You are on page 1of 4

ሴክተር- ተኮር የሪፎርም አተገባበር ማጠናከሪያ ሠነድና የቲም መተዳደሪያ

ሞደል ላይ ለዞኖችና ለልዩ ወረዳዎች በተሰጠ ስልጠና


የቀርበ ሪፖርት

Page 1 of 4
1. መግቢያ
የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በአገር አቀፍም ሆነ በክልላችን ደረጃ ፍትሀዊና ፈጣን የሆነ ቀጣይነት ያለው

ልማት ለማምጣት በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡ ከዚህ አኳያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማት መስፋፋት ለክልሉ

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገትና የድህነት ቅነሳ፣ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ለዲሞክራሲ ግንባታ የሚኖረው

ፋይዳ ቀላል አይደለም፡፡ በመሆኑም በክልሉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ምጣኔ ሀብታዊ ዕድገት ለማምጣት በሳይንስና

ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጠቀም ባህል እንዲዳብር ማድረግ እና የሳኢቴ መሠረተ ልማትን ለህብረተሰብ ተደራሽ

በማድረግ የመረጃ ልውውጥን በሚያፋጥን መልኩ ማስፋፋት የተቋሙ ዋነኛው ተግባር ነው፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ የሪፎርም ስራን ቅልጣፌን፣ ተደራሽነትን፣ ፍትሀዊነትንና ውጤታማነትን እንዲኖረው ለማድረግ

አቅም ለማሳደግ የሚረዱ እና ችግር ፈቺ በሆነ መልኩ ስራን ማቀናጀት የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ

በማተኮር ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡

2. የስልጠናው ዓለማ
የዞን፣ የልዩወረዳ፣ የተቋም የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በሪፎርም መሣሪያዎች አጠቃቀም ላይ
ስለሚስተዋሉ ችግሮችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች የጋራ ውይይት በማድረግ ፡-
 ወጥ የሆነ ግንዛቤ በመያዝ፣
 ወደ ተግባር በመግባት፣
 ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው፡፡

3. የስልጠናዉ አስፈላጊነት
 የሪፎርም መሣሪያዎች ቀጣይነትን በማጠናከር ተቋማት አገልግሎታቸውን ቀልጣፋና ውጤታማ

በማድረግ ተልኮአቸውን መወጣት እንዲችሉ፣ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጠው የነበረውን ድጋፋዊ

ክትትል አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ የሪፎርም መሣሪያዎች ቀርተዋል የሚል የተምታታ አስተሳሰብን

በመስበር ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት፣ የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካት አንጻር የግንኙነትና የቅንጅት

ክፍተት ለመሙላት እና የሪፎርም እንቅስቃሴ ተገቢውን ቦታ አግኝቶ በየደረጃው ባሉ አመራር እንዲመራ

ለማድረግ ነው፡፡

4. የሪፎርም ስልጠና ተሳታፊ የሆኑ አካላት


 የቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና የዞንና ልዩ ወረዳ የሳይንስና ኢንፎ/ቴክ/መምሪያ/ጽ/ቤት ኃላፊዎችና

የመኔጅመንት አባላት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ስልጠናዉ በጌዲኦ ዞን ዲላ ከተማ ጌዴኦ ባህል አዳራሽ ወንድ

84 ሴት 25 በአጠቃላይ 109 ተሳታፊ በተገኘበት ተሰጥቷል፡፡

Page 2 of 4
5. ለስልጠና የሚሆን ሰነድ ያቀረበ አካል

 ከሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የዕቅድና በጀት ዝግ /ክት/ግም/ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተር፡- አቶ ካምባታ ካዌ ናቸዉ፡፡


6. ስልጠና ሂደት በተመለከተ ውይይት ዙሪያ የተሰጠ አስተያየት ስንመለከት፡ -

በዲላ ከተማ በቀን 25/6/2014 ዓ.ም አቶ ሙሂድን ሁሴን የሳኢቴ ቢሮ ም/ኃላፊና የሳይንስ ቴክኖሎጂ

ፈጠራና ስርጸት ዘርፍ ኃላፊ እና አቶ ከንባታ ከዌ የዕቅድና በጀት ዝግጅት ክት /ግም/ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተር አወያይነት የተከናወነ ሲሆን

በስልጠናው የተነሱ ጥያቄዎች ውሳኔ የሚሹ ጉዳዬች፣


 የ 2014 በጀት ዓመት በቀረበው የሪፎርም ስልጠና ላይ ብዙ አስተማሪ ነገር እንዳገኙበት እና

እውቀት እንደቀሰሙ በማስቀመጥ እንደሚከተለዉ አንዳንድ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

 በተነሳ ጥያቄ

 የዜጎች ቻርተር መነሻ የሆነ ከክልል ማዕከል ቢወርድና እኛም ማዘጋጀት ብንችል፣

 የሪፎርም ውይይትን በተመለከተ በእናንተ በኩል በየ 15 ቀኑ እና በማናጅመንት በየወሩ የሚል

ሲሆን አንዳንዶ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ላይ ያለዉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት

መምሪያ/ጽ/ቤት በየሳምንቱ መወያየት ካልቻላችሁ ዉይይታችሁ ተቀባይነት የለዉም የሚል

ሀሳብ እያንጸባረቁ በመሆኑ አስታራቂ ሀሳብ በክልል እንዲወርድልን የሚልና ለእኛ ለስራችን

በየ 15 ቀኑ ዉይይት ብናረግ እጅግ በጣም የተሻለ ነዉና ይህ ጉዳይ የመጨረሻ እልባት ማግኘት

አለበት የሚል፣

 በሳይንስ ዘርፍም ይሁን በኢኮቴ ዘርፍ በወረዳዎች ላይ ቡድን መሪ ያለመኖር እና የመረጃና

ስታስቲክስ አስተባባሪ የለሌ በመሆኑ በቀጣይ የሚተስካከልበት ሁኔታ ብመቻቺ፣

 ለታችኛው መዋቅር ምላሽና የተሰጠበት አግባብ

 ማኑዋሉ ሴክተር ተኮር ስለሚል በዛ አግባብ መመራት እንዳለባቸው እና ከላይ በቀረቡት

ጥያቄዎች የሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመነጋገር ምላሽ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጾላቸዋል፡፡

የተሰጠ የማጠቃለያ አስተያየት

Page 3 of 4
 በክልሉ በዞን በልዩ ወረዳ በተገኙበት በተሰጠ የሪፎርም ስልጠና ላይ በቀጣዩ ግማሽ ዓመት

የተጠናከረ ስራ መስራት እንዲያስችል እና የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ እንዲረዳ ጥረት

ማድረግ ያስፈልጋል፣

 አደረጃጀትን በተመለከተ ለምሳሌ አንድ ዳይሬክቶሬቶች ላይ አንዳንድ ባለሙያ ያለ እንዴት

ማደራጀት እንዳለበት እና ሌሎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ በተቋሙ ምላሽ መሰጠት የሚችሉት

ባጠቃላይ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

ከክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ዉሳኔ የሚሻ ጉዳይ

 የቢሮአችን የሪፎርም ውይይትን በተመለከተ ቢሮዉ እንደየስራበ ባህርዉና ሁኔታዉ መነሻነት

በመነሳት በየ 15 ቀኑ በአደረጃጀት ደረጃ ዉይይት እየተደረገ እና በዘርፍ እና በማናጅመንት ደረጃ

በየወሩ ዉይይት እንደሚደረግ ይታወቃል፡፡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎችም በዚሁ ልክ የሪፎርም

ስራዉን አጠናክሮ እንዲሄዱ የማድረግ ስራ የተሰራ ሲሆን ከቢሮ እስከ ከተማ አስተዳደር ድረስ

አሰራሩ ወጥ እንዲሆን ተደርጎ ሰልጠና ብሰጣቸዉን ከዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት

መምሪያ/ጽ/ቤት ጋር ብዙ እየተግባቡ ስላይደሉ ዉሳኔ የሚሻ ጉዳይ ነዉ፡፡

ሪፖርቱን ያዘጋጀዉ ባለሙያ ስም፡- ወ/ሪት ይፍቱስራ ብርሃኑ ፊርማ……………..….. ቀን…………………..

የተዘጋጀ ሪፖርት ትክክለኛ ስለመሆኑ ያረጋገጠዉ አካል ስም……………………………………………..

ፊርማ……………………………………………

ቀን……………………………………………….

Page 4 of 4

You might also like