You are on page 1of 29

የ ኃ/የተወሰነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት

ሥራ ማህበራት ዩኒየን
መተዳደሪያ ደንብ
(ሞዴል)
የ ኃ/የተወሰነ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን
መተዳደሪያ ደንብ
1. የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ስምና አድራሻ
1.1. የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ስም
2. አድራሻ
2.1. ክልል/ከተማ አስተዳደር
2.2. ዞን/ክፍለ ከተማ
2.3. ወረዳ
2.4. ቀበሌ
2.5. ስልክ ቁጥር
2.6. ፋክስ ቁጥር
2.7. ፖ.ስ.ቁ
2.8. ድረ ገጽ
2.9. ኢሜይል
3. የስራ ክልል
3.1. የስራ ክልሉ

4. አርማ እና ማህተም መግለጫ


4.1. አርማ
4.1.1.

4.2. ማህተም
4.2.1.


5. ትርጉም
በኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009የተቀመጠው ትርጓሜ እንዳለ ሆኖ የቃሉ አገባብ በህግ ሌላ
ትርጉም የማያሰጥ ካልሆነ በስተቀር በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ፡-
5.1. “ግለሰብ”፡-ማለት በህግ መብት የተሰጠው የተፈጥሮ ሰው ማለት ሲሆን ይህም የወንድን ወይም የሴትን ጾታ
የሚያካትት ነው፡፡
5.2. “ሸሪዓ” ማለት የእስልምና ተከታዮች የሚመሩበት ከፈጣሪ የወረደ ትዕዛዝ ነው፡፡

1
5.3. “መደበኛ ቁጠባ” ማለት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበሩ በሚወሰነው የጊዜ ገደብ እና ዝቅተኛ የገንዘብ
መጠን መሰረት በማድረግ አባሉበግሉ የወሰነውን የቁጠባ መጠን በተከታታይነት ያለማቋረጥ የሚቆጠበው ቁጠባ
ነው፡፡
5.4. “የፍላጎት ቁጠባ” ማለት አባሉ በፍላጎቱ ከመደበኛው ቁጠባ በተጨማሪ በተለያዩ የቁጠባ አይነት የሚቆጠበው ቁጠባ
ነው፡፡
5.5. “የልጆች ቁጠባ” ማለት እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑና በኅብረት ሥራ ማህበሩ የስራ ክልል የሚኖሩ ልጆች
በቤተሰቦቻቸው በኩል የሚቆጥቡት የአደራ ቁጠባ አይነት ነው፡፡
5.6. “ብድር” ማለት አባላት ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ የሚሆን ከገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ወይም
ከፋይናንስ ተቋማት በሚደረግ ስምምነት መሰረት በተወሰነ ጊዜ ቆይታ ተመላሽ የሚሆን እና ወለድ የሚያስከፍል
ወይም ወለድ የማያስከፍል ገንዘብ ነው፡፡
5.7. “ወለድ” ማለት ግለሰቦች ወይም ተቋማት ለቆጠቡት ገንዘብ የሚከፈላቸው ወይም ለተበደሩት ገንዘብ የሚከፍሉት ዋጋ
ነው፡፡
5.8. “ወለድ የሚያስገኝ የፋይናንስ አገልግሎት” ማለት የቁጠባ እና የብድር የፋይናንስ አገልግሎት ሆኖቆጣቢዎች ወለድን
የሚያገኙበት ወይም ተበዳሪዎች ወለድ የሚከፍሉበት አገልግሎት ነው፡፤
5.9. “ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት” በሸሪዓ መሰረት በሚሰጡ የቁጠባና የብድር አገልግሎቶች ወለድ መቀበልና
መክፈልን በጥብቅ የሚከለክል አገልግሎት ማለት ነው፡፡
5.10. “ተካፉል አገልግሎት” ማለት በሸሪያ መሰረት የሚሰጥ የአነስተኛ መድን ዋስትና አገልግሎት ነው፡፡
5.11. “አረቦን” ማለት ለአነስተኛ መድን ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎትን ለመስጠትእንዲቻል ከተበዳሪ የሚሰበሰብ
ገንዘብ ነው፡፡
5.12. “ተጨማሪ እጣ” ማለት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ለተለያዩ ኢንቨስትመንት ስራዎች ለማከናወን
ለአባላት የሚሸጠው እጣ ነው፡፡
5.13. “መነሻ እጣዎች” ማለት አንድ ገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የዩኒየን አባል መሆን ሲፈልግ ሙሉ አባል
ለመሆን የሚገዛው እጣ ነው፡፡
5.14. “የአባላት ካፒታል” ማለት አንድ አባል የመደበኛውን ቁጠባ ደህንነት ለመጠበቅ በሚያስችል ምጥጥን ተሰልቶ አባሉ
የሚያስቀምጠው ገንዘብ ነው፡፡
5.15. “የፋይናንስ አገልግሎት አካታችነት” ማለትአባል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የፋይናንስ
አገልግሎቶችን በጥራትና በተደራሽነት መጠቀም ሲችሉ ነው፡፡
6. የዩኒየኑ አላማ፣
6.1. የአባላትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መደበኛ እና የፍላጎት ቁጠባናየተለያዩ የብድር አገልግሎቶች በመስጠት፣
የኢንቨስትመንት አቅም በማጎልበት ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም መፍጠር ነው፡፡
6.2. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት አባላትን መሰረት ያደረገ የፋይናንስ አገልግሎት በመስጠት
የኢንቨስትመንት አቅም ማጎልበት፣
6.3. የአነስተኛ መድን ዋስትና ወይም የተካፉል አገልግሎት በመስጠት የአባላትን ቁጠባና የኅብረት ሥራ ማህበሩ
ያሰራጨው ብድር ደህንነቱ የጠበቀ እንዲሆንናየሚከሰተውን ማህበራዊ ቀውስን ማስወገድ፣
6.4. የፋይናንስ አገልግሎት አካታችነትን በማሳደግ፣ የኅብረተሰቡን የፋይናንስ ክህሎትናየቁጠባ ባህልን በማዳበር
2
የአባላትን በራስ የመተማመን አቅም ማጎልበት፣
6.5. የፋይናንስ ተቋማት እና ኅብረት ሥራ ማህበራት የፋይናንስ ትስስር በመፍጠር የሚከሰተውን የፋይናንስ እጥረትና
ክምችት ችግርን መፍታት፣
7. ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ተግባራት
7.1. የተለያዩ የቁጠባና ብድር አሰራር በመዘርጋት ከአባላት ቁጠባ መሰብሰብና የብድር አገልግሎት መስጠትና ማስመለስ፣
7.2. አባላት ገንዘባቸውን አዋጭነት ባለው ስራ እንዲያውሉ የምክር አገልግሎት መስጠት፣
7.3. የአደራ ገንዘብ ተረክቦ ያስቀምጣል፣የሀዋላ ወይም የገንዘብ መላላክ አገልግሎት መስጠት፣
7.4. ተዘዋዋሪ ብድሮችን ተረክቦ ያስተዳደራል፣
7.5. የወለድ አልባ የፋይናንስ አግልገሎት በአባሉ ሙሉ ፍላጎትና ጥያቄ መሰረት ራሱን በቻለ አደረጃጃት አገልግሎት
መስጠት፣
7.6. የአነስተኛ መድን ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎት ከአባል ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን ለአባሉ
ይሰጣል፣
7.7. ዘመናዊ የሂሳብ አሰራር ስርዓት መዘርጋት፣
7.8. ለአባላት፣ ለአመራር አካላት፣ ቅጥር ሰራተኞች አስፈላጊው ትምህርት፣ ስልጠና መስጠት፣
7.9. የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በመስጠት የዩኒየኑን ካፒታል ማሳደግ፣
7.10. ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓት መዘርጋት ዩኒየኑን እና አባላት የኮር ባንኪንግ ስርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፣
7.11. አግባብ ያለው ባለስልጣን በሚፈቅደው መሰረት ለመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ኦዲት
አገልግሎት መስጠት፣
7.12. ለስራው አጋዥ የሚሆኑ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ማፍራትና ማስተዳደር
7.13. ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር፣
7.14. በዩኒየኑ የስራ ክልል አባል ያልሆኑ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አባል እንዲሆኑ ያደርጋል፣
7.15. ከሌሎች መሰል የገንዘብ ቁጠባ ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመሆን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ
ማህበራት ፌዴሬሽን ማቋቋም፣
7.16. ሌሎች በጠቅላላ ጉባኤ የሚሰጡ ተግባራትን ይፈጽማል፣
8. የኅብረት ሥራ መርሆች
8.1. አባልነት በፈቃደኝነትና በፍላጎት ላይ የተመሰረተ እና ለሁሉም ክፍት ማድረግ፣
8.2. ዲሞክራሲያዊ አሰራና አመራር ማስፈን፣
8.3. አባላት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማስቻል፣
8.4. ራስ አገዝና ራስን በራስ ማስተዳደር፣
8.5. ለአባላት፣ለአመራር አካላትና ለቅጥር ሰራተኞች ተከታታይ ትምህርት ፣ስልጠናና መረጃ መስጠት፣
8.6. ከሌሎች አቻ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር ኅብረት መፍጠር ፣
8.7. በአካባቢ ልማት መሳተፍ፣
9. የኅብረት ሥራ እሴቶች፣
9.1. ራስን በራስ መርዳት፣
9.2. የግል ኃላፊነትን መወጣት፣
3
9.3. የዲሞክራሲ ባህል ማስፋፋት፣
9.4. እኩልነት፣
9.5. ፍትሃዊነት፣
9.6. ወንድማማችነት፣
10. የአባላት የስነ-ምግባር ዕሴቶች፣
10.1. ታማኝነት፣
10.2. ግልጽነት፣
10.3. ተጠያቂነት
10.4. አሳታፊነት
10.5. ማህበራዊ ኃላፊነት፣
10.6. ለሌሎች ማሰብ ናቸው፣
11. አባል ለመሆን የሚያበቁ ሁኔታዎች፣

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ አባል መሆን
ይችላል፣
11.1. በኅብረት ሥራ ማህበራት ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት አግባብነት ባለው ባለስልጣን ተመዝግቦ የህጋዊ ሰውነት
ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያገኘ እና ወቅቱን ጠብቆ ያሳደሰ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር፣
11.2. በሌላ ተመሳሳይ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን አባል ያልሆነ፣
11.3. የዩኒየኑን መተዳደሪያ ደንብ፣ ውስጠ ደንብ፣ ዩኒየኑ ያወጣቸው የተለያዩ የውስጥ የስራ መመሪያዎች፣ የጠቅላላ ጉባኤ
ውሳኔዎችን የተቀበለና ግዴታውን ለመወጣት ፈቃደኛ የሆነ፣
11.4. በመተዳደሪያ ደንቡ የተቀመጠውን መመዝገቢያና የአባልነት መነሻ ዕጣ ለመግዛት የተስማማ፣
11.5. በመተዳደሪያ ደንቡ የተቀመጠውን መነሻ መደበኛ ቁጠባ ለመቆጠብ ፈቃደኛ የሆነ፣
11.6. በህግ ችሎታ ያለውና ተቀባይነት ያገኘ፣
11.7. አባል ለመሆን የመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ማቅረብ የሚችል፣
11.8. አባል ለመሆን የሚፈልግ የመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበሩ የፋይናንስ ሪፖርት ማቅረብ የሚችል፣
12. ለኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን አባልነት ስለሚቀርብ ማመልከቻ፣
12.1. አባል ለመሆን የሚፈልግ ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ለዚህ ተግባር ያዘጋጀውን የአባልነት ማመልከቻ ቅጽ ተሞልቶ
በስራ አመራሩ ፊርማ ለኅብረት ሥራ ዩኒየን የስራ አመራር ቦርድ ያቀርባል፣ ከማመልከቻው ጋር የሚከተሉት ተያይዘው
መቅረብ አለባቸው፣
12.1.1. የመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ
12.1.2. አግባብ ባለው አካል መመዝገቡን የሚያረጋግጥና የታደሰ ሰርተፊኬት፣
12.1.3. የፋይናንስ አቋሙን የሚያሳይ የፋይናንስ ሪፖርት፣
12.1.4. የመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አመራር አካላት ስም ዝርዝር፣ አድራሻና ፊርማ፣
12.2. የዩኒየኑ ቦርድ አመራር የቀረበለትን የአባልነት ማመልከቻ መርምሮ በ ቀናት ውስጥ አባልነት
ለጠየቀው መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባልነቱን ስለመቀበሉ በጽሁፍ መልስ ይሰጣል፣ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ

4
አሟልቶ አባል ይሆናል፣
12.3. አባልነቱን ያልተቀበለው ስለመሆኑ ያልተቀበለበትን ምክንያት በጽሁፉ ይመልስለታል፣
12.4. የዩኒየኑ ቦርድ አመራር አባል የሆነውን መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባል ስለመሆኑ ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት
ያደርጋል፣
12.5. አመልካቹ በውሳኔው ቅሬታ ካለው ለዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ በጽሁፍ ይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል፣
12.6. በድጋሚ አባል ለመሆን የሚፈልግ አመልካች በተመሳሳይ ሁኔታ ማመልከቻውን ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል፣
12.7. የአባልነት ማመልከቻ ዩኒየኑ ያዘጋጃል፣
13. ስለ አባላት ምዝገባ፣

ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ከዚህ በታች በተጠቀሱት ነጥቦች መሰረት የአባላት መዝገብ አዘጋጅቶ መዝግቦ
ይይዛል፣
13.1. የአባልነት መለያ ቁጥር
13.2. የአባል ኅብረት ሥራ ማህበሩ ስም፣ ዓይነት፣ አድራሻ፣ የተቋቋመበት ዓ/ም
13.3. በህግ የተመዘገበበት ቁጥርና ዓ/ም
13.4. አባል ሲሆን ያሉ አባላት በጾታ፣
13.5. አባል የሆነበት ቀን፣ ወር እና ዓ/ም
13.6. የገዛው እጣ መጠን እና የተከፈለ መመዝገቢያ፣
13.7. አባልነት ያቋረጠበት ቀን፣ ወርና ዓ/ም
13.8. ያቋረጠበት ምክንያት፣
14. የአባላት መብት
14.1. ስለ ዩኒየኑ እንቅስቃሴ የሚፈልገውን መረጃ ጠይቆ የማግኘት መብት፣
14.2. በወኪሎቹ አማካኝነት የዩኒየኑ ጉባኤ ላይ መሳተፍ፣ ሃሳብን በነጻ የመግለጽ፣ ድምጽ የመስጠት፣
14.3. አመራሮችን የመምረጥና የማሰናበት፣ እንዲሁም በአመራርነት የመመረጥ፣
14.4. ዩኒየኑ የሚሰጠውን አገልግሎትና ጥቅም የማግኘት፣
14.5. ዩኒየኑን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማንኛውንም ጥያቄ፣ ቅሬታ፣ አስተያየት ማቅረብና መልስ የማግኘት፣
14.6. ጥቅሞቹ ተከብረውለት በጥያቄው መሰረት የመሰናበት፣
15. የአባላት ግዴታዎች

በኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅና መመሪያ መሰረት እያንዳንዱ የዩኒየኑ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር
የሚከተለውን የመፈጸም ግዴታ አለበት፣
15.1. የመመዝገቢያ፣ ዝቅተኛውን የአባልነት እጣ ዋጋ የመክፈል እና ዝቅተኛውን መደበኛ ቁጠባ በወቅቱ የመቆጠብ፣
15.2. የዩኒየኑን መተዳደሪያ ደንብ፣ የውስጥ አሰራር መመሪያዎች፣ ውስጠ ደንቦችና ውሳኔዎች የማክበር እና የመፈጸም፣
15.3. በዩኒየኑ ጉባኤ ላይ መገኘት፣
15.4. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 50.6.1. ከተቀመጠው በላይ ያለ የዩኒየኑን ኪሳራ በጋራ የመካፈል፣
15.5. የዩኒየኑን የጋራ ንብረት መንከባከብ፣
15.6. አባሉ በገባው ውል መሰረት የወሰደውን ብድር በወቅቱ የመክፈል
5
በአነስተኛ መድን ዋስትና በተገባ ውል መሰረት መረጃን የማጠናቀር እና ከግለሰብ አባላት አረቦን ሰብስቦ ገቢ ማድረግ
15.7.

16. የመመዝገቢያ ክፍያ

16.1. ማንኛውም መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር የዩኒየኑ አባል እንዲሆን ሲፈቀድለት የመመዝገቢያ ብር (
) ይከፍላል፣

16.2. ለመመዝገቢያ የተከፈለ ገንዘብ ለከፋዩ ተመላሽ አይሆንም፣ ጥቅምም አይገኝበትም፣

16.3. የመመዝገቢያ ክፍያ ለዩኒየኑ የሚያስፈልጉ ሰነድ ማዘጋጃና ማደራጃ እንዲሁም ስራ ማስኬጃነት ይውላል፣

16.4. አንድ አባል ከዩኒየኑ ከተሰናበተ በኋላ እንደገና አባል እንዲሆን ከተፈቀደለት እንደ አዲስ አባል የመመዝገቢያ ክፍያ
ይከፍላል፣

17. ስለ እጣ (ሼር) ክፍያ

17.1. አባል እንዲሆን የተፈቀደለት መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ዩኒየኑ ካዘጋጀው እጣዎች ውስጥ የእጣ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

17.2. የአንድ እጣ ዋጋ ብር እንዲሆን ወስነናል፣ አንድ መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ቢያንስ


መነሻ እጣዎች (እጣ ) አባል ለመሆን መግዛት ይኖርበታል፣ ሆኖም እንዲሸጥ ከተወሰነው ጠቅላላ የእጣ መጠን
ውስጥ 50 በመቶ በላይ በዩኒየኑ ውስጥ ድርሻ አይኖረውም፣

17.3. ዩኒየኑ የተለያዩ ኢንቨስትመንት ስራዎችን ለማከናወን ሲፈልግ እጣዎችን በጠቅላላ ጉባኤ ወስኖ መሸጥ ይችላል፣
ሆኖም ተጨማሪው እጣ ሽያጭ በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተሸጦ መጠናቀቅ ይኖርበታል፣

17.4. እያንዳንዱ አባል በየጊዜው ከመደበኛ ቁጠባ እድገት ጋር የተጣጣመ የካፒታል መጠን እንዲኖረው የመደበኛው
ቁጠባውን  ያላነሰ ዋጋ ያለው ገንዘብ በካፒታል መልክ በዩኒየኑ በየጊዜው እየለየ
ያስቀምጣል፣

17.5. በአንቀጽ 17.4 መሰረት የካፒታል ገንዘብ ከመደበኛ ቁጠባ ጋር አብሮ ይሰበሰባል፣ የእጣና የአባላት ካፒታል ተለይቶ
ሂሳቡ መመዝገብ ይኖርበታል

17.6. የዩኒየኑ አባል እንዲሆን የተፈቀደለት አመልካች ከተፈቀደለት ቀን አንስቶ በ ጊዜ ውስጥ አባል ለመሆን
የሚያስችለውን የመነሻ እጣ መጠን ከፍሎ ማጠናቀቅ አለበት፣

17.7. ዕጣ እና የአባላት ካፒታል ተመላሽ የሚሆነው አባልነት ሲቋረጥ ነው፣

17.8. በየጊዜው ከቁጠባ ሂሳብ ጋር የሚሰበሰበው የአባለት ካፒታል በአባሉ የቁጠባ ደብተር ላይ ተመዝግቦ መያዝ አለበት፣

6
17.9. ከዩንየኑ ዕጣ ለገዛ ለማንኛውም አባል ኅብረት ሥራ ማህበራት ዕጣ ስለመግዛታቸው የሚያስረዳ የዕጣ ሰርተፍኬት
አዘጋጅቶ መስጠት አለበት፡፡

17.10. ከመደበኛ ቁጠባ ጋር የሚሰበሰብ የአባላት ካፒታል የመደበኛ ቁጠባ ደህንነት የሚጠብቅ በመሆኑ ገቢ በማያስገኙና
በረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት ላይ አይውልም፣ የአባላት ካፒታል አጠቃቀም አስመልክቶ በፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ
መሰረት የሚከናወን ይሆናል፣

18. ቁጠባ አሰራር፣


18.1. የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ከአባል መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር በጠቅላላ ጉባኤ በሚወስነው መሰረት
ወለድ የሚያስገኝ እና የማያስገኝ ቁጠባ ይሰበስባል፣

18.2. ዩኒየኑ ወለድ አልባ እና ወለድ የሚያስገኝ መደበኛ ቁጠባ ከአባላት ይሰብስባል፣
18.3. እያንዳንዱ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ቢያንስ ብር የሚሆነውን ዝቅተኛ መደበኛ
ቁጠባ ገንዘብ ለዩኒየኑ በ ጊዜ ገደብ ገቢ ያደርጋል፣ ሆኖም እያንዳንዱ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ
ማህበር ከዝቅተኛ ቁጠባ መጠን በላይ መቆጠብ ከፈለገ በማመልከቻ ጠይቆ በመደበኛነት መቆጠብ ይችላል፣
18.4. እያንዳንዱ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ዩኒየኑ በሚያዘጋጀው ማመልከቻ መሰረት መቆጠብ የሚፈልገውን
ወለድ አልባ ወይም ወለድ የሚያስገኝ ቁጠባን ለይቶ ለዩኒየኑ በማመልከቻ መጠየቅ ይኖርበታል፣
18.5. አባሉ በወለድ አልባ ወይም ወለድ በሚያስገኝ የመደበኛ ቁጠባ መጠንን ለመለወጥ ቢፈልግ ዩኒየኑ በሚያዘጋጀው
ማመልከቻ መጠየቅ ይችላል፣ ሆኖም ጥያቄው ተቀባይነት የሚኖረው የስራ አመራር ቦርድ ሲወስን ነው፣ መጠኑ
በአንቀጽ 18.3. ከተቀመጠው ዝቅተኛ መደበኛ ቁጠባ መጠን ማነስ የለበትም፣
18.6. የመደበኛ ቁጠባ ተቀማጭ ገንዘብ የብድር መጠንን ለመወሰን እና ለብድር ጥያቄ ዋስትና በመሆን ሊያገለግል
ይችላል፣
18.7. አባሉ ከዩኒየኑ እስካልተሰናበተ ድረስ ወለድ በሚያስገኝም ሆነ በወለድ አልባ የተቀመጠ መደበኛ ቁጠባ በማንኛውም
ጊዜ ለአባሉ ወጪ ሆኖ አይከፈለውም፣
18.8. ዩኒየኑ ከመደበኛ ቁጠባ ውጪ ያሉ የቁጠባ አገልግሎቶች መስጠት የሚችለው ቁጠባውን የመጠቀም አቅሙ ከፍተኛ
ሲሆን ብቻ ነው፣
18.9. ወለድ አልባ ወይም ወለድ በሚያስገኝ የፍላጎት ቁጠባ አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ አባላት ጥያቄዎቻቸውን ዩኒየኑ
ባዘጋጀው ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
18.10. ዩኒየኑ ከአባሉ ጋር በሚያደርገው ስምምነት መሰረት ወለድ በሚያስገኝ እና ወለድ አልባ የጊዜ ገደብ ቁጠባ አገልግሎት
ይሰጣል፣ ሆኖም የጊዜ ገደብ ቁጠባ አገልግሎት ከ ወራት ማነስ የለበትም፣
18.11. አባላት በፍላጎታቸው የቆጠቡት ገንዘብ በገቡት ውል መሰረት ታይቶ ማውጣት ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የቆጠቡትን ገንዘብ
ማውጣት የሚችሉት ገንዘቡ በብድር ዋስትናነት ካልተያዘ ብቻ ነው፣
18.12. ዩኒየኑ የቁጠባ መሰብሰቢያና ማውጫ እለታዊ የባንክ አገልግሎት ይሰጣል፣ ሆኖም ለወለድ አልባ አገልግሎት ራሱን
በቻለ ልዩ መስኮትና የሰው ኃይል መሆን አለበት፣
18.13. ዩኒየኑ ገንዘብና ንብረትን በአደራ የማስቀመጥ አገልግሎቶች ይሰጣል፣
18.14. የተሰበሰበ የቁጠባ ገንዘብ በሙሉ ህጋዊ በሆነ የፋይናንስ ተቋማት መቀመጥ ይኖርበታል፣
7
18.15. ዩኒየኑ ለወለድ አልባ ሆነ ወለድ ለሚያስገኙ የቁጠባ አገልግሎቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የሂሳብ
ሰነዶች፣ መዛግብቶች፣ ካዝናዎች፣ የክፍያ መስኮቶች ያዘጋጃል፣ ይህንን ስራ ማከናወን የሚያስችል የሰው ሀይል
እንዲኖረው ያደርጋል፣
18.16. ዩኒየኑ የቁጠባ መጠን ለማሳደግና እና ለማበረታት ሲባል ለአባላት የተለያዩ ማበረታቻዎችን አዘጋጅቶ መስጠት
ይቻላል፣
18.17. ዩኒየኑ ከአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመሆን የፋይናንስ ተጠቃሚ ያልሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን
እንደየ አካባቢው ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ የቁጠባ አይነቶች በማዘጋጃት ተጠቃሚና ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣
18.18. ዩኒየኑ ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ በጠቅላላ ጉባኤ በሚወስነው መሰረት ወለድ የሚያስገኝ እና ወለድ የማያስገኝ
ቁጠባ አገልገሎቶች አሰጣጥ ሊከተል የሚገው ከዚህ በታች የተጠቀሱት ይሆናሉ፤
18.18.1. ወለድ አልባ ቁጠባ ዓይነቶች

1) የሸሪዓ ህግን መሰረት ያደረገ መደበኛ ወዲዓ የድ ደማን ቁጠባ ከአባላቱ ይሰበስባል፣
2) ዩኒየኑ ከመደበኛ ቁጠባ ውጭ በአባሉ ሙሉ ፍላጎት ወለድ አልባ የሆነ የፍላጎት ቁጠባ አገልግሎት
ይሰጣል፤ እነዚህ የወለድ አልባ የቁጠባ አገልግሎቶች ቀርድ ሀሰን፣ ወዲዓ የድ ደማን የመሳሰሉትን
የወለድ አልባ አገልግሎቶች ይሰጣል፣
3) በወለድ አልባ ለተቀመጠ ቁጠባ ወለድ አይጠየቅበትም ወይም ጥቅም አይገኝበትም፣
4) በወለድ አልባ የተሰበሰበ ቁጠባ በፋይናንስ ተቋማት ሲቀመጥ በወለድ አልባ ሂሳብ ውስጥ መሆን
ይኖርበታል፣
5) የወለድ አልባ ቁጠባ አገልግሎት ሲሰጥ ስራውን ለማከናወን የሸሪያ ህግን ጠንቅቀው በሚያውቁ
ባለሙያዎችና ራሱን በቻለ የሂሳብ አሰራር መሆን አለበት፣
6) አባል ኅብረት ሥራ ማህበራት በአንቀጽ 18.3 የተቀመጠ መደበኛ ቁጠባ ውስጥ የወለድ አልባ ቁጠባ
ለይተው ወደ ዩኒየኑ ገቢ ያደርጋሉ፣

18.18.2. ወለድ የሚያስገኙ የቁጠባ ዓይነቶች


1) በብሄራዊ ባንክ የተቀመጠው የወለድ ምጣኔ መነሻ ሆኖ ዩኒየኑ ለሚሰጠው የቁጠባ አገልግሎት የተለያየ
አይነት የወለድ ተመን በስራ አመራሩ ቦርድ እያጸደቀ ተግባራዊ ያደርጋል፣
2) ወለድ የሚታሰብባቸው የቁጠባ ሂሳቦች ወለድ መታሰብ የሚጀምረው ቁጠባው በዩኒየኑ ሂሳብ
ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፣ወለዱ በ ወራት ሂሳቡ ተሰርቶ ወደ አባላት ቁጠባ
ሂሳብ ተዛውሮ መቀመጥ ይኖርበታል፣
19. የዩኒየኑ ኃላፊነት
ዩኒየኑ ስራውን በሚያከናውኑበት ወቅት ለሚገጥመው ኪሳራ ካለው ጠቅላላ ንብረት በላይ በእዳ ተጠያቂ አይሆንም፣
19.1.
ዩኒየኑ ኃላፊነቱ የተወሰነ ነው፣
20. ህጋዊ ሰውነት፣
20.1. ዩኒየኑ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ በህግ የሰውነት መብት ይኖረዋል፣ ይኸውም ውል የመዋዋል፣ የመክሰስ፣ የመከሰስ፣
የማበደር፣ የመበደር መብትና ግዴታዎች እንዲሁም በስሙ ንብረት የማፍራት መብት ይኖሩታል፣
20.2. ዩኒየኑ አግባብ ያለው ባለስልጣን በሚያወጣው መመሪያ መሰረት በየሶስት ዓመቱ ህጋዊ ሰውነቱን ማሳደስ ይኖርበታል፣
8
20.3. አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት አባልነታቸው ቀጣይነት የሚኖረው አግባብ ባለው አካል ህጋዊ ሰውነታቸው
መታደሱን በየሶስት አመቱ ለዩኒየኑ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ህጋዊ ሰውነት ያልሳደሰ
አባል አባልነቱ ይቋረጣል፣
21. አባልነት ስለመቋረጥ፣
በሚከተሉት ሁኔታዎች አባልነት ሊቋረጥ ይችላል፣
21.1. በፍላጎቱ አባሉ ከዩኒየን ለመውጣት ጥያቄ ካቀረበ
21.2. የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ በሚሰጠው ስራና ኃላፊነት ዘርፍ ከሁለት ጊዜ በላይ ግዴታን ባለመወጣት፣
21.3. የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ ለአንድ ዓመት ባለመሳተፍ፣
21.4. ያለ በቂ ምክንያት ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በመደበኛ ስብሰባዎች ላይ ባለመሳተፍ፣
21.5. ከዩኒየኑ ዓላማና ተግባር ጋር የሚጻረርና የሚያዳክሙ ተግባር ከፈጸመ፣
21.6. የዩኒየኑ ንብረቶች ላይ ሆን ብሎ አደጋ ያደረሰ ወይም እንዲደረስ ያደረገ፣
21.7. በተለያዩ ምክንያቶች በእጁ የገባውን የዩኒየኑን ንብረት ለግል ጥቅም ያዋለ፣
21.8. የዩኒየኑ ገንዘብ ሆን ብሎ በማጉደል ወይም ለማጉደል ሁኔታዎችን ያመቻቸ፣
21.9. በዩኒየኑ ስም ህገወጥ ተግባራትን ለመፈጸም የሞከረ ወይም የፈጸመ፣
21.10. አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ፣ መተዳዳሪያ ደንብና የአባላትን ውሳኔ አለማክበር እና አለመፈጸም፣
21.11. የዩኒየኑ የብድር አስተዳደር መመሪያ በማዛባት ለራስ ጥቅም ሲባል አላስፈላጊ ብድር መውሰድ፣ ለመውሰድ መሞከር
ወይም ሌላ አካልን ማሳሳት፣
21.12. በብድር አስተዳደር መመሪያ ውስጥ ከተቀመጠው የብድር መጠን በላይ ብድር መውሰድ፣
21.13. የዩኒየኑን የፋይናንስ አቋም ለማናጋት ወይም ለማዛባት መሞከር ወይም መፈጸም፣
21.14. ዩኒየኑን ሳያሳውቅ በተቀመጠው የብድር መመለሻ ጊዜ ውስጥ መመለስ ያለበትን ብድር እንዲመልስ ተገልጾለት በቂ
ምክንያት ሳያቀርብ መመለስ ካልቻለ፣
21.15. ዩኒየኑን ሳያሳውቅ የሚፈለገብትን የቁጠባና የእጣ ክፍያ በገባው ውል መሰረት ለ ተከታታይ ጊዜ ሳይከፍል ከቀረ፣
21.16. ዩኒየኑ በህግ ወይም በኪሳራ ወይም በአባሉ ውሳኔ እንዲፈርስ ከተወሰነ፣
21.17. አባሉ በህግ ወይም በፍርድ የታገደ ከሆነ፣
22. የአባልነት ስንብት አፈጻጸም፣
22.1. አባሉ በራሱ ጥያቄ ከዩኒየኑ ለመውጣት ከፈለገ ከ ቀን በፊት ለዩኒየኑ ስራ አመራር ቦርድ በማመልከቻ
ማቅረብ ይኖርበታል፣
22.2. በአባሉ ጥያቄ የሚደረግ ስንበት በስራ አመራር ቦርድ ውሳኔ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፣ የስራ አመራ ቦርድ የተሰናበተ
አባልን ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ያደርጋል፣
22.3. የስራ አመራር ቦርድ አባሉ በህግ የሰውነት መብቱን ማጣቱን ካረጋገጠ አባልነቱ እንዲቋረጥ አድርጎ ለጠቅላላ ጉባኤ
ሪፖርት ያቀርባል፣
22.4. የስራ አመራር ቦርድ አባሉ በህግ ወይም በፍርድ በመታገዱ ምክንያት አባልነቱ መቀጠል የማይችል መሆኑን ካረጋገጠ
አባሉን በማሰናበት ለጠቅላላ ጉባኤ በሪፖርት ያሳውቃል፣
22.5. የስራ አመራር ቦርድ በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ከአንቀጽ 21.2 - 21.15 ከተጠቀሱ ጥፋቶች ውስጥ በአንዱ ሆነ
በሌሎች አባሉ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ለጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ያቀርባል፣
9
22.6. ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ በአባሉ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ የስራ አመራር ቦርዱ በተሰጠው
ውሳኔ መሰረት ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈጽማል፣
22.7. በጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰናበት ውሳኔ የተላለፈበት አባል በ ቀናት ውስጥ የስንብት ደብዳቤ
እንዲደርሰው ይደረጋል፣
22.8. ከዩኒየኑ የተሰናበተ አባል እዳ እንደሌለበት ከተረጋገጠ ጥቅሙና ድርሻው ይጠበቅለታል፣ ይሁን እንጂ ጥቅሙ
የሚጠበቅለት ዩኒየኑ ኦዲት ከተደረገና ኪሳራ እንደሌለበት ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡
22.9. አንድ አባል በማንኛውም ምክንያት ከዩኒየኑ መልቀቅ በሚፈልግበት ጊዜ እዳ እንዳለበት ሲታወቅ ካለው ድርሻ ወይም
ጥቅሞች እዳው ተቻችሎ ቀሪ ገንዘብ ይከፈለዋል፣
22.10. በራሱ ፈቃድ ከአባልነት የተሰናበተ አባል ወደ ዩኒየኑ እንደገና አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበ፣ ከዩኒየኑ ከአንድ የበጀት
አመት በኋላ በስራ አመራር ቦርድ ውሳኔ መሰረት አባል መሆን ይችላል፣ ስለ አባሉ መመለስ ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት
ያቀርባል፣
22.11. ግዴታውን ባለመወጣቱ ከአባልነት የተሰናበተ አባል ጥያቄውን ካቀረበ ከአንድ በጀት አመት በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ
በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት መመለስ ይቻላል፣
22.12. ከዩኒየኑ ጋር በተያያዘ በወንጀል ወይም በተለያዩ ጥፋቶች ከአባልነት የተሰናበተ አባል እንደገና አባል መሆን የሚችለው
ከተሰናበተበት ዓመት ጀምሮ ከአምስት ተከታታይ የዩኒየኑ በጀት አመት በኋላ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ወደ
አባልነት መመለስ ይችላል፣
22.13. እንደገና አባል ለመሆን የሚቻለው በአንቀጽ 11 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሲያሟላ ነው፣
23. ስለ ድምጽ አሰጣጥ፣
23.1. ማንኛውም የዩኒየኑ አባል በጠቅላላ ጉባኤ ላይ በሚወክለው ግልሰብ አባል በአካል ተገኝቶ ድምጽ መስጠት
ይኖርበታል፣ ተወካዩ ግለሰብ ወክሎ ድምጽ መስጠት አይቻልም፣
23.2. ማንኛውም አባል ዩኒየኑ ውስጥ ያለው እጣ መጠን ግምት ውስጥ ሳይገባ የሚሰጠው ድምጽ አንድ ብቻ ይሆናል፣
23.3. መደበኛና አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ እንዲሁም የኮሚቴዎች ስብሰባዎች ላይ የሚወሰኑ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ
ነው፣
23.4. በዩኒየኑ የሚጸድቅ ውሳኔ በአብላጫ ድምጽ (ሀምሳ ሲደመር አንድ) ነው፣ ሆኖም ግን ልዩ ውሳኔ የሚያስፈልጉ ጉዳዮች
በሁለት ሶስተኛ ድምጽ መጽደቅ ይኖርበታል፣
23.5. በድምጽ አሰጣጥ ወቅት የድምጽ አሰጣጡ እኩል የተከፈለ ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል፣
24. የምርጫ ስርዓት፣
24.1. ዩኒየኑን የሚመሩ ኮሚቴዎች የሚሰየሙት በምርጫ ነው፣
24.2. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ወይም የጎደሉ የኮሚቴ አባላትን በምርጫ ይተካል፣
24.3. የስራ አመራር ቦርድና የቁጥጥር ኮሚቴ ምርጫ የሚያከናውኑ አባላት ያሉት አስመራጭ ኮሚቴ
በጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣሉ፣
24.4. ምርጫ ከመደረጉ በፊት በሚኖረው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ይመረጣሉ፣
24.5. አስመራጭ ኮሚቴዎች ለስራ አመራር ቦርድ እና ለቁጥጥር ኮሚቴ የሚሆኑ እጩ ተመራጮችን ባላቸው የመምራት
አቅምና ታማኝነት መሰረት አድርገው ቀጣይ የጠቅላላ ጉባኤ እስከሚደረግ ድረስ ይለያሉ፣ ህጉ በሚያዘው መሰረት
መቀጠል የሚገባቸውን አመራሮች በመገምገም እንዲቀጥሉ በእጩነት ይይዛሉ፣
10
በጠቅላላ ጉባኤ እለት ዩኒየኑ ሲመሩ የነበሩ አመራር አካላት የምርጫውን ስነስርዓት እንዲያከናውኑ ስልጣናቸውን
24.6.
ለአስመራጭ ኮሚቴ ያስረክባሉ፣
24.7. አስመራጭ ኮሚቴው ያዘጋጃቸውን እጩ ተመራጮችን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ያስተቻል፣ ጠቅላላ ጉባኤ
የተቀበላቸውን ዕጩዎች በመውሰድ እና ጠቅላላ ጉባኤ ባልተቀበላቸው እጩዎች ምትክ በእለቱ ከጠቅላላ ጉባኤ
ከተገኙ አባላት መካከል ጠቅላላ ጉባኤው እንዲመርጥ ያደርጋሉ፣
24.8. ለስራ አመራር ቦርድ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ እና ንዑሳን ኮሚቴ አባልነት ምርጫ የሚቀርቡ እጩዎች ለየኮሚቴዎቹ
በሚያስፈልጉ አባላት ብዛት ላይ እጩዎችን በመጨመር እንዲወዳደሩ ይደረጋል፣
24.9. የድምጽ አሰጣጥ ስርዓቱ በቀጥታ ወይም በካርድ ሊሆን ይችላል፣
24.10. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት ለስራ አመራር ቦርድና ለቁጥጥር ኮሚቴ አባልነት በእጩነት ሊቀርቡ አይችሉም፣
24.11. በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ የስራ አመራር ቦርድና ቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ምርጫው እንደተደረገ የስራ ክፍፍል
በማድረግ ወዲያውኑ ለጠቅላላ ጉባኤ የስራ ድርሻቸውን ያሳውቃሉ፣
24.12. የአስመራጭ ኮሚቴ በ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በተሻሩና በተመረጡ የስራ አመራር ቦርድና
የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት መካከል የስራ ርክክብ እንዲፈጸም ያደርጋል፣
24.13. ነባሩ የስራ አመራር ቦርድ እና የቁጥጥር ኮሚቴ ለተተኪው አዲስ አመራር አባላት በ ቀናት ውስጥ ስራውን
የማለማመድና የምክር አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለባቸው፣
25. ለአመራርነት የሚያበቁ መስፈርቶች፣
ማንኛውም አባል የሚከተሉትን የሚያሟላ ከሆነ ለአመራርነት መመረጥ ይችላል፣
25.1. ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነና የአእምሮ መታወክ የሌለበት፣ በፍርድ ወይም በህግ የመስራት መብቱ
ያልተከለከለ፣
25.2. በአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ወይም በዩኒየኑ አመራር አባል ሆኖ የገንዘብ ማባከን፣ ንብረት የማጥፋት እና
ሌሎች ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ያልፈጸመና ከዚህ ተመሳሳይ ደረጀና ክብደት ያለው ድርጊት ያልፈጸመ፣
25.3. ቀደም ሲል በምግባረ ብልሹነት ወይም በእምነት ማጉደል ወንጀል ክስ የሌለበት፣
25.4. ተደራራቢ የስራ ኃላፊነት የሌለበት፣
25.5. ሰዎችን ለመርዳት ጽኑ ፍላጎት እና ተቆርቋሪነት ያለው፣
25.6. ከዚህ በፊት በአመራር ብቃቱና ችሎታው በአካባቢው የተመሰገነና የተከበረ፣
25.7. የትምህርት ደረጃው ቢያንስ ያጠናቀቀ፣
25.8. በኅብረት ሥራ ጽንሰ ሀሳብ ላይ ስልጠና ያገኘ ወይም በቂ ግንዛቤ ያለው፣
25.9. ከአመራር ኮሚቴ አባላት ሆነ ከዩኒየኑ ቅጥር ሰራተኞች ጋር የስጋ ዝምድና ወይም የጥቅም ግንኙነት የሌለው፣
25.10. በዩኒየን አመራርነት ተመርጦ ለመስራት ሙሉ ፈቃደኛ የሆነ፣

26. ዩንየኑ ድርጅታዊ መዋቅር፣


26.1. ጠቅላላ ጉባኤ
26.2. የሥራ አመራር ቦርድ
26.3. የቁጥጥር ኮሚቴ
26.4. የብድር ኮሚቴ፣
11
26.5. የግዥ ኮሚቴ ፣
26.6. የሽያጭና ንብረት ክፍል ኮሚቴ እና ሌሎች ንዑሳን ኮሚቴዎች
26.7. ሥራ አስኪያጅ እና ሌሎች የቅጥር ሠራተኞች ናቸው ፡፡
27. የጠቅላላ ጉባኤ አቋም፣
27.1. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ ማለት የእያንዳንዱ አባል መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ተወካይ የሚገኝበት ዩኒየኑ የበላይ
አመራር አካል ነው፣
27.2. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ በዩኒየኑ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል ነው፣
27.3. ዩኒየኑ ከእያንዳንዱ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት የተውጣጡ የሆኑ እኩል ተወካይ ይኖሩታል፣
የተወካዮች ስብጥር የሚይዛቸው፡-
27.3.1. ከአባላት ከጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጡ ብዛት ፣
27.3.2. ከስራ አመራር ኮሚቴ ሊቀ መንበር፣ ጸሀፊ፣
27.3.3. ከቁጥጥር ኮሚቴ የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይም ተወካይ፣
27.4. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ብዛት በንዑስ አንቀስ 27.3 ከተጠቀሰው መብለጥ የለበትም፣
27.5. የጠቅላላ ጉባኤው ተወካይ በአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት በማንኛወም
ወቅት ውክልናው ተነስቶ በሌላ ሊተካ ይችላል፡፡
27.6. የአንድ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር የጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ በማንኛውም ጊዜ በመሰረታዊ ኅብረት ሥራ
ማህበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴነት ከተነሳ ወይም የሥራ ዘመኑን ሲጨርስ ከዩኒየኑ የጠቅላላ ጉባኤ አባልነት ውክልና
ተነስቶ አዲስ በሚወከል ተወካይ ይተካል፣
27.7. በማናቸውም የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ አንድ ተወካይ አንድ ድምጽ ብቻ ይኖረዋል፣
28. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ ስልጣንና ተግባር፣
28.1. ዩኒየኑን የሚመሩ የስራ አመራር ቦርድንና የቁጥጥር ኮሚቴን ይመርጣል፣ ይሽራል፣
28.2. የዩኒየኑ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚገልጽ በስራ አመራር ቦርድ የቀረበውን ሪፖርት ያዳምጣል፣ ውሳኔ
ያስተላልፋል፣
28.3. የዩኒየኑን የኦዲት ሪፖርት ያዳምጣል፣ መርምሮ ያጸድቃል፣
28.4. የዩኒየኑን ስራ ለማስፋት የሚረዳ የገንዘብ መጠን ከአበዳሪ ድርጅቶች መበደር እንዲችሉ ለስራ አመራር ቦርድ የብድር
ጣሪያ መጠን ይወስናል፣
28.5. በጥፋት እና ግዴታውን ባለመወጣት ከአባልነት እንዲሰረዝ የተወሰነበት አባል ኅብረት ሥራ ማህበር ጉዳይ አይቶ
ውሳኔ ይሰጣል፣
28.6. የዩኒየኑን መተዳደሪያ ደንብ ያሻሽላል፣ የውስጥ አሰራርና አስተዳደር ደንቦችን መመሪያዎችን እንዲዘጋጁ ያዛል፣
ያሻሽላል፣ ያጸድቃል፣ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል፣
28.7. የአመራሩ ስነ-ምግባር ደንብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ ያጸድቃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
28.8. የወለድ አልባ የፋይናንስ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውስጠ ደንብ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን
ይገመግማል፣
28.9. የእጣ ዋጋን፣ የሚሸጥ የእጣ ብዛት እና የመደበኛ ቁጠባ መጠንን ይወስናል፣
28.10. እንደ አስፈላጊነቱ የዩኒየን ሂሳብ ሊመረምር የሚችል የውጭ ኦዲተር አግባብ ያለው ባለስልጣንን በማስፈቀድ
12
ይሰይማል፣
28.11. በዩኒየኑ እና በአመራሩ እንዲሁም በአባሉ እንዲሁም በቅጥር ሰራተኞች መካከል ለሚነሳው አለመግባባት መርምሮ
ውሳኔ ይሰጣል፣
28.12. የአነስተኛ መድን ዋስትና ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔዎችን ያስተላልፋል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
በየጊዜው የአረቦን ክፍያ መጠንን ይመረምራል፣
28.13. የዩኒየኑን የሰው ሀይል አስተዳደር መመሪያ ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ በዩኒየኑ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና የሰው ሀይል ብዛትና
የደመወዝ መጠን ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል፣
28.14. የዩኒየኑን የተጣራ ትርፍ ክፍፍል ድልድል ላይ ውሳኔ ያስተላልፋል፣
28.15. በቁጥጥር ኮሚቴ የሚቀርብለትን ሪፖርት ገምግሞ ውሳኔ ይሰጣል፣
28.16. የዩኒየኑ እቅድና በጀት ገምግሞ ውሳኔ ይሰጣል፣ አፈጻጸሙን በሚቀርብለት ሪፖርት መሰረት ይገመግማል፣
28.17. የፋይናንስ አሰራር መመሪያ እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፣ያጸድቃል፣ አፈጻጸሙን ይገመግማል፣
28.18. የስራ አስኪያጅ ቅጥርን አስመልከቶ በስራ አመራር ቦርድ ሲቀርበልት ገምግሞ ያጸድቃል፣
28.19. የዩኒየኑ የባንክ ሂሳብ በጣምራ የሚያንቀሳቀሱ አመራሮችን ይሰይማል፣
28.20. የዩኒየኑ ስራ አመራር ቦርድ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት እና የስራ አስኪያጁን እገዳ አጣርቶ ውሳኔ ይሰጣል፣
28.21. ዩኒየኑ ከሌላ ዩኒየን ጋር እንዲዋሃድ ወይም ዩኒየኑ እንዲከፈል እንዲሁም የፌዴሬሽን አባል እንዲሆን ይወስናል፣
28.22. ግዴታቸውን ባለመወጣት ወይም በጥፋት የተሰናበቱ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት የአባልነት ጥያቄ
መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣
28.23. ሌሎች በስራ አመራር ቦርድ ተጠንተው የቀረቡ አዳዲስ ስራዎችና አገልግሎቶችን መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣
29. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ አመሰራረት፣

29.1. የሥራ አመራር ቦርዱ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ይሆናል፤


29.2. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ ከኅብረት ሥራ ዩኒየን ጠቅላላ ጉባኤ አባላት መካከል የተመረጡ ሆነው ቁጥራቸው እስከ
አባላት ይኖሩታል፣
29.3. የስራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር፣ ጸሀፊና ሌሎች አባላት ይኖረዋል፣
29.4. ለሥራ አመራር ቦርድ ከሚመረጡ አባላት መካከል ቢያንስ የሚሆኑት ሴቶች ይሆናሉ፡፡
29.5. በስራ አመራር ቦርድ ውስጥ የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል የሸሪአ ህግ የሚያውቁ አባላት
እንዲኖሩት ይደረጋል፣
29.6. የእያንዳንዱ የስራ አመራር ቦርድ አባል ምርጫ ብቃትንና ችሎታን መሰረት ያደረገ ይሆናል፣
29.7. የስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ዘመን በአንድ ምርጫ ጊዜ 3 (ሶስት) አመት ይሆናል፣
29.8. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የስራ ዘመን ከሁለት ጊዜ በላይ ሊሆን አይችልም፣
29.9. አንድ የስራ አመራር ቦርድ አባል የስራ ጊዜውን ጨርሶ ከወረደ በኋላ በድጋሚ መመረጥ የሚችለው ከአንድ የዩኒየኑ
በጀት አመት በኋላ ይሆናል፣
29.10. የስራ አመራር ቦርድ አባል በተመረጠበት የስራ ዘመን ውስጥ ጥፋት አጥፍቶ ከተገኛ ወይም በአባላቱ አመኔታ ካጣ
ወይም መስራት ካልቻለ ወይም የዩኒየኑን እንቅስቃሴ ካዳከመ ወይም የገንዘብ ወይም የንብረት ጉድለት/ ብክነት
ካደረሰ በማንኛውም ጊዜ በጠቅላላ ጉባኤ ሊሻር ይችላል፣

13
29.11. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ አባል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ከደረሰበትና በገዛ ፈቃዱ ለመልቀቅ ከፈለገ የስራ
አመራር ቦርድ መደበኛው ስብሰባ ከመካሄዱ ከ ቀን በፊት በጽሁፍ ማሳወቅ ይኖርበታል፣
29.12. የዩኒየኑ ሊቀ መንበር የአገልግሎት ጊዜውን ሳይጨርስ በገዛ ፈቃዱ አባልነቱን ቢተው የስራ አመራር ቦርድ አባላት
መካከል መርጦ እሰከ ቀጣይ ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ መተካት ይችላል፣
29.13. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ ቋሚ መደበኛ ስብሰባ ጊዜ ይኖረዋል፣ ዝርዝሩ በስራ አመራር ቦርድ ውስጠ ደንብ ውስጥ
የሚጠቀስ ይሆናል፣
29.14. የዩኒየኑ የቦርድ አመራር በማናቸውም ሁኔታ ስራቸውን ሲለቁ በስራ በነበሩበት ወቅት ሲሰሩበት የነበረውን ማንኛወንም
ዶክመንት የማስመርምር ግዴታ አለባቸው፣
29.15. በማንኛውም ጊዜ የሚደረግ መደበኛ የስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ከግማሽ በላይ የሆኑ አባላት ከተገኙ ስብሰባው
ሊካሄድ ይችላል፣
29.16. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ የዩኒየኑን የስራ ኃላፊነት በጋራ ይወጣሉ፣
29.17. የስራ አመራር ቦርድ አባላት መካከል ከተመረጡበት ቀጣይ አመት በኋላ አንድ ሶስተኛው የቦርዱ አባላት በአዲስ
አመራር መተካት አለባቸው፣
29.18. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ በአዋጅ፣በመተዳደሪያ ደንብ፣ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት ውጭ
በሚሰሩት ስራ ምክንያት በዩኒየኑ ላይ በሚደርሰው ኪሳራ ወይም ጥፋት ወይም ጉድለት በጋራ ወይም በግል ተጠያቅ
ይሆናሉ፣
30. የስራ አመራር ቦርድ ስልጣንና ተግባር፣
30.1. የዩኒየኑን ሀብትና እዳ መግለጫ፣ እቅድና በጀት በማዘጋጀት በጠቅላላ ጉባኤ እንዲጸድቅ ያደርጋል፣ ይተገብራል፣
30.2. የዩኒየኑን መተዳደሪያ እና የአሰራርና የአስተዳደር ውስጠ ደንቦችን ያዘጋጃል፣ በጠቅላላ ጉባኤ ያጸድቃል ተግባራዊ
ያደርጋል፣
30.3. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ አሰራሮችና የሂሳብ መዛግብቶች ተለይተው እንዲያዙና በአግባቡ እየተከናወኑ
ስለመሆኑ ያረጋግጣል፣
30.4. ግዥን እና ሽያጭን መሰረት ያደረጉ ብድሮች ተግባራዊ እንዲሆኑ አስፈላጊ የሆኑ አሰራሮችን ተግባራዊ
ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ክትትል ያደርጋል፣
30.5. የዩኒየኑ ሂሳብ አያያዝ ዘመናዊ የሂሳብ አያያዝ የተከተለ እንዲሆን አስፈላጊውን ሁሉ ያሟላል፣ አፈጻጸሙን ክትትል
ያደርጋል፣
30.6. አመታዊ የስራ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፣ አዳዲስ የቁጠባና ብድር አሰራሮችን ይነድፋል ለጠቅላላ
ጉባኤ አቅርቦ ያስወስናል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
30.7. ዘመናዊ የሆነ የብድር መረጃ አያያዝ ስርዓት ይዘረጋል፣ የብድር አሰጣጥና አመላለስ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
30.8. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮችን ይቀይሳል፣ በሰውኃይል፣ በአሰራር እና በቁሳቁስ
ያደራጃል፣ አገልግሎት አሰጣጡ ሸሪዓን የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፣
30.9. የመመዝገቢያ ክፍያ ይሰበስባል፣ እጣን ይሸጣል፣ ቁጠባን ይሰበስባል፣ ተጨማሪ እጣ መሸጥ በሚያስፈግበት ወቅት
በጠቅላላ ጉባኤ አስወስኖ ይሸጣል፣
30.10. የዩኒየኑ የቁጠባና የብድር አስተዳደር መመሪያ ያዘጋጃል፣ ወለድ አልባ አሰራርን ባካተተ ሁኔታ እና ሁሉንም አባላት

14
ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ያዘጋጃል፣ ያሻሽላል፣ በጠቅላላ ጉባዔ ያጸድቃል፣
30.11. የዩኒየኑን እዳ/ቁጠባ ከካፒታል መሸከም አቅም ጋር የተጣጣመ ስለመሆኑ ያረጋግጣል፣ ክፍተት ካለ የማስተካከያ
እርምጃ ይወስዳል፣
30.12. የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥመው በተፈቀደለት እስከ ተፈቀደለት የብድር ጣሪያ ድረስ ከፋይናንስ ተቋማት ብድር
ይበደራል፣ ወቅቱን ጠብቆ ይመልሳል፣
30.13. የወለድ መጠንን ይወስናል፣ በተወሰነው መሰረት ወለድ ይከፍላል፣ ይሰበስባል፣ በብሄራዊ ባንክ የሚደረጉ የወለድ
ለውጥን መሰረት ያደረገ የወለድ ምጣኔ ማስተካከያ ያደርጋል፣
30.14. የአባላት የቁጠባ አቅም እንዲጎለብት የተለያዩ የቁጠባ አይነቶችን ያስፋፋል፣ ማበረታቻዎችን በማዘጋጀት አባላት
እንዲበረታቱ ያደርጋል፣
30.15. የዩኒየኑን የሰው ሀይል አስተዳደር መመሪያ በማዘጋጀት በጠቅላላ ጉባኤ ያጸድቃል፣ የዩኒየኑን አደረጃጀት መዋቅር እና
የሰው ሀይል ብዛት እንዲሁም የክፍያ ሁኔታ ያዘጋጃል፣ በየጊዜው ወቅቱ በሚጠይቀው ሁኔታ ያሻሽላል፣ የጠቅላላ ጉባኤ
ውሳኔ ሲያገኝ ተግባራዊ ያደርጋል፣
30.16. የዩኒየኑ የመረጃ አያያዝ በዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ቴክኖሎጂ እንዲደገፍ ያደርጋል፣ ከአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ
ማኅበራት ጋር በመረጃ መረብ በመገናኘት ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት ያደርጋል፣
30.17. የዩኒየኑን ሥራ አስኪያጅ ቅጥር ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ ያፀድቃል
30.18. በዩኒየኑ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እና የቁጠባና ብድር መመሪያ መሰረት ይበደራል፣ ያበድራል፣
30.19. በዩኒየኑ እና በአባላት መካከል በሚከሰት አለመግባባት ሲኖር ወደ ሽምግልና ዳኝነት ከመሄዱ በፊት
የሚያግባባ የመፍትሄ ሀሳብ ያፈላልጋል፣
30.20. የተካፉልን ወይም አነስተኛ የመድን ዋስትና አሰራር በዩኒየኑ ውስጥ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ለዚህ የሚሆን
መመሪያ ያዘጋጃል፣ በጠቅላላ ጉባኤ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣
30.21. የዩኑየኑን ስብሰባዎች ቃለ ጉባኤ በጽሁፍ ይይዛል፣ መደበኛ እና አስቸኳይ ስብሰባዎን ይጠራል፣ ስብሰባዎችን
ይመራል፣
30.22. የአባልነት ማመልከቻ መርምሮ ውሳኔ ይሰጣል፣ በአባሉ ፈቃድ ከአባልነት የሚሰናበት መሰረታዊ ኅብረት ሥራ
ማህበር ጥያቄ ተቀብሎ ያሰናብታል፣ ግዴታውን ባለመወጣት እና በጥፋት የሚሰናበት አባል መሰረታዊ
ኅብረት ሥራ ማህበር ውሳኔ እንዲሰጥበት ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፣
30.23. የግዥና ሽያጭ አሰራርን ለማከናወን የሚያስችል አሰራር ስርዓት ይቀርጻል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣
30.24. በማንኛውም ጊዜ ዩኒየኑን በሚመለከቱ ጉዳዮች ወክሎ ይቆማል፣ ውሎችን ይዋዋላል፣
30.25. የማይመለስ ብድርን በመለየትና መመለስ የማይቻል መሆኑን በማረጋገጥ ውሳኔ እንዲሰጥበት ለጠቅላላ
ጉባኤ ያቀርባል፣
30.26. በየአመቱ ለማይመለሱ ብድሮች መጠባበቂያ የሚሆን በጀት እንዲመደብ ያደርጋል፣
30.27. ማንኛውም የዩኒየኑን ገቢዎች በዩኒየኑ ደረሰኝ ይሰበስባል፣ አወጣጡ በዩኒየኑ ወጪ ማዘዣ መሆኑን
ይከታተላል፣
30.28. የዩኒየኑ የስራ አመራር ቦርድ አባል ጥፋት አጥፍቶ ሲገኝ ለጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያቀርባል፣
15
የተሻሻለ መተዳደሪያ ደንብ እና የብድር መመሪያ እንዲመዘገብ አግባብ ላለው ባለስልጣን በማቅረብ
30.29.

ያስመዘግባል፣
30.30. በመተዳደሪያ ደንብ እና በሌሎች ውስጠ ደንቦች የተዘረዘሩ ተግባራትንና የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች

ያስፈጽማል፣
31. የስራ አመራር ቦርድ አባላት ስልጣንና ተግባር

31.1. የዩኒየኑ ሊቀ መንበር

የዩኒየኑ ሊቀመንበር በዩኒየን ጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ሆኖ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፣
31.1.1. የዩኒየኑን የጠቅላላ ጉባኤውንና የስራ አመራር የቦርዱን ስብሰባ ይመራል፣

31.1.2. በማንኛውም ጉዳይ ዩኒየኑን ወክሎ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

31.1.3. ለኅብረት
ሥራ ዩኒየኑ አገልግሎት የሚውሉ የብድር እና ሌሎች ውሎችን ከአገር ውስጥና ከውጪ ሀገር
ተቋማት ጋር ይፈራረማል፤
31.1.4. ስለ ኅብረት ሥራ እንቅስቃሴ መግለጫ ይሰጣል፣ ዩንየኑን ይወክላል፤

31.1.5. በዩኒየኑ የሂሳብ ሰነዶችን ያጸድቃል፣ቼክ ላይ ከዩንየኑ ሥራ አስኬያጅ ጋር በጣምራ ይፈርማል፡፡


31.1.6. ለስራ አስኪያጅ ከተሰጠው ሂሳብ የማጽደቅ ኃላፊነት በላይ የሆኑ የዩኒየኑ ወጪዎች ያጸድቃል፣

31.1.7. የዩኒየን ስራ አስኪያጅ ብድርን ለማጽደቅ ከተሰጠው ስልጣን በላይ የሆነውን ብድር ያጸድቃል፣

31.1.8. ለዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ እንዲዋዋል ከተሰጠው ኃላፊነት በላይ የሆነውን የውል ስምምነት ይዋዋላል፣

31.1.9. የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ ስለመሆኑ ግምገማ እና ቁጥጥር

ያደርጋል፣
31.1.10. ፍትሃዊ የሰራተኞች አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል፣ በስራ አስኪያጅና

በቅጥር ሰራተኞች መካከል ያለውን አለመግባባት በሰው ኃይል መመሪያ መሰረት ይፈታል፣
31.1.11. የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ወርሃዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በሥራ አስኪያጅ በኩል ለሥራ አመራር ቦርድ

እንዲያቀርብ ያደርጋል፡፡
31.1.12. K?KA‹ ›eðLÑ> ¾J’< የኅብረት ሥራ ዩኒየኑን Y^ ‹ ÁŸ“¨“M፡፡

31.2. ምክትል ሊቀ መንበር

31.2.1. የቦርዱ ም/ሊቀምንበር በጠቅላላ ጉባኤ የሚመረጥ ሲሆን የሊቀመንበሩ ረዳት ሆኖ ያገለግላል፡፡

31.2.2. ሊቀመንበሩ በማይኖርበት ወይም መስራት በማይችልበት ጊዜ ተክቶ ሥራዎችን ይሰራል፡፡

32. የዩኒየኑ የቁጥጥር ኮሚቴ አቋም


32.1. የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ብዛት ሆኖ በጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣሉ፣
32.2. የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን ሶስት አመት ነው፣
32.3. የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት ለተከታታይ ሁለት ጊዜ በላይ መመረጥ አይችሉም፣ ሆኖም በድጋሚ መመረጥ የሚቻለው
ከአንድ ዩኒየን በጀት አመት በኋላ ይሆናል፣
32.4. የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ ጸሀፊና አባል ይኖሩታል፣

16
32.5. የቁጥጥር ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ነው፣
32.6. ከኮሚቴ አባላት መካከል ስራውን ቢያቆም ከኮሚቴ አባላት መካከል ተክቶ ያሰራል፣
32.7. ከሁለተኛው ምርጫ አመት ጀምሮ አንድ ሶስተኛው የቁጥጥር ኮሚቴ አባላት በአዲስ አባል ተመራጭ በየጊዜው
መተካት አለበት፣
33. የቁጥጥር ኮሚቴ ስልጣንና ተግባር፣
33.1. የቁጥጥር ኮሚቴ በማንኛውም ጊዜ የዩኒየኑ አሰራርና የተለያዩ የሂሳብ ሰነዶችና መዛግብቶችን ይመረምራል፣
ይቆጣጠራል፣
33.2. የዩኒየኑ የቁጠባና ብድር አሰራር በዩኒየኑ መተዳደሪያ ደንብና የውስጥ የቁጠበና ብድር መመሪያ መሰረት መከናወኑን
ያረጋግጣል፣
33.3. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት በአግባቡ እየተሰጠ ስለመሆኑ ያረጋግጣል፣
33.4. ዩኒየኑ የሰው ሀይል አመራር በሰው ሀይል አስተዳደር መመሪያ መሰረት እየተከናወነ ስለመሆኑ ያረጋግጣል፣
33.5. የውስጥ ቁጥጥር አሰራርን ተግባራዊ ያደርጋል፣ ለስራው የሚያስፈልገውን የሰው ሀይልና በጀት በጠቅላላ ጉባኤ
አስወስኖ ተግባራዊ ያደርጋል፣
33.6. የፋይናንስ አፈጻጸም መለኪያዎች ተግባራዊ እንዲሆን ከስራ አመራር ቦርድ ጋር በመሆን ይሰራል፣ ዩኒየኑ ያለበትን ደረጃ
ገምግሞ ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፣
33.7. ከስራ አመራር ቦርድ ጋር በመሆን ኦዲት እንዲደረግ ያደርጋል፣ የኦዲት ግኝቶችና የተሰጡ አስተያየቶች ተግባራዊ
ስለመሆናቸው ክትትል ያደርጋል፣
33.8. በስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ላይ በድምጽ አልባነት ይገኛል፣ የቦርዱ ስብሰባ ህግን በተከተለና ዲሞክራሲያዊ በሆነ
መልኩ መከናወኑን ይታዘባል፣ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ በስራ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮች
እንዲታረሙ ለቦርዱ አስተያየት ይሰጣል፣
33.9. የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል፣
33.10. የቁጥጥር ኮሚቴ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀርባል፣ የስራ እቅድና በጀት አዘጋጅቶ ለጠቅላላ ጉባኤ
ያቀርባል፣ ሲፈቀድለት ተግባራዊ ያድርጋል፣
33.11. የዩኒየኑ ቅጥር ሰራተኞች ኃለፊነታቸውን በአግባቡ ስለመወጣታቸው ክትትል ያደርጋል፣ የተከሰቱ ግድፈቶች እንዲታረሙ
ለስራ አመራር ቦርድ ሪፖርት ያደርጋል፣
33.12. ሌሎች በጠቅላላ ጉባኤ የሚወሰኑ ውሳኔዎች ተግባራዊ ያደርጋል፣
34. ሌሎች ንዑሳን ኮሚቴዎች በተመለከተ፣
34.1. የስራ አመራር ቦርድ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ይሰይማል፣ዩኒየኑ የሚከተሉት ኮሚቴዎች
እንዳስፈላጊነቱ ይኖሩታል፣
34.1.1. የብድር ኮሚቴ
34.1.2. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ክትትል ኮሚቴ
34.1.3. የግዥ ኮሚቴ
34.1.4. የንብረት አስተዳደርና የሽያጭ ኮሚቴ
34.1.5. የቁጠባ፣ የትምህርት እና ቅስቀሳ ኮሚቴ
34.2. ኮሚቴዎቹ ከሶስት ያላነሱ አባላት ይኖራቸዋል፣ የየራሳቸው ሰብሳቢ፣ ጸሀፊና አባል ይኖራቸዋል፣
17
34.3. ኮሚቴዎቹ ተጠሪነታቸው ለስራ አመራር ቦርድ ነው፣ የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን እንዲሁም እቅድና በጀት ለስራ
አመራር ቦርድ ያቀርባሉ፣ ያጸድቃሉ፣ ተግባራዊ ያደርጋሉ፣
34.4. ዝርዝር ተግባር አፈጻጸማቸው ዩኒየኑ በሚያዘጋጀው የውስጥ አሰራር ደንብ ውስጥ የሚገለጽ ይሆናል፣
34.5. የኮሚቴዎቹ የስራ ዘመን የስራ አመራሩ ቦርድ የስራ ዘመን ይሆናል፣
35. የዩኒየን ቅጥር ሰራተኞች
35.1. ዩኒየኑ የሰው ሀይል አስተዳደር መመሪያ እና በጠቅላላ ጉባኤ የጸደቀ አደረጃጀት እና መዋቅር ይኖረዋል፣
35.2. ዩኒየኑ የዕለት ተዕለት ስራውን የሚያከናውኑለት ቅጥር ሰራተኞች ይኖሩታል፣
35.3. ቅጥር ሰራተኞች በዩኒየኑ ሰው ሀይል አስተዳደር መመሪያና አግባብ ባለው አካል በሚያወጣው መመሪያ መሰረት
የሚተዳደሩ ይሆናል፣
35.4. የቅጥር ሰራተኞችን የሚመራና ዩኒየኑን በኃላፊነት የሚያስተዳድር ስራ አስኪያጅ ይኖረዋል፣
35.5. የዩኒየኑ ስራ አስኪያጅ ወይም ቅጥር ሰራተኛ ሲቀጠር አግባብ ባለው ባለስልጣን በሚያወጣው የሀብት ማስመዝገቢያ
ቅጽ መሰረት የተቀጣሪው የግል ንብረት እና ሀብት መረጃ መዝግቦ አስፈርሞ ይይዛል፣
36. የዩኒየኑ ሥራ አስኪያጅ ተግባርና ኃላፊነት
ዪኒየኑ ተጠሪነቱም ለስራ አመራር ቦርድ የሆነ ስራ አስኪያጅ ይኖረዋል፣ሥራ አስኪያጁ የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነት ይኖሩታል፣
36.1. የዩንየኑን የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴ በኃላፊነት ይመራል፣
36.2. የዩንየኑን ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ እና በጀት በማዘጋጀት ለሥራ አመራር ቦርዱ ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፣
36.3. የዩኒየኑ ተቀጣሪ ሰራተኞች በሰው ሀይል አደረጃጃትና አስተዳደር መመሪያ እና አግባብ ባለው አካል በሚያወጣው
መመሪያ መሰረት ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣
36.4. ለሰራተኞች የሥራ ዝርዝር ያዘጋጃል፤የሥራ አፈፃጸማቸውን ይገመግማል፤የሰራተኛ ቅጥርና ስንብት ሀሳብ በማዘጋጀት
ለውሳኔ ለስራ አመራር ቦርድ ያቀርባል፡፡ ሲፀድቅለትም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
36.5. በዩኒየኑ ሥራ አመራር ቦርድ ሊቀመንበር የሚፀድቁ የብድር ውሎችን በማረጋገጥና በሰነዶች ላይ በመፈረም
ወጪዎችን ያፀድቃል፤ ክፍያ እንዲፈፅምም ለሂሳብ ክፍል በደብዳቤ ትዕዛዝ ይሰጣል፤
36.6. እስከ ብር የሆኑ የሂሳብ ወጪዎችን ከፋይናንስ ሃላፊና ከገንዘብ ያዥ ጋር በመሆን በጣምራ በቼክ ላይ
ይፈርማል፡፡ ሂሳቡን ያጸድቃል፣
36.7. እስከ ብር ለአባላት የሚሰጡ ብድሮችን በፊርማ ያፀድቃል፡፡ አመላለሱን ይከታተላል፣
36.8. እስከ ብር የሆኑ የሥራ ማስኪያጃ ወጪዎችን ይፈቅዳል፤ ያጸድቃል፣
36.9. እስከ ብር የሚደርሱ ውሎችን በስራ አመራሩ ቦርድ ሲፈቀድለት ይዋዋላል፣ አፈጻጸሙን
ይከታተላል፣ ሪፖርት ለቦርድ ያቀርባል፣
36.10. በዩንየኑ የሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባዎች ላይ ይገኛል፤ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፤አስተያየት እና መረጃ ይሰጣል፣
ድምፅ አይሰጥም፣
36.11. የዩኒየኑን የጠቅላላ ጉባኤ እና የሥራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ ይይዛል፤
36.12. የዩኒየኑን የስብሰባዎች ጊዜ ለጠቅላላ ጉባኤ እና ለቦርዱ አባላት በወቅቱ ያሳውቃል፤
36.13. የጠቅላላ ጉባኤ እና የስራ አመራር ቦርድ አጀንዳዎችን ከሊቀመንበሩ ወይም ምክትል ሊቀ መንበር ጋር በመሆን
ያዘጋጃል፣
36.14. የዩኒየኑን ጽህፈት ቤት ያደረጃል፣ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ እንዲፈጠር ያደርጋል፣
18
36.15. ቢሮዎች ለስራ ምቹ እንዲሆኑ ያደርጋል፣ የገቢና የወጪ ደብዳቤዎችን አሰራርን ስርዓት ይዘረጋል፣
36.16. የአባላትን መረጃዎችና ፋይሎች በተገቢው ሁኔታ በማደራጀት ይይዛል፤
36.17. ሌሎች ከሥራ አመራር ቦርድ እና ቁጥጥር ኮሚቴ የሚሰጡትን ተግባራት ያከናውናል፤
36.18. ሸሪዓ መር የቁጠባና ብድር አገልግሎቶች እንዲሁም የመድን ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎቶችን ይተገብራል፡፡
37. ዩኒየኑ የስብሰባ ሥነሥርዓት፣
37.1. ዩኒየኑ መደበኛ ወይም አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ይኖሩታል፣
37.2. የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ በአመት ሁለት ጊዜ ይደረጋል፣ ስብሰባውም በሚከተሉት ወቅቶች የጠቅላላ ጉባኤ ይደርጋል፣
37.2.1. የመጀመሪያው ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል፣
37.2.2. ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ይደረጋል፣
37.3. የዩኒየኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት ቢያንስ በ ቀናት ጊዜ ውስጥ የመወያያ ርዕስ፣
የስብሰባ ቀን፣ ቦታና ሰዓት በጥሪ ደብዳቤው ላይ ተጠቅሶ ለሁሉም አባላት የስብሰባ ጥሪው እንዲደርሳቸው ይደርጋል፣
ሆኖም የጥሪ ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት ባሉ 15 ቀናት ውስጥ ለአባላት መድረስ አለበት፣
37.4. የዩኒየኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ካሉት አባላት ውስጥ ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፣
37.5. መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ምልዓተ ጉባኤ ካልተሟላ ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
ይደረጋል፣
37.6. ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ምልዓተ ጉባኤው ካልተሟላ በእለቱ በተገኙ አባላት መደበኛ ጠቅላላ
ጉባኤ ሊካሄድ ይችላል፣
37.7. በአንቀጽ 37.6 መሰረተ ምልዓት ጉባኤው ሳይሟላ የተካሄደ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች ሁሉም
የጉባኤው አባላት በተገኙበት እንደተላለፈ ሆኖ ይቆጠራል፣
37.8. የዩኒየኑ ስራ አመራር ቦርድ ወይም የቁጥጥር ኮሚቴ ወይም ከጠቅላላ አባላት ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ ያላነሱ አባላት
አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራላቸው ሲጠይቁ የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ስራ አመራር ቦርድ በ
ቀናት ውስጥ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ያደርጋል፣
37.9. ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ምልዓተ ጉባኤ ካልተሟላ የስራ አመራር ቦርድ አግባብ ላለው
ባለስልጣን በሪፖርት ያሳውቃል፣
37.10. የስራ አመራር ቦርድ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ካልጠራ የዩኒየኑ አባላት ወይም የቁጥጥር
ኮሚቴ አግባብ ባለው ባለስልጣን አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራላቸው መጠየቅ ይችላሉ፣
37.11. ከጠቅላላ አባላት ውስጥ ሁለት ሶስተኛ አባላት የተገኙበት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል፣
37.12. የስራ አመራር ቦርድና የቁጥጥር ኮሚቴ የራሳቸው መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባ ይኖራቸዋል፣ ዝርዝር አሰራሩ በስራ
አመራር ቦርድ ወይም ቁጥጥር ኮሚቴ ውስጠ ደንብ የሚገለጽ ነው፣
38. የኮሚቴ አባላት እገዳና ስንብት
38.1. የዩኒኑ የስራ አመራር ቦርድ፣ የቁጥጥር እና ሌሎች ንዑሳን ኮሚቴ አባል የሆነ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው
ከአመራርነት ለመሰናበት ከፈለገ ለስራ አመራር ቦርድ ወይም ለቁጥጥር ኮሚቴ ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል፣
38.2. የስራ አመራር ቦርድ ወይም የቁጥጥር ኮሚቴ ጥያቄው በቀረበ በ ¬¬¬¬¬¬ቀናት ውስጥ በጽሁፍ መልስ መስጠት
ይኖርበታል፣
38.3. የስራ አመራር ቦርድ ወይም የቁጥጥር ኮሚቴ ተመራጭ ከዩኒየኑ ደንብና ህግን የሚጻረር ድርጊት ከፈጸመ ተጠሪ
19
በሆነበት የስራ አመራር ቦርድ ወይም ቁጥጥር ኮሚቴ አማካኝነት ከስራው ይታገዳል፣
38.4. የታገደው አመራር የታገደበት ምክንያት በጽሁፍ እንዲያውቀው በማድረግ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጠው
ይደረጋል፣
38.5. አንድ አመራር ለ ተከታታይ የዩኒየኑ ስራዎችና ስብሰባዎች እንዲገኝ ጥሪ ተደርጎለት ያለበቂ ምክንያት
ካልተገኘ ከአመራርነቱ እንዲሰናበት ተደርጎ ለጠቅላላ ጉባኤ እንዲወሰንበት ይቀርባል፣
39. ድርሻና ጥቅምን ስለማስከበር፣ ስለማቻቻልና ስለማስተላለፍ፣
39.1. አንድ አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር በአንቀጽ 21.1፣ 21.16 እና 21.17 የዩኒየኑ አባልነት የሚሰናበት ከሆነ
በዩኒየኑ የሚኖረውን ድርሻና ጥቅም የሚከፈለው በዩኒየኑ ያለበት እዳ ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው ብቻ ነው፣
39.2. አንድ አባል ዩኒየኑ ውስጥ ያለው ጥቅሙ ወይም ድርሻ ከዩኒየኑ ውጭ ላለበት እዳ ወይም ተጠያቂነት ሊከበር፣ ሊያዝ፣
ሊሸጥ አይችልም፣
39.3. ዩኒየኑ ከአባሉ ላይ ለሚፈልገው እዳ የአባሉን ድርሻ እና ሌሎች ጥቅሞች ወይም ካለው የቁጠባ ገንዘብ ላይ በመቀነስ
እዳውን ያቻችላል፣
39.4. የአባሉ እዳ ከሚቻቻለው የእጣ እና ጥቅም ወይም ቁጠባ በላይ የበለጠ ከሆነ በስራ አመራር ቦርድ አማካኝነት
ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ውሳኔ ይሰጥበታል፣
39.5. ዩኒየኑ አባል ኅብረት ሥራ ማህበራት ድርሻና ጥቅም የማስተላለፍ ስራ አይሰራም፣

40. ስለ ብድር አስተዳደር፣


40.1. ዩኒየኑ በጠቅላላ ጉባኤ የጸደቀ የቁጠባና የብድር አስተዳደር መመሪያ ይኖረዋል፣
40.2. የዩኒየኑ ብድር ተፈፃሚ የሚሆነው በዩኒየኑ መተዳደሪያ ደንብና የቁጠባና የብድር አስተዳደር መመሪያ መሰረት ይሆናል፣
40.3. ማንኛውም ብድር የሚሰጠው በብድር ክፍል/ኮሚቴ ተገምግሞ በሥራ አመራር ቦርድ ሲፀድቅ ነው
40.4. ዩኒየኑ ብድር የሚሰጠው ለአባሉና መሰል ኅብረት ሥራ ማህበራት ነው፣
40.5. አንድ አባል የሚፈለግበትን የአባልነት ግዴታውን ካሟላበት ጊዜ ጀምሮ የብድር አገልግሎት የማግኘት
መብት ይኖረዋል፡፡ሆኖም የብድር አሰጣጥ መነሻ የሚያደርገው አባሉ ባለው ቁጠባ መጠንና የአባላት ካፒታል
ተመስርቶ ነው፡፡
40.6. ዩኒየኑ ለብድር አገልግሎት የሚያውለው ገንዘብ መጠን ከዩኒየኑ ጠቅላላ ሀብት ከ በመቶ መብለጥ
የለበትም ፣
40.7. በሥራ አመራር ቦርዱ በበጀት ዓመት ለማበደር ከተመድበው ገንዘብ መጠን ውስጥ ለአንድ አባል የሚሰጠው ብድር
በመቶ በላይ መብለጥ የለበትም፣ ዝርዝር አፈፃፀሙ በዩኒየኑ የብድር መመሪያ የሚቀመጥ ሆናል፣
40.8. ዩኒየኑ ከፋይናንስ ተቋማት የሚበደረው የብድር ገንዘብ መጠን ከጠቅላላ ሀብቱ በመቶ መብለጥ
የለበትም፣
40.9. የሥራ አመራር ቦርዱ ዩኒየኑ በበጀት ዓመቱ ከፋይናንስ ተቋማት ለሚበደረው ብድር የጠቅላላ ጉባኤ ፈቃድ ማግኝት
ይኖርበታል፣
40.10. የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ለአባላት የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ብድር ብቻ ይሰጣል፣ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ
ሲያገኘው የአጭር ጊዜ ብድሮች በሥራ አመራር ቦርድ ተወስኖ ይሰጣሉ፣
40.11. ዩኒየኑ ለሚሰጣቸው የብድር አገልግሎቶች ተመጣጠኝ የሆነ ዋስትና ከተበዳሪዎች መጠየቅ አለበት፣
20
40.12. ዩኒየኑ ለብድር አስተዳደር አመች የሚሆኑ ወለድ የሚታሰብባቸውና የማይታሰብባቸው ብድር መመዝገቢያ የሚሆኑ
ሰነዶች፣ መዝገቦችና ቅጾች ያዘጋጃል፣
40.13. ዩኒየኑ ብድር የሚሰጥባቸውን ስራ ዘርፎች ለይቶ በቅደም ተከተል ያዘጋጃል፣ ለአባሉ ያሳውቃል፣
40.14. ዪኒየኑ ብድር ከመሰጠቱ በፊት የዩኒየኑ ሂሳብ ያለበትን ሁኔታ የሚገልጽ ዝርዝር ሪፖርት ማዘጋጀት ይኖርበታል፣
40.15. ዩኒየኑ የሚያሰራጫቸውን ብድሮች የመመለሻ ጊዜያቸውን እየለየ መያዝ ይኖርበታል፣ የብድር አመላለስ ሂደትን ክትትል
ያደርጋል፣ ከአቅም በላይ የሆኑ ብድሮች ለይቶ ድጋፍ ያደርጋል፣
40.16. ከአቅም በላይ የሆነና የማይመለስ ብድር በመጠንና በአይነት ተለይቶ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጠው ይደረጋል፣
40.17. ለማይመለስ ብድር የሚሆን መጠባባቂያ ከሚሰጠው ብድር ላይ ተሰልቶ በቁጠባ ሂሳብ ውስጥ መቀመጥ
ይኖርበታል፣ የማይመለስ ብድር መጠን የመክፈያ ጊዜው ከደረሰ ብድር ውስጥ በመቶ መብለጥ
የለበትም፣ዝርዝር አፈፃፀሙ በብድር አስተዳደር መመሪያ ውስጥ መካተት ይኖርበታል፡፡
40.18. ዩኒየኑ ከአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራት ጋር በመሆን የፋይናንስ ተጠቃሚ ያልሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን
እንደየአካባቢው ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ የብድር አይነቶች በማዘጋጃት ተጠቃሚና ተደራሽ እንዲሆን ያደርጋል፣
41. የወለድ አልባ የብድር አገልግሎቶች
41.1. ዩኒየኑ ወለድ አልባ የሆኑ የብድር አገልግሎት ለአባሉ ይሰጣል፣ ለሚሰጠው ብድር ምንም አይነት ወለድ አያስከፍልም
ወይም አይቀበልም፣
41.2. ዩኒየኑ የሚሰጠው የወለድ አልባ ብድር አገልግሎቶች እንደ ዩኒየኑ አቅምና ባህሪ ጋር የሚጣጣሙትን እያጠና መሆን
አለበት፣ ሆኖም ግን የሚከተሉት የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎቶች ለአባሉ ይሰጣል፣
41.2.1. ሙራበሃ፣
41.2.2. ሰለም ፣
41.2.3. ኢጃራ ላይ አተኩሮ ይሰጣል፤ ሆኖም ሌሎች የወለድ አልባ የብድር አገልግሎቶችን ዩኒየኑ እያጠና በጠቅላላ
ጉባኤ አጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፣
41.3. ዩኒየኑ ከላይ የተጠቀሱትን ሸሪዓ መር የፋይናንስ አገልግሎት ለብድር አስተዳደር አመቺ የሚሆኑ አሰራሮችና ሰነዶች፣
መዛግብቶች እና ቅፆች ያዘጋጃል፣የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ብድር የሚሰጥባቸውን የስራ ዘርፎች በቅደም ተከተል
ያዘጋጃል፣
41.4. የወለድ አልባ የብድር አገልግሎት መሰረት የሚያደርገው ግዥና ሽያጭን ሲሆን ዩኒየኑ በአባላት ጥያቄ መነሻ መሰረት
የገዛውን እቃ የራሱን ወጪ መሸፈኛ ጨምሮ ለአባሉ መልሶ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ ነው፣ ዝርዝር አሰራሩ በብድር
አስተዳደር መመሪያ ይገለጻል፣
41.5. የወለድ አልባ የብድር አገልግሎት የሚሰጠው ከወለድ አልባ ከተሰበሰበ ቁጠባ ብቻ ይሆናል፣
41.6. በምንም ሁኔታ ወለድ የሚታሰብባቸው ገንዘቦች ለወለድ አልባ አገልግሎት አይውሉም፣
41.7. ከወለድ አልባ የሚሰበሰብ ብድር ገቢ የሚሆነው በወለድ አልባ ሂሳብ ቁጥር ውስጥ ነው፣
42. ወለድ የሚከፈልባቸው የብድር አገልግሎት
42.1. ዩኒየኑ ወለድ የሚያስከፍልባቸውን የብድር አግልግሎት ይሰጣል፣
42.2. የወለድ መጠን ጣሪያ በመቶ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የስራ አመራር ቦርዱ አጥንቶ
ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ በማጸደቅ የወለድ ጣሪያ ሊስተካከል ይችላል፣
42.3. ዩኒየን ለሰጠው ብድር የሚሰበሰበው የወለድ መጠን በስራ አመራር ቦርድ በጥናት በሚወሰነው ወለድ መጠን መሰረት
21
ይሆናል፣
42.4. ዩኒየኑ ወለድ ለሚያስገኝ የብድር አገልግሎት የሚሆን አሰራር ይዘረጋል፣ ዩኒየኑ ለሚሰጣቸው የተለያዩ ብድሮች የተለያየ
የወለድ ምጣኔዎች አዘጋጅቶ ተግባራዊ ያደርጋል፣
42.5. በወለድ የተሰጠ ብድር የሚሰበሰብ ሂሳብ መግባት ያለበት ወለድ በሚያስገኝ የሂሳብ ቁጥር ውስጥ ነው፣

43. አነስተኛ የመድን ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎት ስለመስጠት


43.1. ዩኒየኑ አነስተኛ መድን ወይም ተካፉል አገልግሎትን ከሌሎች መድን ዋስትና ከሚሰጡ ተቋማት በውክልና

ወይም ውል ላይ በተመሰረት ውክልና ራሱን ችሎ አገልግሎቱን ከአባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ጋር


በጋራ ይሰጣል፣
43.2. በመሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባል ላይ በሚደርሰው አደጋ ምክንያት የሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ኪሳራ

ለማካካስ እንዲቻል ዩኒየኑ በውል የተመሰረተ ስምምነት ከኅብረት ሥራ ማህበር በማድረግ አነስተኛ የመድን
ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎት ይሰጣል፣
43.3. የአነስተኛ መድን ዋስትና አገልግሎት ወለድ ለሚሰጣቸው አባላት የሚሰጥ ሲሆን የተካፉል አገልግሎት

ደግሞ ለወለድ አልባ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሚሰጥ ነው፣


43.4. አነስተኛ መድን ወይም ተካፉል ከአባላት በሚሰበሰብ አረቦን የሚሸፈን ሲሆን ለዚህ አገልግሎት ኅብረት ሥራ

ማህበሩ የራሱ የሆነ የሂሳብ አሰራር ይዘረጋል፣


43.5. ዩኒየኑ አነስተኛ መድን ዋስትና ወይም ተካፉል አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ያዘጋጃል፣ በጠቅላላ ጉባኤው

አጸድቆ ተግባራዊ ያደርጋል፣


43.6. በመመሪያ ውስጥ የአረቦን መጠን፣ የአደጋ አይነቶች፣ የካሳ አከፋፈልና እዳ አቻቻል አስመልከቶ በዝርዝር

ይቀመጣል፣
43.7. ለአረቦን ከተሰበሰበ ገንዘብ ውስጥ የካሳ ክፍያ ተከፍሎ ከቀረው ገንዘብ ውስጥ

በመቶ የሚሆነው በአደጋ መጠባበቂያነት የቁጠባ ሂሳብ ተከፍቶለት ተቀማጭ ይሆናል፡፡


43.8. በመጠባበቂያነት የተቀመጠው ገንዘብ አጠቃቀም በተመለከተ አግባብነት ያለው አካል በሚያወጣው

መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፤ ቀሪው ገንዘብ በገቢነት ተይዞ ወደ ትርፍ ክፍፍል ይሄዳል፣
43.9. ሁሉም የዩኒየኑ አባላት ለአባሎቻቸው ብድር የሚሰጡ ከሆነ አባሎች መድን ዋስትና መግባት ይኖርባቸዋል፣

43.10. ከተካፉል አገልገሎት ተጠቃሚዎች የሚሰበሰብ ገንዘብ የጉዳት ማካካሻ ተከፍሎ የሚቀረው ገንዘብ

ተጠቃሚዎች በሚወስኑት ውሳኔ መሰረት ጥቅም ላይ ይውላል፣


44. የመድን ዋስትና ሽፋን

44.1. ዩኒየኑ ንብረቱን ከተለያየ አደጋ ለመጠበቅ እንዲችል የመድን ዋስትና ሊገባ ይችላል፡፡

45. የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ሂሳብና ገንዘብ አያያዝ፣


45.1. ዩኒየኑ በወለድ አልባ እና ወለድ የሚታሰብባቸው ተብለው የተለዩ ሁለት የተለያዩ የሂሳብ አርዕስቶች ይኖሩታል፤ የገንዘብ
አያያዛቸው፣ አመዘጋገባቸው፣ ሪፖርት ዝግጅታቸውና አቀራረባቸው ተለያይተው ይሆናሉ፣ ሆኖም የኅብረት ሥራ
22
ማህበራት ዩኒየኑን የፋይናንስ አቋም ለማወቅ አንድ ወጥ የሆነ የሂሳብ ሪፖርት ይኖራቸዋል፣
45.2. የቁጠባና የብድር እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሂሳቦች ሲቀመጡ በወለድ አልባ እና ወለድ የሚታሰብባቸው የሂሳብ
ቁጥሮች የፋይናንስ ተቋም ተከፍተው መቀመጥ አለባቸው፣ ዝርዝር አሰራሩ በፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ
ይቀመጣሉ፣
45.3. ከተለያየ ገቢዎች የሚሰበስብ የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ገንዘብ በወለድ አልባ እና ወለድ በሚያስገኝ ደረሰኞች
ተሰብስቦ በየዕለቱ ወደ ፋይናንስ ተቋም ገቢ መሆን ይኖርበታል፣
45.4. የገንዘብ አያያዝን በተመለከተ ዩኒየኑ ባዘጋጀው የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፣
45.5. የዩኒየኑ ሥራ አመራር ቦርድ በ……………….. ጊዜ ስለ ኅብረት ሥራ ዩኒየኑ የፋይናንስ አቋም ሪፖርት ላይ ግምገማ
ያደርጋል፣
45.6. የዩኒየኑ ሂሳብ አያያዝ ዘመናዊ አሰራርን የተከተለ መሆን አለበት፣
45.7. በፋይናንስ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ዩኒየኑ የሚከተሉትን የሂሳብ አሰራር ስርዓቶች ይከተላል፡፡
45.7.1. የወለድ አልባ እና ወለድ የሚያስገኝ የቁጠባ ሂሳብ አሰባሰብና አወጣጥ አሰራር ስርዓት
45.7.2. የወለድ አልባ እና ወለድ የሚያስገኝ የብድር አሰጣጥና አመላለስ አሰራር ስርዓት
45.7.3. የአነስተኛ መድን ዋስትና እና የተካፉል አገልግሎት ስርዓት
45.7.4. የወጪና የትርፍ አተማመን ስርዓት
45.7.5. የሂሳብ መግለጫና ሪፖርት አቀራረብ አሰራር ስርዓት ሂደት ይከተላል፣
45.8. የፋይናንስ አገልግሎት የሂሳብ እና መዝገብ የራሱ የሆነ የተለያዩ የሂሳ ሰነዶች፣መዛግቦች እና ቅጻ ቅጾች ይኖሩታል፡፡
የሂሳብ ሰነዶችን አስመልክቶ በፋይናንስ አስተዳደር መመሪያ የሚካተቱ ናቸው፣
46. ስለ ቅጣትና ልዩ ልዩ የአገልግሎት ክፍያ፣

46.1. አዋጅን፣ ደንብን ፣ መመሪያንና የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔን ያላከበረ አባል ቅጣት ይቀጣል፣ የሥራ አመራር
ቦርዱም የጥፋቱን ክብደትና ቅለት በመመርመር የቅጣት ውሳኔ ይሰጣል፣ በውሳኔው ያልተስማማ አባል
ጉዳዩ በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት እንዲታይ ማድረግ ይችላል፣
46.2. ከተቀጣ አባል የሚሰበሰብ ገቢ ለአባላት የማይከፋፈል ወይም ሌላ ጥቅም የማይገኝበት ሲሆን ለኅብረት
ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ስራ ማስኬጃነት ይውላል፡፡
46.3. የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ለሚሰጠው ልዩ ልዩ አገልግሎት በኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ውስጠ ደንብ መሰረት አገልግሎት ክፍያ
ሊሰበስብ ይችላል፣
47. የአበልና ሌሎች ክፍያዎች
47.1. ለስራ አመራር ቦርድና ሌሎች የኮሚቴ አመራሮች እንዲሁም ለቅጥር ሰራተኞች የሚከፈል አበል በፋይናንስ አስተዳደር
ውስጠ መመሪያ መሰረት ይሆናል፣
47.2. የአበልና ሌሎች ክፍያዎች ተመን የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ ማግኘት ያስፈልጋል፣
48. የዩኒየኑ መዛግብትና የሂሳብ ሰነዶች፣
48.1. ዩኒየኑ ለስራ አስፈላጊ የሆኑ መዛግብቶችና ሰነዶች ይኖሩታል፣ ዝርዝሩ በውስጠ ደንብ እና በፋይናንስ አስተዳደር
መመሪያ ይቀመጣል፣
49. የዩኒየኑ የገንዘብ ምንጭ፣

23
49.1. የመመዝገቢያ ክፍያ፣
49.2. ከአባላት የሚሰበሰብ ዕጣ ክፍያ
49.3. ከትርፍ ላይ ተቀንሶ የሚቀመጥ መጠባበቂያ
49.4. ከተለያዩ አካላት የሚሰጡ ስጦታዎች፣
49.5. ከአባሉ የሚሰበሰብ ቁጠባ
49.6. ከውጭ አካላት የሚገኙ የተለያዩ ብድሮች
49.7. ከጥቃቅን ሽያጭ የሚገኝ ገቢ
49.8. ከወለድ የሚገኝ ገቢ
49.9. ከቅጣት የሚገኝ ገቢ፣
49.10. ሌሎች ገቢዎችን ያካትታል፣
50. የተጣራ ትርፍ ክፍፍል፣
50.1. ከዩኒየኑ የተጣራ ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ እየተቀነሰ የካፒታሉን 30 በመቶ እስከሚደርስ ድረስ ዩኒየኑ በሚከፍተው
ቁጠባ ሂሳብ ተቀማጭ ይሆናል፣
50.2. የዩኒየኑ መጠባበቂያ ካፒታል የሚፈለገውን መጠን ከደረሰ በኋላ የተጣራ ትርፍ ሙሉ በሙሉ ለትርፍ ክፍፍል ይውላል፣
ሆኖም ህግ በሚያዘው መሰረት ለኅብረት ሥራ ፈንድ የሚሆን ገንዘብ ተቀናሽ መሆን ይኖርበታል፣
50.3. የዩኒየኑ መጠባበቂያ ሂሳብ በሚፈለገው ደረጃ መገኘቱን ትርፍ ክፍፍል ከመደረጉ በፊት በኦዲተር መረጋገጥ
ይኖርበታል፣ ሆኖም የመጠባበቂያው ሂሳብ በአንቀጽ 50.1 ከተጠቀሰው በታች ከሆነ የመጠባበቂያ ሂሳቡ በሚፈለገው
ደረጃ እስከሚደርስ ድረስ ከትርፉ እየቀነሰ በመጠባበቂያ ሂሳብ ውስጥ ያስቀምጣል፣
50.4. በአንቀጽ 50.1 የተጠቀሰው ሂሳብ ከተቀነሰ በኋላ ቀሪው 70 በመቶ ትርፍ በየአመቱ በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ የሚደለደል
ሆኖ የትርፍ ክፍፍል ድልድሉም እንደሚከተለው በመቶኛ ይሆናል፣
50.4.1. ለእጣና አባላት ካፒታል
50.4.2. ለአባላት ቁጠባ
50.4.3. ለብድር አመላለስ
50.4.4. ለትምህርትና ስልጠና
50.4.5. ለማህበራዊ አገልግሎት
50.4.6. ለኅብረት ሥራ ፈንድ ተከፋይ
50.4.7. ለተለያዩ ማበረታቻዎች
50.5. አባላት ካገኙት ዓመታዊ ትርፍ ክፍፍል ተጨማሪ እጣ ሊገዙ ይችላሉ፣
50.6. የመጠባበቂያ ገንዘብ ወጪ የሚሆነው፣
50.6.1. ዩኒየኑ ኪሳራ በሚደርስበት ጊዜ ለኪሳራ ማካካሻ ለማዋል፣
50.6.2. ዩኒየኑ የፋይናንስ እጥረት ሲያጋጥመው አግባብ ያለው ባለስልጣን በማስፈቀድ ለአጭር ጊዜ ለሆኑ ስራዎች
ማዋል ይቻላል፣
51. ስለማይከፋፈል የዩኒየኑ የጋራ ንብረቶች፣
51.1. በአንቀጽ 50.1 የተገለጸው የመጠባበቂያ ገንዘብ ለአባላት አይከፋፈልም፣
51.2. ዩኒየኑ በስጦታ፣ በሽልማት ያገኛቸው ንብረቶች የዩኒየኑ የወል ንብረት ይሆናል፣
24
51.3. ለመጠባበቂያ የተመደበው ሂሳብ ለብድር አገልግሎት እና ለብድር ዋስትና አይውሉም፣

52. ስለ ዩኒየኑ ሂሳብ ወይም በጀት አመት፣


52.1. የዩኒየኑ ሂሳብ ዓመት ከሀምሌ 1 እሰከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ ይሆናል፣
52.2. የዩኒየኑ ሂሳብ በ………… ግዜ ተዘግቶ የፋይናንስ መግለጫዎች መዘጋጃት አለባቸው፣ ለስራ አመራር ቦርድ መቅረብ
ይኖርባቸዋል፣
52.3. የበጀት አመቱን ተከትለው ዩኒየኑ እቅድና በጀት እንዲሁም የአፈጻጸም ሪፖርት ተዘጋጅተው ለስራ አመራር ቦርድና
ለጠቅላላ ጉባኤ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣
53. የሂሳብ ምርመራ፣
53.1. ዩኒየኑ ሂሳብ እንዲመረመርለት አግባብ ላለው ባለስልጣን ጥያቄ ያቀርባል፣
53.2. የዩኒየኑ ሂሳብ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ አግባብ ባለው አካል በሚመድበው ኦዲተር ይመረመራል፣
53.3. ዩኒየኑ አግባብ ያለውን ባለስልጣን አስፈቅዶ ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይችላል፣
53.4. የዩኒየኑ ሂሳብ ከበጀት ዓመቱ መጀመሪ ጀምሮ በ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ሂሳቡ መመርመር
አለበት፣
53.5. ሂሳቡን የሚመረምረው ኦዲተር የዩኒየኑን ሰነዶችና መዛግብቶች የማየት፣ እዳውንና ጥሬ ገንዘቡን የመመርምር፣
የዋስትና ሰነዶችን፣ የሀብቱን ዋጋ እንዲሁም ኃላፊነቱን ጨምሮ ይመረምራል፣
53.6. በአንቀጽ 53.5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ አመራር አካላትና ቅጥር ሰራተኞች በአዋጅ፣ደንብ፣ መመሪያ፣
በመተዳደሪያ ደንብ እና ዩኒየኑ የሚያወጣቸው መመሪያዎችን መሰረት እየሰሩ መሆኑን የመመርመር ኃላፊነት አለበት፣
53.7. የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ሂሳብ ወለድ ከሚያስገኝ ሂሳብ ለብቻው ተለይቶ ኦዲት መደረግ ይኖርበታል፣
53.8. የሂሳብ ምርመራ ሪፖርት ለዩኒየኑ በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለጠቅላላ ጉባኤ መቅረብ ይኖርበታል፣
53.9. የቀረበው ኦዲት ሪፖርቱ የአሰራር ግድፈቶችና የሂሳብ ጉድለቶች ከታዩበት እንዲስተካካል ውሳኔ ይሰጣል፣
53.10. በኦዲት ሪፖርት ላይ ቅሬታ ያለው አካል ወይም ግለሰብ ሪፖርቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ከጸደቀ በኋላ ባለው 30 ቀናት ውስጥ
ቅሬታውን አግባብ ላለው አካል ማቅረብ ይችላል፣ ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጣ አቤቱታ ተቀባይነት አይኖረውም፣
54. ቁጥጥር
54.1. ዩኒየኑ የፋይናንስ አፈጻጸሙን የሚገመግምበት አግባብ ያለው አካል በሚያወጣው የፋይናንስ አፈጻጸም መገምገሚያና
መከታተያ መመሪያ መሰረት አሰራር ስርዓት ይኖረዋል፣ የፋይናንስ አፈጻጸም መገምገሚያ መከታተያ ስርዓት በዋናነት
በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ማተኮር ይኖርበታል፤-
54.1.1. የሀብት ጥበቃ፣
54.1.2. የሀብት ውጤታማነት፣
54.1.3. የሀብት ጥራት፣
54.1.4. ትርፋማነት፣
54.1.5. የእዳ መጠን፣
54.1.6. የእድገት ምልክቶች፣
54.2. በአንቀጽ 54.1 በተቀመጡት የፋይናንስ አፈጻጸም መገምገሚያ መከታተያ ዝርዝር አሰራር ዩኒየኑ ያዘጋጃል፣ በጠቅላላ
ጉባኤ ያጸድቃል፣ ተግባራዊ በማድረግ በየጊዜው የዩኒየኑ ፋይናንስ ደህንነት በጥሩ ሁኔታ መሆኑን ያረጋግጣል፣
25
የዩኒየኑ መዛግብትና ሰነዶች ለተቆጣጣሪ አካል ክፍት መሆን አለባቸው፣የአመራር አካላትና ቅጥር ሰራተኞች
54.3.
ለቁጥጥር ስራው መሳካት አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ ይኖርባቸዋል፣
54.4. የስራ አመራር ቦርድ ወይም የቁጥጥር ኮሚቴ አባሎች አብዛኞች ወይም ከጠቅላላ የዩኒየኑ አባላት መካከል አንድ
ሶስተኛ ያለነሱ አባላት ቁጥጥር እንዲደረግ ሲጠይቁ ቁጥጥር ይደረጋል፣
54.5. በቁጥጥሩ ሪፖርት የተጠቀሱ የአሰራር ግድፈቶች እና የሂሳብ ጉድለቶች እንዲታረሙ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ መወሰን
አለበት፣
55. የሂሳብ ቁጥጥርና ምርመራ ውጤት ስለማስቀመጥና ክፍት ስለማድረግ፣
55.1. የሂሳብ ቁጥጥርና ምርመራ ውጤት ሪፖርት የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ አባላትና ከኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ጋር የስራ ግንኙት
ያላቸው አካላት በቀላሉ ሊያገኙትና ሊያዩት በሚችሉበት አኳኋን መቀመጥ አለበት፣
56. የዩኒየኑ ንብረትና ገንዘብ ላይ ጉድለት ሲደርስ ስለሚወስድ እርምጃ ፣
56.1. የዩኒየኑን ሥራ እንዲያከናውን ኃላፊነት የተሰጠው አባል መሰረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር ወይም የዩኒየኑ አመራር
ወይም ሠራተኛ የሚከተሉትን ጥፋት ፈጽሞ ከተገኘ፡-
56.1.1. ከኅብረት ሥራ አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያዎች እንዲሁም ከኅብረት ሥራ ዩኒየኑ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ያልተፈቀደ
ክፍያ ፈጽሞ ከተገኘ፣
56.1.2. እምነትን በማጉደል ወይም ሆን ብሎ በማሰብ ወይም በቸልተኝነት በዩኒየኑ ንብረት ላይ ጉድለት አድርሶ ከተገኘ፣
56.1.3. የዩኒየኑ ገንዘብ አላግባብ ከወሰደ፣ የሸጠ፣ያሸሸ፣ የደበቀ ወይም የሀሰት ማስረጃ ሰነድ ያቀረበ፣ ሰነዶችን
ያጠፋ፣የሰረዘ፣የደለዘ፣ወይም ሀሰት የሆነ የምስክር ወረቀት ያዘጋጀ ወይም ፈርሞ የሰጠ፣
56.1.4. የዩኒየኑን ንብረት ወይም ገንዘብ በማጭበርበር ለራሱ ጥቅም ያዋለ ወይም ሌላ ሰው እንዲያጭበረብር ሁኔታዎችን
በማመቻቸት የተባበረ እንደሆነ፣
56.1.5. በዩኒየኑ የውስጥ የፋይናንስ አሰራር ደንብ ውስጥ ከተቀመጠው መስፈርት ውጭ ዩኒየኑን አደጋ ላይ እንዲወድቅ
ያደረገ በጋራም ሆነ በተናጠል ተጠያቂ ይሆናል፣
56.2. ተቆጣጣሪው ወይም መርማሪው ስለሁኔታው ዝርዝር ማስረጃዎችን በማዘጋጀት ለዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ ወይም ለሥራ
አመራር ቦርድ እና አግባብ ያለው ባለሥልጣን ሪፖርት ያደርጋል፡፡
56.3. በዚህም አንቀጽ 56.2. መሠረት ሪፖርት የቀረበለት አግባብ ያለው ባለሥልጣን ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው /
ግለሰብ / በሁለት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መልስ እንዲያቀርብ ዕድል ይሰጠዋል፡፡
56.4. ግለሰቡ በተሰጠው ጊዜ ገደብ መልስ ካልሰጠ የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ ወይም አግባብ ያለው ባለሥልጣን
ጉዳዩን በህግ እንዲጠየቅ ያደረጋል፣

57. የብድር ወይም እዳ አከፋፈል ቅደም ተከተል


57.1. ማንኛውም የዩኒየን አባል በዩኒየኑ ላለበት ብድር ወይም እዳ የአከፋፈል ቅደም ተከተል በሚከተለው ሁኔታ ይሆናል፡-
57.1.1. ወለድ የሚያስገኝ ክፍያዎች
57.1.1.1. ብድሩን ለመስጠትና ለማስመለስ ለወጣው ወጪ ካሳና ኪሳራ
26
ለብድር ወለድ
57.1.1.2.
57.1.1.3. ዋና ብድር ወይም እዳ ይሆናል፣
57.1.2. ወለድ አልባ ለሆነ ብድር

57.1.2.1. ለአባሉ የተሸጠበት ዋጋ ብቻ ነው፣


58. በዩኒየኑ ውስጥ ስለሚነሳ አለመግባባት፣ በዕርቅ ስለመጨረስና ስለ ሽምግልና ዳኝነት፣

58.1. በዩኒየኑ ውስጥ ለሚነሱ አለመግባባት በስራ አመራር ቦርድ ወይም በጠቅላላ ጉባኤ ታይቶ ውሳኔ ሊያገኝ

ይችላል ፡፡
58.2. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 58.1 ውሳኔ ያላገኘ አለመግባባት በዕርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት ማለቅ

ይችላል፣በዕርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት የሚታዩ አለመግባባት በአዋጁ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፣
59. ስለ ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ መፍረስ፣

በሚከተሉት ምክንያቶች ዩኒየኑ ሊፈርስ ይችላል፣


59.1. በጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ውሳኔ፣
የአባል ኅብረት ሥራ ማህበራት ቁጥር ከ 2 በታች ሲሆን ፣
59.2.

59.3. ፍርድ ቤት እንዲፈርስ ሲወስን ፣

59.4. በሂሳብ ምርመራ ውጤት መሰረት ዩኒየኑ የከሰረና የኪሳራው መጠን ህልውናን የሚያሰጣ መሆኑን አግባብ

ያለው ባለስልጣን ሲያረጋግጥና በጠቅላላ ጉባኤ ሲወሰን ፣


59.5. በአንቀጽ 59.1 እስከ 59.4 የተጠቀሱት ነጥቦች እንዳሉ ሆኖ የኅብረት ሥራ ዩኒየኑ እንዲፈርስ አግባብ ላለው

ባለስልጣን ውሳኔውን በሰባት ቀናት ውስጥ እንዲያውቅ ይደረጋል፣


60. ሂሳብ አጣሪ ስለ መመደብና ሌሎች መከናወን ያለባቸው ተግባሮች ፣

60.1. የዩኒየኑ እንዲፈርስ ሲወሰን አግባብ ያለው ባለስልጣን በዩኒየኑ ወጪ ሂሳብ አጣሪ ይመድባል፣

60.2. ሂሳብ አጣሪው በአዋጁ መሰረት ሂሳብ የማጣራት ስራዎችን ያከናውናል፣

60.3. የገንዘብ ጠያቂዎች መብት መጠበቁ ከተረጋገጠ በኋላ የዩኒየኑ ቀሪ ንብረት ለአባላት ባላቸው ዕጣ መሰረት

ይከፋፈላል፣
60.4. ለዩኒየኑ የተሰጠውን የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ላለው ባለስልጣን

ተመላሽ ያደርጋል፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተመለሰበት ቀን ጀምሮ የዩኒየኑ ህጋዊ ሰውነት አይኖረውም፣

61. የመልካም ሥራ ውጤት ማትጊያ አሰጣጥ፣


61.1. የሥራ አመራር ቦርድ፤ የቁጥጥር ኮሚቴ ሌሎች ንዑስ ኮሚቴ እንዲሁም የቅጥር ሠራተኛ በተነሳሽነት ወጪ

ቆጣቢ በሆነ መንገድ የዩኒየኑን ዕድገት ማምጣት እስከቻሉ ድረስ ላከናወኑት ተግባር ከዓመቱ ትርፍ ማትጊያ
በጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ሊከፈላቸው ይችላል፡፡
61.2. ዩኒየኑ አመራር አባላትና የቅጥር ሠራተኞች የመልካም ሥራ ውጤት ማትጊያ የሚፈጸመው አግባብ ያለው
27
አካል በሚያወጠው መመሪያ እና በዩኒየኑ የሰው ኃይል አስተዳደር መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፣
62. የውስጥ ደንብ ስለማውጣት፣

62.1. የሥራ አመራር ቦርድና የቁጥጥር ኮሚቴ በዚህ መተዳዳሪያ ደንብ መሰረት የውስጥ ደንብ አዘጋጅተው

በጠቅላላ ጉባኤ ፀድቆ ለ ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ቀርቦ ከተመዘገበና የክልሉ
የኤጀንሲው ማህተም ተደርጎ ከተላከ በኋላ ሥራ ላይ ያውላሉ፣
63. ስለ ደንብ ትርጓሜ፣

63.1. በዚህ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ አሻሚ የሆኑ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ወይም ክርክር የሚያስነሱ ቃላቶች
ከተፈጠሩ በጠቅላላ ጉባኤ የሚሰጠው ትርጓሜ የመጨረሻ ይሆናል፣
64. ልዩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች፣
64.1. በአባላቱ ላይ አስገዳጅነት እንዲኖረው የሚያስፈልገው ልዩ ውሳኔ ከኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ጠቅላላ

ጉባኤ ውስጥ በሁለት ሶስተኛው መጽደቅ አለበት፣


64.2. የዩኒየኑ መፍረስ፣ መካፈል፣ መዋሀድና ሌሎች የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ
ጉዳዮች ልዩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ይሆናሉ፣
65. የተመዳደሪያ ደንብ ስለማሻሻል፣
65.1. ይህ መተዳደሪያ ደንብ ሊሻሻል የሚችለው በኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ ቢያንስ በሁለት

ሶስተኛው ተገኝቶ ሲወስን ነው፣

65.2. በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ የተደረገ መሻሻልና የዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ የተላለፈ ውሳኔ በሶስት ኮፒ ተዘጋጅቶ
ውሳኔ ከተላለፈበት ጊዜ በ30 ቀን ውስጥ ለ……………….ክልል ኅብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ቀርቦ
ከተገመገመ በኋላ ተመዝግቦ የክልሉ ሕጋዊ ማህተም ተደርጎ ከተላከ በኋላ ሥራ ላይ ይውላል፡፡

66. መተዳደሪያ ደንብ የሚፀናበት ጊዜ፣

66.1. ይህ መተዳደሪያ ደንብ በኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ጠቅላላ ጉባኤ ፀድቆ አግባብ ባለው አካል ቀርቦ
ከተመዝገበበት ቀን ዓ/ም ጀምሮ የፀናይሆናል፡፡

28

You might also like