንዲዘጋጁ እና እንዲለማመዱ የማድረግ ዓላማ ኖሯቸው ከትምህርት ቤት በተውጣጡ የአስረኛ
ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁት ጥያቄዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና
አንፃር መዘጋጀት አለመዘጋጀታቸውን መረዳት ይሻል፡፡ በመሆኑም ጥናቱ በዋናነት በአዲስ አበባ
ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም
ተዘጋጅተው የተሰጡ የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች ከችሎታ

8
መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ እና ይዘቶቹ ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው
የይዘት ዝምድና የተፈተሸበት ነው፡፡

1.2. የጥናቱ መነሻ ችግር

የዚህ ጥናት አድራጊ ለጥናቱ ከመረጠው ርዕስ ጋር የሚዛመዱ እና በቅርብ ያገኛቸውን ቀደምት
ጥናቶች ለመዳሰስ ሞክሯል፡፡ በዳሰሳውም በአማርኛ ቋንቋ ፈተና ላይ የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶችን
ተመልክቷል፡፡ ጠጅቱ (1999)፣ አብርሃም (2003)፣ አበበች (2004)፣ ወንድማገኝ (2005)፣
ሙሉፀሀይ (2005) እና መሰረት (2005) የተባሉ አጥኝዎች የሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ
ጥናታቸውን በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተና ላይ ያካሄዱ ናቸው፡፡

ከነዚህ መካከል ጠጅቱ፣ አብርሃምና ወንድማገኝ ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በሀገር-አቀፍና


በትምህርት ቤቶች ደረጃ የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎችን ያጠኑ ሲሆኑ ጠጅቱ በሀገር-
አቀፍ ፈተናዎች ውጤት የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማወዳደር ጥናቷን ስታካሂድ
አብርሃም ደግሞ ከአንድ ዞን የተመረጡ ትምህርት ቤቶችን ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት
ለመገምገም ሞክሯል፡፡ ወንድማገኝም እንዲሁ በሀገር አቀፍና በሞዴል ፈተናዎች መካከል ባለ
የይዘትና የአቀራረብ ንፅፅር ላይ ትኩረት ያደረገ ጥናት አካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል የአበበች፣ የሙሉፀሀይ እና የመሰረት ጥናቶች ደግሞ ለስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች
በቀረቡ ፈተናዎች ላይ ያተኮሩ ሆነው ከነዚህ መካከል አበበችና መሰረት በክልላዊ ፈተናዎች
ላይ ጥናታቸውን ሲያካሂዱ ሙሉፀሀይ በክልላዊና በሞዴል ፈተናዎች ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው
ጥያቄዎችን ብቻ ነጥላ የይዘትና የአቀራረባቸውን ሁኔታ ለመገምገም ሞክራለች፡፡

9
ቀደም ሲል የተጠቀሱትን ጥናቶች ጠቅለል አድርገን ከአላማቸው አንፃር ስንመለከታቸው
የፈተና ውጤቶችን የማወዳደር፣ የይዘት ተገቢነት ደረጃቸውን የመመርመር፣ በሀገር አቀፍና
በሞዴል ፈተናዎች መካከል ያለውን የይዘትና የአቀራረብ ሁኔታ የማነፃጸር እና በፈተናዎቹ
ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ጥያቄዎችን በተናጠል የመገምገም ዓላማ ያላቸው ሆነው
እናገኛቸዋለን፡፡

ይህ ጥናት ግን ከላይ ከተጠቀሱት በተለየ መልኩ ትኩረት ያደረገው በክፍለ ከተማ ደረጃ
ከትምህርት ቤት በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት በተዘጋጁ የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ
ሞዴል ፈተናዎች ላይ ሆኖ በፈተናዎቹ የተካተቱት ይዘቶች ምን ምን እንደሆኑ፣ ከችሎታ
መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ እና ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸውን የይዘት
ዝምድና የመመርመር ዓላማ ያለው ነው፡፡ ጥናቱን ከተካሄደበት ቦታ አንፃር ስንመለከተው
ደግሞ የዚህ ጥናት አጥኝ ካገኛቸውና በጥናቱ ተተኳሪ የክፍል ደረጃ ላይ ከተከናወኑ ጥናቶች
መካከል አንዱ በሀገር አቀፍና በሞዴል ፈተናዎች መካከል ባለ የይዘትና የአቀራረብ ሁኔታ ላይ
ከማተኮሩ ውጪ ሌሎቹ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ እና በጋምቤላ ክልሎች ላይ የተካሄዱ
ናቸው፡፡ ይህ ጥናት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ባለ አንድ ክፍለ-ከተማ
ፈተናዎች ላይ የተካሄደ ሆኖ የይዘት ዝምድና ፍተሻውም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት ከተዘጋጁት የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ጋር በመሆኑ ከሌሎቹ ሁሉ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም በዚህ
ጥናት የተካተቱት ፈተናዎች ከተዘጋጁበት ጊዜ አንፃርም ስንመለከታቸው ከ2009 ዓ.ም ወዲህ
ያሉ የሶስት ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በመሆናቸው ከሌሎቹ ጥናቶች የተለየ
እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

ከዚህም በላይ አጥኝው ባደረገው ዳሰሳ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በክፍለ ከተማ ደረጃ
በተዘጋጁ የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ላይ የተሰራ ጥናት አላገኘም፡፡ የዚህ
ጥናት ተተኳሪ በሆነው ክፍለ ከተማም ቢሆን ሞዴል ፈተናዎች ከተዘጋጁ በኋላ ምን ምን
ይዘቶችን እንዳካተቱ እና መሰረት ካደረጓቸው የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍል መማሪያ መፅሃፎች
ጋር ያላቸው የይዘት ዝምድና የሚረጋገጥበትም ሆነ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን

10
እንደሚመስሉ የሚፈተሽበት መንገድ አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡ በመሆኑም ጥናቱ አቅጣጫውን
በዚህ ላይ ለማድረግ ያነሳሳው የመጀመሪያው ምክንያት ይህ ነበር፡፡

በሌላ በኩል አጥኚው በመረጠው ልደታ ክፍለ ከተማ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ሀገር አቀፍ
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናዎችን ከመውሰዳቸው በፊት በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚዘጋጁ
ሞዴል ፈተናዎችን እንዲፈተኑ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የፈተናዎቹ ዓላማም ተማሪዎች በተማሩት
ትምህርት ምን እውቀት እንደጨበጡና ምን እንደሚጎላቸው ራሳቸውን እንዲገመግሙ፣
እንዲለማመዱና እንዲዘጋጁ ማድረግ ነው፡፡ የሚዘጋጁት ፈተናዎችም ተማሪዎች ከመማሪያ
መፅሃፎቻቸው በተማሩት ትምህርት ላይ መሰረት ማድረግ እንዳለባቸው ይታመናል፡፡ ስለዚህ
የዚህ ጥናት ሁለተኛ ምክንያትም ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም በክፍለ ከተማው የተዘጋጁት
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች ከሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሃፎች ጋር ያላቸው
የይዘት ዝምድና ምን እንደሚመስል እና ከችሎታ መለኪያ ፈተና አኳይ ምን እንደሚመስሉ
ፈትሾ ማወቅ ለቀጣይ ተመሳሳይ ተግባራት ግብዓቶችን ማግኘት ይቻላል ተብሎ በአጥኚው
መታሰቡ ነው፡፡ ሌላውና ሶስተኛው ምክንያት ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሰጡ የአማርኛ
ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች በባህርያቸው ከድህረ መማር ፈተናዎች ውስጥ የሚካተቱ ስለሆኑ
በተጠቀሱት ዓመታት ውስጥ የተዘጋጁት ፈተናዎች በዕርግጥም ተማሪዎች በታላሚው ቋንቋ
ትምህርት ክሂላትና የዕውቀት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ችሎታ ለመለካት የሚያስችሉ መሆን
አለመሆናቸውን ፈትሾ አጥኝው ማረጋገጥ መፈለጉ ነበር፡፡

የመጨረሻውና አራተኛው ምክንያት ደግሞ አጥኚው "Language teasting & Assessment"


የተሰኘውን ኮርስ ሲወስድ ለኮርሱ ማሟያ ይሆነው ዘንድ በኮርሱ መምህር ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ
አማካኝነት በተሰጠው ሰሞነኛ ስራ (አሳይመንት) በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኘው
ደጃዝማች ባልቻ አባነፍሶ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ለዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎች በ2010 ዓ.ም የተሰጠውን የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት የማጠቃለያ ፈተና (ከ40%)
ከቋንቋ ትምህርት ይዘቶች አንፃር ለመፈተሽ ሞክሮ ነበር፡፡ በዚህም በተጠቀሰው ዓመተ ምህረት
በትምህርት ቤቱ የተሰጠው የአማርኛ ቋንቋ ማጠቃለያ ፈተና ለሁለቱ የእውቀት ዘርፎች (ስነ
ፅሁፍና ሰዋስው) በቁጥር 35 በፐርሰንት ደግሞ 87.5% እድል ሲሰጥ ለአራቱ የቋንቋ

11
ትምህርት ክሂላት (ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍ) የሰጠው እድል ግን በቁጥር 5
በፐርሰንት ደግሞ 12.5% ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ ትምህርት ቤቱ ወይም በትምህርት
ቤቱ የሚያስተምሩት መምህራን ዋናውን የቋንቋ ትምህርት ዓላማ እንደ ዘነጉት ነው፡፡
ምክንያቱም አንድ ተማሪ ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍ ሳይችል ወይም መቻሉ በፈተና
ሳይረጋገጥ ስነፅሁፍንና ስነ ልሳንን (ሰዋስው)ን በማስተማርና በመፈተን በታላሚው ቋንቋ ብቁ
ማድረግ ይቻላል ብሎ ማሰብ አዳጋች ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም አጥኚው ከ2009 እስከ 2011
ዓ.ም ድረስ በልደታ ክፍለ ከተማ ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጁትን ሞዴል ፈተናዎች
ከቋንቋ ትምህርት ይዘቶች አንፃር ምን እንደሚመስሉ መመርመር መፈለጉ ነው፡፡ በመሆኑም
ይህ ጥናት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሯል፡፡

1. በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ ይዘቶች ምን ምን ናቸው?


2. ሞዴል ፈተናዎቹ መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሃፎች ጋር
የይዘት ዝምድና አላቸው?
3. የሞዴል ፈተናዎቹ ጥያቄዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን ይመስላሉ?

1.3. የጥናቱ ዓላማ

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ ከ2009-2011 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ
የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ነው፡፡ ጥናቱ ይህንን አብይ ዓላማ
ለማሳካት የሚከተሉት ንዑሳን ዓላማዎች ነበሩት፡፡

1. በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ ይዘቶችን መለየት፤

2. ሞዴል ፈተናዎቹ መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሃፎች ጋር የይዘት


ዝምድና እንዳላቸው መፈተሽ እና

3. የሞዴል ፈተናዎቹ ጥያቄዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ


መገምገም ናቸው፡፡

12
1.4. የጥናቱ ጠቀሜታ

በትምህርት ዙሪያ የሚካሄዱ ጥናቶች ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑ
እሙን ነው፡፡ የመማር ማስተማር ሂደት ካለ ደግሞ ፈተና መኖሩ እርግጥ ነው፡፡ በመሆኑም
በፈተናዎች ላይ የሚካሄዱ ጥናቶች ለተማሪዎች፣ ለመምህራን፣ ለፈተና አዘጋጆችና ጥናት
ለሚያካሂዱ አካላት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡ Tyler (1969) ይህንን ሀሳብ ሲያጠናክሩ በፈተና
ላይ የሚካሄዱ ጥናቶች ለመማር ማስተማሩ ሂደትና ለፈተና አዘገጃጀት ስልቶች መሻሻል
ጠቃሚ መረጃ በመስጠት በኩል ጉልህ ሚና አላቸው ይላሉ፡፡ በመሆኑም ይህ ጥናት
የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል ተብሎ ይታሰባል፡፡

1. የሞዴል ፈተናዎች ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል መማሪያ መፅሃፎች ጋር ምን ያህል


ዝምድና እንደነበራቸው ለፈተና አዘጋጆች ተጨባጭ መረጃ ይሰጣል፡፡
2. የሞዴል ፈተናዎችን አዘገጃጀት በመፈተሽ ለሚታዩ ችግሮች የመፍትሄ ሀሳብ
በመጠቆም ወደፊት ለሚዘጋጁ የሞዴል ፈተናዎች አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶችን
ያስገኛል፡፡
3. የቋንቋ መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜ የችሎታ መለኪያ ፈተና
አዘገጃጀት ሂደትን በመከተል ለማዘጋጀት ያግዛቸዋል፡፡
4. መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜ መማሪያ መፃህፍቱን መሰረት አድረገው
እንዲያዘጋጁ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
5. የተማሪዎች የቋንቋ ችሎታ በሚገባ እንዲለካ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
6. ከየትምህርት ተቋማት ለሚውጣጡ የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ኮሚቴ አባላት
ፈተናዎች ተዘጋጅተው የተማሪዎችን ችሎታ ከመለካታቸው አስቀድሞ
እንዲገመግሟቸው ያመላክታል፡፡
7. ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ጥልቅ ምርምር ለማድረግ ለሚፈልጉ
ተመራማሪዎች እንደ መነሻ ሀሳብ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡

13
1.5. የጥናቱ ወሰን

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ከ1992 ዓ.ም
ጀምሮ ከየትምህርት ቤቱ በተውጣጡ መምህራን አዘጋጅነት የሞዴል ፈተናዎችን ለአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች ሲፈትን መቆየቱን ከክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት በተደረገው
የሰነድ ፍተሻ አማካኝነት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ጥናት ከጊዜ አንፃር ከክፍለ
ከተማው ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ባሉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ከትምህርት ቤቶቹ
በተውጣጡ መምህራን አዘጋጅነት ተሰናድተው ተግባራዊ በተደረጉት ፈተናዎች ላይ ብቻ
የተገደበ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም በዚህ ጥናት የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ማለትም አራቱ ክሂላትና
ሁለቱ የዕውቀት ዘርፎችን መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች በሙሉ የተዳሰሱ በመሆኑና ከሶስት
ተካታታይ ዓመታት በላይ ቢሰራ ከጥያቄዎቹ ብዛት አንፃር አጥጋቢ ውጤት ላይገኝ ይችላል
ከሚል እሳቤ የተነሳ ነው፡፡ በሌላ በኩል ከ2009 እስከ2011 ዓ.ም ድረስ ያሉት ሶስት ተከታታይ
ዓመታት የተመረጡበት ምክንያት ደግሞ የቅርብ ጊዜ በመሆናቸውና መረጃዎቹን በቀላሉ
ማግኘት ስለተቻለ ነው፡፡

የዚህ ጥናት ጉዳይ የታላሚው ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች በመሆናቸው በክፍለ ከተማ ደረጃ
የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች እንጂ ሌሎች ፈተናዎች በጥናቱ
አልተካተቱም፡፡ ከጥናቱ ዓላማ እና ለሞዴል ፈተናዎቹ ዝግጅት መሰረት ከመሆኑ አኳያም
የይዘት ዝምድ ፍተሻው የተደረገው ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ነው፡፡ በመሆኑም የማዛመዱ
ተግባር የተከናወነው በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር
በ2004 ዓ.ም ከታተሙት የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍል መማሪያ መፃህፍት ጋር ነው፡፡
በተጨማሪም የሞዴል ፈተናዎቹ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ የተፈተሹ
ሲሆን በአንፃሩ ከቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና፣ ከደረጃ መለኪያ ፈተና እና ከጥንካሬና
ድክመት መለኪያ ፈተና ፈተና አኳያ አልተዳሰሱም፡፡ ስለሆነም በዚህ ጥናት በተጠቀሱት
ዓመተ ምህረቶች የተዘጋጁት የሞዴል ፈተናዎች ያካተቷቸው የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች፣
ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የይዘት ዝምድና እና ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን

14
እንደሚመስሉ የተፈተሹ ሲሆን የፈተናዎቹ አስተማማኝነትና ተተግባሪነት እንዲሁም አቀራረብ
የዚህ ጥናት ጉዳይ ባለመሆናቸው በጥናቱ አልተቃኙም፡፡

1.6 የጥናቱ ውስንነት

በተቻለ መጠን ጥናቱ አስተማማኝ ይሆን ዘንድ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም በጥናቱ ርዕሰ ጉዳይ
ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶችን ከመዳሰስ ጀምሮ ለዚህ ጥናት መሰራት ምክንያት የሆኑ ነገሮች
ተለይተዋል፡፡ ለጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉ መረጃዎችም በጥናቱ የመረጃ
መሰብሰቢያ መሳሪያ አማካኝነት ተሰብስበዋል፡፡ ተገቢ የሆነ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ በመምረጥም
የተጠየቁትን መሰረታዊ ጥያቄዎች መሰረት ያደረገ ተገቢ ትንተና እና ማብራሪያ በማድረግ፣
ማጠቃለያ፣ መደምደሚያ እና የመፍትሄ ሀሳብ ለማቅረብ ጥረት ተደርጓል፡፡ ከላይ የተጠቀሱ
ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም ይህ ጥናት ግን ከተለያዩ ችግሮች የፀዳ አይደለም፡፡ ቀደሚው የዚህ
ጥናት ውስንነት ለ፪ኛ ደረጃ ተማሪዎች የሞዴል ፈተና መሰጠት ከተጀመረ ብዙ ዓመታትን
ያስቆጠረ ቢሆንም በዚህ ጥናት የተካተቱት የሶስት ዓመታት ፈተናዎች ብቻ መሆናቸው
ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አስር ክፍለ ከተሞች የሚገኙ በመሆናቸው
እያንዳዳቸው ክፍለ ከተሞች በራሳቸው ሞዴል ፈተናዎችን አዘጋጅተው ለተማሪዎች የሚሰጡ
ቢሆኑም በዚህ ጥናት ግን የተካተተው በአንድ ክፍለ ከተማ አማካኝነት ተዘጋጅቶ ለደረጃው
ተማሪዎች በሚቀርብ ሞዴል ፈተና ላይ መሆኑ ጥናቱ ከውስንነት የፀዳ እንዳይሆን
አድርጎታል፡፡

1.7. የጥናቱ ቁልፍ ቃላት እና ሃረጋት

በዚህ ጥንት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ቁልፍ ቃላት እና ሐረጋት አምስት ሲሆኑ
እነሱም ይዘት፣ የይዘት ዝምድና፣ የይዘት ተገቢነት፣ የሞዴል ፈተና እና የችሎታ መለኪያ

15
ፈተና ናቸው፡፡ እነዚህ ቃላት እና ሐረጋት በዚህ ጥንት ውስጥ ያላቸው ትርጓሜ በአጭሩ
እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1. ይዘት፡- አራቱን የቋንቋ ትምህርት ክሂላት ማለትም ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍ
እንዲሁም ሁለቱን የእውቀት ዘርፎች ማለትም የስነ ልሳንና የስነ ፅሁፍ እውቀትን እና
በስራቸው የሚገኙ ንዑሳን ርዕሰ ጉዳዮችን የሚመለከት ነው፡፡

2. የይዘት ዝምድና፡- አራቱን የቋንቋ ትምህርት ክሂላት እና ሁለቱን የእውቀት ዘርፎች


በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎች የተካተቱ ጥያቄዎች ይዘት ከ፪ኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ
መፃህፍት ይዘት ጋር ያላቸውን ግንኙነት ነው፡፡

3. የይዘት ተገቢነት፡- በጥያቄነት የተካተቱት የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች በአይነትም ሆነ


በመጠን በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ ከተሰጣቸው ሽፋን አንፃር ሲታዩ ተመጣጣኝ ውክልና
ሊኖራቸው ይገባል ማለት ነው፡፡

4. ሞዴል ፈተና፡- ተማሪዎች በተማሩት ትምህርትና በመማሪያ መፅሃፋቸው ማዕከልነት


የሚዘጋጅ ሲሆን ምን ያህል እንዳወቁና ምን እንደቀራቸው ራሳቸውን ገምግመው የማጠናቀቂያ
ፈተናቸውን ከመውሰዳቸው በፊት ባላቸው ጊዜ እንዲዘጋጁ የሚያደርግ የፈተና አይነት ነው፡፡

5. የችሎታ መለኪያ ፈተና፡- በመርሃ ትምህቱ አጋማሽ ወይም መርሃ ትምህርቱ ከተጠናቀቀ
በኋላ ተማሪዎች የተማሩተን ትምህርት በሚገባ መከታተላቸውን ለመለካት ሲባል መማሪያ
መፃህፍቱን መሰረት አድርጎ የሚሰጥ ፈተናን ይመለከታል፡፡

16
ምዕራፍ ሁለት፤ ክለሳ ድርሳናት

2.1. የቋንቋ ፈተና ምንነት

ፈተና በቋንቋ ትምህርት ሒደት ውስጥ ታልመው የነበሩ ዓላማዎች መሳካት አለመሳካታቸውን
የምንፈትሽበት፣ በተማሪዎች ላይ የሚታየውን የአስተሳሰብና የአሰራር ለውጥ ለመለካት
የምንገለገልበት፣ በቋንቋ መርሀ ትምህርትና በተማሪዎች መፅሀፍ ላይ ተመስርቶ የሚከናወን፣
የተማሪው የቋንቋ ችሎታ ብቻ ሳይሆን የመምህሩም የማስተማር ተግባር የሚፈተሸበት፣
በመማር ማስተማሩ ሒደት ላይ ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚገኙበት መሳሪያ ነው፡፡ በተጨማሪም ፈተና የትምህርትን ዓላማ መሰረት አድርጎ በስርዓተ
ትምህርትና በመርሀ-ትምህርት የሚመራ፣ ተማሪዎች ምን ተምረዋል? ምን አውቀዋል? ምን
ይጎድላቸዋል?---ለሚሉት ፅንሰ ሀሳቦች ምላሽ የሚሰጥ የመማር ማስተማሩ አንዱ አካል ነው፡፡

ፈተናን በተመለከተ የተለያዩ ባለሙያዎች የየራሳቸውን ሀሳብ የሚያንፀባርቁ ቢሆንም ከሞላ


ጎደል ሀሳባቸው የቃላት የአገላለፅ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር የፅንሰ-ሀሳብ ልዩነት ግን
አይስተዋልብትም፡፡ ለአብነት ያክልም፡- አረጋ (2014) ፈተና የተማሪዎች ግንዛቤና ብቃት
የሚለካበት መሳሪያ ነው በማለት ሲገልፁት፤ Brown (1994) ደግሞ ፈተና ከዕለት ዕለት
የመማር ማስተማር ተግባር ጋር የተያያዘ ዓላማ ያለውና ተፈላጊውን የተማሪ ችሎታና
እውቀት መለካት የሚያስችል ዘዴ ነው በማለት ይበይኑታል፡፡ በተጨማሪም ደሳለኝ (1994)
ፈተና ተገቢነት ባላቸው ቃላት አማካኝነት ተቀነባብሮ በትልም የሚመራ፣ የተማሪዎችን የግል
ችሎታና ዕውቀት በተወሰነ የትምህርት ዘርፍ የምንለካበት መሳሪያ ነው በማለት
ይተረጉሙታል፡፡

ከምሁራኑ ብያኔ ተነስተን፣ ፈተና ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሒደት ውስጥ እንዲገነዘቡ፣
እንዲከታተሉና እንዲያስተውሉ የምናደርግበት፣ የቀረበውን ትምህርት ምን ያህል

17
እንደተገነዘቡ፣ እንዳስተዋሉና እንደተከታተሉ የምንፈትሽበት፣ ትምህርቱ ያስከተለውን የባህርይ
ለውጥ የምንመረምርበትና የዳበረውን ብቃት የምንለካበት አሀድ ነው ማለት ይቻላል፡፡
በተጨማሪም ፈተና ከመማር ማስተማር ተግባር ጋር ጥብቅ ትስስር ያለውና ለአንድ
የትምህርት ፕሮግራም የተቀመጠ ዓላማ በተማሪዎች ዘንድ ምን ያህል ተፈፃሚ እንደሆነ
ወይም ግብ መምታቱንና አለመምታቱን የምናረጋግጥበት ነው፡፡ ፈተና ተማሪዎች ምን
እንደሚያውቁ፣ የተለያዩ ተግባራትን እንዴት እንደሚያከናውኑ ወይም ምን እንደሚፈልጉ
ለማወቅ ሲፈለግ ተገቢ ጥያቄዎች በመጠየቅ በቂ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡

የቋንቋ ፈተና ከሌሎች የትምህርት ዓይነቶች ፈተና ለየት ይላል፡፡ ምክንያቱም የቋንቋ ትምህርት
ለማስተማር ካለው ዓላማ የሚነሳ በመሆኑ ነው፡፡ Bachman (1990)፣Weir (2005) እና
Alderson እና ሌሎች (1995) እንደገለፁት የቋንቋ ፈተና ተማሪዎች የተማሩትን የትምህርት
ይዘት ምን ያህል እንደተገነዘቡት ለመረዳት የሚያስችል ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች
በእያንዳንዱ የቋንቋ ክሂል እና የእውቀት ዘርፍ ያላቸውን ጥንካሬ እና ድክመት፣ እውቀትና
ችሎታ፣ ፍላጎትና የዕለት ተዕለት መሻሻል ለመለየት የሚዘጋጅ ሲሆን አንድ መምህር
የሚጠበቅበትን የማስተማሪያ ዘዴ ብቃት ለመገምገም እና በተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ ያሉ
ተፈታኞች በዚያ ደረጃ ሊኖራቸው ይገባል ተብሎ የሚታሰብን የቋንቋ ክሂል እና የዕውቀት
ዘርፍ ብቃት ለመለካት የሚሰጥ ነው፡፡

እንደ Heaton (1975)፣ Gronulonad (1981) እና Genessee and Upsher (1996) አገላለፅ
ደግሞ የቋንቋ ፈተና የተማሪዎችን የባህርይ ለውጥ ለመለካት የሚያስችል እና ቀድመው
የተነደፉትን ዝርዝር የቋንቋ ትምህርት ዓላማዎች መገንዘባቸውን ለማወቅ የሚረዳ ሲሆን
ተማሪዎች ከአንድ የክፍል ደረጃ ወደ ሚቀጥለው የክፍል ደረጃ የሚሸጋገሩበትን ሁኔታ
ለመወሰንም በመረጃ ምንጭነት የሚያገለግል እና የቋንቋን ምንነትና አጠቃቀም በተመለከተ
ምላሽ የሚሹ ተግባራትን አካቶ የሚዘጋጅ ስርዓታዊ መሳሪያ ነው፡፡ Mehrens እና Lehman
(1974) በበኩላቸው የቋንቋ ፈተና ተማሪዎች በታላሚው ቋንቋ ያላቸውን የማዳመጥ፣
የመናገር፣ የማንበብና የመፃፍ ችሎታ እንዲሁም የስነፅሁፍና የስነ-ልሳን እውቀት በተመለከተ
ከመማራቸው በፊት የነበራቸውን ቅድመ-ችሎታ ወይም ከተማሩ በኋላ ያላቸውን ለውጥ

18
ገምግሞ ለመረዳት የሚያገለግል መሳሪያ ነው ይላሉ፡፡ ተስፋዬ (1981) እንዲሁ እንደገለፁት
የቋንቋ ፈተና ተማሪዎች በቋንቋ ትምህርት ላይ የሚያሳዩትን መሻሻል ወይም የቋንቋ ችሎታ
እና የሚያስመዘግቡትን የባህርይ ለውጥ ለመገምገም የሚረዳ ሲሆን በቋንቋ መርሀ-ትምህርቱና
በመማሪያ መፅሐፍ ላይ ተመስርቶ የተማሪዎችን የቋንቋ ብቃት ለመመዘንና ለመገምገም
የሚያገለግል ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡

ከላይ የተገለፀውን ሀሳብ ጠቅለል አድርገን ስንገልፀው፡- የቋንቋ ፈተና ከቋንቋ ትምህርት ጋር
ጥብቅ ትስስር ያለው፣ የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ፣ እድገት ወይም መሻሻል በተመለከተ
መረጃዎችን የሚሰጥ፣ ተማሪዎች ያላቸውን የቋንቋ ችሎታ ምን ያህል አውጥተው ለተግባቦት
ስራ ያውሉታል ለሚሉት ፅንሰ ሀሳቦች ፍንጭ የሚጠቁም፣ የቋንቋ ትምህርት አሰጣጡን
ጠንካራና ደካማ ጎን ለመመዘንና ለመገምገም የሚረዳ፣ የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ መዳበሩንና
በቋንቋ ችሎታቸው አማካኝነት ሀሳባቸውን መግለፅ መቻላቸውንና አለመቻላቸውን ለመለየት
የሚያስችል፣ የተማሪዎቹን የተወዳዳሪነት ስሜትከማጎልበቱም በላይ ትምህርቱን ትኩረት
ሰጥተው እንዲከታተሉ የሚያደርግ፣ ተማሪዎች በተማሩት የቋንቋ ትምህርት የክሂልና
የዕውቀት ዘርፎች ረገድ ያላቸውን ችሎታና ያሳዩትን የባህርይ ለውጥ እንዲሁም ስለቋንቋ
ምንነት እና አጠቃቀም ያላቸው ግንዛቤ የሚለይበት አቻ የሌለው የመመዘኛ ስልት ነው::

2.2. የቋንቋ ፈተና ዓላማ

የቋንቋ ፈተና በቋንቋ መማር-ማስተማር ሂደት ላይ እንደዋነኛ የትምህርት መሳሪያ ተደርጎ


እንደሚያገለግል የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ Harrison (1983) እና Ur (1996) እንደሚገልፁት
የቋንቋ ፈተና ዓላማዎች ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ይዘት ምን ያህል እንዳወቁት
መፈተሸ፣ ድክመትና ጥንካሬያቸውን ለይተው በዚያ ላይ እንዲሰሩ ማስቻልና መምህራን
የማስተማር ስልታቸውን ብቃት እንዲገመግሙ የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የፈተና
አይነት በዕቅድ የሚከወን፣ ከቋንቋ ትምህርት በኋላ የሚሰጥ በመሆኑ የሚከተሉት መሰረታዊ
ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

19
ሀ. በተማሪዎቹ መካከል የሚታየውን የችሎታ ልዩነት የመመዘንና የመገምገም ዓላማ ማንገብ፤

ለ. በቋንቋ ትምህርት ሒደት ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉትን ችግሮች ለመለየትና መፍትሔም


ለማፈላለግ እገዛ ማድረግ፤

ሐ. አስቀድሞ የታቀደው የቋንቋ ትምህርት በሚፈለገው መንገድ ከግብ መድረስ መቻሉን


የማረጋገጥ ሚና መጫዎት፤

መ. የቋንቋ ተማሪዎችን ቅድመ ችሎታና ደረጃ ለመለካትና ጥንካሬና ድክመትን የመለየት


ተግባር ላይ መዋል እና

ሠ. የቋንቋ ተማሪዎች ችሎታ ደከም የሚልበትን ይዘት ለይቶ በመረዳትና ክለሳ በማድረግ የላቀ
እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የቋንቋ ፈተና እንደመማር ማስተማሩ ተግባር ሁሉ በዓላማ ላይ ተመስርቶ


የሚቀርብ መሆኑን መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ዓላማውም ተማሪዎች በተማሩት የታላሚ ቋንቋ
ትምህርት የክሂል እና የዕውቀት ዘርፎች ላይ ያላቸውን ድክመትና ጥንካሬ በመለየት
የትምህርቱ ይዘት መሰረት ያደረገው ዓላማ ከግብ እንዲደርስ በሚያስችል መልኩ መዘጋጀት
ይኖርበታል፡፡

2.3. የቋንቋ ፈተና አይነቶች

ፈተናዎች ከትምህርት ቤት ውጭ ወይም በትምህርት ቤት ውስጥ ሊዘጋጁ ይችላሉ፡፡


በትምህርት ቤት ውስጥ የሚዘጋጁ ፈተናዎች በመምህራን ተዘጋጅተው ለተማሪዎች የሚቀርቡ
ሲሆን መሰረት የሚያደርጉትም መርሃ ትምህርቱን ወይም መማሪያ መፃህፍቱን ይሆናል
(Njabili,1993)::

20
ከላይ ለማንሳት እንደተሞከረው በተለያዩ አካላት በተለያዬ አቀራረብ የሚዘጋጁና የየራሳቸው
ዓላማና ይዘት ያላቸው፣ የተለያዩ ችሎታዎችን የሚለኩ በርካታ የፈተና ዓይነቶች ቢኖሩም
Cohen እና Manion (1994)፣ Harrison (1989)፣ Hughes (1989) እና Brown (1980)
እንደሚገልፁት በቋንቋ ትምህርት መስክ የተለመዱ የፈተና ዓይነቶች አራት ናቸው፡፡ እነሱም፡-
የብቃት መለኪያ ፈተና፣ የድክመትና ጥንካሬ መለኪያ ፈተና፣ የቅድመ ችሎታ መለኪያ
ፈተናና የችሎታ መለኪያ ፈተና በመባል ይታወቃሉ፡፡ በሌላ በኩል Heaton (1975) ብዙ
ምሁራን የሚስማሙባቸው የቋንቋ ፈተና አይነቶች የቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና፣ የደረጃ
መለኪያ ፈተና እና የችሎታ መለኪያ ፈተና ናቸው በማለት በሶስት ይከፍሏቸዋል፡፡
በተጨማሪም Kaplan (2001) ፈተና ከሚለካው የባህርይ አይነት አንፃር የችሎታ መለኪያ
ፈተና፣ የቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና እና የግንዛቤ ደረጃ መለኪያ ፈተና በመባል በሶስት
እንደሚከፈል ገልፀዋል፡፡

ከምሁራኑ ሀሳብ በመነሳት የፈተና ዓይነቶችን አከፋፈል በተመለከተ ወጥነት እንደሌለ መረዳት
ይቻላል፡፡ ለፈተና አይነቶቹ መብዛትና መለያየት ደግሞ በምክንያትነት የሚጠቀሰው ፈተናዎቹ
የሚቀርቡበት ዓላማ የተለያየ መሆኑ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከእያንዳንዱ መስፈርት አኳያ የጋራ
ባህርያትን በመለየት ለተፈለገው ዓላማ መጠቀም እንዳለብን መገንዘብ ይቻላል፡፡ የዚህ ጥናት
የትኩረት ነጥብ በሴሚስተር ማጠቃለያ በሚሰጠው የሞዴል ፈተና ላይ ከመሆኑ አንፃር
ይህንኑ የሚመለከተው የችሎታ መለኪያ ፈተና በዝርዝር የሚፈትሽ ሲሆን ሌሎቹ የፈተና
አይነቶች ግን በጥልቀት የማይዳሰሱ ይሆናል፡፡

2.3.1. የቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና

ይህ የፈተና ዓይነት ተማሪዎች ወደ ተፈለገው የትምህርት ደረጃ ከመግባታቸው በፊት


ለደረጃው የሚያበቃቸው ችሎታ እንዳላቸው ለመመዘን የሚያስችል ስለሆነ በተመሳሳይ ችሎታ
ላይ ያሉ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዲመደቡና ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያደርግ
እንደሆነ Harrison (1983) እና Brown (1994) ይገልፃሉ፡፡ በመሆኑም በቋንቋ ትምህርት
የቅድመ ችሎታ መለኪያ ፈተና ተቀዳሚ ዓላማው የተማሪዎችን አጠቃላይ ችሎታ በመለየት

21
የሚመጥናቸውን የቋንቋ ትምህርት ይዘት መንደፍና የአተገባበር ስልቱን አቅጣጫ ማስያዝ
ነው፡፡

2.3.2. የደረጃ መለኪያ ፈተና

የደረጃ መለኪያ ፈተና ከተለያየ ቦታ ወደ አንድ ቦታ የሚሰባሰቡ ተማሪዎች በአንድ የትምህርት


እርከን ላይ ተመሳሳይ ትምህርት ወይም ስልጠና ወስደው መምጣታቸውን ለመፈተሽ የሚዘጋጅ
ሲሆን ዓላማውም ተማሪዎች ካለፈው ስልጠና ወይም ትምህርት የቀሰሙትን እውቀት መለየት
ነው፡፡ Harrison (1983) እና Brown (1994) እንደገለፁትም ይህ የፈተና ዓይነት ተማሪዎች
በተማሩት ትምህርት ላይ ያላቸውን ብቃት በመፈተሽ በሚገኘው ውጤት ደረጃ ለመስጠት
የሚያስችል ነው፡፡ በመሆኑም የደረጃ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች በተለያየ ቦታ ትምህርታቸውን
ሲከተተሉ ቆይተው ወደ አንድ ስፍራ በሚሰባሰቡበት ወቅት በተተኳሪው ትምህርት ላይ
ይዘውት የመጡትን እውቀት ለመፈተሽና ደረጃቸውን ለማወቅ የሚያስችል ነው፡፡

2.3.3. የጥንካሬና ድክመት መለኪያ ፈተና

ተማሪዎች በየትኛው የትምህርት ይዘት ላይ ጥንካሬ እንዳላቸውና በየትኞቹ ደግሞ ደካማ


እንደሆኑ ለመለየት የሚያስችል ሲሆን የማካካሻ ትምህርትም ለመስጠት የሚያስችል የፈተና
አይነት ነው፡፡ Heaton (1975) እና ተስፋዬ (1981) የጥንካሬ ድክመት መለኪያ ፈተና
መምህራን ለተማሪዎች ተተኳሪውን ትምህርት ምን ያህል እንደተረዱትና እንዳልተረዱት፣
የትኛውን ይዘት በሚገባ እንዳወቁትና እንዳላወቁት የሚለዩበት የፈተና አይነት እንደሆነ
በማብራራት በዚህ የፈተና አይነት የሚገኘው ውጤት የሚወሰነው በግል ሳይሆን በጋራ
በሚታየው ውጤት ላይ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ አያይዘውም በፈተናው ከቀረቡት ይዘቶች ውስጥ
ብዙ ተማሪዎች የሚመልሱት በሚገባ መማራቸውን የሚጠቁም ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ በዙ
ተማሪዎች የማይመልሱት ይዘት ደግሞ በተገቢው ሁኔታ አለመማራቸውን የሚያመላክት ነው
በማለት ያስረዳሉ፡፡ በመሆኑም ይህ የፈተና አይነት የተማሪዎችን ጥንካሬ እና ድክመት

22
ለመለየት የሚያስችል ስለሆነ ተማሪዎችን በቀላሉ በመለየት እንደየችግራቸው ለመርዳት
የሚያስችል መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

2.3.4. የችሎታ መለኪያ ፈተና

የችሎታ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች በመርሃ ትምህርቱና በመማሪያ መፅሃፉ መሰረትነት


ሲማሩት የቆዩትን የትምህርት ይዘት ምን ያህል እንደጨበጡት ለመለካት የሚዘጋጅ የፈተና
ዓይነት ነው፡፡ በመሆኑም ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በዳሰሷቸው ምዕራፎች ወይም የትምህርት
ይዘቶች መነሻነት ይሰጣል ማለት ነው (Alderson እና ሌሎች፣ 1995)::

እንደ Hughes (1989) እና Bachman (1990)አገላለፅ ደግሞ የችሎታ መለኪያ ፈተና


የተለያዩ የመማር ውጤቶችን ለመለካት ሲባል የሚዘጋጅ የፈተና አይነት ነው፡፡ የሚዘጋጁት
ጥያቄዎችም ከመማሪያ መፃህፍቱ እና ከመርሃ ትምህርቱ ዝርዝር ይዘቶች እና ከትምህርቱ
ዓላማዎች ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የችሎታ መለኪያ ፈተና ዓላማ ፈተናው
ሊለካ የተፈለገውን ጉዳይ የመለየት፣ ብያኔ የመስጠትና ችሎታ የመለካት ትግባር ነው፡፡ ይሁን
እንጅ ተፈታኙ በሚገኝበት የክፍል ደረጃ፣ በቀረበው መርሃ ትምህርት እና መፃህፍት
መሰረትነት መዘጋጀት አለበት፡፡ ምክንያቱም የፈተናው ዋና ዓላማ በክፍል ደረጃው የሚገኘው
ተማሪ፣ ከተማረው ትምህርት ምን ያህሉን እንደተገነዘበ እና እንዳልተገነዘበ ለማወቅ እና ውሳኔ
ለመስጠት የሚዘጋጅ በመሆኑ ነው፡፡

የችሎታ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች የተወሰነ የትምህርት መርሃ ግብር ማጠናቀቃቸውን ወይም
የተወሰነ ዕውቀት ማዳበራቸውን ለማወቅ በሴሚስተሩ ወይም በዓመቱ መጨረሻ የሚሰጥ ፈተና
ነው፡፡ ስለዚህ በብሄራዊ ደረጃ ወይም በክልል ደረጃ እና በትምህርት ቤት ደረጃ በመምህራን
የሚዘጋጁ ፈተናዎች የችሎታ መለኪያ ፈተና ውስጥ የሚካተቱ ናቸው፡፡ Heaton (1975) እና
ተስፋዬ (1989) ይህን ሀሳብ በማጠናከር በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ሲማሩ የቆዩ

23
ተማሪዎች በአንድ ወቅት በጋራ የሚወስዱት የተወሰነ የትምህርት ደረጃ መጨረሻ ፈተና
የችሎታ መለኪያ ፈተና ይባላል በማለት ይገልፁታል፡፡

Harrison (1983) በበኩላቸው ይህ የፈተና ዓይነት በአንድ የትምህርት አይነት የተሰጡትን


የተለያዩ የትምህርት ይዘቶች እና በርከት ያሉ የትምህርት ልምዶችን ያካተተ በመሆኑ
ከጥንካሬ እና ድክመት መለኪያ ፈተና የተሻለ ነው፡፡ ምክንያቱም የችሎታ መለኪያ ፈተና
በተማሪዎች መካከል የሚኖረውን የችሎታ ልዩነት ለማነፃፀርና ደረጃውን ለመለካት ያገለግላል
በማለት ያብራራሉ፡፡ Cronbach (1970) የችሎታ መለኪያ ፈተናን አስመልክተው ሲገልፁ
ተማሪዎች የተማሩትን ትምህርት ምን ያህል እንደተገነዘቡት ለመዳሰስ ተብለው የሚዘጋጁት
ፈተናዎች በፈተናው ይዘት አመራረጥ ላይ ትልቅ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ
ያስጠነቅቃሉ፡፡ ይኸውም አንዳንድ የፈተና አዘጋጆች በትምህርት ይዘቱ የተወሰነ አካባቢ ወይም
ለጥያቄ ይመቻል ባሉት ይዘት ብቻ ያተኩራሉ፡፡ ይህ ደግሞ የተማሪዎችን ውጤት ከማበላሸት
በተጨማሪ የትምህርቱ ዓላማ መሳካት አለመሳካቱን በትክክል ሊገመግም የማይችል አካሄድ
ነው በማለት ሰፊ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ አይይዘውም ይህን ችግር ለመቅረፍ የፈተና ይዘት
መወሰኛ ሰንጠረዥ በማዘጋጀት ይህንን የሚወክል የፈተና ይዘት ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ
ናሙና መውሰድ ያስፈልጋል በማለት አብራርተዋል፡፡

የችሎታ መለኪያ ፈተና በቀጥታ በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ ከተዳሰሱት ምዕራፎች እና


በአጠቃላይ በመርሃ ትምህርቱ በሰፈረው የትምህርት ይዘት ተመርኩዞ የሚዘጋጅ በመሆኑ
ይህንኑ የሚወክል የፈተና ይዘት በአግባቡ መቅረብ አለበት (Brown,1994):: እንደ Harrison
(1983) አገላለፅም የቋንቋ መርሃ ትምህርቱ እና የመማሪያ መፅሃፉ ይዘቶች የቋንቋ ትምህርት
ዓላማዎችን በዝርዝር ለማስፈር ታቅደው የተዘጋጁ በመሆናቸው በፈተና ናሙና አመራረጥ ላይ
ይበልጥ ትኩረት ሊደረግባቸው እንደሚገባ ያስገነዝባሉ፡፡ እያንዳንዱ በመማሪያ መፅሃፉ ላይ
ያለው ይዘት ለቋንቋ ትምህርት ዓላማ መሳካት እና አለመሳካት የሚያደርገው የራሱ የሆነ
አስተዋፅኦ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ለመለካት በሚያስችለው ፈተና ላይ በአግባቡ እና በትክክል
ተወክሎ ሊገኝ ይገባል በማለት ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

24
በአጠቃላይ የችሎታ መለኪያ ፈተና ማለት ተማሪዎች የተማሩትን የቋንቋ ትምህርት ምን
ያህል እንደተገነዘቡት ለማወቅ የሚሰጥ የፈተና ዓይነት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ የችሎታ
መለኪያ ፈተና መሰረት አድርጎ የሚነሳውም በክፍል ውስጥ የቀረበውን ትምህርት ነው፡፡
ስለዚህ በሴሚስተር ወይም በዓመቱ መጨረሻ በመምህራን ተዘጋጅተው የሚቀርቡ ፈተናዎች
ምድባቸው በዚህ የፈተና ዓይነት ስር ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ተማሪዎች እንዲጨብጡት
የተፈለገውን ትምህርት መያዝ አለመያዛቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል ብቃት ያለው ፈተና
በትክክለኛው እና በወካይ ናሙና አማካኝነት መዘጋጀት አለበት፡፡

አንድ ፈተና ሲዘጋጅ በወካይ ናሙና አማካኝነት እንዲዘጋጅ የሚያስችሉ እና በአበይትነት


የሚጠቀሱ መስፈርቶች ተገቢነት፣ አስተማማኝነት፣ እና ተተግባሪነት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ
የዚህ ጥናት ተተኳሪ መስፈርት የሆነው ደግሞ ተገቢነት ነው፡፡ እንደ Harrison (1983)፣
Hughes (1989) እና Brown (1994) አገላለፅ አንድ የቋንቋ ፈተና ተገቢነት አለው የሚባለው
መለካት ያለበትን ነገር በትክክል መለካት ወይም መመዘን የቻለ እንደሆነ ነው፡፡ Alderson እና
ሌሎች (1995) እንደሚገልፁት ደግሞ አንድ ፈተና ለታቀደው ዓላማ ተገቢነት ያለው ሆኖ
ካልተገኘ ከፈተናው ይገኛል ተብሎ የተጠበቀው መረጃ የታሰበውን ያህል አይሆንም፡፡ ይህም
የሚያሳየን የፈተና ተገቢነት የሚባለው ፈተናው ሊመዝን ወይም ሊለካ የሚችለውን ጉዳይ
በተገቢ መልኩ መለካት ወይም መመዘን መቻሉን ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

በአጠቃላይ ከተሰነዘሩት ሀሳቦች የምንረዳው አንድ የቋንቋ ፈተና ተገቢነት አለው የምንለው
ፈተናው ሊለካ የታሰበውን የቋንቋ ዕውቀት ወይም ክሒል በትክክል መለካት እንዳለበት ነው፡፡
ነገር ግን ፈተናው ተገቢ ካልሆነ ፈተናውን መሰረት በማድረግ የሚሰጠው ውሳኔ ወደተሳሳተ
መንገድ ሊያመራ የሚችል መሆኑን እንረዳለን፡፡ ከዚህ አኳያ የችሎታ መለኪያ ፈተናዎችን
ለመገምገሚያነት የሚውሉ እና አንድ መምህር ከሚጠቀምባቸው የተገቢነት አይነቶች ውስጥ
አንዱ የሆነው እና የህ ጥናትም ትኩረት የሚያደርግበት የይዘት ተገቢነት ነው (Harison,
1983)::

25
2.4. የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርት ዝምድና

Harrison (1989) እንደሚገልፁት ቀደም ባሉት ዘመናት ቋንቋን ማስተማርና ቋንቋን መፈተን
ግንኙነት እንደሌላቸውና ፈተናዎች በመማር ማስተማሩ ሂደት ሚና አልባ ተግባራት ተደርገው
ይቆጠሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ቋንቋን ማስተማርና ቋንቋን መፈተን እርስ በርስ የተቆራኙና
የማይለያዩ ተግባራት እንደሆኑ Woodford (1980) እና Heaton (1975) ያስረዳሉ፡፡ Madsen
(1983)፣ Bertrand እና Sebula (1980) እንዲሁም Brown (1980) ፈተና የተማሪዎችን
እድገት በየጊዜው ለመከታተልና ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የመማር ማስተማሩ አካል ነው
ሲሉት Agarwal (1996)፣ Taiwo (1995) እና Heaton (1990) ደግሞ ፈተና ተማሪዎችን
ለማበረታታት፣ እድገትና መሻሻላቸውን ለመከታተል፣ የመማር ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ
ሃሳብ ለመስጠት፣ ስርዓተ ትምህርቱን ለማሻሻልና በአጠቃላይ የመማር ማስተማሩ ሂደት
የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ ዓላማ ይዞ ከመካሄዱ አንፃር ከማስተማር ተግባርም ተለይቶ
እንደማይታይ ይገልፃሉ፡፡

ከልሂቃኑ ሀሳብ መረዳት እንደሚቻለው የቋንቋ ትምህርትና የቋንቋ ፈተና የማይነጣጠሉ የአንድ
ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው፡፡ ከቋንቋ ፈተና ውጭ ተማሪዎች በመማር ማስተማሩ ዓላማ
በትክክል እየተጓዙ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያዳግታል፡፡ ሁለቱ ተግባሮች የማይነጣጠሉና እርስ
በርስ ተደጋጋፊነት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ ከሁሉም ወገን ይልቅ ለፈተና ቀራቢነት የሚኖረው
መምህሩ እንደሚሆን መረዳት አያዳግትም (Axman, 1989)::

Heaton (1990) እና Harrison (1989) እንደሚገልፁት የተማሪዎችን ማንነት፣ የቋንቋ


ችሎታ፣ ድክመትና ጥንካሬ በማወቅ በኩል መምህራንን የሚስተካከል ባለመኖሩ ከማንኛውም
ፈተና ይልቅ መምህሩ የሚያዘጋጀው የበለጠ ቦታ ይይዛል፡፡ ስለዚህ ቋንቋን ማስተማርም ሆነ
መፈተን የማይነጣጠሉ ከመሆናቸው አንፃር ሁለቱም በተገቢው መንገድ ሊከወኑ ይገባል፡፡
በወጉ የተዘጋጀ ፈተና በመማር ማስተማሩ ሂደት አወንታዊ ሚና ሲኖረው፤ ይህ ካልሆነ ግን
ውጤቱ የተዛባ ስለሚሆን በርካታ ችግሮችን ያስከትላል (Gottfredson, 2004):: በመሆኑም

26
ይህ ጥናትም ታላሚ ያደረገውን የሞዴል ፈተና ቁመና በመፈተሽ ጠንካራ ጎኑ እንዲቀጥል
ድክመት ካለው ደግሞ ለወደፊት እንዲስተካከል የማድረግ ዓላማን የዞ የተነሳ ነው፡፡

የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርት ተደጋጋፊና የማይነጣጠሉ የቋንቋ መማር ማሰተማር


ተግባራት በመሆናቸው በመካከላቸው ጥብቅ ትስስር ሊኖር እንደሚገባ ይታመናል፡፡ የቋንቋ
ትምህርት በሚሰጥበት የቋንቋ ፈተና መሰጠቱ ግድ ሲሆን ጥሩ የሚባል ፈተናም የትምህርቱን
ሂደት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በማመላከት ለመማር ማስተማሩ ስኬታማነት አዎንታዊ
አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡ Heaton (1975) የቋንቋ ፈተና እና የቋንቋ ትምህርትን ዝምድና
ሲገልፁ በቋንቋ መማር ማስተማር ሂደት ማስተማር እና መፈተን አንደኛው ከሌላኛው
ተነጥለው የሚሰጡ እንዳልሆኑና ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው የቋንቋ መማር ማስተማር ተግባር
አካላት እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡ በተመሳሳይ Balker (1989) እንደገለፁት ፈተና በቋንቋ
ትምህርት ሂደት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት
ቤት አስተዳደር አካላት መረጃን፣ ማነቃቂያንና ማረጋገጫን ስለሚፈልጉና ይህንንም የሚያገኙት
ከፈተና ስለሆነ ነው፡፡

የቋንቋ ትምህርት ፈተናዎች በቅድመ መማር፣ በመማር ሂደት እና በድህረ መማር ጊዜያት
ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች በተማሩት ትምህርት ላይ መሰረት አድርገው የሚሰጡት
ፈተናዎች ግን በአብዛኛው በድህረ መማር ጊዜ የሚሰጡ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይህ የፈተና
አይነት ተማሪዎች ከተማሩት የቋንቋ ትምህርት ጋር ያለው ዝምድና ጥብቅ ሊሆን ግድ ይላል፡፡
Hughes (1989) ይህንኑ ዝምድና ሲያመለክቱ ከፈተና አይነቶች መካከል በተለይም የድህረ
መማር ፈተና መሰረት የሚያደርገው ተማሪው የተማረውን ትምህርት በመሆኑ በሁለቱ
መካከል ጥብቅ ግንኙነት ሊኖር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የዚህ ጥናት ጉዳይ የሆኑት በክፍለ ከተማ ደረጃ የተዘጋጁ የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት የሞዴል ፈተናዎች ተማሪዎች በቀረቡላቸው ይዘቶች አማካኝነት ያመጡትን ለውጥ፣
የጨበጡትን ክህሎትና እውቀት ለመመዘን ያለሙ ሆነው ተማሪዎችን የሀገርአቀፍ ማጠናቀቂያ

27
ፈተና ለማዘጋጀት ታስበው የሚሰጡ ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር እንዲማሩ የተደረጉትን የትምህርት
ይዘቶች መሰረት ያደረጉ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ተስፋዬ (1981) ሲገልፁ
ፈተና ተማሪዎች የተሰጣቸውን፣ እንዲማሩ የተደረጉትን ትምህርት ማወቅ አለማወቃቸውን
መለያ ስለሆነ መፈተን ያለባቸው ይህንኑ እንዲያውቁ የተማሩትን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ
ሲሆን ደግሞ በቋንቋ ፈተና እና በቋንቋ ትምህርት መካከል ጥብቅ ትስስር ይኖራል፡፡

በቋንቋ ፈተና እና በቋንቋ ትምህርት ዝምድና ዙሪያ ሃሳብ የሰነዘሩ ብዙዎች ምሁራን በፈተናው
እና በትምህርቱ መካከል ጥብቅ ትስስር ስለመኖሩ ወይም ሊኖር እንደሚገባ ልዩነት
ባይኖራቸውም ቅደም ተከተሉን በተመለከተ ግን ልዩነት አላቸው፡፡ ለአብነት ያህል Davies
(1968) ጥሩ ፈተና ያስተማርናቸውን ይዘቶች በመፈተን ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ከማስተማር
ተከትሎ የሚመጣ ተግባር ነው ሲሉ፣ Hughes (1989) ደግሞ ሁሌ የማስተማር ተግባር
ቀዳሚ ሲሆን መፈተን ደግሞ ተከታይ ተግባር ተደርገው መውሰድ እንደሌለባቸው ይገልፃሉ፡፡

ከልሒቃኑ ሀሳብ መረዳት የሚቻለው ፈተና ከማስተማር ተግባር ቀድሞም ይሁን ተከትሎ
የሚሰጥበት ሁኔታ ያለ መሆኑን ነው፡፡ ተማሪዎች ወደፊት ሊማሩት የሚገባቸውን የትምህርት
ይዘት ለመወሰን ፈተና መቅደም ያለበት ሲሆን፣ ሲማሩ የቆዩትን ማወቃቸውን ለመለካት
ደግሞ ፈተና ከትምህርቱ ተከትሎ መሰጠት ይኖርበታል፡፡ ይህም የቅደም ተከተሉ ሁኔታ
ፈተናውን በምንፈተንበት ዓላማ እንደሚወሰን የሚያመላክት በመሆኑ የHughes (1989) ሀሳብ
ሚዛን የሚደፋ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ስለሆነም በቋንቋ ፈተና እና በቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ
መካከልም ተመሳሳይ ዝምድና መኖሩ ግድ ነው፡፡ ምክንያቱም በክፍል ውስጥ ለተማሪዎች
የሚቀርቡት የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ላይ ሊመሰረት ግድ ስለሚል ነው፡፡ ይህን
አስመልክተው Hughes (1989) ሲገልፁ የቋንቋ ፈተና ይዘቶች በተለይም የችሎታ መለኪያ
ፈተና ይዘቶች ከመርሃ ትምህርቱ ወይም ከመማሪያ መፅሃፉ የተወሰዱ መሆን ይኖርባቸዋል
ይላሉ፡፡

28
የቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ጥቅል የመርሃ ትምህርት ይዘቶች ሊተገበሩ በሚችሉበት መንገድ
በዝርዝርና ለተማሪው በሚመጥን መልኩ የሚቀርቡበት ከመሆኑም ባሻገር ተማሪዎች በቅርብ
ሊያገኙት የሚችሉት የትምህርት መሳሪያ ነው፡፡ ለመምህሩም በክፍል ውስጥ ለሚያቀርበው
የቋንቋ ትምህርት የይዘት ምንጭ በመሆን ከማገልገል በተጨማሪ የመማር ማስተማር
ክንውኖችን እንዲሁም የክትትልና ግምገማ ስልቶችን በዝርዝርና ተግባራዊ ሊሆኑ በሚችሉበት
አቀራረብ ወደ ተማሪዎች ለማድረስ ያግዛል፡፡ Carter (1973) መማሪያ መፅሃፍ የተወሰነ
የትምህርት ይዘትን ይዞ በስርዓት የተደራጀ፣ ለተወሰነ የክፍል ደረጃ የሚዘጋጅና ለአንድ
የትምህርት ዘርፍ ዋና የጥናት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግል ነው በማለት ሲገልፁ፣ Harrmer
(1991) በበኩላቸው የቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ በመርሃ ትምህርቱ በጥቅል የተቀመጡትን
የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች እለት ከዕለት ተግባራዊ በሚሆኑበት መልክ የማቅረብ ሚና አለው
ይላሉ፡፡ የምሁራኑ ገላፃ በሞዴል ፈተና እና በመማሪያ መፅሃፉ መካከል ያለውን የይዘት
ዝምድና መፈተሸ ተገቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

በአጠቃላይ ከዚህ በላይ በዝርዝር ለማየት እንደተሞከረው በቋንቋ ፈተና እና በቋንቋ ትምህርት
መካከል የጠበቀ ዝምድና ሊኖር የሚገባው ከሆነ፣ በተመሳሳይ በቋንቋ ፈተና እና በቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ መካከልም ጥብቅ ዝምድና ሊኖር እንደሚገባ መገንዘብ አያዳግትም፡፡ እንደ
Cronbach (1970)፣ Heaton (1975) እና Hughes (1989) የተባሉ ምሁራን ገለፃ በቋንቋ
ፈተና እና በቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ መካከል ዝምድና መኖር አለበት ሲባል በጥያቄነት
የተካተቱት ይዘቶች በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ ካላቸው ሽፋን አኳያ የተወከሉ ሊሆኑ ይገባል
ማለት ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዝምድና የማይኖር ወይም ዝምድናው ልል የሚሆን ከሆነ
ደግሞ ፈተናው ቀድሞ የታቀደለትን ዓላማ ከግብ ላያደርስ የሚችልበት ሁኔታ ይከሰታል፡፡
በቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ይዘቶች እና በፈተና ጥያቄዎች መካከል ሊኖር ስለሚገባው ጥብቅ
ዝምድና ሲታሰብም ይህንን በትክክል እውን ለማድረግ የሚረዱ ስልቶችን አውቆ አንድ ስርዓት
ያለውን ስልት/መንገድ መርጦ በወጥነት መተግበር ሊዘነጋ የሚገባው ጉዳይ አይደለም፡፡

29
2.5. የቋንቋ ፈተና የይዘት ተገቢነት

አንድ ፈተና በጥራት እንዲዘጋጅ እና ትክክለኛውን መረጃ እንዲሰጥ ከሚያስችሉት ጉዳዮች


ውስጥ አንዱ ተገቢነት መሆኑን ቀደም ብሎ ተገልጿል፡፡ ተገቢነት በተለያዩ መልኮች የሚገለፅ
ቢሆንም በተለይ ደግሞ የይዘት ተገቢነት ከምንም በላይ አስፈላጊና አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ አንድ
ፈተና የይዘት ተገቢነት ይኑረው ሲባል በጥያቄነት ያካተታቸው የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች
በዓይነትም ሆነ በመጠን በመማሪያ መፅሃፉ ወይም በመርሃ ትምህርቱ ውስጥ ከተሰጣቸው
ሽፋን አንፃር ሲታይ ተመጣጣኝ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል ለማለት ነው (Cronbach, 1970)
እና (Gronulonad, 1981)::

እንደ Gronulonad (1981) እና ዳንኤል (2006) አገላለፅ ደግሞ የአንድን ፈተና የይዘት
ተገቢነትለመጠበቅ የናሙና ሂደትን መከተል አስፈላጊ ነው፡፡ ይህን የናሙና ሂደት ለማከናወን
እና የይዘት ተገቢነቱን የጠበቀ ፈተና ለማዘጋጀት የፈተና መወሰኛ ሰንጠረዥ የተሰኘ ባለሁለት
ረድፍ ቻርት ማዘጋጀት ያስፈልጋል በማለት ይገልፃሉ፡፡ ይህ ባለሁለት ረድፍ ቻርት የትምህርት
ይዘት እና ዝርዝር የትምህርት ዓላማዎችን የያዘ ነው፡፡ ይህን ሰንጠረዥ በመጠቀም ቀድሞ
የተነደፉትን የትምህርት ዓላማዎች እና ተማሪዎች የተማሯቸውን የትምህርት ይዘቶች መሰረት
ያደረገ ፈተና አዘጋጅቶ የፈተናውን የይዘት ተገቢነት ደረጃው ከፍ የሚልበትን አጋጣሚ
መፍጠር እንደሚቻል አክለው ያስረዳሉ፡፡

Hughes (1989) በበኩላቸው አንድ ፈተና የይዘት ተገቢነት አለው የሚባለው ተማሪዎች
ከተማሯቸው ይዘቶች ውስጥ በናሙናነት ያካተተ ሲሆን ነው፡፡ ይህም ማለት አንድ ፈተና
የይዘት ተገቢነት እንዲኖረው ከተፈለገ ዝግጅቱ በወካይ ናሙና ላይ መመስረት አለበት፡፡ ይህን
ማድረግ ደግሞ ይዘቶች በፈተናው ሳይካተቱ እንዳይቀሩ ከማድረጉም በላይ ፈተናው ጠቃሚ
በሆኑ እና ትኩረት በተሰጣቸው የትምህርት ክፍሎች ላይ እንዲያተኩር ያደርገዋል በማለት
ያብራራሉ፡፡ ከዚህ ሀሳብ የምንገነዘበው የፈተናውን የይዘት ተገቢነት ለመጠበቅ አንድን ፈተና
የሚያዘጋጅ መምህር ወካይ በሆኑ ጥያቄዎች ላይ መመስረት እንዳለበት ነው፡፡

30
Alderson እና ሌሎች (1995) የአንድን ፈተና የይዘት ተገቢነት ለመመርመር የሚረዱ ሶስት
የአጠናን ስልቶች አሉ በማለት ይገልፃሉ፡፡ እነሱም፡- የፈተናው ይዘት ከመርሃ ትምህርቱ
(ከመማሪያ መፅሃፉ) ይዘት ጋር ማነፃፀር፣ የፅሁፍ መጠይቆችን እና ቃለ መጠይቆችን
በማዘጋጀት ለመምህራን፣ በትምህርቱ የላቀ ችሎታ ለላቸው የመስኩ ምሁራንና ለተግባራዊ
ስነልሳን ሊቃውንት መጠይቆችን እንዲሞሎ ማድረግ እና በፈተና ጥያቄዎች እና ፅሁፎች ላይ
የባለሙያዎችን ዳኝነት መጠቀም ናቸው፡፡ ከእነዚህ የመገምገሚያ ስልቶች መካከል ደግሞ በዚህ
ጥናት ተግባራዊ የሚደረገው የይዘት ተገቢነት መገምገሚያ ስልት የፈተናውን ይዘት ከመማሪያ
መፅሃፉ ይዘት ጋር ማነፃፀር የሚለው ነው፡፡

Finochiaro እና Brumfit (1983) የይዘት ተገቢነትን በተመለከተ እንደገለፁት፣ አንድ ፈተና


በተመሰረተበት መፅሃፍ ውስጥ ያሉትን ይዘቶች ማንፀባረቅ ከቻለ የይዘት ተገቢነት ያለው
ፈተና ነው፡፡ ስለዚህ የአንድን ፈተና የይዘት ተገቢነት ለማረጋገጥ ፈተናው ያካተታቸው
ጥያቄዎች በዓይነትም ሆነ በብዛት መሰረት ከሚያደርጉት መፅሃፍ ይዘቶች ጋር የተጣጣሙ
መሆን አለባቸው፡፡ Harrison (1983) እንደገለፁትም በቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ላይ ተመስርቶ
ይዘቶችን በተመጣጠኑ እና ወካይ በሆኑ ናሙናዎች አማካኝነት የሚያቀርብ ፈተና የይዘት
ተገቢነት አለው ማለት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ይህ የተገቢነት ዓይነት ትኩረት የሚያደርገው ተፈታኞች አንድን የትምህርት ይዘት


በተማሩት የድግግሞሽ መጠን በመፈተን ላይ ነው፡፡ በመሆኑም የይዘት ተገቢነት ያለው የቋንቋ
ፈተና ለማዘጋጀት በመማሪያ መፅሃፉ የተካተቱትን ይዘቶች ሊያንፀባርቅ የሚችል ወካይ ናሙና
ጥያቄዎችን ማካተት ያስፈልጋል፡፡

31
2.6. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ምንነት

የቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ የመማር ማስተማሩ ሂደት ግቡን እንዲመታ የክፍል ደረጃ
ተወስኖለት የቋንቋ ትምህርት ዓላማዎችን ዋና ግብ በማድረግ የሚዘጋጅ ሰነድ ነው፡፡
በመሆኑም በመማር ማስተማሩ እንቅስቃሴ ትምህርቱን በእቅድና በተገቢ ሁኔታ እንዲተላለፍ
ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ነው፡፡

Ur (2006) እንደገለፁት የቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ አንድን የትምህርት ዓይነት ጥቅል ይዘት
የያዘ ጥራዝ ነው፡፡ ይህ ጥራዝ መምህሩም ሆነ ተማሪዎች ቅጅው የሚደርሳቸው ሲሆን
መምህሩና ተማሪው ተገቢውን መርህ እንዲከተሉ የሚያደርግና ለቋንቋ ትምህርት መሰረት
የሆነ የማስተማሪያና የመማሪያ መሳሪያ ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ Allwright (1981) እንደገለፁት
የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ተማሪዎች ለትምህርት የቀረበውን ቋንቋ በራሳቸው እንዲማሩ
የሚያስችሉ መምሪያዎች ከመሆናቸውም በላይ መፃህፍቱ ተማሪዎቹ መማር ያለባቸውን
የትምህርት ይዘቶች፣ ምሳሌዎችና መልመጃዎች ጭምር ይይዛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቋንቋ
መማሪያ መፃህፍት የትምህርቱ ሂደት የተስተካከለ እንዲሆን ታስበው የተዘጋጁ ሲሆን በክፍል
ውስጥ የሚቀርበውን ክንውን የመወሰን አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም እንደ Sheldon
(1987) አገላለፅ የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ከአንድ የትምህርት ተቋም እስከ ተገልጋዩ
ህብረተሰብ ድረስ ላለው የቋንቋ ትምህርት ሂደትና ፍላጎት በተገቢው ምላሽ ለመስጠት በሀገሪቱ
የትምህርት ፖሊሲና በመርሃ ትምህርቱ መሰረት የትምህርት ይዘቶቹ በሙያው በተካኑ
ባለሙያዎች አማካኝነት ተዘጋጅተው ለቋንቋ ትምህርት ዓላማ ግብ መምታት የሚቀርቡ ሰነዶች
ናቸው፡፡ በመሆኑም የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት የመማር ማስተማሩን ሂደት በተሟላ ሁኔታ
እንዲከናወን ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ፡፡

ተስፋዬ (1981) እንደገለፁት የቋንቋ ማስተማሪያ መሳሪያዎች ሆን ተብለው ለቋንቋ


ማስተማሪያነት የተዘጋጁ ወይም የተመደቡ ብቻ ሲሆኑ ለአንድ የተወሰነ ክፍል እንዲያገለግሉ
ስርዓተ ትምህርቱን ወይም የክፍሉ ተማሪዎች ሊኖራቸው ይችላል ተብሎ የሚገመተውን

32
ችሎታ መሰረት በማድረግ ለማስተማሪያነት ታስበው የሚዘጋጁ ሰነዶች ናቸው፡፡ ከዚህ አገላለፅ
እንደምንረዳው የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት መርሃ ትምህርቱንና የተማሪዎችን ፍላጎት መሰረት
አድርገው ከሚዘጋጁ የማስተማሪያ መሳሪያዎች መካከል በዋናነት የሚመደቡ ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ለተማሪዎች ቋንቋ ማስተማሪያነት የተዘጋጁ


መሆናቸውን እና ከሌሎች መፃህፍት በተሻለ ሀኔታ መልመጃዎችን፣ ጥያቄዎችንና ምሳሌዎችን
አካታው በመያዝ ለተማሪች ስለቀረበው የቋንቋ ትምህርት የተለያዩ ተግባራትን በመስጠት
እንዲለማመዷቸው በማድረግ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡ ለመምህሩም ምን
እንደሚያስተምር እና እንዴት እንደሚያስተምር አቅጣጫ የሚጠቁሙ በመሆናቸው
ለተማሪውም ሆነ ለመምህሩ ወሳኝ የመማሪያና የማስተማሪያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ተማሪዎች
በዋናነት የሚማሩት መማሪያ መፅሃፋቸውን በመሆኑም ፈተናዎችም ሲዘጋጁ የተማሪዎችን
መማሪያ መፃህፍት ማዕከል አድርገው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም በአንድ የክፍል ደረጃ
የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ውስጥ እንደ መሪ ሆነው የሚያገለግሉት ለክፍል ደረጃው
ይመጥናሉ ተብለው የተዛጋጁት መማሪያ መፃህፍት በመሆናቸው ነው፡፡

2.6.1. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት አስፈላጊነት

የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት በቋንቋ ትምህርት ውስጥ የሚኖሩ ክንውኖችን፣ ይዘቶችንና


የማስተማር ዘዴዎችን ለመምረጥና ለመተግበር የመነሻ መሰረቶች ናቸው፡፡ Behar (1994)
እንደገለፁት የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት አንድን ይዘት በተቀናጀ፣ ቅደም ተከተሉን በጠበቀና
በተጠየቀው መንገድ በማቅረብ መምህራን ይህን የአካሄድ ቅፅ ተከትለው እንዲያስተምሩ
ያግዛሉ፡፡ ለመምህራንና ተማሪዎችም የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡

ሀ. በተመሳሳይ የክፍል ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ተመሳሳይ ይዘት እንዲቀርብላቸው


ያግዛሉ፡፡

ለ. አንድን የተነደፈ ዓላማ ለማስፈፀም ስልታዊ በሆነ መንገድና በተደራጀ ቅፅ ለማዘጋጀት


ያስችላሉ፡፡

33
ሐ. ለመምህራን አጠቃላይ ትምህርቱን የማስተማር እቅድ ለመንደፍ እንደ ቢጋር ሆነው
ያገለግላሉ፡፡

መ. ለመምህራን፣ እንደተዘጋጀ ቅፅ በማገልገል ለትምህርቱ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እንዲያዘጋጁ


ይረዷቸዋል፡፡

የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ለቋንቋ ትምህርት ዓላማ ግብ መምታት ያላቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ
ነው፡፡ እንደ Richards and Rodgers (1986) አገላለፅ የአንድን ህብረተሰብ እድገት የኑሮ
ሁኔታ፣ ባህል፣ ፍላጎትና እምነት ወዘተ. ባገናዘበ መልኩ የሚዘጋጁ የቋንቋ ማስተማሪያ
መፃህፍት ከፍተኛ ጠቀሜታ ይሰጣሉ፡፡ ከዚህም ሌላ የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት በትምህርቱ
ሂደት ለሚታየው እንቅስቃሴና ለሚጠበቀው ውጤት የጎላ ሚና አላቸው፡፡ በዚህ ሁኔታ
በተማሪው፣ በባለሙያውና በህብረተሰቡ ዘንድ የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ተፈላጊነታቸው
ከፍተኛ ነው፡፡

ተስፋዬ (1981) የቋንቋ መማሪያ መፃህፍትን አስፈላጊነት በሚከተለው መልኩ ገልፀውታል፡፡

1. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ለመምህሩ የትምህርቱን ቅደም ተከተል በመወሰንና


በማቅረብ፣ መነሻውንና መድረሻውን በመጠቆምና ምን ማድረግ እንዳለበት በማመላከት
ትምህርቱን ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲያስተምር እገዛ ያደርጋሉ፡፡
2. የተለያዩ ጉዳዮችን በማቅረብ፣ የሚፈፀሙ ስራዎችን በመወሰን፣ ተማሪው የተማረውን
በተግባር እንዲገልፅ እድል በመስጠት፣ አስተማሪውም ሆነ ተማሪው ሊገነዘቡት
የሚችሉትን ይዘት በማቅረብና ለንባብ የሚቀርቡትን ምንባቦች በቃላት ብቻ ሳይሆን
በልዩ ልዩ ስዕሎች፣ ቻርቶች፣ ግራፎች እና ፎቶ ግራፎች ወዘተ. አጅቦ በማቅረብ
ትምህርቱ አስደሳች እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡
3. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ትክክለኛና ተገቢ የቋንቋ አጠቃቀም ስልትን የሚይዙ
በመሆናቸው በቋንቋ ትምህርት ሂደት ከስህተት የራቀ የቋንቋ ትምህርት ይዘትን
በማቅረብ የመማር-ማስተማር ሂደቱን ያግዛሉ፡፡

34
4. የቋንቋ መማሪያ መፃህፍት በቋንቋ ትምህርት ዘርፎች መካከል ያለውን ቅንጅት አጥጋቢ
በሆነ ስልት ለማጣመር ያግዛሉ፤ ይህም የቋንቋውን ክሂሎች እና የእውቀት ዘርፎች
በተመጣጠነ ደረጃ ለማስተማር ከማገዛቸው በላይ የቃላት አመራረጥን፣ የአገባብ
ስርዓትን፣ የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀምን፣ የአፃፃፍ ውበትን ወዘተ. የሚያጠቃልሉ
በመሆናቸው ጉልህ እገዛ ያደርጋል፡፡

2.6.2. የመማሪያ መፃህፍት ባህርያት

ከቋንቋ ማስተማሪያ መሳሪያዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የመማሪያ መፅሃፍ መሆኑ እሙን
ነው፡፡ ለተወሰኑ የክፍል ደረጃዎች መማሪያ እንዲሆኑ ታስበውና ሆን ተብለው የሚዘጋጁ
መፃህፍት በሚዘጋጁበት ወቅት የሚከተሉትን ባህርያት አሟልተው እንዲይዙ ይጠበቅባቸዋል
(ተስፋዬ፣ 1981)፡፡

ሀ. እውነተኛነት፡- ለትምህርት የቀረበው የቋንቋ ክፍል እውነት የቋንቋው ተናጋሪ ህብረተሰብ


የሚለው መሆን አለመሆኑን የሚዳኝበት ነው፡፡ ተማሪው እንዲማር የሚቀርብለት ርዕሰ ጉዳይ
ቋንቋውን ይበልጥ እንዲያውቀው የሚያደርግና የባለቤትነት ስሜት እንዲያድርበት የሚያደርግ
መሆን አለበት፡፡

ለ. ግልፅነት፡- የማስተማሪያ መሳሪያዎቹ የያዧቸው ርዕሰ ጉዳዮች መምህሩ እንዲያስተምር፣


ተማሪው እንዲማር ለማገዝ ሲባል በግልፅ መስፈር አለመስፈራቸው የሚመዘንበት ነው፡፡
ስለዚህ ግንዛቤ እንዲገኝባቸው የቀረቡ የቋንቋ ትምህርት ጉዳዮች ምንነታቸው በማያሻማ ስልት
መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ሐ. ተለጣጣቂነት፡- በአንድ መፅሃፍ ልዩ ልዩ ምዕራፎች መካከልም ሆነ ለተለያዩ ክፍሎች


በተዘጋጁ መፃህፍት መካከል ተለጣጣቂነት የቅደም ተከተል ጉዳይ ነው፡፡ ተማሪው ቀጥሎ
የሚደርስበት ምዕራፍ ካለፈው የተለየና ያደገ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ያለፈውን
የሚደግም ከሆነ ግን እድገት ወይም አዲስነት የለበትምና መሰልቸት ይከተላል፡፡

35
መ. ተግባራዊነት፡- መምህሩ እንዲያስተምር፣ ተማሪው እንዲማር የሚያግዝ መሳሪያ የመሆኑ
ጉዳይ ነው፡፡ የተዘጋጀው የማስተማሪያ መሳሪያ የያዘው የትምህርት ይዘት በተማሪው ተግባራዊ
የሚደረግ መሆን ይኖርበታል፡፡

ሠ. ተገቢነት፡- የማስተማሪያ መሳሪያው በይዘቱ ለተማሪዎች የክፍል ደረጃ፣ እድሜ፣ እውቀትና


ባህላዊ ዳራ የሚመጥን እና ተገቢ መሆን ይኖርበታል፡፡

በአጠቃላይ የአንድ ቋንቋ ትምህርት መማሪያ መፅሃፍ ለአንድ የክፍል ደረጃ ይመጥናል ተብሎ
ሲዘጋጅ፣ በውስጡ የሚያካትታቸው ይዘቶች እውናዊ፣ ግልፅና የማያሻሙ ከመሆናቸውም
ባሻገር የክፍል ደረጃውን በሚቀላቀሉ ተማሪዎች አቅም ሊተገበሩ የሚችሉ፣ ከእድሜያቸው፣
ከዕውቀታቸውና ከባህላዊ ዳራቸው አንፃር የተፈተሹ፣ ለተማሪዎቹ እውቀት የሚመጥኑ እና
ተገቢ የሆኑ ይዘቶችን ያካተቱ መሆን እንደሚኖርባቸው ሁሉ መማሪያ መፅሃፉን ማዕከል
አድርገው የተማሪዎችን ችሎታ ለመፈተሽ የሚዘጋጁ ፈተናዎችም ተዓማኒ፣ ግልፅና
የማያምታቱ፣ በክፍል ደረጃው ተማሪዎች አቅም ሊሰሩ ወይም ሊተገበሩ የሚችሉ፣ የቋንቋ
ትምህርትን ዓላማዎች መሰረት ያደረጉ እና ከተማሪዎች እድሜ፣ እውቀት፣ የክፍል ደረጃና
ባህላዊ ዳራ አንፃር የተቃኙ ሊሆኑ ይገባል፡፡

2.7. የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች

ፈተና በሚዘጋጅበት ጊዜ አንደኛው ተግባር በመርሃ ትምህርት ተነድፈው የተካተቱ ይዘቶችን


በመዘርዘር ከተሰጣቸው ትኩረት አኳያ በፈተናው እንዲካተቱ ማድረግ ነው (Alderson እና
ሌሎች፣ 1995 እና Hughes፣ 1989)፡፡ በዚህም ንዑስ ርዕስ በተለያዩ ፀሃፍት የተዘረዘሩ
ንዑሳን የማዳመጥ፣ የመናገር፣ የአንብቦ መረዳት እና የማፃፍ ችሎታዎችና የሰዋስውን እውቀት
የሚገለፁ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ጥናቱ ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ በመርሃ ትምህርቱ
የተካተቱ ይዘቶችን በቀላሉ ለይቶ ለመዘርዘር ያስችላል፡፡

36
2.7.1. የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች

የማዳመጥ ክንውን የአድማጭ እና ተናጋሪውን ክንውን የግድ የሚፈልግ ነው፡፡ ተማሪዎች ከስነ
ልሳናዊ ችሎታዎች ባሻገር የማዳመጥ ችሎታዎቻቸውንም ማዳበር አለባቸው፡፡ እነዚህም በቋንቋ
ውስጥ ያሉ ድምፃችን፣ የቃላትን ቅላፄ፣ የቃላትን ልዩ ልዩ ቅርፅ፣ የቃላትን ቅንጅታዉ
ስርዓት፣ ቁልፍ ቃላትን መለየት፣ የቃላትን ፍች ከአውዳቸው መረዳት፣ ሰዋሰዋዊ ቃላትን
መገንዘብ፣ የአያያዥ ቃላትን ሚና መረዳት፣ የዐረፍተ ነገር ክፍሎችን መገንዘብ፣ የሚሉ
አይነት ችሎታዎች ሊኖሩ ይገባል፡፡ እንዲሁም የገለፃውን አላማና አድማስ መረዳት፣ ርዕስና
እድገት መከታተል፣ ዋና ዋና ሃሳቦችን የመለየት፣ መላምቶችን የማመንጨት፣ ምክንያት እና
ውጤትን የማጤን፣ የቃላትን ፍች ከአውዳቸው መረዳት፣ ተናጋሪው ስለገለፃው ያለውን ግምት
መተንበይ፣ ዲስኩር መገንዘብ፣ ተዘዋዋሪ ቃላትን በአሰሳ መለየት፣ በንግግሩ ውስጥ የተካተቱ
ቃላትን እንደየተዛምዷቸው መፈረጅ፣ ስነ ድምፅን መሰረት በማድረግ የንግግሩን ሃሳብ
መረዳት፣ ስነ አገባብን መሰረት በማድረግ ቃላትን በምድባች ማደራጀት፣ አንድን ጉዳይ ከተወሰነ
ክስተት ጋራ ማዛመድ፣ የምክንያት እና ውጤት ግንኙነትን መገመት፣ ውጤትን መተንበይ፣
ርዕስን መገመት፣ መልእክትን በጥልቀት መረዳት፣ የንግግርን ፍሰት በትርጉማዊ ቃላት እና
ሃረጋት መከፋፈል፣ የቃላትን ክፍሎች መረዳት፣ መልእክትን ከዳራዊ እውቀት ጋራ ማዛመድ
እና አብይ የሚባለውን ሃሳብ መረዳት የማዳመጥ ችሎታዎች እንደሆኑ (ማረው፣ 2003)
ዘርዝረው ያቀርባሉ፡፡

Hughes (1989) ደግሞ የማዳመጥ ክሂል ችሎታዎችን እንደሚከተሉት በዝርዝር


ያስቀምጧቸዋል፡፡ እነዚህም፡- ተገቢውን መረጃ መለየት መቻል፣ የመመሪያዎችን ቅደም
ተከተል ፍሰት መከተል፣ የተሰጠንን መረጃ መረዳት፣ ሊገለፅ የተፈለገውን ጉዳይ መረዳት፣
የቀረበውን ጥያቄ ሃሳብ መገንዘብ፣ እርዳታን የሚያመለክት ጥያቄ መረዳት፣ ፍቃድን
የሚያመለክት ጥያቄን መረዳት፣ የክስተቶችን ቅደም ተከተል የሃሳብ ፍሰት መከተል፣
የሚቀርቡ አሰተያየቶችን መገንዘብ መቻል፣ በቀረበ አስተያየት ላይ የተሰጠን ማብራሪያ
መረዳት፣ በንፅፅር የሚቀርብን ሃሳብ መረዳት፣ በቀረበ ሃሳብ ላይ የተሰጠን ጥቆማ መረዳት እና
ማስተዋስ፣ የተሰጠን አስተያየት መገንዘብእና ማስተዋስ፣ አማራጭ ሃሳቦችን መረዳት እና

37
ማስታዎስ እና የግል አስተያየቶችን መረዳት እና ማስታዎስ መቻል ናቸው፡፡ እነዚህ የማዳመጥ
ክሂል ንዑሳን ችሎታዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ጋር በማያየዝ የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ችሎታዎች የሚባሉት የሚከተሉት ሲሆኑ


እነዚህም፡- ሰላምታዎችን እና የመግቢያ ሃሳቦችን፣ የስምምነት አቋም መግለጫዎችን፣
ስምምነት ላይ ያልተደረሰባቸውን ሃሳቦች፣ የንግግሩን ዓላማ፣ ለጥያቄ የተሰጠን ማብራሪያ
መረዳትእና ማስታዎስ፣ የተሰጠን አስተያየት ማስተዎስ፣ በውይይት የዳበሩ ሃሳቦችን መረዳት
እና ማስተዎስ መቻል፣ ተቀባይነት ያላገኙ ሃሳቦች የሚያመላክቱትን፣ በተናጋሪ የቀረበን የሃሳብ
ማስተካከያ፣ አድማጭ የተናጋሪውን ፍላጎት፣ ተናገሪው ሃሳቡን በሚያብራራበት ጊዜ፣
ተናጋሪው የተመለሱ ጥያቄዎች በሌላ ተናጋሪ የቀረቡ መሆናቸውን እና ሌሎችን ለማሳመን
የቀረበን ሃሳብ መረዳት እና ማስተዎስ መቻል ናቸው በማለት (Hughes 1989)
ይዘረዝሯቸዋል፡፡

2.7.2. የንግግር ክሂል ንዑሳን ይዘቶች

Brown (2004) የመናገር ክሂልን ለመፈተን የሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት


ናቸው፡፡ ይህን ክሂልን የምንለካባቸው ተግባራት አስመስሎ መናገር፣ ሰፋ ያለ ይዘት ያለው
ምላሽ የሚሰጥበት፣ ተግባቦታዊ ባለአንድ ገቢር ንግግርና ውስንናሰፊ የንግግር ክህሎት ፈተና
በመባል ይታወቃሉ፡፡

በመናገር ፈተና የሚለኩ የመናገር ክሂል ችሎታዎች:- ቃላትን የማጥበቅና የማላላት ሂደትን፣
የቃላትን ለዛ እንዲሁም የቃላትን ከፍና ዝቅ የማድረግ ሁኔታ መፍጠር፣ ያልተንዛዙ ቃላትና
ሀረጋትን መፍጠር፣ ለተግባራዊ አገልግሎት የሚውሉ በቂ ቃላትን መመስረት፣ በተለያየ
የአቀራረብ ፍጥነት የንግግርን ፍሰት መፍጠር፣ የመልእክቱን ግልጽነት ለመጨመር የተለያዩ
ዘዴዎችን በመጠቀም ማለትም እራስ ማረምን፣ በንግግር መሃል የሚደረግ እረፍትን፣ ክፍተት
መሙያዎችን ወደኋላ በመመለስ እና በማየት ንግግራችን በራሳችን መቆጣጠር፣ የሰዋሰው

38
ህጉን የጠበቁ የቃላት ክፍሎችን መጠቀም፣ ተፈጥሯዊ ባህሪውን የያዘ ንግግር ማዘጋጀት፣
በተለያየ የሰዋስው ቅርጽ ውስን የሆነ መልእክትን ማስተላለፍ፣ በንግግር ጊዜ የሚያስፈልጉ
የሃሳብ ማስተሳሰሪያዎችን መጠቀም፣ ሁኔታውን፣ ተሳታፊውንና ግቡን መሰረት ባደረገ መልኩ
ተገቢ የሆነ የተግባቦቱን ተግባር ማቅረብ፣ አግባብ የሆኑ ብልሀቶችን፣ መደበኛና ኢመደበኛ
የሆኑ፣ ቋንቋዎችን ድግግሞሾችን፣ ስምምነቶችን፣ ህጎችን፣ መድረክ መያዝንና ሌሎችም ፊት
ለፊት በሚደረጉ ንግግሮች የሚገቡ የማህበራዊ ስነልሳን ባህሪያትን መጠቀም፣ በድርጊቶች
መካከል አያያዞችን መጠቀም፣ የፊት ገጽታን፣ የኢቃላዊ የቋንቋ ጥናት፣ የሰውነት እንቅስቃሴ
የሰውነት ቋንቋና ሌሎችም ቃላዊ ያልሆኑ መግባቢያዎችን ከቃላዊ መግባቢያዎች ጋር
በመጠቀም ሀሳብን ማስተላለፍ፣ ባትሪ የሚባለውን የንግግር ዘዴ ቁልፍ ቃላት ላይ ትኩረት
ለማድረግ፣ ሀሳቡን በሌላ መንገድ ለመግለጽ፣ የቃላትን ፍች ለመፍጠር፣ አውዶችን ለማዘጋጀት
የንግግር ዘዴን ማጎልበትና መጠቀም እንደሆኑ (Brown፣ 2004) ይዘረዝራሉ፡፡

እንዲሁም ንዑሳን የመናገር ችሎታዎች (Hughes፣1989) በሦስት የመደባቸው ሲሆን፣


እነዚህም፡- መረጃ የመስጠት ችሎታ፣ የግንኙነት ችሎታ እና ግንኙነትን የመቆጣጠር ችሎታ
ናቸው፡፡ መረጃ የመስጠት ችሎታ የሚባሉት፡- እራስን የማስተዋዎቅ ችሎታ፣ ሌሎችን
የማስተዋዎቅ ችሎታ፣ ክስተቶችን በድርጊት እና ቅደም ተከተል መቅረብ ችሎታ፣ መመሪያ
የመስጠት ችሎታ፣ ሃሳብን በንፅፅር የመግለፅ ችሎታ፣ ገለፃ የመስጠት ችሎታ፣ አከራካሪ ሃሳብ
የማቅረብ ችሎታ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን መግለፅ ችሎታ፣ ስሜትን የማንፀባረቅ ችሎታ፣
እርዳታን የመግለፅ ችሎታ፣ ፍቃድ የመጠየቅ ችሎታ፣ ይቅርታ የመጠየቅ ችሎታ፣ ሃሳብን
የማብራራት ችሎታ፣ አስተያየት የመስጠት ችሎታ፣ አስተያየትን የማብራራት ችሎታ፣
የተቃርኖ ሃሳብ የማቅረብ ችሎታ፣ መላምት የመስጠት ችሎታ፣ ሃሳብን የመተንተን ችሎታ፣
የመተርጎም ችሎታ፣ ማጠቃለያ የመስጠት ችሎታ፣ ጥቆማ የመስጠት ችሎታ፣ አማራጭ
ሃሳቦች የማመቅረብ ችሎታ፣ ሃሳብን የመጠቅለል ችሎታ፣ አስተያየት የመስጠት ችሎታ እና
ለነገሮች ያለን አተያይ የመግለፅ ችሎታ ናቸው፡፡

የግንኑነት ችሎታ የሚባሉት ደግሞ፡- የንግግሩን ጠቀሜታ ወይም ግብ መግለፅ፣ የሌላኛውን


ተናጋሪ ሃሳብ ማስታዎስ መቻል፣ ለቀረበ ሃሳብ አስተያየት መስጠት መቻል፣

39
ለማንስማማባቸው ሃሳቦች ምክንያታዊ ሃሳብ ማቅረብ መቻል፣ የራስን አስተያየት መስጠት
መቻል፣ ገንቢ ሃሳብ መስጠት መቻል፣ የሚቀርቡ አስተያየቶችን አስፋፍቶ መግለፅ መቻል፣
የሚቀርቡ ሃሰቦችን አስተካክሎ ወይም አርሞ መግለፅ መቻል፣ አሳማኝ ሃሳብ ማቅረብ መቻል
እና የተስተካከለ ሃሳብ ማቅረብ መቻል ሲሆኑ ግንኙነትን የመቆጣጠር ችሎታ፡- ግኑኝነትን
የማነሳሳት ችሎታ፣ በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የተነሳን ሃሳብ የመለዋወጥ ችሎታ፣ ሃሳብን
ለሌሎች የማጋራት ችሎታ፣ ሌሎች ሃሳብ እንዲሰጡ የማነሳሳት እና የማስቀጠል ችሎታ፣ ወደ
አንድ ውሳኔ የመምጣትችሎታ፣ የግንኙነት መስተጋብርን የመቋቸት ችሎታ መሆናቸውን
(Hughes፣ 1989) ይዘረዝራሉ፡፡

2.7.3. የንባብ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች

የአንብቦ መረዳት ችሎታዎች ከየምንባብ ስልቶች ጋራ ጥብቅ የሆነ ዝምድና አላቸው፡፡ ማረው
(2003) Harmer (1991)ን ጠቅሰው እነዳስረዱት የአንብቦ መረዳት ስልቶች የሚባሉት በአሰሳ
(Skimming) ማንበብ፡- ስለፅሁፍ አጠቃላይ አተገባበር ለመጨበጥ በፍጥነት የሚከናወን የንባብ
ስልት ነው፡፡ በምልከታ (Scanning) ማንበብ፡- ከፅሁፍ ውስጥ አንድ ተፈላጊ መረጃ ነጥሎ
ለይቶ ማውጣት እና ለይቶ ለመረዳት በፍጥነት የሚከናወን ተግባር ነው፡፡ በስፋት ማንበብ
(extensive) ብዙ ጊዜ ለመዝናናት ሲባል አንድን ረዥም ፅሁፍ በስፋት ማናበብን
ይመለከታል፡፡ በጥልቀት ማንበብ (intensive)፡- የተወሰኑ ሃሳቦችን በጥልቀት ለመገንዘብ ሲባል
በዝርዝር እና በጥልቀት የሚከናወን ምንባብ ነው፡፡

እንደ Hughse (1989) ገለፃ በነዚህ የምንባብ ስልቶች ስር ሊዳብሩ የሚገባቸው የአንብቦ
መረዳት ችሎታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ በገረፈታ ንባብ ስር የሚካተቱ ንዑሳን ይዘቶች
የሚባሉት በፍጥነት ጠቃሚ የሆነውን ጉዳት መለየት፣ በፍጥነት የፅሁፉን አወቃቀር መረደት
እና በፍጥነት ዋናውን ጉዳይ መረዳት ሲሆኑ፣ በአሰሳ ንባብ ውስጥ ደግሞ ቁልፍ ቃላት እና
ሃረጋትን መለየት፣ አሃዞችን እና ፐርሰንቶችን መረዳት፣ ማጣቀሻ መፅሃፍትን መለየት፣
የተውላጦችን አንድምታ መረዳት፣ አስቸጋሪ ዓ.ነገሮችን መረዳት፣ ዋና ዓ.ነገሮችን መተንተን፣
የምንባቡን የሃሳብ አወቃቀር መረዳት፣ አከራካሪሃሳቦችን ማዳበር፣ ዝርዝር ሃሳቦችን ከዋናው

40
ሃሳብ መለየት፣ ግልፅ የሆኑ ዋና ዋና ሃሰቦችን መለየት፣ የፅኃፊውን ትኩረት የሳበውን ነገር
መለየት፣ የፀሃፊውን ተደራሲ መረዳት፣ እውነታን ከግል አስተያየት መለየት እና
መላምትን ከእውነታ መለየት ናቸው፡፡ በአንድምታ ስልት ደግሞ አውድን ተጠቅሞ የአዳዲስ
ቃላትን ፈች መረዳት፣ የፅሃፊውን ግላዊ ፈላጎት መረዳት፣ ሊያስተላልፍ የፈለገውን መልዕክት
አንድምታ ማወቅ እና አስተማማኝ አንድምታ ላይ መድረስ ናቸው፡፡

Alderson (2001) ደግሞ የአንብቦ መረዳት ችሎታወችን በሁለት ይመለከቷቸዋል፡፡ እነዚህም


ጠባብ የምንባብ ችሎታ እና ሰፊ የምንባብ ችሎታዎች ናቸው፡፡ ጠባብ የምንባብ ችሎታ ውስጥ
የአዳዲስ ቃላትን አውዳዊ ፍች መረዳት፣ የአገላለጾችን መልእክት መረዳት፣ ዝርዝር ሃሳቦችን
መለየት፣ የዲስኩር ቃላትን መተንተን፣ ቁለፍ ቃላትን መለየት፣ ሃሳብን አዛምዶ መረዳት እና
የሃሳብ ቅደም ተከተል ማስያዝ መቻል ናቸው፡፡ እንዲሁም ሰፊ የምንባብ ችሎታ ስር የፅሁፍን
ጭብጥ መረዳት፣ የፅሁፉን አላማ መረዳት፣ የደራሲውን አመለካከት መረዳት እና የምንባቡን
ድምፀት መረዳት ናቸው፡፡ ማረው (2003) በበኩላቸው ደግሞ የንባብ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የቃላትን አውዳዊ ፍች መረዳት፣ ዝርዝር የሆኑ ሃሳቦችን መለየት፣ አብይ የሆነን ጉዳይ
መለየትና ከተባለው ነገር ባሻገር መረዳት፣ የፅሁፉን ሙሉ ስዕል መገንዘብ፣ በዝርዝር
የተባለውን መጭመቅ፣ የነገሮችን ትስስር ወይም ተዛምዶ ማጤን፣ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮችን
መለየትና የመከራከሪያ ሃሳቦችን ተጠያቂነት መለየት እንደሆኑ ያስረዳሉ፡፡

2.7.4. የፅህፈት ክሂል ንዑሳን ይዘቶች

የፅህፈት ክሂል መፈተንም ሆነ ማስተማር ውስብስብ እና አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም


ለማስተማርም ሆነ ለመፈተን የሰዋስው እና የአፃፃፍ ዘዴ ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ የስነ-ፅሁፍ
አካባቢን ማወቅና መጠቀም ሁሉ ይጠይቃል፡፡ የመፃፍ ክሂልን ለመፈተን አምስት መሰረታዊ
ነገሮችን ማየት እንደሚያስፈልግ አክለው ገልፀዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አንደኛው የቋንቋ
አጠቃቀም ሲሆን በዚህ ስር ደግሞ ትክክልኛና ተገቢ ወይም ተስማሚ አረፍተ ነገር የመፃፍ
ችሎታ ይካተታሉ፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የአፃፃፍ ችሎታ ነው፡፡ በዚያ ችሎታ ስር ደግሞ ፅሁፍ
ቋንቋ ውስጥ የተለመዱና ተቀባይነት ያላቸውን ነገሮች በትክክል የመጠቀም ችሎታ፣ ለምሳሌ

41
ስርዓተ ነጥቦችና የቃላት አፃፃፍ የመጠቀም ችሎታ ይመለከታል፡፡ ሦስተኛው የፅህፈት ክሂል
ንዑስ ይዘት የይዘት አገላለፅ ሲሆን ሀሳብ የማፍለቅ፣ አላስፈላጊና የማይጠቀሙ ሀሳቦች
ነቅሶየማውጣት ችሎታ አጠቃሎ ይይዛል፡፡ የማስዋብ ክህሎት (የአፃፃፍ ብልሃት) ደግሞ
አራተኛው ችሎታ ሲሆን አረፍተ ነገሮችን፣ አንቀፆችን፣ የማደረጃትና ቋንቋውን በአግባቡ
የመጠቀም ችሎታ ነው፡፡ አምስተኛው የመወሰን ክህሎት (judgment skills) በመባል
የሚታወቅ ሲሆን ለአንድ ለተለየ ዓላማና አንድ የተወሰነ ታዳሚ አተገባበር ውስጥ ማስገባትና
ጠቃሚ የሆነ ሀሳብን የመምረጥ፣ የማደራጀትና የማሳካት ችሎታን የሚመለከት እንደሆነ
Heaton (1988) ያስረዳሉ፡፡

መምህራን የተማሪዎችን የመፃፍ ችሎታ ተገቢ በሆነ ሁኔታ የሚመዘኑበት ዋናው ዘዴ


የድርሰት ፈተና እንደሆነ Heaton (1988) እና Madsen (1983) ይገልፃሉ፡፡ የመፃፍ ክሂል
ፈተና ዋናው የድርሰቱን ተቀባይነት ለመገምገም እንደሆነ እና ይህም የአረፍተ ነገር
ትክክለኛነትን፣ አንድነትን፣ ግጥምጥምነትን እና አቀነባበሩን እንዲሁም ለቀረበው ታዳሚ ሀሳብ
የማስተላለፍ ችሎታን እንደሚያካትት ይገልፃሉ፡፡ Heaton (1988) እንደገለፁት ደግሞ
ተማሪዎች ምን አይነት የፅሁፍ ተግባራት ከሌሎች የትምህርት አይነቶች በየቀኑ
እንደሚያጋጥማቸው ለመወሰን ጥረት መደረግ አለበት፡፡ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ከሆነ ተማሪዎች
መደበኛና ኢመደበኛ የሆኑ ደብዳቤዎችን ለመፃፍ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች በድርሰት
ፈተና በጥንቃቄ በተመረጡ ርዕሶች ላይ ድርሰት ለመፃፍ ከተዘጋጁ የድርሰት ፅህፈት ጠቃሚ
የመፈተኛ መሳሪያ መሆን ይችላል፡፡ ይህ ለተማሪዎች የራሳቸውን የቋንቋ አደረጃጀት ችሎታ፣
የራሳቸውን የቃላት እና የሀሳብ አጠቃቀም እና ተግባቦትን መፍጠር እደሚችሉ የማየት እድል
ይሰጣቸዋል፡፡ በዚህ መንገድ የድርሰት ፈተናዎች ቀጥተኛ ፈተናዎች ሊሰጡት የማይችለውን
ማነሳሳት ይሰጣቸዋል በማለት (Heaton፣ 1988) ይገልፃሉ፡፡

እንዲሁም የመፃፍ ክሂልን ለማዳባር የሚከተሉት ችሎታዎች መዳበር አለባቸው፡፡ እነዚህም


የሆሄያትን ቅራፅና አይነት በአግባቡ ለይቶ ከመረዳት በተጨማሪም የስርዓተነ ጥቦችን
አገልግሎት መገንዘብ፣ የቃላትን አጠቃቀም መልመድ፣ የቋንቋ ህግ የወሰነውን ተገቢ የአረፍተ
ነገር መዋቅር መከተልና ትክክለኛ የአፃፃፍ ዘውግ ለትክክለኛ ጉዳይ ማዋል ማለትም ተፈላጊ

42
መልዕክት የያዘውን አረፍተ ነገር በአግባቡ ማዋቀር እና እንደ አስፈላጊነቱ ዋናውን መልዕክት
እንዲያብራሩ የሚያስፈልጉ አረፍተ ነገሮች በጥንቃቄ መቀመርና የሃሳብ ፍሰት ያለው ፅሁፍ
መፃፍ እንደሆኑ (ጌታቸው፣ 2005) ያስረዳሉ፡፡ የመፃፍ ክሂል በባህሪው ክሂለ ብዙ ነው፡፡
የሃሳብ አደረጃጀት፣ የአንቀፅ አመሰራረት፣ የዓረፍተ ነገር አወቃቀር፣ የቀላት አመራረጥና
አጠቃቀም ለመፃፍ ክሂል ትምህርት ከሚያስፈልጉ ችሎታዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ፡፡
እንዲሁም ክሂሉ በጅምር የቀሩ ዓረፍተ ነገሮችን መጨረስ፣ የአንቀፅ ቅደም ተከተላቸው የተዛቡ
ድርሰቶችን ማስተካከል፣ የአረፍተ ነገር ቅደም ተከተላቸው የተዛቡ አንቀፆችን ማስተካከል፣
ሃሳብ ማመንጨት፣ ሃሳብ ማስፋፈት፣ ሃሳብ መምረጥ ወዘተ. ችሎታዎች እንዳሉትም
(ማረው፣ 2003) ያስረዳሉ፡፡ በዚህ መሰረት በሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሀፍ
ስር የቀረቡ ንዑሳን ይዘቶች ተደራጅተው ተመድበዋል፡፡

2.7.5. የሰዋስው ችሎታ ንዑሳን ይዘቶች

ባየ (1987) የአማርኛ ሰዋስው ሲባል የአማርኛን ድምፆች አይነት አፈጣጠርና አቀነጃጀት


እንዲሁም የሀረጋቱን አይነት እና የአወቃቀር ስርዓት ደረጃ በደረጃ የሚያሳይ የእውቀት ዘርፍ
ማለት ነው። ድምፅ ከድምፅ ጋር ተቀናጅቶ ቃልን፣ ቃል ከቃል ጋር ተጣምሮ ሐረግን፣
እንዲሁም ሀረግ ከሀረግ ጋር ተዋቅሮ አረፍተ ነገርን ደረጃ በደረጃ የሚፈጠርበትን ስርዓት
የሚመለከ ትጥበብ ነው።

የሰዋስው ችሎታ የአንድን ቋንቋ ታህታይ መዋቅረ መረዳት እንደሆነ (ባየ፣ 1987 እና
ጌታሁን፣ 1989) ያስረዳሉ፡፡ ተግባቦታዊ የቋንቋ ችሎታ ተማሪዎች የቋንቋን ቅርፅ፣ ፍችና
አገባብ አጣምሮ የመረዳት ችሎታ እንዲዳብር ያስችላል፡፡ የቋንቋውን ስርአት፣ ፍቺና
አገልግሎት አቀናጅቶ ለማስተማር የሚመቹ ስለሆነ ለተማሪዎች የተለያዩ መዋቅሮችን
እንዴት፣ የትና መቼ መጠቀም እንዳለባቸውና በዲስኩር ጊዜ የትኛው የሰዋስው መዋቅር
መቅደምና መከተል እንዳለበት ስለሚያሳውቁ ነው (Harmer፣ 1991 እና Richards እና
Rodgers 2001):: በመሆኑም የቃላትን ፍች፣ ቅርፅና አገባብ መረዳት፣ የቃላትን አገልግሎ
መረዳት፣ የቃል ክፍሎችን መለየት፣ ለቃላት ተቃራኒ እና ተመሳሳይ ፍች መስጠት፣ የሃረግ

43
አይነቶችን መረዳት፣ የዲስኩር ቃላትና ሃረጋትን መረዳት፣ የዐረፍተ ነገር አይነቶችን መረዳት፣
የአንቀፅ ጊዜያትን መለየት፣ ቃላት መመስረት፣ ድምፆችን መለየት፣ የድምጾችን መካነና ባህሪያ
ፍጥረት መረዳት፣ የቅጥያ ምዕላችን ተግባር መረዳት፣ ከሰዋስዋዊ ስህተት የፀዳ አረፍተ ነገር
መመስረት ወዘተ. የሰዋስው ንዑሳን ችሎታዎች ናቸው፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የቃላት ትምህርት ዋና ዋና ይዘቶች የሚባሉት የቃላትን ትርጉም ወይም


ፍቺ፣ አጠቃቀም፣ አገባብ እናቅርፅ መረዳት ሲሆኑ ቃላትን ከበዙ አቅጣጫ ለመረዳት እንዲቻል
አውዳዊ ትርጉም መስጠት፣ የቃላትን አጠቃቀም መራደት መቻል ማለትም የቃላት ትርጉም
በአጠቃቀም ልዩነት ሊሰፋ ስለሚችል ይህንን መገንዘብ መችል፣ በሰዋስዋዊ አገባባቸው የተነሳ
የትርጉም ለውጥ ያሳያሉ፣ ማለትም የተወሰኑ ቃላት ለተወሰኑ ሰዋስዋዊ ዓረፍተ ነገሮች ተገዥ
ይሆናሉ ማለትም የቃላቱን ሙያ መገንዘብ መቻል እና ቃላት ቅርፅ ስላላቸው ቅርፃቸው
ተለዋዋጭ ነው፤ በዚህም ሰዋስዋዊ ባህሪያው ወይም ተግባራቸው ይለዋወጠል፡፡ ስለዚህ
ተማሪዎች የቃላት ምስረታ እና የተለያ ሰዋስዋዊ አውዶችን ማወቅ እንደሚኖርባቸው (ማረው፣
2003) ያስረዳሉ፡፡

ስለሆነም የቋንቋ ፈተና ተገቢውን ሰዋስዋዊ ቅርፅ እና የመዋቅር አጠቃቀም ችሎታ መለካት
ነው፡፡ የሰዋስው ፈተና አለማ የተማሪዎችን የሰዋስው እውቀት መመዘን ነው፡፡ ትኩረቱም
በተነደፈው የቋንቋ ትምህርት ዓለማ መሰረት የሰዋስው ይዘት ያላቸው ጥያቄዎችን በመጠቀም
ተማሪዎች የተማሩትን የቋንቋ ስርዓት ምን ያህል እንደተገነዘቡ፣ የሰዋስው እውቀት
ቸሎታቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ መለካት እንደሆነ (Heaton፣ 1988) ያስረዳሉ፡፡

2.8. የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት

ይህ ንዑስ ክፍል ውስጥ የሚጠናው ጥናት ከጥናቱ ጋር ተዛማጅ ከሆኑ ቀደምት ጥናቶች ጋር
ሲነፃፀር በምን እንደሚመሳሰልና እንደሚለያይ በዝርዝር የሚዳሰስበት ክፍል በመሆኑጥናቱ

44
ከቀደምት ጥናቶች ጋር ያለውን አንድነትና ልዩነት እንደሚከተለው ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡
ከዚህ ጥናት ጋር ተዛማጅ ከሆኑ የቀደምት ጥናቶች ውስጥ በአማርኛ ቋንቋ ሲሳይ (2007)፣
አንችነሽ (2009) እና ጌታቸው (2011) ያጠኗቸው ጥናቶች እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ደግሞ
Asmare (2006) እና Mekonnen (2017) ያጠኗቸው ጥናቶች ይገኙበታል፡፡ ስለሆነም እነዚህ
ጥናቶች ከዚህ ጥናት ጋር በምን እንደሚመሳሰሉና እንደሚለያዩ እንደሚከተለው ለማሳየት
ተሞክሯል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ሲሳይ (2007) ያጠናውን ጥናት ስንመለክት የሲሳይ ጥናት ያተኮረው
ከ2001-2006 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ ፪ኛ ደረጃ ትምህርት
ማጠናቀቂያ በተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘትና
አቀራረብ ትንተና ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህኛው ጥናት ግን ከ2009-2011 ዓ.ም በልደታ ክፍለ
ከተማ ስር ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት በክፍለ
ከተማው ስር ላሉ ተማሪዎች ታስበው የተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ጥያቄዎች
ከችሎታ ፈተና መለኪያ አንፃር ምን እንደሚመስሉና ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸውን ዝምድና የሚፈትሽ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የሲሳይ
ጥናት ዋና አላማው 2001-2006 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ
ትምህርት ማጠናቀቂያ በተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው
ጥያቄዎች ይዘትና አቀራረብ መተንተን ሲሆን የዚህ ጥናት ዋና አላማ ግን የመዴል ፈተና
ጥያቄዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸውን ትስስር የሚዳስስ ሆኖ ለቋንቋ ትምህርት
ይዘቶች የተሰጠውን ትኩረትና ጥያቄዎቹ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ
የሚተነተንበት ነው፡፡

ሌላው ደግሞ የሲሳይ ጥናት ከ2001-2006 ዓ.ም በሃገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት ለአጠቃላይ
2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ በተዘጋጁ የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች ውስጥ የተካተቱ
የሰዋስው ጥያቄዎች ይዘቶች ምን ምን እንደሆኑ፣ በመማሪያ መፅሃፍቱ ውስጥ የተካተቱ
የሰውስው ትምህርት ይዘቶች አንፃር የተካተቱ እና ያልተካተቱ ይዘቶችን፣ የሰውስው ጥያቄ
ይዘቶችን ከሰዋስው መርህ አኳያ ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለይቶ ያረጋገጠ ሲሆን ይህ ጥናት ግን

45
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተናዎች ይዘት የመማሪያ መፅሃፉን
ይዘትየሚወክሉ መሆናቸውን፣ በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ የተካተቱ ይዘቶች ከተዘጋጀው ፈተና
ይዘትጋራ ያላቸውን ዝምድና የሚፈትሽ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የሲሳይ ጥናት የተሰበሰቡት
መረጃዎች በአይነታዊ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የተነተኑ ሲሆን ይህ ጥናት ግን መጠናዊ
በአይነታዊ የተደገፈ ቀይጥ የመረጃ መተንተኛ መሳሪያን ተጠቅሟል፡፡

በሲሳይ ጥናት መረጃ ሰጪዎችን በዓላማ ተኮር የንሞና አመራረጥ ስልት የተመረጡ ሲሆን
በዚህ ጥናት ግን የተጠናው ክፍለ ከተማ በአመቺ ወይም በግኝት የንሞና ዘዴ፣ የክፍል
ደረጃውን በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት እና የሞዴል ፈተናዎችን ደግሞ በጠቅላይ
የንሞና አመራረጥ ስልት ተመርጠዋል፡፡ የሚመሳሰሉበትን ባህሪ ስንመለከት ደግሞ የሲሳይ
ጥናት ለጥናቱ አስፈላጊ የሆነን መረጃ ለመሰብሰብ ከመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች ውስጥ ሰነድ
ፍተሻን የተጠቀመ ሲሆን ይህ ጥናትም የተጠቀመው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የሰነድ
ፍተሻን ነው፡፡

በሁለተኛ ደረጃ አንችነሽ (2009) ያጠናችውን ጥናት ስንመለክት የአንችነሽ ጥናት ዋና አላማው
የ፪ኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናው በመምህራንና በተማሪዎች አመለካከት ላይ ያለው
ተፅእኖ ምን እንደሚመስል መዳሰስ ሲሆን የዚህ ጥናት ዋና አላማ ግን በአዲስ አበባ ልደታ
ክፍለ ከተማ የሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸውን ትስስር የሚዳስስ
ሆኖ ለቋንቋ ትምህርት ይዘቶች የተሰጠውን ትኩረት፣ ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው
ዝምድና እና ጥያቄዎቹ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ የተተነተነበት
ነው፡፡

ሌላው ደግሞ የአንችነሽ ጥናት የ፪ኛ ደረጃ ብሄራዊ ፈተናዉ መምህራን በክፍል ውስጥ
በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘት አመለካከት ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን ይመስላል? ተማሪዎች
በክፍል ውስጥ በሚማሩት የትምህርት ይዘት አመለካከት ላይ ያለው ተጽዕኖ ምንድን ነው?
በመምህራን የማስተማሪያ ስነዘዴዎች አመለካከት ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን ይመስላል?

46
በመማሪያ መጽሃፉ የቀረቡ የትምህርት ይዘቶችና በብሄራዊ ፈተናዉ የቀረቡ ይዘቶች
ተመጣጥኖ ምን ይመስላል? የሚሉትን መሪ ጥያቄዎች የመለሰ ሲሆን ይህ ጥናት ግን
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተናዎች ይዘት የመማሪያ መፅሃፉን ይዘት
የሚወክሉ መሆናቸውን፣ በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ የተካተቱ ይዘቶች ከተዘጋጀው ፈተና
ይዘት ጋራ ያላቸውን ዝምድና የሚፈትሽ ይሆናል፡፡ እንዲሁም የአንችነሽ ጥናት የተሰበሰቡት
መረጃዎች በአይነታዊና መጠናዊ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የተነተኑ ሲሆን ይህ ጥናትም
መጠናዊ በአይነታዊ የተደገፈ ቅይጥ የመረጃ መተንተኛ መሳሪያን በመጠቀሙ ያመሳስላቸዋል፡፡

በአንችነሽ ጥናት ትምህርት ቤቱ እና ተጠኝ ተማሪዎች በተራ የእጣ ንሞና ስልት፣ መረጃ ሰጭ
መምህራኑ በጠቅላይ ንሞና ስልት እና የጥናቱ ቦታ በዓላማ ተኮር የንሞና አመራረጥ ስልት
የተመረጡ ሲሆን በዚህ ጥናት ግን የተጠናው ክፍለ ከተማ በአመቺ ወይም በግኝት የንሞና
ዘዴ፣ የክፍል ደረጃውን በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት እና የሞዴል ፈተናዎችን
ደግሞ በጠቅላይ የንሞና አመራረጥ ስልት ተመርጠዋል፡፡ የአንችነሽ ጥናት ለጥናቱ አስፈላጊ
የሆነን መረጃ ለመሰብሰብ ከመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች ውስጥ ዝግ የፅሁፍ መጠይቅ፣
ቃለመጠይቅና የሰነድ ፍተሻን የተጠቀመ ሲሆን ይህ ጥናት ግን የተጠቀመው የመረጃ
መሰብሰቢያ መሳሪያ የሰነድ ፍተሻን ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም የተጠቀሙት ንድፍ ገላጭ ነው፡፡

በሶስተኛ ደረጃ ጌታቸው (2011) ያጠናውን ጥናት ስንመለክት የጌታቸው ጥናት ዋና አላማው
በመምህራን የሚዘጋጁ የክፍል ውስጥ ፈተናዎች የይዘትና የአቀራረብ ስልት ተገቢነት እና
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የፈተና አዘገጃጀት ሂደት ፍተሻ ሲሆን የዚህ ጥናት ዋና አላማ ግን
በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር
ያላቸውን ትስስር የሚዳስስ ሆኖ ለቋንቋ ትምህርት ይዘቶች የተሰጠውን ትኩረትና ጥያቄዎቹ
ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ የተተነተነበት ነው፡፡

ሌላው ደግሞ የጌታቸው ጥናት የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ባዘጋጇቸው የክፍል
ውስጥ ፈተናዎች የተካተቱ ይዘቶች ምን ምን ናቸው? የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ

47
መምህራን ባዘጋጇቸው የክፍል ውስጥ ፈተናዎች የተካተቱ ይዘቶች በመማሪያ መፅሀፉ ውስጥ
ከቀረቡ ይዘቶች ጋር ዝምድና አላቸውን? የሰባተኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን
ባዘጋጇቸው የክፍል ውስጥ ፈተናዎች የተካተቱ ይዘቶች የቀረቡበት ስልት በመማሪያ መፅሀፉ
ውስጥ ከተዘጋጁ መልመጃዎች ጋር ዝምድና አላቸውን? የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የፈተና
አዘገጃጀት ሂደት ምን ይመስላል? የሚሉትን መሪ ጥያቄዎች የመለሰ ሲሆን ይህ ጥናት ግን
የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተናዎች ይዘት የመማሪያ መፅሃፉን ይዘት
የሚወክሉ መሆናቸውን፣ በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ የተካተቱ ይዘቶች ከተዘጋጀው ፈተና
ይዘት ጋራ ያላቸውን ዝምድና የሚፈትሽ ይሆናል፡፡ እንዲሁም በጌታቸው ጥናት የተሰበሰቡት
መረጃዎች በአይነታዊና መጠናዊ የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የተነተኑ ሲሆን ይህ ጥናትም
መጠናዊ በአይነታዊ የተደገፈ ቀይጥ የመረጃ መተንተኛ ስልትን በመጠቀሙ ያመሳስላቸዋል፡፡

በጌታቸው ጥናት ተጠኝ መምህራኑ በጠቅላይ ንሞና አመራረጥ ስልት የተመረጡ ሲሆን በዚህ
ጥናት ግን የተጠናው ክፍለ ከተማ በአመቺ ወይም በግኝት የንሞና ዘዴ፣ የክፍል ደረጃውን
በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት እና የሞዴል ፈተናዎችን ደግሞ በጠቅላይ የንሞና
አመራረጥ ስልት ተመርጠዋል፡፡ የጌታቸው ጥናት ለጥናቱ አስፈላጊ የሆነን መረጃ ለመሰብሰብ
ከመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች ውስጥ ቃለ መጠይቅና የሰነድ ፍተሻን የተጠቀመ ሲሆን ይህ
ጥናት ግን የተጠቀመው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ የሰነድ ፍተሻን ብቻ ነው፡፡ ሁለቱም
የተጠቀሙት ንድፍ ገላጭ ነው፡፡

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ Mekonnen (2017) Assessing of the content validity of EGSEC
English Examinations በሚል ርዕስ ጥናት ያካሄዱ ሲሆን አጥኝው ትኩረት ያደረጉት በሀገር
አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት አማካኝነት ለአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ
በተዘጋጁ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፈተናዎች ላይ ሆኖ በፈተናዎች የይዘት ተገቢነት እና የቀራረብ
ስልት ላይ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ግን ትኩረት የተደረገው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጀው
የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ሲሆን ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያለው ዝምድና ደግሞ
ተፈትሾበታል፡፡

48
በአምስተኛ ደረጃ Asmare (2006) ያጠኑት ጥናት ከዚህ ጥናት ጋር በምን እንደሚመሳሰልና
እንደሚለያይ እንመለከታልን፡፡ በመጀመሪያ ልዩነታቸውን ስንመለክት የAsmare ጥናት
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጠና ሲሆን ትኩረቱ ለኮሌጅ በሚዘጋጅ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ላይ
ነው፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ በአዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተዘጋጀው የጥያቄ ይዘት እና በተሰጠው
ትምህርት ይዘት መካከል ያለው ዝምድናም ዝቅተኛ በመሆኑ የፈተናዎቹ ይዘት ደካማ እንደሆነ
ያረጋገጠ ሲሆን ይህ ጥናት ግን በአማርኛ ቋንቋ የተጠና ሲሆን ከ2009-2011 ዓ.ም ለአስረኛ
ክፍል ተማሪዎች የተዘጋጁ የሞዴል ፈተናዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን
እንደሚመስሉ፣ የተካተቱ ይዘቶች ምን ምን እንደሆኑ እና ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው
ዝምድና ምን እንደሚመስል የተፈተሸበት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለአስረኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀው የሞዴል ፈተና ይዘት ከቋንቋ ትምህርት ይዘቶች
እና ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እነደሚመስሉ እና አጠቃላይ የትምህርቱን ይዘት
የሚወክሉ መሆኑን አለመሆናቸውም ተዳሶበታል፡፡

49
ምዕራፍ ሶስት፤ የአጠናን ዘዴ

3.1. የምርምሩ ንድፍ

ቀደም ሲል በምዕራፍ አንድ ላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው


በልደታ ክፍለ ከታማ ከ2009 ዓ.ም እስከ2011 ዓ.ም በተዘጋጁ የሞዴል ፈተናዎች ላይ ነው፡፡
ፈተናዎቹ ከታላሚ ክፍሎች መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸው የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ደግሞ
የጥናቱ አብይ ዓላማ ሲሆን አላማውን ከግብ ለማድረስም ጥቅም ላይ የዋለው ገላጭ ንድፍ
ነው፡፡

3.2. የመረጃ ምንጮች

ይህ ጥናት በክፍለ ከተማ ደረጃ ከየትምህርት ቤቱ በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁ


ሞዴል ፈተናዎች ከሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፎች ጋር ያላቸውን የይዘት
ተገቢነት የሚያጠና ከመሆኑ አንፃር ለጥናቱ በመረጃ ምንጭነት የተገለገለው ሰነዶችን ነው፡፡
በሰነድነት ጥቅም ላይ የዋሉት የመረጃ ምንጮችም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር በ2004 ዓ.ም የታተሙት የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መፅሃፎችና እና ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ካሉ
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች ናቸው፡፡

አጥኚው ለጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በተሟላ ሁኔታ ማግኘት እችላለሁ ብሎ


ያሰበበትና ያለውን የጊዜ እና የጉልበት አቅም ከግምት በማስገባት ከአንድ ክፍለ ከተማ የሶስት
ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በላይ ለማጥናት የሚቸገር ሆኖ በማግኘቱ እንዲሁም

50
የሚሰራውም በዚሁ ክፍለ ከተማ ከመሆኑ አንፃር የልደታ ክፍለ ከተማን በወሳኝ የናሞና
አመራረጥ ዘዴ ስር በሚካተተው በአመቺ የናሞና አመራረጥ ዘዴ አማካኝነት ሊመርጥ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል አሁን ባለው የሀገራችን ኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ሞዴል ፈተናዎች
የሚሰጡት ብሄራዊ ፈተና ለሚወስዱ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች እና ክልላዊ ፈተና ለሚወስዱ
የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ብቻ ነው፡፡ ለስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ታስቦ የሚዘጋጀው
የሞዴል ፈተና የክልላዊ ተማሪዎችን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የሚዘጋጅ ሲሆን
ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የሚዘጋጀው የሞዴል ፈተና ደግሞ ከክፍል ደረጃውም አንፃር የሀገር
አቀፍ ተማሪዎችን የቋንቋ ትምህርት አቀባበል ታሳቢ በማድረግ የሚሰናዳ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር
አጥኚው ትክክለኛ መረጃ ማግኘት የምችለው የአስረኛ ክፍል ሞዴል ፈተናን ብፈትሽ ነው ብሎ
ስላሰበ በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት አማካኝነት ተተኳሪ ከሆነው ክፍለ ከተማ
የአስረኛ ክፍል ሞዴል ፈተናን መርጧል፡፡ እንዲሁም የዚህ ጥናት ትኩረት በክፍለ ከተማው
ስር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁ የአስረኛ ክፍል
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች በመሆናቸው ለጥናቱ በተመረጠው የልደታ ክፍለ
ከተማ ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ለክፍል ደረጃው ተዘጋጅተው የሚገኙ የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች በሙሉ በጠቅላይ የናሙና አመራረጥ ስልት አማካኝነት
የተወሰዱ በመሆኑ ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም ድረስ ያሉት የሶስት ተከታታይ ዓመታት ሞዴል
ፈተናዎች ተካተዋል፡፡ የነዚህ ሶስት ተከታታይ ዓመታት የሞዴል ፈተናዎች በጥናቱ
የተመረጡበት ዋና ምክንያትም የቅርብ ጊዜ በመሆናቸውና ሰነዶችን በቀላሉ ለማግኜት
ስለሚቻል ሲሆን አጥኚው ከጥያቄዎቹ ብዛት አንፃር ከነዚህ በፊት ያሉ ሞዴል ፈተናዎችን
ለማካተት ስለሚቸገር ነው፡፡

3.3. የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ

የአንድ ጥናት ትክክለኛነት የሚወሰነው ትክክለኛ የሆኑ የመረጃ ምንጮችን በመለየት ብቻ


ሳይሆን ከተለዩት የመረጃ ምንጮች በተገቢው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ወይም መሳሪያ

51
አማካኝነት መረጃዎቹን መሰብሰብ ሲቻል ጭምር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር የዚህን ጥናት ዓላማ
በትክክል ከግብ ያደርሳል ተብሎ በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት የተመረጠው የሰነድ ፍተሻ
ነው፡፡ የሰነድ ፍተሻ አንድን ጥናት በማካሔድ ሂደት ለመረጃ መሰብሰቢያነት ከሚያገለግሉ
በርካታ ዘዴዎች መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይህ ጥናትም ቀደም ሲል በመረጃ ምንጭነት
ከተጠቀሱት ከ2009 እስከ 2011 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት
ከየትምህርት ቤቱ በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት የተዘጋጁትን ሞዴል ፈተናዎች
ያካተቷቸውን ይዘቶች፣ መሰረት ካደረጓቸው መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸውን የይዘት
ዝምድና እና ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ የፈተሸ በመሆኑ ከሞዴል
ፈተናዎቹ እና ከመማሪያ መፃህፍቱ መረጃዎችን ለማግኘት የሰነድ ፍተሻን በመረጃ መሰብሰቢያ
መሳሪያነት ጥቀም ላይ አውሏል፡፡ በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት ከሞዴል ፈተናዎቹ እና ከመማሪያ
መፃህፍቱ የተገኙ መረጃዎችም የዚህ ጥናት ዋነኛ ግብዓቶች በመሆን አገልግለዋል፡፡

3.4. የመረጃ አተናተን ዘዴ

ከተለዩት የመረጃ ምንጮች በተመረጠው የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ አማካኝነት በጥናቱ ሂደት
የተሰበሰቡት መረጃዎች መጠናዊ በአይነታዊ በተደገፈ ቅይጥ የመተንተኛ ስልት አማካኝነት
ተተንትነዋል፡፡ መማሪያ መፃህፍቱ ለሞዴል ፈተናዎቹ መሰረት ከመሆናቸው አንፃር
በመጀመሪያ በመማሪያ መፃህፍቱ የተካተቱት ዝርዝር ይዘቶች በድግግሞሽ መጠናቸው
በቁጥርና በመቶኛ ተሰልተው ቀርበዋል፡፡ በመቀጠልም ለማዛመድ ይቀል ዘንድ ከዕያንዳንዱ
ዝርዝር ይዘት ጎን ለጎን በሞዴል ፈተናዎቹ ውስጥ የቀረቡ ጥያቄዎች በየዓመተ ምህረታቸው
በተመሳሳይ በቁጥርና በመቶኛ ተሰልተው ከቀረቡ በኋላ ተተንትነዋል፡፡

በተጠቀሱት ዓመታት የሞዴል ፈተናዎች ውስጥ በእያንዳንዱ የቋንቋ ትምህርት ሂደት የቀረቡ
ጥያቄዎችን እና በመማሪያ መፃህፍቱ የተካተቱ ይዘቶችን መጠን በአሃዝ ለመግለፅ መጠናዊ
የምርምር ዘዴ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በእያንዳንዱ ዓመት ሞዴል ፈተና ምን ዓይነት ይዘቶች
እንደተካተቱና የተካተቱት ይዘቶች ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር ያላቸውን ዝምድና

52
በመለየት መማሪያ መፃህፍቱ ላይ መመስረት አለመመስረታቸውን፣ እንዲሁም በመማሪያ
መፃህፍቱ ውስጥ የተካተቱት ይዘቶች በሞዴል ፈተናዎቹ ውክልና ማግኘትና አለማግኘታቸውን
ለአንባብያን ለመግለፅ ደግሞ ዓይነታዊ የምርምር ዘዴ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በመቀጠልም
በመማሪያ መፃህፍቱና በሞዴል ፈተናዎቸጁ ጥያቄዎች ቁጥር ድግግሞሽ መካከል ያለውን
የተዛምዶ መጠን ለማወቅ ፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዝምዶ መለኪያ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
ይህ መተንተኛ መሳሪያ የሚያገለግለው በሁለት ተለዋዋጮች መካከል ያለን የግንኙነት አቅጣጫ
እና መጠን ለማመልከት ሲሆን፣ ሁለቱ ተለዋዋጮች መጠናዊ፣ በመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴው
አማካኝነት የሚገኘው የልኬታ አይነት ደግሞ እኩል ወይም ተካፋይ ልኬታ መሆን
ይኖርበታል፡፡

የተዛምዶ አቅጣጫ ሲባል በሁለቱ ተዛማጅ ተለዋዋጮች መካከል ያለው የግንኙነት መልክ
ሲሆን ከዚህ መስፈርት አንፃር ተለዋዋጮች ሶስት ዓይንት የግንኙነት አቅጣጫዎች ሊኖሯቸው
ይችላል፡፡ እነዚህም፡- አዎንታዊ ተዛምዶ፣ ተዛምዶ አልቦ እና አሉታዊ ተዛምዶ ናቸው፡፡
አዎንታዊ ተዛምዶ የሚባለው የአንደኛው ተለዋዋጭ መጠን ሲጨምር የሌላኛውም ተለዋዋጭ
መጠን እየጨመረ የሚሄድ ሲቀንስ ደግሞ ሌላኛውም በተመሳሳይ ሁኔታ እየቀነሰ የሚሄድ
ነው፡፡ በሌላ በኩል አሉታዊ ተዛምዶ የሚባለው ሁለቱ ተዛማጅ ተለዋዋጮች በተመሳሳይ
አቅጣጫ አብረው ከመጨመር ወይም ከመቀነስ ይልቅ አንደኛው ሲጨምር ሌላኛው ቀንሶ
የሚስተዋልበት ግንኙነት ነው፡፡ ሶስተኛው ዓይነት ግንኙነት ተዛምዶ አልባ የሚባለው ሲሆን
ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው በሁለቱ ተለዋዋጮች መካከል ያለው ተዛምዶ ዜሮ ወይም ወደ
ዜሮ የሚጠጋበት ነው፡፡ በዚህ የተዛምዶ አይንት የአንደኛው ተለዋዋጭ መጠን መቀነስ
ከሌላኛው ተለዋዋጭ መጠን መጨመር ወይም መቀነስ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡

ሌላው በሁለት ተለዋዋጮች መካከል ያለን ተዛምዶ ስንመለከት የምናገኘው ነገር የተዛምዶ
መጠን ነው፡፡ የተዛምዶው መጠን በአዎንታዊም ሆነ በአሉታዊ አቅጣጫ ከዜሮ እየራቀ ሲሄድ
ጠንካራ ሊሰኝ የሚችል ሲሆን በሁለት ተለዋዋጮች መካከል የሚገኝ የተዛምዶ መጠን ከ +1
እስከ−1 ድረስ ነው፡፡ ስለዚህም የሚገኙት የተዛምዶ ውጤቶች ከ 0 ወደ +1 እየቀረቡ ሲመጡ
የተዛምዶ መጠኑ ጠንካራ አቅጣጫው ደግሞ አዎንታዊ ሲሆን ከ 0 ወደ −1 እየቀረቡ ሲመጡ

53
ደግሞ የተዛምዶ መጠኑ ጠንካራ አቅጣጫው ደግሞ አሉታዊ ይሆናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
የተዛምዶ መጠን ፈርጆች የሚከተሉት ናቸው፡፡ የተዛምዶ መጠን
ትርጉም 0.00 - 0.19 ከሆነ ዝምድና የለሽ ወይም በጣም ዝቅተኛ ተዛምዶ፣ 0.20 - 0.39
ዝቅተኛ ተዛምዶ፣ 0.40 - 0.59 መካከለኛ ተዛምዶ፣ 0.60 - 0.79 ከፍተኛ ተዛምዶ፣ 0.80 -
1.00 በጣም ከፍተኛ ተዛምዶ ይሆናል፡፡ በመጨረሻም አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ስልትን
በመጠቀም የሞዴል ፈተናዎቹ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ በዝርዝርና
በጥልቀት ተፈትሸዋል፡፡

54
ምዕራፍ አራት፣ የመረጃ ትንተናና የውጤት ማብራሪያ

ቀደም ሲል በምዕራፍ አንድ ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የዚህ ጥናት ዐብይ አላማ በአዲስ
አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ከ2009-2011 ዓ.ም
ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከሁለተኛ
ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸውን የይዘት ተገቢነት መፈተሽ ነው፡፡
የህንን ዓላማ ከግብ ለማድረስም የሰነድ ፍተሻን በመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያነት በመጠቀም
መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡

የዚህ ምዕራፍ ጉዳይ ደግሞ የጥናቱን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ጥቅም ላይ በዋለው የመረጃ
መሰብሰቢያ መሳሪያ አማካኝነት የተሰበሰቡትን መረጃዎች አደራጅቶ በማቅረብ መተንተንና
የውጤት ማብራሪያ መስጠት ነው፡፡ በመሆኑም በሰነድ ፍተሻው አማካኝነት ከመማሪያ
መፃህፍቱ እና ከሞዴል ፈተናዎቹ የተገኙት መረጃዎች ቀርበውና ተተንትነው የውጤት
ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

4.1. የመረጃ ትንተና

ይህ ጥናት በመረጃ ማግኘት ከተገለገለባቸው ሰነዶች ውስጥ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ


ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ትምህርት ሚኒስቴር በ2004 ዓ.ም የታተሙት የዘጠነኛ እና የአስረኛ
ክፍል መማሪያ መፃህፍት በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ መፃህፍቱ በዚህ ጥናት
የጊዜ ክልል ውስጥ ጥቅም ላይ ያሉና ለሞዴል ፈተናዎቹ ዝግጅትም መሰረት የሆኑ ሲሆን፣
የዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ቋንቋና ህብረተሰብ፣ ስነቃል፣ ቤተመጻህፍትና
ስነፅሁፍ፣ ልቦለድ፣ ስነ ግጥም፣ ተውኔት፣ የአካባቢ ገለፃ፣ መገናኛ ብዙሃን፣ ምርጥ ንግግር
እና ክርክር የተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮች ያሉት ሆኗ በአስር ምዕራፎች የተከፋፈሉ 185 ገፆች አሉት፡፡
የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ደግሞ ቋንቋና ህብረተሰብ፣ ባህላዊ ጋብቻ፣

55
ልቦለድ፣ ማህበረሰብና ጤና፣ ቀና አመለካከት፣ ግጥም፣ የአረጋውያን ሚና፣ ሴቶች በባህል
ውስጥ፣ ሱስ እና ስራና ምርት የሚሰኙ ርዕሰ ጉዳዮች ያሉት ሆኖ በአስር ምዕራፎች
የተከፋፈሉ 147 ገፆች አሉት፡፡

በመማሪያ መፃህፍቱ መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት አጠቃላይ


ይዘቶች የተማሪዎችን የማዳመጥ፣ የመናገር፣ የማንበብና የመፃፍ ክሂላትን ማጎልበትና
የስነፅሁፍና የስነ ልሳን እውቀትን ማዳብር በመሆኑ እነዚህ ይዘቶች በመማሪያ መፃህፍቱ ላይ
በግልፅ ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ ያሉት ምንባቦች፣
ማብራሪያዎችና መልመጃዎች በአራቱ ክሂላትና በሁለቱ የእውቀት ዘርፎች መሰረትነት
ተደራጅተው የቀረቡ ሲሆን ምንባቦቹ እና ማብራሪያዎቹ ግልፅና ሳቢ፣ መልመጃዎቹ ደግሞ
አሳታፊ እንዲሆኑ ጥረት ተደርጓል፡፡ በየምዕራፉ ማብቂያ ላይም የየምዕራፉ አንኳር አንኳር
ነጥቦች በማጠቃለያ መልክ ከመቅረባቸውም በላይ ተማሪዎች የየምዕራፉን ትምህርት ምን
ያህል እንደተረዱ የሚያመሳክሩባቸው ነጥቦች ተዘጋጅተዋል፡፡

በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ የተካተቱት ብዙዎቹ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች የእውቀትም


ይሁኑ የክሂል ዘርፎች ቅንጅትን የሚጠይቁ ተግባራትን የያዙ ከመሆናቸው አንፃር አንድን
የዕውቀት ወይም የክሂል ዘርፍ ብቻ ነጥለው ለማስተማር የቀረቡ ናቸው ብሎ መደምደም
ያስቸግራል፡፡ ለአብነት ያክልም በዘጠነኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ምንባብ
በሚል አምድ ስር ከገፅ 2-5 የቋንቋ ምንነትን በተመለከተ የቀረበው ምንባብ፣ ከገፅ 16-18
ስነቃልን በተመለከተ የቀረበው ምንባብ፣ ከገፅ 34-36 ስነፅሁፍን በተመለከተ የቀረበው ምንባብ
እንዲሁም ስነፅሁፍ በሚል አምድ ስር ገፅ 28 እና 29 ላይ የቀረቡት በሰርጉ ማግስትና የክፋት
ተጋብዖት ምንባቦች፣ በተጨማሪም ፅህፈት በሚል አምድ ስር ገፅ 47 ላይ ተራኪ ድርሰት
ተብሎ የቀረበው ፈሪው ወታደር ምንባቦች ሰዋስውና አንብቦ መረዳትን፣ ስነፅሁፍንና አንብቦ
መረዳትን፣ እንዲሁም መፃፍንና አንብቦ መረዳትን በጥምረት ለማስተማር የሚያስችሉ ናቸው፡፡
በአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ላይም እንዲሁ ምንባብ በሚል አምድ ስር
ከገፅ 2-4 የቋንቋ አጀማመር በሚል ርዕስ የቀረበው ምንባብ፣ ከገፅ 34-35 ልቦለድን በተመለከተ

56
የቀረበው ምንባብ እና ከገፅ 78-80 ግጥምን በተመለከተ የቀረቡት ምንባቦች ሰዋስውንና አንብቦ
መረዳትን እንዲሁም ስነፅሁፍንና አንብቦ መረዳትን በጥምረት ለማስተማር የሚያስችሉ ናቸው፡፡

ከመማሪያ መፃህፍቱ ሌላ በሰነድነት ያገለገሉት የመረጃ ምንጮች ደግሞ ከ2009-2011 ዓ.ም


ባሉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት
ፅህፈት ቤት አማካኝነት ተዘጋጅተው የቀረቡት የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት
ሞዴል ፈተናዎች ናቸው፡፡ በ2009 ዓ.ም ሞዴል ፈተና ውስጥ 90 ጥያቄዎች እንዲሁም
በ2010 እና በ2011 ዓ.ም በእያንዳንዱ ዓመት 80፣ 80 ጥያቄዎች የሚገኙ ሲሆን፣ እነዚህ
ጥያቄዎችም እንደይዘታቸው በዕውቀት ዘርፎች ረገድ በስነልሳንና በስነ ፅሁፍ፣ በክሂል ዘርፎች
ረገድ ደግሞ በማድመጥ፣ በመናገር፣ በመፃፍና በማንበብ ክሂል መሰረትነት ቀርበዋል፡፡ ልክ
በመማሪያ መፅሃፉ ውስጥ አንድን የዕውቀት ወይም የክሂል ዘርፍ ብቻ በተናጠል ለማስተማር
የቀረቡ ናቸው ለማለት የሚያስቸግሩ ይዘቶች እንዳሉ ሁሉ በሞዴል ፈተናዎቹም አንድን ዘርፍ
ብቻ ለመፈተን የቀረቡ ናቸው ለማለት የሚያዳግቱ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡ ለምሳሌ፡- በ2011
ዓ.ም ሞዴል ፈተና ተራ ቁጥር 60 ላይ የማዳመጥ፣ የመናገር፣ የማንበብና የመፃፍ ክሂላትን
በጣምራ የሚመለከት ጥያቄ ቀርቦ እናገኛለን፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱን ጥያቄ በጥንቃቄ
በመመርመር የበለጠ ሊያጎለብት በሚችለው የዕውቀት ወይም የክሂል ዘርፍ ውስጥ ለመመደብ
ጥረት ተደርጓል፡፡

ከዚህ አኳያ ይህ ጥናት ከመለሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መካከል ቀዳሚው በሞዴል


ፈተናዎች የተከተቱ ይዘቶች ምን ምን ናቸው? የሚለው ጥያቄ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ
ልደታ ክፍለ ከተማ ከ2009-2011 ዓ.ም ከየትምህርት ቤቱ በተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ
መምህራን አማካኝነት በተዘጋጁት የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ጥያቄዎች
ውስጥ ምን ምን ይዘቶች እንደተካተቱ በሚከተለው ሰንጠረዥ ተተንትኖ ቀርቧል፡፡ ለሞዴል
ፈተናዎቹ ዝግጅት መሰረት ከመሆኑ አንፃርም በቅድሚያ የመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች፣
በመቀጠል በዕነርሱ ትይዩ ደግሞ የሞዴል ፈተናዎቹ ጥያቄዎች በቁጥርና በመቶኛ
ተቀምጠዋል፡፡ በሰንጠረዡ ውስጥ የተቀመጡትን የአሃዝ መረጃዎች መሰረት በማድረግም
ከግርጌያቸው ትንታኔ ቀርቧል፡፡

57
ሰንጠረዥ 4.1.1. በሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱና በሞዴል ፈተዎቹ
የተካተቱ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች

የቋን በመማሪያ መፃህፍቱ የተካተቱ የቋንቋ ትምህርት በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች
ቋ ይዘቶች የድግግምሽ መጠን የድግግሞሽ መጠን
ትም
ህርት
በዘጠነኛ በአስረኛ በዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 በ2011 ዓ.ም የሶስቱ
ይዘቶ
ክፍል ክፍል በአስረኛ ክፍል ዓ.ም ተከታታይ

የአማርኛ የአማርኛ የአማርኛ ቋንቋ ዓመታት
ቋንቋ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ሞዴል
መማሪያ ፈተናዎች
መፅሃፍ
በቁ በመቶ በቁ በመቶ በቁጥር በመቶኛ በቁ በመቶኛ በቁ በመቶ በቁ በመቶኛ በቁ በመ
ጥር ኛ ጥር ኛ ጥር ጥር ኛ ጥር ጥር ቶኛ
ማዳ 14 2% 7 1% 21 1.97% 0 0 0 0% 0 0 0 0
መጥ
መናገ 40 7% 22 4% 62 5.83% 3 3.30% 8 10% 4 5% 15 6%

ማንበ 133 23% 127 26% 260 24.44% 11 12.20% 13 16% 14 17.50% 38 15.2
ብ %
መፃፍ 106 19% 43 9% 149 14.00% 13 14.40% 16 20% 13 16.30% 42 16.8
%
ሰዋስ 201 35% 193 39% 394 37.03% 37 41% 28 35% 29 36.30% 94 37.6
ው %
ስነፅ 77 13% 101 20% 178 16.73% 26 28.90% 15 19% 20 25% 61 24.4
ሁፍ %
ድምር 571 100% 493 100% 1,064 100% 90 100% 80 100% 80 100% 250 100
%

ከሰንጠረዥ 4.1.1 መረዳት እንደሚቻለው የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ
አራቱን የቋንቋ ትምህርት ክሂላት ማለትም ማዳመጥ፣ መናገር፣ ማንበብና መፃፍ እንዲሁም
ሁለቱን የእውቀት ዘርፎች ማለትም ስነፅሁፍንና ሰዋስውን መሰረት አድርገው የቀረቡ ሲሆን
58
የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ደግሞ ከአራቱ የቋንቋ ትምህርት ክሂላት አንዱ
የሆነውን የማዳመጥ ክሂል ሳያካትቱ በመናገር፣ በማንበብ እና በመፃፍ እንዲሁም በሰዋስውና
በስነፅሁፍ ይዘት መሰረትነት ቀርበዋል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቱ ስር ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው
የቋንቋ ትምህርት ይዘት ከእውቀት ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው ሰዋስው ሲሆን 394
(37.03%) ጊዜ በመቅረብ አንደኛ ደረጃ ሲይዝ በተመሳሳይ በሞዴል ፈተናዎቹም ከ250
(100%) ጥያቄዎች ውስጥ 94 (37.6%) ጊዜ ተደጋግሞ በመቅረብም ቀዳሚውን ደረጃ
አግኝቷል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ደግሞ የማንበብ ክሂል ዘርፍ
ይዘት ነው፡፡ ይህ የቋንቋ ትምህርት ይዘት በመማሪያ መፃህፍቱ ውስጥ 260 (24.44%) ጊዜ
ተደጋግሞ የቀረበ ሲሆን፣ በአንፃሩ በሞዴል ፈተናዎቹ 38 (15.2%) ጊዜ ተደጋግሞ በመገኘት
አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የስነ ፅሁፍ ዘርፍ ይዘት በመማሪያ መፃህፍቱ በሶስተኛ ደረጃ
ላይ የሚገኝ ሲሆን 178 (14.7%) ጊዜ ተደጋግሞ ተወክሏል፡፡ በሞዴል ፈተናዎቹ ደግሞ 61
(24.4%) ጊዜ ተደጋግሞ በመወከል ሁለተኛ ደረጃን ይዟል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቱ ተደጋግሞ
በመገኘት አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ የቻለው የመፃፍ ክሂል ሲሆን 149 (14%) ጊዜ
ተወክሏል፡፡ በሞዴል ፈተናዎቹ የመፅሃፍ ክሂል 42 (16.8%) ጊዜ በመቅረብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ
ማረፍ ችሏል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቱ በአምስተኛ ደረጃ ተደጋግሞ የቀረበው የመናገር ክሂል
ዘርፍ ይዘት ሲሆን 62 (5.83%) ጊዜ ተደጋግሞ ቀርቧል፡፡ ክሂሉ 15 (6%) ጊዜ ተደጋግሞ
ውክልና በማግኘት በሞዴል ፈተናዎቹም በተመሳሳይ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ስድስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠውና በሶስቱም ተከታታይ ዓመታት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል
ፈተናዎች ውክልና ያላገኘው የማዳመጥ ክሂል ሲሆን በመፃህፍቱ 21 (1.97%) ጊዜ ውክልና
አግኝቷል፡፡

በመሆኑም የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፎች ሲዘጋጁ በርካታ የቋንቋ
ትምህርት ንዑሳን ይዘቶችን አካተው ቢሆንም በዚህ ጥናት ታላሚ ሞዴል ፈተናዎች ግን
በሚገባ አልተወከሉም፤ በሶስቱም ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ውስጥ አንድም የማዳመጥ ክሂል
ዘርፍ ይዘት አለመካተቱ ደግሞ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የመማሪያ መፃህፍቱን ይዘት
መሰረት አድርጎ ጥያቄ በማዘጋጀት ሂደት ችግር እንዳለ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡ የቋንቋ ትምህርት
ንዑሳን ይዘቶች በዝርዝር በአባሪ (አንድ፣ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፣ አምስትና ስድስት) ቀርበዋል፡፡

59
ጥናቱ ከመለሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች መካከል ሁለተኛው ሞዴል ፈተናዎቹ መሰረት
ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሀፎች ጋር የይዘት ዝምድና አላቸው? የሚለው ነው፡፡
በመሆኑም ጥናቱ በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች የቀረቡ ጥያቄዎች ይዘት
በጥቅል በመማሪያ መፃህፍቱ ከቀረቡ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ጋር ያላቸውን የዝምድና
መጠን ለማወቅ ፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የዝምድና መለኪያን (Pearson product-moment
correlation) የተጠቀመ ሲሆን በመካከላቸው ያለቸው የግንኙነት መጠን ከዚህ በታች
በሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 4.1.2. የእያንዳንዱ ዓመት ሞዴል ፈተናዎች መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ
መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን

Correlations

Bookcontent E09cont E10cont E11cont

Pearson Correlation 1 .859* .915* .925**

Bookcontent Sig. (2-tailed) .028 .010 .008

N 6 6 6 6
Pearson Correlation .859* 1 .918** .980**
E09cont Sig. (2-tailed) .028 .010 .001
N 6 6 6 6
Pearson Correlation .915* .918** 1 .955**
E10cont Sig. (2-tailed) .010 .010 .003
N 6 6 6 6
Pearson Correlation .925** .980** .955** 1

E11cont Sig. (2-tailed) .008 .001 .003

N 6 6 6 6

*. Correlation is significant at the 0.05 level (2-tailed).


**. Correlation is significant at the 0.01 level (2-tailed).
ምንጭ፣ SPSS output from the collected data, 2012 E.C.

60
ከዚህ በላይ ከቀረበው ሰንጠረዥ 4.1.2. መረዳት እንደሚቻለው በሶስት ተከታታይ ዓመታት
በተናጠል በተዘጋጀው ፈተና እና በመማሪያ መፃህፍቱ የትምህርት ይዘቶች መካከል ያለውን
ዝምድና በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ (Pearson product-moment
correlation) ተሰልቷል፡፡ በዚህም መሰረት በ2009 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል
ፈተና ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላው የዝምድና መጠን በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.859,
p=0.028) የግንኙነት መጠኑ በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት
ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከላይ ካለው ሰንጠረዥ መረዳት እንደሚቻለው በ2010 ዓ.ም የተዘጋጀው
የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላው የዝምድና መጠን በአዎንታዊ
አቅጣጫ (r=0.915, p=0.010) የግንኙነት መጠኑ በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ
ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡

እንዲሁም ከላይ ባለው ሰንጠረዥ መሰረት በ2011 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል
ፈተና ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላው የዝምድና መጠን በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.925,
p=0.008) የግንኙነት መጠኑ በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት
ይሁንታ መጠን (p<0.01) ሆኗል፡፡

ባጠቃላይ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በተናጠል ከሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን አዎንታዊና በጣም ከፍተኛ ቢሆንም
የ2011 ዓ.ም ሞዴል ፈተና (r=0.925, p=0.008) ቀዳሚውን ቦታ ሲይዝ የ2010 ዓ.ም.
ሞዴል ፈተና (r=0.915, p=0.010) እና 2009 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና (r=0.859, p=0.028)
በቅደም ተከተል የሁለተኛና የሶስተኛ ደረጃ ስፍራን ይዘዋል፡፡

61
ከዚህ በላይ ባለው ትንተና የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በተናጠል ከመፃህፍቱ
ይዘት ጋር ያላቸው ዝምድና የተፈተሸ ሲሆን በመቀጠል ደግሞ የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት
ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል እና የሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መፃህፍቱ ዝምድና ከዚህ በታች
ባለው ሰንጠረዥ ቀርቦ ከግርጌው ትንታኔ ተሰጥቷል፡፡

ሰንጠረዥ 4.1.3. የሶስቱ ዓመት ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ
ደረጃ መማሪያ መፃህፍት ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን

Correlations

Bookcontent Econtent

Pearson Correlation 1 .909*

Bookcontent Sig. (2-tailed) .012

N 6 6
Pearson Correlation .909* 1

Econtent Sig. (2-tailed) .012

N 6 6

*. Correlation is significant at the 0.05 level (2-tailed).


ምንጭ፡- SPSS output from the collected data, 2012 E.C

ከሰንጠረዥ 4.1.3. መረዳት እንደሚቻለው በሶስት ተከታታይ ዓመታት በጥቅል በተዘጋጀው


ፈተና እና በመማሪያ መፃህፍቱ የትምህርት ይዘቶች መካከል ያለው ዝምድና በፒርሰን
ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ (Pearson product-moment correlation) ተሰልቷል፡፡
በዚህም መሰረት በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች
ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909,
p=0.012) የግንኙነት መጠኑም በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት
ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡

62
ጥናቱ ይዞት የተነሳው ሶስተኛው ጥያቄ ደግሞ የሞዴል ፈተናዎቹ ጥያቄዎች ከችሎታ
መለኪያ ፈተና አንፃር ምን ይመስላሉ? የሚል ሲሆን Alderson እና ሌሎች (1995)፣ Huges
(1989) እና Bachman (1990) እንደሚገልፁት የችሎታ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች በመማሪያ
መፃህፍቱ መሰረትነት ሲማሩት የቆዩትን የትምህርት ይዘት ምን ያህል እንደጨበጡት
ለመለካት የሚዘጋጅ የፈተና አይነት በመሆኑ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በዳሰሷቸው ምዕራፎች
ወይም የትምህርት ይዘቶች መነሻነት የሚዘጋጅ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ ከመማሪያ መፃህፍቱ ዝርዝር
ይዘቶች እና ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ቀጥተኛ ተዛምዶ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ከዚህ በላይ
ካለው ፅንሰ ሀሳብ በመነሳት አባሪ (ሰባት፣ ስምንትና ዘጠኝ) ላይ የቀረቡ ከ2009-2011 ዓ.ም
ተግባራዊ የተደረጉ የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ተማሪዎች በመማሪያ መፃህፍቱ
መሰረትነት ሲማሩት የቆዩትን የትምህርት ይዘት ምን ያህል እንደተገነዘቡት ለመለካት
የሚያስችሉና ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው መሆን አለመሆናቸው
ተዳሷል፡፡

በዳሰሳውም በ2009 ዓ.ም ከተዘጋጀው 90 የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና ጥያቄ ውስጥ ሁለቱ
ጥያቄዎች ማለትም በተራ ቁጥር 23. ከፊት የቀረበው ፅንሰ ሀሳብ የኋለኛውን የሚያጎለብትበት
የአንቀፅ ማስፋፊያ ስልት----ነው፡፡ ሀ. የምስያ ስልት ለ. የማዋገን ስልት ሐ. የብያኔ
ስልት መ. የምክንያትና ውጤት ስልት በሚል የአንቀፅ ማስፋፊያ ስልቶችን በተመለከተ
የቀረበው ጥያቄ እና በተራ ቁጥር 36. ከሚከተሉት ውስጥ የዕርባታ ቅጥያ ምዕላድ ያለው ቃል
የትኛው ነው? ሀ. ዝናባማነት ለ. ቁሳዊ ሐ. ዘመኑ መ. ብዕረኛ በሚል የእርባታ ቅጥያ
ምዕላዶችን በተመለከተ የቀረበው ጥያቄ፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም ከተዘጋጀው 80 የአማርኛ
ቋንቋ ሞዴል ፈተና ጥያቄ ውስጥ በተራ ቁጥር 44. ስነቃል ሚለው ሲተረጎም ስነ ማለት
ውበት፣ ለዛ፣ መልክ ወዘተ የሚል ሲሆን ቃል ደግሞ ንግግር፣ በቃል የሚገለፅ የሚለውን
ይይዛል፡፡ በአንድነት ሲገለፅ ደግሞ ስነቃል የአነጋገር ለዛ፣ ውበት የሚልን ፍቺ ይሰጣል፡፡ ይህ
አንቀፅ የተፃፈበት ስልት ምንድን ነው? ሀ. ብያኔ ለ. ገለፃ ሐ. ማዋገን መ. ምስያ
በሚል የአንቀፅ ማስፋፊያ ስልቶችን በተመለከተ የቀረበው ጥያቄ የደረጃው ተማሪዎች
የተማሩትን ትምህርት ታሳቢ ያላደረጉ እና የደረጃውን ተማሪዎች የቋንቋ ችሎታ ለመለካት
የማያስችሉ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በ2009 ዓ.ም በተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና
በሁለቱ ተራ ቁጥሮች ላይ የቀረቡት ጥያቄዎችና በ2011 ዓ.ም በተራ ቁጥር 44 ላይ የቀረበው

63
ጥያቄ ይዘት የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በተማሩት የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ይዘት
ላይ ያልተመሰረቱ እና በ2009 ዓ.ም በተራ ቁጥር 23 ላይ እና በ2011 ዓ.ም በተራ ቁጥር 44
ላይ የቀረቡት የአንቀፅ ማስፋፊያ ስልቶችን የተመለከቱ ጥያቄዎች በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ ገፅ 16 ላይ ያለን ይዘት መነሻ ያደረጉ እና በ2009 ዓ.ም በተራ ቁጥር 36
ላይ የቀረበው የእርባታ ቅጥያ ምዕላድን የተመለከተው ጥያቄ ደግሞ በ11ኛ ክፍል የአማርኛ
ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ገፅ 67 ላይ ያለን ይዘት መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው ነው፡፡ አንድ
ፈተና ደግሞ የችሎታ መለኪያ ፈተና ነው የሚባለው ከላይ እነ Alderson እንደገለፁት የአንድ
የክፍል ደረጃ ተማሪዎች በተማሩት ትምህርት ላይ ብቻ ተመስርቶ ምን ያህል የተማሩት
ትምህርት ሰርጿቸዋል የሚለውን ለመረዳት የሚዘጋጅ ሲሆን ነው፡፡ በመሆኑም በ2009 ዓ.ም
ከተዘጋጁት 90 ጥያቄዎች ውስጥ ሁለት ጥያቄዎች እና በ2011 ዓ.ም ከቀረቡት 80 ጥያቄ
ወስጥ አንድ ጥያቄ የተማሪዎችን የቋንቋ ችሎታ ለመለካት የሚያስችሉ ጥያቄዎች አይደሉም፡፡

ከቋንቋ ትምህርት መሰረታዊ ዓላማዎችና ከመማሪያ መፃህፍቱ ዝርዝር ይዘቶች አንፃርም


ምንም እንኳ በ2009 ዓ.ም ከቀረቡት 90 ጥያቄዎች ውስጥ ሁለት ጥያቄዎችና በ2011 ዓ.ም
ከቀረቡት 80 ጥያቄዎች ውስጥ ከአንድ ጥያቄ ውጭ ያሉት የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት
ሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ቀጥተኛ ተዛምዶ ያላቸው ቢሆኑም ሁሉም የሶስቱ ተከታታይ
ዓመታት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፃህፍት ዝርዝር ይዘቶች እና ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ
ዝምድና ስለሌላቸው የችሎታ መለኪያ ፈተና ናቸው ብሎ መደምደም አልተቻለም፡፡

4.2. የውጤት ማብራሪያ

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት
ፅህፈት ቤት ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም በክፍለ ከተማው ካሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች በተውጣጡ መምህራን አማካኝነት ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ነበር፡፡ ይህንን ዓላማ

64
ከግብ ለማድረስ መረጃዎች በሰነድ ፍተሻ ከተሰበሰቡ በኋላ በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱት
ይዘቶች ድግግሞሽ በቁጥርና በመቶኛ ቀርበው የተተነተኑ ሲሆን የሞዴል ፈተናዎቹ ይዘት
መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሀፎች ይዘት ጋር ያላቸውን የዝምድና መጠን
ውጤት በመቶኛ ከተሰላ በኋላ በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ የዝምድና
ይሁኔታ ታይቷል፡፡ ፈተናዎቹ ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ ድግሞ
አይነታዊ በሆነ የመረጃ መተንተኛ ስልት አማካኝነት በገለፃ መልክ ቀርቧል፡፡

የዚህ ጥናት የመጀመሪያው ንዑስ ዓላማ በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ ይዘቶች ምን ምን


እንደሆኑ መለየት ሲሆን የተገኘው መረጃ ከተደራጀ በኋላ ተተንትኖ ውጤቱ እንደሚያሳየው
በሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ የተካተቱ ንዑሳን ይዘቶች በሶስቱ ተከታታይ
ዓመታት በተዘጋጁት ሞዴላ ፈተናዎች በአግባቡ ውክልና አላገኙም፡፡ በትንተናው ሰንጠረዥ
4.1.1 ማየት እንደሚቻለው በሶስቱም ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ለሁለቱ የቋንቋ
ትምህርት የዕውቀት ዘርፎች ማለትም ለስነፅሁፍና ለሰዋስው ይዘቶች የተሰጠው ውክልና
ለማንበብ፣ ለመፃፍና ለመናገር ክሂላት ዝርዝር ይዘቶች ከተሰጠው ውክልና ጋር ተመጣጣኝ
አይደለም፡፡ በተለይም የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች ደግሞ በሶስቱም ዓመታት ሞዴል
ፈተናዎች ምንም ውክልና አላገኙም፡፡ በሞዴል ፈተናዎቹ ብዙ ጊዜ ተደጋግመው የሚገኙት
የስነ ፅሁፍና የስነ ልሳን ዘርፍ ይዘቶችም ሆኑ ተደጋግመው በመገኘት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው
የማንበብ፣ የመፃፍና የመናገር ክሂል ይዘት ጥያቄዎችም ከንዑሳን ይዘቶች የውክልና
ሚዛናዊነት አንፃር ችግር እንዳለባቸው መረጃው ያሳያል፡፡ የንዑሳን ይዘቶችን ውክልና ከአባሪ
(አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት፣ አራት፣ አምስት እና ስድስት ይመልከቱ)፡፡ Wier (1993) እና
Hughes (2003) እንደሚገልፁት ደግሞ አንድ ፈተና መሰረት ያደረገውን መማሪያ መፅሃፍ
ይዘት ወካይ የሆኑ ጥያቄዎች የማያካትት ከሆነ ተማሪዎቹ በቋንቋው ትምህርት ዙሪያ ያላቸው
ችሎታ ምን እንደሆነ መረዳት አይቻልም፡፡

የዚህ ጥናት ሁለተኛው ንዑስ ዓላማ በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ ይዘቶች በመማሪያ
መፃህፍቱ ውስጥ ከቀረቡ ይዘቶች ጋር ያላቸውን ዝምድና መፈተሽ ሲሆን በፒርሰን ፕሮዳክት
ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ (pearson product-moment correlation) ተሰልቶ ተተንትኗል፡፡

65
በትንተናው መሰረትም የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በተናጠል ከሁለተኛ
ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን አዎንታዊና በጣም
ከፍተኛ ሲሆን የ2011 ዓ.ም ሞዴል ፈተና በ(r=0.925, p=0.008) ቀዳሚውን ቦታ ይዟል፡፡
የ2010 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና (r=0.915, p=0.010) እና 2009 ዓ.ም. ሞዴል ፈተና (r=0.859,
p=0.028) ደግሞ በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ እንደተቀመጡ ጥናቱ
አረጋግጧል፡፡

ጌታቸው (2011) የክፍል ውስጥ ፈተና ከመማሪያ መፅሃፉ ጋር ያላው የዝምድና መጠን
በአሉታዊ አቅጣጫ በጣም ዝቅተኛ የግንኙነት መጠን እንዳለው በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት
ይሁናታ መጠን (p value) 0.05 ደረጃ በንሞና መጠን (sample size) 3 (r(3)=-.199,
p=0.01) እንደሆነ አሳይቶ ነበር፡፡ በአንፃሩ በዚህ ጥናት በጥቅል በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት
የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የዝምድና
መጠን በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909, p=0.012) የግንኙነት መጠን በጣም ከፍተኛ የሚባልና
በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡

ጥናቱ ይዞት የተነሳው ሶስተኛውና የመጨረሻው ንዑስ ዓላማ ደግሞ በሶስቱ ተከታታይ
ዓመታት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን
እንደሚመስሉ መገምገም ነበር፡፡ በግምገማው መሰረትም በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት
የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፃህፍት ዝርዝር ይዘቶች እና ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ
ዝምድና የሌላቸው በመሆናቸው ሁሉም የችሎታ መለኪያ ፈተና ናቸው ብሎ ድምዳሜ ላይ
መድረስ አልተቻለም፡፡ ከሰንጠረዥ 4.1.1 ማየት እንደሚቻለው በ2009 ዓ.ም 90 ጥያቄ፣
በ2010 እና በ2011 ዓ.ም ደግሞ በእያንዳንዳቸው 80 ጥያቄዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በ2010 ዓ.ም
የተዘጋጁት ሁሉም 80 ጥያቄዎች፣ በ2009 ዓ.ም ከተዘጋጀው 90 ጥያቄ ውስጥ 88 እና
በ2011 ዓ.ም ከተዘጋጀው 80 ጥያቄ ውስጥ 79 ጥያቄዎች ደግሞ የችሎታ መለኪያ ፈተናን
ታሳቢ አድርገው የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ምንም እንኳ በሞዴል ፈተናዎቹ ከሁለተኛ ደረጃ
የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ ውጭ የተዘጋጁት ጥያቄዎች ሶስት ብቻ ቢሆኑም

66
Bachman (2002)፣ Alderson እና ሌሎች (1995) እና Weir (1993) የችሎታ መለኪያ
ፈተና ለትምህርት የቀረበውን መርሃ ትምህርትና መማሪያ መፅሃፍ መሰረት አድርጎ መዘጋጀት
እንዳለበትና ከመርሃ ትምህርቱና ከመማሪያ መፅሃፉ ዓላማና ይዘት የተለየ ሊሆን አይገባውም
ከሚሉት ንድፈ ሀሳብ ጋር ተቃርኖ ተገኝቷል፡፡ ማስረጃውም በ2009 ዓ.ም በተዘጋጀው
የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና በተራ ቁጥር 23 እና 36 ላይ የቀረቡት ጥያቄዎችና በ2011
ዓ.ም በተራ ቁጥር 44 ላይ የቀረበው ጥያቄ ይዘት የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በተማሩት
የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ይዘት ላይ ያልተመሰረቱ እና በ2009 ዓ.ም በተራ ቁጥር
23 ላይ እና በ2011 ዓ.ም በተራ ቁጥር 44 ላይ የቀረቡት የአንቀፅ ማስፋፊያ ስልቶችን
የተመለከቱ ጥያቄዎች በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ገፅ 16 ላይ ያለን ይዘት
መነሻ ያደረጉ እና በ2009 ዓ.ም በተራ ቁጥር 36 ላይ የቀረበው የእርባታ ቅጥያ ምዕላድን
የተመለከተው ጥያቄ ደግሞ በ11ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፅሃፍ ገፅ 67 ላይ ያለን
ይዘት መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው የችሎታ መለኪያ ጥያቄዎች አይደሉም፡፡ (አባሪ ሰባትንና
አባሪ ዘጠኝን ይመልከቱ)

Bachman (1990) እንደሚገልፁት የችሎታ መለኪያ ፈተና ተማሪዎች ያሳኩታል ተብሎ


ከታቀደው ትምህርታዊ ዓለማ አኳያ ምን ያክል እንዳከናወኑ የሚለካ የፈተና ዓይነት ሲሆን
በአብዛኛው በመንፈቅ አመት አጋማሽ እና መጨረሻ ላይ ይሰጣል፡፡ ተማሪዎች የተማሩትን
ትምህርት መሰረት አድርጎ ፈተናው በሚዘጋጅበት ጊዜም የይዘት ሽፋንን እና የይዘት
ተዛማጅነትን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ ስለሆንም ፈተናው በሚዘጋጅበት ጊዜ ጥያቄዎቹ ከመማሪያ
መፅሀፉ ጋር ጥብቅ የሆነ የይዘት ዝምድና ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አንድ የችሎታ መለኪያ ፈተና
በአግባቡ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ ተማሪዎቹ የተማሩትን ትምህርት ይዘት ምን ያህል
እንደተረዱትና እንዳልተረዱት፣ እንዲሁም ትምህርቱ የሚሰጥበትን ዓላማ ግብ መምታት
አለመምታቱን ፍንትው አድርጎ የማሳየት አቅም አለው፡፡ በዚህ ጥናት የተዳሰሱት የሶስቱ
ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ግን ትስስራቸው ጥብቅ ባለመሆኑ ሙሉ በሙሉ
የችሎታ መለኪያ ፈተና ናቸው ማለት ያስቸግራል፡፡

67
ምዕራፍ አምስት፤ ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና አስተያየት

5.1. ማጠቃለያ

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት
ፅህፈት ቤት ከ2009 ዓ.ም እስከ 2011 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት ፍተሻ ነው፡፡ በዚህም ዓላማ
መነሻነት ጥናቱ ምላሽ የሰጠባቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፤

1. በሞዴል ፈተናዎቹ የተካተቱ ይዘቶች ምን ምን ናቸው?


2. ሞዴል ፈተናዎቹ መሰረት ካደረጓቸው የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መፅሃፎች ጋር
የይዘት ዝምድና አላቸው?
3. የሞዴል ፈተናዎቹ ጥያቄዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን ይመስላሉ?

ለነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ ለማግኘት አጥኝው የተጠቀመው የምርምር ንድፍ ገላጭ ሲሆን መረጃ
የሰበሰበው ደግሞ በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደበት ክፍለ ከተማ በአመቺ
የናሙና አመራረጥ ስልት የተመረጠ ሲሆን የክፍል ደረጃው በዓላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ
ስልትና ሞዴል ፈተናዎቹ ደግሞ በጠቅላይ የናሙና አመራረጥ ስልት አማካኝነት
ተመርጠዋል፡፡ በልደታ ክፍለ ከተማ ከ2009 እስከ2011 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረጉት የአማርኛ
ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች እና የዘጠነኛ እና የአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት
ደግሞ ለጥናቱ በመረጃ ምንጭነት አገልግለዋል፡፡ በሰነድ ፍተሻው የተገኙት መረጃዎችም
መጠናዊ በአይነታዊ በተደገፈ ቅይጥ የመረጃ መተንተኛ ስልት አማካኝነት ተተንትነዋል፡፡
የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው የይዘት
ዝምድና መጠን በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ አማካኝነት ተሰልቶ
ተተንትኗል፡፡ ትንተናው የተካሄደው በሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍቱ
የተካተቱትን ዝርዝር የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ፈልፍሎ በማውጣትና በሶስቱ ተከታታይ
ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች ውስጥ በአራቱ የቋንቋ ትምህርት ክሂላትና በሁለቱ የዕውቀት

68
ዘርፎች ውሰጥ የተካተቱትን የቋንቋ ትምህርት ንዑሳን ይዘቶችን እንደይዘታቸው በመፈረጅ
ነው፡፡ በሰነድ ፍተሻው አማካኝነት የተገኙትን መረጃዎች መጠናዊ በአይነታዊ በተደገፈ ቅይጥ
የመተንተኛ ዘዴ በመተንተንም የሚከተሉት ግኝቶች ላይ ተደርሷል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ ከእውቀት ዘርፎች አንዱ የሆነው
ሰዋስው ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን በሶስቱ ተከታታይ የዚህ ጥናት ታላሚ የአማርኛ
ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ውስጥም ተደጋግሞ በመገኘት ቀዳሚውን ድርሻ አግኝቷል፡፡
በመማሪያ መፃህፍቱ ተደጋግሞ በመገኘት ሁለተኛውን ደረጃ የያዘው የማንበብ ክሂል ሲሆን
በአንፃሩ በሞዴል ፈተናዎቹ አራተኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ስነፅሁፍን የተመለከቱ ይዘቶች ደግሞ
በመፃህፍቱ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ በሞዴል ፈተናዎቹ ሁለተኛ ደረጃ ላይ አርፈዋል፡፡
እንዲሁም የመፃፍ ክሂልን የተመለከቱ ይዘቶች በበኩላቸው በመማሪያ መፃህፍቱ አራተኛ፣
በሞዴል ፈተናዎቹ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን አግኝተዋል፡፡ በመማሪያ መፃህፍቱ ተደጋግሞ
በመገኘት አምስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የመናገር ክሂል በሞዴል ፈተናዎችም በተመሳሳይ
አምስተኛ ደረጃ ለይ ማረፍ ችሏል፡፡ በመፃህፍቱ ተደጋግሞ በመገኘት ዝቅተኛውንና
የመጨረሻውን ደረጃ የያዘው የማዳመጥ ክሂል በሶስቱም ተከታታይ ዓመታት ሞዴል
ፈተናዎች ምንም ውክልና ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም በሁለተኛ ደረጃ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፃህፍቱም ሆነ በሞዴል ፈተናዎቹ ትኩረት የተሰጣቸው ለሁለቱ የዕውቀት ዘርፎች
ማለትም ለሰዋስውና ለስነፅሁፍ ሲሆን ለአራቱ ክሂላት በተለይም ለሁለቱ ቀዳሚ ክሂላት
ማዳመጥና መናገር የተሰጠው ትኩረት በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ የማዳመጥ ክሂል ሙሉ ለሙሉ
የተዘነጋና የተረሳ እንደሆነ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ በመሆኑም በመማሪያ መፅሃፉ የተቀረፁ
በርካታ የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች በተዘጋጀው ፈተና አልተወከሉም፡፡ በፈተናው የቀረቡት
የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች የስርጭት መጠንም መማሪያ መፅሀፉን መሰረት
እንዳላደረጉ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር


ያላቸው ዝምድናም በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ተሰቶ በሶስቱ ተከታታይ
ዓመታት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ ጋር ያላቸው

69
የዝምድና መጠን በአዎንታዊ አቅጣጫ (r=0.909, p=0.012) የግንኙነት መጠን በጣም ከፍተኛ
የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠን (p<0.05) ሆኗል፡፡

በመጨረሻም በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች


ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ሲታዩ በ2010 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ ፈተና ሙሉ
ለሙሉ የችሎታ መለኪያ ፈተና እንደሆነ ጥናቱ አረጋግጧል፡፡ በአንፃሩ የ2009 እና የ2011
ዓ.ም ሞዴል ፈተናዎች ይዘት ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት
ዝርዝር ይዘቶች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ ዝምድና የሌላቸው በመሆናቸው ሁሉም የችሎታ
መለኪያ ፈተናዎች ናቸው ብሎ መደምደም እንደማይቻል ጥናቱ አመላክቷል፡፡ ማስረጃውም
በ2009 እና በ2011 ዓ.ም የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች የክፍል ደረጃው
ተማሪዎች ካልተማሩትና ከማያውቁት የ11ኛ ክፍል መፅሃፍ ይዘት በፈተናው ማካተታቸው
ለዚህ ግልፅ ማሳያ ነው፡፡

5.2. መደምደሚያ

የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት
ፅህፈት ቤት ከ2009 እስከ2011 ዓ.ም ተዘጋጅተው ለአስረኛ ክፍል ተማሪዎች የቀረቡ የአማርኛ
ቋንቋ ትምህርት ሞዴል ፈተናዎች ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ምን እንደሚመስሉ እና
ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል መማሪያ መፅሃፎች ጋር ያላቸውን የይዘት ዝምድና መፈተሽ
ነው፡፡ በመሆኑም የጥናቱን ትንተናና ውጤት መነሻ በማድረግ ከሚከተሉት መደምደሚያዎች
ላይ ተደርሷል፡፡

በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት የተዘጋጁት የቋንቋ ትምህርት ይዘቶች ማለትም የማዳመጥ፣


የመናገር፣ የማንበብና የመፃፍ ክሂላትና የሰዋስውና የስነፅሁፍ ዘርፍ የሞዴል ፈተና
ጥያቄዎች ይዘት የድግግሞሽ መጠን በመማሪያ መፃህፍቱ ከቀረቡት የማዳመጥ፣ የመናገር

70
የማንበብ፣ የመፃፍ ክሂላትና የሰዋስውና የስነፅሁፍ ዘርፍ ይዘቶች የድግግሞሽ መጠን ጋር
ተመጣጣኝ ውክልና እንደሌላቸው እና በርካታ የማዳመጥ፣ የመናገር የማንበብ፣ የመፃፍ
ክሂላትና የሰዋስውና የስነፅሁፍ ዘርፍ ንዑሳን ይዘቶች በተዘጋጀው ፈተና እንዳልተካተቱ ጥናቱ
አመላክቷል፡፡ ከዚህም በላይ በሞዴል ፈተናዎቹ ከቋንቋ ትምህርት ክሂላት ይልቅ ለቋንቋ
ትምህርት የእውቀት ዘርፎች ትኩረት የተሰጠ በመሆኑ ሞዴል ፈተናዎቹ የመማሪያ መፃህፍቱ
ይዘቶች ነፀብራቅ እንዳልሆኑ ጥናቱ አመላክቷል፡፡ በሌላ በኩል የሶስቱ ተከታታይ ዓመታት
ሞዴል ፈተናዎች በጥቅል ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር ያላቸው የዝምድና መጠን
በፒርሰን ፕሮዳክት ሞመንት የተዛምዶ መለኪያ ስሌት መሰረት በአዎንታዊ አቅጣጫ
የግንኙነት መጠን በጣም ከፍተኛ የሚባልና በስታትስቲክስ ትንተና የስህተት ይሁንታ መጠንም
(p<0.05) ሆኗል:፡

በመጨረሻም በሶስቱ ተከታታይ ዓመታት የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተናዎች


ከችሎታ መለኪያ ፈተና አንፃር ሲታዩ በ2010 ዓ.ም የተዘጋጀው የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና
ጥያቄዎች ሙሉ ለሙሉ የችሎታ መለኪያ ፈተና ሲሆኑ፣ በአንፃሩ የ2009 እና የ2011 ዓ.ም
ሞዴል ፈተና ጥያቄዎች ይዘት ከዘጠነኛ እና ከአስረኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ
መፃህፍት ዝርዝር ይዘቶች እና ከትምህርቱ ዓላማዎች ጋር ሙሉ ለሙሉ ቀጥተኛ ዝምድና
የሌላቸው በመሆናቸው ሁሉም የችሎታ መለኪያ ፈተናዎች ናቸው ብሎ መደምደም
እንደማይቻል ጥናቱ በማረጋገጥ የሞዴል ፈተናዎቹ ይዘቶች ከመማሪያ መፃህፍቱ ይዘቶች ጋር
ያላቸው ትስስር ጥብቅና ቀጥተኛ እንዳልሆነ ከድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡

5.3. አስተያየት

ጥናቱ የተደረሰባቸውን መደምደሚያዎች መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን አስተያቶችና


ጥቆማዎች ሰንዝሯል፡፡

 የቋንቋ መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜ የችሎታ መለኪያ ፈተና


አዘገጃጀት ሂደትን ተከትለው ቢያዘጋጁ፤
71
 መምህራን የሞዴል ፈተናውን በሚያዘጋጁበት ጊዜ የትኛው ይዘት በመማሪያ መፃህፍቱ
እና በክፍል ውስጥ የመማር ማስተማሩ ሂደት ምን ያህል ጊዜ ተደጋግሞ ቀረበ
በማለት እንደየ ሽፋኑ መጠን የይዘት ድግግሞሹን ጠብቀው ቢያዘጋጁ፤
 መምህራን የሞዴል ፈተና በሚያዘጋጁበት ጊዜ መማሪያ መፅሀፉን መሰረት አድረገው
ተፈታኝ ተማሪዎችን ለሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናው ዝግጁ እንዲሆኑ
የሚያደርግ ፈተና አድርገው ቢያዘጋጁ፤
 ሞዴል ፈተና አውጭ መምህራን ስለችሎታ መለኪያ ፈተና አዘገጃጀት ሂደት እና ስለ
መማሪያ መፃህፍትና ፈተና የይዘት ተዘምዶ አጫጭር ስልጠና ቢሰጣቸው፤
 መምህራን የሚያዘጋጇቸው የሞዴል ፈተናዎች የተማሪዎችን ችሎታ እንዲመዝኑ
ጥቅም ላይ ከመዋላቸው አስቀድሞ በፈተና አውጭ ባለሙያዎች ከመማሪያ መፃህፍቱ
ጋር ያላቸው ትስስር ቢፈተሽ፤
 መምህራን ስለሚያዘጋጁት ሞዴል ፈተና ዓላማ ጥያቄው ከመዘጋጀቱ በፊት
አስቀድመው እንዲወስኑ ቢደረግ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለችሎታ መለኪያ ፈተና አላማ
የፈተና ጉዳይ በሚመለከታቸው ባለሞያዎች ስልጠና የሚሰጡበት ሁኔታ ቢመቻች፤
 በየትምህርት ቤቱ መምህራን በሚሳተፉበት ተከታታይ ሞያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ ስለ
ሞዴል ፈተና እና ስለ መማሪያ መፃህፍት ተዛምዶ ትኩረት በመስጠት የእርስ በዕርስ
ውይይት እንዲካሄድ ቢደረግ፤
 በሀገር አቀፍ ደረጃ በፈተና አዘገጃጀት እና ተገቢነት ዙሪያ የተዘጋጁ መፅሀፍቶችን
መምህራን እንዲያነቡ በመገፋፋት አቅማቸውን እንዲያሰድጉ ቢደረግ ችግሩ በተወሰነ
ደረጃ ሊስተካከል ይችላል፡፡

72
ዋቢዎች

መሰረት አለማየሁ፡፡ (2005)፡፡ "በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ተዘጋጅተው ከ1999-2004


ዓ.ም በተሰጡ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ክልላዊ ፈተናዎች ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው
ጥያቄዎች ይዘትና አቀራረብ ግምገማ፡፡" በቋንቋዊች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ
ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ሙሉፀሃይ ገነት፡፡ (2005)፡፡ "ከ2001-2004 ዓ.ም በተሰጡ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ
ትምህርት ሞዴል እና ክልላዊ ፈተናዎች ውስጥ የቀረቡ የሰዋስው ጥያቄዎች መካከል
ያለ የይዘትና አቀራረብ ዝምድና በአማራ ክልል ሰሜን አቸፈር ወረዳ በተመረጡ ሶስት
ትምህርት ቤቶች ናሙናነት፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ
ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ማረው አለሙ፡፡ (2003)፡፡ ዘመናዊ የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ፡፡ አዲስአበባ፣ አልፋ
ማተሚ ቤት፡፡

ማርታ እሸቱ እና ነፃነት ጌትነት፡፡ (2004)፡፡ የአስረኛ ክፍል የተማሪ መማሪያ መፅሃፍ፡፡
የተባበሩት አረብ ኤሜሬት፤ ዱባይ፣ የአል፣ ጉሬር አታሚና አሳታሚና ድርጅት፡፡

ሰለሞን ሓለፎም፡፡ (1994)፡፡ "ቋንቋን የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ፡፡" አዲስ አበባ፣(ያልታተመ)

ሳህሉ አክሊሉ፣ ደመላሽ አለሙ እና የሽጥላ መንግስቴ፡፡ (2004)፡፡ የዘጠነኛ ክፍል


የተማሪዎችመማርያ መፅሀፍ፡፡ የተባበሩት አረብ ኤሜሬት፤ ዱባይ፣ የአልጉሬር
አታሚና አሳታሚና ድርጅት፡፡

ባየ ይማም። (1987)። የአማርኛ ሰዋስው። አዲስ አበባ፣ ት.መ.ማ.ማ.ድ። የታተመ

ተስፋዬ ሽዋዬ። (1981)። ስነልሳንና ቋንቋን ማስተማር። አዲስ አበባ፣ ንግድ ማተሚያ
ድርጅት፡፡

ታለጌታ ይመር፡፡ (2005)፡፡ "በሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ2001-2004 ዓ.ም ድረስ ለርቀት
ትምህርት መርሃ ግብር የቀረቡ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ብሄራዊ

73
ፈተናዎች ከመማሪያ መፅሃፉ ጋር ያላቸው ዝምድና፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ
ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ
(ያልታተመ)፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር፡፡ (2004)፡፡ "የሥርዓተ- ትምህርት ማስፋፋትና የነፍሰ ወከፍ የትምህርት


መርሃ ግብር መመሪያ፡፡" አዲስ አበባ፣ ትምህርት ሚኒስቴር፡፡

አለም እሸቱ፡፡ (1997)፡፡ መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አፃፃፍ (3ኛ እትም)፡፡ አዲስ አበባ፣
ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡፡

አለም እሸቱ እና ፅጌ አበበ (1997):: አማርኛ የመምህሩ መምሪያ ዘጠነኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፣
ንግድ ማተሚያ ቤት (ተሻሽሎ የወጣ)፡፡

አበበች ገብሩ፡፡ (2004)፡፡ "ከ1998-2003 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ
ለሚማሩ ተማሪዎች ተዘጋጅተው የቀረቡ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ፈተናዎች ውስጥ
የሰዋስው ጥቄዎች ግምገማ፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ
ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

አብርሃም መስፍን፡፡ (2003)፡፡ "በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በተመረጡ ሶስት


ትምህርት ቤቶች የሚዘጋጁ የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ ፈተናዎች የይዘት ተገቢነት
ግምገማ፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ
ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ወንድማገኝ አደም፡፡ (2005)፡፡ "ከ2001-2004 ዓ.ም የተሰጡ የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ አገር
አቀፍ እና ሞዴል ፈተናዎች የይዘትና የአቀራረብ ንፅፅር በጋምቤላ ክልል በሁለት
የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መነሻነት፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ
ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ያለው እንዳወቀ፡፡ (2001)፡፡ የምርምር መሰረታዊ መርሆዎችና አተገባበር፡፡ አዲስ አበባ፤ አልፋ
አሳታሚዎች፡፡

ደሳለኝ ኪሮስ፡፡ (1994)። "ፕሮጀክት 17.000፣ ሰሚናርን ሜላን አመሃህራ"፣ ቋንቋ ትግርኛ።

74
ዳንኤል ዘውዴ፡፡ (2006)፡፡ በክፍል ምዘና አተገባበር ተጨባጭ ስልቶች፡፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ
ማተሚያ ድርጅት

ጌታሁን አማረ። (1989)። ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋስው በቀላል አቀራረብ። አዲስ አበባ፣ ንግድ
ማተሚያ ቤት።

ጌታቸው ሆነልኝ፡፡ (2011)፡፡ "በመምህራን የሚዘጋጁ የክፍል ውስጥ ፈተናዎች የይዘትና


የቀረቡበት ስልት ተገቢነት እና የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የፈተና አዘገጃጀት
ሂደት ፍተሻ፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ
ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ ዩኒበርሲቲ (ያልታተመ)፡፡

ጌታቸው በለጠ፡፡ (2005)፡፡ አማርኛ ቋንቋ ከ9ኛ -10ኛ ክፍል፡፡ አዲስ አበባ፣ አስቴር ነጋ
አሳታሚ ድርጃት፡፡

ጠጅቱ በሬቻ፡፡ (1999)፡፡ "በአዲስ አበባ ከተማ በግልና በመንግስት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
መካከል የ10ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ አገር አቀፍ ፈተና ንፅፅር፡፡" በቋንቋዎች ጥናትና
ስነፅሁፍ ክፍል ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ፤ አዲስ አበባ

Agarwal, J.C. (1996). Principles, Methods and Techniques of Teaching. New


Delhi: vikno publishing House pvt. LTD.

Aldeson, J. C. (1999). Testing is too important to be Left to Testers. Lancaster


Univirsity.

Alderson, J.C. (2001). Assessing Reading. Urited Kingdom: Combrideg University


Pre

Alderson, J.C., Clapham, C. & Wall, D. (1995). "Language Testing construction


and Evaluation". CUP. Especially chapters 2,3.

Alderson, J.C., Clapham,C.& Wall,D. (2001). Language Testing construction and


Evaluation. 5th ed, Cambridge: Cambridge University press.

75
Allwright, R.T. (1981). What Do we want Teaching Materials for? ELT. Journal,
Vol 36, No.1,5-18

Arega Mamaru. (2014). Class room Assessment Manual for primary and
Secondary school Teachers. Brana printing,A.A.

Axman, C.K. (1989). "ERIC Clearing House on Test Measurement and


Evaluation." http://www.endigests,org/pig9213/ classroom, htm (Date
Accessed, April 5/2005).

Bachman,L.F. (1990). Fundamental Considerations in Language Testing. Oxford፡


Oxford University Press.

Baker, D. (1989). Language Testing.A critical survey and practical guide.


London: Edward Arnold.

Behar,N. Linda. (1994). The Knowledge Base of Curriculum: An Imperial


Analysis. Lanham, Lanham University Press of America.

Bertrand,A, and Cebula,J.P. (1980). Tests, Measurement and Evaluation.


Philippines: Addision-Western Publishing.

Brown, J.D. (1980). Principles of Learning and Teaching. New Jersey: Prentice
Hall Inc.

Brown, J.D. (1994). A normal referenced engineering reading test. In A.k PuGh
and J.M. ULJN (EDS) Reading for Professionsal Purpose: Heine Mann
Education Books.

Brown, J. D. (2004). Language Assessment Principles and Classroom Practices.


USA: Pearson Education, Inc.

Brown, J.D. and Hudson, T. (2002). Criterion Referenced Language Testing


Cambridge: Cambridge University Press.

76
Callhan, J.F. and Calrk, L.H. (1988). Teaching in the Middle and Secondary
Schools: planning for Competence. 3rded. New York: Macmillan Publishing
Company.

Carter,V. (1973). Dictionary of Education. New York: Mc Graw Inc.

Clark, L.H. and Starr, I.S. (1988). Secondary and Middle School Methods. 5th
ed. New York: Macmillan Publishing Company.

Cohen, L. and Manion,L. (1994). Research Methods in Education. London:


Croom Helm Ltd.

Cronbach, L.J. (1970). Essential and psychological Testing. New York: Harper
and Row.

Davies, A. (1968). Language Testing Symposium. Psycholingustic Approach.


London: Oxford University Press.

Finocchiaro, M. and Brumfit,C. (1983). The Fundamental National Approach:


From Theory to Practice. Oxford: Oxford University Press.

Genessee,F. and Upsher,J.A. (1996). Class room Based Evaluation in Education,


Oxford University press.

Getachew Anteneh and Derib Ado. (2006). "Language policy in Ethiopia history".
Ethiopia Education and Sc Voll.2 Spetember.

Gottfredson,L. (2004). "Educational Assessment for Classroom Teachers".


http:/www.udel/ educ/ gottfredson/451/ (Date Accessed, June 1/2005).

Grouland, N.E. (1986). Measurement and Evaluation in Teaching. New York:


Macmillan.

Harison, A. (1983). A Language Testing Handbook. London: Macmillan


Publishers Ltd.

77
Harison, A. (1989). A Language Testing Handbook. London: Macmillan
Publishing. Harmer, J. (1991). The practice of English language. New
York: long man Publishing.

Harmer, J. (1991). The Practice of English Language Teaching (2 rd Ed).


London: Longman.

Heatan, J.B. (1975). Writing English Language Tests. London: Longman Group
Ltd.

Heaton, J.B. (1988). Writing English language Tests. Londen: Longman.

Heaton, J.B. (1990). Classroom testing. London: Longman Group Ltd.

Hughes,A. (1989). Testing for Language Teachers. Cambridge: Cambridge


University Press.

Hughes,A. (2003). Testing for Language Teachers (2nd Ed). Cambridge:


Cambridge University press.

Kaphlan, R.M. (2001). Psychological Testing: principles Applications and issues


(5thed). New York: Wladsworth.

Madson, H .S. (1983). Techniques in Language Testing. Oxford: OUP.

Mehrens, W.A and Lehman, I.J. (1974). Standardize tests in Education,(2nd ed.)
New York; Holt, Rinenhart and Winston.

Nijabili, A.f. (1993). Practical Guide for Classroom Measurement and Testing:
The Basic Essentials. 3rd ed. Dar Essalaam: Muture Publishers.

Richarde,J. and Rodgers,T. (1986). Approaches and methods in language


Teaching. Cambridge University press.

78
Richards, J, and Rodgers, T. (2001). Approaches and Methods in Language
Teaching (2nd ed).New York: Cambridge University Press.

Taiwo, A.A. (1995). Fundamentals of classroom Testing. New Delhi: Vikas


Publishing House Pvt Ltd.

Tyler, R.W. (1969). Educational Evaluation. New York፡ Cambridge University


Press.

Ur,P. (1996). Acourse in language teaching practice and the Cambridge:


Cambridge University press.

Ur, P. (2006). A Course in Language Teaching: Practice and Theory 3rded


Printing, Cambridge University.

Weir, C. (1990). Commuicative Language Testing. Engllewood Cliffs, NJ:


prentice- Hall Regent.

Woodford, P. (1980). Foreign Language Testing. The Modern Language. Journal.


Vol.64, No.1, 97-101.

79
አባሪዎች

አባሪ አንድ፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የማዳመጥ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የማዳመጥ የመማሪያ መፃህፍቱ የማዳመጥ ክሂል ይዘቶች የድግግምሽ የማዳመጥ ክሂልን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ የቀረቡ
ክሂል መጠን ጥያቄዎች ብዛት
ይዘቶች የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መፅሃፍ መማሪያ መፅሃፍ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ
በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ
አዳምጦ 3 21.40% 1 14.30% 4 19% 0 0 0 0 0 0
ሀሳብ
በማስታዎሻ
መያዝ
የሚነበብን 5 35.70% 6 85.70% 11 52.40% 0 0 0 0 0 0
ፅሁፍ
አዳምጦ
መልስ
መስጠት
የሚነበብን 6 42.90% 0 0 6 28.60% 0 0 0 0 0 0
አጭር
ፅሁፍ
አዳምጦ
ሀሳቦችን
ማዛመድ
ድምር 14 100% 7 100% 21 100% 0 0 0 0 0 0

80
አባሪ ሁለት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የመናገር ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የመናገር ክሂል የመማሪያ መፃህፍቱ የመናገር ክሂል ይዘቶች የመናገር ክሂልን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ
ይዘቶች የድግግምሽ መጠን የቀረቡ ጥያቄዎች ብዛት
የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መማሪያ የአማርኛ ቋንቋ
መፅሃፍ መፅሃፍ መማሪያ
መፅሃፍ
በቁጥ በመቶ በቁጥ በመቶ በቁጥ በመቶ በቁጥ በመቶ በቁጥ በመቶ በቁጥ በመቶ
ር ኛ ር ኛ ር ኛ ር ኛ ር ኛ ር ኛ
ውይይት 17 42.50 6 27.30 23 42.50 0 0 2 25% 1 25%
% % %
ጭውውት 4 10% 3 13.60 7 13% 0 0 0 0 1 25%
%
ክርክር 4 10% 3 13.60 7 13% 1 33.30 3 37.50 0 0
% % %
የቅስቀሳና 1 2.50% 5 22.70 6 11% 1 33.30 1 12.50 1 25%
የማነቃቂያ % % %
ንግግር
በተለያዩ ርዕሰ 8 20% 0 0 0 0 0 0 1 12.50 0 0
ጉዳዮች ላይ %
ንግግር ማድረግ
የፅሁፍን/የንግግ 5 12.50 4 18.20 9 16.70 0 0 0 0 0 0
ርን መልዕክት % % %
በመረዳት በቃል
ማብራራት
ግጥምን ወይም 1 2.50% 0 0 1 1.90% 0 0 0 0 0 0
ዝርው ፅሁፍን
አጥንቶ በቃል
ማቅረብ
የንግግር 0 0 1 4.50% 1 1.90% 1 33.30 1 12.50 1 25%
ዝግጅትና % %
አቀራረብ
መመሪያ
ድምር 40 100% 22 100% 54 100% 3 100% 8 100% 4 100%

81
አባሪ ሶስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የማንበብ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የማንበብ የመማሪያ መፃህፍቱ የማንበብ ክሂል ይዘቶች የድግግምሽ የማንበብ ክሂልን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ የቀረቡ
ክሂል መጠን ጥያቄዎች ብዛት
ይዘቶች የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መፅሃፍ መማሪያ መፅሃፍ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ
በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ
የቀደመ 29 22% 28 22.05% 57 21.92% 1 5.30% 1 7.70% 0 0
እውቀትን
ተጠቅሞ
መተንበይ
በምክንያትና 0 0 0 0 0 0.00% 0 0 0 0 1 7.10%
ውጤት
መካከል
ያለን ትስስር
መረዳት
የቃላትንና 42 32% 17 13.39% 59 22.69% 0 0 3 23% 0 0
ሀረጋትን
አውዳዊ ፍቺ
መረዳት
ዋና ዋና 2 2% 0 0 2 0.77% 0 0 0 0 0 0
ሀሳቦችን
መለየት
ምክንያትን 1 1% 0 0 1 0.38% 0 0 0 0 0 0
ከውጤት
መለየት
የግል 0 0 5 3.94% 5 1.92% 1 5.30% 1 7.70% 0 0
አስተያየትን
ከእውነታ
መለየት
ምንባቡ 5 4% 5 3.94% 10 3.85% 9 47.30% 1 7.70% 1 7.10%
የቀረበበትን
ድምፀት
መለየት
የፅሁፉን 38 29% 46 36.22% 84 32.31% 6 31.50% 4 30.80% 9 64.30%
ጭብጥ
መረዳት

82
በሀሳቦች 4 3% 0 0 4 1.54% 1 5.30% 1 7.70% 0 0
መካከል
ያለን ልዩነት
መረዳት
የፀሃፊውን 0 0 0 0 0 0.00% 1 5.30% 1 7.70% 2 14.30%
አመለካከት
መረዳት
ከምንባብ 1 1% 0 0 1 0.38% 0 0 0 0 0 0
ውስጥ
አያያዦችን
ማውጣት
ከምንባቡ 11 8% 25 19.69% 36 13.85% 0 0 0 0 0 0
ለወጡ
ቃላት
መዝገበ
ቃላት
ተጠቅሞ
ፍቺ
መስጠት
የንባብ 0 0 1 0.79% 1 0.38% 0 0 1 7.70% 1 7.10%
አይነቶችን
መለየት
ድምር 133 100% 127 100% 260 100.00% 19 100% 13 100% 14 100%

አባሪ አራት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የመፃፍ ክሂል ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የመፃፍ ክሂል የመማሪያ መፃህፍቱ የመፃፍ ክሂል ይዘቶች የድግግምሽ የመፃፍ ክሂልን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ የቀረቡ
ይዘቶች መጠን ጥያቄዎች ብዛት
የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መፅሃፍ መማሪያ መፅሃፍ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ
በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ
አንቀፅ መፃፍ 11 10.40% 7 16.30% 18 12% 3 23% 1 6.30% 4 30.80%
የስርዓተ 1 0.90% 0 0 1 0.70% 1 7.70% 1 6.30% 1 7.70%
ነጥቦችን

83
አገልግሎት
እየለዩ መፃፍ
ቃላትንና 1 0.90% 0 0 1 0.70% 1 7.70% 2 12.50% 1 7.70%
ዓ.ነገሮችን
በሀሳብ ቅደም
ተከተል
አደራጅቶ መፃፍ
በቅንፍ ውስጥ 5 4.70% 6 14% 11 7.40% 0 0 0 0 0 0
ያለን ቃል ቅርፅ
በማስተካከል
እንደገና መፃፍ
ያልተሟሉ 5 4.70% 0 0 5 3.40% 0 0 0 0 0 0
የግጥምስንኞችን
እያሟሉ መፃፍ
ድርሰት መፃፍ 3 2.80% 3 7% 6 4% 2 15.40% 3 18.80% 0 0
መንስኤና 7 6.60% 0 0 7 4.70% 1 7.70% 1 6.30% 1 7.70%
ውጤትን እየለዩ
መፃፍ
ዘገባ መፃፍ 0 0 2 4.70% 2 1.30% 0 0 1 6.30% 0 0
ደብዳቤ መጻፍ 6 5.70% 1 2.30% 7 4.70% 0 0 1 6.30% 0 0
ቃለጉባኤ መፃፍ 0 0 1 2.30% 1 0.70% 2 15.40% 1 6.30% 1 7.70%
በዓ.ነገር ውስጥ 5 4.70% 5 11.60% 10 6.70% 1 7.70% 0 0 0 0
ለተሰመረባቸው
ቃላት ፍቺ መፃፍ
በዓ.ነገርና 21 19.80% 3 7% 24 16% 2 15.40% 2 12.50% 2 15.40%
በአንቀፅ ውስጥ
የተጓደሉ ስርዓተ
ነጥቦችን በክፍት
ቦታዎች ላይ
መፃፍ
የቃላትን ፍቺ 6 5.70% 6 14% 12 8% 0 0 0 0 0 0
የሚያሳይ ዓ.ነገር
መፃፍ
አያያዥና 18 17% 5 11.60% 23 15.40% 0 0 0 0 1 7.70%
መሸጋገሪያ
ቃላትን ተጠቅሞ
ዓ.ነገር ማያያዝ
የአንድንፅሁፍ 7 6.60% 2 4.70% 9 6% 0 0 2 12.50% 0 0
ሀሳብ ተረድቶ
በራስ አባባል
መፃፍ
ቃላት ሲጠብቁና 10 9.40% 0 0 10 6.70% 0 0 1 6.30% 2 15.40%

84
ሲላሉ
የሚሰጡትን
ፍቺ መፃፍ
የአንድን ፅሁፍ 0 0 2 4.70% 2 1.30% 0 0 0 0 0 0
ሀሳብ ጥንካሬና
ድክመት መፃፍ
ድምር 106 100% 43 100% 149 100% 13 100% 16 100% 13 100%

አባሪ አምስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የሰዋስው ዘርፍ ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የሰዋስው የመማሪያ መፃህፍቱ የሰዋስው ዘርፍ ይዘቶች የድግግምሽ ሰዋስውን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ የቀረቡ ጥያቄዎች
ዘርፍ መጠን ብዛት
ይዘቶች የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መፅሃፍ መማሪያ መፅሃፍ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ
በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ
የአያያዥ 8 4% 0 0 8 2% 1 2.70% 0 0 0 0
ቃላትና
ሀረጋትን
ተግባር
መለየት
ውስብስብ 0 0 10 5.20% 10 2.70% 0 0 1 4% 0 0
ዓነገሮችን
በመነጣጠል
ተራ
ዓ.ነገሮችን
መፃፍ
ውስብስብ 0 0 9 4.70% 9 2.40% 1 2.70% 2 7% 0 0
ዓ.ነገር
መመስረት
ጥገኛ 6 3% 0 0 6 1.60% 0 0 3 11% 0 0
ምዕላዶችን
ተጠቅሞ
ዓ.ነገር
መመስረት
ዓ.ነገሮችን 0 0 12 6.20% 12 3.20% 0 0 4 14% 0 0

85
አወንታዊና
አሉታዊ
በማለት
መለየት
የዓ.ነገር 6 3% 12 6.20% 18 4.80% 2 5.40% 0 0 3 10.30%
ስልቶችን
ተጠቅሞ
ዓ.ነገር
መመስረት
በዓ.ነገር 13 6.50% 0 0 13 3.50% 0 0 1 4% 0 0
ውስጥ
የቃል
ክፍሎችን
ሙያ
መለየት
በዓ.ነገር 10 5% 0 0 10 2.70% 0 0 0 0 0 0
ውስጥ ያሉ
ቃላትን
የቃል ክፍል
መለየት
የቃላትን 23 11.40% 22 11.40% 45 12% 3 8% 0 0 5 17.20%
ነፃና ጥገኛ
ምዕላድ
መለየት
በዓ.ነገር 5 2.50% 0 0 5 1.30% 1 2.70% 2 7% 1 3.40%
ውስጥ ያሉ
ሰዋስዋዊ
ስህተቶችን
መለየት
ለቃላት 23 11.40% 12 6.20% 35 9.30% 2 5.40% 0 0 1 3.40%
እማሬያዊና
ፍካሬያዊ
ፍቺ
መስጠት
የሐረግ 11 5.50% 24 12.40% 35 9.30% 0 0 3 11% 3 10.30%
አይነቶችን
መለየት
ለቃላት 36 17.90% 17 8.80% 53 14% 5 13.50% 2 7% 2 6.90%
ተመሳሳይና
ተቃራኒ ፍቺ
መስጠት
በዓ.ነገር 10 5% 0 0 10 2.70% 0 0 0 0 0 0

86
ውስጥ
የቃል
ክፍሎችን
ቦታ መለየት
የተለያዩ 23 11.40% 0 0 23 6% 0 0 0 0 0 0
ሐረጋትን
መመስረት
ዓ.ነገሮችን 5 2.50% 11 5.70% 16 4.30% 0 0 0 0 2 6.90%
ተራ እና
ውስብስብ
በማለት
መለየት
በቃላት 10 5% 6 3% 16 4.30% 4 10.80% 3 11% 0 0
ውስጥ
የቅጥያ
ምዕላዶችን
ሙያ
መለየት
የቃላትን 0 0 5 2.60% 5 1.30% 5 13.50% 2 7% 4 13.80%
የቃል ክፍል
መለየት
በዓ.ነገር 0 0 10 5.20% 10 2.70% 3 8% 0 0 0 0
ውስጥ
የሀረጎችን
አይነት
መለየት
ከአንድ 0 0 21 10.90% 21 5.60% 2 5.40% 0 0 1 3.40%
የቃል ክፍል
ሌላ የቃል
ክፍል
መመስረት
ነፃ እና ጥገኛ 0 0 8 4% 8 2% 0 0 2 7% 0 0
ምዕላዶችን
ተጠቅሞ
ቃል
መመስረት
የቋንቋን 12 6% 14 7.30% 26 6.90% 7 18.90% 3 11% 5 17.20%
ምንነትና
ባህርያት
መግለፅ
የቃላትን 0 0 0 0 0 0 1 2.70% 0 0% 0 0
ሰዋስዋዊ

87
ስህተት
መለየት
የቅጥያ 0 0 0 0 0 0 0 0 0 0% 2 6.90%
ምዕላዶችን
ተግባር
መለየት
ድምር 201 100% 193 100% 375 100% 37 100% 28 100% 29 100

አባሪ ስድስት፡- በፈተናው እና በመማሪያ መፅሀፉ የተካተቱ የስነፅሁፍ ዘርፍ ንዑሳን ይዘቶች
የድግግሞሽ መጠን

የስነፅሁፍ የመማሪያ መፃህፍቱ የስነፅሁፍ ዘርፍ ይዘቶች የድግግምሽ ስነፅሁፍን በተመለከተ በሞዴል ፈተናዎቹ የቀረቡ ጥያቄዎች
ዘርፍ መጠን ብዛት
ይዘቶች የዘጠነኛ ክፍል የአስረኛ ክፍል የዘጠነኛ እና በ2009 ዓ.ም በ2010 ዓ.ም በ2011 ዓ.ም
የአማርኛ ቋንቋ የአማርኛ ቋንቋ የአስረኛ ክፍል
መማሪያ መፅሃፍ መማሪያ መፅሃፍ የአማርኛ ቋንቋ
መማሪያ መፅሃፍ
በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ በቁጥር በመቶኛ
ስነቃል 23 29.90% 49 48.50% 72 40.40% 11 42.30% 3 20.00% 6 30%
ግጥም 13 16.90% 9 8.90% 22 12.40% 1 3.80% 3 20.00% 5 25%
ልቦለድ 7 9% 1 1% 8 4.50% 3 11.50% 2 13.33% 3 15%
ተውኔት 1 1.30% 0 0 1 0.60% 2 7.70% 0 0.00% 1 5%
ለዛ ያላቸው 33 42.90% 42 41.60% 75 42% 9 34.60% 7 46.67% 5 25%
የቋንቋ
አጠቃቀሞች
(ፈሊጣዊ
አነጋገር፣ ቅኔ
እና ዘይቤ)
ድምር 77 100% 101 100% 178 100% 26 100% 15 100% 20 100%

88
አባሪ ሰባት፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2009 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና

መመሪያ አንደ፡- ቀጥሎ የቀረበውን ምንባብ በጥሞና አንብባችሁ ከተ.ቁ. 1-10 ድረስ ለቀረቡት
ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ አጥቁር/ሪ፡፡

ምንባብ

ዘገባ ትክክለኛነቱ እና ሀቀኛነቱ ሊመዘን ወይም ሊመረመር የሚችል የፅሁፍ አይነት ነው፡፡ ስለሆነም በዘገባ
የሚቀርብ መረጃ ለፈተና፣ በምርምር በሚመለከተው ባለስልጣን ወይም በሌሎች ምንጮች ሊጣራ ወይም ሊረጋገጥ
ይችላል፡፡ ቸልተኝነት ያጠላበት ግላዊ አስተያት ወይም በይሆናል ላይ የተመሰረተ አገላለፅ በጠንካራ መረጃ
ካልተደገፈ በስተቀር በዘገባ ቦታ አይኖረውም፡፡ እነዚህም የተሰበሰቡ መረጃዎች በጥንቃቄ ይተነተናሉ፡፡ ከዚህ በኋላ
ዘገባው በሚፃፍበት ጊዜ ዘጋቢው የግል አስተያየቱን ከሚቀርበው እውነታ ጋር ሳያማታ በጥንቃቄ እየለየ
ያሰፍራል፡፡ በመጨረሻም በበቂ መረጃ ላይ ተመርኩዞ መደምደሚያውን ያቀርባል፡፡ በዚህ አይነት መንገድ
የሚዘጋጅ ዘገባ ትክክለኛና ሀቀኛ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ትክክለኛ ወይም ሀቀኛ የሚያሰኘውም በውስጥ
ያዘለውን ሀሳብ አስመልክቶ ምን ያህል እውነት ነው? ተብሎ ሲፈተሽና እርግጠኛነቱ ሲጣራ ነው፡፡ ለዚህ ነው በቂ
መረጃ ያላሰባሰበ ዘጋቢ ለድምዳሜ መቸኮል የለበትም የሚባለው፡፡

ዘገባ ተጨባጭ እንዲሆን በተጠያቂ እንጅ ስሜታዊ መሆን አይኖርበትም፡፡ ለዚህም ይረዳ ዘንድ ዘገባው የዘጋቢውን
ግላዊ ስሜት ወይም እምነት ጨርሶ በማያመላክት መንገድ ሊቀርብ ይገባል፡፡ የዘጋቢው ዓላማ ተጠየቃዊነት ባለው
መንገድ ዘገባውን ሌሎች በተጨባጭ ሁኔታውን እንዲረዱ በማገዝ ላይ ማተኮር ይኖርበታል፡፡ ለዘገባው
ተጨባጭነትም ሲባል በተቻለ መጠን ቃላትን በዕማሬያዊ ፍቻቸው መጠቀም መልካም ነው፡፡

በቋንቋ አጠቃቀም ረገድ ዘገባ ከከባድ፣ ከተሰለቹና ከአላስፈላጊ የተውሶ ቃላት መጠበቅ እንዳለበት ሁሉ፣ የሙያ
ቃላትንም አጠቃቀም እንዲሁ በጥንቃቄ ሊይዝ ይገባል፡፡ ከቃላት ምርጫ ባሻገር ዘገባ የዓ.ነገር አወቃቀርን ስርዓት
ጠብቆ መገኘት ይኖርበታል፡፡ ከሰዋስው ግድፈት የጠራ ጥሩ ቋንቋ የግልፅ ዘገባ መሰረቱ ነው፡፡ የዓረፍተ ነገሮች
ሰዋሰዋዊ መሆኑ ብቻም ሳይሆን፣ በዘገባ ውስጥ የሚኖራቸው የአቀነባበር ስርዓትና ግጥምጥምነትም ለዘገባው
ግልፅነት መሟላት ጉልህ ሚና ይኖራቸዋል፡፡ ተጠየቃዊ ቅደም ተከተልን ጠብቆ የሚፃፍ ዘገባ መጀመሪያ ምን
እንደተከናወነ በማስከተል ምን እንደተፈፀማና በመጨረሻም እንዴት እንደተጠቃለለ ስለሚያመለክት ግልፅነቱ
የሚያጠያይቅ አይሆንም፡፡

/አለም እሸቱ፣ መሰረታዊ የምርምርና የዘገባ አፃፃፍ 1992 ዓ.ም ከገፅ 1-11 የተወሰደ/

1. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል በዘገባ ፅሁፍ ቦታ የሚሰጠው የትኛው ነው?


ሀ. በበቂ መረጃ ላይ የተመረኮዘ መደምደሚያ

89
ለ. ግላዊ አስተያየት ወይም በይሆናል ላይ የተመሰረተ አገላለፅ
ሐ. የዘጋቢውን ግላዊ ስሜት እምነት የሚያመለክት ማረጋገጫ
መ. ምናባዊና በጥልቀት ስሜት የተሞላ አቀራረብ
2. ለዘገባ ፅሁፍ ከቃላት ፍካሬያዊ ፍቺ ይልቅ እማሬያዊ ፍቺ መጠቀም መልካም ነው፡፡ ሲባል ምን
ለማለት ተፈልጎ ነው፡፡
ሀ. ዘይቤያዊ አገላለፅና ዘገባ ያላቸውን አስፈላጊነት ለመግለፅ ነው፡፡
ለ. የቃላትን ቀጥተኛ ፍቺ መሰረት ማድረግን ለመግለፅ ነው፡፡
ሐ. የቃላትን አውዳዊ ፍቺ መነሻ ማድረግን ለመግለፅ ነው፡፡
መ. የመዝገበ ቃላትን ፍቺ ብቻ ሳይሆን ፈሊጣዊ አባባሎችን የመጠቀምን አስፈላጊነት ለመግለፅ ነው፡፡
3. በምንባቡ ሁለተኛው አንቀፅ የመጀመሪያው ዓ.ነገር በሌላ አባባል ሲገለፅ ከቀረቡት አማራጮች መካከል
የበለጠ የሚስማማው የቱ ነው?
ሀ. ተጠየቃዊ የሆነ ዘገባ ተጨባጭና ስሜታዊ አይደለም
ለ. ስሜታዊ መሆን ስለሚኖርበት ተጠየቃዊ ዘገባ ተጨባጭ ነው
ሐ. ከስሜታዊነት ርቆ ተጠየቃዊ ሆኖ የቀረበ ዘገባ ተጨባጭ ነው
መ. ዘገባ ተጠየቃዊ እንዲሆን ተጨባጭና ስሜታዊ መሆን አይኖርበትም፡፡
4. የዓረፍተ ነገሮች ሰዋስዋዊ መሆን የሚለው ሀረግ ምንን ያመለክታል?
ሀ. ባለቤትና ማሰሪያ አንቀፅን ያሟሉ ዓ.ነገሮችን ለማመልከት ነው፡፡
ለ. የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም አግባብነትን ለማመልከት ነው፡፡
ሐ. ተገጣጥመው አንቀፅ የመሰረቱ ዓ.ነገሮችን ለማመልከት ነው፡፡
መ. የቋንቋውን ስርዓት ጠብቀው መገኘትና መልዕክትን በአግባቡ ማስተላለፍ መቻላቸውን ነው፡፡
5. በምንባቡ ውስጥ እንደቀረበው ምን ያህል እውነት ነው የሚፈተሸው ምንድን ነው?
ሀ. የፀሃፊው ችሎታና የአፃፃፍ ስልት
ለ. ውበት ያለው ወይም የሌለው ፅሁፍ መሆን
ሐ. የዘገባን ባህርያት በተለይም ስሜታዊነትን ያሟላ ፅሁፍ መሆኑን
መ. በዘገባው የተንፀባረቀውን የድምዳሜ ሀሳብ እርግጠኝነት
6. በምንባቡ ውስጥ የሙያ ቃላትንም አጠቃቀም በጥንቃቄ ሊይዝ ይገባል፡፡ ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ለሙያ አጋሮች የሚፃፍ ዘገባ የሙያ ቃላትን ይዞ መገኘት ስለሌለበት ነው፡፡
ለ. የግልፅነት ጉድለት ሊያስከትል አይችልም ለማለት ነው፡፡
ሐ. የዘገባው አንባቢዎች ወይም አድማጮች እነማን እንደሆኑ መሌት አለበት ለማለት ነው፡፡
መ. የሙያ ቃላትን ፈፅሞ መጠቀም አያስፈልግም ለማለት ነው፡፡
7. በቋንቋ አተቃቀም ረገድ ዘገባ ከከባድ ቃላት መጠበቅ ያለበት ለምንድን ነው?
ሀ. ዘገባውን ብቻ ስለሚያስመሰግኑ ለ. የዘገባውን ሀሳብ ስለሚያጨልሙ
ሐ. በፍጥነት ለሚከናወን ንባብ ስለሚያግዙ መ. ለዘገባው የሚሰጠው ቦታ ትልቅ እንዲሆን
ስለሚያደርጉ
8. በምንባቡ መሰረት ከሚከተሉት አንዱ ስለዘገባ ትክክል አይደለም፡፡

90
ሀ. ዘገባ ግልፅ ሆኖ የመገኘቱ ጉዳይ ብቻ ተነባቢነትን ያስገኝለታል፡፡
ለ. ግልፅ ዘገባ የቀጥተኛ አስተሳሰብ ውጤት ነው፡፡
ሐ. ወቅታዊነት የዘገባ ባህርይ ነው፡፡
መ. ዘገባ የጉዞ ላይ ፅሁፍ ነው፡፡
9. ትክክለኛውን የዘገባ አዘገጃጀት ቅደም ተከተል የጠበቀው አካሄድ ከሚከተሉት የትኛው ነው?
ሀ. መረጃዎችን በጥንቃቄ መተንተን፣ በበቂ ጭብጦች በመንተራስ መደምደሚያውን ማቅረብ፣ ተጨባጭና
ትክክለኛ መረጃዎችን መሰብሰብ፤ እውነታንና የግል ስሜትና እየለዩ ውጤቱን መመዝገብ፡፡
ለ. ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰብሰብ፤ እውነታንና የግል ስሜትና እየለዩ ውጤቱን መመዝገብ፣
መረጃዎችን በጥንቃቄ መተንተን፣በበቂ ጭብጦች በመንተራስ መደምደሚያውን ማቅረብ፣
ሐ. በበቂ ጭብጦች በመንተራስ መደምደሚያውን ማቅረብ፣ እውነታንና የግል ስሜትና እየለዩ ውጤቱን
መመዝገብ፣ ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰብሰብ፤ መረጃዎችን በጥንቃቄ መተንተን፣
መ. እውነታንና የግል ስሜትና እየለዩ ውጤቱን መመዝገብ፣ ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃዎችን
መሰብሰብ፤ መረጃዎችን በጥንቃቄ መተንተን፣በበቂ ጭብጦች በመንተራስ መደምደሚያውን ማቅረብ፣
10. ከሚከተሉ አንዱ ስለዘገባ ትክክል ነው፡፡
ሀ. በዘገባ የሚቀርብ መረጃ በሚመለከተው አካል ሊረጋገጥ ይችላል፡፡
ለ. ዘገባ ምናባዊ ነው፡፡
ሐ. ዘገባ የአንባቢን ወይም የአድማጭን ስሜት የመመሰጥ አላማ የለውም፡፡
መ. ሁሉም ትክክል ናቸው

መመሪያ ሁለት፡- ከተራ ቁጥር 11-85 ላሉ ጥያቄዎች እንዳጠያየቃቸው ትክክለኛውን መልስ


በመምረጥ መልሱ፡፡
11. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ከቋንቋ ባህርያት አንፃር ትክክል አይደለም፡፡
ሀ. ከአንደበት የሚፈልቁ ድምፆች ሁሉ ስለሚያግባቡ ቋንቋ ዘፈቀዳዊ ነው፡፡
ለ. ውሰት የቋንቋዎች ሁሉ የጋራ ባህርይ ነው፡፡
ሐ. ከጊዜና ከቦታ ክልል ውጭ መልዕክትን በላቀ ደረጃ በማስተላለፍ ቋንቋ ረቂቅ ነው፡፡
መ. ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡
12. ከሚከተሉት ውስት ሥለቋንቋ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከሰው ልጅ በስተቀር ቋንቋ ያለው ሌላ ፍጡር የለም፡፡
ለ. ቋንቋ ሰዎች የሚማሩት እንጂ በተፈጥሮ የሚያገኙት አይደለም፡፡
ሐ. ሁሉም ቋንቋዎች የተናጋሪዎቻቸውን ባህል በመግለፅ እኩል ናቸው፡፡
መ. ሁሉም ትክክል ናቸው፡፡
13. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ስለቋንቋ ትክክል አይደለም፡፡
ሀ. ውሰት የቋንቋን ማህበራዊ ስርዓት የሚጠይቅ ነው፡፡
ለ. በዓለም ላይ ያለውን ነገር ሁሉ መግለፅ የሚችል አንድም ቋንቋ የለም፡፡

91
ሐ. የማህበረሰብ አስተሳሰብ እያደገ በሄደ ቁጥር ቋንቋም ያድጋል፡፡
መ. አንድ ቋንቋ ተናጋሪውን የማግባባት አቅም ቢነረውም ምሉዕነት ላይኖረው ይችላል፡፡
14. መለኮታውያን ስለ ቋንቋ አመጣጥ የሚከተሉት የትኛውን ነው?
ሀ. ከዘር በውርስ የተገኘ ነው፡፡
ለ. ከሰማያዊ ሀይል የተሰጠ ፀጋ ነው፡፡
ሐ. የምርምር ውጤት ነው፡፡
መ. የአዝጋሚ ለውጥ ሂደት ውጤት ነው፡፡
15. የሰው ልጅ ቋንቋ ይዞ ይወለዳል፡፡ የሚለው ሀሳብ ከሚከተሉት ውስጥ የየትኛው ሊቃውንት መላምት
ነው?
ሀ. የመለኮታውያን ለ. የቁስ አካላውያን
ሐ. የስነሰብ ተመራማሪዎች መ. ለናሐ መልስ ናቸው፡፡
16. ከሚከተሉት ውስጥ ቁስ አካላውያን ስለቋንቋ የትመጣነት ከሚያስረዱበት የትኛው ትክክል ነው?
ሀ. የሰው ልጅ ቋንቋን ያገኘው ባላሰበውና በልተገነዘበው መንገድ ነው
ለ. የቋንቋ አመጣጥ ከተግባርና ከማህበራዊ መግባባት ፍላጎት ጋር ማያያዙ
ሐ. ሀናለ መልስ ናቸው
መ. መልስ አልተሰጠም
17. ከሚከተሉት ውስጥ የቋንቋ መሰረታዊ ባህርይ ያላሆነው የቱ ነው?
ሀ. ዘፈቀዳዊነት ለ. ረቂቅነት ሐ. በፀጋ መገኘት መ. በትምህርት መገኘት
18. "መፅሃፎቻችን" በሚለው ቃል ውስጥ ያሉት ምዕላዶች ከይዘት ረገድ ምንን ያመለክታሉ?
ሀ. ድርጊትና ጉዳይን ለ. አይነትና መጠንን
ሐ. በዛትንና ባለንብረትነትን መ. ብዛትና ተግባርን
19. ከሚከተሉት ተጣማሪዎች አንዱ ትክክል አይደለም፡፡
ሀ. ቅፅል------ክፉኛ ለ. ግስ----ደረሰ ሐ. ስም--------ጤዛ መ. ተውሳከ ግስ------ገና
20. አንድን ዓረፍተ ነገር አሟልቶ ለመመስረት የግድ የማይቀሩ የቃል ክፍሎች የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ግስና መስተዋድድ ለ. ቅፅልና ተውሳከ ግስ ሐ. ስምና ቅፅል መ. ስምና ግስ
21. አለሙ ከበደን አስጠናና ፈተና ፈተና ፈተነው፡፡ ዓ.ነገሩ ከየትኛው ይመደባል?
ሀ. ከጥያቄያዊ ለ. ከትዕዛዛዊ ሐ. ከሀተታዊ መ. ከአሉታዊ
22. ከሚከተሉት አንዱሰዋስዋዊ ስህተት ይታይበታል፡፡
ሀ. ልጅነት ለ. ቀናቶች ሐ. ሰማያዊ መ. ዛፎቻችን
23. ከፊት የቀረበው ፅንሰ ሀሳብ የኋለኛውን የሚያጎለብትበት የአንቀፅ ስልት-------ነው፡፡
ሀ. የምስያ ስልት ለ. የማዋገን ስልት ሐ. የብያኔ ስልት መ. የምክንያትና ውጤት ስልት
24. መስራት የመናገርን ያህል ቀላል አይሆንም፡፡ የሚለውን ሀሳብ የማይተካው የትኛው ዓ.ነገር ነው?
ሀ. መስራት ከመናገር ከብዶ መታየት የለበትም፡፡ ለ. መናገር ከመስራት ይልቅ የቀለለ ነው፡፡
ሐ. መስራት ከመናገር ይበልጥ ፈታኝ ነው፡፡ መ. የመናገርን ያህል መስራት ቀላል አይደለም፡፡

92
25. የጊዜ አጠቃቀምና የቀጠሮ አከባበር ጉድፋችን በብዙዎቻችን ዘንድ ጎልቶ ይታያል፡፡ የተሰመረበት ቃል
ትርጉም-------ነው፡፡
ሀ. ጥራጊ ለ. ቆሻሻ ሐ. ጉድለት መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡
26. ጠይም ፀጉረ ዞማ ሰው በጣም እወዳለሁ፡፡ በሚለው ዓረፍተ ነገር የስም ገላጭ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ጠይም ፀጉረ ዞማ ለ. ጠይም ፅጉር
ሐ. ዞማ ሰው መ. ጠይም ፀጉረ ዞማ ሰው
27. ከሚከተሉት አማራጮች ትክክለኛውን አፃፃፍ የያዘው የትኛው ነው?
ሀ. የሚታይ እንዲሁም የማይበላ ፍሬ ለ. የሚታይ እንጅ የማይበላ ፍሬ
ሐ. የሚታይ ነገር ግን የማይበላ ፍሬ መ. የሚታይም የማይበላም ፍሬ
28. ከሚከተሉት ውስጥ ሰዋስዋዊ ስህተት የማይታይበት ዓ.ነገር የቱ ነው?
ሀ. የደጃ.ባልቻ አባነፍሶ የወጣት የሴቶች ማህበር በቅርብ ይቋቋማል፡፡
ለ. የደጃ.ባልቻ አባነፍሶ የወጣት ሴቶች ማህበር በቅርብ ይቋቋማል፡፡
ሐ.የደጃ.ባልቻ አባነፍሶ የወጣት የሴቶች ማህበር በቅርብ ይቋቋማል፡፡
መ.የደጃ.ባልቻ አባነፍሶ የሴቶች እና የማህበር በቅርብ ይቋቋማል፡፡
29. አስተማሪው በትርፍ ጊዜው አትክልት ይኮተኩታል፡፡ በተሰመረበት ቃል ላይ ያለው "ው"------ነው፡፡
ሀ. የባለቤት ገላጭ ለ. ፆታ አመልካች ሐ. እምርነት አመልካች መ. ለናሐ መልስ ናቸው
30. "ሰዎቻችንን" የሚለው ቃል በምዕላድ ተከፋፍሎ ሲፃፍ-------ነው፡፡
ሀ. ሰው-ዎች-ኣችን-ን ለ. ሰው-ኦቻ-ችን-ን ሐ. ሰው-ኦች-አችን-ን መ. ሰው-ዎች-አች-ን
31. ዳንኤል መኪና እንደገዛ ሰማሁ፡፡ በሚለው ዓ.ነገር የተሰመረበት ቃል------ነው፡፡
ሀ. ቅፅላዊ ሀረግ ለ. ስማዊ ሀረግ ሐ. የስም ገላጭ መ. የግስ ገላጭ
32. "ታምኜ" ከሚለው ቃል ሊመሰረት የሚችለው የሶስተኛ መደብ የቃል ቅርፅ የትኛው ነው?
ሀ. ታምነው ለ. ታምነን ሐ. ታምናችሁ መ. ታምነህ
33. እስካሁን ታላላቅ ሁለት የዓለም ጦርነቶች መካሄዳቸውን ታሪክ ያስገነዝባል፡፡ በተሰመረበት ቃል ውስጥ
ያለው ነፃ ምዕላድ የትኛው ነው?
ሀ. ጦር ለ. ጦርነት ሐ. ጦሮች መ. ጦረኞች
34. ከመጠን በላይ መመገብ ቁንጣን ያስይዛል፡፡ በተሰመረበት ቃል ላይ መድረሻ ምዕላድ ሆኖ ቢቀጠል ቃሉን
ቅፅል ሊያደርገው የሚችለው የትኛው ነው?
ሀ. -ነት ለ. -ኦች ሐ. -ኡ መ. -ኣም
35. ለትምህርት ቤታችን ጥሩ ዝና እያንዳንዳችን ጠንክረን መስራት ይኖርብናል፡፡ በተሰመረበት ቃል ውስጥ
ያለው የምዕላድ ብዛት------ ነው፡፡
ሀ. ሁለት ለ. ሶስት ሐ. አራት መ. አምስት
36. ከሚከተሉት ውስጥ የዕርባታ ቅጥያ ምዕላድ ያለው ቃል የትኛው ነው?
ሀ. ዝናባማነት ለ. ቁሳዊ ሐ. ዘመኑ መ. ብዕረኛ
37. ከሚከተሉት ቃላት መካከል ቅፅል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ወላድ ለ. ሀዘን ሐ. ቁንፅል መ. ወልካፋ

93
38. በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ምርቃት ከፍተኛ ግምት ይሰጠዋል፡፡ የተሰመረበት ቃል ከየትኛው የቃል
ክፍል ይመደባል?
ሀ. ከስም ለ. ከግስ ሐ. ከቅፅል መ. ከተውሳከ ግስ
39. ጥበበ ከጠንካራ ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል በአብነት ትጠቀሳለች፡፡ የተሰመረበት ሐረግ
ከሚከተሉት ውስጥ ለየትኛው ምሳሌ ይሆናል?
ሀ. ለግሳዊ ሀረግ ለ. ለቅፅላዊ ሀረግ ሐ. ለመስተዋድዳዊሀረግ መ. ለተውሳከ ግሳዊ ሐረግ
40. የኢትዮጵያ ህዝቦች አለባበስ እጅግ በጣም ይማርካል፡፡ በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ የግስ ገላጩ የቱ ነው?
ሀ. እጅግ በጣም ለ. እጅግ በጣም ይማርካል
ሐ. የኢትዮጵያ ህዝቦች መ. የኢትዮጵያ ህዝቦች አለባበስ
41. ከሚከተሉት አንዱ ውስብስብ ዓ.ነገር ነው፡፡
ሀ. መፅሃፉን ከቦታው አጣሁት ለ. ሀና በርካታ የልቦለድ መፃህፍት ገዛች
ሐ. ልጁ ህመሙ የባሰበት ስላልታከመ ነው ሐ. ለጁ በአራት የሩጫ አይነቶች አንደኛ ወጣ
42. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች ውስጥ አጠራታሪ ሀሳብ ያለው በየትኛው ነው?
ሀ. በሽታው የተላለፈው በጥንቃቄ ጉድለት ይሆናል፡፡
ለ. ሰውነታችን በበሽታ እንዳይጠቃ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ይኖርብናል፡፡
ሐ. የእናት ጡት ወተት ለህፃናት እድገት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
መ. መንገዱ የተሰራው በህዝብ ተሳትፎ መሆኑ ታውቋል፡፡
43. በአንድ አንቀፅ ውስጥ የሚካተቱ ዓ.ነገሮች መሰረት የሚያደርጉት ምንን ነው?
ሀ. ምሳሌዎችን ለ. ሀይለቃልን ሐ. ማብራሪያን መ. ስዕላዊ መግለጫን
44. ከሚከተሉት የቃለ ጉባኤ ክፍሎች ውስጥ መጨረሻ የሚሆነው የትኛው ነው፡፡
ሀ. የስብሰባው ርዕስ ለ. የስብሰባው ተሳታፊዎች ዝርዝር
ሐ. የስብሰባው ባታ መ. የስብሰባው መወያያ አጀንዳ
45. አንድን አንቀቀፅ አንቀፅ የሚያሰኘው አብይ ጉዳይ የትኛው ነው?
ሀ. የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀሙ ትክክል መሆን ለ. የዓ.ነገሮች ስብስብ መሆን
ሐ. አንድ ሀሳብ ብቻ መግለፅ መ. ከብዙ ዓ.ነገሮች መመስረት
46. ቀጥለው ከቀረቡት አገላለፆች ለቅስቀሳ ተግባር የትኛውን በተሻለ መነሻ ሀሳብነት መውሰድ ይቻላል?
ሀ. የተጀመሩ የልማት ስራዎች ቢቋረጡ የታሪክ ተወቃሽ እንሆናለን፡፡
ለ. የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዳይቋረጡ የታሪክ ባላደራዎች መሆናችንን አውቀን እንነሳ!
ሐ. የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዳይቋረጡ የተለያዩ ስልቶችን መቀየስ አለብን፡፡
መ. የተጀመሩ የልማት ስራዎች ቢቋረጡ ኢኮኖሚያችን ላይ ተፅእኖ ያሳድራሉ፡፡
47. በምክንያትና ውጤት የተገነባው ዓ.ነገር የትኛው ነው?
ሀ. ሰፈሩ ውስጥ በተነዛው ወሬ የቤተሰቡ ሰላም ታወከ፡፡
ለ. ፖሊሶች ሰላም የማስከበር ተግባራቸውን በትጋት እያከናወኑ ነው፡፡
ሐ. ስለ ኤች አይቪ ኤዲስ አሁንም ጥንቃቄየሚጎድላቸው ሰዎች አሉ፡፡
መ. በተለያዩ ት/ቤቶች በኩረጃ ስልቶች ላይ ውይይት ተካሄድ፡፡

94
48. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ከንግግር ዝግጅት መመሪያ ውስጥ ይካተታል፡፡
ሀ. የተደራስያንን ስሜትና ፍላጎት መጠበቅ ለ. ተደራስያንን በአይን መቃኘት
ሐ. ለቃላት ምርጫ ልዩ ትኩረት መስጠት መ. የርሱን ጥልቀት መወሰን
49. ከሚከተሉት ውስጥ ያንዱ ባለቤት ማህበረሰቡ ነው፡፡
ሀ. እንቆቅልሽ ለ. ልቦለድ ሐ. ፅሁፋዊ ግጥም መ. ተውኔት
50. ቁጥብ ሆነው ሰፊ መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉ ቃላት ይበልጥ ጥቅም ላይ የሚውሉት በየትኛው
ስነፅሁፍ ነው?
ሀ. በረጅም ልቦለድ ለ. በግጥም ሐ. በአጭር ልቦለድ መ. በተውኔት
51. በተመልካች ፊት ህይዎትን በድርጊት የሚያቀርብ በመሆኑ ከሌሎች የስነፅሁፍ ዘርፎች የሚለየው
የትኛው ነው?
ሀ. ንግግር ለ. ክርክር ሐ. ተውኔት መ. ወግ
52. ኧረተው አንተ ሰው አትውረድ በደጄ፤
እንደገለባ እሳት ትጠፋለህ በጄ፡፡ ይህን ቃላዊ ግጥም የሚያንጎራጉር ሰው---------------ነው፡፡
ሀ. የደከመው ለ. የራበው ሐ. ግራ የገባው መ. የከፋው
53. ከሚከተሉት ውስጥ የስነቃል ዘርፍ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. እሰጣገባ ለ. ተረት ሐ. ምሳሌያዊ ንግግር መ. ልቦለድ
54. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በልቦለድ መቼት ውስጥ ይካተታል፡፡
ሀ. ገፀባህርያተ የሚገጥማቸው የህይዎት ውጣ ውረድ
ለ. ገፀባህርያቱ በውስጣቸው የሚያምሰላስሉት ሀሳብ
ሐ. ገፀባህርያቱ የሚገበያዩበት የመንደር ገበያ
መ. ገፀባህርያቱ ዕርስ በዕርስ የሚያደርጉት የሀሳብ ልውውጥ
55. ለተውኔትና ለረጅም ልቦለድ የጋራ የሆነው የትኛው ስነፅሁፋዊ እሳቤ ነው?
ሀ. ገቢር ለ. ታሪክ ሐ. ኮሜዲ መ. ትዕይንት
56. የአንድ ልቦለድ ደራሲ ለአንባብያን የሚያስተላልፈው መልዕክት ምን ይባላል?
ሀ. ጭብጥ ለ. አንፃር ሐ. መቼት መ. ትልም
57. አቀበት ቁልቁለት አይልም ጉልበቴ፣
ጥርሶችሽ መካከል ይሰራልኝ ቤቴ፡፡ ይህ ቃላዊ ግጥም የትኛውን ይመለከታል?
ሀ. ሰራተኛን ለ. ጀግናን ሐ. አፍቃሪን መ. ሀሜተኛን
58. የሌላ ሰውም ሆነ የራስ የህይዎት ታሪክ የሚፃፍበት ምክንያት ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ
ከነማብራሪያው ተገቢ መልስ በፅሁፍ ቢቀርብ የድርሰቱ አይነት ምን ሊሆን ይችላል?
ሀ. አመዛዛኝ ድርሰት ለ. ገላጭ ድርሰት ሐ. ተራኪ ድርሰት መ. ስዕላዊ ድርሰት
59. ከሚከተሉት ርዕሶች መካከል አመዛዛኝ ድርሰት ለመፃፍ አመቺ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ቴክኖሎጅን በመቀበል ረገድ ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ፈጣን ናቸው፡፡
ለ. የዘንድሮው የዘመን መለወጫ በዓል በድምቀት ተከበረ፡፡
ሐ. ትምህርት ለአገር ብልፅግና አስተዋፅኦ እንዳለው ምሁራን ይገልፃሉ፡፡

95
መ. የወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ለአገር ልማት እንደሚጠቅም ተገለፀ፡፡
60. ሰው ሆኖ ሳይሳሳት የሚኖር የለም፤ አልተፈጠረም------------አይፈጠርምም፡፡ ለባዶ ቦታው ተስማሚ
የሚሆነው ስርዓተ ነጥብ የቱ ነው?
ሀ. ቅንፍ ለ. አራት ነጥብ ሐ. ነጠላ ሰረዝ መ. ድርብ ሰረዝ
61. ዳኖች፣ ልጅቷ ባሏን ሸሽታ አክስቷ ዘንድ መደበቋንና -----------ይደበድበኝ ነበር---------------ብላ መናገሯን
ሰሙ በባዶ ቦታዎች ሊገባ የሚችለው ስርዓተ ነጥብ የቱ ነው?
ሀ. ድርብ ሰረዝ ለ. ነጠላ ሰረዝ ሐ. ድርብ ጥዕምርተ ጥቅስ መ. ነጠላ ትዕምርተ ጥቅስ
62. ከሚከተሉት አንዱ ተመሳሳይ የሆኑ ቃላትን ለመዘርዘር የሚያገለግል ስርዓተ ነጥብ ነው፡፡
ሀ. ነጠላ ሰረዝ ለ.ሁለት ነጥብ ሐ. አራት ነጥብ መ. ድርብ ሰረዝ
63. ደረቅ የሚለው ቃል በፍካሪያዊ ፍቹ የገባው በየትኛው ዓ.ነገር ነው?
ሀ. የእንጫቱ ደረቅነት በቀላሉ ለመጫን ጠቅሟል፡፡
ለ. የደረቀውን ልብስ በፍጥነት አስገባችው፡፡
ሐ. ደረቅ ኬክ ከባክቴርያ ነፃ ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡
መ. ደረቅ በመሆኑ ሰዎች ሊያሳምኑት አልቻሉም፡፡
64. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች መካከል አንዱ በቃሉ እማሬያዊ ፍቺ የተመሰረተ ነው፡፡
ሀ. ጣሪያው ላይ ያረፈውን ጩልሌ በድንጋይ አባረርኩት፡፡
ለ. የበሽታ አይነቶቹ በልጁ ላይ ጎጆ ሰርተዋል፡፡
ሐ. በቃሪያ እድሜው በደባል ሱሶች ተጠምዷል፡፡
ሐ. ልጅቷ ዛሬም በቤተሰቦቿ ትክሻ ላይ ናት፡፡
65. ሀገር እናት ነች፤ እየመገበቸና እያስተማረች ታሳድጋለች፡፡ የሚለው አገላለፅ ለየትኛው የዘይቤ አይነት
ምሳሌ ይሆናል?

ሀ. ተለዋጭ ለ. ሰውኛ ሐ. ግነት መ. አነፃፃሪ

66. ፊቱ ተነቅሎ የተጣለ የአረም ቅጠል ይመስላል፡፡ የቀረበበት ዘይቤ---------ነው፡፡


ሀ. ተምሳሌታዊ ለ. ተለዋጭ ሐ. አነፃፃሪ መ. ግነት
67. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ በአነፃፃሪ ዘይቤ የቀረበ ነው፡፡
ሀ. አገጩ መሬት ሊነካ ምንም አልቀረውም
ለ. አበቦቹ በመስከረም ፀሀይ ፈነደቁ
ሐ. ህይዎት ያለው በድን
መ. ልጁ እንደተቆረጠ ዛፍ ዥው ብሎ ወደቀ
68. አባይ አሁንስ ሆድህ ምናለ? ዓ.ነገሩ የቀረበው በየትኛው የዘይቤ አይነት ነው?
ሀ. እንቶኔ ለ. ሰውኛ ሐ. ግነት መ. ምፀት
69. ከልቦለድ አላባውያን ውስጥ የጀርባ አጥንት በመባል የሚታወቀው ከሚከተሉት ውስጥ የትኛው ነው?
ሀ. ጭብጥ ለ. ግጭት ሐ. ታሪክ መ. ትልም
70. ከሚከተሉት አንዱ የምክንያትና ውጤት ትስስር ያላቸውን ዓ.ነገሮች ለማያያዝ ያገለግላል፡፡

96
ሀ. ወይም ለ. በተጨማሪም ሐ. ስለዚህ መ. ቢሆንም
71. አንድ አዲስ ተገኝቶ ሌላው ግን ካረጀ፣
የሚናደው ነገር ለአዲሱ ከበጀ፣
ጠቃሚ ከሆነ ሲነቀል ሲጠፋ፣
ማፍረስም መስራት ነው ይለናል ፈላስፋ፡፡ የቀረበበት የዘይቤ አይነት---------ነው፡፡
ሀ. ሰውኛ ለ. ግነት ሐ. ተለዋጭ መ. አያዎ
72. "ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም" ለሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር አቻ ሊሆን የሚችለው
ከሚከተሉት ውስጥ የትኛው ነው?
ሀ. ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲሰበር በአንዱ ተንጠልጠል
ለ. ሁለት ብልጥ ኑግ አያደቅ
ሐ. ሁለት የተመኘ አንድም አላገኘ
መ. ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት
73. አትቁም ያሉት ለማኝ ከሰጡት እኩል ነው፡፡ ለሚለው ምሳሌያዊ ዓነጋገር በትርጉም አቻ የሚሆነው ------
--ነው፡፡
ሀ. እሳትና ድሃ ሲነኩት አይወድም ለ. ካላዩ አይነዱ ካለሰሙ አይቆጩ
ሐ. ከአነጋገር ይፈረዳል ከአያያዝ ይቀደዳል መ. ከረባ ግብር ይሻልል ጦም ማደር
74. ደባ ራሱን ስለት ደጉሱን፡፡ ለሚለው ሚሳሌያዊ አነጋገር ትርጉም ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ተንኮለኛ በተንኮለኛ ይጠፋል ለ. ለድግስ ስለት ያለው ቢላዋ ይመረጣል
ሐ. ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ ሐ. የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሊጥ
75. የእናታቸው አንጀት ጥኑ መሆን ልጆቻቸውን አስገርሟቸዋል፡፡ ለተሰመረበት ፈሊጣዊ አነጋገር ፍቺ
ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ጨካኝ ለ. ተናዳጅ ሐ. ጎበዝ መ. የዋህ
76. ሰዎቹ ሆድና ጀርባ ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ ለተሰመረበት የፈሊጥ ፍቺ ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ኋላ እና ፊት ለ. አጠገብ ላጠገብ ሐ. ተቀያይመዋል መ. ተዛዝለዋል
77. "አስተማረ" ከሚለው ግስ ሊመሰረት የሚችል አርዕስታዊ ስም--------ነው፡፡
ሀ. ማስተማር ለ. መማር ሐ. ትምህርት መ. አስተማሪ
78. አንድ ሰው ካነበበው ፅሁፍ ማስታዎሻ ለመያዝ ከሌሎች አስቀድሞ የሚከናወነው ተግባር-------ነው፡፡
ሀ. ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን ብቻ መርጦ መያዝ
ለ ማስታዎሻውን ለተገቢው ባለማዋል
ሐ. ሀሳቡን ሰብስቦ በሚነበበው ነገር ላይ ማተኮር
መ. ዋና ዋና ነጥቦችን በአጭር በአጭሩ መመዝገብ
79. ክርክርን በተመለከተ ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. በተቻለ መጠን ተቃራኒውን ወገን አባብሎም ቢሆን መሸነፍ
ለ. በተከራካሪ ወገን የሚቀርበውን ሀሳብ አጥብቆ መቃዎም
ሐ. ትኩረትን በተከራካሪ ወገን ስብዕና ላይ በማድረግ አድማጭን መሳብ

97
መ. ሀሳብን ተጠየቃዊ እና አሳማኝ በሆነ መንገድ መግለፅ
80. ከሚከተሉት ውስጥ በጅምር የቀረውን ምሳሌያዊ ዓ.ነጋገር የሚያሟላው የቱ ነው?
"ሌባ ቢያዩኝ እስቅ ባያዩኝ-----------፡፡"
ሀ. እሰርቅ ለ. እላለሁ ድርቅ ሐ. እታረቅ መ. ለቀቅ
81. ፍቅር ሲጠና----------፡፡ ምሳሌያዊ አነጋገሩን ሊያሟላ የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ዳቦ ያጎራርሳል ለ. ቆሎ ያጎራርሳል ሐ. ገንፎ ያዋውጣል መ. ማር ያላልሳል
82. በኮሜድያን አለባቸው ተካ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የሰው ነጭ ታየ፡፡ ለተሰመረበት ፈሊጣዊ ዓነጋገር ፍቺ
ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. የውጭ ሰው ለ. ሀብታም ሰው ሐ. ብዙ ህዝብ መ. ተራ ሰው
83. የአቶ ደጉ ልጅ ብዕር ነቀል ሆነ፡፡ ለተሰመረበት ፈሊጣዊ ዓነጋገር ፍቺ ሊሆን የሚችለው የቱ ነው?
ሀ. ትምህርት አልገባው አለ ለ. እስክርቢቶ አልበረክትለት አለ
ሐ. ስር ነቃይ ሆነ መ. ትምህርቱን ጨረሰ
84. -----------------የመሰለ የጀበና ቡና ጠጣሁ፡፡ ለባዶ ቦታው ተስማሚ የሚሆነው የቱ ነው?
ሀ. የፈረስ ጭራ ለ. የዶሮ አይን ሐ. ኩል መ. አጫ
85. ውሃ ያድናልም ይገድላልም፡፡ ይህ ዓ.ነገር በየትኛው የዓ.ነገር ስልት የቀረበ ነው?
ሀ. በትዕዛዛዊ ለ. በሀተታዊ ሐ. በጥያቄያዊ መ. በአጋናኝ

መመሪያ ሶስት በጥያቄ ቁጥር 86-90 ከቀረቡት ቃላት መካከል ልዩ የሆነውን


በመምረጥ መልሱ፡፡

86. ሀ. አልፋ ለ. መጀመሪያ ሐ. ኦሜጋ መ. በኩር


87. ሀ. ድርስ ለ. ወረግቡ ሐ. ጥጉብ መ. እመጫት
88. ሀ. ዳዋ ለ. ዳና ሐ. ዱካ መ. ፈለግ
89. ሀ. ይፋ ለ. ገሀድ ሐ.ህቡዕ መ. ግልፅ
90. ሀ. አመነዠከ ለ. አመሰኳ ሐ. አኘከ መ. ሰለቀጠ

98
አባሪ ስምንት፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2010 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና

መመሪያ አንድ፡- ቀጥሎ የቀረበውን ምንባብ በጥሞና አንብባችሁ ከተ.ቁ. 1-10 ድረስ ለቀረቡት
ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ አጥቁር/ሪ፡፡

ምንባብ

ኢትዮጵያ በአንድነት፣ የዘመኑን የአውሮፓ ስልጣኔ እንድትቀስም ብርቱ ፍላጎት የነበራቸው አባ ታጠቅ ካሳ፣
ከጀግንነታቸው ሌላ የሚያቃጥል የሀገር ፍቅር ያደረባቸው ሰው እንደነበሩ የታሪክ ፀሃፊዎች በሰፊው ያወሳሉ፡፡
ስለዚህ እንደቀንዲል ዘወትር የሚጠቀሰውን ያን ጊዜ ወደሀገራችን ገብተው የነበሩ የውጭ ሰዎች የሀገሪቱን ምድር
ለቀው ሰወጡ፡- በሉ! የሀገሬን አፈር ይዛችሁ እንዳትሄዱ መጫሚያችሁን አውልቃችሁ አራግፋችሁ ሂዱ
ማለታቸው ነው፡፡ ድርጊቱ ለሀገር የመሳሳት ስሜት፣ ለነፃነቷ፣ ለህዝብ፣ ሁለንተናዊ ፍቅር ከዮሀንስ እንዴት
ተደፍሮ የሚለው ለሀገር የመሳሳት ስሜት ጥርኝ አፈርዋን እንኳን እስከ መከልከል እንደሚያደርስ ያሳያል፡፡

በእርግጥም ኢትዮጵያ የምትደምቅ፣ የምትወደድ፣ የምትፈቀር ሀገር ናት፡፡ በዚች ምድር ላይ ተወልዶ አድጎ፣
ከህልውናዋ ህልውናዋ ነስቶ ኢትዮጵያ የሚለውን ክብር ስም ለተቀዳጀ ቀርቶ ለአንዳፍታ ያያት ጎብኝ እንኳን
ውበቷን፣ ማራኪነቷን፣ ሳያደንቅ የሚሄድ የለም፡፡ ቢሆንም "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲሉ መጠነረቀቅ
ያሻል፡፡ ከትውልድ ትውልድ ሲሸጋገር የቆየው ባህሏ የብዙ ሺ ዘመናት ቁሳዊና መንፈሳዊ ስልጣኔዋ፣ ይልቁንም
በተፈጥሮ የታደለችው ቅርሷ "አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፤ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል" እንዲሉ፡፡ ራሳችንን
ከመደለሉ ላይመጠንቀቅ ተገቢ ነውና እናስተውል፡፡ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የታደለች ልምላሜዋ ልዩ ሞገስ
አሰጥቷታል፡፡ ባለቅኔው በተዋቡ ቃላት ብዕሩን ሰድሮ ሰዓሊው ሹራቡን በአሻራው ላይ ረጭቶ እንዲስላት ምክንያት
ሆኖታል፡፡

ስለዚህ በዚችው ውብ ምድር የበቀለ ኢትዮጵያዊ ከሀገሩ ጋር ያለውን ጥብቅ ቁርኝት፣ የፅኑ ፍቅር የመተሳሰብ
ስሜት ለመግለፅ ስሜት አፈርሽን ዘግኜ-ብሎ ስሜቱን ለመደምደም ይቸግረዋል፡፡

አፈርሽን ዘግኜ - ሲል ለዕሱ የሚታየው በእርሷ የመመሰጡ፣ የታሪክ - ሁዳዴ ባለፀጋነቷ የተንጣለለ ሀብት
ባለቤትነቷና ለነፃነቷ ቀናኢ የሆኑ - ህዝቦች ባለሙያ እናት መሆንዋን ነው እንጅ የሀገሩን አለመቆጠር ያሳየ
አይደለም፡፡ ልቁጠርህ ቢሉትስ ባህርይዋ…እስከ የት አለውና!

ምንጭ/ ትግራይ ፋይን አርት ኮሌጅ/

1. ለምንባቡ የሚስማማው ርዕስ-----------ነው፡፡


ሀ. አንዲት ኢትዮጵያ ለ. የቱሪስት መስህብ
ሐ. የሚያቃጥል ፍቅር መ. አፈርሽን ዘግኜ
2. ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ እንዲሉ ሲል --------ማለት ነው፡፡
ሀ. የቖጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
ለ. በገንዛ ራሱ እባብ ጠመጠመ

99
ሐ. ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ
መ ሀናለ መልስ ናቸው
3. አፈርሽን ዘግኜ ሲል------------ማለቱ ነው፡፡
ሀ. የታሪክ ሁዳዴ ባለፀጋነቱን ለ. የሀገሩን መቆጠር ነው
ሐ. ቃል ገብቼ መ. በልቼ ጠጥቼ
4. ባለ ቅኔው ከተዋቡ ቃላት፣ ሰዓሊ በሸራው እንዲስላት ምክንያት የሆነው ምንድን ነው?
ሀ. የሶስት ሺ አመታት ታሪክ ስላላት ለ. የብዙ ዘመናት ቁሳዊና መንፈሳዊ ስልጣኔ ስላላት
ሐ. የአንድ ሺ ዓመታት ታሪክ ስላላት መ. ሁሉም መልስ ናቸው
5. በዚች ውብ ምድር የበቀለ ኢትዮጵያዊ ሲል---- ማለቱ ነው፡፡
ሀ. ኢትዮጵያዊ ያልሆነ ለ. ኢትዮጵያን የሚረዳ የውጭ ዜጋ ያልሆነ
ሐ. በኢትዮጵያ የተወለደ መ. ሁሉም መልስ ናቸው
6. አሳ ጎርጓሪ ዘንዶያዎጣል፣ የሰው ፈላጊ ራሱን ያጣል፡፡ ሲል ------ማለቱ ነው፡፡
ሀ. አተርፍ ባይ አጉዳይ ለ.ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
ሐ. ድንጋይ ቢያጎኑት ተመልሶ ባናት መ. የቸገረው ርጉዝ ያገባል
7. የታሪክ ሁዳዴ ባለታሪኳ ሲል-----------ማለቱ ነው፡፡
ሀ. ኢትዮጵያ በሰፊ የእርሻ ምርት የምትታወቅ አገር ነች ማለቱ ነው
ለ. ኢትዮጵያ ለዱር አራዊትና ለቱሪስ መስህብ አላት ማለት ነው
ሐ. ብዙ የሚለሙ አፈሮች ስላሉ አፈርሽን ዘግኜ ለምርት ማለቱ ነው
መ. ኢትዮጵያ ሰፊ የሆነ የማያልቅ ታሪክ አላት ማለቱ ነው
8. የኢትዮጵያ ውበትና ማራኪነት የተገለፀው------------አንቀፅ ላይ ነው፡፡
ሀ. አንቀፅ ሁለት ለ. አንቀፅ ሶስት ሐ. አንቀፅ አንድ መ. አንቀፅ አራት
9. ፀሐፊው አባታጠቅ ካሳን እንዴት ገለፃቸው?
ሀ. የሚያቃጥል የሀገር ፍቅር ያላቸው
ለ. ኢትዮጵያ የአውሮፓን ስልጣኔ እንድትቀስም የሞከሩ
ሐ. ኢትዮጵያ በአንድነት ፀንታ እንድትኖር ያደረጉ
መ. ሁሉም መልስ ነው
10. የአባታጠቅ ካሳ ፍላጎት ምንድን ነው?
ሀ. ኢትዮጵያ መከፋፈልና መገዛት
ለ. ኢትዮጵያ በአንድነቷ ፀንታ የዘመኑ የአውሮፓ ስልጣኔ እንድትቀስም
ሐ. የመሳፍንት ስርዓት እንዲሰፍን
መ. ሁሉም መልስ ናቸው

መመሪያ ሁለት፡- ከተራ ቁጥር 11-15 ድረስ የቀረቡትን ቋንቋ ነክ ጥያቄዎች በጥሞና በማንበብ
ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛ መልስ በመምረጥ አጥቁር/ሪ፡፡

11. የሀሳባውያን መላምት አራማጅ የሆኑ የቋንቋ ምሁራን ዋና መከራከሪያ ሀሳብ ምንድን ነው?
ሀ. በቅዱሳት መፃህፍት ይደገፋል፡፡ ለ. በፈጣሪ በራሱ ህልውና ይደገፋል፡፡
ሐ. በፀጋ ስጦታነቱ ይታመናል፡፡ መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ፡፡
12. ማንኛውም ቋንቋ በራሱ ምሉዕ ነው የሚባልበት ምክንያት ምንድን ነው?
ሀ. ማህበረሰቡን በሁለንተናዊ ገፅታው ሊያግባባ በመቻሉ ነው፡፡
ለ. አፍ መፍቻ ስለሆነ ነው፡፡
ሐ. አሰዳደሩ ትክክል ስለሆነ ነው፡፡

100
መ. በቂ የቃላት ክምችት ስላለው ነው፡፡
13. ከሚከተሉት ሃሰቦች መካከል ትክክል የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. መዋዋስ ለቋንቋዎች መበላሸት በር ይከፍታል፡፡
ለ. ውሰት የተወሰኑ ቋንቋዎች ባህርይ ነው፡፡
ሐ. ቋንቋዎች ከውሰት ተጠብቀው ማደግ ይችላሉ፡፡
መ.መዋዋስ የቋንቋና የማህበራዊ ሥርዓት መገለጫ ነው፡፡

14. "ውሃ" የሚለው ቃል በሮምኛ "ቢሻን" በትግርኛ "ማይ" በሌላም ቋንቋ ሌላ ስያሜ መኖሩ ከቋንቋ
ባህርያት ውስጥ የትኛውን ይገልፃል?

ሀ. ረቂቅነት ለ. ዘፈቀዳዊነት ሐ. አንደበታዊነት መ. ተዋዋሽነት

15. ቋንቋ የማንነት መገለጫ መሆኑን የሚያሳየን የቋንቋ አገልግሎት የትኛው ነው?

ሀ. ስነ ልቦናዊ ለ. የቋንቋ ባህሪ ሐ. ማህበራዊ መ. ስነ ልሳናዊ

መመሪያ ሶስት፡- ከተራ ቁጥር 16-53 ድረስ ለቀረቡት ጥያቄዎች እንደአጠያየቅ ባህርያቸው ትክክለኛ
መልስ የያዘውን መልስ በመምረጥ አጥቁር/ሪ፡፡

16. በውኑ ዓለም በሁለት ሰዎች መካከል የሚደረግ የሀሳብ ወይም የንግግር መለዋወጥ--------- ይባላል፡፡

ሀ. ክርክር ለ. ውይይት ሐ. ጭውውት መ. ሙግት

17. ሰዎች ጊዜና ቦታ ወስነው በመገናኘት አንድና ከአንድ በላይ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ
የሚለዋወጡበትና መግባባት ላይ የሚደርሱበት --------ይባላል፡፡

ሀ. ጭውውት ለ. ክርክር ሐ. እሰጣ ገባ መ. ውይይት

18. የምንፈልገውን መረጃ ብቻ ብድግ ብድግ በማድረግ የምናነብበት የንባብ አይነት ------ይባላል፡፡

ሀ. ምርምራዊ ንባብ ለ. ጥልቅ ንባብ

ሐ. የገረፍ ገረፍ ንባብ መ. ሁሉም መልስ ናቸው

19. ከሚከተሉት መካከል የጥሩ ንግግር አቀራረብ ዋና መለያ ባህርይ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ግልፅነት ለ. ክብደት ሐ. ስሜታዊነት መ. አወዛጋቢነት

20. ቀጥሎ ከቀረቡት አገላለፆች ለቅስቀሳ ተግባር የትኛው የተሸለ ነው?

ሀ. የትምህርት ውጤታችንን ለማሻሻል በርትተን ማጥናት አለብን

ለ. ነገ የችግር አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀን እንዳንሰቃይ በርትተን እንማር

ሐ. እድሜው ለትምህርት የደረሰ ሁሉ ት/ቤት መግባት አለበት

መ. መማር ለሁሉም የተሰጠ መብት ነው

101
21. በቤተ መፃህፍት ውስጥ መፃህፍት በደራሲው ስም የሚደረደሩ ቢሆን ትክክለኛው የቱ ነው?

ሀ. ከድር፣ ተሰማ፣ ረጋሳ፣ ወርቁ፣ አወቀ ለ. ረጋሳ፣ በርሄ፣ ተሰማ፣ አወቀ፣ ከድር፣ ወርቁ

ሐ. ረጋሳ፣ ተሰማ፣ በርሄ፣ ከድር፣ አወቀ፣ ወርቁ መ. ተሰማ፣ በርሄ፣ ረጋሳ፣ ከድር፣ አወቀ፣ ወርቁ

22. ቃለ ጉባኤ ስንፅፍ በስብሰባው ላይ ያልተገኙ አባላት ስም ከተፃፈ በኋላ የሚፃፈው ምንድን ነው?

ሀ. በስብሰባው ላይ የተገኙ አባላት ለ. የስብሰባው አጀንዳ

ሐ. ስብሰባው የተካሄደበት ቦታ መ. በስብሰባው ላይ የተነሱ ዋና ዋና ሀሳቦች

23. ድንቄም ነጋዴ---------በሚል ርዕስ ግጥም አነበብኩ፡፡ በክፍት ቦታው የሚገባው ስርዓተ ነጥብ የቱ ነው?

ሀ. ? ለ. ! ሐ. I መ. ፣

24. ፈተናውን ማለፍ ትፈልጋላቸሁ-------------ጠንክራችሁ አጥኑ፡፡ በሁለቱ ዓ.ነገሮች መካከል ሊገባ የሚችለው
የቱ ነው?

ሀ. ስለዚህ ለ. ሆኖም ሐ. ይሁንና መ. በመሆኑም

25. ውሃ ያድናል፣ ይገድላልም፡፡ ይህ ዓ.ነገር የቀረበው በየትኛው ስልት ነው?

ሀ. አጋናኝ ለ. ሀተታዊ ሐ. ጥያቄያዊ መ. ትዕዛዛዊ

26. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች አንዱ በጥያቄያዊ ዓ.ነገር ስልት የተነገረ ነው፡፡

ሀ. እንዴት ደስ የሚል ቀን ነው

ለ. እንኳን መጣህ ሲባል መልስ የለውም

ሐ. አሟት ቀርታለች አልተባለም ነበር እንዴ

መ. ሁሉም መልስ ናቸው

27. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች ውስጥ አንዱ ሀይለቃል፣ ቀሪዎች ደግሞ ዘርዛሪ መሆን ይችላሉ፡፡ ሃይለቃል መሆን
የሚችለው የቱ ነው?

ሀ. ተማሪዎችን በጣም እወዳቸዋለሁ ለ. ተማሪዎች በጊዜ ወደ ት/ቤት ይሄዳሉ

ሐ. ተማሪዎቹ በርትተው ያጠናሉ መ. ተማሪዎች የቤት ስራቸውን ይሰራሉ

28. የአልማዝ እህት አጭር ነች፡፡ የዓ.ነገሩ ስልት ------ነው፡፡

ሀ. አሉታዊ ለ. ትዕዛዛዊ ሐ. ጥያቄያዊ ሐ. አወንታዊ

29. የንግግረ ክሂል ከማሳደግ አንፃር አሉታዊ ተፅእና ያለው የትኛው ነው?

ሀ. ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባበትም ለ. ለመዋጥ ማላመጥ ይሻላል

ሐ. አፈምላጭ በደረቁ ይላጭ መ. ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል

30. ከሚከተሉት ውስጥ በዝርው ስነቃል ዘውግ ውስጥ የሚመደበው የትኛው ነው?

102
ሀ. ምርቃል ለ. ሀተታ ተፈጥሮ ሐ. ሽለላና ፉከራ መ. ምሳሌያዊ ንግግር

31. አንድ ልቦለድ በምዕራፍ ሲከፈል ተውኔት በ------------ይከፈላል፡፡

ሀ. በትይንት ለ. በምዕራፍ ሐ. በገቢር መ. ሀናሐ መልስ ናቸው

32. ሰውየው አይነልም ስለሆነ ሰዎች ይሸሹታል፡፡ የተሰመረበት ፈሊጣዊ ንግግር ትርጉም፡-

ሀ. በሽተኛ ለ. ሰላይ ሐ. ተጠራጣሪ መ. ተንኮለኛ

33. "አስር ጊዜ ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ" ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ከስነቃል ተግባራት ውስጥ የቱን ያመለክታል?

ሀ. መግለፅ ለ. መግታት ሐ. ማስተማር መ. መቆጣጠር

34. "አፍንጫ ሲነካ አይን ያለቅሳል" የሚለው ምሳሌያዊ ንግግር አቻ የሚሆነው የቱ ነው?

ሀ. ድር ሲያብር አንበሳ ያስር ለ. ትንሽ ስጋ እንደመድፌ ትወጋ

ሐ. ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ መ. ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያን አንድ አለ

35. ዘወትር ጎህ ሲቀድ ከቤቱ የሚወጣው ጎረቤቴን አንድም ቀን አይኑን አይቼው አላውቅም፡፡

ሀ. ሲጨልም ለ. ሲነጋጋ ሐ. ሲረፋፍድ መ. ሲመሽ

36. ዮሃንስ ሰማይ ቅርቡ መሆኑን ስለማያውቅ ሀላፊነቱን በብቃት ይወጣል ብየ---------፡፡ በዓ.ረፍተ ነገሩ ውስጥ
ያለውን ክፍት ቦታ ለመሙላት የትኛው ተስማሚ ነው?

ሀ. አላምንም ለ. እገምታለሁ ሐ. አምናለሁ መ. ለናሐ መልስ ናቸው

37. አንድ እጣት ቁንጫ አይገድልም፡፡ ይህ ምሳሌያዊ ንግግር ለመኮነን የሚፈልግ ሰው ሀሳቡን ለማጠናከር
ሊጠቀምበት ይችላል፡፡

ሀ. መለያየትን ለ. ስንፍናን ሐ. ጭካኔን መ. ደካማነትን

38. "ጆሮ ስጡኝ" እያለ ቢጮህም ጉዳይ ያለው አነበረም፡፡ ለተሰመረበት ፈሊጥ ፊቺ---------ነው፡፡

ሀ. ላዳምጣችሁ ለ. ፊት አትንሱኝ ሐ. አድምጡኝ መ. ሀናለ መልስ ናቸው

39. ንግግሩ ሬት ነው፡፡ይህ ዓ.ነገር በየትኛው የዘይቤ አይነት የተዋቀረ ነው?

ሀ. ምስያ ለ. አነፃፃሪ ሐ. ግነት መ. ተለዋጭ

40. የአንቀፁን ሀሳብ ጠቅልሎ የሚይዘው ዓ.ነገር ምን ይባላል?

ሀ. መሪ ዓ.ነገር ለ. ርዕሳዊ ዓነገር ሐ. አብይ ዓ.ነገር መ. ሁሉም

41. ስለ አንድ ሀሳብ የሚያትቱ ዓ.ነገሮች ስብስብ ምን ተብሎ ይጠራል?

ሀ. ድርሰት ለ. ዘገባ ሀ. አንቀፅ መ. ልቦለድ

42. የአንቀፅ ቅርፅ የሚወሰነው በምንድን ነው?

ሀ. በያዘው ፍሬ ሀሳብ ለ. በፅሁፉ ርዕስ

103
ሐ. በሃይለቃል መገኛ ቦታ መ. በዝርዝር ዓ.ነገሮች አገላለፅ

43. የሀይል እጥረት ለደኖቸ መመናመን ዋነኛ ችግር ነው፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ በውጤትነት የተጠቀሰው -------
ነው፡፡

ሀ. እጥረት ለ. መመንመን ሐ. የደኖች መመናመን መ. የሃይል እጥረት

44. ከሚከተሉት ውስጥ የምክንያትንና የውጤትን ግንኙነት በግልፅ የሚታየው በየትኛው ነው?

ሀ. ልጁ ተናደደ ለ. በርሃብ ሞተ ሐ. ተነስቶ አጨበጨበ መ. በጣም አዘነ

45. ኧረተይ ዝንጀሮ ክፉ አትናገሪ፣

አሁን ትገኛለሽ አውድማ ስትጭሪ፡፡ የሚለው ቃላዊ ግጥም በ--------ይካተታል

ሀ. በስራ ዘፈን ለ. በሰርግ ዘፈን ሐ. በልጆች ጨዋታ መ. በክብረበዓል ዘፈን

46. ጉዱ ካሳ --------- እብድ ------- ሲባል ኖረ፡፡ ካገሩ ተባረረ በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ በባዶ ቦታው መግባት
ያለበት ስርዓተ ነጥብ የቱ ነው?

ሀ. ነጣላ ትምህርተ ጥቅስ ለ. እዝባር ሐ. ቅንፍ መ. ደርብ ትምህርተ ጥቅስ

47. አብይ ጉደል ጉደል ቀጭን መንገድ አውጣ፤

ከሙሽሪት ጋራ ተጫውቼ ልምጣ፡፡ ግጥሙ የቀረበበት ዘይቤ -------ነው፡፡

ሀ. አያዎ ለ. ሰውኛ ሐ. እንቶኔ መ. አነፃፃሪ

48. ድርሰት ከመፃፍ በፊት በቅደም ተከትል መከናወን ያለባቸውን ተግባራት የሚያመለክተው የቱ ነው?

ሀ. ርዕስ መምረጥ፣ አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ርዕስ ማጥበብ (መወሰን)

ለ. ርዕስ መምረጥ፣ ርዕስ መወሰን፣ አስተዋፅኦ መንደፍ

ሐ. አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ርዕስ መምረጥ፣ ርዕስ መወሰን

መ. ርዕስ መወሰን፣ አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ርዕስ መምረጥ

49. በአከራካሪ ድርሰት ለሚቀርብ ፅሁፍ መነሻ ለመሆን ይበልጥ የሚመረጠው የቱ ነው?

ሀ. መርሃችን "መማር መማር አሁንም መማር" የሚለው ነው፡፡

ለ. በእረፍት ጊዜው አያቱን ለመጎብኘት ወደገፀር አካባቢ ተጉዞ ነበር፡፡

ሐ. እንደሰንሰለት የተያያዙ ረጃጅም ተራሮች ከርቀት ይታያሉ፡፡

መ. ምንጊዜም ባህላዊ መደሃኒቶቸን መጠቀም ጉዳት የለውም፡፡

50. አጭር ልቦለድን በተመለከተ ትክክለኛ አገላለፅ የትኛው ነው?

ሀ. የአጭር ልቦለድ ባህርያት በታሪኩ ውስጥ ብዙ ግጭቶች ይገጥሙታል፡፡

ለ. አጭር ልቦለድ ደራሲው የራሱን አመለካከት በዝርዝር እንዲያቀርብ ያስችዋል፡፡

104
ሐ. የአጭር ልቦለድ ዋና ጭብጥ አንደ ብቻ ነው፡፡

መ. አጭር ልቦለድ የረጅም ልቦለድ ቅንጭብጫቢ ነው፡፡

51. በአንድ የልቦለድ ድርሰት ውስጥ ገፀባህርያት የሚኖሩበት አካባቢና የሚጠቀሙባቸውን ቃሎች በግለፅ
የትኛውን ያመለክታል?

ሀ. ታሪክ ለ. መቼት ሐ. ገፀ ባህሪ መ አንፃር

52. ከሚከተሉት የልቦለድ አላባውያን መካከል ሌሎች አላባውያንን በውስጡ የሚያካትተው የትኛው ነው?

ሀ. ታሪክ ለ. ጭብጥ ሐ. መቼት መ. ግጭት

53. ነጠላ ሰረዝን ለመጠቀም ተገቢ የሚሆነው የትኛው አማራጭ ነው?

ሀ. በትራፊክ አደጋ ህይዎት ማለፉ ንብረት መውደሙና የሚደርሰው ጥፋት ሁሉ አስደንጋጭ ነው፡፡

ለ. አለማየሁ እንደወንበር ጠረጴዛ አልጋና ቁምሳጥን የመሳሰሉትን እቃዎች ብዙ ገንዘብ አውጥቶ ገዛ፡፡

ሐ. ሮዛ ቀሚስ ከጀርመን ጫማ ከጣልያን ሽቶ ከፈረንሳይ ወዘተ የሚያመጡላት ብዙ ወዳጆች አሏት፡፡

መ. ሁሉም መልስ ናቸው፡፡

መመሪያ አራት፡- ከተራ ቁጥር 54 – 58 ላሉት ጥያቄዎች እንደአጠያየቅ ባህርያቸው መልስ


ስጡ፡፡

54. ከሚከተሉት ውስጥ ባህርይን አመልካች ጥገኛ ምዕላድ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. -ኣቸው ለ. -ኢት ሐ. -ኣም መ. -ኣዊ

55. "ሳቅ" ከሚለው ስም ውልድ ቅፅል መመስረት ቢፈለግ፣ የትኛውን ቅጥያ ምዕላድ መውሰድ ተገቢ ነው?

ሀ. -ኢታ ለ. -ኧኛ ሐ. -ኣም መ. -ኣማ

56. "ስለወገኖቻችሁ" በሚለው ቃል ውስጥ የሚገኙት ጥገኛ ምዕላዶች በቁጥር ስንት ናቸው?

ሀ. ሁለት ለ. ሶስት ሐ. አራት መ. አምስት

57. "ዘመናዊነቱን" የሚለው ቃል ባለ ስንት ምዕላድ ነው?

ሀ. አራት ለ. ሶስት ሐ. አምስት መ. ስድስት

58. "ዘብጥያ" ለሚለው ቃል ተመሳሳይ የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ወህኒ ለ. ሸንጎ ሐ. ገዳም መ. ገበያ

መመሪያ አምስት፡- ከተራ ቁጥር 59-61 ከተዘረዘሩት ውስጥ ልዩ የሆነውን አውጡ፡፡

59. ሀ. ሰነፈጠ ለ. ከረፋ ሐ. ጎመዘዘ መ. አወደ

60. ሀ. ዋቢ ለ. ቤዛ ሐ. ምትክ መ. ምስጉን

105
61. ሀ. ውበት ለ. ውርጭ ሐ. ብርድ መ. ቁር

62. "አንፈታም" የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ የሚኖረው ምን ሲሆን ነው?

ሀ. "ን" ጠብቆና ላልቶ ሲነበብ ለ. "ፈ" ጠብቆና ላልቶ ሲነበብ

ሐ. "ታ" ጠብቆና ላልቶ ሲነበብ መ. "ን" ጠብቆ ሲነበብና "ፈ" ላልቶ ሲነበብ

63. "ዋና" የሚለው ቃል ጠብቆ የሚነበበው በየትኛው ዓ.ነገር ነው?

ሀ. የልጁ ሱስ ዋና ብቻ ከሆነ በጣም ቆየ

ለ. በአሁኑ ጊዜ ዋና ለመለማመድ ከፍተኛ ፍላጎት አለ

ሐ. የመስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ለዘብተኛ ናቸው፡፡

መ. አሁን አሁን ወላጆች ልጆቻቸውን ዋና ያለማምዳሉ፡፡

64. "ነከረ" የሚለው ቃል በእማሬያዊ ፍቺው የገባው በየትኛው ዓ.ነገር ነው?

ሀ. ገመዱን ውሃ ውስጥ ነከረ፡፡

ለ. አንድም ቀን በሳል ሀሳብ አቅርቦ አያውቅም፣ የተነከረ ነው፡፡

ሐ. እየነከሩ ያወጡት መሆኑ በአነጋገሩ ያስታውቃል፡፡

መ. ሰሎሞን ከተነከረ ያልተጠመዘዘ ነው፡፡

65. ከሚከተሉት ውስጥ ከግስ በላይ ለተመሰረተ ውልድ ስም ምሳሌ የሚሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ዓይናማ ለ. ለምለም ሐ. ክፉኛ መ. ከበሬታ

66. "ተነገረ፣ ጥሩ፣ ዜና" የሚሉት ቃላት የሚመደቡባቸውን የቃል ክፍሎች ለመዘርዘር ብንፈልግ በቅደም ተከተል
የትኞቹ ናቸው?

ሀ. ግስ፣ ስም፣ ቅፅል ለ. ቅፅል፣ ስም፣ ግስ ሐ. ቅፅል፣ ግስ፣ ስም መ. ግስ፣ ቅፅል፣ ስም

67. የሚከተሉት ቃላት በየቃል ክፍላቸው ቢመደቡ በተለየ የቃል ክፍል የሚመደበው የትኛው ቃል ነው?

ሀ. መፈለግ ለ. አፈላለግ ሐ. ፍላጎት መ. ፈለገ

68. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል በአንድ አይነት የቃል ክፍል የማይመደቡ ቃላትን ያሰባጠረው የትኛው
አማራጭ ነው?

ሀ. ተራራ፣ ረጅም፣ ደፈረሰ ለ. ገና፣ ቶሎ፣ ክፉኛ

ሐ. አስቀመጠ፣ ጀመርኩ፣ አገኘች መ. አጭር፣ ጠንካራ፣ ወፍራም

69. ከሚከተሉት ውስጥ ግሳዊ ሀረግ የሆነው የትኛው ነው?

ሀ. የተፋጠነ የለውጥ ሂደት ለ. ህክምናውን ለመከታተል

ሐ. የምትጓዘው ወዴት ነበር መ. ከምዕራፍ ወደ ምዕራፍ መሸጋገሪያ

106
70. እኔ ሁለተኛውን በትክክል የሰራሁት አይመስለኝም፡፡ በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ የተሰመረበት ሀረግ የትኛውን
የሀረግ አይነት ይወክላል?

ሀ. ግሳዊ ሀረግ ለ. ተውሳከ ግሳዊ ሀረግ ሐ. ቅፅላዊ ሀረግ መ. መስተዋድዳዊ ሀረግ

71. አርጅቶ የነበረው የአያቴ ቤት በአዲስ ሁኔታ እንደገና ተሰራ፡፡ በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ የተውሳከ ግሳዊ ሀረጉ
መሪ ማን ነው?

ሀ. የተጎዳ ለ. ቤት ሐ. እንደ መ. ገና

72. መስኮቶች ስለታሸጉ ክፍሉ ጨለመ፡፡ በሚለው ዓ.ነገር የተሰመረበት ሀረግ ወደስማዊ ሀረግ ብንለውጠው--------
--ነው፡፡

ሀ. ክፍሉ ስለጨለመ ለ. ክፍሉ በመጨለሙ ሐ. ጨለማ ክፍል መ. ክፍላችን ጨለመ

73. ቀጥሎ ከቀረቡት ዓ.ነገር አንዱ ለውስብስብ ዓ.ነገር ሚሳሌ ነው፡፡

ሀ. ለጤንነቱ ሁልጊዜ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡

ለ. የስራ ሃላፊው ከሰራተኞቹ ጋር አልተስማማም፡፡

ሐ. ደጋግማ ብትመክረውም ከጥፋቱ ሊታረም አልቻለም፡፡

መ. ኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት መርሃ ግብሮችን ነድፋለች፡፡

74. ከሚከተሉት ውስጥ ተራ ዓ.ነገር የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ልጁ ወደ ት/ቤት ሄዶ መጣ፡፡ ለ. እንግዶቹ ቆመው አጨበጨቡ፡፡

ሐ. ሰውየው በድንገት በጠዋት መጣ፡፡ መ. ከበደ እያየኝ ይስቅ ጀመር፡፡

75. ሰውየው የተናገሯቸው ቃላቶች አሸማቀቁን፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ የሚታየው ስህተት የምን ስህተት ነው?

ሀ. የመደብ ለ. የቁጥር ሐ. የጾታ መ. የቁጥርና የፆታ

መመሪያ ስደስት፡- ከተራ ቁጥር 76-80 ድረስ የቀረቡ ጥያቄዎች ቀጥሎ በቀረበው ግጥም ላይ
ተመስርተው የቀረቡ ናቸው፡፡ ስለሆነም በግጥሙ መሰረት ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ
አጥቁር/ሪ፡፡

መቃብር

አንተ መቃብር ሆይ አንተ ፍጥረት ፈጁ፣

ስትበላ ምትኖረው የሰራህን በጁ፣

አንተ አይጠግብ በልቶ፣

አንተ አይሞላ ከቶ፣

ስትውጥ ትኖራለህ ተው የሚልህ ጠፍቶ፡፡

107
አንተ አይጠየፌ አንተ ጠርጎ በሌ፣

በልቶ አይወፍር ሁሌ፡፡

ሁሉን እየዋጥከው፣

ሁሉን እየጋጥከው፣

ሃይ!---የሚልህ ታጥቶ ስንቱን ዘመን ኖርከው?

አንተ መቃብር ሆይ፣

ተወቀስ በምድር ተገሰፅ በሰማይ፡፡

ተከሰስ በሙታን፣

ተሞገት በህያዋን፡፡

ቆሞ ይመስክርብህ ቆፋሪ ቀባሪ፣

በመንበሩ ሆኑ ፍርድ ይስጥህ ፈጣሪ፡፡

/አለማየሁ ዘውዴ፣ ንስሐ እና ሌሎች ግጥሞች፣2003፣115/

76. ግጥሙ ስንት ስንኞች አሉት?

ሀ. 16 ለ. 7 ሐ. 8 መ. 12

77. የአምስተኘው ስንኝ መድረሻ ሀረግ የቱ ነው?

ሀ. ተው የሚልህ ለ. ተው የሚልህ ጠፍቶ

ሐ. ትኖራለህ ተው የሚልህ ጠፍቶ መ. የሚልህ ጠፍቶ

78. ግጥሙ በስንት አርኬ የተገነባ ነው?

ሀ. 7 ለ. 10 ሐ. 9 መ. 6

79. "ተወቀስ በምድር ተገሰፅ በሰማይ" የሚለው ስንኝ በየትኛው የግጥም ምጣኔ የጠገነባ ነው?

ሀ. ሰንጎ መገን ለ. ቡሄ በሉ ሐ. በፀጋዬ ቤት መ የወል ቤት

80. በግጥሙ ውስጥ ያለው ተራኪ ውስጣዊ ስሜት ምንድን ነው?

ሀ. ቁጭት ለ. ትዝብት ሐ. ፍርሃት መ. ሁሉም

108
አባሪ ዘጠኝ፡- በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የ2011 ዓ.ም የአማርኛ ቋንቋ ሞዴል ፈተና

መመሪያ አንደ፡- ቀጥሎ የቀረበውን ምንባብ በጥሞና አንብባችሁ ከተ.ቁ. 1-10 ድረስ ለቀረቡት
ጥያቄዎች በምንባቡ መሰረት ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ አጥቁር/ሪ፡፡

ምንባብ

አጤሚኒሊክ በምጥዋትም በእርጥባንም በምንም ቢማስኑ ለድፍን ኢትዮጵያ ድሃ እንደማይበቃ አዩትና አንድ
ብርቱ ነገር አገኙ፡፡ ነገሩም እንዲህ ነው፡፡ ቅድም እንደተናገርኩት የገጠር አራሽ የአገር ጓንዴ እህሉን በየገደሉ እና
በየጎታው ሸሽጎ አንዳንድ ቁልቢጥ እህል በአንዳንድ ብር እያቀና ብሩን ይጎደጉድና ያምቅ ጀመረ፡፡ ሰውም ለማለቅ
አልቦዝን አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ልበ ብርሃን ንጉስ መኳንንቱን በየአገሩ ሰደዱ እና የተሸሸገውን ሁሉ እህል እያስያዙ
ለባለ እህሉ፣ ለቤተሰቡ እና ለራሱ ለአንድ አመት የሚበቃ ቀለብ እያሳተው የቀረውን ለተራበ ድሃ አስናኙት
አከፋፈሉት፡፡

ይህን የሚኒሊክ ወሬ የሰማ ባለ እህል ሹም ሁሉ የሸሸገውን እንዳይያዝበት እያወጣ ያቀና ጀመር፡፡ ገበያውም ከዚህ
ወዲያ መጥገብ ጀመረ፡፡ ሰውም በረሃብ መሞቱ ቀረ፡፡ደጉ ንጉስ በዚህ ብቻ ነገሩን አልተውትም፡፡ እንደ ድሃ ባላገር
መጥረቢያ አስለው መቆፈሪያ አዋደው ካንቻ መቁረጥ መሬት መቆፈር ጀመሩ፡፡

አንድ ቀን ከዕንጦጦ ማርያም በታች ያለውን የኤካን ዱር በንጉስ እጃቸው መጥረቢያ ይዘው ካንቻ ሲመቱ
እግራቸውን ጋሬጣ እና እሾህ ስላደማቸው መኳንንቱ በሻማ ደማቸውን ለመጥረግ ተጎነበሱ፡፡ ደጉ ሚኒሊክ በቁጣ
"ተው አትንኩኝ ይልቁንስ እኔ ለዕናንተ እንዳሳየሁ እናንተም ለቤተሰቦቻችሁ አሳዩ ከዚያ በመቀጠል ጥቅሙን
ታዩታላችሁ" አሉ፡፡ የዚህን ጊዜ ቃላቸውን የሰማ ተግባራቸውን ያየ መኳንንት ሁሉ በንጉሱ ድርጊት በመገረም
እና በመደነቅ በስራው ተሰማራ፡፡

ምንጭ፡- አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ (አጤ ሚኒሊክ)

1. በምንባቡ መሰረት ደራሲው ለአንባብያን ለማስተላለፍ የፈለገው መልዕክት ምንድን ነው?


ሀ. የአጤ ሚኒሊክን ኋላቀርነት ለ. የመኳንንቱን መፍትሄ ሰጭነት
ሐ. የአጤ ሚኒሊክን ብልህነትና ጠንካራ መሪነት መ. የህብረተሰቡን ራስ ወዳድነት
2. በምንባቡ ውስጥ አንቀፅ አንድ ላይ "አስናኙት" የሚለው ቃል ትርጉም ምንድን ነው?
ሀ. ሰበሰቡት ለ. አከፋፈሉት ሐ. አከማቹት መ. አጨቁት
3. ፀሃፊው በሚፅፍበት ጊዜ በአመዛኙ የተጠቀመው ቃል የቱ ነው?
ሀ. መደበኛ የሆኑ ቃላት ለ. የተውሶ ቃላት
ሐ. የአራዳ ቃላት ሐ. ኢ-መደበኛ ቃላት

109
4. በምንባቡ የመጀመሪያ አንቀፅ ላይ "ቢማስኑ" ለሚለው ቃል አውዳዊ ፍቺው የትኛው ነው?
ሀ. ቢለግሱ ለ. ቢለፉ ሐ. ቢዋሱ መ. ቢተው
5. በምንባቡ ውስጥ በብዛት የምናያቸው አዳዲስ ቃላት እና ሌት ያሉ አገላለፆች ምንን ይገልፃሉ?
ሀ. ደራሲው የመጣበትን አካባቢ ለ. የደራሲውን ዘመናዊ ትምህርት አለመቅሰም
ሐ. የደራሲውን የጤና ችግር መ. ደራሲው በዕውቀት የበለፀገ መሆኑን
6. በምንባቡ የመጀመሪያ አንቀፅ፣ ሶስተኛ ዓ.ነገር "ያገር ጓንዴ" ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ያገሩ ጨካኝ ለ. ያገሩ ጀግና ሐ. ያገሩ ሀብታም መ. ያገሩ ሽፍታ
7. ምንባቡ ያለበትን ችግር ከሞላ ጎደል ሊገልፀው የሚችለው አማራጭ የትኛው ነው?
ሀ. ዘዬ፣ አገላለፅ፣ ፈጠራ ለ. ዘዬ፣ ሰዋስው፣ አገላለፅ
ሐ. ዘዬ፣ ውሰት፣ ሰዋስው መ. ሰዋስው፣ ውሰት፣ ፈጠራ
8. በምንባቡ አንቀፅ አንድ ላይ "ቁልቢጥ" የሚለው ቃል ምንን ለመግለፅ የገባ ነው?
ሀ. የዘመኑን ሹም ለ. የዘመኑን ስርዓት
ሐ. የዘመኑን ሚዛን መ. የዘመኑን ባለፀጋ
9. ገበያውም ከዚያ ወዲያ መጥገብ ጀመረ፡፡ የሚለው ዓ.ነገር የተገለፀበት ዘይቤ የቱ ነው?
ሀ. አነፃፃሪ ለ. ሰውኛ ሐ. በስመአዳሪ መ. እንቶኔ
10. በምንባቡ አንቀፅ ሶስት ላይ "ካንቻ ሲመቱ" ሲል ምን ማለቱ ነው?
ሀ. ደኖችን ሲመነጥሩ ለ. ሰብል ሲቀጥፉ
ሐ. እፅዋትን ሲንከባከቡ መ. እፅዋትን ሲመለምሉ

መመሪያ ሁለት፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንደአጠያየቅ ባህርያቸው ከተሰጡት አማራጮች


መካከል ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ በመልስ ምስጫ ወረቀቱ ላይ አጥቁር/ሪ፡፡

11. ቀጥሎ ከቀረቡት ሀሳቦች ውስጥ ስለ ቋንቋ ትክክል ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ. ቋንቋ ድምፃዊ መግባቢያ ነው፡፡ ለ. ቋንቋ የድምፆች ስብስብ ነው፡፡
ሐ. ቋንቋ ልክ እንደሰው ይወለዳል እንጅ አያድግም፡፡ መ. ቋንቋ ተዋዋሽ ነው፡፡
12. የሰው ልጅ ቋንቋ ከእንስሳት መግባቢያ የሚለየው በምንድን ነው?
ሀ. የሰው ልጅ ቋንቋ ደመነፍሳዊ ሲሆን የእንስሳት ግን ኢ-ደመነፍሳዊ ነው፡፡
ለ. የሰው ልጅ ቋንቋ ኢ-ደመነፍሳዊ ሲሆን የእንስሳት ግን ደመነፍሳዊ ነው፡፡
ሐ. የሰው ልጅ ቋንቋ ደመነፍሳዊም ኢ-ደመነፍሳዊም መሆን ሲችል የእንስሳት ግን አ-ደመነፍሳዊ
መግባቢያ ነው፡፡
መ. የሰው ልጅ ቋንቋ ከእንስሳት መግባቢያ የሚለይበት ምንም አይነት መመዘኛ የለውም፡፡
13. ስለ ቋንቋ ጥንተ አመጣጥ በስነሰብ (በስነልሳን) ተመራማሪዎች ዘንድ ሰፊ ተቀባይነት ያለው መላምት
የቱ ነው?
ሀ. የቁስ አካላውያን ለ. የመለኮታውያን ሐ. የሀሳባውያን መ. የደመነፍሳውያን

110
14. "ሚስታቸው" የሚለው ቃል በነፃና በጥገኛ ምዕላድ ተተንትኖ ሲፃፍ፡-
ሀ. ሚስት-አቸው ለ. ሚስት-ኣ-ቸው ሐ. ሚስታ-ቸው መ. ሚስት-ኦች-ው
15. "ካህናት" የሚለውን ቃል መሰረት በማድረግ ከቀረቡት አማራጮች መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ነፃ ምዕላዱ ቃል ነው፡፡ ለ. የጥገኛ ምዕላዱ ፋይዳ አብዥነት ነው፡፡
ሐ. ጥገኛ ምዕላዱ ራሱን የቻለ የይዘት ፍቺ አለው፡፡ መ.ጥገኛ ምዕላዱ /-ናት/ ነው፡፡
16. "ሰበረች" በሚለው ግስ ውስጥ የ3ኛ መደብ፣ ነጠላ ቁጥር አንስታይ ፆታ መደብ አመልካች ቅጥያው
ምንድን ነው?
ሀ. /-ረችች/ ለ. /-ች/ ሐ. /-ረች/ መ. /-ኧችች/
17. ከሚከተሉት ቃላት ውስጥ የግዕዝ አብዢ ምዕላድ ያልተጠቀመው የቱ ነው?
ሀ. መምህራን ለ. ካህናት ሐ. መፃህፍት መ. ወንዞቻቸን
18. ቶሎ ተግባቢ ባይሆንም በስራው ሲበዛ ከተፎ ነው፡፡ በዓ.ነገሩ ውስጥ የተሰመረበት ቃል ቀጥተኛ ፍቺ ምን
ይሆናል?
ሀ. ምስጉን ለ. ፈጣን ሐ. ቅልብልብ መ. ጥንቁቅ
19. እንዴት አይነት እኩይ ሰው ነው እባካችሁ! የተሰመረበት ቃል ተመሳሳይ ፍቺ ምንድን ነው?
ሀ. ተንኮለኛ ለ. ምላሰኛ ሐ. ነገረኛ መ. ክፉ
20. ከሚከተሉት አንዱ ጠብቆ እና ላልቶ መነበብ የማይችል ቃል ነው፡፡
ሀ. የሚገባው ለ. መቅደላዊት ሐ. ሲጠብቅ መ. የሚረዳ
21. ጎረቤታችን እራሱን እስኪስት ድረስ ገና በጠዋቱ ለምን እንደሚጠጣ አይገባኝም፡፡ የተሰመረበት ቃል
ከየትኛው የቃል ክፍል ይመደባል?
ሀ. ቅፅል ለ. መስተዋድድ ሐ. ግስ መ. ተውሳከ ግስ
22. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ስማዊ ሐረግ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. እንደወንድሙ በጣም ቀልጣፋ ለ. ወንደሜ የገዛት ቀይ መኪና
ሐ. ትናንት አየኋት የአልማዝ እህት መ. ከስራ የተሰናበቱት መስሪያ ቤቱ ኃላፊ
23. "እጅግ በጣም ቂመኛ" የሚለው ሀረግ--------ነው፡፡
ሀ. ግሳዊ ሀረግ ለ. ቅፅላዊ ሀረግ ሐ. ተውሳከ ግሳዊ ሀረግ መ. ስማዊ ሀረግ
24. ከሚከተሉት አማራቾች መካከል ለአገላለፃችን ጥንካሬ ለመስጠትና የምናስተላልፈው መልዕክት ግልፅ ሆኖ
ወይም ጎልቶ እንዲታይ ለማድረግ የምንጠቀምበት አባባል ወይም የአነጋግር ስልት ምን ይባላል?
ሀ. ፈሊጥ ለ. ዘዬ ሐ. ዘይቤ መ. ዘዴ
25. ትናንትና የተቀጠረው አጭሩ ዘበኛ እየሮጠ መጣ፡፡
የተሰመረባቸው ቃላት በቅደም ተከተል----------------እና----------------ናቸው፡፡
ሀ. ስምና ግስ ለ. ቅፅልና መስተዋድድ ሐ. መስተዋድድና ስም መ. ቀፅልና ተውሳከ ግስ
26. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል "ተራ ዓ.ነገር" ሆነው የቱ ነው?
ሀ. የትምህርት ቤታችን ርዕሰ መምህር በርካታ ተማሪዎችን አነጋገሩ፡፡
ለ. ልጁ የተሸለመው መጽሀፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ሐ. የአማርኛ ፈተናውን የኮረጀው ተማሪ ተቀጣ፡፡

111
መ. ትናንት የገዛሁት ደብተር ጠፍቶብኝ ሌላ ገዛሁ፡፡
27. በዝናብ ውሃ ልብሱን አጠበ፡፡ በሚለው ዓ.ነገር ውስጥ የተሳቢነትን ሙያ የተወጣው ቃል የቱ ነው?
ሀ. በዝናብ ለ. አጠበ ሐ. ውሃ መ. ልብሱን
28. ከዚህ ቀጥሎ ቅደም ተከተላቸው የተዘበራረቁ ዓ.ነገሮች ቀርበዋል፡፡ ትክክለኛውን ቅደም ተከተል
የሚያሳየውን መልስ ምረጡ፡፡
ሀ. መልስ ከመስጠቷ በፊት አካባቢውን በገጿ ፈገግታ አንፀባረቀችው፡፡
ለ. ፀዳል ማለት ትርጉሙ ምንድን ነው? ስል ጠየኳት፡፡
ሐ. ትርጉሙን ከዚህ አግኘው ማለቷ ይሆን!
መ. ለማንኛውም ብዙ አወጋን፣ ብዙ አጫወተችኝ፣ ታሪኳ በጣም አሳዘነኝ፡፡
ሀ. ሀ፣ለ፣ሐ፣መ ለ. ለ፣ ሀ፣ሐ፣መ ሐ. ለ፣ሐ፣መ፣ሀ መ. ለ፣መ፣ሐ፣ሀ
29. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች መካከል አንዱ ቀስቃሽ ነው፡፡
ሀ. አንድም ሰው በኤች አይቪ እንዳይያዝ፣ እንዳይገለልና እንዳይሞት ሁሉም ሃላፊነቱን ይወጣ፡፡
ለ. ኤች አይቪ በዓለም ለይ መኖሩ ከተረጋገጠ ሰላሳ አመታትን አስቆጥሯል፡፡
ሐ. ኤች አይቪ በደማቸው የሚገኙ እናቶች የባለሙያን ምክር ከሰሙና ተግባራዊ ካደረጉ ከቫይረሱ ነፃ
የሆነ ልጅ የመውለድ እድል አላቸው፡፡
መ. በ2011 ዓ.ም ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የኤች አይቪ ኤዲስ የምክርና ምርመራ
አገልግሎት ጠጠቃሚ ሆነዋል፡፡
30. የአንቀፅን ምንነት በትክክል የሚገልፀው የትኛው ዓ.ነገር ነው?
ሀ. አንቀፅ የተለያዩ ዓ.ነገሮች ስብስብ ነው፡፡
ለ. አንቀፅ ስለተለያዩ ሀሳቦች የሚያትት ፅሁፍ ነው፡፡
ሐ. አንቀፅ ተያያዥነት ያላቸው ዓ.ነገሮች ተገጣጥመው የሚፈጥሩት ስለአንድ ሀሳብ ብቻ የሚያትት
ፅሁፍ ነው፡፡
መ. አንቀፅ ሀይለቃሉን መጀመሪያ፣ መጨረሻ፣ መካከል በማምጣት ከሁለት በላይ በሆኑ ሀሳቦች ዙሪያ
የሚያጠነጥን ፅሁፍ ነው፡፡
31. ወደታች የተገመደው ፀጉሯ፣ ሊጨፈኑ የተቃረቡ ይመስል የጠበቡ አይቿ፣ ድፍጥጥ ያለው አፍንጫዋ፣
ወፍራም ከንፈሯ፣ ወተት የመሰሉት ጥርሶቿ----፡፡ ይህ አንቀፅ ከሚከተሉት የድርሰት አይነቶች ውስጥ
ለየትኛው ምሳሌ ሊሆን ይችላል?
ሀ. ገልጭ ድርሰት ለ. አመዛዛኝ ድርሰት ሐ. ተራኪ ድርሰት መ. ስዕላዊ ድርሰት
32. ልቦለድን አጭርና ረጅም ብለን እንከፍለዋለን፡፡ ረጅም ልቦለድ ሰፋ ያለ ታሪክ በማንሳት ከልደት እስከ
ሞት መተረክ ይችላል፡፡ አጭር ልቦለድ ደግሞ አንድ ታሪክ ብቻ በማንሳት የሚተርክ ነው፡፡ ይህ ፅሁፍ
በየትኛው የድርሰት አይነት የተፃፈ ነው?
ሀ. ስዕላዊ ለ.ተራኪ ሐ. አመዛዛኝ መ. አስረጅ
33. ከሚከተሉት መካከል በፅህፈት ቅድመ ዝግጅት ሂደት መጀመሪያ ላይ መከናወን ያለበት ተግባር የቱ ነው?
ሀ. እንደመጣ ሀሳብን ማቅረብ ለ. ረቂቅ ማዘጋጀት
ሐ. ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ መ. ግብረመልስ ማዘጋጀት

112
34. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ትክክለኛውን የድርጊት ቅደም ተከተል የያዘው የቱ ነው?
ሀ. ድርሰት መፃፍ፣ ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ፣ አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ርዕስ መወሰን
ለ. ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ፣ ርዕስ መወሰን፣ አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ድርሰት መፃፍ፣
ሐ.ርዕስ መወሰን፣ ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ፣ አስተዋፅኦ መንደፍ፣ድርሰት መፃፍ፣
መ. አስተዋፅኦ መንደፍ፣ ርዕስ መወሰን፣ድርሰት መፃፍ፣ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ፣
35. "ትንፋሿ ሽቶ ነው ድምጿም የመረዋ፣
የሞተን ያስነሳል ደማቅ ፈገግታዋ፡፡" ይህ ግጥም ያካተታቸው ዘይቤዎች በቅደም ተከተል ምንና ምን
ናቸው?
ሀ. ሰውኛና ምፀት ለ. ግነትና አነፃፃሪ ሐ. ተለዋጭና ግነት መ. ምፀትና ተለዋጭ
36. ኢትዮጵያውያን እናት ሀገራቸውን አረንጓዴ ሻማ ለማልበስ ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ ዓ.ነገሩ ለየትኛው
የዘይቤ አይነት ምሳሌ ይሆናል?
ሀ. ምፀት ለ. አያዎ ሐ. ሰውኛ መ. እንቶኔ
37. ልብ ስልቻ ነው ምስጢር የሞላበት
ማሰሪያው ምላስ ነው የተቋጠረበት፡፡ የሚለው ግጥም በየትኛው የዘይቤ አይነት የተፃፈ ነው?
ሀ. ተነፃፃሪ ለ. ግነት ሐ. ተለዋጭ መ. ሰውኛ
38. ራቤ ጥማቴ እርዛት ስስቱ፤
ይደበድቡኛል ባንድ እየዶለቱ፡፡ ግጥሙ የተፃፈበት ዘይቤ--------------ነው፡፡
ሀ. ተለዋጭ ለ. ሰውኛ ሐ. ግነት መ. ተነፃፃሪ
39. ጎረቤቴ ወረግቡ ስለሆነች እንከባከባታለሁ፡፡ በዚህ ዓ.ነገር ውስጥ የተሰመረበት ፈሊጣዊ አባባል አቻ
ትርጉም-------------ነው፡፡
ሀ. ምግባረ ሰናይ ለ. መልከ መልካም ሐ. የደረሰች እርጉዝ መ. ሁሉንም ተግባቢ
40. አቶ ሰሎሞን የአየው ነገር ሆዱን በላው፡፡ የተሰመረበት ፈሊጥ ፍቺ----------------ነው፡፡
ሀ. አመመው ለ. አቃጠለው ሐ. አሰቃየው መ. አሳዘነው
41. ወ/ሮ መሰረት ለወዳጃቸው ለቅሶ ደረት ጥለው ነበር፡፡ የተሰመረበት ፈሊጥ ፍቺ --------ነው፡፡
ሀ. አዝነው ለ. ወድቀው ሐ. ደረታቸውን አሳይተው መ. ጎብጠው
42. "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል" ከሚለው ምሳሌያዊ ዓነጋገር ጋር የሚቃረነው የቱ ነው?
ሀ. የቸኮለ አፍሶ ለቀመ ለ. የታገሰ ከሚስቱ ይወልዳል
ሐ. የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሊጥ ሐ. ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
43. ስንቅህን ባህያ----------------------፡፡ ይህን ምሳሌያዊ ንግግር ሊያሟላ የሚችለው ሀረግ የቱ ነው?
ሀ. አመልህን በጉያ ለ. በሪህን ወደገበያ ሐ. ጭነህ ተጓዝ መ. እህልህን ወደገበያ
44. ስነቃል ሚለው ሲተረጎም ስነ ማለት ውበት፣ ለዛ፣ መልክ ወዘተ የሚል ሲሆን ቃል ደግሞ ንግግር፣
በቃል የሚገለፅ የሚለውን ይይዛል፡፡ በአንድነት ሲገለፅ ደግሞ ስነቃል የአነጋገር ለዛ፣ ውበት የሚልን ፍቺ
ይሰጣል፡፡ ይህ አንቀፅ የተፃፈበት ስልት ምንድን ነው?
ሀ. ብያኔ ለ. ገለፃ ሐ. ማዋገን መ. ምስያ
45. ተደራሲው እንዲመራመር እና የበለጠ እንዲፈላሰፍ እድል የሚሰጠው ስነቃል የቱ ነው?

113
ሀ. ተረት ለ. ምሳሌያዊ ዓነጋገር ሐ. ሀተታ ተፈጥሮ መ. እንቆቅልሽ
46. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ስነቃልን አስመልክቶትክክል የሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ያልተፃፈ ነገር ሁሉ ስነ ቃል ሊባል ይችላል፡፡
ለ. ስነቃል ግለሰባዊ ባለቤት የለውም፡፡
ሐ. ስነቃል ከስነፅሁፍ የሚለየው ኪናዊ ስላልሆነ ነው፡፡
መ. ስነ ቃል ሊለወጥ የማይችል የህዝብ ሀብት ነው፡፡
47. ግጥም ተለክቶ የሚያልቀው በምን ውስጥ ነው?
ሀ. ቀለም ለ. ስንኝ ሐ. ሀረግ መ. ቤት
48. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል የልቦለድን ምንነት በትክክል የሚገልፀው የትኛው ነው?
ሀ. ልቦለድ ሙሉ በሙሉ እውነት የሆነ የኪነጥበብ ስራ ነው፡፡
ለ. ልቦለድ ተጨባጭ እውቀትን ለማስተላለፍ የሚፃፍ ድርሰት ነው፡፡
ሐ. ልቦለድ ታሪኩ የሚያቅፈው መቼት በትክክል የሚገለፅበት ድርሰት ነው፡፡
መ. ልቦለድ የደራሲው ምናባዊ ፈጠራና ኪነጥበባዊ ስራ ነው፡፡
49. ስነፅሁፍን በተመለከተ ከሚከተሉት አማራጮች መካከል ትክክል የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ከኢ-ልቦለድ ፅሁፎች መካከል አንዱ ስነፅሁፍ ነው፡፡
ለ. ውበት ባለው ቋንቋ ተቀነባብሮ የሚቀርብ የኪነ ጥበብ ስራ ነው፡፡
ሐ. የስነፅሁፍ ዋናው ጉዳይ ቋንቋ ነው፡፡
መ. ከልቦለድ ዘርፎች መካከል አንዱ ስነፅሁፍ ነው፡፡
50. ሰብለ ወንጌልና በዛብህ በፍቅር ይወድቃሉ፡፡ ፊት አውራሪ ይህን እንዳወቁ አንድ መናጢ ድሃ ልጄን
ለፍቅር እንዴት ያስባታል በማለት ይበሳጫሉ፡፡ ከዚያም በዛብህን ለመቅጣት ይዝታሉ፡፡ ይህ ፅሁፍ
ከልቦለድ አላባውያን የቱን ያሳያል፡፡
ሀ. ታሪክ ለ. መቼት ሐ. ገፀባህርይ መ. ግጭት
51. አንድ ተውኔት መድረክ ላይ በሚቀርብበት ጌዜ ታዳሚን የማዝናናትና መድረክ የመምራት ሚና የማን
ነው?
ሀ. የደራሲው ለ. የከዋኙ ሐ. የአድማጩ መ. የአጃቢው
52. የተውኔት ገፀባህርያት ከልቦለድ ገፀባህርያት የሚለዩት በምንድን ነው?
ሀ. በምናብ ሳይሆን በዕውን በመታየት
ለ. የገሀዱን አለም ሰዎች ፍንትው አድርገው በማሳየት
ሐ. በአይነ ህሌና ድርጊት በመፈፀም
መ. ለስሜት ቅርብ በመሆን
53. በክርክር ወቅት ከተከራካሪ የማይጠበቅ ተግባር የትኛው ነው?
ሀ. የጊዜ ገደብን ማክበር ለ. ከርዕሱ አለመውጣት
ሐ. ሀሳቦችን ከአድማጭ ችሎታ በላይ ማቅረብ መ. ፍሬ ሀሳብን በቅደም ተከተል ማቅረብ
54. በሽታው እየተነሳ ያሰቃየዋል--------------እስካሁን ግን እርሱ የሰውን ነገር ከመጤፍ አልቆጠረውም፡፡
በክፍት ቦታው ገብቶ ትክክለኛ ትርጉምና አገልግሎት ሊሰጥ የሚችለው ስርዓተ ነጥብ የትኛው ነው?

114
ሀ. ፣ ለ. ፤ ሐ. / መ. ፡-
55. ከሚከተሉት ውስጥ በትክክለኛ ስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም የተፃፈው የትኛው ዓ.ነገር ነው?
ሀ. ከበደ፣ አስቴርና በቀለ ወደ ትምህርት ቤት ሔዱ፡፡
ለ. ከበደ፣ አስቴርና፣ በቀለ ወደትምህርት ቤት ሄዱ፡፡
ሐ. ከበደ፣ አስቴር፣ በቀለ ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ፡፡
መ. ከበደና አስቴር፣ በቀለ ወደትምህርት ቤት ሄዱ፡፡
56. በውይይት ሂደት የትኛውን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ ነው?
ሀ. የትኛውም የውይይት ተሳታፊ የሚያቀርበውን ሀሳብ ሙሉ በሙሉ መቀበል
ለ. ንግግርን በመረጃና በምሳሌ አስደግፎ በማቅረብ የውይይቱን ተሳታፊ ቀልብ መሳብ
ሐ. በውይይቱ ሂደት የራስ ሀሳብ ብቻ እንዲንሸራሸር ተሳታፊዎችን ማግባባትና ማስገደድ
መ. በውይይት ሂደት ከራስ ጋር የማይስማማ አቋም የሚያራምድ ተሳታፊን መገሰፅ
57. ከሚከተሉት ውስጥ በደብዳቤ አፃፃፍ ስርዓት መሰረት ለሁሉም የደብዳቤ አይነቶች የጋራ ያልሆነው
የትኛው ነው?
ሀ. የላኪው አድራሻ ለ. የተቀባዩ አድራሻ ሐ. ቁጥር መ. ቀን
58. በቤተመፃህፍት አጠቃቀም መመሪያ መሰረት ስህተት የሆነው መመሪያ የትኛው ነው?
ሀ. ጠቃሚ በሚመስል ሀሳብ ላይ አለማስመር ለ. የጎንዮሽ ወሬ አለማውራት
ሐ. የግል መፃህፍትን ይዞ መግባት መ. የተጠቀምንባቸውን መፃህፍት በአግባቡ ማስቀመጥ
59. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል በክርክር አቀራረብ ወቅት የማይተገበረው የትኛው ነው?
ሀ. ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ አለማድረግ
ለ. መረጃዎችን ማደራጀትና አለባበስን ማስተካከል
ሐ. ለተከራካሪዎች፣ ለአድማጮችና ለዳኞች ክብር መስጠት
መ. ንግግርን ከአድማጮች ችሎታ ጋር የተጣጣመ ማድረግ
60. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል መማርን የሚጠይቁት የቋንቋ ክሂሎች የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ማዳመጥና መፃፍ ለ. መናገርና ማንበብ ሐ. ማንበብና መፃፍ መ. ማዳመጥና መናገር
61. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች መካከል በመንስኤና ውጤት የተገለፀው የትኛው ነው?
ሀ. ሾፌሩ ሰክሮ ስለነበር አደጋ ሊከሰት ችሏል፡፡
ለ. ትምህርቱን በአግባቡ ቢማርም ጥሩ ውጤት አላመጣም፡፡
ሐ. በተሸለምኩት ገንዘብ መፅሃፍ ገዛሁበት፡፡
መ. በጣም ቢደክመኝም መምጣቴ ግን አይቀርም፡፡
62. ቃለጉባኤ ሲፃፍ ከአባላት ስም ዝርዝር ቀጥሎየሚሰፍረው ጉዳይ ከሚከተሉት መካከል የትኛው ነው?
ሀ. የተሳታፊው ሀሳብ ለ. የስብሰባው ቦታና ጊዜ ሐ. የውይይቱ አጀንዳ መ. የውሳኔ ሀሳብ
63. አንድ ሰው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የቀረቡ መረጃዎችን ለማንበብ በዋናነት ሊጠቀምበት የሚችለው
የንባብ ዘዴ የትኛው ነው?
ሀ. ጥቅል ንባብ ለ. ግርፍ ንባብ ሐ. ሂሳዊ ንባብ መ. ምርምራዊ ንባብ
64. ከሚከተሉት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ይበልጥ የሚያከራክረው የትኛው ነው?

115
ሀ. ስኬት በፆታ ላይ ይመሰረታል፡፡ ለ. ንባብ አዕምሮ ማደሻ ነው፡፡
ሐ. ፅናት ስኬት ላይ ያደርሳል መ. ዓለማችን በችግሮች ታምሳለች፡፡
65. ሀቅ ላይ ለተመሰረተ ፅንሰሀሳብ ምሳሌ የሚሆነው የትኛው ዓ.ነገር ነው?
ሀ. በልጅነቴ የተለየኋትን እህቴን አንድ ቀን የማገኛት ይመስለኛል፡፡
ለ. የሀገራችን ድምፃውያን የዜማ ስልት በጣም ተወዳጅ እየሆነ ነው፡፡
ሐ. በጣም ከምወዳቸው ቀኖች መካከል አንዱ ሰኞ ነው፡፡
መ. የአፈር መሸርሸር ለበርሃማነት መስፋፋት ምክንያት ይሆናል፡፡
66. የተናጋሪውን የመናገር ብቃት ወይም አንደበተ ርቱዕነት ከማሳየት አንፃር ውስንነት ያለበት የንግግር
አይነት የትኛው ነው?
ሀ. የዝግጅት ንግግር ለ. የቅስቀሳ ንግግር ሐ. የፅሁፍ ንግግር መ. የማነቃቂያ ንግግር
67. ከሚከተሉት አማራጮች መካከል የዘገባ ዋነኛ መገለጫ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. እውነተኛ ክስተት ላይ መመስረት ለ. ውብና እምቅነት ያላቸውን ቃላት መጠቀም
ሐ. ምናባዊ ትረካ ማካተት ሐ. ለዘጋቢው እይታ ቅድሚያ መስጠት
68. እያነበቡ ማስታወሻ በመያዝ ሂደት በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውለው የቱ ነው?
ሀ. ያነበቡትን ፍሬ ሀሳብ መፃፍ ለ. ያነበቡትን ቃል በቃል መያዝ
ሐ. ያነበቡትን ሸምድዶ መያዝ ሐ. ያነበቡትን በጥንቃቄ መገልበጥ
69. አንደን ፅሁፍ በራሳችን አባባል አሳጥረን ለመፃፍ ስንፈልግ ልንከተላቸው ከሚገቡ ተግባራት መካከል
የማይካተተው የትኛው ነው?
ሀ. በፅሁፉ አጠቃላይ ሀሳብ ላይ ማተኮር ለ. የፅሁፉን ድምፀት ማጤን
ሐ. ፅሁፉን ደጋግሞ ማንበብ መ. የፀሃፊውን ቃላት እንዳለ መጠቀም
70. ማንኛውም ተማሪ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም --------- ትምህርትቤቱን ህግና ደንብ ማክበርና መልካም
ስነምግባር መላበስ አለበት፡፡ በዓ.ነገሩ ባዶ ቦታ ላይ መግባት ያለበት ስርዓተ ነጥብ የትኛው ነው?
ሀ. ፣ ለ. ፤ ሐ. ? መ. !

መመሪያ ሶስት፡- ከተራ ቁጥር 71-75 ድረስ ለሚገኙ የቅኔ ጥያቄዎች እንደአጠያየቃቸው መልስ ስጡ፡፡

71. አንተ የጓሮ ፍየል ብትስል ብታነጥስ፤


ዛሬ ባልነውና ቅጠልም አልበጥስ፡፡ የዚህ ቅኔያዊ ግጥም ህብረቃል የቱ ነው?
ሀ. ቅጠል ለ. አልበጥስ ሐ. ባልነውና መ. ባል
72. ቢነግሩሽ አትሰሚ ቢጠቅሱሽ አታይ፣
ዝግ ብለሽ ሂጂ ብር ብር አትበይ፡፡ የዚህ ቅኔያዊ ግጥም ሰሙ የቱ ነው?
ሀ. ሁልጊዜ ገንዘብ አትጠይቂ ለ. ቢጠቅሱሽ ማየት አትችይም
ሐ. በፍጥነት እየሮጥሽ አትሂጅ መ. ለወደፊት ሲነግሩሽ ብትሰሚ መልካም ነው
73. ማር ቀምሼ አላውቅም እኔ ወንድማችሁ፣
የልደታ ልጆች ተማሩ እባካችሁ፡፡ የቅኔው ወርቅ--------ነው፡፡

116
ሀ. ምር ስጡኝ ለ. እውቀት ቅሰሙ ሐ. የሚላስ ማር አቅምሱኝ መ. እውቀት አካፍሉ
74. "እድሜ ይስጠኝ እንጅ ብድሬን እከፍላለሁ፡፡ በሚለው ዓ.ነገር የተሰመረበት ሀረግ እማሬያዊ ፍ---------
ነው፡፡
ሀ. እዳየን ከላየ አወርዳለሁ ለ. ወረታየን እመልሳለሁ
ሐ. ቂሜን አወራርዳለሁ መ. ውለታየን እመልሳለሁ
75. ከሚከተሉት ዓ.ነገሮች መካከል ለግላዊ አስተያየት ምሳሌ የሚሆነው የትኛው ነው?
ሀ. ወርቅን በማግኔት መሳብ አይቻልም፡፡
ለ. ሳይንስ በተጨባጭ መረጃ ላይ የተደገፈ አስተሳሰብ ነው፡፡
ሐ. ከእንቅልፍ ተነስቶ ከማጥናት ይልቅ አጥንቶ መተኛት ይሻላል፡፡
መ. ከአጭር ልቦለድ ባህርያት መካከል አንዱ ቁጥብነት ነው፡፡

መመሪያ አራት፡- ከተራ ቁጥር ከ76-80 ያሉ ጥያቄዎች ግጥሙን መሰረት አድርገው የቀረቡ ሲሆን
ከቀረቡት አማራጮች መካከል ተገቢውን መልስ በመምረጥ ጥያቄ ወረቀቱ ላይ አጥቁር/ሪ፡፡

የሱን አለመቻል
የኔማ ጓደኛ
ይኸው እስከዛሬ
ፊቴ ተጎልቶ፤
አትችልም ይለኛል
የሱን አለመቻል
እኔ ውስጥ ከቶ፡፡
(ምንጭ፡- ይስማዕከ ወርቁ፡፡ (2002)፡፡ የቀንዳውጣ ኑሮ)
76. ግጥሙ ስንት ሀረጋት አሉት?
ሀ. አራት ለ. ስድስት ሐ. ስምንት መ. አስር
77. ግጥሙ ባለስንት ስንኝ ነው?
ሀ. ሶስት ለ. ስድስት ሐ. ሁለት መ. አራት
78. ግጥሙ በየትኛው የግጥም ቤት የቀረበ ነው?
ሀ. ሰንጎ መገን ቤት ለ. ቡሄ በሉ ቤት ሐ. የወል ቤት መ. ፀጋየ ቤት
79. የግጥሙ ቤት ምንድን ነው?
ሀ. ል ለ. ቶ ሐ. ሬ መ. ኛ
80. የግጥሙ ቤት መምቻ ቃል የቱ ነው?
ሀ. ተጎልቶ ለ. ይለኛል ሐ. አለመቻል መ. ከቶ

117

You might also like