You are on page 1of 92

DSpace Institution

DSpace Repository http://dspace.org


þÿGe½ez Thesis and Dissertations

2020-11-13

þÿpµ3íë• Cu `sè e( -ë =H 0Ë5Í

þÿHCñ 5M•

http://hdl.handle.net/123456789/11610
Downloaded from DSpace Repository, DSpace Institution's institutional repository
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ
የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው

በፈቃዱ መስፍን

ሐምሌ 2012
ባሕር ዳር
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ

የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው

የአርትስ ማስተርስ ዲግሪ በግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ለማግኘት


ከሚያስፈልጉ ነጥቦች ከፊሉን ለማሟላት የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ

በፈቃዱ መስፍን

የጥናቱ አማካሪ

አብርሃም አዱኛ

ሐምሌ 2012
ባሕር ዳር
© 2019 ፈቃዱ መስፍን
ማረጋገጫ

“ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው” በሚል ርእስ በባሕር ዳር
ዩኒቨርሲቲ፣ ሂውማኒቲስ ፋኩልቲ፣ የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ለአርትስ
ማስተርስ ዲግሪ በግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ለማግኘት እንደ ማሟያ ያቀረብኩት ይህ
ጥናት ከዚህ በፊት በማንኛውም አካል ያልተሠራ የራሴ ወጥ ሥራ መኾኑንና
የተጠቀምኩባቸው ድርሳናትም በትክክል ዋቢዬ የኾኑና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም የጥናቱ
ሕጋዊ የባለቤትነት መብት ያለው መኾኑን በፊርማዬ አረጋግጣለሁ፡፡

……………………….. ……/……/……… …………………


ስም ቀን ፊርማ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የሂውማኒቲስ ፋኩልቲ

የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

የመመረቂያ ጽሑፉ ለተቋቁሞ ብቁ መኾኑን ማረጋገጫ

በኔ አማካሪነት በፈቃዱ መስፍን የተዘጋጀውን “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም


መጽሐፈ ሰዋስው” የሚል ርእስ ያለውን ይህን የመመረቂያ ጽሑፍ ክትትል ማድረጌን፣
ማንበቤንና መገምገሜን አረጋግጣለኹ፡፡ ይህ የመመረቂያ ጽሑፍ ለተቋቁሞ እንዲቀርብ
የይኹንታ ሐሳቤን አቀርባለኹ፡፡

……………………….. ………………… ……/……/………


ያማካሪ ስም ፊርማ ቀን
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

የሂውማኒቲስ ፋኩልቲ

የግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

የመመረቂያ ጽሑፍ ተቋቁሞ ውጤት ማረጋገጫ

እንደ ፈተና ቦርድ አባላት ይህን “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ
ሰዋስው” በሚል ርእስ በፈቃዱ መስፍን የቀረበውን የመመረቂያ ጽሑፍ ፈትነናል፡፡ ይህ
የመመረቂያ ጽሑፍ “የአርትስ ማስተርስ ዲግሪ በግእዝ ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ” ለማግኘት
የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን በማሟላቱ ተቀባይነት ማግኘቱን እናረጋግጣለን፡፡

የፈተና ቦርድ አባላት

……………………….......... ………………… ……/……/………


የውጭ ፈታኚ ስም ፊርማ ቀን

……………………….......... ………………… ……/……/………


የውስጥ ፈታኚ ስም ፊርማ ቀን

……………………….......... ………………… ……/……/………

ሊቀ መንበር ስም ፊርማ ቀን
.

ምስጋና

በመጀመሪያ እሱ በፈቀደ ከዚህ ላደረሰኝ የኹሉ ጌታና ባለቤት ለኾነው ለልዑል


እግዚአብሔር ምሰጋና አቀርባለኹ፡፡ በመቀጠልም ጥናቱ ከዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ
ተገቢዉን እገዛና ምክር በመስጠት ለረዳኝ ለአማካሪዬ ለመምህር አብርሃም አዱኛ የከበረ
ምስጋናዬን አቀርባለኹ፡፡ እንዲሁም ለሥራዉ ውጤት ላይ መድረስ በማቴሪያልም ኾነ
በሐሳብ ለረዱኝ መምህራኖቼ እና ጓደኞቼ ኹሉ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና
ይገባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ጊዜዬን በአግባቡ በመጠቀም ሥራዬን እንድሠራ አይዞኽ በማለት እና ሞራል


በመስጠት ቤተሰቦቼ በሙሉ ያላቸው ድጋፍ ከፍተኛ በመኾኑ ክብርና ምስጋና
ይድረሳቸው፡፡

i
.

አኅጽሮተጽሑፍ

ይህ ጥናት “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው” በሚል ርእስ
ተመሥርቶ የተከናወነ ሲኾን ዐላማዉም ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች እና ምሁራን
መጣጥፎች አንጻር ታየ በገለጸበት አግባብ የቃላት ሞኵሼነት ያለ ስለመኾን አለመኾኑ
መመርመር ነው፡፡ ለዚህ ጥናት የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው መነሻ የተደረገው
ከሌሎች ምሁራን ጽሑፎች በተለየ መልኩ ተመኵሳይያን ቃላት በተለይ በተለምዶ ሞኵሼ
ተብለው የሚጠሩ ፊደላትን መሠረት በማድረግ በሰፊው መብራራታቸው ነው፡፡ ይህም
በሌሎች ምሁራን ዘንድ እንዳለ መቀጠሉ ተለምዷዊ ሞኵሼ ፊደላት እውን ተመሳሳዮች
ናቸውን በእነዚህ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላትስ
ሞኵሼነትን ያሟላሉን የሚል ጥያቄ በመነሣቱ ነው ፡፡ የጥናቱ መረጃም የተሰበሰበው
በዋናነት ሰነድ በመፈተሽ ሲኾን ምርመሩ ከዐይነታዊ የምርምር ዘውግ የሚመደብ
እንደመኾኑ መጠን ገላጪ ንጽጽራዊ ዘዴን በመጠቀም ነው ማስረጃዎቹ የተተነተኑት፡፡
በጥናቱም ታየ ተለምዷዊ መኵሼ እየተባሉ የሚጠሩ ፊደላትን በዘፈቀደ እንደሚጠቀም
እና ቃላት የተዋቀሩባቸው ፊደላት ቅርጻቸዉ ግምት ውስጥ ሳይገባ በድምፃቸዉ መመሳሰል
ብቻ ተመኵሳይያን እንደሚባሉ እንዲሁም አዕማድ ግሶች ከተዋቀሩበት ፊደላት መለያየት
በተጨማሪ የተለየ ትርጕም ሳይኖራቸውና የአድራጊነትን፣ የተደራጊነትንና የአስደራጊነትን
ቅርጽ ሳያሟሉ ተመኵሳይያን የሚባሉ መኾናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከአንድ የግስ ሥር
በርባታ የተገኙ እና በርባታቸዉ ምክንያት የተለያየ ፆታ፣ መደብና ቁጥር የሚገልጹ ኾነው
በንባብ በመመሳሰላቸው ቃላት ሞኵሼዎች የተባሉ ስለመኾናቸውም ጥናቱ አሳይቷል፡፡
በመጨረሻም ይህ ጥናት በቅርጽ እንጅ በድምፅ የማንለያቸውን ፊደላት ድምፃቸዉን
መልሶ ለማገኘት እንደመነሻ ኾኖ እንደሚያገለግል እና በምሁራኑ ዘንድም ስሕተትን
ከማረም ጀምሮ ለተጨማሪ ጥናት መነቃቃትን በመፍጠር በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው
ተመላክቷል፡፡

ii
.

የይዘት ማውጫ
ርእስ ገጽ
ምስጋና .............................................................................................................................. i

አኅጽሮተ ተጽሑፍ ........................................................................................................... ii

የምኅጻረ ቃላት መፍቻ ..................................................................................................... v

ምዕራፍ አንድ .................................................................................................................. 1

1. መግቢያ ....................................................................................................................... 1

1.1 የጥናቱ ዳራ ............................................................................................................ 1

1.2. የጥናቱ አነሣሺ ምክንያት ...................................................................................... 5

1.3. የጥናቱ ጥያቄዎች .................................................................................................. 7

1.4. የጥናቱ ዐላማ ......................................................................................................... 8

1.4.1 የጥናቱ ዝርዝር ዐላማዎች .................................................................................... 8

1.5. የጥናቱ አስፈላጊነት ............................................................................................... 8

1.6. የጥናቱ ዘዴ ........................................................................................................... 9

1.6.1. የመረጃ ምንጭ ................................................................................................ 9

1.6.2. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ............................................................................... 10

1.6.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ................................................................................. 10

1.7. የጥናቱ ወሰን ....................................................................................................... 10

ምዕራፍ ኹለት ............................................................................................................... 12

2. የተዛማጂ ጽሑፎች ዳሰሳ/ ክለሳ ድርሳን ..................................................................... 12

2.1. ፅንሰ ሐሳባዊ ዳራ ................................................................................................ 12

2.1.1 የተመኵሳይያን ምንነት .................................................................................. 12

2.1.2 ተመኵሳይያን የተባሉ የግእዝ ቃላት ክፍሎች ምንነት .................................... 16

2.1.3. ተመኵሳይያንን ለማዋቀር ሥራ ላይ የዋሉ መሠረተ ሐሳቦች ........................ 21

iii
.

2.1.4. ተዛማጂ ጽሑፎች .......................................................................................... 25

ምዕራፍ ሦስት ................................................................................................................ 34

3. ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ..................................... 34

3.1. በምስጢር የማይገናኙ እየራሳቸው የቆሙ ኾነው አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ


የመሰሉ ግሶች ............................................................................................................. 35

3.1.1 አድራጊና አስደራጊ የመሰሉ ግሶች ................................................................. 36

3.1.2 አድራጊ እና ተደራጊ የመሰሉ ግሶች............................................................... 43

3.2 በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና በመላላት ኹለት ፍች ያላቸው ቃላት ............ 50

3.2.1 በትርጕም ተለያይተው የፊደላት አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ቃላት............... 51

3.2.2 የፊደላት አጠቃቀም ችግር ሳይኖራቸው በትርጕም አንድ የኾኑ ቃላት ........... 55

3.3 በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ቃላት................................................... 56

3.3.1 በትርጕም ተለያይተው የፊደላት አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ቃላት............... 56

3.3.2 የፊደላት አጠቃቀም ችግር ሳይኖራቸው በትርጕም አንድ የኾኑ ቃላት 61

3.3.3 ከፊደል አጠቃቀምና ከትርጕም አንጻር .......................................................... 62

3.4 ባላቸው የምስጢርና የአመጣጥ ልዩነት ተመኵሳይያን የተባሉ ቃላት .................... 65

ምዕራፍ አራት ................................................................................................................ 68

4. ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና የይኹንታ ሐሳብ.............................................................. 68

4. 1 ማጠቃለያ ........................................................................................................... 68

4.2 መደመደሚያ ........................................................................................................ 72

4.3. የይኹንታ ሐሳብ ................................................................................................. 75

ማጣቀሻ መጻሕፍት ........................................................................................................ 77

iv
.

የምኅጻረ ቃላት መፍቻ

ሊጉ. የሊቃውንት ጉባኤ

ሕዝ. መጽሐፈ ሕዝቅኤል

መዝ. መዝሙረ ዳዊት

ማር. የማርቆስ ወንጌል

ሚክ. ትንቢተ ሚክያስ

ሳሙ. መጽሐፈ ሳሙኤል

ኢመቅማ. የኢትየጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር

ኢኦተቤ. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ዓ. ም ዓመተ ምሕረት

የሐዋ. የሐዋርያት ሥራ

ያዕቆ. ያዕቆብ

ግን. ግንዘት

ዘሌ. ኦሪት ዘሌዋውያን

ዘፍ. ኦሪት ዘፍትረት

v
.

ምዕራፍ አንድ

1. መግቢያ
1.1 የጥና ቱዳራ

ቋንቋ የሰው ልጅ መግባቢያ እና የመልእክት ማስተላለፊያ መንገድ እንደመኾኑ መጠን


(ባየ፣ 2001፣ 131) የቋንቋዉን ሰዋስዋዊ ውቅር ማወቅና በቋንቋዉ መዝገበ ቃላት በልጽጎ
መገኘት የዕለት ተዕለት ሥራዎችን ተግባብቶ ለማከናወንና መልእክትን በተሟላ መንገድ
ለማስተላለፍ ጠቀሜታ አለው፡፡ በተለይ ደግሞ በቀደምት ጊዜያት ብዙ ቁም ነገሮች
የተሰነዱባቸውንና አሁን ላይ በአፍ መፍቻነትም ኾነ በዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴ
ላይ አገልግሎት የማይሰጡትን እንደ ግእዝ ዐይነት ቀደምት ቋንቋዎችን ከድምፅ ውክልና
ጀምሮ አጠቃላይ የቋንቋዉን ሥርዐተ ጽሕፈት እና ሰዋስዋዊ መዋቅር ማጥናቱ በውስጡ
ያሉትን ቁም ነገሮች በአግባቡ ተገንዝቦ ሥራ ላይ ለማዋል እና ለቀጣዩ ትውልድ
ለማስተላለፍ ጠቀሜታዉ የጎላ ነው፡፡

የግእዝ ቋንቋ ከደቡባዊ የሴም ቋንቋዎች ምድብ ውስጥ የሚካተት ሲኾን በሀገር ቤት የሴም
ቋንቋ ምደባ መሠረት ደግሞ የኢትዮጵያ ሰሜናዊ ቋንቋ በመባል ነው የሚታወቀው
(ሊፒንስኪ፣ 1997፣ 49፣ 81፣) ፡፡ ስለቋንቋዉ የትመጤነትና እድገት በምሁራን ዘንድ
የተለያየ አመለካከት ቢኖርም በዓለም ከሚነገሩ ቀደምት ጥቂት ቋንቋዎች መካከል አንዱ
ግእዝ ስለመኾኑ ግን አከራካሪ አይደለም፡፡

የዚህም ማሳያ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በመጀመሪያዎቹ ስድስት መቶ ዓመታት መጽሐፍ


ቅዱስ ከተተረጐመባቸው ጥቂት የዓለም ቋንቋዎች ውስጥ ግእዝ አንዱ መኾኑ ነው (ምክረ
ሥላሴ፣ 2000፣ 158)፡፡ የራሳቸውን አመክንዮ በማስቀመጥ የመጽሐፍ ቅዱስ የትርጒም
ሥራ የተጀመረው ከክርስቶስ ልደት በፊት በንግሥተ ሳባ ዘመን ቀዳማዊ ምኒልክን
ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ ሌዋውያን ሊቃውንት መኾኑን ገልጸው የሚከራከሩ
ሌሎች ሊቃውንትም አሉ (አስረስ፣ 1951፣ 200)፡፡ ይህም ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው
ቢኾንም ቅሉ የግእዝ ቋንቋ የድምፅ መስጫ አናባቢዎች ወደ ቋንቋዉ የገቡት በአራተኛዉ
መቶ ክፍለ-ዘመን በከሣቴ ብርሃን መኾኑ (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 16) እስከተረጋገጠ እና
ከዚህ ዘመን በፊት ደግሞ ይጻፍበት በነበረው አናባቢ በሌለው በግእዝ ፊደል ብቻ

1
.

የተተረጐመ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እስካልተገኘ ድረስ የትርጕም ሥራዉ የተጀመረው


በአራተኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ነው የሚለው መከራከሪያ አሳማኚ ነው የሚኾነው፡፡

አማርኛ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ መኾኑን ተከትሎ የግእዝ ቋንቋ በ12ኛዉ ወይም
በ13ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ከመነጋገሪያ ቋንቋነቱ የተገታ ስለመኾኑ በምሁራኑ
ዘንድ የሚታመን ሲኾን (ዲልማን፣ 1907፣ 2፤ ሌስሎው፣ 1991፣ መግቢያ) በጽሑፍ ረገድ
ግን በተለይ በቀጣዮቹ ሦስት ምዕት ዓመታት እንደገና ያበበበት ጊዜም ነበር (ዝኒ ከማሁ)
፡፡ ቋንቋዉ ካለው ጥንታዊነት እና በቋንቋዉ ከተሰነዱት ቁም ነገሮች ጠቀሜታ አንጻር
በውጭና በሀገር ቤት የብዙ ምሁራንን ትኩረት እንደሳበ በተለይ ደግሞ በውጭ ምሁራንና
ተቋማት በቋንቋዉ ላይ የተሠሩ ሥራዎች በዐይነትም ኾነ በብዛት ከሀገር ውስጡ ጋር
ሲነጻጸር የላቀ ስለመኾኑ አምሳሉ (2006፣ 10) በአንደኛዉ ሀገር አቀፍ የግእዝ ጉባኤ ላይ
“የግዕዝ ጥናት ምጥን ምልከታ” በሚል ርእስ ባቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ላይ አረጋግጧል፡፡

በሀገር ውስጥ ምሁራንም በረካታ ሥራዎች የተሠሩ ሲኾን በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱ
ሥራዎች መካከል አንዱ እና የመጀመሪያዉ በ1889 ዓ. ም የታተመው የታየ ገብረ
ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ነው (ሌስሎው፣ 1991፣ መግቢያ) ፡፡ ይህም መጽሐፍ
በሃይማኖት መሪዎችና በሊቃውንት ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና እንደ አብነት የሚጠቀስ
ስለመኾኑ ዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ በ1958 ዓ. ም ባሳተመው የታየ ገብረ ማርያም
መጽሐፈ ሰዋስው (ይህ ዕትም ከዚህ በኋላ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሰ2 በሚል ተወክሏል)
መግቢያዉ ላይ ገልጧል፡፡ ብዙዎቹ የውጭና የሀገር ውስጥ ምሁራን ሥራዎች ባብዛኛዉ
የሚያተኩሩት ስለፊደላት አመጣጥና አጠቃቀም፤ ስለቃላት አመሠራረትና ዐይነቶቹ እና
ስለዐረፍተ ነገር አወቃቀር ነው፡፡ የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ግን ከሌሎች
ቀደምት የግእዝ መጻሕፍተ ሰዋስው በተለየ መልኩ የዚህ ጥናት ርእሰ ጉዳይ የኾኑትን
ተመኵሳይያን ቃላትን በየፈርጃቸዉ በመመደብ ሞኵሼነትን በተጨማሪ በስፋት
አብራርቷል፡፡

ተመኵሳይያን ማለት ምን ማለት ነው? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ሲኾን ነገር ግን ለዚህ ጥያቄ
ምላሽ ከመሰጠቱ በፊት መጀመሪያ ስለ መጽሐፉ ባለቤት ታየ ገብረ ማርያም የተወሰነ
ግንዛቤ መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡

2
.

እንደ ዓለም (1971-72፣ 14) ገለጻ ታየ ገብረ ማርያም የተወለደው በበጌምድር1 ከምከም
ቃሮዳ2 ይፋግ3 በተባለ መንደር በ1853 ዓ. ም በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግሥት ሲኾን
ከዚህ ዓለም ሕይወቱ ያለፈው ደግሞ በነሐሴ ወር 1916 ዓ.ም ነው፡፡ ታየ እናቱ በልጅነቱ
በመሞቷ እና አባቱም በአካባቢዉ ባለመኖሩ ምክንያት አጎቱን ፍለጋ ወደ ትግራይ ሲኼድ
አጎቱም ወደ ህንድ ቦምባይ ኺዶ ስላገኘው ወደ ህንድ ለመሄድ ምጽዋ በደረሰ ጊዜ
እምኩሉ4 ከሚባል የሚሽን ትምህርት ቤት ገብቶ የትርጕም እና የማስተማር ሥራ
ማከናወን ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ ነበር መጽሐፈ ሰዋስው የተባለውን ሥራዉን ያዘጋጀው፡፡

ነገር ግን ታየ በመጽሐፈ ሰዋስው ላይ የሠራው ሥራ ወደ አማርኛ የመተርጐም ሥራ


እንጅ የመጽሐፉ የመጀመሪያ አዘጋጂ ወይም ጸሓፊ እንዳልኾነ የሚገልጹ ምሁራን አሉ
(ዓለም፣ 1971-72፣ 14) ፡፡ ስማቸው እና መሠረትም (2009፣ 36፣ 96) ታየ የዋሸራ ተማሪ
እንደኾነና መጽሐፈ ሰዋስው በሚል የጻፈው አገባብም የዋሸራ አገባብ እንደኾነ
ግምታቸዉን አስቀምጠዋል፡፡

በመጽሐፈ ሰዋስው መቅድሙ ላይ “መጽሐፈ ሰዋስው ዘተቀድሐ እም፹ ወ፩ መጻሕፍት


ወእምአበዊነ ሊቃውንት/” ከሰማኒያ አንዱ እና ከአባቶቻችን ሊቃውንት የተቀዳ መጽሐፈ
ሰዋስው እንዲሁም በመሰ2 ከመጽሐፉ ሽፋን ላይ እና ቋንቋ በሚል ርእስ ከተጠቀሰው
የመጽሐፉ መቅድም ላይ ˝መጽሐፉ ከግእዝ ወደ አማርኛ በአለቃ ታየ ተተረጐመ ወይም
እንደተተረጐመ ̋ የሚለው አገላለጽ ታየ የመጽሐፉ ተርጓሚ እንጅ ጸሓፊዉ እሱ አይደለም
የሚለውን ሐሳብ በመጠኑም ቢኾን ጠቋሚ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በጥናት የሚመለስ ቢኾንም
ቅሉ ነገር ግን መጽሐፉ መጸሐፈ ሰዋስው በሚል በግእዝ እና በአማርኛ በተደራጀ መልኩ
ተዘጋጅቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1889 ዓ.ም የታተመው በታየ ነው በሚለው ላይ ክርክር ያለ
ስለመኾኑ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂ ባደረገው የሰነድ ዳሰሳ መረጃ አላገኘም፡፡ በዚህ መነሻነት
ነው የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂ “ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው”
በሚል ርእስ የመጽሐፉን ባለቤትነት ለታየ ገብረ ማርያም ያደረገው፡፡

1
በጌምድር- በምሥራቅ ተከዜ፣ በምዕራብ ጣና ሐይቅ፣ በሰሜን በለሳ ወንዝ፣ በደቡብ በሽሎና ዐባይ ወንዝ የሚያዋስኑት ኮረብታማ ሀገር ነው (ቤሪ
,2003 )፡፡ በአሁኑ ሰአት አብዛኛውን የደቡብ እና የሰሜን ጎንደር ዞኖችን ያካልላል፡:
2
ከምከም- ቃሮዳ- በአሁኑ ሰአት በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ውስጥ የተወሰኑ ቀበሌዎች በጋራ የሚጠሩበት ስም ነው፡፡

3
ይፋግ-በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦ ከምከም ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ቀበሌዎች አንዱ ነው
4
ምንኩሉ/እምኩሉ- ምጽዋ አካባቢ የሚገኝ የሰዊድሽ ወንጌላውያን መልእክተኞች ማእከል የነበርና የአካባቢ ልጆችን የሚያስተምሩበት የነበር ቦታ
ነው (ስሚድት,2005)::

3
.

ታየ በዐፄ ምኒልክ ትእዛዝ መሠረት የአማርኛ እና ግእዝ ቋንቋ አስተማሪ ኾኖ ጀርመን


ሀገር ለሦስት ዓመታት የቆየ ሲኾን ከመጽሐፈ ሰዋስው በተጨማሪ ከሠራቸዉ ሥራዎች
መካከል በ1920 ዓ. ም የታተመ “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” እና “መዝገበ ቃላት”
(ያልታተመ) የሚሉት የጽሑፍ ሥራዎቹ ይጠቀሳሉ (ዓለም፣1971-72፣ 22) ፡፡

ወደ ጥያቄዉ ስንመለስ የተመኵሳይያንን ምንነት በተመለከተ በመጽሐፈ ሰዋስው ግልጽ


የኾነ ትርጕም አልተሰጠውም፡፡ በምዕራፍ ኹለት ከሌሎች የመስኩ ምሁራን እይታ አንጻር
ጭምር በዝርዝር ትርጕሙ የሚዳሰስ ሲኾን በዚህ ክፍል የሚነሣው በመጽሐፈ ሰዋስው
ከተጠቀሱት ምሳሌዎች ውስጥ የተወሰኑትን በማውሳትና ከተሰጠው ዐወዳዊ ፍች በመነሣት
ታየ ተመኵሳይያንን የተረዳበትን አግባብ በመጠኑ ለመገንዘብ ነው ፡፡

ተመኵሳይያን የሚለው የግእዝ ቃል ተመኵሳዪ የሚለው ሣልስ ውሰጠዘ5 ብዙ ቁጥር ሲኾን


ተመኵሰየ ሞኵሼ ኾነ ከሚለው ግስ የወጣ ቃል ነው፡፡ በመጽሐፈ ሰዋስው ከተጠቀሱት
ማሳያዎች እንደምንረዳው ለቃላት ሞኵሼነት ባብዛኛዉ መነሻ የተደረጉት አሁን ላይ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት ናቸው ፡፡ እነዚህ ፊደላት በዘፈቀደ ሥራ ላይ
የዋሉ ሲኾን ቃላቱ የተዋቀሩበት ፊደላት በቅርጽ ቢለያዩም በድምፅ ተመሳሳዪ እስከኾኑ
እና በቃላቱ መካከል የትርጕም ልዩነት አለ ተብሎ የሚታሰብ ከኾነ ቃላት ተመኵሳይያን
የሚባሉ መኾናቸው ነው በመጽሐፉ የተገለጸው ፡፡ ለምሳሌ፦ ዐቀመ---ፈጸመ (ቀ
ይጠብቃል) እና አቀመ--መለሰ (ቀ አይጠብቅም) (ገጽ 36) የሚለውን ብንመለከት ጥንድ
ግሶቹ በድምፅ/ አነባበብ ተመሳሳዪ ቢመስሉም በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ግን ልዩነት
አላቸው፡፡

ሌላዉ ደግሞ ሰብሐ--አመሰገነ (ብ) ይጠብቃል እና ሰብሐ--ሰባ/ወፈረ (ብ) ይላላል (ገጽ 36)
የሚለውን ብንወስድ የግእዙ ኹለቱም ግሶች ከ ‘ብ’ መጥበቅና መላላት ውጭ በአጻጻፍ
ቅርጻቸዉ ተመሳሳዪ ናቸው፡፡ ነግር ግን ሰባ ወይም ወፈረ የሚለው የግእዝ ግስ የሚጻፈው
በ“እሳቱ ሰ” ወይስ በ“ንጉሡ ሠ” የሚለውን ከሌሎች ምሁራን ጽሑፎች አንጻር ስናየው
ኪዳነ ወልድ (1948፣ 660) እና ዲልማን (1907፣248) ሰባ ለሚለው የአማርኛ ቃል
የሚጠቀሙት የግእዝ ግስ ሠቢሕ -ሠቢሖት ከሚለው አርእስት የሚገኘውን ሠብሐን ነው፡፡

5
ሣልስ ውስጠዘ- አገባብ ሳይኖረው በውስጡ ‘የ’ የሚል ትርጕም የሚያሰጥ እና መጨረሻዉ ፊደል ሣልስ የኾነ ቅጽል (አቤሴሎም 2009) ነው ፡፡
ምሳሌ፡ጸሓፊ--የሚጽፍ፡፡

4
.

መጽሐፈ ሰዋስው አመሰገነ እና ሰባ ለማለት በተመሳሳዪ ሰብሐን መጠቀሙ ከሌሎች


ሊቃውንት ጽሑፎች አንጻር ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን በዘፈቀደ
የሚጠቀም መኾኑን የሚያመላክት ነው፡፡ ይህ ተመኵሳይያን በመጽሐፈ ሰዋስው
የተገለጹበት መንገድ ነው ፡፡

1.2. የጥናቱ አነሣሺ ምክንያት

የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ከቀደምት የሀገር ውስጥ ሥራዎች አንዱ ሲኾን
ሞኵሼነትንም ተመኵሳይያን በሚል ንኡስ ርእስ ሥር በሰፊው በማብራራት ቀዳሚዉ
ነው፡፡ አጥኚዉ ይህን መጽሐፍ መሠረት በማድረግ ጥናቱን ተመኵሳይያን ላይ ያደረገበት
ዋናዉ አነሣሺ ምክንያት ሞኵሼነት የተገጸበት መንገድ በተለይ አሁን ላይ ድምፃቸዉ
የማይለየው ፊደላት ( ሀ፣ ሐ እና ኀ፤ አ እና ዐ፤ ሰ እና ሠ፤ ጸ እና ፀ) ተመሳሳዪ እንደኾኑ
በመቁጠር በመጽሐፉ ውስጥ በዘፈቀደ መጻፋቸውና በእነዚህ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላት
ተመኵሳይያን መባላቸው፤ እንዲሁም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉም ኾነ በሌሎች
ፊደላት የተዋቀሩ አዕማድ ግሶችም አንዱ የሌላው አስደራጊ ወይም ተደራጊ ግስ ኾኖ እያለ
እና የተለየ ትርጕም በመካከላቸው ሳይኖር በምስጢር የተለያዩ አድራጊ፣ አስደራጊ እና
ተደራጊ የመሰሉ ተመኵሳይያን/ ሞኵሼዎች ቃላት መባላቸው እና ከአንድ የግስ ሥር
በርባታ የተገኙ እና በርባታቸው ምክንያት የተለያየ ጾታ፣ መደብና ቁጥር የሚገልጹ ቃላት
በትርጕም ተለያይተው በንባብ የተመሳሳሉ ተመኵሳይያን ቃላት መባላቸው እና ይህን
መነሻ በማድረግም ሌሎች ጸሓፊዎችና መምህራንም መጻፋቸውና ማስተማራቸው ሲታይ
በእርግጥስ በመጽሐፉ በተገለጸው አግባብ ሞኵሼነት አለ? የለም? የሚለው ጥያቄ መነሣቱ
ነው ፡፡

በዘርፉ ምሁራንም በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ መንገድ ታየ በገለጸበት መንገድ


ተመኵሳይያን ቃላትን ከማብራራት ባለፈ የመጽሐፈ ሰዋስው አገላለጽ ተገቢነት ያለው
ስለመኾን አለመኾኑ የተደረገ ጥናት የለም፡፡ ለምሳሌ የለይኩን ብርሃኑን (1997) እና የአፈ
ወርቅ ዘውዴ (1988) ሥራዎችን ስንመለከት በመጽሐፈ ሰዋስው በምድብ ኹለትና ሦስት
የተጠቀሱት የተመኵሳይያን ዐይነቶች ናቸው የተገጹት ፡፡

እንዲያውም ተመሳሳዪ ደምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን የቅርጻቸዉ መለያየት ግምት


ውስጥ ሳይገባ በድምፅ ለጊዜው በመመሳሰላቸው ብቻ አንድ ዐይነት እንደኾኑ ተቆጥረው

5
.

ከመልክእ ደራሲዎች እስከ ቅኔ ዘራፊዎች ድረስ ፊደላቱ በቤት መምቻነት በዘፈቀደ ጥቅም
ላይ የሚውሉ ስለመኾኑ ተከታዮቹ ምሳሌዎች ማሳያዎች ናቸው ፡፡

ለምሳሌ፦ መልክእ--መልክአ ማርያም -ለከናፍርኪ

“…ባልሕኒ እምነ ወይሌ ወአንግፍኒ እምላሕ፤

እስመ ለልብየ ኀዘኑ ብዙኅ፡፡” (ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ 1984)

በዚህ መልክእ “ሐመሩ ሐ” እና “ብዙኃኑ ኀ” ለቤት መምቻነት አገልግለዋል ፡፡

ቅኔ--ዕዝል ክብር ይእቲ

“ተአስረት ሔዋን በዕዳሃ በኀጉለ ንዋይ ዘኤርሁ፤

ወአዳም ተአስረ በዘፈድፈደ ዕዳሁ፤

ወኢየሱስሀ ዋሕሶሙ እንዘ ያቀርቡ ናሁ፤

አዳም ወሔዋን ሙቁሐን እማእሰሮሙ ተፈትሑ፡፡” (ታደለ፣ 2009፣ 151)

ከዚህ ላይ ባለቅኔዉ “ሃሌታዉ ሀ” ን እና “ሐመሩ ሐ” ን ለቤት መምቻነት ተጠቅሟል፡፡

ይህ ዐይነት አጠቃቀም በአንድ ፊደል የአናባቢ ርባታ ውስጥም በግእዝና በራብዕ ፊደላት
መካከል ይስተዋላል፡፡ ለምሳሌ ያክል፦ ጉበኤ ቃና ቅኔ-

“መርቆሬዎስ አብ ይደልወከ ፍስሓ፤

ሃይማኖት ወልድከ እስመ ለፈረስ በጽሐ፡፡” (አፈወርቅ፣ 1988፣ 34)


የሚለውን ብንመለከት ለቤት መምቻነት ባለቅኔዉ የተጠቀመው ራብዑ ን “ሓ” እና ግእዙ
ን “ሐ” ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው አሁን ላይ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት
አንድነትና ልዩነት በሊቃውንቱ ዘንድ ትኩረት ያልተሰጣቸው መኾኑን ነው ፡፡

በእርግጥ አሁን ባለው ተጨባጪ ኹኔታ በጕረሮ እና በጥርስ የሚነገሩ ፊደሎችን በቅርጽ
እንጅ በድምፅ መለየት ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ እንደ ዲልማን (1907፣ 2፣
47) አገላለጽ ይህ ኹኔታ የተፈጠረው አማርኛ የመንግሥት የሥራ ቋንቋ መኾኑን ተከትሎ
በአማርኛ ቋንቋ ተጽዕኖ እና የቋንቋዉ ተናጋሪ የሴሜቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ካልኾኑ ህዝቦች

6
.

ጋር በነበረው የዕለት ተዕለት መስተጋብር ምክንያት ኾኖ በመጀመሪያ በንግግር ቀጥሎም


ቀስ በቀስ በጽሑፍ ሥራውም ችግሩ እንደተስፋፋ ነው፡፡

̋ጊዜውን በትክክል መጥቀስ ባይቻልም የፊደላት የአጻጻፍ ችግሩ የተፈጠረው የብራና


መጻሕፍትን መጻፍ እንደ ንግድ ሥራ ከተቆጠረበት ጊዜ ጀምሮ ነው˝ የሚለው ደግሞ በላይ
(2009፤ 10) ነው፡፡ ይህም አሁን ላይ በሊቃውንቱ የሚታየውን ዕውቀትን ከጽሕፈት
አስተባብሮ ላለመያዝ እንደ አንድ ምክንያት ሊኾን ስለሚችል አመክንዮዉ ተገቢነት
ያለው ስለመኾኑ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅም ያምናል፡፡

ምንም እንኳ ተግባራዊ ውጤት ባይመጣም የእነዚህ ፊደላት ድምፅ ከመጥፋቱ የተነሣ
ለአንድ ድምፅ ተደጋጋሚ ፊደላትን መጠቀም አያስፈልግም በሚል አስተሳሰብ ፊደላቱን
የመቀነስ እንቅስቃሴ ከዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት
ዘንድ ሲከወን የቆየ ተግባር ነው (ሙሉሰው፣ 2001፣ 96-97) ፡፡ ይህንም ሐሳብ በመደገፍ
ፊደላቱን ቀንሶ ድርሰቱን እንደጻፈ ሀዲስ (1996፣ 8) ይገልጻል፡፡

በተቃራኒዉ ደግሞ ሥርዐተ ጽሕፈቱ በዋናነት የጥንታዊ ሥልጣኔና ማንነት ምልክት


በመኾኑና ለውጡ የዛሬዉ ትውልድ ቀደምት ጽሑፎችን አንበቦ እንዳይረዳ ያደርገዋል
በሚል ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን ጨምሮ ባጠቃላይ የሥርዐተ
ጽሕፈቱን መሻሻልና መለወጥ የሚቃወሙ ግለሰቦችና ተቋማት እንደነበሩም ሙሉሰው
(2001፣ 98) ያብራራል፡፡ይህም ሐሳብ ተገቢነት ያለው ስለመኾኑ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅም
የሚጋረው ነው ፡፡

በመኾኑም ይህ ጥናት በመጽሐፈ ሰዋስው በተገለጸው አግባብ የቃላት ሞኵሼነት መኖር


አለመኖሩን የሚመረምረው ቃላትን ተመኵሳይያን ለማለት መነሻ በኾኑትና አሁን ላይ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት መካከልም ሞኵሼነት ያለ ስለመኾን
አለመኾኑ ጭምር በመፈተሽ ነው ፡፡

1.3. የጥናቱ ጥያቄዎች

ይህ ጥናትም ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣል፡፡

 ተመኵሳይያን ሲባል ምን ማለት ነው?

7
.

 በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን እንዴት ነው የተገለጹት?


 የተገለጹበት መንገድስ ከሌሎች ሊቃውንት እይታና ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች አንጻር
እንዴት ይታያል?
 ተመሳሳዪ ድምፅ ባላቸው ፊደላት በተዋቀሩ ቃላት ሞኵሼነት አለ?
 በፊደላቱ መካከልስ ሞኵሼነት አለ? የለም?

1.4. የጥናቱ ዐላማ

የጥናቱ ዋና ዐላማ በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው በተገለጸው አግባብ


ተመኵሳይያን ቃላት ያሉ ስለመኾን አለመኾናቸው መመርመር ነው፡፡

1.4.1 የጥናቱ ዝርዝር ዐላማዎች

ከዚህ ዋና ዐላማ በመነሣት ጥናቱ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዝርዝር ዐላማዎች አሉት፡፡
እነሱም

 ስለተመኵሳይያን ምንነት መግለጽ፤


 በመጽሐፈ ሰዋስው ሞኵሼነት የተገጸበትን አግባብ መፈተሽ፤
 ተመኵሳይያን የተገለጹበት መንገድ ከሌሎች ሊቃውንት እይታና ተዛማጂ የሴም
ቋንቋዎች አንጻር ትክክል ስለመኾን አለመኾኑ መመርመር፤
 ተመሳሳዪ ድምፅ ባላቸው ፊደላት በተዋቀሩ ቃላት ሞኵሼነት ስለመኖር አለመኖሩ
ማሳየት፤
 ተመሳሳዪ ድምፅ ባላቸው ፊደላት መካከል ሞኵሼነት ያለ ስለመኾን አለመኾኑ ማሳየት
የሚሉት ናቸው፡፡

1.5. የጥናቱ አስፈላጊነት

ይህ ጥናት የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች ያስገኛል ተብሎ ይታሰባል ፡፡

ስለ ተመኵሳይያን ቃላት ምንነት በጠቅላለው በተለይ ደግሞ በጕረሮ እና በጥርስ በሚነገሩ


ፊደላት መካከል እንዲሁም በእነዚህ ፊደላት በተዋቀሩ ቃላት መካከል ሞኵሼነት መኖር
አለመኖሩን ለመለየት ይጠቅማል፡፡

8
.

ቅርጻቸዉን ይዘን ድምፃቸዉን ያጠፋናቸውን ፊደሎች ልዩነታቸዉን ተገንዝቦ ተገቢዉን


ፊደል በተገቢዉ ቦታ በመጻፍ አሁን ያለውን በዘፈቀደ የመጻፍ እና የግጥም ቤት
የመምታት ችግር ለመቅረፍ እንደመነሻ ያገለግላል፡፡

በግእዝ ቋንቋ የተሰነዱ ጥንታዊ መዛግብትን መርምሮ ለመረዳት እና ለተገቢዉ ዐላማ


ለማዋልና ለቋንቋዉ ኹለንተናዊ እድገት ይጠቅማል ተብሎ ይታሰባል፡፡

1.6. የጥናቱ ዘዴ

ይህ ክፍል ጥናቱ ይዞ የተነሣውን ዐላማ ከግብ ለማድረስ መረጃዎቹ የሚገኙበትን ምንጭ፣


የሚሰበሰቡበትን እና የሚተነተኑበትን መንገዶች የሚመለከት ሲኾን፣ እያንዳንዳቸውም
እንደሚከተለው በአጭር በአጭሩ ይብራራሉ፡፡

1.6.1. የመረጃ ምንጭ

አንድ ጥናት ይዞ ለተነሣው ጥያቄ መፍትሔ ለማፈላለግ እና ችግሮችን ለመፍታት በቂና


አስተማማኚ መረጃ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ጥናት የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያ ሰነድ ፍተሻ
ሲኾን በዋና የመረጃ ምንጭ በመኾን ያገለገሉት የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው
እና በሌሎች አካላት በ1958፣ 1982 እና 1992 ዓ. ም የታተሙ የዚሁ መጽሐፈ ሰዋስው
ሦስት ቅጅዎች ናቸው፡፡ በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ናሙናዎች
የተመረጡትም በዐላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴን በመጠቀም ነው፡፡ እንደ በርግ
(2001፣ 32) አገላለጽ ዐላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴ በሚመረጥበት ጊዜ አጥኚዉ
ናሙናዎችን ለመምረጥ ጥናቱ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ውስጥ በተወሰኑት ጉዳዮች ላይ
ያለውን የተለየ ዕውቀት በመጠቀም እንደኾነ ነው የምንገነዘበው ፡፡ በዚህ መሠረት ነው
የተወሰኑ ተመኵሳይያን ቃላት በናሙናነት የተመረጡት ፡፡

በካልኣይ ምንጭነት ደግሞ ሥራ ላይ የሚውሉት ሌሎች የተጻፉ ሰነዶች ሲኾኑ ለዚህ


ጥናት ዐላማ ሲባል የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው መነሻ ኾኖ ከጉዳዩ ጋር
ተያያዥነት ያላቸው በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ሰዎች በግእዝ ቋንቋ ላይ የተጻፉ
መጻሕፍት እና የተደረጉ ጥናቶች፤ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እና ሌሎች
ድርሳናት እንዲሁም ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች መዝገበ ቃላትን በመረጃ ምንጭነት አጥኚው
ተጠቀሟል፡፡

9
.

1.6.2. የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ

ለዚህ ጥናት መነሻ የኾነው በ1889 ዓ.ም የታተመው የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ
ሰዋስው ሲኾን የጥናቱን ጥያቄዎች መፍትሔ የሚሰጡ መረጃዎች ደግሞ የሚገኙት ከላይ
እንደተገለጸው ሰነድ በመፈተሽ ነው፡፡ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና አስተማማኚ
መረጃዎች ለማግኘት ደግሞ አጥኚዉ የተለያዩ ሰነዶችን የተጠቀመ ሲኾን ለጉዳዩ
አግባብነት ያላቸው መረጃዎች የተገኙት ከተመረጠው ርእሰ ጉዳይ ጋር ተዛማጂ ጉዳዮችን
ከየሰነዶቹ በመፈተሽ ነው፡፡

1.6.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ

ይህ ዘዴ የተሰበሰቡ መረጃዎች ከጥናቱ ርእሰ ጉዳይ እና ከጥናቱ ጥያቄዎች ጋር ተገናዝቦ


የሚመረመርበትን መንገድ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ጥናትም በመጽሐፈ ሰዋስው
ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን አግባብ የሚመረምረው ከሌሎች ተዛማጂ የሴም
ቋንቋዎችና ሌሎች መጣጥፎች ጋር በማነጻጸር በመኾኑና መረጃዎቹም የሚገኙት ሰነድ
በመፈተሽ በመኾኑ የጥናቱ ዐይነት ዐይነታዊ ምርምር ነው፡፡ ምክንያቱም ዐይነታዊ
የምርምር ዘዴ ከቁጥር ይልቅ ያንድን ነገር ከትርጕም፣ ከፅንሰ ሐሳብ፣ ከውክልና እና
ካጠቃላይ የቁሱ ምንነት ላይ የሚያተኩር በመኾኑ ነው (በርግ፣ 2001፣ 2-3) ፡፡ መረጃዉ
የተተነተነው ደግሞ ገላጪ የአተናተን ዘዴን በመጠቀም ሲኾን በመጀመሪያ ለጥናቱ መነሻ
የኾነው መጽሐፈ ሰዋስው እና በሌሎች አካላት የታተሙ የዚሁ መጽሐፍ ቅጅዎች በርእሰ
ጉዳዩ ላይ ያላቸው አንድነትና ልዩነት ከተዳሰሰ በኋላ የተገኙ ልዩነቶች ጭምር ከልዩ ልዩ
ሰነዶች ከተሰበሰቡት መረጃዎች ጋር በማነጻጸር ለተነሡት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል
፡፡

1.7. የጥናቱ ወሰን

ይህ ጥናት የሚያተኩረው በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን


የተገለጹበትን አግባብ መመርመር ላይ በመኾኑ በዋናነት መነሻ ኾኖ የሚያገለግለው
ይኸው በ1889ዓ. ም የታተመው መጽሐፈ ሰዋስው ሲኾን በሌሎች አካላት የታተሙ የዚሁ
መጽሐፈ ሰዋስው ሦስት ቅጅዎችም ከዚሁ ቀዳማይ ዕትም ጋር ይመሳከራሉ፡፡ በዚህ
መጽሐፍም ሞኵሼነት የተገለጸው ግስን፣ ነባርን፣ ዘርንና አገባብን መሠረት በማድረግ

10
.

ነው፡፡ በመኾኑም ጽሑፉ በእነዚህ የቃል ክፍሎች በተለይ በተለምዶ ሞኵሼ እየተባሉ
በሚጠሩ ፊደላት በተዋቀሩ ቃላት ላይ ሞኵሼነት አለ? የለም? የሚለውን ከተሰበሰቡ
መረጃዎች አንጻር መመርመር በመኾኑ ጥናቱ በእነዚህ የቃላት ክፍሎች ላይ ብቻ የተገደበ
ነው፡፡ እንዲሁም ጥናቱ በመጽሐፈ ሰዋስው “ተመኵሳይያን” በሚለው ርእስ ብቻ የተገደበ
በመኾኑ ሌላዉን የዚሁን መጽሐፍ ክፍል አይዳሰስም ፡፡ በተጨማሪም ከመጻሕፍቱ
ተደራሽነት አንጻር ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን በሥርዐተ ጽሕፈት
አጠቃቀማቸዉ የተለያዩ ስለመኾናቸው በአስረጂነት እና በማነጻጸሪያነት ሥራ ላይ የዋሉት
ተዛማጂ ሌሎች የሴም ቋንቋዎች የዐረብኛ፣ የዕብራይስጥ፣ ትግረ እና የትግረኛ ቋንቋዎች
በመኾናቸው ንጽጽሩ በእነዚህ ቋንቋዎች ብቻ የታጠረ ነው፡፡

11
.

ምዕራፍ ኹለት

2. የተዛማጂ ጽሑፎች ዳሰሳ/ ክለሳ ድርሳን

ይህ ምዕራፍ በዋናነት ኹለት ንኡሳን ርእሶችን የያዘ ሲኾን፣ የመጀመሪያዉ ከዋናዉ ርእሰ
ጉዳይ ተመኵሳይያን ማለት ምን ማለት ነው ከሚለው ጀምሮ በመጽሐፈ ሰዋስው
ተመኵሳይያን የተባሉ የቃላት ክፍሎች (ግስ፣ አዕማድ፣ ዘር፣ ነባርና አገባብ) እንዲሁም
ተመኵሳይያንን በየፈርጁ ለመመደብ ሥራ ላይ የዋሉ መሠረታዊ ሐሳቦችን ማለትም
የቃላት ሥርዐተ ንባብ (ጥብቀት፣ ወዳቂና ተነሺ፣ ተጣዪና ሰያፍ) እና የአንድ ቃል
የተለያየ ትርጕም መስጠት በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ በዝርዝር የሚብራሩበት ክፍል ነው፡፡
ኹለተኛዉ ክፍል ደግሞ በርእሰ ጉዳዩ ዙሪያ የተጻፉ መጻሕፍትና የተሠሩ ጥናታዊ
ጽሑፎች የሚዳሰሱበት ነው፡፡

2.1.ፅንሰ ሐሳባዊ ዳራ

2.1.1 የተመኵሳይያን ምንነት

ተመኵሳይያን የሚለው የግእዝ ቃል የወንድ ፆታን የሚያመለክት ብዙ ቁጥር ሲኾን


ተመሳሳዪ/ ሞኵሼ የኾኑ ተብሎ በገላጪነት ሊተረጐም ይችላል፡፡ይህን በሚደግፍ መልኩ
ሞኵሼ የሚለው ቃል የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል በ1993 ዓ. ም
ባሳተመው የአማርኛ መዝገበ ቃላት “አንድ ዓ(ዐ)ይነት መጠሪያ ስም ያላቸው ሰዎች ወይም
ተመሳሳይ(ዪ) መጠሪያ ወይም ድምፅ ያላቸው ሆሄያት ወይም ፊደላት” በማለት ትርጕም
ተሰጥቷል፡፡

በኦክስፎርድ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላትም (ብራድቤሪ፣ 1948) ኔምሴክ (namesake)


የሚለው አቻ የእንግሊዝኛ ቃል የተሰጠው ትርጒም “Namesake-One who is named
after another or for whom another is named. …-A person with the same name
as another…” ወደ አማርኛ በግርድፉ ሲመለስ ሌላ ሰው ይጠራበት በነበረ ስም የሚጠራ
ሰው ወይም እሱ ይጠራ በነበረበት ስም ሌላ ሰው የሚጠራበት፣…ከሌላ ሰው ጋረ ተመሳሳዪ
ስም ያለው ሰው…የሚል ነው፡፡

12
.

በኹለቱም መዛግብተ ቃላት ሞኵሼ/ ተመኵሳዪ የሚለው ቃል በአብዛኛዉ የስም


ተመሳሳዪነትን የሚያመለክት መኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡ መመሳሰል በጠቅላላዉ የስም
ተመሳሳዪነት ደግሞ በተለየ ኹኔታ ሲባል ምን ማለት ነው የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ሲኾን
ይህንም የዘርፉ ምሁራን ለቃሉ ከሰጡት ትንታኔ በመነሣት እንደሚከተለው ይዳሰሳል፡፡

ቃሉ የተገኘበትን ግስ መሠረት በማድረግ የተለያዩ ምሁራን ሞኵሼ/ ተመኵሳዪ የሚለውን


ቃል በተለያየ መንገድ አብራርተውታል፡፡ በመጀመሪያም የኪዳነ ወልድን(1948፣ 552)
ትርጓሜና ማብራሪያ ስንመለከት መኵሰየ፤ ተመኵሰየ /ኰሰየ/ ለሚለው ቃል አሞካሼ፤
ሞኵሼ ኾነ፤ በስም ተባበረ በማለት ትርጕም የሰጠው ሲኾን ከዚህም ተመኵሳዪ በአማርኛ
ሞኵሼ የኾነ ወይም በስም የተባበረ የሚል ገላጪ ቃል ይወጣበታል፡፡ በማስረጃነት
ከጠቀሳቸው ጥቅሶች ውስጥ አንዱ ከመጽሐፈ ምስጢር ላይ የተወሰደው ነው፡፡ ይህም
“ተመኵሰዩ መልከ ጼዴቅ ወኢያሱ ምስለ ክርስቶስ በጸዊረ ስም ወአኮ በአማን” - ወደ
አማርኛ ሲመለስ - “መልከ ጼዴቅና ኢያሱ በመኾን ያይደለ ስምን በመያዝ ከክርሰቶስ ጋር
ሞኵሼዎች ሆኑ” (ጊዮርጊስ፣ 2001፣ 270) የሚል ሲኾን ተመኵሰዩ--መኵሼ ኾኑ የሚለው
ግስ በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ የተሰጠውን ዐውዳዊ ፍች ስንመለከት መልከ ጼዴቅና ኢያሱ
ከክርስቶስ ጋር በስም ሞኵሼዎች ሆኑ ከተባሉባቸው ምክንያቶች ውስጥ መልከ ጼዴቅ
የእግዚአብሔር ካህን ተብሎ እንደተጠራ ኢየሱስ ደግሞ በጳውሎስ አንደበት ሊቀ ካህናት
መባሉ፤ ኢያሱ ደግሞ በገባኦን ፀሐይን እንዳቆመና ኹለተኛዉን ቀንም አንድ ቀን
እንዳደረገ፤ ኢየሱስም በቀራንዮ ፀሐይን ማጨለሙ እና አንዲቱንም ቀን ኹለት ዕለት
ማድረጉ የሚሉት ይገኙባቸዋል (ዝኒ ከማሁ፣ 269-270)፡፡

ከተጠቀሰው ማስረጃ መረዳት እንደሚቻለው መልከ ጼዴቅ እና ኢየሱስ ኹለቱም ካህናት


በመባላቸው የስም ተመሳሳዪነት ሲኖራቸው ኢያሱ እና ኢየሱስ ግን የድርጊት እንጅ የስም
ተመሳሳዪነት የላቸውም፡፡ ድርጊቱንም ስንመለከት ኢየሱስ ፀሐይን በማጨለም በፀሐይ
አንድ ቀን የነበረውን ኹለት ቀን ማድረግ ሲኾን ኢያሱ ደግሞ ፀሐይን ከብርሃኗ በማቆም
ኹለቱን ቀን አንድ ቀን ማድረግ ነው፡፡ይህም ድርጊቱ የተፈጸመበት ቁስ አካል (ፀሐይ)
ተመሳሳዪ ከመኾን ባለፈ በኹለቱም የተፈጸመው ድርጊት ተመሳሳዪነት የለውም፡፡ ነገር
ግን ኢያሱ እንደ ኢየሱስ የፀሐይን ተፈጥሮአዊ ኺደት መቀየር በመቻሉ በፀሐይ ላይ
በተሰጠው ሥልጣን የሚመሳሰል መኾኑን ያሳያል፡፡

13
.

ከዚህም የምንረዳው መልከ ጼዴቅ በመኾን ያይደለ (አኮ በአማን) እንደ ኢየሱስ ካህን
መባሉ በተቀብዖ ስም6 ተመሳሳዪነት ያለው በመኾኑ፤ ኢያሱ ደግሞ በባሕርይ ያልኾነ
እንደ ኢየሱስ ተፈጥሮአዊ ኺደትን መቀየር መቻሉ የድርጊት ተመሳሳዪነት ያለ በመኾኑ
ከኢየሱስ ጋር ስምን በመያዝ ሞኵሼዎች የተባሉ መኾኑን ነው፡፡

ሌላዉ ሞኵሼ ማለት ምስጢሩ ልዩ ኾኖ በጽሕፈትና በአነጋገር የሚገጥም ቃል ነው


በማለት ለሞኵሼ ትርጕም የሰጠው ደስታ (1962፣ 34) ነው፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ከጠቀሳቸዉ
ማሳያዎች መካከል የተወሰኑትን ስንመለከት፦

- የተጣለ እና የተጣላ ቅጽል ተጣይ /ዪ/

- በመጥበቅና በመላላት ደግሞ ሀለወ--አለ/ ለ ይጠብቃል/

ብህለ--አለ/ ለ አይጠብቅም/

-የአድራጊና የተደራጊ አርእስት- ፈወሰ--መፈወስ--መፈወሻ / ወ ይጠብቃል/

ተፈወሰ--መፈወስ--መፈወሻ / ፈ ይጠብቃል/ የሚሉት


ይገኙበታል፡፡

በመጀመሪያዎቹ ኹለት ምሳሌዎች የአማርኛ ቃላቱ በጽሕፈትና በአነጋገር ተመሳስለው


ትርጕማቸዉ የተለያየ መኾኑን ያሳያል፡፡ ምክንያቱም ተጣለ ከሚለው ግስ የወጣው ተጣዪ
የሚለው ገላጪ ቃል የተተወ፣ የተናቀ ነገርን ሲገልጽ ከተጣላ የሚወጣው ቃል ደግሞ
የሚጣላ፣ ፀባይ የሌለው ሰውን ወይም ነገርን የሚገልጽ በመኾኑ እንዲሁም አለ ብሎ
በመጥበቅ መኖርን፤ በመላላት መናገርን የሚያመለክት ግስ በመኾኑ በቃላቱ መካከል
ግልጽ የኾነ የትርጕም ልዩነት፤ የአጻጻፍና የአነባብ አንድነት በመኖሩ ነው፡፡

ነገር ግን ሦስተኛዉን ምሳሌ በተመለከተ መፈወስ--መፈወሻ /ወ ይጠብቃል/ ሲል ማዳንና


ማዳኛን፤መፈወስ--መፈወሻ /ፈ ይጠብቃል/ ሲል ደግሞ መዳንና መዳኛን የሚያመለክት
በመኾኑ በአድራጊነቱና በተደራጊነቱ ከሚለያይ በቀር መፈወስ ወይም መፈወሻ የሚለው
ቃል ተመሳሳዪ /አንድ ዐይነት/ድርጊትን ወይም ቁስን የሚያመለክት ነው፡፡ ይህም
የተጠቀሱት ቃላት እንደ ተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ትርጕማቸዉም ተመሳሳዪ ነው
ከሚባል ባለፈ የተለየ ትርጕም አላቸው በሚል ሞኵሼዎች ናቸው ለማለት የሚያስችል

6
በሹመት የሚገኝን ስም የሚያመለከት ስያሜ ሲኾን ምሳሌ ዲያቆን፣ ጳጳስ ደጅ አዝማቺ ወዘተርፈ (ታየ፣ 1889፣ 4)፡፡

14
.

አይደለም፡፡ ይህም ደስታ ለሞኵሼ ከሰጠው ትርጕም አንጻር ምሳሌነቱ ተገቢነት ያለው
አይደለም፡፡

ለይኩን (1998፣ 325) ደግሞ አንድ ግስ ከአንድ በላይ ትርጕም ኖሮት በተለያየ ንባብ
የተለያየ ትርጕም ሲሰጥ ሞኵሼነት እንደሚፈጠር ምሳሌዎችን በመጥቀስ ያብራራል፡፡
የተጠቀሱት ማሳያዎችም በመጽሐፈ ሰዋስው ላይ የተገለጹት በመጠበቅና በመላላት
የተለያየ ትርጕም የሚሰጡ እና ባንድ ቃል ተነበው የተለያየ ፍች የሚሰጡ ግሶች ናቸው፡፡

ባጠቃላይ ከላይ ከቀረበው የምሁራን ገለጻ የምንረዳው በስም ሳይመሳሰሉ ነገር ግን


በሚያከናውኑት ተግባር መመሳሰል ምክንያት ኹለትና ከዚያ በላይ የኾኑ አካላትም
ተመኵሳይያን መባላቸው እንዳለ ኾኖ ሞኵሼ/ተመኵሳዪ የሚለው ቃል ባብዛኛዉ
ተግባራዊ የሚኾነው የተለያዩ ነገሮች ወይም ሰዎች በተመሳሳዪ ስም ሲጠሩ መኾኑን እና
ይህም የኹሉም ምሁራን ሐሳብ መኾኑን ነው፡፡ በባህላችን ተመሳሳዪ ስም ያላቸዉ ሰዎች
በመጠሪያ ስማቸዉ ከመጠራራት ይልቅ አንዱ ሌላዉን ሞኵሼ በሚል መጠራራት
የተለመደ መኾኑ የዚሁ ማሳያ ነው፡፡ ነገር ግን የስም ተመሳሳዪነታቸው በጽሕፈትና
በአነጋገር ወይስ በአጠራር/በአነጋገር ብቻ በሚለው ላይ በምሁራኑ ዘንድ ስምምነት ያለ
አይመስልም፡፡ በመኾኑም ለሞኵሼነት ወጥ የኾነ ትርጕም ተሰጥቶታል ለማለት የሚቻል
አይደለም፡፡

በብዙኃኑ ምሁራን ዘንድም ሞኵሼነትን ለማሳየት ከተጠቀሱት ምሳሌዎች ውስጥ በድምፅ


ተመሳሳዪነት ያላቸው የሚመስሉ ኾነው ነገር ግን በተለያየ ፊደል የተዋቀሩ ግሶች በብዛት
ይገኙበታል፡፡ ነገር ግን ግሶቹ የተዋቀሩባቸው በተለምዶ ሞኵሼ እየተባሉ የሚጠሩ ፊደላት
በድምፅ መመሳሰላቸው የቋንቋዉ ተጠቃሚ ድምፁን መለየት አለመቻሉን የሚያሳይ እንጅ
በፊደላቱ መካከል የድምፅ አንድነት ኖሯቸው አለመኾኑ በምሁራኑ ዘንድ የታወቀ ነው፡፡
ይህ ከኾነ ደግሞ የቃላት ሞኵሼነት መታየት ያለበት ቃላት አሁን ያላቸውን ያጠራር/
ያነባበብ ተመሳሳዪነት መሠረት በማድረግ ሳይኾን ቃላቱ የተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት
መመሳሰል አለመመሳሰል ግምት ውስጥ በማስገባት ነው ፡፡ ምክንያቱም ቃላቱ
የተዋቀሩባቸው ፊደላት በቅርጽ በተለያዩ ቁጥር በድምፅም እንዲሁ የተለያዩ በመኾናቸው
ነው ፡፡

15
.

ነገር ግን ባብዛኛዉ የሚታየው የፊደላቱን ድምፅ መልሶ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ፈንታ
ለፊደላቱ እና በእነዚህ ፊደላት ተዋፅኦ ለተዋቀሩትም ቃላት/ግሶች ጭምር ሞኵሼ የሚል
ስያሜ በመስጠት ፊደላቱን ማመሳሰልና በዘፈቀደ መጠቀም ነው፡፡ ከዚህም አልፎ ፊደላቱ
አላስፈለጊ ናቸው በሚል ይቀነሱ የሚል ዝንባሌ በምሁራኑ መቀንቀን ከጀመረም ውሎ
አድሯል፡፡ ይህ ደግሞ ከታሪክና ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አንጻር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ
የሚያመዝንና ፊደላቱ ከተቀረጹበት ዐላማና ከሥነ ልሳን መርሕ ጋርም የሚቃረን ነው
የሚኾነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ላይ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው ፊደላት ለጊዜው ድምፃቸዉ
የተመሳሰለ ቢመስልም ነገር ግን የፊደላቱ መካነ ፍጥረትና ባሕርየ ፍጥረት የተለያየ
መኾኑ ፊደላቱ የተለያየ ድምፅ፣ ትርጒምና ዐላማ ያላቸው መኾኑን ስለሚያሳይ ነው፡፡

በዚህ መነሻነት ነው በምዕራፍ ሦስት ተመኲሳይያን ቃላት በመጽሐፈ ሰዋስው የተገለጹበት


አግባብ ሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎችን ምስክር በማድረግ የሚመረመሩት እና
የመጨረሻ ብያኔ የሚሰጠው፡፡

2.1.2 ተመኵሳይያን የተባሉ የግእዝ ቃላት ክፍሎች ምንነት

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል በ1993 ዓ. ም ባሳተመው የአማርኛ


መዝገበ ቃላት መሠረት ቃል አንድን ፅንሰ ሐሳብ ለመወከል በድምፅ የተነገረ ወይም
በጽሑፍ የሰፈረ የድምፅ ምልክቶች ቅንብር፤ አነስተኛ የዐረፍተ ነገር ክፍልፋይ ሲኾን
ይህም በፊደላት ቅንጅት የሚፈጠር ራሱን ችሎ የሚቆም ትርጕም ያለው አነስተኛ አሐድ
ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ቃላት ኹልጊዜ ኹለትና ከዚያ በላይ በኾኑ ፊደላት
ብቻ ይፈጠራሉ ማለት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ትርጕም (አንድን ሐሳብ መግለጽ)
እስከሰጠ ድረስ አንድ ፊደልም ቢኾን እንደ ቃል ሊቆጠር ስለሚችል ነው፡፡ ለምሳሌ ‘ኦ’
ብሎ ሆይ፣ ወዮ ተብሎ በመተርጐም ቃለ ጽዋዔ እና ቃለ ብካይን (የጩኸትና የልቅሶ
ቃል) ሲያመለክት ‘ዝ’ ደግሞ ይህ፣ ይኸ በማለት ስለሚቀጸል (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 194፣
409) ትርጕም ይሰጣሉና ነው ፡፡ ነገር ግን አንድን ድርጊት አጋኖ ለመግለጽ
የምንጠቀምባቸውን በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በኾኑ ፊደሎች የሚነገሩትን አሐዶች
ከቃል ክፍሎች የማይካተቱ ስለመኾኑ የሚገልጹ ምሁራን አሉ (አቤሴሎም፣ 2009፣ 43)፡፡
ይህ አገላለጽ ግን ለቃል ከተሰጠው ትርጕም አንጻር ተገቢ ካለመኾኑም በላይ ስያሜውን
ቃለ አጋኖ በሚል ተጠቅሞ መደቡን ከቃል ክፍል ማውጣቱ ተገቢነት ያለው አይደለም፡፡

16
.

የግእዝ ቃላት ክፍሎችን አመዳደብ በተመለከተ በምሁራን ዘንድ ወጥ የኾነ ምደባ የለም፡፡
እያንዳንዱን የቃላት ክፍሎች እና የምደባ ዐይነቶች ከዚህ ላይ መዘርዘር የዚህ ጽሑፍ
ዐላማ ባለመኾኑ በዚህ ክፍል በተወሰነ መልኩ የሚብራሩት በመጽሐፈ ሰዋስው ሞኵሼነትን
ለማሳየት የተጠቀሱት ግስ ከነአዕማዱ፣ ዘር፣ ነባርና አገባብ የተባሉት ውሱን የቃላት
ክፍሎች ብቻ ናቸው፡፡

ሀ. ግስ

የግስ መነሻዉ ዘመድ ዘር7? ወይስ አርእስት8? በሚለው ላይ ያለው የተለያየ የሊቃውንት
እይታ እንዳለ ኾኖ (አቤሴሎም፣ 2009፣ 93) ግስ የሚለው ቃል የተገኘው- ገሲስ ገሲሶት
ከሚል አርእስት ወይም ገሰሰ-ገሰሰ/ዳሰሰ ከሚል ቀዳማይ አንቀጽ እንደኾነና ገሰሳ፣ ዳሰሳ፣
ግስገሳ ተብሎ እንደሚተረጐም፤ የቃላት መውጫና መግቢያ በመኾኑ አንቀጽ፤
ተቀነባብረው የሚነገሩ የተለያዩ ቃላትን ስለሚያስር ማሰሪያ እና ቃላትን በመሳቡ ሳቢ
በሚል የሙያ ስም እንደሚጠራ አፈወርቅ (1988፣ 266-270) ያብራራል፡፡ ግስ ማለት
ከቀዳማይ ወደ ካልኣይ ከካልኣይ ወደ ሣልሳይ የሚገሰግስ ማለት ነው የሚል ትርጕም
የሰጠው ደግሞ ዐቢይ (2010፣ 167) ነው፡፡

ኪዳነ ወልድ (1948፣ 54) ደግሞ የቋንቋ ጓዝ የዘርና የነባር ማከማቻ ግሰት ነው ብለው
በመወራረስ እና በመመላለስ መርባቱና መዘርዘሩ ደግሞ ተወራራሺ ተመላላሺ የሚል
ትርጕም መስጠት እንደሚሻል ይገልጻል፡፡

ባጠቀላይ በግእዝ ቋንቋ ግስ የሚባለው 3ተኛ መደብ በወንድ ነጠላ ቁጥር በኀላፊ ጊዜ
የሚነገረው ቃል በመኾኑና ይህ አንዱ አንቀጽ /ግስ/ በዐሥሩ መራሕያን9 እስከ ሰማኒያ
ተጠቃሺ መደብ10 ድረስ መርባቱና መዘርዘሩ ሲታይ ግስ በትርጕም ደረጃ የማይረጋ/
የሚገሰግስ ኾኖ የቋንቋዉ የብዙ ዐይነት ቃላት መፈልፈያ እና መራቢያ ማለት ነው ብሎ
የምሁራኑን ገለጻ ማጠቃለል ይቻላል፡፡

7
ዘመድ ዘር--ግሱን መስሎ የሚወጣ ስም፣ ምሳሌ--ቀተለ ብሎ ቀትል ይላል፡፡

8
አርእስት--ሥረ ነገር፣ ምንጭ ማለት ሲሆን ምሳሌ ቀተለ ብሎ ቀቲል ቀቲሎት ይላል፡፡
9
የአንድ ዐረፍተ ነገር ባለቤት ኾነው የሚያገለገሉ ዐሥሩ ተውላጠ ስሞች/ የስም ምትኮች (ታየ፣ 1889፣ 21)

10
ሰማኒያ ተጠቃሺ መደብ የተባለው እያንዳንዱ ግስ በዐሥሩ መራሕያን ባለቤትነት ከራሱ ውጭ ያሉትን ዘጠኙን
መራሕያንን በተጠቃሺነት ወይም በተሳቢነት በመጠቀም እንደ አእመረ የሚረባበት መንገድ ነው ( አፈወርቅ፣
1988፣ 271) ፡፡

17
.

በግእዝ ቋንቋ መዝገበ ቃላት አዘጋጆች ዘንድ ለቃላት ትርጕም ለመስጠት መጀመሪያ
የሚጠቀሰው ነጠላ ግስ መኾኑ እና በየቅኔ ጉባኤ ቤቱም ከስሙ ጀምሮ ግስ ማውረድ
የሚባለውና ግሱ ሲወርድም መነሻዉን ነጠላ ግስ በማድረግ ርባታዉን ማስከተሉ ግስ
የቃላት መራቢያ እና መፈልፈያ ነው የሚለውን ሐሳብ የሚያጠናክር ነው፡፡

ነገር ግን ግስ የሚለው ቃል የሚጻፈው በ“ንጉሡ ሠ” ነው በ“እሳቱ “ሰ” በሚለው ላይ


በሊቃውንቱ ዘንድ ወጥ የኾነ አቋም የለም፡፡ ታየ “ንጉሡ ሠ”ን ሲጠቀም ኪዳነ ወልድን
ጨምሮ ሌሎች ምሁራን ደግሞ በ“እሳቱ ሰ” ነው የሚጽፉት፡፡ ነገር ግን ጌሠ--ገሠገሠ
ከሚለው ግስ ይልቅ ገሰ/ ገሰሰ--ገሰሰ፣ አረባ ከሚለው ግስ የሚወጣው ዘመድ ዘር (ግስ) ከላይ
የተገለጸውን የግስ ትርጕምና ባሕሪ ይበልጥ ገላጪ በመኾኑ ተቀባይነት ያለው በ“እሳቱ ሰ”
የተጻፈው ስያሜዉ ነው፡፡

የግስ አርእስትን /የግስ አለቆች እና ሠራዊትን አከፋፈል በተመለከተም በምሁራኑ ዘንድ


ተመሳሳዪ አመዳደብ የለም፡፡ ለምሳሌ ታየ (1889፣ 6) የነጠላ ግስ ዋና ዋናዎቹን በስምንት
አርእስት በአርእስቱ ሥር የሚመደቡትን ግሶች ደግሞ ኀምሳ ሠራዊት በማድረግ
የመደባቸው ሲኾን ኪዳነ ወልድ (1948፣ 61፣ 63) አርእስቱ እንደ ፊደላቱ ሰባት ኾነው
ሠራዊት ግን ለቀተለ እንጅ ለሌሎቹ አርእስተ ግስ ጭፍራ እንጅ ሠራዊት የላቸውም
በማለት ነው የሌሎችን ሐሳብ የሚሞግተው፡፡ ይህም ራሱን ችሎ የሚተነተን በመኾኑ በዚህ
ጽሑፍ ማብራሪያ የሚሰጥበትና አቋም የሚያዝበት አይደለም፡፡ እንዲሁም ነጠላ ግሶች
በዋናነት ‘አ’፣ ‘አስ’፣ እና ‘ተ’ የተባሉትን ቅድመ ቅጥያዎች በመጨመር የሚረቡበት እና
የሚመደቡበት መንገድም አለ፡፡ ይህም ከዚህ ቀጥሎ የሚብራረው ነው፡፡

ለ. አዕማድ

አዕማድ --ዐመደ--ቆመ፣ ቀጥ አለ የሚል ትርጕም ካለው ግስ የተገኘ የዐምድ ብዙ ቁጥር


ሲኾን የግስ ነገዶች/ ፀዋትወ ግስ የሚባሉት አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ፣ ተደራራጊ እና
አደራራጊ ግሶች መጠሪያ ስም ነው (ኪዳነወልድ፣ 1948፣ 697)፡፡

መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ደግሞ እነዚህ የግስ ነገዶች ለግስ ርባታ መነሻ፣ መቋቋሚያ
በመኾናቸው አዕማድ ወይም ምሰሶዎች የሚል ስያሜ እንደተሰጣቸው ይገልጻል (1948፣
79) ፡፡

18
.

የአዕማድ ግሶችን ቁጥር በተመለከተ ታየ ገብረ ማርያምን ጨምሮ በብዙ የሀገር ውስጥ
ሊቃውንት የተለመደው አምስት እንደኾኑ ሲኾን ነገር ግን በላይ (2009፣ 101)
በተለመዱት አምስት አዕማድ ውስጥ ተዳራጊዉ--ተደራራጊ፣ አዳራጊዉ--አደራራጊ ኾኖ
መቀመጡ ተገቢ እንዳልኾነ በመግለጽ እንደ አማርኛ ቋንቋ ደራራጊ፣ ተደራራጊ እና
አደራራጊ የተባሉትን ሦስት ዐምዶችን በመጨመር የግእዝ አዕማድ ወደ ስምንት ከፍ ሊሉ
እንደሚችሉ በጥናቱ እንዳረጋገጠ ያብራራል ፡፡ በእነዚህ ሦስት ተጨማሪ አዕማድ ውስጥ
በአድራጊና በደራራጊ፤በአዳራጊና በአደራራጊ፤ በተዳራጊና በተደራራጊ ግሶች ውስጥ
የድርጊቱ ፈጻሚ (ባለቤት) ተመሳሳዪ ቢኾንም ነገር ግን በድርጊቱ መደጋገም እና
አለመደጋገም ላይ ልዩነት ስለሚያሳይ ግኝቱ ተገቢነት ያለው ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ በአምስቱ አዕማድ ውስጥ አቅተለ የአድራጊ አስደራጊን የሚመለከትና
የተደራጊዉ አስደራጊ የሌለ በመኾኑ ለተደራጊዉ አስደራጊ አስተቅተለን በመጨመር
አዕማድን በስድስት የሚከፍለው አቤሴሎም (2009፣104) ነው፡፡ በኹለቱም ምሁራን ዘንድ
የተጨመሩት አዕማድ ከሚሰጡት የተለየ ትርጕም አንጻር ሐሳቡ ተቀባይነት ያለው
በመኾኑ የግእዝ አዕማድ እስከ ዘጠኝ ሊደርሱ እንደሚችሉ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ነገር ግን ኹሉም የግሶች አርእስት በተጠቀሱት አዕማድ ቁጥር ልክ ይረባሉ ማለት


አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ በግስ አርእስቱ መነሻ ምክንያት በአንድ ዐይነት ንባብ ኹለት
አዕማድን ደርበው የሚይዙ አሉ፡፡ ለምሳሌ በባረከ ቤት ተባረከ ብሎ በተደራጊና
በተደራራጊ፤ በማህረከ ቤትምተማህረከ ብሎ በተደራጊና በተደራራጊ ይፈታል፡፡ ይህም
ነጠላ ግሱ መነሻዉ ራብዕ ፊደል በመኾኑ ነው ተደራጊው ከተደራራጊው ጋር የተደረበው፡፡
እንዲሁም መጽአን በመሰለ አጓጕል ግስ11 ባንድ ጊዜ በማድርግና በማስደረግ ልማድ
ይፈታል፡፡ ምሳሌ አምጽአ ብሎ አመጣ እና አስመጣ ተብሎ ይፈታል፡፡

ሐ. ዘር

እንደ ኪዳነ ወልድ (1948፣ 50) አገላለጽ ዘር ማለት ነጠላ ግስን ከነርባው የሚያስገኝ
በሦስት ፊደል የተዋቀረ ቃል ሲኾን መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ የተባለውን መዝገበ ቃላቱን
ሲያዘጋጅም ዘሩን/ አርእስቱን በማስቀደም ግሱን ከነርባተዉ ማስከተሉ ከዚህ ትርጕም
በመነሣት እንደኾነ አብራርቷል፡፡ በታየ (1889፣ 4) መጽሐፈ ሰዋስው ደግሞ አንቀጽ

11
አጓጕል ግስ--የተለየ ገባሪም ኾነ ተሳቢ የሌላው አድራጊዉም ተደራጊዉም እሱ ራሱ የኾነ ግስ ( ኪዳነ ወልድ፣
1948፣ 65) ፡፡

19
.

የሌላው ኹሉ ዘር ተብሎ እንደሚጠራ እና በልዩ ልዩ ርባታ የሚረባ፤ የግስ ኹሉ ሥር


ወይም እናት እንደኾነ ነው የተገለጸው፡፡ ይህም ማለት የቀተለ አስገኚ ቀቲል/ ቀቲሎት፣
የቀደሰ-ቀድሶ/ ቀድሶት፣ የባረከ-ባርኮ/ባርኮት መኾኑን ያሳያል፡፡ በኹለቱም ምሁራን
የቀረበው ሐሳብ ተደጋጋፊነት ያለው ነው፡፡

በታየ መጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያንን ለማሳየት የተገለጹት እንደ ዘመድ ዘር፣ ባዕድ
ዘር12፤ ቅጽል13 እና የመሳሰሉት የቃል ክፍሎች በዘር መካተታቸው አስገኘዉ አርእስት
ከኾነው ነጠላ ግስ በርባታ መገኘታቸውን የሚያመላክት ነው፡፡ ምክንያቱም ታየ
በአራተኛዉ የተመኵሳይያን ምድብ ውስጥ የንባብ አንድነት የነገር ልዩነት በማለት
የመደበው አንዱ ዘር ሲኾን በምሳሌ የተጠቀሱት ደግሞ ቅጽል፣ ዘመድ ዘር እና ባዕድ ዘር
በመኾናቸው ነው ፡፡

መ. ነባር

ነባር በታየ (1889፣ 4) እርባ [ርባ] የሌለው በቁም ቀሪ በማለት ትርጕም ሲሰጠው በኪዳነ
ወልድ (1948፣ 5) ደግሞ ዘርነት የሌላው፣ ከዘር የማይገኝ፣ የማይለወጥ ስም ኾኖ
በውስጡም ነባር የመሰለ አንቀጽና አገባብ የሚወጣበት እንደኾነ ነው የተገጸው፡፡ ከነባር
የሚገኘው አንቀጽ ነባር የሚመስል መባሉ ከዘር የሚገኘው አንቀጽ በኀላፊ፣ በትንቢት፣
በዘንድና በትእዛዝ እና በዝርዝር ርባታ ሲረባ ነባር አንቀጹ ግን በኀላፊ ብቻ በዐሥሩ
መደብ/ መራሕያን በመዘርዘሩ (ደስታ፣ 1962፣ 8) የርባታዉን ውሱንነት ለመግለጽ እንጅ
ሙሉ ለሙሉ ርባታ የለውም ለማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ከተጸውዖ ስሞች ውጭ
የማይረባ ነባር ስም እንደሌለ እና ብዙ ነባር ስሞችም ለምሳሌ ሰብእ ብሎ ተሰብአ፣
ደብተራ ብሎ ተደብተረ በማለት አንቀጽ ሊወጣለት እንደሚችል ኪዳነ ወልድ (1948፣ 52)
ያብራራል፡፡

ሠ. አገባብ

አገባብ በተለያዩ ሊቃውንት በተለያየ መንገድ የተገለጸ ሲኾን ኪዳነ ወልድ (1948 86) “---
የብትን ቃል ኹሉ መሰብሰቢያና ማስማሚያ፤ የቋንቋ ቅመም፤ የንባብ ማጣፈጫ፤የምስጢር

ባዕድ ዘር--ከግሱ በሌለ ባዕድ ፊደል ዘሩ ሲነሣ፡፡ ለምሳሌ ነበረ ካለው ግስ መንበር የሚል ዘር ሲወጣ፡፡
12
13
ቅጽል-- የአንድን ነገር ምንነት ማለትም የነገሩን መጠን፣ ቀለም፣ ግብር፣ ዐይነት፣ ወዘተርፈ በተጨማሪነት
የሚገልጽ ቃልን የሚያመለክት ነው፡፡

20
.

መግለጫ” በማለት ሲገልጸው፤ ታየ (1889፣ 5) ደግሞ “---የመጽሐፍን አካኼድ፣ የቅኔን


መንገድ፣ የቁጥርን እርባታ (ርባታ)፣የቋንቋዉን ጠባይና ልማድ፣ የነገርን ምርምርና ሐተታ
ኹሉ የሚያስታውቅ” ነው በማለት ይተረጕመዋል፡፡ ይህም ማለት የአንድ ቋንቋ ሥርዐተ
ጽሕፈት ተጠብቆ፤ ቃላቱ በተገቢው መንገድ ገብተውና ተሰድረው ቋንቋዉ የተሟላ
ትርጕም እንዲሰጥ የማድረጊያ መንገድ መኾኑን ያስገነዝባል፡፡ አገባብ የተለያዩ ክፍሎች
ያሉት ሲኾን ዋና ዋናዎቹ ዐቢይ፣ ደቂቅ እና ንኡስ አገባቦች14 ናቸው፡፡ በመጽሐፈ
ሰዋስው ተመኵሳይያንን ለማሳያነት የተገለጹት በዐቢይ አገባብ ሥር የሚመደቡት እመ
እና እም የተባሉት የአገባብ ዐይነቶች ናቸው፡፡

እም የአንቀጽ ማሰሪያነትን የማያስቀርና ከስም ቀድሞ በመግባት አንድን ዐረፍተ ነገር


ትርጕም እንዲኖረው የሚያደርግ በመኾኑ ከዐቢይ አገባብነቱ በተጨማሪ በደቂቅ አገባብ
ሥርም ሊመደብ ይችላል፡፡ ለምሳሌ “ወኀለፋ ፍጠነ እምኀበ መቃብር… / …ከመቃብሩ
ፈጥነው ኼዱ” (ማቴ. 28÷8) ብሎ ደቂቅ አገባብን፤ “…እምትደቅ አሐቲ ቃል… /…
አንዲት ቃል ከምትወድቅ…” (ሉቃ. 16÷17) በሚለው ሐረግ ውስጥ ከትእዛዝ አንቀጽ ላይ
በመውደቅ ማሰሪያነትን በማስቀረቱ በዐቢይ አገባብ ውስጥ ይመደባል፡፡

2.1.3. ተመኵሳይያንን ለማዋቀር ሥራ ላይ የዋሉ መሠረተ ሐሳቦች

ሀ. የቃላት ሥርዐተ ንባብ

የቃላት ሥርዐተ ንባብ ማለት ከቃሉ መረዳት እንደሚቻለው ቃላት አንዴትና በምን
ዐይነት መንገድ/ ስልት ሊነበቡ እንደሚችሉ የሚያሳይ ሕገ ንባብ ነው በማለት መተርጐም
ይቻላል፡፡ በብዙ የሀገር ውስጥ ምሁራን ዘንድ የግእዝ ሥርዐተ ንባብ ሲባል የሚታወሰው
ተነሺ፣ ተጣዪ፣ ሰያፍና ወዳቂ የተባሉት አራቱ የንባብ ዐይነቶች ናቸው፡፡ በቅኔ ቤትም
ዜማ ልክ የሚሰፈረውና የሚለከው በነዚሁ የንባብ ዐይነቶች መነሻነት ነው፡፡ ነገር ግን
ከእነዚህ የንባብ ዐይነቶች ተጣዪ ወይም ወዳቂንና ተነሺን በመያዝ ማጥበቅና ማላላት፤
መዋጥና መቁጠር፤ ማናበብና አለማናበብ የሚሉትን በመጨመር የግእዝ የንባብ ዐይነቶች

14
ዐቢይ አገባብ በማሰሪያ አንቀጽ ላይ እየወደቀ ማሰሪያነትን የሚያስቀር ፤ ደቂቅ አገባብ በዐቢይ አናቅጽ እየገባ
ማሰሪያነትን የማያስቀር ቢኾንም በሰዋስው ላይ እየወደቀ ማድረጊያ መነሻ፣ መገስገሻ፣ መድረሻ፣ አቀባዪ፣ ተሳቢ
ወዘተ..በመኾን የሚያገለግል ፤ ንኡስ አገባብ ደገሞ በነባር፣ በዘማቺ፣ በዐቢይ፣ በንኡስ፣ በአናቅጽ ኹሉ እየገባ
ማሰሪያነትን የማያስለቅቅ ጥያቄ እና አንክሮ፣ ደስታ እና ሐዘን፣ ልመና እና ምኞት፣ አሉታ እና አፍራሺ፣ እሽታ
እና እንቢታ ሌላም ይኸን የመሳሰሉትን የሚያሳይ ፊደል ወይም ቃል ነው፡፡

21
.

ስምንት መኾናቸውን በመግለጽ ያብራሩ ምሁራንም አሉ (አፈወርቅ፣ 1988፣ 62፤ ደሴ፣


2007፣ 275 )፡፡

ለይኩን (1998፣ 353) ደግሞ ተነሺ፣ ወዳቂ፣ ጠባቂ፣ የሚላላ እና ተናባቢ በማለት በዐምስት
ይከፍላቸዋል፡፡ ባጠቃላይ በኹሉም ምሁራን ዘንድ የተጠቀሱት የንባብ ዐይነቶች በቋንቋዉ
ሥርዐተ ንባብ ውስጥ መኖራቸው እሙን እሰከኾነ ድረስ ኹሉም የግእዝ ቋንቋ ሥርዐተ
ንባብ ክፍሎች ናቸው በማለት መደምደም ይቻላል፡፡

እነዚህን የአነባብ ዐይነቶች በተለይ ጠብቆና ላልቶ እንዲሁም ውጦና ቆጥሮ የሚነበበውን
ፊደል ሊያስለይ የሚችል ምልክት በቋንቋዉ ሥርዐተ ጽሕፈት ውስጥ አለመኖር ቋንቋዉን
በቀላሉ ለመልመድ አስቸጋሪ ከመኾኑም በላይ ሥርዐተ ንባቡን ጠብቆ ማንበብ አለመቻል
ደግሞ የሚያስከትለው የትርጕምና የምስጢር መፋለስ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ ላይ ኹሉንም
መዘርዘር ባይቻልም በተወሰነ ደረጃ ግን ታየ በመጽሐፉ የጠቀሳቸው ጥብቀት፣ ተነሺና
ወዳቂ፤ ሰያፍና ተጣዪ እንደሚከተለው ይብራራሉ፡፡

ጥብቀት (gemination)

ጥብቀት ማለት የተነባቢን ድምፅን የቆይታ መጠን የሚያመለክት ሲኾን ይህም በኹሉም
የሴም ቋንቋዎች እንደሚንጸባረቅ እና የፊደላትን ድምፅ ከማለያየት በተጨማሪ ሥነ
ምዕላዳዊ ለውጥ በማምጣት በኩል የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደኾነ ምሁራን ይገልጻሉ
(ኡሌንዶርፍ፣ 1951፣ 215፤ ጎልደንበርግ፣ 2013፣ 72)፡፡

የግእዝ ቋንቋ የሥነ ጽሕፈት ዘዴ ቀለማዊ እንደመኾኑ መጠን ተነባቢዉና አናባቢዉ


ሳይለይ በአንድ ምልክት መወከሉ በአጻጻፍ ሥርዐቱ ጊዜና ቦታ ቆጣቢ ቢኾንም ጠብቆ
የሚነበበውን ፊደል ለመለየት የሚያስችል ባለመኾኑ በቋንቋዉ የአጻጻፍ ሥርዐት ውስጥ
እንደ አንድ ችግር የሚጠቀስ ነው (ላምበዲን፣ 1978፣ መግቢያ፤ ኡሌንዶርፍ፣ 1951፣
215)፡፡

ቀደም ሲል አንዳንድ የሀገር ውስጥ ምሁራን (ለምሳሌ አባ ጎርጎሬዎስ የሉደልፍ አስተማሪ)


የጭረት ምልክት የማጥበቂያ ምልክት ይጠቀሙ እንደነበርና ነገር ግን በዋናነት ሥራ ላይ
ማዋል የተለመደው በአውሮፓውያን ተመራማሪዎች ነው በማለት ኡሌንዶርፍ (1951፣
215) ያብራራል ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ለሚጠብቀው ፊደል ‘ጥ’ ለሚላለው ደግሞ ‘ላ’
የሚል ምልክት ኪዳነ ወልድ (1948፣ 225—226) ከግሱ በፊት ሲያመለክት፤ አፈ ወርቅ

22
.

(1988፣ 219) ደግሞ ከሚጠብቀው ፊደል በላይ ኹለት ነጥብ በማስቀመጥ ጠብቆ
የሚነበበውን ፊደል ለመለየት ጥረት ሲያደርግ ይታያል፡፡ ቢኾንም ግን ለኹሉም ጠብቀው
ለሚነበቡ ፊደላት ምልክቱ ካለመቀመጡም በላይ ምልክቶቹ የሚቀመጡበት ቦታ ወጥነት
ያለው አይደለም፡፡ ከዚህም የምንረዳው ቋንቋዉ አሁንም ከዚህ ዐይነት ችግር ያልወጣ
መኾኑን ው፡፡

በግእዝ ቋንቋ ብዙ ጊዜ ጥብቀት የሚከሠትው በቀደሰ ቤት- በቀዳማይ፣ በካልአይ፣ በዘንድና


በትእዛዝ አንቀጽ እንዲሁም በአርእስቶች፣ በውስጠ ዘዎቹ፣ በሣልስ ውስጠ ዘዎቹ፣
በመድበሎች እና በመስም ቅጽሎች፤ ‘ሀ’ እና ‘አ’ በመካከል የሌሉበት ግስ ኹሉ ካልኣይ
አንቀጽ ቅድመ መድረሻ ፊደሉ፤ በ‘ወ’ እና በ‘የ’ የሚጨርሱ ግሶች በካልኣይ አንቀጽ
ጎርደው ሲጨርሱ የመጨረሻዉ ፊደል፤ በ‘ከ’ እና በ‘ቀ’ በሚጨርሱ ግሶች የድርጊቱ ባለቤት
አንደኛ መደብ ነጠላ ቁጥር፣ ኹለተኛ መደብ የሴትና የወንድ ነጠላ እና በዙ ቁጥር
በሚኾንበት ጊዜ እና በአንደኛ መደብ ብዙ ቁጥር በ‘ነ’ የሚጨርስ ግስ መደብ አመላካቹ
ፊደል ሲዋጥ እና የመጨረሻዎቹ ኹለት ፊደላት ተመሳሳዪ የኾኑበት ግስ ከሦስት ወደ
ኹለት ፊደል በሚወርድበት ጊዜ መካከለኛው ፊደል የመጨረሻዉን ፊደል ሲውጥ ነው፡፡
ታየ በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያንን ለማሳየት የተጠቀመው በቀደሰ ቤት መሀል ፊደሉ
ጠብቆ የሚነበበውንና ከዚሁ አንቀጽ የሚወጡትን የዘር ዐይነቶች ነው፡፡

ተነሺና ወዳቂ

ተነሺ ማለት የመጨረሻ ፊደሉ ከሳድስ ፊደል ውጭ ከግእዝ እስከ ሳብዕ ባሉት ፊደሎች
የሚጨርስ ኾኖ በከፍተኛ ድምፅ የሚነገር ወይም የሚነበብ ቃል ነው (ደሴ፣ 2007፣ 275)፡፡
ይህም አብዛኛዎቹ ግሶች የሚነበቡበት ሥርዐት ነው፡፡ ለምሳሌ በዐሥሩ መራሕያን
ከሚዘረዝሩት ግሶች ውስጥ ቀተልኩ፣ ቀተልነ፣ ቀተልከ፣ ቀተልክሙ፣ቀተልኪ፣ ቀተለ፣ ቀተሉ፣
ቀተላ (ብዙ ሴቶች) በከፍተኛ ድምፅ በተነሺነት ሲነበቡ ቀተልክን ከፍ ባለ ድምፅ
ባለመነበቡ፤ ቀተለት ደግሞ በሳድስ ፊደል በመጨረሱ ተነሺ አይባሉም፡፡ እንዲሁም
ዝንቱሰ፣ ዝንቱመ በማለት ‘ሰ’ እና ‘መ’ ትራስ የኾኑበት ወዳቂ ቃልም በተነሺነት ይነበባል
(አፈወርቅ፣ 1988፣ 63)፡፡

ወዳቂ ንባብ ደግሞ በሰባቱም ፊደሎች የሚጨርስ ኾኖ ቃሉ ሲነበብ ከተነሺ በተቃራኒ


ኀይል በሌለው ድምፅ የመጨረሻ ፊደሉን ረገጥ በመድረግ ነው፡፡ በሳድስ ግን ‘ዝ’ ትራስ

23
.

ከኾነበት ቃል ውጭ በሌላ ሲጨርስ አይገኝም (ዐበይ፤2010፣ 45) ፡፡ በሳድስ ፊደል


ሲጨርስ ከተጣዪ የሚለየው የመጨረሻ ፊደሉን ረገጥ አድርጎ በመነበቡ ነው፡፡

ጣይና ሰያፍ

ኹለቱም የሥርዐተ ንባብ ዐይነቶች የሚጨርሱት በሳድስ ፊደል ሲኾን ተጣዪ የመጨረሻ
ፊደሉን ያዝ ሳያደርግ ኀይል በሌላው ድምፅ የሚነበብ ሲኾን ሰያፍ ደግሞ ተነሺ
በተነበበት አግባብ በከፍተኛ ድምፅ የሚነበብ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ግስንና ከግስ ርባታ የሚገኙ
ዘሮችን/ ስም/ በተመለከተ ሰያፍ ወይስ ተጣዪ ነው የሚለውን ለመለየት ባያዳግትም ነገር
ግን ከነባር ስሞች ጋር በተያያዘ በአነባበብ ሥርዐቱ ላይ በሊቃውንቱ ዘንድ ስምምነት
የለም፡፡

ለ. የአንድ ቃል የተለያየ ትርጓሜ መኖር

ትርጓሜ ተርጐመ--ተረጐመ ከሚል ግስ የወጣ ጥሬ ዘር ሲኾን መተርጐም፣ አተረጓጐም፣


ትርጐማ፣ አመላለስ፣ ምስጢር አገላለጥ ወዘተርፈ የሚል ፍች አለው (ኪዳነ ወልድ፣1948፣
903)፡፡ ብዙዉን ጊዜ ትርጓሜ አንድን ቃል ከቋንቋ ወደ ቋንቋ ለመመለስ ሲያገለግል
በግእዙ መጽሐፍ ቅዱስ በአብዛኛዉ የሚገኘው ፍካሬ ደግሞ በአንድ ቋንቋ ውስጥ ኅቡእ
የኾነን ነገር ለማብራራት እንደሚውል ነው ምክረ ሥላሴ (2000) የገለጸው፡፡ ነገር ግን
ለቃሉ ከተሰጠው ትርጕም አንጻር ትርጓሜ ፍካሬ የሚለውን የግእዝ ቃልንም የሚተካ
በመኾኑ በአንድ ቋንቋ ውስጥም ቢኾን ትርጓሜ ግልጽ ያልኾነን ነገር ለማብራራትም
እንደሚጠቅም ነው የሚያሳየው፡፡

ይህም በአንድ ቋንቋ ውስጥ አሻሚ ሐሳብ/ ቃል ወይም ዐረፍተ ነገር / በሚኖርበት ወይም
አንዱ ሐሳብ ከሌላው ሐሳብ በሚጋጭበት ጊዜ ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግና ተቃርነኖዉን
ለማስታረቅ ነው፡፡ በዋናነት ለዚህ በማሳያነት የሚጠቀሰው በኢኦተቤ የመጻሕፍት ትርጓሜ
ትምህርት ቤት የሚሰጠው የአንድምታ ትርጓሜ ስልት ነው፡፡ አንድ ተርጓሚ ለአንድ ገጸ
ንባብ በአንድም ትርጓሜ ማብራሪያ የሚሰጠው አማራጪ ትርጕሞች በሚኖሩበት ጊዜ
እንደኾነና ይህም ከገጸ ንባቡ ጀርባ ያለውን ምስጢር ይበልጥ ግልጽ እንደሚያደርገው
መርሻ (2003፣ 36) አብራርቷል፡፡ ከትርጕም ባሕርያቱ ውስጥ ደግሞ ይበልጥ ገዢ እና
ተስማሚ የኾነ ተዛማጂ ትርጕም [association of meanings] መስጠትና ከኹኔታዎች
በመነሣት ትርጕም ማስፋት [extention by inference] የሚሉት ይገኙበታል (ዝኒ

24
.

ከማሁ)፡፡ ይህም በተመሳሳዪ ለአንድ ቃል የተለያየ ትርጕም እንዲኖረው ዕድል ይሰጣል


ማለት ነው፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ለአንድ ቃል ወይም ዘር ካንድ በላይ ትርጕም አለው
(ምክረ ሥላሴ፣ 2000፣ 175) የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡

2.1.4. ተዛማጂ ጽሑፎች

ስለ ተመኵሳይያን ቃላት በጠቅላለዉ በተለይ ደግሞ በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን


ስለተገለጹበት አግባብ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂ ባደረገው ቅኝት ብዙም የተሠሩ ሥራዎች
የሉም፡፡ አልፎ አልፎ የሚገኙት ሥራዎችም ቢኾኑ ከሌሎች ርእሰ ጉዳዮች ጋር ተዳብለው
የቀረቡ እና በዝርዝር የቀረቡ አይደሉም ፡፡ እነዚህም ሥራዎች ወደ ኋላ በዝርዝር
የሚዳሰሱ ናቸው ፡፡ ይልቁንስ ብዙ ምሁራን በተለይ የውጭ ሀገር አጥኚዎች በትኩረት
የጻፉትና ያብራሩት በተለምዶ ሞኵሼ ተብለው ስለሚጠሩት ፊደላት እና አጠቃቀማቸዉ
ነው፡፡ ታየ የቃላትን ሞኵሼነት ለማሳየት በዋናነት መሠረት ያደረገው የእነዚህን ፊደላት
አሁን ላይ ያለውን የድምፅ መመሳሰል በመኾኑ ፊደላቱ በሥርዐተ ጽሕፈት ያላቸዉን
አጠቃቀም በተመለከተ የተደረጉ ጥናቶችንና መጣጥፎችን በመጠኑም ቢኾን በቅድሚያ
መዳሰሱ ለርእሰ ጉዳዩ አስፈላጊ ነው፡፡

አሁን ላይ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ የግእዝ ፊደሎች በጊዜ ኺደት ድምፃቸዉ
ቢመሳሰልም እንደ ቅርጻቸዉ ድምፃቸዉም የተለያየ እንደነበር በምሁራኑ ዘንድ ሲያወዛግብ
አይታይም፡፡ ለዚህ ሐሳብ ቅቡልነት ደግሞ በብዙ ምሁራን ተደጋግሞ እንደተጠቀሰው
ፊደላቱ የሚፈጠሩበት ቦታና ኹኔታ የተለያየ መኾኑ (አቤሴሎም፣ 2009፣ 30-31፣
ጎልደንበርግ፣ 2013፣ 67) እና በሌሎች የሴም ቋንቋዎች ድምፃቸዉ ተለይቶ የሚታወቅ
መኾኑ ነው፡፡ ለምሳሌ ኡሌንዶርፍ (1995፣ 41) ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ አ እና ዐ በዐረብኛ ቋንቋ
እንደሚገኙ እንዲሁም ከ ‘ኀ’ ውጭ ያሉት አራቱ የጒረሮ ድምፆች በትግረኛ እና በትግረ
ቋንቋዎች እንደሚገኙ ገልጧል፡፡

በሥነ ልሳን ጥናት መሠረትም ለአንድ ድምፅ የሚሰጠው ውክልና አንድ በመኾኑ (ሀበተ
ማርያም፣ 1986፣ 324) ለአንድ ድምፅ ኹለትና ከዚያ በላይ ውክልና ሊኖር የሚችልበት
አግባብ የለም፡፡ በሥነ ልሳን ተመራማሪዎች ዘንድም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው ለሚመስሉ
ፊደላት ለእያንዳንዳቸው ልዩ ልዩ የመተርጐሚያ ምልክት መስጠት የተለመደ ነው
(ኡሌንዶርፍ፣ 1995፤ 33-34፤ ሌስሎው፣ 1991፣ መግቢያ) ፡፡

25
.

ከዚህ በተጨማሪም የግእዝ ፊደላት የራሳቸዉ ትርጕምና ሥዕላዊ መግለጫ ያላቸው


በመኾኑ በዘፈቀደ ሲጻፉ የትርጕም ለውጥና የምስጢር መፋለስ ሊያመጡ እንደሚችሉ
ኪዳነ ወልድን ዋቢ በማድረግ ደሴ (2007፤ 7) ያብራራል፡፡ ለምሳሌ አኀዛዊ
ትርጕማቸዉን/ ውክልናቸዉን በተመለከተ ፊደላቱ የየራሳቸው ቁጥር ስላላቸው አዳም
(የመጀመሪያዉ ሰው) የሚለው ስም ቁጥሩ 144 ሲኾን በተመሳሳዪ ኢየሱስ የሚለው ስምም
የፊደላቱ ቁጥር ሲደመር 144 እንደሚኾንና ይህም ኢየሱስ ዳግማይ አዳም መባሉ
ከአኀዛዊ ትርጓሜዉ በመነሣት እንደኾነ አስረስ የኔሰው ያስራዳል (1952፣ 163)፡፡ ይህም
አዳም የሚለው ቃል በ“ዐይኑ ዐ” ወይም ኢየሱስ የሚለው ስም በ“እሳቱ ሰ” ምትክ በ“ንጉሡ
ሠ” ቢጻፍ ኢየሱስ ዳግማይ አዳም የሚለው ምስጢራዊ ትርጕም ተፋለሰ እንደማለት
ነው፡፡ ነግ ግን እነዚህ ስሞች የግእዝ ቃላት መኾናቸው ባልተረጋገጠበት ኹኔታ ስሞቹ
ሲወጡ ምስጢራዊ ትርጕም እንዲይዙ ተደርገው ነው መባሉ ጥያቄ የሚያስነሣ በመኾኑ
ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው ነው የሚኾነው፡፡

ነገር ግን ግእዝ ከሚለው የቋንቋዉ ስያሜ ጀምሮ በጕረሮ እና በጥርስ የሚነገሩ ፊደላት
ወጥ በኾነ መንገድ ሲጻፉ አይታይም፡፡ ችገሩ በ13ኛዉ መቶ ክፍለ ዘመን ከተጻፉ የብራና
መጻሕፍት ጀምሮ እየባሰ እንደመጣና በተለይ ትግረኛና ትግረ ከሚናገሩ ይልቅ አማርኛ
ተናጋሪ በኾኑ ጸሓፊዎች በተጻፉ መጻሕፍት ላይ በስፋት እንደሚንጸባረቅ ኡሌንዶርፍ
(1995፣ 35-36) ይገልጻል፡፡ የተወሰኑ በጕረሮ የሚፈጠሩ ፊደላት ድምፃቸዉ በትግረኛ እና
በትግረ ቋንቋዎች እስካሁን ድረስ ተጠብቆ መቆየቱ የዚህ ማሳያ ሊኾን ይችላል፡፡ በግእዝ
ቋንቋ ውስጥ ለድምፆቹ መጥፋት የአማርኛ ቋንቋ ተፅእኖ ነው የሚለው የብዙኃኑ ምሁራን
ሐሳብም ከዚሁ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው፡፡ይህ የፊደላት አጠቃቀም ችግር የታየ ገብረ
ማርያም መጽሐፈ ሰዋስውን ጨምሮ በዘመናዊ የኅትመት ውጤቶች ላይም በስፋት
ይንጸባረቃል፡፡

በግእዝ ቋንቋ ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ምሁራንም ትክክለኛዉን የፊደላት አጠቃቀም


ለመለየት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ጥረት ሲያደርጉ ይሰተዋላል፡፡ ከውጭ ሀገር
ምሁራን ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያክል፦ በመጀመሪያም የሌስሎው ሥራዎችን
ስንመለከት ሌሰሎው(1991፣ መግቢያ፤ 1972፣ መግቢያ) እንግሊዝኛ- አማርኛ መዝገበ
ቃላትን (English-Amharic Context Dictionary) እና ንጽጽራዊ የግእዝ መዝገበ ቃላትን
(Comparative Dictionary Of Geez) በሚያዘጋጅበት ጊዜ ተገቢዉን ፊደል በተገቢዉ ቦታ

26
.

ለመጠቀም “principle of etymology for the standardization of the orthography”


የተባለውን መርሕ ተጠቅሟል፡፡ ይህም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት
በሌሎች የሴም ቋንቋ ቤተሰቦች የሚገኙ እንደመኾኑ መጠን የግእዝን አጻጻፍ ሥርዐት
ከእነዚህ ቅርበት ካላችው ቋንቋዎች የአጻጻፍ ሥርዐት ጋር በማነጻጸር ትክክለኛዉን አጻጻፍ
ለመከተል ጥረት የሚደረግበት መርሕ ነው፡፡ በዚህ መሠረትም “አልፋዉ አ”ን እና “ዐይኑ
ዐ”ን ለይቶ ለመጻፍ ከሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ውስጥ በዋናነት ትግረኛ እና ትግረ፤ እነዚህ
ፊደሎችን ጨምሮ ለሌሎች ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደሎች ደግሞ እንደ
ዐረብኛ ያሉ ኹሉንም የሴም ቋንቋዎችን በመጠቀም የአጻጻፍ ችግሩን ማስወገድ
እንደሚቻል ሌስሎው በመዛግብተ ቃላቱ መግቢያ ላይ ገልጧል፡፡

ኡሌንዶርፍም (1955፣ 38፣ 29) በኢትዮጵያ የሴም ቋንቋዎች ላይ ባደረገው የሥነ ድምፅ
ንጽጽራዊ ጥናት [The Semitic Languages of Ethiopia Comparative Phonology] የ‘አ’
እና ‘ዐ’፣ እንዲሁም የ‘ሀ’ እና ‘ሐ’ ልዩነት በትግረኛ እና በትግረ ቋንቋዎች በግልጽ
እንደሚንጸባረቅ ያረጋገጠ ሲኾን ኮምፓራቲቭ ኢቲሞሎጅ (comparative etymology)
ዘዴን በመጠቀም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደሎችን አስተካክሎ መጻፍ
እንደሚቻል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ይህም የሌስሎውን ሐሳብ የሚደግፍ ነው፡፡

ኮውሊም (1967፣ 1) “the Standardization of Amharic Spelling” በተባለው ጥናቱ


ከአማርኛ ቋንቋ የአጻጻፍ ደንቦች ውስጥ ኢቲሞሎጂካል መርሕን መጠቀም ካልተቻለ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው ከሚመስሉ ፊደላት መካከል ተመራጮቹ ‘ሀ’፣ ‘አ’ እና ‘ሰ’
እንደኾኑ አትቷል፡፡ይህም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን ለይቶ ለመጻፍ
ተመራጩ መንገድ በተመሳሳዪ ኮምፓራተቭ ኢቲሞለጂ መኾኑን ያሳያል፡፡

የዲልማንን መዝገበ ቃላት አጻጻፍንም በጽሑፋቸው ውስጥ እንደማመሳከሪያነት


የተጠቀሙም ምሁራን አሉ (ላምብዲን፣ 1978፣ 14፤ ሌስሎው፣ 1991፣ መግቢያ) ፡፡

ከሀገር ውስጥ ምሁራን መካከል ደግሞ የሴም ቋንቋዎችን በማነጻጸሪያነት በመጠቀም


የፊደላትን አጠቃቀም ለማስተካከል ጥረት ከተደረገባቸው ሥራዎች ውስጥ በቀዳሚነት
የሚጠቀሰው የኪዳነ ወልድ (1948) መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ነው፡፡ ኪዳነ
ወልድ ለማነጻጸሪያነት በአብዛኛዉ የተጠቀመው የውጭ ሀገር የሴም ቋንቋዎችን ሲኾኑ
ዋናዎቹ ዐረብኛና ዕብራይስጥ ናቸው፡፡

27
.

ሌላው ደግሞ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት ላይ ከተደረጉ ጥናቶች ውስጥ
የሚጠቀሰው የዙፋን ገብረ ሕይወት “Why the Gee Pharyngeal Sounds Pronounced
as Glottal Sounds” (2018) በሚል ርእስ የቀረበው ጥናት ነው፡፡ በዚህ ጥናትም “ሐመሩ
ሐ” እና “ዐይኑ ዐ” ከ“ሃሌታዉ ሀ” እና ከ“አልፋዉ አ” እንደቅደም ተከተላቸዉ የተለየ ባሕሪ
እና አጠቃቀም ያላቸው ስለመኾኑና ድምፃቸዉም የተመሳሰለው በአማርኛ ቋንቋ ተፅእኖ
ስለመኾኑ ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ ጥናቱም ትንተናዉን መሠረት ያደረገው የግእዝ ቋንቋ
ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች ጋር ያለውን ግንኙነት፣ ዒላማ የተደረጉትን የኹለቱን ፊደላት
ቅርጻዊ ባሕሪ እና ታሪካዊ የጥናት ውክልናን (Linguistic, Pictographic and Historic
Functions) ነው፡፡ ከእነዚህም የመተንተኛ መንገዶች ውስጥ አንደኛዉ ንጽጽራዊ
የመተንተኛ ዘዴ አጥኚዋ የተጠቀመች ስለመኾኑ መረዳት ይቻላል፡፡

ባጠቃላይ ከዚህ በላይ ከቀረበው የዘርፉ ምሁራን ገለጻ መረዳት የሚቻለው ተመሳሳዪ
ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት እንደ ሌሎች የሴም ቋንቋዎች ኹሉ በግእዝ ቋንቋም
ድምፃቸዉ የተለያየ ስለመኾኑ በኹሉም ምሁራን ዘንድ ስምምነት ያለ ስለመኾኑና አሁን
ላይ ድምፃቸዉን መለየት ባይቻልም ነገር ግን በጽሕፈት ደረጃ ታሪካዊ ንጽጽራዊ ዘዴን
በመጠቀም በዘፈቀደ የመጻፍ ችግርን ማስወገድ እንደሚቻል ነው፡፡

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅም ተመኵሳይያን ቃላት በመጽሐፈ ሰዋስው የተገለጹበትን አግባብ


የሚመረምረው የቃላትን አወቃቀር (ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት
የተዋቀሩትን) ቅርበት ካላቸው የተወሰኑ የሴም ቋንቋዎች እና ከሌሎች ምሁራን ጽሑፎች
ጋር በማነጻጸር በመኾኑ የምሁራኑ ገለጻ ከዚህ ርእሰ ጉዳይ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አለው፡፡

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ሌሎች ምሁራን ተመኵሳይያን ቃላትን ያብራሩበትንና


የመደቡበትን አግባብ መከለስ ሲኾን ነገር ግን ከዚህ በፊት ከ1889 ዓ. ም የታየ ገብረ
ማርያም የመጀመሪያ ዕትም በኋላ የተለያዩ ዕትሞች ያሉ በመኾኑ በመጀመሪያዉ ዕትምና
በኋለኞቹ ዕትሞች (ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱት) መካከል ስላለው አንድነትና ልዩነት
በንጽጽር መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ ከመጀመሪያዉ ዕትም በኋላ በ1943 ዓ. ም የታተመ
መጽሐፈ ሰዋስው ስለመኖሩ ስማቸው (2009፣ 129) “ቅኔና ባለቅኔዎች” በሚል ርእስ
ባቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ በዋቢ መጻሕፍት ዝርዝሩ ላይ የጠቀሰ ቢኾንም ነገር ግን በዚህ
ጽሑፍ ዝግጅት ጊዜ ለአዘጋጁ ተደራሺ ባለመኾኑ ለመዳሰስ የተሞከረው ከዚህ በኋላ
የታተሙትን ሦስት ዕትሞች ነው፡፡

28
.

የመጀመሪያዉ በ1958 ዓ.ም በዘመንፈስ ቅዱስ አብርሃ አማካኝነት የታተመው ቅጅ (መሰ2)


ሲኾን የመጽሐፉ አዘጋጅም ታየ ገብረ ማርያም ስለመኾኑ ከመጽሐፉ መግለጫ ላይ
ተመልክቷል፡፡ ቀጥሎ በ1982 ዓ. ም በተስፋ ገብረ ሥላሴ “መጽሔተ አእምሮ” በሚል
ርእስ የታተመው መጽሐፈ ሰዋስው (ከዚህ በኋላ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሰ3 በሚል ነው
የተጻፈው) ሲኾን ሦስተኛዉ ደግሞ በ1992 ዓ. ም በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት
የታተመው ዕትም (ይህ ዕትም ደግሞ ከዚህ በኋላ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ መሰ4 በሚል ነው
የተገለጸው) ነው፡፡ የመጨረሻዎቹ ኹለት ዕትሞች መጽሐፉ ከአባቶች ሰወርድ ሲዋረድ
የመጣ ሰወስወ ግእዝ/ መጽሐፈ ሰወስው ከማለት ባለፈ ስለመጽሐፉ አዘጋጂ ዕውቅና
አይሰጡም፡፡ ነገር ግን የኋለኞቹ ሦስቱም ዕትሞች የመጀመሪያዉ ዕትም ቀጥታ ቅጅዎች
ስለመኾናቸው ማስረጃዉ ተመኵሳይያን ቃላትን ጨምሮ መላዉ ይዘታቸው ተመሳሳዪ
መኾኑ ነው፡፡

ነግር ግን ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን በተመለከተ ግን በእያንዳንዱ


ኅትመት የአጠቃቀም ልዩነት አለ፡፡ ለምሳሌ ጎሰቆለ የሚል ትርጕም ያለውን የግእዝ ግስ
ስንመለከት በመጀመሪያዉ ዕትም እና በመሰ2 (ገጽ 42) ሐስረ በማለት “ሐመሩ ሐ”ን እና
“እሳቱ ሰ”ን፤ በመሰ3 (ገጽ 45) ኀሥረ ብሎ “ብዙኃኑ ኀ” ን እና “ንጉሡ ሠ” ን፤ በመሰ4
(ገጽ 42) ደግሞ ሐሥረ በማለት “ሐመሩ ሐ”ን እና “ንጉሡ ሠ” ን ነው መጻሕፍቱ
የተጠቀሙት፡፡ ይህ አንዱ ማሳያ ሲኾን በተለይ የመጨረሻዎቹ ኹለት ዕትሞች (መሰ3
እና መሰ4) ከመጀመሪያ ኅትመት ጋር በፊደል አጠቃቀም ረገድ ያላቸው ልዩነት ሰፊ
መኾኑን ተመኵሳይያን በሚለው ንኡስ ርእስ ውስጥ ብቻ ያሉትን ልዩነቶች ማየቱ በቂ
ነው፡፡ነገር ግን ይህ የአጻጻፍ ልዩነት ጉዳዩን የበለጠ ውስበስብ ከማድረግ ባለፈ አለቃ ታየ
ተመኵሳይያን ቃላትን የገለጸበት አግባብ ተገቢ መኾን አለመኾኑን አያሳይም፡፡

እንዲሁም አንዱ ከሌላው ኅትመት የፊደል አጠቃቀም ልዩነት እንዳለው ኹሉ በአንዱ


ኅትመትም በግሱ እና ለግሱ ትርጕም በማስረጃነት በተጠቀሰው ዐረፍተ ነገር ውስጥ
በተጠቀሰው ከግሱ በወጣው ቃል መካከልም የፊደል አጠቃቀም ልዩነት አለ፡፡ ይህም
ልዩነት በመጀመሪያዎቹ ኹለት ዕትሞች ጎልቶ የሚታይ ሲኾን አንዳንድ ማሳያዎቹን
እንደሚከተለው እንመልከት፡፡ በመጀመሪያዉ ዕትም እና በመሰ2 ላይ ሐስረ--አፈረ ብሎ
ማስረጃዉ “ምላእ ውስተ ገጾሙ ኀሳረ” ( ገጽ 32) ይላል፡፡ ከዚህ ላይ ግሱ በ “ሐመሩ ሐ”
ሲጻፍ ከግሱ የተገኘው ዘመድ ዘር “ኀሳር” ደግሞ በ “ብዙኃኑ ኀ” ነው የተጻፈው፡፡ በመሰ3

29
.

(ገጽ 44) እና በመሰ4 (ገጽ 41) ደግሞ ቀሠመ--አጣፈጠ ብሎ ማስረጃዉ “ወእመሰ ጼው


ለስሐ በምንት ይቄስምዎ” ብሎ ቀዳማይ አንቀጹን በ “ንጉሡ ሠ” ካልኣይ አንቀጹን ደግሞ
በ “እሳቱ ሰ” የተጻፈ መኾኑን ልብ ይሏል፡፡

ከዚህ ቀጥሎ በርእሰ ጉዳዩ ላይ የሌሎች ምሁራን ሥራዎች የሚዳሰሱ ሲኾን በመጀመሪያም
አፈወርቅ ዘውዴ ሀገረ--መጻሕፍት/ ሰዋስው ግእዝ ወዐማርኛ/ (1988) በሚል ርእስ
ባሳተመው መጽሐፍ ስለተመኵሳይያን ቃላት ከገጽ 31-32 ያሰፈረውን ነው
የምንመለከተው፡፡ አፈወርቅ ለሞኵሼነት ትርጕም ባይሰጠውም የቃላት ሞኵሼነትን
በሦስት መንገዶች በጥብቀት፣ በልህላሄ እና በፊደል ዐይነቶቹ መለየት እንደሚቻል
ይገልጻል፡፡ ከተጠቀሱት ምሳሌዎች ውስጥ ጥብቀት የሌለው ኾኖ በፊደል ዐይነት የሚለይ
ሠረቀ--ወጣ/ተወለደ እና ሰረቀ--ሰረቀ፤ በመጥበቅና በመላላት እንዲሁም በፊደል ዐይነት
ደግሞ የሚለይ ቀሠመ--ቀሠመ እና ቀሰመ/ ሰ ይጠብቃል/--አጣፈጠ የሚሉትን መጥቀስ
ይቻላል፡፡ ኹለቱም ጥንድ ግሶች በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ልዩነት አላቸው፡፡ ነገር ግን
ተመሳሳዪ ድምፀ ንባብ ያላቸው በመኾኑ ነው ኹለቱም ግሶች ተመኵሳይያን የተባሉት፡፡

ከዚህም የምንረዳው ቃላት ተመኵሳይያን ለመባል የተዋቀሩባቸው ፊደላት አሁን ላይ


በድምፀ ንባብ ተመሳሳዪ መኾናቸው አንጅ የፊደላቱ ቅርጽ ግምት ውስጥ የማይገባ
መኾኑን ነው፡፡ ይህም ታየ በገለጸው አግባብ ተመኵሳይያን ግሶች የተቃኙ መኾኑን
ስለሚያሳይ ይህ ጥናት ይዞ የተነሣውን ዐላማ የሚቃኝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የዚህ
ጥናት ትኩረት በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን አግባብ መመርመር
ላይ ነውና፡፡

ኹለተኛ ዐቢይ ለቤዛ “ዐምደ ግእዝ” (2010) በተሰኘው መጽሐፉ ስለተመኵሳይያን ቃላት
ከገጽ 261-263 በመጠኑ ዳሷል፡፡ ዐቢይ “ለማንኛዉም ነገር ተመሳሳዪ እንዳለው ኹሉ
ለስሞችና ለግሶች ኹሉ ተመሳሳዪ ወይም ሞኵሼዎች አላቸው” በማለት ይጀምርና
ተመሳሳዪነታቸዉም በፊደል ተመሳስለው በትርጕም የሚለያዩ እና በፊደል ተለያይተው
በትርጕም የሚመሳሰሉ ቃላት በማለት ይከፍላቸዋል፡፡

በፊደል ከሚመሳሰሉት ውስጥ ሰርሐ--ሠራ እና ሠርሐ--አቅናና/ አከናወነ፤ ሰብሐ--አመሰገነ


እና ሠብሐ--ሰባ የሚሉት በምሳሌነት የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ከገጸ ንባቡ እንደምንረደው
ከኹለቱም ምሳሌዎች ላይ የመጀመሪያዎቹ ግሶች የተጻፉት በ “እሳቱ ሰ” ኹለተኛዎቹ

30
.

ግሶች ደግሞ በ “ንጉሡ ሠ” ነው፡፡ ከዚህም በግሶቹ መካከል በተለይ በመጀመሪያዉ ጥንድ
ግስ የትርጕም ልዩነት አለ የለም የሚለው ጥያቄ እንዳለ ኾኖ ዐቢይ በፊደል መመሳሰል
ምክንያት የተፈጠሩ ሞኵሼዎች በማለት የጠቀሳቸው ጥንድ ግሶች አሁን ላይ ተመሳሳዪ
የሚመስሉት በድመፀ ንባብ እንጅ በቅርጸ ፊደል አለመኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡ ይህም
በመጽሐፈ ሰዋስው ኹለተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሰው የሞኵሼ ዐይነት ነው፡፡

ሌላው የትርጓሜ ተመሳሳዪነትን የሚመለከት ሲኾን ይህም በተለያየ የግእዝ ቃል እየተነገሩ


አንድ ዐይነት የአማርኛ ትርጕም ያላቸውን ቃላት የሚያመለክት ነው፡፡ ለምሳሌ በአማርኛ
አመሰገነ ለሚለው ግስ በግእዝ ዘመረ፣ ቀደሰ፣ ወደሰ፣ እና ባረከ የመሳሰሉ ግሶችን መጠቀም
እንደማለት ነው፡፡ ይህም በመጽሐፈ ሰዋስው ባንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ
የግእዝ ግሶች በማለት የተገለጹት ተመኵሳይያን ግልባጭ በመኾኑ ታየ ከጠቀሳቸው
የተመኵሳይያን ዐይነቶች ጋር በቀጥታ የሚገናኝ አይደለም፡፡

በሦስተኛ ደረጃ ተመኵሳይያን የተብራሩት “የግዕዝ መማሪያ” (1998) በሚል በለይኩን


ብርሃኑ በተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡በዚህ መጽሐፍ በትርጕም ክፍሉ እንደተገለጸው
ከሞኵሼነት ትርጕም ጀምሮ ተመኵሳይያን ግሶች ለማሳያነት ከገጽ 325-338 በዝርዝር
ተቀምጠዋል፡፡ በመጀመሪያ ተመኵሳይያን የሚለው ቃል የተጻፈበትን ፊደል ስንመለከት
ቃሉ የተገኘበትን ግስ ተመኵሰየን ጨምሮ ተመኵሳይያን የሚለው ቃል የተጻፈው በዲቃላ
ፊደሉ15 ‘ኵ’ ሳይኾን በካዕብ ፊደል ‘ኩ’ ነው፡፡ ይህም ‘ኵ’ የሚለው ዲቃላ ፊደል ሳድስ
ስለመኾኑ ባለመገንዘብ የተጻፈ እንጅ የግእዝ ግስ ሥርዐተ ጽሕፈት የሚፈቅድ ኾኖ
አይደለም፡፡ ምክንያቱም ተመኵሰየ የሚለው ግስ የሴም ቋንቋዎች የጋራ ባሕሪ ወደ ኾነው
ባለ ሦስት እግር ግስ ሲቀየር ኮሰየ (የመጀመሪያዉ ፊደል ሳብዕ በመኾኑ ከወሰየ ስለሚኾን)
ሳይኾን ኰሰየ ወይም መኩሰየ (ኹለተኛ ፊደሉን ካዕብ የሚያደርግ የግእዝ የግስ አርእስት
ባለመኖሩ) ሳይኾን መኵሰየ የሚል በመኾኑ ነው ፡፡

ወደ ማሳያዎቹ ስንመለስ “አንድ ግስ ከአንድ በላይ ትርጕም ኖሮት በተለያዩ ንባቦች


የተለያዩ ትርጕሞች መስጠታቸው” የሚለው የለይኩን (1998፣ 325) አገላለጽ ለአንድ ግስ
የተለያየ ትርጕም መስጠት አነባበቡም የተለያየ መኾን እንዳለበት ያመለክታል፡፡ የንባብ
ልዩነቱ ግሱ የተዋቀረበትን ፊደል መጥበቅና መላላት የሚያመለክት ቢኾንም ነገር ግን

15
መልካቸዉን፣ ድምፃቸውንና አካኼዳቸዉን ለውጠው ካዕብንና ሳብዕን ትተው በሕጹጹነት የሚጻፉ አራቱ ፊደሎች ሲኾኑ እነሱም ኰ፣ ኈ፣ ቈ እና
ጐ ናቸው (ኪዳነ ወልድ፣ 1926፣ 10)፡፡

31
.

ለማሳያነት ከጠቀሳቸው ምሳሌዎች ውስጥ በተመሳሳዪ ንባብ ከአንድ በላይ ትርጕም


የሚሰጡ ግሶችም ይገኙበታል፡፡ ሤመ--ሾመ፣ አደረገ፣ ገለጸ እና ኮነ--ኾነ፣ ተቆጠረ፣ ነገሠ፣
ሞተ ወዘተርፈ (1998፣ 330፣ 334) የሚሉትን ግሶች በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሌላው አንድ ዐይነት ግስ ኾነው የተለያየ ትርጕም በመስጠታቸው ተመኵሳይያን ከተባሉት


ግሶች መካከል -ሠርሐ--አቀና፣ አሰላ፣እና ሠርሐ--ደከመ፣ ሠራ፤ -ነስሐ--ተፀፀተ እና ነስኀ--
ሸተተ/ከረፋ (ለይኩን፣ 1998፣ 325) የሚሉት ተጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ላይ እንደ ለይኩን ገለጻ
ግሶቹ በትርጕም የተለያዩት በመጥበቅና በመላላታቸው ነው፡፡ የፊደል አጠቃቀሙ ትክክል
ነው አይደለም የሚለው እንዳለ ኾኖ ሠርሐ የሚለው ግስ በቅርጽ ተመሳሳዪ ሲኾን ነስሐ--
ተፀፀተ እና ነስኀ--ሸተተ/ከረፋ ግሶች ግን በ“ሐመሩ ሐ” እና በ“ብዙኃኑ ኀ“ የተጻፉ
በመኾናቸው አሁን ላይ የድምፅ እንጅ የቅርጽ ተመሳሳዪነት የሌላቸው መኾኑን ያሳያል፡፡
ይህም ለይኩን አንድ ዐይነት ግስ በተለያየ ንባብ የተለያየ ትርጕም መስጠት በማለት
ለተመኵሳዪ ትርጕም ከሰጠ በኋላ በተመሳሳዪ ንባብ የተለያየ ትርጕም የሚሰጡ ግሶችን
እንዲሁም አንድ ዐይነት ተብለው ነገር ግን በተለያየ ፊደል የተዋቀሩ ግሶች በምሳሌነት
መጠቀሳቸው ከትርጕሙ ጋር አብሮ የሚኼድ ካለመኾኑም በላይ ማሳያዎቹ ከዚህ በላይ
በተጠቀሱት ምሁራንና በመጽሐፈ ሰዋስው ከተገለጸው የተለየ አይደለም፡፡ ይህም
በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን አግባብ የሚዳስስ ባለመኾኑ ከዚህ
የጥናት ዐላማ ጋር የይዘት አንድነት የለውም ፡፡

አራተኛ በአቤሴሎም ነቅዐ ጥበብ “መሠረታዊ ሰዋስወ ግእዝ (በቀላል አቀራረብ)” (2009)
በሚል በተዘጋጀው መጽሐፉ ላይ ነው ተመኵሳይያን ቃላት የተብራሩት ፡፡ ነገር ግን
በአመዳደብም ኾነ በዐይነት በቀጥታ ከመጽሐፈ ሰዋስው የተወሰደ እንጅ ተመኵሳይያን
ቃላት በተለይ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላት ሞኵሼነትን
የሚያሟሉ ስለመኾን አለመኾናቸው የሚገልጽ አይደለም ፡፡

ባጠቃላይ የግእዝ ተመኵሳይያን ቃላትን በተመለከተ በተለያዩ ምሁራን የተሠሩ ሥራዎች


በነጠላ ግሶች ላይ ያተኮሩና በመጽሐፈ ሰዋስው አንደኛ እና ኹለተኛ የተመኵሳይያን
ዐይነቶች ተብለው የተመደቡትን ሞኵሼዎች የሚዘረዝሩ በመኾናቸው እንደ መጽሐፈ
ሰዋስው በዝረዝር የቀረቡ አይደሉም፡፡ የተብራሩትም ቢኾን የዚሁ የመጽሐፈ ሰዋስው
ግልባጮች ናቸው ከሚባል ባለፈ በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን
አግባብ የሚዳስሱ አይደሉም፡፡ ይህም የሚያሳየው በተያዘው ርእሰ ጉዳይ ላይ ከዚህ ግባ

32
.

የሚባል ሥራ ያልተሠራ መኾኑን ነው፡፡ የዚህ ጥናት ትኩረትም በተለይ ተመሳሳዪ ድምፅ
ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ ቃላትን እንዲሁም ቃላት ካላቸው የትርጕም
አንድነትና ልዩነት አንጻር ተመኵሳይያን ቃላት በመጽሐፈ ሰዋስው የተገለጹበትን አግባብ
መመርመር ላይ በመኾኑ ይህም በሌሎች ምሁራን ያልተዳሰሰ ከመኾኑ ጋር ተያይዞ በዚህ
ላይ ያለውን ክፍተት ይሞላል በሚል ሐሳብ ነው፡፡

33
.

ምዕራፍ ሦስት

3.ተመኵሳይያን ቃላት በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው

ይህ ምዕራፍ አጥኚዉ ይዞት የተነሣውን ዐላማ ከግብ ለማድረስ የተሰበሰቡትን ማስረጃዎች


በአስረጂነት በመጠቀም በተመኵሳይያን ቃላት ላይ በዝርዝር ትንታኔ የሚሰጥበት ነው፡፡
በማነጻጸሪያነት ሥራ ላይ የዋሉት አስረጂዎችም የተሰበሰቡት በምዕራፍ አንድ ላይ
እንደተገለጸው ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች እና በግእዝ ቋንቋ ላይ ከተጻፉ የምሁራን
መጣጥፎች ሲኾን ታየ ገብረ ማርያም ተመኵሳይያን ቃላትን የገለጸበት አግባብ
በተሰበሰቡት ማስረጃዎች ሚዛንነት ይመረመራል፡፡

በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት በምስጢር የማይገናኙ እየራሳቸው የቆሙ ኾነው


አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ የመሰሉ ግሶች አንድ ወገን፤ በአንድ ቃል ኹለት ነገር
እየተፈቱ በመጥበቅ የቀደሰ በመላላት የቀተለ የሚኾኑ ግሶች አንድ ወገን፤ በአንድ ቃል
ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ግሶች አንድ ወገን፤ ከአገባብ፣ ከነባር፣ ከዘር፣ የሚገኙ በንባብ
አንድነት በነገር ልዩነት ያላቸው ፊደላት አንድ ወገን በማለት ነው በአራት የተከፈሉት፡፡
በእያንዳንዱ ክፍልም ለማሳያነት የሚኾኑ ብዛት ያላቸው ጥንድ ቃላት (በተለይ ግሶች)
ከነማስረጃዎቻቸው ተዘርዝረው ቀርበዋል፡፡

የዚህ ጥናት ይህ ምዕራፍም በተመሳሳዪ በአራት ክፍሎች የተከፈለ ሲኾን የመጀመሪያዉ


በምስጢር የማይገናኙ እየራሳቸው የቆሙ ኾነው አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ የመሰሉ
ግሶችን የሚመለከት ነው፡፡ በሥሩም አድራጊና አስደራጊ የመሰሉ ግሶች በአንድ፤
አድራጊና ተደራጊ የመሰሉ ግሶች በአንድ እንዲኾኑ ተደርጎ በመጀመሪያዉ አምስት፤
በኹለተኛዉ አምስት በድምሩ ዐሥር ጥንድ ግሶች በማሳያነት ተጠቅሰው ትንታኔ
ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ኹለተኛዉ ክፍል ደግሞ በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና በመላላት
በኹለት ነገር የሚፈቱ ቃላትን የሚመለከት ሲኾን አራት ጥንድ ግሶች ተዘርዝረው
ተተንትነዋል፡፡ ሦስተኛዉ ሰባት ጥንድ ግሶችን የያዘውና በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር
በሚፈቱ ግሶች ላይ ትንታኔ የሚሰጥበት ነው፡፡ አራተኛዉና የመጨረሻዉ በንባብና በፊደል
ተመሳስለው በምስጢርና በአመጣጥ ልዩነት አላቸው የተባሉትን ግሶች የያዘ ኾኖ
ለማሳያነት የተጠቀሱት ምሳሌዎች ደግሞ ኹለት ጥንድ ግሶች ናቸው ፡፡

34
.

3.1.በምስጢር የማይገናኙ እየራሳቸው የቆሙ ኾነው አድራጊ፣ አስደራጊ፣


ተደራጊ የመሰሉ ግሶች

አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ ግሶች የአምስቱ ፀዋትወ ግስ ክፍሎች ስለመኾናቸው እና


የሚገኙትም ከአንድ የግስ ሥር ላይ ‘ተ’፣ ‘አ’፣ ‘አስተ’ የተባሉ ቅጥያዎችን (ልማዶችን)
በመጨመር ስለመኾኑ በምዕራፍ ኹለት ላይ ተገልጧል፡፡

አዕማድ ግሶች ድርጊቱን በቀጥታ የሚፈጽመውን አካል ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ


የሚያስፈጽመውን አካል ወይም የድርጊቱን መፈጸም የሚያመላክቱ ሲኾኑ በመሠረታዊነት
የሚፈጸመው ድርጊት ተመሳሳዪ ነው፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው በአዕማድ ግሶች ላይ ሞኵሼነትን
ያሳየው ግሶች በምስጢር (በትርጕም) የተለያዩ ኾነው እያለ በቅርጽ ደረጃ ግን የአንዱ ግስ
አስደራጊ ወይም ተደራጊ ከሌላው አድራጊ ግስ ጋር ተመሳሳዪነት አለ በሚል ነው፡፡ ነገር
ግን በመጽሐፉ ውስጥ አስደራጊዉ ወይም ተደራጊዉ ከሌለኛዉ አድራጊ ግስ ጋር
ተመሳሳዪ ነው የተባለው ግስ አስደራጊዉ ወይም ተደራጊዉ አለመገለጹ እና በአስረጂነት
የቀረበው ጥቅስም የአስደራጊዉ ወይም የተደራጊዉ አለመኾኑ ጉዳዩን በቀላሉ ለመረዳት
አስጀጋሪ አድርጎታል፡፡

ለምሳሌ ከመጽሐፉ ሠገረ--ተራመደ እና

አሥገረ--አጸመደ (አጠመደ) የተባሉትን ግሶች ብንወስድ ለማለት


የተፈለገው ተራመደ የሚል ፍች ያለው የግእዝ ግስ ሠገረ ወደ አስደራጊነት ሲቀየር
አጠመደ የሚል ትርጕም ካለው የግእዝ ግስ አሥገረ ጋር ተመሳሳዪነት ስላለው ግሶቹ
ተመኵሳይያን ናቸው የሚል ነው፡፡ የሠገረ--ተራመደ ማስረጃዉ ደግሞ “ክህለ ሠጊረ
ዘእንበለ በትር/ ያለ ምርኩዝ መራመድ ቻለ/” የሚል ሲኾን በማስረጃነት በተጠቀሰው
ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተጠቀሰው ግስ የሚመለከተው አድራጊዉ እንጅ አስደራጊዉን ግስ
አይደለም፡፡ማስረጃዉ የሠገረ--ተራመደ አስደራጊዉን የሚመለከት ቢኾን ኖሮ ቢያንስ
በቅርጽ ደረጃ አሥገረ--አጠመደ ከሚለው ግስ ጋር ተመሳሳዪ ነው አይደለም የሚለውን
በቀላሉ መረዳት ይቻል ነበር፡፡

ያም ቢኾን በዚህ ክፍል በመጽሐፈ ሰዋስው በተገለጸው መሠረት በየምሳሌዎቹ በተጠቀሱት


ግሶች መካከል ሞኵሼነት ስለመኖር አለመኖሩ ለመለየት ጥረት የሚደረገው ተመኵሳይያን
የተባሉ ግሶች በመጀመሪያ በአድራጊነት የተጠቀሰው ግስ ወደ አስደራጊነት ወይም
35
.

ተደራጊነት ሲቀየር ከሌላኛዉ ትርጕሙ ልዩ ነው ከተባለው ግስ ጋር በተዋቀረበት የፊደል


ዐይነትም ኾነ በቅርጽ ተመሳሳዪነት ያለው ስለመኾን አለመኾኑ እንዲሁም በግሶች
መካከል የምስጢር (የትርጕም) ልዩነት ያለ ስለመኾን አለመኾኑ በመመርመር ሲኾን
ይህም የሚኾነው የተወሰኑ ግሶችን በማሳያነት በመጥቀስ ነው ፡፡

3.1.1 አድራጊና አስደራጊ የመሰሉ ግሶች

በዚህ ሥር የግሶች ሞኵሼነት የሚብራረውና የሚተነተነው ግሶቹ ከተዋቀሩበት የፊደል


ዐይነትና ከሚሰጡት ትርጕም አንጻር በኹለት ምድብ በመክፈል ነው ፡፡

ሀ ከፊደላት አጠቃቀም አንጻር

ምሳሌ አንድ፦ ረአየ--ጠበቀ

አስተርአየ --ታየ/ተገለጠ (1889፣ 35)

በምሳሌው የተጠቀሱት ግሶች የተዋቀሩበትን በተለይ በተለምዶ ሞኵሼ በመባል


የሚታወቁትን ፊደላት ስንመለከት በኹለቱም ግሶች የተጠቀሰው “አልፋዉ አ” ስለመኾኑ
ከምሳሌዉ መረዳት ይቻላል፡፡ ረአየ--ጠበቀ ለሚለው ግስ የተጠቀሰው ምስክር/ አስረጂ
ደግሞ እንኪያስ ግልገሎቼን ጠብቅ የሚል ትርጒም ያለው “ ረዐይኬ አባግዕየ ” (ዮሐ.
21÷17) የሚለው ዐረፍተ ነገር ነው፡፡ በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ጠብቅ በሚለው ትእዛዛዊ
አንቀጽ ላይ በ“አልፋዉ አ” ምትክ የገባው “ዐይኑ ዐ” መኾኑን እንገነዘባለን ፡፡ በመሰ2
በተመሳሳዪ የተገለጸ ቢኾንም ነገር ግን በመሰ3 (ገጽ 38) እና በመሰ4 (ገጽ 35) ላይ ጠበቀ
የሚል ትርጕም ያለው የግእዝ ግስ እና ማስረጃዉም ጭምር የተጻፈው በ“ዐይኑ ዐ” ነው ፡፡
ይህም የሚያሳየው ከኅትመት ኅትመት ባለፈ በአንደኛዉ ኅትመትም ቢኾን የፊደላት
አጠቃቀም ችግር ያለ መኾኑን ነው፡፡

በመኾኑም ረአየ--ጠበቀ የሚለው ግስ ወደ አስደራጊነት ሲቀየር አስተርአየ--ታየ/ተገለጠ


ከሚለው ግስ ጋር ሞኵሼ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ለመለየት በመጀመሪያ ረአየ
(ጠበቀ) የሚለው ግስ የሚጻፈው በ“አልፋዉ አ” ወይስ በ“ዐይኑ ዐ” የሚለው ጥያቄ ምላሽ
የሚያሻው ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ እልባት የሚሰጠው ሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎችን
ዋቢ በማድረግ ነው፡፡

36
.

በአማርኛ-እንግሊዝኛ-ዐረብኛ መዝገበ ቃላት ላይ በግ ጠባቂ ለሚለው የአማርኛ ስም


የተሰጠው የዐረብኛ አቻ ቃል ራዒይ አልኺራፍ /ኸሩውፍ/ የሚል ነው (ሙኒር፣ 2007፣
481) ፡፡ በዚህ ዐረፍተ ነገር ውስጥ ኸሩውፍ /አልኺራፍ/ በግ የሚለውን ስም የሚወክል
(ዝኒ ከማሁ፣ 171) በመኾኑ ራዒይ ደግሞ ጠባቂ የሚል ትርጕም ያለው ነው ማለት ነው፡፡
ቃሉም የተጻፈው በ“ዐይኑ ዐ”ስለመኾኑ ከገጸ ንባቡ መረዳት ይቻላል፡፡ ኪዳነ ወልድ
(1948፣ 835) መጠበቅ ለሚለው ስም መሰል ቃል የተጠቀመው የግእዝ ቃል በ“ዐይኑ ዐ”
የተጻፈውን ርዕይ፣ ርዕዮት የሚለውን አርእስት ሲኾን በዐረብኛ ቋንቋም ቃሉ ረዐይ በሚል
በ“ዐይኑ ዐ” እንደሚጻፍ ነው የገለጸው፡፡ በመኾኑም ረአየ--ጠበቀ በማለት በመጽሐፈ
ሰዋስው የተጻፈው ግስ የሚጻፈው በ“አልፋዉ አ” ሳይሆን በ“ዐይኑ ዐ” ነው ማለት ነው፡፡

ሌላዉ አስተርአየ--ታየ /ተገለጠ የሚለው ቃል በአራቱም የመጽሐፈ ሰዋስው ዕትሞች


የተጻፈው በ“አልፋዉ አ” ሲኾን አየ የሚለው ግስ በትግረኛ ረአየ ተብሎ እንደሚጻፍ ሀብተ
ማርያም (1986፣ 393) ግእዝ፣ ትግረኛና አማርኛ እንዴት እንደሚገናኙ በገለጸበት ምዕራፍ
ላይ አመልክቷል፡፡ በዐረብኛም አየ ለሚለው ቃል ከተሰጡት አቻ የዐረብኛ ግሶች መካከል
አንዱ ረኣ ስለመኾኑ በአማርኛ-እንግሊዝኛ-ዐረብኛ መዝገበ ቃላት (ሙኒር፣ 2007፣ 284)
ተመልክቷል፡፡ ኪዳነ ወልድም (1948፣ 816) አየ ለሚለው የአማርኛ ቃል በዐረብኛ
ረአይ፤ በግእዝ ርእየ በማለት ነው አቻ ትርጕም የሰጠው ፡፡ ይህም ርእየ የሚለው የግእዝ
ግስ ከዐረብኛ እና ከትግረኛ ቋንቋዎች አቻ ትርጕሙ ጋር ተመሳሳዪ የግስ ቅንጣጢት
ያለው መኾኑን ያሳያል፡፡

በመኾኑም አስተርአየ የሚለው ግስ አስተ የሚለውን ቅድመ ቅጥያ ርእየ ከሚለው ግስ


ላይ በመጨመር የተገኘ አስደራጊ ግስ በመኾኑ በፊደል አጠቃቀም ረገድ በመጽሐፈ
ሰዋስው የተጻፈበት አግባብ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ በመጽሐፈ ሰዋስው ረአየ--ጠበቀ በሚል
የተጻፈው ግስ ደግሞ “በዐይኑ ዐ” የሚጻፍ ስለመኾኑ ከተረጋገጠ አስደራጊዉም ሊጻፍ
የሚችለው የአድራጊዉን የግስ ሥር በመከተል በ“ዐይኑ ዐ” እንጅ አስተርአየ በሚል
በ“አልፋዉ አ” ሊኾን አይችልም፡፡ በኪዳነ ወልድ (1948፤ 835) እና በሌስሎው (1991፣
459) መዛግብተ ቃላት አስጠበቀ የሚለው የጠበቀ አስደራጊ የግእዝ ግስ አርዐየ በሚል
በ“ዐይኑ ዐ” የተጻፋውም ለዚህ ነው ፡፡

ሲጠቃለል ከተጠቀሰው ምሳሌ መረዳት የሚቻለው በመጽሐፈ ሰዋስው በመጀመሪያ ረአየ--


ጠበቀ የሚለውን ግስ በተገቢዉ ፊደል ያልተዋቀረ መኾኑና የዚሁ ግስም አስደራጊዉን

37
.

ይመስላል ተብሎ የተጠቀሰው አስተርአየ --ታየ/ተገለጠ የሚለው ግስ ያለ ቦታው የገባ


መኾኑን ነው፡፡ በመኾኑም በመጀመሪያዉ ዕትም እና በመሰ2 ጠበቀ የሚለውን የግእዝ ግስ
በተገቢዉ ፊደል ባለመዋቀር፤ በመሰ3 እና በመሰ4 ደግሞ ኹለቱ ጥንድ ግሶች በተለያየ
ፊደል ተዋቅረው እያለ አስተርአየ --ታየ/ተገለጠ የረዐየ--ጠበቀን አስደራጊ ስለሚመስል
ኹለቱን ግሶች ተመኵሳይያን ግሶች ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው ትክክል
አለመኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ መሐረ--አስተማረ

አምሐረ --አሳዘነ

አስተምሐረ--ለመነ፣አማለደ (1889፣ 33)

እንደ መጽሐፈ ሰዋስው አገላለጽ ሦስቱም ግሶች የተለያየ ትርጕም ሰላላቸው፣ አምሐረ
የመሐረ አስደራጊ፣ አስተምሐረ የአምሐረ አስደራጊ ወይም የመሐረ አደራራጊ
ስለሚመስሉ በግሶቹ መካከል ሞኵሼነት አለ ማለት ነው፡፡ የግሶቹን የትርጕም መለያየት፣
በተመሳሳዪ ፊደል መጻፋቸው እና አንዱ የሌላዉ አስደራጊ መምሰላቸዉን እንዲሁ
ስንመለከት አባባሉ ትክክል ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን በጥልቀት ስንመለከተዉ
ከፊደል አጠቃቀም ጀምሮ በግሶቹ መካከል የትርጕም ልዩነት መኖር አለመኖርና አንዱ
የሌላዉ አስደራጊ መምሰል አለመምሰል ላይ ጥያቄ ይነሣል፡፡

በመጀመሪያም የፊደላት አጠቃቀምን ስንመለከት ከምሳሌዉ እንደተገለጠው በመጀመሪያዉ


ዕትም እና በመሰ2 ሦስቱም ግሶች በ“ሐመሩ ሐ”የተጻፉ ሲኾን በመሰ3 (ገጽ 36) እና በመሰ4
(ገጽ 33) ደግሞ መሐረ--አስተማረ በማለት በምሳሌው የተገለጸው ግስ ተለይቶ በ“ሃሌታዉ
ሀ” ነው የተጻፈው፡፡ የአጻጻፍ ልዩነቱ እንዳለ ኾኖ በኹሉም ዕትሞች መሐረ
(በመጀመሪያዉ ዕትም እና መሰ2) ወይም መሀረ (መሰ3 እና መሰ4) የሚለው ግስ አስተማረ
ከሚለው ትርጕሙ በተጨማሪ ራራ፣ መጸወተ፣ ይቅር አለ የሚል ትርጕም እንዳለው
ተገልጧል (ዝኒ ከማሁ)፡፡ ይህ ማለት መሐረ የተለያየ ትርጕም ቢኖረውም
በመጀመሪያዎቹ ኹለት ዕትሞች መሠረት የሚጻፈው በ“ሐመሩ ሐ” ሲኾን በመጨረሻዎቹ
ኹለት ዕትሞች ደግሞ በ“ሃሌታዉ ሀ” ነው ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በመሰ3 (ገጽ 36) እና
በመሰ4 (ገጽ 33) ዕትሞች በሦስተኛዉ የተመኵሳይያን ክፍል ላይ ይኸው ግስ ራራ፣
መጸወተ፣ ይቅር አለ ተብሎ ሲተረጐም መሐረ ተብሎ በ“ሐመሩ ሐ” ነው የተጻፈው፡፡

38
.

ይህም በኹሉም ዕትሞች በምሳሌዉ ከተጠቀሱት ጥንድ ግሶች ውስጥ በመጀመሪያዉ


የግእዝ ግስ ላይ በፊደል አጠቃቀም ረገድ አንድነትም ኾነ ወጥነት የሌለ መኾኑን ነው
የሚያሳየው፡፡

በመኾኑም በምሳሌዉ መሠረት አስተማረ የሚል ትርጕም ያለው የግእዝ ግስ የሚጻፈው


በ“ሐመሩ ሐ” ነው ወይስ በ“ሃሌታዉ ሀ” የሚለውን ጥያቄ ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች ጋር
በማጻጸር ስንመለከት በዐረብኛ ቋንቋ አዋቂ ወይም ምሁር/ skillful ለሚለው ቅጽል ማሂር
የሚል ትርጕም ነው የተሰጠው (ስቴይንጋስ፣ 1882፣ 362) ፡፡ በዕብራይስጥ ቋንቋም
የተማረ/ skilled/ ለሚለው ቃል ትርጕሙ ማሂር እንደኾነ በሌስሎው (1991፣ 334)
የግእዝ መዝገበ ቃላት ተገልጧል ፡፡

በሌላ በኩል በ“ሐመሩ ሐ” ሲጻፍ ምሕረት እና ርሕራሔ ማድረግን የሚመለከት እንደኾነ


ነው በሌሎች ምሁራን የተገለጸው (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 584 ፤ ያሬድ፣ 2000፣ 97) ፡፡
በትግረኛ ቋንቋም መሀረ ተብሎ ሲጻፍ አስተማረ፤ መሓረ ተብሎ ሲጻፍ ደግሞ ምሕረት
አደረገ ተብሎ ነው የሚተረጐመው (ሀብተ ማርያም፣ 1986፣ 393 እና 400) ፡፡

ከላይ ከቀረበው ገለጻ የምንረዳው አስተማረ ለሚለው የአማርኛ ግስ የግእዝ ትርጕሙ


በ“ሃሌታዉ ሀ” የተጻፈው መሀረ የሚለው ቃል እንጅ በምሳሌው የተገለጸው መሐረ
አለመኾኑን ነው፡፡ይህ ከኾነ ደግሞ የመሀረ አስደራጊዉ በተመሳሳዪ በ“ሃሌታዉ ሀ” አምሀረ
(ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 579) በሚል የሚጻፍ በመኾኑ አምሐረ--አሳዘነ ወይም አስተምሐረ--
ለመነ፣ አማለደ ከሚለው ግስ ጋር በቅርጸ ፊደል ይለያል ማለት ነው ፡፡

እንዲሁም አምሐረ--አሳዘነ እና አስተምሐረ--ለመነ፣ አማለደ የሚሉት ግሶች መሐረ


ከሚለው ግስ ቅድመ ቅጥያ በመጨመር የተገኙ በመኾኑ (ሌሎው፣ 1991፣ 336) እና እንደ
ጉዳዩ ዐይነት በተለያየ መልኩ ዐውዳዊ ትርጕም ቢሰጣቸውም መሠረታዊ ልዩነት
ስለሌላቸው በመካከላቸው የምስጢር ልዩነት የላቸውም ፡፡

በመኾኑም በታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስው መሐረ የሚለው ግስ በተገቢዉ ፊደል
ሳይከተብ፤ በኋለኞቹ ኹለት ዕትሞች ደግሞ አስተማረ ለሚለው የግእዝ ግስ የተጠቀሙት
ተገቢዉን ፊደል ቢኾንም ነገር ግን ከአምሐረ እና አስተምሐረ ከሚሉት ግሶች ጋር በቅርጸ
ፊደል የተለያዩ ኾነው እያለ ግሶቹ ተመኵሳይያን መባላቸው ተገቢ አለመኾኑን

39
.

እንረዳለን፡፡ በአምሐረ--አሳዘነ እና አስተምሐረ--ለመነ፣ አማለደ በሚሉት ግሶች መካከልም


በመካከላቸው የትርጕም ልዩነት ባለመኖሩ ሞኵሼዎች ሊባሉ የሚችሉበት አግባብ የለም፡፡

ምሳሌ ሦስት፦ መልአ--መላ

አመልአ--ወደ ፊት ሄደ፣ መራ (1889፣ 34)

አመልአ--ወደ ፊት ሄደ፣ መራ የሚለው ግስ መጨረሻ ፊደሉ “አልፋዉ አ” ቢኾንም ነገር


ግን ለዚሁ ግስ ትርጕም በማስረጃነት “ራትዓን የሐውሩ ወያሜልዑ ቅድመ” / በአማርኛ
ቀናዎቹም ይኼዱበታል በማለት በተጠቀሰው ዐረፍተ ነገር ውስጥ ወያሜልዑ የሚለው
ቀዳማይ አንቀጽ በ“ዐይኑ ዐ” ነው የተጻፈው ፡፡ በመኾኑም የመልአ--መላ አስደራጊ
አመልአ--ሄደ፣ መራ ከሚለው ግስ ጋር የሚሞካሽ ስለመኾኑ በመጀመሪያ የሚመረመረው
ግሶቹ የተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ትክክል መኾን አለመኾን በመፈተሽ ነው፡፡

ኪዳነ ወልድ (1948፣ 591) በመዝገበ ቃላቱ መልአ--መላ የሚለው ግስ በዐረብኛ መለአ፣
መሊአ፤ በዕብራይስጥ ማሌእ ተብሎ እንደሚተረጐም የገለጸ ሲኾን በእንግሊዝኛ--ዐረብኛ--
አማርኛ መዝገበ ቃላት መሙላት/ fill up የሚለው ግስ መለአ የሚል ትርጕም ነው ያለው
(ሙኒር፣ 2007፣ 62) ፡፡ እንዲሁም መሮጥ/ run የሚለው የእንግሊዝኛ ግስ በዐረብኛ
መለዐ፤ በትግረኛ ደግሞ ማምለጥ/ escape ብሎ አመልዔ የሚል አቻ ትርጕም ያለው
ሲኾን (ሌስሎው፣ 1991፣ 342) ይህም አመልአ--ወደ ፊት ሄደ፣ መራ ከሚለው ግስ ጋር
ተቀራራቢ ትርጕም ያለው ነው፡፡ ከዚህም ንጽጽራዊ ትንተና የምንረዳው መልአ--መላ
በመጽሐፈ ሰዋስው በ“አልፋዉ አ” መጻፉ ትክክል ሲኾን አመልአ-ወደ ፊት ሄደ፣ መራ
የሚለው ግስ ግን በ“ዐይኑ ዐ” ምትክ በ“አልፋዉ አ” መጻፉ ስሕተት መኾኑን ነው ፡፡

አመልአ የመልአ--መላ አስደራጊዉ ቢመስልም ነገር ግን በ“ዐይኑ ዐ” ምትክ በ“አልፋዉ አ”


በመጻፉ ምክንያት ወደ ፊት ሄደ፣ መራ የሚል ትርጕም አይሰጥም፡፡ በመኾኑም አመልአ
የሚለውን የግእዙን ቃል ብቻ ስንወስድ የመልአ አስደራጊ ግስ እንጅ የተለየ ትርጕም
ያለው ግስ ባለመኾኑ፤ ወደ ፊት ሄደ፣ ተራመደ የሚል ትርጕም እንዲሰጥ ከተፈለገ ደግሞ
አመልዐ በማለት የሚጻፍ በመኾኑና ይህም በፊደል አጠቃቀም ልዩነት ስላለ በምሳሌዉ
የተጠቀሱት ግሶች በምሳሌዉ በተገለጸው አግባብ ሞኵሼነትን የሚያሟሉ አይደሉም ፡፡
በመሰ3 (ገጽ 37) እና በመሰ4 (ገጽ 34) ወደ ፊት ሄደ፣ መራ የሚል ትርጕም ያለው

40
.

ኹለተኛዉ ጥንድ ግስ በ“ዐይኑ ዐ” የተጻፈ ቢኾንም ግሶቹ በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት


ልዩነት ስላለ ከላይ ከተገለጸው ሐተታ የተለየ ውጤት የለውም፡፡

ለ. ቃላት ካላቸው ትርጕም አንጻር

ምሳሌ አንድ፦ ጸንሐ---ቆየ እና

አጽንሐ---አደባ/ ሸመቀ (1889፣ 32)

በመጽሐፈ ሰዋስው በእነዚህ ጥንድ ግሶች ሞኵሼነት አለ የተባለው ጸንሐ--ቆየ የሚለው ግስ


አቆየ ወደሚል አስደራጊ ግስ ሲቀየር አደባ ወይም ሸመቀ የሚል ትርጕም ካለው የግእዝ
ግስ አጽንሐ ጋር በትርጕም ተለያይተው በቅርጽና በአነባበብ ተመሳሳዪነት አላቸው በሚል
ነው፡፡ የፊደላት አጠቃቀምን በተመለከተ ኹለቱም ግሶች በ“ጸሎቱ ጸ” እና በ“ሐመሩ ሐ”
የተጻፉ በመኾናቸው እንዲሁም ጸንሐ--ቆየ የሚለው ግስ አስደራጊዉ አጽንሐ በመኾኑ
(ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 760) በኹለቱ ግሶች መካከል በቅርጽም ኾነ በአነባበብ ተመሳሳዪነት
አላቸው፡፡

የትርጕም (የምስጢር) መለያየትን በተመለከተ ጸንሐ--ቆየ ለሚለው ግስ የተጠቀሰው


ማስረጃ በመጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ 19 ቁጥር 29 ላይ “ይጸንሕ መቅሰፍት ለእኩያን”
የሚለው ጥቅስ ሲኾን ወደ አማርኛ ሲመለስ ለክፉዎች ሰዎች መቅሠፍት ተዘጋጅቶላቸዋል
የሚል ትርጕም እንደተሰጠው በኢመቅማ ለኢኦተቤክ በ2000 ዓ.ም በታተመው መጽሐፍ
ቅዱስ ላይ ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም አጽንሐ-- አደባ /ሸመቀ/ ለሚለው ግስ ደግሞ የተጠቀሰው ማስረጃ “እስመ ሊተሰ
አጽንሑኒ ይቅስፉኒ” የአማርኛ ትርጕሙ እኔንስ ይገርፉኝ ዘንድ አቆዩኝ የሚለው ነው
(መዝ. 38 (37)÷ 17) ፡፡ ከዚህ ላይ ጸንሐ የሚለው ግስ የአማርኛ አቻ ትርጕሙ ተዘጋጀ፤
አጽንሐ ደግሞ አቆየ የሚል ትርጕም እንደተሰጠው ልብ ይሏል፡፡ ምንም እንኳ አደባ
ወይም ሸመቀ የሚለው የአማርኛ ግስ አንድን ነገር ለመያዝ በመደበቅ ተዘጋጅቶ
መጠባበቅን የሚያመላክት ኾኖ እያለ ቀድሞ የተያዘን ነገር ቀጣይ ሌላ እርምጃ ለመውሰድ
ማቆየትን የሚመለከተውን ጥቅስ ለዚህ ግስ በማስረጃነት መጥቀሱ ተገቢ ባይኾንም አደባ/
ሸመቀ የሚለው ግስ የአቆያየቱ ኹኔታ በድብቅ መኾኑን ከማሳየት ባለፈ ቆየ ከሚለው ግስ
ጋር የተለየ ትርጕም ያለው አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ግስ በተለያየ ዐረፍተ ነገር

41
.

ሲገባ መሠረታዊ ትርጕሙን ሳይለቅ እንደ ጉዳዩ ኹኔታ ዐውዳዊ ትርጕም የሚሰጠው
በመኾኑ ነው፡፡

እንዲሁም ጸንሐ--ቆየ፣ አደባ፣ ሸመቀ-- የሚል ትርጕም ያለው ስለመኾኑ በተለያዩ ምሁራን
ተገልጧል (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 759፤ ሌስሎው፣1991፣ 560) ፡፡ ለምሳሌ “ወሶበ ጠየቁ (ቁ
ይጠብቃል) ዘይገብሩ አይሁድ ዲበ ዝ ብእሲ በጸኒሕ ፈነውክዎ ኀቤከ/ አይሁድ በዚህ ሰው
ላይ በመሸመቅ የሚያደርጉትን በተረዳኹ ጊዜ ወደ አንተ ላኩት” (የሐዋ. 23፣ 30)
የሚለውን ስንመለከት ጸኒሕ መሸመቅ የሚል ትርጕም የተሠጠው መኾኑን እንገነዘባል፡፡
ይህም የሚያሳየው አጽንሐ የሚለው ግስ የጸንሐ አስደራጊ ግስ እንጅ ራሱን የቻለ የተለየ
ትርጕም ያለው አድራጊ ግስ ያለመኾኑን ነው ፡፡ በመጽሐፈ ሰዋስው ኹለቱ ግሶች
አድራጊና አስደራጊ የሚመስሉ ተመኵሳይያን መባላቸው ተገቢ አለመኾኑን ሐተታዉ
ያመለክታል፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ሐለየ--ዘፈነ፣ ዘመረ

አሕለየ--መማለጃ ተቀበለ (1889፣ 35)

ሐለየ--ዘፈነ፣ ዘመረ የሚለው ግስ በ“ሐመሩ ሐ” መጻፉ ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች


ክተባ አንጻር ትክክል ስለመኾኑ ኹሉም ሊቃውንት የሚስማሙበት በመኾኑ (ኪዳነ ወልድ፣
1948፣ 444፤ ያሬድ፣ 2000፣ 261፤ ሌስለው፣ 1991፣ 231) የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂም በዚህ
ላይ ልዩነት የለውም፡፡ እንዲሁም ላልቶ የሚነበብ ስለመኾኑ “ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ
ለከ”/ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እዘምርልሃለኹ በሚል ከተጠቀሰው ማስረጃ የካልአይ
አንቀጹ አሐሊ መካከለኛዉ ፊደል ኃምስ ባለመኾኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ከኾነ ደግሞ በርባታ
ጊዜ የሚከተለው የቀተለን መንገድ በመኾኑ ወደ አስደራጊነት ሲቀየር መነሻ ፊደሉን ወደ
ሳድስ በመቀየር እና ‘አ’ ን ቅድመ ቅጥያ በመጨመር አሕለየ የሚል አስደራጊ ግስ
ይኾናል፡፡ ይህም አሕለየ--መማለጃ ተቀበለ ከሚለው ግስ ጋር ተመሳሰለ ማለት ነው፡፡ ነገር
ግን ከዚህ መመሳሰል ባለፈ ኸለቱም ጥንድ ግሶች ራሱን ከቻለ ከተለያየ የግስ ቅንጣጢት
የመጡ ናቸው አይደሉም የሚለውን መመርመር አስፈላጊ ነው፡፡

ኪዳነ ወልድ (1948፣ 444) ሐለየ ዘፈነ/ ዘመረ ከሚለው ትርጕሙ በተጨማሪ ሌሎች
ትርጕሞችም እንዳሉት የገለጸ ሲኾን ከነዚህም ውስጥ አንዱ ጉቦ ወይም መማለጃ መስጠት
የሚለው ተጠቅሷል፡፡ ኪዳነ ወልድ በማስረጃነት የጠቀሰው “ወሐለይኪዮሙ ይምጽኡ

42
.

ኀቤኪ”/ በዙሪያሽ ይከቡሽ ዘንድ መማለጃን ትሰጫቸዋለሽ (ሕዝ.፣ 17÷33) የሚለው አንዱ
ነው፡፡ ይህም ዋጋ ወይም ጉቦ በመስጠት ዝሙት በምትፈጽም ሴሰኛ ሴት ስለተመሰለች
ኢየሩሳሌም እምነት ማጉደል የተነገረ ቃል ነው፡፡ በዚህ ላይ ሐለየ ጉቦ ወይም መማለጃ
ሰጠ የሚል ትርጕም ነው የተሰጠው፡፡ይህም አሕለየ የሐለየ አስደራጊ ግስ እንጅ ራሱን
የቻለ የተለየ ትርጕም ያለው ግስ አለመኾኑን ነው ማስረጃዉ የሚያሳየው፡፡

በመኾኑም በመጽሐፈ ሰዋስው ሐለይኪዮሙ የሚለው አሕለይኪዮሙ ተብሎ መቀመጡ እና


መማለጃ ተቀበለ በሚል በተደራጊነት መተርጐሙ ስሕተት መኾኑን ከሐተታዉ የምንረዳ
ሲኾን ይህም በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች በምስጢር የማይገናኙ አድራጊና አስደራጊ
የመሰሉ ተመኵሳይያን ግሶች ከሚል የተሳሳተ ድምዳሜ እንዲያዝ አድርጓል፡፡

3.1.2 አድራጊ እና ተደራጊ የመሰሉ ግሶች

በዚህ ክፍልም ጥንድ ግሶቹ ካላቸው ትርጕም እና ከተዋቀሩበት የፊደላት ዐይነት ነው


ተመድበው የተመረመሩት ፡፡

ሀ ከፊደላት አጠቃቀም አንጻር

ምሳሌ አንድ፦ ሰሐለ--ሳለ

ተሠሃለ--ይቅር አለ (1889፣ 32)

ሰሐለ የሚለው ግስ በ“እሳቱ ሰ” እና በ“ሐመሩ ሐ” ፤ተሠሃለ ደግሞ በ“ንጉሡ ሠ” እና


በ“ሃሌታዉ ሀ” የተጻፉ በመኾናቸው ኹለቱም ግሶች በፊደል አጠቃቀም ረገድ ተመሳሳዪነት
የሌላቸው ስለመኾኑ ከገጸ ንባቡ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን የፊደላቱን ዐይነት
በማየት ብቻ በግሶቹ መካከል ሞኵሼነት የለም ከማለታችን በፊት ግሶቹ በተገቢዉ ፊደል
የተጻፉ ስለመኾናቸው በቅድሚያ መመርመሩ አስፈላጊ ነው፡፡

ሰሐለ--ሳለ ለሚለው ግስ በመጽሐፈ ሰዋስው የተጠቀሰው አስረጂ “ዘይስሕል ሰይፈ ለቢጹ


ይትቀተል ቦቱ ለሊሁ” የአማርኛ ትርጕሙም ለጓደኛው ሰይፍን የሚስል እሱ ራሱ
ይጠፋበታል የሚል ሲኾን ይህም ሰሐለ የአንድን ነገር ማሾል፣ መሞረድ የሚያመላክት
ነው፡፡ የትግረኛ ቋንቋም ሳለ ለሚለው የአማርኛ ግስ የሚጠቀመው ሰሓለ የሚል ግስ ነው
(ሀብተ ማርያም፣1986፣ 401)፡፡ የዐረብኛ ቋንቋም በተመሳሳዪ ሰሐለን እንደሚጠቀም ኪዳነ
ወልድ (1948፣ 857) በመዝገበ ቃላቱ ላይ ገልጧል፡፡ በመኾኑም ሰሐለ--ሳለ የሚለው ግስ
43
.

በ“እሳቱ ሰ” እና በ“ሐመሩ ሐ” መጻፉ የፊደል አጠቃቀም ችግር የሌለበት መኾኑን


ያሳያል፡፡

ሌላው ተሠሃለ--ይቅር አለ የሚለውን ግስ በተመለከተ በ“ንጉሡ ሠ” እና በ“ሃሌታዉ ሀ”


መጻፉ ትክክል ሰለመኾን አለመኸኑ ለመለየት ከተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች አንዱ በኾነው
ዐረብኛ ቋንቋ ሠሁለ የሚል ትርጕም ነው ያለው ( ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 662) ፡፡ በግእዝ
መጻሕፍትም ቃሉ ብዙ ጊዜ ተጽፎ የሚገኘው በ“ንጉሡ ሠ” እና በ“ሃሌታዉ ሀ” ነው፡፡
ለምሳሌ በ1984 ዓ.ም በተስፋ ገብረ ሥላሴ በታተመው መዝሙረ ዳዊት “አንሰ እቤ እግዚኦ
ተሣሀለኒ”/ እኔስ አቤቱ ይቅር በለኝ…አልኹ (መዝ. 40÷4) ፤ “ሣህሉ ለእግዚአብሔር
መልአ ምድረ”/ የእግዚአብሔር ይቅርታዉ ምድርን ሞላ (መዝ.፣ 32÷5) ፤ እንዲሁም
በ2009 ዓ.ም በሊጉ በታተመዉ የግእዝ ሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ “…ከመ አዕበየ
እግዚአብሔር ሣህሎ ላዕሌሃ…/”…እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት…(ሉቃ፣ 1÷58)
የሚሉትን ጥቅሶች ማንሣት ይችላል፡፡ ያሬድም (2000፣ 40) በተመሳሳዪ መርኆ
መጻሕፍት በተሰኘው ግስ ላይ የተጠቀመው “ንጉሡ ሠ”ን እና “ሃሌታዉ ሀ”ን ነው ፡፡
በመኾኑም ቃሉ በተዋቀረበት የፊደል ዐይነት ችግር የለበትም ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ከአናባቢ አንጻር የፊደላቱን ዐይነት ስንመለከት በመሰ2 እና በመሰ4 ዓ. ም


ዕትሞች ግሱ በተመሳሳዪ እንደ መጽሐፈ ሰዋስው የተጻፈ ሲኾን በመሰ3 ደግሞ ተሣሃለ
በማለት በ“ራብዑ ሣ” ነው የተጻፈው፡፡ በኹሉም ዕትሞች የግሱ አጻጻፍ ትክክል ስለመኾን
አለመኾኑ ለመለየት ግሱ የወጣበትን አርእስት መመልከት ተገቢ ነው፡፡ ግሱም በቀተለ
ቤት ወይም በባረከ ቤት ሊመደብ እንደሚችል ነው በኪዳነ ወልድ (1948፣ 662)
የተገለጸው፡፡ ይህ ማለት ሠሀለ ወይም ሣሀለ ኹኖ በኹለቱም መንገድ ሊገሰስ እንደሚችል
ነው የምንረዳው፡፡ ይህ ከኾነ ደግሞ ‘ተ’ ቅድመ ቅጥያ ሲጨመርበት
ተሠህለ/ተሥህለ/ተሠሀለ (ባለዐመል ‘ሀ’ ፊደል በመሀል ስላለ) ወይም ተሣሀለ ነው
የሚኾነው፡፡ በመኾኑም ኹሉም ዕትሞች “ንጉሡ ሠ”ን እና “ሃሌታዉ ሀ” ን መጠቀማቸው
ትክክል ቢኾንም ነገር ግን በኹሉም ዕትሞች ላይ የ“ሃሌታዉ ሀ” ራብዑ ፊደል መጻፉ ግሱ
የተገኘበትን አርእስት ያልተከተለ በመኾኑ ስሕተት መኾኑን እንገነዘባለን፡፡

ጉዳዩ ሲጠቃለል ምንም እንኳን በ “ሃሌታዉ ሀ” እና በ“ሐመሩ ሐ” እንዲሁም በ በ“እሳቱ


ሰ” እና በ“ንጉሡ ሠ” መካከል ያለውን የድምፅ ልዩነት ማዎቅ ባይቻልም ነገር ግን

44
.

ፊደላቱ ካላቸው የቅርጽ ልዩነት አንጻር ተመሳሳዪ ናቸው ለማለት የማይቻል በመኾኑ
በምሳሌዉ የተጠቀሱት ጥንድ ግሶች ተመኵሳይያን መባላቸው ተገቢነት ያለው አይደለም፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ሐለፈ--አለፈ

ተሐለፈ--ተነጋገረ (1889፣ 35)

ከገጸ ንባቡ መረዳት እንደሚቻለው የኹለቱ ግሶች ትርጕም የተለያየ በመኾኑ የሐለፈ--
አለፈ ተደራጊ ግስ ተነጋገረ ከሚል ትርጕም ካለው ግስ ተሐለፈ ጋር የሚሞካሽ ስለመኾን
አለመኾኑ የሚመረመረው ግሶቹ የተዋቀሩበትን የፊደል ዐይነት እና ቅርጸ ፊደሉን
መሠረት በማድረግ ነው፡፡

ሌስለው (1991፣ 260) መከተል /follow/፣ መተካት/succeed የሚሉት የእንግሊዝኛ ቃላት


በዐረብኛ ቋንቋ ኀለፈ፤ ትቶ መኼድ/leave behind/ የሚለው ቃል ደግሞ ኀለፈ (ለ ጠብቆ
ይነበባል) ተብሎ እንደሚተረጐም የገለጸ ሲኾን ኪዳነ ወልድም (1948፣ 478) ዐለፈ
የሚለው ግስ በዐረብኛ ኀለፈ የሚል ትርጕም እንዳለው ነው በመዝገበ ቃላቱ ያሰፈረው ፡፡

በሌላ በኩል ይኸው ሐለፈ--አለፈ የሚለው ቃል በትግረኛ ሐላፋ፤ በትግረ ደግሞሐልፈ


በሚል ነው ሌስሎው (1991፣ 260) በመዝገበ ቃላቱ የገለጠው ፡፡ ነገር ግን ሌስሎው በዚሁ
መዝገበ ቃላት መግቢያ ላይ በትግረኛ እና በትግረ ቋንቋዎች ልዩነታቸው ተጠብቆ
የሚገኙት “አልፋዉ አ” እና “ዐይኑ ዐ” እንደኾኑና ሌሎቹ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው
የሚመስሉ ፊደላት አንዱ ከሌላዉ ጋር ተቀላቅሎ እንደሚገኝ አትቷል፡፡ ኡሌንዶርፍም
በጕረሮ ከሚነገሩ ድምፆች ውስጥ “ብዙኃኑ ኀ” በትግረኛ ቋንቋ ከሌሎቹ ተመሳሳዪ ድምፅ
ያላቸው ከሚመስሉ ፊደላት ጋር ግልጽ የኾነ ልዩነት እንደሌለው ነው የገለጸው፡፡
ከምሁራኑ ገለጻ የምንረዳውም “ብዙኃኑ ኀ” ን በተመለከተ በግእዝ ቋንቋ የፊደላትን
አጠቃቀም ተገቢነት ለመመርመር የትግረኛ እና የትግረ ቋንቋዎችን በማነጻጸሪያነት
መጠቀሙ ተገቢ አለመኾኑን ነው፡፡

በመኾኑም ለተያዘው ጉዳይ በማነጻጸሪያነት የሚያገለግለው የዐረብኛ ቋንቋ ነው ማለት


ነው፡፡ በሌስሎው የተገለጹት የዐረብኛ ቃላት ከተጠቀሰው ምሳሌ ጋር በትርጕም
ተቀራራቢነተ ያላቸው ስለኾነ እና ቃላቱም የተጻፉት በ“ብዙኃኑ ኀ” በመኾኑ ሐለፈ--አለፈ
የሚለው ቃል መጻፍ ያለበት በ“ሐመሩ ሐ” ሳይኾን በ“ብዙኃኑ ኀ” ነው በማለት ማጠቃለል
ይቻላል፡፡

45
.

ሌላው ተሐለፈ--ተነጋገረ የሚለውን ቃል በተመለከተ ሐለፈ--ማለ የሚለው ቃል በዐረብኛ


ቋንቋ ሐለፈ የሚል አቻ ትርጕም እንዳለው ሌሰሎው(1991፣ 229) አመልክቷል ፡፡
የምሳሌዉ ኹለተኛዉ ተሐለፈ--ተነጋገረ የሚለው ግስ የተደራጊነት በተለይ የአማርኛዉ
ትርጕም ተደራራጊነትን ስለሚያሳይ ተሐለፈ (ሓ)--ተነጋገረ ሐለፈ ከሚለው አድራጊ ግስ
የመጣ ነው ማለት ይቻላል፡፡ መሀላ መፈጸምም ከንግግር ክፈሎች አንዱ በመኾኑ ተሐለፈ
(ሓ) ብሎ ተማማለ በማለትም ሊተረጐም ይችላል፡፡በመኾኑም ከጥንድ ግሶቹ ውስጥ
የመጀመሪያዉ ግስ በ“ብዙኃኑ ኀ”፤ ኹለተኛዉ ጥንድ ደግሞ በ“ሐመሩ ሐ” የሚጻፍ
በመኾኑ ግሶቹ በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት አንድነት የላቸውም ማለት ነው፡፡ እንዲሁም
ኀለፈ--ዐለፈ የሚለው ግስ ወደ ተደራጊ ዐምድ ሲቀየር ተኀልፈ፤ ወደ ተደራራጊነት ሲቀየር
ተኃለፈ በማለት ነው፡፡ ይህም ጥንድ ግሶቹ በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነትና ከአናባቢ
ፊደላት አንጻርም የቅርጽ ልዩነት ያላቸው በመኾኑ ሊሞካሹ የሚችሉበት አግባብ የለም፡፡

ምሳሌ ሦስት፦ ሰአለ--ለመነ

ተሥእለ--ጠየቀ (1889፣ 32)

ጥንድ ግሶቹ የተዋቀሩት ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ኹለት ፊደላት በመኾኑ
በመጀመሪያ የሚፈተሸው በፊደል አጠቃቀም ረገድ ተመሳሳዪ መኾን አለመኾናቸዉና
ተገቢነታቸዉ ነው፡፡ ከገጸ ንባቡ እንደሚታየው የመጀመሪያዉ ግስ “እሳቱ ሰ” ን ሲጠቀም
ኹለተኛዉ ግስ ደግሞ በ“ንጉሡ ሠ” ነው የተጻፈው፡፡ በመኾኑም እንዲሁ ገጸ ንባቡን
በመመልከት በፊደል አጠቃቀም ረገድ በግሶቹ መካከል ተመሳሳዪነት ስለሌለ እና ሰአለ--
ለመነ የሚለው ግስ ወደ ተደራጊነት ሲቀየር በ“እሳቱ ሰ” ስለሚጻፍ የሰአለ--ለመነ
ተደራጊዉና ተሥእለ--ጠየቀ ሞኵሼዎች አይደሉም ማለት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከዚህ
ድምዳሜ ላይ ከመድረሳችን በፊት በመሰ3 እና በመሰ4 ዕትሞች ተሥእለ--ጠየቀ የሚለው
ግስ የተጻፈው ተስእለ በሚል በ“እሳቱ ሰ” በመኾኑና ይህም ከኅትመት ኅትመት የፊደል
አጠቃቀም ልዩነት መኖሩን ስለሚያሳይ የየዕትመቶችን የፊደል አጠቃቀም ተገቢነታቸዉን
እንመለከታለን፡፡

ለመነ ከሚለው አማርኛ ግስ የተገኘው ልመና የሚለው ጥሬ ዘር በዐረብኛ ከተሰጠው አቻ


ትርጕም አንዱ ሱኣል ሲኾን ፤ ጠየቀ ለሚለው የአማርኛ ግስ ደግሞ ሰአለ የሚል ዐረብኛ

46
.

ግስ ነው (ሙኒር፣ 1882፣ 8፣ 485) ፡፡ ይህም በኹለቱም ቃላት ዐረብኛዉ የተጠቀመው


“እሳቱ ሰ” ን እና “አልፋዉ አ” ን መኾኑን ያሳያል፡፡

ሌስሎውም (1991፣ 480) በግእዝ--እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላቱ ለመነ፣ ጠየቀ የሚል


ትርጕም ላለው የእንግሊዝኛ ግስ የተጠቀመው ሰአለ፣ ስእለ የሚል የግእዝ ግስ ሲኾን
ትግረኛ ቋንቋም ጠየቀ ለማለት ሰኣለ የሚል ግስ እንደሚጠቀም አመልክቷል፡፡ ከዚህም
የምንረዳው በኹሉም ዕትሞች ሰአለ--ለመነ የሚለው ቃል በተገቢዉ መንገድ የተጻፈ
መኾኑንና ነገር ግን ተሥእለ--ጠየቀ የሚለው ግስ በመጽሐፈ ሰዋስው ኅትመት በ“ንጉሡ
ሠ” መጻፉ ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች አንጻር ተገቢ አለመኾኑን ነው፡፡

ከትርጕም አንጻርም ስንመለከተው ለመነ የሚለው ግስ በሰጪዉ ችሮታ የሚገኝ ነገርን


መጠየቅ ሲያመለክት ጠየቀ የሚለው ግስ ደግሞ ጠያቂዉ ካለው መብት አንጻር
እንዲደረግለት የሚፈልገውን ነገር መፈለግን ጨምሮ ኹሉንም የጥያቄዎች ዐይነት
የሚመለከት ነው፡፡ ይህም መለመን ከጥያቄዎች እንደ አንዱ የሚቆጠር እንጅ ጠየቀ
ከሚለው ግስ የተለየ አለመኾኑን ያሳያል፡፡

ሌስሎው (1991፣ 480) እና ኪዳነ ወልድ (1948፣ 842) ሰአለ ለሚለው የግእዝ ግስ ለመነ፣
ጠየቀ፣ ፈለገ ወዘተርፈ የሚል ትርጕም በመስጠት ተስእለ የሚለው ግስም የ ሰአለ ተደራጊ
ግስ እንደኾነ መግለጻቸው ሰአለ የሚለው ግስ እንደአገባቡ ትርጕም በሚሰጥ መልኩ
የሚፈታ እንጅ ጠየቀ የሚለው የአማርኛ ግስ የተለየ ትርጕም ያለው ሌላ የግእዝ ግስ
አለመኖሩን ያሳያል፡፡ ለዚህም ነው ኪዳነ ወልድ ጠየቀ ለሚለው የአማርኛ ግስ ሰአለ
በማለት ፈንታ ተስእለ እያለ መገኘቱ በልማድ የመጣ ስሕተት እንጅ ትክክል አለመኾኑን
የገለጸዉ (ዝኒ ከማሁ) ፡፡

ባጠቃላይ በመጽሐፈ ሰዋስው በምሳሌዉ ከተመለከቱት ጥንድ ግሶች ውስጥ ኹለተኛዉ ግስ


በተገቢዉ ፊደል ያልተዋቀረ ከመኾኑም በላይ ኹለቱም ግሶች የተለያየ ትርጕም
እንዳላቸው ተቆጥሮ ተሥእለ ከሰአለ ተደራጊ ግስ ጋር ሞኲሼ ነው መባሉ ከልማደ
መጻሕፍት የመጣ ስሕተት እንጅ ትክክል አለመኾኑን ጥናቱ ያሳያል፡፡

ለ. ቃላት ካላቸው ትርጕም አንጻር


ምሳሌ አንድ፦ ነሥአ--ወሰደ
ተንሥአ--ተነሣ (1889፣ 34)

47
.

ኹለቱም ጥንድ ግሶች ስለተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት በኹሉም የመጽሐፈ ሰዋስው ዕትሞች
ልዩነት የለም፡፡ ኪዳነ ወልድም (1948፣ 642) ነሥአ የሚለው ግስ በዕብራይስጥ ቋንቋ
ናሣእ ተብሎ እንደሚተረጐም በመግለጽ ግሶቹን በ“ንጉሡ ሠ” እና በ“አልፋዉ አ” ነው
በተመሳሳዪ የከተባቸው፡፡ ዲልማንም (1907፣ 64) የተሻሉ በሚባሉ የብራና መጻሕፍት
ኹሉ በ“እሳቱ ሰ” ተጽፈው ከማይገኙ የግእዝ ግሶች ውስጥ አንዱ ነሥአ እንደኾነ ነው
የገለጸው፡፡ይህም የሚያሳያው ግሶቹ ስለተዋቀሩበት ፊደል አከራካሪ ጉዳይ የሌለ መኾኑን
ነው፡፡ ይህ ከኾነ ደግሞ የጥንድ ግሶቹ ሞኵሼነት መኖር አለመኖሩ የሚመረመረው
ከተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ሳይኾን ካላቸው የትርጕም አንድነትና ልዩነት እና አንዱ
የሌላዉ ተደራጊ ወይም አድራጊ መምሰል አለመምሰል አንጻር ነው፡፡

ነሥአ--ወሰደ ከሚለው ትርጕሙ በተጨማሪ መሠረታዊ ትርጕሙን ሳይለቅ


እንደሚያስረው/ እንደሚቋጨው የጉዳይ ዐይነት ያዘ፣ ተቀበለ፣ አነሣ ተብሎ ይተረጐማል
(ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 642) ፡፡ የዚህ ማስረጃዉ ደግሞ “ወእንዘ ይበልዑ ነሥአ ኅብስተ
እግዚእ ኢየሱስ.../ ሲበሉም ጌታ ኢየሱስ ኅብስቱን አንሥቶ…” (ማቴ.፣ 26፣26) ብሎ
አነሣ፤ “ንሥኡ መስዋዕተ ወባኡ ውስተ አዕጻዲሁ/ መስዋዕት (ን) ያዙ ወደ አደባባዮችም
ግቡ” (መዝ.፣ 95፣8) ብሎ ያዘ በሚል በመጽሐፍ መገኘቱ ነው፡፡ ይህም ነሥአ በትርጕም
ደረጃ ተንሥአ--ተነሣ ከሚለው ግስ ጋር የትርጕም ልዩነት የሌለው መኾኑን ያሳያል፡፡
በመካከላቸዉ ያለው ብቸኛዉ ልዩነት ነሥአ--አነሣ በሚለው ግስ ውስጥ ድርጊት ፈጻሚዉና
ድርጊት ተቀባዩ/ ሳቢና ተሳቢዉ/ ተለይቶ የሚታወቅ ሲኾን ተንሥአ--ተነሣ በሚለው ግስ
ውስጥ ግን ድርጊት ተቀባዩ ራሱ ድርጊት ፈጻሚዉ በመኾኑ ሳቢና ተሳቢ ያልተለየ መኾኑ
ነው፡፡

በመኾኑም በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች በምስጢር/ በትርጕም የማይገናኙ እየራሳቸዉ


የቆሙ ግሶች ሊያስብል የሚችል ልዩነት የላቸውም ማለት ነው፡፡

ሌለላው ተንሥአ የነሥአ ን ተደራጊ መመሳሰልን በተመለከተ ነሥአ ከቅርጸ ፊደላቱ


አንጻር ወደ ተደራጊነት ሲቀየር በቀተለ ወይም በገብረ ቤት ስለሚረባ ቅድመ ቅጥያ ‘ተ’ ን
በመጨመር ተነሥአ ነው የሚኾነው፡፡ ትርጕሙም እንዲነሣ ተደረገ ተብሎ በተደራጊነት
የሚተረጐም ሲኾን ከቅድመ ቅጥያው ‘ተ’ ቀጥሎ ያለው ፊደል ወደ ሳድስ ባለመቀየሩ
ተንሥአ--ተነሣ ከሚለው ግስ በቅርጸ ፊደል ይለያል፡፡

48
.

በመኾኑም ተንሥአ--ተነሣ የገቢር እና የተገብሮ ባሕሪ ባላቸው ግሶች መካከል የሚገኝ


አጓጉል ግስ ሲኾን በትርጕም ነሥአ--ወሰደ ከሚለው ግስ ልዩነት የሌለው እና ነገር ግን
በቅርጸ ፊደል የሚለያይ በመኾኑ ነሥአ--ወሰደ ከሚለው ግስ ተደራጊ ጋር የሚሞካሽ
አይደለም፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ዘከረ--ጠራ

ተዘከረ--አሰበ (1889፣ 34)

ዘከረ የሚለው ግስ ዘክሮ፣ ዘክሮት ብሎ በመጥበቅ በቀደሰ ቤት ወይም ዘኪር፣ ዘኪሮት ብሎ


በመላላት በቀተለ ቤት ሊመደብ ይችላል (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 420) ፡፡ የዚህ ማስረጃዉም
ለቀተለ ቤት ሲኾን “ኢትዝር ለነ አበሳነ ዘትካት” (መዝ. 79)፤ የቀደሰ ሲኾን ደግሞ
“ወኢይዜከር አስማቲሆሙ በአፉየ” (መዝ. 60) የሚለው ጥቅስ ነው (ዝኒ ከማሁ)፡፡ እንደ
መጽሐፈ ሰዋስው አገላለጽ በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች ተመኵሳይያን የተባሉት የዘከረ
ተደራጊ ተዘከረ--አሰበ ከሚለው ግስ ጋር ተመሳሳዪነት አለው የሚል በመኾኑና ተዘከረ
ደግሞ ጠብቆ የሚነበብ ግስ በመኾኑ ከዚህ ላይ የተጠቀሰው ግስ በቀደሰ ቤት የሚረባው
ዘከረ ነው ማለት ነው፡፡

በዘከረ ተደራጊ እና በተዘከረ መካከል የሞኵሼነት መኖርን ለመለየት በኹለቱ ግሶች


መካከል የትርጕም ልዩነት መኖሩን መመርመር ግድ ነው፡፡ መነሻ የሚኾነውም በመጽሐፈ
ሰዋስው ለግሶቹ ትርጕም መለያየት የቀረበው ማስረጃ ነው፡፡ ዘከረ--ጠራ ለሚለው ግስ
የተጠቀሰው ማስረጃ “ወኤልያስኒ ሶበ ዘከራ ለኤልዛቤል አእመሮ ዮሐንስ ታኦሎጎስ” (ያዕቆ.
ዘእልበራድዒ) የሚለው ሲኾን የአማርኛ ጥሬ ትርጕሙ ኤልያስም ኤልዛቤልን በጠራት
ጊዜ ታኦሎጎስ ዮሐንስ ኤልያስን አወቀው የሚል ነው፡፡ ይህም ዮሐንስ ኤልያስ ሲጣራ
ሰምቶ በድምፁ ኤልያስን ያወቀው መኾኑን ያሳያል፡፡

“ተዘከረኒ እግዚኦ አመ ትመጽእ በመንግሥትከ” (ሉቃ. 23÷ 42) የሚለው ጥቅስ ደግሞ
የተዘከረ--አሰበ የሚለው ግስ ማስረጃ ሲኾን ወደ አማርኛ ሲመለስ አቤቱ በመንግሥትህ
በመጣህ ጊዜ ዐስበኝ ማለት ነው፡፡ ይህም በዕለተ ዐርብ ጌታ በመስቀል ላይ እያለ ፈያታይ
ዘየማን የተናገረው ቃል ነው፡፡ ምንም እንኳን ጌታ “አማን እብለከ እመን ፈድፋደ ከመ
ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት” (ሉቃ. 23÷43) ትርጕሙም እውነት እልኻለኹ ዛሬ
በገነት አብረኸኝ እንደምትኾን ፈጽመኽ እመን በማለት ወዲያውኑ መልስ የሰጠው

49
.

ቢኾንም ፈያታይ ዘየማን ግን ጌታ በኋላ ለፍርድ በሚመጣ ጊዜ “…ንዑ ኀቤየ ቡሩካኑ


ለአቡየ ትረሱ መንግሥተ ሰማያት/ አባቴ የባረካችኹ መንግሥተ ሰማያትን ትወርሱ ዘንድ
ኑ ወደ እኔ…” (ማቴ.፣ 25÷34) እያለ ከሚጠራቸው ወዳጆቹ (ጻድቃን) ጋር በቀኙ
እንዲያቆመው /እንዲጠረው በማሰብ የተነገረ ስለመኾኑ ከዐረፍተ ነገሩ መገንዘብ ይቻላል
፡፡

ከማብራሪያዉ መረዳት የሚቻለው ጠራ እና አሰበ በተለያየ ዐውድ ቢገቡም በትርጕም


ደረጃ ግን ተመሳሳዪ መኾናቸውን ነው፡፡ ተዘከረ የሚለው ግስም የዘከረ ተደራጊዉ ኹኖ
እያለ በአድራጊ ቦታ ገብቶ መተርጐሙ ልማደ መጻሕፍት ኾኖ እንጅ ትክክል እንዳልኾነ
ኪዳነ ወልድ (1948፣420) ይገልጻሉ፡፡ ይህን ሐሳብ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂም የሚጋረው
ነው፡፡

በመኾኑም በመጽሐፈ ሰዋስውተዘከረ የዘከረ ተደራጊ ግስ ኹኖ እያለ ራሱን የቻለ የተለየ


ትርጕም እንዳለው ተቆጥሮ ከዘከረ ተደራጊ ጋር ሞኵሼ መባሉ ትክክል አለመኾኑን ነው
የምንገነዘበው፡፡

3.2 በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና በመላላት ኹለት ፍች ያላቸው ቃላት

ቀድሞ እንደተገለጸው በግእዝ ቋንቋ ውስጥ ጠብቆ የሚነበበው ፊደል ተደግሞ የማይጻፍ
ወይም ጠብቆ ለመነበቡ የሚያሳይ ምልክት ባለመኖሩ ከተሰጡት ግሶች ውስጥ የትኛዉ
ግስና ፊደል ጠብቆ እንደሚነበብ በቀላሉ ለመለየት አይቻልም፡፡ ታየ ይህን ችግር
በመገንዘብ ይመስላል ከተሰጡት ጥንድ ግሶች ውስጥ የመጀመሪያዉ ግስ የቀደሰን
ኹለተኛዉ ደግሞ የቀተለን አካኼድ እንደሚከተል የገለጸው፡፡ የየግሶቹ ማስረጃዎችም
የሚያሳዩት ይህንኑ ነው፡፡

በዚህ ክፍልም ለማሳያነት ተመርጠው ከቀረቡት ጥንድ ቃላት ውስጥ ጠብቆ የሚነበበው
የመጀመሪያዉ ቃል ኾኖ ፊደሉም ከመድረሻ ፊደሉ ቀድሞ የሚገኘው ፊደል ነው፡፡
የተጠቀሱት ጥንድ ቃላትም ተመኵሳይያን መኾን አለመኾናቸው የሚመረመረው ቃላቱ
ከተዋቀሩበት ፊደል ተመሳሳዪ መኾን አለመኾን እና ካላቸው የትርጕም ልዩነት አንጻር
ሲኾን በእያንዳንዱ ክፍል ለማሳያነት ምሳሌዎችን በመጥቀስ ነው፡፡

50
.

3.2.1 በትርጕም ተለያይተው የፊደላት አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ቃላት

ምሳሌ አንድ፦ሰርሐ--አቀና፣ አሰላ


ሰርሐ--ሰራ፣ ደከመ (1889፣ 37)
እነዚህ ጥንድ ግሶች የተዋቀሩት ተመሳሳዪ በኾኑ ኹለት ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው
በሚመስሉ ፊደላት ሲኾን ነገር ግን በኋለኞቹ በመሰ3 (ገጽ 39) እና በመሰ4 (ገጽ 36)
ዕትሞች ላይ “ሐመሩ ሐ” እንዳለ ኾኖ በ“እሳቱ ሰ” ምትክ በ“ንጉሡ ሠ” ነው ኹለቱም
ግሶች የተጻፉት፡፡ በመጀመሪያም የምናየው ሥርዐተ ጽሕፈቱን ሲኾን በኪዳነ ወልድ
(1948፣ 677) እና በሌስሎው (1991፣ 533) መዛግብተ ቃላት አቀና፣ አሰላ የሚል ትርጕም
ያለውን የግእዝ ግስ ሠርሐ በሚል በ“ንጉሡ ሠ” ነው የተጻፈው፡፡ በዐረብኛ ቋንቋም
ማስፋት የሚል ትርጕም ያለው የእንግሊዝኛ ግስ /expand, widen/ ሸረሐ የሚል የዐረብኛ
ትርጕም እንዳለው ነው በሌስሎው (ዝኒ ከማሁ) የግእዝ መዝገበ ቃላት የተገለጸው፡፡
ማስፋት፣ ማስፋፋት የሚለው ቃል ከተቃና ወይም ከሰላ የሥራ እንቅስቃሴ ጋር የሚገናኝ
በመኾኑ ሌስሎው አቀና፣ አሰላ ለሚለው ግስ ሸረሐ የሚለውን የዐረብኛ ግስ በአቻነት
መጠቀሙ ተገቢ ነው፡፡ የዐረብኛ ‘ሸ’ ፊደል ደግሞ በግእዝ የሚወከለው በ“ንጉሡ ሠ”
ስለመኾኑ ዲልማን (1907፣ 60፣ 63) በሰዋስወ ግእዝ መጽሐፉ አመልክቷል፡፡ በመኾኑም
አቀና፣ አሰላ የሚል ትርጕም ያለው የግእዝ ግስ በ“ንጉሡ ሠ” መጻፍ ሲገባው በምሳሌዉ
በተገለጸው አግባብ በ“እሳቱ ሰ” መጻፉ የመጽሐፈ ሰዋስው አንዱ ስሕተት ነው ማለት
ነው፡፡

በሌላ በኩል ሰራ፣ ደከመ የሚል ትርጕም ካለው የግእዝ ግስ ጋር በዐረብኛ እና


በዕብራይስጥ ቋንቋ ቀጥታ ግንኙነት ያለው ግስ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጂ ባደረገው ዳሰሳ
ባያገኝም ነገር ግን በትግረኛ ሳርሔ እና በትግረ ደግሞ ሳርሐ በሚል እንደሚተረጐም ነው
ሌስሎው (1991፣ 513) የገለጸው፡፡ እንደ ያሬድ (2000፣ 6) እና ኪዳነ ወልድ (1948፣ 885)
ያሉ የሀገር ውስጥ ምሁራንም የተጠቀሙት “እሳቱ ሰ” ን ነው ፡፡ይህም ሰርሐ--ሰራ፣ ደከመ
የሚለው ግስ በመጀመሪያዉ ዕትም እና በመሰ2 የፊደል አጠቃቀም ችግር የሌለበት
መኾኑን ያሳያል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ መሰ3 እና መሰ4 “ንጉሡ ሠ” ን መጠቀማቸዉ ትክክል
አለመኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡ በመኾኑም ጥንድ ግሶቹ በመጀመሪያዉ ዕትም እና
በመሰ2 ዕትሞች በ“እሳቱ ሰ” በመሰ3 እና በመሰ4 ዕትሞች ደግሞ በ“ንጉሡ ሠ” ተገቢ
ባልኾነ መንገድ ተጽፈው ተመኵሳይያን ቃላት መባላቸው ነው ትክክል ያልኾነው፡፡

51
.

ምሳሌ ኹለት፦ ዐቀመ--ፈጸመ

አቀመ--መለሰ (1889፣ 36)

ግሶቹ በ“ዐይኑ ዐ” እና በ“አልፋዉ አ” በመዋቀራቸው ምክንያት የመልክአ ፊደል ልዩነት


ያላቸው ስለመኾኑ ገጸ ንባቡ ያሳያል፡፡ ነገር ግን በምሳሌዉ በግልፅ የሚታዩትን ልዩነቶች
እንዳለ ከመቀበላችን በፊት ለልዩነቱ ምክንያት የኾኑትን ፊደሎች በገቡበት ግስ ውስጥ
ያላቸውን የአጠቃቀም ተገቢነት መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ ይህም የሚኾነው ከጥንድ ግሶች
ጋር ተመሳሳዪ የግስ ቅንጣጢት እና ትርጕም ያለው የሌላ ቋንቋ ቃል በመፈለግ ነው፡፡

በሌስለው(1991፣ 67) የግእዝ መዝገበ ቃላት በዐረብኛ ዐቂም ብሎ የተዘጋ፣ የታገደ/


obstricted, constructed፤ በትግረኛ ዐቀመ ብሎ መቻል/ be able፤ በትግረ ዐቅሚ ብሎ
ችሎታ/ ability, limit በሚል አቻ ትርጕም ተሰጥቶታል፡፡ በኪዳነ ወልድ (1948፣ 706)
መዝገበ ቃላት ደግሞ ዐቀመ--ፈጸመ ለሚለው ግስ የተሰጠው አቻ የዐረብኛ ቃል ዐቀመ
ሲኾን ትርጕሙም አመከነ የሚል ነው፡፡ ዐቀመ የሚለው ግስ ፈጸመ ከሚለው ትርጕሙ
በተጨማሪ ወሰነ፣ አሠረ፣ አቆየ፣ ያዘ የሚል ትርጕም ያለው በመኾኑ (ዝኒ ከማሁ) በአቻነት
ከላይ የተጠቀሱት የዐረብኛ፣ የትግረኛ እና የትግረ ቃላት ተገቢነት ያላቸው ናቸው፡፡
በመኾኑም ዐቀመ--ፈጸመ የሚለው ግስ ከሌሎች ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች ሥርዐተ
ጽሕፈት አንጻር በመጽሐፈ ሰዋስው በ“ዐይኑ ዐ” መጻፉ ትክክል ነው ማለት ነው፡፡

አቀመ--መለሰ የሚለውን ግስ ስንመለከት ቆመ--ቆመ ከሚል ግስ ላይ ‘አ’ ን በመጨመር


የተገኘ እንጅ ራሱን የቻለ ከቆመ የተለየ ትርጕም ያለው ግስ አይደለም፡፡ የዚህ ማስረጃዉ
ደግሞ “ዘአቀመ ስምዐ ለዮሴፍ አመ የሐውር ብሔረ ግብፅ” ወደ አማርኛ ሲመለስ ወደ
ግብፅ ሀገር በኼደ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ ( መዝ.፣ 80፣ 5) የሚለው ጥቅስ ነው፡፡

በመጽሐፈ ሰዋስው ለግሱ በማስረጃነት “አቀውም ገጽየ ላዕለ ይእቲ ነፍስ”/ በዚያ ሰው ላይ
ፊቴን አከብድበታለሁ (ዘሌ. 17፣ 10) በማለት የተጠቀሰውም ደም መብላት የተከለከለ
ስለመኾኑና ደም በሚበላ ሰው ላይም የእግዚአብሔር ቁጣዉ የከበደ እና የምሕረት ፊቱንም
የሚመልስ ስለመኾኑ የተነገረ በመኾኑ አቀመ ብሎ ፊቱን መለሰ/ ገታ ወይም አከበደ/
አበረታ ተብሎ ቢተረጐም ልዩነት የለውም፡፡ ይህም ቆመ--ቆመ ተብሎ በቁሙ16

16
በቁሙ መተርጐም ማለት የግእዙ እና የአማርኛዉ ቃላት በመልክአ ፊደልም ኾነ በትርጕም ተመሳሳዪ በመኾናቸው የግእዙን ትርጕም አማርኛዉ
እንዳለ መጠቀሙን ለማሳየት ነው፡፡

52
.

ከሚተረጐመው በተጨማሪ ለቆመ ያለው አማራጪ ትርጕም ነው (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣


785) ፡፡ ስለዚህ አቀመ የቆመ አድራጊ ወይም አስደራጊ ነው ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ኪዳነ ወልድ (1948፣ 785) ቆመ በውስጡ የያዘው አንድ ዐመል17 ኾኖ እያለ
አቆመ እያለ መርባት ሲገባው እንደ ባለኹለት ዐመሉ ቦአ (የቦአ አስደራጊዉ አብአ ተብሎ
ስለሚረባ) አቀመ በሚል መገኘቱ ትክክል እንዳልኾነ ይገልጻል፡፡ አፈወርቅም (1988፣
294፣ 296) በተመሳሳዪ ቆመን ወደ አድራጊ ወይም አስደራጊ ግስ የሚቀይረው አቆመ
በሚል ሲኾን አቀመ ብሎ በመጽሐፍ እንደሚገኝም ጨምሮ ገልጧል፡፡

ሥርዐተ ሰዋስውን የሚገዛው መጽሐፍ ነው ወይስ ርባ ግስ የሚለው እንዳለ ኾኖ አቀመ


የቆመ አድራጊ ወይም አስደራጊ መኾኑ እስከተረጋገጠ ድረስ በ“አልፋዉ አ” መጻፉ
ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ምክንያቱም በነጠላ ግስ ላይ በተውሳክነት እየገቡ ግሶችን ወደ
ተለያየ አዕማድ ከሚቀይሩ ልማዶች18 ውስጥ አንዱ “አልፋዉ አ” በመኾኑ ነው (ታየ፣
1889፣ 22)፡፡

በምሳሌዉ በተጠቀሱት ግሶች ውስጥ የ“አልፋዉ አ” እና የ“ዐይኑ ዐ” አጠቃቀም ተገቢ


ቢኾንም ነገር ግን የመልክአ ፊደል ልዩነት ያለ በመኾኑ ጥንድ ግሶቹ በመጽሐፈ ሰዋስው
በተገለጸው አግባብም ቢኾን ሞኵሼነትን አያሟሉም፡፡

ምሳሌ ሦስት፦ አሠረ--አደመ፣ አቃጠረ፣ ሰበሰበ፣ ካሥር አንድ ሰጠ

አሰረ--አሰረ (1889፣ 36)

“አልፋዉ አ”፣ “እሳቱ ሰ” እና “ንጉሡ ሠ” ፊደሎች ናቸው በነዚህ ጥንድ ግሶች ውስጥ
የአጠቃቀም ተገቢነታቸው የሚመረመረው፡፡ አሠረ የሚለው ግስ በምሳሌዉ ላይ በ“አልፋዉ
አ” የተጻፈ ቢኾንም ነገር ግን በማስረጃነት በተጠቀሰው ዐረፍተ ነገር ላይ ካልአይ አንቀጹ
“አሥራተ ይዔሥር” በማለት የተጻፈው በ“ዐይኑ ዐ” ነው፡፡

እንዲሁም በመሰ3 እና በመሰ4 ላይ በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች የመጀመሪያዉ አሠረ--


ካሥር አንድ ሰጠ… የሚለው ዐሠረ፤ ኹለተኛዉ አሰረ--አሰረ የሚለው ደግሞ አሠረ
በማለት የተጻፈ ሲኾን “አሥራተ ይዔሥር” ብሎ ከዐሠረ የወጣው ዘር አሥራተ ደግሞ

17
ዐመል ማለት የግስ ዐመልን የሚመለከት ኾኖ እነዚህም አ፣ ዐ፣ ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ ወ፣ የ እና ደጊመ ቃል ሲኾኑ እነዚህ ፊደላት ያሉበት ግስ ቤቱን ሳይለቅ
የፊደላትን ቅረጽ እና መደበኛዉን የአረባብ መንገድ በመለወጥ የሚረባበት መንገድ ነው (ኪዳነ ወልድ፣ 1948፣ 54)፡፡
18
ልማድ ማለት የአዕማድ ግሶች መነሻ ፊደላትን የሚመለከት ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ አ፣ ተ፣ አስ፣ አስተ፣ አን በማለት በአምስት የመደባቸው ሲኾን
(1948፣ 59 ) ታየ ደግሞ ተ፣ አ እና አስተ በማለት በሦስት ነው የመደባቸው (1889፣ 22)፡፡

53
.

በ“አልፋዉ አ” ነው የተጻፈው፡፡ ይህም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት


በኹሉም ዕትሞች ላይ በዘፈቀደ የገቡ መኾኑን ያሳያል፡፡ ለዚህም ነው እነዚህ ፊደላት
የተጻፉበት አግባብ የሚመረመረው፡፡

በመጀመሪያዉ ግስ ከኅትመት ኅትመት ልዩነት የተፈጠረው በመጀመሪያዉ ፊደል


በመኾኑ ግሱ የሚጻፋው በ“አልፋዉ አ” ነው ወይስ በ“ዐይኑ ዐ” የሚለውን ጭብጥ
በመጀመሪያ እንመለከታለን፡፡ ዐሥር የሚለው አኀዝ በዐረብኛ ዐሽር፤ በትግረኛ ዐሳርቴ፤
በትግረ ዐስር የሚል ፍች ነው ያለው (ሌስሎው፣ 1991፣ 74)፡፡ አሠረ--ዐሥር አደረገ ወይም
ካሥር አንድ ሰጠ ተብሎ የሚተረጐም በመኾኑ ዐሥር ወይም ዐሥራት ከዚሁ ግስ
የሚወጡ ቃላት ናቸው፡፡ በመኾኑም እነዚህ ቃላት በ“ዐይኑ ዐ” የተጻፉ በመኾኑ የርባታ
መነሻቸዉ ግስም ዐሠረ እንጅ አሠረ ተብሎ በ“አልፋዉ አ” የማይጻፍ መኾኑን ያሳያል፡፡
አሠር፣ አሥራት ተብሎ ሲጻፍ ፍለጋ፣ አብነት፣ዱካ፣ጥርጊያ ወዘተ ተብሎ እንደሚተረጐም
ከዐረብኛና ከዕብራይስጥ ቃላት ጋር በማነጻጸር ኪዳነ ወልድ (1948፣ 235) የጻፈውም
ይህን የሚያጠናክር ነው፡፡

ሌላው አሰረ--አሰረ የሚለውን ግስ በተመለከተ ከዚህ ግስ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው


ማሰር/ bind፣ tie የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል ሲኾን በትግረኛ አሳረ፤ በትግረ አስረ፣
በዐረብኛ አሰረ፤ በዕብራይስጥ አሳር የሚል ትርጕም ነው ያለው (ሌስሎው፣ 1991፣ 44) ፡፡
ይህም አሰረ--አሰረ የሚለው የግእዝ ግስ ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች ጋር ተመሳሳዪ የግስ
ሥር ያለው መኾኑን ስለሚያሳይ አሰረ--አሰረ የሚለው ግስበ በመጽሐፈ ሰዋስው በ“አልፋዉ
አ” እና በ“እሳቱ ሰ” መዋቀሩ ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡

ከንጽጽሩ መረዳት የሚቻለው በምሳሌዉ የተጠቀሱት ጥንድ ግሶች የመጀመሪያዉ ግስ


ዐሠረ ኹለተኛዉ ደግሞ አሰረ ተብሎ መጻፍ ሲገባዉ በመጀመሪያዎቹ ኹለት ዕትሞች
ዐሠረ የሚለው አሠረ በመጨረሻዎቹ ኹለት ዕትሞች ደግሞ አሰረ በማለት ፈንታ አሠረ
ተብሎ መጻፉ በኹሉም የመጽሐፈ ሰዋስው ቅጅዎች ግሶቹ በተገቢዉ ፊደል ያልተዋቀሩ
መኾኑን ነው፡፡ በመኾኑም የመጀመሪያዉ ግስ ጠብቆ ኹለተኛዉ ደግሞ ላልቶ በመነበብ
የተለየየ ትርጕም ቢኖራቸውም፣ ግሶቹ በምሳሌዉ በተቀመጡበት አግባብም ኾነ
ተስተካከለው ሲዋቀሩ የመልክአ ፊደል ልዩነት ስላላቸው በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና
በመላላት የተለያየ ትርጕም የሚሰጡ ተመኵሳይያን ግሶች ተብለው ሊመደቡ አይችሉም፡፡

54
.

3.2.2 የፊደላት አጠቃቀም ችግር ሳይኖራቸው በትርጕም አንድ የኾኑ ቃላት


ምሳሌ አንድ፦ መሰለ--በምሳሌ ተናገረ

መሰለ--መሰለ (1889፣ 36)

በኹሉም ዕትሞች ጥንድ ግሶቹ በተመሳሳዪ በ“እሳቱ ሰ” የተጻፉ ሲኾን መሰለ--መሰለ


የሚለው ግስ በትግረኛ ማሳላ፤ በሐረሪ ማሳለ በሚል እንደሚጻፍ ነው ሌስሎው (1991፣
366) የገለጸው፡፡ ዲልማንም (1907፣ 64) ጠብቆ የሚነበበው ይኹን ላልቶ የሚነበበው
ስለመኾኑ ባይገልጽም በጥቅሉ መሰለ የሚል የግእዝ ግስ በብራና መጻሕፍት ላይ በ“ንጉሡ
ሠ” ተጽፎ እንዳማይገኝ ገልጧል ፡፡ ይህም የሚያሳየው በመጽሐፈ ሰዋስው የጥንድ ግሶቹ
ሥርዐተ ጽሕፈት ተገቢ መኾኑን ነው ፡፡

የግሶችን የትርጕም ልዩነት ስንመለከት መሰለ--በምሳሌ ተናገረ የሚያመለክተው የአንድን


ነገር ኹናቴ በግልጽ ለማስረዳት ከተገላጩ ጋር ተመሳሳዪነት ያለውን የሌላ ነገር ኹናቴ
በማንሣት ጉዳዩን ለማብራራት ጥረት የሚደረግበት ነው፡፡ ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
የሚባለው ልማዳዊ መርሕም ነገሩ በምሳሌ ሲገለጥ የአገላለጡን ማማር /የነገሩን ግልጽ
መኾን የሚያሳይ ነው፡፡ መሰለ--መሰለ የሚለው ግስ ደግሞ ከነገሮች መመሳሰል የተነሣ
አውቀውም ኾነ ሳያውቁ አንድን ነገር ከሌላ ነገር ጋር ማመሳሰልን የሚመለከት ነው፡፡
ለምሳሌ “ወይመስሎሙ ወልደ ዮሴፍ ውእቱ” (.ሉቃ፤ 3÷ 23) ብሎ ሳያውቁ የመሰላቸውን
ሲያመለክት “ይመስሎ ዝንቱ ወልድ ለጦቢት” (ጦቢት፣ 7÷2) የሚለው ደግሞ እያወቁ
ማመሳሰልን ያመለክታል፡፡ እያወቁ ማመሳሰል የሚለው በምሳሌ ተናገረ ከሚለው ግስ ጋር
ተመሳሳዪነት ያለው ነው፡፡

በመኾኑም ኹለቱም ጥንድ ግሶች ነገሮችን ከማመሳሰል ጋር የተያያዙ በመኾኑ


በመሠረታዊነት የትርጕም ልዩነት በመካከላቸው አለ ለማለት የሚቻል አይደለም፡፡ ይህም
በመጽሐፈ ሰዋስው የተጠቀሱት ጥንድ ግሶች በቅርጽ ተመሳስለው ጠብቀውም ኾነ ላልተው
ሲነበቡ በትርጕም ደረጃ ልዩነት ስለሌላቸው ተመኵሳይያን መባላቸው ተገቢ አለመኾኑን
እንገነዘባለን፡፡

55
.

3.3 በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ቃላት

በዚህ ክፍል ቃላት በአንድ ንባብ በብዙ ነገር የሚፈቱ መኾኑ የሚመረመው በእያንዳንዱ
ምሳሌ የተጠቀሱት ቃላት በአጻጻፍ፣ በንባብ ተመሳሳዪ መኾን አለመኾናቸው እንዲሁም
የሚሰጡት ትርጕም የተለያየ መኾን አለመኾኑን በመመርመር ነው፡፡

3.3.1 በትርጒም ተለያይተው የፊደላት አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ቃላት

ምሳሌ አንድ፦ ሠረቀ--ሠረቀ

ሠረቀ--ተወለደ

ሠረቀ--ወጣ

ሠረቀ--ባተ (ታየ፣ 1889፣ 45)

በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች የተጻፉት በተመሳሳዪ ፊደል ሲኾን ቃላቱ ከተዋቀሩባቸው


ፊደላት መካከል አንዱ ከ“እሳቱ ሰ” ጋር ተመሳሳዪ ድምፅ ያለው የሚመስለው “ንጉሡ
ሠ” በመኾኑ በመጀመሪያ የምንመለከተው ሥርዐተ ጽሕፈቱን ነው፡፡ ሰረቀ/አንድን ነገር
ያለባለቤቱ ፈቃድ መውሰድ/ የሚለው ግስ አቻ የዐረብኛ ትርጕሙ ሰረቀ የሚለው ግስ
ነው (ስቴይንጋስ፣ 1882፣ 379፤ ሙኒር፣ 2007፣ 89)፡፡ ሌስሎውም (1991፣ 514)
በተመሳሳዪ ዐረብኛን ጨምሮ በትግረኛ እና በትግረ ቋንቋዎች ሠረቀ--ሠረቀ በማለት
በምሳሌዪ የተጠቀሰው ግስ በ“እሳቱ ሰ” እንደሚጻፍ ነው የገለጸው፡፡ ከዚህም የምንረዳው
ሠረቀ--ሠረቀ የሚለው የግእዝ እና የአማርኛ ግስ የሚጻፈው በ“እሳቱ ሰ” መኾኑንና
በመጽሐፈ ሰዋስው በ“ንጉሠ ሠ” መጻፉ ተገቢ አለመኾኑን ነው፡፡

በሌላ በኩል ሠረቀ--ወጣ የሚለው ግስ በዐረብኛ ሸረቀ፤ በትግረኛ ሰረቀ እና በትግረ


ሰርቃ በሚል ነው የሚጻፈው (ሌስሎው፣ 1991፣ 534) ፡፡ ዐረብኛ ‘ሸ’ን ትግረኛ እና
ትግረ ቋንቋዎች ደግሞ “እሳቱ ሰ”ን እንደመጠቀማቸው መጠን ትክክለኛው የቱ ነው
የሚለውን መለየት ያስፈልጋል፡፡

ሌስሎው (1991) በግእዝ መዝገበ ቃላት መግቢያዉ ላይ እንደገለጸው ተመሳሳዪ ድምፅ


ያላቸው ከሚመስሉ ፊደላት መካከል “አልፋዉ አ” እና “ዐይኑ ዐ” ልዩነታቸው ተጠብቆ
የሚገኘው በትግረኛ እና በትግረ ቋንቋዎች በቻ ነው፡፡ ሌሎች ተመሳሳዪ ድምፅ

56
.

ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት ግን በኢትዮጵያ የሴም ቋንቋዎች አንዱን ከሌላው ጋር


ያለውን የድምፅ ልዩነት መለየት እንደማይቻልና ይህን የፊደል አጠቃቀም ችግርም
እንደ ዐረብኛ ቋንቋ ያሉ ሌሎች የውጭ የሴም ቋንቋዎችን በመጠቀም መቅረፍ
እንደሚቻል ነው ያብራረው፡፡

ኡሌንዶርፍም (1995፣ 34) የግእዝንና የሌሎች የኢትዮጵያ የሴም ቋንቋዎችን ፊደላት


ባነጻጸረበት ሰንጠረዡ ላይ ትግረኛ እና ትግረ ቋንቋዎች የሚጠቀሙት “ንገሡ ሠ”ን
ሳይኾን “እሳቱ ሰ”ን ብቻ መኾኑን መግለጹ የሌስሎውን አገላለጹ የሚያጠናከር ነው፡፡

በመኾኑም በግእዝ ሥርዐተ ጽሕፈት ውስጥ የ“እሳቱ ሰ”ን እና የ“ንጉሡ ሠ”ን ትክክለኛ
አጠቃቀም ለመለየት ከሀገር ቤት የሴም ቋንቋዎች ይልቅ የዐረብኛ ቋንቋ መኾኑን ነው
ገለጻው የሚያስረዳው፡፡ ከዐረብኛ ቋንቋ አንጻርም ሠረቀ--ወጣ የሚለው ግስ የአጻጻፍ
ችግር የሌለበት መኾኑን ነው ከገለፀው የምንገነዘበው፡፡ በመኾኑም በአማርኛ ሰረቀ
የሚለው ግስ በግእዝ የሚጻፈው በ“እሳቱ ሰ” ሰረቀ በሚል በመኾኑ ሠረቀ--ወጣ ከሚለው
ግስ ጋር በተዋቀረበት የፊደል ዐይነት ልዩነት አለ ማለት ነው፡፡

ሌላው በኹሉም ግሶች መካከል ያለውን የትርጕም አንድነትና ልዩነት ስንመለከት


ሰረቀ--ሰረቀ የሚለው ግስ ሠረቀ--ተወለደ፣ ወጣ፣ ባተ የሚል ትርጕም ካለው ግስ ጋር
ግልፅ የኾነ ልዩነት ያለው ስለመኾኑ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ተወለደ፣
ወጣ፣ ባተ በሚሉት የአማርኛ ግሶች ላይ የጎላ ልዩነት የሌለ ስለመኾኑ በመጽሐፈ
ሰዋስው በማሳያነት የተጠቀሱት አስረጂዎች ራሳቸው ጠቋሚ ናቸው፡፡ ምክንያቱም
ሠረቀ--ወጣ የሚለው ቃል ብዙዉን ጊዜ የሚያመለክተው የፀሐይ ወይም የጨረቃን ብቅ
ማለት ወይም መታየትን ሲኾን የዚህ ማስረጃዉ ደግሞ “ሠረቀ ለነ ፀሐየ ጽድቅ”/
የእውነት ብርሃን ወጣልን የሚለው ጥቅስ ነው (ታየ፣ 1889፣ 45)፡፡ ይህ ዐረፍተ ነገር
ውጫዊ ትርጕሙ የፀሐይ መውጣትን የሚየመለክት ቢኾንም በምስጢር ግን የጌታን
መወለድ ጭምር የሚገልጽ ነው፡፡ የዚህ ማስረጃዉ ደግሞ “ሠረቀ ለነ እምኔኪ ፀሐየ
ጽድቅ” ብሎ ጌታ ከአንቺ ተወለደልን ሲል መገኘቱ ነው ( የዐርብ ውዳሴ ማርያም)፡፡

ሠረቀ--ባተ የሚለው ግስም ወሩ አንድ ብሎ መጀመሩን የሚያመለክትና ወጣ ወይም


ብቅ አለ ከሚለው ግስ ጋር ልዩነት የለውም፡፡ ባተ ሲል የወሩ የመጀመሪያ ቀን

57
.

እንደመኾኑ መጠን “ወወለደት ወልደ ዘበኩራ/ የበኩር ልጇንም ወለደች” (ሉቃስ፣ 2÷7)
ከሚለው ዐረፍተ ነገር ጋርም አብሮ የሚሄድ ነው፡፡

ባጠቃላይ ሰረቀ--ሰረቀ በሚለው ግስና ሠረቀ--ተወለደ፣ ወጣ፣ ባተ በሚሉት ግሶች


መካከል የትርጕም ልዩነት ቢኖረም የቅርጸ ፊደል ልዩነት ያለ በመኾኑ እንዲሁም
ሠረቀ--ተወለደ፣ ወጣ፣ ባተ በሚሉት ግሶች መካከል ደግሞ የትርጕም ልዩነት የሌለ
በመኾኑ በመጽሐፈ ሰዋስው ኹሉም ግሶች ባንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ
በማለት በምሳሌዉ ላይ የተጠቀሱትን ግሶች ሞኵሼዎች ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ
መድረሱ ትክክል አለመኾኑን ሐተታው ያሳያል፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ መልሐ--አጣፈጠ

መልሐ--መዘዘ

መልሐ--ነቀለ

መልሐ--አወጣ

መልሐ--ምግባር ሠራ

መልኀ--አንጸባረቀ (1889፣ 37)

አንጸባረቀ የሚል ትርጕም ካለው ግስ ውጭ ሌሎቹ ግሶች በ“ሐመሩ ሐ” የተጻፉ


ስለመኾኑ ከገጸ ንባቡ መረዳት ይቻላል፡፡ በመሰ3 እና በመሰ4 ደግሞ አጣፈጠ፣ መዘዘ
አና ምግባር ሠራ የሚል ትርጕም ያላቸው ግሶች በተመሳሳዪ በ“ሐመሩ ሐ”፤ ከዚህ
ውጭ ያሉት ግሶች ደግሞ በ“ብዙኃኑ ኀ” ነው የተጻፉት፡፡

የግሶቹን የፊደላት አጠቃቀም ተገቢነት ስንመለከት በኪዳነ ወልድ (1848፤ 592)


መዝገበ ቃላት መልሐ--አጣፈጠ በሚል ጠብቆ የሚነበበው ግስ በዐረብኛ መለሐ እና
በዕብራይስጥ ማላሕ ተብሎ በ“ሐመሩ ሐ” እንደሚጻፍ የተገለጸ ሲኾን መልኀ ተብሎ
በ“ብዙኃኑ ኀ” ሲጻፍ ደግሞ መዘዘ፣ ነቀለ፣ አወጣ በሚል ነው የተተረጐመው፡፡ አጣፈጠ
የሚል ትርጕም ያለው የመጀመሪያዉ ግስ በጨው ማጣፈጥን የሚመለከት ኾኖ ነገር
ግን ባለቅኔዎች መልሐ-- ምግባር ሠራ ብለው እንደሚገሱትና ምክር በማለት ፈንታ
“አልቦሙ ምልሕ ወኢሃይማኖት” ብሎ በመጽሐፍ መገኘቱ የትርጕም ስሕተት እንጅ
ትክክል እንዳልኾነ ኪዳነ ወልድ ሲገልጽ ሌስሎው (1991፣ 343) በበኩሉ ጨው የጥሩ

58
.

ሥራ መገለጫ በመኾኑ መልሐ--ሠራ ብሎ መገኘቱ ጥሩ ሥራ መሥራትን ሊገልጽ


እንደሚችል ሐሳቡን አስቀምጧል፡፡

የኹለቱን ምሁራን ሐሳብ ለማስታረቅ ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው ቢኾንም ቅሉ


ነገር ግን ምግባር ሠራ የሚለው ቃል የመልሐ--አጣፈጠ ተጨማሪ ትርጕም ነው ወይም
ራሱ አጣፈጠ ተብሎ የሚተረጐመው ግስ ነው በማለት መደምደም ይቻላል፡፡
በመኾኑም መልሐ--አጣፈጠ እና መልሐ--ምግባር ሠራ የሚለው ግስ በ“ሐመሩ ሐ”
መጻፉ ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡

መዘዘ፣ ነቀለ፣ አወጣ በማለት የተጠቀሱት የአማርኛ ግሶች የአንድን ጉዳይ ከተጣበቀበት
ነገር መለየትን የሚያመለክት በመኾኑ ግሶቹ በአንዱ የግእዝ ግስ ሥር የሚጠቃለሉ
እንጅ የተለየ ትርጕም አላቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡ አንጸባረቀ በሚል
የተተረጐመው ግስም ወጣ (አወጣ) ተብሎ እንደሚተረጐም በራሱ በመጽሐፈ ሰዋስው
የተገለጸ በመኾኑ መልሐ --ወጣ በሚለው ግስ ውስጥ የሚካተት ነው የሚኾነው፡፡

መልሐ--ወጣ፣ መዘዘ፣ ነቀለ፣ አንጸባረቀ በሚል የሚተረጐም ከኾነ መጻፍ ያለበት


በ“ሐመሩ ሐ” ነው ወይስ በ“ብዙኃኑ ኀ” ነው የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው፡፡ በዐረብኛ
መንቀል/ pull out/ የሚለው ቃል መለኀ በሚል እንደሚተረጐም ነው በኪዳነ ወልድ
(1948፣ 592) እና በሌስሎው (1991፣ 343) መዛግብተ ቃላት የተገለጠው፡፡ ነገር ግን
በትግረኛ ቋንቋ ማልሔ ተብሎ በ“ሐመሩ ሐ” እንደሚጻፍ ሌስሎው በተጨማሪ የገለጸ
ሲኾን ይህም በዐረብኛ እና በትግረኛ ቋንቋዎች የአጻጻፍ ልዩነት ያለ መኾኑን
ያሳያል፡፡ በትግረኛ ቋንቋ ከ‘ሀ’ እና ከ‘ሐ’ በቀር በ“ብዙኃኑ ኀ” ላይ ግልጽ የኾነ ልዩነት
የሌለ በመኾኑ (ኡሌንዶርፍ፣ 1995፣ 34) ገዥነት ያለው የዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡
በመኾኑም ሥርዐተ ጽሕፈቱ መልኀ እንጅ መልሐ አለመኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡

ከላይ ከተሰጠው ሐተታ በመነሣትም በግሶቹ መካከል የትርጕም ልዩነት ሲኖር የፊደል
ዐይነት ልዩነት በመኖሩ ፤ በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ሲመሳሰሉ ደግሞ የትርጕም
ልዩነት ባለመኖሩ ምክንያት በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች ተመኵሳይያን ቃላት
አይደሉም በማለት ማጠቃለል ይቻላል፡፡

ምሳሌ ሦስት፦ ፀልዐ--ጠላ

ፀልዐ--ቈሰለ (1889፣ 48)

59
.

የግሶቹን ገጸ ንባብ እንዲሁ በመመልከት ግሶቹ ተመኵሳይያን ናቸው ልንል እንችላለን


፡፡ ምክንያቱም በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ተመሳስለው የትርጕም ልዩነት ያላቸው
በመኾኑ ነው፡፡ ነገር ግን የትርጕም ልዩነት መኖሩ ባያሻማም ግሶቹ በኹለት የተለያዩ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ እና በመሰ3 እና በመሰ4 ጥንድ
ግሶቹ በተለየ ኹኔታ በ“ጸሎቱ ጸ” የተዋቀሩ በመኾናቸው የፊደላት አጠቃቀማቸዉን
በጥልቀት መመልከቱ ተገቢ ነው፡፡ እነዚህ ጥንድ ግሶች በተጻፉበት ፊደል የተዋቀረ
እና በትርጕምም ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ቃል የሚገኘው በትግረኛ እና በትግረ
ቋንቋዎች በመኾኑ በማነጻጸሪያነት የምንጠቀመው እነዚህን ቋንቋዎች ነው፡፡

ፀልዐ--ጠላ የሚለው ግስ በትግረኛ ጻልኤ፣ በትግረ ጻልአ፤ ፀልዐ--ቈሰለ የሚለው ግስ


ደግሞ በትግረኛ እና በትግረ ጻልዐ የሚል አቻ ትርጕም ያለው ስለመኾኑ ከሌስሎው
(1991፣ 554) የግእዝ መዝገበ ቃላት ላይ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ ላይ የምንረዳው ትግረኛ
እና ትግረ ቋንቋዎች ለኹለቱም ግሶች የተጠቀሙት “ፀሐዩ ፀ” ን ሳይኾን “ጸሎቱ ጸ” ን
እንዲሁም ጠላ በሚል ለተተረጐመው ግስ “ዐይኑ ዐ” ን ሳይኾን “አልፋዉ አ” ን
መኾኑን እንገነዘባለን፡፡ ይህም በምሳሌው የተጠቀሱት ግሶች በተገቢዉ ፊደል
ያልተዋቀሩና በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነትም አንድነት የሌላቸው መኾኑን ያሳያል፡፡

ነገር ግን ኪዳነ ወልድ (1948፣ 757) ጸልአ እና ጸልዐ አንድ ዘር እንደኾኑ እና ‘ዐ’ በ‘አ’
መለወጡ የቁስሉን ዐይን ወይም አፍ ለማመልከት ነው በማለት ጸልአ ብሎም ቈሰለ
ተብሎ እንደሚተረጐም ነው የገለጸው፡፡ ኾኖም ግን ጸልዐ--ቈሰለ ከሚለው ግስ ለወጣው
ጸልዕ--ቁስል/ እባጭ ለሚለው ዘር የተጠቀመው ሰልዐት የሚለው አቻ የዐረብኛ ቃል
የተጻፈው በ“ዐይኑ ዐ” መኾኑ በራሱ ሲታይ የኪዳነ ወልድ አመክንዮ ትክክል
አለመኾኑን ነው የሚያሳየው፡፡ በመኾኑም ጸልዐ--አቄመ ተብሎ ሲተረጐም የቁስሉ
አለመዳንን የሚገልጽ እንጅ ሰው በሰው ላይ ያለውን ጥላቻ እንደማይመለከት ኹሉ
ጸልአ--ጠላ ሲልም ባንድ ነገር ላይ ያለን ጥላቻ የሚያመለክት በመኾኑ ጸልአ--ቈሰለ
ብሎ መተርጐም ተገቢነት የለው አይደለም፡፡

ባጠቃላይ በምሳሌው በተጠቀሱት ግሶች መካከል የትርጕም ልዩነት የመጣው ግሶቹ


ከተዋቀሩበት ፊደል ልዩነት እንጅ በምሳሌው በተገለጸው አግባብ ተመሳሳዪ የፊደል
ውቅር ኖሯቸው በትርጕም ስለሚለያዩ ባለመኾኑ ሞኵሼነትን አያሟሉም፡፡

60
.

3.3.2 የፊደላት አጠቃቀም ችግር ሳይኖራቸው በትርጕም አንድ የኾኑ ቃላት

ምሳሌ አንድ፦ ቀደመ--ቀደመ

ቀደመ--ጀመረ (1889፣ 41)

በዚህ ምሳሌ ግሶቹ የተዋቀሩት ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት ባለመኾኑ
በፊደል አጠቃቀም ረገድ የሚነሣ ጥያቄ የለም፡፡ ነገር ግን እነዚህ ግሶች ተመኵሳይያን
ናቸው በማለት በመጽሐፈ ሰዋስው የተጠቀሱት በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር
የሚፈቱ ግሶች በሚል በመኾኑ በመካከላቸው ያለውን የትርጕም አንድነትና ልዩነት
እንመረምራለን፡፡ ለዚህ መነሻ የሚኾነው ደግሞ በመጽሐፈ ሰዋስው የግሶቹን ትርጕም
መለያየት ለማሳየት የተጠቀሱት አስረጂዎች ናቸው፡፡

ቀደመ--ቀደመ ለሚለው ግስ የተጠቀሰው ማስረጃ “ሑሩ ቅድሜየ ቅድሙኒ አነኒ


እተልዎክሙ/ አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ እነሆም (እኔም) እከተላችኋለሁ” (፪ (፩) ሳሙ.
25÷19) የሚል ሲኾን ቀደመ--ጀመረ ለሚለው ግስ ደግሞ “ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ
እግዚአብሔር/ የጥበብ መጀመሪያ (ዋ) እግዚአብሔርን መፍራት ነው” (መዝ. 111
(110) ÷10) የሚል ነው፡፡ አስቀድማችኹ ኺዱ ሲል መጀመሪያ መኼድን ፤ የጥበብ
መጀመሪያዋ ሲል ደግሞ የጥበብ ኹሉ ቀዳሚ ነገርን የሚያመለክት በመኾኑ በግሶቹ
መካከል መሠረታዊ የትርጕም ልዩነት የለም ፡፡

በተለይ “በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ”/ በመጀመሪያ እግዚአብሔር


ሰማይንና ምድርን ፈጠረ (ዘፍ.1÷1) በሚለው ጥቅስ ውስጥ በመጀመሪያ የሚለው ቃል
አስቀድሞ በሚል ቃል ቢተካ ለስሜት የሚጎረብጥ አይደለም፡፡ ይህም ኹለቱ የአማርኛ
ቃላት ምን ያህል ተመሳሳዪ ስሜትን አንደሚገልጹ ያሳያል፡፡ በምሳሌዉ የተጠቀሱት
ግሶችም አንዱ ከሌላዉ የተለየ ትርጕም/ ፍች የሌላዉ በመኾኑ በመጽሐፈ ሰዋስው
በተገለጸው አግባብ ግሶቹ ሞኵሼነትን የሚያሟሉ አይደሉም፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ቅዳሕ--ቅዳ

ቅዳሕ--ክፍል (1889፣ 53)

61
.

ጥንድ ቃላቱ ተመሳሳዪ ቅርጸ ፊደል ያላቸው እንደመኾኑ መጠን የቃላቱን


ተመኵሳይያን መኾን አለመኾን መለየት የሚቻለው ቃላቱ የተገኙበትን ግስና
የሚሰጡትን ትርጕም በመመርመር ነው፡፡

ኹለቱም ቃላት ቀድሐ--ቀዳ ከሚል ነጠላ ግስ የተገኙ ናቸው፡፡ ቅዳሕ--ቅዳ የሚለው


ትእዛዝ አንቀጽ ሲኾን ቅዳሕ--ክፍል የሚለው ደግሞ ግሱን መስሎ የወጣ ዘመድ ዘር
ነው፡፡ ቀድሐ--ቀዳ የሚለው ግስ የፈሳሽ ነገር መቅዳትን/ መጥለቅን፤ የአንድን
መጽሐፍ ቃል ወይም ይዘት መገልበጥን ኹሉ እንደሚያካትት በኪዳነ ወልድ (1948፣
782) መዝገበ ቃላት ላይ ተመልክቷል፡፡ በመጽሐፈ ሰዋስው ቅዳሕ--ክፍል መኾኑን
ለማሳያነት የተጠቀሰው ማስረጃ “ትትነበብ ዛቲ ቅዳሕ እመዝሙር” (ግን. 53) ወደ
አማርኛ ሲመለስ ከመዝሙር ያችኛዋ ክፍል ትነበባለች የሚል ሲኾን ይህም ቅዳሕ
የሚለው ቃል የሚነገረውን/ የሚነበበውን የተወሰነውን የመጽሐፍ ክፍል የሚያመለክት
ነው፡፡

በመኾኑም ቅዳሕ የሚለው ዘር ቀድሐ--ቀዳ ከሚለው ግስ የተገኘና በገባበት ዐውዳዊ


ፍች መሠረት የሚቀደውን/ የሚገለበጠውን የመጽሐፍ ክፍል ከማመልከት ባለፈ ራሱን
ችሎ ከሌላ ግስ የተገኘ ዘር አለመኾኑን ነው የምነገነዘበው፡፡ በትርጕም ደረጃም ዋናዉ
ግስ ቀዳ በሚል የያዘውን የአማርኛ ትርጕም ያለቀቀ በመኾኑ ቅዳሕ--ቅዳ ጋር በንባብ
አንድ ኾኖ የተለየ ትርጕም የሚሰጥ ቃል ሊባል አይችልም፡፡ ይህ ከኾነ ደግሞ ከአንድ
ግስ በርባታ የተገኙ ቃላት በርባታዉ ውስጥ የተለያየ ሙያ ከሚኖራቸው በቀር የተለየ
ትርጕም ስለማይኖራቸው በአጻጻፍ መመሳሰላቸው ብቻ ተመኵሳይያን ሊያስብላቸው
እንደማይችል ነው የምንገነዘበው፡፡

3.3.3 ከፊደል አጠቃቀምና ከትርጒም አንጻር

ምሳሌ አንድ፦ ኀፀነ--አሳደገ

ሐፀነ--መገበ

ሐፀነ--ጠወረ (1889፣ 46)

በመጽሐፈ ሰዋስው እነዚህ ግሶች በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ በማለት
የተመደቡ በመኾኑ በመጀመሪያ የምናየው የንባብ አንድነታቸውን ነው፡፡ ከምሳሌዉ ገጸ

62
.

ንባብ እንደሚታየው ታየ አሳደገ የሚል ትርጕም ላለው ቀዳማይ የግእዝ ግስ


የተጠቀመው “ብዙኃኑ ኀ” ን ሲኾን ነገር ግን “ማይ የሐፅኖ ለዕፅ” በሚለው ማስረጃ
ላይ “ሐመሩ ሐ” ን ነው የተጠቀመው፡፡ ቀሪዎቹ ኹለት ግሶችም በ“ሐመሩ ሐ” ነው
የተዋቀሩት፡፡ መሰ3 እና መሰ4 ደግሞ ለኹሉም ግሶች የተጠቀሙት “ሐመሩ ሐ” ን
ነው፡፡ ይህም በኹሉም ዕትሞች በፊደላት አጠቃቀም ረገድ ችግር ያለ መኾኑን
ያሰያል፡፡ በመኾኑም የፊደላት አጠቃቀም ተገቢነትን ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች ጋር
በማነጻጸር እንመረምራለን፡፡

በዐረብኛ ቋንቋ ማሳደግ/ bring up ሐፀነ ፤ ጡት/ breast ሒፅን፤ በዕበራይስጥ ደግሞ
ደረት/ bosom ሔጻን፤ ልጅ/ boy, child/ በትግረኛ ሕጽኒ፣ በትግረ ሕጽን ወይም
ሕፃን--ሕጻን ተብሎ እንደሚተረጐም በሌስሎው (1991፣ 226) የግእዝ መዝገበ ቃላት
ላይ ተመላክቷል፡፡

ኪዳነ ወልድም (1948፣ 458) በተመሳሳዪ ሕፅን--መታቀፊያ፣ ጭን፣ ደረት ለሚለው


ቃል በዐረብኛ ሒፅን፤ በዕብራይሰጥ ሖጼን የሚል ትርጕም ነው የሰጠው፡፡ ይህም
የሚያሳየው ለማነጻጸሪያነት የተጠቀሱት ሌሎች የሴም ቋንቋዎች አሳደገ እና ይህ
መሠረት አድርገው ለሚወጡት ቃላት ኹሉ “ሐመሩ ሐ” ን የተጠቀሙ መኾኑን ነው፡፡
ነገር ግን “ጸሎቱ ጸ” ን እና “ፀሐዩ ፀ” ን በተመለከተ በዐረብኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች
መካከል ስምምነት የለም፡፡ በዚህ ጽሑፍ አዘጋጂ እምነት ትግረኛ እና ትግረ ቋንቋዎች
እነዚህን በጥርሰ የሚነገሩ ፊደላትን ቀላቅለው “ጸሎቱ ጸ” ን ስለሚጠቀሙ(ሌስሎው፣
1991) ፤ የዕብራይስጥ ቋንቋን በተመለከተ ደግሞ የግእዝ ቋንቋ ከዕብራይስጥ ቋንቋ
ይልቅ ከዐረብኛ ቋንቋ ጋር ካለው የበለጠ ታሪካዊ ግንኙነት አንጻር ለተያዘው ጉዳይ
ብያኔ ለመስጠት ተመራጪ የኾነው የዐረብኛ ቋንቋ ነው፡፡ይህን በሚያጠናክር መልኩ
ያሬድም (2000፤ 174) በተመሳሳዪ ሐፀነ--አሳደገ በማለት የተጠቀመው “ሐመሩ ሐ” ን
እና “ፀሐዩ ፀ” ን ነው፡፡

በመኾኑም አሳደገ የሚል ትርጕም ያለው የግእዝ ግስ በምሳሌዉ በተጠቀሰው አግባብ


ኀፀነ በሚል ሳይኾን ሐፀነ በሚል መከተብ እንዳለበት ነው ከሐተታዉ የምንገነዘበው፡፡

በግሶቹ መካከል የትርጕም አንድነትንና ልዩነትን በተመለከተ አሳደገ ሲል መመገብ


እና መነከባከብን አካቶ የሚይዝ በመኾኑ አንዱ ግስ ከሌላዉ የተለየ ትርጕም አለው

63
.

ለማለት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ወጥቶ ወርዶ ሳይመገቡና ሳይንከባከቡ ማሳደግና


ለቁም ነገር ማድረስ አይታሰብምና ነው፡፡ ሐጸነ የሚለው ግስም እንደ ጉዳዩ ዐይነትና
እንደ ተርጓሚዉ ስሜት በተለያየ ዐውድ ሊተረጐም ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሐፀነ--ጠወረ
ለሚለው ግስ “የሐፅኖ ለሢበትኪ”/ በእርጅናሺ ይጠውርሻል (ሩት. 4÷15) በማለት
በመጽሐፈ ሰዋስው የጠቀሰው ማስረጃ ይጠውርሻል በማለት ምትክ ይመግብሻል
በማለት በኢመቅማ ለኢኦተቤ በ2000 ዓ.ም ባሳተመው መጽሐፍ ቅዱስ መተርጐሙ
የዚህ ማሳያ ነው፡፡

በመኾኑም በመጽሐፈ ሰዋስው በምሳሌዉ የተጠቀሱት ግሶች የተዋቀሩበት


የመጀመሪያዉ ፊደል ተመሳሳዪ ሳይኾን፤ ከላይ በተሰጠው ትንታኔ መሠረት በመልክአ
ፊደል ተመሳሳዪነት ቢኖርም ነገር ግን በግሶቹ መካከል የትርጕም ልዩነት የሌለ
በመኾኑ ግሶቹ በመጽሐፈ ሰዋስው በተገለጸው አግባብ ተመኵሳይያን ሊባሉ
አይቻልም፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ሰምአ--ሰማ

ሰምአ--መሰከረ (1889፣ 47)

መጽሐፈ ሰዋስው እነዚህን ጥንድ ግሶች ተመኵሳይያን ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ


የደረሰው የግእዝ ግሶቹ ተመሳሳዪ ቅርጸ ፊደል እና ንባብ ኖሯቸው በትርጕም የተለያዩ
ናቸው በሚል ነው፡፡ ነገር ግን መሰ3 እና መሰ4 ከመጀመሪያዎቹ ኹለት ዕትሞች
በተለየ መልኩ ሰምዐ በሚል “ዐይኑ ዐ” ን የተጠቀሙ በመኾኑ ትክክለኛዉን የፊደላት
አጠቃቀም ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች አንጻር ግሶቹ የተጻፉበትን ፊደል በመመርመር
መለየት አስፈላጊ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ ጥያቄዎችና ባሕሎች በተሰኘው መጽሐፍ (ሀብተ ማርያም፣ 1986፣


401) እና በአማርኛ- እንግሊዝኛ- ዐረብኛ መዝገበ ቃላት (ሙኒር፣ 2007፣87) እንደ
ቅደም ተከተሉ ሰማ የሚለው የአማርኛ ግስ በትግረኛ ሰምዓ፤ በዐረብኛ ሰሚዐ በማለት
በ“ዐይኑ ዐ” የተጻፈ ሲኾን ሌስሎውም (1991፣ 501 እና 502) በተመሳሳዪ ይህንኑ ነው
ያረጋገጠው፡፡ በሌሎች መጻሕፍትም ሰማ የሚል ትርጕም ላለው የግእዝ ግስ
የሚጠቀሙት “ዐይኑ ዐ” ን ስለመኾኑ የሚከተሉትን ማሳያዎች ማንሣት
ይቻላል፡፡ለምሳሌ በ1984ዓ.ም በታተመው መዝሙረ ዳዊት “ይሰምዖሙ ጸሎቶሙ

64
.

ወያድኅኖሙ”/ ልመናቸዉንም ይሰማቸዋል ያድናቸዋልም (መዝ. 144÷19)፤


በመጽሐፈ ምስጢር “ኢይነግር ዘእማኀቤሁ ዘሰምዐ ዳእሙ ይነግር”/ ከራሱ አንቀቶ
አይናገርም የሰማውን ይናገራል እንጅ (ጊዮርጊስ፣ 2001፣ 7) ፤ በሊጉ በ2009 ዓ. ም
በታተመው የግእዝ ሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ “ወሶበ ሰምዑ ሐዋርያት…”/ ሐዋርያት
በሰሙ ጊዜ…/ (የሐዋ. 8÷14) የሚሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመኾኑም በግእዝ ቋንቋ
ሰምዐ--ሰማ እንጅ ሰምአ--ሰማ ተብሎ የማይጻፍ መኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡

መሰከረ እና ሰማ ያላቸውን የትርጕም ልዩነት በተመለከተ ኪዳነ ወልድ (1948፣ 871)


ሰምዐ--ሰማ ከሚለው ትርጕሙ በተጨማሪ መሰከረ የሚል ትርጕም ያለው ሰለመኾኑ
በመዝገበ ቃላቱ ላይ ገልጧል፡፡ ይህም የሚያሳየው መሰከረ የሚለው ግስ ሰምዐ ከሚለው
የግእዝ ግስ የተገኘ ተጨማሪ ትርጕም እንጅ ራሱን የቻለ ግስ አለመኾኑን ነው፡፡
ይህም ኹለትና ከዚያ በላይ ሙያዎች ያሉትን አንድ ሰው በተለያየ ስም እንደመጥራት
ማለት ነው፡፡ በመኾኑም በምሳሌዉ የተጠቀሱት ኹለቱ ግሾች በተገቢዉ ፊደል
ካለመጻፋቸውም በላይ አንዱ ግስ የሌላው ተጨማሪ ትርጕም ኾኖ እያለ በተመሳሳዪ
ንባብ የተለያየ ትርጕም ያላቸው ግሶቸ እንደኾኑ ተቆጥሮ በመጽሐፈ ሰዋስው
ተመኵሳይያን መባላቸው ስሕተት መኾኑን ነው የምንገነዘበው፡፡

3.4 ባላቸው የምስጢርና የአመጣጥ ልዩነት ተመኵሳይያን የተባሉ ቃላት

በዚህ ክፍል በሥዐርተ ንባባቸው በተለይ ተነሺ፣ወዳቂ እና ሰያፍ የኾኑ ቃላት


በተዋቀሩበት ፊደላት ተመሳስለው በፍችና በአመጣጥ በመለያየታቸው ምክንያት
ተመኵሳይያን የተባሉ ቃላት የሚመረመሩበት ክፍል ነው፡፡ በውስጡም ኹለት
ምሳሌዎችን በማንሣት ነው ምዕራፉ የሚቋጨው፡፡

ምሳሌ አንድ፦ አእመራ--አወቃት

አእመራ--አወቁ (1889፣ 51)

የኹለቱን ጥንድ ቃላት ሞኵሼነት ከማየታችን በፊት አእመረ የሚለው ግስ አድራጊ


ወይስ አስደራጊ ግስ በሚለው ላይ ያለውን የተለያየ የሊቃውንት እይታ ለመዳሰስ ያክል
በመጽሐፈ ሰዋስው አእመረ የሚለው ግስ ከስምንቱ የግስ አርእስቶች ውስጥ አንዱ
ሲኾን በውስጡም ስምንት ሠራዊት እንዳሉት ነው የተገለጸው (ታየ፣ 1889፤ 6፣ 9) ፡፡

65
.

በሌላ በኩል ኪዳነ ወልድ (1948፤ 228፣ 229) ዐወቀ ለሚለው የአማርኛ ግስ
ትክክለኛዉ የግእዝ ግስ አመረ (መ ሳይጠብቅ) እንደኾነና አእመረ--አወቀ ብሎ
አስደራጊዉ በአድራጊነት መተርጎሙ ስሕተት እንደኾነ ነው የሚገልጸው፡፡ ለዚህ
ምክንያቱ ደግሞ የሴም ቋንቋዎች የጋራ ባሕሪ የግስ ሥር/ ቅንጣጢት ሦስት መኾኑ
እና በትግረ ቋንቋም ዐወቀ ለማለት አመረ ተብሎ የሚገኝ መኾኑ ነው፡፡ ሌስሎውም
(1991፤ 25) የኪዳነ ወልድ ሐሳብን በሚያጠናክር መልኩ ማዎቅ፣ መገንዘብ/ know,
understand/ የሚለው ግስ በትግረ ኣማረ ተብሎ እንደሚጻፍ በመዝገበ ቃላቱ ያመለከተ
ቢኾንም ነገር ግን ዐወቀ ለማለት የተጠቀመው የግእዝ ግስ አእመረ የሚለውን ግስ
ነው፡፡

ባንድ በኩል የኪዳነ ወልድ ሐሳብ ተገቢነት ያለው ቢመስልም በሌላ በኩል እንደ
አጥረየ፣ ተንበለ፣ ኖለወ/ ነውለወ የመሳሰሉ ባለአራት እግር ግሶች መኖራቸው ሲታይ
አእመረም ከዚሁ የሚመደብ እንጅ የአስደራጊ ግስ መነሻ በኾነው ‘አ’ ስለተነሣ ብቻ
አስደራጊ ግስ ነው መባሉ ተገቢ አይደለም የሚል መከራከሪያም ሊያስነሣ ይችላል፡፡

ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ጥናት የሚያስፈልገው መኾኑ እንደተጠበቀ የዚህ ጥናት ዐላማ


ሞኵሼነት መኖር አለመኖሩን መለየት ላይ በመኾኑ አጥኚዉ የተጠቀመው ግሶቹ
በመጽሐፈ ሰዋስው የተሰጣቸውን ትርጕም መሠረት በማድረግ ነው፡፡

ወደ ዋናዉ ጉዳይ ስንመለስ አእመራ-አወቃት የሚለው ግስ ሩቁ ወንድ /ሦስተኛ መደብ


ወንድ ነጠላ ቁጥር/ ሩቋን ሴት/ ሦስተኛ መደብ ሴት ነጠላ ቁጥርን/ ማዎቁን
የሚያመለክት ሲኾን ወዳቂ ግስ ነው፡፡ አእመራ--አወቁ የሚለው ግስ ሩቆቹ ሴቶች
ማዎቃቸውን የሚመለከት እና ሲነበብም ተነሥቶ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሰዋስው ኹለቱ
ጥንድ ግሶች ተመኵሳይያን የተባሉት በፊደልና በንባብ ተመሳስለው ባመጣጥና
በምስጢር የተለያዩ ናቸው በማለት ነው፡፡ ነገር ግን ኹለቱም ግሶች በቅርጸ ፊደል
ተመሳሳዪ ቢኾኑም አእመራ--አወቃት የሚለው ግስ ወዳቂ ንባብ በመኾኑና አእመራ--
አወቁ የሚለው ግስ ደግሞ ተነሺ ንባብ በመኾናቸው ተመሳሳዪ ንባብ አላቸው ለማለት
አይቻልም፡፡

ሌላው የግሶቹን አመጣጥና ምስጢር በሚመለከት የኹለቱም ግሶች የርባታ መነሻቸዉ


አእመረ በመኾኑ እና ትርጕማቸዉም መነሻ ግሱን በመከተል የግሱን ባለቤት ፆታና

66
.

ቁጥር የሚያሳይ እንጅ በግሶቹ መካከል የምስጢር ልዩነት ያለ ስለመኾኑ አያሳይም፡፡


በመኾኑም ለተመኵሳይያን ከተሰጠው ትርጕም አንጻር ጥንዶቹ ግሶች ሞኵሼነትን
የሚያሟሉ አይደሉም፡፡

ምሳሌ ኹለት፦ ኢይመውት--አልሞትም

ኢይመውት--አይሞትም (1889፣ 51)

እነዚህ ጥንድ ቃላት ተመኵሳይያን የተባሉት በንባብና በፊደል አንድ ኾነው


በአመጣጥና በምስጢር የተለያዩ ናቸው በሚል ነው፡፡ የመጀመሪያዉ ግስ አንደኛ
መደብ ነጠላ ቁጥርን ኹለተኛዉ ደግሞ ሦስተኛ መደብ ነጠላ ቁጥር ወንድ ጾታን
የሚያመለክቱ ትንቢታዊ የኾኑ ግሶች በመኾናቸው በሰያፍ ሥርዐተ ንባብ የሚነበቡና
በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነትም ተመሳሳዮች ናቸው፡፡ ነገር ግን አመጣጣቸዉንና
ምስጢራቸዉን ስንመለከት ኹለቱም ግሶች ሞተ ከሚል ነጠላ ግስ ከአንድ የግስ ሥር
የተገኙ ናቸው፡፡ ትርጕማቸዉም የግሱን ባለቤት ከማመላከት ውጭ አለመሞትን ነው
የሚገልጹት፡፡ ይህም የትርጕም ልዩነት ያለመኖሩን ያሳያል፡፡ በመኾኑም ጥንድ ግሶቹ
የሚለያዩት የድርጊቱን ገባሪ/ ባለቤት በማመላከት በኩል እንጅ መነሻቸዉና
ትርጕማቸዉ ተመሳሳዪ በመኾኑ በፊደልና በንባብ ተመሳስለው በአመጣጥና በምስጢር
የተለያዩ ተመኵሳይያን ሊባሉ የሚችሉበት አግባብ የለም፡፡

67
.

ምዕራፍ አራት

4. ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና የይኹንታ ሐሳብ

4. 1 ማጠቃለያ

የዚህ ጥናት ዋና ዐላማ በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን አግባብ


መመርመር ነው፡፡ ጥናቱም ተመኵሳይያን ማለት ምን ማለት ነው ? በመጽሐፈ ሰዋስው
ተመኵሳይያን ቃላት እነዴት ነው የተገለጹት? የተገለጹበት መንገድስ ከሌሎች ሊቃውንት
እይታና ከተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች አንጻር እንዴት ይታያል? ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው
በሚመስሉ ፊደላት በተዋቀሩ ቃላት መካከል ሞኵሼነት አለ? የፊደል ሞኵሼነት አለ?
የለም? የሚሉ ጥያቄዎችን ይዞ ተነሥቷል፡፡

መረጃዎችም ሰነድ በመፈተሽ የተሰበሰቡ ሲኾን ተመኵሳይያን ማለት ምን ማለት ነው


ከሚለው ጀምሮ በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን የተባሉ የቃላት ዐይነቶችና ክፍሎች
እንዲሁም ተመኲሳይያንን በየፈርጁ ለመመደብ ሥራ ላይ የዋሉ የቃላት ሥርዐተ ንባብ
(ጥብቀት፣ ወዳቂና ተነሺ፣ ተጣይና ሰያፍ)፤ የአንድ ቃል የተለያየ ትርጕም መስጠት
የሚሉት ጉዳዮች በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ በዝርዝር ተብራርተዋል፡፡

በርእሰ ጉዳዩ እና ከርእሰ ጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ
ከተብራሩ በኋላ በምዕራፍ ሦስት በተሰበሰቡት መረጃዎች መነሻነት በርእሰ ጉዳዩ ላይ
ንጽጽራዊ ትንተና ተደርጎ ለተነሡት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡ ለማነጻጸሪያነት
አጥኚዉ የተጠቀማቸዉ ተዛማጂ የሴም ቋንቋዎች ዋና ዋናዎቹ የዐረብኛ፣ የዕብራይስጥ፣
የትግረኛና የትግረ ቋንቋዎች ሲኾኑ ብዙዎቹ ማስረጃዎች የተወሰዱት ከኪዳነ ወልድ
መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት (1948) እና ከሌስሎው ንጽጽራዊ የግእዝ መዝገበ
ቃላት/ Comparative Dictionary of Geez (1991) ነው፡፡ የያሬድ መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው
(2000) እና የግእዙ ሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስም (2009) እንዳስፈለጊነታቸው
ለማነጻጸሪያነት ተጠቅሰዋል፡፡

በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት በአራት መደብ ተለይተው የተብራሩ ሲኾን በዚህ
ጥናትም ተመኵሳይያን የተብራሩት በተመሳሳዪ በአራት ክፍሎች ተመድበው ነው፡፡

68
.

የመጀመሪያዉ በምስጢር የማይገናኙ አድራጊ፣ አስደራጊ እና ተደራጊ የመሰሉ ግሶችን


የሚመለከት ሲኾን መጽሐፈ ሰዋስው በአዕማድ ግሶች ላይ ሞኵሼነትን ለማሳያት ጥረት
ያደረገው ግሶች በምስጢር (በትርጕም) የተለያዩ ኾነው እያለ በቅርጽ ደረጃ ግን የአንዱ
ግስ አስደራጊ ወይም ተደራጊ ከሌላው አድራጊ ግስ ጋር ተመሳሳዪነት አለ በሚል ነው፡፡
በዚህ ጽሑፍም የመጀመሪያዎቹን ተመኵሳይያን ቃላት አድራጊና አስደራጊ የመሰሉ ግሶች
በአንድ፤ አድራጊና ተደራጊ የመሰሉ ግሶችን በአንድ አድርጎ በመክፈል ግሶቹ
ከተዋቀሩበት የፊደላት ዐይነት እና ከሚሰጡት ትርጕም አንጻር ተመርምረዋል፡፡

አድራጊና አስደራጊ ግሶችን በተመለከተ ትርጕማቸዉ የተለያየ ነገር ግን የፊደላት


አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ሦስት ጥንድ ግሶች፤ የፊደል አጠቃቀም ችግር የሌለባቸው
ነገር ግን በትርጕም ተመሳሳዪ የኾኑ ኹለት ጥንድ ግሶች በድምሩ አምስት ጥንድ ግሶች
እንዲሁም ከአድራጊና ተደራጊ ግሶች ውስጥ የፊደል አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ሦስት ፤
በትርጕም ተመሳሳዪነት ያላቸው ኹለት በድምሩ አምስት ጥንድ ግሶች በማሳያነት
ተጠቅሰው በዝርዝር ተመርምረዋል፡፡

የምርምሩ ውጤትም የፊደላት አጠቃቀምን በተመለከተ ታየ በተለምዶ ሞኵሼ እየተባሉ


የሚጠሩ ቃላትን በዘፈቀደ የሚጠቀም መኾኑን ያሳያል፡፡ የዚህ ማስረጃዉ ደግሞ አንድ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የሚዋቀርን ግስ በተገቢዉ ፊደል ካለመጻፉም
በላይ ይኸው ግስ ሌላ ቦታ ላይ ሲጠቀስ እንዲሁም ለግሱ በማስረጃነት ከሚጠቀሰው ዐረፍተ
ነገር ውስጥ ግሱ ወደ ሌላ የቃል ክፍል ሲቀየር በሌላ ተመሳሳዪ ድምፅ ባለው ፊደል
ተጽፎ መገኘቱ ነው፡፡ይህም ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት አንድ ዐይነት
ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ ታየ የደረሰ ይመስላል፡፡ ከመጀመሪያዉ የመጽሐፈ ሰዋስው
ዕትም በኋላ በተለያዩ ምሁራን የታታሙ የዚሁ የመጽሐፈ ሰዋስው ቅጅዎች በተመሳሳዪ
ዘፈቀዳዊ የኾነ የፊደል አጠቃቀም ነው የተከተሉት፡፡

በዘርፉ ምሁራንም በጽሑፍም ኾነ በቃል ድርሰቶቻቸው ተመሳሳዪ የኾነ የፊደል


አጠቃቀም ነው የተከተሉት፡፡ ይህም መጀመሪያ የነበረውን ችግር ከማረም ይልቅ ጉዳዩን
ይበልጥ ውስብስብ ያደረገው መኾኑን ያሳያል ፡፡

ቃላት ካላቸው ትርጕም አንጻር ደግሞ በጥናቱ የተረጋገጠው አድራጊና አስደራጊ ወይም
አድራጊና ተደራጊ መስለው ጥንድ ኾነው የተቀመጡት ግሶች ከአንድ የግስ ቅንጣጢት

69
.

የተገኙና መሠረታዊ የትርጕም ልዩነት ሳይኖራቸው እንደገቡበት ዐውድ ትርጕም


ስለተሰጣቸው ብቻ ከተለያየ የግስ ሥር እንደተገኙ ተቆጥረው ተመኵሳይያን የተባሉ
መኾኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ እንዲሁም ጥንድ ግሶቹ የትርጕም ልዩነት አለመኖርና
የፊደላት አጠቃቀም ችግር እንዳለ ኾኖ በአድራጊነት የተጠቀሰው ግስ ወደ ተደራጊነት
ሲቀየር ይመስለዋል ከተባለው ኹለተኛዉ ጥንድ ግስ ጋር በቅርጽ ደረጃም ተመሳሳዪነት
የሌላው ግስ ኹሉ እንዳለና እነዚህም ግሶች ተመኵሳይያን እንደተባሉ ነው በምርምሩ
የተገለጠው፡፡

በኹለተኛ ደረጃ በዝርዝር ሐተታ የተሰጠበት በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና በመላላት


ኹለት ፍች የሚሰጡ ቃላት ሲኾን በፊደል አጠቃቀም ረገድ ችግር ያለባቸው ሦስት ጥንድ
ግሶች፤ በተገቢው ፊደል የተከተበ እና የተለየ ትርጕም የሌለው ደግሞ አንድ ጥንድ ግስ
በድምሩ አራት ጥንድ ግሶች ተመርምረዋል፡፡

በምርመረውም የፊደል አጠቀቀም ችግር የሌለበት አንድ ጥንድ ግስ ጠብቆም ኾነ ላልቶ


ሲነበብ በተለያየ ዐውድ ከመግባቱ በዘለለ የተለየ ትርጕም እንደሌለ ነገር ግን ትርጕሙ
የተለየ እንደኾነ ተቆጥሮ ጠብቆና ላልቶ ሲነበብ አንዱ ከሌላው ጋር ሞኵሼ እንደተባለ
ጥናቱ አሳይቷል፡፡ አንደኛዉ ጥንድ ግስ ደግሞ በፊደል አጠቃቀም በኩል ችግር
ባይኖርበትም ኹለቱም ግሶች በተለያየ ፊደል ተዋቅረው እያለ የፊደላቱ መለያየት ግንዛቤ
ውስጥ ሳይገባ ግሶቹ ተመኵሳይያን ተብለዋል፡፡ በቀሪዎቹ ኹለት ጥንድ ግሶች ደግሞ
ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት ያለ ቦታቸዉ አንዱ በሌላዉ ቦታ በዘፈቀደ
በመጻፉ ምክንያት በንባብም ኾነ በቅርጽ ተመሳሳዪ እንዲኾኑ ተደርገው ሞኵሼነትን
እንዲያሟሉ ተደርጓል፡፡

ሌላው ደግሞ በመጽሐፈ ሰዋስው በስፋት የተዘረዘሩትና እና በዚህ ጥናትም በሰፊው


የተዳሰሱት በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ቀላትን የሚመለከተው ሦስተኛው
ክፍል ነው፡፡ ይህ ክፍልም የፊደላት አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ሦስት ጥንድ ግሶች፤
የትርጕም ልዩነት የማይታይባቸው ጥንድ ግሶች ኹለት፤ የትርጉም ልዩነት የሌላቸውና
የፊደል አጠቃቀም ችግር ያለባቸው ደግሞ ኹለት ጥንድ ግሶች በድምሩ ሰባት ጥንድ
ግሶችን በያዙ ሦስት ንኡሳን ክፍሎቸ ተከፍሎ ግሶቹ በንጽጽራዊ ተንተና ተዳሰዋል፡፡

70
.

ውጤቱም ከላይ በሌሎቹ ንኡሳን ክፍሎች እንደተገለጸው ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው


የሚመስሉ ፊደሎችን በዘፈቀደ መጠቀም ችግር በሰፊው ተስተውሏል፡፡ በተገቢው ፊደል
የተዋቀሩ ቃላትም ቢኾን በቃላቱ መካከል የትርጕም ልዩነት ሳይኖር በገቡበት ዐረፍተ
ነገር የተሰጣቸውን ዐውዳዊ ፍች መነሻ በመድረግ የተለየ ትርጕም እንዳላቸው
ተቆጥረዋል፡፡ ነገር ግን በቃላቱ መካከል የተለየ ትርጕም እንደሌለ ለቃላቱ በማስረጃነት
ከተጠቀሱት ጥቅሾች ሳይቀር ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እንዲያውም በአንዳንዶቹ ማስረጃዎች
ተመኵሳይያን የተባሉት ቃላት የተሰጣቸው የአማርኛ አቻ ትርጕም አንዱ በሌላው
ተቀይሮ ቢገባ በዐረፍተ ነገሩ ውስጥ ይዘታዊ ለውጥ የማያመጣ መኾኑን ነው ከጥናቱ
የተረጋገጠው፡፡

የተለየ ትርጕም ያላቸው ቃላትም የቃሉ የግስ ቅንጣጢት አንድ እስከኾነ ድረስ ለቃሉ
የተለያየ ትርጕም መሰጠቱ ትርጕም ማስፋት ከሚባል ውጭ ሞኵሼነትን የሚያሟላ
አይደለም፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው የተለያየ ሙያ ባለቤት በመኾኑ ምክንያት በተካነበት
ሙያ ኹሉ መጠራቱ ሰውየውን የተለያየ ሰው እንደማያደርገው ኹሉ ቃላቱም በተመሳሳዪ
በትርጕም የበለጸጉ መኾኑን የሚያሳይ በመኾኑ ነው፡፡ ቃላቱ የተለየ ትርጕም
ባይኖራቸውም ተደጋግመው በተጻፉ ቁጥር የተዋቀሩበት ፊደልም እንደሚለያይ ነው
በጥናቱ የተረጋገጠው፡፡

ሌላው በንባብና በፊደል ተመሳስለው በምስጢርና በአመጣጥ ልዩነት አላቸው የተባሉትን


ግሶች የሚመለከት ሲኾን ለዚህም በማሳያነት የተጠቀሱ ኹለት ጥንድ ግሶች ናቸው፡፡
ከነዚህም ውስጥ አንደኛዉ ጥንድ ግስ የመጀመሪያዉ ተነሺ ንባብ ኹለተኛዉ ግስ ደግሞ
ወዳቂ እንደመኾኑ መጠን በተዋቀሩበት የፊደል ዐይነት ቢመሳሰሉም በሥርዐተ ንባቡ ጊዜ
ለጀሮ የሚሰማው ድምፀት ተመሳሳዪ አይደለም፡፡ እንዲሁም የግሶቹን አመጣጥና ምስጢር
በተመለከተ የኹለቱም ጥንድ ግሶች የርባታ መነሻቸው ተመሳሳዪ በመኾኑ እና የሥርዐተ
ንባቡ መለያየትም የግሱን ባለቤት፣ ፆታና ቁጥር የሚያሳይ ከመኾን ባለፈ በግሶቹ መካከል
የምስጢር ልዩነት ያለ ስለመኾኑ አያሳይም፡፡ በመኾኑም ለተመኵሰይያን ከተሰጠው
ትርጕም አንጻር በንባብ ልዩነት የትርጕም ለውጥ የሚያመጡ ቃላት በማለት ግሶቹ
ከተመኲሳይያን ቃላት ውስጥ መመደባቸው ትክክል አለመኾኑን ነው ጥናቱ ያረጋገጠው፡፡

71
.

4.2 መደመደሚያ

የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት የተገለጹበትን አግባብ


መመርመር ነው፡፡ በጥናቱም በመጽሐፈ ሰዋስው ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ
ፊደላት ቃላትን ለማዋቀር በዘፈቀደ ጥቅም ላይ የዋሉ ስለመኾኑና በእነዚህ ፊደላት
የተዋቀሩ ቃላትም የፊደላቱ ዐይነት ግምት ውስጥ ሳይገባ ተመኵሳይያን የተባሉ
ስለመኾናቸው ነው የተረጋገጠው፡፡ እንዲሁም ቃላት በመካከላቸው የተለየ ትርጕም
ሳይኖር በገቡበት ዐረፍተ ነገር ውስጥ የተሰጣቸው ዐውዳዊ ፍችም ለሞኵሼነት መነሻ
የተደረገ ስለመኾኑም በጥናቱ ተገለልጧል፡፡ አዕማድ ግሶችንም በተመለከተ የፊደላት
አጠቃቀም ችግርና በግሶቹ መካከል የተለየ ትርጕም ካለመኖር በተጨማሪ በቅርጽ ደረጃም
ቢኾን አንዱ የሌላው አስደራጊ ወይም ተደራጊ ሳይመስል ጥንድ ግሶቹ የተሞካሹ
ስለመኾኑ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ባጠቃላይ የጥናቱን ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ የጥናቱን
ውጤት እንደሚከተለው መደምደም ይቻላል፡፡

በመጽሐፈ ሰዋስው ተመኵሳይያን ቃላት በምስጢር የማይገናኙ እየራሳቸው የቆሙ ኾነው


አድራጊ፣ አስደራጊ፣ ተደራጊ የመሰሉ ግሶች አንድ ወገን፤ በአንድ ቃል ኹለት ነገር
እየተፈቱ በመጥበቅ የቀደሰ በመላላት የቀተለ የሚኾኑ ግሶች አንድ ወገን፤ በአንድ ቃል
ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ግሶች አንድ ወገን፤ ከአገባብ፣ ከነባር፣ ከዘር፣ የሚገኙ በንባብ
አንድነት በነገር ልዩነት ያላቸው ፊደላት አንድ ወገን በማለት ነው በአራት የተከፈሉት፡፡
በእያንዳንዱ ክፍል የመጽሐፈ ሰዋስው አገላለጽን ከሌሎች የሴም ቋንቋዎች ጋር በማነጻጸር
የተወሰኑ ማሳያዎችን በማንሣት ለማሳየት ከአዕማድ ግሶች እንጀምራለን፡፡

መጽሐፈ ሰዋስው በአዕማድ ግሶች ላይ ሞኵሼነትን ያሳየው ግሶች በምስጢር (በትርጕም)


የተለያዩ ኾነው እያለ በቅርጽ ደረጃ ግን የአንዱ ግስ አስደራጊዉ ወይም ተደራጊዉ
ከሌላው አድራጊ ግስ ጋር ተመሳሳዪነት አለ በሚል ነው፡፡ ነገር ግን ይህን ያሳያሉ
ተብለው የተጠቀሱት ጥንድ ግሶች ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላትን
በተመለከተ የዘፈቀዳዊ አጠቃቀም ይታያል፡፡ ለምሳሌ ረአየ--ጠበቀ እና አስተርአየ --
ታየ/ተገለጠ በማለት በመጽሐፈ ሰዋስው የተጠቀሱትን ጥንድ ግሶች ከሌሎች የሴም
ቋንቋዎች አንጻር ስንመለከት ረአየ--ጠበቀ የሚለው ግስ በ“ዐይኑ ዐ” መጻፍ እየተገባው
በ“አልፋዉ አ” ተከትቦ ከኹለተኛዉ ጥንድ ግስ ጋር በፊደል አጠቃቀም እንዲመሳሰል

72
.

ተደርጎ ነው አስተርአየ የረአየ ን አድራጊ ይመስላል የሚል ድምዳሜ ላይ የተደረሰው፡፡


ነገር ግን የረዐየ--ጠበቀ ን አስደራገዉን ስንመለከት አርዐየ--አስጠበቀ በሚል የሚከተብ
ኾኖ ነው የሚገኘው፡፡ በመኾኑም አስተርአየ--ታየ/ ተገለጠ የሚለው ግስ በተዋቀረበት
ፊደልም ኾነ በቅርጽ ደረጃ የረዐየ--ጠበቀ ን አስደራጊ የማይመስል ስለመኾኑ ነው ጥናቱ
ያሳየው፡፡

አድራጊና ተደራጊ የሚመስሉ ግሶችን በተመለከተ ሐለፈ--አለፈ እና ተሐለፈ--ተነጋገረ


የሚሉትን ጥንድ ግሶች ስንመለከት ከዐረብኛ ቋንቋ አንጻር ዐለፈ የሚል ትርጕም ያለው
የግእዝ ግስ የሚጻፈው ኀለፈ--ዐለፈ በሚል በ“ብዙኃኑ ኀ” ነው፡፡ ይህ ግስ ደግሞ ወደ
ተደራጊነት ሲቀየር ተኀልፈ--እንዲያልፍ ተደረገ በሚል ነው፡፡ ይህም ተሐለፈ--ተነጋገረ
የሚለው ግስ በተዋቀረበት ፊደልም ኾነ በቅርጹ ከ ኀለፈ--ዐለፈ ተደራጊ ግስ ጋር
የማይሞካሽ መኾኑን ነው ጥናቱ ያሳየው፡፡

ከትርጕም አንጻርም ስንመለከት አድራጊ እና አስደራጊ ለሚመስሉ ግሶች ጸንሐ---ቆየ እና


አጽንሐ--አደባ/ ሸመቀ፤ አድራጊ እና ተደራጊ ለሚመስሉ ግሶች ደግሞ ዘከረ--ጠራ እና
ተዘከረ--አሰበ የሚሉትን ጥንድ ግሶች ብንመለከት ግሶቹ እንደጉዳዩ ዐይነት በተሰጣቸው
ዐውዳዊ ትርጕም የተለያዩ ቢመስሉም መሠረታዊ የትርጕም ልዩነት ግን የሌላቸው
ናቸው፡፡ በአስደራጊነትና በተደራጊነት የተጠቀሱት ግሶችም በአድራጊነት መተርጐማቸው
በተለይ ተዘከረ--አሰበ የሚለው ግስ ታሰበ ተብሎ በተደራጊነት መተርጐም ሲገባው
በአድራጊነት መተርጐሙ ልማደ መጻሕፍት ኾኖ እንጅ ግሱ የተለየ ትርጕም ኖሮት
እንዳልኾነ ነው የተረጋገጠው፡፡

በኹለተኛ ደረጃ በዝርዝር ሐተታ የተሰጠበት በአንድ ቃል ተነበው በመጥበቅና በመላላት


ኹለት ፍች የሚሰጡ ቃላት ናቸው፡፡ በዚህ ክፍልም ተመሳሳዪ ድምፅ ባላቸው ፊደላት
በተዋቀሩ ግሶች ውስጥ ፊደላቱ በዘፈቀደ የሚከተቡ መኾኑንና ግሶቹ የተዋቀሩበት ፊደል
የተለያየ ኾኖ እያለም ግሶቹ ተመኵሳይያን የተባሉ መኾኑን ነው ጥናቱ ያሳየው፡፡ ለምሳሌ
አሠረ--አደመ፣ አቃጠረ፣ ሰበሰበ፣ ካሥር አንድ ሰጠ እና አሰረ--አሰረ በሚል የተጠቀሱትን
ጥንድ ግሶች ብንመለከት የመጀመሪያዉ ጥንድ ግስ በ“ዐይኑ ዐ” መጻፍ እየተገባው
መጽሐፈ ሰዋስው የተጠቀመው “አልፋዉ አ” ን ነው፡፡ እንዲሁም በኹለቱም ጥንድ ግሶች
የየግሶቹ መካከለኛ ፊደል በድምፅ እንጅ በቅርጽ ተመሳሳዪነት የለውም፡፡ ይህም

73
.

በመጽሐፈ ሰዋስው ግሶችን ተመኵሳይያን ለማለት የፊደላት ድምፅ መመሳሰል እንጅ


ቅርጻቸዉ ግምት ውስጥ ያልገባ መኾነኑን ያሳያል፡፡

በተመሳሳዪ ግሶች በተገቢዉ ፊደል ሳይከተቡ፤ የተጻፉበት ፊደልም የተለያየ መኾኑ ከገጸ
ንባቡ በግልጽ እየታየ እና በመካከላቸዉ የትርጕም ልዩነት ሳይኖር ግሶች ተመኵሳይያን
የተባሉበት ሌላዉ ክፍል ደግሞ በአንድ ቃል ተነበው በብዙ ነገር የሚፈቱ ቀላትን
የሚመለከተው ክፍል ነው፡፡

ለምሳሌ፦ ኀፀነ--አሳደገ

ሐፀነ--መገበ

ሐፀነ--ጠወረ በማለት የተጠቀሰውን ግስ ብንወስድ አሳደገ የሚል ትርጕም


ያለው የመጀመሪያዉ ግስ በ“ሐመሩ ሐ” መጻፍ እየተገባው በ“ብዙኃኑ ኀ”መጻፉ አንዱ
ስሕተት ነው፡፡እንዲሁ የተጻፈውን እንዳለ ብንወስደውም የመጀመሪያዉ ግስ በፊደል
አጠቃቀም ረገድ ከሌሎቹ ኹለት ግሶች የተለየ ስለመኾኑ ገጸ ንባቡ በግልጽ እያሳየ እያለ
እና ለሦስቱም ግሶች የተሰጣቸው ትርጕም ተመሳሳዪ ኾኖ እያለ ነገር ግን ሦስቱም ግሶች
አንዱ ከሌላኛዉ ጋር ሞኵሼዎች እንደኾኑ ነው በመጽሐፈ ሰዋስው የተቀመጠው፡፡ ይህ
ምሳሌም በመጽሐፈ ሰዋስው በጥናት የተረጋገጡትን የፊደላት አጠቃቀም ችግርን፤ ለቃላት
ሞኵሼነት የፊደላት ቅርጽ መለያየት ግምት ውስጥ አለመግባትን እና በቃላት መካከል
የትርጕም ልዩነት ሳይኖር የቃላት ተመኵሳይያን መባልን በአንድ ላይ የሚያሳይ ነው፡፡

ሌላዉ በንባብና በፊደል ተመሳስለው በምስጢርና በአመጣጥ ልዩነት አላቸው የተባሉትን


ግሶች የሚመለከት ሲኾን ለዚህም በማሳያነት አንድ ምሳሌ ብንጠቅስ-

አእመራ--አወቃት

አእመራ--አወቁ የሚለውን ግስ ነው፡፡ ይህም አንደኛዉ


ጥንድ ተነሺ ንባብ ኹለተኛዉ ግስ ደግሞ ወዳቂ እንደመኾኑ መጠን በተዋቀሩበት የፊደል
ዐይነት ቢመሳሰሉም በሥርዐተ ንባቡ ጊዜ ለጀሮ የሚሰማው ድምፀት ተመሳሳዪ
አይደለም፡፡ እንዲሁም የግሶቹን አመጣጥና ምስጢር በተመለከተ የኹለቱም ጥንድ ግሶች
የርባታ መነሻቸዉ ተመሳሳዪ በመኾኑ እና የሥርዐተ ንባቡ መለያየትም የግሱን ባለቤት፣
ፆታና ቁጥር የሚያሳይ ከመኾን ባለፈ በግሶቹ መካከል የምስጢር ልዩነት ያለ ስለመኾኑ

74
.

አያሳይም፡፡ በመኾኑም ለተመኵሳይያን ከተሰጠው ትርጕም አንጻር በንባብ ልዩነት


የትርጕም ለውጥ የሚያመጡ ቃላት በማለት ግሶቹ ከተመኵሳይያን ቃላት ውስጥ
መመደባቸው ትክክል አለመኾኑን ነው ጥናቱ ያረጋገጠው፡፡

4.3. የይኹንታ ሐሳብ

ይህ ጥናት የታየ ገብረ ማርያም መጽሐፈ ሰዋስውን መነሻ በማድረግ ተመኵሳይያን ቃላት
ላይ በማተኮር የተደረገ ሲኾን ታየ ቃላትን ለማዋቀር በተለምዶ ሞኵሼ እየተባሉ የሚጠሩ
ፊደላትን በዘፈቀደ የተጠቀመ መኾኑ የጥናቱ አንዱ እና ዋናዉ ውጤት ነው፡፡ የዚህ ቀላል
ማስረጃ ደግሞ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው በሚመስሉ ፊደላት የሚዋቀሩ ግሶች በተገቢዉ
ፊደል ካለመዋቀራቸውም በላይ ግሶቹ ሌላ ቦታ ላይ ሲጠቀሱ እንዲሁም ለየግሶቹ
በማስረጃነት ከሚጠቀሰው ዐረፍተ ነገር ውስጥ ግሶቹ ወደ ሌላ የቃል ክፍል ሲቀየሩ በሌላ
ተመሳሳዪ ድምፅ ባለው ፊደል ተጽፈው መገኘታቸው ነው፡፡ ይህም ተመሳሳዪ ድምፅ
ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት አንድ ዐይነት ናቸው ከሚል ድምዳሜ ላይ ታየ የደረሰ
መኾኑን ያሳያል፡፡ በቅርጽ ተለያይተው በድምፅ ተመሳሳዪ በሚመስሉ ፊደላት የተዋቀሩ
ጥንድ ቃላትም ተመኵሳይያን መባላቸውም የዚሁ ውጤት ነው፡፡

በዘርፉ ምሁራንም ችግሩን ከማረም ይልቅ እንዳለ ማስቀጠላቸው ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸው
የሚመስሉ ፊደላትን አጠቃቀም በተመለከተ በዘፈቀደ መጠቀም የታየ ገብረ ማርያም ብቻ
ሳይኾን የሌሎች ምሁራንም አቋም መኾኑን ያሳያል፡፡ የዚህ ማሳያ ደግሞ ከመጀመሪያዉ
የመጽሐፈ ሰዋስው ዕትም በኋላ በተለያዩ ምሁራን የታታሙ የዚሁ የመጽሐፈ ሰዋስው
ቅጅዎች አንዳንዶቹ ከመጀመሪያዉ ዕትም ጋር ተመሳሳዪ በኾነ መልኩ ሌሎቹ ደግሞ
ከመጀመሪያዉ ዕትም በተለየ መልኩ ሌላ ዘፈቀዳዊ የኾነ የፊደል አጠቃቀም መከተላቸው
ነው፡፡ በመልክእ ደራሲዎች፣ በቅኔ ዘራፊዎች እና በግጥም ገጣሚዎችም ሳይቀር ተመሳሳዪ
ድምፅ ያላቸው የሚመስሉ ፊደላት በቤት መምቻነት በዘፈቀደ ጥቅም ላይ መዋላቸውም
ሌላዉ ማሳያ ነው ፡፡

ሌላው በጥናቱ የተረጋገጠው ቃላት ካላቸው ትርጕም አንጻር ተመኵሳይያን የተባሉበት


ኹኔታ ነው፡፡ይህም ተመኵሳይያን ቃላት በሚል በመጽሐፈ ሰዋስው ጥንድ ኾነው
የተቀመጡት ግሶች ከአንድ የግስ ቅንጣጢት የተገኙና መሠረታዊ የትርጕም ልዩነት
ሳይኖራቸው እንደገቡበት ዐውድ ትርጕም ስለተሰጣቸው ብቻ ከተለያየ የግስ ሥር

75
.

እንደተገኙ ተቆጥረው ተመኵሳይያን የተባሉ መኾኑን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ እንዲሁም


አድራጊ፣ አስደራጊ እና ተደራጊ የሚመስሉ ግሶችን በተመለከተ በአድራጊነት የተጠቀሰው
ግስ ወደ ተደራጊነት ወይም ወደ አስደራጊነት ሲቀየር ይመስለዋል ከተባለው ኹለተኛዉ
ጥንድ ግስ ጋር በቅርጽ ደረጃም ተመሳሳዪነት ሳይኖረው ጥንድ ግሶቹ ተመኵሳይያን
እንደተባሉ ነው በምርምሩ የተገለጠው፡፡ የምርምሩ ውጤት ሲጨመቅ ከላይ የተገለጸውን
ሲመስል የአጥኚዉ የመፍትሔ ሐሳብ ደግሞ የሚከተለው ነው፡፡

 ቋንቋ በተለይ የራሱ የኾነ ፊደል ያለው ቋንቋ ያንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የማንነት
መገለጫ እና መለያ እንደመኾኑ መጠን የግእዝ ቋንቋ ከነፊደላቱ ተጠብቆ መቆየት
ያለውን ታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በጥናትና በምርምር ተመሥርቶ ትውልዱ
ግንዛቤ እንዲኖረው ቢሠራ፡፡ ይህም በምላሹ በግእዝ ቋንቋ የተጻፉ ቀደምት
መዛግብትን አንብቦ ለመገንዘብና ከያዙት ቁም ነገርም ትውልዱ የጥቅሙ ተካፋይ
እንዲኾን ያስችላል፡፡
 ፊደላት የሚቀረጹት ለአንድ ድምፅ አንድ ውክልና በሚል መርሕ መኾኑ እየታወቀ
በተለምዶ ሞኵሼ እየተባሉ የሚጠሩት ፊደላት ተመሳሳዪ አንደኾኑ ተቆጥሮ በሥርዐተ
ጽሕፈት ጊዜ ፊደላቱን በዘፈቀደ መጠቀምና ከዚህም አልፎ የፊደላት ድግግሞሽ ስለበዛ
ፊደላት ይቀነሱ የሚል መከራከሪያ መነሣቱ የፊደላቱን ድምፅ ለይቶ ካለማወቅ የተነሣ
በመኾኑ ድምፃቸዉን መልሶ ለማግኘት ፊደላቱን በጽሑፍ አንዳንዶቹንም ደግሞ
በድምፅ ለይቶ በማቆየት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን አካላትና የሌሎች ተዛማጂ
የሴም ቋንቋዎች ምሁራንን ጭምር በመጋበዝ ተገቢዉን ጥናትና ምርምር ቢደረግ፡፡
 የግእዝ ቋንቋ የአንድ ሃይማኖትና ብሔር ቋንቋ ነው የሚል ዕሳቤ በትውልዱ እንዳይኖር
የሌሎች እምነት ተከታዮችም ኾኑ የሌሎች ብሔር ተወላጆች በግእዝ ቋንቋ ጥናትና
ምርምር ውስጥ እንዲሳተፉ ኹኔታዎችን ማመቻቸትና ዕድሎችን ማስፋት፡፡
 ፊደላቱ ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ ይኾኑ ዘንድ ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ የተደገፈ
ሥርዐተ ጽሕፈት እነዲኖር በማድረግ ተመሳሳዪ ድምፅ ያላቸውን ፊደላት ብሎም
አጠቃላይ የቋንቋዉን ተቀባይነት ማስፋት፡፡
 የቋንቋዉን ሥርዐተ ሰዋስውና ርባታ በተመለከተ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ይገኛል
በማለት በደፈናው ከመቀበል ይልቅ ትክክል የኾነውንና ያልኾነውን በምርምር ለይቶ
በማውጣት እና ስሕተት ኾኖ የተገኘውን በማረም ቋንቋዉን ማበልጸግ የሚሉት
በመፍትሔ ሐሳብነት የቀረቡ ናቸው፡፡
76
.

ማጣቀሻ መጻሕፍት

ሀብተ ማርያም አሰፋ፡፡ (1986) ፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ጥያቄዎችና ባሕሎች፡፡

አዲስ አበባ፣ አሳታሚ ድርጅቱ ያልተገለጸ፡፡

ሀዲስ ዓለማየሁ፡፡ (1996) ፡፡ ፍቅር እስከ መቃብር፡፡ አዲስ አበባ፣ ሜጋ አሳታሚ

ድርጅት፡፡

ላምብዲን = T.O, Lambdin. (1978), Introduction to Classical Ethiopic (Ge‟ez).

Harvard Semitic Studies 24. (Missoula, Mont.) Scholars Press.

ሌስሎው = Wolf,Leslau. 1991. Comparative Dictionary of Ge’ez (Classical

Ethiopic). Wiesbaden: Harrassowitz.

………… .(1972). English—Amharic Context Dictionary. Los Angeles.

………… .(1957). Observation on a Conparative Phonology of Semitic

Ethiopic.Annalese d’Ethiopie, Vo. 2, pp. 147-166, Los Angeles፡

CaliforniA.

መርስዔ ኀዘን ወ/ ቂርቆስ፡፡ (1948) ፡፡ ያማርኛ ሰዋስው፡፡ አዲስ አበባ፣ አርቲስቲክ

ማተሚያ ቤት፡፡

መርሻ = Mersha Alehegne. ([2003). Andemta as an Interepretive strategy with

Reference to the book of Genesis (Unpublished Degree of Masteres

Thesis). Adiss Abeba University, Adiss Abeba.

ሙሉሰው አስራቴ ፡፡ (2001) ፡፡ የአማርኛን ሥርዓተ ጽሕፈት ለማሻሻል የተደረጉ

ጥረቶችና ውጤታቸዉ፡፡ መድበለ ጉባኤ ፡፡ አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ

ደራስያን ማኅበር ፡፡

77
.

ሙኒር አብራር፡፡ (2007) ፡፡አማርኛ--እንግሊዝኛ--ዐረብኛ መዝገበ ቃላት፡፡ ሦስተኛ

ዕትም፣አዲስ አበባ ፣ አሳታሚዉ ያልተገለጸ፡፡

ምክረ ሥላሴ ገብረ አማኑኤል፡፡ (2000) ፡፡ የመጀመሪያዉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጕም

በግእዝ ቋንቋ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ


እስከ ፳፻፡፡ አዲስ አበባ፣ ትንሣኤ አሳታሚ ድርጅት፡፡

ስሚድት = Wolbert, Smidt. (2005), “Ǝmkulu” (እምኩሉ) In Siegbert Uhlig (ed.),

Encyclopedea Aethiopica (Vol. II, pp. 274-275). Wiesbaden: Harrassowitz

Verlage

ስማቸው ንጋቱ፡፡ (2009) ፡፡ ቅኔና ባለቅኔዎች ፡፡ 3ኛዉ ሀገር አቀፍ የግእዝ ዐውደ

ጥናት መድበል፣ ገጽ 110—131፡፡ ባሕር ዳር፣ ሚና ማተሚያ ቤት ፡፡

ስማቸው ንጋቱ እና መሠረት ዐሥራት፡፡ (2009) ፡፡ማዕዶት (መጽሐፈ አዋጅ ወአገባብ)፡፡

ባሕረር ዳር፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማተሚያ ቤት፡፡

ስቴይንጋስ = F, Steingass. (1982). English—Arabic Dictionary. London, W. H.

Allen.

በላይ መኮነን፡፡ (2009) ፡፡ የግእዝ ቋንቋ ትላንት፣ ዛሬና ነገ፡፡ 3ኛዉ ሀገር አቀፍ የግእዝ

ዐውደ ጥናት መድበል፣ ገጽ 88—109፡፡ ባሕር ዳር፣ ሚና ማተሚያ ቤት፡፡

በርግ= Bruce L, Berg. (2001). Qualitative Research Methods for Social Sciences.

{4thed}, A Pearson Education Company.

ባየ ይማም ፡፡ (2001) ፡፡ ቁዋንቁዋና ማኅበራዊ ለውጥ ፡፡ መድበለ ጉባኤ ፡፡ አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ደራስያን መኅበር ፡፡

ቤሪ = LaVerle, Berry. (2003). “Bägemdər”. In Siegbert Uhlig (ed.), Encyclopedea

Aethiopica (Vol. I, pp. 438-440). Wiesbaden: Harrassowitz Verlage.

78
.

ተስፋ ገብረ ሥላሴ፡፡ (1982) ፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው (መጽሔተ አእምሮ) ፡፡ አዲሰ አበባ፣

ተስፋ ገብረ ሥላሴ ማተሚያ ቤት፡፡

ታየ ገ/ ማርያም፡፡ (1889) ፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው፡፡ (የታተመበት ከተማ ያልተገለጸ)

ምንኩሉ ሚሲዮን ማኅተምያ፡፡

………………፡፡1958) ፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው፡፡ (በአብርሃ ደስታ ትጋት የታተመ)

አሥመራ፣ ፖሊግራፊኮ ማተሚያ ቤት፡፡

አምሳሉ ተፈራ ፡፡ (2006) ፡፡ “ዓለም አቀፍ የግዕዝ ጥናት - ምጥን ምልከታ” ፡፡ ሐቃፌ

ሐገር ቀዳማይ ጉባኤ ግዕዝ ጥንቅር፣ ገጽ 9-20 ፡፡

አምሳሉ ተፈራ፡፡ (2011) ፡፡ ነቅዐ መጻሕፍት፡፡ አዲስ አበባ፣ ዲዘሎፐርስ ኃ. የተ.የግ.ማ፡፡

አስረስ የኔሰው፡፡ (1951) ፡፡ ትቤ አክሱም መኑ አንተ? ፡፡ አዲሰ አበባ፣ ንግድ ማተሚያ

ቤት፡፡

አቤሴሎም ነቅዐ ጥበብ፡፡ (2009) ፡፡ መሠረታዊ ሰዋስወ ግእዝ (በቀላል አቀራረብ)፡፡

አዲስ አበባ፣ ፋር ኢስት ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግ. ማኅበር፡፡

አፈወርቅ ዘውዴ፡፡ (1988) ፡፡ ሀገረ መጻሕፍት (ሰዋስወ ግእዝ ወዐማርኛ)፡፡ ክፍል

አንድ፡፡አዲስ አበባ፣ ትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት፡፡

ኡሌንዶርፍ = Edward, Ullendorf. (1955). The Semitic Languages of Ethiopia a

Comparative phonology. London: Taylor [Foreign} Press.

………… (1951). Studies in the Ethiopic Syllabary, Journals of

International African Institute, Vol.21, No.7, pp 207—217, Cambridge

University.

79
.

ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፡፡ (1948) ፡፡ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፡፡ አዲስ

አበባ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡

ካኔ = T. L, Kane. (1990), Amharic-English Dictionary, Volume 1, Otto

Harrassowitz. Wiesbaden

ኮውሊ = R, Cowley. (1967). The Standardaization of Amharic Spelling. Journal of

Ethiopian Studies, Vol. 5, No. 2, pp 1-8. Institute of Ethiopian studies.

ዐለም = Aleme Eshete. (1971-72). Alaqa Taye Gabra Mariam (1861-1924).

Rassegna di Studi Etiopici, 25, 14-30.

ዐቢይ ለቤዛ፡፡ (2010) ፡፡ ዐምደ ግእዝ፡፡ ማተሚያ ቤቱ ያልተገለጸ፡፡

ዙፋን= Zufan Gebrehiwet. (2018). Why the Geez Pharyngeal Sounds

Pronounced as Glottal Sounds. International Journal of Innovative

Research and Development, 17, 547-552. Doi: 10.24940/ ijird.

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማእከል፡፡ (1993) ፡፡ አማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡

አዲስ አበባ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (1992) ፡፡ መጽሐፈ ሰዋሰው፡፡ አዲስ

አበባ፣ትንሣኤማሳተሚያ ድርጅት፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (1993) ፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር (በግእዝ

እና በአማርኛ) ( ከመጋቢት እስከ ጳጉሜን) (ሦስተኛ ዕትም)፡፡ አዲስ አበባ፣ ትንሣኤ


ማሰተሚያ ድርጅት፡፡

ያሬድ ሽፈራው (ሊቀ ሊቃውንት) ፡፡ (2000) ፡፡ መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው መርኆ

መጻሕፍት፡፡ ባሕረ ዳር፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማተሚያ ቤት ፡፡

80
.

ደሴ ቀለብ፡፡ (2007) ፡፡ ትንሣኤ ግእዝ፡፡ አዲስ አበባ፣ አፍሮ የሕትመት ሥራ

ድርጅት፡፡

ደስታ ተክለ ወልድ፡፡ (1946) ፡፡ ግእዝ መሠረተ ትምህርት፡፡ አደስ አበባ፣ አርቲስቲክ

ማተሚያ ቤት፡፡

ዲልማን = A, Dillmann. (1907), Ethiopic Grammear. Trans. James A. Crichton.

London: Williams and Norgate.

ዲዩተር= M, Deuter, ቱሩቡል= J,Turubull, ብራድቤሪ=J, Bradbery. (1948). Oxford

English Dictionary. Oxford University.

ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (አባ) ፡፡ (2001) ፡፡ መጽሐፈ ምስጢር (በግእዝና በአማርኛ) (በሕሩይ

ኤርምያስ የተተረጐመ)፡፡ በቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እና በቅዱስ አባ በጸሎተ


ሚካኤል አንድነት ገዳም የታተመ፡፡

ጎልደንበርግ=Gideon, Goldenberg. (2013). Semitic Languages: feathurs,

structures,relations, processes. UK: Oxford University Press.

81

You might also like