Professional Documents
Culture Documents
Page 1 of 2
Page 1 of 2
የእለቱ አጀንዳዎች፦
ስብሰባዉ አባላቱ ዉይይት በተደጋጋሚ እንዲደረግ ሊቀመንበሩ ቢነገራቸዉም ሊፈጽሙት ባለመቻላቸዉ አባላት
በቴሌግራምና በስልክ በመጠራራት በማህበሩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ላይ ዉይይት በማስፈለጉ የተደረገ ስብሰባ
ሲሆን አመራሮችን በነጻነት ለመገምገም እንዲቻልና ሊቀመንበሩ ባለመገኘታቸዉ ዉይይቱን በጊዜያዊነት
እንዲመሩ አቶ------------------------------ እና --------------------------------- መርጠን ከላይ የተያዙ አጀንዳዎችን
እንዲታዩ አባላቱ በሙሉ ድምጽ በመስማማት ስብሰባዉ የተጀመረና ሰፊ ዉይይት ከተደረገ በኋላ የሚከተሉትን
ዉሳኔዎች አባላቱ አስተላልፏል።
አጀንዳ 1. የማህበሩ አመራሮች የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በመወያየት ግምገማ ማድረግና ዉሳኔ ማስተላለፍ
Page 1 of 2
አጀንዳ አንድን በተመለከተ ማህበራችን በተለያዩ ጊዜያት ዉይይት እንዲደረግና የፋይናንስ እንቅስቃሴዉን መረጃ
ሪፖርት እንዲቀርብና እንዲያወያዩ በአባላቱ በተደጋጋሚ ለማህበሩ ሊቀመንበሩ ጥያቄ ቢቀርብላቸዉም ሊያወያዩ
ፈቃደኛ ባለመሆናቸዉና ስራቸዉም ግልጸኝነት የጎደለዉ ከመሆኑ ባሻገር አንዳንድ ዉሳኔዎችን ቃለጉባኤ በማዞር
ብቻ አባላቱ ሃሳብ ሳይሰጥ የሚፈልጉትን ዉሳኔ እያስቀመጡ በአባላቱ የስራ ቦታ በመሄድ በተናጠል አንተ ብቻ ነህ
የቀረህ በማለት እያስፈረሙ ዉሳኔዎችን የሚያስፈጽሙ በመሆኑ፣የማህበር አባላቱ የሚፈለጉ መረጃዎችን
እንዲሰጣቸዉ ሲጠይቁ ባልተገባ ቢሮክራሲ አባላቱን ላልተገባ እንግልትና ወጪ እየዳረጉ መሆኑ፣ የአገልጋይነት
መንፈስን ተላብሰዉ እየሰሩ ባለመሆኑ አባላቱን በእኩል አይን ያለማየት ችግሮች የሚስተዋልባቸዉ በመሆኑ ከጊዜ
ወደ ጊዜ እየባሰባቸዉ የመጣና ሁሉም አባላት የደረሰበትን በከፍተኛ እሮሮ ካቀረበ በኋላ የማህበሩ አባላት ትክክለኛ
አገልግሎት አድሎና ግልጸኝነት ያለዉን አገልግሎት እንዲያገኝ ከማህበሩ አመራሮች መካከል ችግር ያለባቸዉ
ያላቸዉን ማንሳት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በምትካቸዉ ሌሎች አመራሮችን መቀየር እንዳለባቸዉ በሙሉ
ድምጽ በመታመኑ
2 ኛ. አቶ ---------------------------------------------------------------------- የነበሩት
በአቶ/ወ/ሮ------------------------------- ተተክተዉ የማህበሩ ---------------------------- ሆነዉ እንዲሰሩ
በሙሉ ድምጽ ተስማምተን የወሰን በመሆኑ የተመረጡ አመራሮች አስፈላጊዉን ሂደት ከማህበራት አደራጅ
ቢሮዎች ጋር በመነጋገር አስፈላጊዉን ሁሉ እንዲፈጽሙ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ቀጣይ በማህበሩ መሰራት ያለባቸዉን ጉዳዮች በሰፊዉ አባላቱ ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡
ማህበሩ እስካሁን ከመጀመሪያ ጀምሮ የተከናወኑ ተግባራትንና የወጡ ወጪዎች ሪፖርት ለጠቅላላ አባላት አቅርቦ
ያላስገመገመነ እንደ አስፈላጊነቱ ኦዲት መደረግ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ካሉ ለመወሰን እንዲመች በአድስ የተመረጡና ነባር
የቀጠሉ አመራሮች እስከ ነሐሴ 16 ድረስ ሪፖርቱን በማዘጋጀትና በማህበሩ የተከፈቱ የባንክ አካዉንቶችን ባላንስ
ጭምር በማጣራት የስብሰባ ጥሪ በማድረግ ሪፖርቱን እንዲያሰማ ተወስኗል፡፡
የቀጣይ ስራዎችንና አገልግሎቶችን በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አመራሮች በቅንነትና በታማኝነት
ያለአድሎ እንዲያገለግሉ ጠቅላላ ጉባኤዉ አደራ በመስጠት ስብሰባዉ ተጠናቋል፡፡
Page 2 of 2