You are on page 1of 30

ወሎ ዩኒቨርሲቲ

የማህበራዊና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

የፎክሎርና የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ድሕረ ምረቃ መርሃ ግብር

ሚዜና ሚዜነት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ወረዳ

ይሳለሙሽ ዓባይ

ታህሳስ, 2016 ዓ.ም

ደሴ, ኢትዮጵያ

ሚዜና ሚዜነት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ

ወሎ ዩኒቨርሲቲ
የማህበራዊና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል ድህረ ምረቃ መርሃ ግብር

በፎክሎርና የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ድህረ ምረቃ መርሃ ግብር

ለማስተርስ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ትልመ ጥናት

በ:

በይሳለሙሽ ዓባይ

አማካሪ:

ብርሃን አሰፋ (ዶ/ር)

ታህሳስ, 2016 ዓ.ም

ደሴ, ኢትዮጵያ
ማውጫ

ይዘት ገ


ማውጫ..........................................................................................................................................i

ምዕራፍ አንድ..................................................................................................................................1

1. መግቢያ......................................................................................................................................1

1.1. የጥናቱ ዳራ...........................................................................................................................1

1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያቶች.........................................................................................................5

1.3. የጥናቱ ዓላማዎች...................................................................................................................6

1.4. የጥናቱ መሪ ጥያቄዎች..............................................................................................................6

1.5. የጥናቱ ወሰን.........................................................................................................................6

ምዕራፍ ሁለት..................................................................................................................................7

2. ክለሳ ድርሳናት..............................................................................................................................7

2.1. ጽንሰ ሃሳባዊ ዳሰሳ....................................................................................................................7

2.1.1. ሥርዓተ ከበራ.................................................................................................................7

2.1.2. የሥርዓተ ከበራ መገለጫዎች.............................................................................................10

2.1.3. ጋብቻ.........................................................................................................................12

2.1.4. ሰርግ..........................................................................................................................12

2.1.5. ሚዜ..........................................................................................................................13

2.1.6. ሚዜነት........................................................................................................................13

2.1.6.1 አንድነት................................................................................................................14

2.1.6.2 የአንድነት መከሰቻዎች...............................................................................................14

2.1.6.2.1 መስተጋብር.....................................................................................................14

2.1.6.2.2. የግንኙነት ቅጥ.................................................................................................15

2.1.7. የአንድነት መለኪያዎች....................................................................................................15

i
2.1.7.1. ግንዛቤ.................................................................................................................15

2.1.7.2. መግባባት..............................................................................................................15

2.1.7.3. ግንኙነት...............................................................................................................16

2.1.7.4. የጋራ ተጽዕኖ.........................................................................................................16

2.2. የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት..........................................................................................................16

2.3. ንድፈ ሀሳባዊ ቅኝት...............................................................................................................18

2.3.1. ግልጋሎታዊ ንድፈ ሀሳብ..................................................................................................18

2.3.2. ፍካሬ ልቦናዊ ንድፈ ሀሳብ................................................................................................19

ምዕራፍ ሶስት.................................................................................................................................20

3. የጥናቱ ዘዴ...............................................................................................................................20

3.1 የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች......................................................................................................20

3.1.1 የምልከታ ዘዴ..................................................................................................................20

3.1.2 ቃለ መጠይቅ..................................................................................................................21

3.1.3 የተተኳሪ ቡድን ውይይት....................................................................................................22

3.1.4 ሰነድ ፍተሻ.....................................................................................................................22

3.2. የናሙና አመራረጥ ዘዴ...........................................................................................................23

3.3 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ............................................................................................................23

3.4. የጥናቱ የጊዜና የበጀት ዕቅድ....................................................................................................24

3.4.1. የበጀት እቅድ................................................................................................................24

3.4.2. የጊዜ ሠሌዳ..................................................................................................................26

ዋቢ ጽሁፎች.................................................................................................................................27

ii
ምዕራፍ አንድ

1. መግቢያ
ይህ ትልመ ጥናት ሚዜና ሚዜነት በሰሜን ወሎ ዞን ራያቆቦ ወረዳ ላይ እንዴት እንደሚከወን ማሳየትን
ትኩረቱ ላደረገው ጥናት የተዘጋጀ ትልመ ጥናት ነው፡፡

ትልመ ጥናቱ በሶስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን በምዕራፍ አንድ የጥናቱ ዳራ፣ አነሳሺ ምክንያት፣
ዓላማ፣ መሪ ጥያቄዎች፣ አስፈላጊነትና ወሰን የተካተቱበት ሲሆን በምዕራፍ ሁለት ደግሞ ክለሳ ድርሳናትና
የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት ቀርቦበታል፡፡ በምዕራፍ ሶስት ደግሞ የአጠናን ዘዴ ቀርቦበታል፡፡

1.1. የጥናቱ ዳራ

ይህ ጥናት በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ማህበረሰብ ውስጥ በሰርግ ስነ-ስርአት ስር ያለው ሚዜና


ሚዜነትን በመተንተን ትርጉሙንና ያለውን ማህበራዊ ፋይዳ በመግለጽ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ጥናቱ ሰፊ
ስርዓተ ከበራ ያለውን የሰርግ ስነ-ስርዓት መነሻ በማድረግ ተነሳበትን ሚዜና ሚዜነት ተንትኖ ያሳያል፡፡
ይህንንም ከስሩ ማለትም ከፎክሎር በማንሳት ይጀምራል፡፡

ፎክሎር የሚለው ስያሜ በጣም ሰፊ ጽንሰ ሃሳቦችን በውስጡ የያዘ ቃል በመሆኑ ቁርጥ ያለ አንድ ወጥ
ብያኔ ለመስጠት እንደሚያስቸግር በመግለጽ ከፋፍሎ ማጥናት እንደሚገባ በርካታ ምሁራን ያስረዳሉ፡፡
ከነዚህ ምሁራን መካከል በተለይ ዶርሰን ፎክሎርን በአራት ዘርፎች የሚከፍሉት ሲሆን እነ ማርታ(2005)
ደግሞ ፎክሎር ስለ ጥበብ፣ ስለ ሰወች፣ የሰወችን መማሪያ መንገድ፣ እንዲሁም የእኛን ማንነት ለማወቅና
በአካባቢያችን ስላለው ዓለም ትርጓሜ ለመስጠት የሚረዳ መሆኑን ገልጸው በሶስት መደበውታል፡፡
በሃገራችን ገና ላልዳበረው ዘርፍ የሪቻርድ ዶርሰን ፍች የተሸለ መነሻ ሊሆን እንደሚችል ፈቃደ(1991)
ይገልጻሉ፡፡ በዚሁ በዶረሰን (1972፣3) ፍች መሰረት ‹‹ ፎክሎር፡- ስነቃል፣ ሃገረሰባዊ ትውን ጥበባት፣
ሃገረሰባዊ ልማድና ቁሳዊ ባህል ›› በማለት በአራት ዘርፎች ከፍሏቸዋል፡፡ ሆኖም እነዚህ ዘርፎች አነረዱ
በአንዱ ውስጥ እንዳይገናኙ ግድግዳ ሰርተው የቆሙ አይደሉም፤ በአብዛኛው አንዱ በሌላው ሊንጸባረቅ
ይችላል፡፡

ከቃሉ ትርጉም አንጻርም ፎክሎር ‹‹ፎክ›› እና ‹‹ሎር›› ከሚሉሁለት ቃላት የተገነባ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡
‹‹ፎክ›› ህዝብ/የሰወች ስብስብ ማለት ሲሆን ‹‹ሎር›› ደግሞ ዕውቀት ማለት ነው፡፡ የሁለቱ ቃላት ጥምረት
‹‹የቡድን ዕውቀት›› የሚል ነው (Dundes, 1980,]:: ፎክሎር በሰዎች የተፈጠረ ሰዎች የሚኖሩበትና
የሚኖሩት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ ሰዎች የፎክሎር መሰረታዊ ጉዳይ ናቸው፡፡ በፎክሎር እሳቤ ቡድን
ማለት የጋራ ፍላጎትና ልምድ ያላቸው ሰዎች የፈጠሩት ስብስብ ማለት ነው፡፡ ቡድን ወይም ‹‹ፎክ››

1
የሚለውን ቃል ለማስረዳት (Dundes, 1980,6) ‹‹የጋራ ጉዳይ ያሰባሰባቸው ሁለትና ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች
ስብስብ ‹‹ፎክ›› ወይም ቡድን ይባላል›› ይላሉ፡፡ በብያኔው ውስጥ የቡድኑ አባላት ለመሰባሰብ ምክንያት
የሆናቸውን የጋራ ባህሪ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ቡድኑም ሆነ
እያንዳንዱ የቡድን አባላት ‹‹ማነህ?›› ተብሎ ሲጠየቅ ማንነቱን የሚገጽበትና ለምን የቡድኑ አባል እንደሆነ
የሚሰጠው ምክንያት አለው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ብያኔ እንደምንረዳው ሚዜነትም አንዱ ፎክን ሊወክል
የሚችል ስብስብ እንደሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም የራሱ እኔነትና የጋራ መተዳደሪያ ደንብ አለው፡፡

Toelken (1996,56) ቡድን መገለጫቸው ባህልን መሰረት ያደረገ ተግባቦት ያላቸው ሰዎች ስብስብ ነው፡፡
የእሳቸው ብያኔ ከደንደስ ብዙም ያልራቀ ሲሆን በእሳቸው አገላለጽ ለቡድኑ መሰባሰብ ምክንያት የሆነው
ጉዳይ ባህላዊ መሰረት ያለው ነው፡፡ ይህ ባህላዊ መሰረት ደግሞ ኢ-መደበኛነትን ውስብስብ አለመሆንንና
ከመደበኛ ይልቅ ላማዳዊ ገጽታን የሚጠቁም እንደሆነ Simd and Stephens (2005,34) ይገልጻሉ፡፡
በጥቅሉ የፎክሎር ባለሙያዎች ስለፎክ ቡድን ምንነት ሲያስረዱ ዘር፣ ጎሳ፣ ጾታ፣ ስራ፣ መደብ፣ ዕድሜ፣
የጋራ ፍላጎት ወዘተ ለመሰባሰባቸው ምክንያት የሆኗቸው ከመደበኛ ህጎች ይልቅ ልማዳዊ በሆነ መንገድ
የተመሰረቱና የሚኖሩ ሰዎች ስብስብ ‹‹ፎክ›› ቡድን ይባላል ይላሉ፡፡ በዚህ ጥናት ትኩረት የተደረገባቸው
ሚዜወችም ዕድሜንና የጋራ ፍላጎትን ምክንያት አድርገው የተሰበሰቡ ወጣቶች የፈጠሯቸው ቡድን
መሆናቸውን ማጠየን ይቻላል፡፡

ልምድ በፎክሎር ጥናት ውስጥ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ ይህንን መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ በመተርጎም
ሂደት በርካታ የፎክሎር ባለሙያወች የተለያዩ ብያኔወችን ሰጥተዋል፡፡ ለምሳሌ፡- Hield (2007,59)
Glassie (1995)ን ጠቅሰው <<Tradation has widely been associated with stability through
processes of unchanging transmission and the preservation of authentic practices>> ሲሉ
Green (1997,800) ደግሞ <<Tradition as something passed down from one generation to the
next, generally by informal means, with little or no change in the transmission of that item or
in the item that is transmitted>> ብለዋል፡፡ ከነዚህ ምኑራን ሃሳብ የምንረዳው ልምድ የአንድ ነገር
ከአንድ ትውልድ ወደ ሌላው በጥቂት ለውጥ አለዚያም ያለምንም ለውጥ ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ
እንደሚተላለፍ ነው፡፡ የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው ሚዜና ሚዜነትም ጥንተ አመጣጡም ሆነ አሁን ያለበት
ህልውና የተመሰረተው በልምድ ላይ መሆኑን እንረዳለን፡፡ ለዚህም ማሳያው ስለቃሉ ትርጉም ተጽፎ
የሚገኝ ምሁራዊ ብያኔ እንኳ ብዙ አለመገኘቱ እውነትም ህልውናውም ሆነ ትርጓሜው ልማዳዊና
ማህበረሰባዊ መሆኑን ያመለክታል፡፡

በተጨማሪ ልምድ ቡድኑ ባለው እውቀት ማንነቱን ለመገንባትና ለማጠናከር የሚያገለግለው ጉዳይ
እንደሆነ ቡድኖች ልምድን የሚተገብሩት መርጠው በመውሰድም እንደሆነ ምሁራኑ ያስረዱ ሲሆን ይህም
በሚዜነት ሂደት ውስጥ አይቀሬ ነው፡፡ Glassie (1995) ም ልምድ ካለፈው ጊዜ መጭውን ጊዜ መፍጠር
ነው ሲሉ ከጊዜ ጋር የተያያዘ ሃሳብ እንደሆነ ሲገልጹ Horner(1990) በበኩላቸው ልምድ በትውልድ
መካከል ያለ የዕውቀትና የአስተሳሰብ ቅብብሎሺ ነው ይላሉ፡፡ ቅብብሎሹ ግን ካለፈው ዘመን ወደ አሁኑ

2
ብቻ የሚተላለፍ አይደለም፡፡ ይልቁንም በተመሳሳይ ወቅት የሚገኙ ቡድኖች ሊጋሬት ይችላሉ በማለት
የልምድ ቅብብሎሺ በተጓዳኝም ሆነ በተዋረድ በሚገናኙ ቡድኖች መካከል ሊካሄድ እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡

በአጠቃላይ ከላይ ከቀረቡ ብያኔወች የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነውን ሚዜና ሚዜነት ጥንተ አመጣጥ
የሚያመላክቱ ናቸው፡፡

ይህ ጥናትም በሃገረሰባዊ ልማድ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በተለይም ከፍተኛ ስርአተ ከበራ ከሚፈለጉ ስርአተ
ከበራዎች በሰርግ ስነ-ስርአት ውስጥ በሚካተተውን ሚዜና ሚዜነት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

እንዲሁም የሰው ልጅ ትላንትን እየጠየቀ ዛሬን እየኖረ ነገን ለማለም በግሉ ሳይሆን በጋራ ተፈጥሮን
ለመግራትና ገዝቶ ለመኖር ጥሯል፤ እየጣረ ነው፤ ነገም ይጥራል፡፡ ታዲያ ተፈጥሮን ያክል ኃይል አስገኝውንና
አስተዳዳሪውን በግልጽ ማግኘት በማይቻልበት ዓለም ገርቶ ለማለፍ ማህበረሰባዊ ህግ ይወጣል
ይተገበራል፡፡ ይህን ከሚያደርግበት ሁኔታ አንዱ ሰርግ ሲሆን ማህበረሰባዊ ህልውናውን ሰላማዊና ቀጣይ
ለማድረግ ሰርግን እንደ ተቋም /ህሊናዊ ተቋም/ የአፈጻጸም ሂደቱን እንደ ህግ በመጠበቅና በማስቀጠል
በአንድነት በሚኖርበት ዓለም ላይ ዝምድናን በተለያዬ መልኩ ለመመስረት ጥረት ያደርጋል፡፡ ይህም ጥናት
ዝምድናን ለመመስረት ከሚጠቀምባቸው ማህበራዊ አውዶች መካከል አንዱ የሆነውን ሚዜነት
በማንሳት፤ ለመሆኑ ሚዜና ሚዜነት ለራያ ቆቦ ወረዳ ማህበረሰቦች ምንድነው ዋና ዓላማውስ የሰርግ ሥነ-
ስርዓቱና ማጀብ ብቻ ነው ወይስ ከዛ ያለፈ ፋይዳ አለው የሚለውን በማሳየት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡

ጋብቻ የሁለት ጥንዶችን አንድ መሆን የሚያመላክት ሲሆን ሰርግ ከነዚህ ጥንዶች አንድ መሆን ባለፈ
ለአንድነታቸው መነሻ ከሆነው ሀሳብ ጀምሮ እስከ ጋራ ህይወታቸውና እስከ መጨረሻ ጥምረታቸው
ያለውን ጥንዳዊ፣ ቤተሰባዊ አልፎም ማህበረሰባዊ ሁነቶችን የሚያጠቃልል ሰፊ ስርዓተ ከበራ ነው፡፡ ሰርግ
ማህበራዊ እንደመሆኑ መጠን ሂደቱም ሆነ ህግጋቱ ማህበረሰባዊ ናቸው፡፡ ሂደቱም የሚከወነው በማህበረ-
ባህላዊው ሥርዓተ-ከበራ ነው፡፡

የሰርግ እሳቤ የሰው ልጆች ዘመናትን ተሻግሮ ለመኖርና ህልውናቸውን ለማስቀጠል ካላቸው ጥልቅ ፍላጎት
ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ይህንን ጥልቅ ፍላጎታቸውን እውን ለማድረግና ስርአቱን ማህበራዊ እውቅና
ለማሰጠት ስፊ ስርአተ ከበራ በማዘጋጀት ያጸድቁታል፡፡ በዚህ ወቅት ያለውን ክዋኔ፣ ቁሳዊ ትዕምርት፣
የሚዜሙና የሚባሉ ስነቃሎች፣ የስርአተ ከበራው ባህላዊ አፈጻጸም ሂደትና የመሳሰሉት በበርካታ የዘርፉ
ምሁራንና ፍላጎቱ ባላቸው አማተሮች በየጊዜው ጥናት ተደረጎባቸዋል፡፡ በዚህም የዚያን ማህበረሰብ
ማንነት፣ እሴት፣ ፍላጎት፣ ስነ-ልቡና ጥበብና የመሳሰሉ ጉዳዩችን በውል ለመረዳት ተችሏል፡፡ በዚህ ጥናት
የተዛማጅ ጽሑፍ ቅኝት ላይ የቀረበውን የሙሉቀን የኔሰው ጥናትን ለማሳያነት ያክል ብናነሳ በባሶ ሊበን
አካባቢ የሚከወነውን ባህላዊ የሰርግ ስነ-ስርአት በማጥናት ሰርግ በማህበረሰቡ ዘንድ እንዴት የለውጥ
ሽግግር ማሳያ እንደሆነ፣ በቀድሞ የነበሩ የትጭጭት ስርአት መስፈርቶችና በሙሽሪትና ሙሽራው ላይ
ስላለው ጫና ወዘተ በማንሳት በስርአተ ከበራው ማሳያነት ማህበረሰቡን እንድናየውና እንድንመረምረው
አድርጋናለች፡፡ በአጠቃላይ ማህበረሰባዊ ማንነቶችን በውል ለመረዳት ማህበረሰባዊ ስርአተ ከበራወችን

3
ማጥናት ጥልቅና እውናዊ መልስ ለማግኘት መሰርት እንደሆኑ መመልከት ይቻላል፡፡ በዚህም ጥናት በሰርግ
ስርአተ ከበራ ውስጥ የሚካተተው ሚዜና ሚዜነት በራያ ቆቦ ማህበረሰብ እንዴት ይገለጻል? ምን
አስተዋጽኦስ አለው የሚለውን ለማወቅ ከስርግ ለይቶ ብቻውን ማጥናት ተገቢ መልስ እንደሚያስገኝ
በማመን ነው ጥናቱ የሚከናወነው፡፡

የጥናቱ ዋና ትኩረት ከይዘት አንጻር ሚዜና ሚዜነት ላይ የሚመሰረት ሲሆን ሰርግ በየትኛውም ማህበረሰብ
ዘንድ እንደየ ባህሉ ስርአት፣ ወግ፣ የአተገባበር ልማድ፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታ ወዘተ ልዩልዩ የከበራ
ሂደቶች ያሉት ሲሆን ሚዜነትም እንዲሁ እንደዬ ማህበረሰቡ ባህለ ማህበራዊ ሁኔታ ይለያያል፡፡ ይህ
ጥናትም በራያ ቆቦ ወረዳ ማህበረሰብ ብሎ ከቦታ አንጻር ወስኖ የተነሳው ይህንን ልዩነት ታሳቢ አድርጎ ያ
ማህበረሰብ ለሚዜና ሚዜነት ያለውን አስተሳሰብ፣ ፍልስፍናና እምነት በውል መርምሮ ለመመልከት
በማሰብ ነው፡፡

በአጠቃላይ በባህልና ፎክሎር መነጸርነት የአንድን ማህበረሰብ ማንነት፣ ዕውቀት፣ ልምድ፣ አሰራር ወዘተ
ለማወቅ በፊት በአንትሮፖሎጅስት ባለሙያዎች ከዚያም በባህል ተመራማሪዎች ማጥናቱ የተለመደ
ሲሆን ጥናቶቹን ስንመለከት ግን አብዛኞቹ የአፍሪካውያን ባህሎች የተጠኑት በራሳቸው ባለመሆኑ ብዙ
ክፍተቶች ያለባቸውና መደምደሚያቸውም ባህል የልማት አደናቃፊ ነው ወደሚል ያዘነበለ ከመሆኑም
ባሻገር እንደሚዜና ሚዜነት ያሉት ጉዳዮች ደግሞ ጭራሽ ያልተዳሰሱ በመሆኑ የዚህ ጥናት መጠናት
ይህንን ክፍተት ለመሙላት ያስችላል፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች ባህል አጥኝዎችም መነሻ በመሆን መንገድ
ይከፍታል፡፡

1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያቶች

ይህንን ጥናት እንዳጠና ያነሳሱኝ ምክንያቶች በዋናነት ሁለት ሲሆኑ

የመጀመሪያው እኔ ተወልጄ ባደኩበት ራያ ቆቦ አካባቢ ደገሞ ሚዜነት ምንም እንኳ መሰረቱ ሰርግ ቢሆንም
ድንገት ተመስርቶ ወዲው የሚፈርስ ተራ ጉዳይ ሳይሆን ትልቅ ግምት የሚሰጠው ማህበራዊ ሁነት
መሆኑን ስለማውቅ ይህንን ሁኔታ እራሱን አስችሎ ማጥናት ጥልቅ ማህበረ ባህላዊ እውቀት ያስገኛል
የሚል እምነት ስላለኝ ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ለማጥናት ተነሳስቻለሁ፡፡

ሁለተኛው እንደፎክሎር ተማሪነቴ ሚዜና ሚዜነት የሙሽራውና የሙሽሪት ጉዳይ በቻ ሳይሆን


የወላጆችም ጉዳይ ሆኖ መመልከቴ ለመሆኑ ሚዜና ሚዜነት ማህበረሰባዊ አንደምታው ምንድን ነው
እንዴትስ ይመሰረታል ማህበረሰባዊ ፋይዳስ ይኖረው ይሆን የሚሉትን ጥያቄወች በተጨባጭ ማህበረሰባዊ
ማሰረጃዎች ላይ በመመስረት መልስ የመስጠት ፍላጎቴ ይህንን ጥናት ለማድረግ አነሳስቶኛል፡፡

4
1.3. የጥናቱ ዓላማዎች

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በሰርግ ሥነ-ስርዓት ውስጥ የሚከወነው ሚዜና
ሚዜነት ያለውን ማህበራዊ ፋይዳ መርምሮ ማሳየት ሲሆን በስሩ ሶስት ዝርዝር ዓላማዎችም አሉት፡፡
እነሱም፡-

1. በራያ ቆቦ ወረዳ የሚዜና ሚዜነትን እሳቤ ተንትኖ ማሳየት፡፡


2. ሚዜነትን ለመመስረት የሚያስችሉና የሚከለክሉ ማህበረሰባዊ ደንቦችን ዘርዝሮ ማሳየት፡፡
3. የሚዜነትን ማህበራዊ ፋይዳ መግለጽ፡፡ የሚሉ ዝርዝር ዓላማዎችን ይዟል፡፡

1.4. የጥናቱ መሪ ጥያቄዎች

1. በራያ ቆቦ ወረዳ የሚዜና ሚዜነት እሳቤ ምን ይመስላል?


2. ሚዜነትን ለመመስረት የሚያስችሉና የሚከለክሉ ማህበራዊ ደንቦች ምን ምን ናቸው?
3. ሚዜነት ያለው ማህበራዊ ፋይዳ ምንድን ነው?

1.5. የጥናቱ ወሰን

ጥናቱ ከርዕሰ ጉዳይ አንጻር ከሀገረሰባዊ ልማድ ዘርፎች በህዝባዊ ሁነት ላይ የሚካተተውን ከበራ መሰረት
ያደረገ ሲሆን ከሥርዓተ-ከበራዎችም በሰርግ ሥርዓተ-ከበራ ስር ያለውን ሚዜና ሚዜነትን ምንነትና
ማህበራዊ ፋይዳ ማሳየት ላይ ያተኩራል፡፡

ከቦታ አንጻር ደግሞ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ላይ የተመሰረተ ሲሆን ወረዳዋ በ 4 የከተማና በ 44


የገጠር ቀበሌ የተዋቀረች ናት፡፡ ነገር ግን የሰርግ ሥርዓተ-ከበራው በተለይም የገጠሮቹ ቀበሌዎች
ተመሳሳይነት ያለው ስለሆነና ከሁሉም ናሙና ለመውሰድ ያለኝ ጊዜ፣ ገንዘብና ጉልበት በቂ ስላልሆነ ይህ
ጥናት በአረቋቴ፣ አይናማ እንዲሁም በገደመዩ ቀበሌ ላይ ናሙና በመውሰድና መረጃ በማሰባሰብ ለመስራት
አስባለች፡፡

5
ምዕራፍ ሁለት

2. ክለሳ ድርሳናት
ይህ የጥናቱ ክፍል የጥናቱን ርዕሰ ጉዳይ በተመለከተ በተለያዩ ምሁራን የተንጸባረቁ ሀሳቦች ተብራርተው
በመጀመሪያው ክፍል ማለትም በጽንሰ ሃሳባዊ ዳራ የቀረቡ ሲሆን በተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት ደግሞ ከርዕሰ
ጉዳዩ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተዛማጅነት ያላቸው ጥናቶች ተንጸባርቀውበታል፡፡

2.1. ጽንሰ ሃሳባዊ ዳሰሳ


በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የሥርዓ-ከበራ ምንነት፣ የሥርዓተ ከበራ መገለጫዎችና፣ የሰርግና ጋብቻ ምንነት
እንዲሁም ሚዜ እና ሚዜነት ምንድን ናቸው? በእነዚህ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያስ ምሁራን ምን አሉ
የሚለውን በማጣቀስ ሃሳቦቹ ተብራርተው ቀርበውበታል፡፡

2.1.1. ሥርዓተ ከበራ

የከበራ ምንነትን በተመለከተ በርካታ ፎክለረኞች ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ከበራ ምንድን ነው? ምን ላይ
ያተኩራል? እንዴት ይጠናል? አይነቶቹ ምን ምን ናቸው? እና ከመሳሰሉት ጉዳዮች ጋር በተያያዘ
ሀሳባቸውን በጽሁፍ ካሰፈሩት በርካታ ፎክለረኞች መካከል የተወሰኑት ከሰነዘሩት ሀሳብ ውስጥ
የሚከተለውን እንቃኝ፡፡

ጽንሰ ሀሳቡን በተመለከተ ሀሳብ ካሰፈሩ ጽሁፎች መካከል አንዱ የሆነው Encyclopidia of social and
cultural antropology ከተለያዩ ትወራዎች በነሳት ‹‹ከበራ በድርጊትም ሆነ በፋይዳ ከሰዎች የእለት
ከእለት ህይወት የተለየና በውስጡ የሚፈጸሙ ድርጊቶች የተለየ ፋይዳና ትርጉም በመኖራቸው የሚከወኑ
መሆናቸውን (2002፣738)፡፡›› ይጠቁማል፡፡ ከበራን ከበራ ከሚያሰኙት ጉዳዮች አንዱ ድግግሞሽ ነው፡፡
ድግግሙ ወቅትን ጠብቆ ተደጋግሞ በመከወንና በአንድ የከበራ አውድ ላይ አንድን ድርጊት ወይም ንግግር
ደጋግሞ ማቅረብን የሚገልጽ ነው፡፡ ተመሳሳይ አከዋወን በተደጋጋሚ ሲከወን የግለሰብ ብሎም
የማህበረሰብ መለያ ይሆናል፡፡ ምንም እንኳን ከዋኝ በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀያየር ቢችልም የክዋኔ ስርዓቱ
ግን አንዴ በተፈጠረውና በማህበረሰቡ ዘንድ በተለመደው መልኩ የሚቀጥል ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ሲደጋገም
ባህሪ ይሆናል፡፡ Sims and Stephens (2005,98) እንደሚያስረዱት <… Rituals are performances that
are repeated and patterned and frequently include seremonial symbols and acions>> ይህ
ማለት ከበራዎች የሚደጋገሙ፣ ቅደም ተከተል ያላቸውና ተከታታይ የክብረ በዓል ትእምረቶችንና
ድርጊቶችን ያካተቱ ክዋኔዎች ናቸው በማለት ገልጹታል፡፡

ይህ ብያኔ የከበራን ተደጋጋሚነት በድርጊት የሚገለጹ ክንውኖች ያሉበት እንዲሁም ድርጊቶቹ


ትእምርታዊ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ ከላይ ከተሰነዘሩት ብያኔዎች በመነሳት ከበራ ታስቦባቸው
ተደጋግመው የሚከወኑና የግለሰብን ብሎም በማበረሰብ ደረጃ ሊፈጸሙ የሚችሉ እደሆነ እንረዳለን፡፡

6
ሥርዓተ ከበራዎችን ስናይ ሁለት አይነት የስርዓተ ከበራ አይነቶች መኖራውን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
እነዚህም የከፍተኛ አውድ የበዓል ስነስርዓትና የዝቅተኛ አውድ በዓል ስነስርዓት ናቸው፡፡

Sims and Stephens (2005,99) ይህ ሲገልጹ የዝቅተኛ አውድ የበዓል ስነስርዓት


የምንለው ዝግጅቱ አስቀድሞ የማይነገርለትና እቅድና ዝግጅት የማይጠይቅ ከመሆኑም
በላይ በታዳሚም ሆነ በከዋኝ ብዙ ጊዜ የማይሰጠው በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን የበዓል
ስነስርዓት ነው፡፡ የከፍተኛ አውድ የበዓል ስነ-ስርዓት የምንለው ግን የሆነ ዓላማን ለማሳካት
ተብሎ በተለይም በማህበራዊ ህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ለየት ያሉ ህይወት
አጋጣሚዎችን ለማብሰር የሚዘጋጅ አስቀድሞም ለህዝብ የሚነገርና የሚታወቅ ሰፋ ያለ
ዝግጅትን የሚጠይቅ የበዓል የአከባር ሥነስርዓት ነው ይላሉ፡፡

ከላይ ለማለት እንደተሞከረው የዚህ ጥናት ርዕሰ ጉዳይ በሰርግ ሥነ-ስርዓት ስር በሚገኘው ሚዜና ሚዜነት ላይ
የተመሰረተና የሚዜነትን ምንነትና ያለውን ማህበራዊ አስተዋጽኦ የሚመረምር በመሆኑ በከፍተኛ አውድ የበዓል
አከባበር ስነስርዓት ስር የሚመደብ ነው፡፡ ምክንያቱም ሚዜነት ድንገትና በፈለጉት ጊዜ ድንገት ሚከዎን ስርዓተ ከበራ
ሳይሆን ሰፊ እቅድና ዝግጅትን የሚጠይቅ የራሱ ማህበራዊ አፈጻጸምና ደንብ ያለው ሰርግን ሙሉ የሚያደርግ ከበራ
ነው፡፡

የታቀደ አውድ የበዓል ስነስርዓት እንዲሆን ከሚያስችሉ ጉዳዮች ውስጥ ለሰው ልጅ ወሳኝ ከሆኑት ክዋኔዎች አንዱ ሰርግ
ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማበረሰቡ ዘንድ አስቀድሞ ዝግጅት የሚደረግበትና በታቀደ ጊዜ ውስጥ አንድ ዓላማን ለማሳካት
ተብሎ የሚፈጸሙ የተለያዩ ዝግጅቶች ያሉት ሲሆን ከዚህም ዝግጅት ውስጥ ሚዜነት ዐቢይና አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ
በመሆኑ የሰርግ ሥነ-ስርዓት ጊዜ ተወስኖለት፣ እቅድ ወጥቶለጥ የሚከወን ከፍተኛ አውድ ያለው የበዓል ሥነ-ስርዓት
ነው፡፡

ሥርዓተ ከበራዎቹም ከዋኙ በፈለገበት ሁኔታ የሚያከናውናው ሳይሆኑ ራሳቸውን የቻሉ፣ የታወቁና ቅደም ተከተል
ያላቸው ናቸው፡፡ ሰዎች ሥርዓተ ከበራ የሚያደርጉባው ምክንያች የተለያዩ ናው፡፡ ተመሳሳይ በሆኑ ጉዳዮችም የሚደረጉ
ስርዓተ ከበራዎች እንደየ ባህላቸውና እምነታቸው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላል፡፡ ይህም ጥናት ከቦታ ወሰን አንጻር ወስኖ
ማስቀመጥ ያስፈለገው ለዚህ ነው፡፡

ሥርዓተ ከበራ ከሚፈጸምባቸው የህይወት ዑደት አይነቶች ውስጥ የሰርግ ሥነ-ስርዓት በግንባር ቀደምትነት ተጠቃሽ
ነው፡፡ ይህን በተመለከተ Dorson (1972፣160) ሲያስረዱ አንድ ክበረ በዓል ከሚገለጽባቸው ጉዳዮች መካከል
የሰርግ ሥነ-ስርዓት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በአንድ በዓል የሚፈጸሙ ተለያዩ ሥነ-ስርዓቶች እንደየ ማህበረሰቡ ባህል፣
እምነት እንዲሁም ልምድ የተለያዩ ቢሆኑም በዓሉ ህልውና ይኖረው ዘንድ እነዚህ ሥነ-ስርዓቶች መፈጸማቸው አስፈላጊ
ነው፡፡

የሰው ልጅ በህይወት ሲኖር ከሚያልፋቸው ወሳኝ ምዕራፎች ውስጥ ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህም ጋብቻ
ዕውቅና ለመስጠት ብሎም ማህበራዊ መሰረት ለመጣል የሰርግ ሥነ-ስርዓት ከበራ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ ሰው
ይወለዳል ያድጋል ይሞታል፡፡ በዚህ ሂደት ተወልደው ካደጉበት ቤተሰብ ተነጥለው በእንድ ጣራ ስር /ቤት/
የሚኖሩበትና በኃይማኖታዊም ሆነ በባህላዊ ሰርግ ሥነ-ስርዓት አማካኝነት ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ዘር የመቀጠል

7
የህጋዊና የመንፈሳዊ መሰረት የሚጣልበት ሥርዓተ ከበራ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል በሰርጉ ሥነ-ስርዓት ላይ የሚፈጸሙና
የማህበረሰቡን ህልውና ሊያስጠብቁ የሚችሉ ባህልና እምነታውን የሚገልጹበት፣ መተባበርና አንድነታቸውን
የሚያሳዩበት ሥነ-ስርዓቶች ያሉት በመሆኑ ክብረ በዓሉ ህልውና ኑሮት እንዲቀጥል አስችሎታል፡፡

አንድ ማህበረሰብ በሰርግ ሥነ-ስርዓት ላይ የራሱን ባህል፣ እምነት፣ ወግና ፍልስፍና በተለያዩ ክዋኔዎች ይገልጻል፡፡ ያ
ማህበረሰብ ትውልዱን ሊቀርጽ በፈለገበት መንገድ በመቅረጽ ህልውናቸውን ያስጠብቁበታል፡፡ ይህንን በተመለከተ
Chatherine (1997፣19) ስታስረዳ ‹‹በአንድ የሰርግ ሥነ-ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የተለያዩ ሥነ-ስርዓቶች የማህበረሰቡ
ማንነት ማሳያ እና የባህሉ መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማህበረሰቡ አባል የሆነ ሰው በክብረ በዓሉ መከወን ያለባቸውን
የተለያዩ ሥነ-ስርዓቶች የሚፈጽሙት በጉዳዩ ላይ ሙሉ እነምት ስለሚኖራቸው ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

ከዚህ ሃሳብ መረዳት የሚቻለው ምንም እንኳን በአንድ ክብረ በዓል ውስጥ ያሉ ጉዳዮች በሙሉ ሥነ-ስርዓቶች ናቸው
ብለን ማለት ባንችልም በአንድ ክበረ በዓል ውስጥ በተግባር ሚንጸባረቁና የሚፈጸሙ የተለያዩ ሥነ-ስርዓቶች
መኖራውን ከዚህ ሀሳብ መረዳት እንችላለን፡፡ የዚህ ጥናት ርዕሰ ጉዳይ የሆነው ሚዜና ሚዜነት በሰርግ ሥነ-ስርዓት ላይ
በሚፈጸሙ ተግባራት የማበረሰቡ አባላት በየማህበረ ባህላዊ አደረጃጀታቸው በሚከውኗቸው ተግባራት በስነ ልቦና፣
በቁስና በአካል ብዙ ሁነው ሳለ ሲተባበሩ እንመለከታቸዋለን፡፡ እነዚህም ተግባራት ከመተጫጨት ጊዜ
ጀምሮ እስከ ግጥግጥ/የቤተሰብ ትውውቅ/ ድረስ በተለያየ ሥርዓተ ከበራ የሚንጸባረቅና በግልጽ
የሚፈጸሙ ሀገረሰባዊ ድርጊቶች ሲሆኑ ሚዜነትን በዚህ ውስጥ እጅግ ጎልቶ እንመለከተዋለን፡፡

በሰርግ ሥነ-ስርዓት ከበራ ላይ ከሰርጉ ባለቤቶች ውጭ የሆኑ ወንፈልተኞች የሚፈጽሟቸው


ድርጊቶች ሁሉ ነገ ለእነርሱ የሚደረጉላቸው እንደሆኑ እርግጠኞች ናቸው፡፡ ያ እንኳ ሳይሆን ቢቀር
በዚህ ሥርዓተ ከበራ ኃላፊነታቸውን አለመወጣት ወይም አለመሳተፍ ማህበረሰባዊ መገለልን
ሊያስከትልባቸው እንደሚችል ስለሚያስቡ የግድ በከበራው ይሳተፋሉ፡፡

2.1.2. የሥርዓተ ከበራ መገለጫዎች

የስርዓተ ከበራ መገለጫዎችን Ignou (2018) Eliade (1959)ን በመጥቀስ የሥርዓተ ከበራ
መገለጫዎችን በሶስት መድበው ገልጸዋል፡፡

ሀ. ከበራ በዋናነት አራት ነገሮችን ይፈልጋል

አንድ ከበራ በሚከበርበት ጊዜ አስፈላጊና አይቀሬ ሆኑ ጉዳዮችን የሚመለከት ሲሆን እነዚህም፡-

ቦታ፡- አንድን ከበራ ለመከወን በማህበረሰቡ ዘንድ የተወሰነና የታወቀ ቦታ ያለ ሲሆን ይህ ቦታ


በአክባሪው ማህበረሰብ ዘንድ የሆነና በአብዛኛው የማህበረሰቡ አባል የተወሰነና ቋሚ ነው፡፡
በአንዳንድ ስርዓተ ከበራዎች እንደ ቅዱስ ተደርጎም ይወሰዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ እንደመከሰቻ
አጋጣሚው አስገዳጅነት ጊዚያዊ ተብሎ ተወሰነ ማክበሪያ ቦታ ሊኖር ይችላል፡፡

8
ተሳታፊ ወይም ታዳሚ፡- ይህ በከበራው ተሳታፊ ሆኑ ሁሉንም ግለሰቦች የሚመከት ነው፡፡ ማለትም
ተመሳሳይ አማኞች፣ ከበራን ለመሳተፍ የመጡ ተመልካቾች፣ እንዲሁም ከበራውን በመሪነት
የሚመሩና የሚከውኑ ከዋኞችን ከነረዳቶቻቸው የሚመከት ነው፡፡ በሥነ-ስርዓቱ ወቅትም እያንዳንዱ
ተሳታፊ የሚያበረክተው ሚና ወይም የሚያሳየው እንቅስቃሴ አለው፡፡

ለከበራው የሚያስፈልጉ ቁሶች፡- በከበራው ወቅት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ሁሉንም ቁሶች


የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህ ቁሶች ምንም እንኳን ግዑዝ ነገሮች ቢሆኑም በከበራ ስርዓት ወቅት
የተገኙበትና አስፈላጊ ሆኑበት አንዳች ፋይዳ ይኖራቸዋል፡፡ ከበራውን በተመለከተ ወክለውት
የሚመጡትና ስለማህበረሰቡ አተያይ የሚያንጸባርቁት አንዳች ትእምርትም ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም
እነዚህን ቁሶች በስርዓት መመርመር ተገቢ ነው፡፡

ቃላዊ ወይም እንቅስቃሴያዊ ምላሽ፡- ከበራዎች በጉልበት መንበርከክ፣ እጅ መንሳትና የመሳሰሉትን


አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ ጸሎት ማቅረብን፣ ዜማዎችን፣ ዝማሬዎችንና ፉከራዎችን
በድምጽ መመለስን ያካትታል፡፡ እነዚህ አካላዊ እና ቃላ ምላሾች ቃላዊ መነባንቦች፣ የተወሰነ ቅጥና
ቅደም ተከተልን የሚከተሉ ናቸው፡፡

ለ. ከበራ ታስቦበትና በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ የሚከበር ነው

ከበራ በማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ተራ በሆነ መንገድ ሚከበር ሳይሆን ታስቦበትና
ታቅዶበት በስርዓት በተደራጀ መልኩ ማህበረሰቡ ራሱን የከበራው አንድ አካል በማድረግና ደንቦችን
በመከተል የራሱን ሚና ለመወጣት የሚሳተፍበት ነው፡፡ ስለዚህም ግለሰቦች የየራሳቸውን የግል
ፍላጎትና ነጻነት ወደ ጎን በማለት ለከበራው ህግና ደንብ የሚገዙበትና ሚናቸውን የሚወጡበት
ነው፡፡ ተሳታዎች የአካ እንቅስቃሴዎቻውን፣ ገጽታዎቻቸውን እንዲሁም ቃላዊ
ምላሾቻቸውንከበራው በሚፈልገው መልኩ በተመሳሳይ ቅጥ አምባር ይከውናሉ፡፡ ስለዚህም
ለከበራው መሳካት እያንዳንዱ ግለሰብ የየራሱን አስተዋጽኦ መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ ይህ የሚሆነው
በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ ነው፡፡

ሐ. ከበራ በተደጋጋሚና ስልታዊ በሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ ይከወናል

ከበራዎች የሰውን ልጅ አካል የአምልኮ ተግባር ግልጽ ማሳያዎች መሆናቸውን የሚያሳዩ ናቸው፡፡
የሰው ልጅ አካል በጣም አስፈላጊ ሆነ የኃይማታዊ ተግባራት አካል ነው፡፡ ይህም ማለት በአንድ
በቀረበ ኃይማኖታዊ ተግባር ውስጥ አለዚያም በማህበረሰባዊ ክዋኔ ውስጥ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎችና
አካላዊ ምልክቶች ቅጥ መያዝ ብቻ ሳይሆን ተግባራቱን ወደውስጥ ማዋሀድን ጭምር ሚጠይቅ
ነው፡፡ ይህ አስፈላጊነት የሚረጋገጠውም የሰው ልጅ ከህጻንነት ጊዜው ጀምሮ ዓለምን እየተገነዘበ
ያድግና ይህ ግንዛቤ በወጣትነት ጊዜ የሚኖርን የቦታ፣ የጊዜ፣ የቁጥርና የማንነት አተያይን ወይም
ልምድን ያስጠብቃል፡፡ ስለሆነም በከበራ ውስጥ ስልታዊ የተደራጀና ተደጋጋሚ የሆነው ድርጊት ቅጥ

9
የያዘውን የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያመጣ ብቻ ሳይሆን የሰውነት አካል ከተቀደሰው አካል ጋር
ወይም ማህበረሰባዊ ክዋኔ ጋር ያለውን ተግባቦትም የሚያስጠብቅ ነው፡፡ ይህ ቅጥ ያለው ድግግሞሽ
ከባህሉ ውጭ ለሆነ ተመልካች ትርጉም የለሽ ቢመስልም ለባለቤቶችና ከዋኞች ግን ቅርጽ ያለውና
ትርጉም ሰጭ ነው፡፡

2.1.3. ጋብቻ

ጋብቻ የምንለው ማህበራዊ ተቋም ሲሆን ከሰው ልጆች አብሮ መኖር ጋር ተያይዞ የመጣ
የዝምድና መመስረቻ መንገድ ነው፡፡ ጋብቻ ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ቁርኝት ፈጥረው የሚያዋቅሩት
አንድነትና በሂደት የሚያፈሩትን ቤተሰብና ንብረት ጭምር የሚመሩበት ማህበራዊ ተቋም ነው፡፡
ጋብቻ ከህይወት ወሳኝ ክዋኔዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ የተለያዩ ምሁራን ይገልጻሉ (የተሻሻለው
የቤተሰብ ህግ፣ አያሌው ሲሳይ)፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያትም ሰዎች ከአንደኛ የህይወት ገጽታ ወደ ሌላ የሚሸጋገሩበት፣ በስነ ልቦና፣


በአካል፣ በቁስና መሰል ጉዳዮች ከሌሎች ጋር ህብረት ከሚፈጥሩበት መንገዶች ውስጥ አንዱና
ዋነኛው በመሆኑ ነው፡፡ የጋብቻ ስነስርዓት ከሰርግ ስነስርዓት ውስጥ አንዱና ቀድሞ የሚጀመረው
ሲሆን ይህም ከሽምግልና ወይም መተጫጨት ይጀምራል፡፤ ከመተጫጨቱ ሥነ-ስርዓት ጀምሮ እስከ
ግጥግጥ /ቤተሰባዊ ትውውቅ/ እንደየ ማህበረሰቡ ባህል በሚከወኑ ልዩ ልዩ ስርዓቶች ይፈጸማል፡፡
ጋብቻ በሁለቱ ተጋቢዎች መካከል በሚፈጸም ውል የሚጸና ሲሆን እንደ ተጋቢዎቹ ፍላጎትና ባህል
በሁለቱ ስምምነትና በአዋዋዮች ምስክርነት አለዚያም በማህበረሰቡ ሽምግልና እንዲጸና ሊደረግ
ይችላል፡፡

2.1.4. ሰርግ

የሰርግ ሥነ-ስርዓት በሁሉም ማህረሰብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ነው፡፡ ይህ ስነ-ስርዓትም
ተጋቢዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ዘመዶቻቸው ስለጋብቻው የተሰማቸውን ደስታ የሚገልጹበት ነው፡፡
እንዲሁም ሁለቱ ተጋቢዎች በትዳሩ ዓለም ወደፊት የሚኖራውን ኃላፊነት ማስተዋወቂያ መንገድ
ከመሆኑም በላይ በትዳር ዓለም ለመጣመራቸው ይሁንታ የሚያገኙበት ነው፡፡ ጋብቻ በሁለቱ
ተጋቢዎች መካከል ብቻ ሊፈጸም ይችላል፡፡ ሰርግ ግን ቤተሰባዊ ሲሰፋም ማህበረሰባዊ አንድነትን
እና ትብርን የሚጠይቅ በውስጡ በርካታ ንዑሳን ከበራዎች የሚካተቱበት ባለሰፊ አውድ ስርዓተ
ከበራ ሲሆን በዚህ ሂደት ውስጥ ሚዜነት የሰርግ ሃሳቡ ሳይኖር በፊት አልያም ከሰርጉ ሃሳብ ጀምሮ
የሚጀምርና ከሰርጉም ቡሃላ የሚቀጥል ትልቅ ማህበራዊ ትስስር ነው፡፡

10
2.1.5. ሚዜ

ሚዜ የሚለውን ቃል የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር (2004) የዮሐንስ ወንጌል ም.3፣19 ን


በመጥቀስ ሲተረጉመው ‹‹ሚዜ በጋብቻ ጊዜ የሙሽራውና የሙሺሪት ዋና ረዳት ነው፡፡›› ይለዋል፡፡
ከዚህ ትርጓሜ እንደምንረዳው ሚዜ የሁለቱ ተጋቢዎች የቅርብ ረዳትና ለአንድነታቸው አጋዥ
የቅርብ ሰው መሆኑን እንረዳለን፡፡

2.1.6. ሚዜነት
ሰዎች አንድነትን፣ ዝምድናን፣ ቅርርብን ወዘተ… ከሚመስረቱባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ በሰዎችች
መካከል ሊከሰት የሚችል መስተጋብር ሲሆን ማህበራዊ አንድነት በሰዎች መካከል ያለን የተለያየ ቅጥ
መዋኸድና እድሜን መሰረት ያደረገ ቅርርብን የሚያመለክት እንደሆነ ራህመት ታጁ(2021) ትገልጻለች፡፡
እንደራህመት አገላልጽ ሰዋዊ ግንኙነቶች ብዙ ጊዜ በሰዎች መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ
በማሳደር የጋራ አንድነትን የሚያመቻች የግንኙነት ሂደት ነው፡፡ እያንዳንዱ መስተጋብር ከፍተኛ፣ መካከለኛ
ወይም ዝቅተኛ እንዲሆን ምክንያት የሚሆነው የግንኙነቱ ቅጥና የግንኙነቱ ተሳታፊዎች መስተጋበራዊ
የድግግሞሽ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ መስተጋብር ከሌሎች ሰዎች ተጓዳኝ ምላሽ እንዲፈጠር ታልሞና
ስልታዊ በሆነ መንገድ ባለማቋረጥ የሚከወን ድርጊት መሆኑን ያሳየናል ትላለች፡፡ ከዚህ አገላለጽ
የምንረዳው የሚዜነት ግንኙነት ከሰርግ ሃሳብ ጋር እኩል ወይም ቀድሞ ሊጀመር የሚችል ሲሆን
የድግግሞሺ መጠኑም ሆነ የግንኙነት ቆይታው ምናልባትም በተጋቢዎች መካከል ፍች እንኳ ቢፈጠር
በዚያም የማይቋረጥና ዘላቂነት ያለው የአንድነት ድልድይ መሆኑን ነው፡፡

በማህበራዊ ግንኙነት ጊዜ የመስተጋብሩ መሰረት የሆኑ ሰዎች(ግለሰቦች) ግንኙነታቸው እንዲጠብቅ ወይም


እንዲላላ ሊያደርግ የሚችል የጋራ ፍላጎት ነው፡፡ የጋራ ፍላጎት ይሁን እንጅ የግለሰብ እሳቤ በውስጡ
አለበት፡፡ ይህ ከግል አልፎ ማህበራዊ መስተጋብርን የፈጠረው እሳቤ የአንድነት መሰረተ ወይም ቅጥ ነው፡፡
በዚህ ስር ፈቃድ፣ ግጭት፣ መላመድና ተቃውሞ ያሉ ሲሆን በማህበራዊ መስተጋብሩ ውስጥ እየተገፋፉም
ቢሆን ሳያፈነግጡ አብረው ይቀጥላሉ፡፡

ተስማምተው እራሳቸውን ወደ ሚዜነት ያመጡ ሰዎች አብረው ለመዘለቅ የጋራ ግንዛቤ፣ ዓላማ፣
መግባባት፣የውይይት ጊዜና የጋራ ተጽዕኖ መሰረት ናቸው፡፡ ሰዎች ለመስማማት ወይም ተቃውሟቸውን
ለማሰማት በነገረ ጉዳዩ ወይም ሁነቱ ምንነት ላይ እውቅና ወይም ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ያ ግንዛቤ
ሰዎችን የጠበቀ አንድነት እንዲኖራቸው ወይም ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ የጠበቀ አንድነት መኖሩን
ወይም ልዩነት መፈጠሩን ለመለካት መስፈርት ይሆናል፡፡

2.1.6.1 አንድነት

አንድነት ሁኔታዊ ድጋፍ ወይም ለአንድ ጉዳ መፈፈጸም ወይም ለሌሎች ፍላጎት መከበር
መተባበርን የሚመለከት ጽነሰ ሀሳብ ነው፡፡ ሁለትና ከዚያ በላይ ሰዎች አንድ ላይ ሲሰባሰቡና የጋራ

11
ግብን ለማሳካት ሲተባበሩ ስለ አንድነት እንነጋገራለን፡፡ አብሮነት ቁስንም ሆነ ስሜትን ለሌሎች
ማካፈል ነው፡፡ ይህም በብዙሀን መካከል የጋራ ትብብርን ይፈጥራል፡፡ ከዚህ አንጻር ቀይ መስቀል
በጦርነትና በሁከት የተጎዱትን ህይወትና ክብር መጠበቅንና መልሶ መገንባትን የሚያካትት የአብሮነት
መርህ ላይ የተመሰረተ ሰብአዊ ተልእኮ ለው ገለልተኛ ድርጅት በመሆኑየአብሮነት ምልክት ተደርጎ
ሊወሰድ ይችላል፡፡ አንድነት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገነባው ከጽንሰት ጀምሮ እስከ ሞት ሲሆን
በጽንስ ጊዜ የሚደረጉ ስርዓተ ከበራዎች፣ ልጆችን የምናሳድግበት ስነ-ቃሎች፣ ወጣቶች ከቤት
ወጥተው ጎጆ የሚመሰርቱበት ስርዓተ ከበራ፣ ሰዎች በሞት ሲለዩ የሚደረደር ሙሾና የቀብር ስነ-
ስርዓት በአጠቃላይ የማህበረሰባዊ አንድነት ማጥበቂያ ስልቶች ናቸው፡፡

2.1.6.2 የአንድነት መከሰቻዎች

አንድነት ሁለትና በላይ በሆኑ ነገሮች መካከል ሊከሰት የሚችል መስተጋብር ሲሆን ማህበራዊ አንድነት
በሰዎች መካከል ያለን የተለያየ ቅጥ መዋኸድ የሚያመለክት ሲሆን አንደ ራህመት ታጁ (2021) አገላለጽ
የሚከተሉት መከሰቻዎች አሉት፡፡

2.1.6.2.1 መስተጋብር

ይህ በሰዎች መካከል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጽዕኖ በማሳደር የጋራ አንድነትን የሚያመቻች የግንኙነት
ሂደት ነው፡፡ እያንዳንዱ መስተጋብር ከፍተኛ፣ መካከለኛ ወይም ዝቅተኛ እንዲሆን ምክንያት ሚሆነው
የግንኙነቱ ቅጥና የግንኙነቱ ተሳታፊወች መስተጋበራዊ የድግግሞሽ ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ መስተጋብር
ከሌሎች ሰዎች ተጓዳኝ ምላሽ እንዲፈጠር ታልሞና ስልታዊ በሆነ መንገድ ባለማቋረጥ የሚከወን ድርጊት
መሆኑን ያሳየናል፡፡

2.1.6.2.2. የግንኙነት ቅጥ

በማህበራዊ ግንኙነት ጊዜ የመስተጋብሩ መሰረት የሆኑ ሰዎች(ግለሰቦች) ግንኙነታቸው እንዲጠብቅ ወይም


እንዲላላ ሊያደርግ የሚችል የጋራ ፍላጎት ነው፡፡ የጋራ ፍላጎት ይሁን እንጅ የግለሰብ እሳቤ በውስጡ
አለበት፡፡ ይህ ከግል አልፎ ማህበራዊ መስተጋብርን የፈጠረው እሳቤ የአንድነት መሰረተ ወይም ቅጥ ነው፡፡
በዚህ ስር ፈቃድ፣ ግጭት፣ መላመድና ተቃውሞ ያሉ ሲሆን በማህበራዊ መስተጋብሩ ውስጥ እየተገፋፉም
ቢሆን ሳያፈነግጡ አብረው ይቀጥላሉ፡፡

2.1.7. የአንድነት መለኪያዎች

አንድነት ውስብስብ ባለብዙ ደረጃና ሁለገብ ሂደት ሲሆን በዚህ ጊዜ መግባባት፣ ግንዛቤ፣ ግንኙነትና የጋራ
ተጽዕኖ የአንድነቱን ደረጃ ይለኩልናል፡፡

12
2.1.7.1. ግንዛቤ

ለማህበራዊ አንድነት የጋራ ግንዛቤ መሰረት ነው፡፡ ሰዎች ለመስማማት ወይም ተቃውሟቸውን
ለማሰማት በነገረ ጉዳዩ ወይም ሁነቱ ምንነት ላይ እውቅና ወይም ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ያ ግንዛቤ
ሰዎችን የጠበቀ አንድነት እንዲኖራቸው ወይም ራሳቸውን እንዲያገሉ በማድረግ የጠበቀ አንድነት መኖሩን
ወይም ልዩነት መፈጠሩን ለመለካት መስፈርት ይሆናል፡፡

2.1.7.2. መግባባት

በሰዎች መካከል አንደነት መኖሩን የምንለካበት የመጀመሪያው መለኪያ መግባባት ሲሆን በሰዎች መካከል
አንድነት ተፈጥሯል ለማለት በጉዳዩ ወይም ሁነቱ ላይ ያላቸውን መግባባት መመልከት ግድ ነው፡፡ በጉዳዩ
ወይም ሁነቱ ላይ መግባባት በሌለበት ሁኔታ አንድነት አለ ለማለት አይቻልም፡፡

13
2.1.7.3. ግንኙነት

ሰዎች ባላቸው ግንዛቤ መሰረት እና በሚፈጥሩት መግባባት መሰረት የሚፈጥሩት መስተጋብር ወይም
ግንኙነት ሲሆን ይህ ግንኙነት የተጠናከረ ወይም የላላ እንዲሆን የሚያደርገው ማህበራዊ ቅጡ ወይም
የጋራ ሁነቱ ነው፡፡ የጋራ ሁነቱ የሚከወንበት ድግግሞሽ መብዛት ግንኙነትን የጠበቀ ማነሱ ደግሞ
በተቃራኒው የላላ እንዲሆን ሊያደርገው ይችላል፡፡

2.1.7.4. የጋራ ተጽዕኖ

በሰው ልጅ የማህበራዊ ህይወት ውስጥ የጋራ ተፅዕኖ አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ሰዎች ለራሳቸው
ፍላጎት በመታዘዝ ወይም ከማህበራዊ መገለል ለመዳን ሲሉ የሚገዙባው ያልተጻፉ ማህበረ ባላ
ደንቦች አሉ፡፡ የእነዚህ ደንች የአፈጻጸም ሁኔታ እንደ ማህበረሰቡ ስምምነት የሚወሰን ሲሆን
ለጠበቀ ወይም ለላላ አንድነት ምክንያ ይሆናሉ፡፡

በዚህ ጥናት የራያ ቆቦን የሚዜና ሚዜነትን ትርጉም እንዲሁም ማህበራዊ ፋይዳ ለማየት እነዚህ
ጉዳዮች ማለትም አንድነትና የአንድነት መከሰቻዎች ሃሳቦቹን የበለጠ ተጨባጭ ለማድረግ ያግዛሉ፡፡

2.2. የተዛማጅ ጥናቶች ቅኝት


ይህ ክፍል ቀደም ሲል የተጠኑና ከዚህ የጥናት ርዕሰ ጉዳይ ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተዛማጅነት
ያላቸው ጥናቶች ተዳሰዋል፡፡ ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር ተያዥነት ያቸውን ጥናቶች ለማግኘት የተደረገው ዳሰሳ
ሰፊ ነው ለማለት አያሥችልም፡፡ ምክንያቱም አሁን ባለው ወቅታዊ ሃገራዊ የሰላም ችግር ምክንያት
የኢንተርኔት ችግር በመኖሩና ከቦታ ቦታ ለመዘዋወርም አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ነገር ግን የተለያ
አማራጮችን በመጠቀም አጥኝዋ ባደረገችው ዳሰሳ ከርዕሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ጥናት ለማግኘት
አልቻለችም፡፡ ነገር ግን ከጥናቷ ርዕሰ ጉዳይ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ሁለት ጥናታዊ ስራዎች ከጥናቷ ጋር
እያዛመደች ያላቸውን ተመሳስሎና ልዩነት ለመመልከት ሞክራለች፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ዳሰሳ የተደረገበት ጥናታዊ ስራ በጅማ ዩንቨርሲቲ በ 2001 ዓ.ም በጣሂር አሊ የተሰራው
‹‹በባህላዊ /Kaadhimmachuu/ የጋብቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የሚፈፀሙ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች ትዕምርታዊ
ጉዳዮች ይዘት ትንትና›› የሚለውን ስራ ሲሆን የዚህ ስራ ዋና ዓላማ በባህላዊ የጋብቻ ሥነ-ስርዓቱ ላይ
የሚፈፀሙ ሃገረሰባዊ ዕምነቶች ጉዳዮችን መተንተንና መተርጎም ሲሆን በዚህ ጥናት ውስጥ የመረጃ
ትንተናውን ሂደትን ስናይ በጋብቻ ሥነ-ስርዓቱ ውስጥ የሚዜና ሚዜነትን ሚና ተንትኖ ተመልክቷል፡፡

በወንዱ ሙሽራ ቤት የሚካሄድ የወዳጅ ዱኣ በሚል ንኡስ ርእስ ስር ‹‹… ሙሽራው ከሚዜዎቹ ጋር
በመሆን በአቅራቢያ ካለው ከተማ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማሟላት እንደሄዱ ማወቅ ተችሏል፡፡
…››(ከገጽ 61 ጀምሮ)

14
በተጨማሪም ከመረጃ ምንጭና መሰብሰቢያ ዘዴ አንጻር እንዲሁም ጋብቻ ላይ በመመስረት በኩል ደግሞ
አንጻራዊ ተመሳስሎ አላቸው፡፡ ጣሂር የጋብቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመመስረት የትዕምርታዊ ጉዳዮችን ይዘት
ሲተነትን ይህ ጥናት ደግሞ በጋብቻ ላይ በመመስረት በሰርግ ሥነ-ስርዓቱ ስር ያለውን ሚዜና ሚዜነት
ምንነትና ማህራዊ ፋይዳ ለመተንተን ይሞክራል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የሙሉቀን የኔሰው ‹‹የለውጥ ሽግግር በባሶ ሊበን ማህበረሰብ ባህላዊ የሰርግ ስነ-
ስርዓት የተሰኘ ምርምር በመፈተሸ ከዚህ ጥናት ጋር ያለውን ዝምድና በተመሳስሎና ልዩነት በመዳሰስ
ቀርቦበታል፡፡ የዬኔሰው ጥናት ከቦታ አንጻር ከዚህ ጥናት ጋር ፈጽሞ የማይገናኝ ቢሆንም ከርዕሰ ጉዳዩ
አንጻር ግን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይገናኛል፡፡

የሙሉቀን የኔሰው ጥናት ዋና ዓላማ የባሶ ሊበን ማህበረሰብን የሰርግ ሥነስርዓት ክዋኔን በማሳየት የለውጥ
ሽግግር ሂደቱን መመርመር ሲሆን የዚህ ጥና ዋና ዓላማ ደግሞ የሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ በሰርግ ሥነ-
ስርዓት ስር የሚከወነው የሚዜነት ስርዓት ምንነቱንና ማህበራዊ ፋይዳውን መርምሮ ማሳየት ነው፡፡
ከዓላማ አንጻር እነዚህ ጥናቶች የሰርግ ሥነ-ስርዓትን ማሳያ ወይም መሰረት ማድረጋቸው ሲያመሳስላቸው
የሙሉ ቀን ጥናት በሰርግ ሥነ-ስርዓቱ የለውጥ ሽግግር ሂደት ላይ ሲያተኩር ይህ ጥናት ደግሞ በሰርግ ሥነ-
ስርዓቱ ስር የሚካተተውን ሚዜና ሚዜነት ምንነትና ባለው ማህበራዊ ፋይዳ ላይ ያተኩራል፡፡ ሙሉቀን
በጥናቷ ከአቢይ ዓላማው የመነጩ ዝርዝር ዓላማዎችን ያስቀመጠች ሲሆን ዓላማዎቹ የሰርግ ሥነ-ስርዓቱ
እንዴት ለሽግግር አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ የሚያሳዩ ሲሆኑ ከቀዳማይና ከካልአይ የመረጃ ምንጮች
በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በቡድን ተኮር ውይይት መረጃ ትሰበስባለች፡፡ የሰበሰበቻቸውን መረጃዎች በስነ
ልቦናዊና ተግባራዊ ንድፈ ሀሳቦች መቀንበቢያነት ተንትና አቅርባለች፡፡

ከዚህ አንጻር ይህ ጥናትም ከአቢይ ዓላማዎቹ የወጡ ዝርዝር ዓላማዎች ያሉት ሲሆን በሰርግ ሥነ-ስርዓቱ
ማሳያነት የሚዜና ሚዜነትን ምንነትና ማህበራዊ አስተዋጽውን ከራያ ቆቦ አንጻር የሚያሳ ነው፡፡ ከዚህ
አንጻር ሁለቱ ጥናቶች ይለያያሉ፡፡ በተጨማሪም ሙሉቀን ሥነ ልቦናዊና ተግባራዊ ንድፈ ሀሳብን
የተጠቀመች ሲሆን ይህ ጥናት የተጠቀመው ግልጋሎታዊና ስነ ልቦናዊ ንድፈ ሀሳብን አጣምሮ ነው፡፡ ከዚያ
ውጭ የመጀመሪያና ሁለተኛ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀምም ይሁን በምልከታ በቃለ መጠይቅና በቡድን
ተኮር ውይይትና ሰነድ ፍተሻ መረጃ በመሰብሰብ ይመሳሰላሉ፡፡

2.3. ንድፈ ሀሳባዊ ቅኝት

2.3.1. ግልጋሎታዊ ንድፈ ሀሳብ

በፎክሎር ጥናት ውስጥ እያንዳንዱ ሎር ለከዋኙ ማህበረሰብ የሚሰጠው ባህላዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም
ስነ-ልቦናዊ ፋይዳ እንዳለው ይታመናል፡፡ ስለሆነም ተግባራዊ ንድፈ ሀሳብ ማህበረሰቡ በዕለት ተዕለት
ህይወቱ የሚከወነው ሎር ለከዋኝ ማህበረሰቡ የሙሰጠው ፋይዳ ምንድ ነው? የሚለው ሀሳብ የሚጠናበት

15
ነው፡፡ በፎክሎር ጥናት እንዲሁም በሌሎች የማህበራዊ ሳይንስ ጥናት ዘርፎች ተጽእኖ የፈጠሩ ሶስት
የተግባራዊነት ንድፈ ሀሳቦች አሉ፡፡

አንደኛው የማህበረሰብ ሎርን ከግለሰቦች ፍላጎት ማርኪያነት አንጻር የሚያየውና በ Malinowski


የሚቀነቀነው ሀሳብ ነው፡፡ ሁለተኛው የ Radcliffe – Brown ሀሳብ የሆነው ለማህበራዊ ተቋማት ቅድሚያ
የሚሰጠውና ፎክሎርን ከማህበራዊ ደንብና ተቋም ማስጠበቂያነት አንጻር የሚያየው ነው፡፡ ሶስተኛው
ማህበራዊ ውህደትና ጥምረት ለማምጣት ፎክሎር ዋና መሳሪያ (Device fore social cohesion) እንደሆነ
የሚያምነው የ Durkheim ሀሳብ ነው፡፡ (Glazer, 2011, 595-597). ለዚህ ጥናት ተመራጭ ሆነው ንድፈ ሀሳብ
ሶስተኛው ማለትም ማህበራዊ ውህደትና ጥምረት ለማጣት ፎክሎር ዋና መሳሪያ (Device fore social
cohesion) እንደሆነ የሚያምነው የ Durkheim ሀሳብ ነው፡፡ እንደ Durkheim ሀሳብ አስተሳሰብ የሰው
ልጅ መሰረታዊ ፍላጎቱ እርካታ የሚያገኘው በሚከውነው ሎር አልያም በማህበራዊ ተቋማቱ ነው፡፡
ማህበረሰባዊ ተቋማቱ የማህበረሰቡና ለማህበረሰቡ አገልግሎት ሰጭ ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ እነዚህም
አገልግሎቶች ማህበራዊ ውህደትና ጥምረት እነዲኖርና ይህም ስር ሰዶ እንዲቀጥል አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡
የግለሰብ ፍላጎት ማህበራዊ ተቀባይነት ከሌለው ስር የመስደድና የመቀጠል ህልውና አይኖረውም፡፡
የማህበረሰቡን ማንነትና ፍላጎት ለማጥናት ማህበራዊ ተቋማትንና ማህበራዊ ስርዓተ ከበራዎችን
መምርመር ጠቃሚ ነው ይላሉ፡፡ በመሆኑም ለዚህ ጥናት የ Durkheim አስተሳሰብ ተመርጧል፡፡

2.3.2. ፍካሬ ልቦናዊ ንድፈ ሀሳብ

ይህ ንድፈ ሀሳብ በስነ-ልቦና አስተምሮ ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ያለው የፍካሬ ስነ-ልቦና (Psychoanalysis)
መስራች ሲግመንድ ፍሩድን (1856-1939) አስተሳሰብ መሰረት ያደረገ ነው sims stephens (2005፣187)፡፡
ንድፈ ሀሳቡ የሰው ልጆችን ውስጣዊ አስተሳሰብ፣ ፍልስፍናና አመለካከት ለማወቅ ይጠቅማል፡፡ ሰሎሞን
(2007፣77) የፍሩይድን ሀሳብ መሰረት አድርገው የተለያዩ ፎክሎርስቶች በስርዓተ ከበራዎች፣ በሚቶች፣
በተረቶች፣ በእምነቶች፣ በሙዚቃዎች እንቆቅልሾችና ሌሎች ሎሮች ማስተላለፍ የፈለጉትን ስነልቦናዊ
ጉዳዮች ለመተንተን እንደተቻለ ያስረዳሉ፡፡

Lois (2006፣10) ዓለምን በስነ ልቦናዊ መነጽር መመልከት መቻል እያንዳንዱን ግለሰብ ህይወት ምን
እንደሚመስል ጠንቅቆ ለማወቅ ያስችላል፡፡ የአንድ ሰው የስነ ልቦና ታሪክም ከልጅነት ዕድሜው የሚጀምር
ሲሆን ቤተሰብ፣ ማህበረሰብ፣ ትምህርት ቤትና አካባቢ የሚፈጥሩት የርስ በርስ ግንኙነቶች ሁሉ የሰውን
ልጅ ስብዕናን ለመቅረጽ ወሳኝ ድርሻ አላቸው፡፡

ንድፈ ሀሳቡ የስነ-ልቦና እሳቤን ከተለያየ አቅጣጫ ከሚያይባቸው፣ ከሚመረምርባውና ከሚፈክርባቸው


ትውሮች መካከል በዚህ ጥናት ማህበረሰባዊ መስተጋብር ስነ-ልቦናን የመገንባት ቲወሪ የሚለው አገልግሎት
ይሰጣል፡፡

16
በዚህ ትውር አማካኝነት ማህበረሰባዊ መስተጋብር ከሚፈጠርባው አንዱ የሆነው በሰርግ ሥነ-ስርዓት ስር
የሚካተተው ሚዜነት እንዴት የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና አንድ ያደርጋል? በመካከላችው የሚፈጥረው
የዝምድናና ጥልቅ የጓደኝነት ፍቅር እንዴት ተመስርቶ ስር ሰዶ ይቀጥላል? የሚለውን ለመፈከር በእጅጉ
ይጠቅማል፡፡

17
ምዕራፍ ሶስት

3. የጥናቱ ዘዴ
በዚህ ክፍል የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች፣ የናሙና ዘዴና የመረጃ መተንተኛ ዘዴ የተሰኙ ንዑሳን ርዕሶች
ቀርበውበታል፡፡

3.1 የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች


ጥናቱ አይነታዊ የምርምር ዘዴን የተከተለ ነው፡፡ መረጃዎች ከቀዳማይና ከካልአይ የመረጃ ምንጮች
የሚሰበሰቡ ሲሆን የተዛማጅ ስራዎች፣ የጽንሰ ሀሳብና የንድፈ ሀሳብ ማዕቀፎችን የሚመለከቱ መረጃዎች
የሰነድ ፍተሻ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴን በመጠቀም ከቤተ መጻህፍትና ቤተ መዛግት ይሰበሰባሉ፡፡ ለጥናቱ
መሰረት የሆኑ ጥሬ መረጃዎች ደግሞ በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ውይይት ከመስክ
ተሰብስበው ይተነተናሉ፡፡

3.1.1 የምልከታ ዘዴ
በአውዳዊ ጥናት መረጃ ከሚሰበሰብባቸው ዘዴዎች ውስጥ ምልከታ አንዱ ነው፡፡ ምልከታን በተመለከተ
Gray(2004፣238) ምልከታ የሰዎችን ድርጊት በንቃት የመከታተልን፤ ትዕይንቱን በአግባቡ ቀርጾ
የማስቀመጥንና የተጠኞችን ባህሪ የመተርጎምን እውቀት የሚጠይቅ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በተመሳሳይ Gold
stein (1964,77) እንደሚከተለው ይገልጻሉ፡፡ መረጃን በቀጥተኛ ምልከታ ማግኘትና ነባራዊ ሁኔታን
እንደሚመለከቱት አድርጎ መግለጽ ነው፡፡ ምልከታ ዕይታዊ የሆነውን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡
ይልቁንም እንደየ እስፈላጊነቱ ሙሉ የስሜት ህዋሳትን ትብብር (ማሽተት፣ መዳሰስ፣ ማዳመጥ፣
መቅመስና መሰል ስሜቶችን) የሚያካትት ነው፡፡

ምልከታ እንደሚጠናው ርዕሰ ጉዳይ መለያየትና አጥኝው ከሚያጠናው የባህል ባለቤት ጋር እንዳለው
ቅርበት በሁለት መንገድ ይካሄዳል፡፡ በተሳትፏዊ ምልከታና በኢ-ተሳትፏዊ ምልከታ ሲሆን ተሳትፏዊ
ምልከታ ክዋኔውን ከሚያካሂደው ማህበረሰብ ጋር በመቀላቀልና ክዋኔውን በመከወን መረጃ የሚሰበሰብበት
ሲሆን ኢ-ተሳትፏዊ ምልከታ ደግሞ አጥኝው ዳር ሆኖ በመመልከት መረጃ የሚሰበስብበት ዘዴ ነው (SiMs
and Stethens, 2005, 220)::

ይህ ጥናት የምልከታ ጊዜው የዐቢይ ጾም ከመጀመሩ በፊት ባለው ጊዜ ለማካሄድ ታስቧል፡፡ ይህ ወቅት
የተመረጠው የገና ጾም የሚያልቅበትና የዐቢይ ጾም ደግሞ ከመጀምሩ በፊት ስለሆነና ብዙ ሰርጎች
ስለሚኖሩ ስለሚዜ አውዳዊ መረጃዎችን ከተፈጥሯዊ መቸት ለመሰብሰብ ምቹ ነው፡፡ በየሰርግ ቦታዎቹ

18
በመገኘት በየማህበረሰብ ክፍሉ ማለትም በዳሪ ቤተሰብ፣ በአስዳሪ ወንፈልተኞች፣ በሚዜዎችና አጠቃላይ
የሰርግ ታዳሚዎች ይደረግ የነበረውን እንቅስቃሴ በመመልከትና አስፈላጊ ሲሆን በመሳተፍ አንዳንዴም
ከዳር ሁኖ በመመልከት በሥርዓት ከበራው ወቅት ተሳታፊ ከሆኑት ሁሉና በተለይም ከራሳቸው ከሚዜወቹ
አባላትና ከሚዜ አለቆች መረጃ መሰብሰብ ያስችላል፡፡ ይህንንም የሚያስረዱ መረጃዎችን በመቅረጽ እና
በመጻፍ ምልከታው ይካሄዳል፡፡

3.1.2 ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠይቅ በአጥኝውና በመረጃ አቀባዩ መካከል በቃል የሚካሄድ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ነው፡፡ ‹‹An
interview is a conversation between people in which one person has the role of researcher. (Gray,
2004, 213)፡፡

በምልከታ ወቅት ግልጽ ያልሆኑ ድርጊቶችና ስሜቶች እንዲሁም የአንዳንድ ክንውኖችን አንድምታዊና
ባህላዊ ትርጉም ለማወቅ ከቃለ መጠይቅ አይነቶች ነጻ ወይም ልቅ የቃለ መጠይቅ ዘዴ አገልግሎት ላይ
ይውላል፡፡ ያለው (2009፣185-186) እንደገለጸው ነጻ ወይም ልቅ ቃለ መጠይቅ ጠያቂው በሚያጠናው ጥናት
ዙሪያ መረጃ ያስገኙልኛል ብሎ የሚያስባቸውን ጥያቄዎች በፈለገውና ለተጠያቂው ይመቻል ብሎ ባሰበው
መንገድ ማቅረብ የሚችልበት ተጠያቂው ደግሞ ነጻ ሁኖ መልስ ይሆናል ብሎ ያመነውን መረጃ የሚሰጥበት
ስልት ሲሆን ጥልቅና የተብራራ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የቃለ መጠይቅ አይነት ነው፡፡

ስለዚህም የአካባቢው ማህበረሰብ አስቦትም ይሁን ሳያስበው በስርዓተ ከበራው ላይ የሚፈጽማቸው


ተግባራት (ከቅድመ ሚዜ ምስረታ እስከ ሰርግ ማግስት ድረስ ያለውን የሚዜነት አጠቃላይ ሂደት) ምን
ያክል በስነ ልቦናዊና አካላዊ አንድነት፤ በመካከላቸው ስለሚፈጥረው ዝምድናዊ ስሜትና ጓደኝነት
ለመረዳት የሚያስችል መረጃ ነጻ ቃለ መጠይቅን በመጠቀም ይሰበሰባል፡፡ ቃለ መጠይቁን ከስድስት ቁልፍና
ከሶስት ንዑስ መረጃ ሰጭዎች ለመሰብሰብ የታሰበ ሲሆን ቁልፍ መረጃ ሰጭዎች የወንድና የሴት ሚዜ
አለቆችና ሚዜ አባላት እንዲሁም ከሙሺሮች ለመሰብሰብ የታሰበ ሲሆን የሙሺሮች እናትና አባቶች፣
አውራጅ ያዥ ግለሰቦችና ጎረቤቶች ጋር የሚደረግ ሲሆን፤ ሶስቱ ንዑስ መረጃ ሰጭዎች ደግሞ ከሰርጉ
ታዳሚዎች ፈቃደኞችን በመምረጥ የሚደረጉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም በተለይ ለማህበረሰቡ ትልቅ
ዕውቅናና ተቀባይነት ካላቸው ሰዎች ጋር በከበራው በመሳተፍና ጥያቄዎችን ኢ-መደበኛ በሆነ መንገድ
በማንሳት በጨዋታና በወሬ መልክ በመቅረጸ ድምጽና በማስታወሻ ደብተር በመጠቀም የተለያዩ
መረጃዎችን ለመሰብሰብ ይሞከራል፡፡

3.1.3 የተተኳሪ ቡድን ውይይት


የተተኳሪ ቡድን ውይይት ግልጽ ያልሆኑና ማብራሪያ የሚፈልጉ መረጃዎችን ስለ ባህሉ ያውቃሉ ከተባሉ
አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት መረጃ የሚሰበሰብበት ዘዴ ነው፡፡ ‹‹በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ በቂ መረጃ ሊኖራው
ይችላል ተብሎ የሚታሰቡ ሰዎችን በመውሰድ በሚነሳው ጥያቄ ዙሪያ በቡድን በመሆን እየተወያዩ መረጃ
እንዲሰጡ የሚደረግበት ስልት ነው፡፡›› (ያለው፣ 2009፣197)፡፡ የተተኳሪ ቡድን ውይይትን ተጠቅሞ በርካታና

19
አስተማማኝ መረጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰብሰብ እንደሚቻል እነ Schensul (1999,52) ይገልጻሉ፡፡
በመሆኑም ይህንን የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ በመጠቀም የማህበረሰቡን ባህል ከሚያውቁ አካላት ማለትም
ከሚዜ አለቆችና አባላት፣ ልጅ ከዳሩ ወላጆች፣ ከሀገር ሽማግሎችና ስለ ባህሉ የተሻለ ዕውቀት አላቸው
ከሚባሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ከተውጣጡ መረጃ አቀባዮች ጋር ቢያንስ ሶስት የቡድን ውይይቶች
ይካሄዳሉ፡፡

3.1.4 ሰነድ ፍተሻ


በዚህ ጥናት ዋናዋና የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች ምልከታ ቃለ መጠይቅና የተተኳሪ ቡድን ውይይት ሲሆኑ
ለተዛማጅ ጽሁፍ ቅኝትና ለጽንሰ ሀሳባዊ ዳሰሳ የሰነድ ፍተሻ ዘዴም ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ እንደ ያለው
(1998) አገላለጽ መዛግብት ፍተሻ ተግባራዊ የሚደረግባቸው መረጃዎች በቤተ ማጻህፍትና በቤተ
መዘክሮች ተሰብስበው የሚገኙ የታተሙና ያልታተሙ መጻህፍት ናቸው፡፡ ስለሆነም በነዚህ መጽሀፍት
ውስጥ ከጥናቱ ርዕሰ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና መረጃ ሊገኝባቸው የሚችሉ መጽሃፍት በማንበብና
ማስታወሻ በመያዝ በጥናቱ ይሰራል፡፡

20
3.2. የናሙና አመራረጥ ዘዴ
በዚህ ጥናት መረጃ ለመሰብሰብ የተመረጡ ቦታዎች በዓላማ ተኮር የናሙና ዘዴ የተመረጡ ሲሆን
በወረዳው ከሚገኙ 48 ቀበሌዎች ውስጥ በዚህ ወቅት ብዙ ሰርግ ያለባቸው ሶስት ቀበሌዎች ማለትም
አይናማ፣ አረቋቴና ገደመዩ ተመርጠዋል፡፡ እነዚህ ቀበሌዎች የተመረጡበት ምክንያት አጥኝዋ በወቅቱ ብዙ
ሰርግ ይኖርባቸዋል የሚል ሃሳብ ስላላትና አሁን ባለው ወቅታዊ ሁኔታ አንጻራዊ ሰላም ስላላቸው በቀላሉ
መረጃውን ለመሰብሰብ ያስችላል በሚል እምነት ነው፡፡ በተጨማሪም ወደ ቀበሌዎቹ ለመሄድ ከሌሎቹ
ቀበሌዎች የተሻለ ትራንስፖርት ማግኘት የሚቻሉባቸው ስለሆኑ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ መረጃ ሰጭዎችን ከወሳኝ የናሙና ዘዴዎች ውስጥ በዓላማ ተኮርና ጠቋሚ ወይም
ተያያዥ የናሙና ዘዴዎች ለመምረጥ ታስቧል፡፡ ዓላማ ተኮር የናሙና ዘዴ አጥኝው ለሚፈልገው ግብ
ይመቹኛል የሚላቸውን መረጃ አቀባዮች መርጦ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ ስለሆነም በዚህ ጥናት በዋናነት
የሚዜ አለቆችንና የሚዜ አባላት፣ የተጋቢዎች እናትና አባት፣ የአጭታ ሽማግሌዎች፣ የአውራጅ
ወንፈልተኞችና እንዲሁም ስለባህሉ የተሻለ እውቀት ያላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለመረጃ አቀባይነት
ይመረጣሉ፡፡ በሌላ በኩል በጠቋሚ ወይም ተያያዥ ናሙና አማካኝነት የተሻለ መረጃ ሊሰጡ የሚችሉ
ሰዎች ቀድመው መረጃ በሰጡ ሰዎች በሚደረግ ጥቆማ መረጃ እንዲሰጡም በማድረግ መረጃውን የበለጠ
ገላጭ ለማድረግ አስባለች፡፡

3.3 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ


በዚህ ጥናት መረጃዎቹ ከመስክ ከተሰበሰቡ በኋላ በየምድባቸው ተመድበው በገላጭ የትንተና ዘዴ
ተተንትነው ይቀርቡበታል፡፡ ገላጭ የትንተና ዘዴ በከበራው ወቅት የሚኖረውን ልዩ ልዩ ክዋኔ ዝርዝር በሆነ
መልኩ መግለጽ የሚያስችል ስልት ነው፡፡

በተጨማሪም የሚሰበሰቡ ጥሬ መረጃወችን ለመተንተን ተግባራዊና ፍካሬ ልቦናዊ ንድፈ ሀሳቦች በዚህ
ጥናት ለመረጃ መቀንበቢያነት ተግባር ላይ ይውሉ ዘንድ ተመርጠዋል፡፡ ስለሆነም ሚዜነዘ ሚዜነት በራያ
ቆቦ ያለውን ስነ-ልቡናዊ መሰረትና ፋይዳ ሊያሳይ በሚችል መልኩ ይተነተናሉ፡፡

3.4. የጥናቱ የጊዜና የበጀት ዕቅድ

3.4.1. የበጀት እቅድ

የወጪ ዓይነት

21
የጽሕፈትና የመረጃ ቋት

ተ.ቁ መሳሪያዎች ብዛት መለኪያ የብር መጠን ጠቅላላ ብር

1. የመቅረጸ ምስል ወድምጽ ኪራይ 10 በቀን 400 4,000

2. የመረጃ ቋት 32 GB 1 በቁጥር 500 500

3. ፍላሽ ዲስክ 16 GB 1 በቁጥር 500 500

4. ወረቀት 2 በደስጣ 600 1,200

5. እስኪብርቶ 10 በቁጥር 20 200

6. ማባዣ 400 በገጽ 5.00 2,000

7. ለህትመት 400 በገጽ 5.00 2,000

8. ማስጠረዣ 4 በቁጥር 200 800

ጠቅላላ ድምር 11,200

የውሎ አበልና የባለሙያ ክፍያ

22
የክፍያው ዓይነት ተግባር ብዛት መለኪያ የብር ጠቅላላ ክፍያ
መጠን

9 ለመረጃ ሰጭ ማነቃቂያ መረጃ መሰብሰብ 30 በቀን 200 6,000

10. ለመቅረጸምስል ወድምጽ ምስል ወድምጽ መቅረጽ 10 በክፍለጊዜ 300 3,000


ባለሙያ

11. መረጃ ለመገልበጥ ከምስል ወድምጽ 4 በክፍለጊዜ 500 2,000


ወደጽሑፍ መቀየር

ጠቅላላ ድምር 11,000

የትራንስፖርት ክፍያ

12 ቦታ የምልልስ የብር መጠን በአንድ ጉዞ/ደርሶ መልስ ጠቅላላ ክፍያ


መጠን

ከደሴ ራያ ቆቦ 4 ዙር 300 ብር 1,200

መጠባበቂያ 1,500

የጥናቱ አጠቃላይ በጀት 24,900

3.4.2. የጊዜ ሠሌዳ

ጥናቱ ህዳር 2016 ዓ.ም ተጀምሮ መጋቢት 24/2016 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ሲሆን በታቀደው የጊዜ ሠሌዳ
መሰረት የሚከናወኑ ተግባራት አንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት ጊዜ የአማካሪ ተመካሪ ምልልስ

1. ትልመጥናት ማዘጋጀትና በአማካሪ ህዳር 2016 -ታህሳስ 30/2016  ታህሳስ 21-ታህሳስ 30


አስተያየት እንደገና ማደራጀት

23
2. ትልመጥናቱን ማቅረብና ማስጸደቅ ከጥር 05-ጥር 15/2016

3. ተዛማጅ ድርሳናትን መከለስ ኅዳር 6/2016 - ታህሳስ 19/2016  ታህሳስ 21/2016

4. የዋናውን ጥናት መረጃ መሰብሰብ ከጥር 20/2016 - የካቲት 20/2016

5. መረጃውን መገልበጥ የካቲት 21/2016 - የካቲት 25/2016  የካቲት 30/2016

6. የዋናውን ጥናት መረጃ መተንተን መጋቢት 02/20116 - መጋቢት 5/2016  መጋቢት 6-10/2016

7. የጥናቱን ረቂቅ ዘገባ መጻፍ መጋቢት 12/2016  መጋቢት 15/2016

8. ረቂቅ ዘገባውን መከለስ መጋቢት 20/2016

9. የጥናቱን የመጨረሻ ዘገባ ማዘጋጀት እና መጋቢት 24/2016


ማቅረብ

ዋቢ ጽሁፎች
ሙሉቀን የኔሰው። (2010)። “የለውጥ ሽግግር በባሶ ሊበን ማህበረሰብ ባህላዊ ሰርግ ስነስርአት”
በፎክሎር የሁለተኛ ድግሪ ለማግኘት የቀረበ ጥናት። ባህርዳር ዩኒቨርስቲ።ያልታተመ።

ራህመት ታጁ። (2001)። የአንድነት ትርጉም። ያልታተመ

ሰሎሞን ተሾመ። (2007)። ፎክሎር ምንነቱና የጥናቱ የትኩረት አቅጣጫ። አዲስ አበባ፣ ፋር ኢስት
ትሬዲንግ ሃላ. የተ .የግ. ማ።

ያለው እንዳወቀ ሙሉ። (2009)። የምርመር መሰረታዊ መርሆዎችና አተገባበር። 3 ኛ እት. ተፈራ ስዩም
ማተሚያ ድርጂት ።

24
አያሌው ሲሳይ። (1996)። የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ። ያልታተመ፡፡

ጣሂር አሊ፡፡ (2011)፡፡ በባህላዊ (Kaadhimmachuu) የጋብቻ ሥነ-ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ሀገረሰባዊ


እምነቶች ትዕምርታዊ ጉዳዮች ይዘት ትንተና፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኤም ኤ ዲግሪ ለማግኘት
የቀረበ ጥናት፡፡

ፈቃደ አዘዘ። (2004)። “ቁዘማ:- ፎክሎር (ባህል) እና ልማት በኢትዮጵያ” ከ ሽፈራው በቀለ
(አርታኢ)። ባህልና ልማት በኢትዮጵያ። ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ አዱስ አበባ ገጽ 97-138።

Dawson, Catherine. (2009). Introduction to Research Methods: A Practical guide for anyone
undertaking a research project. 4th ed. Xford:How To Content, A division of How To
Books Ltd.

Dorsen.Richard.Folklore and folk Life introduction Chicag and London The Univeresty of
Chicago Press.1972.

Encyclopidia of Social and Cultural Anthropology.

Leung, A.K. –Y., & Cohen, D. (2011). Within- and between-culture variation:
Individual differences and the cultural logics of honor, face, and dignity
cultures, Journal of personality & Social Psychology, 100, 507-526.

Lois, T.(2006). Critical theory to day: A user-friendly guide. New York.

Glazer, Mark. (2011). Functionalism. In McCormick Charlie T. and White Kim


Kennedy, (Eds). Folklore፡ an Encyclopedia of Beliefs, Customs, Tales, Music
and Art. (595-597). California፡ ABC-CLIO, LLC

Goldestein, K. A Guide for field workers in Folkl ore. Pennsylvania: Folklore


Associates, Inc, 1964.

Gray David E. (2004). Doing Research in the Real World. London: SAGE

Publications Ltd.

Schensul J, Jean and etal. (1999). Enhanced Ethnographic Methods. New York፡ Altamira
Press.

Sims, Martha C. and Stephens, Martine. (2005). Living Folklore: An Introduction to


the Study of People and their Traditions. Logan: Utah State University Press.

25
Sims, M. C. and Stephens, M. (2005). Living Folklore: An Introduction to the Study
of People and their Tradition. Utah: Utah state university press.

26

You might also like