Professional Documents
Culture Documents
Benefits of Marriage
Benefits of Marriage
com
የትምህርቱ ዓላማዎች
በትምህርቱ መጨረሻ ላይ ተማሪዎች፡
❖ ማግባት ለተጋቢዎች እንዲሁም ለኅብረተሰቡ የሚሰጠውን ጥቅሞች
ያብራራሉ፡፡
❖ እነዚህን የጋብቻ ጥቅሞችን እውን ለማድረግ ወይም በሕይወት ለመለማመድ
ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ይገልጻሉ፡፡
እግዚአብሔር ለአዳም ሔዋንን የፈጠረበት አንዱ ዓላማ ለአዳም ረዳት (የሕይወት ዘመን ጓደኛ)
እንድትሆነው ነው (ዘፍ.2፡18)፡፡ እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት ለሕይወት እርካታ አስፈላጊ ነው፡፡ ‹‹ሰው
ብቻውን ይሆን ዘነድ መልካም አይደለም›› የሚለው ሐሳብ የወዳጅነትን አስፈላጊነት
ያመለክታል፡፡ ሰው ማሕበራዊ ፍጡር በመሆኑ ወዳጅን ይፈልጋል፡፡ ሚሉ የሆነ ወዳጅ ደግሞ
የሚገኘው በጋብቻ ውስጥ ነው፡፡ ከፍጥረት በኋላ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ነገሮች ሁሉ
ከትዳር ጓደኛ ጋር
ሲገመግም መልካም እንደሆነ ተናገረ፡፡ ወደ አዳም ሲመጣ ግን ብቻውን በመሆኑ መልካም
የሚኖረው ወዳጅነት እንዳልሆነ ተናገረ፡፡ ስለዚህ ሴትን መፍጠር አስፈለገ፡፡ ያገባ ሰው ከአባት፣ ከእናት፣ ከወንድም፣
ከሌሎች ሰዎች ጋር ካለን ከእህትና ከማንኛውም ሰው ይልቅ የምትቀርበውን የሕይወት ዘመን ወዳጅ ያገኛል፡፡ ሴትም
ወዳጅነት በምን ይለያል እንዲሁ፡፡ ወዳጅነታቸው ሁለንተናዊ ሕይወትን ሁሉ የሚነካ ነው፡፡
እንደ አዳም አንድ ሰው በጥሩ አካባቢ ወይም ቤት ውስጥ ቢኖር፣ ለምግብ፣ ለመጠጥ፣
ለመዝናኛ የሚሆኑ ነገሮች ሁሉ ቢኖረው፣ ደስ የሚሰኝነበት ሥራ ሁሉ ቢኖረው፣ እቤት ውስጥ
የሚያጫውቱት ውሾችና ድመቶች ቢኖረው፣ ከወላጆቹ ወይም ወንድም እህቶቹ ጋር ጥሩ
Page 1 of 4
Poimen Ministry Email: poimenministry516@gmail.com
ግንኙነት ቢኖረው የትዳር ጓደኛን አይተኩም፡፡ ሁሉ ነገር ቢኖር በትዳር ጓደኛ የሚሞላ የሕይወት
ክፍል ግን ባዶ ሆኖ ይኖራል፡፡
የባልና ሚስት አንድ ሥጋ መሆን ከትዳር ውጭ ከሚደረገው የተለየ ኅብረት ነው፡፡ በጋብቻ
ከጋብቻ ውጭ እና ውስጥ ወሲብ ወዳጅነትን ይገልጻል፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ
በጋብቻ ውስጥ የሚያሳድግ ነው፡፡ ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም ወሲብ በአብዛኛው የወሲብ ፍላጎትን ለማርካት
በሚደረግ የወሲብ ነው፡፡ በትዳር ውስጥ ወሲብ ሲፈጸም የፍቅር ሙላትን ይገልጻል፡፡ ፍቅር ለማግኘት ሳይሆን
ግንኙነት መካከል ያለው
ያለውን ፍቅር ለማጎልበት ያገለግላል፡፡ ከትዳር ውጭ የሚፈጸም ወሲብ ግን ሲደጋገም ያሰለቻል፣
ከዚያም ወደ መለያየት ያመራል፡፡ የወሲብ ግንኙነት ትክክለኛው ቦታ ጋብቻ ውስጥ ነው፡፡
ልዩነት ምንድነው
በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት መሠረት ልጆች መወለድ ያለባቸው ከባልና ከሚስት ነው፡፡ ጋብቻ
አንዱ ዓላማው ዘር ለመተካት ነው፡፡ ልጆች ደግሞ መወለድ ብቻ ሳይሆን ማደግም አለባቸው፡፡
የልጆች ሁለንተናዊ ዕድገት መልካም እንዲሆን ደግሞ አባትና እናት አብረው ሆነው ማሳደግ
ይኖርባቸዋል፡፡ ሁለቱም አንድ ላይ ሲሆኑ የልጆችን ሁለንተናዊ ፍላጎት የማሟላት ዕድላቸው ከፍ
ይላል፡፡
ሳያገቡ ልጆችን ወልደው በአብዛኛው በጋብቻ ውስጥ ተወልደው በአባትና እናት የሚያድጉ ልጆች ተገቢውን እንክብካቤ
በሚያሳድጉና ተጋብተው ስለሚያገኙ ጤናማ አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ መንፈሳዊና ሥነልቦናዊ ሕይወት ይኖራቸዋል፡፡
ልጆችን ወልደው አብረው የወላጆቻቸውን የቅርብ ድጋፍና ክትትል ስለሚያገኙ በትምህርታቸውና በተሠማሩባቸው የሥራ
በሚያሳድጉ መካከል ምን መስኮች ፍሬያማ የመሆን ዕድላቸው ይሰፋል፡፡ እነዚህ ልጆች ስለቤተሰብ ሕይወት ከወላጆቻቸው
ልዩነት ይኖራል መልካም ምሳሌነትን ስለሚያገኙ ወደፊት ሕይወታቸውን በዚያ መሥመር የመቃኘት ሁኔታን
ያሳያሉ፡፡
ጋብቻ ለጤንነት አስተዋጽኦ እንዳለው ተጋቢዎች ላያውቁ ይችላሉ፡፡ ይህ በብዙ መንገድ ሊከሰት
ይችላል፡፡ ባለትዳሮች በአብዛኛው የሚመገቡት ከቤታቸው ነው፡፡ ይህ ደግሞ የሚመገቡትን
በጥንቃቄ በመምረጥ እንዲመገቡ ይረዳቸዋል፡፡ የተመጣጠነ እንዲሁም እንደ ዕድሜያቸው
ሁኔታ መመገብ ይችላሉ፡፡ በምግብ ዝግጅት ጊዜም ንጽሕናው የተጠበቀ እንዲሆን ማድረግ
ማግባት እንዴት ለሰዎች
ወይም መከታተል ይችላሉ፡፡ ከምግብ ዐይነት እንዲሁም ከንጽሕና ጉድለት የሚመጣውን በሽታ
ጤንነት አስተዋጽኦ
መከላከል ይችላሉ፡፡
ሊያደርግ ይችላል
ጋብቻ የመሠረቱ ሰዎች ለበሽታ ሊያጋልጡአቸው ከሚችሉ ነገሮች ራሳቸውን ይከላከላሉ፡፡ ባልና
ሚስት በወሲብ ግንኙነት ለእርስ በርሳቸው ታማኞች ከሆኑ በወሲብ ግንኙነት ከሚመጡ ተላላፊ
Page 2 of 4
Poimen Ministry Email: poimenministry516@gmail.com
አንዳንድ ጥናቶች በተገቢው ጊዜ ትዳር የመሠረቱ ሰዎች ረጅም ዕድሜ እንደሚኖሩ ይናገራሉ፡፡
ባለትዳሮች በሽታን የመቋቋም አቅማቸው ከፍ ይላል፡፡ በቤተሰብ ውስጥ ያለው መተሳሰብና
መደጋገፍም ጉልበት ይሆናቸዋል፡፡
በዚህ ዓለም እጅግ ባለጠጋ የሆኑ ሰዎች ባለትዳሮች ናቸው፡፡ በአገራችንም ሁኔታ ስንመለከት
በእናንተ እይታ ማግባት
ከፍተኛ ሀብት ያላቸው ሰዎች ባለትዳሮች ናቸው፡፡ ባለትዳሮች ሀብት እንዲያፈሩ አስተዋጽኦ
የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ ከእነዚህም ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡
ሀብት ለማፍራት ያግዛል
• ዋስትና ያለውን ሥራ ለመያዝ ጥረት ያደርጋሉ፤ ሥራቸውን እንዲሁ በቀላሉ
ወይስ ሰው በኢኮኖሚ
አይለቁም፣ ሥራቸውን በትጋት ይሠራሉ፣
እንዳያድግ ያደርጋል፡
• ባለትዳሮች ከሚያገኙት ገቢ የተወሰነውን ገንዘብ ይቆጥባሉ፣ ይህ ደግሞ ቀስ በቀስ
ተወያዩበት፡፡
እያደገ በመሄድ ትልቅ ሀብት ይሆናል፤ ይህን ገንዘብ በሌላ ትርፋማ ሥራ ላይ ያውላሉ፣
• የሚያዋጣቸውን ትርፋማ የሥራ መስክ በጥንቃቄ ይመርጣሉ፣
• ሁለት ሆነው ይሠራሉ፣ ወጪዎቻቸውን ይቀንሳሉ
በአጠቃላይ ለብቻ ከመኖር ቤተሰብ መሥርቶ መኖር በርካታ ጥቅሞች አሉት፡፡ በቤተሰብ ውስጥ
በቀጣይነት የሚኖር የስሜት ድጋፍ፣ መብትና ግዴታዎችን መፈጸም ይኖራል፡፡ አንድ ጊዜ
የሕይወት አጋራችንን ከመረጥን ወይም ልጆች ከወለድን ሁልጊዜ ፍለጋ አንሄድም፡፡ እነዚህ
የቤሰብ አባላት ደግሞ የራሳቸውን ሚና ያከናውናሉ፡፡ የትዳር ጓደኛ፣ ልጅ፣ ወላጅ ፣ ወይም
ወንድም ወይም እህታችን የቤተሰባችን አባላት በመሆናቸው ሚናቸውን በሕይወት ዘመናቸው
ሁሉ በቤተሰብ ተግባራት ውስጥ እንደሚሳተፉ እንጠብቃለን። መስጠትና መቀበል የሚለው
መርሕ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የቤተሰብ አባላቶቻቸውን በሆነ ሁኔታ ውስጥ ብንገኝ
እንደሚደርሱልን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
Page 3 of 4
Poimen Ministry Email: poimenministry516@gmail.com
ጥያቄዎች
❖ ……………………………………………..……….
❖ ………………………………………………………
Page 4 of 4