You are on page 1of 19

አምድ 1.

የግንዛቤ ፈጠራና የዉጭ ሀገር ሥራ ስምሪት

ዓላማ 1.1፡ በፍልሰት ዙሪያ የህብረተሰቡ ግንዛቤ ማደግና የባህሪ ለዉጥ መምጣት
ዓላማ 1.2: ፍትሃዊና ዘመናዊ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን ማስፋፋት
ግብ 1. በመደበኛና መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ችግሩን መቀነስ
ውጤት፡ ግንዛቤው ያደገ ህብረተሰብና የቀነሰ ችግር

የግቡ ማስፈጸሚያ ተግባራት

1. የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂው በፌዴራል ደረጃ ሲጸድቅ እንደክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ተግባራዊ


ማድረግ ፣
2. በአገር ዓቀፍ ደረጃ የሚዘጋጀውን የግንዛቤ መፍጠሪያ ሰነድ የክልሉ ቋንቋዎች ማዘጋጀትና
ተደራሽ ማድረግ ፣
3. ክልላዊ የማህበረሰብ ንቅናቄ ሥራ ማከናወን፣
4. በየደረጃው የሚገኙ መንግስታዊ እና ሌሎች አደረጃጀቶችን በመጠቀም ማህበረሰቡን
ማንቃት
5. የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም እና በተለያዩ በክልሉ ውስጥ በሚነገሩ ቋንቋዎች በፍልሰት
ነባራዊ ሁኔታ ዙሪያ የሕብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን መከላከል ፣
6. የትምህርት ተቋማት የሚገኙ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የትምህርት ማህበረሰቡን ግንዝቤ
ማሳደግ
7. ታዋቂ ሰዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና
በየደረጃው የሚገኙ ህዝባዊ አደረጃጀቶችን አቅም በማሳደግ የህብረተሰቡን ግንዛቤ መፍጠር፣

ግብ 2. በሕጋዊ መንገድ ለሥራ ወደ ውጭ አገር መሄድ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች መብታቸውና


ደህንነታቸው በማስጠበቅ የስራ ዕድሎችን ማሳደግ፣

ውጤት፡ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አገልግሎት ያገኙ ዜጎች መጨመር

የማስፈጸሚያ ተግባራት
1. ለሥራ ወደ ውጭ አገር የሚሰማሩ ዜጎች ተገቢውን የሙያ እና የቅድመ ጉዞ ስልጠና
ማግኘታቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤
2. በመካከለኛው ምስራቅ እና የባህረሰላጤ ትብብር ሀገራት ያልተጠናቀቁ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን
ማጠናቀቅ፤
3. አዳዲስ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በማዘጋጀት ከተለያዩ ፍላጎት ካላቸው አገሮች ጋር መደራደርና
መፈራረም፤
4. ወደ ውጭ አገር ለስራ የሚሄዱ ዜጎችን መረጃ አያያዝ ማጠናከር፤
5. ለዜጎች ሥልጠና የሚሰጡ ማሰልጠኛ ተቋማትንና የቅድመ ጉዞ መስጫ ማዕከላትን ማጠናከር፣
6. በውጭ አገር ሥራና ሠራተኛ ለማገናኘት ፈቃድ ያወጡ ኤጀንሲዎች ሕግና ስርዓትን ተከትለው
መሥራታቸውን ለማረጋገጥ ቁጥጥር ማድረግ፣
7. ከውጭ አገር ሥራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እና
በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ፣
8. የውጭ አገር ሥራ ስምሪት አዋጅ ማሻሻያ እንዲጸድቅ መከታልና ተግባራዊ ማድረግ፣
አምድ 2. የተጎጂዎች ጥበቃ እና መልሶ ማቋቋም

ዓላማ፡ ተጎጂዎች የጥበቃና መልሶ ማቋቋም ስራዎች በተቀናጀ አግባብ ፍትሃዊ፣ ተደራሽና ወጥ የሆነ

ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻል፡፡

ግብ 1. የተሻለ የተጎጂ ፍልሰት ተመላሽ ዜጎችና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ መረጃ ይኖራል፤

ውጤት፡- የተደራጀ የተጎጂ ፍልሰት ተመላሽ ዜጎችና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ መረጃ ስርአት

የማስፈፀሚያ ተግባራት

1. በአገር ውስጥ የተጎጂ ከፍልሰት ተመላሾችን መረጃ መያዝ፣

2. የተጎጂ ፍልሰት ተመላሾችና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ አገር አቀፍ የመረጃ ቋት ተግባር ላይ

እንዲውል ማድረግ፣

3. የተጎጅዎችን መረጃ በተመለከተ ከክልሎች ጋር የመረጃ ልዉዉጥ ስርአት መዘርጋት፤

4. በብሔራዊ የቅብብሎች ስርዓት የተሰጡ አገልግሎቶችና ድጋፍ ያገኙ ተጠቃሚዎች እንዲለዩ

ማድረግ፣

5. የተጎጂ ፍልሰት ተመላሾችና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ አገር አቀፍ የመረጃ ቋት አተገባበር ላይ

ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተግባራዊ ስልጠና መስጠት፣

ግብ 2. በተጎጂ ከፍልሰት ተመላሾች ዙሪያ የፈፃሚና ባለድርሻ አካላት የማስፈፀም አቅም ማሳደግ፤

ውጤት 1- የተጠናከረ የተጎጂዎች እንክብካቤ፤ ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ወጥነት ባለው
መልኩ ለማስፈፀም የሚረዳ የአሰራር ስርዓት፣
የማስፈፀሚያ ተግባራት

1. በየደረጃው በሚገኘው መዋቅር የተጎጂ ፍልሰት ተመላሽ ዜጎች ድጋፍ ሰጪ ጥምረት

እንዲቋቋምና እንዲጠናከር ማድረግ፣

2. የተጎጂ ከፍልሰት ተመላሾች የቅብብሎሽ ስርዓት እንዲዘረጋና እንዲጠናከር ማድረግ፣

3. ተጎጂዎችን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎች አተገባበር ዙሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ


አካላት ግንዛቤ መፍጠር፣
4. የተጎጂዎችን ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ምህዳር ከማስፋት አንፃር የግሉን ሴክተር ተሳትፎን

ማሳደግ፣

ውጤት 2- እዉቀትና ክህሎቱ ያደገ የተጎጅዎች የድጋፍና መልሶ ማቋቋም ባለሙያና ተቋም፣

የማስፈፀሚያ ተግባራት

5. በተጎጂዎች መልሶ ማቋቋም ስራ ጋር ተያይዞ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ


ስልጠናዎችን መስጠት፣
6. ፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን፣ (ስልጠና፣

የቴክኒክና ቁሳቁስ፣ ልምድ ልውውጥ፣

7. የተለያዩ ተቋማት የተጎጂዎች ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን ያካተተ እቅድና ትግበራ

እንዲኖራቸው አስፈላጊ ድጋፍ መስጠት፣

8. አማራጭ የተጎጂዎች ማቆያ ማዕከላትን ማቋቋምና ማጠናከር፣

ግብ 3. የተጎጂ ከፍልሰት ተመላሾችና ተጋላጮች ዘላቂ የስነ-ልቦና፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ

ማሳደግ፤

ውጤት 1፡- ለተጎጂዎች የተሰጠ ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ፤ ጥበቃና መልሶ ማቋቋም ድጋፍ፣

የማስፈፀሚያ ተግባራት

1. የተጎጂ ፍልሰት ተመላሽ የተጋላጭነት እና የድጋፍ ፍላጎቶች በዳሰሳ ጥናት እንዲለይ ማድረግ፣

2. ተመላሾች አጠቃላይ ስለሚያገኙት ድጋፍ እና የድጋፍ አሰጣጥ ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣

3. ለተጎጂ ፍልሰት ተመላሾች የቅድመ ቅበላና የተሃድሶ አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
4. ለተጎጂ የፍልሰት ተመላሽ ዜጎች ተጋላጭነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሳይኮ ሶሻል አገልግሎት

ድጋፍ መስጠት፣

5. ለተጎጂ የፍልሰት ተመላሽ ዜጎች ተጋላጭነትን መሰረት ባደረገ መልኩ የማህበራዊ አገልግሎት

ድጋፍ መስጠት፣

6. ለተጎጂ የፍልሰት ተመላሽ ዜጎች የኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ

(ቴክኒክ ክህሎት ስልጠና፣ የስራ ፈጠራ አስተሳሰብ ክህሎት ስልጠና፣ ህጋዊነት ማስፈን አገልግሎት፣

መነሻ ካፒታል ብድር አቅርቦት፣ ገበያ ትስስር፣ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍና ሌሎችም)
1. በፍልሰት ተጎጂ የሆኑ አካባቢዎችን የመለየት ስራ ማከናወን፣
2. ተጋላጮችንና ተጎጂ የፍልሰት ተመላሾችን ሊያግዙ የሚችሉ ማህበረሰብ አቀፍ የልማት
ስራዎችን መለየት፣
3. ተጋላጮችንና ተጎጂ የስደት ተመላሾችን የጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን
መተግበር፣

አምድ 3. የወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር

ዓላማ: ከፍልሰት ጋር የተያያዙ የሕግ ማዕቀፎችን በማውጣት፣ ማጠናከር፣ ንቃተ ህግ በመፍጠር እና


አጥፊዎቸን ለህግ በማቅረብ የሕግ ተፈፃሚነትን ማረጋገጥ

ግብ 1. በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በህገወጥ መንገድ ሰውን ወደ ውጭ
ሀገር ለስራ መላክ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፍ ስራዎችን
ማጠናከር፣

ውጤት. የተዘጋጁ የህግ ማዕቀፎች /አዳዲስ ወይንም የተሻሻሉ/

የማስፈጸሚያ ተግባራት

1. በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን አስመልክቶ ለመከላከልና
ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 1178/2012 ን ስራ ላይ ማዋል፤
2. አዋጁንም ለማስፈጸም ዝርዝር ደንብ እና መመሪያ ማዘጋጀት እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶችን
መዘርጋት

ግብ 2- የህግ ማስከበር ተግባራትን አጠናክሮ በማስቀጠል ተጠርጣሪዎችን ለፍርድ ማቅረብ፣


ውጤት 1. በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ
ወደ ውጭ ሀገር መላክና ተያያዥ ወንጀሎች ላይ አቅማቸዉ የጎለበተ የፍትህ አካላትን ቁጥር
ማሳደግ፤
የማስፈጸሚያ ተግባራት
1. በሰው የመነገድ፤ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ
ሀገር መላክ ወንጀልን ለመቆጣጠር ውጤታማ የቅንጅትና አለምአቀፍ የትብብር አሰራሮችን በጋራ
የዘረጉ የፍትህ አካላት፤ የድንበር ተቆጣጣሪዎች፤ የኢሚግሬሽንና የደህንነት ተቋማት ቁጥር ማሳደግ፣
2. ለፍትህ አካላት የድንበር ተቆጣጣሪዎች ለኢሜግሬሽን እና የደህንነት ተቋማት አቅም ግንባታ ስራ
መስራት
3. በሰው የመነገድ፤ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርና በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ
ሀገር መላክ ወንጀሎች ላይ ግንዛቤያቸዉ ያደገና የህግ ማስከበር አፈጻጸማቸዉን ያሻሻሉ ከፌደራል
እስከ ታችኛዉ እርከን ያሉ የህግ አስፈጻሚ አካላትና የድንበር ተቆጣጣሪዎችን ቁጥር ማሳደግ፣

ውጤት 2. በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ

ወደ ውጭ ሀገር መላክና ተያያዥ ወንጀሎች ላይ የተጎጂዎች እና ምስክሮች ጥበቃ በህግ እንዲረጋገጥ


ማድረግ

የማስፈጸሚያ ተግባራት
4. የምስክሮች ጥበቃን ና አቆያየት የተሻለ ለማድረግ ፕሮጅክቶችን ቀርጾ ወደ ስራ ማስገባት
5. በሰው መነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር በህገ ወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ
ሀገር መላክና ተያያዥ ወንጀሎች ላይ ለተጎጂዎች እና ለምስክሮች መጠለያ ግንባታ ማስጀመር
6. የህግ አስከባሪ አካላት እና የመጠለያ እና የተለያዩ አገልግሎቶችን ከሚሰጡ የግል ድርጅቶች ና ድጋፍ
ከሚያደረጉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት
ግብ 3. የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ የህግ ማስከበር ብቃቱ የጎለበተ የህግ ተቋም መገንባት
ውጤት. ተሳትፎው ያደገ ህብረተሰብ እና የህግ ማስከበር ብቃቱ የጎለበተ የህግ ተቋም የማስፈጸሚያ
ተግባራት
7. የማህበረሰቡንና የህግ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን የሚያሳድጉ ተግባራትን ማከናወን፣
8. ህብረተሰቡ ወንጀልን ሪፖርት የሚያደርግበት ቀላል ስርዓት መዘርጋት
9. በአዋጁ አፈጻጸመም ዙሪያ የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረኮቸን ማዘጋጀት

ግብ 4. ለህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላትን የንቃተ ህግ ግንዛቤ ማሳደግ


ውጤት-ግንዛቤው ያደገ ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት
የማስፈጸሚያ ተግባራት
10. የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ስለ አዋጁ ግንዛቤ መፍጠር
11. በፍልሰት ዙሪያ ለሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በፍልሰት ዙሪያ እና ተያያዥ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ልዩ ልዩ
የግንዛቤ መፍጠሪያዎች በመጠቀም ማስገንዘብ
አምድ 4. የፍልሰት ጥናትና ምርምር

ዓላማ. በጥናት እና ምርምር የተደገፈና የተጠናከረ ሁሉን አቀፍ የፍልሰት አስተዳደር ስርአት
መዘርጋት

ግብ 1. ጥራት ያለው እና ችግር ፈቺ የፍልሰት ጥናትና ምርምር ስራዎችን በተለያዩ የመንግስትና የግል ከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት እንደካሄዱ በማድረግ ተደራሽነትን ማሳደግ

ውጤት፡ ለፖሊሲ እና የፍልሰት አስተዳደር የሚሆኑ የምርምር ግኝቶች እና ምክረ ሃሳቦች መጨመር
የግቡ ማስፈጸሚያ ተግባራት

12. የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርትና የምርምር ተቋማት የፍልሰት ጥናትና ምርምር ስራዎችን
በየተቋማቱ የምርምር የትኩረት መስኮች ውስጥ እንዲያካትቱ ማድረግ፣
13. በፍልሰት ጥናትና ምርምር ዙሪያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመራማሪዎች ተገቢውን ድጋፍ
እንዲሰጡ ማድረግ፣
14. ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና የምርምር ተቋማት ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለድርሻ
አካላትና እርስ በርሳቸው በመተሳሰርና በጋራ በመሆን የፍልሰት ጥናትና ምርምር ፕሮጀክቶች
እንዲቀርጹና እንዲተገብሩ ማድረግ፣
15. የፍልሰት ምርምር ውጤቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ቋንቋዎች የተግባቦት
መንገዶችን በመጠቀም እንዲሰራጩ ማድረግ፣
16. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት ለስራ ፈጠራ የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን
ማበረታታት
17. ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላትን እርስ በእርስና ከአቻ የዓለም ተቋማት እና
ማዕከላት ጋር በልምድ ልውውጥ በማስተሳሰር አጋርነት ማሳደግ
ግብ 2. ለፍልሰት አስተዳደር እና ለምርምር ብቁ የሆነ የሰው ሀብት ለማልማት የፍልሰት ትምህርት ክፍል
በተመረጠ የከፍተኛ ትምህርት እንዲቋቋም ማድረግ
ውጤት፡ በዘርፉ የሰለጠነ በብዛትና በጥራት የሰው ሀብት ማፍራት
የማስፈጸሚያ ተግባራት

1. በጉዳዩ ላይ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ


2. በተመረጠው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ጋር ስራውን ማስጀመር
1. የስርአተ ትምህርት ዝግጅት ማድረግ
አምድ 5. የዳያስፖራ ተሳትፎና ልማት
ዓላማ፡ መብቱና ደህንነቱ የተጠበቀና በሀገሪቷ ልማት ተሳታፊ የሆነ የዳያስፖራ ማህበረሰብ መፍጠር
ግብ 1፡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ልማት ስራን ውጤታማነት ማሳደግ
ውጤት፡ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ የደረሰ እና ለዘላቂ ልማት ላይ በብዛትና በንቃት የተሳተፈ
የዳያስፖራ ማሕበረሰብ፣
የግቡ ማስፈጸሚያ ተግባራት
1. የዳያስፖራው ማህበረሰብን ተሳትፎ ልማትና ማህበራዊ መስተጋብር የሚያጠናክሩ የግንዛቤ
ማስጨበጫ መድረኮችንና ኩነቶችን ማካሄድ፣
2. ነባር የዳያስፖራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኖችን ማጠናከር እና አዳዲስ ቡድኖችን በመመስረት
የአገራችንን ገፅታ መገንባትና ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣
3. በውጭ አገራትና በሀገር ውስጥ ያሉ የዳያስፖራ አደረጃጀቶችን ማጠናከር
1. ግብ 2፡ ከዳያስፖራ የሚገኘውን የልማት ተሳትፎና የሀብት ፍሰት ማሳደግ፣
ውጤት
ያደገ የዳያስፖራ የልማት ተሳትፎ
የግቡ ማስፈጸሚያ ተግባራት
2. የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ፖሊሲና
ስትራቴጂዎችን ማዘጀት፣
3. የዳያስፖራ አባላት በዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር፤ ንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና በበጎ
ተግባር አገልግሎቶች እንዲሳተፉ ድጋፍ ማድረግ፣
4. የዳያስፖራ ዕውቀት፣ ክህሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ
ወጥ ሀገራዊ የዕውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕቀፍ ማዘጋጀት፣
5. ከዳያስፖራው ወደ ሀገር ቤት ያለው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሀብት ፍሰት እንዲጠናከር ህጎችና
አሰራሮች እንዲሻሻሉ ማድረግ፣
6. በፌዴራል ባለድርሻ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች የዳያስፖራ
ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች አቅምና ቅንጅት ማጠናከር
7. በሀገር ውስጥ ያለው ማህበረሰብና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዳያስፖራው ለሀገር ልማት
በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
ግብ 3፡ ዘመናዊ የዳያስፖራ መረጃ አሰባሰብ እና ስርጭት ስርአት መዘርጋት
ውጤት፡ በዘመናዊ መንገድ የተሰባሰበና የተሰራጨ መረጃ
ማስፈጸሚያ ተግባራት
8. ማዕከላዊ የዳያስፖራ መረጃ መመዝገቢያ፣ መያጃ ማደራጃና ማሰራጫ ስርዓቶችን መዘርጋት
9. በዳያስፖራ መረጃ አሰባሰብና የመረጃ ቋት አያያዝ ላይ አቅም መገንባት
10. በዳያስፖራ ተሳትፎ ዋና ዋና ጉዳዮች ዙሪያ ጥናቶችን ማከናወን
11. የዳያስፖራ ፍኖተ ካርታ (ማፒንግ) ማከናወን
ግብ 4፡ በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎች መብት፣ክብርና ደህንነት ማስጠበቅ፣
ውጤት
መብቱ፣ ክብሩና ደህንነቱ የተረጋገጠ በዉጭ ሀገር የሚኖር ዜጋ፣
የግቡ ማስፈጸሚያ ተግባራት
12. ዜጎች ከአገር ከመውጣታቸው በፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ስልጠና እንዲያኙ
በትብብር መስራትና ክትትል ማድረግ፣
13. ዜጎች ከመነሻ እስከ መዳረሻቸው አንዲሁም የመመለሻቸው ሂደት ደህንነታቸውን የተጠበቀ እንዲሆን
አሰራር መዘርጋት፤
14. የዳያስፖራ ማህበረሰብ (በተለይም በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ አገሮች የሚኖሩ) መብታቸው
ተከብሮ፣ ጥቅማቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ እገዛ ማድረግ፣
አምድ 6. የፍልሰት መረጃና አስተዳደር

ዓላማ
በእቅድ ዘመኑ ከቆጠራ እና ከናሙና ጥናት የሚገኝ የፍልሰት መረጃ ሽፋን ማሻሻል እና ከአስተዳደራዊ
መዛግብት የፍልሰት መረጃ የሚመነጭበትን ስርአት መዘርጋት
ግቦች
ግብ 1፡- የስራ ቡድኑን ተቋማት በአይሲቲ መሰረተ ልማት በማስተሳሰር መረጃ የሚለዋወጡበትን ስርአት
መዘርጋት እና መረጃን ከአስተዳደር መዛግብት ማመንጨት
ውጤት፡- ደረጃውን የጠበቀ የፍልሰት መረጃ ከአስተዳደር መዛግብት ማመንጨት

ማስፈጸሚያ ተግባራት

1. በፍልሰት ዙሪያ በሚሰሩ ተቋማት ግንዛቤ በማሳደግ የመግባቢያ ሰነድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ

2. ከተቋማት የሚገኙ ጠቋሚ መለኪያዎች (indicators) የመለየቱን ስራ ማጠናቀቅ እና የስራ ትስስሩን


በመለየት ለአውቶሜሽን በሚመች መልኩ ማደራጀት

3. ለጠቋሚ መለኪያዎች (indicators) በተባበሩት መንግስታት የስታቲስቲክስ ተቋም የተሰጡትን


ትርጓሜዎች በመጠቀም በሀገራችን ከተሰሩ ሌሎች ጥናቶች ጋር የማስታረቅ ስራ መስራት
4. የፍልሰት መረጃ ባለሙያ ለማሰልጠን የሚያገለግል የስልጠና መመሪያ ማዘጋጀት እና ማሰልጠን
1. ከአስተዳደርመዛግብት የሚገኙ መረጃዎች ጥራት መከታተያ እና መቆጣጠሪያ ስርአት መዘርጋት

ግብ 2፡- ብሄራዊ ስትራቴጂ ለስታቲስቲክስ ልማት lll (NSDS lll) እና የአስር አመት ስታቲስቲክስ መሪ እቅድ
ላይ የፍልሰት መረጃ አያያዝ ስርዓትን ማሳደግ

ውጤት፡- የተደራጀና የበለፀገ የፍልሰት መረጃ አያያዝ ስርዓት

ማስፈጸሚያ ተግባራት

1. የፍልሰት ናሙና ጥናት ማካሄድ እና በጥናቶች እንዲካተቱ የሚፈለጉ የፍልሰት መረጃ ዓይነቶች
መለየት
2. ለፍልሰት መረጃ አስተዳደር የሚያገለግል ስትራተጂክ ሰነድ ማዘጋጀት
ግብ 3፡- የፍልሰት መረጃ አስተዳደር ስራን አቅም ማጎልበት

ውጤት፡- የተጠናከረ የፍልሰት መረጃ አመንጪ ተቋማት እና አቅሙ የዳበረ ባለሙያ

ማስፈጸሚያ ተግባራት

1. የፍልሰት መረጃ አመንጪ ተቋማትን የአይሲቲ መሰረተ ልማት የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት
2. የተቋማት የመረጃ አያያዝ እና ቅብብሎሽ አሰራር ስርዓትን ማዘመን
3. የፍልሰት መረጃ አስተዳደር ላይ ልምድ ካላቸው ተቋማት እና ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ
1. መርሆች

በዚህ እስትራቴጂክ ሰነድ ውስጥ የተያዙ ዕቅዶችን በአግባቡ በማሳካት ሁሉን አቀፍ ዘለቄታዊ ለውጥ

ለማምጣት ከአለም አቀፍ መለኪያዎች፣ ከህግ ማዕቀፎች፣ ከምርጥ ተሞክሮዎችና ከሀገራችን ነባራዊ
ሁኔታዎች የመነጬ በሰዎች መነገድ፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መነገድ ሰዎችን

ለስራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ፤ ከፍልሰት የሚገኝን ፀጋ በአግባቡ

ለመጠቀምና ብሎም የፍልሰት አስተዳደሩን የተሻለ ለማድረግ ስራው የሚመራባቸው መርሆዎችን በመለየት

ማስቀመጥ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡

1. ሰብአዊ መብት

ይህ መርሆ በዚህ ሰነድ የተገለጹት እና ተያያዥ ወንጀሎች ሰዎች ላይ የሚያደርሱትን የከፋ እና አሰቃቂ

ጉዳቶች በመገንዘብና ለችግሮቹም ምላሽ ለመስጠት የተጎጂውን መብትና ፍላጎቶች ማዕከል ማድረግ፣

ለተጎጂና ተጠቂ የሆኑ ድምጻቸው እንዲሰማና ምላሽ እንዲሰጣቸው የሚያስችል ነው፡፡ የሰብአዊ መብት

አጠባበቅ የተጎጂዎችን መብት የሚጠብቅና የራሳቸውን ውሳኔ እንዲሰጡና ህይወታቸውን እንዲመሩ

የሚያበቃ ነው፡፡

1. የስርዓተ ፆታ እኩልነት

የስርዓተ-ጾታ እኩልነት ማለት ለሴቶች እና ለወንዶች እኩል መብትን፣ ሀላፊነትን እና እድሎችን መስጠት

ሲሆን ይህ ማለት ሴቶችና ወንዶችን በሁሉም ጉዳዮች አንድ ማድረግና ማመሳሰል ማለት ሳይሆን ለሴቶች እና

ለወንዶች የምንሰጣቸው መብቶች፣ ሀላፊነቶች እና እድሎች ሴት እና ወንድ ሆኖ መፈጠርን መሰረት ሊያደርጉ

አይገባም ማለት ነው፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ሰው ሴትም ሆነ ወንድ ራሳቸውን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በመወሰን ሂደት ለጥበቃና

ለተሳትፎ ተመሳሳይ መብት አላቸው፡፡ ሴቶች ለማህበራዊ ጉዳይም ሆነ በፍልሰት ዙሪያ እንዲሁም

ወንጀሎቹን ለመከላልና ለመቆጣጠር በሚደረጉ ልዩ ልዩ ውይይቶች እና ምክክሮች እኩል ተሳትፎና ተደራሽነት

ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ሶስቱን ወንጀሎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ለተጎጂዎች የሚሰጡ ምላሾች ሲቀረጹ ለተለያዩ

ተጠቂ ለሆኑ ሴቶችና ወንዶች ፍላጎቶች የሚያማክል መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ ሴት ተጎጂዎች በሴት ፖሊሶች

እንዲጠየቁ፣ ሪፖርቶች፤ ጥናትና ምርምሮች እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎች ሲሰበሰቡም ሆነ ሲደራጁ በፆታ

ላይ የተመሰረተ መረጃ እንዲኖራቸው እና የፆታን ልዩ ባህሪ ከግንዛቤ ያስገቡ አገልግሎቶች መስጠትን

ያካትታል፡፡
2. የህፃናት መብት ማክበር

እንደሚታወቀው በሀገራችን በሰው የመነገድና ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች ላይ ህፃናት

በከፍተኛ ሁኔታ ተጎጂዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ብሎም

ምላሽ ለመስጠት የሚነደፉ ስትራቴጂዎች እና ማንኛውም ስራዎች ታዳጊ ሴቶችንና ወንዶችን የሚያበቃ፣

የሚደርስባቸውን ጥቃት የሚቀንስ፣ የከለላና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ የሚያሰጥ እንዲሁም የህፃናት ልዩ

ፍላጎት እና የህፃናን ምርጥ ፍላጎት ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡

2. ዘርፈ ብዙ ምላሽ አሰጣጥ

ወንጀሎችን የመከላከልም ሆነ አጠቃላይ የፍልሰት ስርዓቱን የማስተባበርና የማደራጀት እንቅስቃሴ ሁሉንም

አይነት ችግሮች፣ ዑደቶች፣ ሁኔታዎችን የሚመለከት እንዲሁም የሚመለከታቸውን አካላት የሚያሳትፍና

የተሟላ ሁሉን አቀፍ ምላሽ መስጠትን ማዕከል ባደረግ መልኩ መሆን ይኖርበታል፡፡

3. የመንግስት ባለቤትነት እና ቁርጠኝነት

መንግስት የዜጎችን መብትና ደህንነት የመጠበቅ እና የማረጋገጥ ጉዳይ ህገ-መንግስታዊ ኃላፊነት በመሆኑ

በሰው የመነገድ፣ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ

ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎች መከላከል እና መቆጣጠር እንዲሁም የፍልሰት ስርዓቱን የማስተካከልና

የመምራት ስራው ፕሮግራም በመንደፍ፣ በጀት በመመደብና ሁሉንም አካላት በማሳተፍና የማስተባበር

የመሪነትና ሚናውን በቁርጠኝነት ይወስዳል፡፡

4. የህብረተሰብ ተሳትፎ

ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ በመደበኛ፣ ኢመደበኛ፤ ባህላዊና በየአካባቢያዊ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች

የህብረተሰብ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ ህብረተሰቡን በአግባቡና በሙሉ አቅም ማሳተፍን ላይ ትኩረት

ያደርጋል፡፡

5. ጥራት ያለውና ዘለቄታዊነት


በሁሉም አቅጣጫ ሁሉን የሚያሳትፍ፣ ብቃት ባለው ባለሙያ አግልግሎቱ የሚሰጥ፣ በተገቢው የአቅም ግንባታ

ስራ የተደገፈና ውጤታማ፣ ስኬታማና በትብብርና በአጋርነት የሚሰጥ የአገልግሎት አሰጣጥ የሚያረጋግጥ እና

ተከታታይነት ያለው ይሆናል፡፡

6. ግልጽነትና ተጠያቂነት

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት የግልጽነትና የተጠያቂነት መርህን በመከተል እና ይህንኑ የሚያረጋግጥ

ይሆናል፡፡

7. ሚስጥራዊነት

የሚሰበሰቡ መረጃዎች የሚተነተኑበትና የሚሰራጩበት አግባብ ሚስጥራዊነትን መሰረት ያደረገና እና

በየደረጃው የሚከናወኑ ተግባራት ትክክለኛ መረጃን መሰረት በማድረግ ይከናወናል፡፡

3.5.8 አጋርነት

የፍልሰት ስራዎች በአንድ ተቋም ብቻ የሚከናወኑ እነዳለመሆናቸው እና የተለያየ አካላትን ትብብርና ቅንጅት
የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህ ዙሪያ የሚሰሩ ሁሉም አካላት በዚህ ስትራቴጅ አተገባበር ሂደት ውስጥ
አስፈላጊውን ቅንጅትና ትብብር ይፈጥራሉ።

ምዕራፍ አራት
4 የአተገባበር/አፈጻጸም/ አደረጃጀት
ኢትዮጵያ የፍልሰተኞች መነሻ፤ መተላለፊያና መዳረሻ ሀገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡ በሰው የመነገድ፣ ሰውን
በሕገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር፣ በህገወጥ መንገድ ሰውን ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎች እና
የሀገር ውስጥ መፈናቀሎች ከመደበኛ ካልሆነ ፍልሰት ማሳለጫ መንገዶች ውስጥ የሚጠቀሱ ሲሆን በርካታ
ኢትዮጵያዉያንን ለአካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችና እና ለሞት እንዲዳረጉ
ከማድረጋቸው በተጨማሪ የሀገር ገጽታንም ከማበላሸት አኳያ ተጽዕኖው ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል
ይታመናል፡፡

መንግስትም በሀገራችን ስር እየሰደደና ስፋቱ እየጨመረ የመጣውን በሰዎች መነገድና ሰዎችን በህገ ወጥ

መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ሰዎችን ለስራ ወደ ውጭ ሀገር መላክ ወንጀሎችን ለመግታት

እንዲሁም የፍልሰት አስተዳደሩን ለማጠናከር በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሔራዊ ም/ቤት

በማቋቋም በስሩ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሚመራ የትብብር ጥምረት በማዋቀር ባለፉት ዓመታት
እቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ የተገባ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በክልል መንግስታትና በከተማ

አስተዳደሮችም አደረጃጀቱን ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ በተዋረድ ለማዋቀርና ችግሩን ለመከላከል

ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በተቀናጀ እና በተደራጀ አግባብ ፍልሰት ለመምራትና ለማስተዳደር እንዲሁም አጥጋቢ በሆነ መልኩ ምላሽ

ለመስጠት ይቻል ዘንድ ጠንካራ አደረጃጀት ለመፍጠር የ 5 ዓመት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ

ለመግባት ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

ይህን ስትራቴጅክ እቅድ ከግብ ለማድረስ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብረኃይል አደረጃጀት ጠንካራና ደካማ

ጎኖች በመገምገም በአዋጅ ቁጥር 1178/2012 መሰረት በማድረግ የሚከተለው አደረጃጀት ውጤታማ ይሆናል

በማለት ከዚህ በታች ተዘርዝሯል፡፡

1. በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ

ወደ ውጭ መላክ ወንጀል ተከላካይ ብሔራዊ ም/ቤት

ምክር ቤቱ በአዋጅ 1178/2012 መሰረት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሰብሳቢነት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን

የሚኒስቴር መ/ቤቶች፣ የክልል መንግስታት ፕሬዝዳንቶችን፣ የብዙሀን ማህበራት ተቋማት ተወካዮችን፤

የሀይማኖት መሪዎችና ታዋቂ ሰዎችን አካቶ የተደራጀ ሲሆን ተግባርና ኃላፊነቱም በአገር አቀፍ ደረጃ

ወንጀሎቹን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ፖሊሲ፣ ህግ እና ስትራቴጂ የማመንጨት በሌላ አካላት

እንዲሰሩ የማስተባበርና የመምራት፣ ተጎጂዎችን ማዳን፣ መልሶ ማቋቋም እና ልዩ ልዩ ድጋፍ ስለሚያገኙበት

ሁኔታ እና አጠቃላይ የፍልሰት አስተዳደሩ የሚመራባቸው ስርዓቶችን ሚዘረጉ መመሪያዎችን የማውጣት እና

ተግባራዊነታቸውን የመከታተል ነው፡፡ በተጨማሪም ም/ቤቱ በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የሚተገበሩ

ስራዎችን አፈፃፀማቸውን በተወሰነ ጊዜ ገደብ በመገናኘት በመገምገም አቅጣጫዎች ያስቀምጣል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታም በክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች የሚመራ ክልላዊ ምክር ቤቶች በየክልሉ ይደራጃሉ፣

በየክልሉ እስከ ቀበሌ ያለውን ስራ ይመራሉ።

2. በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ

ወደ ውጭ መላክ ወንጀል ተከላካይ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት


በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሚመራው በሰው መነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር እና በህገወጥ

መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ መላክ ወንጀል ተከላካይ ብሔራዊ የትብብር ጥምረት ጉዳዩ የሚመለከታቸው

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ ሲቪክ ማህበራትን፣ የሀይማኖት ተቋማትን፣ የሴትና የወጣት አደረጃጀትን

በማካተት የተደራጀ ነው፡፡ የጥምረቱ የስራ ኃላፊነትም የፍልሰትን አሉታዊ ውጤቶች ለመቀነስና ከፍልሰት

የሚገኙ ጥቅሞችን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል የትብበር ጥምረቱን አባል ተቋማትን እና ሌሎች ባለድርሻ

አካላትን ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ድረስ የሚያከናውኗቸውን ከፍልሰት ጋር የሚገናኙ ተግባራት

ይከታተላል፤ ያስተባብራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አባል ተቋማትና ሌሎች በፍልሰት ጉዳዮች ዙሪያ ኃላፊነት

ያለባቸው ባለድርሻ አካላት ስለፍልሰት ወቅታዊ ኩነቶች ተመሳሳይ የሆነ አረዳድና ወጥ የሆነ

አፈፃፀም እንዲኖራቸው ለማድረግ ተከታታይነት ያለው የመረጃና የእውቀት ልውውጥ እንዲያደርጉ

መድረኮችን ያመቻቻል፤ በክልሎች የትብብር ጥምርቶች እንዲደራጁ ድጋፍ ያደርጋል፣ በትብብር ጥምረቶች

መካከል ተከታታይነት ያለው የመረጃና የእውቀት ልውውጥ እንዲኖር መድረኮችን ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፡፡

ተመሳሳይ አደረጃጀት በክልሎች እስከ ቀበሌዎች የየአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት

እየተደራጁ ይገኛል በቀጣይም የሚደራጅ ይሆናል።

በፌዴራል እና በክልሎች እስከ ወረዳ የትብብት ጥምረቱን ስራ የሚያስተባብሩ እና የሚያቀናጁ ጽ/ቤቶች

በአዋጁ መሰረት ይደራጃሉ፡፡ የብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ ጽ/ቤት ኃላፊነትም ብሔራዊ ትብበር ጥምረቱ

ተግባርና ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ እና የሚያካሂዳቸው ስብሰባዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል

አስፈላጊውን የድጋፍና የማስተባበር ሥራዎች ያከናውናል፤የታቀዱ ሥራዎች ማስተባበር፣ አተገባበሩን

መከታተል፣ መደገፍ፣ ሪፖርቶችን መቀመርና የማደራጀት ስራዎች ያከናውናል፡፡ እንዲሁም ከፍልሰት ጋር

በተያያዘ የሚያስፈልጉ ፖሊሲዎችና ህጎች እንዲዘጋጁ ለትብብር ጥምረቱ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል በአጠቃላይ

ለጥምረቱ የሴክሬታሪያት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ የስራ ቡድኖች እና የክልል ጽ/ቤቶች አፈፃፀም ሪፖርት

ለመሰብሰብ የሚያስፈልጉ የሪፖርት አደራረግ ስርዓቶችን ይዘረጋል፡፡ ጽ/ቤቱ ተግባራቱን ሲያከናውን

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ማለትም አለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች እና ከሌሎች መሰል

አደረጃጀቶች ጋር በጋራ ይሰራል፡፡

4.1. የሥራ ቡድኖች /Thematic working group/


የፍልሰት አስተዳደሩም ሆነ በሰነዱ የተካተቱት ወንጀሎች በባህሪያቸው የተለያዩ ተግባራትና ምላሾችን

የሚጠይቅ በመሆኑ እንደ ምላሹ አግባብ ስድስት ዋና ዋና ተግባራት ላይ ያተኮረ የስራ ቡድን ተዋቅሯል፡፡ እነዚህ

የስራ ቡድኖች በአስተባባሪ ተቋማት የሚመሩ ሆነው የተለያዩ ተቋማትን፣ የግል ድርጅቶችን፤ የሚዲያ

አካላትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን፣ የወጣትና የሴቶች አደረጃጀቶችን ያቀፉ ይሆናል፡፡ የአስተባባሪ

ተቋማቱም በስራቸው ያሉ ተቋማትን የስራ እንቅስቃሴ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ የቡድኖችን እንቅስቃሴ

የተደራጀና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል የቅርብ አመራርና ድጋፍ የሚያደርግ በሰብሳቢ ተቋማት የሚወከል

አንድ አስተባባሪ ይኖራል፡፡

1. የግንዛቤ ፈጠራ እና የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት የሥራ ቡድን

የዚህ የሥራ ቡድን ከፍተኛ የሥራ ሃላፊነትና ድርሻ የሚኖረው ሲሆን ዋና ዋና ተግባሩም የግንዛቤ

በተለይም የአመለካከት ባህሪ ለውጥ ላይ ትኩረት ማድረግ የሥራ እድል ፈጠራ አማራጮችን

ማፈላለግ፣ የዜጎችን ክብር ደህንነት ሞራልና ጥቅም የሚያረጋግጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት

አገልግሎትን ማስፈን፣ መዳረሻ ሀገራትን በማፈላለግ አማራጮችን ማስፋትና የሁለትዮሽ የስራ

ስምምነት እንዲደረግ የሎጀስቲክ ድጋፍ ማፈላለግና መስራት ዋና ዋና ተግባሮቹ ይሆናሉ፡፡ይህ ቡድን

በዋናነት በሠራተኛና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራ ሲሆን ሌሎች ጉዳይ የሚመለከታቸው

የመንግስት መ/ቤቶች ድርጅቶች ማሕበራትና ተቋማት ያቀፈ ይሆናል፡፡ በክልልም በተመሳሳይ ሁኔታ

በክልል ሠራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ቢሮ የሚመራ ይሆናል፡፡

2. የተጎጂዎች ድጋፍና መልሶ ማቋቋም የሥራ ቡድን

የዚህ ቡድን አወቃቀር በዋነኛነት ለሰው የመነገድና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ተጎጂዎች

ድጋፍ እንክብካቤና መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን ጉዳይ በቀጥታ ከሚመለከታቸው

የመንግስት ተቋማት ተወካዮች በተጨማሪ በጉዳዩ ላይ የሚሰሩ የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና አገር በቀል

መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያካትታል፡፡ ተግባራቸውም ተጎጅዎችን በተገቢው መልኩ ለመደገፍ

የቅብብሎሽ አሰራር መዘርጋት፣ ስራውን በተቀላጠፈ እና ተመሳሳይነት ባለው መልኩ ለማከናወንና

አገልግሎቱን ለመስጠት የተሟላ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት እንዲኖር በማድረግና በአጠቃላይ ከተጎጂዎች
ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ስራ ጋር የተገናኙ አስፈላጊ የአሰራር ስርዓቶችን የሚዘረጋ ይሆናል፡፡ ቡድኑ በዋናነት

በከተማ ስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ የሚመራ ሲሆን ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸውን

መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ያቀፈ ይሆናል፡፡ በክልልም በተመሳሳይ ሁኔታ በክልል

የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ቢሮ ወይም ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ይህን ስራ የሚመራው የመንግስት

ተቋም የሚያስተባብረው ይሆናል፡፡

3. የወንጀል መከላከልና ህግ ማስከበር የሥራ ቡድን

ይህ ቡድን በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚንቀሳቀሰው አገሪቱ በወንጀሎቹ ዙሪያ የፈረመቻቸውና

ያፀደቀቻቸውን እንዲሁም የህግ አካል ያደረገቻቸውን ዓለም አቀፍ ሰነዶች፣ ህጎች ደንቦች ፕሮቶኮሎች

ተፈጻሚነት መከታተልና ማስተግበር፣ የድንበር አካባቢን ቁጥጥር እንዲጠናከር ለጉዳዩ ባለቤቶች የአቅም

ግንባታ ስራን ማከናወን፣ በህግ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ ትብብሩ እንዲጠናከር የተለያዩ ፕሮግራሞችን ነድፎ

የሚንቀሳቀስ ነው፡፡ የስራ ቡድኑ የሚመራው በጠቅላይ ዐ/ሕግ ሆኖ የተለያዩ የህግ አስከባሪ አካላትን ያቀፈ

ይሆናል፡፡ በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ያሉ የህግ ማእቀፎች አተገባበር የመገምገም እና ማሻሻያ የማድረግ፣ ክስ

ከመመስረትና የድንበር ቁጥጥር ሁኔታንም የእለት ተእለት ተግባሩ በማድረግ ያከናውናል፡፡ በክልልም

በተመሳሳይ በጠቅላይ ዐ/ሕግ የሚመራ ይሆናል፡፡

4. የጥናትና ምርምር የስራ ቡድን

የዚህ የስራ ቡድን ኃላፊነት የተቀናጀ የፍልሰት አስተዳደር ለመዘርጋት የሚያስችል ጥናት ከስራ ቡድኖች እና
ከብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር እንዲካሄድ ያደርጋል፤ ከዚህ ቀደም
በፍልሰት ዙሪያ የተጠኑና በየወቅቱ የሚከናወኑ ጥናቶችን በማሰባሰብ ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ የከፍተኛ
የትምህርት ተቋማት በፍልሰት ዙሪያ ጥናት እንዲካሄዱ የማስተባበር ስራ የሚሰራ ሲሆን የስራ ቡድኑ
የሚመለከታቸውን አካላት በማስተባበር በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሰብሳቢነት የሚመራ
ይሆናል፡፡ በየክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከዚህ የስራ ቡድን ጋር በጋራ እና በቅንጅት የሚሰሩ
ይሆናል፡፡

5. የዳያስፖራ ተሳትፎና ልማት የስራ ቡድን

ይህ የስራ ቡድን በዳያስፖራ ኤጀንሲ ሰብሳቢነት የሚመለከታቸውን ተቋማት በማካተት የተደራጀ ሲሆን
ኃላፊነቱም የዳያስፖራ አባላትን በሀገራቸው የልማት ጉዳይ በተለይም የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ከማሳደግ፤
በኢንቨስትመንት መስክ እንዲሁም በሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ በያገባኛል ስሜት የበኩላቸውን
አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ምቹ ሁኔታዎች መዘርጋታቸውን ይከታተላል፤ ከዳያስፖራው የሚገኙ የእውቀት እና
የቴክኖሎጂ ሽግግር እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን ይከታተላል፤
የዳያስፖራው ማህበረሰብ ባህላቸውንና ታሪካቸውን የሚያውቁበትና የሚያዳብሩበት ምቹ ሁኔታዎች
እንዲፈጠሩ ይሰራል እንዲሁም ያስተባብራል፡፡

በክልል ይህን የስራ ቡድን በመስተዳደር ጽ/ቤት ስር የሚገኙት የዳያስፖራ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሚመራ ሆኖ
የሚመለከታቸውን አካላት በማካተት የሚደራጅ ይሆናል፡፡

6. የፍልሰት መረጃ እና አስተዳደር የስራ ቡድን

የዚህ የስራ ቡድን ዋነኛ ኃላፊነት ከመረጃ አሰባሰብና ትንተና ብሎም ስርጭት ጋር የተያያዙ የአሰራር

ስርዓቶችን በመቅረጽ በተለያዩ ኩነቶች ለአብነት በህዝብና ቤት ቆጠራ ሥራዎች፣ በስነ-ህዝብ እና ሌሎች

የናሙና ጥናቶች ውስጥ የስደት፣ የሀገር ውስጥ መፈናቀል እና አጠቃላይ የፍልሰት ጉዳዮች በማካተት መረጃ

ለመሰብሰብና ለመተንተን የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀርጻል፡፡ በመረጃ አሰባሰብና አያያዝ ረገድ

የሚመለከታቸውን አካላት ያማክራል፤ ድጋፍ ያደርጋል፤ ሀገራዊ የተጣጣመ የፍልሰት መረጃ እንዲኖር

ከሚመለካተቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፡፡ በተጨማሪም የስራ ቡድኑ በፍልሰት ጉዳይ

ለሚወሰኑ ውሳኔዎች፣ ለሚወጡ ፖሊሲዎች፣ ህጎች እና ስተራቴጂዎች ግብዓት የሚሆን መረጃ አደራጅቶ

ይይዛል፣ ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ ያደርጋል፡፡

የስራ ቡድኑም የሚመለከታቸውን በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ የሚሰበስቡ ተቋማትን በማካተት በማዕከላዊ

እስታስቲክስ ኤጀንሲ ሰብሳቢነት የሚመራ ነው፡፡

2. የብሔራዊ እና የክልል ትብብር ጥምረት ግንኙነት ስርዓት

በሰው መነገድ እና ሰውን በህገወጥ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚከናወኑ ተግባራት ብሎም
አጠቃላይ እንደ ሀገር ያለውን የፍልሰት አስተዳደር ስርዓት ለማጠናከርና በአግባቡ ለመምራት እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ
ከፍልሰት ጋር ተያይዞ የሚወጡ ፖሊሲዎችና የእስትራቴጂክ አቅጣጫዎች በተጨባጭ ተግባራዊ ለማድረግ የብሔራዊ
የትብብር ጥምረቱ ከክልሎች ጋር የሚኖረው ግንኙነት መሰረታዊና ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ብሔራዊ የትብብር ጥምረቱም ሆነ የስራ ቡድኖች ከክልል የትብብር ጥምረትና የስራ ቡድኖች የሚኖረውን
ግንኙነት ማሰቀመጡ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ለማሳየት ተሞክሯል፡፡
በዕቅድ ዝግጅት የሚኖር ግንኙነት፡- የብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ አጠቃላይ እንደ ሀገር በሚከናወኑ ዕቅዶች እና
እስትራቴጂክ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከክልል የጥምረት አደረጃጀቶች ጋር የተናበበ ስራ ለመስራት ያስችል ዘንድ በዕቅድ ዝግጅት
ወቅት የሚኖር ግንኙነት ወሳኝ ነው፡፡ ይህ ማለት በብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ ስር የተደራጁት ስድስቱ የስራ ቡድኖች
በክልሎች ከሚደራጁ ተመሳሳይ የስራ ቡድኖች ጋር በዕቅድ ዝግጅት ላይ ወጥነት ያለው እና የተናበበ ዕቅድ ያዘጋጃሉ ማለት
ነው፡፡ ሁሉም የሚታቀዱ ስራዎች በፌዴራል ደረጃ ብቻ የሚፈጸሙ እንዳለመሆናቸው መጠን በዕቅድ ዝግጅት የሚኖር
ግንኙነት በክልል እና በፌዴራል ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራትን ለመለየት እና በጋራ የሚፈጸሙ ጉዳዮችንም ለማየት ወሳኝ
ምዕራፍ ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም የመጀመሪያውና ዋነኛው የግንኙነት ስርዓት በዚህ አግበብ የሚታይ ይሆናል፡፡ እዚህ
ጋር አብረን የምናየው ጉዳይ በፌዴራል ደረጃም ሆነ በክልል ደረጃ አጠቃላይ የጥምረቱን ስራ የማስተባበር ኃላፊነት
የተጣለባቸውን የጠቅላይ ዐ/ሕግ አደረጃጀቶችን ሲሆን እነዚህ ተቋማትም እነደ ስራ ቡድን የሚኖራቸው ግንኙነት እንዳለ
ሆኖ የፌዴራሉ ጥምረት ጽ/ቤት እና የክልል ጥምረት ጽ/ቤቶችም በተመሳሳይ ሁኔታ በዕቅድ ዝግጅት ወቅት የመናበብና
የመቀናጀት ስራ ወሳኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ በየወቅቱ በየዘርፉ በሚለዩ የግንኙነት አግባብ ላይ በመመርኮዝ ሌሎች የግንኙነት
ዘርፎችን ይኖራሉ፡፡

ምዕራፍ አምስት
5 የክትትል፤ የድጋፍ እና የግምገማ ስርዓት
1. የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ሥርዓት፣
በስትራቴጂክ ዕቅዱ ዘመን የዕቅዱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ሥርዓት መዘርጋት
ያስፈልጋል፡፡
2. የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ሥርዓት ዓላማ፡-
1. በብሔራዊ የትብብር ጥምረቱ ስትራቴጂ የተቀመጡ ግቦች፣ ውጤቶች፣አቅጣጫዎች የማስፈጸሚያ ስልቶች
የሥራ ቡድኖች በዓመታዊ ዕቅድ ተካተው እየተፈጸሙ ስመሆናቸው ለማረጋገጥ፣
2. የሚከናወኑ ሥራዎች ወደፊት ተጠናክረው የሚሄዱበትን አቅጣጫ ለማመላከት፣
3. በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመለየት፣ ትክክለኛና ወቅታዊ መፍትሔ ለማፈላለግና ድጋፍ
ለመስጠት እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ
በዚሁ መሠረት የክትትል፣ የድጋፍልና የግምገማ ዓላማዎችን ለማሳካት ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው የምንከተላቸው
የክትትል፡ ድጋፍና ግምገማ ስትራቴጂዎች እንደሚከተለው ይሆናል ፦
1. ስትራቴጂክ ዕቅዱን መሠረት ያደረገ ዓመታዊ ዕቅድ በጥምረቱና በሥራ ቡድኖች አማካይነት
ይዘጋጃል፣
2. ስትራቴጂክ ዕቅዱን መሠረት ያደረገ ዝርዝር ድርጊት መርሃ ግብር በጥምረቱና በሥራ ቡድኖች
አማካይነት ይዘጋጃል፣
3. በዕቅድ ዘመኑ የጥምረቱ አባላት የግማሽ ዓመትና ዓመታዊ የአፈጸጸም ሪፖርቶች አዘጋጅው ያቀርባሉ;
4. የአፈጻጸም ግምገማ መድረኮች ይዘጋጃሉ፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ምርጥ ተሞክሮዎች ይቀመራሉ፣
5. በተሰጠው ግብረ መልስ መሠረት አስፈላጊው ማስተካከያዎች ይደረጋሉ፣
6. በፌዴራልና በየደረጃው የመስክ ምልከታዎች /ሱፐርቪዥን/ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ሌሎች የግንኙነት
ዘዴዎችን በመጠቀም የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ሥራዎች ይሰራሉ፣
7. የትራቴጂክ የዕቅዱ የመካከለኛ እና የመጨረሻ ጊዜ አፈጻጸም (ግምገማ ይደረጋል)፣
8. በግምገማው በተገኘው ግብረ መልስ መሠረት ቀሪ የዕቅድ ዘመኑ እንዳስፈላጊነቱ ክለሳ ሊደረግ
ይችላል፡፡
9. በክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሂደት የብሔራዊ ምክር ቤት ሚና ፣
1. ብሔራዊ የፍልሰት አስተዳደር አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፣
2. የዕቅድ አፈፃፀም ወቅታዊ ሪፖርቶች የሚመለከታቸው አካላት እንዲያቀርቡ ያደርጋል፣
3. የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችን ይገመግማል፣ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
4. በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ክትትልና ድጋፍ ይሰጣል፣የእርምት አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፡፡
5. በክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሂደት የብሔራዊ የትብብር ጥምረት ሚና፣
1. የጥምረቱንና የሥራ ቡድኖችን ዕቅድ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
2. ወቅታዊ የአፈጻጸሞ ሪፖርቶችን ይገመግማል፣ አቅጣጫ ይሰጣል፣
3. በየደረጃው ለተዋቀሩ የክልል የትብብር ጥምረት መዋቅሮች ይከታተላል ይደግፋል፡፡ እንዲሁም የመስክ
ጉብኝት ፕሮግራም ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፡
4. በክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ሂደት የየቡድን አስተባባሪ ተቋማት ሚና፣
1. ከስትራቴጂክ ዕቅድ የተቀዳ የቡድን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃሉ፣
2. የዕቅድ አፈጻጸማቸውን ሪፖርት በየጊዜው በማዘጋጀት ያቀርባሉ፣
3. በየደረጃው ለተዋቀሩ የክልል የትብብር ጥምረት የሥራ ቡድኖች ይከታተላሉ፣የደግፋሉ፣ የዕቅድ አፈጻጸማቸውን
ይገመግማሉ፣
4. የየክልሉን የሥራ ቡድኖች ሪፖርት በመሰብሰብ ለብሔራዊ ትብብር ጥምረት ጽ/ቤት ያቀርባሉ፣
5. የዕቅድ አፈጻጸሙ ከተገመገመ በኋላ በሚሰጣቸው ግብረ መልስ መሠረት የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡

You might also like