You are on page 1of 2

በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የማዕከላዊ አካባቢ ጽ/ቤት

የግዢ ኮሚቴ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔ

ቦታ፡ የአከባቢ ጽ/ቤቱ የሠራተኞች ሻይ ክበብ

ቀን፡ ነሐሴ 03/2013

ሰዓት፡ ከቀኑ 09:30

የኮሚቴው አባላት፡-

1. አቶ ተሾመ አልበኔ ሰብሳቢ ---------------------


2. አቶ ውድነህ ታዬ አባል ---------------------
2. ብርሃኑ ደሬሳ አባል ---------------------
3. ወ/ሮ ቤተልሔም ተስፋ ፀሐፊ ---------------------
4. አቶ ዲሳሳ ደበላ አባል ---------------------

አጀንዳ

በአዳማ ወጣት ማዕከል የሚገኘው የሙዚቃ ቡድን የተለያዩ ዓይነት ባህላዊና ዘመናዊ አልባሳትን መግዛት ይቻል ዘንድ የውሳኔ ሀሳብ
ለማቅረብ

በዚህ መሠረት

የተለያዩ ዓይነት ባህላዊና ዘመናዊ አልባሳትን ለመግዛት ከዚህ ሰኔድ ጋር በአባሪነት በተያያዘው ግዥ መጠየቂያ መሠረት
በአከባቢ ጽ/ቤታችን የግዥ ባለሙያ ፕሮፎርማ(የዕቃ ዋጋ) ለመሰብሰብ የተሞከረ ቢሆንም በዋጋ ማቅረቢያ ለእነዚህ
አልባሳቶች ዋጋ ለመስጠት ፈቃደኛ የሚሆን ከአንድ አቅራቢ (ስንዱ ስዩም (አባ ገዳ) የባህል አልባሳት ንግድ) ውጪ
ማግኘት አልተቻለም፡፡ይህንን ችግር በተመለከተ በቀን 08/11/2013 ዓ/ም በግዥ ባለሙያው በኩል ማመልከቻ ተጽፎ
ቀርቦ በአከባቢ ጽ/ቤቱ ኃላፊ እና በአስተዳደርና ፋይናንስ አገልግሎት ክፍል በኩል ለዝርዝር የመስክ ምልከታ ለግዥ
ኮሚቴ በተመራው መጠይቅና ማመልከቻ መሠረት ኮሚቴው ማህበሩ የግዥ ሂደትን በተመለከተ እንዲመራበት
ካስቀመጠው መመሪያ አንጻር ተወዳዳሪ ድርጅቱ የምርቱ(አገልግሎቱ) ብቸኛ አቅራቢ ወይም አምራች ካልሆነ በስተቀር
ከአንድ አቅራቢ ቀጥታ ግዥን መፈጸም የሚከለክል ቢሆንም ኮሚቴው በዚህ ጉዳይ ላይ በቀን ሐምሌ 12/2013 ዓ/ም
የገበያ ዳሰሳ ሥራ የሰራ ሲሆን በዚህም በአቅራቢ ደረጃ የተለያዩ የተዘጋጁ የባህል አልባሳትን የሚሸጡና ሰርተው
የሚያቀርቡ ድርጅቶችን ያገኘ ቢሆንም ከስንዱ ስዩም (አባ ገዳ) የባህል አልባሳት ንግድ) ውጪ ፍቃደኛ ሆኖ የዋጋ
ማቅረቢያ የሚሰጥ ድርጅት ማግኘት አለመቻሉን አረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ግዥውን ለመፈጸም ይቻል ዘንድ በግዥ
ባለሙያ ማመልከቻና በኮሚቴው የመስክ ምልከታ ግብረ-መልስ መሠረት ግዥው በቀጥታ ከስንዱ ስዩም (አባ ገዳ)
የባህል አልባሳት ንግድ) በየአልባሳቱ ዓይነት በተሰጠው ዋጋ እንዲፈጸም የውሳኔ ሀሳብ እያቀረበ በኮሚቴው ውሳኔ ላይ
የመ/ቤቱ የማናጅመንት ኮሚቴም አስተያየት እንዲሰጥበት ክፍት መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

የአከባቢ ጽ/ቤቱ የማናጅመንት ኮሚቴ ጥቅል አስተያየት ----------------------------------------------------

You might also like