You are on page 1of 21

በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የአብዲ ቦሪ መረዳጃ ማህበር

መተዳደሪያ ደንብ

መስከረም 01/2016 ዓ/ም


ጋምቤላ፣

በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የአብዲ ቦሪ


መረዳጃ ማህበር መተዳደሪያ ደንብ
ማውጫ
ይዘት ገጽ

1. መግቢያ ............................................................................................................................ 2

2. የመረዳጃ ማህበሩ ስም፣አድራሻ፣ ትርጉምና ዓላማ ………………………………………………. 3

3. የመረዳጃ ማህበሩ ዓላማ ……………………………………………………………….……… 5

4. የመረዳጃ ማህበሩ አባልነት ፣ የአባላት መብት፣ ግደታና እርዳታ ………………..…………6

5. አባል የስብሰባ ጊዜ በተመለከተ …………………………………………………………….… 7

6. የመረዳጃ ማህበሩ የአባል መብት ………………………………………………………………7

7. የመረዳጃ ማህበሩ አባላት ግዴታ ……………………………………………………………. 9

8. ስለ ማህበሩ መዋጮ አሰባሰብና አስተዳደር በተመለከተ ……………………………………11

9. ከመዋጮ ውጭ ሌሎች ግዴታዎች ……………………………………………………………11

10. የመረዳጃ ዕድሩ የገቢ ምንጭ፣የገንዘብና ንብረት አያያዝና አጠቃቀም ………………………12

11. መረዳጃ ማህበሩ ገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም፣ ………………………… …………….…..12

12. የመረዳጃ ማህበሩ ንብረት አያያዝና አጠቃቀም …………………………...…………………12

13. የመረዳጃ ማህበሩ አደረጃጀት ………………………………………………………………….14

14. የመረዳጃ ማህበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር ……………………………………….14

15. የአባላቱ የገቢ ምንጭ ስለማሳደግ ………………………………………..……………………15

16. የመረዳጃ ማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ሥልጣንና ተግባር …………………………..15

17. ሥነ ሥርዓት እና መቀጮ --------------------------------------------------------------------------------17

18. ደንቡ ስለሚፀናበት የማሻሻያ ጊዜ……………………………………………………………..18

19. የማህበሩ ህጋዊነት እና የደንብ መሻሻል …………………………………………………. 19

መግቢያ

የማህበሩ አስፈላጊነት እና ትኩረት ማህበሩ ለመመስረት መነሻ የሆነው ሀሳብ የመኖሪያ አካባቢን መሰረት አድርጎ
እርስ በእርስ ለመረዳዳት ያቋቋሙት ማኅበራዊ ተቋም በመሆኑ መልካም ግንኙነት ለመፍጠር፣ለማዳበርና የመረዳዳት ባህልን ለማዳበር፣
መረዳጃ ማህበሩም በነዋሪዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት ሳያደርግ በጋራ መልማትንና ማደግን እንዲሁም የነዋሪውን አብሮ

1|Page
የመኖር እሴትን ማዳበር፣ በአባላት ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ችግሮችን እና አደጋዎችን በጋራ ለማቃለል እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

በደስታና በሌሎች ሁኔታዎች ላይ በመሳተፍ የደስታው ተካፋይ መሆን፣ ከደጋ በተለያየ ምክንያት ወደ ጋምቤላ የመጣን
ሰዎች ስንታመም እንዲሁም ዘመድ ስሞትብን አስክሬን ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ከፍተኛ ችግር እያጋጠመን
በመሆኑ ነው፡፡ እንዲሁም በብዙ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ችግሮች ተጎሳቁለው የሚታዩ ሰዎች
ስለሚስተዋላሉ ነው፡፡

ስለሆነም ማሰብ የሚችል አእምሮ እያለን፣ መስራት የሚችል እጅ እያለን እንዲሁም መሄድ የሚችል እግር
እያለን እነዚህን ችግሮች መሸከም የለብንም በሚሉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች የተጠነሰሰ ሀሳብ ነው፡፡
እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ዕውቀታችን፣ ገንዘባችን እና ጉልበታችንን አጣምረን ሲንነሳና ሲናለማ ብቻ
ነው፡፡
በዚሁ መሠረት የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስታት የእርሻ መሬት፣ የንግድና እና
የመኖሪያ ቤት ግንባታ መስሪያ ቦታ በመስጠት ከጎናችን እንደሚሆኑ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡ ሁለቱም
ክልሎች አጎራባች በመሆናቸውና በብዙ መንገድ ስለሚተሳሰሩ ይህ ማህበር ከራሱም አልፎ በሁለቱ
ክልሎች መካከል ያለውን መልካም ግንኙነት የሚያጠናክር ይሆናል፡፡

በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ ማህበር


መተዳደሪያ ደንብ
ክፍል አንድ
የመረዳጃ ማህበሩ ስም፣አድራሻ፣ ትርጉምና ዓላማ፣
አንቀጽ አንድ
1. ስለማህበሩ መቋቋምና ስያሜ
1.1 የማህበሩ ስም “በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ ማህበር በመባል ይጠራል “ የመረዳጃ ማህበር በመባል
ይጠራል ፡፡
1.2 መረዳጃ እድር መተዳደሪያ ደንብ /እንደተሻሻለ -“በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ ማህበር ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡

2|Page
1.3 የእድሩ መስራች ጠቅላላ ጉባኤ በቀን ------------------------ ባደረገው ስብበሳባ ረቂቅ መተዳደሪያ ደንቡን
አፅድቆ እና ደንቡ እንዲዳብር የወሰነባቸው ማሻሻያዎች እንዲጨመርበትና እንዲስተካከል አዝዞ ይህን ማህበር
በዚህው ዕለት በይፋ አቋቁሟል፡፡

አንቀጽ ሁለት
የመረዳጃ ማህበሩ አድራሻ
2. የመረዳጃ ዕድሩ አድራሻ በጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ዋና ከተማ 05 ቀበሌ በተለምዶ ስሙ ኦፔኖ ሠፈር አካባቢ ነው፣

አንቀጽ ሦስት
3. የቃላት ትርጉም

3.1 አብዲ ቦሪ ማለት በህግ ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በቀር የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም ገነ ከዛሬ የተሻለ

እንደሚሆን በማመንን የነገ ተስፋ የሚል የሚያመላክት ትርጉም አለው፡፡

3.2 በምንም ልዩነት ሳይደረግ ማለት በአባላት በቀለም፣ በቋንቋ፣በመጡበት አቅጣጫ፣ በጾታ ወዘተ አድሎ አይደረግም
ማለት ነው፡፡
3.3 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ እሱ ተብሎ የተጠራው ለእሷም የሚያገለግል ነው፡፡
3.4 በዚህ የመረዳጃ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ የቃል አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር የተጠቀሱት
ቃላት የሚከተሉት ትርጉም ይኖራቸዋል;
3.5 መረዳጃ ዕድር ወይም ዕድር ማለት በዚህ መተዳደሪያ መሰረት የተቋቋመ ` “በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ
ማህበር `” ነው፤

3.6 "አባል"ማለት የመቆያ ጊዜውን ያሟላ እና ወርሃዊ መዋጮና ሌሎች ግዴታዎችን በአግባቡ እየተወጣ የሚገኝ የመረዳጃ ዕድሩ
አባል ወንድ ወይም ሴት ሰው ነው፣ባልና ሚስት በትዳር ውስጥ እስካሉ ድረስ ሁለቱም እኩል የአባልነት መብት አላቸው፣
3.7 የመጠበቂያ ጊዜ ማለት ማንኛውም ሰው የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን አመልክቶ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተፈቅዶለት
የመግቢያ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ካጠናቀቀ በኋላ የ 30 (ሰላሳ)ቀን እስኪሞላው የሚቆይበት ጊዜ ነው፣
3.8 ጠቅላላ ጉባዔ ማለት የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ሁሉም አባላት የሚደረግ ስብሰባ ማለት ነው፣
3.9 መተዳደሪያ ደንብ ወይም ደንብ ማለት በመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባዔ የጸደቀና በሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት የተመዘገበ
የዕድሩ ሰነድ ነው፣
3.10 ኮሚቴ ማለት በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ መንብ መሰረት በጠቅላላ ጉባዔ የሚመረጡ የመረጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አባላት ማለት ነው፣
3.11 የኦዲት ኮሚቴ ማለት በጠቅላላው ጉባዔው የሚመረጥ በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት አጠቃላይ የመረዳጃ ዕድሩን
የሥራ እንቅስቃሴ የሚከታተልና የሚቆጣጠር ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ የሆነ ነው፣
3.12 ወርሃዊ ክፍያ ማለት በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ከእያንዳንዱ አባል በየወሩ የሚሰበሰብ ገንዘብ ነው፣
3.13 ቅጣት ማለት ማንኛውም አባል በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ሳያከብር ሲቀር ተፈጻሚ የሚሆን
ማንኛውም ዓይነት ቅጣት ነው ፣

3|Page
3.14 ንብረት ማለት በመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ በግዥ ወይም በስጦታ ወይም በማናቸውም ሁኔታ የተገኘ በመረዳጃ ዕድሩ ስም
የተመዘገበ አላቂና ቋሚ ንብረት ማለት ነው፣
3.15 ቅጥር ሠራተኛ ማለት ለመረዳጃ ዕድሩ ወቅታዊ ሥራዎች ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ሥራ እንዲሰራ የሚቀጠር ጊዚያዊ
ሠራተኛ ማለት ነው፣
3.16 ወኪል ወይም ተወካይ ማለት የአባሉን ጉዳይ የሚከታተልና አባሉን የተመለከቱ ጉዳዮች የሚፈጽምና የሚያስፈጽም በአባሉ
በጽሁፍ የተወከለ ወኪል ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የሆነ ሰው ወይም አባል ያልሆነ ማንኛውም ሰው ማለት ነው፣
3.17 የምርጫ ዘመን ማለት በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የመረዳጃ ዕድሩ የሂሳብ ዓመት ነው፣የመረዳጃ ዕድሩ የሂሳብ ዓመት
ከመስከረም 01 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ ያለው ይሆናል፣
3.18 ቤተሰብ ማለት የመረዳጃ ዕድሩ አባል ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ስማቸውን ዘርዝሮ በፊርማው ያረጋገጠው
የሰዎች ስም ዝርዝር ነው፣

3.19 ልጅ ማለት የመረዳጃ ዕድሩ አባል የተወለደ ልጅ ሲሆን፣የጉድፈቻ ልጅንም የሚያጠቃልል ነው፣
3.20 የጉድፈቻ ልጅ ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐብሄር ህግ መሰረት የጉድፈቻ ልጅ ለመሆኑ በሕግ የተረጋገጠ መሆን አለበት ነው፣
3.21 ደራሽ እንግዳ ማለት በአባሉ ቤት በመደበኛነት የማይኖር ለሕክምና ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት በአባሉ ቤት በሞት
የተለየና አስከሬኑ ከአባሉ ቤት ወጥቶ የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የተፈጸመ ወይም አስከሬኑ የተሸኘ ሰው ነው፣ጥገኛ ነዋሪን ያጠቃልላል፣
3.22 ዕርዳታ ማለት አባሉ ወይም በአስመዘገበው የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚሰጥ
የገንዘብና ሌሎች እርዳታዎች ማለት ነው፣
3.23 በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ በወንድ ፆታ የተጠቀሱት አገላለፆች ሁሉ ለሴት ፆታም በእኩል ያገለግላል፤
አንቀጽ አራት
የመረዳጃ ማህበሩ ዓላማ
4. የመኖሪያ አካባቢን መሰረት አድርጎ እርስ በእርስ ለመረዳዳት ያቋቋሙት ማኅበራዊ ተቋም በመሆኑ መልካም ግንኙነት
ለመፍጠር፣ለማዳበርና የመረዳዳት ባህልን በማዳበር የመረዳዳትና የመተዛዘን ዓላማ ይኑረው እንጅ በኣባላቱ መልካም ተሳትፎ እና በፍላጎት
ላይ የተመሠረተ ተጨማሪ የልማት ተግባራትን ለማከናወን የሚከተሉትን የሥራ እንቅስቃሴዎችን በማንገብ ይንቀሳቀሳል፡፡
4.1 መረዳጃ ዕድሩ በነዋሪዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት ሳያደርግ በጋራ መልማትንና ማደግን እንዲሁም የነዋሪውን አብሮ የመኖር
እሴትን ማዳበር፣
4.2 መንግስት ለሚያወጡአቸው ህጎች ተገዥ በመሆን የማኅበሩ አባላት በምንም አይነት ልዩነት ሳይደረግበት በችግር
ጊዜ ማለትም በሞትና በበሽታ ጊዜ ለመረዳዳት እና የልማት ዕቅዶችን በመንደፍ የአባላቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅም
መገንባት ነው፡፡
4.3 በጋምቤላ ከተማ በአምስቱም ቀበሌ ለቢሮ እና ለመጋዝን ግንባታ የሚሆን ቦታ በአቦል ወረዳ የእርሻ የሚሆን ቦታ
ወስደን በማረስ እና የተለያዩ ሸቀጦችን በማምጣት የገቢያ ማረጋጋት ስራ በጋምቤላ ከተማ እንሰራለን፡፡ በኦሮሚያ
ከተሞችም በተመሳሳይ ሁኔታ ለቢሮና ለምርት ማከማቻ ግንባታ የሚሆን እንዲሁም የእርሻ ቦታ ወስደን እናለማለን፡፡
4.4 በአባላት ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ችግሮችን እና አደጋዎችን በጋራ ለማቃለል እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በደስታና በሌሎች
ሁኔታዎች ላይ በመሳተፍ የደስታው ተካፋይ መሆን፣
4.5 መረዳጃ ዕድሩ ነዋሪው የጋራ ተጠቃሚነት አስተሳሰብ በማጎልበት ምቹና ተመራጭ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆን ማድረግ ነው፣
4|Page
4.6 የመረዳጃ ዕድሩ ነዋሪውንና አባሉን ያለምንም ልዩነት ሊጠቅሙ በሚችሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የነቃ ተሳትፎ
ማድረግ፣
4.7 የአባላትን ዕውቀት፣ገንዘብና ሀብት በማስተባበርና በመጠቀም የነዋሪውን፣የአባሉንና የቤተሰቡ የኑሮ ሁኔታ የሚሻሻልበትን የልማት
እንቅስቃሴዎችን በማጥናት በሥራ ላይ እንዲውን ማድረግ፤
4.8 ጤናማ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆን መጣር፣አቅም ደካማና ሕሙማን አባላትን አቅም በፈቀደ በሁሉም ረገድ መደገፍ፣መንከባከብና
መርዳት፣
4.9 በአባሉና በአስመዘገበው የቤተሰብ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ ቀብር ማስፈጸም፣ማስተዛዘንና ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት
የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣
ክፍል ሁለት
የመረዳጃ ዕድሩ አባልነት ፣ የአባላት መብት፣ ግደታና እርዳታ
አንቀጽ አምሥት
የመረዳጃ ዕድር አባል ስለመሆን፣
5. ማንኛዉም በጋምቤላ ህ/ብ/ክ/መንግሥት ጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የሆነ ዕድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው የመረዳጃ ዕድሩ አባል
ለመሆን ይችላል፣ሆኖም መኖሪያቸው ከጋምቤላ ከተማ ውጪ በአጎራባች አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች አባል ለመሆን ከፈለጉ ደንቡን ተቀብለው
አባልነቱ ሊፈቀድላቸው ይችላሉ፤
5.1 ወንድምና እህት ወይም ወንድማማቾች ወይም እህትማማቾች በተመሳሳይ ወቅት የመረደጃ ዕድሩ አባል ሊሆኑ አይችሉም፣
5.2 ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን በጽሁፍ መጠየቅ አለበት፣ነዋሪው የዕድር አባል ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ በሥራ
አስፈጻሚ ኮሚቴው አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ በደንቡ መሰረት አባል ይሆናል፤
5.3 ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ ሙሉ አባል መሆን የሚችለው የመመዝገቢያ 1,500/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ሙሉ
በሙሉ ከፍሎ ካጠናቀቀ ብቻ ነው፤
5.4 አዲስ የሚገባው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመመዝገቢያ ክፍያው ብር 1,500/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር በአንድ ጊዜ በ 3 ጊዜ
ውስጥ ከፍሎ ማጠናነቀቅ ይችላል፤
5.5 የመረዳጃ ዕድሩ የመመዝገቢያ ክፍያ እና ወርሃዊ መዋጮ መጠንና የአከፋፈል ሁኔታ በጠቅላላ ጉባኤ ሊሻሻል ይችላል፣
5.6 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል አዲስ የተወለደ ልጅን በተወለደ በ 3 (በሶስት)ወር (90)ቀናት ውስጥ እንዲሁም የጉድፌቻ ልጅ
በፍርድ ቤት ውሳኔ ባገኘ በአንድ ወር ወይም በ 30(ሰላሳ)ቀናት ውስጥ የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ
የመመዝገብና የማሳወቅ ግዴታ አለበት፣
5.7 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል በሥራ ምክንያት ወይም ለትምህርት ሲሄድ ወይም የመኖሪያ አድራሻ ለውጥ አድርጎ
አካባቢውን ከለቀቀ በአባልነት መቀጠል ከፈለገ ወርሃዊ መዋጮ
5.8 እየከፈለ በአባልነቱ መቀጠል ይችላል፤ሆኖም በዕድሩ ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ራሱ ወይም ቤተሰቡ መገኘት ካልቻሉ መረዳጃ ዕድሩ
ባዘጋጀው ቅጽ መሰረት በጽሁፍ ተወካይ ሊወክል ይችላል፤
አንቀጽ ስድስት
ለዕድርተኛው የሚደረግ የክፍያ አፈፃፀም
6. ማንኛውም የእድሩ አባል የሚጠበቅባቸውን የመቀጮም ሆነ የልማት ግዴታ እየተወጣ መሆኑ ከተረጋገጠ የሚከተሉት
ክፍያዎች በደንቡ መሠረት የምግኘት መብት አለው፡፡

5|Page
6.1 በዕለተ ሞት ከሣጥንና ከፈን ውጪ ብር 1,500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ፣ለተለያዩ ወጪዎች ይሆንና የተረፈ በእጅ ይሰጣል
፡፡
6.2 እድርተኛው ከሚኖርበት አካባቢ ውጪ ባል ፣ሚስት ፣ልጅ አባትና እናት በሪፌር ወይም ለህክምና ወደ ሌላ ቦታ በሚሄድበት

ወቅት እዚያው ህይወቱ ቢያልፍ 3,000/ሦስት ሺህ ብር / በተጨማሪም የ 3 ቀን መስተንግዶ ይደረግለታል ፡፡

6.3 ማንኛውም የእድሩ አባል መርዶ ሲነገረው ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር / ይከፈላል፡፡

6.4 የሩቅ ዘመድ ማለትም አጎት ፣አክስት፣ከእድርተኛው ጋር በጥገኝነት የሚኖር ሆኖ በሞት ቢለይ የቀብር ሥነ ሥርዓት

ይፈፀምለታል፣ የ 3 ቀናት መስተንግዶ ብቻ ይደረግለታል ፡፡ ሌላ ክፍያ አይኖረውም ፡፡

6.5 የእድሩ አባል ባል ፣ ሚስት ፣ልጅ ፣አባትና እናት አምስት ቀን በክልሉ ዕውቅና ካለው ሆስፒታል ገብቶ ሲተ በሚያቀርበው

ማስረጃ መሠረት እስከ ብር ---------- ይከፈለዋል፡፡

6.6 የእድሩ አባል ባል፣ ሚስት፣እናት፣ አባትና ልጅ ከጋምቤላ ከተማ ውጪ የሪፈር ህጋዊ ማስረጃ ሲያቀርብ ለትራንፖርት ብር

7,000/ሰባት ሺህ / ብር ይከፈለዋል፡፡
6.7 አንድ የእድሩ አባል (አባወራ/እማወራ /) በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቃሚ ይሆናል

6.8 የእድሩ አባል ልጁራሱን ችሎ ከቤት ከወጣ በኃላ ለሚደርስበት እክል ለእድርተኛው ወላጅ እንደመርዶ ይቆጠራል ፡፡

6.9 እድሩ አባላት አባል፣ሚስትና ልጅ አባት እናት በሌላ አከባቢ ቀብሮ ሲመጣ ሀዘን የማይቀመጥ ከሆነ ከሴቶች እድር

በመስተንግዶ ፋንታ በተጨማሪ ብር 1,500/አንድ ሺህ አምስት መቶ /ብር ወጪ ሆኖ ይከፈላል ፡፡

አንቀጽ ስድስት

አባል የስብሰባ ጊዜ በተመለከተ


7 ወር በገባ በመጀመሪያው እሁድ ከ 8፡00 እስከ 9፡00 ሠዓት አንድ ጊዜ የጋራ ስብሰባ
ይኖራል ፤
7.1 አስቸኳይ ስብሰባ እንደየሁኔታው በሰብሳቢው ይወሰናል፤
አንቀጽ ሰባት
የመረዳጃ ማህበሩ የአባል መብት
8 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በመረዳጃ ዕድሩ ደንብ መሰረት የሚሰጠውን ማናቸውንም ጥቅም የማግኘትና የመጠቀም መብት
አለው፣
8.1 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ዕድሩ በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ የመሳተፍ፣ ሀሳብ የማቅረብ፣ ሂስ ማደረግ እንዲሁም
የመምረጥና የመመረጥ ፣ቅሬታ የማቅረብ ፣በደል ደርሶብኛል ካለ በደሉን የማሰማት መብት አለው፣

6|Page
8.2 ማንኛውም የህብረቱ አባል በምልዓቴ ጉባኤ በሚተላለፈው ውሳኔ ላይ ሃሳብን
የማቅረብና የራሱን ድምጽ የመስጠት መብት አለው /አላት፤
8.3 የማህበሩ አባል በህምም ጊዜ ብር……..በሀዘን ጊዜ ብር……… የማግኘት መብት አለው /አላት፤፡፡
8.4 ማህበሩ ከሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች ከሚያገኘው ትርፍ
እንደየተሳትፎው/ዋ ተሰልቶ የሚያገኝ/ የሚታገኝ ይሆናል፤
8.5 ማንኛውም የዕደሩ አባል ዕድሩ የሚሻሻልበትንና የሚያድግበትን ሀሳብ የማቅረብ መብት አለው፣ ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል
የዕድር አባልነቱን የሚገልጽና ወርሃዊ መዋጮ የሚከፍልበት ደብተር ይኖረዋል፣
8.6 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል የዕድሩን መገልገያ እቃዎችና ቁሳቁሶች ለሰርግ፣ ለ 40 እና ለ 80 ቀን መታሰቢያና ለሌሎቹም
ጉዳዮች ለመጠቀም መብት አለው፣
8.7 ማንኛውም የእድሩ አባል እድሩን ለቆ ከክልሉ ውጪ ሲሄድ ብር 1,500.00/አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር /ይከፈለዋል ፡፡

8.8 የመረዳጃ ዕድሩ አባል አካቢውን ከለቀቀ ከፈለገ ባለበት ቦታ ሆኖ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ በአባልነቱ መቀጠል ይችላል፣ነገር
ግን የመረዳጃ ዕድሩን ዕቃና ቁሳቁስ መጠቀም ከፈለገ በራሱ ወጪ መውሰድና በሚፈቀደው የጊዜ ገደቡ ውስጥ መመለስ አለበት፣
8.9 ማንኛው የመረዳጃ ዕድር አባል ባልና ሚስት በህግ ሙሉ መብት ስላላቸው በአንድ ጊዜ የመረዳጃ ዕድሩ አባል መሆን
አይችሉም፣ከባል ወይም ከሚስት ከሁለቱ አንዱ በሞት ሲለይ በሕይወት ያለው የትዳር አጋር የመረዳጃ ዕድሩ አባል ሆኖ መቀጠል ይችላል፣
8.10 የመረዳጃ ዕድሩ አባል የነበሩ ባልና ሚስት ሁለቱም በሞት ከተለዩ ከህጋዊ ወራሾቻቸው መካከል ትዳር የሌላቸው ልጆች የአባልነት
መብታቸው ተጠብቆ የመግቢያ ክፍያ ሳይከፍሉ በተመረጠው ልጅ ወይም ሌሎቹ ባለመብት የሆኑ ልጆች የወከሉት አንድ ልጅ ብቻ አባል
ሆኖ መቀጠል ይችላል፣
8.11 በሟች እናትና አባቱ ምትክ የተወከለው የሟቾች ልጅ የቤተሰቡንም ዝርዝር በአዲስ መልክ የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ
መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ማስመዝገብ አለበት፣
8.12 በሞት በተለዩ አባትና እናት ምትክ የተወከለው ትዳር ያለው የሟቾቹ ልጅ ከሆነ በወቅቱ አዲስ ገቢ የሚከፍለውን 50% ወይም
ግማሹን ክፍያ ከፍሎ በመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ በአዲስ መልክ ቤተሰቡን መመዝገብ አለበት፣
8.13 የመረዳጃ ዕድሩ አባል የነበሩት እናትና አባት በሞት ሲለዩ በቤት ውስጥ ያሉ ልጆች የመረዳጃ ዕድሩ አባልነታቸውን የተወካይ ሆኖ
ከልጆቹም ውስጥ አንዱ በሞት ቢለይ የሚከፈለው የማስተዛዘኛ ክፍያ በሞት የተለየው ልጅ እንደ አንድ የዕድር አባል ልጅ እንደሞተ ተቆጥሮ
ለልጅ የሚከፈለው የማስተዛዘኛ ገንዘብ የሚከፈለው ይሆናል፣
8.14 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል ባልና ሚስት በፍቺ ምክንያት ቢለያዩ ማስረጃ ሲያቀርቡ በስምምነታቸው መሰረት ከባል ወይም
ከሚስት አንደኛው አባል ሆኖ መቀጠል ይችላል፣ ነገር ግን ባልና ሚስት የነበሩና ፍቺውን ያጸኑ ካልተስማሙ የሁለቱም መብት እኩል
በመሆኑ ባል ለብቻው ሚስትም ለብቻዋ የአባልነት የመግቢያ ክፍያ ግማሹን በመክፈል እንደ አዲስ የመረዳጃ ዕድሩ ያዘጋጀውን የቤተሰብ
መመዝገቢያ ቅጽ ሞልተው በየራሳቸው በአባልነት መቀጠል ይችላሉ፣ በአደጋ ወቅት የጋራ ልጅ ቢሞት አስከሬን የወጣበት ቤት ሙሉ እርዳታ
የሚያገኙ ይሆናል፣

7|Page
8.15 በሞት የተለየው ልጅ ራሱን ችሎ የሚኖር ከሆነ ወይም አስከሬን ከራሱ ቤት የወጣ ከሆነ ከመረዳጃ ዕድሩ የሚፈጸመው የገንዘብ
ዕርዳታ በፍቺ ለተለያዩ ባልና ሚስት እኩል ይሆናል፣
8.16 ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድሩ አባል ለመሆን ---------------- የመመዝገቢያ ክፍያ ይከፍላል፤ ክፍያውንም በአንድ
ጊዜ ወይም እስከ 2 ጊዜ ከፍሎ ሊያጠናቅቅ ይችላል፣

8.17 ማንኛውም ነዋሪ የመረዳጃ ዕድር አባል ለመሆን ------------------- ዓ.ም.ጀምሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር)
ወርሃዊ መዋጮ ይከፍላል፣ክፍያው የሚፈጸመው ወር በገባ በመጀመሪያው እሁድ ከሰዓት 9፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት
ድረስ ብቻ ይሆናል፣
አንቀጽ ስምንት
የመረዳጃ ማህበሩ አባላት ግዴታ፣
9 ማንኛው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመረዳጃ ዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ ጠንቅቆ አውቆ ማክበርና ማስከበር አለበት፣
10 ማንኛውም የእድሩ አባል ወራዊ ክፍያ ብር 100/አንድ መቶ / በሰዓቱ ተገኝቶ የመክፈል ግዴታ አለበት ፡፡
10.1 ማንኛውም አባል በጠቅላላ የአባላት ስብሰባ ላይ በሰዓትና በቦታው በመገኘት የስብሳበው ተካፋይ መሆን ግዴታ
አለበት፣
10.2 ማንኛው የመረዳጃ ዕድሩ አባል የመረዳጃ ዕድሩን በልዩ ልዩ ሁኔታ እንዲያገለግል በአባላት ሲመረጥ ወይም ሲመደብ
የማገልገል ግዴታ አለበት፣አባሉ የተመረጠው ወይም የተመደበው በሥራ አስፈጻሚ ወይም ኦዲት ኮሚቴነት ከሆነ ቢያንስ
አንድ የምርጫ ዘመን የማገልገል ግዴታ አለበት፣
10.3 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ያለበቂ ምክንያት የአባላትን ምርጫ ተቀብሎ በተመደበበት ሙያ ለማገልገል
ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም እምቢተኛ ከሆነ ወይም አውቆ ቅነነት በጎደለው ሁኔታ የተመደበበትን ኃላፊነት በአግባቡ ካልተወጣ
ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻ ብር ------------- እንዲከፍል ፣ድርጊቱን በዚያው የምርጭ ዘመን ከደገመ ከማስጠንቀቂያ ጋር ብር
------------- ተቀጥቶ በአባልነቱ ይቀጥላል ፣ከቀጠለ ለጠቅላላ ጉባኤው ቀርቦ የሚወሰነው ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል፣
10.4 ማንኛውም አባል የመረዳጃ ዕድሩን ንብረት እንዳይጠፋ ወይም ጉዳት እንዳይደርስበት የመጠበቅ ወይም
የመንከባከብ ጥፋት ወይም ጉዳት ሲደርስበት እንዲታረም ማድረግ አለበት፣
10.5 ማንኛውም አባል ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ ማስመዝገቢያ ቅጽ ላይ በቅጹ መሰረት መመዝገብ አለበት፣የቤተሰብ
ለውጥ ሲኖርም በወቅቱ ለኮሚቴው በጽሁፍ ማስወቅና ለውጡን መመዝገብ አለበት፣ሆኖም የጋብቻ ለውጥ ከሆነ ቀደም
ሲል የነበረው ጋብቻ መፍረሱን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣
10.6 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በዚህ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ
ሲደርስ ለመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተገኘው የመገናኛ ዘዴ በወቅቱ ማሳወቅ አለበት፣

10.7 የመረዳጃ ዕድሩ አባል በዕድሩ ከተወሰነው ክልል ውጪ ካልሆነ በስተቀር በቤተሰቡ ላይ ሞት አደጋ ሲደርስ ፣ ወይም
መርዶ ሲረዳ በሚደረገው ጥሪ ማንኛውም አባል ወዲያውኑ ከጥሪው ቦታ ወይንም ከዕድሩ ዕቃ ቤት በመገኘት እክል ወደ
ደረሰበት አባል ቤት ዕቃ መውሰድና ድንኳን መትከል፣የቀብር ስነ ስርዓት ማስፈጸም እና በዕለቱ የተመደበበትን የሥራ ድርሻ

8|Page
ማከናወንና እንዲሁም እስከ ሁለት ቀን ምሽት የማስተዛዘን ግዴታ አለበት፣ይህን ያልተወጣ አባል በእድሩ ደንብ መሰረት
ይቀጣል፣
10.8 የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሆኑ አረጋውያን እና የጤና ችግር ያለባቸውን ቀብር ለማስፈጸም ወይም ምሽት
ለማስተዛዘን የማይችሉ መሆኑ ሲረጋገጥ፣የአባሉ ቤተሰብ ወይም ተወካዩ እርሱን በመተካት ኃላፊነቱን ይወጣል፣ሆኖም
አባሉን የሚተካው ቤተሰብ ወይም ወኪል ከሌለው አስፈላጊው ትብብር ይደረግላቸዋል፣
10.9 በመረዳጃ ዕድሩ አባል የቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ያልተመዘገበ ነገር ግን ለሕክምና ወይም በማናቸውም
ምክንያት በአባሉ ቤት በሞት ሲለይ እና አስከሬኑ ከአባሉ ቤት ተሸኝቶ የቀብር ስነ-ስርዓቱ በአባሉ አማካይነት ከተፈጸመ ብር
--------------------ይከፈላል፣
10.10 የመረዳጃ ዕድሩ አባል በቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ ያልተመዘገበ ልጅ ወይም 3 ወር (90)ቀን ያልሞላው ሕጻን
ከሞተ ሁኔታውን በሚያውቁ በ 3 (ሦስት)የመረዳጃ ዕድሩ አባላት ፊርማ ተረጋግጦ ብር .------------------------ ብር
ይከፈላል፣
10.11 የትዳር አጋሩ በሞት የተለየበት የመረዳጃ ዕድር አባል ሌላ ትዳር እስካልመሰረት ድረስ ለሟች የትዳር አጋሩ
ዘመዶች በትዳር እንዳሉ የሚቀጥል ሲሆን፣አባሉ/ሏ ሌላ ትዳር ከመሰረተ/ች የትዳር አጋሩ ዘመዶች ዝርዝር በአዲስ መልክ
ስለሚመዘገብ በሟች ዘመዶች ስም መረዳጃ ዕድሩ ምንም አይነት የዕርዳታ ክፍያ ሊፈጽም አይችልም፣
10.12 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ላይ የሞት አደጋ ሲደርስ በ 3 (ሦስት)ወር ወይም
በ 90(ዘጠና)ቀናት ውስጥ የዕርዳታ ጥያቄውን ራሱ ወይም በወኪሉ አማካይነት ማቅረብ አለበት፣ በቂ ባልሆነ ምከክንያት
ከ 3(ሦስት)ወር ወይም ከ 90(ዘጠና)ቀናት በኋላ የሚቀርብ የዕርዳታ ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፣
10.13 ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባላት ስም ለሚቀርበው የዕርዳታ የክፍያ ጥያቄ አጠራጣሪ ሆኖ
ካገኘው ወይም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተጨማሪ ማስረጃ ከቀበሌ፣ ከቀበሌ ገበሬ ማህበር ወይም ከሰፈር ዕድርና
ከመሳሰሉት ህዝባዊ ድርጅቶች ማረጋገጫ ሊጠይቅ ይችላል፣ ያለአግባብ የተከፈለ የዕርዳታ ገንዘብ ካለ በመረዳጃ ዕድሩ
መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ይፈጸማል፣

10.14 የመረዳጃ ዕድሩ አባል ማንኛንም የእርዳታ ጥያቄውን ማቅረብ የሚችለው የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋቸው የዕርዳታ
መጠየቂያና መፍቀጃ ቅጽ ሲሆን፣የገንዘብ ዕርዳታም ሊከፈለው የሚችለው የመረዳጃ ዕድሩ ባዘጋጀው የቤተሰብ
መመዘገቢያ ቅጽ ላይ በአግባቡ ለመዘገባቸው የቤተሰቡ አባላት ስም ብቻ ነው፣
10.15 የእድሩ ክፍያ ሰዓት እሁድ ከሰዓት በኃላ ከ 9፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት በመሆኑ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የመክፈል ግዴታ
አለበት ፡፡
10.16 በጠቅላላ ስብሰባ ጊዜ ልጅ ወይም ተወካይ መላክ አይቻልም ፡፡
10.17 ማንኛውም አባል ከእድሩ ሲሰናበት የእድሩን መታወቂያ ደብተር የመመለስ ግዴታ አለበት
አንቀጽ አሥራ አንድ

አንቀጽ ዘጠኝ
ስለ ማህበሩ መዋጮ አሰባሰብና አስተዳደር በተመለከተ
9|Page
11 የህብረቱ መዋጮ ወር በገባ በመጀመሪያ ሣምንት ባለው እሁድ ከ 8፡00 ሰዓት እስከ 9፡00

ሰዓት ይሰበሰባል፤
11.1 የህብረቱ አባል መዋጮውን ወር በገባ በመጀመሪያ እሁድ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/
ይከፍላል፣ ለህብረቱ መመስረቻ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ለወርሃዊ ክፍያ ብር 100 (አንድ

መቶ ብር) ይሆናል፤
11.2 ማንኛውም የህብረቱ አባል መዋጮውን ሳይከፍል 1 ወር ከቆየ ብር 50 ( ሃምሳ ብር) ሁለት
ወር ከቆየ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ሶስት ወር ከደረሰ ከማህበሩ ጋር መቀጠል ስለማይችል
ምንም ሳይከፈለው በነጻ ይሰናበታል፤
11.3 አዲስ የማኅበሩ አባል ለመሆን የሚፈልግ ካለ እንደ የአስፈላጊነቱ በኮሚቴ ታይቶ
ተጨማሪ ክፍያ የሚጣልበት ይሆናል፤
አንቀጽ አሥር
ከመዋጮ ውጭ ሌሎች ግዴታዎች
12 ማንኛውም አባል ከገንዘብ ውጭ በዕዉቀቱና በጉልበቱ በቅንነት የማገልገል ኃላፊነት አለበት፤
12.1 የማህበሩ አባል በሐዘን (ሬሳ ከቤት ሲወጣ ወይም በመርዶ ምክንያት ሀዘን ስቀመጥ) እንዲሁም በወሊድና በህመም
ምክንያት አባል ሆስፒታል ከተኛ በኮሚቴው በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት ሁለት ሰዎች አብረው እንድሆኑ ይደረጋል፤
12.2 ማንኛውም አባል በማህበሩ ኮሚቴ እና በምለልአተ-ጉባኤ የተጣለበትን ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ አለበት /አለባት
/፤
12.3 የማህበሩ አባል በስብሰባ፣ በመዋጮ ጊዜ ፣ በሀዘን እና በልማት ቦታ መገኘት አለበት /አለባት/፤
12.4 የስብሰባ ጥሪ ሰምቶ የቀረ አባል 50 ብር ይቀጣል/ትቀጣለች፤
ክፍል ሦስት
የመረዳጃ ዕድሩ የገቢ ምንጭ፣የገንዘብና ንብረት አያያዝና አጠቃቀም
አንቀጽ አሥር አንድ
የመረዳጃ ዕድሩ የገቢ ምንጭ
13 አዲስ ከሚገቡ የአባልነት የመግቢያ ክፍያ፣
13.1 ከአባላት ወርሃዊ መዋጮና የቅጣት ገንዘብ ፣
13.2 ከልማት ከሚገኘው ገቢ
13.3 ከአባላት የመታወቂያ ደብተር ሽያጭ፣
13.4 ከመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኪራይ የሚገኝ ገንዘብ
አንቀጽ አሥራ ሁለት
መረዳጃ ማህበሩ ገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም፣

10 | P a g e
14 ከመረዳጃ ዕድሩ አባላት በየወሩ የሚሰበሰበው ወርሃዊ መዋጮ እና የቅጣት ገንዘብ በደብተርና በመዝገብ ሆኖ
ሌሎችም ገቢዎች ገንዘብ ያዡ መረዳጃ ዕድሩ ደረሰኝ የሚሰበሰብ ይሆናል፣
14.1 በመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ የተሰበሰበው ገቢ ገንዘብ በአምስት የሥራ ቀን ውስጥ በመረዳጃ ዕድሩ ስም
በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ገቢ ማድረግ አለበት፣ገንዘቡ ገቢ የሆነበትን የባንክ ደረሰኝ ቅጅ (ኮፒ)ለሂሳብ ሹሙ ይሰጣል፣
14.2 በመረዳጃ ዕድሩ ስም የተከፈው የባንክ ደብተሩ በሊቀመንበሩ ፣ በሂሳብ ሹሙና በገንዘብ ያዥ ጥምር ፊርማ
ይንቀሳቀሳል፣
14.3 ማንኛውም ገቢና ወጭ ማስረጃና ጥራዞች ተመርምረው ካለቀላቸውና ጠቅላላ ጉባዔው ሪፖርት ቀርቦለት ጉባኤው
ካጸደቀው ሰነዶቹ ከነሪፖርቱ በመረዳጃ ዕድሩ ጽሕፈት ቤት በኩል በፀሐፊው ኃላፊነት ተጠብቀው ይቀመጣሉ፣ 10.1.5.
የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃዎች በኪራይ ሲሰጡ ሆነ የጠፋ ንብረትን ዋጋ ሲከፍል የተቀመጠውን የኪራይ ሂሳብ ወይም የዕቃውን
ወቅታዊ ግምት ዋጋ በደረሰኝ ገቢ ይደረጋል፣
አንቀጽ አሥራ ሦስት
የመረዳጃ ማህበሩ ንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣
15 የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የሚገለገልበት ንብረት፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች ይኖሩታል፣ ንብረቶቹ በንብረት ኃላፊው
ክትትልና ጥበቃ ይደረግላቸዋል፣

15.1 የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስፈላጊ ሆኖ ባገኘው ጊዜ ለመረዳጃ ዕድሩ አገልግሎት የሚውሉ
እቃዎችና ቁሳቁሶች እንዲገዙና በአገልግሎት ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤
15.2 የመረዳጃ ዕሩ ንብረቶች፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለአባላት ጥቅም በሥራ ላይ እንዲውሉ
ያደርጋል፣
15.3 የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የዕድሩን ንብቶች፣ዕቃዎችና ቁሳቁሶች በተመለከተ የአፈጻጸም ዝርዝር
መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፣
15.4 የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ንብረቶችና ቁሳቁሶቹን ለማከራየት የወቅቱን ዋጋ ያገናዘበ፣የኪራይ
ተመን ሊያወጣና በሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፣
15.5 የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት የሆኑ እቃዎችና ቁሳቁሶች ጥገናና እድሳት ሲያስፈልጋቸው እንዲታደሱና እንዲጠገኑ
ያደርጋል፣
15.6 የመረዳጃ ዕድሩ ዕቃ አጠቃቀም በመረዳጃ ዕድሩ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በዕቃዎቹ የመጠቀም መብት ያለው
አባል ወይም በተመዘገቡ የቤተሰቡ አባል ላይ በሞት ሲለይ ወይም መርዶ ሲረዳ እንዲጠቀም ያደርጋል፣
15.7 የመረዳጃ ዕድሩ አባላት የዕድሩን ንብረቶች እና ቁሳቁሶች በትውስት ወይም በኪራይ እንዲሰጣቸው ጥያቄ
ሲያቀርቡ ኮሚቴው እንደአስፈላጊነቱ ሊፈቅድ ይችላል፣
15.8 የንብረት ኃላፊው የመረዳጃ ዕድሩ ኮሚቴ አባሉ ወይም ነዋሪው በነጻ ወይም በኪራይ የወሰዳቸውን የመረዳጃ ዕድሩ
ንብረቶች እና ቁሳቁሶች በተወሰነው ጊዜ መመለሳቸውን ይከታተላል፣በወቅቱ ካልመለሱ ለዘገየበት ጊዜ የተወሰነውን ክፍያ
እንዲከፍሉ ያደርጋል፣

11 | P a g e
15.9 የመረዳጃ ዕድሩ ንብረትና ቁሳቁሶች ንጽህናና ደህንነት የተጠበቀ መሆኑን ያጋግጣል፣ይቆጣጠራል፣ንብረቶቹን
የወሰደው ወይም የተከራየው ሰው ካበላሸ ወይም በንጽህና ካልመለሰ የተበላሸው እንዲጠገን ወይም እንዲተካ ወይም
ንጽህናው እንዲጠበቅ ያደርጋል፣
15.10 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድር አባል ወይም ነዋሪ በነጻ ወይም በኪራይ የወሰዳቸውን የመረዳጃ ዕድሩን እቃዎችና
ቁሳቁሶች በ 3(ሶስት)ቀናት ውስጥ መመለሱን ያረጋግጣል፣አባሉ የተወሰኑት ዕቃዎች ወይም ቁሳቁሶች እንዲቆዩለት ከጠየቀ
የሚፈልገውን ዕቃ የኪራይ ዋጋ ግማሹን ከፍሎ እስከ 7 (ሰባት)ቀናት ብቻ እንዲጠቀም ያደርጋል፣
15.11 በዚህን ጊዜ ውስጥ በሌላ የዕድሩ አባል ላይ የሞት አደጋ ወይም መርዶ ቢደርስ የንብረቶቹን ወይም እቃዎቹ ቢፈለጉ
አባሉ የወሰዳቸውን እቃዎች በሙሉ እንዲመልስ ተደርጎ በተመሳሳይ ለሚፈልገው ለሌላው አባል እንዲሰጥ ሊያደርግ
ይችላል፣

15.12 ማንኛውም የመረዳጃ ዕድሩ አባል የዕድሩን መገልገያ እቃዎች ለ 40 እና ለ 80 ቀን መታሰቢያዎች፣ ወይም ለሰርግ
እና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች መጠቀም ከፈለገ የኪራዩን ግማሽ ከፍሎ እንዲጠቀም ሊያደርግ ይችላል፣
15.13 የመረዳጃ ዕድሩ አባል ያልሆነ ሰው ንበረቱን ለመከራየት የኪራይ ጥያቄውን በጽሁፍ አቅርቦ ሲፈቀድለት
ለሚከራያቸው ንብረቶች ዋስ ወይም በቂ ገንዘብ ማስያዝና መውሰድ ይችላል፣በኪራይ የወሰዳቸውን ንብረቶች በአግባቡ
ሲመልስ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ይመለስለታል፣
ክፍል አራት
አንቀጽ አሥራ አራት
የመረዳጃ ማህበሩ አደረጃጀት፤
16 የመረዳጃ ዕድሩ የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖሩታል፡፡
16.1 የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባዔ፣
16.2 .የመረዳጃ ዕድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣
16.3 የመረዳጃ ዕድሩ የኦዲት ኮሚቴ
16.4 የመረዳጃ ዕድሩ የዲስፕሊን ኮሚቴዎች ናቸው፤
አንቀጽ አሥራ አምሥት
የመረዳጃ ማህበሩ የጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር
የመረዳጃ ዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ የመረዳጃ ዕድሩ አባላት በሙሉ ሲሆኑ፣
17 ተግባርና ኃላፊነት
17.1 ጠቅላላ ጉባዔ የመረዳጃ ዕድሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፣ይቆጣጠራል፣
17.2 የመረዳጃ ዕድሩን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የኦዲት ኮሚቴ አባላትን ይመርጣል፣ይሽራል፣
17.3 የመረዳጃ ዕድሩን መተዳደሪያ ደንብ ያፀድቃል፣ያሻሽላል፣ይሰርዛል ወይም ይሽራል፣
17.4 የመረዳጃ ዕድሩን በተመለከተ በማናቸውም ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ያስቀምጣል፣ ይወስናል፣

12 | P a g e
17.5 መደበኛና አስቸኳይ የሂሳብና የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን መርምሮ ያጸድቃል፣ውሳኔ ይሰጣል፣በሪፖርቶች ላይ
ግድፈቶች ካሉ የማስተካከያ ወይንም የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፣
17.6 የመረዳጃ ዕድሩን መተዳደሪያ ደንብን ባለማክበር የሥነ ስርዓት ወይንም የገንዘብ ጉድለት በሚፈጽሙ አባላትና
የሥራ አስአስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላይ የእርምት እርምጃ ይወስዳል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሕግ እንዲጠየቁ ያደርጋል፣
17.7 የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አጥንቶ በሚያቀርባቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣

17.8 በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ተጠንቶ ሲቀርብ የመረዳጃ ዕድሩ እንዲፈርስ ወይም ከሌላ መሰል መረዳጃ
ዕድር(ሮች)ጋር እንዲዋሃድ ይወስናል፣
17.9 ጉባዔው በሚቀርበው የውሳኔ ሀሳብ መሰረት የመረዳጃ ዕድሩን ሀብት አያያዝና አጠቃቀምን በተመለከተ ይወስናል፤
አንቀጽ አሥራ ስድስት
የአባላቱ የገቢ ምንጭ ስለማሳደግ
18 ማህበሩ የራሱን አቅም ለማሳደግ የተለያዩ የገቢ ማመንጫ ሥራዎችን ይሰራል ፡፡ ለምሳሌ፡-
18.1 ከአባላት የማቋቋሚያ መዋጮ
18.2 ከአባላት ቅጣት
18.3 በበጋምቤላ ከተማ አምስቱ ቀበሌ ውስጥ እና በተወሰኑ የኦሮሚያ ከተሞች ለቢሮ እና ለንግድ የሚሆን
ግንባታ በመገንባትና የተለያ|ዩ የንግድ ስራዎችን በመስራት ከሚገኝ ትርፍ፤
18.4 ከሁለቱም ክልላዊ መንግሥታት የእርሻ ቦታ በመጠየቅና በመውሰድ የግብርና ስራዎችን በመስራት ከሚገኝ
ትርፍ፤
18.5 ሁለቱም ክልላዊ መንግሥታት በከተማ በሚሰጡን ቦታ ላይ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን በማቋቋም
ከሚገኝ ትርፍ፣
አንቀጽ አሥራ ሰባት
የመረዳጃ ማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ሥልጣን እና ተግባር
19 የመረዳጃ ዕድሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔ ሲሆን፣ 6 (ስድስት)አባላት ይኖሩታል፤ 1 ኛ/
የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር፤ 2 ኛ/ የመረዳጃ ዕድሩ ፀሐፊ፣ 3 ኛ/ የመረዳጃ ዕድሩ ሂሳብ ሹም፣ 4 ኛ/ የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ
ያዥ፣ 5 ኛ/ የመረዳጃ እድሩ የውስጥ ኦዲት፣6 ኛ/ የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኃላፊ ናቸው፣
19.1 የመረዳጃ ዕድሩ ሊቀመንበር፤
 መረዳጃ ማህበሩ የተቋቋመበትን አላማ፤ የመተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የማህበሩን ህግ በትክክል በስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል።
 በመረዳጃ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔም ሆነ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ስብሰባን ይመራል።
 የመረዳጃ ማህበሩን ጠቅላላ ጉባዔ እና የስራ አስኪያጅ ኮሚቴውን በሚመለከት ማንኛውም ሰነድ ላይ ይፈርማል።
 የማህበሩ ሊቀመንበር የስራ አስኪያጅ ኮሚቴው በወሰነው መሰረት የቀረበውን ቼክ ይፈርማል።

13 | P a g e
19.2 የመረዳጃ ዕድሩ ፀሐፊ፣
 የጠቅላላ ጉባኤውንም ሆነ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን መደበኛም ሆነ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል
 ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴም ሆነ ከቡድን መሪዎች የተረከበውን ማንኛውንም ሰነድ እና መዝገብ በጥንቃቄ ይይዛል
 ለመረዳጃ ማህበሩ አባላት መድረስ የሚገባቸውን ማንኛውንም ጽሁፎች ለቡድን መሪዎች መላክ ይኖርበታል
 በጠቅላላ አስፈላጊ የሆኑትን ቅጾች ማሳተም እንዲሁም ለቡድን መሪዎች ማስረከብ ይኖርበታል
 የማህበሩን የአባላት የስም ዝርዝር ይይዛል::
 የቦርዱንና የስራ አስፈጻሚውን ኮሚቴ አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅዱ በየወሩ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሎችን: በየሶስት ወሩ
የባለአደራ ቦርድ አባላትን እንዲሁም በየጊዜው ሲወሰን የማህበሩን ሙሉ አባላት ለስብሰባ ይጠራል:;
 የስብሰባዎችን ቃለ ጉባዔ ይይዛል:; ያዘጋጃል:: ለቦርድም ያቀርባል::
 የማህበሩን ጽህፈት ቤት ስራ ያከናውናል:
19.3 የመረዳጃ ዕድሩ ሂሳብ ሹም፣
 የማህበሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል::
 የማህበሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል:: ከባንክ ደብተሮችም ያስታርቃል::
 ከሊቀመንበሩ ጋር በመሆን ቼክ ይፈርማል::
 ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል::
 የማህበሩን ስራ ማካሄጃ በጀት ያዛጋጃል:ሲጸድቅም በስራ ላይ ያውላል::
 ወጪዎች በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል:;
 የማህበሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል:: ያቀርባል::
 በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል::
 የማህበሩን ስራ ማካሄጃ በጀት ከሊቀመንበሩ ጋር በመሆን ያዘጋጃል:: ሲጸድቅም በስራ ላይ ያውላል።
19.4 የመረዳጃ እድሩ የውስጥ ኦዲት፣
 በጠቅላላ ጉባዔው የሚመረጥ አንድ ኦዲተር ይሰይማል::
 ኦዲተሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው ይሆናል::

 ኦዲተሩ በሂሳብ ባለሙያው ተዘጋጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፖርት መርምሮ የደረሰበትን ለጠቅላላ ጉባዔውና ለቦርዱ በጽሁፍ
ያቀርባል::
 አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተር ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልሉ የወራት: የሩብ አመታት: ወይም የግማሽ አመታት ሪፖርቶችን ሊያዘጋጅ
ይችል::
 የኦዲተሩ የስራ ዘመን ከቦርዱ የስራ ዘመን ጋር አንድ ይሆናል::

14 | P a g e
 የመረዳጃ ማህበሩን ገንዘብ ከምን ደረጃ እንዳለ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴም ሆነ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል
 ማንኛውንም ለመረዳጃ ማህበሩ የተሰበሰበ ገንዘብ ወደ መረዳጃ ማህበሩ ባንክ አካውንት መግባቱን ያረጋግጣል፤ የገባበትንም ደረሰኝ እና
የባንክ ስቴትመንት ኮፒ በጥንቃቄ ያስቀምጣል።
19.5 የመረዳጃ ዕድሩ ገንዘብ ያዥ፣
 በቡድን መሪዎች የተሰበሰበውን ገንዘብ በደረሰኝ ተረክቦ የመረዳጃ ማህበሩ አካውንት ውስጥ ያስገባል እንዲሁም በየውሩ ባንክ የገባበትን
ደረሰኝ ከባንክ ስቴትመንቱ ጋር አያይዞ ለኦዲተሩ ያስረክባል
 በማህበሩ የቡድን መሪ የሚሰበሰበውን ማንኛውንም ገንዘብ ደረሰኝ በመስጠት ይረከባል
 በመተዳደርያ ደንቡ መሰረት ለማህበሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብ በየጊዜው እየሰበሰበ በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል::
 በመመርያው መሰረት ማህበሩ ለአባሎች የሚሰጠውን እርዳታ ወይም ክፍያ ይፈጽማል::
 ቼኮች በሁለት ስራ አስፈጻሚ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል:: 5.4.4.4 የባንክ ደብተሮችን ይይዛል::
19.6 የመረዳጃ ዕድሩ ንብረት ኃላፊ
 የማህበሩን ንብረት በጥንቃቄ ያስቀምጣል፣
 ደህንነታቸውን ይቆጣጠራል፣
 ለአባላት አገልግሎት ስታዘዝ ወጪ እና ገቢ ያደርጋል፡፡
አንቀጽ አሥራ ስምንት
ሥነ ሥርዓት እና መቀጮ
20 ማህበሩን የሚጎዳ ድርጊቶችን መፈጸም እንዲሁም ማንኛውንም ከማህበሩ አላማና ተግባር ውጭ የሆኑ የግል ወይም የሌላ ድርጅት
አላማዎችን ማንጸባረቅ
20.1 የማህበሩን መልካም ስም የሚያጎድፍ ተግባር የፈጸመ ወይም በአባላት መካከል ሊኖር የሚገባውን መልካም ግንኙነት የሚያበላሽ
ተግባር በፈጸመ አባል ላይ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተወያይቶ ማስጠንቀቅያ ይሰጣል::

20.2 ከላይ በ 16.1 በተሰጠው ማስጠንቀቅያ ያልተሻሻለ እንደሆነ የስራ አስፈጻሚ አባሉ የፈጸመውን ጉድለት በጽሁፍ አቅርቦ በቦርድ
እንዲታይ ያደርጋል:: ቦርዱ ጉዳዩን ተመልክቶ ከአባልነት እስከማገድ የሚደርስ እርምጃ ይወስዳል::
20.3 ከአባልነት የታገደ አባል ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት በጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊያቀርብ ይችላል::
20.4 በማንኛውም ሁኔታ ከማህበሩ የተሰናበተ ወይም የተወገደ አባል ከዚህ ቀደም አባል ሆኖ የከፈላቸው ክፍያዎችን በተመላሽነት
አያገኝም::
20.5 በአንቀጽ ------------------ የተጠቀሱትን የአባልነት ግዴታዎች አለሟሟላት።
20.6 በማህበሩ የተደነገጉ መተዳደሪያ ደንቦችን መጣስ።
20.7 አንድ የማህበሩ አባል በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ውሳኔ በበቂ መረጃ ተረጋግጦ ከማህበሩ ከተወገደ ወደ ማህበሩ መመለስ ፈጽሞ
አይችልም።
20.8 የአባልነት ክፍያ ካልከፈለ ----------- ወር የጽሁፍ ማስጠንቀቅያ ይሰጠዋል::

15 | P a g e
20.9 የአባልነት ክፍያ ሳይፈጽም ------------------- ወር የዘገየ አባል በራሱ ወይም በቤተሰቡ ላይ የሞት አደጋ ከደረሰ የሚሰጠው
እርዳታ ---------- የተጠቀሰው የእርዳታ መጠን ግማሽ ብቻ ይሆናል::
20.10 ያለበቂ ምክንያት (ለምሳሌ - በህመም ወይም ከስራ መፍናቀል በማህበሩ ቦርድ ተረጋግጦ ) የአባልነት ክፍያ ሳይፈጽም ወይም
በጠቅላላ ጉባዔ የተወሰነዉን መዋጮ ሳይፈጽም ------------- ወር ያለፈ እንደሆነ ከማህበሩ በራሱ ፈቃድ እንደተሰናበተ ይቆጠራል::
20.11 አንድ አባል የቤተሰብ ማስመዝገብያ ቅጽ በትክክል ካልሞላ ወይም የተሳሳተ መረጃ ከሰጠ እርዳታ ሊያገኝ አይችልም:: የስራ
አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህንን ባደረገ አባል ላይ ከአባልነት እስከማገድ የሚደርስ ተገቢ እርምጃ ይወስዳል ::
20.12 ከአባልነት የታገደ አባል ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት በጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ሊያቀርብ ይችላል::
20.13 በማንኛውም ሁኔታ ከማህበሩ የተሰናበተ ወይም የተወገደ አባል ከዚህ ቀደም አባል ሆኖ የከፈላቸው ክፍያዎችን በተመላሽነት
አያገኝም::
አንቀጽ አሥራ ዘጠኝ
21 ደንቡ ስለሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ ---------------- /2016 ዓ.ም በተካሄደው የእድሩ መሥራች ጠቅላላ ጉባኤ ባፀደቀውና እንዲሻሻል በወሰነው
መሠረት ተዘጋጅቶ ከመስከረም 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ነው፡፡

አንቀጽ ሃያ
22 ህጋዊነት
22.1 በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ ማህበር መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሠረት
ህልውናውም ሆነ የሥራ እንቅስቃሴው ህጋዊነቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

አንቀጽ ሃያ አንድ
23 ስለ ደንቡ መሻሻል
23.1 ይህ ደንብ ከመስከረም 1/2016 ዓ.ም በምልአተ ጉባዔ አብላጫ ድምጽ ከጸደቀበት ጊዜ ጀምሮ ስራ ላይ
የሚውል ሲሆን በአባላት የማሻሻያ ጥያቄ ሲቀርብ እና በምልዓተ-ጉባኤ 2/3 ኛ ድምጽ ተቀባይነት ሲያገኝ ከሁለት
ዓመት በኋላ ይሻሻላል፡፡

16 | P a g e
የመስራች አባልት ስም ፣ፆታ ፣አድራሻ ፣ ኃላፊነት እና ፊርማ

ተ/ ቁ የአባላት ሙሉ ስም ጾታ አድራሻ የሥራ ኃላፊነት ፊርማ

1.
2.
3.
4.
5.
6.
7.
8.
9.
10.
11.
12.
13.
14.
15.
16.
17.
18.
19.
20.

17 | P a g e
21.
22.
23.
24.
25.
26.
27.
28.

29.
30.
31.
32.
33.
34.
35.
36.
37.
38.
39.
40.
41.
42.
43.
44.
45.
46.
47.
48.
49.
50.
51.

18 | P a g e
52.
53.
54.
55.
56.

በጋምቤላ ከተማ አስተዳደር አብድ ቦሪ መረዳጃ ማህበር የስነ ስርአት እርምጃ

19 | P a g e
20 | P a g e

You might also like