You are on page 1of 13

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት


መድኃኔዓለም አቢያተ ክርስቲያናት በተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት እና
በአጥቢያው ያሉት ወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት መካከል ያለው
ተግዳሮትና መፍትሔዎቻቸው
ለጥናት የተዘጋጀ ምክረ አሳብ

የጥናት ቡድኑ አባላት፡-

ሐምሌ ቀን 2014 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

Contents
1. መግቢያ...............................................................................................................................................2
2. ለጥናቱ አስፈላጊነት መነሻ ነጥቦች................................................................................................................4
3. የጥናቱ ዓላማዎች...................................................................................................................................5
3.1. ጥቅል ዓላማ?....................................................................................................................................5
3.2. ዝርዝር ዓላማዎች...............................................................................................................................5
4. የጥናቱ ይዘት (ትኩረት ነጥቦች)..................................................................................................................5
4.1. የሚታዩ ጉዳዮች.................................................................................................................................6
4.2. የእይታ አቅጣጫዎች...........................................................................................................................6
4.3. የጥናቱ ትኩረት የሚሆኑ (የጋራ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት) ዐውዶች..............................................................7
5. በጥናቱ ሊመለሱ የሚገባቸው ዐበይት ጥያቄዎች...............................................................................................8
6. የጥናቱ ወሰን.........................................................................................................................................8
7. የጥናቱ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እና የዘገባ አቀራረብ.......................................................................................8
7.1. የመረጃ ምንጮች እና የናሙና አወሳሰድ....................................................................................................8
7.2. መረጃ የሚሰበሰብባው ዘዴዎች...............................................................................................................9
7.3. መረጃ የሚተነተንባቸው ሁኔታዎች..........................................................................................................9
7.4. የጥናት ውጤቶች ማቅረብያ መንገዶች......................................................................................................9
7.4.1. የጽሑፍ ዘገባ (ሪፖርት)................................................................................................................9
7.4.2. የጥናት ማቅረብያ መድረክ...........................................................................................................10
7.4.3. በቤተ ክርስቲያኒቱ ሰበካ ጉባኤ ሽፋን እንዲሰጥ (እውቅና )ማድረግ ።.................................................10
7.5. ጥናቱን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ጊዜ /የጊዜ ሰሌዳ/.................................................................................10
7.6. የሰው ኃይል (የጥናት ቡድኑ አባላት ይዘትና ሱታፌ)....................................................................................11
7.7. የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና/ወይም ገንዘብ................................................................................................11
8. ከጥናቱ የሚጠበቁ ውጤቶች እና የጥናቱ ውጤት ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚኖረው ጠቀሜታ................................12
8.1. የሚጠበቁ የጥናቱ ግኝቶች...................................................................................................................12
8.2. ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት....................................................................................................................12
8.3. የጥናቱ አዎንታዊ ተጽዕኖ (ጠቀሜታ) ለባለድርሻ አካላቱ..............................................................................12

1. መግቢያ
በኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ታሪክ የወጣቶች ሰንበት ት/ቤት ማቋቋም የተጀመረው ከ 1936 ዓ.ም
ጀምሮ ነው፡፡ ይኸውም ከብዙ ዓመታት በፊት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የሃይማኖት ትምህርት
ይከታተሉ የነበሩ ወጣቶች “የሥላሴ ማህበር” ተብሎ የሚጠራ አንድ ማህበር መሠረቱ፣ ይህ ማህበር ለወንዶች ብቻ
የተቋቋመ ነበር ይሁንና ከጥቂት ዓመታት በኋላ የካቴድራሉ አስተዳደር ወጣት ልጃገረዶችም የራሳቸውን ማህበር

Page 2 of 13
መመሥረት እንዳለባቸው አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘው ለጸሎትና ለአምልኮ ወደ ካቴድራሉ የሚመጡ ልጃገረዶችን ሰብስቦ
እነርሱም የራሳቸውን ማህበር እንዲያቋቁሙ አበረታታቸው በመሆኑም “ማህበረ ክርስቶስ” በሚል መጠሪያ የሚታወቅ
ማህበር መሠረቱ፡፡

የእነዚህ ማህበር አባላት የተሻለ የሃይማኖትና የሥነ ምግባር ትምህርት ማግኘት ሲጀምሩ የቤተክርስቲያንን ትምህርት
እየተማሩና እያወቁ በመምጣታቸው በተለይም ልጃገረዶች የቤተክርስቲያንን ዜማ በማጥናት በቤ/ክ ውስጥ ከቁርባን
በኋላ መዘመር ጀመሩ፡፡ ይህም እንደ አዲስ ክስተት ታይቶ በካህናቱና በምእመናኑ ዘንድ የሚወደድ ሆኖ ተገኘ የእነዚህ
ማህበራት ዓላማቸውም የሚከተሉት ነበሩ፡-

የክርስትና ሃማኖትን መሰረታዊ ዓላማዎች መማርና ማስተባበር ፣

ሰብአዊ ተግባራትን ማካሄድ፣

የክርስቲያንን ብሔራዊ ባህል መጠበቅ፣

ወጣት ልጃገረዶች ያለፍርሃት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉና ለህበረተሰቡ አገልግሎት የሚስፈልገውን የሥራ አመራር
ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ናቸው፡፡

ከላይ እንደተጠቀሰው በቅዳሴ ጊዜ የወጣት ልጃገረዶች ተሰጥዎ መቀበልና ከቅዳሴም በኋላ ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎችን
ማስማታቸው እንደ አዲስ ነገር በመታየቱ ተግባሩ በሌሎችም አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶች ቀጥሎ ተስፋፍቷል፡፡

የምስካየ ኅዙናን ቤተክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በሚሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት የተፈሪ መኮንን እና
የእቴጌ መነን ት/ቤት ተማሪዎችን በብዛት መሳብ በመቻሉ በየሳምንቱ እሑድ ተማሪዎች በብዛት ወደ ቤ/ክ እየመጡ
በመንፈሳዊ አገልግሎት ተሳታፊ ከሆኑ በኋላ ብዙዎች በቤ/ክ እንዳንድ ሥራዎች በፈቃደኝነት መሳተፍ ጀመሩ፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ በተማሪዎችና በገዳሙ መካከል አንድነትን መፍጠር የሚችልና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚሰጥበት
ሰንበት ት/ቤት እንዲቋቋም ወጣቶቹ በመጠየቃቸው “ተምሮ ማሰተማር” የተባለው ታዋቂው ሰንበት ት/ቤት በ 1939
ዓ.ም ተመሠረተ፡፡

የተምሮ ማሰተማር ማህበር ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለማህበሩ አባላትና ለህብረተሰቡ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እየሰጠ
ይገኛል፡፡ ከዚያ በመቀጠል በ 1942 ዓ.ም የተቋቋመው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሲሆን የወንጌል መልዕክተኞችና
የእሑድ ት/ቤት ማህበር ተመሠረተ፣ በዚሁ ጊዜም ነበር የአሥመራው ማህበረ ሐዋርያት ፍሬ ሃይማኖት ማህበር
የተቋቋመው፡፡

ቀጥሎም ወደ ታዕካ ነገስት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል፣ ወደ ገነተ ጽጌ መናገሻ ቅዱስ
ጊዮርጊስና ወደ ሌሎች የአዲስ አበባ ታላላቅ ገዳማትና አድባራት ተስፋፋ ከዚያም አልፎ ወደ ዋና ዋና (በጊዜው አጠራር
ጠቅላይ ግዛት) ከተሞችና ታላላቅ አውራጃዎች የተቋቋሙበት የደብሩን መለያ ስም በመያዝ በልዩ ልዩ የቅጽል ስም
የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራት እየተባሉ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ተጓዙ፡፡ የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት የወጣቶች
መንፈሳዊ ማህበር የቀድሞ አመሠራረቱ ከላይ እንደተጠቀሰው በወጣቶችና ልጃገረዶች ግላዊ ተነሳሽነት ፤በብጹዓን
ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአንዳንድ ዓላማው በገባቸው የአድባራት አለቆችና ሰባክያነ ወንጌል በጎ ፈቃድና ድጋፍ ነበር፡፡

Page 3 of 13
በተለይም በ 1936 ዓ.ም በወቅቱ የመንበረ ጸባኦት ቅዱስት ሥላሴ ካቴድራል አስተዳዳሪ የመጀመሪው ሊቀሥልጣናት
ሆነው የተሾሙት ሊቀ ሥልናናት አባ መልዕክቱ በኋላም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ፓትርያሪክ
ተብለው የተሸሙት ማህበሩ እንዲመሰረት ከፍተኛ ጥረት ከማድረጋቸውም በላይ ማህበሩ በአገልግሎቱ ቀጣይነት
እንዲኖረው ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡ ይሁንና እነዚህ ማህበራት በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ቀስ በቀስ በሁሉም ገዳማትና
አድባራት ተቋቁሞ ስለነበር ከቤተ ክህነቱ ጋር የሚያገኛኘው መስመር የግድ ስለነበር በጊዜው በስብከተ ወንጌልና
ማስታወቂያ መምሪያ ስር የወጣቶች መንፈሳዊ ማህበራት አንድነት ማእከላዊ ጽ/ቤት በጠቅላይ ቤተ ክህነት
ተቋቁሞለት እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ ይህ ማዕካላዊ ጽ/ቤት እስከ 1965 ዓ.ም ድረስ በመጠኑም ቢሆን
የወጣቶች መንፈሳዊያን ማህበራትን ሲያስተባብር ቆይቷል፡፡ ከ 1965 ዓ.ም ጀምሮ ግን ወደ ወጣቶች ጉዳይ መምሪያነት
አደገ፡፡

ይህ በዚህ እንዳለም በ 1966 ዓ.ም በመላው አዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የተቋቋሙት የወጣቶች መንፈሳውያን
ማህበራት የለውጡን ሂደት ተጠቅመው በራሳቸው ውሳኔ አጠቃላይ ጉባኤን መሰረቱ ይህ የወጣቶች መንፈሳውን
ማህበራት አጠቃላይ ጉባኤ በዚያ ክፉ የደርግ ዘመን በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ እጅግ ብዙ ቁም ነገሮችን ለቤተ ክርስቲያኒቷ
በቆረጥነት አበርክቷል መምሪያውንም ያጠናከረው አጠቃላይ ጉባኤው ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤውና በመምሪያው የተጠናከረ ትብብር የአሁኑ ሰንበት ት/ቤት እንደቀድሞው የወጣቶች መንፈሳዊ
ማህበር እየተባለ በ 1970 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጣው ቃለ ዓዋዲ የቤተ ክርስቲያኒቱ ህጋዊ አካልነቱ ተረጋግጦ ሙሉ በሙሉ
ዐውቅና አገኘ እስከ 1974 ዓ.ም ድረስ ስያሜው ቀጥሎ በመላ ኢትዮጵያ በስፋት ተስፋፋ፡፡

ይሁን እንጂ ከ 1974 ዓ.ም ካቲት ወር ጀምሮ የደርግ መንግስት “ከአኢወማ” ጋር በስም ይሞካሻል፣ ይመሳሰላል ብሎ
በውስጥ በደረገው ተጽዕኖ ምክንያት ሁሉም የወጣቶች መንፈሳውያን ማህበራት በቅዱሳት ቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ
ሲኖዶስ ብልህነት የተመላው ውሳኔ ነበሩ ስማቸው ተለውጦ ይኸውና ከዕለቱ በመነሳት የሰንበት ት/ቤት ተብሎ እስከ
አሁን ሊደርስ ችሏል፡፡ መምሪያውም የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የተባለው ከዚያን ወዲህ ጀምሮ ነው፡፡

ከላይ ባየነው መልኩ ከተቋቋሙ እና አሁንም በየአጥቢያቸው ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ከሚያደርጉ ሰንሰት ትምህርት
ቤቶች መካከል በደብራችን የሚገኘው የቀድሞው የልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ወጣቶች ማህበር በአሁኑ አጠራር
የማኅ/ስ/ቅ/ል/ለማ እና ደ/መ/መድ/ዓለም የተ/ሳ/ሰ/ት/ት/ቤት አንዱ ነው። ይህ ሰ/ት/ቤት በአሁኑ ወቅት ከግማሽ
ምዕተ አመት በላይ የቆየው ተቋም የተመሰረተው በአቶ ሀረገወይን መለሰ ህዳር 7/1957 ዓ/ም ነበር ።ይህም ሰ/ት/ቤት
በወቅቱ ያካባቢውን መንፈሳውያን ወጣቶች በማሰባሰብ እና በስሩ በማቀፍ የሚከተሉትን መንፈሳዊ ስራወች ይሰራ
ነበር።

1 ድራማ እና ሥነ ጽሁፍ

2 የስብከተ ወንጌል እንዲሁም መስተንግዶ እና በጎ አድራጎት የሚሉ ሦሥት ክፍላትን በማቋቋም አገልግሎት
መስጠት እና እራሱን ማጎልበት ጀመረ

ይህም ሰ/ት/ቤት በማህደረ ስብኀት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና በሐውልተ ስምዕ መድኃኔዓለም ገዳም በሚል ለሁለት
ተከፍለው ነበር ። ከዚህም በኋላ ሁለቱን ወደ አነድነት በማምጣት ለተሻለ አገልገሎት በ 1974 ዓ/ም ከደብራቱ
ቀድመው እነርሱ ተዋሀዱ ።ይሁንም እንጂ ይህ በእዲህ እንዳለ ከጥቂት አገልግሎት በኋላ በሀገር አቀፍ ደረጃ
በቤተክርስቲያን ላይ በተነሱ የታህድሶ መናፍቃን እጅ ላይ በመውደቁ ብዙ አባላት እና አመራሮችንም ጭምር በዚህ
የምንፍቅና ትምህርት በመወሰዳቸው ጠባሳ ታሪክ ጥሎ አልፏል ።ከዚህም በላይ ታህድሶ መናፍቃን በሀገር ደረጃ

Page 4 of 13
የመናፍቃን እንደ አንድ ዋና ማዕከል ሆነው በምንፍቅና ትምህርት በየክፍለ ሀገራትም ጭምር ማስፋፊያ ሆነ
።በዚህም አካሔድ ጥቂት ዓመታትን አሳልፏል ። ከዚህም በኋላ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ በነበሩ ቆራጥ አባቶች እና
በሰ/ት/ቤቱ ውስጥ በነበሩ ጥቂት ትክክለኛ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች አማካኝነት ተንሰራፍቶ የነበረው የታህድሶ
የምንፍቅና እንቅስቃሴ በከፍተኛ ትግል እንዲቆም ተደረገ ።በዚህም ምክንያት ለጥቂት ዓመታት አገልግሎት ተቋርጦ
ከቆየ በኋላ በ 1986 ዓ/ም ስያሜው ተለውጦ ደብሯን በመሠረቷት በብፁ አቡነ ሳዊሮስ ስም ተክለ ሳዊሮስ
ሰ/ት/ቤት በመባል እንደ አዲስ ተቋቋመ ።ከዚህም እንደ አዲስ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን እስካለበት ዘመን
ድረስ ከቀድሞው በተሻለ መልኩ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍላትን በማደራጀት መንፈሳዊ ስራዎችን አጠናክሮ
በመስራት ላይ ይገኛል ።ይሁንም እንጂ እንደ አዲስ ከተቋቋመ በኋላም አልጋ በአልጋ የሆነ ምቹ አገልግሎት ነበረ
ማለት አይደለም ። በበርካታ ፈተናዎች ሲፈተን ቆይቷል። በተለይ በ 1994 ዓ/ም በቤተክርስቲያናችን ተፈጥሮ
በነበረው ከፍተኛ አለመግባባት አባላቱ በሃሳብ በመከፋፈላቸው ለተወሰነ ጊዜ የመዘጋት እና የመበተን እክል አጋጥሞት
ነበር ። ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር አጋዥነት እና በቆራጥ አንዳንድ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ይህን ሁሉ ፈተና
አልፎ እስካሁን ድረስ በአገልግሎት ላይ ይገኛል ። (ምንጭ ልደታ ለማርያም በመምህር እሱባለው ይማም ነሃሴ 2012
ዓ/ም የተጻፈ ከገጽ 107__112)

2 የጥናቱ አስፈላጊነት /አሳሳቢት/ እና መነሻ ነጥቦች


ከላይ የወጣት መንፈሳዊ ማኅበራትና የሰ/ት/ቤት አመሠራረት የዘመናት የአገልግሎት ሁኔታና የአስተምህሮ እንቅስቃሴ
አንፃር የወደፊት የሰ/ት/ቤት የስነምግባር አሰተምሮና አያያዝ የወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት የመዋቅርና የመመሪያ ደንብ

ቀላልነት እንዲሁም የደብሩ አሰተዳደር ክትትልና ቁጥጥር ማነስ በሰ/ት/ቤቱ በወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት ብሎም
በደብራችን የምንፍቅና ሰርጎ ገብነትና የሰ/ት/ቤትና የማኅበራት አባላት ከአገልግሎት የመራቅ ከአባልነት የመውጣት

ብሎም በመናፍቃን አስተምህሮ የመወሰድ ሁኔታ ከላይ ያየነው የሰ/ቤታችን የዘመናት ተግዳሮትና አሁን በዘመናችን
የምናየው አንዳንድ የሰ/ት/ቤት እና የወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት የስነምግባር ችግርና ከሁሉም በላይ ለቤ/ክ አሳሳቢ

የሆነው በመልካም ወጣትነት ስም የሚስተጋባው የምንፍቅና አስተምህሮ በሰ/ት/ቤታችንና በወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት
ላይ ኢላማ ሊያደርግ ይችላል ብለን ማሰባችን ነው።

በተጨማሪም እንደ እውነቱ ከሆነ በጥንቱ ትውፊታችን እና መጽሐፋዊ አብነታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአንድ
ጉባኤ ብቻ ሦስት ሺህ ነፍሳትን ታሳምንና ታጠምቅ ነበር (የሐዋ.2፡41)፡፡ በአንጻሩ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ሦስት ሺህ
ጉባኤያት ዘተጋጅተው እንኳ በእነዚህ ሁሉ ጥረቶች ግን ምን ያህል ነፍሳት ለድኅነት እንደሚበቁ ሥላሴ ብቻ ያውቁታል
(በልዩ የእግዚአብሔር ድንቅ ቸርነት ታግዘን፣ ወደ እነርሱ ሳንሄድ ቆይተን በእነርሱ ጥሪ መሠረት አጋጣሚውን ተጠቅመን
በአንዳንድ ሰንበት ትምህርት ቤት እና ማኅበራት በጋራ በርካታ የቤተክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እያከናወኑ
ይገኛሉ።በዚህም የወንጌል እውነትን ከሐሰት ትምህርት መለየት የሚችሉበት ዕድሜያቸው ላይ ተገቢው ትምህርት
ስላልተሰጣቸው ወደ ሌሎች አዳራሽ በመጉረፍ ላይ ያሉ በርካታ ናቸው፡፡ ይህ አካሄዷ ታዲያ ‹‹ጌታም የሚድኑትን ዕለት
ዕለት በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር›› (የሐዋ.2፡47) የተባለላት ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለት ስለሚቀነሱባት ልጆቿ ምን
ያህል አካሄዷን ልትፈትሸ እንደሚገባት የሚያመላክት ነው፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዋና ተልዕኮዋ፣ የሕልውናዋም
ትርጉም የሆነውን የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራትን በጋራ እያስተባበረች አገልግሎቱን

Page 5 of 13
በአግባቡ እየተወጣች ነው ወይ/ ምን ያህል ውጤታማ ሆናለች? ወደፊትስ ከታሪካዊ ጉዞዋችን ተምረን እንዴት መቀጠል
ይኖርብናል? የሚሉ ቁልፍ ጥያቄዎችን በመረጃ አስደግፎ መመለስ የለውጡ አንድ እርምጃ ሊሆን ይችላል በሚል ይህ
ጥናት ትኩረት አግኝቷል፡፡

2. የጥናቱ ዓላማዎች

2.1. ጥቅል ዓላማ?


የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት የጋራ አገልግሎት ሂደትና ውጤታማነት በመፈተሽ በቀጣይነት
ልንከተል የሚገባትን አዋጭ አካሄድ መጠቆም፡፡

2.2. ዝርዝር ዓላማዎች


3.2.1 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት
መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት በስብከተ ወንጌል አገልግሎት በጋራ
ያደረግናቸውን ጥረቶች/ጥንካሬዎቿ፣ የተገኙትን አዎንታዊ ውጤቶች፣ የገጠሙን ችግሮች (ውሳጣዊ ድክመቶችን
ጨምሮ) እና የነበረንን ምቹ አጋጣሚዎች ፈትሾ በዝርዝር ማስቀመጥ፤

3.2.2 ሰንበት ት፣ምህርት ቤቱ እና ማኅበራቱ በዚህ አገልግሎት ከነበሯት ክፍተቶች (ድክመቶች) ተምረው፣
ያላቸውን እምቅ አቅም አሟጠው በመጠቀም የተሻለ ውጤት ልናስመዘግብ የምትችልበትን አቅጣጫ መጠቆም፤

3.2.3 በተለይ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት እንደ አንድ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ክንፍ የነበረውን አስተዋጽኦ
በመፈተሽ ወደፊትም

ሊኖረው የሚገባውን ድርሻ ማመላከት፡፡

3.2.4 የሰ/ት/ቤት የተሻለ የአባለት አያያዝና መዋቅራዊ አደራጃጀት ማመላከት

3.2.5 ወጣት መንፈሳዊ ማኅበራት ከሰ/ት/ቤት እና ከደብሩ አስተዳደር ጋር የተግባቦት ሁኔታን ማሳየት

Page 6 of 13
3. የጥናቱ ይዘት (ትኩረት ነጥቦች)
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት ከተመሠረቱበት ጀምሮ ታሪካዊ /ትውፊት ጀምራ እስካሁን ድረስ
የመጡባቸው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጉዞዎች ቅኝት የወደፊቱን አቅጣጫ በሚያመላክት መልኩ ዳሰሳ ይደረጋል፡፡
ከዚያም ጥናቱ ያለፈውን፣ አሁን ያለውን እና ወደፊት ሊኖር የሚገባውን አቅጣጫ በንጽጽር ለማስቀመጥ ይቻለው
ዘንድ በዋናነት ሊታዩ የሚገባቸውን ጉዳዮች፣ ጉዳዮቹ የሚታዩባቸውን አቅጣጫዎች እና ጥናቱ ሊያተኩሩባቸው
የሚገቡ አሁናዊ የጋራ የስብከተ ወንጌል ዐውዶችን ማመላከት ያስፈልጋል፡፡

3.1. የሚታዩ ጉዳዮች


ይህ ጥናት በሚከተሉት አራት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል፡- በጋራ የሚሰጡ መሠረታዊ ትምህርቶች ፤
መምህራኑ ፤ የትምህርቱ ዘዴ እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊነት፡፡

መሠረታዊ ትምህርቶች ፡- ዛሬ በዘመናችን እየተሰጠ ያለው ትምህርት ዋና ትኩረት ምንድን ነው /ዶግማዊ፣ ሥርዓተ
አምልኮአዊ፣…. የወጣቶችን ፍላጎትና ስሜት የተከተለ ወይስ ሊነገር የሚገባው ነው የሚለው መታየት አለበት /፡፡
በተጨማሪም የትምህርቱ ጥልቀት (ብስለት) እና አግባቢያዊ ወቅታዊነት ሊፈተሹ የሚገባው ነጥቦች ናቸው፡፡

መምህራን ፡- በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ በመምህርነት ደረጃ ያላቸው እና እነርሱ ራሳቸውን ለማጉላት
የሚጠቀሙበት እንጂ ሕጋዊነታቸውን እና የዕውቀት ደረጃቸውን የማይለካ እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ትውፊት
ያልተለመደ አገላለጽ መሆኑን ልብ ይሏል)፣ የትምህርታቸው ብቁነት፣ ትጋታቸው፣ ሥነ ምግባራቸው እና ክህሎታቸው
(በዘመናውያን ጉዳዮች ላይ ያላቸው የመረጃ ቋት፣ የቋንቋ ክህሎትን የማሳደግ፣ ከተሰባኪያንም የግንዛቤ አድማስ ቢያንስ
በአንድ እርምጃ የመቅደማቸው ጉዳይ፣ ወዘተ.) ሊታዩ ከሚገቡ ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የትምህርቱ ዘዴ፡- የተማሪዎችን ሁኔታ (መልክዐ ምድር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ ወዘተ)፣ የቦታ ተደራሽነት እና የትምህርት
አቀራረብ (ምጣኔ፣ ፍሰት፣ ጥልቀትና ድምፀት ሊጠቀሱ ይችላሉ ) ተገቢነትን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆኑን መፈተሽ
ያስፈልጋል፡፡

የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊነት፡- በየአጥቢያው ያሉ የስብከተ ወንጌል ክፍሎች፣ ሰ/ት/ቤቶች፣ ማኅበራት እና በግል
ተነሳሽነት ለዚህ አገልግሎት መስፋፋት በማስተባበር የሚተጉ ምዕመናን (‹‹የግል ሰባኪ›› የሚባል ቋንቋ እየተለመደ
የመጣ ቢሆንም እንዲህ የሚል የቤተ ክርስቲያን አካሄድ አለመኖሩም ተያይዞ ሊታይ የሚገባው መሆኑን ልብ ይሏል )፡፡

3.2. የእይታ አቅጣጫዎች


? ከቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ተልእኮ አንጻር (ወጣቱን በሚገባ ማስተማር ፣ ከሃይማኖት የወጡትን መመለስ፣
ያሉትን ማጽናት/ለቅድስና ማብቃት)፣

? ምዕመናኑ ከደረሱበት ደረጃ፣ እንዲደርሱም ከምንፈልገው ዓላማ አንጻር፣


Page 7 of 13
? ወቅቱ ከሚጠይቀው (ዓለም ከደረሰችበት፣ አገራችንም ካለችበት፣ ከትውልዱም የግንዛቤ አድማስ ሁኔታ) አንጻር፡፡

3.3. የጥናቱ ትኩረት የሚሆኑ (የጋራ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት) ዐውዶች


ምንም እንኳን ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌልን የምታስፋፋባቸው ዐውዶች (ቦታዎች እና ሁኔታዎች) ውሱን ባይሆኑም
የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት ለማመላከት ሲባል የሚከተሉት ዐሥር ነጥቦች ተለይተውል፡-

? (ዕለታዊ) የሠርክ ጉባኤያት፤

? (ሳምንታዊ) የዕለተ ሰንበት (ድኅረ ቅዳሴ) ስብከተ ወንጌል አገልግሎት፤

? ወርሐዊ ልዩ ጉባኤያት (‹‹የጧፍ መርሐ ግብር›› ተብለው የሚታወቁት)፤

? የንግሥ በዓላት (በተለይ ሌሊቱን በማኅሌት ወቅት እና ቀን ጽላት ቆሞ የሚደረጉቱ)፤

? ዓመታዊ የመስቀልና የጥምቀት በዓላት የጋራ አገልግሎቶች፤

? ‹‹ልዩ›› እና ‹‹ታላቅ›› በሚሉ ቅጽሎች የሚዘጋጁ ጉባኤያት (በጥቅሉ በአጥቢያዎችና በማኅበራት የሚዘጋጁት)፤

? የሰ/ት/ቤቶች (ሕጻናት እና ጎልማሶች) ሳምንታዊ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብራት፤

? የማኅበራት ስብከተ ወንጌል (በራሳቸው የሚካሄዱ እና ከደብሩ ስብከተ ወንጌል በሚላኩ መምህራን የሚካሄዱት፤

? በመንፈሳዊ ጉዞዎች ወቅት የሚሰጡ የጋራ ስብከተ ወንጌል አገልግሎቶች፤

? የደብሩ ሰበካ ጉባኤ (በተለይም በየወሩ በልዩ መልክ የሚዘጋጁት መርሐ ግብራ፣ አልፎ አልፎ የሚካሄዱት ሐዋርያዊ
ጉዞዎች/የሕዝብ ጉባኤያት፣ እና የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር አፈጻጸም በዚህ ክፍል ሥር በመጠኑ
ሊዳሰሱ ቢሞከሩ መልካም ይሆናል)፡፡

4. በጥናቱ ሊመለሱ የሚገባቸው ዐበይት ጥያቄዎች


? የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት ታሪካዊ/ትውፊታዊ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አሰጣጥ
ሂደት በየዘመናቱ ምን ይመስል ነበር?

? ከጥንቱ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጥረቶቿ እና ዘመኑ ከሚጠብቀው አንጻር ዛሬስ ቤተ ክርስቲያኒቱ በዘርፉ
እያደረገችው ያለው እንቅስቃሴ እና ውጤታማነት ምን ይመስላል?

Page 8 of 13
? የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት ከእነዚህ ሁሉ ሂደቶች ተምረው ወደፊት በምን መልኩ
ውጤታማ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ሊያቅዱ/ ሊያከናውኑ ይገባቸዋል?

5. የጥናቱ ወሰን
ይህ ጥናት ምንም እንኳን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት
መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ግምገማዊ ጥናት ላይ
የሚያተኩር ቢሆንም ሁሉንም ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ የመዳሰስ አቅም አለው ማለት አይደለም፡፡ ጥናቱ ተሠርቶ
ይጠናቀቃል ተብሎ ከተቀመጠለት ጊዜ አነስተኛነትና የአጥኚ ቡድኑ አባላትም ሙሉ ጊዜአቸውን ለዚህ ተግባር ብቻ
የሚያውሉ ስላልሆኑ (ተደራራቢ አገልግሎቶችና ሥራዎች ስለሚኖሩባቸው) ከርዕሰ ጉዳዩ አሳሳቢነትና ‹‹ጥናቱ
ማምጣት አለበት›› ተብሎ ሊታሰብ ከሚችለው አንጻር የሚመጣጠን ውጤት ላያስገኝ እንደሚችል ያሰጋል፡፡ ይልቁንም
ደግሞ ጥናቱ ምንም እንኳን ከእነዚህም መማር ተገቢ መሆኑን ቢያምንም ‹‹በጎ ገጽታዎችን›› ከማንጸባረቅ ይልቅ
ለተሻለ ተግባር በሚያተጋ መልኩ በሚታዩ ክፍተቶች ላይ ለማተኮር ይገደዳል፡፡

6. የጥናቱ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች እና የዘገባ አቀራረብ

6.1. የመረጃ ምንጮች እና የናሙና አወሳሰድ


በመጀመርያ ደረጃ ካሉት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ
መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት ካሉት ውስጥ ------ ያህሉ
(አመክንዮአዊ ወካይነትን ለማረጋገጥ ሲባል) በዕድላዊ/ ሎተሪ አመራረጥ መንገድ እንዲመረጡ ይደረጋል፡፡ የተመረጡቱን
ማኅበራት እና ጽዋ ማኅበራት በቤተ ክርስቲኒቱ ሥር ካሉ እና በዋናነት በዚሁ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላይ
ተሠማርተው የሚገኙ ማኅበራት (የጉዞ ማኅበራትንና ለሌሎች ተግባራት የተደራጁትን ሳይጨምር ) የጥናቱ ትኩረቶች
ይሆናሉ፡፡

6.2. መረጃ የሚሰበሰብባው ዘዴዎች


? ጥቅል ቅኝት /የአጥኚ ቡድኑ አባላት ምልከታ በአገልግሎት ቆይታቸው ወቅት/፤

? የቁልፍ መራጃዎች ቃለ መጠይቅ (ለጉዳዩ ቅርበትና የጎላ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብለው ለሚታሰቡ ሊቃውንትና
አገልጋይ ምዕመናን)፤

? የጽሑፍ ቃለ መጠይቅ፤

Page 9 of 13
? የሰነዶች ዳሰሳ (በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ ደረጃዎች የረቀቁና የተተገበሩ ዕቅዶች፣ ዘገባዎች፣ መጻሕፍት፣
መመሪያዎች፣ ወዘተ)፡፡

6.3. መረጃ የሚተነተንባቸው ሁኔታዎች


አስፈላጊ መረጃዎች አስቀድመው በተገለጹት መንገዶች ከተሰበሰቡ በኋላ እንደ አመቺነታቸው በሚከተሉት ዘዴዎች
ሊተነተኑ ይችላሉ፡-

? በማብራርያ መልክ (በተለይ ኢ-አሓዛዊ የሆኑ መረጃዎችን)፤

? በሰንጠረዥ (በተለይ ንጽጽራዊ መረጃዎች)፤

? በሥዕላዊ መግለጫ (ግራፍ) (በተለይ የየጊዜያቱን ክስተቶች/ለውጦች በልዩነት ለማሳየት)፡፡

6.4. የጥናት ውጤቶች ማቅረብያ መንገዶች

6.4.1. የጽሑፍ ዘገባ (ሪፖርት)


የሚያስፈልጉ መረጃዎች ሁሉ ተሰብስበው ሲጠናቀቁ የመጀመርያው ዘገባ (ረቂቅ) ተጽፎ በቡድኑ አባላት እና
በአስተባባሪ ክፍሉ አማካይነት አስተያየት ይሰጥበታል፡፡ በተሰጡት የማዳበሪያ አሳቦች መሠረትም የጥናቱ ሁለተኛ
(መደበኛ) ዘገባ ተጠናቅሮ ለጥናት መድረክ በሚቀርብበት መልኩ ይመቻቻል፡፡ በመጨረሻም ከጥናት መድረኩ
በሚገኙ ተጨማሪ አስተያየቶች ዳብሮ የመጨረሻው ዘገባ ተሠርቶ ለአስተባባሪ ክፍሉ እንዲገባ ይደረጋል፡፡ ተክለ
ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤቱ በሂደት እንደ አስፈላጊነቱ በቤተ ክርስቲኒቱ ላሉት ባለ ድርሻ አካላት የሚደርስበትን ሁኔታ
የማመቻቸቱን ሓላፊነት ይወስዳል፡፡

6.4.2. የጥናት ማቅረብያ መድረክ


ተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ትምህርት ቤት ባወጣው ምክረ አሳብ መሠረት ጥናቱ ተሠርቶ ሲጠናቀቅ (ነሐሴ 2014 ዓ.ም
መጨረሻ አካባቢ) የጥናቱ ውጤቶች የሚቀርቡበትን መድረክ ያመቻቻል፡፡ በዚሁ መድረክ ላይም ጉዳዩ በቀጥታ
የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይኽም የጥናቱን ውጤት ከማካፈልም
ባሻገር አስፈላጊ የአሳብ ግብዓቶች የሚሰበሰቡበት፣ የጥናቱ ግኝቶችም በበቂ አስተያየቶች ዳብረው ተዓማኒነታቸው
የሚረጋገጥበት፣ እንዲሁም የተጋበዙት ተሳታፊዎችም የየራሳቸውን የቤት ሥራ የሚወስዱበት ምቹ አጋጣሚ
ይሆናል፡፡

Page 10 of 13
6.4.3. በቤተ ክርስቲያኒቱ ሰበካ ጉባኤ ሽፋን እንዲሰጥ (እውቅና )ማድረግ ።
ጥናቱ በአግባቡ ከተጠናቀቀ ዘንዳ አስፈላጊው የአርትዖት ሥራ ተሠርቶለት በጥናት መድረኩ ላይ ላልተገኙት እጅግ
በርካታ የቤተ ክርስቲያኒቱ አካላት (በየደረጃው ላሉት አገልጋዮች) መረጃው በተገቢው መልኩ ይደርስ ዘንድ ባሉት
የቤተ ክርስቲያኒቱ ልሳናት በዋና ጉዳይነት ማሳወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ በተለይም በደብሩ ሰበካ ጉባኤ በቂ ሽፋን
ያገኛል ተብሎ ይታሰባል፡፡

6.5. ጥናቱን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገው ጊዜ /የጊዜ ሰሌዳ/


የክንውን ጊዜ ሰሌዳ
ተ. ምርመ
ዝርዝር ተግባራት ሐም
ቁ ሰኔ ነሐሴ መስከረም ጥቅምት ራ

1 የጥናቱን ርዕሰ ጉዳይ እና ወሰን መለየት X
2 የጥናቱን ምክረ አሳብ አዘጋጅቶ ለሰንበት ት/
X
ቤቱ ማጸደቅ
3 የጥናቱን መረጃ መሰብሰብያ ቅጾች ማዘጋጀት X

4 መረጃ መሰብሰብ X X X X X X
5 መረጃ መተንተን እና የዘገባ ረቂቅ ማዘጋጀት X
6 ረቂቅ ዘገባውን በቡድን አዳብሮ ለሰ/ት/ቤቱ
X
ማስረከብ
7 የሰንበት ት/ቤቱን አስተያየቶች ማካተትና
X
ዘገባዉን ማጠናቀቅ (ማስረከብ)
8 የጥናቱን ግኝቶች ባለድርሻ አካላት ባሉበት
X
መድረክ ማቅረብ
9 የባለድርሻ አካላቱን አስተያየቶችና ጥቆማዎች
X
በማካተት ለጠቃሚ ሰነድነት ማብቃት

6.6. የሰው ኃይል (የጥናት ቡድኑ አባላት ይዘትና ሱታፌ)


? ቡድኑ ከሰንበት ት/ቤቱ ጋር የሚኖረውን ግንኙነት የሚከታተል አንድ ተወካይን ጨምሮ ስምንት አጥኚ ቡድን
አባላት ያሉት ሲሆን በተለይ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ዙርያ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ
መዋቅራት አስተባባሪዎች መረካ ከመሰብሰብም ያለፈ ድጋፍ እንዲቸሩ ይጠበቃል፡፡

Page 11 of 13
6.7. የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና/ወይም ገንዘብ
? ለመረጃ መሰብሰብያ የሚውሉ ቅጾች ማባዣ ወረቀቶችና ቀለም (ከሰንበት ትምህርት ቤቱ እና ከሰበካው ጉባኤ
ድጋፍ ሊደረጉ ይችላሉ)፤

? መቅረጸ ድምጽ፤

? የቡድኑ አባላት መገናኘትና መወያይ በሚኖርባቸው ጊዜ ምቹ ቦታዎችን ማመቻቸት፤

? በተለይ ወደ አንዳንድ ማኅበራት ለሚደረጉ የስልክ ጥሪዎች የሰንበት ትምህርት ቤቱን ስልክ መፍቀድ አልያም
የሞባይል ካርድ መሙላት (ምናልባት የግድ በአካል መሄድ የሚጠይቅ መሆኑ ከታመነበት ደግሞ ተያያዥ የጉዞ
ወጪዎችን መሸፈን)፡፡

7. ከጥናቱ የሚጠበቁ ውጤቶች እና የጥናቱ ውጤት ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚኖረው ጠቀሜታ

7.1. የሚጠበቁ የጥናቱ ግኝቶች


? የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም
ቤተክርስቲያን የምንገኝ ሰንበት ት/ቤት እና ማኅበራት በተለይ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ጉዞ በአግባቡ ይዘገባል፤
? በአገልግሎቱ ሂደት የነበሩ/የሚኖሩ ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ስጋቶች (የውጭ ተጽዕኖ) እና ምቹ አጋጣሚዎች ይለያሉ፤
? ለተሻለ አገልግሎት የሚያበቁ አቅጣጫዎች ይጠቆማሉ፡፡

7.2. ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት


? በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ መዋቅሮች የሚገኙ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት አስተባባሪዎች በአጠቃላይ፤
? መምህራነ ወንጌል፤
? ምዕመናን (ተሰባኪዎቹ)፤
? በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የሚሳተፉ በደብሩ የሚገኙ ማኅበራት (በተለይ የጥምቀት ተመላሽ ማኅበራት)
? የደብሩ ተክለ ሳዊሮስሰንበት ትምህርት ቤት ሥራ አስፈጻሚ እና ንኡሳን አስፈጻሚዎች

7.3. የጥናቱ አዎንታዊ ተጽዕኖ (ጠቀሜታ) ለባለድርሻ አካላቱ


? በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ረገድ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ መዋቅሮችና አካላት ሲደረጉ የነበሩትን ጥረቶች፣ የተገኙትን ዐበይት
ውጤቶች፣ ያጋጠሙትን ዋና ዋና ተግዳሮቶች/ችግሮች ዘግቦ ለታሪክ (ለትውልድ) ማቆየት፤
? የነበረውን ፈትሾ ለቀጣይ ተግባራት ትምህርት መቅሰም፤

Page 12 of 13
? ሁሉም የየራሱን ድርሻ ሊወጣ በሚችልበት አደረጃጀት ወጥ ቅንጅታዊ /የመናበብ/ አካሄድ መዘርጋት፤

? የጥናቱን ግኝቶች በግብዓትነት ተጠቅሞ ቀጣይ ዕቅዶችን መከለስ፡፡

Page 13 of 13

You might also like