You are on page 1of 2

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ ቤተሰቦች እንዴት ሰነበታችሁ?

በሃገር ውስጥም በሃገር ውጭም ያላችሁ ዎንድሞች


እህቶች እንዴት አላችሁ? ስራ ኑሮ ጤና ሁሉም ቆንጆ ነው? እኔ እግዚያብሔር ይመስገን ደህና ነኝ፡፡ የሰላም አምላክ ቸሩ
እግዚያብሔር በያላችሁበት ሰላማችሁን ያብዛላችሁ እያልኩ፤ ያው እንደምታቁት ማህበራችን በሂደት በደምብ
እንዲደራጅ ለማድረግ እና ማህበራችን ህጋዊ ቁመና እንዲኖረው ለማድረግ በምንጉዛቸው ሂደቶችም ግባት የሚሆኑንን
የተለያዩ ውሳኔዎች በቅደም ተከተል እየወሰንን እየተጉዝን እንገኛለን፡፡

ከነዚህ ውሳኔዎችም መካከል በመጀመሪያ የቴሌግራም ግሩፑ የአድሚን ግሩፕ እንዲኖረው ማድረግ፣ ማህበሩ ህጋዊ
ከመሆኑ በፊት የሚያስፈልገን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ነበር እና እሱን ገንዘብ ለመሰብሰብ የባንክ አካውንት እንዲከፈት
ማድረግ እና ዐካውንቱን የሚከፍቱልን ዎንድሞቻችንን መሰየም፣ እንዲሁም የማህበሩ አባላት ወርሃዊ መዋጮ ምን
ያክል ይሁን የሚሉትን እና የማህበሩን መተዳደሪያ ህግ እና ደንብ፣ ራዕይ እና ተልዕኮዎችን ሚያዘጋጁልን ዎንድሞቻችንን
ከመሰየም አንፃር ውሳኔዎችን ወስነን አልፈናል፡፡

ዛሬ ደግሞ እናንተ ውድ ቤተሰቦች እንደምታቁት ላለፉት ሁለት ሳምንታት ልንመሰርተው ያሰብነው ማህበር ስሙን ማን
እንበለው በሚል እያንዳንዱ የግሩፑ አባል የግል ሃሳብ እና አስተያየት እንዲያስቀምጥ ባስተላለፍነው መልክት መሰረት እና
ምንም እንኩአ እናንተ ቤተሰቦች በሚፈለገው ልክ ያልተሳተፋችሁበት ቢሆንም የግድ ይሄን አጀንዳ ጨርሰን ዎድ
ሌላኛው ወሳኝ ምዕራፍ ማለፍ ያለብን ስለሆነ በቀናህነት ሃሳብ እና አስተያት የሰጡንን ዎንድሞቻችን እና እህቶቻችንን
ሃሳበ መሰረት አድርገን ወስነን ይሄን አጀንዳ እንዘጋለን፡፡

በዚህም መሰረት አንደኛ የማህበሩ አባላት የሰጡትን አስተያት ብዛት በአንጻራዊነት ተመልክተን፣ ሁለተኛ ማህበራችን
ሊኖረው ከሚችለው አላማ አንጻር አይተን፣ ሶስተኛ ማህበራችን ታርጌት አድርጎ ከተነሳበት አካባቢ እና ለዎደፊት
ሊተገብራቸው ከሚያስባቸው የልማት እና የበጎ አድራጎት ተግባራት አንጻር አይተን የማህበሩን ስም ሰይመናል፡፡ በዚህ
መልክ እናንተ የግሩፑ ቤተሰቦችም እንደታዘባችሁት በአባላት ከተጠቀሱት ስሞች መካከል አባላት ደጋግመው የጠቀሱት
በመሆኑ እና ከማህበሩ አላማ እና ተግባር ጋር አብሮ ይሄዳል ብለን ስላመንን ‘ ’የጉግ እንሱኝ በጎ አድራጎት እና ልማት
ማህበር’’ ተብሎ እንዲሰየም ወስነናል፡፡

ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የማህበራችንን (የጉግ እንሱኝ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበርን) እጣፈንታ ወደ ዎሳኝ ምዕራፍ
የሚያሻግርልንን ውሳኔ ለመዎሰን እንዲያስችለን ታላቅ አጀንዳ ወደ እናንተ ወደ ግሩፑ ቤተሰቦች አቀርባለሁ፡፡ በዚህም
ልክ ማሀበራችን የሚያስፈልገውን ሁሉ ለማሙአላት እና ለወደፊት መስራት ያለበትን ስራ መስራት እንዲችል በቅርበት
የሚከታተሉት ወሳኝ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን ማዋቀር ለነገ የማይባል ተግባራችን ነው፡፡ በመሆኑም ከቦታ አንጻር፣
ከሚሰሩት እና ከተሰማሩበት የስራ መስክ አንጻር ማህበሩን ለማገዝ ጊዜ አላቸው ዎይስ የላቸውም የሚለውን ከግምት
ውስጥ በማስገባት፣ እንዲሁም ግለሰቦች ካላቸው ስቭዕና እና የማስተባበር እና የመምራት ችሎታ አንጻር
ያመናችሁባቸውን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች መምረጥ እንድትችሉ ማሳሰብ እፈሊጋለሁ፡፡

ማሳሰቢያ፡- በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴነት ምትመርጡቸው ሰዎች ብዛታቸው ከ 7-9 መሆን አለባቸው ምክንያቱም፡-
ሰብሳቢ፣ ም/ሰብሳቢ፣ ጽሃፊ፣ ገንዘብ ያዥ፣ የሒሳብ ሹም፣ እንዲሁም ኦዲተር እና በአባልነት ሶስት ሰዎችን ምንጨምር
ዪሆናል፡፡

ውድ ቤተሰቦች የ ኢትዮጲያ ሲቪክ ሶሳይቲ (Ethiopian Civic Society) ህግም ስለማይፈቅድ የምትመርጡአችው
ኮሚቴዎች ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አመራርነት እና አባልነት ነጻ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡ ዕባካችሁ ውድ ቤተሰቦች
በተቻላችሁ መጠን በቀናህነት ሃሳብ እና አስተያታችሁን አጋሩን በሃሳብ እና በሁሉመ ነገር ካልተጋገዝን ብዙ መጉአዝ
አንችልም ስለዚህ የሁላችሁም የማህበሩ አባላት ሃሳብ አስተያየታችሁ ያስፈልገናል፡፡ ምንም የሚያቆመን ንግር የለም፤
ግን ከተባበርን ነው!!!!!!!!!

ሰላም ለናንተ ይሁን መልካሙን ሁሉ ተመኘሁላችሁ!!!

You might also like