You are on page 1of 3

9/6/2021 ታላቁ የቤት ስራ፣ የራስን መንፈስ፣ አዕምሮና ስሜትን መለወጥ – Bayissa Olana Gonfa Law Office

BAYISSA OLANA GONFA LAW OFFICE


MENU
Ethiopian Lawyers
ታላቁ የቤት ስራ፣ የራስን መንፈስ፣ አዕምሮና ስሜትን መለወጥ

Posted on July 12, 2019 by Bayissa Olana Gonfa


ጥቂት የማን ባል ሰዎች መለወጥና ለውጥን እንፈራለን፡፡ ለለውጥ ያለን አመለካከት የወረደ ነው፡፡ ለውጥ ግን በትዕይንተ ዓለሙ ላይ በተደጋጋሚና
በቋሚነት ህልው የሚሆን ነው፡፡ ሰውም በዚህ ድንቅ ተፈጥሮ ውስጥ እየኖረ በመሆኑ የለውጡ አካል ነው፡፡ ተፈጥሯዊው ለውጡ እሱ ላይ የሚታይ
ለውጥ ያመጣል፤ ሰውም ለውጥን ከተገበረ በሕይወቱ ላይ የሚታይ ለውጥን ማምጣት ይችላል፡፡ ለውጥ በሁለት በኩል እንደተሳለ ሰይፍ ነው፡፡
አንድም ራስን መለወጥ፤ አንድም ዓለሙን መለወጥ ነው፡፡ የለውጥ ባለቤት የሆነ ሰው ተለውጦ ለዋጭ ይሆናል፡፡ ራሱ ላይ የሚሠራውን ፕሮጀክት
በድል ያጠናቅቃል፡፡

አንዳንድ ለውጥ ሳንዘጋጅበት ከች ይላል፡፡ ተፈጥሯችን ላይ የሚመላለሰው ለውጥ ከፍቃዳችን ውጪ የሆነ ነው፡፡ ለውጡን ብንገፋም ጊዜ ተገን
አድርጎ መለወጣችን አይቀሬ ነው፡፡ ለውጡ እኛ ካመጣነው ይልቅ እሱ በራሱ በእኛ ላይ ያመጣው ይልቃል፣ ይበዛል፡፡ ልጆች ነበርን እንደልጆች
እንጫወትና እናስብ ነበር፡፡ ለውጥ መጣና ልጅነታችንን ሽሮ ወጣትነት ጎራ ውስጥ ከተተን፡፡ ልጅነታችንን ብንናፍቀውም ልጅ እንሁን ብንል
በወጣትነታችን አያምርብንም፡፡ ትኩስነታችን የለውጣችን አንደኛው አካል ነው፡፡ በዚህ ጊዜ መፍጠን ምልክታችን ነው፡፡ መረጋጋት የትአባቱ!
ትኩስነታችንን የሚያበርድ የእድሜ ባቡር ይመጣና ወደለብታው ጉልምስና ይወስደናል፡፡ ለብታው ወደቀዝቃዛው ሽምግልና ያሸጋግረናል፡፡ ይሄ ሁሉ
የለውጥ ውጤት ነው፡፡

አዎ አንዳንዶች ሽማግሌ ሆነው እንደልጅ ሲያስቡ የብዙዎች መሳቂያ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱም ለውጥን ደፍጥጠው ወደኋላ ስለተመለሱ የሚያደርጉት
ሁሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በለውጥ ውስጥ ስታልፍ ለውጥ ያመጣውን ነገር ትቀበላለህ፤ ራስህን ከለውጡ ጋር ትዋጃለህ፡፡ አዎ ለውጡን
የሚቀበልና የሚገራ ማንነት ግን ቀድሞ መገንባት አለበት፡፡ ዕድሜ ብቻውን ለውጥን የሚቀበል ማንነት አያጎናፅፍም፡፡ አለበለዚያ ለውጡ ይከብደንና
ይጫነናል፡፡

ታዋቂው ጥንታዊው ፈላስፋ ሄራክሊተስ እንዲህ ይላል፡-

‹‹በሕይወት ውስጥ ብቸኛው ቋሚ ነገር ለውጥ ነው፡፡ (Change is the only constant in life)›› ይለናል፡፡

ሐቅ ነው! ለውጥ የማይቀር ዕዳ ነው፡፡ ለውጥ ተፈጥሮን ማኖሪያ መንገድ ነው፡፡ ተፈጥሮ ራሱን በራሱ ያስተዳድር ዘንድ አምላክ ለውጥን ፈጠረለት፡፡
ለውጥ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ላይ ይኖር ዘንድ ተፈጥሯል፡፡ ሰው የለውጥ ወኪል ነው፡፡ የተፈጥሮን ለውጥ የሚገነዘበው ሰው ነው፡፡ ተፈጥሮ ራሱን
በራሱ አይመለከትም፡፡ በተፈጠረለት የተፈጥሮ ህግ ኡደቱን እየከወነ፣ ለውጡን እያስቀጠለ ዘላለም ይኖራል፡፡ ሰው ግን የተፈጥሮንና የራሱን ለውጥ
በመገንዘብና በመመልከት ብቻ አያበቃም፡፡ እርሱም በአቅሙ ለውጥን ይከውን ዘንድ አቅም ታድሎታል፡፡ በእሱ አቅም የሚለወጡ ስራዎች
ሞልተውታል፡፡ በለውጥ ውስጥ እንደሚያልፈው እሱም ለዋጭ ሆኖ ለውጥን ይከውናል፡፡ ዛሬ ዓለማችን ለደረሰችበት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ርቅቀት
የለውጥ አጋፋሪዎች በሰሩት ታላቅ የለውጥ ስራ ነው፡፡ ለውጥ መፈለግ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ነገር ግን ብንፈልገውም ባንፈልገውም ለውጥ በጊዜው
መምጣቱን አይተውም፡፡ ለውጥ አይተወንምና እኛም አንልቀቀው!!

ጂም ሮህን የተባለ ፀሐፊ፡- ‹ያንተ ሕይወት የተሻለ የሆነው በእድል ሳይሆን በለውጥ ነው፡፡›› ይለናል፡፡ እውነት ነው! ዕድል አለ ብለን ብናምን እንኳን
እድል የለውጥ ወኪል ነው፡፡ አንድ ሰው ከነበረበት አስተሳሰብና የኑሮ ሁኔታ ወደሌላ አዲስ የሕይወትና የአስተሳሰብ ከፍታ ባላሰበው መንገድና ጊዜ
ሲሻገር ለውጥን መሰረት አድርጎ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ለውጥ ግለሰቡ ሳይዘጋጅ ዓለሙ ይዞበት የመጣው ጣጣ ሊሆን ይችላል፡፡ ዓለም የደረሰበት
የአስተሳሰብ ደረጃ ሁሉም ጋር ይደርስ ዘንድ ለውጥ የለውጥ ባቡር ሆኖ ሁሉንም ያሳፍራል፡፡

ትልቁ ነገር ለውጥን መሸከም የሚችል ጭንቅላት ማዘጋጀት ነው፡፡ በሐገራችን ዛሬ ዛሬ የሚታየው ችግር ለውጥን በአግባቡ መጠቀም አለመቻል ነው፡፡
ለውጡ ይዞት የመጣውን ነፃነት መሸከም የሚችል ጭንቅላት ማበጀት ያሻናል፡፡ የሰዎች አስተዋፅኦ ቢኖረውም በሐገራችን ለውጡ እውን ሆኗል፡፡ ነገር
ግን አንዳንድ ጊዜ ለውጡ ቀደመን የሚያስብሉ ክስተቶችን እናያለን፡፡ ለውጡን ማስተናገድ የሚችል አዕምሮ ሳናዘጋጅ ነው ለውጡ የመጣብን፡፡

https://baissalalaof.wordpress.com/2019/07/12/ታላቁ-የቤት-ስራ፣-የራስን-መንፈስ፣-አዕም/ 1/3
9/6/2021 ታላቁ የቤት ስራ፣ የራስን መንፈስ፣ አዕምሮና ስሜትን መለወጥ – Bayissa Olana Gonfa Law Office

“ለውጡን አመጣነው ሳይሆን መጣብን” የሚል ድምዳሜ ውስጥ አድርሶናል፡፡ ለውጡ ባስገኘልን ትሩፋት መጠቀም ሲገባን ቀድሞ ከነበረው
ምስቅልቅል የባሰ ችግሮች እየተከሰቱ ነው፡፡ አንዳንዶች የለውጥ ባህሪው ነው ይላሉ፡፡ የለውጡን ባህሪ እኛ መወሰን አንችልም ወይ ብለን
ስንጠይቃቸው ለዛ አልደረስንም ይሉናል፡፡

አዎ ለአቅመ ለውጥ ያልደረሰ ለውጥን ተቀብሎ ማስተናገድ አይችልም፡፡ ህጻን ልጅን የአዋቂ ስራ ማሰራት አይቻልም፡፡ ወይፈኑን ለብቻ መጥመድ
ውጤት አያመጣም፡፡ ባይሆን ወይፈኑንም ልምድ ካለው በሬ፤ ህፃኑንም ከአዋቂው ጋር ልምድ እንዲቀስሙና እንዲማሩ ማድረግ ለውጥን የሚቀበል
አዕምሮ ማዘጋጀት ይሆናል፡፡

ታዋቂዋ ተዋንያን፣ ኮሜዲ፣ ፀሐፊና ዘፋኝ የሆነችው አሜሪካዊቷ ካሮል በርኔት፡-

‹‹በሕይወቴ ላይ ለውጥ የማመጣው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ ማንም ይሄን ሊያደርግልኝ አይችልም፡፡›› ትላለች፡፡

አዎ ታላቁ የህንድ መሪ የነበሩት ጋንዲም እንዲህ ብለዋል፡-

‹‹በዓለም ላይ ልታየው የምትፈልገውን ለውጥ ሁን›› ይላሉ፡፡

እውነት ነው! በሀገር ደረጃ የተለወጠውን ለውጥ ለመደገፍ መጀመሪያ በራስ ላይ ለውጥ ማምጣትን ይፈልጋል፡፡ ያልተለወጠ ጭንቅላት ለውጥን
ለመቀበል ፍላጎት አይኖረውም፡፡ ሌሎች ላይ ጣትን ከመቀሰር ራስን ለውጦ የሚፈልጉትን ለውጥ ማምጣት ትልቅ መፍትሄ ነው፡፡

ልክ ነው! ለለውጥ ዝግጁ የሆነ አዕምሮ ለውጥን ተረድቶ ለመቀበል ጊዜ አይወስድበትም፡፡ ይሄ ማለት ግን የመጣውን ለውጥ አሜን ብሎ መቀበል
ያስፈልጋል ማለት አይደለም፡፡ ለውጥን መመርመር ያስፈልጋል፡፡ መርምሮና መዝኖ ለውጥን መቀበል የሚችል አስተዋይነት ያሻል፡፡ አንዳንዶች
ለውጥን ዝም ብላችሁ ተቀበሉ ይላሉ፡፡ የመጣው ለውጥ ላይ ጥያቄ ስትጠይቅ ለውጥ አደናቃፊ ብለው ስም ያወጡልሃል፡፡ አዎ ለውጥ
የተምታታባቸው የለውጥ ደጋፊዎች ብዙ ናቸውና አትፍረድባቸው፡፡

ሆኖም ግን ለውጥ የሚጫንብህ ሳይሆን ተረድተህና ፈልገህ እውን የምታደርገው ነው፡፡ እርግጥ ነው ተፈጥሯዊው ለውጥ ወደድክም ጠላህም
ይጫንብሃል፡፡ በሕይወትህ ላይ የሚመጣው ለውጥ ግን በአንተ የአስተሳሰብ ጥላ ስር የሚወሰን ነው፡፡ ለውጥን አደናቃፊ ሳይሆን መርምሮ አትራፊ
ሁን የዛሬው መልዕክት ነው! ወደፊት የሚያሻግርና የሚለውጥ ለውጥ እንጂ ወደባሰው የሚወስድ ለውጥ እውነተኛ ለውጥ አይባልም፡፡ ታሪክህን
መለወጥ ባትችልም የወደፊትህን ለመለወጥ አቅም አለህ!

Advertisements

https://baissalalaof.wordpress.com/2019/07/12/ታላቁ-የቤት-ስራ፣-የራስን-መንፈስ፣-አዕም/ 2/3
9/6/2021 ታላቁ የቤት ስራ፣ የራስን መንፈስ፣ አዕምሮና ስሜትን መለወጥ – Bayissa Olana Gonfa Law Office

REPORT THIS AD

Published by Bayissa Olana Gonfa

Bayissa Olana Gonfa law office is a private law office based in Addis Ababa, Ethiopia. I, the law office
owner is LLB holder, graduated from AAU law school, in 1999 GC. I'm licensed lawyer by federal
attorney general office and Oromiya justice bureau, to work as legal advisor on Ethiopian laws and as an
attorney in Federal and Oromiya courts. Currently I run my law office. My phone contact address is
+251921407324. View all posts by Bayissa Olana Gonfa

BLOG AT WORDPRESS.COM.

https://baissalalaof.wordpress.com/2019/07/12/ታላቁ-የቤት-ስራ፣-የራስን-መንፈስ፣-አዕም/ 3/3

You might also like