You are on page 1of 3

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ


የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ
መግለጫ፤

“ወለእመቦ ዘሰከበ ምስለ ተባዕት ከመ አንስት ርኵሰ ገብሩ ክልኤሆሙ …ወጊጉያን እሙንቱ..ማንኛውም ሰው
ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል።
ደማቸውም በላያቸው ነው "(ዘሌ.፳ ፥፲፫)ግብረ ሰዶማዊነት በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር
ፈጽሞ ተቀባይነትየሌለው፣ዓለምንበልዩ ጥበብ በፈጠረ አምላክ ፈቃድ፣መለኮታዊ ሥርዓቱ በተገለጠባቸው ቅዱሳት
መጻሕፍት ፈጽሞ የተከለከለ፣በቀኖናተ ቤተክርስቲያን፣ በፍትሕ መንፈሳዊና በፍትሐ ብሔር ድንጋጌዎች፣በሥነ ልቦና
ደንቦች የተወገዘ፣ሥነ አእምሮዊ ሚዛንን የሚያዛባ፣ግለሰባዊ ማንነትንና ማኅበራዊ ትሥሥርን የሚያናጋ የረከሰ
ተግባር ነው፡፡

ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ
ተግባር ሲሆን የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ
አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስም ግብረ ሰዶማውያን የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም በማለት የግብሩን አስከፊነት፣
በማኅበረ ሰብእ ላይም የሚያመጣውን ጥፋት
በአጽንዖት ይነግረናል: (ሮሜ ፩፳፮ ፩ቆሮንቶስ ፮፱፣I፣)
ይህንንም ግብረ ርኩሰት ቅዱሳት መጻሕፍት በተለያየ ሥያሜ ጠርተውታል፤ከእነዚህም ርኩሰት፣ ጸያፍ፣ ትልቅ
ኃጢአት፣ በደልና አመጻ የሚሉት ቃላት ይገኙበታል፡፡ (ዘሌ ፲፰-፳)
የኃጢአተኛውን ሞት የማይሻው እግዚአብሔር ሌሎች ሕዝቦች በሚበድሉበት ጊዜ በዕዶምና በገሞራ የደረሰውን
ጥፋት እየጠቀሰ ከጥፋታቸው እንዲመለሱ ማስጠንቀቁን በቅዱሳት መጻሕፍት በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
(ኢሳ፫÷፱፣ኤር፶÷፵፣ ሰቆ ኤር ፬÷፮፣ ሕዝ ፲÷፵፱፣ አሞ ፬÷፲፩፣ ማቴ ፲÷፲፭፣ ፪ ጴጥ ፪÷፮)በመሆኑም ቅድስት
ቤተክርስቲያን ማንኛውም በጾታ ተፈጥሯዊ ስጦታ ላይ የሚሠራ ኃጢአት ሕገ ተፈጥሮን የሚጻረር ጽኑዕ በደል
እንደሆነ ታስተምራለች፡የያዕቆብ ወንድም ይሁዳም “እንደ እነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላን ሥጋ የተከተሉ ሰዶምና
ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተማዎች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል” በማለት ይህ ተግባር የተወገዘና
በዘላለም እሳት የሚያስቀጣ መሆኑን አስረግጦ ይናገራል።

ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ ኪዳንም
ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡

ጌታችንም ሲያሰተምር “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው"በማለት ጾታ የፈጣሪ ሥጦታ መሆኑን እና


ይህንም መጠበቅ ግዴታ እንደሆነ ያስረዳል፡ (ማቴ፲፱÷፲፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ግብረ ሰዶማዊነት አጸያፊ
ድርጊት መሆኑን
“እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ
ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ
በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት
በራሳቸው ተቀበሉ የሚገባውን እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ
አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው"በማለት ገልጾታል፡፡

ቅድስት ቤተክርስቲያንም ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን
የምታስተምረው ከዚህ የተነሣ ነው፡(፩ ቆሮ ፯፡፪፣ ፩ ጢሞ ፩፡፱)ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት
የሚንድ፣መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ
ገጽ የቆመ፣ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

በመሆኑም ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና
ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ
እንዲሆን
አትፈቅድም።

በ፲፱፻፺፮ በወጣው የሀገራችን የወንጀል ሕግ ክፍል፪ አንቀጽ ፮፻፳፱ ጠቅላላ ድንጋጌ “ግብረ ሰዶምና ለንጽሕና
ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች, በሚለው ንዑስ አንቀጽ ርእስ ሥር ይህ ድርጊት ወንጀል ስለሆነ በትክክል
የሚያስቀጣ መሆኑን አስቀምጧል። በተለይ አንቀጽ ፮፻፴፩ዕድሜያቸው ፲፰ ዓመት ያልሞላቸው ለአካለ መጠን
ያልደረሱ ልጆች ላይ ለሚፈጸም ግብረ ሰዶማዊነት ከ፭ እስከ ፳፭ ዓመታት የሚያስቀጣ መሆኑ በግልጽ
ተጽፏል።በተሻሻለውም የሀገራችን የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 13 መሠረት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ
መሆኑ ተደንግጓል፡፡

ይሁን እንጅ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው
እንደ ጥሩ ነገርእንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው
ግልጽነው።

እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣በባሕላቸው በማኀበራዊ
መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል
በማግባባት፣
ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ
ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎች ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ ይቃወማል፡፡

ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣


የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች፣ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት
አግኝተው እንዳይፈጸሙ ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል።

ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት
ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ፣የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና
በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ
እንዲፈተሽ የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ
ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ቋሚ ሲኖዶስ ጥብቅ የሆነ የአደራ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በስምምነቱ ሰነድ ጤናማ መስለው የሠረፁ ዐረፍተ ነገሮች ውስጥ እንደታየው በጾታና ሥርዓተ ጾታ መብት፣
የሥርዓተ ጾታ ትምህርት ጋር በማያያዝ ጾታን በቀዶ ጥገና የመቀየር ውርጃ፣ልቅ የሆነ የተመሳሳይና ተቃራኒ ጾታ
ግንኙነትን መፍቀድ፣ግለሰቦችን እና ማኅበረሰብን መረን በማድረግ ውስብስብ ለሆኑ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ
ችግሮች የሚዳርጉ መሆናቸውን ቅዱስ ሲኖዶስያምናል።

በመሆኑም በብዙ መስዋዕትነት ተጠብቆ የቆየው እምነት፣የባህልና የሥነ ምግባር ማኅበራዊ ዕሴት የክብር ስፍራውን
ይዞ እንዲቀጥልና በእጅ አዙር ቅኝ ግዛት
ኃጢአትንና ርኩሰትን አባብሎ በማስረጽ፣ለዚህ አጸያፊ ድርጊት ትውልዱ እንዳይጋለጥ የሚመለከተው ሁሉ በልዩ
ጥንቃቄ እንዲመለከተው ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ግብረ ሰዶማዊነት በማንኛውም የቃላት አግባብ ተገልጦ በጾታ መብት መካተት የማይችል የመደበኛ ተፈጥሯዋዊ
ክስተት ጋር በጭራሽ አቻ የማይሆን በመሆኑናተግባሩንም
መቃወም ቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊ ተልእኮዋ ስለሆነ ይህን አስመልክተው የሚደረጉ ስምምነቶች የሀገራችንን
ሃይማኖታዊ፣ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴት የሚጥሱ መሆኑ ታውቆ ሁሉም ዜጎች እንዲቃወሙት፣የፈዴራል
መንግሥትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለው ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ
ያሳስባል፡፡

ግብረ ሰዶምን እና ተያያዥ የጾታ ሥርዓትን የሚበርዙ፣ ጾታን መቀየር፣ ሁለት ዓይነት ጾታን መጠቀምና የመሳሰሉት
ተግባራት በሙሉ ሀገራችን በሃይማኖት፣በሕግ፣ በማኅበራዊ ዕሴቶቿ፣በሥነ ምግባር መመሪያዎቿ የማትቀበላቸው
ጉዳዮችና ልምምዶች ስለሆኑ በማናቸውም ይፋዊ ግንኙነቶች እንደማንቀበላቸው በግልጽ እንዲቀመጡ ቋሚ
ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

ግልጽ የሆኑ ግብረ ሰዶማዊነትን የሚያበረታቱ፣


የሚያዛምቱ፣ድብቅና እንቅስቃሴዎች የሚያደርጉ
አካላት ከድርጊቸው እንዲቆጠቡ፣በንሥሓ እንዲመለሱ
ቅድስት ቤተክርስቲያን በጥብቅ ታሳስባለች፡

ለወደፊቱም ማናቸውም የሥርዓተ ትምህርት መማሪያ ሲዘጋጅ፣ሀገር በቀል ደንቦችና መመሪያዎች ሲወጡየዓለም
አቀፍ ግንኙነት ስምምነቶች ሲፈጸሙ በሀገሪቱ ያሉ የእምነትና የባህል፣ዕሴቶችን፣የሕግ ማዕቀፎችንና የሥነ ምግባር
መርሆችን ተጠብቀው እንዲፈጸሙ፣መላው ሕዝባችንም የእምነት መሠረቱን፣የቀኖና ሥርዓቱን፣ማኅበራዊ ዕሴቱን
ጠብቆ እንዲኖር፣ሀገራችን ሰላም እንድትሆን ሁላችንም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በጸሎት እንድንተጋ ቋሚ ሲኖዶስ
መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲ወ፮ ዓ/ም

You might also like