You are on page 1of 31

የዳኞችና የዐቃቤ ህጎች የሙያ ሥነ ምግባር

መግቢያ
የዚህ ሥልጠና ተሳታፊዎች ይህንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ካጠናቀቃችሁ በኋላ የፍትህ
ዘርፉን ትቀላቀላላችሁ፡፡ እንዳንዶቻችሁ ዐቃቤ ህጎች ትሆናላችሁ፡፡ በዚያን ወቅት ከአንድ ዐቃቤ
ህግ የሚጠበቀውን የስነምግባር ደረጃ አውቃችሁ መገኘት ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ዐቃቤ ህጎች
ሙያዊ የስነምግባር መርሆዎች እንዲትገነዘቡ ያደርጋችኃል፡፡
ይህ ሰነድ በሶስት ክፍል ተከፍሎ ቀርቧል፡፡ በመጀመሪያው ክፍል ስለስነምግባርና ስለሙያ
ስነምግባር ጽንሰሀሳብ በጥቅሉ የቀረበበት ሲሆን ክፍል ሁለት ዋናው የዚህ ግንዛቤ ማስጨበጫ
ሰነድ ክፍል ሲሆን ዐቃቤ ህጎች ሊያከብሯቸው ስለሚገቡ የስነምግባር መርሆዎች በዝርዝር
ቀርቧል፡፡ በክፍል ሶስት ስለሚጠበቁ የስነምግባር ደረጃዎች በአጭሩ ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡
በዚህ የስልጠና ሰነድ የተካተቱትን ነጥቦች ለማብላላትና ለመረዳት እንዲቻል በርካታ
የመወያያ ጥያቄዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ሰልጣኖች በእነዚህ የመወያያ ጥያቄዎች ላይ
በጥልቀትና በስፋት እንድትወያዩበት ይጠበቃል፡፡
ዝርዝር ዓላማዎች
ሰልጣኞች ይህንን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሲያጠናቅቁ ፣
1. ስነምግባር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
2. ስነምግባራዊ ወይም ትክክለኛ ነው ወይም ትክክለኛ ያልሆነ ባህርይ ነው ለማለት
ለማለት መለኪያ መስፈርቶችን ያስረዳሉ፡፡
3. ሙያ ማለት ምን እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
4. የሙያ ስነምግባር ምን ማለት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
5. ዐቃቤ ህጎች የሙያ ስነምግባር የሚያሰፈልጋቸው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

1.1. መግቢያ
ሁላችንም E ንደምናውቀው የሰው ህሊና E ውነትን ፍለጋ ሁልጊዜም E ንደወጣና
E ንደወረደ ነው፡፡ ቀድሞ ይታመንበት የነበረውን ሁሉ ከመቀበላችን በፊት E ስቲ E ንመርምረው
ይህ E ኮ E ውነት ላይሆን ይችላል በሚል መንገድ ጥያቄ የምናነሳ ጥቂት A ይደለንም፡፡
ከምንሰማው ሁሉ E ውነተኛው የትኛው ይሆን? በማለት ከጥርጣሬ ማ E በል ውስጥ
ገብተን ስንጨነቅ መገኘታችን E ውቅ ነው፡፡

ሰዎች በቀን ተቀን ህይወታችን ምርጫችን የተለያየ ነው፡፡ A ንዳንዱ ከረባት A ድርጎ
መገኘት ሲመርጥ ሌላው ደግሞ ቀለል ያለ ልብስ መልበስ ይመርጣል፡፡ A ንዳንዶቻችን ቅመም
የበዛበትን ምግብ ስንመርጥ A ንዳንዶቻችን ደግሞ ምርጫችን A ይሆንም፡፡ E ንዲህ E ያለ
በፖለቲካ A መለካከት፣ በሀይማኖት፣ ወዘተ ዋጋ የምንሰጣቸው ነገሮች ይለያያሉ፡፡

የዚህ የልዩነታችን ምክንያት ምንድነው? A ንዱ ዋጋ የሚሰጠውን ሌላው ዋጋ የማይሰጠው


ለምንድነው? A ንዳንዱ ፍትህን ለማስከበር መስዋ E ትነት ሲከፍል ሌላው ደግሞ ጉዳዩን
በቸልተኝነት የሚያየው ለምንድነው? በመሰረቱ ለምንሰጠው ዋጋ ከዚህ በፊት ያሳለፍነው
የህይወት ተሞክሮና ልምድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
A ንዳንድ ጊዜ ሰው ዋጋ የሚሰጠውና መልካምና ክፉ የሚለው ነገር የግድ ያስፈልገዋል ወይ?
ብለው የሚጠይቁ A ሉ፡፡ A ንዳንድ ጊዜ ይህ ሰው ህሊና የለውም ሲባል E ንሰማለን፡፡
E ውነት A ንዳንድ ጊዜ E ንደሚባለው A ንዳንድ ሰዎች ህሊና የላቸውም የሚባለው E ውነት
ነው?
E ንግዲያስ የ A ንድ ተግባር ትክክለኛነቱና መጥፎነቱ የሚለየው በምንድነው? A ንደኛውን
ትክክል ሌላኛውን መጥፎ ብለን የምንጠራው በምን ምክንያት ነው? በህይወታችን ዋጋ
ልንሰጠው የሚገባው ነገር ምንድነው? በሙያችን ዋጋ ልንሰጠው የሚገባው ነገር ምንድነው?
A ገራችንን ህዝባችንን በሚመለከት ዋጋ ልንሰጠው የሚገባና ልንተገብረው የሚገባው ነገር
ምንድነው? E ነዚህን ጥያቄዎች በ A ግባቡ ለመመለስ ጉዳዩን A ጥንቶ A ንድ መስመር
ማስያዝ ይገባል፡፡ ኤቲክስ የሚባለውም ይህንን ጉዳይ የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ነው፡፡

1.2. የኤቲክስ ስነቃል A መጣጥና ትርጉም


ethics የ E ንግሊዝኛ ቃል ሲሆን የመጣውም ethos ከሚል የግሪክ ቃል ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ
ethos ሰዎች በጋራ የሚኖሩበት ቦታ የሚል ትርጓሜ የነበረው ሲሆን ይህን ፍቺ በማስፋት ልምድ
ጸባይ A ነጋገር ባህርይ የ A ስተሳሰብና የ A ነጋገር ዘይቤ የሚሉ ትርጉሞችን E ንደያዘ
የመስኩ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡

በጥንታዊቷ ሮም በላቲን ቋንቋ የግሪኩ ቃል የ ethos A ቻ ቃል mos የተባለው የላቲን


ቃል ሲሆን ትርጉሙም ከሞላ ጎደል ከ ethos ጋር ተመሳሳይ ሆኖ በተጨማሪ ህግ ደንብ
ያለባበስ ስር A ት ወዘተ የሚሉ ትርጉሞችን ይይዛል፡፡ morality የሚለው የ E ንግሊዝኛ ቃል
የተገኘውም ከዚሁ mos ከተባለው የላቲን ቃል ነው፡፡ ስለሆነም ሞራል E ና ኤቲክስ
ተመሳሳይ ሀሳብን ለመግለጽ በመቀያየር የምንጠቀማቸው ናቸው፡፡2

የIንካርታ Iንሳይክሎፒዲያ 2004 በ Eንግሊዝኛው A ጠራር ኤቲክስን ሲተረጉም


በግርድፉ ጠባይ፣ ልምድ፣ የሰው ልጅ ባህርይ የሚመራባቸው መርሆዎች ወይም E ሴቶች
ማለት ነው በማለት ይተረጉማል፡፡
ከላይ ያየናቸው ትርጉሞች ውስጥ ኤቲክስ የሰውን ተግባር ባህሪና ጠባይ ትክክልና ስህተት
በማለት የሚገልጽ E ንደሆነና ባህሪያችን/ ድርጊታችን መቼ ተቀባይነት E ንደሚያገኝ
ወይም E ንደሚያጣ የሚያመለክት ስታንዳርድ ወይም የህጎች ስብስብ E ንደሆነ የ A ንድን
ግለሰብ ወይም የሙያ A ባላትን ባህሪያት የሚገዙ መርሆዎች E ንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡
በ A ጠቃላይ ኤቲክስ ማለት ጥሩ E ና መጥፎ በጎ E ና E ፉ ሀሳብ ንግግርና ድርጊትን
የሚገልጽ ስር A ት ነው ብንል ከ E ውነት A ንርቅም፡፡ A ንድ ሀሳብ ወይም ድርጊት
መልካም ወይም መጥፎ ትክክል ወይም ስህተት ዋጋ ያለው ወይም ዋጋ የሌለው ፍትሀዊ
ወይም Iፍትሀዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚጠቅም መለኪያ ነው፡፡
1.4. የሙያ ስነምግባር ምንድነው?

በመጀመሪያ ስለሙያ ስነምግባር ከመነጋገራችን በፊት ሙያ ምንድነው? የሚለውን መመለስ


ተገቢ ነው፡፡

ሙያ በስልጠና የሚገኝ ንድፈሀሳባዊ E ውቀት ችሎታና ክህሎት መሰረት ያደረገ የዳበረ ልምድና
የጠለቀ ግንዛቤ የሚጠይቅና ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ጠቀሜታ የሚሰጥ ስራ ነው፡፡

ብዙዎች ሙያ A ራት መሰረታዊ ባህርያት E ንዳሉት ይገልጻሉ፡፡4


E ነርሱም
 ልዩ የሆነ E ውቀት የሚጠይቅ፣
 ወደሙያው ለመግባት የተወሰነ የመግቢያ መስፈርት ያለው፣
 ማህበራዊ E ሴት ያለውና ለሌሎች ጥቅም የሚሰራ ወይም A ገልግሎት የሚሰጥ፣
 ስራውን በሚመራና በሚቆጣጠር የስነምግባር ደንብ የሚመራ መሆኑ ናቸው፡፡

ከባለሙያ ልዩ ባህርያት መካከል በመስኩ በሌሎች በቀላሉ ሊተካ የማይችል በረጅም


ስልጠናና ጥረት የተገነባ E ውቀትና ክህሎት ባለቤት መሆን ማለት ነው፡፡

ሙያተኛ በተወሰነ የስራ መስክ ላይ በከፍተኛ ስልጠና ወይም ትምህርት የተገኘ ልዩ E ውቀት
ክህሎትና ልምድ ያላቸው E ውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ ለማዋል
ሌሎችን ለመምራትና ለማሰልጠን A ቅም ያላቸው ሰዎች መለያ ነው፡፡5

የሙያ ስነምግባርስ ምንድነው?


ህብረተሰቡ በተለያየ ደረጃ የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት በየዘርፉ የተለየ E ውቀትና
ችሎታ ያላቸውን ሙያተኞች ይሻል፡፡ ይህ E ውቀት በ A ግባቡ ከተጠቀሙበት ከፍተኛ
ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ በ A ግባቡ ካልተጠቀሙበት ደግሞ ሊጎዳ ይችላል፡፡ ይህንን ደግሞ
ህብረተሰቡ ሊቆጣጠር A ይችልም፡፡
በዚህ ምክንያት ሙያተኞች ያላቸውን E ውቀት ክህሎትና ችሎታ ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ
E ንዲያውሉትና ህብረተሰቡ የጣለባቸውን A መኔታ E ንዲጠብቁ በ A ንድ የሙያ መስክ
የተሰማሩ ሙያተኞች የሚመሩበት የሚከተሉትና የሚተዳደሩበት የስነምግባር ደረጃ ሊኖራቸው
ያስፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሙያ ስነምግባር በ A ንድ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ A ባላት በጋራ የሚመሩበት


የሚከተሉትና የሚተዳደሩበት ራሳቸውንና ስራቸውን ለመቆጣጠር የሚያግዝ የስነምግባር
ደረጃን የሚያመለክት መርህ ወይም ደንብ ነው፡፡ በሌላ A ነጋገር በ A ንድ ሙያ የተሰማሩ
ሙያተኞች E ውቀታቸውንና ችሎታቸውን በ A ግባቡ E ንዲጠቀሙ ሙያዊ ግዴታቸውንና
ሀላፊነታቸውን በ A ግባቡ E ንዲወጡ A ቅጣጫ የሚያሲዝና የሚገዙበት ደንብ ማለት ነው፡፡

በጥቅሉ ስንመለከተው የሙያ ስነምግባር ማለት የ A ንድ ሙያ ባለቤት የሆኑ ሰዎች የዚያን


ሙያ የስነምግባር መመሪያዎች ይዘትና A ስፈላጊነትን በተመለከተ የደረሱበት ስምምነት ወይም
A ስተያየት ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ከዚህም በመነሳት የሙያ ስነምግባር የተለየ
ግብረገባዊ E ሴት ሳይሆን በ A ንድ ሙያ ውስጥ የታቀፉ ሰዎች በስራቸው ሂደት
የሚመሩበት ትክክለኛ ጠባይ ወይም ተቀባይነት የሌለውን የሚያመለክት ነው ቢባል
ስህተት A ይሆንም፡፡

1.5. የዳኞችና የ A ቃቤ ህግ የሙያ ሥነምግባር አስፈላጊነት


የሙያ ሥነምግባርን ማክበር ለዳኞችም ሆነ ለ A ቃብያነ ሕግ E ጅግ በጣም A ስፈላጊ
መሆኑ የሚያከራክር ጉዳይ A ይደለም፡፡ ምክንያቱም ዳኞችም ሆኑ A ቃብያነ ህግ በዜጎች
ነጻነትና ሀብት ላይ ትልቅ ተጽ E ኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ውሣኔዎችን በ E ለት ተ E ለት
የፍትህ A ስተዳደር ተግባራቸው ውስጥ ሲያሳልፉ ነው የሚውሉት፡፡ የዜጎች መሠረታዊ
ነጻነቶችና መብቶች ላይ የሚወስኑ ሙያተኞች ደግሞ ከሌሎች A ካላት ሁሉ በላቀ ደረጃ
ሥነምግባርን የተላበሱ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ዳኞችና A ቃብያነ ሕግ የሚቀርቡላቸውን ጉዳዮች
ሕጉንና ፍሬ ነገሩን በማየት ብቻ በማናቸውም ሌሎች ምክንያቶች ሳይመሩ መወሰን
A ለባቸው፡፡ ይህ ደግሞ ከዳኞችና ከ A ቃብያነ ሕግ ከፍ ያለ የሥነምግባር ደረጃን
የሚጠይቅ ነው፡፡
በተለይም ዳኞች በ A ንድ ህብረተሰብ ውስጥ የበጎ ምግባርና ግብረገብ መገለጫ
E ንደመሆናቸው መጠን ህብረተሰቡ መብቶቹ ሳይከበሩ ሲቀሩ ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጣ
በመሆኑ ያለ A ንዳች A ድሎ በመሥራት በህብረተሰቡ ተ A ማኒነት ማግኘት ይገባቸዋል፡፡
ህብረተሰቡ የፍትህ ተቋማት ከሙስና የፀዱ A ይደሉም ብሎ ማመኑ በራሱ በጣም
A ደገኛ ነው፡፡ በፍትህ ወይም በሕግ ል E ልና ላይ ህብረተሰቡ ጥርጣሬ ካሳደረ ልማትም ሆነ
ዴሞክራሲ A ይታሰብም፣ ይልቁንም ሙስና ይንሰራፋል፡፡ ለዚህ ነው የሙያ ሥነምግባር
ለልማትም ሆነ ለዴሞክራሲ E ንዲሁም ለመልካም A ስተዳደር መረጋገጥ ከፍተኛ
A ስተዋጽ O A ለው የሚባለው፡፡ የዳኝነት ሥርዓቱ ባጠቃላይ የህዝብ A ደራን የተሸከመ
በመሆኑ በፍትህ A ስተዳደር ሥራ ላይ የላቀ ሥነምግባር ባላቸው ሙያተኞች የተደራጀ
መሆን ይገባዋል፡፡ የሥነምግባር A ስፈላጊነትም ከዚህ A ንጻር ነው መመዘንና ትኩረት
ማግኘት ያለበት፡፡

ዳኞች Eና A ቃቤ ህጎች በ Iትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት


A ንቀጽ 9/2) መሰረት ህገመንግስቱን የማክበርና የማስከበር ሀላፊነት A ለባቸው፡፡
በተለይም በ A ንቀጽ 13 የተቀመጡትን መሰረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ከማክበር ባሻገር
የማስከበር ሀላፊነት ስላላቸው ይህን ህገመንግስታዊ ግዴታዎችን በ A ግባቡ E ንዲወጡ ይህንን
ያለ A ግባቡ ሲሸራረፉ ወይም ስልጣናቸውን ያለ A ግባብ ሲጠቀሙና ፍርድን ሲያዛቡ ደግሞ
ተጠያቂ E ንዲሆኑ ለማስቻል ሙያቸው የሚመራበትን የስነምግባር መርሆዎች ጠንቅቀው
ማወቅና መተግበር ይጠበቅባቸዋል፡፡

ክፍል ሁለት
የዳኝነት/ዓቃብያነ ሕግ የሙያ ሥነምግባር በጠቅላላው

ዝርዝር A ላማዎች
ሰልጣኞች ይህንን ክፍል ሲያጠናቅቁ፣
1. የዳኞችንና የ A ቃቤ ህጎችን የሙያ ስነምግባር ለመወሰን በ A ለም A ቀፍ ደረጃና
በ A ገር ውስጥ የተከናወኑ ዋና ዋና ክንዋኔዎችን ያስረዳሉ፡፡
2. የዳኝነት ነጻነትን ለማረጋገጥ ከዳኞች የሚጠበቁ ሙያዊ ስነምግባራዊ ባህርያትን
መለየትና ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. ከ A ድልዎ በጸዳ መልኩ ለመስራት የሚያስችለውን የዳኝነት ባህርይን መለየትና
ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
4. የፍርድ ስራን በሀቀኝነት ለማከናወን ከዳኛው የሚጠበቁ ሙያዊ ስነምግባራዊ
ባህርያትን ተረድተው ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
5. ዳኛው ሊያከብራቸው የሚገቡ የቅንነት ባህርይ መገለጫዎችን ተረድተው ተግባራ
ማድረግ ይችላሉ፡፡
6. በዳኝነት ስራ የ E ኩልነት መርህን ተረድተው ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡
7. በዳኝነት ስራ ትጋትና ጥረት ማሳየት A ስፈላጊነትን ይረዳሉ፡፡ በተግባራቸውም
ለዚህ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡
8. A ቃቤ ህግ A መዛዛኝና ከ A ድልዎ በጸዳ መልኩ መስራት E ንደሚገባው ይረዳሉ፡፡
ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መነሳሳት ይኖራቸዋል፡፡
9. ፍትሀዊነት የ A ቃቤህግ ሊያከብረው የሚገባ ባህርይ መሆኑን ተረድተው
ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡
10. A ቃቤ ህግ ስራውን ለማከናወን ነጻነት E ንደሚያስፈልገውና ከነጻነት ጋር
በተያያዘ ከ A ቃቤ ህግ የሚጠበቁ ባህርያትን ይገልጻሉ፡፡
11. ከ A ቃቤ ህግ ስለሚጠበቅ ተጠያቂነት ይረዳሉ፡፡
12. ምስጢር የመጠበቅ የ A ቃቤ ህግ ሀላፊነት መሆኑን ተረድተው ያውቃሉ፡፡
13. የሙያ ብቃት ከ A ቃቤ ህግ የሚጠበቅ ባህርይ መሆኑን ይረዳሉ፡፡
2.1. መግቢያ
ሕግ E ንደ A ንድ የሙያ ዘርፍ በታሪክ ቀደምትነት ካላቸው ሙያዎች መካከል የሚመደብ
ነው፡፡ ታሪክ E ንደሚያሳየን ከሆነ ሕግና የሕግ ሙያተኞች ከቀደምት ጊዜ ጀምሮ የተደራጁ
ማህበረሰቦች ሁሉ ዓይነተኛ መገለጫ ሆነው መሰንበታቸውን ነው፡፡ ዊድሮው ዊልሰን
የተባሉ A ንድ ምሁር ì
....ማንኛውም የፖሊስ ጥያቄ በሂደት የህግ ክርክር የሚያስነሳ
ጭብጥ መሆኑ A ይቀርም ....î7 ብለው የተናገሩት በተለይም ዛሬ የዓለም A ቀፍ
ህብረተሰብ ለሕግ ል E ልና፣ መልካም A ስተዳደርና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ከሰጠው
ትኩረት A ንጻር ስንመዝነው ሕግና ፍትህ በታሪክ ብቻ ሳይሆን ዛሬም የሰው ልጆች
መሠረታዊ E ሴት መሆናቸውን ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሮናልድ A ሮንሰንና ዶናልድ ዌክስቴይን
የሕግ ሙያተኞች በ A ንድ ህብረተሰብ ውስጥ ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ሲያብራሩ E ንዲህ
በማለት ነው፡፤

....(1) lawyers are instrumental in accompanying the purposes of
law; the establishment and operation of governmental processes, the
protection of individuals from over reaching by government; the
accommodation of individual freedom with essential societal peace
and order; the assertion and balanced response to often conflicting
human wants and desires; the settling and prevention of disputes;
the application of general rules and policies to individuals; the
invocation of and design of the other means of ordering human
conduct in accordance with the perceived goals of society; the
administration of justice,8

ይህም ወደ A ማርኛ ሲመለስ ከሞላ ጎደል የሚከተለውን ግርድፍ ትርጉም ይሰጠናል፡፡ የሕግ
ሙያተኞች ለሕጉ ዓላማ በመቆምና ህጉን ተግባራዊ በማድረግ፣ የመንግሥት A ወቃቀርንና
A ሰራርን በመወሰን ረገድ፣ የግለሰቦች መብትና ነጻነት ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዲጠበቅ
በማድረግ በኩል፣ የግለሰብ ነጻነት ከማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት A ንጻር ሚዛናዊ በሆነ
መልኩ E ንዲከበር ከማድረግ A ኳያ፣ E ርስ በ E ርሳቸው የማይጣጣሙ የሰዎችን ፍላጎትና
ጥቅም በመለየት ሚዛናዊነት የተላበሰ ምላሽ ከመስጠት A ንጻር፣ A ለመግባባቶችን
ከመፍታትና E ንዳይከሰቱ ከመከላከል A ንጻር፣ A ጠቃላይ ሕጎችና ፖሊሲዎች በ E ያንዳንዱ
ግለሰብ ላይ ተፈጻሚነት A ንዲኖራቸው በማድረግ በኩል፣ ከህብረተሰቡ የመጨረሻ ግብ
A ንጻር የሰዎች ጠባይ የሚመራባቸውን ስለቶች በመቀየስና የተሳካ የፍትህ A ስተዳደር
E ንዲኖር በማድረግ በኩል ወሳኝ ሚና ነው ያላቸው፡፡

የሕግ ሙያተኞች E ነዚህን ተግባራት የሚያከናውኑት በዳኝነት፣ በማማከር፣ በማደራደር፣


በማቀድ፣ ጥብቅና በመቆም፣ በማርቀቅ፣ በምርመራ፣ በመክሰስ፣ በማስተማር፣ በመጻፍ፣
በመሟገትና ወዘተ ሥራዎች ላይ በሚያሰማሩበት ጊዜ ነው፡፡ Eነዚህን A ገልግሎቶች
በሚገባ ለማበርከትም የሕግ ሙያተኞች ... በቂ የመሠረታዊ የሕግ
ì
ሥነ-ሥርዓት
Eውቀት...î የመግባባትና የሙግት ክህሎት፣ ታማኝነት፣ ታታሪነት፣
ሚስጢራዊነት፣ ቅንነት፣ ሀቀኝነት፣ በንቃት ነገሮችን መከታተልና ውሣኔ የሚሹ ነገሮች
ላይ ቆራጥነትን መላበስን፣ ለሕጉ ግቦች ተግባራዊነትና ለሂደቱም መከበር በጽናት
መቆምን...î9 ይጠይቃል፡፡ በመሆኑም የህግ ሙያተኞች ከላይ የተዘረዘሩትን ባህርያት
E ንዲያዳብሩና ከመጥፎ ምግባር ራሳቸውን E ንዲያርቁ ለማድረግ የሙያ ሥነምግባርን
ማወቅና A ምነውበት መተግበር ይገባቸዋል፡፡ A ጠቃላይ የፍትህ ስር A ቱ በጠንካራና
A ስተማማኝ መሰረት ተገንብቶ በሃገራችን ሊረጋገጥ ለሚፈለገው ዘላቂና A ስተማማኝ
ሰላም፣ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት መስፈን ዋስትና ሊሆን የሚችለው በሃቀኝነት በራስ
መተማመን ከጉቦ ከ A ድልዎ E ና ከወገናዊነት የጸዱ በስነምግባራቸው ከህብረተሰቡ ከበሬታ
የተቸራቸው ዳኞችና A ቃቤ ህጎችን ያካተተ ሲሆን ነው፡፡ በዚህ ክፍል የህግ ሙያተኞች
የሆኑ ዳኞችና A ቃቤ ህጎች ከሙያቸው A ንጻር ሊከተሉት ስለሚገባ ስነምግባር
E ንመለከታለን፡፡

የ A ቃብያነት ህግ ባለሙያዎችን በሚመለከት

የ A ቃብያነ ሕግ A ደረጃጀትና በወንጀል ፍትህ A ስተዳደር ውስጥ ያላቸው ሚና


በየ A ገሩ የተለያየ ከመሆኑ የተነሳ ረዘም ላለ ጊዜ A ንድ ወጥ የሆነ
ዓለም A ቀፋዊ የሥነምግባር መርህን ለ A ቃብያነ ሕግ ማውጣቱ A ስቸጋሪ ሆኖ
ቆይቷል፡፡ ይሁን E ንጂ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ A ቃብያነ ሕግ የሚመሩበት
የሥነምግባር ደንብ E ንዲወጣ የተለያዩ ግፊት የሚፈጥሩ ሁኔታዎች የታዩ ሲሆን
ከነዚህ ውስጥ ሁለቱን ለ A ብነት ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የተለያዩ
የዓለም ሀገራት A ለምዓቀፋዊ ሰብዓዊ መብት ስምምነቶችን መፈረማቸው የሚታወስ
ሲሆን E ነዚህ ስምምነቶችም በ A ግባቡ E ንዲከበሩ የ A ቃብያነ ሕግን የላቀ
ተሳትፎና ሚና የሚጠይቁ ናቸው፡፡ ከተባበሩት መንግሥታት ቻርተርና የሰብዓዊ
መብቶች ሁሉ A ቀፍ መግለጫ ባሻገር የ A ቃብያነ ህግን ከፍተኛ ተሳትፎ የሚጠይቁ
የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም A ቀፍ ስምምነት፣
ማሰቃየትንና ሌሎች ጭካኔ የተሞላባቸው ሰብ A ዊነት የጎደላቸውና A ዋራጅ የሆኑ
A ያያዞችንና ቅጣቶችን ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት፣ የህጻናት ኮንቬንሽን ወዘተ...
መጥቀስ ይቻላል፡፡ E ነዚህ ስምምነቶች ለሰብዓዊ መብት A ያያዝ ከፍተኛ
A ስተዋጽ O ያላቸውን ከፍርድ በፊት የተያዙና የተከሰሱ ሰዎችን መብት ይደነግጋሉ፡፡
ለምሳሌ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች በፍጥነት ወደ ፍርድ ቤት
E ንዲቀርቡ(የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮንቬንሽን A ንቀጽ 9(3)) E ንዲሁም
ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመዳኘትና ራስን የመከላከል መብትን ((የሲቪልና የፖለቲካ
መብቶች ኮንቬንሽን A ንቀጽ 14) መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም A ቃቤ ሕግ
ገለልተኛ A ካል E ንደመሆኑ መጠን በወንጀል ምርመራ ሂደት የተያዙ ሰዎች ሰብዓዊ
መብት በሚጣስበት ጊዜ የመርማሪ A ካላትን ሕግ የተላለፈ ርምጃ የማረም ኃላፊነት
E ንዳለበት ይገነዘባሉ፡፡ ((የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ኮንቬንሽን A ንቀጽ 6/1/ E ና 7
ሰብዓዊ መብት ሁሉን A ቀፍ መግለጫ A ንቀጽ 3 E ና 5፣ ማሰቃየትንና ሌሎች ጭካኔ
የተሞላባቸው፣ ሰብዓዊነት የጎደላቸውና A ዋራጅ የሆኑ A ያያዞችንና ቅጣቶችን
ለማስቀረት የተደረገ ስምምነት A ንቀጽ 15)፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የ A ስገዳጅነት
ባህርይ ያላቸው ስምምነቶች E ንደተጠበቁ ሆነው ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች
A ለምዓቀፋዊ ይዘት
ያላቸው A ስገዳጅ ያልሆኑ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
ለምሳሌ E ንደ A ውሮፖ A ቆጣጠር በ 1990 ዓ.ም. የፀደቀውን የተባበሩት
መንግሥታት የ A ቃብያነ ህግ ሚናን በተመለከተ የወጣውን መመሪያ መመልከት
ይሻል፡፡ ይህ መመሪያም ዓቃብያነ ህግ የሚመሩበትን የተግባር መርሆዎችና
የሥነምግባር E ሴቶችን የያዘ ነው፡፡ በ E ርግጥ የዚህ መመሪያ ድንጋጌዎች
በመንግሥታት ላይ የ A ስገዳጅነት ባህርይ ባይኖራቸውም የመንግሥታትን ሀሣብ
ስለሚገልጹ በትብብርና በቅን ልቦና መንፈስ በመንግሥታት ላይ ኃላፊነት
ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡

በሁለተኛ ደረጃ A ቃብያነ ሕግ A ለም A ቀፋዊ ጠባይ ያላቸውን የሥነምግባር


ደንቦች ማውጣት A ስፈላጊ ያደረገው በ A ሁኑ ጊዜ E የተስፋፋ የመጣው ድንበር
ተሻጋሪ የሆኑ ወንጀሎች ናቸው፡፡ E ነዚህን የተደራጁ ወንጀሎች መከላከልም ሆነ
መቆጣጠር በተለያዩ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ A ቃብያነ ሕግን ትብብር የሚጠይቁ
በመሆኑ ለዚሁ ትግል ፍሬያማነትም የ A ቃብያነ ህግን የሥነምግባር ደንብ በጋራ
ማበጀቱ A ስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ ዓይነት A ስተሳሰብም በመነሳት የ A ውሮፓ
ህብረትም "Recommendation on the Role of Public Prosecution in the
criminal justice system" በመባል የሚታወቅ A ቃብያነ ህግን ሚናና ሥነምግባር
የሚያትት ህግ A ውጥቷል፡፡ A ቃብያነ ህግም የጋራ ትብብር E ንደሚያስፈልጋቸው
በማጤን በዓለም A ቀፍ የ A ቃብያነ ሕግ ማህበር በኩል E ንደ A ውሮፖ A ቆጣጠር
በ 1999 ዓ.ም. "Standards of Professional Responsibilitiy and Statement
of the Essential duties and Rights of Prosecutors" ተብሎ የሚጠራ የተግባር
መመሪያ A ውጥቷል፡፡ በዚህ የተግባር መመሪያና በተባበሩት መንግሥታት የ A ቃብያነ ህግ
ሚና መመሪያ ላይ E ንደተመለከተው A ቃብያነ ሕግ የሙያ ተግባራቸውን በሚወጡበት
ወቅት ሥራዎቻቸውን በፍጹም ገለልተኝነት፣ ሀቀኝነትና ሚዛናዊነት E ንዲሁም
በፍጹም ነጻነትና የተጠያቂነት መንፈስ ማከናወን E ንደሚገባቸው ያትታሉ፡፡

በመጨረሻም ሳይወሳ መታለፍ የሌለበት ነገር ቢኖር ህግ A ስከባሪዎችን በተመለከተ


የተባበሩት መንግሥታት "UN Code of Conduct for Law
Enforcement officials" ተብሎ የሚታወቀውን የህግ A ስከባሪ ባለሥልጣናት የተግባር
መመሪያ በዲሴምበር 1979 ዓ.ም. የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ
A ጽድቋል፡፡ በዚህ የተግባር መመሪያ መሠረትም የሕግ A ስከባሪ ባለስልጣናት
የሕዝብ A ገልጋይ መሆናቸውና ተጠሪነታቸውም ለህብረተሰቡ E ንደመሆኑ መጠን
ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ የሙያ ግዴታቸውን በሚገባ መወጣት
E ንደሚገባቸው ከዚህም ባሻገር በሥራቸው ሂደት ኃይልን የሚጠቀሙት A ስፈላጊ በሆነ
መጠን ብቻ መሆኑንና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊትን ከመፈጸም መቆጠብ
E ንደሚገባቸውና ሲፈጽምም A ይተው E ንደሆነ ይህንን A ዋራጅ የሆነ ቅጣት ወይም
A ያያዝ ዝም ብለው ማለፍ E ንደማይገባቸው ይተነትናል፡፡

የ A ቃቤ ህግ የስነምግባር መርሆዎች

የተለያየ የህግ ስር A ት በሚከተሉ A ገሮች ተመሳሳይ የሆነ የ A ቃቤ ህግ ሚና


ለማስቀመጥ ያስቸግራል፡፡ ይሁንና በብዙዎቹ A ገሮች በ A ቃቤ ህግ የሚሰሩት ስራዎች
የሚከተሉት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡
1. የወንጀል ምርመራ ስራን መምራትና መቆጣጠር፣
2. የወንጀል ምርመራ መዝገብን መርምሮ ክስ ለመመስረት ወይም መዝገቡን
ለመዝጋት መወሰን‹
3. በፍርድ ቤት የወንጀል ክስ መስርቶ መከራከርና ክሱን ለማቆም መወሰን፣
4. በማስረጃ ከተረጋገጠው የወንጀል ድርጊት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የቅጣት ውሳኔ
ማቅረብ፣
5. በፍርድ ቤት በሚሰጥ ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማቅረብና መከራከር
6. በህግ የተፈቀደ በሆነ ጊዜ ለ A ነስተኛ የወንጀል ድርጊቶች ከወንጀል ክስ ውጭ
በሌላ መልኩ ክርክሩን መጨረስ፣
7. የወንጀል ፖሊሲ ተግባራዊ E ንዲሆን መቆጣጠር
8. የወንጀል ፍትህ ስር A ቱን ለ A ጠቃላይ ህብረተሰቡ ማሳወቅና ማስተማር

A ቃቤ ህግ በህግ ከሚያከናውነው ስራ A ንጻር ሊከተላቸውና ሊተገብራቸው የሚገቡ ሙያው


የሚጠይቃቸው የስነምግባር ደረጃዎች A ሉ፡፡
2.3.1. መልካም ሙያዊ ተግባር

በወንጀል ፍትህ A ስተዳደር ውስጥ መሰረታዊ A ንቀሳቃሾች E ንደመሆናቸው መጠን


A ቃብያነ ሕግ ዘወትር ለሙያቸው ክብር መታመንና በጽኑ መቆም A ለባቸው፡፡42
E ንደሚታወቀው ሁሉ ዓለም A ቀፍ የሰብዓዊ መብቶች መግለጫ በሕግ ፊት E ኩል ሆኖ
የመታየትን ፣ ንፁህ ሆኖ የመገመትን፣ E ንዲሁም ነፃና ገለልተኛ በሆነ የፍርድ A ካል

ፍትሃዊና ግልፅ በሆነ መንገድ የመዳኘት መብትን፣ E ንደቁልፍ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች
መደንገጉ ግልፅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ A ቃብያነ ሕግ በወንጀል ፍትህ A ስተዳደር ውስጥ
በ E ነኚህ መርሆዎች ለመመራትና E ነዚህን መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ሙያዊ
ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ A ቃብያነ ሕግ በፍትህ A ስተዳደር ውስጥ ወሳኝ ሚና
የሚጫወቱ በመሆኑና A ስፈላጊ የሆኑ ሃላፊነቶቻቸውን ስለመወጣት ያሉት ሕጐች
E ነዚህን መርሆዎች A ቃብያነ ሕግ E ንዲያከብሯቸውና E ንዲገዙባቸው ሊያበረታቱ
ይገባል፡፡ በዚህም ፍትህና ርት E የተሞላው የወንጀል ፍትህ ስርዓትና ለዜጐች ከወንጀል
መጠበቅ ከፍተኛ E ገዛ የሚያደርግ ስርዓትን መፍጠር ይቻላል፡፡

A ቃብያነ ሕግ በወንጀል ፍርድ ሂደት ውጤታማ፣ ገለልተኛና ፍትሃዊ E ንዲሆኑ የሚያስፈልግ


ሲሆን E ነዚህን የሥነምግባር መርሆዎች ለመላበስም ለሙያቸውና ለሕግ መታመን
ይኖርባቸዋል፡፡ ሥራቸውንና ኃላፊነታቸውንም በነዚሁ የሙያ የስነምግባር መርሆዎች መሰረት
ማከናወን የግድ ይላል፡፡ ከ A ቃብያነ ሕግ የላቀ ስብ E ናና ከፍ ያለ ሥነምግባር ይጠበቃል፡፡ ከዚሁ
ጐን ለጐን በየጊዜው የሚደረገውን የሕጐች ለውጥና A ዳዲስ ሕጐችን በመከታተል
ራሳቸውን በበቂ መረጃና E ውቀት ማነፅ ይገባቸዋል፡፡ ይህም ማለት የሙያቸውን ኃላፊነት
በሚገባ ለመወጣት የራሳቸውን E ውቀትና ክህሎት ለማሳደግ ተገቢውን ጥረት ማድረግ
A ለባቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ A ቃብያነ ሕግ በወንጀል ፍርድ ሂደት ውስጥ ወጥነት
ባለው መልኩ፣ ገለልተኝነታቸውን በሚያረጋግጥ A ኳኋን፣ E ንዲሁም ያለ A ድሎ
መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል የቀረበላቸውን የወንጀል ምርመራ መዝገብ
በሚመረምሩበት ወቅት ክስ ለመመስረት ወይም ላለመመስረት የሚያደርጉት ውሣኔ ሁሌም
ቢሆን ተገማችነት ሊኖረው የሚገባና ከማስረጃዎች ምዘና A ንፃር የሚያራምዷቸው A ቋሞች
E ርስ በርሳቸው የማይቃረኑ መሆን A ለበት፡፡ ክስ ለመመስረት በሚያደርጉት ውሳኔም
በማናቸውም A ካል ጣልቃ ገብነት ወይም ተፅ E ኖ ሊመሩ A ይገባም፡፡ ይልቁኑ በሕጉ ላይ ብቻ
በመመስረት የቀረበላቸውን ፍሬ ነገር ገለልተኛ ሆኖ መመዘን ነው የሚኖርባቸው፡፡ A ሰራራቸው
ለ A ድሎ A ዊነት በተጨባጭ የተጋለጠ ወይም A ድሎ የሚያደርጉ መስሎ ለሌሎች ሰዎች
መታየት E ንደሌለበት በመገንዘብ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
A ቃብያነ ህግ ሁሌም ቢሆን ተከሳሾች ነፃና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የመዳኘት መብታቸው
E ንዲከበር ተገቢውን ጥረት ማድረግ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተከሳሾች ጠቀሜታ ያለው
ማስረጃ በ E ጃቸው በሚኖርበት ወቅትም E ነዚህኑ ማስረጃዎች በተገቢው የሕግ ሥነሥርዓት
መሰረት ለተከሳሾች መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተለይም ተከሳሾ ወደ ዋናው የፍርድ ሂደት
ከመግባታቸው በፊት በክስ መስማት ደረጃ A ቃብያነ ሕግ የሚያቀርቡባቸውን ማስረጃዎች
ለተከሳሾች ግልጽ ማድረግ (pre trial disclosure of relevant evidences to accused
persons) ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም A ቃብያነ ሕግ ለፍትህና E ውነት ነው መቆም
ያለባቸው E ንጂ ተከሳሹን መርታትን E ንደ ሙያቸው ግብ A ድርገው መመልከት
A ይኖርባቸውምና፡፡

በሌላ በኩል A ቃብያነ ሕግ ሁልጊዜም ቢሆን የሕዝቡን ጥቅም ማስጠበቅ ላይ ትኩረት ሊያደርጉ
ይገባል፡፡ ክስ ለመመስረትም ሆነ ላለመመስረትም ወይም ለፍርድ ቤት የቀረቡ ክሶችን ለማንሳት
በሚወሰኑበት ጊዜ የሕብረተሰቡን ጥቅም ከግምት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
ሰብዓዊ መብቶች E ንዲከበሩና E ንዲጠበቁ ተገቢውን ጥረት ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የሙያ
ግዴታቸውን በሚወጡበት ጊዜ የሰዎች ስብ E ና፣ክብርና መሰረታዊ ነፃነቶች E ንዲጐለብቱ
ብርቱ ጥረት ማድረግ A ለባቸው፡፡43
የሙያ ነጻነት
A ቃብያነ ሕግ ውጤታማና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ E ንዲሁም ያለ A ንዳች A ድሎ
ገለልተኛ ሆነው ሥራቸውን ማከናወን የሚችሉት ከተለያዩ A ቅጣጫዎች ሊመጡ
ከሚችሉ ተጽኖዎች ነፃ ሲሆኑ ብቻ ነው፡፡44 በዚህ ረገድ የ A ቃብያነ ሕግን ሚና
ለመወሰን በተባበሩት መንግሥታት የወጣው መመሪያና በ A ቃብያነ ሕግ ዓለም A ቀፍ ማህበር
የወጣው የተግባር መመሪያ ሁሉም ሀገራት የ A ቃብያነ ሕግን ሙያዊ ነፃነት ለማስጠበቅ ግዴታ
E ንዳለባቸውና ተጨባጭ ርምጃዎችን መውሰድ E ንደሚገባቸው ነው፡፡ መንግሥታት
A ቃብያነ ሕግ ሙያዊ ግዴታቸውን ያለ ማስፈራራት፣ E ክል፣ ትንኮሳ፣ A ግባብ ያልሆነ
ጣልቃ ገብነት፣ ወይም ለምክንያት A ልባ የፍትሃብሄር፣

የወንጀል ወይም ሌላ ሃላፊነት ሳይጋለጡ መወጣት መቻላቸውን ማረጋገጥ A ለባቸው፡፡45


የ A ቃብያነ ሕግ የ A ገልግሎት ሁኔታዎች፣ ደመወዝና የ A ገልግሎት ዘመን
ገለልተኝነታቸውንና ነፃነታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ ነው መደራጀት የሚገባው፡፡46
ተገቢነት ያላቸው የ A ቃብያነ ሕግ የ A ገልግሎት ሁኔታዎች፣ በቂ ደመወዝ፣ E ንዲሁም
A ግባብነት ባለው ጊዜ የ A ገልግሎት ዘመን፣ ጡረታና የጡረታ E ድሜ በሕግ ሊደነገጉ
ወይም በታተሙ ሕጐች ወይም ደንቦች ሊወጡ ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ስርዓቱ
በሚፈቅድበት ሁሉ የ A ቃቤ ሕግ የሥራ E ድገት በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በተመሰረተ
ህግ በተለይም ሙያዊ ብቃትን፣ ችሎታን፣ ጠንካራ ስብ E ናን፣ E ና ልምድን መሰረት
ያደረገ ፍትሃዊና ገለልተኛ የሆነ ስነ ስርዓት ተከትሎ የሚወሰን መሆን A ለበት፡፡47 ከዚሁ
ጋር ተያይዞ A ቃብያነ ህግ የመክሰስ ውሳኔን ለመስጠት ወይም ክስን
ላለመመስረት ለመወሰን ዲስክሬሽን ባላቸው ጊዜ ውሳኔያቸውን በህግና በቀረቡላቸው ፍሬ
ነገሮች ላይ በመመስረት Eንጂ ከየትኛውም A ቅጣጫ በሚመጣ ተፅኖ ወይም ግፊት
መወሰን የለባቸውም፡፡ በተለይም ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት A ቃብያነ ህግ ነፃ መሆን
E ንደሚገባቸው የ A ለም A ቀፍ A ቃብያነ ህግ ማህበር የተግባር መመሪያ A ንቀፅ 2/1/
ያትታል፡፡ ሌሎች የመንግስት ባለስልጣናት ለ A ቃብያነ ህግ ክስ E ንዲመሰርቱ ወይም
E ንዳይመሰርቱ ት E ዛዝ ለመስጠት በህግ ስልጣን ያላቸው E ንደሆነ E ነዚህ የመንግስት
A ካላት ወይም ባለስልጣናት ይህንን ስልጣን ላይ ማዋል የሚገባቸው በግልፅነት፣ ህጋዊ
የስልጣን ገደባቸውን ሳይተላለፉና የ A ቃብያነ ህግን የመወሰን ሙያዊ ነፃነት ሳይገፉ መሆን
ይገባዋል፡፡48

2.3.3. የ A ቃቤ ህግነት ስራን ያለ A ድሎ A ዊነት ማከናወን


A ቃብያነ ህግ ስራቸውን ያለ A ድሎ፣ ፍትሃዊ ግልፅ በሆነ መንገድ E ንዲያከናውኑ
የ A ቃቢያነ ህግን ሚና ለመወሰን በተባበሩት መንግስታት የወጣ መመሪያና የ A ለም A ቀፍ
የ A ቃቢያነ ህግ ማህበር የተግባር መመሪያ ያስገነዝባሉ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የ A ቃቢያነ
ህግን ሚና ለመወሰን የወጣው መመሪያ A ቃቢያነ ህግ በወንጀል ፍርድ ሂደት

ውስጥ ስራቸውን ፍትሃዊ፣ ወጥና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ E ንዲወጡ፣ ለሰብ A ዊ መብቶች
መከበር E ንዲቆሙና ስራቸውን በገለልተኝነት ያለ A ንዳች A ድሎ E ንዲያከናውኑ፣
E ንዲሁም በፖለቲካ፣ በማህበራዊ A ቋም፣ በሃይማኖት፣በዘር፣በባህል ወይም በሌሎች
ምክንያቶች A ድሎ A ዊ ልዩነት ማድረግ A ይገባቸውም፡፡49 A ቃብያነ ህግ በሕጉ መሰረት
ግዴታቸውን ፍትሃዊ በሆነ፣ በ A ንድ ወጥና በቀልጣፋ ሁኔታ መወጣት A ለባቸው፡፡ E ንዲሁም
ሰብ A ዊ ክብርን መጠበቅ፣ ሰብ A ዊ መብቶችን ማክበር፣ በዚህም A ግባብ ያለው የህግ A ካሄድ
E ና E ንከን የሌለው የወንጀል ፍትህ ስርዓት A ሰራር E ንዲኖር ለማስቻል የበኩላቸውን
A ስተዋፅ O ማድረግ A ለባቸው፡፡ ከዚህም ባሻገር ስራቸውን ገለልተኛ በሆነ መልኩ
ማከናወን E ና ከማናቸውም የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ሃይማኖታዊ፣የዘር፣ባህላዊ ፣የጾታ፣
ወይም ሌላ ማናቸውም A ይነት A ድሎ ነፃ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

የህዝብን ጥቅም መጠበቅ፣በተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ መመስረት፣ የተጠርጣሪውንና የተጠቂውን


ሁኔታ በ A ግባቡ ከግምት ማስገባት፣ ለተጠርጣሪው ጠቀሙም A ልጠቀሙም ማናቸውንም
A ግባብ ያላቸውን ሁኔታዎች ማስተዋል A ስፈላጊ ነው፡፡ ገለልተኛ የሆነ ምርመራ ክሱ መሰረተ
ቢስ መሆኑን ሲያሳይ A ቃብያነ ህግ ክስ A ይጀምሩም፡፡ A ይቀጥሉም፣ ወይም ሂደቱ
E ንዲቆም የተቻላቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡50 A ቃብያነ ህግ ክስ የሚመሰርቱት የቀረበላቸው
ማስረጃ A ጥጋቢና A ሳማኝ E ንዲሁም ተዓማኒነት ያለው E ንደሆነ ብቻ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር
ተያያዞ የክሱ ማስረጃ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ የተሰበሰበ E ንደሆነ ወይም የተከሳሹን
መሰረታዊ መብቶች በመጣስ የተሰበሰበ ማስረጃ E ንደሆነ የዚህ A ይነቱ ማስረጃ ለሚቀርበው
ክስ በማስረጃነት E ንዲያገለግል ማድረግ የማይገባ ሲሆን የተከሳሹን መብቶች በመጣስ
ማስረጃውን ህገ ወጥ በሆነ መንገድ E ንዲሰበስብ ባደረጉ A ካላት ላይ ተገቢውን ማጣራት
ተካሂዶ ለህግ E ንዲቀርቡ ማድረግ የ A ቃብያነ ህግ ግዴታ ነው፡፡ ይህም ማለት A ቃቢያነ ህገ
ወጥ በሆነ መንገድ የተጠርጣሪውን መብቶች በብርቱ በሚጥስ በተለይም ማሰቃየት፣ጭካኔ
የተሞላበት፣ Iሰብ A ዊ፣ ወይም A ዋራጅ A ያያዝን ወይም ቅጣትን ወይም ሌላ
የሰብ A ዊ መብት

መጣስን በመጠቀም E ንደተገኘ የሚያውቁትን፣ ወይም በበቂ ምክንያት ይህ ስለመሆኑ


የሚያምኑበትን በተጠርጣሪ ላይ የቀረበ ማስረጃ በድርጊቱ ፈፃሚዎች ላይ ካልሆነ በቀር በማንም
ሰው ላይ ላለመጠቀም መወሰን፣ ወይም ፍርድ ቤቱን ስለሁኔታው ማስረዳት E ንዲሁም
E ንደዚህ ያለውን መንገድ የተጠቀሙ ሁሉ ለፍርድ E ንዲቀርቡ A ስፈላጊ የሆኑትን
E ርምጃዎች ሁሉ መውሰድ A ለባቸው፡፡51
A ቃቢያነ ህግ ስራቸውን ያለ A ድሎ ለማከናወን ለሚከተሉት ነጥቦች ትኩረት ማድረግ
ይኖርባቸዋል፡፡
በግለሰቦች ወይም በተወሰኑ ቡድኖች ወይም በሚዲያና በህብረተሰብ ግፊት ስር ባለመውደቅ
የህዝብን ጥቅም መጠበቅ፣
ለተጠርጣሪው ጠቀሜታ ያላቸውም ሆነ A ልሆኑ A ግባብ ያላቸውን ሁኔታዎች(
All relevant circumstances)
በ A ካባቢው ህግ የተፈቀደ E ንደሆነ ወይም ፍትሃዊ የፍርድ ሂደት E ንዲኖር
የሚያስፈልግ ከሆነ ደግሞ የተጠርጣሪውን ንፅህና ወይም ጥፋተኝነት በሚመለከት
ተገቢው ምርመራ E ንዲካሄድና የምርመራውም ውጤት ይፋ E ንዲደረግ የማድረግ
በህግና ርት E መሰረት በተከሳሹ፣ በተጎጂውና በህብረተሰቡ መካከል ፍርድ ቤቶች
ትክክለኛውን ፍትህ E ንዲያደርጉና E ውነትን E ንዲያፈላልጉ ተገቢውን ጥረት
ማድረግና ፍርድ ቤቶችን መርዳት ነው፡፡

2.3.4. A ቃቢያነ ህጎች በወንጀል የፍርድ ሂደት ሊኖራቸው የሚገባ ሚና


የዓቃቤ ህግ ስራ ግልፅ በሆነ መንገድ ከዳኝነት ስራ መለየት ያለበት ሲሆን ክስ
መመስረትን ፣በህግ በተፈቀደ ወይም በ A ካባቢው A ሰራር የተለመደ በሆነ ጊዜ ደግሞ
የወንጀል ምርመራን፣ የነዚህ ምርመራዎችን ህጋዊነት መቆጣጠርን፣ የፍርድ ቤቶች ውሳኔ
A ፈፃፀምን መቆጣጠርን E ንዲሁም የህዝብ ጥቅም በመወከል የሚፈፀሙ ሌሎች
ስራዎችን ጨምሮ A ቃብያነ ህግ በወንጀል የፍርድ ሂደት ውስጥ ንቁ ሚና መጫወት A ለባቸው፡፡
52
የወንጀል ምርመራን በሚቆጣጠሩበትና በሚመሩበት ወቅትመርማሪ
A ካላት ህጉን A ክብረው E ንዲሁም የተጠርጣሪውን ሰብ A ዊ መብቶች ባረጋገጠ A ኳኋን

ምርመራውን E ንዲያከናውኑ ክትትል ማድረግ የሚገባቸው ሲሆን ለመርማሪ A ካላት ምክር


በሚለግሱበት ወቅትም ገለልተኝነትና ፍትሃዊነትን ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ክስ መመስረት
ያለባቸው ደግሞ በቂና A ስተማማኝ ማስረጃ ሲኖራቸው ብቻ መሆን A ለበት፡፡ A ቃብያነ ህግ
የወንጀል ፍርድ ሂደትም በተቻለው መጠን ሁሉ ፍትሃዊና ግልፅነት ያለው E ንዲሆን
የበኩላቸውን A ስተዋፅ O ማድረግ A ለባቸው፡፡ በህግ በተፈቀደላቸው ጊዜ ወይም
የ A ካባቢው A ሰራር ልምድ በሚፈቅድላቸው ወቅት የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን A ፈፃፀም
በሚቆጣጠሩበት ጊዜ ወይም ሌሎች ተግባራትን በሚያከናውኑበት ጊዜ የህዝብ ጥቅም መጠበቅ
ቀዳሚ A ላማቸው ሊያደርጉ ይገባል፡፡
ከዚሁ በተጨማሪ A ቃብያን ህግ በህዝብ ባለስልጣናት ለሚፈፀሙ በተለይም ሙስና፣ በስልጣን
A ላ A ግባብ መገልገል፣ ከባድ የሰብ A ዊ መብቶች ረገጣ፣ E ና ሌሎችም በ A ለም A ቀፍ ህግ
ለተደነገጉ ወንጀሎች የክስ ሂደት ተገቢውን ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡53 የግል ጥቅማቸው
በሚነካበት ጊዜ የተጠቂዎችን A መለካከቶች ከግምት ማስገባት፣ በወንጀልና በስልጣን
A ላ A ግባብ መገልግል ተጠቂዎች መሰረታዊ የፍትህ መርሆዎች ድንጋጌ መሰረት
ተጠቂዎች ስለመብቶቻቸው E ንዲያውቁ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የተጠቂዎች መብት
E ንዲከበርም ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው መስራት የሙያ ግዴታቸው ነው ፡፡ በሌላ A ነጋገር
A ቃብያነ ህግ ስራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ በስራ A ጋጣሚ E ጃቸው የገባውን ሚስጥር
የመጠበቅ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን የወንጀል ተጠቂዎች ሆነ የምስክሮች መብት መከበሩን
ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል፡፡
በተለይም A ቃብያነ ህግ የሚከተሉት ተግባራት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡
በነርሱ ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን ካለ ቀጥሎ ወደ ሚገኙት ባለስልጣናት ወይም የሚቻል
ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ቅሬታውን የማቅረብ መብት E ንዳለው የማሳወቅ ግዴታ፣( seek
to ensure that any aggrieved party is informed of the right of
recourse to some higher authority) court, where that is possible)
የተከሳሹን መብቶች ከፍርድ ቤቶችና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው A ካላት ጋር
በመተባበር E ንዲከበር ብርቱ ጥረት ማድረግ፣(safeguard the right of the
accused in cooperation with the court and other relevant agencies)

በህግ ወይም ፍትሃዊ ዳኝነት ማስፈን በሚጠይቀው A ግባብ ለተከሳሹ የሚጠቅምም


ሆነ የማይጠቅም ማስረጃ በተቻለ ፍጥነት ይፋ ማድረግ፣(disclose to the
accused relevant prejudicial and beneficial information as soon as
reasonably possible, in accordance with the law or the requirements of
a fair trial)

ክስ በሚመሰርትበት ጊዜ A ቃብያነ ህግ ሊጠቀሙበት ያቀዱትን ማስረጃ ህጋዊነት በሚገባ


መፈተሽ፣Examine proposed evidence to ascertain if it has been
lawfully or constitutionally obtained)
በህገ ወጥ መንገድም በተለይም የተጠርጣሪውን ሰብ A ዊ መብቶች በመጣስና
በተጠርጣሪው ላይ ጭካኔ የተሞላበትና A ዋራጅ የሆነ A ያያዝን በመፈፀም የተሰበሰበ
ማስረጃ ለመሆኑ በቂ ጥርጣሬ ካለ A ቃብያነ ህግ E ንዲህ A ይነቱን ማስረጃ ለክስ
A መሰራረት መጠቀም A ይኖርባቸውም፡፡(refuse to use evidence reasonably
believed to have been obtained through recourse to un lawful
methods which constitute a grave violation of the suspect’s human
rights and particularly methods which constitute torture or cruel
treatment)
E ንደዚህ ያለውን መንገድ በመጠቀም ማስረጃን በህገ ወጥ መልኩ ያሰባሰቡ መርማሪ
A ካላት ካሉ በነዚሁ ላይ ተገቢውን E ርምጃ E ንዲወሰድ ማድረግ ነው፡፡

ከላይ ከተገለፁት ተግባራት ባሻገር A ቃብያነ ህግ ብሄራዊ ህግን መሰረት በማድረግ ክስን
ለመተው ያለምንም ቅድመ ሁኔታም ሆነ በቅድመ ሁኔታ ለማቋረጥ፣ ወይም ከመደበኛው
የፍትህ ስርዓት ጉዳዮችን በ A ማራጭ E ልባት ወደሚያገኙበት መድረክ ለመምራት
ተገቢውን ትኩረት መስጠት A ለባቸው፡፡ ይህንን ሲያደርጉ ግን የተጠርጣሪዎቹንና
የተጠቂዎቹን መብቶች ሙሉ በሙሉ ማክበር ይገባቸዋል፡፡ ለዚህም ሲባል የፍርድ ቤቶች
የስራ ጫና ለማቃለል ብቻ ሳይሆን ቅድመ ክስ፣ E ስር
፣መከሰስ፣ጥፋተኛ በመባሉ የሚያስከትለው የመገለል ስሜትና E ስር ሊያስከትል
የሚችለውን ፅኑ ውጤት ለማስቀረት መንግስታት በተቻላቸው A ቅም A ማራጮች
E ንዲያፈላልጉ ግፊት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡54

2.3.5. ከሌሎች የፍትህ A ካላት ጋር በቀና የትብብር መንፈስ ተቀናጅቶ


ስለመስራት
የክስ ሂደትን ፍትሃዊነትና ውጤታማነት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ A ቃብያነ ህግ በተቻላቸው
A ቅም ከፖሊስ፣ ፍርድ ቤቶች፣የህግ ባለሙያዎች፣ተከላካይ ጠበቆችና ሌሎች የመንግስት
A ካላት ወይም ተቋማት ጋር ለመተባበር መሞከር A ለባቸው፡፡55 A ቃብያነ ህግ በሌሎች
ሀገሮች ለሚገኙ የ A ቃብያነ ህግ ተቋማትና የሙያ A ጋሮቻቸው ጋርም ተባብረው መስራት
E ንደሚጠበቅባቸው ተመልክቷል፡፡

ከሌሎች A ካላት ጋር A ቃብያነ ህግ በሚኖራቸው የስራ ግንኙነት የሙያ ነፃነታቸው በሚገባ


E ንዲጠበቅ የበኩላቸውን ጥረት ማድረግ ይጠቅባቸዋል፡፡
በተለይም የ A ቃቤ ህግነት ስራቸውን ከስራ A ስፈፃሚ የመንግስት ተቋማትና ከህግ
A ውጪው ክፍል ተፅ E ኖ ሳይደረግባቸው በህግና በህጉ መሰረት ብቻ ነው ማከናወን ያለባቸው፡፡
56
በርግጥ በብዙ ሀገሮች የ A ቃቢያነ ህግ ተቋማት በስራ A ስፈፃሚነት የመንግስት A ካል ስር
የተደራጁና ተጠሪነታቸውም ለነዚሁ A ካል ሲሆን የተባበሩት መንግስታት የ A ቃብያነ ህግ ሚናን
በተመለከተ የወጣው መመሪያም ሆነ የ A ለም A ቀፍ A ቃብያነ ህግ ማህበር የተግባር መመሪያ
ይህንን A ደረጃጀት መቀየር ላይ ሳይሆን ትኩረቱ A ቃብያነ ህግ ከስራ A ስፈፃሚ የመንግስት
A ካል A ንድ ጉዳይ ላይ ክስ E ንዳይቀርብ የሚያስተላልፈው ት E ዛዝ ገደብ ሊበጅለት
E ንደሚገባ ነው የ A ውሮፓ ህብረት A ስተያየቶች የሚጠቁሙት፡፡

የስራ A ስፈፃሚው የመንግስት A ካላት E ንዲህ A ይነቱን ስልጣን A ልፎ A ልፎ ብቻ


መጠቀም E ንደሚገባቸውና E ንዲህ በሚደረግበት ጊዜ በግልፅነት በታወቁ መስፈርቶች ላይ
መመስረት ወሳኝ E ንደሆነ ነው፡፡57

2.3.6. ስልጣንና ተሰሚነት


A ቃብያነ ህግ ስራቸውን በፍፁም ነፃነትና ስለ A ቃቤ ህግነት በወጡ A ለም
A ቀፍ መርሆዎች መሰረት E ንዲያከናውኑ ከሌሎች የመንግስት A ካላት ጣልቃ
ገብነት መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የ A ቃቤ ህግነት ስልጣናቸውንም በህግ A ግባብ
ለህብረተሰቡ ጥቅምን በሚያስገኝ መልኩ ነው በትክክል ስራ ላይ ማዋል
የሚያስፈልጋቸው ፡፡ በተለይም የ A ቃቤ ህግነት ስልጣናቸውን ተግባራዊ
በሚያደርጉበት ወቅት የሚከተሉት ጥበቃዎች ከመንግስት ሊደረግላቸው ይገባል፡፡58
የሙያ ግዴታቸውን ያለ ማስፈራራት፣ E ንቅፋት፣ወከባ ፣A ግባብ ያልሆነ ጣልቃ
ገብነት ለምክንያት A ልባ የፍትሃብሄር ፣ወንጀል ወይም ሌላ ኃላፊነት ሳይጋለጡ
E ንዲወጡ ዋስትና መስጠት፣
A ቃብያነ ህግ የስራ ግዴታቸውን በሚወጡበት ወቅት የግል ደህንነታቸው A ደጋ ላይ
በወደቀ ጊዜ ከመንግስት ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው የ A ካላዊ ደህንነት ጥበቃን
የማግኘት
ከሚያከናውኑት ቁልፍ ተግባርና ኃላፊነት ጋር የሚመጣጠን የ A ገልግሎት
ሁኔታ፣ተመጣጣኝ ክፍያና በቂ ደመወዝ E ንዲሁም የ A ገልግሎት ዘመን
በተቻለ መጠን ሁሉ የ A ቃብያነ ህግ ምልመላና የስራ E ድገት በተጨባጭ
ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ E ንዲሆን ሙያዊ ብቃትን ፣ችሎታን፣ ጠንካራ
ስብ E ናንና ልምድን መሰረት ያደረገ ሆኖ ፍትሃዊና ገለልተኛ የሆነ ስርዓት(Fair
and impartial Procedure0 ተከትሎ E ንዲወሰን
A ቃብያነ ህግ ግልፅ በሆነ መንገድ ከሙያዊ ደረጃቸው ወሰን ዉጪ የሆነ
Iስነምግባራዊ ድርጊት ፈፅመዋል የሚል ቅሬታ በቀረበባቸው ጊዜ የዲስፒሊን
ክስ ሂደቱን በፍጥነትና ፍትሃዊ በሆነ ሁኔታ A ግባብ ባላቸው ስነ ስርዓቶች መሰረት
E ንዲታይ፣
በዲስፒሊን ክስ ሂደት A ቃብያነ ህግ ገለልተኛ በሆነ መንገድ የመሰማትና ፍትሃዊ
ውሳኔ የማገኘት መብታቸውን ሊረጋገጥላቸው E ንደሚገባ፣ በ A ቃቢያነ ህግ ላይ
የሚደረግ የዲስፒሊን የክስ ሂደት ተጨባጭ ግምገማና ውሳኔ E ንዲኖረው ማድረግ
ተገቢነት ያለው ሲሆን ሂደቱም በህግ፣ በሙያዊ ስነምግባርና በሌሎች ተቀባይነት ባገኙ
የኖሩ ደንቦች ላይ የተመሰረተ መሆን ይገባዋል፡፡
E ንደ ሌሎች ዜጎች ሁሉ A ቃብያነ ህግ ሃሳብን የመግለፅ፣የ E ምነት፣የመደራጀትና
የመሰብሰብ ነፃነት A ላቸው፡፡ በተለይም ህግን፣ የፍትህ A ስተዳደርን፣ የሰብ A ዊ
መብቶችን መስፋፋትና መጠበቅን በሚመለከቱ ህዝባዊ ሰብሰባዎች የመካፈል
መብት A ላቸው፡፡ E ነዚህን መብቶች በስራ ላይ በሚያውሉበት ጊዜ ሁሉ
A ቃብያነ ህግ ራሳቸውን ለህጉና በሙያቸው ለታወቁ መመዘኛዎችና ስርዓቶች
ተገዢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ A ቃብያነ ህግ የሙያ
ማህበራቸውን ወይም ሌሎች ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁላቸው ድርጅቶችን
በማቋቋምና A ባል በመሆን ሙያዊ ስልጠናቸውን ለማስፋፋትና A ቋማቸውን
ለመጠበቅ የምንቀሳቀስ መብት A ላቸው፡፡

2.3.7. A ቃቤ ህጎች A ጠቃላይ በግል ኑሮ A ቸው ሊያከብሩት የሚገባ ስነምግባር

1. A ቃቤህግ ሰብ A ዊ መብቶችና ነጻነቶችን የጣሱ ሰዎችን ለፍርድ የሚያቀርብ


ከመሆኑ A ንጻር E ሱም E ራሱ በድርጊቱ ሰብ A ዊ መብቶችንና ነጻነቶችን
የሚያከበርና A ር A ያ መሆን A ለበት፡፡
2. A ቃቤ ህግ በግል A ኗኗሩ ተቋሙን ጥያቄ ውስጥ ከሚከት A ኗኗር መጠበቅ A ለበት፡፡
ተቋሙ ተገቢውን ክብርና ድጋፍ የሚያገኘው A ቃቤ ህጉ በግል A ኗኗሩ በሚያሳየው
ባህርይ ነው፡፡
3. A ቃቤ ህግ የጥቅም ግጭት በሚፈጥር ስራ ውስጥ መግባት የለበትም፡፡ ከሙያው ጋር
የሚቃረን ተግባር ተሰማርቶ ገቢን ለማግኘት መሞከር የለበትም፡፡
4. A ቃቤ ህግ የፍርድ ቤቱን ነጻነት መቀበልና መጠበቅ A ለበት፡፡ የፍርድ ቤትን ውሳኔ
ሊቃወመው የሚችለው ይግባኝ በማቅረብ ብቻ E ንጂ በ A ደባባይ በመተቸት
A ይደለም፡፡

መወያያ ጥያቄዎች
1. A ንድ የምርመራ መዝገብ ተጠናቆ የመጣለት A ቃቤ ህግ የተሰባሰቡትን ማስረጃዎች
ሲመረምር A ንዳንዱ ተከሳሽን የሚጠቅም ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ስለሆነም ተከሳሽን
የሚጠቅመውን ማስረጃ በማስቀረት በተከሳሽ ላይ ክሱን ለማስረዳት የሚጠቅመውን
ማስረጃ ብቻ A ያይዞ ክስ ይመሰርታል፡፡ A ቃቤ ህግ ተከሳሽን የሚጠቅም ማስረጃ
ለተከሳሹ ማሳወቅና መስጠት ይገባው ነበር፡፡ ይህንን ባለማድረጉ የሙያ ስነምግባሩን
A ላከበረም ይባላል?
2. A ቃቤ ህግ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ማስረጃ መኖሩን E ያወቀ ማስረጃውን ይዞ ፍርድ
ቤት ቀረበ፡፡ ይህ የ A ቃቤ ህግ ድርጊት ሊያስጠይቀው ይገባል ወይ?
3. A ቃቤ ህግ በሚመረምረው የምርመራ መዝገብ በቂ ማስረጃ E ንደሌለው በሚያውቀው
መዝገብ ላይ ክስ መስርተህ ተከራከር የሚል የበላይ ት E ዛዝ ቢመጣ ምን ማድረግ
A ለበት? E ንዲህ A ይነት ግንኙነት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ ምን
A ይነት ሲስተም መዘርጋት ይኖርበታል?

4. A ቃቤ ህግ በ A ንድ የወንጀል ድርጊት ክስ በመመስረቱ፣ የወንጀል ድርጊቱ ሰለባ የሆኑ


ሰዎች በድርጊቱ በመደሰት ከፍ ያለ ስጦታ ያቀርቡለታል፡፡ E ርስዎ A ቃቤ ህግ
ቢሆኑ ስጦታውን ይቀበላሉ? ለምን?የማይቀበሉ ከሆነስ; ለምን?

5. A ቃቤ ህግ ከመርማሪ የመጣለትን መዝገብ ሲመለከት ወንጀሉ የተፈጸመ መሆኑን


ያመለከታል፡፡ ይሁንና A ቃቤ ህግ በግሉ E ንደሚያውቀው ተከሳሽ ሆኖ የቀረበው
ወንጀሉን E ንዳልፈጸመ ያውቃል፡፡ ምን ማድረግ A ለበት? ጉዳዩን ስለማውቀው ብሎ
መዝገቡን መዝጋት ነው? ወይስ በጉዳዩ ላይ E ኔ ክስ A ልመሰርትም ብሎ መተው
ነው? ለምን?

10 ስለ A ቃቤ ህግ ተጠሪነት
1. A ቃቤያነ ህግ ተጠሪነታቸው ለሚኒስትሩ ይሆናል፡፡
2. በዚህ A ንቀጽ ን U ስ A ንቀጽ 1 የተደነገገው E ንደተጠበቀ ሆኖ በማንኛውም ደረጃ
የሚገኝ A ቃቤ ህግ ከ E ርሱ ለሚቀጥለው የበላይ ሀላፊ A ቃቤ ህግ ተጠሪ ይሆናል፡፡

A ንቀጽ 11 ቃለመሀላ
‹Eኔ --------- ለሀገሬ ታማኝ በመሆን የIትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ህገመንግስትንና ሌሎች ህጎችን ላከብርና ላስከበር በፌዴራሉ መንግስት የወጡና ወደፊት
የሚወጡ ህጎችን በማስፈጸም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ልሰራ የስራ ድርሻዬን ህግ
በሚደነግገው መሰረት በመፈጸም የሰዎችን ክብርና ሰብ A ዊ መብት ላከብርና ላስጠብቅ የግል
ጥቅም ሳልፈልግ ማንንም በመውደድ በመጥላት ወይም በሌላ በማንኛውም ምክንያት A ድልዎ
ሳላደርግ ማንኛውንም A ይነት ተጽ E ኖ ሳልፈራ በሃቀኝነት በቅንነትና በትጋት ሀላፊነቴን
ለመወጣት ቃል E ገባለሁ›

A ንቀጽ 16 ከመደበኛ የስራ ሰ A ት በላይ መስራት


1. ስራው የሚመለከተው የበላይ ሀላፊ በ A ዘዘ ጊዜ ማንኛውም A ቃቤ ህግ ከመደበኛው
የስራ ሰ A ት በላይ መስራት ግዴታው ነው፡፡

ስለ A ቃቤያነ ህግ ግዴታ
A ንቀጽ 61 ስለታማኝነት
ማንኛውም A ቃቤ ህግ መላ ጉልበቱንና ችሎታውን በታማኝነት ለመንግስትና ለህዝብ
A ገልግሎት ጥቅም ማዋል A ለበት፡፡

A ንቀጽ 62 ስለ E ያንዳንዱ A ቃቤ ህግ ጠባይ


1. ማንኛውም A ቃቤ ህግ የህዝብን A ክብሮትና E ምነት E ንዲያገኝ በመስሪያ ቤቱም
ሆነ ከመስሪያ ቤቱ ውጭ በማናቸውም ጊዜ መልካም ጠባይና ስነምግባር E ንዲኖረው
ያስፈልጋል፡፡
2. በማንኛውም ጊዜ የሙያውን ክብር ለማስጠበቅ የሚያስፈልገውን ሁሉ A ሟልቶ
መገኘት A ለበት፡፡
A ንቀጽ 63. ስለታዛዥነት
1. ማንኛውም A ቃቤ ህግ ስራውን ባለው ከፍተኛ E ውቀትና ችሎታ መፈጸም
A ለበት፡፡ የተመደበበትን መደበኛ ስራና ሌላውንም ተመሳሳይ ስራ መፈጸም ግዴታው
ነው፡፡
2. A ቃቤ ህጉ ከበላይ ሀላፊው የሚሰጠው ት E ዛዝ በግልጽ ከህግ ውጭ ካልሆነ በቀር
E ንደት E ዛዙ መፈጸም A ለበት፡፡ በማንኛውም A ኳኋን የበላይ A ቃቤ ህግ
ለሚሰጠው ት E ዛዝ ህጋዊነት ሀላፊ ነው፡፡

A ንቀጽ 64. A ቃቤ ህግ ከህዝብ ጋር ስላለው ግንኙነት


1. A ቃቤ ህግ የሚፈጽማቸው ተግባሮች በጠቅላለው የመላውን ህዝብ ጥቅም
የሚመለከቱ መሆናቸውን ምን ጊዜም መዘንጋት የለበትም፡፡
2. A ቃቤ ህግ የሰዎችን ሰብ A ዊ መብትና ክብር መንካት የለበትም፡፡

A ንቀጽ 65 ምስጢር ስለመጠበቅ


ማንኛውም A ቃቤ ህግ
1. መረጃው ተራ ወይም በህዝብ ዘንድ የታወቀ ካልሆነ ወይም መደበኛ ስራውን በህጋዊ
መንገድ ለመፈጸም A ስፈላጊ ካልሆነ በቀር በስራው A ጋጣሚ ወይም ምክንያት ወይም
በሌላ A ኳኋን ያገኘውን መረጃ ለማናቸውም ሰው መግለጽ የለበትም፡፡

2. ስልጣን ባለው ሀላፊ በ A ግባቡ ካልታዘዘ በቀር በ A ሰራር ምስጢር የተባሉትን መረጃዎች
ቃለጉባኤዎች የስራ E ቅዶችና E ነዚህን የመሳሰሉ ምስጢራዊ ጉዳዮች ሁሉ
በስራው ላይ ሆነ ከስራ ውጪ ጉዳዩን E ንዲያውቀው በደንቡ ለተፈቀደደለት ሰው
ካልሆነ በቀር ለሌላ ማናቸውም ሰው መግለጽ የለበትም፡፡

A ንቀጽ 66 ገንዘብ ስለመበደር


1. A ዘውትሮ ገንዘብ መበደር ክልክል ነው፡፡

2. A ቃቤ ህግ በስራው ምክንያት ከሚያጋጥመው ማናቸውም ሰው ገንዘብ መበደር


ወይም ለመበደር መሞከር ፍጹም ክልክል ነው፡፡
A ንቀጽ 67 ስለስጦታዎች
ማንኛውም A ቃቤ ህግ ከስራወ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ስለሰጠው ወይም ወደፊት ስለሚሰጠው
A ገልግሎት ከማናቸውም ሰው ማናቸውም A ይነት ስጦታ ወይም ዋጋ መጠየቅ ወይም
መቀበል የለበትም፡፡

A ንቀጽ 68 በመንግስት ስራና በግል ጉዳዮች ወይም ጥቅሞች መካከል ስለሚፈጠር ግጭት
1. ማናቸውም A ቃቤ ህግ የራሱ የዘመዶቹ ወይም የወዳጆቹ የግል ጉዳይ ወይም ጥቅም
ከስራው ወይም በስራወ ምክንያት ከያዘው የህዝብ ወይም የግለሰብ ጉዳይ ጋር የሚጋጭ
ሆኖ ሲገኝ ይህንነ ችግር ለበላይ ሀላፊው ወዲያውኑ በማሳወቅ ጉዳዩ በሌላ A ቃቤ
ህግ E ንዲታይ ማመልከት A ለበት፡፡

2. ጉዳዩ የቀረበለት የበላይ A ቃቤ ህግም A ስፈላጊ የመሰለውን ውሳኔ መስጠት


A ለበት፡፡

A ንቀጽ 69 ስለግል ደብዳቤዎች


1. A ቃቤያነ ህግ በመስሪያ ቤቱ A ድራሻ የግል ደብዳቤ ሊጽፉ ወይም ከሌላ ሊጻፍላቸው
ይችላለ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን የመላላክ ወጪ ጉዳዩ የሚመለከተው A ቃቤ
ህግ መክፈል A ለበት፡፡

2. በመስሪያ ቤቱ A ድራሻ የተላከ የማንኛውም A ቃቤ ህግ ደብዳቤ ጥቅል ወይም


E ቃ ቢጠፋ መስሪያ ቤቱ በሀላፊነት A ይጠየቅም፡፡

A ንቀጽ 70 በመስሪያ ቤቱ መገልገያዎች ስለመጠቀም


A ቃቤያነ ህግ ስራቸውን በሚገባ ለመፈጸም ያህል ብቻ በመስሪያቤቱ ልዩ ልዩ መገልገያዎች
መጠቀም ይችላሉ፡፡

A ንቀጽ 71. ለሌሎች መስሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ስለመስራት


1. ማንኛውም A ቃቤ ህግ
ሀ. በመደበኛ የስራ ሰ A ት መላ ጉልበቱን ችሎታውንና A ሳቡን በደመወዝ በተመደበበት
የመስሪያ ቤቱ ስራ ላይ ማዋል A ለበት፡፡ ሆኖም A ቃቤ ህጉ በ A ግባቡ ሲታዘዝ
ለሌላ መንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግስት ልማት ድርጅት መስራት A ለበት፡፡
ለ. ለመስሪያ ቤቱ የሚያበረክተውን A ገልግሎት የሚያጓድል ወይም ለተሰጠው ስራና
ሀላፊነት ተቃራኒ የሆነ ወይም ከስራውና ከሀላፊነቱ ወይም ከሙያ ስነምግባር ጋር
የማይጣጣም ማናቸውንም የውጭ ስራ ሊሰራ A ይችልም፡፡

2. በዚህ A ንቀጽ ን U ስ A ንቀጽ 1 የተደነገገው E ንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም A ቃቤ


ህግ የውጭ ስራ ለመስራት በቅድሚያ የሚኒስትሩን ፈቃድ ማግኘት A ለበት፡፡

A ንቀጽ 75 የዲሲፕሊን ጥፋቶች


1. የሚከተሉት ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋቶች ናቸው፡፡
ሀ. ጉቦ መቀበል ወይም E ንዲሰጠው መጠየቅ
ለ. ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለራስ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ
በ A ማላጅ መስራት
ሐ. ራስን ወይም ሶስተኛ ወገንን ለመጥቀም በጽሁፍ የሰፈረውን መረጃ ሆነ ብሎ
ወደሀሰተኝነት መለወጥ
መ. ከስራ ጋር ግንኙነት ካላቸው ሰዎች ገንዘብ መበደር
ሠ. A ግባብ ያለውን መረጃ ወይም ፍሬነገር ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት
ለሚመለከተው ባለማሳወቅ ወይም በመደቡት ውሳኔውን የሚያዛባ ሁኔታ መፍጠር
ረ. ያለበቂ ምክንያት ስራን በማዘግየት ባለጉዳይን ማጉላላት
ሰ. AE ምሮን በሚያደነዝዝ ወይም ሱስ በሚያሲዝ ህገወጥ E ጽ መጠቀም
ሸ. ሰክሮ በስራ ላይ መገኘት ወይም በ A ደባባይ በመታየት የሙያውን ስነምግባርና
የመስሪያ ቤቱን ክብር ማጉደፍ
ቀ. ያለበቂ ምክንያት ወይም ያለፈቃድ A ዘውትሮ ከስራ መቅረት
በ. በስራ ቦታ ላይ ለሞራልና ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነ ድርጊት መፈጸም ቸ.
ሆነ ብሎ ወይም በከባድ ቸልተኝነት በመስሪያ ቤቱ ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት
ማድረስ
ኀ. ሌሎች በተመሳሳይ ደረጃ የሚታዩ ከባድ ጥፋቶች
ነ. በጽሁፍ ወይም በቃል ከመስሪያ ቤቱ ወይም ከበላይ ሀላፊው የተሰጠውን
ግልጽና ህጋዊ ት E ዛዝ A ለመቀበል ወይም ተግባራዊ A ለማድረግ

2. የሚከተሉት ቀላል የዲሲፕሊን ጥፋቶች ናቸው፡፡


ሀ. በስራው ላይ ተገቢ ጥረትና ትጋት A ለማሳየት
ለ. ከስራ ባልደረቦች ጋር በመግባባት ተባብሮ መስራት ባለመቻል በስራ ሂደት ላይ
E ንቅፋት መሆን ወይም
ሐ. A ዘውትሮ መበደር
መ. ሌሎች በተመሳሳይ ደረጃ የሚታዩ ቀላል ጥፋቶችን መፈጸም

You might also like