You are on page 1of 72

ከፍል..

1 
የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የንብረትአስተዳደር መመሪያ

DRAFT
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
በመመሪያ ላይ የተካተቱት ዋና ዋና ኃሣቦች
ክፍል 1 ጠቅላላ መግቢያ

DRAFT
ክፍል 2 የቋሚ ንብረት አስተዳደር
ክፍል 3 የቋሚ ንብረት ቆጠራ
ክፍል 4 የእስቶክ አስተዳደር ሥርዓት
ክፍል 5 የንብረት አወጋገድ

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማርን፣ የምርምር እና

DRAFT
ማህበረሰብ አገልገሎትን፣ ቀልጣፋ ብቁ ተመራቂዎችን ማፍራት፣
ፍላጎትን መሰረት ያደረገ የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት እና
ችግርን ፈቺ የምርምር ውጤቶችን እና በፈጠራና ትምህርት፣
በምርምርና በማማከር የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
እድገት ማጎልበት አላማውን ከግብ እንዲመታ የንብረት
አስተዳደርን ዘመናዊ እና አንድ ወጥ ማድረግ ነው ፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባለቤትነት ስር የሚገኙ ንብረቶችን አንድ
ወጥ እና ዘመናዊ በሆነ የአሰራር ስርዓት ለማስተዳደር እንዲቻል

DRAFT
በተጨማሪም ዩንቨርስቲው በሚያወጣው መመሪያ መሰረት
እያንዳንዱ የመስሪያቤቱ ንብረት በአግባቡ የመያዝ፣ የመጠቀም እና
አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የማስወገድ ተግባር ለማከናወን ይህ
መመሪያ በዩኒቨርስቲ ንብረት አስተዳደር ውሰጥ የሚሰሩ ኃላፊዎች
እና ሠራተኞች የንብረት አስተዳደር ሥራዎች አተገባበር ላይ ዝርዝር
አሠራር ግልፅ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም የአሰራር ወጥነት እንዲኖር
ያደርጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ክፍል ሁለት ፡- የቋሚ ንብረት አስተዳደር
2.1 የቋሚ ንብረት ትርጓሜ
 ቋሚ ንብረት ማለት ግዙፋዊ ህልዎት ያለው፣
የተናጠል ዋጋው 5000.00/ከአምስት ሺህ/ብር

DRAFT
በላይ ለሆኑ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ንብረት
አስተዳደር መመሪያ የሚወሰን ፣ ከአንድ ዓመት
በላይ ለሆነ ግዜ የጠቀሜታ እሴት የሚኖረው እና
አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ንብረት ሲሆን
እንደ የቢሮ ዕቃ፣ ኮምፒውተር፣ ተሽከርካሪ፣ ሕንፃ፣
የመሳሰሉትን ይጨምራል ፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የዩኒቨርስቲዉ ቋሚ ንብረቶችን ከተገዛበት ግዜ ጀምሮ ያሉ
መረጃዎችን ለእያንዳንዱ ንብረት የታሪክ ማህደር በመክፈት

DRAFT
በትክክልና በተሟላ ሁኔታ ወይም በኤሌክትሮኒክስ መረጃ ስርዓት
በመጠቀም ተመዝግበው መያዝ አለባቸው፡፡
 የንብረት አስተዳደር ተግባርን የሚያከናውነው የስራ ክፍል
የተጠናቀረ መረጃ የያዘ የቋሚ ንብረት መመዝገቢያ ካርድና
መዝገብ መያዙን የመከታተልና መቆጣጠር ኃላፊነት አለበት፡፡
 የንብረቱ ተጠቃሚ ሰዎችን የንብረት ምዝገባ ካርድ መያዝ
አለባቸው፡፡
 ለእያንዳንዱ ቋሚ ንብረት የራሱ የሆነ መለያ ቁጥር መስጠት ያለባቸው ሲሆን
ይህ ቁጥር በቋሚ ንብረቱ ላይ መለጠፍ ወይም መፃፍ አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


የቀጠለ………
 በየዓመቱ የቋሚ ንብረቶች ቆጠራ ማካሄድ አለባቸው፡፡የቋሚ ንብረቶቹ ያሉበት ተቋም
ወይም የሚገኙበት ቦታ ላይ ማናቸውም ለውጥ ቢኖር በቋሚ ንብረት ካርዱ ፣ በቋሚ
ንብረት መዝገብ እና በጠባቂዎች የንብረት ወይም የመጋዘን ኃላፊ ዝርዝሩን እንዲመለከት
መደረግ አለበት፡፡

DRAFT
 ንብረት ቆጠራ ሲደረግ ያልተገኙ ቋሚ ንብረቶች ሲያጋጥሙ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ
ሪፖርት ይቀርባል፡፡ በምርመራውም ሪፖርት ጉዳይ የወንጀል ድርጊት ያለው መሆኑ በማስረጃ
ሲደገፍ ለመስሪያ ቤቱ የሕግ ተግባርን ለሚከታተል የስራ ክፍል ሪፖርት ይደረጋል፡፡
 ዋጋቸው ከ4999.00/አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር/ በታች ሆነው የአገልግሎት
ዘመናቸው ከአንድ አመት በላይ የሆኑ ንብረቶች ለብክነት ሊዳረጉ ስለሚችሉ ለብቻ መዝግቦ
በመያዝ የወጪና ገቢ እንቅስቃሴያቸው ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፡፡
 ቋሚ ንብረት ለአንድ የስራ ክፍል ወይም ሰራተኛ ወጪ ሆኖ ከተሰጠ በኋላ ወደ መጋዘን
ሳይመለስ በዚያው ወደ ሌላ ሰራተኛ ወይም የስራ ክፍል በርክክብ ከተላለፈ በስቶክ ያለው
የቋሚ ንብረቱ መዝገብና ካርድ ከዚህ አኳያ መስተካከል አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የተገዙ ንብረቶች የመጀመሪያ ዋጋ የሚረጋገጠው በንብረት
ካርዱ ላይ የተመዘገበውን የኢንቮይስ ዋጋ መሰረት በማድረግ ነው
 ያለፉት ግዥዎች ዋና ኢንቮይስ በማይገኘበት ግዜ የመንግስት
መስሪያ ቤቶች የመጀመሪያውን ዋጋ የሚገምቱት ተመሳሳይ

DRAFT
ወይም አንድ አይነት ንብረቶች በተመሳሳይ ግዜ የተገዙበትን ዋጋ
ኢንቮይስ መሰረት በማድረግ ይሆናል፡፡ እነዚህ ተሟልተው
ካልተገኙ ዋጋው በግምት ተተምኖ ይሰራል፡፡
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መስሪያ ቤቶች ያከናወኑዋቸውን የግንባታ
ስራዎች እንደ ቋሚ ንብረቶች በተለየ መዝገብ መመዝገብ
አለባቸው፡፡
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ህንፃዎችን ለመስራት የተደረገን የቅድመ
ግንባታ ቀጥተኛ ወጪዎች እና የአስተዳደርና ምከር አገልግሎት
እና የመሳሰሉትን ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎችን በቋሚ ንብረት
ካርድ መመዝገብ አለባቸው፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


የቀጠለ……
 በግንባታ ላይ የሚገኙ ስራዎችን የሚተምኑት የተጠናቀቁት
ስራዎች የመተመኛ ስሌት ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ
ይሆናል፡፡
 ለሕንፃው የእርጅና ቅናሽ የሚታሰበው ሕንፃውን ለመስራት
ወይም ለመግዛት የተደረገውን ጠቅላላ ወጪ በመነሻነት

DRAFT
በመውሰድ ከዚሁ ሂሳብ ላይ በየዓመቱ አምስት በመቶ በመቀነስ
ይሆናል፡፡ሕንፃውን ለመስራት ወይም ለመግዛት የተደረገው
ጠቅላላ ወጪ የማይታወቅ ከሆነ የህንፃው ወቅታዊ የመተኪያ
ዋጋ እንደመነሻ ይወሰዳል፡፡
 ህንፃዎችን በሽያጭ ማስወገድ ሲፈለግ እንደቅደም ተከተላቸው
የተቀመጡትን ደንቦች ተከትሎ የህንፃውን ዋጋ መተመን
ይቻላል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


በመጋዘን ውስጥ ያሉ ቋሚ ንብረቶች ገና ጥቅም ላይ ያልዋሉ ወይም
ጥቅም ላይ ውለው የተመለሱ ናቸው፡፡ እነዚህ ቋሚ ንብረቶች
የስቶክ ክፍል በመሆናቸው የሚተዳደሩት በስቶክ አስተዳደር ስርዓት
ነው፡፡

DRAFT
2.5. በግንባታ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረቶች
በግንባታ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረቶች ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው
ስራ ላይ እንዳሉት ቋሚ ንብረቶች አይቆጠሩም፡፡ ይሁን
እንጂ በመጋዘን ውስጥ እንዳሉ ቋሚ ንብረቶች ዓይነትም
አይደሉም፡፡ ስለዚህ እነሱን በተመለከተ ልዩ አካሂድ
ያስፈልጋል፡፡ የሚከተሉት መከናወን ይኖርባቸዋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


በሂደት ላይ ያሉትን የግንባታ ሥራዎች መለየት ፡- የንብረት
አስተዳደር ክፍሉ የግንባታውን ሂደት ለመከታተል ኃላፊነት
ከሌለበት ወይም በእንደዚህ ዓይነት ንብረቶች ላይ የተሟላ መረጃ
ከሌለው በመ/ቤቱ ስር ላሉ ለሚመለከታቸው ለሁሉም የስራ
ክፍሎች በሂደት ላይ ስላሉ ግንባታዎች የሚከተለውን የያዘ ዝርዝር
መረጃ የሚጠይቅ ደብዳቤ መላክ ይኖርበታል፡፡

DRAFT
1. የንብረቱ አይነት (ሕንፃ፣ ፋብሪካ፣ መንገድ ወዘተ.)
2. የሚገኝበት ቦታ
3. ባለቤትነት
4. ግንባታው የተጀመረነት ቀን
5. ግንባታው የተጠናቀቀበት ደረጃ(በመቶኛ)
6. ግንባታው ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅበት ግዜ
7. ግንባታው እስካሁን የፈጀው ዋጋ፣ ካልሆነም ግምት ዋጋው
8ሥራው በሥራ ተቋራጭ የሚሰራ ከሆነ የኮንትራቱ ዋጋና እስካሁን
የተደረገ ክፍያ
9. ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝሮች የሚደግፍ ሰነዶች መሟላት
ይገባቸዋል
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በስራ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረቶች በእያንዳንዱ
ሰራተኛ ጥበቃ ስር የሚገኙትንና ለጋራ አገልግሎት የዋሉትን ሁሉ

DRAFT
ያጠቃልላል፡፡ለምሳሌኮምፒውተር፣ወንበሮች፣ጠረጴዛዎች፣መደርደሪ
ዎች፣ ፕሪንተሮች የመሳሰሉት በቀላሉ በእያንዳንዱ ሰራተኛ ጥበቃ
ስር ተለይተው ሊታወቁ የሚችሉ የንብረት አይነቶች እና
ሕንፃ፣መኪና፣ማሽነሪዎች ያሉትን ደግሞ በስራ ክፍል ደረጃ ካልሆነ
በስተቀር በየትኛው ሰራተኛ ስር እንዳሉ ለመለየት የሚያዳግቱ
የንብረት አይነቶች ሲሆኑ እነዚህን መሰረት በማድረግ አጠቃላይ
ቆጠራ በሶስት ደረጃ ተከፍሎ ቆጠራው ይከናወናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ሁሉም ቋሚ ንብረቶች መቆጠራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
 በቆጠራው ቅፅ ላይ በተተወው ክፍት ቦታ ላይ የንብረቱን ሁኔታ
ጥሩ፣የተጎዳ፣የተበላሸ በማለት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡
 እያንዳንዱ ንብረት መቆጠር ስለሚኖርበት የታሸጉ ፓኮዎች ቢኖሩ እንኳን

DRAFT
በመክፈት ቆጥሮ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
 የቆጠራ ቡድን አባላቱና ተቆጣጣሪው እያንዳንዱን ቆጠራ የተከናወነበትን ቅፅ
ላይ መፈረም ይገባቸዋል፡፡ ቆጠራው እስኪጠናቀቅ ድረስ ቋሚ ንብረቶችን
ከመጋዘን ማውጣት ማቆም ካልተቻለም የሚወጡት ንብረቶች ሁሉ በቆጠራው
ቅፅ ውስጥ መመዝገባቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
 ቆጠራው ከተጀመረ በኋላ ወጪ የሚደረጉ ቋሚ ንብረቶች ሁሉ በተለየ ዝርዝር መያዝ
የሚገባቸውንና ዝርዝሩም ለሚከታተለው ለቋሚ ንብረት አስተዳደር ክፍል መላክ
ያለባቸው መሆኑን ለመጋዘን ክፍል መመሪያ መስጠት ይገባል፡፡
 የቆጠራው ቅፅ በሁለት ኮፒ ተዘጋጅቶ ግልፅ የእጅ ፅሁፍ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ
በሁለቱም ዓምዶች ላይ መሙላት ይኖርበታል፡፡
 በመጨረሻም የቋሚ ንብረት አስተዳደር የስራ ክፍል ኃላፊ ትክክለኛነቱን
አረጋግጦ ይፈርማል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ለቆጣሪዎች የተሰጡ የቆጠራ መመዝገቢያ ሁሉ የተበላሹትም ጭምር
ከቆጠራ በኋላ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
 የቆጠራ ቅፆችን ሁሉ ማረጋገጥ፣ያልተሟሉትን ማሟላት፣ ከዚያም
በቅድሚያ ቆጣሪዎችና ተቆጣጣሪዎች በቆጠራ ቅጾቹ ላይ ከፈረሙ በኋላ

DRAFT
በቋሚ ንብረት አስተዳደር የስራ ክፍል ኃላፊ ተረጋግጦ ይፈርማሉ፡፡
 አገልግሎት ሊሰጡ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ያሉ ንብረቶች ዝርዝራቸው
ከተዘጋጀ በኋላ ንብረቶቹን ወደ አገለገሉ ስቶኮች መጋዘን እንዲገቡ
ማድረግ ያስፈላጋል፡፡
 በስራ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረቶችና ሌሎችም ዋጋቸው ትንሽም ቢሆን
እድሜያቸው ግን ረጅም የሆኑ ዕቃዎችን በተጠቃሚዎች እጅ በሚገኙ
ቋሚ ንብረቶች መቆጣጠሪያ ካርድ ላይ መመዝገብ ያስፈልጋል(ለናሙና
በተጠቃሚዎች እጅ ላይ የሚገኙ ቋሚ ንብረቶችን መቆጣጠሪያ
ካርድ(UC))፡፡
 ቋሚ ንብረቶቹ በሙሉ በቋሚ ንብረት መዝገብ ላይ መመዝገብ
ያስፈልጋል፡፡
 ቆጠራው እንዴት እየተከናወነ፣ከጥቅም ውጭ የሆኑት ንብረቶች ወደ
በአስተዳደርና
መጋዘንተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
ስለመመለሳቸው፣ንብረቶች የተዘጋጀ
ስለመመዝገባቸው የሚገልፅ ሪፖርት
4.1. የስቶክ ቁጥጥር ሥርዓቶች
 የስቶክ ቁጥጥር ሥርዓት በእያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት መዘርጋት ያለበት
ሲሆን በስቶክ የሚቀመጡ ዕቃዎች ለጤና አደገኞች ወይም ባላቸው ዋጋና በቀላሉ
የመንቀሳቀስ ባህሪይ ምክንያት ለስርቆት የሚጋለጡ ናቸው ተብሎ ሲታመን ልዩ

DRAFT
ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡
 የስቶክ ቁጥጥር አሰተማማኝ ተገቢና መሰረታዊ የስቶክ መዛግብትን መሰረት ያደረገ
መሆን አለበት፡፡ እነዚህ የስቶክ መዛግብት በተለምዶ የስቶክ ካርዶች እና ቢን ካርዶች
በመባል የታወቃሉ፡፡
 የዕቃዎች መቀበያና ማውጫ ሰነዶች የሚገኝበት መንግድ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸው
ሆነው አሰቀድመው የታተሙና ተከታታይ ቁጥጥር የሉዋቸው መሆን አለባቸው፡፡
 ንብረት ገቢ እና ወጪ ከተደረጉ በኋላ በተቻለ ፍጥነት በዋናው የስቶክ መዛግብቶች ላይ
ማሻሻያ መደረግ አለበት ፡፡
 የንብረት መጉደል ወይም መጭበርበር ተከስቷል የሚል ጥርጣሬ ሲኖር ንብረቱ ከመቀበል
ጀምሮ ማውጣትን፣ ጥቅም ላይ ማዋልንና አግባብ ያለው ሆኖ ሲገኝ እስከ ማስወገድ
ድረስ ያለውን እንስቅስቃሴ ወደ ኋላ ሄዶ የታተሙት ሰነዶች ቁጥራቸው ተከታታይና
ይዘታቸው ያልተደለዘ ለውጥ ያልተደረገባቸው መሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


4.3 መሰረታዊ የስቶክ መዛግብቶች

DRAFT
 የዚህን መመሪያ ድንጋጌዎች በማይፃረር መንገድ
በሚዘጋጅ የኤሌክትሮኒክስ ዘዴ የስቶክ መረጃን መያዝና
ማስተዳደር ይችላሉ፡፡

 የስቶክ መረጃቸውን በተለየ ሁኔታ ለመያዝ አስፈላጊ ሆኖ


ሲገኙት ለዩንቨርስቲው የበላይ ሀላፊዋች ጥያቂ በማቅረብ
ሲፈቀድ መረጃውን በተለየ ፎርም ተመዝግቦ መያዝ
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 የስቶክ ቆጠራው የሚያካሂደው ኮሚቴ የቆጠራውን
ዝርዝር ሪፖርት ለንብረት አስተዳደር ተግባራትን
ለሚያከናውነው የስራ ክፍል ኃላፊ ማቅረብ አለበት፡፡

DRAFT
 የስቶክ ቆጠራው ሪፖርት በስቶክ መዝገቡ፣በዕቃ
መቀበያ ሰነድ፣ በስቶክ መጠየቂያ እና በስቶክ ማውጫ
ሰነድ እና በትክክለኛው ቀሪ ስቶክ መካከል የታዩትን
ማናቸውንም ልዩነቶች በዝርዝር መገለፅ አለበት፡፡
ልዩነቶች ከታዩም በዚህ መመሪያ መሰረት ንብረቱ
እንዲተካ ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.1 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ንብረት አወጋገድ
 ንብረቱ ለመስሪያ ቤቱ አላማ የማይፈለግ ሲሆን
 ንብረቱን ይዞ መቀጠል የሚያስከትለው ወጪ ከፍተኛ በመሆኑ የማያዋጣ ሲሆን
 በልዩ ልዩ ምክንያት ንበረቱ የሚፈልግበትን አገልግሎት ብቃት መስጠት የማይቻል

DRAFT
ወይም ከአገልግሎት ወጪ ሲሆን
 ዪንቨርስቲው ከሚኖረው የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የሥራ ዕቅድ አንፃር ትርፍ
መሆኑ ሲታመን
 ከላይ በተገለፀው መልኩ የማይፈለጉ ንብረቶችን በወቅቱ ማስወገድ አለባቸው
ሲሆን የነጠላ ዋጋቸው ከ ብር 5000 /አምስት ሺ ብር/ በላይ የ ሆኑ ንብረቶች
ተሰባስበው ለማስወገድ ስልጣን በተሰጠው በዩንቨርስቲው በበላይ አካል ውሳኔ
እንዲወገድዱ ያደረጋል፡፡ሆኖም የነጠላ ዋጋቸው ከ ብር 4999 /አራት ሺህ ዘጠኝ
መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር/ / በታች ቢሆንም በአንድ ግዜ ለሽያጭ የሚቀርቡት
ንብረቶች ዋጋ ከብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር / በላይ ከሆነ
በዩንቨርስቲው በበላይ አካል የሚወገዱ ይሆናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 በዩንቨርስቲው ንብረቶችን በባለቤትነት የመከታተል ኃላፊነት
የተሰጠው የስራ ክፍል የሚወገድ ንብረት ዝርዘርን በቅጽ ሞልቶ

DRAFT
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የበላይ ኃላፊ በወቅቱ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የበላይ ኃላፊ የቀረበለትን መጠየቂያ ቅጽ
መርምሮ ለመንግስት ንብረቶች አስወጋጅ ኮሚቴ ይመራል፡፡
 የዩንቨርስቲው ንብረቶች አስወጋጅ ኮሚቴ የተመራለትን
መጠየቂያ ቅጽ መርምሮ በዚህ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን
ይፈጽማል፡፡
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የበላይ ኃላፊ ከንብረት ሽያጭ ውጤት
በስተቀር ከመንግሰት ንብረቶች አስወጋጅ ኮሚቴ የቀረበለትን
ንብረቶች በወቅቱ እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ንብረት ለማስወገድ የሚችሉባቸው ስድሰት አማራጮች ዘዴዎች
አሉ፤-

DRAFT
5.3.1ለሌላ የመንግሰት መስሪያ ቤት በማዘዋወር / ማስተላለፍ/፤
 ንብረትን ለህዝብ በሐራጅ ወይም በጨረታ መሸጥ
የሚያስከትለው ወጪ የሚታወቅ ስለሆነ የአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ለማስወገድ የፈለጉትን ንብረት ወደ ሌላ የመንግስት
መስሪያ ቤት ለማዘዋወር ይቻል እንደሆነ በቅድሚያ ጥረት
ማድረግ አለባቸው፡፡
 በመንግሰት መስሪያ ቤቶች መካከል የሚደረገው የንብረት
ዝውውር የሚፈፅመው የወቅቱን የንብረቱን ዋጋ ግምት
በመመዝገብ መሆን አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.3.2 ባሉበት ሁኔታ ለህዝብ በጨረታ ወይም በሐራጅ
በመሸጥ፤
ንብረትን በጨረታ ወይም በሐራጅለመሸጥ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዋች፤
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የዩንቨርስቲ ንብረትን በጨረታ ወይም በሐራጅ በመሸጥ
ማስወገድ ይችላሉ፡፡

DRAFT
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተሻለ ዋጋ ለማግኘት፤ በፍጥነት ሽያጩን በመፈፀምና
የሚያስከትሉትን ችግሮች በመገምገም የተሻለውን የመሸጫ ዘዴዋች መምረጥ
ይኖርባቸዋል፡፡
 የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ለጨረታ ወይም ለሐራጅ የሚቀርቡትን ዕቃዋች የመነሻ
ዋጋ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የበላ ኃለፊ እንዲያፀድቀው ማቅረብ አለበት፡፡
 ተፈታተው እንዲሸጡ የተወሰነባቸው መለዋወጫዎች እንዲሁም ወዳቂ ብረታ ብረቶች
የጨረታ ወይም የሐራጅ መነሻዋጋ የመለዋወጫውን ወይም የብረታ ብረቱን ዓይነት
፤የገበያውን ሁኔታና ሌሎች መረጃዎችን መሰርት በማድረግ የተገመተ መሆን አለበት፡፡
 ማናቸውም የዩንቨርስቲው ወጪን ለመቀነስ ሲባል የሚሸጠውን ንብረት በአንድ ጊዜ
በጥቅል መሸጥ አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.3.3 ንብረቱን ፈታቶ በመለዋወጫነት ጥቅም ላይ
በማዋል ወይም መሸጥ
 ተሸከርካሪዎችና መሣሪያዎች ላይ ጠቃሚ አካሎችን ፈታቶ አግባብ
ባለው የዕቃ አስተዳደር አሠራር መሠረት ገቢ እንዲሆኑና ጥቅም ላይ

DRAFT
እንዲውሉ ወይም በጨረታ እንዲሸጡ ማድረግ ይቻላል፡፡
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአንድን ንብረት አካላት ፈታተው በመለዋወጫ ዕቃነት
መጠቀም ወይም መሸጥ የሚችሉት ንብረቱን ባለበት ሁኔታ መሸጥ የማይቻል
ሲሆን ወይም ባለበት ሁኔታ ከመሸጥ ይልቅ ፈታቶ መጠቀም ወይም መሸጥ
የበለጠ ጥቅም የሚያሰገኝ ሲሆን ነው፡፡
 ተፈታተው እንዲሸጡ የተወሰነባቸው መለዋወጫዎች የጨረታ መነሻ
ዋጋ የመለዋወጫውን ዓይነት፣የገበያውን ሁኔታና ሌሎች መረጃዎች
መሠረት በማድረግ ይገመታል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.3.4 ንብረቱን በስጦታ በመስጠት ማስወገድ፤
 የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ አንድን ንብረት ለሌላ የመንግሥት መስሪያ
ቤት ወይም በማህበራዊ አገልግሎና ልማት ተግባራት ላይ ለተሰማሩ
የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ወይም ለክልል መንግሥታት፣ለሰራተኞች

DRAFT
በስጦታ ሊያስተላልፍ የሚችለው ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት
ሊሆን ይችላል፡፡
 ንብረቱ ለመስሪያ ቤቱ ሥራ የማይውል ሲሆን፡፡

 ንብረቱ እንዲወገድ ቢደረግ የሚገኘው ገቢ ንብረቱን ለመሸጥ


ወይም ለመጠበቅ ከሚወጣ ወጪ በጣም አነስተኛ መሆኑ
ሲረጋገጥ፡፡
 ንብረቱ የሚተላለፍለት አካል በንብረቱ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ
አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ያግዛል ተብሎ በመሰሪያ ቤቱ ሲታመን፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.3.5 ንብረቱን በወዳቂነት ማስወገድ፤
 ከማናቸውም የንብረት ማስወገድ ሂደት የሚገኘው ገቢ ለማስወገድ
የሚደረገውን ወጪ የማይሸፈን ነው ተብሎ ሲገመት ንብረቱ በውዳቂነት
እንዲወገድ ይደረጋል፡፡የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴው የተሻለ ስለሚሆነው
ዘዴና ማናቸውንም ከውዳቂው ሊገኝ የሚችለውን የሽያጭ ገቢ
በማመለከት ምክር ይሰጣል፡፡በውዳቂነት እንዲወገዱ የሚደረጉ ሁሉ

DRAFT
በዩንቨርስቲው የበላይ ኃላፊ መጽደቅ አለባቸው፡፡
 ጠቃሚ አካሎቻቸው የተወሰዱባቸው ቀሪ ብረታ ብረቶች እና ውዳቂ
ብረታ ብረቶች የመነሻ ዋጋ የገቢውን ሁኔታና ሌሎች መረጃዎች መሠረት
በማድረግ መገመት አለበት፡፡
 በውዳቂ ብረታ ብረትነት እንዲወገዱ የተወሰነባቸውን ተሸከርካሪዎችና
መሣሪያዎች እንዲሁም ተፈታተው ጠቃሚ አካሎቻቸው የተወሰዱባቸው
ቀሪ ብረታ ብረቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ወይም በጨረታ እንዲሸጡ
ይደረጋል፡፡
 ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጋር በመሆን ሥነ ምህዳርን
በማይጎዳ ሁኔታ ውዳቂ ንብረቶችን በማቃጠልና በመቅበር ማሰወገድ
ይቻላል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


5.3.6 ንብረቱን በመቅበር ወይም በማቃጠል ማስወገድ፡፡
◦ የሚወገደው ንብረት ምንም ዓይነት የሰነምህዳር
ወይም የጤና ችግር የማያስከትል ከሆነ መስሪያ
ቤቱ በራሱ ኃላፊነት ንብረቶቹን ለይቶ በመቅበር

DRAFT
ወይም በማቃጠል ማስወገድ ይችላል፡፡
◦ የሚወገደው ንብረት ክፍተኛ የሥነምህዳር ወይም
የጤና ችግር የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ስለአወጋገዱ
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር
ንብረቱን በተገቢው መንገድ ማስወገድ
ይኖርበታል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


1) የህንጻ እና መኖሪያ ቤት አስተዳደር
የህንጻ ጥገና እና እድሳት አስተዳደር

DRAFT
2)
3) የምድረ ግቢ ጽዳት እና ውበት አስተዳደር
4) የህንጻዎች፣ ክፍሎች፣ አዳራሾች አገልግሎት፣ የህትመት
እና የዩቲሊቲ አቅርቦት ክትትል

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ሀ.መግቢያ
 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር የተሰጠዉን የመንግስት ውሳኔ
ተከትሎ የስራ ክፍሎቹን የአሰራር እና የአደረጃጀት ማስተካከያ ማድረግ ተገቢ መሆኑ

DRAFT
ታምኖበታል፡፡ በዚሁ መሠረት የዩኒቨርሲቲዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር ቀደም ሲል
የታዩበትን የአሰራር ክፍተቶችን በማስተካከል ውጤታማ እና ቀልጣፋ የስራ መመሪያ
ረቂቅ አዘጋጅቷል፡፡

ለ. ዓላማው
 መመሪያዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር አገልግሎትን በማሳለጥ እና ቀልጣፋ አሰራር
በመዘርጋት ውጤታማነትን ማረጋገጥ ነዉ፡፡

ሐ. የመመሪያው ወሰን
 መመሪያዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋሲሊቲ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እና በስሩ
በሚገኙ የዋናዉ ግቢ፤ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ፤ተፈጥሮ እና ኮምፒቲሽናል
ሳይንስ ኮሌጅ፤ የስነ ጥበብ ፣ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ
ሆስፒታል፣ ንግድ ስራ ትምህርት ቤት፣ኢትዮ.አርክቴክት ህንጻ ግንባታና ከተማ ልማት
ኢንስቲቲዩት፣ቴክኖሎጂ ኢንስቲዩት & እንስሳት ሕክምና እና ግብርና ኮሌጅ የፋሲሊቲ
አስተዳደር ቡድን መሪዎችን የሚመለከት ነው፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


የህንጻ ምዝገባ ስለማድረግ፣
 በዋናዉ ግቢ እና በስሩ በሚመሩት ግቢዎች የሚገኙትን

DRAFT
ህንጻዎች ለመመዝገብ የሚያስችል አሰራር ይዘረጋል፤ በየግቢዉ
ከሚገኙት አደረጃጀት ጋር በመሆን እንዲመዘገቡ ያደርጋል፤
የምዝገባ ዝርዝር መረጃ፣አሰራር እና ፎርማት ያወጣል፡፡
 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል፡፡ ተረክቦም
ይይዛል፡፡
 በዋናዉ ግቢ እና በስሩ በሚመሩት ግቢዎች የሚኖሩትን
የመረጃ ለውጦች እየተከታተለ ወቅታዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
 በህንጻ ምዝገባ እና አስተዳደር አጫጭር ስልጠናዎችን
በማዘጋጀት ለሚመለከታቸው ሰራተኞች ይሰጣል፤ተገቢውን
ክህሎት እንዲኖራቸዉ ያደርጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 በዋናዉ ግቢ እና በስሩ በሚገኙ ግቢዎች የሚገኙ ህንጻዎች
ስትራቴጂክ እና ዓመታዊ የጥገና ዕቅድ እና በጀት ያዘጋጃል፤ ዕቅዱን
ተከትሎም እንዲተገበር ተገቢዉን ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል፡፡

DRAFT
 መለስተኛ የህንጻ ጥገናዎች እና እድሳት በራስ ሀይል እንዲከናወኑ
ይደረጋል በየግቢዉ ተገቢዉን የአቅም ግንባታ ድጋፍ እና ክትትል
ያደርጋል፡፡
 ከፍተኛ የህንጻ ጥገናዎችን እና እድሳት እንዲከናወን ለሚመለከተው
ክፍል ጥያቄ ያቀርበል፡፡
 የእድሳት እና ጥገና አፈጻጸም ይገመግማል፤ሪፖርቶችን ያጠናቅራል፤
ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
 በዩኒቨርሲቲዉ የህንጻ እና መኖሪያ ቤቶች የደህንነት፤ጥገና እና
እድሳት ማኑዋል ያዘጋጃል፤ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 በተለይ ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ሙሉ ጥገና
ተደርጎ የተማሪዎች ማደሪያ፣መመገቢያ አዳራሽ፣ቤተ-
መጽሀፍት፣ላብራቶሪ፣መማሪያ ክፍሎች፣ መሰብሰቢያ
አዳራሾች፣ቢሮዎች ዝግጁ ይሆናል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በየግቢዉ ያሉትን የመኖሪያ ቤቶች ደህንነት ይከታተላል፡፡
 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በራሱ ያስገነባቸው ህንፃዎች ከፌደራል

DRAFT
ቤቶች አስተዳደር በኪራይ የተቀበላቸውን ቤቶች በቦርድ
የፀደቀው የቤቶች አስተዳደር ህግና ደንብ መሰረት ክፍት
ቤቶችን ለመምህራን አወዳድሮ ከፍተኛ ነጥብ ላላቸው
በተዋርድ ያሉትን ክፍት ቤቶችን ይሰጣል፡፡
 ቤት ለማግኝት ከተወዳደሩ መምህራን መካከል
በተጠባባቂነት ለተቀመጡ ቤቶች በተለቀቁ ጊዜ ዳግመኛ
ማስታቀወቂያ ሳይወጣ በነጥባቸው ቅደም ተከተል መሰረት
እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
 በዳይሬክተር ደረጃ ላሉ የአስተዳደር ሰራተኞች እንደ
አካዳሚክ ሰራተኞች ተወዳድረው ህጉ በሚፈቅደው
መሰረት ቤት እንዲሰጣቸው ይደረጋል ፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በመኖሪያ ቤት ግቢዎች ላይ ጽዳት እና ውበቱን እንዲሁም
የሕንጻው ደህንነት የሚከታተሉ የሕንጻ አስተዳደር ተጠሪዎች

DRAFT
አስፈላጊ በሆኑበት ቦታ/ግቢ ላይ ይመደባሉ፡፡
 የዩኒቨርሲቲው አፓርታማ በኪረይ መልክ ሰራተኞች የመኖሪያ
ቤት የምደባ መመሪያ እና ማሻሻያ በማጥናትለሚመለከተው
ያጸድቃል፤ ተግባራዊም ያደርጋል፡፡
 የዩኒቨርሲቲው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ተመን እና ማሻሻያ
በማጥናት ለሚመለከተው አካል አቅርቦ ያጸድቃል፤
ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 በዩኒቨርሲቲው በአውት ሶርሲንግ አገልግሎቶች ለሚከራዩ ቢሮዎች
እና የመስሪያ ግንባታዎች የኪራይ መነሻ ተመን እና ማሻሻያዎችን
ያዘጋጃል፤አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 የጽዳት እና ዉበት ክትትል እና ድጋፍ ያደርጋል
የጽዳት እና ዉበት ስትራቴጂክ እና ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፤

DRAFT

ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 የጽዳት እና ውበት ስራ ከከተማዉ እና ከሀገሪቱ የገጽታ
ግንባታ ስራ ጋር የተቀናጀ ይሆን ዘንድ ከሚመለከታቸዉ
አካላት ጋር በመነጋገር እና በመቀናጀት አማራጭ ዲዛይኖችን
በዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ተሳትፎ ጭምር እንዲዘጋጁ
በማድረግ መተግበር፤
 በአዉት ሶርሲንግ ለሚከናወኑ የጽዳት እና ዉበት ስራዎች
የጨረታ ዶክመንት ያዘጋጃል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ከፍተኛ የህንጻ ጥገና እና እድሳት ጥያቄ አቀራረብ እና አፈጻጸም
 በየእርከኑ ያለዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር ቡድን መሪ ከተገልጋይ

DRAFT
በሚቀርብለት እና በጥገና ክፍሉ በሚደረገዉ ዳሰሳ ከፍተኛ
ጥገና እና እድሳት የሚደረግላቸዉን ህንጻዎች በመለየት
ተገቢዉን ጥገና እና እድሳት እንዲደረግለት ለፋሲሊቲ
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡
 የፋሲሊቲ አስተዳደር ቡደን መሪ ከዳይሬክቶሬት የቀረበለትን
ጽሁፍ መነሻ በማድረግ ተገቢዉን ባለሙያ በመመደብ
የእድሳት እና ጥገናዉን ደረጃ በመገምገም የመነሻ በጀት
እንዲያዝ ያደርጋል፡፡ የጥገና እና እድሳት ዝርዝር አፈጻጸም
ያዘጋጃል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 መለስተኛ ሕንጻ ጥገና እና እድሳት በመማሪያ ህንጻ እና
አዳራሾች፤በመኖሪያ ህንጻዎች እንዲሁም ቢሮዎች፣የመማሪያ

DRAFT
ክፍሎች፣ቤተ-መጽሀፍት፣ላብራቶሪ፣የተማሪዎች መኝታ ቤት፣
ምግብ ቤት እና መገልገያዎች ላይ የሚደረግ የቀለም
እድሳት፤የፍሳሽ ማስተካከያዎች፤የበር እና የመስኮት ብልሽት
ጥገናዎች እና አነስተኛ የግንባታ ስራዎችን ኤሌክትሪክ
የመሳሰሉትን የሚያካትት ነዉ፡፡
 በየእርከኑ የሚገኘዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር የሚገኝበትን ግቢ
ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ መለስተኛ ጥገና ለማከናወን የሚያስችል
አደረጃጀት እና ተገቢ ሎጂስቲክስ እንዲኖረዉ ይደረጋል፡፡
 መለስተኛ ጥገና የሚከናወነዉ ከተገልጋዩ በሚቀርብ ጥያቄ
ወይም በጥገና ክፍሉ በሚደረግ ፍተሻ መነሻ ይሆናል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
ጽዳት እና ዉበት የማስጠበቅ ግዴታ
 በየእርከኑ የሚገኘዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር የሚገኝበት ግቢ

DRAFT
የተሟላ ጽዳት እና ዉበት እንዲኖረዉ የማረጋገጥ ግዴታ እና
ሀላፊነት አለበት፡፡
 የግቢ ጽዳት እና ዉበት ለማስጠበቅ ተገቢ የሆነ አደረጃጀት፤
የሙያ ስብጥር፤በቂ ክህሎት እና ሎጂስቲክስ እንዲሁም
በጀት መኖሩን መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
 የጽዳት ስራዉን እና የዉበት ስራዉን እንደባህሪያቸዉ
የሚመራ ተገቢ ክህሎት ያላቸዉ ተጠሪ ባለሙያዎች
የሚመደቡ ይሆናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የግቢ ዉበትን ለማስጠበቅ እንዲቻል የራስ ሀይል በቂ
አለመሆኑ በፋሲሊቲ አስተዳደር ሲታመንበት ዲዛይን

DRAFT
ከማዘጋጀት ጀምሮ የማስዋብ ስራዎችን በዉጭ ሀይል
እንዲታገዝ የኮንትራት ቅጥር መፈጸም እንደአማራጭ
የሚተገበር ይሆናል፡፡
 የየግቢዉ የጽዳት አፈጻጸም በዩኒቨርሲቲዉ የዉሳኔ አቅጣጫ
መሰረት በራስ ሀይል ወይም በዉጭ ሀይል የሚፈጸም ሆኖ
የየግቢዉ የጽዳት ተጠሪ እና የፋሲሊቲ አስተዳደሮች ተገቢዉ
መፈጸሙን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸዉ፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ይህ አገልግሎት በየግቢዉ የሚገኙ
ህንጻዎች፤ቢሮዎች፤የመማሪያ ክፍሎች እና አዳራሾች መረጃን

DRAFT
የመመዝገብ እና የማደራጀት፤የተገልጋይ ጥያቄን በመቀበል
በቋሚነት እና በጊዜያዊነት መመደብ፤የመማሪያ እና
መሰብሰቢያ አዳራሾች ለፈተና እና ለወርክሾፕ እንዲሁም
ለተለያዩ ወቅታዊ ለስብሰባ ጥያቄ በመቀበል ተገቢዉን ህጋዊ
ክፍያ በመፈጸም እንዲስተናገዱበት የማመቻቸት፤
በአዳራሾች እና በመማሪያ ክፍሎች ጽዳት መጠበቃቸዉን
ማረጋገጥ፤በክፍሎች እና አዳራሾች ዉስጥ የሚገኙ
መገልገያዎች እንዳይጠፉ እና እንዳይበላሹ የመከታተል እና
መቆጣጠር፤ የማባዣ አገልግሎት መስጠት
የዉሀ፤መብራት፤ቴሌፎን እና የፖስታ አገልግሎት አቅርቦት
እና ክፍያ መከታተል እና ማረጋገጥ እንዲሁም የመላላክ
አገልግሎትን
በአስተዳደርና የማመቻቸት
ተማሪዎች አገልግሎት የመሳሰሉት
ም/ፕሬዝዳንት ናቸዉ፡፡
ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በየእርከኑ ያለዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር በየግቢዉ ያለዉን
ህንጻ ከዋናዉ ግቢ የሙያ ድጋፍ ጭምር በመጠየቅ

DRAFT
በየግቢዉ ያለዉን ህንጻ ቆጠራ በማድረግ መመዝገብ እና
መረጃዉን በማደራጀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
 የየግቢዉ የህንጻ ቆጠራ እና ምዝገባ መረጃ የህንጻዉን
አገልግሎት፤የህንጻዉን ዕድሜ፤የህንጻዉን የጥገና እና እድሳት
ሁኔታ በመሰረታዊነት ያካተተ መሆን አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ለአካዳሚክ ሰራተኞች እንዲሁም ለተለያዩ የምርምር ስራዎች
የሚቀርቡ የቢሮዎች ጥያቄ የጥያቄዉ አስፈላጊነት

DRAFT
በዲፓርትመንት ሀላፊዉ እና በግቢዉ ዲን ቢሮ በኩል
ሲረጋገጥ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
 ለአስተዳደር ሰራተኞች የቅጥር ሁኔታቸዉ ተጠቅሶ በየእርከኑ
ባለዉ የሰዉ ሀይል አስተዳደር በኩል ጥያቄዉ ሲቀርብ
ምደባዉ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
 የቢሮ ኪራይ በጀት ያላቸዉ ፕሮጀክቶች ከግቢ ዉጭ
ቢሮዎችን ተከራይተዉ የሚጠቀሙ ሆኖ በቂ እና ክፍት
ቢሮዎች መኖራቸዉ ሲረጋገጥ በኪራይ አግባብ በዲን ዉሳኔ
ሊስተናገዱ ይችላሉ፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 ለፈተና፤ለስብሰባ እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከግቢዉ ዉጭ
ለሚገኙ አካላት ክፍሎች እና አዳራሾች የይመደብልን

DRAFT
ጥያቄዉ ከተጠቃሚዉ የአገልግሎቱ አግባብ እና
የሚያስፈልገዉ ጊዜ ተጠቅሶ ለዲን ቢሮ ሲቀርብ በሚወሰነዉ
ዉሳኔ መሰረት በአገልግሎት ክፍያ ወይም ያለአገልግሎት
ክፍያ በትብብር የሚመደብ ይሆናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የዉሀ፤የመብራት፤የስልክ እንዲሁም የፖስታ አገልግሎት
በአዲስ ደንበኝነት እንዲቀርብ ጥያቄዉ በአስገቢዉ ክፍል

DRAFT
ሀላፊ አስፈላጊነቱ ታምኖበት እና በጀት መኖሩ ተረጋግጦ
ሲቀርብ አገልግሎቱ ተገቢዉን ሂደት ተከትሎ እንዲቀርብ
የሚደረግ ይሆናል፡፡
 የዉሀ፤የመብራት እንዲሁም የስልክ አገልግሎት በብልሽት
መቋረጡ በተገልጋይ ክፍል በኩል ጥያቄዉ ሲቀርብ
ለመሰረታዊ አገልግሎት አቅራቢዉ አካል ጥያቄዉ ቀርቦ
ብልሽቱ እንዲስተካከል የሚደረግ ይሆናል፡፡
 በግቢዉ ለሚገኙ የዩቲሊቲ አቅርቦት ከዩቲሊቲ አቅራቢዉ
አካል በሚቀርብ የክፍያ ጥያቄ መሰረት ተገቢዉ እንዲፈጸም
ክትትል ያደረጋል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በየእርከኑ ያለዉ የፋሲሊቲ አስተዳደር ለፈተና፤ለትምህርት
እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚቀርቡለትን የማባዣ እና

DRAFT
የመጠረዝ አገልግሎት በየክፍሎቹ ሀላፊዎች ተረጋግጠዉ
ሲቀርቡ ተገቢዉን ቅደም ተከተል ይዘዉ አገልግሎቱ
እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡
 በየእርከኑ የሚገኝ የፋሲሊቲ አስተዳደር የማባዣ ማሺኖች እና
የህትመት መሳሪያዎች ተገቢዉን የቅድመ ብልሽት ሰርቪስ
እንዲደረግላቸዉ በራስ ሀይል እና በዉጭ ሀይል በክፍያ
የማከናወን ሀላፊነት አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ትርጓሜ
 ክፍል አንድ፡-መግቢያ
ክፍል ሁለት፡-የትራንስፖርተ ስምሪትና ተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት አወቃቀር፤የአገልግሎት

DRAFT

አይነትና የመኪኖች አይነት
 ክፍል ሶስት፡-የዩኒቨርስቲዉ ተሽከርካሪ መረጃ አያያዝ፤ሥምሪት፤አጠቃቀምና ቁጥጥር

 ክፍል አራት፡-ስለ ተሽከርካሪ ድልድልና የትራንስፖርት አበል አከፋፈል


 ክፍል አምስት፡-ለተሽከርካሪ የሚውሉ ግብዓቶች አጠቃቀም፤አያያዝና ቁጥጥር
 ክፍል ስድስት፡የተሽከርካሪ አቅርቦት፤ ምደባና አጠቃቀም መመሪያ
 ክፍል ሰባት፡-የተሽከርካሪዎቸ ጥገና አገልግሎት
 ክፍል ስምንት፡የክትትልና የቁጥጥር ስልት
 ክፍል ዘጠኝ፡-የተሽከርካሪ አወጋገድ
 ክፍል አስር፡-የትራንስፖርት ስምሪት እና የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የስራ ክፍል
ተግባርና ኃ ላፊነት
 ከፍል አስራ አንድ፡-ስለመድህን ዋስትና/ኢንሹራንስና ደህንነት (Safety)
 ክፍል አስራ ሁለት፡-ስለ ሪፖርት አቀራረብ
 ክፍል አስራ ሶስት፡-የተለያዩ ቅጾች አጠቃቀም
 ክፍል አስራ አራት፡-ስለመመሪያዉ ኃለፊነት፣ ተጠያቂነት እና አተገባበር

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


1.1 መግቢያ
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥራ አመራር ቦርድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
ሚ/ር በኢትዩጵያ ፌድራላዊ መንገስት የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ

DRAFT
ቁጥር 649/2001 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት አድርጎ ይህንን መመሪያ
አውጥቷል፡፡
አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ “የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተሽከርካሪዎች አያያዝና አጠቃቀም ሪቂቅ
መመሪያ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡
1.2 የመመሪያው ዓላማ
የትራንስፖርትና ተሽከርካሪ ስምሪት እና የተሸከርካሪ ጥገና አጠቃቀም ወጭ ቆጣቢ፣
ቀልጣፋ፣ ኃላፊነትንና ተጠያቂነትን ባካተተ አሠራር የተጠቃሚዎችን ፍላጐት
በማርካት የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ እንዲሳካ ለማድረግ ነው፡፡
1.3 የመመሪያው ተፈጻሚነት ወሰን
የመመሪያዉ ተፈጻሚነት ወሰን፤ ይህ መመሪያ የዩኒቨርሲቲው ንብረት በሆኑ
ተሽከርካሪዎች፤ ተሽከርካሪዎቹን በሚያስተዳድሩ የስራ ክፍሎች፤ በተሽከርካሪዎቹ
በሚጠቀሙ የስራ ክፍሎች፤ በስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፤ በነዳጅ አቅርቦት እና በጥገና
ስራ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የዩኒቨርሲቲው ቦርድ
 ፕሬዚዳንት

DRAFT
 የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት
 ዳሬክተር
 የተሸከርካሪ ጥገና ኃላፊ
 የማዕከል ሰምሪት ነዳጅና ቅባት አስተዳደር ኃላፊ
 የኮሌጆች/ማዕከላት/ት/ቤቶች ስምሪት ኃላፊ
 የሹፌርና የጥገና ሰራተኛ

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 የማዕከል መረጃ አያያዝና ምዝገባ
 የማዕከል የጥገናና ፍተሻ አገልግሎት

DRAFT
 የተሽከርካሪ ምደባ አገልግሎት
 የስምሪት አገልግሎት
 የማስወገድ አገልግሎት
 የመድን ሽፍን አገልግሎት

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ዊልቼር
 ባለሁለት እግር ያለሞተር የሚንቀሳቀስ

DRAFT
 ባለሁለት እግር በሞተር የሚንቀሳቀስ
 ፎርክሊፍት
 ባለአራት እግር አውቶሞቢሎች
 ባለአራት እግር ፒክአፕ
 ባለአራት እግር ፎርዊል ድራይቭ
 ባለ አራት እግር ሚዲ ባስ
 ባለ አራት እግር አውቶቡስ
 ባለተጎታች

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ለቢሮ ኃላፊዎች በቋሚነት የተመደበ መኪና አጠቃቀም ስርዓት
 ለተቋሙ ኃላፊዎች በቦርድ/በማኔጅመንት ዉሰኔ መሰረት ተሸከርካሪ እና ነዳጅ ይመደባል

DRAFT
ለስራዉ የሚጠቀሙበት ይሆናል፣
 ለመደበኛ የመላላክ ስራ የተመደበ ተሽከርካሪ
 ከየስራ ከፍሎች በሚመጡ የተሸከርካሪ ጥያቄ መሰረት በስምሪት ባለሙያ እንደየስራዉ
ባህሬ ስምሪት ይሰጣል፣
 ለመደበኛ ንብረት ማመላለሻ የተመደበ ተሽከርካሪ
 በሥራ ከፍሎች በሚመጡ የጭነት የተሸከርካሪ ጥያቄ መሰረት በሰምሪት ባለሙያ
ስምሪት ይሰጣል በስራዉ ስፍትና ክብደት ጊዜዉ ይወሰናል ፣
 ለህክምናና ለአጣዳፊ ሁኔታዎች የተመደበ ተሽከርካሪ (አምቡላንስ)
 አገልገሎት በሚሰጡ የዩኒቨርስቲዉ የጤና ተቋማት (ሆስፒታል እና ክሊኒከ) አንቡላንሶች
በተረኛ የጤና ባለሙያዎች እየታዘዙ የ24 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ለየኒቨርሲቲው ተቋማት የጋራ አገልግሎት የተመደበ ተሽከርካሪ
 እንደ ሰራተኞች የስራ ባህሬ ክብደትና ቅለት የተለያዩ ደረጃ ያለቸዉን ተሽከርካሪዎች በተቋሙ
የበላይ ኃላፊዎች ሲወሰን በጋራ የትራንስፖረት አገልገሎት ይሰጣል ፡፡

DRAFT
ለሰራተኞች፤ተማሪ አገልግሎትና ለረጅም ጉዞ የተመደበ ተሽከርካሪ
 ተማሪዎች የመማር ማስተማር ጉዞ ሲኖራቸዉ እና ተመራማሪዎች በጋራ የሚያደርጉት የመስክ
ትምህርታዊ ጉዞ መኖሩን ከማዕክል፣ከኮሌጆች እና ኢንስቲትዩቶች የትምህረት ክፈሎች ሲቀርብ
አገልገሎቱን እንዲገኙ ይደረጋል፡፡
ለሌላ አገልግሎት በጊዜያዊነት የሚመደብ ተሽከርካሪ
 የተማሪዎች ቅበላ፣ ምረቃ እና ልዩ ዝግጅት ሲኖር ዝገጅቱ የሚፈልገዉ የተሸከርካሪ መጠን
ከታወቀ በኋላ በዉስጥ አቅም የሚሸፈን ከሆነ በዩኒቨርሲቲዉ ተሽከርካሪዎች አገልግሎቱ
የሚሰጥ ሲሆን መሸፈን የማይቸልከሆነ አገልገሎቱ በሚፈልገዉ መጠን በኪራይ ይከናወናል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ዩኒቨርሲቲዉ በግዥ፣በግለሰብ ፣ በቡድን ተመራማሪዎች በተነደፈ ፕሮጀክት የሚገኝ በስጦታ ተረክቦ
ለሚጠቀምበት እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በአ.አ.ዩ ባለቤትነት ይመዘገባል ኢንሹራንስም ይገባለታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የተለየ የግል ማህደር በመክፈት በማህደሩ ውስጥ ቢያንስ የሚከተሉትን መረጃዎች

DRAFT
መዝግቦ ይይዛል፡፡
ሀ) የተሸከርካሪው ሰሌዳ ቁጥር፣ አይነትና ሞዴል
ለ) የጭነቱ ልክ (በሰው፣ በኩንታል፣ በኪዩቢክ ሜትር፣ በሊትር)
ሐ) የቻንሲና የሞተር ቁጥሮች
መ) የሚጠቀመው የነዳጅ ዓይነት
ሠ) የተገዛበት ወይም በመ/ቤቱ ባለቤትነት ስር የዋለበት ቀንና ዓመተ ምህረት
ረ) ተሸከርካሪው የተገኘበት ሁኔታ፡-በግዥ፤በስጦታ፤በርዳታ ወዘተ...
ሰ) የተሽከርካሪው ዋጋ
ሸ) የባለቤትነት መታወቂያ ደብተር
 የእያንዳንዱ የዩኒቨርስቲዉ ተሽከርካሪ የህይወት ታሪክ መዝገብ የተሽከርካሪው ርክክብ
ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ እስኪወገድ ድረስ በኪ/ሜ የሚጠቀመውን የነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት
ፍጆታ መጠን፣ የጥገና ወጪ የተጓዘው ኪ/ሜ መጠን በማን ይዞታ ስር እንደነበረ ወዘተ አካቶ
መያዝ አለበት፡
 የተሽከርካሪው የህይወት ታሪክ መዝገብ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየተፈተሸ ወቅታዊ መደረግ
ይኖርበታል፡፡
 መረጃ አያያዙ ዘመናዊ የሆነና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በዩኒቨርስቲዉ ዋናው ግቢ፣ በኮሌጅ፣ በኢንስቲትዩት እና ት/ቤቶች ቀላልና ከባድ
ተሽከርካሪዎች ለመስክ ጉዞ፣ ለከተማ ውስጥ ሥራና ለሠራተኞች ትራንስፖርት
አገልግሎት ተለይተው ይደለደላሉ፣

DRAFT
 ለማንኛውም የተፈቀደ የመስክ ጉዞ ተሽከርካሪ ለማሰማራት የመንግስት
የተሸከርካሪዎች አገልግሎት መጠየቂያና መዘዋወሪያ ቅፅ መያዝ አለበት፡፡
 የሥራ ሂደቶች ሠራተኞች የከተማ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት ሲፈልጉ
የተሽከርካሪ አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ ተሞልቶና በሚመለከተው የሥራ ኃላፊ
ተፈቅዶ ለትራንስፖርት ሥምሪት ቡድን ከቀረበ በኋላ አገልግሎቱ የሚሰጠው
በቅደም ተከተልና በማቀናጀት ይሆናል፡፡
 በግል ተሸከርካሪ የተመደበላቸው ሃላፊዎች በበላይ ኃላፊ ካልተፈቀደላቸው በስተቀር ከአዲስ
አበባ ከተማ ውጭ ማሽከርከር አይችሉም፡፡
 የትራንስፖርት ስምሪት ባለሙያው በቀረበው ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የተሽከርካሪ ጥያቄ
መሠረት በተሽከርካሪዎች መዘዋወሪያ ቅጽና በበር የይለፍ ፈቃድ ላይ መነሻ ኪሎ ሜትርን
ጨምሮ በመመዝገብ እየፈረመበት አገልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፣
 ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመ በቀር የተሸከርካሪዎችን አያያዝ ውጤታማ ለማድረግ
ለአንድ ተሽከርካሪ አንድ ሾፌር እንዲመደብ ይደረጋል፡፡
 ዩኒቨርሲቲዉ ተሸከርካሪ የሚመድበው ባለው አቅም ነው፡፡ ሆኖም ከሥራው አስፈላጊነት
አንጻር የተሸከርካሪ ዕጥረት ሲያጋጥም በጀት መኖሩን በማረጋገጥ የመንግስት የአገልግሎት
ግዢን ደንምብና መመሪያ በመከተል ተሸከርካሪ በመከራየት አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


◦ በግል ስለሚመደብ ተሸከርካሪ
 በዩኒቨርስቲዉ የሚገኙ ሁሉም ፕሬዚዳንት ፣ም/ፕሬዚዳንት፣ዲኖች፣
ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች፣ ቺፍ አከስኪዩቲቭ ዳይሬከተሮች፣የምርምር

DRAFT
ዳይሬክተሮችና የማዕከል ዳይሬክተሮች፣ ማኔጅንግ ዳይሬክተሮች እና
ልዩ ረዳቶቸ የተሸከርካሪ አገልግሎት እንደሚያስፈልጋቸው ይታወቃል፡፡
ስለሆነም የስራ ኃላፊነትንና ባህሪን ባገናዘበ መልኩ የተሸከርካሪ
ድልድሉ በቦርድ ታይቶ ይወሰናል፡፡
◦ የትራንስፖርት አበል አከፋፈልና የነዳጅ ድልድል
 ዩኒቨርስቲዉ በተሽከርካሪ ውስንነት ከላይ ለተገለፁት የሥራ ኃላፊዎች
በሙሉ ተሽከርካሪ መደልደል የማይቻል ሆኖ ሲገኝና እንዲሁም ያሉትን
ተሽከርካሪዎች ዕድሜ በማራዘም፣ በቁጠባ ለመጠቀም እንዲቻል
የትራንስፖርት አበል እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡ የአበሉ ተመን
አመዳደብ ተሽከርካሪ ቢመደብ ሊወጣ የሚችለውን የተሽከርካሪ ወጪ
/የነዳጅ፣ ዘይት፣ የቅባት፣ የጥገናና ..ወዘተ/ በማገናዘብ ነው፡፡
 የነዳጅ ድልድል ወጥ በሆነ መንገድ በቦርድ የሚወሰን ይሆናል

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት አያያዝ፣ አጠቃቀምና ቁጥጥር

DRAFT
 የነዳጅ እና ቅባት አቅርቦትን በተመለከተ ከነዳጅ አስመጪ ካምፓኒዎች ጋራ በጊዜ በተገደበ የዉል
ስምምነት መሰረት የሚቀርብ ይሆናል፡
 ዩኒቨርስቲዉ የራሱ የነዳጅ ዲፖ ይኖረዋል
 የነዳጅ አጠቃቀምን በተመለከተ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ በአንድ ሊትር ነዳጅ ስንት ኪሎ ሜትር
እንደሚሄድ ከጋራዥ፤ከትራንስፖርትና ከንብረት አስተዳደር የስራ ክፍሎች የሚመደቡ አባላት
በሚገኙበት ኮሚቴ እና በቴክኖሎጂ ከሚገኝ ንባብ ፍጆታዉ ተጠንቶ እንዲታወቅ የሚደረግ ሲሆን
ለተሽከርካሪ የሚመደበው ሳምንታዊ የነዳጅ ኮታ የተሽከርካሪውን የአገልግሎት ዘመንና
የሚመደብበትን የስራ ክፍል የስራ ባህሪ ያገናዘበ ይሆናል፡፡
 ለከፍተኛና ለመካከለኛ የስራ አመራሮች ለሚመደቡ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም በግል ተሽከርካሪያቸው
ነዳጅ ለሚፈቀድላቸው የስራ ኃላፊዎች የሚሰጥ ሳምንታዊ የነዳጅ ኮታ በቦርድ የሚወሰን ይሆናል ፡፡
 በዩኒቨርሲቲው ተሽከርካሪ የመጠቀም መብት ያለው የስራ ኃላፊ በተሽከርካሪ እጥረት ምክንያት
ተሽከርካሪ ሊመደብለት ካልቻለ ወይም የግሉን ተሽከርካሪ ማሽከርከር ከመረጠ በግል ተሽከርካሪው
ነዳጅ እንዲቀዳ ይደረጋል፡፡ ሆኖም የንግድ ታርጋ ባለው ተሽከርካሪ ለስራ ኃላፊ የተመደበ ነዳጅ
ከዩኒቨርሲቲው ማደያ አይሰጥም፡፡
 እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲ ተሽከርካሪ ለመስክ ስራ ከከተማ ርቆ ካልሄደ ወይም ነዳጅ ከዩኒቨርሲቲው
ማደያ ካልታጣ ነዳጅ መሙላት ያለበት ከዩኒቨርሲቲው የነዳጅ ማደያ ነው፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 በንብረት ክፍል ውስጥ በቂ ክምችት ያለመኖሩ እንዲሁም ለግዢው በቂ
በጀት መኖሩ ሲረጋገጥ የጠቅላላ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ባትሪ፣
ጐማና የውስጥ ላስቲክ(ከነመዳሪ) እና ለሁሉም ተሸከርካሪዎች የሚሆን

DRAFT
ቶሎ ቶሎ በየሰርቪሱ የሚቀየሩ መለዋወጫዎች ግዥ ጥያቄ በጥገና
ባለሙያ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፣
 በመስክ ጉዞ ላይ ለሚያጋጥሙ ያልተጠበቁ የተሸከርካሪ ብልሽቶቸ
የሚደረግ ግዥ በመስክ ሰራተኛው አስተባበሪ፣ በሹፌሩ እና የማዕከል
የጥገና ቡድን መሪው ጋራ በመነጋገር ጥገናዉ አሳማኝ ሆኖ ሲገኝ
ባለበት ቦታ ጥገናዉ ይከናወናል፣ የተለወጡ የመለዋወጫ ዕቃዎችንም
አሽከርካሪው በጥንቃቄ ይዞ ለጥገና ክፍሉ ያስረክባል፣ የጥገናውም
አግባብነት በጥገናው ባለሙያ ይረጋገጣል፣
 የተሽከርካሪ ጥገና ባለሙያው በግዢ የሚቀርቡ የመለዋወጫ ዕቃዎች
ክፍያ ከመፈፀሙ በፊት በተጠየቀው መሠረት ጥራታቸው ተጠብቆ
መቅረባቸውን ያረጋግጣል፣
 ማንኛውም ግዥ ከተመዘገበ አስመጪ ኩባንያ ወይም ዕቃ አቅራቢ
መሆን ይኖርበታል፣
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
 በአስመጪ ኩባንያዎች ጋራዥ ውስጥ ከሚከናወን የተሽከርካሪዎች ጥገና
በስተቀር፣ በውስጥና በውጪ ጋራዦች ለሚደረግ ጥገና የሚያስፈልግ

DRAFT
የመለዋወጫ ዕቃ ግዥ በማዕከላት፣ በከሌጅ እና በኢንስትዩቶች
ይፈጸማል፣
 ማናቸውም በግዥ ወይም በእርዳታ ወይም በስጦታ የሚመጡ
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች በንብረት ክምችትና ክፍፍል ክፍል
ገቢና ወጪ ይደረጋሉ፣
 ከንብረት ክምችትና ክፍፍል ክፍል ወጪ የሆኑ የተሽከርካሪ
መለዋወጫዎች በማዕከላት ጋራዥ የመለዋወጫ ግምጃ ቤት ገቢ
ተደርገው በሲስተም ወጪ እየሆኑ በተሽከርካሪ ላይ እንዲገጠሙ
ይደረጋል፣
 የጥገና ባለሙያው አዳዲስ መለዋወጫዎች በትክክል በተሽከርካሪው ላይ
መገጠማቸውን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
 የጥገና ባለሙያው ያገለገሉ መለዋወጫዎችን በትክክል መዝግቦ
ላገለገሉ መለዋወጫ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ለመጋዝን ኃላፊ በቅጽ
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
አስፈርሞ ያስረከባል፣
6.1. የተሽከርካሪ አቅርቦት
ሀ/ በመደበኛ በጀት የሚፈጸም ግዥ

DRAFT
ለ/ ለግለሰብ ተመራማሪ በተነደፈ ፕሮጀክት የሚገኝ
ሐ/ በቡድን ተመራማሪዎች በተነደፈ ፕሮጀክት የሚገኝ
መ/ በስጦታ የሚገኝ

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ኮሌጆች/ ኢንስቲትዮቶች ት/ቤቶች/ተቋማት እና የአስተዳደር የስራ ክፍሎች
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት ቋሚ የተሽከርካሪ ምደባ ጥያቄ ለአስተዳደርና የተማሪዎች
አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ያቀርባሉ፡፡

DRAFT
 የሚያቀርቡት ቋሚ የተሽከርካሪ ምደባ ጥያቄ በኮሚቴ ተገምግሞ የሚቀርበው
የውሳኔ ሃሳብ በአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ሲፀድቅ
ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
 ቋሚ የተሽከርካሪ ምደባን የሚመለከት ጥያቄ ግምገማ የተሽከርካሪ ጠያቂውን የስራ
ክፍል የስራ ባህሪ፤ ስፋትና ጥልቀት ያገናዘበ ይሆናል፡፡
 በራሳቸው እና ወይም በሾፌር የሚገለገሉባቸው ተሽከርካሪዎች የሚመደቡላቸው
ከፍተኛ አመራሮች የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም/ፕሬዚደንቶች ናቸው፡፡
 ለመስክ ስራና ለጋራ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ተሽከርካሪዎች በማዕከልና በኮሌጅ
ደረጃ በአግባቡ በሚደራጁ ፑሎች ተይዘው አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡
 ለጋራ አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ ትልልቅ አውቶብሶችና የጭነት ተሽከርካሪዎች
በማዕከል በፑል ተይዘው የጋራ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል
 ለፕሮጀክት አገልግሎት የተገዙ/የተሰጡ ተሽከርካሪዎች በፕሮጀክት ሰነድ መሰረት
እስከ ፕሮጀክቱ ፍፃሜ ድረስ ለዚያ ፕሮጀክት ዓላማ መሳካት አገልግሎት እንዲሰጡ
ይመደባሉ፡፡
 ለዩኒቨርሲቲው የተለገሱ ተሽከርካሪዎች ለጋራ አገልግሎት በየፑሉ እንዲመደቡ
ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 ማንኛውም የስራ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ የዩኒቨርሲቲው ተሽከርካሪ እንዲያሽከረክር
የሚፈቀድለት በቅድሚያ የተመደበለትን ተሸከርካሪ ለማሽከርካር የሚያስችለው የመንጃ
ፍቃድና የስራ ልምድ ማስረጃ ለአስተዳደርና የተማሪዎች አገልግሎትም/ፕሬዚዳንት

DRAFT
ጽ/ቤት ከማመልከቻ ጋር አቅርቦና የማስረጃው አግባብነት ባለሙያዎች ባሉበት ጊዜያዊ
ኮሚቴ ታምኖበት ሲፈቀድ ብቻ ነው፡፡
 የዩኒቨርሲቲውን ተሽከርካሪ እንዲያሽከረክር የተፈቀደለት የስራ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ
እንዲያሽከረክር የተሰጠውን ተሽከርካሪ በማንኛውም ሁኔታ ለሌላ ሶስተኛ ወገን ያለ
ዩኒቨርሲቲው እውቅና አሳልፎ አይሰጥም፡፡
 የዩኒቨርሲቲውን ተሽከርካሪ እንዲያሽከረክር የተፈቀደለት የስራ ኃላፊ ወይም ሰራተኛ
ተሽከርካሪውን ለዩኒቨርሲቲው ስራና ዓላማ መሳካት አስተዋጾኦ ለሚያደርጉ አገልግሎቶች
ብቻ ማዋል አለበት፡፡
 ማንኛውም የዩኒቨርሲቲን ተሽከርካሪ እንዲያሽከረክር የተፈቀደለት የስራ ኃላፊ ወይም
ሰራተኛ የተሰጠውን ተሽከርካሪ አጠቃላይ የውስጥና የውጭ ክፍሎች ደህንነት የመጠበቅ፤
የመንከባከብና የመከታተል ኃላፊነት አለበት፡፡
 ለስራ ኃላፊዎች በሾፌር አገልግሎት እንዲሰጥ የተመደበ ተሽከርካሪ የስራ ኃላፊው
በማይጠቀምበት ጊዜ ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሌሎች ሰራተኞች አገልግሎት እንዲሰጥ
ማድረግ ይቻላል፡፡
 የትራንስፖርት የስራ ክፍልም ሆነ ማንኛውም አሽከርካሪ አንድን ተሸከርካሪ ስራ ላይ
ከማዋሉ በፊት ተሽከርካሪው በቴክኒክ ረገድ ለስራ ብቁ መሆኑንና የመድህንና የሶስተኛ
ወገን ዋስትና ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 በግለሰብ ተመራማሪ ወይም በቡድን ተመራማሪዎች
አማካይነት የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በስራ ላይ

DRAFT
ከመመደባቸው በፊት በማዕከል ንብረት ከፍል
እንዲመዘገቡ፤ የትራንስፖርት የስራ ክፍል የተሟላ ፋይል
እንዲከፈትላቸውና ለስምሪት ዝግጁ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
 በግለሰብ ተመራማሪ ወይም በቡድን ተመራማሪዎች
አማካይነት የተገኙ ወይም የሚገኙ ተሽከርካሪዎች
የሚመለከተው ፕሮጀክት ስራ እስከሚጠናቀቅ ድረስ
በፕሮጀክቱ መሪ ቁጥጥርና አስተዳደር ስራ ሆነው ይቆያሉ
ፕሮጀክቱ እንዳለቀ ተሸከርካሪዉ ፐሮጀክቱን ላመጣዉ
ኮሌጅ/ ኢንስቲትዩት ተመላሽ ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


 በትምህርት ክፍሎች ጥረት በስጦታ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች በስራ ላይ
ከመመደባቸው በፊት በማዕከል ንብረት ክፍል እና የትራንስፖርት የስራ

DRAFT
ክፍል እንዲመዘገቡ፤ፋይል እንዲከፈትላቸውና ለስምሪት ዝግጁ እንዲሆኑ
ይደረጋል፡፡
 የትምህርት ክፍሎች በስጦታ የሚያገኙአቸው ተሽከርካሪዎች በትምህርት
ክፍሉ አስተዳደር ስር ሆነው አገልግሎት ይሰጣሉ፤ ነገር ግን
ከተሽከርካሪዎቹ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በትምህርት ክፍሉ
በጀት መሸፈን አለባቸው፡፡
 አንድ የትምህርት ክፍል በስጦታ ያገኘውን ተሽከርካሪ ወጪ ሙሉ
በሙሉ ሸፍኖ መጠቀም ካልቻለ ተሽከርካሪው ወደ ማዕከል ፑል
እንዲገባ ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


◦ ዩኒቨርሲቲው የራሱ የተሸከርካሪ መጠገኛ ጋራዥ ይኖረዋል
◦ እያንዳንዱ ተሸከርካሪ በየጊዜው 5,000 (አምስት ሺ) ኪሎ ሜትር ከተጓዘ በኋላ የሰርቪስ
አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

DRAFT
◦ አግባብነት ያላቸው መሳሪያዎች እና ባለሙያዎች እስከአሉ ድረስ የአነስተኛና የመካከለኛ
ተሽከርካሪዎች ጥገና በዩኒቨርሲቲው ጋራዥ እንዲካሄድ ይደረጋል፡፡
◦ አዲስ የተገዙ ተሽከርካሪዎች የዋስትና ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ሰርቪስና ጥገናቸው
የሚካሄደው በአቅራቢው ድርጅት አማካይነት ብቻ ይሆናል፡፡
◦ የትልልቅ ተሽከርካሪዎች ጥገናን በተመለከተ በዉስጥ ባለሙያዎች አቅም በላይ ካልሆነ
በሰተቀር ጥገና የሚካሄደው በዉስጥ ጋራዥ እና በአስመጪዉ ካምፓኒ የሚጠገን ይሆናል
፡፡ ሆኖም ግን ከአቅም በላይ ከሆነ የትልልቅ ተሽከርካሪዎች ጥገና፣ የፖምፓ እና የማሽን
ስራዎች በውጪ በውድድር በሚመረጥ/በሚመረጡ የማሽን ሾፕ እና የፖምፓ ስራ ከሚሰሩ
ድርጅቶች ዩኒቨርሲቲው በጊዜ ገደብ በተፈጸመ ውል የሚሰራ ይሆናል፡፡
◦ የመንግስት ግዥ ደንብ እንደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው የአንድ ዓይነት ተሽከርካሪ አስመጪ
ከሆነ ወይም በአንድ የጥገና አገልግሎት ዓይነት ልምድ ካካበተ /ስፔሻላይዝ ካደረገ/ ድርጅት
ቀጥታ የሰርቪስ፣ የጥገና አገልግሎት እና የመለዋወጫ ግዥ ሊፈጽም ይችላል፡፡
◦ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ በተቻለ መጠን በማዕቀፍ የግዥ አሰራር ኦሪጅናል
እቃ አስመጪ ከሆኑ አቅራቢዎች እንዲፈጸም ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


◦ ተሽከርካሪ በግዥ በፕሮጀክት ወይም በስጦታ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጣ ተሽከርካሪውን
የሚመለከቱና በሰነድ የተደገፉ ማስረጃዎች ምዝገባ ይደረጋል፡፡

DRAFT
◦ የአንድ ተሽከርካሪ ፋይል በየጊዜው ተሽከርካሪውን በተመለከተ ከሚደረጉ የስራ
እንቅስቃሴዎች አንጻር ማስተካከያዎች እየተደረጉበት እንዲሄዱ ይሆናል፡፡
◦ በየዓመቱ በነሐሴ ወር በባለሙያዎች የተሽከርካሪ ቆጠራና ምርመራ
ይካሄዳል፤በምርመራው ውጤት መሰረትም የጥገና መርሐግብር ተዘጋጅቶ በቅደም
ተከተል ተሽከርካሪዎች አስፈላጊውን የጥገና አገልግሎት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
◦ የእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ማህደር በየሁለት ዓመቱ ከህዳር ወር መጀመሪያ እስከ ጥር
ወር መጨረሻ ምርመራ እንዲካሄድ እየተደረገ ከአገልግሎት ውጪ መደረግ ያለባቸው
ተሽከርካሪዎች ተለይተው እንዲወገዱ የውሳኔ ሃሳብ ይቀርባል፡፡
◦ የዩኒቨርሲቲውን ሀብትና ንብረት በአግባቡ በመጠበቅ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል
ለማድረግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የተሸከርካሪዎች ክትትል ሥርዓት (Vehicle tracking
System) በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲገጠም ይደረጋል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


◦ በየሁለት ዓመት በሚካሄድ የተሽከርካሪዎች ማህደራት ግምገማ ውጤት
መሰረት ለአገልግሎት ብቁ ያልሆኑ ተሽከርካሪዎች ከተለዩ በኋላ
የተሽከርካሪዎች የአወጋገድ ስልት ከመንግስት ንብረት አስተዳደርና

DRAFT
መመሪያ አንጻር ታይቶ ይመረጣል፡፡
◦ በተመረጠው የአሰራር ስልት ወይም በተመረጡት የአሰራር ስልቶች
መሰረት ተሽከርካሪዎቹ እንዲወገዱና ከንብረት መዝገብ ላይ እንዲሰረዙ
ይደረጋል፡፡
◦ የዩንቭርስቲዉ ተሸከርካሪ፤ መለዋወጫ፤ባትሪና ጎማ አወጋገድን
በተመለከተ በመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 9/2003 ላይ
ስለ መንግስት ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ የሚደነግጉ አንቀፆች በሥራ
ላይ ያሉት የመንግስት የቋሚ ንብረት አስተዳደር እና የስቶክ አስተዳደር
ማንዋሎች እንደአግባብነታቸው በዩንቨርስቲዉ ተሸከርካሪዎች ተፈፃሚነት
ይኖራቸዋል፡፡
◦ አገልግሎታቸውን የጨረሱ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በመንግስት
የንብረት አወጋገድ መመሪያ መሰረት እንዲወገዱ ይደረጋል፡፡
◦ በተወገዱት ተሽከርካሪዎች ምትክ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች እንዲተኩ
በማዕከላዊ የትራንስፖርት አገልግሎት የስራ ክፍል በኩል የግዥ ጥያቄ
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡
◦ የትራንስፖርት ስምሪት ክፍል ተግባርና ኃላፊነት

DRAFT
◦ የአሽከርካሪ ተግባርና ኃላፊነት
◦ የተጠቃሚዎች ተግባርና ኃላፊነት
◦ በፑል ተሽከርካሪዎችን ስለመጠቀም

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


የመድን ዋስትና/ ኢንሹራንስ
 ማንኛዉም የመድን ዋስትና ሽፍን በማዕከል ይደረጋል፡፡ በማንኛውም የዩንቨርስቲዉ ተሸከርካሪ ላይ
የሚደርስ አደጋ ዩኒቨርስቲዉ በገባው ውል መሰረት የመድህን ሽፋን እንዲያገኝ ይደረጋል፡፡

DRAFT
ደህንነት
 የትራንስፖርት ስምሪት፣ ምደባ እና አጠቃቀም በዩኒቨርስቲዉ የታቀዱ የምርምር ፣የመማር ማስተማር
እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን በሚፈለገው መጠንና ጥራት በአጭር ጊዜ እንዲሳኩ
ከሚያደርገው ያላሰለሰ ጥረት ጐን ለጐን በማዕክል እና በኮሌጆች ሠራተኞች፣ጋራዦች ውስጥና
በተሽከርካሪዎች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱት ተግባራት
መከናወን አለባቸው፣
 ዩኒቨርስቲዉ በማዕከላት እና በኮሌጆች በሚገኙ ጋራዦች ውስጥና በተሽከርካሪዎች ላይ
ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የሚረዱ መሣሪያዎችንና የእሳት ማጥፊያዎችን
በየጊዜው ጥራታቸውና የአገልግሎት ጊዜያቸው እየታየ እንዲታደሱና እንዲስተካከሉ በማድረግና
አመቺ በሆኑ ሥፍራዎች በማስቀመጥ አደጋውን ለመከላከል እንዲያስችሉ ዝግጁ ማድረግ፣
 እሳት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ለማስወገድ ጥረት እየተደረገ አደጋዎች
ቢያጋጥሙ ሠራተኞች ሳይደናገጡ አደጋውን በቁጥጥር ሥር ሊያውሉ ስለሚችሉበት ሀኔታና
ስለ እሳት አደጋ መከላከያ መሣሪያዎች አጠቃቀም ለጥገና ባለሙያዎች፣
ለአሽከርካሪዎች፣ለጥበቃ ሠራተኞች.. ወዘተ ሥልጠና መስጠት፣
 ኤሌክትሪክ በሚሽከረከሩ መሣሪያዎች፣ በብረታብረት ብየዳና ቅጥቀጣ እንዲሁም በቀለም
ቅብ ወቅት የተለያዩ አደጋዎች ሊደርሱ ስለሚችሉ፣ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ፣
 እያንዳንዱ ተሸከርካሪ ላይ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲገጠም ማድረግና መጠቀም፣

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


◦ በዩኒቨርስቲዉ ሥር የሚገኙ ሁሉም ኮሌጆች/ ኢንስቲትዩቶች እና
ት/ቤቶች በተሸከርካሪ ስምሪት አጠቃቀም ላይ የተከናወኑ

DRAFT
ተግባራትን ያጠቃለለ ግልጽና ተጨባጭ የሆነ ወርሃዊ ሪፖርት
በየሩብ ዓመቱ ለማዕከል ያቀርባሉ፡፡
◦ ማዕከልም በየሩብ ዓመቱ የተሽከርካሪ ነዳጅ፣ ዘይትና ቅባት አያያዝ፣
አጠቃቀም እና የጥገና ወጪን ሪፖርት በማጠናቀር ለመንግስት
ግዥና ንብረት ባለስልጣን ይልካል፡፡

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


በተሽከርካሪ አቅርቦት ምደባና አጠቃቀም የስራ ሂደት ስራ ላይ የሚውሉ
ቅጾች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሳምንታዊ የነዳጅ ኮታ ቅጽ

DRAFT

 የነዳጅና ቅባት መጠየቂያ ቅጽ
 የተሸከርካሪ አጠቃላይ መረጃ መመዝገቢያ ቅጽ
 ተሸከርካሪ መረካከቢያ ቅጽ ዕለታዊ የመኪና/
 ተሸከርካሪ አገልግሎት መጠየቂያና መዘዋወሪያ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ስምሪት መከታተያ ቅጽ (የሚዘጋጅ)
 የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚ አስተያየት መስጫ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ሰርቪስ መከታተያ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ብልሽት ማሳወቂያ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ጥገና ስራ ትዕዛዝ መስጫ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ጥገና መከታተያ ቅጽ
 ለጥገና የሚያስፈለግ የመለዋወጫ እቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ቅጽ
 የአሮጌ መለዋወጫ እቃ መረካከቢያ ቅጽ
 ተሸከርካሪ ቆጠራ ውጤት መግለጫ ቅጽ (የሚዘጋጅ)

በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ


ኃላፊነት
 ይህን መመሪያ የማስፈፀምና እንዲፈፀም የመከታተል ኃላፊነት

DRAFT
የትራንስፖርት ስምሪት እና የተሸከርካሪ ጥገና አገልግሎት የስራ ክፍል
ነው፡፡
ተጠያቂነት
 ማንኛውም የሚመለከተው የዩኒቨርስቲዉ የስራ ኃለፊ ወይም ባለሙያ
ወይም ሠራተኛ ከመመሪያው ውጪ ለፈፀማቸው ተገቢ ያልሆኑት
ተግባራት ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
መመሪያዉን ስለማፅደቅ
 ይህ መመሪያ በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ከፀደቀበት ጊዜ
ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

መመሪያዉን ስለማሻሻል
 ይህ መመሪያ እንደየአስፈላጊነቱ በሙሉ ወይም በከፊል ሊሻሻል
ይችላል፡፡
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ
DRAFT
በአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የተዘጋጀ

You might also like