You are on page 1of 11

የአንድነት ይበልጣል መረዳጃ

ዕድር መተዳደርያ ደንብ


May 30 2016 እ . .
አ አ
አንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር መተዳደሪያ ደምብ

ማዉጫ፥-

አንቀጽ 1 የዕድሩ ዓላማና፣ ዕድሩ ሊመሰረትበት የቻለበት ምክንያት ቁጥር 2. የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ስለ

ማቋቋም አንቀጽ 2 የዕድሩ ሥም በተመለከተ ሥያሜና ትርጉሙ ቁጥር 1 ሥያሜና ትርጉም ቁጥር 2 መዋጮ ማለት

ቁጥር 3 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ጠቅላላ ተከፋይ ተጠቃሚ (Beneficiary) ማለት ቁጥር 4 የአንድነት

ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ቡድን ማለት ቁጥር 5 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የቡድን ሃላፊ ማለት ቁጥር 6
የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የአባል ወኪል(ተወካይ)ማለት ቁጥር 7 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር

የቤተሰብ ተወካይ ማለት ቁጥር 8 አባል ማለት አንቀጽ 3. ሥምና ዓርማን በተመለከተ ቁጥር 1 ስምናዓርማ

አንቀጽ 4. ሥምና ዓርማን ስለመጠበቅ ቁጥር 1 ሥምና ዓርማን ስለመጠበቅ አንቀጽ 5 የአስተዳደር ኮሚቴ ቁጥር 1

የአስተዳደር ኮሚቴን በተመለከተ አንቀጽ 6. የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል ስለመሆን ቁጥር.1 አባል

ስለመሆን ቁጥር.2 ከዘር ከሀይማኖት ከፖለቲካ መድሎ ነጻ መሆኑን ቁጥር.3 የመመዝገብያ ፎርም አሞላልን የሚገልጽ

ቁጥር.4 የአባልነት ማረጋገጫ አንቀጽ 7. የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የቡድን መሪ የሥራ ሃላፊነት

ቁጥር 1.የቡድን መሪ የስራ ድርሻ ተግባር እና ዝርዝርን በተመለከተ አንቀጽ 8.የዕድሩ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት

በሚለዮበት ግዜ ለጽሕፈት ቤቱ ስለ ማሳወቅ ቁጥር 1 የአባላት ሞት ሪፖርት ስለ ማድረግ ቁጥር.2 አባሉ የሞተዉ

በቶሮንቶ ከተማ ከሆነ መታወቅ ያለበት የግዜ ገደብ ቁጥር 3. አባሉ የሞተዉ ከቶሮንቶ ከተማ ዉጭ ከሆነ ሪፖርት

መደረግ ስላለበት የግዜ ገደብ ቁጥር 4. ከላይ በቁጥር 2 እና 3 የተጠቀሰዉ ከሆነ መቅረብ ስለአለበት የጽሁፍ

ማስረጃ በተመለከተ ቁጥር 5. ከቁጥር 1 እስከ 5 ድረስ ያሉት ድንጋጌዎች ካልተፈጸሙ ሊያስከትሉ የሚችሉት

ችግሮች አንቀጽ 9. በሞት ስለተለየ የዕድሩ አባል ለዕድርተኛዉ ስለማሳውቅ

ቁጥር.1. የዕድሩ ጽህፈት ቤት የአባሉን ሞት በተመለከተ ለቡድን መሪ የሚገልጽብትን የአሰራር መንገድን በተመለከተ።

ቁጥር.2. የዕድሩ አባላት በሞት በሚለዩበት ግዜ ዕድሩ ለአባላት ለማሳውቅ የሚጠቀምበተን መገናኛ ዘዴን

በተመለከተ። አንቀጽ 10. የዕድሩ አባላት ዕድርተኛ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የሚደረግን የገንዘብ መዋጮን በተመለከተ

ቁጥር.1.የዕድሩ አባላት ሞት በደረሰበት ግዜ ዕድርተኛዉ ማዋጣት ያለበት የገንዘብ መጠን እና ተሰብስቦ ሊድርስዉ የሚችለዉን
የገንዘብ ሃይልን በተመለከተ የሚገልጽ።

1
ቁጥር.2.የዕድሩ አባላት ቁጥር አየጨመረ እና እየቀነሰ በሚመጣ ግዜ ለአባላቱ ሊከፈል ስለሚችል የገንዘብ መጠንና

ዕድርተኛዉ ሊያዋጣ ስለሚገባዉ የገንዘብ መጠን ገለፃን በተመለከተ አንቀጽ 11. የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር

አጠቃላይ ክፍያ በተመለከተ አንቀጽ 12. የዕድሩ የገንዘብ ማሰባሰብያን በተመለከተ አንቀጽ 13. የአባላት የገንዝብ ክፍያን
የማጠቃላያ የግዜ ገደብ በተመለከተ

አንቀጽ 14. የዕድሩ አባላት በመተዳደሪያ ደምቡ መሰረት የግዜ ገደብን ባለመከተል ሊደርስባቸዉ የሚችል ስንብትን በተመለከተ

አንቀጽ 15. የዕድሩ አባላት በተለያዩ ጉዳዮችና የጤና መታወክ ሲደርስባቸዉ ሊደረጉ ስለሚገባቸዉ ዝርዝር
ሁኔታዎች

ቁጥር 1. በወቅቱ ክፍያን ለመፈጸም የማያስችሉትን ልዮ ልዩ ምክንያቶችን በተመለከተ

ቁጥር 2. በአንቅጽ 15/በቁጥር 1.በተዘረዘረዉ ምክንያት ለሚደርሱት ችግሮች የማመልከቻ ተቀባይነት የግዜ ገደብን በተመለከተ

አንቀጽ 16. የዕድሩ አባላትን የመዋጮ አከፋፈለ ሥርዓትን በተመለከተ አንቀጽ 17. ዉክልናን ስለመስጠት

ቁጥር 1. ተወካይ የተሰጠዉን አደራ ባለ መወጣት አባሉን ሊያስጠይቁ ስለሚችሉት ዝርዝር መግለጫዎችን ድንጋጌን በተመለከተ

አንቀጽ 18. ከአባልነት ለመታገድ የሚያስችሉ ዝርዝር ሁኔታዎች በተመለከተ አንቀጽ 19. ከዕድሩ የተሰናበቱ አባላትን ስለማሳወቅ

አንቀጽ 20. የመኖሪያን አድራሻን ስለመቀየር ቁጥር


1. አድራሻን ስለመቀየር ቁጥር 2. ስልክና ኢሜልን
ስለ መቀየር አንቀጽ 21. የጉዞ ቅፅን ስለ መሙላት

ቁጥር 1. የጉዞ ሰንዱን የሞላ የዕድሩ አባል ከሃገር ዉጭ(ከካናዳ)ስለሚቆይበት የግዜ ገደብን የሚደነግግ ዝርዝር መግለጫ
ቁጥር 2. በአንቀጽ 21/ቁጥር 1 ከተገለጸዉ የግዜ ገደብ በላይ ስለሚቆዩ አባላት ዝርዝር ሁኔታዎች የሚያስረዳ አንቀጽ 22. የዕድሩ

አባላት በራስ ፍቃድ አነሳሽነት ከዕድሩ መሰናበትን

አንቀጽ 23. በአንቀጽ 22 ቁጥር 2 በራሳቸዉ ፍቃድ የተሰናበቱት አባላት ተመልሰዉ እድሩን ለመቀላቀል ሲፈልጉ በምን መልኩ
ዕድሩ ሊቀበላቸዉ የሚችልበትን ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ
አንቀጽ 24. በዕድሩ ላይ ተደራራቢና(ተከታታይ)ሞት በደረሰ ግዜ በምን መልኩ መስተናገድ እንዳለበት የሚዘረዝር
ድንጋጌ

አንቀጽ 25. የዕድሩ የገንዘብ መክፈያ ዘዴን በተመለከተ አንቀጽ 26. የዕድሩ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩ ግዜ

የፎቶግራፍ ስርጭትን በተመለከተ አንቀጽ 27. የዕድሩ አበላትን ጠቅላላ አሃዛዊ መረጃን ስለማሳወቅ አንቀጽ 28.

የሟች ቤተሰብና የዕድሩ ጽህፈት ቤት ተወካዮች ሓላፊነትና የሥራድርሻ፣ከቁጥር 1 እስከ 5


አንቀጽ 29. ቤተሰብ የሌለዉ የዕድሩ አባል በሞት በሚለይበት ግዜ ከጽህፈት ቤቱ ሊያገኝ ስለሚችለዉ ዕገዛ ዝርዝር መግለጫ

አንቀጽ 30. የዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊ ስብስባንና የድምጽ አሰጣጥን ሥርዓት በተመለከተ አንቀጽ 31.

የዕድሩን መተዳደሬያ ደንምብ ስለማሻሻልና መለወጥን አንቀጽ 32. የዕድሩ የሥራ አስኪያጅ አባላትን በሕግ አለ

2
መጠየቅን የሚገልጽ ድንጋጌ በተመለከተ አንቀጽ 33. ለዕድሩ ጠቃሚና ገንቢ የሆኑ አዳዲስ የአስራር ሃሳቦችን

ስለማመንጨት በተመለከተ አንቅጽ 34. የዕድሩ አባልተኛ ለሆነ ሰው ህይውቱ ባለፈ ግዜ የሚያድርገው ክፍያን

በተመለከተ አንቀጽ 35. የቦርድ የሥራ አኪያጅ አባላት የስራ ዘመን አንቀጽ 36. የዕድሩ የመተዳደሪያ ደምብ

የሚፀናበት ዘመን

3
የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር መተዳደሪያ ደምብ

አንቀጽ 1 የእድሩ ዓላማና ሊመሰረት የቻለበት ምክንያት:-

1.1 የዕድሩ ዓላማና፣ ሊመሰረትበት የቻለበት ምክንያት በካናዳ ኦንታርዮ ግዛት፣ በቶሮንቶ ከተማ እና አካባቢዋ ነዋሪ የሆኑ
ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያኖች እንዲሁም ሌሎች ዓላማዉን የሚደግፉና ደንምቡን የተቀበሉ ተቀራራቢ ባህል
ያላችዉ ሁሉ በአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ስር በመሰባሰብ አንድ የዕድሩ አባል ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ለቀብሩ
ማስፈጽሚ የሚወጣዉ የገንዘብ መጠን ለአንድ ሰዉ ወይንም ለቤተሰቡ አቅም በላይ እየሆነ በማስቸገሩ በየግዜዉ የሟችን
ፎቶ ግራፍ በሳጥን ላይ ለጥፎ በየንግድ ቤቱ፤ በየሃይማኖት ተቋሞችና በመሳሰሉት ድርጅት ውስጥ ለቀብር የሚሆን
አስፈላጊዉ የገንዘብ መጠን እስኪሰበሰብ ድረስ የሟች አስክሬን ሳይቀበር ለረጅም ቀናት በማቆየት ከዚያም አልፎ ተርፎ ወደ
ተለያዩ ተቈሞችና ድርጅቶች እንዲሁም ወደ ግለሰቦች ቤት በማምራት ከባህላችን ዉጭ በሆነ ተግባር ላይ ከተሰማረን ዉለን
ከርመናል ይህንን ከፍተኛ ችግር ለማቃለል ይቻል ዘንድ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር ቀለል ባለና ሁሉንም
የህብረተሰብ ክፍል ባሳተፈ መልኩ በዚህ ደንምብ ውስጥ የተገለጽዉን የገንዘብ መጠን በማዋጣት የሟቹን የቀብር ሥነ -
ሥርዓት በክብር ለማስፈጽም ይረዳ ዘንድ በማሰብ ሕግና ደንምብ ረቆ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መሠረተ ሃሳቦች ላይ
በመመርኮዝ በዚህ መተዳደሪያ ደንምብመሠረት ሊቋቋም ችሏል።

1.2 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ስለማቋቋም


ይህ ዕድር ከዛሪ May
30 2016 እ.አ.አ ጀምሮ በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ የኦንታርዮ ህግ በሚያዘዉ መሰረት ከትርፍ
ነጻ በሆነ ድርጅት ሥር ተመዝግቦ ተቋቁሟል አንቀጽ 2 የዕድሩ ስያሜ ትርጉም:-

2.1 ምንም ትርጉም እስካልተሰጠዉ ድረስ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ትርጉም የጋራ ሃይልን፤ጉልብትንና የመሳስሉትን
አባባልን የሚገልጽ ምሳሌዊ ዘይቤን ተመርኩዞ የተሰየመ ነው።

2,2 በዚህ የመተዳደሪያ ደንምብ ዉስጥ የተገለጹት ቃላቶች የሚኖራቸዉ ትርጉሞች በመተዳደሪያ ደንምቡ በተገለጸዉ መሠረት ብቻ
ነዉ

2.3 የአባላት መዋጮ ማለት:አንድ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል በሞት ሲለይ የዕድሩ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት
ለተለዩት ዕድርተኛ እያንዳንዳችዉ አባላቶች የሚያዋጡት መጠኑ በሕግ የተወሰነ የአንድ ግዜ ክፍያ መዋጮ ይባላል

2.4 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ጠቅላላ ተከፋይ(Beneficiary) ማለት:በአንድ አባል ላይ ሞት በደረሰ ግዜ በአባልነት
ተመዝግበዉ የሚገኙት አባላት በሙሉ እያንዳንዳቸዉ የሚያዋጡት የአንድ ግዜ ክፍያ(መዋጮ) በአንድነት ተጠቃሎ
የሚገኘዉን ገንዘብ የሚረከብ ሰው ተከፋይ ይባላል

2.5 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር ቡድን ማለት:የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የግኑኝነት መስመር ይቀላጠፍ
ዘንድ ለእያንዳንዱ አባል በሃያ አምስት(25)የአባላት ቁጥር የተደራጀበት ምድብ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር
ቡድን ተብሎ ይታወቃል

2.6 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ቡድን ሃላፊ ማለት:-


የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር ዉስጥ በሃያ አምስት (25)የአባለት ብዛት የተመደበዉን ቡድን በሃላፊነት የሚሰራዉ
አባል የቡድን ሃላፊ በመባል ይታወቃል

2.7 የአንድነት ይበልጣል የአባል ወኪል(ተወካይ) ማለት:የዕድሩ አባል በተለያየ አጋጣሚ በአካል ከአካባቢዉ ቢርቅ ፤ ክፍያን
ለመፈጽም ባይችል እንደራሱ ሆኖ ክፍያዉንም ሆነ ሌሎች ጎዳዮችን እንዲያስፍጽምለት የወከለዉ ግለሰብ የአባል
ወኪል(ተወካይ)በመባል ይታወቃል

4
2.8 የቤተሰብ ተወካይ ማለት:የሟች ቤተሰብ ከዕድሩ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ለሚሰበሰበዉ የአባላት መዋጮና ሌሎች
ጉዳዮችንም ጭምር በሃላፊነት የሚመድቧቸዉ ሶስት የቤተሰብ ተወካዮች ናቸዉ

2.9 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል ማለት:የዕድሩን ዓላማና ቃል ኪዳንን የፈጸመ የራሱን መብትና፣ ግዴታዉን በዉል
ተረድቶ መመዘኛዉን በሟሟላት በአባልነት ዕድሩ ባህረ መዝገብ ላይ ሙሉ ስም አድራሻዉና ፊርማው የተመዘገበና በዕድሩ
ሥራ አስኪያጅ አባላት በፊርማ የጸደቀ ነዉ

2.10 የመዋጮ መሰብሰብ ማለት:የዕድሩ አባላቶች ክፍያቸዉን ወይንም መዋጮ በግዜው ለእድሩ
ማስገባት ማለት ነው

2.11 የአባላት እንደራሴ ማለት:የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል በዕድሩ ደንምብ መሰረት የአባልነቱን ቅጽ ሲሞላ
ሞት ቢያጋጥመዉ የቀብሩን ሥርዓት የሚስፈጽምለት ብሎም ከዕድሩ የሚከፈለዉን ጠቅላላ ክፍያ እንዲረከብ ዉክልና
የተሰጠዉ ግለሰብ ማለት ነዉ

አንቀጽ 3 ስምና አርማ:-

በአንቀጽ 2 ቁጥር 1 ላይ በተደነገገዉ መሰረት የዕድሩ ስምና ዓርማዉ ምንም አባባል እስከአልተሰጠዉ ድረስ የዕድሩ ዓርማ

በእያንዳንዱ አባላት መታወቂያ ደብተርና፣ የዕድሩ ደረሰኞችና በመሳሰሉት ፋይሎች ሁሉ ይቀመጣል አንቀጽ 4 ስምና ዓርማን

ስለመጠበቅ:-

ይህ የመረዳጃ ዕድር የስምና የዓርማዉ ብቸኛ ተጠቃሚ ባለቤት ሲሆን ማንኛዉም ሰዉ ወይንም ድርጅት ይህንን ስምና ዓርማ
በማስመስል፣ በመለወጥ ቃላት በመቀነስም ሆነ በመጨመር ለግል ጥቅማችዉ ወይንም ለማንኛዉም የድርጅት ስራ
ማራመጃነት መጠቀም በህግ የተከለከለ ነዉ።

4.2 ይህ ዕድር ከዚህ ዓለም በሞት ከሚለዩ አባላት እና እድሚያቸው ክ 18 አመት በታች ለሆኑ ልጆቻቸው መዋጮ በስተቀር ለሌሎች
የተለያዩ ምክንያቶች ወይንም ችግሮችየዕድሩ ዓባላትን ገንዘብእንዲያሰባስቡ አያደርግም

4.3 ይህ ዕድር ከሃይማኖት ፣ከፖለቲካ ወዘተ እንዲሁም ከእድሩ ዓላማ ዉጭ የሆኑትን ማንኛዉንም ነገሮች አያስተናግድም
አንቀጽ 5 የአስተዳደር ኮሚቴ:-

የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የአስተዳደር ኮሚቴ አንድ ሰብሳቢ፣ አንድ ጸሃፊ፣ አንድ የሂሳብ ሹም፣ ሁለት የሕዝብ
ግኑኝነት ሃላፊ፣ በአጠቃላይ አምስት ኮሚቴ አባላትን በመያዝ የዕድሩን የሥራ እንቅስቃሴ በመከፋፈልና በመረዳዳት እንደ አንድ አካል
በጋራ እየተንቀሳቀሱ የዕድሩን ሥራ በበላይነት የሚመሩ ሲሆን ቁጥራችዉ እንደአስፈላጊነቱ ሊጨምር ወይንም ሊቀንስ ይችላል።
አንቀጽ 6 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል ለመሆን የሚስፈልጉት መስፈርቶች:-

6.1 ማንኛዉም ግለሰብ ዕድሜዉ ከአሥራ ስምንት (18)ዓመት በላይ የሆነና ነዋሪነቱ በቶሮንቶና አካባቢዉ የሆነ፣ የዕድሩን ዓላማ
በመረዳት ወዶ በፈቃዱ የተቀበለ ዕድሩ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ፍቃደኛ የሆነና እራሱን ለዕድሩ ህግ ለማስገዛት የወሰነ
ማንኛዉም ሰዉ ሁሉ ዕድሩ የተቋቋመበትን የቃል ኪዳን መርሆዎች ለወገኔ እደርሳለሁ፣ እርሴን አዛለሁ፣ ሞትን አሰባለሁ፣
ቃሌን አከብራለሁ በማለት እራሱን ለገባበት ቃል ኪዳን ለማስገዛት የወሰነ ሁሉ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል
መሆን ይችላል

6.2 ማንኛዉም ሰዉ በዘሩ፣ በጽዎታዉ፣ በሃይማኖቱ፣ በሥራዉና በፖለቲካ አመለካከቱና በጤናዉ መታወከ ምከንያት የዕድር አባል
ከመሆን አይከለከልም

5
6.3 ማንኛዉም ከጂቲኤ ክልል ውጭ የሚኖር ሰዉ አባል ለመሆን የኦንታርዮ መንጃ ፍቃድ ወይም የፓስፖርት መታወቅያ ፎቶ ኮፒ
ከአባልነት ቅጽ ጋር ሞልቶ አያይዞ በኢሜል ማቅረብ አለበት፡ የኮምፒውተር መጠቀምን የማይችሉ አባላት የእድሩን አመራር
በስልክ ደውልው ቢያነጋግሩ ፎርሙ እንዲደርሳቸው ይደረጋል

6.4 ማንኛዉም ሰዉ የዕድሩ አባል መሆኑን የሚያረጋግጠዉ የዕድሩን የአባልነት ፎርም ሲሞላና የእድሩን መለያ ቁጥር ሲወስድ ብቻ
ነው

አንቀጽ 7 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የቡድን መሪ የሥራ ሃላፊነት:-

የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር የቡድን መሪ ወይንም ምክትል መሪ በስሩ ካሉት ሃያአምስት (25) አባላት ጋር የቅርብ
ግኑኝነት በመፍጠር ከአመራር አባላት የሚደርሰዉን ወቅታዊ መረጃ በአስቸኳይና በፍጥነት በተገኘዉ የመገናኛ ዘዴ በመታገዝ በስሩ
ላሉት አባላት ማስተላለፍና የተላለፈዉን መረጃ ለአባላቱ በሙሉ መድረሱን በማረጋገጥ ከአባላት የቀረቡ ጥያቄዎችና ችግሮች ካሉ
የአስትዳደር ኮሚቴዉ እንዲያዉቀዉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት። አንቀጽ 8 የአባላትን ሞት ለዕድሩ ጽህፈት ቤት ስለማሳወቅ:-

8.1 አንድ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ ሟቹ የአንድነት ይበልጣል
የመረዳጃ ማህበር አባል መሆኑን ማረጋገጥ የቻለ ማንኛዉም የዕድሩ አባል የራሱን ስምና የአባልነቱን ቁጥር በመግለጽ ለዕድሩ
ጽህፈት ቤት ማሳወቅ ይኖርበታል አንድ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር አባል ሲሞት ይህንኑ ሁኔታ ከዕድሩ ዉጭ ሰዉ
ሲያሳዉቅ የሟቹን ስምና የመታወቂያ ቁጥሩን ለዕድሩ ጽህፈት ቤት መግለጽ ይኖርበታል

8.2 አባሉ የሞተዉ በቶሮንቶና አካባቢዉ ከሆነ እጅግ ቢዘገይ በሰባት(7) ቀን ዉስጥ ዕድሩ ማወቅ አለበት
8.3 አባሉ የሞተዉ ከኦንታርዮ ዉጭ ከሆነ ነገርግን በሰሜን አሜሪካን ከሆነ በሃያ (20)ቀን ውስጥ ዕድሩ ማወቅ አለበት
8.4 አባሉ የሞተዉ ከሰሜን አሜሪካን ክልል ዉጭ ከሆነ(30)ቀናት ዉስጥ የሞቱ ሪፖርት ለዕድሩ መቅረብ ይኖርበታል
8.5 በአንቀጽ 8.4 እንደተጠቀሰዉ የአባሉ ሞት የደረሰዉ ከሰሜን ከአሜሪካን ክልል ዉጭ ከሆነ የሟቹን የአሟሟት ሁኔታ የሚገልጽ
የሀኪም ማስረጃ (Death Certificate)በካናዳ መንግስት ተረጋግጦ ሪፖርቱ በሰላሳ(30)ቀን ዉስጥ ለዕድሩ ማቅረብ
ግዴታ ነዉ

8.6 ከዚህ በላይ በአንቀጽ 8 ቁጥር 1-5 የተገለጠዉ የቀን ገደብ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተዘረዘረዉ ቀን ገደብ በኃላየ ሚቀርበዉ የሞት
ሪፖርትም ሆነ ማስረጃ ዋጋ ስለማይኖረዉ ዜናዉን ለአባላት ከመግለጽ ዉጭ የገንዘብ መዋጮ ሊጠይቅበት አይችልም አንቀጽ 9
የዕድርተኛዉን ሞት ለጠቅላላ አባላት ስለማሳወቅ:-

9.1 የአንድነት ይበልጣል ዕድር ጽህፈት ቤት የአንድ አባልን ሞት እንደሰማ ስለሪፖርቱ እዉነተኛነት ማረጋገጥና ሁኔታዉን በአስቸኳይ
ለቡድን መሪዎች በማሳወቅ አባላቶች በግዜዉ ግዴታቸዉን እንዲወጡ ያደርጋል

9.2 በተጨማሪም ዕድሩ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በመጠቀም የሟችን ማንነት የሚገጽ ፎቶግራፍን ለቡድን መሪዎች
ያስተላልፋል አንቀጽ 10 ስለ አባላት መዋጮ:-

10.1 አንድ አባል ከዚህ አለም በሞት ሲለይ የሚከፈለው ክፍያ በአባላት ብዛት ቁጥር በ 25 ብር ተባዝቶ ክፍያው ጣርያ ክ
20000.00 የካናዳ ብር አይበልጥም

6
10.11 የአባላት ጠቅላላ ቁጥር በአሁኑ ሰዓት አምስት መቶ(500)ይሆናል በማለት የተገመተ ነዉ ነገር ግን የአባላቱ ቁጥር
በመመርኮዝ ጠቅላላ ክፍያዉን ለአባላት እንደ የግዜዉ ሁኔታ የዕድሩ ጽህፈት ቤት ለአባላቱ ያስታዉቃል አንቀጽ 11 የአንድነት
ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር ጠቅላላ ክፍያ:-

11.1 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ጠቅላላ ክፍያ ማለት በወቅቱ በዕድሩ ዉስጥ ያሉት አባላት የከፈሉት መደበኛ መዋጮ
በአንድነት ተጠቃሎ ከሃያሺ ዶላር($20,000.00)ሳይበልጥ ለሟች ቤተሰብ የሚከፈል ይሆናል አንቀጽ 12 የክፍያ ዘዴዎች:-

12.1 ወደ ፊት ለጠቅላላ አባላቱ አመቺነትና እንደ ባንክ አሰራር በዝርዝር ይነገራሉ


12.2 ዘመናዊ ይባንክ መክፍያና ገንዝብ ማዘዋወርያ ዘዴዎችን በመጠቀም ክፍያን መፈጸም ማለት ነው አንቀጽ 13 የአባላት የክፍያ

ግዜ ገደብ:-

13.1 አንድ አባል ከዚህ ዓለም በሞት በሚለይበት ግዜ ለዕድርተኞች በተለያየ የዕድሩ የመገናኛ ዘዴዎች ከተገለጸበት ግዜ ጀምሮ እስከ
አስር(10)ቀን ድረስ በዚህ ደንምብ ዉስጥ በተዘረዘሩት የክፍያ ዘዴ በመጠቀም ክፍያቸዉን ይፈጽማሉ አንቀጽ 14 አባላት ከዕድሩ

በግዚያዊነት ስለመስናበት:-

14.1 ማንኛዉም የዕድሩ አባል ክፍያዉን በወቅቱ ያልከፈለ አባል ክፍያዉን በአምስት(5)ቀናት ዉስጥ ማጠናቀቅ ግዴታዉ ይሆናል
ሆኖም ክፍያዉን በአሥር(10)ቀናት ዉስጥ ሳያጠናቅቅ የሞት አደጋ ቢደርስበት የእድሩ ተጠቃሚ አይሆንም።

14.2 በአንቀጽ 14 ቁጥር 1 መሰረት አስፈላጊዉን ክፍያ ያለምንም ምክንያት ያልፈጸመ አባል ከዕድሩ ይሰናበታል

አንቀጽ 15 የዕድሩ አባላት በተለያዩ ጉዳዮችና የጤና መታወክ ሲደርስባቸዉ ሊደረጉ ስለሚገባቸዉ ዝርዝር ሁኔታዎች:-

15.1 ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሁኔታዎች ክፍያን በወቅቱ ላለመክፈል እንደበቂ ምክንያት ሆነዉ ሊታዩ ይችላሉ
ሀ.በወቅቱ አባሉ በሆስፒታል ዉስጥ ተኝተዉ በሃኪም እየተረዱ ከሆነ
ለ.አባሉ በወቅቱ በእስር ላይ የሚገኝ ከሆነ

15.2 በአንቀጽ 15.1 ሀ፣ለ በተጠቀሰዉ መሠረት ከሆነና በቂ የሆነ የጽሁፍም ሆነ የሰዉ ማስረጃ ማቅረብ ከቻለ ከዕድሩ አይሠናበትም
ሞትም በደረሰበት ግዜ ዕድሩ አስፈላጊዉን ሁሉ ዕርዳታ ያደርግለታል ኮሚቴዉም ጉዳዩን በማጥናት ዉሳኔ ይሰጥበታል

15.3 ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ምክንያት አንቀጽ 15 ቁጥር/1 ሀ፣ለ አባላት ምክንያታቸዉን በመዘርዘር ክፍያዉ ከመጠናቀቁ
ከአምስት ቀን(5)በፊት ለዕድሩ አመራር አካል በምንኛውም መገናኛ በኢሜል፣ በወረቀት ጽሁፍ ወይንም በስልክ ማቅረብ
ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ይህንን ሳይፈጽሙ አሥር ቀን(10) ካለፈ የሚቀርበዉ ማንኛዉም የጹሁፍም ሆነ የስልክ ሪፖርት
ተቀባይነት የለዉም በአባልነትም አይቀጥሉም!

አንቀጽ 16 የዕድሩ አባላትን የመዋጮ አከፋፈል ሥርዓት:-

7
16.1 አባላት ክፍያችዉን የሚፈፅሙት በባንክ የቀጥታ ክፍያ ብቻ ይሆናል

አንቀጽ 17 ስለ አባላት ዉክልና መስጠት(ወኪል):-

17.1 ማንኛዉም አባል በቅርብ እያለም ሆነ ርቆ ሲሄድ የሚፈልግዉን ሰዉ እንደራሱ አድርጎ ሊወክል ይችላል ሆኖም ተወካይ
ባልፈጸመዉ ግዴታ ከመጠየቅ አያድነዉም

አንቀጽ 18 ከአባልነት ለመታገድ የሚያስችሉ ዝርዝር ሁኔታዎች:-

18.1 አንድ የዕድሩ አባል በዚህ ደንምብ ዉስጥ ያሉትን ግዴታዎች ባለመፈጸም ወይንም የዕድሩን ህልዉና የሚያናጋ፣የሚያፈርስና
ብሎም የሚጎዳ አባላትን የሚከፋፍል፣የሚበትን ድርጊትን ሲፈጽም የተገኘ አባል የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ጥሪ አድርጎለት እንዲመክር
ይደርጋል ነገር ግን ይህንን ሁሉ ህግ ጥሶ የተገኘ አባል ከዕድሩ ያሰናብታል ከመሰናበቱም በፊት በነበሩት ማንኛዉም ጉዳዮች ዕድሩን
አይጠይቅም። አንቀጽ 19 ከዕድሩ የተሰናበቱ አባላትን ስለማሳወቅ:-

19.1 አንድ አባል ከአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ማህበር ከአባልነቱ በጥፋቱም ይሁን በራሱ ፈቃድ ሲሰናበት ዝርዝር ሁኔታዉና
የአብልነት የመለያ ቁጥሩ ለቡድን መሪዎችና ለጠቅላላ አባላት እንዲያዉቁት በተለያየ መገናኛ ዘዴዎች ይሰራጫል። አንቀጽ 20
የመኖሬያን አድራሻንና ስልክ ወይንም ኢሜልን ስለመቀየር:-

20.1 ማንኛዉም የዕድሩ አባል ከካናዳ ሃገር ሳይወጣ በማንኛዉም ቦታ ሆኖ የዕድሩን ህግና ደንምብ ተከትሎ ግዴታዉን እስከተወጣ
ድረስ በአባልነት መቀጠል ይችላል
20.2 ማንኛውም የዕድሩ አባል የስልክ ወይንም የኢሜል ለውጥ ማድረጉን ወድያውኑ ለዕድሩ ማሳወቅ ይኖርበታል አንቀጽ 21 የጉዞ

ቅጽን ስለመሙላት:-

21.1 ማንኛዉም የዕድሩ አባል ከካናዳ ዉጭ ለሚያደርገዉ ጉዞ የዕድሩ ተጠቃሚ ለመሆን ይችል ዘንድ የጉዞ ቅጽ መሙላት አለበት
21.2 አባሉ የጉዞዉን ቅጽ ከሃገር ዉጭ ለሚቆይባቸዉ ዘጠና ቀናት(90) ከዕድሩ ሙሉሽፋን የሚያገኝ ሲሆን የጉዞ ቅጹን እራሱ
ወይንም ወኪሉ በኢሜል ወይንም በስልክ መሙላት ይኖርብታል ነገር ግን ይህንን ሳያደርግ አባሉ በሄደበት የሞት አደጋ
ቢያጋጥመዉ ተጠቃሚ አይሆንም።

21.3 የጉዞ ቅጹን ሞልቶ የሄደ የዕድሩ አባል በዘጠና ቀናት ዉስጥ ለሚደርስበት የሞት አደጋ የዕድሩን ሙሉ ክፍያ ያገኛል ሆኖም
በአንቀጽ 20 ቁጥር 1 እንደተጠቀሰዉ የአሟሟቱን ዝርዝር የሚገልጽ በሃኪም እና በካናዳ መንግስት የተረጋገጠ የሞት ማስረጃ

(Death Certificate)ማቅረብ ይኖርበታል ነገር ግን ከዘጠና ቀናት (90) በኋላ ለሚደርስ የሞት አደጋ ለአባላቱ ከመግለጽ ሌላ
ምንም ሊጠይቅበት አይችልም አንቀጽ 22 የዕድሩ አባላት በራስ ፍቃድ አነሳሽነት ከዕድሩ መሰናበትን:-

22.1 ማንኛዉም አባል በማንኛዉም ግዜና ሰዓት በፁሁፍ ደብዳቤ ወይም በኢሜል ለእድሩ በማሳወቅ አባልነቱን ማቋረጥ ይችላል፣
ነገርግን ወደፊት ወደዕድሩ መመለስ በፈለገ ግዜ እንደ አድስ መመዝገብ ይችላል

አንቀጽ 23 ከ 18 አመት በታች ላሉ የተመዘገቡ የአባልተኛ ልጆች ላይ የሚደርስን የሞት አደጋ በተመለከተ።

23.1 በአንድነት ይበልጣል ዕድር ውስጥ የተመዘገበ ማንኛውም አባል በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ከ 18 አመት በታች
የሚገኙትን

8
ሀ. የውለዳቸውን ልጆቹን
ለ. በህጋዊ አሳዳጊነት (Legal Guardian) ያሚያሳድጋቸውን ልጅቹን ማስመዝገብ ይችላል።
23.2 በእነዚህ ልጆቹ ላይ የሞት አደጋ ቢደርስባቸው ዕድሩ ለማንኛውም አባል የሚያደርገውን ክፍያም ሆነ እርዳታ ያደርግለታል።
23.3 የአንድነት ይበልጣል ዕድር በእነዚህ የተመዘገቡ ልጆች ላይ የደረሰው የሞት አደጋ ባስመዘገቧቸው ወላጆች ምክንያት
የተፈጸመ የሰው ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ከሆነ እና በልጆቹ የሞት አድጋ ከፍርድ ቤትም ሆነ ከፖሊስ በቂ የሆነ ከወንጀሉ ነፃ
መሆናቸውን የሚያሳይ መረጃ እስካላቀረቡ ድረስ ምንም አይነት እርዳታን አያደርግም
23.4 የአንድነት ይበልጣል ዕድር በተመዝገቡ የአባላት ልጆች ላይ የሞት አደጋ ቢደርስ
ሀ. እርዳታ የሚሰጠው አንድ ክፍያ በአንድ ልጅ ብቻ የተወሰነ ይሆናል ባልና ሚስት የአንድነት ይበልጣል
አባሎች ቢሆኑም
እንኳ የሚያገኙት ክፍያ በአንደኛው አባል በኩል ብቻ የተወሰነ ይሆናል።
ለ. የአንድነት ይበልጣል ዕድር ከትዳራቸው በፍቺም ሆነ በሌላ ምክንያት የተለያዩ ወላጆች ዕድሩን ሳይመዘገቡም
ሆነ ከተመዘገቡ በኋላም ከትዳራቸው የተለያዩ ከሆነ ክፍያውን የሚሰጠው ለአንድ ልጅ አንድ ክፍያ ብቻ ይሆናል
ሐ. በትዳር ለተለያዩ አባላት የአንድነት ይበልጣል ዕድር ክፍያውን የሚሰጥው ለሞተው(ችው) ልጅ ህጋዊ አሳዳጊነት
ላለው አባል ወላጅ ብቻ ይሆናል።
መ. አባላት ከትዳራቸው ተለያይተው ነገር ግን ምንም አይነት በህግ የተረጋገጠ የህጋዊ አሳዳጊነት ማስረጃ
የሌላቸው ከሆነ አንዱን ክፍያ ለሁለቱም ወላጆች እኩል በመክፍል ክፍያውን
ያስረክባል።

አንቀጽ 24 በዕድሩ ላይ ተደራራቢና(ተከታታይ)ሞት በደረሰ ግዜ:-

24.1 በሁኔታዎች አጋጣሚ ከሁለት አባላት በላይ በተመሳሳይ ቀን ወይንም በአንድ ሳምንት ዉስጥ የሞት አደጋ ቢያጋጥም በዚህ ሕግ
ደንምብ ዉስጥ ያለዉ የክፍያ መጠን እንደተጠበቀ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ የክፍያ የግዜ ገደብን በሚመለከት የአስተዳደር
ኮሚቴዉ አስቸኳይ ዉሳኔ በመወሰን ለአባላት ያሳዉቃል

አንቀጽ 25 የዕድሩ የገንዘብ መክፈያ ዘዴን በተመለከተ:25.1 ዕድሩ ማናቸውንም ክፍያ በቼክ ያከናውናል

አንቀጽ 26 የዕድሩ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩ ግዜ የፎቶግራፍ ስርጭትን በተመለከተ:-

26.1 የዕድሩ አባላት ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩ ግዜ የፎቶግራፍ ስርጭትን በተመለከተ የሟቹ ቤተሰቦችን ሙሉ ፈቃድኝነትን
የሚጠይቅ ይሆናል ማለትም ቤተሰብ ፎቶዉ እንዲበተን ካልፈልገ ቃላቸዉ የተከበረ ይሆናል ፈቃደኛ ከሆኑ ለየቡድን መሪ ይበተንና

ለአባላት ሊደርስ ይችላል እንዲሁም በዕድሩ ድረ ግፅ ላይ ይለጥፋል አንቀጽ 27 የዕድሩ አባላትን ጠቅላላ አሃዛዊ መረጃን ስለማሳወቅ:-

27.1 የዕድሩ ድረ ገፅ የአባላትን ጠቅላላ አሃዛዊ ቁጥር በየግዜው ያሳውቃል አንቀጽ 28 የሟች
ቤተሰብ ተወካዮች ሃላፊነትና የሥራ ድርሻ:-

28.1 በሟች ቤተሰብ የተወከሉ ሦስት(3) ሰዎች ከዕድሩ አመራር ኃላፊ ጋር በመሆን ሙሉ ኃላፊነቱን በመዉሰድ ማናቸውንም
ጉዳይ ለዕድሩ የሚያቀርቡ ይሆናሉ ያለዉን ሥራ በቅደም ተከተል የሚሰሩ ሲሆን የዕድሩም አስተዳደራዊ ሥራዉን በበላይነት

9
ይመራል ለተፈጻሚነቱም የእያንዳንዱን የዕድር አባልተኛ ሙሉ ትብብር ያስፈልገዋል አንቀጽ 29 ቤተሰብ የሌለዉ የዕድሩ አባል
በሞት በሚለይበት ግዜ:-

29.1 አንድ የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር አባል የቅርብ ቤተሰብ ሳይኖረዉ በሞት በተለየ ግዜ የዕድሩ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት
በአስቸኳይ ለሟች እንደቤተሰብ ሆነዉ የሚያገለግሉ ኮሚቴዎችን ያዋቅራሉ።

29.2 በአንቀጽ 29 ቁጥር 1 የተዋቀረዉ ኮሚቴ በአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ኃላፊ አመራር ሰጪነት ሙሉ ዝግጅቱን እስክ
ፍጻሜዉ ድረስ ከሌላዉ አባል ባልተለየ መልኩ ምንም ነገር ሳይጎድል ሥርዓቱ እንዲፈጽም ያስደርጋሉ በምን መልኩ መፈጽም
እንዳለበት የዕድሩ አመራር የስራ ዝርዝር ያወጣል እንደአስፈላጊነቱም የዕድሩ አመራር ለጠቅላላ የዕድሩ አባላት ሪፖርት ያቀርባል።
አንቀጽ 30 የዕድሩ ጠቅላላ ጉባኤ ዓመታዊ ስብስባንና የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት:-

30.1 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ጠቅላላ ጉባኤ በዓመት አንድ ግዜ ብቻ ይሆናል
30.2 የጠቅላላ ጉባኤዉን ዉሳኔ የሚሹ ግዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ አስቸኳይ ጉባኤ ሊጠራ ይችላል
30.3 ከግማሽ በላይ የሚሆኑ አባላት ጠቅላላ ጉባኤን እንዲጠራ ሊጠይቁ ይችላል አንቀጽ 31 የዕድሩን

መተዳደሬያ ደንምብ ስለማሻሻልና መለወጥን:-

31.1 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር መተዳደሪያ ደንምብ ዓላማዉንና የቆመበትን ተግባር እስካልተፃረረ ድረስ የኦንታርዮ እና
የካናዳን ከትርፍ ነጻ ለሆኑ ድርጅቶች ያወጣዉን ህግ (Not-for-Profit Corporations Act, 2010, S.O. 2010, c.
15) እስከአልጣሰ ድረስ ለማህበረሰቡና ለዕድሩ ዕድገት ጠቃሚ ሆኖ ከተገኘ የመተዳደሪያ ደንቡን እንደአስፈላጊነቱ ማሻሻል ይቻላል
ይህንንም ለማድረግ የጠቅላላ የአመራር አባላቱን አባላጫ ድምጽን ማግኝትን ይጠይቃል ለእድሩ አባላትም የተለወጠውን የህጉን
ማሻሻያ አንቀጽና ቁጥር ጠቅሶ እዲያሳዉቅ ይህ መተዳደሪያ ደንምብ ያስገድዳል። አንቀጽ 32 የዕድሩ የሥራ አስኪያጅ አባላትን በሕግ
አለመጠየቅን የሚገልጽ ድንጋጌ በተመለከተ:-

32.1 የዕድሩ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በሙሉ ፈቃደኝንት በተመሠረተ የሚሰሩ ግለሰቦች ናቸዉ ምንም ዓይነት ክፍያም ሆነ ካሳ ከእድሩ
አያገኙም ሆኖም እነዚህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎታቸዉን በማበርከት ላይ ሌት ከቀን ለዕድሩ ማደግና መሻሻል የሚጥሩ ናቸዉ
ስለሆነም ለዕድሩ ስራ ላይ ለሚፈጽሙት ከሥራቸዉ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠረዉ ስህተት በህግ ሊጠየቁ አይችሉም

አንቀጽ 33 ለዕድሩ ጠቃሚና ገንቢ የሆኑ አዳዲስ የአስራር ሃሳቦችን ስለማመንጨት በተመለከተ:-

33.1 የዕድሩን ደንምብና ህግ ሳይነካ ከዓላማዉ በተቃራኒ እስካልቀረበ ድረስ በማንኛዉም ግዜ ለአባላቶች ጥቅምና ለዕድሩ መጎልበት
ሲባል ማሻሻያዎች ይደረጉበታል ገንቢ ሃሳቦችንም ከአባላት ይቀበላል የአስተዳደር ኮሚቴም የራሱን ጠቃሚ ሃሳቦችን እያመነጨ

ይሰራል። አንቀጽ 34 ማህበሩ አባልተኛ ለሆነ ሰው ህይውቱ ባለፈ ግዜ የሚያድርገው ክፍያን በተመለከተ

34.1 አንድ የማህበሩ አባልተኛ ህይወቱ ማለፉን የስራ አስካሄጆቹ ባፋጣኝ ማረጋግጥ

10
34.2 አባልተኛው ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ከተረጋገጠ በኋላ የዕድሩ ሊቀምንበር፣ገንዝብ ያዥ እና አንድ ሌላ የዕድሩ ስራ አስኪህጅ
በመሆን በባንክ የወጭ ሰነድ ላይ ስማቸውን እና ፊርማቸውን በማስፈር አስፍላጊውን ገንዝብ ከባንክ ወጭ በማድረግ
ክፍያውን ለሟች አባል ለወከለው ተጠቃሚ(Beneficiary) ሰው ያስረክባሉ
34.3 በተለያየ ምክንያት ሊቀመንበሩ ውይንም ገንዘብ ያዡ ከህገር ውጭ፣ብህመም በመሳሰሉት ምክንያት እክል ቢገጥማቸውና የባንክ
ወጭ ሰነድ ለመፈርም ባይችሉ የቀሩት አመራር አባላት እነሱን ተክተው ተፍላጊውን ወጪ ማድረግ ይችላሉ
34.4 አባል የወከለው ሰው ሳይኖረው ከዚህ አለም በሞት ቢለይ አንቀጽ 29 ላይ የተጠቀሰው ይፈጸማል። አንቀጽ 35 የዕድሩን ድህረ
ገጽ በተመለከተ

35.1 የመረዳጃ ዕድሩ ከሚጠቅምባችዉ የመገናኛ ዘዴዎች ዉስጥ አንዱ የማህበሩ ድረ ገጽ ነዉ ይህንንም በተመለከተ የድረ ገጹ ሥምና
አድራሻ www.andinetyebeltal.com በመባል ይታወቃል

35.3 የዕድሩ አባላት በዚሁ ድረ ገፅ ላይ ማንኛዉንም የዕድሩን አገልግሎት በተመለከተ መረጃን፣አስተያይቶችን መስጠትም ሆነ
ማግኘት ይችላሉ የመመዝገብያ ቅፆችንም መቅዳት ይችላሉ።

35.4 የዕድሩ ድረ ገጽ የማንንም የፖለቲካ ድርጅት፣የሃይማኖትና የዘረኝነት ሊያንፀባርቅ የሚችልን ማንኛዉንም ማስታወቂያ
አያስተናግድም ይህንንም እንዳያደርግ የኦንታርዮ ህግ ከትርፍ ነጻ ለሆኑ ድርጅቶች ያወጣዉ ህግ አጥብቆ ይመክራል አንቀጽ 36
የቦርድ የሥራ አሥኪያጅ አባላት የስራ ዘመን

36.1 የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር የሥራ አስኪያጅ ዘመን ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ይሆናል የዋና ሰብሳቢና ጸሀፊ የስራ
ዘመን አምስት አመት ሲሆን የተቀረዉ የስራ አስኪጅ የስራ ዘመን ሶስት ዓመት ብቻ ይሆናል

36.2 የስራ ዘመናችዉን የፈጽሙ የስራ አስኪያጆች ጠቅላላ አባላት ባሉብት የመሸኛ ዝግጅት ተደርጎላችዉ በአባልነታችዉ ይቀጥላሉ
አዲሱ የስራ አስኪያጅ ችግር ሲያጋጥመዉ የስራ ልምዳችዉን በማካፈል በጋራ ይሰራሉ

36.3 ማንኛዉም የዕድሩ አመራር አባል የስራ ዘመኑን ቢጨርስም የዕድሩ አባላት ለቦታዉ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸዉ እንደ አዲስ
ሊመርጡት ይችላሉ

አንቀጽ 37 የዕድሩ የመተዳደሪያ ደምብ የሚፀናብት ዘመን

ይህ ዕድር ከዛሪ ከ May


30,2016 እ.አ.አ የኦንታሪዮ ህግ በሚያዘዉ መሰረት Not-for-Profit
Corporations Act, 2010, S.O. 2010, c. 15 ከትርፍ ነፃ በሆነ ድርጅትነት ተመዝግቧል ስለዚህም
የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር ተብሎ ይጠራል ይህንንም ስም በተመለከተ በኦንታሪዮ ጠቅላይ ግዛትና በፊደራላዊ
መንግሥት የሃገር ዉስጥ ገቢ ቢሮም በኩል በህጋዊነት ተመዝግቦ ይገኛል።

May 30,2016

የአንድነት ይበልጣል የመረዳጃ ዕድር መተዳደሪያ ደምብ።


Andinet Yebeltal By laws

11

You might also like