You are on page 1of 2

ጥሩ ውጤት ለማምጣት ምን ላድርግ?

ሰላም ጤና ይስጠልን ውድ የዳዊት ድሪምስ የማህበራዊ መገናኛ ገጽ ተከታታይ ቤተሰቦቻችንን፡፡ ተደራሽነታንን ይበልጥ
ለማስፋትእንዲሁም በግል እና በሀገር ደረጃ ልናሳካቸው ይዘናቸው የተነሳናቸውን ሕልሞቻችንን እውን ለማድረግ
የሒወት ስኬት ሚስጥራትን በተለያዩ መንገዶች እና አውታሮች በሰፊው ይዘን መምጣታችንን ስናበስራቹ ታላቅ ደስታ
ይሰማናል፡፡ ሰላማዊት የሆነች፣ የፍቅር ሀገር፣ የተትረፈረፈች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ በሁሉም
መስኮች ጉዞ ጀምረናል፡፡በዚህ ጉዞ ላይ ያለን አማራጭ ማሸነፍ ወይም ማሸነፍ ነው፡፡(አይዟቹ…ተሳስቼ ሳይሆን
በምክንያት ስለተፃፈ ነው)

በተያያዝነው እሩጫም ላይ በየእለቱ ድንቅ የሆኑ ስኬቶችን እያስመዘገብን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሰላም ነች፣ ኢትዮጵያ ፍቅር
ነች፣ ኢትዮጵያ የተትረፈረፈች ሀገር ነች፡፡ ዛሬ አንድ ዶላር ከአንድ ብር እኩል ነው፡፡

በዛሬው ዕለት ድንቅ የሆነውን አፈጣጠራችንን በድንቅ ውጤት የምናጅብበትን አስተማሪ ጽሑፍ ይዘንላቹ ቀርበናል፡፡
መልካም ቆይታ፡፡

ለብዙዎቻችን ዛሬም ድረስ ያልተመለሱልን፣ አእምሯችን ዘውትር የሚጠይቀን ጥያቄዎች አሉ፡፡ እንዴት አድርጌ ባጠና
ነው ጥሩ ውጤት የማመጣው? እንዴት አድርጌ ባስጠናቸው ነው ልጆቼን፣ወንድም እህቶቼን በትምህርታቸው ጥሩ
ውጤት ማምጣት እንዲችሉ የማደርጋቸው? እና መሰል ጥያቄዎች በብዙዎቻችን ዘንድ ይነሳሉ፤ አሊያም በተደጋጋሚ
ጊዜ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሲጠየቁ እንሰማለን፡፡

ለኛ ለሰው ልጆች ሁሉም ነገር ይቻላል!!! ታዲያ ለሰው ልጆች ሁሉ ከተቻለ እንዴት ከላይ ያስቀመጥናቸው ጥያቄዎችን
ማሳካት ከበደን?

እባክዎትን ከዚህ በታች የሰፈረውን ሃሳብ ከማንበቦ በፊት 1 ደቂቃ ወስደው እራሶትን ቀጥሎ ያለውን ጥያቄ ይጠይቁ፡፡

››››ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዴት አቃተኝ?‹‹‹‹

የምንጠይቃቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ እና ቀጥተኛ ሲሆኑ ትክክለኛ እና ቀጥተኛ መልሶችን እናገኛለን፡፡ ዓለም መስታወት
ነች፡፡ የሰጠናትን ነው የምትመልስልን፡፡ ስትመልስልን ግን በሰጠናት ልክ ሳይሆን አብዝታ ነው የምትሰጠን፡፡ ሕጉ እንግዲህ
እንደዚ ከሆነ ታዲያ፤ ዓለም ምን ስለሰጠናት ነው የማንፈልገውን ዝቅተኛ ውጤት እየሰጠችን ያለችው? ጥሩ ውጤት
ማምጣት እንዴት አቃተኝ?

ቃላትን በአግባቡ እና በጥንቃቄ ከተጠቀምናቸው በራሳቸው መድኃኒት ናቸው፡፡ ትክክልኛ ጥያቄን ለመጠየቅ ትክክለኛ
ቃላትን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ትክክለኛ ጥያቄን ካልጠየቅን ደግሞ ትክክለኛ መልስን ማግኘት አዳጋች ነው፡፡ ስለዚህ
ትክክለኛ መልስን ለማግኘት ትክክለኛ ቃላትን መጠቀም ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ ይህን ሃሳብ በዚህ ላይ እናዳለ እንያዘው
እና ከዚህ ጋር ወደተያያዘው የእለቱ ዋና ሃሳባችን ልውሰዳቹ፡፡

ቃል የሃሳብ መገለጫ ነው፡፡ ቃል ያልሆነን ሃሳብ ማሰብ ከባድ ነው፡፡ እስቲ በቃል የማትገልጡትን ወይም በቃላት
የማይገለጽ ሃሳብን አስቡ?

በቃል የማይገለጽ ሃሳብ ከሌለ እና ቃልም የሃሳብ መገለጫው ከሆነ ዘንዳ፤ ይሄን ሃሳብ ይዘን ወደ ቀደመ አርዕስታችን
እንመለስ፡፡ ›››ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዴት አቃተኝ?‹‹‹ በሉ እንግዲ አብረን ወደ ቃላት ቀዶ ጥገና ክፍል እንግባ፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ትክክለኛ መልስ ለማግኘት ትክክለናውን ጥያቄ መጠየቅ አንዳለብን ተግባብተናል፡፡ ስለዚህ ጥሩ
ውጤት ማምጣት ፈልጌ ዝቅ ያለ ውጤት ካመጣው፤ ጥያቄዬ ላይ ክፍተት አለ ማለት ነው፡፡
አንድ ነገር የሚጨበጥ እንዲሆን መለካት፣ መሰፈር፣ መመዘን አለበት፡፡ ስለሆነም ጥሩ ውጤት ማምጣት እፈልጋለው
ስንልም እንደዛው መለካት፣ መሰፈር፣ መመዘን የሚችል መሆን ይገባዋል፡፡ ለእኛ ጥሩ ውጤት ስንት ነው 70፣80፣100
ማምጣት ነው ወይስ A? B? C?.......ምንድነው?

ጥሩ ውጤትን እንዲህ ተርጉመን ስናስቀምጠው ለምንፈልገው ነገር ግልጽ ያለ መዳረሻ ነጥብ አስቀመጥን ማለት ነው፡፡
ይህ ማለት በሌላ ቛንቛ የምንፈልገው ስኬት ላይ እንዳንደርስ ሳናውቀው ሰበብ ሆኖብን የነበረውን አንደኛው
ማሰሪያችንን ፈታን ማለት ነው፡፡

ታዲያ አሁን ምን ቀረን? ወደ ፊት መጓዝ >>>>>>

ወደ ፊት ለመጓዝ ደግሞ አንድ ልንመልሰው ያነሳነው ጥያቄ መመለስ ይቀረዋል፡፡ >>>”እንዴት”<<<

እንዴት አድርጌ ባጠና ነው ጥሩ ውጤት የማመጣው? እንዴት አድርጌ ባስጠናቸው ነው ልጆቼን፣ወንድም እህቶቼን
በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዲችሉ የማደርጋቸው?

እንዴት የሚለውን ጥያቄ በክፍል ሁለት የምንመለሰው ሲሆን እስከዛው ግን እራሳችንን በነዚህ ጥያቄዎች እንፈትሽ::

እራሴን ጥሩ፣ ብዙ፣ የተሻለ፣ …… እና እንደነዚ በመሰሉ የተቆረጠ መድረሻ ነጠብ በሌላቸው እምነት በጎደላቸው
ፍላጎቶች አስሬ እያኖርኩት ነው? ስንት ሺህ እንደምንሮጥ ሳንወስን “መሮጥ ነው” የምፈልገው ብለን የጀመርናቸው
መድረሻቸው ያልተለካ የሒወት ሩጫዎችን አሉን?

እራሳችንን በነኚህ ጥያቄዎች በመመርመር ያገኘነውን ትምህርት በሃሳብ መስጫ ሳጥኑ ላይ ያጋሩን፡፡

በማህበራዊ መገናኛ ገፆቻችን YouTube, Facebook, Instagram, Tiktik, Telegram, LinkedIn, እና Twitter ላይ
ያግኙን፡፡ መልካም ጊዜ፡፡

#ሰላም

#ፍቅር

#መትረፍረፍ

#ፈገግ_በይ_ሀገሬ

#ዛሬ_አንድ_ዶላር_ከአንድ_ብር_እኩል_ነው

#ሲደክመኝ_እሮጣለው

#ኢትዮጵያ

#ዳዊት_ድሪምስ

#የዳዊት_ድሪምስ_ተከታዮች

You might also like