You are on page 1of 3

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች


ሀገር አቀፍ ስልጠና መርኃ ግብር
የባሕር ዳር ሥልጠና ማዕከል ቡድን የውይይት ቃለ ጉባዔ ቁጥር ሶስት (3)
የስብሰባው ቀን ፡- መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

የስብሰባው ሰዓት ፡- 11፡00 ሰዓት

የስብሰባው ቦታ ፡- በኢ.ል.ባ ባሕር ዳር ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ ቢሮ

በስብሰባው ላይ የተገኙ አባላት


ስም ዝርዝር ኃላፊነት ፊረማ
1. አቶ ስንታየሁ ልንገረው ……………………ሰብሳቢ ………….
2. አቶ ታምራት አባተ……………………….…..አባል ………….
3. አቶ ሃብቴ መብሬ ……………………….…...አባል ………….
4. አቶ በአምላኩ ታዬ …………………………. አባል ………….
5. አቶ ጌታሁን ታምሬ …………………….……አባል ………….
6. አቶ ታጠቅ ሞላ ……………………………. አባል ………….
7. አቶ ሙሉቀን አመነ …………………….……ፀሐፊ …………

አጀንዳ ፡-

 በባሕርዳር ስልጠና ማዕከል የድርጊት መርሃ-ግብር መሠረት የመጋቢት 8 ቀን 2013


ዓ.ም የቀን ውሎ የስራ ክንውን ሪፖርትን በተመለከተ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከየፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዝ ማስፋፊያ


ባለስልጣን ጋር በመተባበር ለአነስተኛና መካለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች አቅማቸውን በመገንባት
እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የስልጠና መረሐ ግብር ማዘጋጅቱ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሠረት ለባሕርዳር የስልጠና ማዕከል ቡድኑ ለስልጠናው አስከላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ
እና የተለያዩ ስራዎችን እንዲሠሩ በተሠጠው መመሪያ መሠረት ዛሬ ለሶስተኛ ቀን በድርጊት መርሃ ግብሩ
እቅድ አግባብ መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም የተከናወነውን ስራም እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡

አጀንዳ አንድ፡

ሁሉም የቡድን አባላት የዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ ቢሮ ከጠዋቱ 2 ሠዓት በመገኘት ከትናንት የቀጠሉ ስራዎች
ላይ በመወያየት ዛሬ መከናወን የሚገባቸውን ነገሮች ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስራ
ጀምሯል፡፡ ባለፉት ሁለት ቀናት በተከታታይ የተሠሩ ስራዎች ዝርዝር የያዘ ቃለ-ጉባኤ ቁጥር 1 እና 2 ተፈርሞ
ለስቲሪንግ ኮሚቴው እንዲደርሠው ተደርጓል፡፡

አጀንዳ ሁለት፡

ባንኩ ለሚሠጠው ስልጠና በኪራይ የተገኘውን አዳራሽ በዋነኝነት የሚጎድለው የኢንተረኔት አገልግሎት ስለሆነ
አገልግሎቱ ሊገባ የሚችልበት አግባብ ላይ ከባህል ማዕከሉ አስተዳዳሪ እና ከኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ
ሪጅን ኃላፊ ጋር ቡድኑ ውይይት አድርገናል፡፡ በውይይቱም የሙሉዓለም ባህል ማዕከል አዳራሽ ከዚህን ቀደም
የኢንተርኔት አገልግሎቱ up-grade እንዲደረግለት የጠየቀ መሆኑን ከማዕከሉ አስተዳዳሪ በመረዳት ጉዳዩን
ለኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ ሪጅን በማንሳት እና ውይይት በማድረግ እና ለምን እኛ አንደፈለግነው
በዝርዝር በማስረዳት ማዕከሉ በጠየቀው መሠረት አገልግሎቱ እንዲገባ የተስማማን ሲሆን አገልግሎቱም እስከ
ነገ ማለትም ሐሙስ መጋቢት 09 ቀን 2013 ዓ.ም ምሳ ሠዓት ድረስ እንደሚጠናቀቅ እና ለሙከራ ዝግጁ
እንደሚሆን ከተወያየን በሗላ ወደ ስራ በመግባት ዛሬ መሠራት ያለባቸውው ስራዎች ማለትም የመእከሉን
የኢንተርኔት አገልግሎት ቁጥር በደብዳቤ ለኢትዮ ቴሌኮም የማሳወቅ ስራ ተሰርቷል በተጨማሪም ለፋይበር
ዝርጋታው የሚያስፈልግ ፖል መትከያ ጉድጓድ አንዲቆፈር ተደርጓል መስመሩም ከተዘረጋ በሗላ አዳራሽ
ውስጥ ለማስገባት የአዳራሹን ግድግዳ በድሪል አንዲበሳ በመድረግ ለነገ ማለትም ለሐሙስ ስራ ዝግጁ
የማድረግ ስራ ተሠርቷል፡፡ በሌላ በኩል ከኢንተርኔት ፍጥነት ጋር በተያያዘ በባንኩ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተቀመጠው መስፈርት 20 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ በመሆኑ አሁን የሚዘረጋው
መስመር ደግሞ ማዕከሉም የጠየቀው 15 ሜጋ ባይት ፐር ሰከንድ ስለሆነ ልዩነቱን እንዲያስተካክሉልን እና
በልዩነቱ ምክንያት የሚመጣውን ወጪ ባንኩ አዳራሹ ላይ ያለውን ስራ እኪጨርስ ድረስ ያለውን ክፍያ
በዲስትሪክቱ እንዲሸፈን በመስማማት ዲስትሪክቱ ለኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ ሪጅን በደብዳቤ
እንዲጠይቅ አቅጣጫ ካስቀመጥን በሗላ ፍጥነቱን ለመጨመር ጊዜ እንደሚወስድ የቴሌኮሙን ሃላፊ በስልክ
አናግረን መስመሬ ከተዘረጋ የ 20 ደቂቃ ስራ እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል፡፡

አጀንዳ ሶሶት፡
ቡድኑ በተጨማሪም ዛሬ መጋቡት 08 ቀን 2013 ዓ.ም ካከናወናቸው ስራዎች መካከል በባሕርዳር የስልጠና
ማዕከል ከሚሳተፉት ደንበኞች ካሉበት ቅርንጫፍ ማለትም በባሕርዳር ዲስሪክት ስር ሰባት ቅርንጫፎች
በጎንደር ዲስትሪክት ስር ሶስት ቅርንጫፎች የሚሠቀል በኮሙኒኬሽን ሚዲያ ቡድን ተዘጋጅቶ በባንኩ ስትሪንግ
ኮሚቴ እና በተከበሩ የባንኩ ፕሬዚዳንት የፀደቀውን ፖስትር ህትመት ስራ እንዲሠራ የተደረገ ሲሆን
የባሕርዳርን አዚሁ ሲታተም የጎንደር እዛው ታትሞ እንዲሠቀል ተደርጓል፡፡

You might also like