You are on page 1of 6

መልእክት ለኦርቶዶክሳዊ የአገልግሎት ተቋማትና ማኅበራት

ለሰንበት ት/ቤቶች

ለማኅበረ ቅዱሳን

ዳንዲ አቦቲ

ሞዐ ተዋሕዶ ግብረ ኃይል

ለጥምቀት ተመላሾችና ወጣቶች ማኅበራት

ለጴጥሮሳውያን የማኅበራት ሕብረት

ለማኅበረ ካህናት

ጉዳዩ፡ በየተጠራንበት ኃላፊነት የሚገባውን በመፈጸም በቤተክርስቲያንና በሀገር ላይ የተደቀነውን ሁለገብ


የህልውና አደጋ የማስቀረትና ድርሻንን ስለመወጣት፤

«በጎውን ሥራን እያወቀ የማይሰራት በደል ትሆንበታለች» ያዕ 4፡17

«የቤትህ ቅናት በላኝ» ዮሐ 2፡17

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መዋቅር ሥር በቃለ ዓዋዲ እና እንደየሁኔታው በአገር ደረጃ ፥
በቅዱስ ሲኖዶስ እና በአህጉረ ስብከቶች ደረጃ በሊቀጳጳስ ፈቃድ ሕጋዊ ሆነው የተቋቋሙ ተቋማት ፣ ማኅበራት
እና ኦርቶዶክሳዊ የአገልግሎት ሕብረቶች ሐዋርያዊት የሆነችውን ቅድስት ቤተክርስቲያን እንደ አቅማችሁና
ጸ ጋዎቻችሁ እያገለገላችሁ ትገኛላችሁ። ዘመኑ ያመጣቸውን ፈተናዎችና የሚያቀርበውን እድሎች ያገናዘበ
አገልግሎት ከመሥጠት አንጻር አገልግሎቶች ሲመዘኑ ሊደርግ ከሚገባውና ከሚቻለው እንፃር ከአቅም በታች እጅግ
ዝቅ ያለ አገልግሎት እንደሆነ ማስተባበል እንዳንችል የሚያድርገው ቤተክርስቲያን ከዓመት ወደ ዓመት በከፍተኛ
ደረጃ ጉዳት እየደረሰባት መገኘቱ ነው። ልጆቿ በአካል ተፈናቅለው ይሰደዳሉ ፣ ከእምነታቸው ወጥተው ይፈልሳሉ ፣
ሀብታቸውን ተነጥቀው ይደኸያሉ ፣ እርስ በእርስ ተለያይተው ይተላለቃሉ ፣ ሲኖዶሱ ከውስጥ በፖለቲካ አደር
ተበክሎ በጎሣ ይሿሿማል ፣ ፖለቲካው በቀጥታ ጣልቃ ገብቶ ያሻውን የመፈጸም አቅም ከማግኘቱ የተነሳ
የሐዋሪያትን ቀኖና በመንግሥት ባለሥልጣት ፍላጎት እስከመቀየጥ ተደርሷል።

1
ይህ ሁሉ አሉታዊ የቁልቁለት ጉዞ የሚያሳየን የአገልግሎት ተቋማት ስልታዊ ባልሆኑና ዘመኑን ከመዋጀት ይልቅ
ችግሮችን እየተከተሉ የበለጠ ጉዳት እንዳይደርስ በማድረግ የተወሰኑ መሆናቸውን ያመለክተናል ፤ በሌላ በኩል
ዘመኑን የሚዋጁ አገልግሎቶችን አቅደውና አልመው የሚሠሩትን ተቋማት ውጤታማ እንዳይሆኑ ከአጠቃላይ
የቤተክህነት እና ከቤተ መንግሥት መዋቅር ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ጫና የሚደርስባቸውም ብዙ እንደሆኑ በአገልግሎት
የምንሳተፍ ሁሉ እናውቃለን።

እነዚህ ተቋማት የቤተክርስቲያናችን አካልና ወሳኝ ሚና ያላቸው የምእመናን ፣ የካህናትና የገዳማዊያን ስብስቦች
በመሆናቸው ውጤታማነታቸውም ሆነ ውድቀታቸው ለቤተክርስቲያን ተልእኮ መፋጥንም ሆነ አሁን ከተደቀነባት
ሁለገብ ፖለቲካዊ ጥቃት ፣ የኑፋቄና የዓለማዊ ፍልስፍና ጦር ራስን ለመከላከልና ለማሸነፍ ወይንም ዘገምተኛ
ለውጥ ለማምጣት ምክንያት ይሆናሉ። የተቋማቱ መኖር ኃላፊነታቸውን ዘመኑን በሚዋጅ ደረጃ የማይወጡ ሆነው
ሲገኙ መኖራቸው በያዙት ስምና በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ባላቸው ተአማኒነት ብዙኃንን በማዘናጋት ፥
ምእመናን በየአካባቢያቸው የተለያዩ ፈጠ ራዎችን ተጠ ቅመው ጉዳት እንዳይቀንሱ አሉታዊ አስተዋጽኦ
ይኖራቸዋል። ክርስቲያኖች እየተዘናጉና መፍትሔ በማይሰጡ ስብሰቦች ላይ በማይገባ ደረጃ እየተማመኑ አመራጭ
ሳይፈልጉ በመቅረት ቤተክርስቲያንን ለበለጠ አደጋ ታጋላጭ እያደረጓትም ይገኛሉ።

ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ አምላክ የለሽ መንግሥታት ሲፈራረቁ በፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊና የመናፍቃን የተቀናጀ
ርብርብ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ምእመናን ከሃይማኖታቸው የፈለሱበት ፣ አብያተ ክርስቲያናት የነደዱበት እና
አገልጋዮቿ በመሰዊያው ፊት ምእመኖቿ በአደባባይ የተሰዉባት ፣ በሀገሪቱ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ለስደት
ለመከራና ለረሃብ የተጋለጡበት ፣ የጥምቀት ልጆቿ በዘር የፖለቲካ ልሂቃን አመራር ሥር ወድቀው በአእምሮ
ባርነት ተይዘው እርስ በእርስ በጦርነት በሚሊዮኖች ያለቁባት ፣ በዘር ደዌ የተያዙ በምንፍቅና ያበዱ ምንደኛ የቤተ
ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ አባቶች ራሳቸውን ከመደበቅ ወደ መዋቅራዊ አሠራር በመሸጋገር ራሳቸውን
በግልጽ ያወጁበት ፣ ከሃይማኖታዊ ባህል ወደ ባህላዊ ሃይማኖት የተዛወርንበት ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እና ሕገ
ቤተክርስቲያን ተጥሎ ፖለቲካዊ ጣልቃገብነት ተንሰራፍቶ የረዘመ የፖለቲካ እጅ ቤተክርስቲያነችንን የሚመራበት
፣ የአስተዳደር ብልሹነት እና ሙስና በግልጽ መዋቅራዊና ሕጋዊ መስሎ በግልጽ የታየበትና ባህል የሆነበት ፣
የፖለቲካ እና የቤተክርስቲያን የግንኙነት መስመር የተዘበራረቀበት ፣ የምእመናን እርስ በእርስ እንዲሁም ከአባቶች
ጋር ሰፊ ልዩነት እና አለመተማመን ያሳዩበት ጊዜ ነው ። በይበልጥ ነገሩ ገኖ በዚህ 5 ዓመት ውስጥ መውጫው
እስኪጠፋን ድረስ ግራ አጋብቶ በፊታችን ቤተክርስቲያናችንን እና ምእመኖቿን ፖለቲካው በዘር ሲካፈሉ ያየንበት
ነው።

2
እኛ ምእምናን ፣ ካህናት ፣ ሊቃውነተ ቤተክርስቲያን ብዙውን ነገር በተዋረዳዊ ሥርዓት ለበላዮቻችን በመተው
መፍትሔ ይመጣ ይሆናል በማለት በዝምታ መቆየታችን መከራችን እንዲበዛ ሆነ እንጂ መቀነስ አልተቻለም።
በመሆኑም ኦርቶዶክሳውያን ከሀገር ባለቤትነት ተወግደው ታሪካቸውን ፣ ትውፊታቸውን ፣ ቅርሳቸውንና ነባር
ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ለመግለጽ የፖለቲካ ባለሥልጣናት ፈቃድ በሚሹበት ፣ ሐዋሪያዊ ቀኖና ተጥሶ ኤጲስ
ቆጶስነት በመንግሥትና በፓርቲዎች የፖለቲካ ፍላጎት አንጻር በሚታደልበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል። ምእመናንን አንድ
አድርገው መንፈሳዊ ሕይታቸውን እንዲያሳድጉ እና ቤተክርስቲያናቸውንም ሆነ ሀገራቸውን እንዲጠብቁ
ለማስተማር ዋና ድርሻና ኃላፊነት ያለበትን የቤተ ክህነት መዋቅር ለማገዝና ስልታዊ ድርሻዎችን ዘመኑን በዋጀ
መንገድ መፈጸም የሚጠበቅባቸው የአገልግሎት ተቋማት/ማኅበራት ይህን አውድ ያገናዘበ አገልግሎት የመስጠት
ሚናቸው ከፍተኛ መሆን ነበረበት።

በመሆኑም አቅማችንን ያባከንባቸው ያለፉት ዘመናት ይበቃል በሚል መንፈስ የአበውን ፍኖት በመከተል
የሰማዕታትን ጽናት እና በረከት በመናፈቅ ለዘመኑ የሚመጥን የኦርቶዶክሳውያን ንቃተ ኅሊና በመፍጠር
የመጣውንና እየመጣ ያለውን የባሰ ጽኑ መከራ ለመከላከል ብሎም ለማሸነፍ የሚያስችል ቁመና መፍጠር ዛሬ
ነገ የማያስብል አገልግሎታችን ሊሆን ይገባል።

የተለመደው በውስጥና በውጭ አፅራረ ቤተክርስቲያን ፈቃድና የአገልግሎት ወሰን ልክ የማገልገል ልማድ
የተቋማቱን መኖር ትርጉም አልባ ብቻ ሳይሆን ከቅድሰት ቤተክርስቲያን ጠቀሜታ አንፃር ምእመናን አማራጮችን
እንዳይፈልጉ በማድረግ የጎጅ ተዋንያንነት አካል ሆኖ ከመቀጠል የማይተናነስ በደል እንዳይሆንብን ሁላችንም
በየተቋሞታችን/ማኅበራችን ራሳችንን በመገምገም አገልግሎታችን ዘመኑን ያገናዘበ ማድረግ ይጠበቅብናል።

አገልግሎቶቻችን ሁሉ ቤተክርስቲያናችን እንደ ተቋምና የሃይማኖት መዋቅር ፣ ምእመኗ እንደ ክርስቲያን ቤተሰብ
እየደረሰበት ያለውን ሥርዓታዊ ፣ ተቋማዊና ፖለቲካዊ ሁለገብ ህልውናን አደጋ ላይ የጣለ ጥቃት በሚመጥን ብሎም
በሚያሽነፍ ደረጃ ከፍ በማድረግ በቤተመንግሥትና በቤተክህንት ውስጥ በተሰለፉት በአጽራረ ቤተክርስቲያን ላይ
ጥገኛ ከሆነ አገልግሎት መላቀቅ ጊዜ የሚሰጥ ውሳኔ እንደማይሆን እጅጉን እናምናለን።

ባሳላፍናቸው 50 ዓመታት ፣ በተለየ ሁኔታ ባሳለፍናቸው 5 ዓመታት በፖለቲካ ፣ በኑፋቄ ፣ በትምህርት ፣ በምጣኔ
ሀብት ፣ በቀጥታ በጦር መሣሪያ ፣ በማሳደድና በማፈናቀል ፣ በመከፋፍልና በማጋጨት የተባባሰውን
ቤተክርስቲያንን የማዳከምና የማጥፋት ሂ ደት ከሚመሩና ከሚያስፈጽሙ አካላት ፈቃድና መመሪያ ተቀብሎ
አገልግሎት መቀጠል የማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሳችንን የምንገነዘበው ሐዋሪያዊ ቀኖናው በመንግሥት
ትዕዛዝ የሚሻርበት ፣ ምእመናን በቤተመቅደስ ውስጥ በመንግሥት ሠራዊትና ከቤተክህነት ይልቅ ራሳቸውን

3
በአባትነት በሚሾሙ ኢአማንያን ትብብር አባት ተብዬ መነኮሳት ግድያና ቅሚያ ሲከናወን መታየቱ ነው። ይህን
ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበ አገልግሎት ለመስጠት ተቋማት ሁሉ ተግባራቸውን እንደ አዲስ የመገምገምና ራሳቸውን
የመለወጥ ግዴታ ከፊታቸው ተደቅኗል። የሚያስፈልገው ለውጥም የተቋማትን፡

 የአገልግሎት አጠቃላይ ፍልስፍና ከዘመኑ ውስብሰብ ፈተና አንፃር የሚያገናዝብ፤


 የተቋማቱን መዋቅርና ተጠሪነትን በተመለከተ፤
 ተቋማቱን አመራር ፣ የተመሪዎችና የአገልጋዮች ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ሕይወትና ዓለማዊ ግንዛቤ፤
 የአፅራረ ቤተክርስቲያን ሥርዓታዊ ፣ መዋቅራዊና የብዙ አጥቂ አካላትን ፍላጎቶችና ቅንጅትን መረዳት ፤
 ኦርቶዶክሳዊ ቀኖናን ፣ የቤተክርስቲያንን ፍጹም አንድነትና ሲኖዶሳዊ ሥርዓት በመጠበቅ ፤

እንዲሁም የመንግሥትን በሰብአዊ አኩልነት ፣ በዜጎች ሙሉ የማምለክ ነፃነትና በሁሉ ቦታ የመገልገል መብቶችን
አንፃር አግባብነት ያላቸውን ሕጎች በማክበርና በተቃራኒው ቤተክህነቱም ሆኑ ቤተመንግሥቱ የሚጠበቅባቸውን
ግዴ ታዎች በሚቃረን የሚያደርጉትን ተግባር በመቃወምና በመጋደል መካከል ያለውን ውጥረት ያገናዘብ
አስተሳሰብና አሠራር የሚሸከም ተቋም ሆኖ መውጣት ጊዜ የሚሰጥ ባለመሆኑ:-

 ቅዱስ ሲኖዶሱ የተቋሟቱን ውጤታማነት የሚገድቡና ዘመኑን አንዳይዋጁ እንቅፋት የሚሆኑ


አሮጌ ሕጎችና ደንቦች ፥ አደናቃፊ የውስጥ አሠራሮችን መርምሮ መለወጥ
 ውጭ-ገብ እና ዘመን ያለፈባቸውን ኢክርስቲያናዊ ጎጅ ባህሎችን መርምሮ ተገቢ ቀኖና መቆነን፤
 በምእመናን መብዛት ፥ መታነፅ ፥ በአገራቸው በሁሉ ቦታና ሁኔታ ውስጥ እኩል መከበርና
መብታቸው መጠ በቅን የሚመለከት አገራዊ የምእመናን መንፈሳዊና ዓለማዊ አስተዳደር
መስተጋብርን የሚመለከት አሠራር ግልጽ ማድረግ፤
 የሰው ኃይልና የገንዘብ አቅምን ፥ እውቀትና ተቋማዊ መረቦችን ከማስቻል በተቀራኒ ሽባ
የሚያደርጉ ልማዶች በአስቸኳይ እንዲያስወግድ ግልጽና በጊዜ ገደብ ምላሽ ለማስገኘት
መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት እናምናለን። ለክርስትና አፅራር የሆነው ፖለቲካና አገራዊ ሂደቱና
እና ሲኖዶስ ውስጥ እየታየ የሚገኘው ከቀኖና ሐዋሪያት የማፈንገጥን በዝርዝር ቆጥሮ
የሚስተካከልበትን ውሳኔ በሶስተኛ ወገን የሊቃውንትና የአኀት አቢያተ ክርስቲያናት ፊት
ማስተላለፍና ይፋ ማድረግ፤
 ሕገ ቤተክርስቲያንን በጎሣ ፖለቲካ ጫጫታና የመንጋ ድምጽ የመበየንና በሲኖዶሳዊ የተቀደሰ
የሐዋርያት ሥርዓት ላይ በተለይ ፍቀረ ሲመት ባሳወራቸው መነኮሳትና የፖለቲካ ተቋማት ትብብር

4
የሚካሄደው አመፅ ምእመናን አውቀው አንዲቃወሙትና ከሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያንና ክህነት
መጠ በቅ ጎን እንዲቆሙ ማንቀሳቀስ፤

ያለንበት አሉታዊ ሁኔታ እንደሚያሳየን ለአገልግሎት የተሰለፉት ተቋማት ልዩ መፍትሔ ፍለጋ ላይ ካላተኮሩ
በስተቀር ሐዋርያዊ የክህነት ሰንሰለታችን ተበጥሶ ከድኅነት የሚያስወጣን መንገድ ላይ እየተንደረደርን እና በቀጥታ
ሊያጠፋን ከሚፋጠነው ፖለቲካ ራሳችንን አሳልፈን መስጠጣችንን ማስተባበል አይቻለም። በመሆኑም አንደ
ክርስቲያን የቤተሰብ አባላት የሚከተሉትን ጥሪ ለአገልግሎት ማኅበራት ፣ ለሰንበት ት/ቤቶች እና በምንም ቅርፅ
በቤተክርስቲያን ስም ለተደራጃችሁ ተቋማት ሁሉ የሚከተሉትን ጥሪ እናደረጋለን፡

፩) የምንገኝበትን ሁለገብ የውስጥና የውጭ የጥፋት ጦርነት ከግምት ያስገባ ፣ የቤተክርስቲያንን እና


የክርስቲያኖችን የህልውና አደጋ ያገናዘበ የአገልግሎት ወሰን እና ቅድሚያ የሚሰጠው የአገልግሎት አይነት
ምርጫ በማድረግ የተቋማቱን ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች ህልውና መቆም የሚያስመሰክር አቋም
በተግባር እንድታሳዩ፤

፪) በቤተ ክህት መዋቅር ውስጥ በሚገኙ ሠራተኞች እና በቤተመንግሥት ቅንጅት የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ
ማደናቀፍ ፣ ሐዋሪያዊነቷን ማሳጣት ፣ ምእመናኖቿን ከእምነት ማስወጣት ፣ ምጣኔ ሀብታዊና አካላዊ
የማጥፋት ዘመቻ ያገናዘበ የአገልግሎት አሰላለፍና ግኑኝነትን እንድታስተካከሉ እንጠይቃለን፤

፫) ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት እንቅፋት የሆኑ የቤተክህነት ደንቦች ፣ የአሠራር ባህሎች እና
ግኑኙነቶች ዘመኑን በሚዋጅ መንገድ እንዲቀየርና የአገልግሎት ተቋማት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው
የዘመኑን ፈተና የሚጋፈጡበት አሠራር እንዲኖር ህግ አውጭ በሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ላይ አዎንታዊ ጫና
ማድረግ፤

፬) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው ለዘር ፖለቲካ ፣ ለመናፍቃን ድርጀት ፣ ሀበት ለማካባት እና ለልዩ ልዩ
ተልእኮዎች የሚሰሩትን አካላት በመለየትና በማጋለጥ መራዳት፤

ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን


ቅድስት ቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሐዋሪያዊነት ፥ ቅድስት አገራችንን ይጠብቀልን

5
* ከዚህ በታች የተያያዙት ሊንኮች ለብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ለሚጀመረው ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አጀንዳ አድርገው እንዲወያዩበት እና ትኩረት


እንዲሰጡት በማለት የሊቃውንቱን እና የልጆቻቸውን ጩኽት እና ድምጽ እንዲሁም የብዙ
ዘመናት የክርስቲያኖች መከራ እና ስጋት በሰፊው የሚያሳስብ ጥራዝ እና ጽሑም ምስክር ይሆን
ዘንድ ለእናንተም ለተቋማት እንዲደርሳችሁ ተመልክታችኋቸው ለተቋማዊ አሰራራችሁ
ይጠቅም ዘንድ አያይዘን ልከንላችኋል!!

https://drive.proton.me/urls/YANZMTH3CW#wRGGv8xshSpS
[የተማጽኖዎች እና የደብዳቤዎች ስብስብ - 104 ገጽ]

https://drive.proton.me/urls/AHMNEKN2CW#1qvGa0251NOE
[የሊቃውንት እና የምእመናን ጩኸት - 55 ገጽ]
https://drive.proton.me/urls/P2MJXYR990#RN4lWQxsvD5G
[የሠላሳ ዓመታት የሰማዕትነት ጉዞ - IOTA ሪፖርት - 229 ገጽ]

https://drive.proton.me/urls/JYAYD8FR1G#XArVVmN3abi8
[የዘር ማጥፋት ዝግጅት በኢትዮጵያ - 115 ገጽ]

You might also like