You are on page 1of 21

ቀን 05/06/2016 ዓ/ም

ለክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ


ጋምቤላ
ጉዳዩ ፡- ስለወሳኝ ቦርድ አባላት የጥቅማ ጥቅም ክፍያን ይመለከታል
1. መግቢያ
የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ አባላት በሥራ ላይ ያለው የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011
እና ፍትሐብሔር የሥነ - ሥርዓት ህግ ግብ በፍ/ቤት የሚካሄዱ ክርክሮች ቀልጣፋ ፣ወጪ ቆጣቢና
ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንዲቋጩ ማስቻል ነው፡፡ የዚህም ግብ ዓላማ መሳካት በተለይ በሥራ ክርክሮች
ላይ የተለየ እንደምታ አለው፡፡ የሥራ ውል መቋረጥ በሠራተኛውና በቤተሰቡ ዕለታዊ ኑሮ ላይ
ከሚያሳድረው ከባድ ጫና አንፃር አሠሪው ላይ የሚያቀርባቸው የመብት ጥያቄዎች ሳይውሉ ሳያድሩ
በፍጥነት መቋጨት ይኖርባቸዋል ፡፡ይህን እውን ለማድረግ የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ አባላት ይህን አዋጅ
በሥራ ለመተግባር ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል ፡፡
ለአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ የሚቀርብ እንዲሁም በሠራተኛው ወይም ማህበራት የሚቀርብ
የሥራ ክርክር ከዳኝነት ክፍያ ነፃ በመሆኑ ፣ቦርዱም የቀረበለትን ጉዳይ በ 30 ቀናት ውሳኔ መስጠት
እንዳለበት ፣ እንዲሁም ቦርዱ በልዩ የስነ ሥርዓት ደንቦች እንዲገዛ መደረጉ እና ቦርዱ ራሱን ሥነ
ሥርዓት ደንቦች እንዲያወጣ ሥልጣን መስጠቱን ይደነግጋል ፡፡
ስለዚህ የአሠሪኛ ሠራተኛ ህጉን ዓላማ ውጤት በሚሰጥ መልኩ የመተርጎም አስፈላግነት ለማሳየት
በቦርዱ ላይ ተጣለ ኃላፊነት ነው ፡፡
በአሠሪና ሠራተኛ የህግ ማዕቀፍ ለአሠሪዎችም ሆነ ለሰራተኞች የመደራጀት መብት የተካተተ
በመሆኑ መነሻነት እነዚህ የሥራ ክርክሮች የተሰጠውም ኃላፊነት የወል የሥራ ክርክሮችን
የሚታይበት ሂደት ነው ፡፡

ቦርዱ በፍሬ ነገር ደረጃ የሚሰጣቸ ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን በህግ አተረጓጎም ስህተት ተፈፅሞ ሲገኝ
ቅር የተሰኘው ወገን ለከፍተኛ ፍ/ቤት የሥራ ክርክር ቦርዱ ውሳኔ ለተከራካሪ ወገኖች ከተሰጠ ጊዜ
ጀምሮ 30 ቀናት ጊዜ ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ የሚችሉበት ሂደት ነው ፡፡

2. የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ አባላትም የሥራ ኃላፊነት እና ተግባራት በተመለከተ


በሀገራችን የሠራተኛን ጉዳይ የሚገዙ ሁለት የህግ ማዕቀፎች ያሉ መሆኑና እነርሱም የመንግሥት
ሠራኞች እና የአሠርና ሠራኛየህግ ማዕቀፎች እንደሆኑ ይታወቃል ፡፡

በሥራ ላይ ያለው የአሠርና ሠራኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 በአንቀጽ 4 የአሠርና ሠራተኛ
ግንኙነት ስለሚመሠረትበት ውል የሚደነግግ ድንጋጌ ነው ፡፡ በአሥርነ ሠራተኛ የህግ ማዕቀፍ
ከመንግሥት ሠራተኛ የህግ ማዕቀፍ በብዙ መልኩ የተለየ ነው ፡፡ ይህውም ከመንግሥት ሠራተኛ አዋጅ
በተቃራኒ በአሠርና ሠራተኛ አዋጅ በአሠር ድርጅት ውስጥ ቅረታ ማስተናገጃ የሚባል በአሠራር
የሌለ ሲሆን በአንፃሩ አለመግባባቶቹ የሚገለፁት የሥራ ክርክር በሚል ነው ፡፡

የሥራ ክርክሮች ሁለት ይዘት ያሏቸው ሲሆኑ 1 ኛ/ የግለሰብ ሠራተኛ የሥራ ክርክር እና 2 ኛ/ የወል
የሥራ ክርክሮች ሲሆኑ አነዚህ የሥራ ክርክሮች የሚታዩበት ሂደትም የተለያዩ ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
ከእነዚህ የሥራ ክርክሮች መሃል የአሠርና ሠራተኛ ጉዳይ ቦርድ የሚመለከታቸው ጉዳዮች የወል የሥራ
ክርክሮች ሲሆኑ በባህሪያቸው የግለሰብ ሠራተኛን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የጠቅላላውን ፣ የአብዛኛውን
ወይም በርከት ያሉ ሠራተኞችን ጥቅም የሚነኩ ናቸው ፡፡እነዚህም የወል የሥራ ክርክሮች በሥራ
ደንብ ወይም በህብረት ስምምነት ያልተነሱ የደመወዝና ሌሎች ጥቅሞች አወሳሰን ፣አዲስ የሥራ
ሁኔታዎችን ስለመመሥረት ፣ የህብረት ስምምነት ስለመፈራረም፣ ስለማሻሻል ፣ፀንቶ ስለሚቆይበት
ጊዜና ስለሚፈርስበት ሁኔታ ፣በአዋጁ፣የህብረት ስምምነት ወይም የሥራ ደንብ ድንጋጌዎች
በሚመለከት ስለሚነሳ የትርጉም ክርክር ፣ ስለሠራተና አቀጣጠርና ደረጃ ዕድገት አሰጣጥ ሥርዓት
አጠቃላይ የሠራተኞችን እና የድርጅቱን ህልውና የሚነኩ ዳዮች ፣ዕድገት ዝውውርና ሥልጠና
አስመልክቶ አሠሪው በሚያወጣቸው የአፈፃፀም ሥርዓቶች ላይ የሚቀርቡ ክሶች፣ ስለሠራተኞ ቅነሳ
ሥርዓት እና ሌሎች መሰል የወል የሥራ ክርክር ጉዳዮች የመዳኘት ሥልጣን ያለው ሲሆን በአማራጭ
የግጭት መፍቻ ዘዴዎች በአዋጅ 1156/211 አንቀጽ 143(1) መሠረት የሚቀርቡ ጉዳዮችን ተቀብሎ
የማስተናገድ ሥልጣን በህግ ተሰጥቶት በማከናወን ላይ ይገኛል ፡፡

2. የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ በሚሰጠው አገልገሎት ተጠቃሚዎች የሆኑ አካላት

የአሠርና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የወል የሥራ ክርክሮችን የሚያዩ በአዋጅ ቁጥር 1156/2011
አንቀጽ 145 መሰረት የአየር መንገድ አገልግሎት፣የኤሌክትሪክ መብራት አገልግሎት የሚሰጡ
ድርጅቶች ፣የውሃ አገልግሎት የሚሰጡ እና የከተማ ጽዳት የሚጠብቁ ድርጅቶች ፣ የከተማ ቀላል
የትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣ የመድሃኒት ማከፋፈያ ድርጅቶች እና የመድሃት
መሸጫ ቤቶች ፣ እሳት አዳጋ አገልግሎት ፣እና የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ያሉ ድርጅቶች በአዋጅ
አንቀጽ 137(2) ለህዝብ የማያቋርጥ አገልግሎት የሚሰጡ እጅግ አስፈላጊ የህዝብ አገልግሎት
ድርጅቶች ውስጥ የሚነሱ የወል የሥራ ክርክሮችን የሚያይ አካል ነው ፡፡

ቦርዱ ለእነዚህ አካላት በአዋጁ ዙሪያ የህግ ግንዛቤ ማጣት ምክንያት ሚፈጠሩ የአሠራር ክፍተቶችን
በመለየት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እንዲያገኘ ያደርጋል፡፡

3. በአዋጅ 1156/211 አንቀጽ 145 መሠረት የተቋቋሙት የአሠርና ሠራተኛ የቦርድ አባላት ብዛት
በተመለከተ

የአሠሪና ሠራተኛ ቦርድ አባላት ብዛት 7 ሲሆን አመራረጣቸውም ስለ አሠርና ሠራተኛ ጉዳይ ብቃትና
ልምድ ያላቸው ሁለት ባለሙያዎች ፣ ከአሠሪ ማህበራት ሁለት፣ ከሠራተኞች ማህበራት ሁለት ፣
ከአሠሪዎች ና ከሠራተኞች ማህበራት የሚመከሉ አንድ አንድ ተተኪ አባላት የሚኖራቸው ሲሆን
በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 145(2) መሠረት አሁን ሥራ ላይ የሚገኙ የቦርድ አባላቶች ፡-

1. ከክልል ፍትህ ቢሮ አንድ የህግ ባለሙያ


2. ከአሰሪ ማህበር ሁለት ተወካይ
3. ከሰራተኞች ማህበር ሁለት ተወካይ
4. ከሥራና ክህሎት ሁለት ተወካዮች የተቋቋሙ ናቸው ፡፡

የቦርዱ አባላት በሣምንት ሁለት ጊዜ የስራ ቀናት ያላቸው ሲሆኑ በታማኝነት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ
በመወጣት ላይ ይገኛል ፡፡

4. ለእነዚህ የቦርድ አባላት የተጠየቀው የውሎ አበልና የትራንስፖርት ክፍያ ማሻሻያ ጥያቄ
አስፈላጊነቱ በተመለከተ
4.1 የቦርዱ አባላት ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ አስፈላጊ የሆኑ ሠነዶችን ከማናቸውም ጉዳዩ
ከሚመለከታቸው ጉዳዩ ከሚመለከተው ሰው ወይም ድርጅት በአካል ቀርቦ የመጠየቅ፣
4.2 ተከራካሪ ወገኖችና ምስክሮች እንዲቀርቡ ወይም የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ
ማድረግ ፣አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን የመሰብሰብና ምሥክሮችን የመስማት ፣ሠነዶች
እንዲቀርቡ የማድረግ፣
4.3 የአሠራር ክፍተቶች በሚታዩባቸው ተቋማት በአካል በመገኘት በአዋጁ መሠረት
የማስተካከያ ሥራዎችን ማከናወን፤
4.4 ከአሠሪ ተቋማት ለቦርዱ የሚቀርቡ ቅረታዎችን መርምሮ ህጋዊ የመፍትኤ
አቅጣጫዎችን በመስጠት አፈፃፀማቸውንም የመከታተል ሥራዎችን ያከናውናል ፡፡
ለዚሁም ሥራ እየተከፈለው ያለው የውሎ አበል እና የትራንስፖርት ክፍያ ጥቅማጥቅም በተመለከተ
ከሌሎች ክልሎች አከፋፈል በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ተረጋግጦ መ/ቤቱ በ 2015 ዓ/ም በበጀት ተደግፎ
ማስተካያ ተደርጎ ከፍያው እንዲፈፀም ቢታዘዝም ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል ፡፡

ስለሆነም የቦርዱ አባላት ያላቸውን ክህሎት እና ሙያቸውን አሟጥተው በትጋት የተሰጣቸውን


ሥራ በህግ አግባብ በማከናወን ላይ ስለሚገኙ እነዚህን ሥራዎች ለመሥራት እና በሚንቀሳቀሱበት
ጊዜም ሆነ ወደ ችሎቱ የሚመጡበት ጊዜ የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈንላቸው በዚሁ ተቋም
በመሆኑ የሥራው አድካሚነት ከግንዛቤ በማስገባት ቀደም ሲል ሲከፈላቸው የነበረው ብር
400 /አራት ሺህ ብር / ማሻሻያ ተደርጎላቸው የሥራ ሞራላቸው በማይነካ መልኩ ለሰብሳቢ 1000
ብር ለፀሐፊ 800 ብር እና ለቀሩትም አባላት 800 ብር እንዲከፈላቸው ይህንን መግለጫ
ለማቅረብ ተችሏል ፡፡

በዚሁ መሠረት የቦርዱ አባላት በአዋጅ ቁጥር 1156/2011 ለተቋሙ የተሰጠዉ ሥልጣንና ኃላፊነት
በአግባቡ እየተወጣ ሥራውንም በህግ አግባብ እያከናወነ ሲሆን ለነዚህ ቦርድ አባላት የሚከፈል
ክፍያ ወቅቱን ያላገናዘበና በጣም አነስተኛ ክፍያ መሆኑ ታውቆ በሂሳብ መደብ ቁጥር 6116
የተያዘና በየወሩ የሚከፈል የአመት በጀት እንደመሆኑ ማናጅመንቱ ይህን ተገንዝቦ
እንዲያፀድቅልን ስንል የቦርድ አባላት ስም ዝርዝር ፣ የሥራ ኃላፊነት ፣በየወሩ ሊከፈላቸው
የሚገባ የገንዘብ መጠን እና የዓመቱን ወጪ ያዘ 1 ገጽ ከዚህ መግለጫ ጋር አያይዘን አቅርበናል
፡፡
ቀን ---------------------------
ለክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ
ጋምቤላ
ጉዳዩ ፡- አላቂ የፅህፈት መሣሪያ ይመለከታል
ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የጋምቤላ አሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ አገልግሎት የሚውል የፅህፈት

መሣሪያዎች በዚህ በ 2016 ዓ/ም ተገዝቶ የተሰጠን ባለመሆኑ በሥራችን ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከተለ ስለሆነ

-

1. ለአገልግሎቱ የሚውል አጀንዳ ብዛት -------- 7


2. /
ጥቁር እስክሪብቶ ጭቃ ቀለም / በቁጥር -------- 10
3. ክላሰር ብዛት ------- 50
4. የኮምፒውተር ወረቀት ብዛት -------- 2
5. ባለገመድ አቃፍ ብዛት ----------- 5
6. መካከለኛ መዝገብ ብዛት --------- 2
7. የኮምፒውተር ቀለም ብዛት ---------- 1
ተገዝቶ እንዲሰጠን በአክበሮት እንጠይቃለን ፡፡
የአሠሪና ሠራተኛ ወሳኝ ቦርድ አባላት ስም ዝርዝር፣ አሁን የሚከፈላቸው የገንዘብ መጠን እና አዲስ የተጠየቀላቸው ገንዘብ መጠን

ተ.ቁ የሥራ ኃላፊነት አሁኑ የሚከፈላቸው አዲሱ ክፍያ በየወሩ የሚከፈል የዓመት ክፍያ መጠን ምርመራ
ክፍያ
ብር ሣንቲም ብር ሣንቲም ብር ሣንቲም ብር ሣንቲም
1 ሰብሳቢ 400 00 1000 00 1000 00 12,000 00
2 ም/ሰብሳቢ 400 00 1000 00 1000 00 12,000 00
3 ፀሐፊ 400 00 800 00 800 00 9,600 00
4 አባል 400 00 800 00 800 00 9,600 00
5 አባል 400 00 800 00 800 00 9,600 00
6 አባል 400 00 800 00 800 00 9,600 00
7 አባል 400 00 800 00 800 00 9,600 00
ድምር 2,800 00 6,000 00 6,000 00 72,000 00
የጋምቤላ ባሮ ማዶ አጥቢያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የየካቲት ወር 2016 ዓ/ም ወራዊ የአገልግሎት ፕሮግራም

ተ/ቁ የአገልግሎት የአገልግሎት ፕሮግራም መሪ ስም የቃል አገልጋይ የዝማሬ አገልግሎት ምርመራ


ቀን ዕለት ስም
1 01/07/2016 እሁድ ወ/ም ወንድሙ ለማ ወ/ዊ ታከለ ሰንበቶ የህፃናት መዘምራን
2 03/07/2016 ማክሰኞ ወ/ም ወንድሙ ወዕሜቦ ወ/ም ናትናኤል አባይነህ
3 08/07/2016 እሁድ ፓ/ር ቶማስ መ/ር ምትኩ ሃሌሎ “ ሀ ” መዘምራን
4 10/07/2016 ማክሰኞ ወ/ዊ ታከለ ሰንበቶ እህት ሰናይት ማሞ
5 15/07/2016 እሁድ ወ/ዊ ጌታሁን ጤልታ እህት ድንቅነሽ ደነቀ “ ለ ” መዘምራን
6 17/07/2016 ማክሰኞ ወ/ም ግዛቸው ጆርጋ ወ/ም ሚልኪያስ ጌተሁን
7 22/07/2016 እሁድ ወ/ም ታምራት ሾንኮሩ እህት ብርሃኔ አበራ “ ሐ ” መዘምራን
8 24/07/2016 ማክሰኞ ወ/ም እሸቱ ተስፋዬ ወ/ም ወንድሙ ለማ
9 29/07/2016 እሁድ ወ/ም ጎሳዬ አሰፋ ወ/ም ወንድሙ ወዕሜቦ “ ሀ “ መዘምራን
ቀን ---------------------------

የጋምቤላ ባሮ ማዶ አጥቢያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የጉብኝት ቅጽ

የተጎበኘው ቤተሰብ /አባወራ/ እማወራ/ ሙሉ ስም ----------------------------------------------------

አድራሻ ----------------------------------------------------- ልዩ ስም ----------------------------------------

1. በቤትዎ እና በቤተክርስቲያን ያሎዎት መንፈሣዊ ትጋት ምን ይመስላል ?


-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
2. መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አስመልከቶ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያሎዎት አስተያየት
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
--------------------------------------------
3. የፀሎት ርዕሶች ካለ በዝርዝር ይግለፁ
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
4. የጉብኝት አባላት አስተያየት
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ቀን --------------------

የጋምቤላ ባሮ ማዶ አጥቢያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የጉብኝት ቅጽ

የተጎበኘው ቤተሰብ /አባወራ/ እማወራ/ ሙሉ ስም


----------------------------------------------------------------------

አድራሻ ----------------------------------------------------- ልዩ ስም
----------------------------------------------------

1. በቤትዎ እና በቤተክርስቲያን ያሎዎት መንፈሣዊ ትጋት ምን ይመስላል?


-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
2. መንፈሳዊ እንቅስቃሴ አስመልከቶ በቤተክርስቲያን ዙሪያ ያሎዎት አስተያየት?
----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
3. የፀሎት ርዕሶች ካለ በዝርዝር ይግለፁ?
----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
4. የጉብኝት አባላት አስተያየት?

-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

ምእራፍ አራት የስነ ስርአት እርምጃ ***

4.1 የአባልነት ክፍያ ካልከፈለ በሶስተኛዉ ወር የጽሁፍ ማስጠንቀቅያ ይሰጠዋል::

4.2 የአባልነት ክፍያ ሳይፈጽም 3 ወር የዘገየ አባል በራሱ ወይም በቤተሰቡ ላይ የሞት አደጋ ከደረሰ የሚሰጠው እርዳታ ምእራፍ 3
የተጠቀሰው የእርዳታ መጠን ግማሽ ብቻ ይሆናል::

4.3 ያለበቂ ምክንያት (ለምሳሌ - በህመም ወይም ከስራ መፍናቀል በማህበሩ ቦርድ ተረጋግጦ ) የአባልነት ክፍያ ሳይፈጽም ወይም በጠቅላላ
ጉባዔ የተወሰነዉን መዋጮ ሳይፈጽም 4 ወር ያለፈ እንደሆነ ከማህበሩ በራሱ ፈቃድ እንደተሰናበተ ይቆጠራል::

4.4 አንድ አባል የቤተሰብ ማስመዝገብያ ቅጽ በትክክል ካልሞላ ወይም የተሳሳተ መረጃ ከሰጠ እርዳታ ሊያገኝ አይችልም:: የስራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ ይህንን ባደረገ አባል ላይ ከአባልነት እስከማገድ የሚደርስ ተገቢ እርምጃ ይወስዳል ::

4.5 የማህበሩን መልካም ስም የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸመ ወይም በአባላት መካከል ሊኖር የሚገባውን መልካም ግንኙነት የሚያበላሽ ተግባር
በፈጸመ አባል ላይ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ማስጠንቀቅያ ይሰጣል::

4.6 ከላይ በ 4.5 በተሰጠው ማስጠንቀቅያ ያልተሻሻለ እንደሆነ የስራ አስፈጻሚ አባሉ የፈጸመውን ጉድለት በጽሁፍ አቅርቦ በቦርድ እንዲታይ
ያደርጋል:: ቦርዱ ጉዳዩን ተመልክቶ ከአባልነት እስከማገድ የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል::

4.7 ከአባልነት የታገደ አባል ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት በጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊያቀርብ ይችላል:: 4.8 በማንኛውም ሁኔታ ከማህበሩ
የተሰናበተ ወይም የተወገደ አባል ከዚህ ቀደም አባል ሆኖ የከፈላቸው ክፍያዎችን በተመላሽነት አያገኝም:: 4.9 በአንቀጽ 2.3.1 መሰረት
በዓመት አንድ ጊዜ በሚደረገዉ ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ መገኘት ግዴታ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያልተገኘ አባል $25 ሲቀጣ ለሁለተኛ
ከደገመ ከማስጠንቀቂያ ጋር $50 ይቀጣል:: ለሶስተኛ ጊዜ ሳያሳዉቅ ከቀረ ከማህበሩ በገዛ ፈቃዱ እነደተሰናበተ ተቆጥሮ ከአባልነት ይሰረዛል::
ምእራፍ አምስት የማህበሩ አመራር አካላት ማህበሩ: 5.1 ጠቅላላ ጉባዔ 5.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ 5.3 የስራ አስፈጻሚና 5.4 ኦዲተር
ይኖረዋል:: 5.1 ጠቅላላ ጉባዔ 5.1.1 ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ አባላት የሚገኙበት ጠቅላላ ስብሰባና የማህበሩ ከፍተኛ የስልጣን አካል ነው::
5.1.2 ጠቅላላ ጉባዔ በአመት አንድ ግዜ ይጠራል:: 5.1.3 ከግማሽ አባላት በላይ የተገኙበት ጠቅላላ ስብሰባ ምልአተ ጉባዔ ይሆናል:: 5.1.4
ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ምልአተ ጉባዔ ካልሞላ ተከታይ ሁለተኛ ስብሰባ ጠርቶ የተገኙት አባላት ከግማሽ በታች ቢሆኑም ስብሰባው ምልአተ
ጉባዔእንደተሟላ ተቆጥሮ ስብሰባዉ ይካሄዳል ዉሳኔም ይተላለፋል ። 5.1.5 ከላይ በቁጥር 5.1.3 እና በ 5.1.4 በተጠቀሰው መሰረት
ምልአተ ጉባዔው ከታች በአንቀጽ 5.1.6 የተጠቀሰውን ሳይጨምር ሌላ ማንኛውንም ውሳኔ ማስተላለፍ ይችላል:: 5.1.6 ማህበሩን ለማፍረስ
የጠቅላላ ጉባዔ 2/3 ኛ ድምጽ ያስፈልጋል:: 5.1.7 ማህበሩ የፈረሰ እንደሆነ የማህበሩ ገንዘብና ሌሎች ንብረቶች ቦርዱ ለሚወሰነው የበጎ
አድራጊ ድርጅት ይሰጣል:: 5.1.8 ማህበሩ ሲፈርስ ስለመፍረሱ ለተገቢዉ የመንግስት አካል ቦርዱ ያስታዉቃል። 5.1.1 የጠቅላላ ጉባዔ
ተግባርና ስልጣን 5.1.1 የዳይሬክተሮች ቦርድ ይመርጣል:: 5.1.2 የማህበሩን መተዳደርያ ደንብ ያጸድቃል ያሻሽላል:: 5.1.3 የማህበሩን ስራ
ማካሄጃ በጀት ይፈቅዳል:: 5.1.4 ኦዲተር ይመርጣል:: 5.1.5 የማህበሩን ገቢ ሰብሳቢ ወጪ አደራረግና ሌሎች የማህበሩን ገንዘብ
አጠቃቀምና እንቅስቃሴ በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል:: 5.1.6 የቦርዱን ረፖርት ያዳምጣል:: ይመረምራል:: እንዳስፈላጊነቱም
መመርያዎችን ይሰጣል:: 5.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ የማህበሩን ስራ በቅርብ እንዲቆጣጠር በጠቅላላው ጉባዔ የሚሰየም አካል ነው:: 5.2.1
የዳይሬክተሮች ቦርድ ይዘት 5.2.1 የቦርድ አባላት ቁጥር አስራ አንድ ይሆናል:: 5.2.2 የቦርዱ አባላት የስራ ዘመን አራት ዓመት ይሆናል::
5.2.3 ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል:: 5.2.4 አንድ የቦርድ አባል በጠቅላላዉ የአባላት ጉባዔ ከተመረጠና
ፈቃደኛ ክሆነ በተከታታይ ሊያገለግል ይችላል:: 5.2.5 በማናቸውም የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜ የስራ ዘመናቸውን የጨረሱ የቦርድ አባላት
ለምርጫ ሊቀርቡ ይችላሉ:: 5.2.6 አንድ የማህበሩ የቦርድ አባል የስራ ዘመኑን ሳይጨርስ አገልግሎቱን በማናቸውም ምክንያት ቢቋረጥ
ለቀሪው የስራ ዘመን ተክቶ የሚያገለግል የቦርድ አባል በቦርዱ ውሳኔ ይሰየማል:: 5.2.7 በማናቸውም የቦርድ አባላት ምርጫ ጊዜ የቦርዱ
የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆነ አባል ተመልሶ ለቦርድ አባልነት ቢመረጥ ቀድሞ ይዞት የነበረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስፍራ ለቀሪዎቹ የቦርድ
አባላት በውድድር ይሰጣል:: n 5.2.2 የዳይሬክተሮች ቦርድ ተግባርና ስልጣን 5.2.2.1 ከቦርዱ አባላት መካከል አምስት የስራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል:(እነርሱም የማህበሩ ሊቀመንበር ፤ም/ሊቀመንበር፤ ጸሃፊ፤ ገንዘብ ያዥና ሂሳብ ሹም ይሆናሉ) 5.2.2.2 የስራ
አስፈጻሚ ኮሚቴው የማህበሩን ስራ ለማካሄድ የሚያወጣቸው የአፈጻጸም ስልቶችን ይመረምራል::

ከማህበሩ የሚያስወግዱ ምክንያቶች

1. ማህበሩን የሚጎዳ ድርጊቶችን መፈጸም እንዲሁም ማንኛውንም ከማህበሩ አላማና ተግባር ውጭ የሆኑ የግል ወይም የሌላ ድርጅት
አላማዎችን ማንጸባረቅ

2. በአንቀጽ 4 የተጠቀሱትን የአባልነት ግዴታዎች አለሟሟላት።

3. በማህበሩ የተደነገጉ መተዳደሪያ ደንቦችን መጣስ።

ከማህበሩ ስለተወገደ አባል

1. አንድ የማህበሩ አባል በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ውሳኔ በበቂ መረጃ ተረጋግጦ ከማህበሩ ከተወገደ ወደ ማህበሩ መመለስ ፈጽሞ
አይችልም።

1 ኛ= የቀላል ዲሲኘሊን የቅጣት አይነቶች:-


፩= የቃል ማስጠንቀቂያ
፪=የጽሑፍ ማስጠንቀቂያና
፫=እስከ 15 ቀን የሚደርስ የደመወዝ ቅጣት ናቸው፡፡
2 ኛ= የከባድ ዲሲኘሊን የቅጣት አይነቶች:-
፩=እስከ ሶስት ወር የሚደርስ የደመወዝ መቀጫ
፪= እስከ 2 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ከስራ ደረጃና ደመወዝ ዝቅ ማድረግና
፫=ከስራ ማሰናበት ናቸው፡፡
3 ኛ=የመርሱ የቅጣት ውሰኔ ሪከርድ ሊቆይ የሚችለው :-
፩=ቀላል ዲሲኘሊን ቅጣት ከሆነ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ለ 1 ዓመት ሲሆን
፪=ለከባድ ደሲኘሊን ቅጣት 2 ዓመት በመሆኑ የሁለቱም ውሳኔዎች እግዱ እስከ ሚነሳ ደረጃ ዕድገት ቢከለክልም የት/ት ማሻሻል ግን
አያግድም::
4 ኛ=የመ/ራን የከባድ ዲሲኘሊን ቅጣት የሚያበቁ ነጥቦች:-
፩=በተሙማ አለማሳተፍ ፪=ተማሪዎች ሳያቋርጡና ክፍል ሳይደግሙ እንዲጨርሱ ስልት ቀይሶ አለመንቀሰቀስ
፫=የተማሪዎች ፈተና በተቀመጠው ጊዜ ገደብ አርሞ ውጤት አለማሳወቅ
፬=እገዛ ተደርጎ የመ/ሩ የብቃት ማነስ
፭=ዕለታዊ፣ ሳምንታዊና ዓመታዊ የት/ት ዕቅድ በተቀመጠው ጊዜ ገደብ እየሰሩ አለማቅረብና ክፍል ውስጥ አለመጠቀም
፮=ግቢ ውስጥ እያሉ ክፍለ ጊዜ መሸራረፍ (ሠዓት ሳይደርስ ከክፍል ቀድሞ መውጣትና ዘግይቶ ክፍል መግባት)
፯=የመማር ማስተማር ስራ በአግባቡ እንዳይካሄድ ሆን ብሎ ማወክ (መተባበር)
፰=ለተማሪውች ያለአግባብ ውጤት መጨመር ፣በፈተና ሠዓት እንዲኮርጁ ማድረግ፣ የፈተና ሚስጢራዊነትን አለመጠበቅና
፱=ሌሎች ከዚህ በፊት የነበሩና ተመሳሳይ ክብደት ያላቸው፡፡
5 ኛ= የት/ቤት አመራሮችን ለከባድ ዲሲኘሊን የሚደረጉ ጥፋቶች:-
፩=ተሙማ አለመስራትና አለማስተባበር
፪=ያለ በቂ ምክንያት ከስራ መቅረትና የስራ ሠዓት አለማክበር
፫=ደረጀ 1 እና ደረጃ 2 የሆኑ ት/ቤቶችን በኢንስፔክሽን ግምገማ ደረጃ አለማሳደግ
፬=ምርጥ ተሞክሮን ለሌሎች ቀምሮ አለማስፋት
፭=የወላጅ ምክክር ያለ ማድረግ
፮=በስራ ቦታ ፆታዊ ትንኮሳ መፈፀም
፯=በክፍል ምልከታ መ/ራንን አለመደገፍ
፰=የት/ቤት ሀብትና ንብረት በአግባቡ አለመጠቀም
፱=የት/ት ሠዓት ብክነት አለመቀነስ
፲=የተማሪ ምዝገባ እቅድ አለማሳካትና ተማሪዎች ሳያቋርጡ ከክፍል ክፍል አለማሸጋገር
፲፩=ጥራት ያለው መረጃ ለሚመለከተው አካል አለማድረስና ፲፪=ሌሎች ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለቸውና ከዚህ በፊት የነበሩ ናቸው፡፡
6 ኛ=የት/ቤት የዲሲኘሊን ኮሚቴ:-
፩=የት/ቤት ም/ር/መ/ር (ከሌለ ወመህ) ሰብሳቢ
፩=ሁለት ወመህ አባል
፫=ሁለት መ/ራን ማህበር አንዷ ሴት አባል
፬=አንድ የወመህ አባል መ/ር አባልና ፀሐፊ ናቸው፡፡
፭=በት/ቤት ደረጃ የሚታየው የመ/ራን ዲሲኘሊን ብቻ ነው፡፡
7 ኛ= በወረዳ ደረጃ የዲሲኘሊን ኮሚቴ:-
፩=ም/ትም/ጽ/ቤት ኃላፊ ሰብሳቢ
፪=የመርሱ አንድ ባለሙያ አባል
፫=ሁለትየወረዳ መ/ራን ማህበር አንዷ ሴት አባል
፬=የመርሱ ቡድን መሪ አባልና ፀሐፊ ናቸው፡፡
8 ኛ= የመርሱ ዲሲኘሊን ቅሬታ አቀራረብ:-
፩=ለመ/ራን በ 7 የስራ ቀናት ለቀትስቦ ሲሆን ለር/መ/ሩ ግን አፅዳቂ ስለሆነ ቅሬታ አይቀርብም፡፡ ፪=የት/ቤት አመራሮች ደግሞ
በ 7 ቀናት ውስጥ ለትም/ጽ/ቤት ኃላፊ ይቀርባል፡፡ ቅሬታው ከሰበር ፍ/ቤት በላይ መብቱ ነው፡፡
9 ኛ= የይርጋ ጊዜ የቀላልና የከባድ ዲሲኘሊን ጥፋቱ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ 6 ወር ውስጥ እርምጀ ካልተወሰደ ተጠያቂ
አይሆንም፡፡ ግን ያልጠየቀው አካል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
10 ኛ=የመርሱ የ 2007 ዓ,ም መመሪያ እና ደብደቤዎች በዚህ መመሪያ ቁጥር

ክፍል አንድ የመረዳጃ ዕድሩ ስም፣አድራሻ፣ ትርጉምና ዓላማ፣ አንቀጽ አንድ የመረዳጃ ዕድሩ ስም፣ 1. የመረዳጃ ዕድሩ ስም
“በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ የሚገኝ «አድማስ ኮዬ-2»የነዋሪዎች መረዳጃ ዕድር ነው፣ አንቀጽ ለት የመረዳጃ ዕድሩ አድራሻ
2.1 የመረዳጃ ዕድሩ አድራሻ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር፣በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ቱሉዲምቱ
ወረዳ ኮዬ ፈጬ አድማስ ኮዬ -2 ሕንጻ ቁጥር ከ 704-708 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለንብረቶች ኃ/የተ/የኅብረት ሥራ ማኀበር
ነው፣ አንቀጽ ሦስት ትርጉም በዚህ የመረዳጃ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የተጠቀሱት ቃላት የሚከተሉት ትርጉም
ይኖራቸዋል;3.1. "መረዳጃ ዕድር ወይም ዕድር ማለት በዚህ መተዳደሪያ መሰረት የተቋቋመ “የኮዬ-ፈጬ 2 ከሕንጻ ቁጥር
704-708 ነዋሪዎች ያቋቋሙት አድማስ ኮዬ-2 መረዳጃ ዕድር” ነው፤ 3.2. "አባል"ማለት የመቆያ ጊዜውን ያሟላ እና
ወርሃዊ መዋጮና ሌሎች ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ የሚገኝ የመረዳጃ ዕድሩ አባል ወንድ ወይም ሴት ሰው ነው፣ባልና
ሚስት በትዳር ውስጥ እስካሉ ድረስ ሁለቱም እኩል የአባልነት መብት አላቸው፣ 3.3. የመጠበቂያ ጊዜ ማለት ማንኛውም
ሰው የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን አመልክቶ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተፈቅዶለት የመግቢያ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ
ከፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ የ 30 (ሰላሳ)ቀን እስኪሞላው የሚቆይበት ጊዜ ነው፣ 3.4. ጠቅላላ ጉባዔ ማለት የመረዳጃ ዕድሩ
ጠቅላላ ሁሉም አባላት የሚደረግ ስብሰባ ማለት ነው፣ 3.5. መተዳደሪያ ደንብ ወይም ደንብ ማለት በመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ
ጉባዔ የጸደቀና በሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት የተመዘገበ የዕድሩ ሰነድ ነው፣ 3.6. ኮሚቴ ማለት በመረዳጃ ዕድሩ
መተዳደሪያ መንብ መሰረት በጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጡ የመረጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ማለት ነው፣ 3.7.
የኦዲት ኮሚቴ ማለት በጠቅላላው ጉባዔው የሚመረጥ በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አጠቃላይ የመረዳጃ
ዕድሩን የሥራ እንቅስቃሴ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ የሆነ ነው፣ 3.8. ወርሃዊ ክፍያ ማለት
በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከእያንዳንዱ አባል በየወሩ የሚሰበሰብ ገንዘብ ነው፣ 3.9. ቅጣት ማለት
ማንኛውም አባል በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ሳያከብር ሲቀር ተፈጻሚ የሚሆን
ማንኛውም ዓይነት ቅጣት ነው ፣ 3.10. ንብረት ማለት በመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ በግዥ ወይም በስጦታ ወይም
በማናቸውም ሁኔታ የተገኘ በመረዳጃ ዕድሩ ስም የተመዘገበ አላቂና ቋሚ ንብረት ማለት ነው፣ 3.11. ቅጥር ሠራተኛ
ማለት ለመረዳጃ ዕድሩ ወቅታዊ ሥራዎች ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ እንዲሰራ የሚቀጠር ጊዚያዊ ሠራተኛ
ማለት ነው
ወኪል ወይም ተወካይ ማለት የአባሉን ጉዳይ የሚከታተልና አባሉን የተመለከቱ ጉዳዮች የሚፈጽምና የሚያስፈጽም በአባሉ
በጽሁፍ የተወከለ ወኪል ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የሆነ ሰው ወይም አባል ያልሆነ ማንኛውም
ሰው ማለት ነው፣ 3.13. የምርጫ ዘመን ማለት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የመረዳጃ ዕድሩ የሂሳብ ዓመት
ነው፣የመረዳጃ ዕድሩ የሂሳብ ዓመት ከመስከረም 01 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ ያለው ይሆናል፣ 3.14. ቤተሰብ ማለት
የመረዳጃ ዕድሩ አባል ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ስማቸውን ዘርዝሮ በፊርማው ያረጋገጠው የሰዎች
ስም ዝርዝር ነው፣ 3.15. ልጅ ማለት የመረዳጃ ዕድሩ አባል የተወለደ ልጅ ሲሆን፣የጉድፈቻ ልጅንም የሚያጠቃልል ነው፣
3.16. የጉድፈቻ ልጅ ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ህግ መሰረት የጉድፈቻ ልጅ ለመሆኑ በሕግ የተረጋገጠ መሆን አለበት
ነው፣ 3.17. ደራሽ እንግዳ ማለት በአባሉ ቤት በመደበኛነት የማይኖር ለሕክምና ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት
በአባሉ ቤት በሞት የተለየና አስከሬኑ ከአባሉ ቤት ወጥቶ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የተፈጸመ ወይም አስከሬኑ የተሸኘ ሰው
ነው፣ጥገኛ ነዋሪን ያጠቃልላል፣ 3.18. ዕርዳታ ማለት አባሉ ወይም በአስመዘገበው የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ
ሲደርስ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚሰጥ የገንዘብና ሌሎች እርዳታዎች ማለት ነው፣ 3.19. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ
ውስጥ በወንድ ፆታ የተጠቀሱት አገላለፆች ሁሉ ለሴት ፆታም በእኩል ያገለግላል፤ አንቀጽ አራት የመረዳጃ ዕድሩ ዓላማ 4.1.
የመኖሪያ አካባቢን መሰረት አድርጎ እርስ በእርስ ለመረዳዳት ያቋቋሙት ማኅበራዊ ተቋም በመሆኑ መልካም ግንኙነት
ለመፍጠር፣ለማዳበርና የመረዳዳት ባህልን ለማዳበር፣ 4.2. መረዳጃ ዕድሩ በነዋሪዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት
ሳያደርግ በጋራ መልማትንና ማደግን እንዲሁም የነዋሪውን አብሮ የመኖር እሴትን ማዳበር፣ 4.3. በአባላት ላይ የሚደርሱ
የተለያዩ ችግሮችን እና አደጋዎችን በጋራ ለማቃለል እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በደስታና በሌሎች ሁኔታዎች ላይ
በመሳተፍ የደስታው ተካፋይ መሆን፣ 4.4. መረዳጃ ዕድሩ ነዋሪው የጋራ ተጠቃሚነት አስተሳሰብ በማጎልበት ምቹና
ተመራጭ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆን ማድረግ ነው፣ 4.5. የመረዳጃ ዕድሩ ነዋሪውንና አባሉን ያለምንም ልዩነት ሊጠቅሙ
በሚችሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ፣ 4.6. የአባላትን ዕውቀት፣ገንዘብና ሀብት
በማስተባበርና በመጠቀም የነዋሪውን፣የአባሉንና የቤተሰቡ የኑሮ ሁኔታ የሚሻሻልበትን የልማት እንቅስቃሴዎችን በማጥናት
በሥራ ላይ እንዲውን ማድረግ፤ 4.7. ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆን መጣር፣አቅም ደካማና ሕሙማን አባላትን አቅም
በፈቀደ በሁሉም ረገድ መደገፍ፣መንከባከብና መርዳት፣ 4.8. በአባሉና በአስመዘገበው የቤተሰብ አባላት ላይ የሞት አደጋ
ሲደርስ ቀብር ማስፈጸም፣ማስተዛዘንና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ

ክፍል ለት የመረዳጃ ዕድሩ አባልነት ፣ የአባለት መብት፣ ግደታና እርዳታ አንቀጽ አምስት የመረዳጃ ዕድር አባል ስለመሆን፣
5.1. ማንኛዉም በኮዬ ፈጬ-2 በሕንጻ ቁጥር 704፣705፣706፣707 እና 708 ነዋሪ የሆነ ዕድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ
ሰው የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን ይችላል፣ሆኖም መኖሪያቸው ከፓርሴል 65 ውጪ በአጎራባች ፓርሴል የሚኖሩ ሰዎች
አባል ለመሆን ከፈለጉ ደንቡን ተቀብለው አባልነቱ ሊፈቀድላቸው ይችላሉ፤ 5.2. ወንድምና እህት ወይም ወንድማማቾች
ወይም እህትማማቾች በተመሳሳይ ወቅት የመረደጃ ዕድሩ አባል ሊሆኑ አይችሉም፣ 5.3. ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ
አባል ለመሆን በጽሁፍ መጠየቅ አለበት፣ነዋሪው የዕድር አባል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው
አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ በደንቡ መሰረት አባል ይሆናል፤ 5.4. ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ ሙሉ አባል መሆን
የሚችለው የመመዝገቢያ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ካጠናቀቀ ብቻ ነው፤ 5.5. አዲስ የሚገባው
የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመመዝገቢያ ክፍያው ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በአንድ ጊዜ በ 3 ጊዜ ውስጥ ከፍሎ ማጠናነቀቅ
ይችላል፤ 5.6. የመረዳጃ ዕድሩ የመመዝገቢያ ክፍያ እና ወርሃዊ መዋጮ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታ በጠቅላላ ጉባኤ ሊሻሻል
ይችላል፣ 5.7. ማንኛውም የመግቢያ ክፍያ ያጠናቀቀ ከ 31 ኛው ጀምሮ መረዳጃ ዕድሩ ያዘጋጀውን የቤተሰብ መመዝገቢያ
ቅጽ ሞልቶ አባል ይሆናል፣ 5.8. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል አዲስ የተወለደ ልጅን በተወለደ በ 3 (በሶስት)ወር
(90)ቀናት ውስጥ እንዲሁም የጉድፌቻ ልጅ በፍርድ ቤት ውሳኔ ባገኘ በአንድ ወር ወይም በ 30(ሰላሳ)ቀናት ውስጥ
የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ የመመዝገብና የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣ 5.9. ማንኛውም
የመረዳጃ ዕድሩ አባል በሥራ ምክንያት ወይም ለትምህርት ሲሄድ ወይም የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ አድርጎ አካባቢውን
ከለቀቀ በአባልነት መቀጠል ከፈለገ ወርሃዊ መዋጮ እየከፈለ በአባልነቱ መቀጠል ይችላል፤ሆኖም በዕድሩ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ
ራሱ ወይም ቤተሰቡ መገኘት ካልቻሉ መረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው ቅጽ መሰረት በጽሁፍ ተወካይ ሊወክል ይችላል፤ አንቀጽ
ስድስት የመረዳጃ ዕድሩ የአባል መብት 6.1. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በመረዳጃ ዕድሩ ደንብ መሰረት የሚሰጠውን
ማናቸውንም ጥቅም የማግኘትና የመጠቀም መብት አለው፣ 6.2. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ዕድሩ በሚያካሂደው
ስብሰባ ላይ የመሳተፍ፣ ሀሳብ የማቅረብ፣ ሂስ ማደረግ እንዲሁም የመምረጥና የመመረጥ ፣ቅሬታ የማቅረብ ፣በደል
ደርሶብኛል ካለ በደሉን የማሰማት መብት አለው፣ 6.3. ማንኛውም የዕደሩ አባል ዕድሩ የሚሻሻልበትንና የሚያድግበትን
ሀሳብ የማቅረብ መብት አለው፣ 6.4. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል የዕድር አባልነቱን የሚገልጽና ወርሃዊ መዋጮ
የሚከፍልበት ደብተር ይኖረዋል፣ 6.5. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል የዕድሩን መገልገያ እቃዎችና ቁሳቁሶች ለሰርግ፣
ለ 40 እና ለ 80 ቀን መታሰቢያና ለሌሎቹም ጉዳዮች ለመጠቀም መብት አለው፣

የመረዳጃ ዕድሩ አባል አካቢውን ከለቀቀ ከፈለገ ባለበት ቦታ ሆኖ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ በአባልነቱ መቀጠል
ይችላል፣ነገር ግን የመረዳጃ ዕድሩን ዕቃና ቁሳቁስ መጠቀም ከፈለገ በራሱ ወጪ መውሰድና በሚፈቀደው የጊዜ ገደቡ ውስጥ
መመለስ አለበት፣ 6.7. ማንኛው የመረዳጃ ዕድር አባል ባልና ሚስት በህግ ሙሉ መብት ስላላቸው በአንድ ጊዜ የመረዳጃ
ዕድሩ አባል መሆን አይችሉም፣ከባል ወይም ከሚስት ከሁለቱ አንዱ በሞት ሲለይ በሕይወት ያለው የትዳር አጋር የመረዳጃ
ዕድሩ አባል ሆኖ መቀጠል ይችላል፣ 6.8. የመረዳጃ ዕድሩ አባል የነበሩ ባልና ሚስት ሁለቱም በሞት ከተለዩ ከህጋዊ
ወራሾቻቸው መካከል ትዳር የሌላቸው ልጆች የአባልነት መብታቸው ተጠብቆ የመግቢያ ክፍያ ሳይከፍሉ በተመረጠው ልጅ
ወይም ሌሎቹ ባለመብት የሆኑ ልጆች የወከሉት አንድ ልጅ ብቻ አባል ሆኖ መቀጠል ይችላል፣ 6.9. በሟች እናትና አባቱ
ምትክ የተወከለው የሟቾች ልጅ የቤተሰቡንም ዝርዝር በአዲስ መልክ የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ
ቅጽ ላይ ማስመዝገብ አለበት፣ 6.10. በሞት በተለዩ አባትና እናት ምትክ የተወከለው ትዳር ያለው የሟቾቹ ልጅ ከሆነ
በወቅቱ አዲስ ገቢ የሚከፍለውን 50%ወይም ግማሹን ክፍያ ከፍሎ በመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ
ላይ በአዲስ መልክ ቤተሰቡን መመዝገብ አለበት፣ 6.11. የመረዳጃ ዕድሩ አባል የነበሩት እናትና አባት በሞት ሲለዩ በቤት
ውስጥ ያሉ ልጆች የመረዳጃ ዕድሩ አባልነታቸውን የተወካይ ሆኖ ከልጆቹም ውስጥ አንዱ በሞት ቢለይ የሚከፈለው
የማስተዛዘኛ ክፍያ በሞት የተለየው ልጅ እንደ አንድ የዕድር አባል ልጅ እንደሞተ ተቆጥሮ ለልጅ የሚከፈለው የማስተዛዘኛ
ገንዘብ የሚከፈለው ይሆናል፣ 6.12. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል ባልና ሚስት በፍቺ ምክንያት ቢለያዩ ማስረጃ
ሲያቀርቡ በስምምነታቸው መሰረት ከባል ወይም ከሚስት አንደኛው አባል ሆኖ መቀጠል ይችላል፣ ነገር ግን ባልና ሚስት
የነበሩና ፍቺውን ያጸኑ ካልተስማሙ የሁለቱም መብት እኩል በመሆኑ ባል ለብቻው ሚስትም ለብቻዋ የአባልነት የመግቢያ
ክፍያ ግማሹን በመክፈል እንደ አዲስ የመረዳጃ ዕድሩ ያዘጋጀውን የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ሞልተው በየራሳቸው
በአባልነት መቀጠል ይችላሉ፣ በአደጋ ወቅት የጋራ ልጅ ቢሞት አስከሬን የወጣበት ቤት ሙሉ እርዳታ የሚያገኙ ይሆናል፣
6.13. በሞት የተለየው ልጅ ራሱን ችሎ የሚኖር ከሆነ ወይም አስከሬን ከራሱ ቤት የወጣ ከሆነ ከመረዳጃ ዕድሩ
የሚፈጸመው የገንዘብ ዕርዳታ በፍቺ ለተለያዩ ባልና ሚስት እኩል ይሆናል፣ አንቀጽ ሰባት የመረዳጃ ዕድሩ አባላት ግዴታ፣
7.1. ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን ብር 300.00 ሦስት ቶ ብር) የመመዝገቢያ ክፍያ ይከፍላል፤
ክፍያውንም በአንድ ጊዜ ወይም እስከ 3 ጊዜ ከፍሎ ሊያጠናቅቅ ይችላል፣ 7.2. ማንያውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድር አባል
ለመሆን ከሚያዝያ 01 ቀን 2015 ዓ.ም.ጀምሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)ወርሃዊ መዋጮ ይከፍላል፣ክፍያው
የሚፈጸመው ወር በገባ በመጀመሪያው እሁድ ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት እስከ 2:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፣ 7.3. ማንኛውም
አባል የመረዳጃ ዕድሩ በከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ አድርጎ ገቢ ያደረገበትን ሰነድ (Credit Advice)በዚያው ወር
ለዕድሩ ገንዘብ ያዥ ደርሶ ደብተሩ መሞላት አለበት፣በዚያው ወር ገቢ ካልሆነ በሚቀጥለው ወር አባሉ የሚከፍለው ወርሃዊ
መዋጮ ቅጣት ብር 25.00 ብር (ሃያ አምስት)ብርን ጨምሮ ይሆናል፣ 7.4. ማንኛው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመረዳጃ
ዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ ጠንቅቆ አውቆ ማክበርና ማስከበር አለበት፣ 7.5. ማንኛውም አባል በጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ
በሰዓትና በቦታው በመገኘት የስብሳበው ተካፋይ መሆን ግዴታ አለበት፣ 7.6. ማንኛው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመረዳጃ
ዕድሩን በልዩ ልዩ ሁኔታ እንዲያገለግል በአባላት ሲመረጥ ወይም ሲመደብ የማገልገል ግዴታ አለበት፣አባሉ የተመረጠው
ወይም የተመደበው በሥራ አስፈጻሚ ወይም ኦዲት ኮሚቴነት ከሆነ ቢያንስ አንድ የምርጫ ዘመን የማገልገል ግዴታ አለበት፣

ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ያለበቂ ምክንያት የአባላትን ምርጫ ተቀብሎ በተመደበበት ሙያ ለማገልገል ፈቃደኛ
ካልሆነ ወይም እምቢተኛ ከሆነ ወይም አውቆ ቅነነት በጎደለው ሁኔታ የተመደበበትን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ
ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ)ብር እንዲከፍል ፣ድርጊቱን በዚያው የምርጭ ዘመን ከደገመ
ከማስጠኝቀቂያ ጋር ብር 2000.00 ( ለት ሺህ) ብር ተቀጥቶ በአባልነቱ ይቀጥላል ፣ከቀጠለ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ
የሚወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል፣ 7.8. ማንኛውም አባል የመረዳጃ ዕድሩን ንብረት እንዳይጠፋ ወይም ጉዳት
እንዳይደርስበት የመጠበቅ ወይም የመንከባከብ ጥፋት ወይም ጉዳት ሲደርስበት እንዲታረም ማድረግ አለበት፣ 7.9.
ማንኛውም አባል ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ ማስመዝገቢያ ቅጽ ላይ በቅጹ መሰረት መመዝገብ አለበት፣የቤተሰብ ለውጥ
ሲኖርም በወቅቱ ለኮሚቴው በጽሁፍ ማስወቅና ለውጡን መመዝገብ አለበት፣ሆኖም የጋብቻ ለውጥ ከሆነ ቀደም ሲል
የነበረው ጋብቻ መፍረሱን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣ 7.10. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል
በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ ለመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴው በተገኘው የመገናኛ ዘዴ በወቅቱ ማሳወቅ አለበት ፣ 7.11. የመረዳጃ ዕድሩ አባል በዕድሩ ከተወሰነው ክልል ውጪ
ካልሆነ በስተቀር በቤተሰቡ ላይ ሞት አደጋ ሲደርስ ወይም መርዶ ሲረዳ በሚደረገው ጥሪ ማንኛውም አባል ወዲያውኑ
ከጥሪው ቦታ ወይንም ከዕድሩ ዕቃ ቤት በመገኘት እክል ወደ ደረሰበት አባል ቤት ዕቃ መውሰድና ድንኳን መትከል፣የቀብር ስነ
ስርዓት ማስፈጸም እና በዕለቱ የተመደበበትን የሥራ ድርሻ ማከናወንና እንዲሁም እስከ ሁለት ቀን ምሽት የማስተዛዘን
ግዴታ አለበት፣ይህን ያልተወጣ አባል በእድሩ ደንብ መሰረት ይቀጣል፣ 7.12. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሆኑ አረጋውያን እና
የጤና ችግር ያለባቸውን ቀብር ለማስፈጸም ወይም ምሽት ለማስተዛዘን የማይችሉ መሆኑ ሲረጋገጥ፣የአባሉ ቤተሰብ
ወይም ተወካዩ እርሱን በመተካት ኃላፊነቱን ይወጣል፣ሆኖም አባሉን የሚተካው ቤተሰብ ወይም ወኪል ከሌለው
አስፈላጊው ትብብር ይደረግላቸዋል፣ አንቀጽ ስምንት የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሚሰጥ ዕርዳታ 8.1. የመረዳጃ ዕድሩ አባል
ወይም የትዳር አጋሩ በሞት ሲለይ ብር .00 ( )ብር ይከፈላል፣ 8.2. ከአባሉ ወይም ከትዳር አጋሩ የተወለደ ራሱን ያልቻሉ
ልጅ ወይም ህጋዊ የጉድፈቻ ልጅ፣ በሞት ሲለይ ብር .00 ( )ብር ይከፈላል፣ 8.3. የመረዳጃ ዕድር አባል እና የትዳር አጋሩ
አባት እና እናት እንዲሁም ወንድምና ወይም እህት በሞት ሲለዩ ብር .00 ( )ብር ይከፈላል፣ 8.4. በመረዳጃ ዕድሩ አባል
የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ያልተመዘገበ ነገር ግን ለሕክምና ወይም በማናቸውም ምክንያት በአባሉ ቤት በሞት ሲለይ
እና አስከሬኑ ከአባሉ ቤት ተሸኝቶ የቀብር ስነ-ስርዓቱ በአባሉ አማካይነት ከተፈጸመ ብር .00 ( )ብር ይከፈላል፣ 8.5.
የመረዳጃ ዕድሩ አባል በቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ያልተመዘገበ ልጅ ወይም 3 ወር (90)ቀን ያልሞላው ሕጻን ከሞተ
ሁኔታውን በሚያውቁ በ 3 (ሦስት)የመረዳጃ ዕድሩ አባላት ፊርማ ተረጋግጦ ብር .00 ()ብር ይከፈላል፣

68.6. የትዳር አጋሩ በሞት የተለየበት የመረዳጃ ዕድር አባል ሌላ ትዳር እስካልመሰረት ድረስ ለሟች የትዳር አጋሩ ዘመዶች
በትዳር እንዳሉ የሚቀጥል ሲሆን፣አባሉ/ሏ ሌላ ትዳር ከመሰረተ/ች የትዳር አጋሩ ዘመዶች ዝርዝር በአዲስ መልክ
ስለሚመዘገብ በሟች ዘመዶች ስም መረዳጃ ዕድሩ ምንም አይነት የዕርዳታ ክፍያ ሊፈጽም አይችልም፣ 8.7. ማንኛውም
የመረዳጃ ዕድር አባል በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ በ 3 (ሦስት)ወር ወይም በ 90(ዘጠና)ቀናት
ውስጥ የዕርዳታ ጥያቄውን ራሱ ወይም በወኪሉ አማካይነት ማቅረብ አለበት፣ በቂ ባልሆነ ምከክንያት ከ 3(ሦስት)ወር
ወይም ከ 90(ዘጠና)ቀናት በኋላ የሚቀርብ የዕርዳታ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፣ 8.8. ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው
በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ስም ለሚቀርበው የዕርዳታ የክፍያ ጥያቄ አጠራጣሪ ሆኖ ካገኘው ወይም አስፈላጊ ሆኖ
ሲያገኘው ተጨማሪ ማስረጃ ከቀበሌ፣ ከቀበሌ ገበሬ ማህበር ወይም ከሰፈር ዕድርና ከመሳሰሉት ህዝባዊ ድርጅቶች
ማረጋገጫ ሊጠይቅ ይችላል፣ ያለአግባብ የተከፈለ የዕርዳታ ገንዘብ ካለ በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት
ይፈጸማል፣ 8.9. የመረዳጃ ዕድሩ አባል ማንኛንም የእርዳታ ጥያቄውን ማቅረብ የሚችለው የመረዳጃ ዕድሩ ባዘገጋቸው
የዕርዳታ መጠየቂያና መፍቀጃ ቅጽ ሲሆን፣የገንዘብ ዕርዳታም ሊከፈለው የሚችለው የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ
መመዘገቢያ ቅጽ ላይ በአግባቡ ለመዘገባቸው የቤተሰቡ አባላት ስም ብቻ ነው፣ ክፍል ሦስት የመረዳጃ ዕድሩ የገቢ
ምንጭ፣የገንዘብና ንብረት አያያዝና አጠቃቀም አንቀጽ ዘጠኝ የመረዳጃ ዕድሩ የገቢ ምንጭ 9.1. አዲስ ከሚገቡ የአባልነት
የመግቢያ ክፍያ፣ 9.2. ከአባላት ወርሃዊ መዋጮና የቅጣት ገንዘብ ፣ 9.3. ከአባላት የመታወቂያ ደብተር ሽያጭ፣ 9.4.
ከመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ

አንቀጽ አስር መረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም፣ 10.1.1. ከመረዳጃ ዕድሩ አባላት በየወሩ የሚሰበሰበው ወርሃዊ
መዋጮ እና የቅጣት ገንዘብ በደብተርና በመዝገብ ሆኖ ሌሎችም ገቢዎች ገንዘብ ያዡ መረዳጃ ዕድሩ ደረሰኝ የሚሰበሰብ
ይሆናል፣ 10.1.2. በመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ የተሰበሰበው ገቢ ገንዘብ በአምስት የሥራ ቀን ውስጥ በመረዳጃ ዕድሩ ስም
በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ አለበት፣ገንዘቡ ገቢ የሆነበትን የባንክ ደረሰኝ ቅጅ (ኮፒ)ለሂሳብ ሹሙ ይሰጣል፣
10.1.3. በመረዳጃ ዕድሩ ስም የተከፈው የባንክ ደብተሩ በሊቀመንበሩ ፣ በሂሳብ ሹሙና በገንዘብ ያዥ ጥምር ፊርማ
ይንቀሳቀሳል፣ 10.1.4. ማንኛውም ገቢና ወጭ ማስረጃና ጥራዞች ተመርምረው ካለቀላቸውና ጠቅላላ ጉባዔው ሪፖርት
ቀርቦለት ጉባኤው ካጸደቀው ሰነዶቹ ከነሪፖርቱ በመረዳጃ ዕድሩ ጽሕፈት ቤት በኩል በፀሐፊው ኃላፊነት ተጠብቀው
ይቀመጣሉ፣ 10.1.5. የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃዎች በኪራይ ሲሰጡ ሆነ የጠፋ ንብረትን ዋጋ ሲከፍል የተቀመጠውን የኪራይ
ሂሳብ ወይም የዕቃውን ወቅታዊ ግምት ዋጋ በደረሰኝ ገቢ ይደረጋል፣

አንቀጽ አስራ አንድ የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ 11.1. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሚገለገልበት
ንብረት፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች ይኖሩታል፣ ንብረቶቹ በንብረት ኃላፊው ክትትልና ጥበቃ ይደረግላቸዋል፣ 11.2. የመረዳጃ
ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችና ቁሳቁሶች
እንዲገዙና በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ 11.3. የመረዳጃ ዕሩ ንብቶች፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች በመተዳደሪያ ደንቡ
መሰረት ለአባላት ጥቅም በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ 11.4. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዕድሩን
ንብቶች፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች በተመለከተ የአፈጻጸም ዝርዝር መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፣ 11.5. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴው ንብረቶችና ቁሳቁሶቹን ለማከራየት የወቅቱን ዋጋ ያገናዘበ፣የኪራይ ተመን ሊያወጣና በሥራ ላይ
እንዲውል ያደርጋል፣ 11.6. የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት የሆኑ እቃዎችና ቁሳቁሶች ጥገናና እድሳት ሲያስፈልጋቸው
እንዲታደሱና እንዲጠገኑ ያደርጋል፣ 11.7. የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃ አጠቃቀም በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት
በዕቃዎቹ የመጠቀም መብት ያለው አባል ወይም በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባል ላይ በሞት ሲለይ ወይም መርዶ ሲረዳ
እንዲጠቀም ያደርጋል፣ 11.8. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የዕድሩን ንብረቶች እና ቁሳቁሶች በትውስት ወይም በኪራይ
እንዲሰጣቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ኮሚቴው እንደአስፈላጊነቱ ሊፈቅድ ይችላል፣ 12. የንብረት ኃላፊው የመረዳጃ ዕድሩ
ኮሚቴ አባሉ ወይም ነዋሪው በነጻ ወይም በኪራይ የወሰዳቸውን የመረዳጃ ዕድሩ ንብረቶች እና ቁሳቁሶች በተወሰነው ጊዜ
መመለሳቸውን ይከታተላል፣በወቅቱ ካልመለሱ ለዘገየበት ጊዜ የተወሰነውን ክፍያ እንዲከፍሉ ያደርጋል፣ 13. የመረዳጃ ዕድሩ
ንብረትና ቁሳቁሶች ንጽህናና ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያጋግጣል፣ይቆጣጠራል፣ንብረቶቹን የወሰደው ወይም የተከራየው
ሰው ካበላሸ ወይም በንጽህና ካልመለሰ የተበላሸው እንዲጠገን ወይም እንዲተካ ወይም ንጽህናው እንዲጠበቅ ያደርጋል፣
14. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ወይም ነዋሪ በነጻ ወይም በኪራይ የወሰዳቸውን የመረዳጃ ዕድሩን እቃዎችና
ቁሳቁሶች በ 3(ሶስት)ቀናት ውስጥ መመለሱን ያረጋግጣል፣አባሉ የተወሰኑት ዕቃዎች ወይም ቁሳቁሶች እንዲቆዩለት ከጠየቀ
የሚፈልገውን ዕቃ የኪራይ ዋጋ ግማሹን ከፍሎ እስከ 7 (ሰባት)ቀናት ብቻ እንዲጠቀም ያደርጋል፣ 15. በዚህን ጊዜ ውስጥ
በሌላ የዕድሩ አባል ላይ የሞት አደጋ ወይም መርዶ ቢደርስ የንብረቶቹን ወይም እቃዎቹ ቢፈለጉ አባሉ የወሰዳቸውን
እቃዎች በሙሉ እንዲመልስ ተደርጎ በተመሳሳይ ለሚፈልገው ለሌላው አባል እንዲሰጥ ሊያደርግ ይችላል፣ 15.1.
ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል የዕድሩን መገልገያ እቃዎች ለ 40 እና ለ 80 ቀን መታሰቢያዎች፣ ወይም ለሰርግ እና
ለመሳሰሉት አገልግሎቶች መጠቀም ከፈለገ የኪራዩን ግማሽ ከፍሎ እንዲጠቀም ሊያደርግ ይችላል፣ 15.2. የመረዳጃ ዕድሩ
አባል ያልሆነ ሰው ንበረቱን ለመከራየት የኪራይ ጥያቄውን በጽሁፍ አቅርቦ ሲፈቀድለት ለሚከራያቸው ንብረቶች ዋስ
ወይም በቂ ገንዘብ ማስያዝና መውሰድ ይችላል፣በኪራይ የወሰዳቸውን ንብረቶች በአግባቡ ሲመልስ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ
ይመለስለታል፣

. ክፍል አራት አንቀጽ አስራ ሁለት የመረዳጃ ዕድሩ አደረጃጀት፤ የመረዳጃ ዕድሩ የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖሩታል፡፡
12.1. የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባዔ፣ 12.2.የመረዳጃ ዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ 12.3. የመረዳጃ ዕድሩ የኦዲት
ኮሚቴ ናቸው፤ አንቀጽ አስራ ሦስት የመረዳጃ ዕድሩ የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ
የመረዳጃ ዕድሩ አባላት በሙሉ ሲሆኑ፣ ተግባርና ኃላፊነት

፤ 13.1. ጠቅላላ ጉባዔ የመረዳጃ ዕድሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፣ይቆጣጠራል፣ 13.2. የመረዳጃ ዕድሩን
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የኦዲት ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል፣ይሽራል፣ 13.3. የመረዳጃ ዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ
ያፀድቃል፣ያሻሽላል፣ይሰርዛል ወይም ይሽራል፣ 13.4. የመረዳጃ ዕድሩን በተመለከተ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ
ያስቀምጣል፣ ይወስናል፣ 13.5. መደበኛና አስቸኳይ የሂሳብና የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን መርምሮ ያጸድቃል፣ውሳኔ
ይሰጣል፣በሪፖርቶች ላይ ግድፈቶች ካሉ የማስተካከያ ወይንም የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፣ 13.6. የመረዳጃ ዕድሩን
መተዳደሪያ ደንብን ባለማክበር የሥነ ስርዓት ወይንም የገንዘብ ጉድለት በሚፈጽሙ አባላትና የሥራ አስአስፈጻሚ ኮሚቴ
አባላት ላይ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሕግ እንዲጠየቁ ያደርጋል፣ 13.7. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ አጥንቶ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ለይ ውሳኔ ይሰጣል፣ 13.8. በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተጠንቶ ሲቀርብ
የመረዳጃ ዕድሩ እንዲፈርስ ወይም ከሌላ መሰል መረዳጃ ዕድር(ሮች)ጋር እንዲዋሃድ ይወስናል፣ 13.9. ጉባዔው
በሚቀርበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት የመረዳጃ ዕድሩን ሀብት አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ይወስናል፤ አንቀጽ አስራ
አራት የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን፣ 5
(አምስት)አባላት ይኖሩታል፤ 14.1. የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር፤ 14.2. የመረዳጃ ዕድሩ ፀሐፊ፣ 14.3. የመረዳጃ ዕድሩ
ሂሳብ ሹም፣ 14.4. የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ፣ 14.5. የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኃላፊ ናቸው፣

አንቀጽ አስራ አምስት የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት፣ 15.1. የመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ
ሙሉ በሙሉ በሥራ ላይ ያውላል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል ፣ ይቆጣጠራል፣ 15.2. ለመረዳጃ ዕድሩ አስፈላጊ የሆነውን
የሥራ ማስኬጃ እና ለልዩ ልዩ ወጪዎች የሚሆን የገንዘብ መጠን ይወስናል፣ በደንቡ መሰረት በሥራ ላይ
ያውላል፣ይከታተላል፣ 15.3. የመረዳጃ ዕድሩ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ጠቅላላ ጉባዔ የተወሰኑትን ውሳኔዎች ሁሉ
በሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ 15.4. ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውል ዕድሩን ማኅተም፣የገንዘብ መሰብሰቢያና
የወጪ ደረሰኞችን፣የአባልነት መታወቂያ እና የክፍያ ደብተር እንዲታተም ያደርጋል፣ 15.5. የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን
አዲስ የሚያመለክቱ ዕጩ አባላትን ሁኔታ አጣርቶ አባል እንዲሆኑ ይወስናል፤ 15.6. ማንኛውም መረዳጃ ዕድሩን ለቆ የቆየ
ነዋሪ እንደገና በአባልነት ለመቀጠል ሲያመለክት መርምሮ አባልነቱን ይቀበላል፣ለጠቅላላ ጉባኤ መቅረብ ካለበት አቅርቦ
ያስወስናል፣ 15.7. የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመረዳጃ ዕድሩም ሆነ ለአባላቱ ኑሮ መሻሻል የሚጠቅሙ የልማት
እንቅስቃሴዎችን እያጠና በተግባር እንዲተረጎም ያደርጋል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 15.8. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ከአባላት የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በጊዚያዊነት ወይም በቋሚነት በማቋቋም
ያቀደውን ሥራ ሊያሰራ ይችላል፣ 15.9. የመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል ሲያስፈልግ አጥንቶ በጠቅላላ ጉባዔ
እንዲሽሻልና እንዲጸድቅ ያደረጋል፣ 15.10. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ችግር ገጥሟቸው በመረዳጃ
ዕድሩ ደንብ መሰረት ለቀብር ለማስፈጸም ወይም ለማስተዛዘን ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት ካልቻሉ
አንደማንኛውም አባል መታየትና መቀጣት ከሌለባቸው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እስካመነበት ድረስ ነጻ ሊያደርጋቸው
ይችላል፣ 15.11. የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዕድሩ በሚከስበትም ሆነ የሚከሰስበት ጉዳዮችን
የሚያስፈጽምለት አንድ የህግ ባለሙያ እንደ ጉዳዩ ሁኔታ ቀጥሮ በውክልና ሊያሰራ ይችላል፣ 15.12. የመረዳጃ ዕድሩ
ተሰብሳቢ ገንዘብ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ባንክ መግባቱን ይከታተላል ወጪውንም በትክክል ወጪ መሆኑንና በአግባቡ
በሥራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣ 15.13. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት በነዋሪውና በአባላት ላይ
ለሚደርሰው የሀዘንና የደስታ ጊዜ ተካፋይ እንዲሆኑ መረጃ ይሰጣል፣ ያስተባብራል፣አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም የሥራ
ፕሮግራም በማውጣት አባላትን መድቦ እንዲሳተፉ ሊያደርግ ይችላል፣ 15.14. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት በቤተሰብ
መመዝገቢያ ቅጽ ላይ የመዘገቡት በአግባቡ መሆኑን በማጣራት የማስተዛዘኛ እርዳታውና ከፍያው ለሚመለከተው የዕድሩ
አባል በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፣ይከታተላል፣ 15.15. ለአባላት ለሀዘንም ሆነ ለደስታ በትውስት የተሰጠው የመረዳጃ
ዕድሩ ንብረት በወቅቱ መመለሱንና የጎደለ ወይም የተበላሸ ተለይቶ ሪፖርት መደረጉንና ይከታተላል፣ የጎደለ ወይም
የተበላሸ ንብረት ካለ በዓይነት ወይም በገንዘብ እንዲተካ ያደርጋል፣የንብረት አጠባበቅና ኃላፊነትን በተመለከተ ጥናት
በማድረግ ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ያስወስናል፣ 15.16. መደበኛ ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሰቸኳይ ስብሰባዎችን
እንዲጠራ ሊያደርግ ይችላል፣ሁሉም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የጠቅላላ ጉባል ስብሰባ ቃለ-ጉባዔዎችን ይአንቀጽ አስራ
ስድስት የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር ተግባርና ኃላፊነት፣ 16.1. የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር ተጠሪነቱ ለጥቅላላ ጉባዔ ሆኖ
የዕድሩ መሪና ተጠሪ ሲሆን፣ተግባርና ኃላፊነቱን በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ይፈጽማል፣ያስፈጽማል፤ 16.2. የመረዳጃ
ዕድሩ ሊቀመንበር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የዕድሩን ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባዎችን በሊቀመንበርነት ይመራል፣ ሊቀመንበሩ
ሕጉ በሚፈቅድልት መሰረት የመረዳጃ ዕድሩን ወክሎ ከሦስተኛ ወገር ጋር ይወያያል፣ ይደራደራል፣
ይፈራረማል፣ውሳኔውንና ድርድሩን እንደአስፈላጊነቱ እንዲፈጸም ያደርጋል፤ 16.3. ለመረዳጃ ዕድሩ እድገትና መሻሻል
ጠቃሚ መስሎ የሚታየውን ሀሳብ እያመነጨ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀርባል፣በኮሚቴው ሲታመንበት በሥራ ላይ
እንዲውል ያደርጋል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 16.4. የመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብና ጠቅላላ ጉባዔው የሚያወጣቸውን
መመሪያዎችና የሚወስናቸውን ውሳኔዎች በትክክል መከበራቸውን እና በተግባር ላይ መዋላቸውን
ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣ 16.5. አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በመሰብሰብ ውሳኔ
እንዲሰጥበት ያደርጋል፣ጉዳዩ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውሳኔ ካላገኘ ጠቅላላ ጉባዔን በመጥራት የመጨረሻ ውሳኔ
እንዲያገኝ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣ያስፈጽማል፣ 16.6. ለመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ወጪ እንዲሆን
በወጪ ማዘዣ ሰነድ ላይ ይፈርማል፣ ያፀድቃል፣ ገንዘቡም ለተፈለገው አገልግሎት መዋሉን ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣
16.7. ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ከባንክ ወጪ እንዲሆን ከሂሳብ ሹሙ እና ከገንዘብ ያዡ ጋር በጥምር
ይፈርማል፣ 16.8. የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር ሁሉም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የተመደበለትን የሥራ ድርሻ በትክክል
እያከናወኑ መሆኑን ይከታተላል፣ያግዛል፣ይቆጣጠራል፣ 16.9. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሚያቀርቡትን አቤቱታ እየመረመረ
በደንቡ መሰረት ውሳኔ ይሰጣል፣ከእርሱ ኃላፊነት በላይ ከሆነ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅርቦ ውሴኔ እንዲሰጥበት
ያደርጋል፣ አንቀጽ አስራ ሰባት የመረዳጃ ዕድሩ ፀሐፊ ተግብርና ኃላፊነት፣ 17.1. የመረዳጃ ዕድሩ ፀሐፊ የሊቀመንበሩ
የቅርብ ረዳት ሆኖ ተግባሩን ያከናውናል፤ 17.2. የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር በማይኖርበት ወቅት እሱን በመተካት
የሊቀመበሩን ስልጣንና ተግባር በአግባቡ ይፈጽማል፣ያስፈጽማል፣ 17.3. የመረዳጃ ዕድሩን ጽህፈት ቤት በበላይነት
ይመራል፣የጽህፈት ቤቱን ተግባርና ኃላፊነት ያከናውናል፣የመረዳጃ ዕድሩን ሰነዶችና የአባላትን ማኅደርና መረጃዎች
በጥንቃቄ ይይዛል፤ የዕለት ተዕለት የመረዳጃ ዕድሩን አስተዳደር ሥራዎች በኃላፊነት ያከናውናል፣ 17.4. የመረዳጃ ዕድሩ
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የጠቅላላ ጉባዔን ስብሰባ ሲደረግ ቃለ-ጉባዔ ይይዛል፣ ቃለ-ጉበዔውን በጥንቃቄ ያስቀምጣል፣
17.5. የመረዳጃ ዕድሩን ገቢና ወጭ ደብዳቤዎችንና ሰነዶችን በጥንቃቄ ይይዛል፣በተገቢው ሁኔታ ያስቀምጣል፣ለመረዳጃ
ዕድሩ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ቅጾችን እንዲዘጋጁ ያዘጋጃል፣ያዘጋጃል፣ በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ 17.6. በመረዳጃ ዕድሩ
አባልና በተመዘገበ የቤተሰቡ አባል ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ የመረዳጃ ዕድሩ አባላት እንዲያውቁት ያደርጋል፣በሞት
የተለየውን የቤተሰብ አባል ስም ከአባሉ የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ዝርዝር ላይ በሞት የተለየበት ቀን በመጥቀስ
ይሰርዛል፤ኖራቸዋል፣

አንቀጽ አስራ ስምንት የመረዳጃ ዕድሩ ሳብ ሹም ተግብርና ኃላፊነት፣ 18.1. የመረዳጃ ዕድሩን የገቢና የወጪ መዝገብ
ያቋቁማል፣በደንቡ መሰረት ይይዛል፣ ይከታተላል፣ በኃላፊነት ይቆጣጠራል፣ 18.2. የመረዳጃ ዕድሩን የባንክ ሂሳብ እንቅስቃሴ
ይከታተላል፣የገቢና የወጪ ደረሰኞችን እንዲታተሙ በማድግ በጥንቃቄ ይይዛል፣በሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፣ 18.3.
ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ከባንክ እንዲወጣ ከሊቀመንበሩ እና ከገንዘብ ያዡ ጋር በጥምር ፊርማ
ያደርጋል፣ 18.4. የመረዳጃ ዕድሩን የገንዘብ መሰብሰቢያ እና የወጪ ማድረጊያ እንዲሁም የዕቃ ኪራይ ደረሰኞችን ባጠቃላይ
በኃላፊነት ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣ኦዲት ሲደረግም ለኦዲት ኮሚቴው አቅርቦ ኦዲት ያስደርጋል፣ 18.5. የመረዳጃ ዕድሩ
የተሰራባቸውን የገቢ ደረሰኝ እየመረመር ሂሳቡን በመዝጋት ቀሪውን በጥንቃቄ እንዲቀመጡ ያደርጋል፣ 18.6. የመረዳጃ
ዕድሩን የገቢና የወጪውን ሂሣብ የሚያሳይ መዝገብ አዘጋጅቶ ከኦዲተሩ ጋር በጋራ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውና ለጠቅላላ
ጉባዔው መግለጫ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ 18.7. በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ወርሃዊ መዋጮ ሂሣባቸውን
በየጊዜው የማይከፈሉትን አባላት ስም ዝርዝር ይለያል፣ሁኔታውን ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እያቀረበ ውሳኔ እንዲሰጥበት
ያደረጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ 18.8. የመረዳጃ ዕድሩ ኦዲት ኮሚቴ ሂሳቡን ለመመርመር ሲጠይቅ መረዳጃ ዕድሩ
የሰራባቸውን የገቢና ወጪ ደረሰኞችን አቅርቦ እንዲመረመሩ ያደርጋል፣ 18.9. የመረዳጃ ዕድሩን ገንዘብና የንብረት
መመዝገቢያ ሰነዶችና ሌሎች ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በጥንቃቄ ይይዛል፣ 18.10. በመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ እጅ
ለመጠባበቂያ ከሚፈቀድለት ብር .00 ( )ብር በላይ የሆነው ገንዘብ ባንክ ሂሳቡ ገቢ መሆኑን ይከታተላል፣ቆጣጠራል፣

አንቀጽ አስራ ዘጠኝ የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ ተግብርና ኃላፊነት፣ 19.1. የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ ለዕድሩ ገንዘብ
እና ሰነድ አጠባበቅ ኃላፊ ነው፣ 19.2. በየወሩ የአባላትን ወርሃዊ መዋጮ በደብተርና በመዝገብ ይሰበስባል፣በመረዳጃ ዕድሩ
ስም በተከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ባንክ ገቢ ያደርጋል፣እንዲሁም በመረዳጃ ዕድሩ የባንክ ሂሳብ ገቢ ያደረጉ አባላትን ዝርዝር
በመያዝ ገቢ የሆነበትን ማስረጃ ይቀበላል፣ገንዘቡንም 19.3. ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ከባንክ እንዲወጣ
ከሊቀመንበሩ እና ከሂሳብ ሹሙ ጋር በጥምር ፊርማ እየፈረመ ወጪ እንዲሆን ያደርጋል፣ 19.4. በመረዳጃ ዕድሩ ስም
የተከፈተው የመረዳጃ ዕድሩ የባንክ ደብተር በጥንቃቄ በኃላፊነት ይይዛል፣ 19.5. በመረዳጃ ዕድሩ አባላትና አባሉ
በአስመዘገባቸው የቤተሰቡ ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የወጭ ሰነድ ሊቀመንበሩና ሂሳብ
ሹሙ ተፈርሞ ሲደርሰው ክፍያ ይፈጽማል፣ 19.6. ለመረዳጃ ዕድሩ የተለያዩ አገልግሎት የሚውል ገንዘብ ሲያስፈልግ
የወጪ ማዘዣ ተዘጋጅቶ ሲደርሰው በአግባቡ ክፍያውን መፈጸም፣ 19.7. ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚፈለግ
ለመጠባበቂያ የተመደበው ብር ተሟልቶ መገኘቱን ያረጋግጣል፣ገንዘቡንም በጥንቃቄ ይይዛል፣ለተፈለገው ዓላማ ብች
የውላል፣

19.8. በመረዳጃ ዕድሩ አባል ወይም በአባሉ በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ላይ ግልጽ የሆነና የሚታወቅ ድንገተኛ አደጋ
ሲገጥምና የሚፈቀደውን የእርዳታ ገንዘብ የመፍቀድ ወይም በወጪ ማዘዣ ላይ የመፈረም ኃላፊነት ያላቸው ሊቀመንበሩ
ወይም ፀሐፊው በቅርብ ባይገኙ ከመረዳጃ ዕድሩ ሂሳብ ሹም ጋር በመነጋገር ፣ ሂሳብ ሹሙም በተመሳሰይ በቅርብ ካልተገኘ
የደረሰውን ችግር በመገንዘብ የሚፈቀደውን የገንዘብ መጠን ከመጠባበቂያ ሂሳቡ ሊከፍል ይችላል፣ነገር ግን የሚመለከታቸው
የመረዳጃ ዕድሩ አመራሮች ሲገኙ በድንቡ መሰረት የወጪው ሰነድ እንዲጸድቅና የመጠባበቂያ ገንዘቡን መተካትና ማሟላት
አለበት፣

አንቀጽ ሃያ የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት፤ 20.1. የመረዳጃ ዕድሩ የንብረት ኃላፊ ለመረዳጃ ዕድሩ
ንበረት አያያዝና አጠቃቀም ኃላፊና ተጠሪ ነው፣ 20.2. የመረዳጃ ዕድሩን የአላቂና የቋሚ ንብረት መዛግብትን
ያቋቁማል፣ይመዘግባል፣በጥንቃቄ ይይዛል፣ 20.3. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የዕድሩን ንብረቶች እና ቁሳቁሶች በውሰት ወይም
የኪራይ ጥያቄ ሲያቀርቡ በሊቀመንበሩ ወይም በፀሐፊው ሲፈቀድ በዝርዝር መዝግቦ አስፈርሞ ያስረክባል፣በወቅቱ
እንዲመለስ ያደርጋል፣ 20.4. የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃ አጠቃቀም በመረዳጃ በዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መሆኑን
ያረጋግጣል፣ የመረዳጃ ዕድሩ አባልና በተመዘገቡ የቤተሰብ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ እና መርዶ ሲረዳ ዕቃዎቹን በነጻ
በውሰት አስፈርሞ ይሰጣል፤ 20.5. አባሉ ወይም ነዋሪው በነጻ ወይም በኪራይ የተሰጡት የመረዳጃ ዕድሩ ንብረቶች እና
ቁሳቁሶች በተወሰነው ጊዜ እንዲመለሱ ይከታተላል፣ካልመለሱ ለዘገየበት ጊዜ ክፍያ እንዲከፍሉ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው
ያሳውቃል፣ 20.6. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩን ንብረትና ቁሳቁስ የተዋሰ ወይም የተከራየ ሰው የተረከባቸውን ንብረቶች
በተረከበበት ሁኔታ በንጽህና እና ምንም ዓይነት ጉዳት ሳይደርስበት መልሶ ማስረከቡን ያጋግጣል፣ይቆጣጠራል፣ 20.7.
የመረዳጃ የዕድሩ ንብረቶችና ቁሳቁሶች የንጽህና ጉድለት ካለባቸው ንጽህናቸው እንዲጠበቅ ወይም ብልሽት ካለባቸው
ብልሽቱ እዲስተካከል ያደርጋል፣ ካላስተካከለ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያሳውቃል፣ 20.8. የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኃላፊ
ጥገና ወይም እድሳት የሚያስፈልጋቸው የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃዎች ለይቶ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አቅርቦ ያስወስናል፣
የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሲወስን የንበረቶቹ እንዲታደስና እንዲጠገን ያደርጋል፣ ሂደቱንም ይከታተላል፣ 20.9. በዚህን ጊዜ
ውስጥ በሌላ የዕድሩ አባል ላይ የሞት አደጋ ወይም መርዶ ከተረዳና የመገልገያ እቃዎቹ ቢፈለጉ አባሉ የወሰዳቸውን እቃዎች
በሙሉ እንዲመልስ ተደርጎ በተመሳሳይ ለሚፈልገው ለሌላው አባል የሚሰጥ ይሆናል፣ 20.10. በተመሳሳይ ወቅት በአባላት
ላይ ተደራራቢ የሞት አደጋ ሃዘን ከደረሰ እና ድንኳን ወይም ሌላ መገልገያ እቃዎችና ቁሳቁሶች ቢፈለጉ መረዳጃ ዕድሩ
እነዚህን እቃዎች በኪራይ የማቅረብ ኃላፊነት ይኖርበታል፣ አንቀጽ ሃያ አንድ የመረዳጃ ዕድሩ ኦዲት ኮሚቴ ተግባርና
ኃላፊነት፣ 21.1. የመረዳጃ ዕድሩ ኦዲት ኮሚቴ የመረዳጃ ዕድሩን ጠቅላላ ጥቅምና ሕልውና የሚከታተልና የሚቆጣጠር
አካል ሲሆን፣ተጠሪነቱም ለጠቅላላ ጉባኤው ነው፣ 21.2.የመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ በአግባቡ በሥራ ላይ መዋሉን
ያረጋግጣል፣በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ያልተተገበረ ካለ መርምሮ እንዲስተካከል ያደርጋል፣ 21.3. የመረዳጃ ዕድር አባላት
በደንቡ መሰረት ግዴታቸው በአግባቡና በወቅቱ መወጣታቸውን፣ ያረጋግጣል፣
1321.4. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ወጪ የተደረገው በደንቡ መሰረት ተፈቅዶ ተገቢውን የአሰራር ሥርዓት
ተከትሎ በሰነድ መከፈሉን ያረጋግጣል፣ይቆጣጠራል፣ 21.5. በየወሩ የተሰበሰበው የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ በዕድሩ ስም
በተከፈተው የቁጠባ ሂሳብ ባንክ ገቢ መሆኑን የባንክ ሰነዶችን በመመርመር ያረጋግጣል፣የአሰራር ክፍተት ካለም እንዲታረም
ያደረጋል፣ 21.6. በገንዘብ ያዥ እጅ ለመጠባበቂያ የተፈቀደው ገንዘብ በአግባቡ መያዙንና ለታቀደለት ዓላማ እየዋለ መሆኑን
በየጊዜው ይከታተላል፣ይቆጣጠራል፣ 21.7. የመረዳጃ ዕድሩን የወር የገቢና የወጪ ሰነዶችና ደረሰኞችን ይመረምራል፣
የተሰራባቸውንና ያልተሰራባቸውን ደረሰኞች እና ሰነዶች በአግባቡ መያዛቸውን ይቆጣጠራል፣ይመረምራል፤ 21.8. የመረዳጃ
ዕድሩ የኦዲት ኮሚቴ በማናቸውም ጊዜ የመረዳጃ ዕድሩን ሂሳብ ኦዲት በማድረግ የገንዘብና ንብረት አያያዝን
ይቆጣጠራል፣አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የማሻሻያ ሀሳብ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ያቀርባል፣አፈጻጸሙን ይከታተላል፣
21.9. የኦዲት ኮሚቴ የመቆጣጠር ተግባሩን በሚያከናውንብት ጊዜ ለሚያቀርበው ተገቢ ጥያቄ ሁሉ ሊቀመንበሩ፣ የሂሣብ
ሹሙና ገንዘብ ያዡ በአጠቃላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በጋራ ወይም በተናጠል አስፈላጊው እንዲሟሉ መጠየቅ
ይችላል፣ 21.10. የመረዳጃ ዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አጠቃላይ የሥራ እንቅሰቃሴዎቻቸውንና ተግባራቸውን
መተዳደሪያ ደንቡን የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፣የአሰራር ችግር ካላ እንዲታረም ያደረጋል 21.11. በመረዳጃ ዕድሩ አባል
ወይም አባሉ በአስመዘገበው የቤተሰቡ አባል ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ የተፈጸሙት ክፍያዎችና ሌሎች እርዳታዎችን
አፈጻጸም ይመረምራል፣ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፣ክፍተት ካለበትም አፈጻጸሙ እንዲስተካከል ወይም እንዲታረም
ያደርጋል፣ 21.12. የመረዳጃ ዕድሩ እንቅስቃሴ ለጠቅላላ ጉባዔ በየአመቱ 1 (አንድ)ጊዜ ሪፖርት ያቀርባል፣ ክፍል አምስት
አባልነት ስለሚቋረጥበት ፣ እንደገና አባል ስለመሆን፤ የአባልነት ግዴታን አለመወጣትና ሥነ-ሥርዓት እርምጃዎችን
የተመለከቱ ጉዳዮች አንቀጽ ሃያ ሁለት አባልነት ስለሚቋረጥበት ሁኔታ 22.1.ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በፈለገው
ጊዜ በራሱ ፈቃድ አባልነቱን ሊያቋርጥና ዕድሩን ሊለቅ ይችላል፣ 22.2. ማንኛውም የመረደጃ ዕድር አባል በሞት ሲለይ
አባልነቱ ይቋረጣል፣ 22.3. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ያለ በቂ ምክንያት ወርሃዊው መዋጮ ለተከታታይ 3
(ሦስት)ወራት ካልከፈለ በራሱ ፈቃድ ከመረዳጃ ዕድሩ እንደተሰናበተ ተቆጥሮ አባልነቱ ይቋረጣል፣ 22.4. ማንኛውም
የመረዳጃ ዕድር አባል በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ከባድ ዲስፕሊን ጥፋት ፈጽሞ በጠቅላላ ጉባዔ ከአባልነት እንዲሰናበት
ሲወሰን አባልነቱ ይቋረጣል፣ 22.5. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል መረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ
ላይ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አስቦ የማጭበርበር ድርጊት ከፈጸመና ድርጊቱ ከተረጋገጠ ከመረዳጃ ዕድሩ አባልነት
እንዲሰናበት ይደረጋል፣ 22.6. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በማናቸውም ምክንያት አባልነቱ ሲቋረጥ የሚከፈልም
ክፍያ ወይም ያዋጣው መዋጮ አይመለስለትም፣በመረዳጃ ዕድሩ ንብረትም ለመጠቀም አይችልም ፣ወይም መተዳደሪያ
ደንቡ ከሚፈቅደቀው ውጪ አባልነቱ ለሌላ ሰው ሊተላለፍ አአይችልም፣

14 አንቀጽ ሃያ ሦስት እንደገና የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን የሚቻልበት ኔታ፤ 23.1.ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል
የነበረና አባልነቱ የተቋረጠ ሰው እንደገና የመረዳጃ ዕድር አባል ለመሆን ጥያቄውን በጽሁፍ የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ
ኮሚቴ ያቀርባል፤ 23.2.አባል የነበረው ሰው መረዳጃ ዕድሩን የለቀቀው በሥራ ወይም በትምህርት ወይም በሌላ ከአቅም
በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ሲረጋገጥ አባልነቱ ከተቋረጠ እስከ 3 (ሦስት)ዓመት ከሆነ አባልነቱ የተቋረጠበትን ጊዜ ውዝፍ
ወርሃዊ መዋጮ ክፍያ ያለመቀጮ ከፍሎ የመረዳጃ ዕድሩ አባል ሆኖ ሊቀጥል ይችላል፣ 23.3 ሆኖም አባልነቱ በተቋረጠበት
ጊዜ ወርሃዊ መዋጮ ያከፈለበት ጊዜ በመሆኑ በቤተሰቡ ላይ የሞት አደጋ ደርሶ ከሆነ የገንዘብ ክፍያ አይደረግለትም፣
23.4.ከአባልነት የተቋረጠው ከሦስት ዓመት በላይ ከሆነ እንደ አዲስ አባል የወቅቱን የመመዝገቢያ ክፍያ ሙሉ በሙሉ
በመክፈል የመረዳጃ ዕድሩ አባል ሊሆን ይችላል፣ 23.5. አመልካቹ የመረዳጃ ዕድሩን የለቀቀው ጥፋት በመፈጸም ወይም
በዲስፕሊን ጉድለት ወይም መረዳጃ ዕድር አባልነት ባለመፈለግ ከሆነ ኮሚቴው የአባልነት ጥያቄው ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ
በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፣

አንቀጽ ሃያ አራት

ግዴታን በአግባቡ አለመወጣትና የሥነ-ሥርዓት እርምጃዎች፣ 24.1. ማንኛው የመረዳጃ ዕድር አባል በዚህ መተዳደሪያ ደንብ
ላይ የተደነገገውን ሁሉ በማክበር አሟልቶ ካልፈጸመ ተጠያቂ ይሆናል ፤ 24.2. ማንኛው የመረዳጃ ዕድር አባል ያለ በቂ
ምክንያት መረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚጠራው ጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ ካልተገኘ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀሪ
የሆነ ብር 20.00(ሃያ ብር)ይቀጣል፣ 24.3. ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ ከቀረ ብር 50.00(ሃምሳ ብር)ይቀጣል፣ 24.4. ለሦስተኛ
ጊዜ ቀሪ ከሆነ ብር 75.00(ሰባ አምስት ብር)ተቀጥቶ በኮሚቴው የቃል ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው ይደረጋል፤ 24.5. አባሉ
ለአራተኛ ጊዜ ቀሪ ከሆነ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)ይቀጣል፣ በኮሚቴው የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ እንዲደርሰው
ይደረጋል፤ 24.6. ለአምስተኛ ጊዜ ደግሞ ከቀረ ከሆነ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር)ይቀጣል፣ ኮሚቴው የጽሁፍ
ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ድጋሜ እንዲደርሰው ይደረጋል፤ 24.7. አባሉ ለስድስተኛ ጊዜ ደግሞ ቀሪ ከሆነ ጉዳዩ ለጠቅላላ
ጉባኤው ቀርቦ ጉባዔው ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል፣ 24.8. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ
በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ወርሃዊ መዋጮ ካልከፈለ ወይም በባንክ የሚከፍለው በተወሰነው ጊዜ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ
ማስጃ Credite Advice ካላቀረበ ብር 25.00 (ሃያ አምስት)ብር ይቀጣል፣አባሉ ወርሃዊ ክፍያ በሚከፈልበት ቀን ሳይከፍል
ቢቀር ላልከፈለባቸው ጊዚያትና ውዝፍ መዋጮ ሲከፍል የሚከፍለው ቅጣት በቋሚነት ብር 25.00 (ሃያ አምስት)ይሆናል፣
24.9. ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት አስቦ በሞት ያልተለየበትን ቤተሰቡን ሞቷል
በማለት ወይም በሞት ከተለየ በቆየ የቤተሰቡ አባል ስም የገንዘብ ዕርዳታ እንዲከፈለው ጥያቄ አቅርቦ ከተከፈለው አላግባብ
የተከፈለውን ገንዘብ እንዲመልስና ለፈጸመው የማጭበርበር ድርጊት የተከፈለውን ገንዘብ እጥፍ እንዲከፈል ተቀጥቶ
በአባልነቱ እንዲቀጥል ይደረጋል፣

24.10. አላግባብ የተከፈለውን ገንዘብ ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆና የተወሰነበትን ቅጣት ለመክፈል ፈቃደኛ ካልሆነ አባሉ
የፈጸመው የማጭበርበር ደርጊት መሆኑ ተረጋግጦ ከመረዳጃ ዕድር አባልነት እንዲሰናበት ይደረጋል፣ድርጊቱ የማጭበርበር
ወንጀል በመሆኑ በወንጀል እንዲጠየቅ ሊደረግ ይችላል፣ 24.11. ማንኛው የመረዳጃ ዕድር አባል በሥራ አጋጣሚ እጁ
የገባውን የመረዳጃ ዕድሩን ገንዘብና ንብረት አለአግባብ መውሰዱ በማስረጃ ከተረጋገጠ የወሰደውን ገንዘብ ወይም ንብረት
እንዲመልስ ሆኖ ለፈጸመው ያልተገባ ድርጊት ብር 1000.00(አንድ ሺህ ) ብር ቅጣት ተቀጥቶ በአባልነቱ እንዲቀጥል
ይደረጋል፣የተወሰደውና የሚመለሰው የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ባለበት ሁኔታ መሆኑን ወይም ተመሳሳይ ለመሆኑ በሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴው ወይም በባለሙያ መረጋገጥ አለበት፣ 24.12. በመረዳጃ ዕድሩ ማህተም የማይገባ ጥቅም ለማግኘት
አስቦ ወይም በቸልተኛነት ተገቢ ያልሆነ ማስረጃ የሰጠ ወይም በዕድሩ ማህተም የማጭበርበር ድርጊት የፈጸመ የመረዳጃ
ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወይም አባል ብር 2000.00 ( ለት ሺህ)ብር ይቀጣል፣በተጨማሪም አባሉ የፈጸመው
የማጭበርበር ወንጀል በመሆኑ በህግ እንዲጠየቅ ሊደረግ ይችላል፣ 24.13. በመረዳጃ ዕድሩ ማኅተም የተፈጸመው ድርጊት
የሚታወቅ ከሆነ የማረሚያ ደብዳቤ መጻፍ ወይም ማስተካከያ ማድረግ አለበት፣ ክፍል ስድስት የስብሰባ ስነ-
ስርዓት፣ምልዓተ-ጉባዔ፣የምርጫ እና የርክክብ አፈጻጸም፣ አንቀጽ ሃያ አምስት የስብሰባ ስነ-ስርዓትና ምልዓተ-ጉባዔ 25.1.
የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባዔ መደበኛ ስብሰባውን በዓመት 1(አንድ)ጊዜ ያደረጋል፣ ሆኖም አስቸኳይ ሁኔታ ሲገጥም
ወይም 1/3 ኛ የሆኑ አባላት በጽሁፍ ሲጠይቁ፣ወይም የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጠቅላላ ጉበኤ መጥራት
ሲፈልግ በማናቸውም ጊዜ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፣

25.2. የመረዳጃ ዕድሩ አባላት በስብሰባው ላይ እንዲገኙ በዕድሩ ሊቀመንበር በደብዳቤ ወይም በማስታወሻ ወይም በየመኖሪያ ሕንጻ
መግቢያ ላይ ማስታወቂያ በመለጠፍ ወይም በስልክና ሌሎች የመገናኛ ዘዴዎች ጥሪ ሊያደርግ ይችላል፣ 25.3. የመረዳጃ ዕድሩ አጠቃላይ
ጉዳይ የሚወሰነው በድምጽ ብልጫ ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባዔው በዕለቱ አጀንዳ ላይ ተወያይቶ ለመወሰን የሚያስችል ምልዓተ ጉባዔ ሞልቷል
የሚባለው ከጠቅላላ የዕድሩ አባላት ከግማሽ በላይ (50+1)ሃምሳ ሲደመር አንድ አባላት ከተገኙ ይሆናል፣በጉባኤው ዕለት ለውሳኔ
የሚቀርበው አጀንዳ የሚጸድቀው በዕለቱ በስብሰባው ላይ ከተገኙት አባላት በአብላጭ ድምጽ ይሆናል፣ 25.4. የጠቅላላ ጉባኤ አባላት
ስብሰባ ምልዓተ-ጉባኤ ካልተሟላ ቀጣይ ስብሰባ በ 2 (ሁለት)ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደገና በተመሳሳይ ጥሪ ይደረጋል፣ለሁለተኛ ጊዜ
በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙት አባላት ቁጥር ምልዓተ-ጉባኤ አሁንም ካልተሟላ በግልጽ በቃለ-ጉባኤ ተይዞ በዕለቱ በተገኙት አባላት
የጠቅላላ ጉባዔው ስብሰባ ይደረጋል፣ውሳኔ ይተላለፋል፣ የምርጫ አፈጻጸም እና የርክክብ አፈጻጸም፣ አንቀጽ ሃያ ስድስት 26.1.በሥራ ላይ
ያለው የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሥራ ዘመኑ ከማብቃቱ ከ 1 (አንድ)ወር በፊት ኦዲት አስደርጎ የጠቅላላ ጉባዔ አባላትን
ይጠራል፣ 26.2. በመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው የሥራ ዘመኑን አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም፣የሂሳብና
የኦዲት ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ ይቀርባል፣

1626.3. የጠቅላላ ጉበዔ ስብሰባን የነባሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ ከጉባዔተኛው መካከል ከየሕንጻው ሁለት ሁለት ሰዎች
በድምሩ 10 (አስር)አባላት ተጠቁመው አምስት አባላት ስለሚመረጡ እያንዳንዱ አባል 5 (አምስት)ጊዜ ድምጽ እንዲሰጥባቸው በማድረግ
5 ቱ (አምስቱ)ከፍተኛ ድምጽ ያገኙ አባላት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ይመረጣሉ፤ በምርጫው ዕለት በተደረገው ምርጫ 2 ቱ
(ሁለቱ)የተሻለ ደምጽ ያላቸው አባላት ተተኪ ሆነው ስማቸው ተይዞ፣በምርጫ ዘመን በልዩ ልዩ ምክንያ በሚጓደሉ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አባላት ምትክ ተመድበው እንዲሰሩ ይደረጋል፣

26.4. የተለየ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር ለመረዳጃ ዕድሩ አመራር ኮሚቴ አባልነት የሚመረጡ ሰዎች አምስቱንም የመኖሪያ ሕንጻች እና
ፆታን ያታሳቢ ያደረገ መሆን ይኖርበታል፤

26.5. በዕለቱ ምርጫ ሲደረግ በተሰጠው ድምጽ ሁለት ዕጩ ተመራጮች እኩል ድምጽ ካገኙ የእለቱን ስብሰባ ሲመራ የነበረው ሰብሳቢ
ድምጽ የሰጠበት ዕጩ የሚረጥ ይሆናል፤ 26.6. የተመረጡት አምስቱ አባላት የዕለቱን ስብሰባ በሚመራው ሰብሳቢ አማካይነት ተስብስበው
እርስ በእርሳቸው የሥራ ክፍፍል በማድረግ የተመደቡበት የሥራ ድርሻ ወዲያውኑ ለጠቅላላ ጉባኤው አባላት ይገለጻል፣ 26.7. የመረዳጃ
ዕድሩ ጠቅላላ ጉባዔ ከአቅም በላይ በሆነ አስገዳጅ ምክንያት በ 1 (አንድ)ወር ጊዜ ውስጥ ኦዲት ማስደረግና አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ከሚቴ
ተመርጦ ርክክብ መፈጸም ካልቻለ የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ እንዳይስተጓጎል ሲባል ነባሩ ኮሚቴ ሥራውን ቢበዛ ለ 3 (ሦስት)ወር እየሠራ
ይቆያል፣ በ 3(ሦስት)ወራት ጊዜ ውስጥ ነባሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲስ ምርጫ እንዲደረግና ርክክቡ እንዲፈጸም ማድረግ አለበት፣ 26.8.
የመረዳጃ ዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሥራ ዘመን ለ 2 (ሁለት)ዓመት ነው፤ሆኖም እንደገና በተከታይ እንዲሰሩ ለአንድ ጊዜ ብቻ
በድጋሜ ሊመረጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን በተከታታይ ለ 2 (ሁለት)ጊዜ ተመርጦ ያገለገለ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለተከታታይ ሦስተኛ
ጊዜ ሊመረጥ አይችልም፣ 26.9. የሥራ ዘመናቸውን የፈጸሙትና አዲስ ተመርጠው ሥራ የሚጀምሩ የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አባላት የመረዳጃ ዕድሩን ገንዘብና ንብረት እንዲሁም የሰነድ ርክክብ የሚፈጽሙት የነባሩ ኦዲት ኮሚቴ እና አዲስ የተመረጠው የኦዲት
ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ተወካይ በጋራ በተገኙበት ይሆናል፣ 26.10. የሥራ ዘመኑን የፈጸመው መረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
የመረዳጃ ዕድሩ ማኅተም፣ ጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ ያላው ሂሳብ ከባንክ ሂሳብ መግለጫው የ(Bank Statement)ጨምሮ የባንክ
ደብተር፣የመረዳጃ ዕድሩን ንብረቶች፣የአባላት ፋይል እና ሌሎች ሰነዶችን በዝርዝር ርክክብ በቃለ-ጉባዔ መፈጸም አለበት፣ርክክቡ
እንደተፈጸመ አዲስ የተመረጠው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወድያውኑ ኃላፊነቱን ተረክቦ ሥራውን ይጀምራል፣ 26.11. በተመሳሳይ የጠቅላላ
ጉባዔው የአገልግሎት ዘመናቸውን ባጠናቀቁ የመረዳጃ ዕድሩ የኦዲት ኮሚቴ አባላት ምትክ ምርጫ ያከናውናል፣ 26.12. በነባሩ የመረዳጃ
ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አማካይነት ከጠቅላላ አባላት መካከል 5 (አምስት)አባላት ተጠቁመው 3 (ሦስት)ሰዎች ስለሚመረጡ
3(ሦስት)ጊዜ ድምጽ እንዲሰጥባቸው በማድረግ 3 ቱ (ሦስቱ)ከፍተኛ የአባላት ድምጽ ያገኙ አባላት የመረዳጃ ዕድ የኦዲት ኮሚቴ አባል
ሆነው ይመረጣሉ፤የተሻለ ድምጽ ያገኘው 1 (አንድ)አባል ተተኪ ሆኖ ስሙ ተይዞ ይቆያል፣ 26.13. በዕለቱ ከፍተኛ የአባላት ድምጽ ያገኙ
አባላት የዕለቱን ስብሰባ በሚመራው ሰብሳቢ አማካይነት እርስ በእርሳቸው የሥራ ክፍፍል በማድረግ ሰብሰቢ፣ፀሐፊና አባል ሆነው
የተመደቡትን የኦዲት ኮሚቴ አባላት ወዲያውኑ ለጠቅላላ ጉባዔ አባላት ይገለጻል፣

17 ክፍል ሰባት መመሪያ የማውጣት፣የመረዳጃ ዕድሩ ዕድሜ፣መተዳደሪያ ደንቡ የሚሻሻልበትና የሚጸናበት ጊዜ፣ አንቀጽ ሃያ ሰባት መመሪያ
ስለማውጣት፣ የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስፈላጊነቱን ሲያምንበት መተዳደሪያ ደንቡን በማይጻረር መልኩ የተለያዩ የውስጥ
የአሰራር መመሪያዎችን ሊያወጣና በሥራ ላይ እንዲውሉ ሊያደርግ ይችላለል፤ አንቀጽ ሃያ ስምንት ደንቡ የሚሻሻልበት ኔታ በዚህ መረዳጃ
ዕድር መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ መሻሻል ያለባቸው አንቀጾች ሲኖሩ ወይም ደንቡን ሙሉ በሙሉ ማሻሻል ቢያስፈልግ በማንኛውም ጊዜ
በጠቅላላ ጉባኤው ሊሻሻል ይችላል፣ አንቀጽ ሃያ ዘጠኝ የመረዳጃ ዕድሩ ዕድሜ ይህ የአድ ስ ኮዬ-2 የ ረዳጃ ዕድር የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ
ሲሆን፣ ዕድሩ ሊፈርስ የሚችለው በአባላት በሙሉ ወይም 3/4 ኛው በድምጽ ሲወሰን ወይም ከሌሎች መሰል የመረዳጃ ዕድር (ሮች)ጋር
እንዲዋሃድ በበጠቅላላ ጉባኤ አብላጫ ድምጽ ሲወሰን አዲስ መተዳደሪያ ደንብ ስሚወጣ ሕልውናው ሲከስም ወይም በህግ ሊፈርስ ነው፣
አንቀጽ ሰላሳ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ የ“አድማስ ኮዬ-2 የነዋሪዎች ረዳጃ ዕድር” መተዳደሪያ ደንብ ከኅዳር 01 ቀን 2016 ዓ.ም.ጀምሮ
ጸንቶ በሥራ ላይ ይውላል፣ ጥቅምት 04 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት

You might also like