You are on page 1of 6

ብዙሚስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡


መግቢያ
ስለ ጋብቻ የሚያጠናው የትምህርት ዘርፍ በምሁራን ዘንድ ማትሪሞኒ”matrimony” ይባላል፤ ይህም ስነ-
ጋብቻ ጥናት የሚያጠኑ ምሁራን በዋነኝነት ለሁለት ይከፍሉታል፦
1. ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ሆሞ-ሴክሹአል”homosexual”
2. ተቃራኒ ፃታ ሄትሮ-ሴክሹአል”Heterosexual” ይባላሉ። መቼም ተመሳሳይ ፃታ ግንኙነት ለጊዜው
አርስታችን ስላልሆነ ወደ ተቃራኒ ፃታ ጋብቻ እንሂድ፤ ተቃራኒ ፆታ ጋብቻ እራሱ በአራት ይከፈላል፤
እነርሱም፦
1 ኛ. አንድ ወንድ ለአንድ ሴት አንዲት ሴት ለአንድ ወንድ ሲሆን ሞኖጋሚ”Monogamy” ይባላል፤
“Monogamy” የግሪክ ቃልነው፥ “mono” ማለት “ብቻ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት
ነው።
2 ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጋሚ”Polygamy” ይባላል፤ “polygamy”
የግሪክ ቃል ነው፥“poly” ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gamy” ደግሞ “ጋብቻ” ማለት ነው።
3 ኛ. አንድ ወንድ ለብዙ ሴት ሲሆን ፓሊአንድሪ”Polyandry” ይባላል፤ “Polyandry” የግሪክ ቃል ነው፥
“poly” ማለት“ብዙ” ማለት ሲሆን “andry” ደግሞ “ወንድ” ማለት ነው።
4 ኛ. አንዲት ሴት ለብዙ ወንድ ሲሆን ፓሊጂኒ”Polygyny” ይባላል፤ “Polygyny” የግሪክ ቃል ነው፥ “poly”
ማለት “ብዙ” ማለት ሲሆን “gyny” ደግሞ “ሴት” ማለት ነው፤ ይህኛው ጋብቻ በማህበራዊ
ጥናት”sociology” ላይ የተቀመጠ መረጃ እንጂ ስነ-መለኮታዊ ጥናት”theology” ላይ አልተቀመጠም።
ይህን በግርድፉ እና በሌጣ ካየን ዘንዳ ደርዝና ፈርጅ ባለው መልኩ ስለ አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry”
ከቁርአን እና ከባይብል እናያለን፦
“ብዙ ሚስት በቁርአን”
“አሕካም” “ ‫ أحكام‬የሑክም” ُብዙ ቁጥር ሲሆን “ፍርድ” ወይም “ህግ” ማለት ነው፤ በኢስላም “ህጎች”
በአምስት ይከፈላሉ፤ እነርሱም፦
1 ኛ. “ፈርድ” ‫ فرض‬ማለትም “የታዘዘ” (ግዴታ)
2 ኛ. “ሙስተሐብ” ”‫ مستحب‬ማለትም “የተወደደ”
3 ኛ. “ሙባሕ” ‫ مباح‬ማለትም “የተፈቀደ”
4 ኛ. “መክሩህ” ”‫ مكروه‬ማለትም “የተጠላ”
5 ኛ. “ሐራም” ”‫ حرام‬ማለትም “የተከለከለ ናቸው።
ይህ “ፊቅህ” ‫فقه‬የተባለውን የስነ-ህግ ጥናት ዋቢና ታሳቢ ያደረገ ነው፤ “ፊቅህ” ስነ-ህግ ጥናት”the study of
law” ሲሆን ህግ አዋቂ ደግሞ “ፈቂህ” ‫ فقيه‬ይባላል፤ ይህንን ነጥብ ያነሳሁት ስለ አሕካም ለመዳሰስ ሳይሆን
አንድ ወንድ ለብዙ ሴት”Polyandry” የተባለው የጋብቻ አይነት በኢስላም በኒያ ሙስተሐብ ሲሆን በፍትህ
ሙባሕ ነው፤ ነገር ግን ፈርድ አይደለም፦
4:3 በየቲሞችም ማግባት አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ፣ ዝሙትንና ከተወሰነላችሁ በላይ ማግባትንም ፍሩ፤
ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም፣ አራት አራትም አግቡ። አለማስተካከልንም
ብትፈሩ፣ “”አንዲትን ብቻ””፣ ወይም እጆቻችሁ ንብረት ያደረጉትን ያዙ፤ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ
ነው።
በኢስላም በፍትህ ማስተካከል ከተቻለ እስከ አራት ማግባት ይቻላል፤ ነገር ግን ያ ካልሆነ አንዲት ብቻ ነው
ማግባት ያለበት፤ እዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄ አላህ የጋብቻን ገደብ እስከ አራት ካለ ለምንድን ነው
ነብያችን እስከ ዘጠኝ ያገቡት? የሚል ነው፤ አንደኛ ምላሽ የሚሆነው አምላካችን አላህ ስለፈቀደ ነው፤
ሁለተኛ እንደሚታወቀው ቁርአን በአንድ ጊዜና ቦታ የወረደ ግህደተ-መለኮት ሳይሆን በሒደት የወረደ ግህደተ-
መለኮት ነው፤ መካ ላይ ለአስር ዓመታትን ሲወርድ መዲና ላይ ደግሞ ለአስራ ሶስት ዓመታትን
ወርዷል፤ የዓለማቱ ጌታ አላህ ጋብቻን የመጨረሻ ገደብ አራት ብቻ መሆኑን የሚያበስረው አንቀፅ ሲያወርድ
ነብያችን ቀደም ብለው ዘጠኝ ሚስቶች ነበሯቸው፤ ይህ የቁርአን ታሪካዊ ዳራ ከአለመረዳት የሚመጣ ጥያቄ
ነው።
በእስልምና ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ለምን ተፈቀደ?
ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት (Polygamy) ከአንድ በላይ የትዳር ጓደኛ መያዝ የሚቻልበት የጋብቻ ስርዓት
ነው፡፡ይህ አይነቱ ጋብቻ በሁለት አበይት ክፍሎች ይከፈላል፡፡
ሀ. አንድ ወንድ ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት የሚቻልበት ስርአት
ለ. አንዲት ሴት ከአንድ ባል በተጨማሪ ማግባት የምትችበት ሥርዓት ናቸው፡፡
እስልምና ለአንድ ወንድ ከአንዲት ሴት በላይ ማግባትን በወሰን የፈቀደ ሲሆን ፣አንዲት ሴት ከአንድ በላይ ከሆኑ
ወንዶች ጋር የምታደርገው ጋብቻም ሆነ ማንኛውም መሰል ግንኙነት በጥብቅ ያወግዛል፡፡ወደ ዋናው ጥያቄ
እንምጣና እስልምና ለምድን ነው
ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት ለወንዶች የፈቀደው የሚለውን እንይ፡፡
1.«አንድ ብቻ አግቡ»የሚል ቃል በብቸኛነት ሰፍሮ የሚገኘው በቁርአን ብቻ ነው፡፡
ሀ. በምድራችን ላይ ያለ የትኛውም ሀይማኖት ጋብቻን ጋብቻን በተመለከተ የስቀመጠው ወሰን የለም፡፡
የትኛውም የሐይማኖት መጽሐፍ በጥቅሉ የጋብቻን ቅዱስነትና የመሳሰሉትን ከመጥቀስ ባለፈ አንድ ወንድ
አንድ ሴት ብቻ ያግባ ወይም ብዙ ያግባ በሚል የጋብቻ ወሰን አላስቀመጠም፡፡መጽሐፍ ቅዱስ ፣በቬዳስ
፣በራማያን፣በማሀባራት ፣በጊታም (የሕንድ ቅዱሳን መጽሐፍት ናቸው) ሆነ በታልሙድ (የአይሁዶች
መጽሐፍ) የዚህ አይነቱን ወሰን አናገኝም፡፡በሌላ አባባል የነዚህ ሀይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው የፈለገውን
ያህል ሚስት ቢያገባ ማንም ከልካይ አልነበረበትም፡፡ ከጊዜ ብዛት ግን ከባህልና ለአንዳንድ ውጫዊ ተጽዕኖዎች
የተነሳ የሒንዱና የክርስቲያን ቀሳውስት ከአንድ ሚስት በላይ ማጋባትን ከለከሉ፡፡
ለ. ጥንታዊያን ክርስቲያኖች የፈለጉትን ያህል ሚስት ያገቡ ነበር ፡፡ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ሌሎች
ቅዱሳን መጽሐፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ያስቀመጡት ክልከላ ስላልነበረ ነው፡፡ከጥቂት መቶ ዓመታት በፊት ግን
ቤተ-ክርስቲያን ለክርስቲያን ወንዶች ከአንድ ሚስት በላይ ማግባትን ክልክል ያደረገውን ሕግ አወጣች፡፡
ሐ. ወደ አይሁዶች ስንመጣ ከ 950-1030 የኖረው ራቢ ጌርሾም ቤን የሁዳ ወንድ ከአንድ ሴት በላየ እንዳያገባ
የሚከለክለውን ሕግ እስካወጣበት ጊዜ ድረስ ይህ ጋብቻ ቀጥሎ ነበር፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ አብርሀም ሁለት ሚስቶች ሰለሞን ደግሞ 700 ሚስቶች ነበሩት ይላል፡፡በስፔንና ፓርቹጋል
እንዲሁም በሙስሊም አገሮች የሚኖሩ የአይሁድ ማህበረሰቦች በ 1990 ዋናው የእስራኤል ራቢኔት
እስከከለከለበት ጊዜ ድረስ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ያገቡ ነበር፡፡
2. ቁርአን ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት ከወሰን ጋር ይፈቅዳል፡፡
ቀደም ሲል እንደጠቀስነው አንድ ብቻ አግቡ የሚል ሐረግ የያዘ የሀይማኖት መጽሐፍ ቁርአን ብቻ
ነው፡፡«ከሴቶች ለናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ፣ ሦስት ሦስትም ፣አራት አራትም አግቡ፡፡
አለማስተካከልንም ብትፈሩ አንዲት ብቻ አግቡ፡፡» {ሱረቱ አል ኒሳእ፡3)
ከቁርአን መውረድ በፊት በሚስት ቁጥር ላይ በየትኛውም ሀይማኖት ሕግ ምንም አይነት ገደብ አልነበረም፡
ብዙ ሰዎች በርካታ ሚስቶችን ያገቡ ነበር ፡፡እንደውም አንዳንድ ወንዶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ሚስቶችን
ያገቡ ነበር፡፡እስልምና ግን የሚስቶችን ቁጥር እስከ አራት ብቻ ብሎ ወሰን አበጀለት፡፡አንድ ሙስሊም ወንድ
በተገቢው ሁኔታ ሳያዳላ ሊያስተዳድራቸው የሚችል ከሆነ ሁለትም ሦስትም ሆነ አራት ሴቶችን ማግባት
ይችላል፡፡በዚያው አል-ኒሳእ ምዕራፍ ቁጥር 129 ላይ እንዲህ ይላል፡፡
«በሴቶች መካከል ምንም እንኳን ብትጓጉ(በፍቅር) ለማስተካከል አትችሉም፡፡»{ሱረቱ አል ኒሳእ፡ 129)
ስለዚህ ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት በእስልምና የተለየ ፈቃድ (Exceptional Permission) እንጂብዙ
ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እንደሚያስቡት ሕግ ወይም ትእዛዝ አይደለም፡፡
በእስልምና የፈቃድና የክልከላ ህግጋት በአምስት ይከፈላሉ፡፡ ከላይ ለመጥቀስ አንደተሞከረው..
ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በሦስተኛው ሙባህ ወይም የሚፈቀድ ከሚለው ሕግ ውስጥ የሚመደብ ሲሆን
፣ብዙ ሚስቶች ያሉት
አንድ ሙስሊም አንድ ሚስት ብቻ ካለው ሌላ ሙስሊም የሚሻልበት ምንም ምክንያት አናገኝም፡፡
ምክንየያቱም ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት ወደ ሁለተኛው ወይም የሚበረታታ እና የሚወደድ ከሚለው ሕግ
ውስጥ ገብቶ እንኳ አናገኘውምና ነው፡፡ ሴቶች በተፈጥሮ ከወንድ የበለጠ ረጀም እድሜ ይኖራሉ፡፡በተፈጥሮ
ሴቶችና ወንዶች በተመሳሳይ መጠን ይወለዳሉ፡፡ነገር ግን በሕፃንነት እድሜ ከሚሞቱት ወንዶች ሕጻናት
አንፃር ሲታይ በሕፃንነት የሚሞቱ ሴት ህፃናት ቁጥር ዝቅተኛ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሴትሕፃናት ከወንድ ሕፃን
የተሸለ በሽታንና ጀርምን መዋጋት የሚችሉ ሲሆኑ ይህም በቁጥር ከወንዶች በልጠው እንዲገኙ ያደርጋቸዋል፡፡
በተጨማሪም አለማችን በተለያዩ ጦርነቶችና ሰው ሰራሽ ሆነ በተለያዩ አደጋዎች የተከበበች ናት፡፡ በዚህ የተነሳ
በጦርነትም ሆነ በተለያዩ አደጋዎች የሚሞቱት ወንዶች ቁጥር ከሴቶቹ ጋር ሲነፃፀር እጀግ ከፍተኛ ሆኖ
ይገኛል፡፡ በአለማችን የሴቶች ቁጥር ከወንዶች የበለጠ ነው።
• በአሜሪካ አገር የሴት አሜሪካዊያን ቁጥር ከወንዶች በ 7.8 ሚሊዮን ይበልጣል፡፡ሌላው ቀርቶ በኒውዮርክ
ከተማ ብቻ 1 ሚሊዮን ትርፍ ሴቶች ይገኛሉ፡፡ከጠቅላላው የኒውዮርክ ከተማ ሕዝብ ውስጥ አንድ ሶስተኛው
ወንድ ግብረሰዶማውያን (ጌይ)ናቸው፡፡ በአሜሪካ ደግሞ 25 ሚሊዮን ግብረሰዶማውያን ይገኛሉ፡፡ ይህ ማለት
ከጠቅላላው የአሜሪካ ወንዶች ውስጥ 25 ሚሊዮን ሚስት ማግባት የማይፈልጉ (የማይችሉ) ወንዶች አሉ
ማለትነው፡፡
• በእንግሊዝ ሀገር 4 ሚሊዮን ትርፍ ሴቶች ሲኖሩ ጀርመን ውስጥ ደግሞ 5 ሚሊዮን ባል ሊያገቡ (ሊያገኙ)
የማይችሉ ሴቶች አሉ፡፡ ሩሲያ ደግሞ 9 ሚሊዮን የጋብቻ ያለህ የሚሉ ሴቶችን ለዓለማችን አበርክታለች፡፡
በዚህ እንቀጥል ካልን ዓለማችን ላይ በአጠቃላይ ምን ያህል ከፍተኛ የሆነ የወንዶች ችግር እንዳለ ሊያውቅ
የሚችል አላህ (ሱ.ወ) ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
ሁሉንም ወንድ ከአንድ በላይ እንዲያገባ መከልከል በተግባር ሊፈፀም አይችልም፡፡
ከላይ እንዳየነው ሁሉም ወንዶች አንድ ሚስት ብቻ ያግቡ የሚል ሕግ ብናወጣና ይህንን ህግ ተፈፃሚ ብናደርግ
በአሜሪካ ብቻ 30 ሚሊዮን ትዳር አልባ ሴቶች እንፈጥራለን፡፡ከላይ ያየናቸውን የእንግሊዝ እና ሩሲያ ትርፍ
ሴቶች ብናክልበት ደግሞ ቁጥሩ የትየለሌ ይሆናል፡፡
እስቲ የኔና ያንተ እህቶች ባል ማግባት ካልቻሉ 30 ሚሊዮን ሴቶች መካከል እንደሆኑ አድርገን እናስብ ከነዚህ
ሴቶች መካከል የተቃራኒ ፆታ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች የሚኖራቸውን አማራጭ እንመልከት፡፡ባጭሩ ሁለት
አማራጭ ብቻ የሚኖራቸው ሲሆና ፣
• አንደኛው ሁለተኛ ሚስት ሆኖ መኖር ሲሆን፣
• ሁለተኛው ቀሪ አማራጭ ደግሞ«የብዙሀን ሚስት» ወይም «የሕዝብ ንብረት» (አመንዝራ) ፣ሴተኛ አዳሪ
መሆን ነው፡፡
መቼም ማንኛዋም ጨዋና ጤነኛ ሴት የመጀመሪያውን ትመርጣለች ተብሎ ይታሰባል፡፡ እንግዲህ ባጠቃላይ
ሲታይ አሁን ከዘረዘርናቸው ምክንያቶች በተጨማሪ እስልምና ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት ሲፈቅድ ሌሎች
ብዙ ምክንያቶች በተጨማሪ እስልምና ከአንድ ሚስት በላ ማግባትን ሲፈቅድ ሌሎች ብዙ ምክንያቶች
ቢኖሩትም በዋነኛነት ግን የሴቷን ክብር ጠብቆ ለማቆየት ሲባል ነው፡፡
ወደ ሳይንሱ ዓለም ጎራ እንበል እስኪ በቅርቡ የተካሄዱ ሳይንሳዊ ጥናቶች ወንድ ዘንድ የሚገኘው የፍቅር
ቅመም ሴትዋ ዘንድ ከሚገኘው የፍቅር ቅመም የሚለይ መሆኑን አረጋግጠዋል። ይህም አያሌ የሳይንስና
የምርምር ተቋማትን በወንድና በሴት መካከል በሚገኙት የፍቅር ስሜቶች ልዩነቶች ላይ ጥልቅ
ምርምር እንዲያደርጉ ገፋፍቷቸዋል። ሳይንቲስቶቹ የደረሱበት ውጤት በጣም አስደማሚ ሲሆን፣የወንድ
ጂኖች ብዙ ግንኙነቶች እንዲኖሩት ሲገፋፉት የሴቷ ጂኖች ደግሞ ወደ መረጋጋትና ወደ ነጠላ ግንኙነት
ይገፋፏታል። ወንድ ከአንድ በላይ ሴቶችን በአንድ ጊዜ ለአንዷ ያለው ፍቅር ለሌላዋ ባለው ፍቅር ላይ ምንም
ተጽእኖ ሳይፈጥርበት ማፍቀር የሚችል መሆኑን ዘመናዊው ሳይንስ በተጨባጭ አረጋግጧል።
• የ CNN ድረገጽ በዮታ እስቴት ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑትን ሊዛ ዳይመንድን በመጥቀስ
እንዳስነበበው፣ የወንዶች ወሲባዊ ግንኙነት ከአንድ በላይ ሴት ጋር የመሆኑ ሁኔታ ከአካላዊ አፈጣጠራቸው
የሚመነጭ ስለመሆኑ ስነሕይወታዊ ማስረጃዎች መኖራቸው ተረጋግጧል።
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተመራማሪዎች ቡድን በ 2007 ባካሄደው አንድ ምርምር ሴቶች ከወንዶች በተቃራኒ፣
ዋነኛ ትኩረታቸው የሚያነጣጥረው በሰውነቶቻቸው ላይ ወይም በልጆቻቸው እንክብካቤ ላይ መሆኑንና
ይህም ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የመተሳሰር ስሜት በሚጨምረው አክስቶሲን ሆርሞን ምክንያት መሆኑን
ደርሰውበታል።የተወሰኑ የወንዶች የአንጎል ክፍሎች ከሴቶቹ በእጥፍ
ያህል የሚበልጡ መሆናቸውን፣በተባዕትና በእንስት አንጎል መካከል ያለው ትልቁ ልዩነትም፣በወንዶች ዘንድ
ላለው ወሲባዊ ፍላጎት ተጠያቂ የሆነው የአንጎል ክፍል፣ከሴቶቹ ተመሳሳይ የአንጎል ክፍል በሁለት ተኩል እጥፍ
ያህል የሚበልጥ መሆኑ ነው።እነዚህ ሳይንሳዊ መረጃዎች ትክክለኛነት ስለተረጋገጠ ተጽእኖ ማሳደራቸው
እሙን ነው።

☞በአይሁድ ሃይማኖት ውስጥ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን፣ራቢ ገርሹም አሽክናዚ (960-1040) ከአንድ በላይ
ማግባትን ክልክል
እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የተፈቀደ ሆኖ ቆይቷል።
☞በክርስቲያኑ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ግን ብዙ ሚስት ማግባት ከአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ
እንጂ ክልክል
ተደርጎ አያውቅም። እስከ ዛሬም ድረስ ሞርሞንን በመሳሰሉ አንዳንድ ቤተክርስቲያኖች ዘንድ እንደ ተፈቀደ
ቀጥሏል።
እውን ብዙ ሚስት ማግባት በክርስትና ክልክል ነውን?
☞ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።" መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 12 : 8) እግዛብሄር
ለነቢዩ ዳዊት የሰጠሁህ ሚስቶች ካነሱህ እጨምርልሃለው ጠይቀኝ እያለው ነው።
☞"የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ የጌታህንም ሚስቶች በብብትህ ጣልሁልህ፤ የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት
ሰጠሁህ፤
#ይህም_አንሶ_ቢሆን_ኖሮ_ከዚህ_የበለጠ_እጨምርልህ_ነበር።" መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 12 : 8)
ታድያ ክርስቲያን ወገኖች ለምን ይሆን ነብይ ዳዊት ከ አንድ በላይ ሚስት ያገባው በእግዛብሄር ፍቃድ ሳይሆን
በራሱ ፍቃድ ነው ብለው የሚሚግቱን? እግዛብሄር እኮ ለዳዊት ያለው እኮ☞ከሰጠሁህ ሚስቶች ይህም አንሶ
ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር።
ስለዚህ ከ አንድ በላይ ሚስት ማግባት እንደሚፈቀድ ከነቢዩ ዳዊት እንማራለን ማለት ነው።እውን ብዙ ሚስት
ማግባት ክልክል ነውን?

ከአንድ ሚስት በላይ ማግባት በክርስትና ክልክል(ሀጢያት) ነውን?


በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ አራት ሴት የሚያገባበት አግባብ እንዳለ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ
ክርስቲያኖች ይህን መነሻ በማድረግ ኢስላምን ሲያብጠለጥሉ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ይህ አካሄዳቸው ሰዎቹ
ምን ያክል ለመፅሐፎቻቸው ወይ ባይተዋር ወይ ደግሞ ሽፍታ እንደሆኑ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡እንጂ
በመፅሐፎቻቸው ይሄ ጉዳይ እጅግ በተጋነነ እና ኢስላም ከሚፈቅደውም በራቀ መልኩ የሚገኝ ነው፡፡ ነብያት
ሳይቀሩ ብዙ ሚስቶች እንነበራቸው ተገልጿል፡፡
ለምሳሌ ያክል፡-
1.”ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፣ አንዲቱም የተጠላች ሁለት #ሚስቶች ቢኖሩት…” [ዘዳግም 21:15]
2. “ዔሳው ከከነዓን ልጆች #ሚስቶችን አገባ፡፡” [ኦሪት ዘፍጠረት 36፡2]
3. “ላሜሕም #ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው..” [ኦሪት ዘፍጥረት 4፡23]
4. “ለጌዴዎንም #ብዙ_ሚስቶች ነበሩትና…” [መፅሃፈ መሳፍንት 8:30]
5. “የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራሀም ሚስት ትሆነው ዘንድ
ሰጠችው።”
[ኦሪት ዘፍጠረት 16:3]
6. “ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን #ቁባቶቹንናሚስቶቹን ከእየሩሳሌም ወሰደ፣…” [መፅሐፈ
ሳሙኤል ካልእ፡ 5፡13]
7. “ያዕቆብም ተነሳ፣ ልጆቹንና #ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፡፡” [ኦሪት ዘ ፍጥረት 31፡ 17]
8. 14 ሚስቶች!!! “አብያም ጸና፣ #አስራአራትን #ሚስቶች አገባ” [መፅሐፈ ዜና መዋእል ካልእ 13፡21]
9. “ሮብአምም ከሚስቶቹና ከእቁባቶቹ ሁሉ የአቤሴሎምን ልጅ ሞአብን ወደደ #18 ሚስቶች #60 እቁባቶች
ነበሩት፡፡”
[መፅሃፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 11:21]
10. 700 ሚስቶች እና 300 ቁባቶች ለሰሎሞን!!! “ለእርሱም ወይዛዝር የሆኑ #700 ሚስቶች #300
ምቁባቶች ነበሩት፤ ሚስቶቹም ልቡን አዘነበሉት።” [መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ 11:3]
ከአንድ በላይ ማግባት በባይባል የተከለከለበት አንድ ጥቅስ የለም፤ ከዚያ ይልቅ ከአንድ በላይ ያገቡ ነቢያት በቁና
ሰፍሯል፦
1 ኛ ሳሙኤል 1፥2 ሕልቃ…””ሁለትም ሚስቶች” ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና የሁለተኛይቱም ስም ፍናና
ነበረ፤
1 ኛ ሳሙኤል 25፥43 ዳዊትም ደግሞ ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ወሰደ፤ “”ሁለቱም ሚስቶች” ሆኑለት።
1 ኛ ዜና መዋዕል 4፥5 ለቴቁሔም አባት ለአሽሑር ሔላና ነዕራ “”የተባሉ ሁለት ሚስቶች”” ነበሩት።
1 ኛ ዜና መዋዕል 14፥3 ዳዊትም በኢየሩሳሌም “”ሚስቶችን”” ጨምሮ ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች
ወለደ። አይ እነርሱ አደረጉት እንጂ ፈጣሪ አልፈቀደላቸውም ከተባለ ፈጣሪ አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ካሉት
እንዴት መንከባከብ እንዳለበት የተናገረው ሳይፈቅድ ነውን? እስቲ እንይ፦
ዘዳግም 21፥15-17 ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች አንዲቱም የተጠላች “”ሁለት ሚስቶች”” ቢኖሩት፥
ለእርሱም የተወደደችው ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው
ልጅ ቢሆን፥ ለልጆቹ ከብቱን በሚያወርስበት ቀን ከተጠላችው ሚስት በተወለደው በበኵሩ ፊት ከተወደደችው
ሚስት የተወለደውን ልጅ በኵር ያደርገው ዘንድ አይገባውም፤ ነገር ግን ከከብቱ ሁለት እጥፍ ለእርሱ በመስጠት
ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ በኵር እንደ ሆነ ያስታውቅ። የኃይሉ መጀመሪያ ነውና በኵርነቱ የእርሱ
ነው።
እግዚአብሔር ከአንድ በላይ ማግባት ቢከለክል ኖሮ ለዳዊት ለዛውን የሰውን ሚስቶችን ይሰጠው ነበርን?
የጌታው የሳኦን ሚስቶች ሰቶት ነበር፤ ከዚያ የበለጠም ካስፈለገ እንደሚጨምርለት ቃል ገብቶለታል፦
2 ኛ ሳሙኤል 12 : 8 የጌታህንም ቤት ሰጠሁህ፥ “”የጌታህንም ሚስቶች” በብብትህ “”ጣልሁልህ””፤
የእስራኤልንና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ “”ይህም አንሶ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ እጨምርልህ ነበር””።”
ሌላው የአዲስ ኪዳን ነብይ ኢየሱስ ነው፤ ኢየሱስ ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው አላለም፤ በብሉይ
የነበረውን ህግ አልሻረም።
ሌላው እራሳቸውን የሚያስጠጉበት ጳውሎስ ነው፤ ሲጀመር ጳውሎስ ነብይ አይደለም፤ ሲቀጥል የሚናገረው
በሞኝነት እንጂ ጌታ አዞት አይደለም፤ ንግግሩ የራሱ እንጂ የጌታ አይደለም፦
2 ኛ ቆሮ 11፥17 እንደዚህ ታምኜ ስመካ “”የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም””።”
ሲሰልስ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ባል ይኑራት አለ እንጂ ለእያንዳንዱ ለራሱ አንድ ሚስት ትኑረው
አንድ ባል ይኑራት አላለም፦
1 ኛ ቆሮ 7፥2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ
ባል ይኑራት።”
ከአንድ በላይ ማግባት ክልክል ነው ያሉት ምዕራባውያን እንጂ ባይብል አይደለም፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ
ማግባት ቢከለክሉም ከአንድ በላይ ዝሙት ማድረግ የአንድ ሰው መብቱና ነፃነቱ ነው የሚል መርህ አላቸው፤
ምዕራባውያን በ 17 ኛው ክፍለ-ዘመን ሰው እንዲዋለድና እንዲባዛ ስላልፈለጉ እንጂ የመጡበትን ዳራ መሰረት
አድርገው አይደለም፤ ለዛ ነው ግብረ-ሰዶም እንዲስፋፋ የተፈለገው፤ ይህንን እንደ ሥልጣኔ ቤተ-ክርስቲያን
ግብረ-ሰዶም ታጋባለች፤ ይህ ደግሞ መሠልጠን ሳይሆን መሰይጠን ነው፤
ሥልጣኔ በምጣኔ ካልሆነ ጥፋት ነው፤ ምዕራባውያን ከአንድ በላይ ዝሙት ሲፈቅዱ ኢስላም ደግሞ ከአንድ
በላይ በሃላል ኒካ ማድረግ ይፈቅዳል፦
24:32 ከእናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፤ “ከወንዶች ባሮቻችሁ” ِእና “ከሴቶች ባሮቻቹሁም” َ ለጋብቻ
ብቁ የሆኑትን “አጋቡ” َ፤ ድሆች ቢሆኑ፤ አላህም ከችሮታው ያከብራቸዋል፤ አላህም ስጦታ ሰፊ ዓዋቂ ነው።
2:221 አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ “አታግቡዋቸው”፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ
“ያመነችው ባሪያ” ُ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ

You might also like