You are on page 1of 3

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

በእግዚአብሔር ቸርነትና መልካም ፍቃድ፣በድንግል ማርያም አማላጅነት፣በጻርቃን ሰማዕታት ፀሎት፣በመላእክት ጥበቃና


አማላጅነት መንፈሳዊ ፅሁፌን እጀምራለሁ።

የላፍቶ ሌንጫ ቅ/ገ/ቤ/ክ/ሰ/ት/ቤት በተለያዩ ግዜያት በመንፈሳዊ አገልግሎት ሲጠናከርና እንዲሁም አንዳንድ ግዜ
ደግሞም አባላቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሲበተኑ(ከአገልግሎት ሲቀሩ) ይስተዋላል። ከዚህም በተጨማሪ በማህበረሰቡ
ህሌና የመንፈሳዊ አገልግሎት ይዘት እንዳይኖረው አድርጎታል። በመሆኑ እነዚህን እና መሰል ችግሮችን ለመፍታት
ወይም ለመታደግ የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦችን እንዳቀርብ ተገድጃለሁ።

ሀ) የአባላት ወይም ማህበራት አደራጃጀት ስልት


1. የቀድሞው የሰ/ት/ቤት አባላትን እና ከአሁን በፊት በተለያየ ግዜያት በሰ/ት/ቤት ያላገለገሉ ነገር ግን መንፈሳዊ
የአኗኗር ዘይቤ ያላቸው እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን በቤ/ክርስቲያናችን እንዲገኙ አሁን በአለው
የሰ/ት/ቤትአባላትና ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት አማካኝነት ጥሪ ማድረግ።

2. የአገር ሽማግሌዎችን (አባቶች)፣ እናቶች በፕሮግራሙ እንዲገኙ ለነሱም ጥሪ ማድረግ።

3.በዕለቱ ፕሮግራም ሰባኪ መምህራን መጋበዝ ( መምህራን በደብሩ ወይም በቀድሞው የሰ/ት/ቤት አባላት ከሌለ)።

4. የቀድሞ የሰ/ት/ቤት አባላትን በርቀት ወይም በማህበር መልኩ ማደራጀት እና የራሱ የሆነ አመራሮች እንዲኖራቸው
ማድረግ።

5. ሰናይ (ጥሩ) መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው እህትና ወንድሞችን ከቀድሞ የሰ/ት/ቤት አባላት ወይም አሁን እያገለገሉ
ከአሉ አባላት ጋር ማደራጀት።

ለ) የማህበሩ መደራጀት ለሰ/ት/ቤቱ ያለው ሚና


1.ሰ/ት/ቤቱ የሚገጥሙትን ማንኛውንም ዓይነት የኢኮኖሚ እጥረት ወይም ችግሮች ለመታደግ

2. የሰ/ት/ቤቱ አገልግሎት በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንድያገኝ ለማድረግና ልጆቻቸውን ወደ ቤ/ክርስቲያን


እንዲልኩ ለማስቻል።

3.የሰ/ት/ቤቱ አመራሮች ጠንካራ የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ

4.የሰ/ት/ቤቱ አባላት ምንም ዓይነት የደህነት ስጋት እንዳያድርባቸውና ጠንክረው በቤተክርስቲያን የህይወት
ዘመናቸውን እንዲያሳልፉ ለማስቻልና በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲታደጉ ለማድረግ።

5. ሰ/ት/ቤቱ በአቅራቢያው ባሉ አድባራት አርአያ ሆኖ እንዲገኝ ለማስቻል።

6.በሰ/ት/ቤቱ በተጠናከረ መልኩ የቤተክርስቲያን ትምህርቶችና ተያያዥነት ያላቸው ትምህርቶችንም ለመስጠት


እንዲያስችል።
7.የሰ/ት/ቤቱ አባላት በሰ/ት/ቤቱ ስራ አስፈፃሚዎች የሚደርስባቸውን ጫናዎች ለመታደግ ወይም ጥያቄዎቻቸው
ምላሽ ያገኛሉ።

8. የሰ/ት/ቤቱን አባላት ለመበተን /ሰ/ት/ቤት እዳይጠናከር የሚፈልጉ አካላት በፅኑለመታደግ ያስችላል።

9.የሰ/ት/ቤት አባላት በማህበረሰባቸው መታመንእንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

10.በስራ ወይም በተለያየ ምክንያት ከአከባቢው ርቀው ሲሄዱ በወቅቱ የነበራቸው ቆይታ ቤተክስርስቲያኑንና
ሰ/ት/ቤታቸው እንዲያስታውሱ ትልቅ እድል ይፈጥርላቸዋል።

ሐ)የማህበሩ መደራጀት ለቤተክርስቲያናችን ያለው ሚና


1.በቤተክርስቲያናችን የተሟላ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲስፋፋ ለማስቻል።ለምሳሌ የአብነት ትምህርት፣ለወጣቶች
ዘመኑ የዋጀ የትምህርት አገልግሎት፣ የአንድነት ጉባኤ.....

2.ጠንካራ አገልጋዮች እንዲኖሩ ማስቻል። ለምሳሌ በአግባቡ ትምህርታቸውን የተማሩ ዲያቆናት፣ካህናት፣ መርጌታ፣
መምህራን.... የመሳሰሉትን

3. ጠንካራ የቤተክርስቲያን አመራሮች ለማፍራት ወይም ለማብቃት።

4.ቤተ ክርስቲያናችን የሚገጥማትን ማንኛውንም ዓይነት ችግሮች ያለ ማንም ጣላቃ ገብነት በተገልጋዮቿ ብቻ
መፍትሔ እንድታገኝ ለማስቻል።

መ) የማህበሩ መደራጀት ለማህበረሰቡ ያለው ሚና


1 .በቤተክርስቲያናችን ተገልጋይ ምዕመናን የባዕድ አምልኮ እምነታቸውን በመተው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት
አማኝ ብቻ እንዲኖራቸው ለማድረግ።

2. ስጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ለማስቻል።

3 የእምነታቸውን ምንነት ለነርሱ እግዚአብሔር በገለፀላቸውና በፈቀደላቸው ልክ እንዲረዱ ወይም እንዲገነዘቡ


ለማስቻል።

4. በማህበረሰቡ አንድነትን፣ መተባበርን፣ መተጋገዝን፣ ፍቅርን... ለማጎልበት።

5.በተለያየ ሱስ የተጠመዱ እህትና ወንድሞችን በመምከርና የመንፈሳዊ ህይወት ምንነት እየኖሩ ለማሳየት ያስችላል።

6.ብቸኝነት እንዳይሰማቸው ያስችላል። ለምሳሌ እህት ወይም ወንድም የሌለው /የሌላት ስለሚኖሩ ለነርሱ ታላቅ ዕድል
ይሆናል።

ሠ)የማህበሩ መደራጀት ለራሱ የሚኖረው ሚና


1.በሰ/ት/ቤት ሲያገለግሉ ቆይተው በስራ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች የተለያዩ እህቶቻችንንና ወንድሞቻችንን
አንድነታቸውን ለማጠናከር
2.በሰ/ት/ቤት ማገልገል ሲፈለጉ የነበሩ እህትና ወንድሞች ነገር ግን በተለያየ መንገድ ማገልገል ያልቻሉ ከአሁን በኋላ
ማገልገል እንዲችሉ ለማስቻል።

3.በማህበሩ ውስጥ ያሉ አባላት በተለያየ ምክንያት የሚገጥሟቸውን ከአቅም በላይ ችግሮች በጋራ በመተባበር መፍታት
ለማስቻል።

ለምሳሌ፦

እግዚአብሔር አይበለውና አንድ እህት ወይም ወንድም በአደረበት የህመም ደዌ ለህክምና ወጪ 20,000 ብር ብትጠየቅ
ወይም ቢጠየቅ ነገር ግን የመክፈል አቅም ባይኖራት ወይም ባይኖረውም እንዲሁም ደግሞ የማህበሩ አባላት ብዛት
ሁለት መቶ ቢሆን እያንዳንዱ 200 ብር ብቻ በማዋጣት የእህታችንን ወይም የወንድማችንን ህይወት መታደግ
እንችላለን።

4.ሰበካ ጉባኤ አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን በመክፈል በአሉበት ቦታና ግዜ ሁሉ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማግኘት
እንዲችሉ ለማድረግ ያስችላል።

5.በደስታም ሆነ በሀዘን ግዜ በአንድነት መተባበር መተጋገዝ እንዲኖር ለማስቻል።

6.በተቻለ መጠን በዓላት አብሮ ለማክበር። ለምሳሌ ጥምቀት፣ ፋሲካ፣ ገና፣ መስቀል....

ታዲያ ይህን ሁሉ አስተዋጽኦ ያለው ማህበር እስከ አሁን ድረስ መደራጀቱ አያስቆጭም ትላላችሁ እህትና ወንድሞቼ
እንዲሁም እናትና አባቶቼ? ስለዚህ ሁላችንም እናስብበት ለማድረግም እራሳችንን እናዘጋጅ ያለማንም ቀስቃሽና
ጎትጓች።

ይህንንም ሀሳብ የሚመለከተው ሁሉ በጥልቀት በመመርመርና በማገናዘብ የየራሱን ሀሳብ ወይም መፍትሔ እንዲሰጥ
በልዑል እግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ።

አስጀምሮ ላስጨረሰኝ ለልዑል እግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ይግባው፣ ለወለደችው ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያም
ክብርና ምስጋና ይድረሳት እንዲሁም የጻርቃን ሰማዕታት የአበው ቅዱሳን የመላእክት ስማቸው እርሱ ልዑል
እግዚአብሔር በአከበራቸው ልክ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው።

"ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር


✞ ይቆየን ✞ አሜን!"

You might also like