You are on page 1of 12

‫باللغة اإلثيوبية (أمهري)‬

‫حقوق المرأة في االسالم‬


‫‪የሴቶች መብትና እኩልነት በኢስላምና በክርስትና‬‬
‫‪ዝግጅት ፡ ዳዒ ፡ ኻሊድ ካሳሁን‬‬
‫‪አርታኢ ፡ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ‬‬
‫ْ‬
‫إعـــداد ‪ :‬خالد كاساهون‬
‫مراجعة ‪ :‬محمـد حسن مـامي‬
*^* የፍቺ መብት *^*
ከሴቶች መሰረታዊ መብቶች ውስጥ ፍቺ
ይገኝበታል፡፡ ለዘላቂ ህይወት ሴት ከአንድ
ወንድ ጋር በጋብቻ ስትጣመር እና ጋብቻው
ሊሰምር ካልቻለ የመጨረሻው አማራጭ
መፍታት እና ከሚሆናት ሌላ ወንድ ጋር ዳግም
ጋብቻ መመስረት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ግን
ይህንን የማይቀበል ሲሆን ሴትም ብትፈታ *^* ምንም እንኳ ኢስላም ለስኬታማ
የተሰጣት አማራጭ ሳታገባ መኖር ነው፡፡ ጋብቻና ጠንካራ ቤተሰብ ምስረታ የሚረዱ
ስለፍቺ በመጽሐፍ ቅዱስ በዚህ መልኩ ትእዛዝ መርሆች ያስቀመጠ ቢሆንም የሰው ልጅ ግን
ተላልፏል ፡- ሁል ጊዜ በተወሰነላቸው ገደብና በተቀረጸላቸው
ተምሳሌት ይጓዛል የሚል እምነት የለም ፡
‹‹ሚስትም ከባልዋ አትለያይ ብትለያይ ግን
፡ ያለ መግባባት ሁከትና ግጭት ሊፈጠር
ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፡፡››(1ኛ
የሚችልበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ በባልና
ቆሮንቶስ 7፡10-11 )
ሚስት መካከል የተፈጠረው ውዝግብ አብረው
ይህን ጥቅስ የእምነቱ አስተማሪዎች እንዲህ እንዲኖሩ የማያስችልና መለያየትን የተሻለ
በማለት ያብራራሉ፡- ‹‹በጠቅላላው ሰዎች አማራጭ ሆኖ በሚገኝበት ወቅት ለሁለቱም
እንዲፈቱ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆንም ጾታዎች ደህንነት መለያየታቸው ባይወደድም
አንዳንድ ጊዜ በራሳቸው ፍቃድ የሚፋቱ በመጨረሻ አማራጭነት ፍች አስፈላጊ ሆኖ
ሰዎች ይኖራሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች የሚፋቱ ይገኛል፡፡
ከሆነ ማድረግ ያለባቸው ሳያገቡ መኖር
ነገር ግን የክርስቲያን ሚሽነሪዎች እና
ወይም መታረቅ ነው፡፡(ወርቁወልደ ዮሐንስ
ኦሬንታሊስቶች ኢስላም በሴቶች ላይ ካለው
ክርስቲያናዊ ጋብቻ፤ ገጽ 123)
አቋም ጋር በተያያዘ የከፈቱትን ዘመቻ ከቅርብ
በሌላ ምዕራፍ ላይ መጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› ጊዜ ወዲህ በሁለት ነጥቦች ማለትም በፍችና
በዝሙት ምክኒያት ብቻ መፋታት (ፍቺ) ከአንድ በላይ ማግባት ላይ አተኩሯል፡፡
እንደሚቻልና ከዚህ ሌላ ምክንያት ተቀባይነት የሚገርመው ሁለቱም ኢስላም የሚኮራባቸው
እንደሌለው ደንግጓል፡፡ አቋሞች ናቸው፡፡ አንዳንድ ሙስሊሞች
‹‹እኔ ግን እላችኋለሁ ያለዝሙት ምክኒያት የነርሱን ተቀብለው በማስተጋባት እነዚህን
ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ አጀንዳዎች ከቤተሰብና ከማህበረሰብ ችግሮች
ያመነዝራል የተፈታችውንም የሚያገባ ፈርጀው ያስተጋቧቸዋል ፡፡ አሁን አሁን
ያመነዝራል አላቸው፡፡(የማቴዎስ ወንጌል 19፡ ደግሞ የታላቁን ኢስላምና የአንጸባራቂውን
ሸሪዓውን ልዕልና ለማጉደፍ ይጠቀሙባቸው
‹‹ሴት በቧላ ህይወት የታሰረች ናት ››(1ኛ ይዘዋል፡፡ እውነታው ግን ኢስላም የደነገጋቸው
ቆሮንቶስ 7፡39) በሁለቱም ጾታዎች እንዲሁም በቤተሰብና

2
በኅብረተሰብ ሕይወት ውስጥ ለሚከሰቱ እጅግ ‹‹ከሁለቱም (ሰዎች) ባልንና ሚስትን
በርካታ ችግሮች መፍትሄ ይሆን ዘንድ ነው፡ የሚለያዩትን (የድግምት ዕውቀት) ይማራሉ፡፡
፡ እውነተኛው ችግር የአላህን ሕግና ድንጋጌ ››(ሱረቱ አል-በቃራህ 2፡102)
ካለመረዳት ወይም በአግባቡ ካለመተግበር ኢስላም የደነገገው የፍች ሥርዓት በአካል
የሚመነጭ ነው፡፡ አንድን ነገር በተገቢው ላይ እንደሚደረግ አሳማሚ ቀዶ ጥገና ሊወሰድ
መንገድ ጥቅም ላይ አለማዋል የከፋ ጉዳት ይችላል፡፡ አካሉ ሲቀደድና ሲሰፋ፤ ከዚህም
ሊያስከትል ይችላል፡፡ አልፎ ተቆርጦ ሲጣል ቀሪውን የአካሉን ክፍል
*^* ፍች ለምን? *^* ከበሽታ ለመፈወስ ሲል ማንም ጤነኛ ሰው
ሕመሙን መሸከም አይከብደውም ፡፡
በኢስላም የሚደገፉት ፍቺዎች ሁሉም
አይደሉም ፡፡ እንዳንዱን ፍች ኢስላም እንደዚሁም በሁለት ተጋቢዎች መካከል
ይጠላዋል፡፡ ሌላኛውን ደግሞ እርም ያደርገዋል፡ ጥልና አለመግባባት ሲነግስ፤ ለማስማማት
፡ ፍችን ኢስላም እንዲታነጽ የሚጓጓለትን የተደረጉ ጥረቶች ሁሉ ሲከሽፉ፤ በዚህ ጊዜ
ከታነፀም በኋላ እንዳይናጋ የሚንከባከበውና ፍች ብቸኛ አማራጭ ይሆናል፡፡ መድኃኒቱ
ቤተሰባዊ ሕይወት መናድ ነውና፤ ያለጥንቃቄ እርሱም ብቻ ነውና ቢመርም ይወሰዳል፡፡
በዘፈቀደ እንዲፈጸም አይሻም ፡፡ ለዚህም ‹‹ስምምነት ከጠፋ መለያየት ደግ ነው›› ይበላል
ነው በአቡዳውድ በተዘገበው በተከታዩ ሐዲስ ፡፡ ታላቁ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-‹‹ከተለያዩም
የአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ያሉት፡- (ከተፋቱ) አላህ ለሁሉም ከሲሳዩ ይለግሳል፡፡
አላህ (ችሮታው) ሰፊ፤ ጥበበኛ ነውና፡፡››(ሱረቱ
‹‹ከአላህ ዘንድ የሚጠላ ሐላል ነገር ፍች
አል-ኒሳእ፤ 130)
ነው፡፡››
የኢስላምን አቋም አዕምሮ ያጸድቀዋል፡
ይህ ከመሆኑ አኳያ ቁርአን ባልንና ሚስትን
፡ ጥበብም ያፀድቀዋል፡፡ ከጥቅምም አኳያ
ማለያየትንና ማፋጀትን ከከሐዲያን ደጋሚዎች
አወንታዊ ነው፡፡ በአንድ የሽርክና ተግብር
እኩይ አድራጎት መፈረጁ አያስገርምም፡፡ አላህ
ላይ የተስማሙ ሁለት ሰዎች እርስ በርስ
እንዲህ ይላል፡-
የማይስማሙ፤ የማይጣጣሙና የማይተማመኑ
ሆነው እያለ ዘልዓለም ‹‹አንድ ላይ
ተቆራኝታችሁ ኑሩ›› ብሎ ማስገደድ ጤነኛ
አስተሳሰብ አይቀበለውም፡፡

3
ኢስላም የፍቺን መጠን በከፍታ ሁኔታ
ሊቀንሱት የሚችሉ መርሆችን ድንጋጌዎችን
ያስቀመጠ ሲሆን፤ ከነዚህም መርሆችዎች
ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1) በትዳር ጓደኛ አመራረጥ ላይ ጥንቃቄ
ማድረግ፤ ከገንዘብ፤ ከስልጣንና ከውበት
ይልቅ ለዲንና ለስነምግባሩ ትኩረት መስጠት፡፡
ቡኻሪና ሙስሊም ባሰፈሩት ዘገባ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ሴት ለአራት ነገሮች ሲባል ለጋብቻ
እንዲህ ዓይነት ሰዎችን በሕግ ማስተሳሰር ትመረጣለች ፡፡ ለገንዘቧ፤ ለዘሯ፤ ለውበቷና
ትልቅ ቅጣት ነው፡፡ ትልቅ ወንጀል ለፈፀመ ለዲኗ፡፡ አደራ የዲን ባለቤት የሆነችዋን ምረጥ፡
ሰው ካልሆነ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት፡፡ ከዕድሜ ፡››
ይፍታህ እስራት የሚተናነስ አይደልም፡፡
የሚያሰቃይ የገሃነም ኑሮ ነው፡፡ በቀድሞው 2)ጋብቻ ከመፈጸሙ በፊት እጮኛን ማየት
ዘመን አንድ ጠቢብ እንዲህ ብለዋል፡- ተገቢ ነው ፡፡ የትዳር ጓዳኛ ውበት አይቶ
ልብ መፍቀዱን ለማረጋገጥ ፡፡ ከጋብቻ በፊት
‹‹ከመከራዎች ሁሉ ትልቁ መካራ መተያየት መግባባትንና ፍቅርን ይጠነስሳል፡፡
ከማትጣጣመውና ሁሌም ከማይለየህ ሰው ጋር ይህም በመሆኑ ነው የአላህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ)
አብሮ መኖር ነው፡፡›› ሴት ላጨ አንድ ባልደረባቸው ፡- ሂድና
አቡ ጦዩብ አል-ሙተንቢ የተባለ ገጣሚ እያት፡፡ በመካከላችሁ መግባባት እንዲፈጠር
የሚከተለውን ስንኝ ቋጥሯል፡- ይጠቅማችኋል›› ያሉት፡፡(አህመድ፤ ዳረል
ቁጥኒ፤ ሐኪምና በይሃቂ ዘግበውታል)
ለጨዋ መከራና ጭንቁ፣
ነብዩ ‹‹እያት›› በማለት የሰጡት ትእዛዝ
ከስቀይ ሁሉ ትልቁ ፣
ማየት ግዴታ መሆኑን ባያመለክትም
ጠላቱ አብሮት እንደሚኖር ማወቁ። እንደሚወደድ ግን ያስተምራል፡፡ ተመሳሳይ
ይህ ገጣሚ ‹‹ጭንቅ›› ያለው ከሳምንት መልእክት ያዘሉ ሌሎች ሀዲሶችም ተላልፈዋል፡
አንድ ቀን ወይም ለቀናት በቀን ውስጥም ፡ ጃቢር ስላገቧት ባለቤታቸው ሁኔታ ሲናገሩ፡
ለሰዓት ወይም ለሰዓታት ብቻ ሊያገኘው - ‹‹እርሷን እንዳገባ የሚያስችለኝ እና የሚስበኝ
የሚችለውን ጓደኛውን በማስመልከት ከሆነ ነገር እስከማይ ድረስ በዛፍ እየተደበቅኩ አያት
ሁሌም ከአጠገቡ የማትጠፋ የትዳር ጓደኛ፤ ነበር፡፡
የጎጆው ተጋሪስ ምን ልትሰኝ ነው?
*^* ቅድሚያ መስኩን ማጥበብ *^*

4
ያፈቀዱትን ጋብቻ እንድተፈጽም ለመከላከል
ይህ መስፈርት ጠቃሚ ነው፡፡ ከነርሱም ሐሳብና
ፈቃድ ከወጣች ይቆጡባታል፤ ያኮርፏታል፡
፡ እርሷም ከቤተሰቦቿ ትነጠላለች ፡፡ ጥሉ
በጋብቻ ሕይወቷ ውስጥ ያንጸባረቃል፡፡ መጥፎ
ተጽእኖም ያሳርፋል፡፡
6)በሴት ልጅ የጋብቻ ጉዳይ እናቷን
ማማከር ተገቢ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
3) ሴቷና የቅርብ ዘመዶች (ወልዮች) ጋብቻው በሁለቱም ወገኖች ፈቃድና ይሁንታ
የሚመርጡት ባል መልካም ፤ ዲኑና ባህሪው እንዲጠነሰስ ከጠንካራ መሰረት ላይ እንዲታነጽ
ያማረ እንዲሆን የሚያደርጉት ጥረትም ፍቺን ፡፡
ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ሴቶቻችሁን በሴት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይህን አስመልክቶ እንዲህ ልጆቻችሁ ጋብቻ ጉዳይ አማክሯቸው››
ብለዋል፡- ‹‹ዲኑና እና ስነምግባሩን የምትወዱት ማለታቸው ተዘግቧል።
ወንድ ልጃችሁን ከጠየቃችሁ ስጡት››
ማለታቸው ተጠቅሷል፡፡ 7) ሚስትን በመልካም መተዳደርና
መንከባከብ ግዴት መሆኑ፤ የተጋቢዎች
ቀደምት የሙስሊም ሊቃውንቶች እንዲህ መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ መቀመጣቸው፤
በማለት ይመክራሉ፡- የአማኝ ልቦናና ሕሊና የአላህን ሕግ ላለመጣስ
‹‹ልጅህን ዲኑና ስነ-ምግባሩ መልካም ለሆነ ጥንቃቄና የአላህ ፍራቻ ለጋብቻ ትልቅ
ሰው ስጥ፡፡ ምክኒያቱም ከወደዳት ያከብራታል፤ ዋስታናዎች ናቸው፡፡ ከእያንዳንዱ መብት
ይንከባከባታል፡፡ ካልወደዳትም አይበድላትም፡ ተጓዳኝ ግዴታ አለ ፡፡ ሙዕሚን(አማኝ)
፡›› መብቱን ከመጠየቁ በፊት ግዴታዎቹን
መወጣት እንዳለበት ኢስላም ያስተምራል፡፡
4) ለሴቷ ባሏን የመምረጥ መብት መሰጠቱም
አላህ (ሱ.ወ) አንጸባራቂ በሆነው ቃሉ በሱረቱ
ፍቺን ለመቀነስ አስተዋጽኦ አለው፡፡ከዚህ
አል-በቀራህ 2፡228 እንዲህ ይላል፡-
ቀደም እንዳየነው ሴት ልጅ የማትፈልገውን
ወንድ እንድታገባ ማስገደድ ፈጽሞ አይፈቀድም ‹‹(ከባሎቻቸው ሸሪዓው የሚፈቅደውን)
፡፡ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላልወደደችውና መልካም አያያዝና እንክብካቤ የማግኘት መብት
ላልፈቀድችው ባል የተሰጠ ችን ልጅ ጋብቻ አላቸው፡፡››(ሱቱ አል-በቀራህ 2፡228)
ማፍረሳቸው ይታወቃል፡፡ (የአላህ ሱ.ወ ፍቃዱ ከሆነ የባል እና
5) የቅርብ ቤተሰቦቿም በጋብቻው ሚስት መብት በኢስላምና በክርስትና በሚል
መስማማታቸው የሚወደድ መሆኑ ርዕስ ጊዜውን ጠብቆ በሰፊው የምንዳስሰው
በመስፈርትነት ተቀምጧል ፡፡ ይህም ፍቺን ይሆናል!!! )
ይቀንሳል ፡፡ ሴት ልጅ ቤተሰቦቿ ያልወደዱትና

5
ሲያይል እና የመለያየት አዝማሚያ ሲታይ
ኅብረተሰቡ ከባልም ከሚስትም ዘመዶች
በተውጣጡ ታማኝ የቤተሰብ ዳኞች
አማካኝነት ጣልቃ እንዲገባ እና የጠፈጠረውን
ችግር በጥበብ ለመፍታት እንዲጥር ኢስላም
ያስተምራል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
‹‹በመካከላችሁ አለመግባባት እንዳለ
ባል ምንጊዜም ተጨባጩን መዘንጋት ከተረዳችሁ ከርሱ ቤተሰብ የሆነነ ከርሷ ቤተሰብ
እንደሌለበት ኢስላም አጽኖት ሰጥቶ የሆነን ቤተሰብ ዳኞች ሰይሙ፡፡ እርቅን የሚሹ
ያስተምራል፡፡ ከሚስቱ ምሉዕነትን ከሆነ አላህ ያስማማቸዋል፡፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ
እንዳይጠብቅ ፤ ከድክመቶች በተጓዳኝ ጠንካራ 4፡35)
ጎኗን እንዲያስታውስ ይመክረዋል፡፡ እንዱ *^*^ የኢስላም አስተምሮ ይህንን ይመስላል፡
ባህሪዋ ቢያስከፋው ሌላው ያስደስተዋል፡፡ ፡ ኢስላም ቅድሚያ ፍቺ እንዳይከሰት መስኩን
በሀዲስም ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው አጥብቦታል ሙስሊሞች እነዚህን አስተምሮዎች
ተላልፏል፡- ቢተገብሯቸው ኖሮ ፍቺ በከፍተኛ ደረጃ በቀነሰ
‹‹አማኝ ወንድ አማንኝ ሴት ሙሉ ነበር *^*^
በሙሉ አይጥላ፡፡ አንድ ባህሪዋ ቢያስከፋው *^በኢስላም አስተምሮ መሰረት ፍች መቼ
ሌላኛው ያስደስተዋል፡፡››(አህመድና ሙስሊም
እና እንዴት ይፈጸም ?*^*
ዘግበውታል)
9) ባል ሚስቱን የመጥላት ስሜት
ሲያድርበት ለዚህ ስሜቱ ቶሎ እጅ እንዳይሰጥ
፤ እንዲያመዛዝን፤ ወደፊት ሁኔታዎች ወደ
ተሸለ ደረጃ ሊቀየሩና ሊስተካከሉ እንደሚችሉ
ተስፋ እንዲያደርግ እምነቱ ይመክረዋል ፡፡
ይህን አስመልክቶ አላህ ሱ.ወ በተከበረው ቃሉ
እንዲህ ይላል፡-
‹‹በመልካም ሁኔታ ያዟቸው ፡፡ **ኢስላም በተገኘ ወቅትና ሁኔታ ፍች
ብትጠሏቸውም(በትእግስ አብራችኋቸው እንዲፈፀም አልፈቀደም፡፡ በቁርአንና በአዲስ
ለመኖር ሞክሩ)፡፡ አላህ የጠላችሁትን ነገር የተጠቀሰው ህጋዊ የፍች ስርዓት ወቅትንና
በርካታ መልካም ነገሮች ያደርግበት ይሆናልና፡ ሁኔታና ማገናዘብን ይጠይቃል፡፡ ሚስት
፡››(ሱረቱ አል-ኒሳእ 4፡19) በወር አበባ ወቅት፣ ከወር አበባ ብትፀዳም
ግንኙነት ከፈፀመ በኃላ መፍታት ያልተፈቀደና
10) በተጋቢዎች መካከል አለመግባባት ያልተደነገገ /ቢድዓ/ እና ሐራም የፍች አፈፃፀም

6
ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተፈፀመ ፍች ተቀባይነት ** ከላይ የተዘረዘሩት የፍች አፈፃፀም
እና ተፈፃሚነት እንደሌለው ከፊል የህገ – ሸሪዓ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ የሚቀረው ሰውየው
ጠበብት ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም አፈፃፀሙ አስቦና ተጨንቆ ጉዳዩን በሚገባ አጥንቶና
የአላሀንና የመልዕክተኛውን ፍቃድ የተከተለ አጢኖ ሊታገሰው ካልቻለው የጋብቻ ህይወት
አይደለምና፡፡ በሀዲስ የሚከተለው ተላልፏል፡፡ ለመውጣት ብቸኛውና የተሻለው መንገድ
“የኛ ፍቃድ ያልታከለበትን አንድ ተግባር ፍች መሆኑን ካመነበት በኃላ የሚፈጽመው
የፈፀመ ስራው ውድቅ ነው፡፡” ሙስሊም/ ፍች ነው፡፡ ተከታዩ የኢብን ዐባስ ቃል ይህን
ያመለክታል፡-
** አንድ ወንድ ፍች በሚፈጽምበት ወቅት
አዕምሮውን ያልሳተና በምርጫው መሆን “ፍች ተቀባይነት የሚኖረው ታስቦበት
አለበት፡፡ አዕምሮውን ስቶ፣ ተገዶ ወይም ሲፈፀም ብቻ ነው፡፡” /ቡኸሪ/
ህሊናውን የሚሸፍንና የማመዛዘመን ክህሎቱ *^ ከፍች በኋላ ያለው ሁኔታ በኢስላም
የሚያጠፋ ቁጣ ተቆጥቶ እያለ ፍች ቢፈጽም፣ አስተምሮ ምን ይመስላል? *^*
ፍችው ተቀባይነት እንዳሌለው ተመራጭ
የሆነው የፊቅህ ጠበብት አቋም ይገልፃል፡፡
በሀዲስ የሚከተለው ተላልፏል፡፡
“በቁጣ ወቅት ወይም ተገዶ የተፈፀመ ፍች
ውድቅ ነው፡፡” /አቡ ዳውድና ኢብን ማጃህ/
“ኢግላቅ” የሚለውን የሐዲስ ቃል አቡ
** ፍች መፈፀም የጋብቻን ገመድ መልሶ
ዳውድ “ቁጣ” ሲሉ ተርጉመውታል፡፡ ሌሎች
እንዳይቀጠል አድርጐ ከነጭራሹ አየበጥሰውም፡
ደግሞ
፡ ቁርአን ፍች ለፈፀመ ሰው ሁለት የማሰቢያና
“መገደድ” እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ሁለቱም የማስተንተኛ ጊዜዎችን ይሰጣል፡፡ ተጋቢዎት
ትርጉሞች ያስኬዳሉ፡፡ እየተፋቱ እንደገና የመጋባት ሁለት ዕድል
** ፍችውን የፈፀመው ከሚስቱ ጋር አላቸዉ፡፡ ከዚያ በኃላ ግን ሶስተኛ ፍች
ለመለያየት አስቦና ወስኖ መሆን አለበት፡፡ ከተፈፀመ የመጨረሻና የመቆራረጫ ይሆናል፡፡
ፍችን መሐላ ማድረጉ በርሱ ዛቻ መስንዘሩና ሚስት ሌላ ወንድ አግብታ እስካልፈታች ድረስ
ማስፈራራቱ ግን ተፈፃሚነትን ያሳጣዋል፡ ዳግም በትዳር መኖር አይፈቀድላቸውም፡፡
፡ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው የህገ- ሸረዓ ከዚህ ድንጋጌ አንፃር ሲታይ በአንድ
ምሁራን ዕይታ ይህን ያመለክታል፡፡ ከፊል ቅጽበትና ቃል ሶስት ጊዜ መፍታትን መናገር
የሰለፍ ምሁራን ይህን ዕይታ አራምደዋል፡፡ የቁርአንን አስተምህሮ የሚፃረረ ነው፡፡ ኢማም
ኢማም ኢብነል ቀይም እና ሸይኻቸው ኢብን ኢብን ተይሚያህ እና ተማሪያቸው ኢብነል
ተይሚያህም ሚዛን የሚደፋው ሀሳብ ይህ ቀይም ይህን አቋም በመረጃ አስደግፈው
እንዳሆነ ተናግረዋል፡፡ አብራርተዋል፡፡ የበርካታ ዐረብ ሀገሮች የሸርዓ

7
ፍርድ ቤቶችም በዚህ አቋም በመስራት ላይ አቅም ግምት ውስጥ የከተተ/ የገንዘብ ድጐማ
ይገኛሉ፡፡ ተደንግጐላቸዋል፡፡ ይህ /ድጐማ/ አላህን
** ፍች ሴት ከባሏ የምታገኘውን ቀለብ በሚፈሩ ሰዎት ላይ በገዴታነት ፀና፡፡” (አል –
አያሳጣትም፡፡ በ”ዒዳ” ወቅት ሊቀልባት በቀራህ፡ 2:241)
ግድ ይላል፡፡ ባልም ከቤቷ ሊያስወጣት ይህ ቁሳዊ ድጋፍ ሁሉንም በፍች ከባላቸው
አይፈቀድለትም፡፡ ከርሱ ቀረብ ብላ እንደትቆይ የተለዩ ሴቶችን ያጠቃልላል፡፡ ድንጋግጌው
ሸርዓው ያስገድደዋል፡፡ ይህ የሆነበት የፍቅር ሴቷ በፍች የሚደርስባትን የቀልብ ስብራት
ስሜት ዳግም እንዲያንሰራራ፣ ጥልና ብዥታ ለመጠገን የታለመ ነው፡፡
ተገፎ ትዳርን የማደስ ሀሳብ ህያው እንዲሆን ** ባልም የፈታትን ሚስቱን ስም ማጥፋት፣
ዕድል ለመስጠት ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- እርሷንም ሆነ ቤተሰቧን ማወክ አይፈቀድለትም፡
“አላህ ከዚህ /ፍች/ በኋላ አዲስ ሁኔታን / - አላህ(ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-
ዳግም የመጣመርን ጉጉት ይፈጥር እንደሆነ “ከዚያ በኋላ /ባል ሚስቱን/ በመልካም
የምታውቀው ነገር የለምና፡፡” (ሱረቱ አል – ሁኔታ መያዝ ወይም በበጐ አኳኋን /
ጦላቅ፡ 1) ሳይበድላትና መብቷን ቅንጣት ሳይደፈር
ማሰናበት ግድ ይሆንበታል፡፡” (አል – በቀራህ፡
2:229)
“በመካከላችሁ /ባለ ግንኙነት/ ችሮታን /
ከግዴታ በላይ መስጠት፣ ለሌሎች ጥቅም ሲሉ
የራስን ድርሻ መተውን/ አትዘንጉ፡፡”(አል –
** ፍች ወንዱ የሴቷን የጥሎሽ ገንዘብ / በቀራህ፡ 2: 237)
መህር/ እንዲያስቀር ወይም ያበረከተላትን *^* የኢስላም የፍች ስርዓት ይህን
ስጦታ እንዲያስመልስ ዕድል ወይም ፍቃድ ይመስላል፡፡ በሚፈለገው ጊዜ፣ ቦታ፣
የሚሰጥ አይደለም፡፡ አላህ(ሱ.ወ) ይህን
መጠን፣ ጥሩ በሆነ የአፈፃፀም ስልትና
አስመልክቶ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡-
ለበጐ ዓላማ ብቻ የሚፈፀም ስርዓት ነው፡
“እናንተ ባሎች፣ ለሚስቶቻችሁ ፡*^*
ከሰጣቸኃቸው ጥሎሽ /መህር/ ቅንጣት
ልትቀበሉ አይፈቀድላችሁም፡፡” (አል – በቀራህ
2:229)
** ቁሳዊ ድጋፍ የማግኘት መብት አላት፡
፡ የባልን አቅምና የህብረተሰቡን ተጨባጭ
ባገናዘበ መልኩ፡፡ አላህ(ሱ.ወ)እንዲህ ይላል፡-
“የተፈቱ ሴቶች በ”መዕሩፍ” /የባልን

8
** ከዚህ በፊት እንዳየነው በክርስትናው መህር/ የከፈለው እርሱ ነው፡፡ ከዚያ በኃላ
ዓለም ካቶሊኮች ፍችን ከነጭራሹ እርም ያሉትን ኃላፊነቶች የሚወጣውም እርሱ ነው፡
አድርገዋል፡፡ ኦርቶዶክሶች ደግሞ ከዝሙት ፡ ቤተሰባዊዉ ህይወት በርሱ ትከሻ ላይ
ውጭ ባለ የትኛውም ምክንያት ፍች ተገንብቷል፡፡ እናም ይህን ያህል ከፍተኛ ዋጋ
እንዳይፈፀም አቅበዋል፡፡ መነሻቸውም፡- የከፈለበት ቤተሰብ እጅግ ፈታኝ እና አስቸጋሪ
“እግዚአብሔር ያጣመረውን የሰው ልጅ ሁኔታ ካልተከሰተ በቀር እንዲሀም በቀላሉ
አይፈታም” የሚል ነው፡፡ እንዲፈርስ አይፈቅድም፡፡

በአንፃሩ ሙስሊሞች፡- “አላህ በህጋዊ ** የፍች ስልጣን ለፍርድ ቤት መስጠቱም


ድንጋጌዎች መቁጠርም መምታትም ይችላል፡፡ አግባብ አይደለም፡፡ ከጓዳ መውጣት፣ አደባባይ
” ድንጋጌዎቹም የሰውን ልጅ ጥቅም፣ ደህንነትና መስማት የሌለባቸዉ የፍች ምክንያቶች
ምቾት ያገናዘቡ ናቸዉ፡፡ የሰው ልጆችን ጥቅም አሉ፡፡ ችሎት ቀርበው ዳኞች ሊሰማቸው፣
ከነርሱ ይበልጥ እርሱ ያውቃልና” የሚል ነው፡፡ ፀሐይ ሊሞቋቸው፣ ጠበቆች ሊቀባበሏቸው፣
ጋዜጦችም የዓምድ ማድመቂያ ሊያደርጓቸው
የማይገቡ የጓዳ ጉዳዮች አሉ፡፡
በተጨማሪ ምዕራባዊያን የፍችን ስልጣን
ለፍርድ ቤት የሰጡ ቢሆንም ፍች አልቀነሰም፡፡
ፍች የሚፈልጉ ተጋቢዎችን ፍላጐት መገደብና
ፍችውን ማስቀረት አልሆነላቸውም፡፡
*^ * ታዲያ ሴቷ እንዴት ትገላገል?*^*
** ክርስትና በፍች ላይ ያለውን አቋም
** ብዙ ሰዎችን የሚያሳስብ ጥያቄ አለ፡፡
በርካታ ክርስቲያኖችን በህጉ ላይ እንዲያምፁ
ይኸውም፣ ፍች ከላይ ለተሰጡት ምክንያቶች
አድርጓል፡፡ በመሆኑም አብዛኛዎቹ ክርስቲያን
ሲባል – በወንድ እጅ ከተደረገ ሸረዓው ለሴቱ
ሀገሮች ፍችን በተመለከተ ሰው ሰራሽ ህጐችን
ምን ዋስትና ሰጥቷል? ባሏ ፀባየ ከርዳዳ፣
ለማጽደቅ ተገደዋል፡፡ እነዚህ ህጐቻቸው ፍችን
ወይም ስነ ምግባር የሌለው ወይም መብቷን
ኢስላም ያስቀጠመጣቸዉ አይነት ገደቦች፣
በግልጽ የሚጋፋ ቢሆን፣ ኃላፊነቱን መወጣት
ግዴታዎችና የሞራል ደንቦች ሳይደረግባቸዉ
የሚያስችል አካላዊና ቁሳዊ አቅም ባይኖረው፣
እንዳሻቸው እንዲፈጽሙ መብት ይሰጧቸዋል፡
ወይም በሌላ ምክንያት ከባሏ ጋር መኖር
፡ እናም ለተራና መናኛ ምክንያት ፍች ቢፈጽሙ
ባትፈልግ በምን መንገድ መገላገል ትችላለች?
አያስገርምም፡፡ የጋብቻ ህይወታቸው ምንጊዜም
የመንኮታኮት አደጋ እንዳንዣበበበት ነው፡፡
*^* ፍቺ ለምን በወንዶች እጅ ሆነ ?*^*
** ምላሻችን፣ ወንዱ የቤተሰቡ ተንከባካቢና
የመጀመሪያ ተጠሪ ስለሆነ ነው፡፡ ጥሎሽ /

9
** የዚህ ጥያቄ ምላሹ ሸሪዓዉን የደነገገው
ጥበበኛ አምላክ ለሴት ልጅ በርካታ መውጫ
መንገዶችን አመቻችቶላታል፡፡ አንዱን ተጠቅማ
ጋብቻዋን ማፍረስ ትችላለች፡፡ እነርሱም፡-
1. በጋብቻ ውል ወቅት ፍች በእጂ ይሆን
ዘንድ መዋዋል ትችላለች፡፡ በአቡ ሐኒፋና
በኢማም አህመድ መዝህቦች ይህን ማድረግ
የተፈቀደ ነው፡፡ በሶሒሕ የሀዲስ ዘገባ
የሚከተለው ተላልፏል፡-
* በሀዲስ እንዳተላለፈውም የሳቢት ቢንት
“ከውሎች ሁሉ ልትፈጽሙት ይበልጥ ቀይስ ሚስት ከነቢዩ ዘንድ ቀረበችና ባሏን እጅግ
የተገባው የጋብቻ ውል ነው፡፡” /ቡኸሪና እንደምትጠላው ነገረቻቸው፡፡ የአትክልት
ሙስሊም/ ስፍራውን ትመልሽለታለሽን? አሏት፡፡ በጥሎሽ
2. “ኹልዕ” ሌላው መንገድ ነው፡፡ ይኸውም /መህር/ ተቀብላው ነበር፡፡ “አዎ” አለች፡፡
ባሏን ያልወደደችና መፍታታ የፈለገች ሴት መልዕክተኛውም ሳቢትን የአትክልት ቦታውን
ለርሷ የሰጠውን ጥሎሽና ሌላ ነገር ለባሏ እንዲረከብና ተጨማሪ ነገር እንዳይጠይቅ
መልሳ ፍች ማስፈፀም ትችላለች፡፡ ፍችውን አዘዙት፡፡ /ብኸሪ/
የጠየቀችው፣ የጋብቻ ህይወቷን ማፍረስ 3. የቤተሰብ ዳኞች ጋብቻውን ማፍረስ
የከጀለችው እርሷ ሆና እያለ ኪሳራውን ባል ይችላሉ፡፡ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-
ብቻ እንዲሸከም መፍረድ ፍትሃዊ አይደለም፡
፡ አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- “በመካከላቸው አለመግባባት እንዳለ
ከተረዳችሁ ከርሱ ቤተሰብ የሆነን ከርሷም
“ሁለቱም ወገኖች የአላህን ህግጋት ቤተሰብ የሆነን የቤተሰብ ዳኞች ሰይሙ፡
ወሰኖች እንጥሳለን የሚል ስጋት ካደረባቸዉ ፡ እርቅን የሚሹ ከሆነ አላህ ያስማማቸዋል፡
በቀር፣ እናንተ /ባሎች/ጥሎሽ /መህር ቅንጦት ፡” (ሱረቱ አን -ኒሳእ፡ 35)ቁርአን የቤተሰብ
ልትቅበሉ አይፈቀድላችሁም፡፡”(ሱረቱ አል – ሽማግሌዎችን “ዳኞች” በማለት መሰየሙ
በቀራህ 229) የመፍረድ ስልጣን እንዳላቸው ያመለክታል፡
፡ ከሶሐቦች አንዱ ለቤተሰብ ዳኞች እንዲህ
ብሏቸዋል፡- “ማስማማት ከፈለጋችሁ
አስማሟቸው ካልፈለጋችሁም አለያዩዋቸው፡፡”
4. ባል ወሲብ መፈፀም የሚያስችለው
አካላዊ ነውርና ድክመት ካለበትም ሚስት
ጉዳዩን ለፍርድ ቤት አቅርባ ዳኛው ጋብቻውን
እንዲያፈርስ ማድረግ ።

10

You might also like