You are on page 1of 34

ማውጫ

i
ክፍል አንድ...............................................................................................................................1
1. መ ግ ቢ ያ.......................................................................................................................1
2. ምርጥ ተሞክሮ ምን ማለት ነው?............................................................................................1
3. ዓላማ..............................................................................................................................2
3.1 ዋና ዓላማ.................................................................................................................2
3.2 ዝርዝር ዓላማ...........................................................................................................2
4. የሰነዱ አስፈላጊነት..............................................................................................................3
5. ወሰን...............................................................................................................................3
6. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ስልት................................................................................................3
6.1 የቦታዎች አመራረጥ.......................................................................................................3
6.2 ምርጥ ተሞክሮዎችን መለያ ስልት.....................................................................................4
ክፍል ሁለት..............................................................................................................................5
ሁለት
7. የምርጥ ተሞክሮው ይዘት......................................................................................................5
ይዘት
7.1 በ 2003 ዓ.ም የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎች...............................................................5
ተሞክሮዎች
7.1.1 ከክልል እስከ ወረዳ በኢኮቴ ዙሪያ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...............................5
7.1.2. ከማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...................................25
ተሞክሮዎች
7.1.3 ከማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...............................................26
ተሞክሮዎች
7.1.4 ከባህር ዳር ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...................................27
7.2 ከ 2004 ዓ.ም እስከ 30/04/2005 ዓ.ም የተሰሩ አዲስ ምርጥ ተሞክሮዎች................................28
7.2.1 ከክልል እስከ ወረዳ በኢኮቴ ዙሪያ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች.........................................28
ተሞክሮዎች
7.2.2 ከማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች....................................35
ተሞክሮዎች
7.2.3 ከማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...............................................35
ተሞክሮዎች
7.2.4 ከባህር ዳር ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች...................................35
ተሞክሮዎች
አባሪ.................................................................................................................................38

ii
ክፍል አንድ

1. መ ግ ቢ ያ
የአማራ ክልል በልማት፣ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና በመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ረገድ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን
በማስፋት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ኢኮቴ) ልማት ኤጀንሲም በክልሉ በኢኮቴ ዙሪያ የተከናወኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን
ቀምሮ ማስፋፋት በማሰፈለጉ በ 2003 ዓ.ም አራት አባላትን የያዘ ቡድን ሰይሞ አሰማርቷል።

ቡድኑም በክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ በዞኖች በኩል የተመረጡ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን የመስክ ጉብኝት በማድረግ እንዲሁም
የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቶችን መሰረት በማድረግ የተሻለ ተሞክሮ የሚባሉትን በመቀመር የ 2003 ዓ.ም የምርጥ
ተሞክሮ ሰነድ አዘጋጅቷል፡፡

ይህ ሰነድ ከ 2003 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2005 ዓ.ም በክልሉ በኢኮቴ ዙሪያ የተከናወኑ ምርጥ ተሞክሮዎችን አካቶ
ይዟል፡፡
ሰነዱ በሁለት ክፍል የተደራጀ ሲሆን በክፍል አንድ መግቢያ፣የምርጥ ተሞክሮ ምንነት፣ ዓላማ፣ የሰነዱ አስፈላጊነት፣ ወሰንና፣
ምርጥ ተሞክሮዎች ለመምረጥና ለመቀመር ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶችን፤በክፍል ሁለት ደገሞ የምርጥ ተሞክሮዎችን ይዘት፣
ማጠቃለያና አባሪ አካቶ ይዟል።

2. ምርጥ ተሞክሮ ምን ማለት ነው?


ምርጥ ተሞክሮ አንድ ወጥ የሆነ ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት ያለው ትርጉም የለውም። በመሆኑም ፀሐፊያን የተለያየ ትርጉም
ሰጥተውታል።
ጥቂቶችን እንመልከት፡-
 A best practice is a method or technique that has consistently shown results superior to
those achieved with other means, and that is used as a benchmark. /Wikipedia/
  A best practice is a technique or methodology that, through experience and research,
has proven to reliably lead to a desired result. /Whalts.com/
 A best practice a set of guidelines, ethics or ideas that represent the most efficient or
prudent course of action. /Investopedia/  
በዚህ ሰነድ ምርጥ ተሞክሮ ማለት በአንድ አካባቢ በተከታታይነት ተገምግሞና ተፈትሾ ውጤታማ የሆነ በተጠቃሚው
ዘንድም ተቀባይነት ያገኘ ፤ ወደሌሎች አካባቢዎችም ሊስፋፋና ቀጣይነት ባለው መልኩ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል አዲስ
የአሠራር ዘዴ ወይም ቴክኒክ ነው፡፡

1
የምርጥ ተሞክሮ መገለጫ ባሕሪያት በተለያየ መልኩ የሚገለጹ ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና
የባሕል ድርጅት/United States Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO)/ ለአብነት
ያህል ባሕሪያቱን እንደሚከተለው ገልጿቸዋል።
 አዲስ ሐሳብ፤አሠራር፤ልምድ ወዘተ መሆኑ፤
 በፊት ከነበረው አሠራር የተለየና ለውጥ የሚያመጣ መሆኑ፤
 ቀጣይነትና ዘለቄታነት ያለው ውጤት የሚያመጣ መሆኑ፤እና
 ወደሌሎች አካባቢዎችም በቀላሉ ሊስፋፋ የሚቸል መሆኑ ናቸው።

3. ዓላማ
3.1 ዋና ዓላማ
በኢኮቴ ዙሪያ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በማስፋፋት ዘርፉ ለልማት፣ ለመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ያለውን
አስተዋጽኦ በማሳደግ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በተጀመረው የዕድገትና ትራንፎርሜሽን ዕቅድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ
ለማድረግ

3.2 ዝርዝር ዓላማ


 በክልላችን የተሠሩትን ምርጥ ተሞክሮዎች በመቀመር ከክልል እስከ ቀበሌ ማስፋፋት፣
 በተሻለ ደረጃ የተሰሩ ስራዎች ነጥረው እንዲወጡ በማድረግ በቀጣይም ለበለጠ ሥራ ተነሳሽነትን መፍጠር፣
 ተናባቢነትን፣ ደረጃውን የጠበቀና ለክልሉ የልማትና መልካም አሰተዳድር መፋጠን የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን
ለማስፋፋት፣
 የተሰሩ ሥራዎችን በማሰራጨት የስራ ድግግሞሽን በመቀነስ ጊዜን፤ ወጪንና የሰው ኃይልን በአግባቡ መጠቀም፣

4. የሰነዱ አስፈላጊነት
ሰነዱ በተወሰኑ መ/ቤቶች በላቀ ደረጃ የተሰሩትን፣ በቀደምት ዓመታት የተከናወኑ ነገር ግን ቀጣይነት ያላቸው ተግባራትን
የያዘ፣ የህብረተሰቡን ችግር ሊያቃልል የሚችል፣ ጊዜና ወጭ ቆጣቢ፣ አዲስና የተሸሻሉ የቴክኖሎጂ ግኝቶችን ያካተተ፣ በቀላሉ
ሊስፋፉ የሚችሉ መሆኑን የለየና የመሳሰሉትን አካቶ የያዘ በመሆኑ አስፈላጊነቱን የላቀ ያደርገዋል።

በአጠቃላይ የሰነዱ አስፈላጊነት በተለያየ ደረጃ ተግባራዊ የሆኑ የኢኮቴ ምርጥ ተሞክሮዎችን በሁሉም ደረጃ ተግባራዊ
በማድረግ በክልላችን በአጭር ጊዜ ኢኮቴን ለማልማትና ለማስፋፋት የሚረዳ በመሆኑ ነው፡፡

2
5. ወሰን
በቅመራ ደረጃ የምርጥ ተሞክሮ ሰነዱ በኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ ስር በሚገኙ አደረጃጀቶችና /ከክልል እስከ ቀበሌ/ በክልል
ሴክተር መ/ቤቶች በኢኮቴ ዙሪያ የተከናወኑ ምርጥ ስራዎችን ያካተተ ሲሆን በትግበራ ደረጃ ደግሞ እንደተጨባጭ ሁኔታው
በሁሉም የክልሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚፈፀም ይሆናል፡፡

6. የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ስልት


6.1 የቦታዎች አመራረጥ
በ 2003 ዓ.ም ተደረገው የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ የሚከተሉትን መመዘኛዎች መሠረት በማድረግ የተሰራ ነው፡፡
 በቀደምት ዓመታት በላቀ ደረጃ የተከናወኑ ነገር ግን ቀጣይነት ያላቸው ተግባራትን በመለየት፣
 ከክልል እስከ ወረዳ የ 2003 ዓ.ም የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት ሪፖርት በማየት፣
 በ 2003 ዓ.ም ደብረማርቆስና ደሴ ላይ የተካሄዱ አውደ ጥናቶች ጭብጦችን መሠረት በማድረግ፣
 የዋና የስራ ሂደት ፈጻሚዎች ለድጋፍ በተንቀሳቀሱበት ወቅት ባደረጉት ምልከታ የተሻለ ልምድ ያላቸውን
ዞኖች/ወረዳዎች እንዲለዩ በማድረግና
 የሚታዩ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን ዞኖች እንዲመረጡ በማድረግ ነው።
በ 2005 ዓ.ም የተደረገው የምርጥ ተሞክሮ መሰረት ያደረገው ከክልል እስከ ወረዳ ከ 2004 ዓ.ም እስከ 30/04/ 2005 ዓ.ም
የተላኩ ሪፖርቶችን በማየት እና ከክልል ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ፣ ከዞኖችና 3 ቱ ትላልቅ ከተሞች መካከል የምርጥ ተሞክሮ
መሰብሰቢያ ቅጹን በመሙላት ምላሽ ከሰጡት በመውሰድ ነው፡፡

6.2 ምርጥ ተሞክሮዎችን መለያ ስልት


በ 2003 ዓ.ም የተደረገው ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ በዞኖች፣ በተመረጡ ክልል መስሪያ ቤቶች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች
ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ምርጥ ተሞከሮ ይሆናሉ ብለው የለዩዋቸውን ስራዎች እንዲገልጹ በመጋበዝና ቡድኑ የበለጠ
ሊብራሩ የሚገባቸውን ጉዳዮች በጥያቄ አንስቶ ማብራሪያ እንዲሠጥባቸው በማድረግ ስምምነት ላይ በመድረስ ነው።

3
ክፍል ሁለት

7. የምርጥ ተሞክሮው ይዘት


የምርጥ ተሞክሮ ሰነዱ ይዘት ለንፅፅር በሚያመች መልኩ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አራት
አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ተለይቶ ቀርቧል።
 ከክልል እስከ ወረዳ በኢኮቴ ዙሪያ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች
 ከማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ መዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች
 ከማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች
 ከባህር ዳር ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች

የእያንዳንዱ ምርጥ ተሞክሮ የተሰራበትን ቦታ፣ የአሰራር ስልቱንና የተገኘውን ውጤት በሚያሳይ መልኩ እንደሚከተለው
ቀርቧል።

7.1 በ 2003 ዓ.ም የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎች

7.1.1 ከክልል እስከ ወረዳ በኢኮቴ ዙሪያ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


1. ኔት ሚቲንግ
ብዙ የኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ኔት ሚትንግን አክቲቬት በማድረግ አይጠቀሙበትም።
ነገር ግን ሰ/ጎንደር ዞን፤ ደ/ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ፤ ሰ/ወሎ ዞን፣ቆቦ ወረዳ፤ላስታ ወረዳ፤ ሰ/ሸዋ ዞን፤ አዊ ብ/አስተዳደር ዞን፤
ኦሮሞ ብ/አ/ዞን፤ ምስ/
ምስ/ጎጃም ዞን ኔት ሚቲንግን በመጠቀም በርቀት ላይ ያለን ደስክቶፕ ማጋራት ተችሏል፡፡
ስልት
በኮምፒዩተሮች ላይ ያለውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በመጠቀም ኔት ሚትንግን አክትቬት በማድረግ መጠቀም
ውጤት
 ኢንተርኔት በማይኖርበት ጊዜ መልዕክትን መለዋወጥ አስችሏል ።
 በርቀት ላይ ያለ ኮምፒተርን ዴስክቶፕ በመጋራት ሶፍትዌሮች መውሰድ ተችሏል
 ፕሮግራሚንግ ለመስራት እርዳታ መስጠት ተችሏል ።
 በጥገና ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል ።
 ጊዜና ወጭን መቆጠብ ተችሏል።

2. IP Messenger
IP Messenger መልእክትን ከኮምፒዩተር ወደ ኮምፒዩተር ያለኢንተርኔት ግንኙነት መለዋወጫ መንገድ ነው፡፡ኢኮቴ ልማት
ኤጀንሲ ከክልል እስከ ወረዳ እንዲደርስ አድርጓል።

4
ስልት
ሶፍትዌሩን ከኢንተርኔት በማውረድ ስለአጠቃቀሙና ስለሚሰጠው አገልግሎት በቂ የሆነ መረጃ ከተገኘ በኋላ የተጠቃሚዎች
ማንዋል በማዘጋጀት ከክልል እስከ ወረዳ በማዳረስ
ውጤት
IP Messenger በመጠቀም ማንኛውንም መረጃ በተቀላጠፈና በቀላሉ መለዋወጥ ተችሏል፡፡

3.ዌብ
3.ዌብ ሜል መጠቀም
ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ውስጥ ያሉ ክፍሎች በዌብ ሜል መረጃወችን መለዋወጥ እንዲችሉ ተደርጓል።
ስልት
ዊንዶው 2003 ሰርቨር ላይ ኤክስቸንጅ ሰርቨር በመጫን
ውጤት
በመስሪያ ቤቱ መልዕክት በቀላሉ መለዋወጥ በመቻሉ ወጭና ጊዜን መቆጠብ ተችሏል።

4. የሥራ መለማመጃ ስልጠና (Induction Training) መስጠት


አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች የቅድመ ሥራ ስልጠና መስጠት የሚቀጠሩ ሠራተኞ ብዥታን በመቀነስ ለሥራው አዲስ
እንዳይሆኑ ይረዳል፡፡
ይህን በመገንዘብ ሰሜን ጎንደር ዞን እና አዊ ብ/ አስተዳደር ዞን አዲስ ለሚቀጠሩ ሠራተኞች የቅድመ ሥራ ስልጠና
ሰጥተዋል፡፡
ስልት
የሥልጠና ማንዋል በማዘጋጀት አዲስ ተቀጣሪ ሠራተኞችን በማሠልጠን
ውጤት
 በሠራተኛ ላይ የራስ መተማመንን ፈጥሯል።
 ለሰራተኞች የሥራ አቅጣጫ ሰጥቷል።
 በአሰራር ዙሪያ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀድሞ መከላከል ተችሏል።

5. ፋይሎች በቫይረስ እንዳይጠቁ ማድረግ


የፋይል ኤክስቴንሽን የሚያጠቃ ቫይረስ ፋይሎች ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ የሚያደርግ በመሆኑ አደገኛ ከሆኑት ቫይረሶች
አንዱ ነው፡፡ ይህን በመረዳት ሰ/ጎንደር ዞን ፋይሎች በቫይረስ እንዳጠቁ አድርጓል፡፡
ስልት
የፋይል ኤክስቴንሽናቸውን ስም መቀየር ለምሳሌ የፋይሉ ስያሜ አበበ ዶት ዶክ (Abebe.Doc) ቢሆን አበበ ዶት ኬ
(Abebe.k) በማለት በመቀየርና ፋይሉን ለመጠቀም በሚፈለግበት ጊዜ ወደ ቀድሞው ፋይል ኤክስቴንሽን ስያሜ በመመለስ
መጠቀም
ውጤት
 ፋይሎች በቫይረስ እንዳይጠቁ መከላከል ተችሏል።

5
 ወጪንና ጊዜን ማዳን ተችሏል፡፡

6. የኔትወርክ ዝርጋታ
6.1 ሰፊ የኔትወርክ ሽፋን
በክልሉ በሚገኙ አብዛኞቹ ዞኖችና ወረዳዎች የኔትወርክ ዝርጋታ የተስፋፋ ቢሆንም በተለይ ሰ/ወሎ ዞንና በስሩ በሚገኙ
ወረዳዎች በሰፊው የኔትወርክ ዝርጋታ ተከናውኗል።
ስልት
ለአመራሮች ግንዛቤ በመፍጠር በቂ በጀት እንዲመደብ በማድረግ
ውጤት
 ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል፡፡
 ሀብትን ተጋርቶ መጠቀም በመቻሉ ያለአግባብ የሚወጣ ወጭን መከላከል ተችሏል።

6.2 የኔትወርክ ዲዛይን በማዘጋጀት ኔትወርክ መዘርጋት


በምዕ/
በምዕ/ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ፤ሰሜን ጎንደር ዞን ላይ እና ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኔትወርክ ከመዘርጋታቸው በፊት የኔትወርክ
ዲዛይን ሠርተዋል፡፡

ስልት
 ለአመራሮች ግንዛቤ በመፍጠርና በጀት እንዲመደብ በማድረግ የኬብሎችን ደህንነት ባገናዘበ መልኩ በመሬት
በመቅበርና በአየር ላይ በመዘርጋት በሰፊው የኔትወርክ ዝረጋታ በማካሄድ
 ማይክሮ ሶፍት ቪዚዮን በመጠቀም የኮምፒውተሮችንና የስዊች አቀማመጥን በሚያሳይ መልኩ ዲዛይን በማድረግ
ውጤት
 የተሠራውና ያልተሰራው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይረዳል፡፡
 ችግር ሲያጋጥም በቀላሉ መፍታት ያስችላል፡፡
 ማስፋፋት ቢፈለግ በቀላሉ ማስፋፋት ያስችላል፡፡
 ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል፡፡

6.3 የኔትወርክ ዝርጋታን ያገናዘበ ህንፃ ስራ


የህንፃ ስራ ከመጠናቀቁ በፊት የኮምፒዩተር ኔትወርክን ያገናዘበ ቅድመ ዝርጋታ ቢደረግት ህንፃው ከተጠናቀቀ በኋላ
የሚደረገውን የህንፃ መቦርቦር ያስቀራል፡፡ በሰ/
በሰ/ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳና በክልሉ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት ይህ ሥራ ተከናውኗል፡፡
ስልት
የሕንፃው ፕላን ሲሰራ የኮምፒዩተር ኔትወርክ ፕላኑ ላይ እንዲካተት በማድረግ

6
ውጤት
 ለተለያዩ አደጋዎች ተጋለጭ ያልሆነ ኔትወርክ መዘርጋት ተችሏል።
 የሕንፃውን ውበት መጠበቅ ተችሏል።

7. ጀንዩን ዊንዶው አክቲቬሽን የሚጠይቁ መልዕክቶችን መከላከል


ኮምፒውተሮች ላይ ጀንዩን ዊንዶው ኢንስታሌሽን የሚጠይቅ መልዕክት ብዙ ጊዜ ይገጥመናል፡፡ መጫን ትፈልጋለህ ወይስ
አትፈልግም? ኮምፒዩተር በከፈትን ቁጥር የሚመጣ መልዕክት ስለሆነ ብዙ ጊዜ የኮምፒዩተር ተጠቃሚ አንዴ በድንገት እሽ
መጫን አፈልጋለሁ የሚለው መልዕክት መጫኑ አይቀርም፡፡ በሚጫንበት ጊዜ የኮምፒውተሩን ፍጥነት በመቀነስና አሠራሩን
በማዘግየት ያስቸግራል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር የሚፈታ ዘዴ ሰ/ጎንደር ዞን ላይ ተሰርቷል።

ስልት
የኮምፒዩተራችንን c:\drive ፓርትሽንን በመክፈት ዊንደውስ ሲስተም 32 ከዚያ ዶት ዲኤልኤል (wagalogu.DLL)
የሚለውን ኤክስቴንሽን በዶት ባክ (.back) በመቀየር
ውጤት
 ኮምፒዩተር እንዳይዘገይ ያደርጋል።
 ሥራ እንዳይስተጓጎል ረድቷል።

8. ኮምፒዩተር እንደ ፋክስ መጠቀም


አብዛኞቹ ዞኖችና ወረዳዎች ኮምፒዩተርን እንደፋክስ እየተጠቀሙ ያለ ቢሆንም በተለይ ዳባት፣ ደባርቅ፣ ላስታ ወረዳ፤ ደ/ወሎ
አልብኮ ወረዳ፤ ኦሮሞ ብ/አ/ዞን፤ ሰ/ሸዋ ዞን፤ አዊ ብ/አ/ዞን፣ ቡሬ ወረዳ የኮምፒተር ፋክሲንግ በተሻለ ሁኔታ ይጠቀማሉ፡፡
ስልት
ከክልል የተላከውን ማኑዋል መሰረት በማድረግ ማይክሮሶፍት ኦፕሬቲንግ ሲስተም አፕልኬሽን በመጠቀም አክትቬት
በማድረግ መጠቀም
ውጤት
 በኮምፒዩተር ፋክስ ማድረግ በመቻሉ ፋክስ ማሽን ለመግዛት የሚወጣውን ወጭ ማዳን ተችሏል።
 መልዕክትን በፍጥነት ማስተላለፍና መቀበል ተችሏል።

9. በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ የማይክሮ ሶፍት ኦፊስ ስልጠና በቪዲዮ ካሴት መስጠት
በዋግኽምራ ብ/አስተዳደር ዞንና በሰ/
በሰ/ሸዋ በረኽት ወረዳ በአማርኛና በአካባቢው ቋንቋ የማሠልጠኛ ቪዲዮ አዘጋጅተው
ማቅረብ ችለዋል፡፡
ስልት
 ኩይክ ስክሪንና ቪዲዮ ካፕቸር የሚባሉ ኦፕን ሶርስ ሶፍትዌሮችን ከኢንተርኔት በማውረድ
 በቪዲዮ ቀርፆ አባዝቶ በማቅረብ

7
ውጤት
 ጊዜ ለሌላቸው የኮምፒዩተር ሰልጣኞች ደጋግመው በማየት ክህሎታቸውን ለማዳበር ረድቷል፡፡
 ሰልጣኞች በማንኛውም ጊዜ ያለ አስተማሪ በቀላሉ እንዲረዱትና እንዲጠቀሙበት ማድረግ ተችሏል፡፡

10. የድረ ገፅ /Website/


Website/ ስራ

10.1 ስታቲክ ድረ ገፅ /Static Website/ ማጎልበት


ደቡብ ጎንደር ዞን ላይ፣ ላስታ፤ ቆቦና አልብኮ ወረዳዎች ስታቲክ ድረ ገፅ ተሰርቷል፡፡ እንዲሁም ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት
ቢሮና፣ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አጎልብተዋል።
ስልት
 ለድረ ገጽ ዝግጅት ልማት የሚያገለግሉ መረጃወችን በማሰባሰብ እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው ማሻሻል በሚያስችል
መልኩ እስታቲክ ድረ ገፅ በማልማት
 በኤች ቲ ኤም ኤል/HTML/
ኤል/HTML/ ዌብ ቱል በመጠቀም
ውጤት
 ተፈለጊ መረጃወችን በሀገር ውስጥም ሆነ በሀገር ውጭ ለተጠቃሚወች ማዳረስ ችሏል።
 ኢንቨስተሮችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ወደ ክልሉ ብሎም ወደ አገሪቱ እንዲመጡ ያደርጋል።
 ቱሪስቶች ወደ ክልሉ እንዲመጡ በመሳብ የገቢ ምንጭን ያዳብራል።

10.2 ዳይናሚክ ድረ ገጽ /Dynamic Website/ ማጎልበት


ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲና የርዕሰ መስተዳድርና የክልል መስተዳድር ም/ቤት ጽ/ቤት ዳይናሚክ ድረ ገጽ አጎልብተዋል።
ስልት
ለድረ ገጽ ዝግጅት ልማት የሚያገለግሉ መረጃወችን በማሰባሰብ እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው ማሻሻል በሚያስችል መልኩ
ዳይናሚክ ድረ ገጽ በማልማት
ውጤት
የሚፈለጉ መረጃወችን በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ለተጠቃሚዎች ማዳረስ ተችሏል፡

11. ስፖንሰር በማፈላለግ ኢኮቴን ማጠናከር


የኢኮቴ ዕቃዎችን በመንግስት በጀት ብቻ ማሟላት አስቸጋሪ በመሆኑ በተለያዩ መንገዶች ስፖንሰር በማፈላለግ ማሟላት
ያስፈልጋል፡፡ በደ/
በደ/ወሎ ዞን በተሁለደሬና አምባሰል ወረዳዎች እንዲሁም በሌሎች በርካታ ዞኖች ስፖንሰር በማፈላለግ የኢኮቴ
ዕቃዎቸን ማሟላት ተችሏል፡፡
ስልት
 ሂልባተስ ከተባለ አገር በቀል ድርጅት ጋር በመነጋገር የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት/
በማዘጋጀት/ በተሁለደሬና አምባሰል
ወረዳዎች/
ወረዳዎች/
 የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት የትራንስፖርት ወጪን በመሸፈን/
በመሸፈን/ሌሎች

8
ውጤት
 የኢኮቴ ዕቃዎችን ማሟላት ተችሏል።
 ህብረተሰቡ የኢኮቴ ተጠቃሚ እንዲሆን እረድቷል።

12.በኢኮቴ
12.በኢኮቴ ዙሪያ ለአመራሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ
በኢኮቴ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ በመሆኑም በደ/
በደ/ጎንደር ዞንና ደራ ወረዳ፤ በሰ/
በሰ/ወሎ
ዞን፤ በደ/
በደ/ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ እና በአልብኮ ወረዳ ስለኢኮቴ የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ተሰርቷል፡፡
ስልት
በየሩብ ዓመቱ የኢኮቴን ቀን በማክበር ለካቢኔዎችና ለሌሎች አመራር አካላት ግንዛቤ በመፍጠር
ውጤት
ለአመራሮች ግንዛቤ በመፍጠርና ለዘርፉ ትኩረት እንዲሰጠው በማድረግ በጀት ማስመደብ ተችሏል።

13. ኢኮቴን ማስፋፋትና ድጋፍ መስጠት


13.1 ለቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ድጋፍ መስጠት
የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንደጨረሱ የጥራት ማረጋገጫ ፈተና እንዲወስዱ ይጠበቃል። ፈተናውን ለማለፍ
በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር ትምህርት ማዳበር ይጠይቃል። ይህን በመገንዘብ ሰ/ወሎ ዞንና አዊ ብ/አ/ዞን
ለቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች የተግባር ስልጠና ሰጥተዋል። /ወደፊት በትብብር ስልጠና ስርዓት የሚጠናከር/
የሚጠናከር/

ስልት
ከቴክኒክና ሙያ መምህራን ጋር በመነጋገር ተማሪዎች ይበልጥ እገዛ የሚፈልጉበትን ርዕስ በመለየት የተግባር ሰልጠና
በመስጠት
ውጤት
 የመማር ማስተማሩን ሂደት በማሳለጥ ቲወሪን በተግባር መደገፍ ተችሏል።
 የብቃት ማረጋገጫ ፈተና /Center of Competence (COC)/ በቀላሉ እንዲያልፉ አስችሏል።

13.2 ኢኮቴን ማስፋፋት


ኢኮቴ የሚሰጠውን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማዳረስ ተገቢ ነው፡፡ በመሆኑም በዋግኽምራ ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ፣ሰሜን ወሎ
ዞንና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢኮቴን የማስፋፋት ሥራ ተሰርቷል።
ስልት
 ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ለቴክኒክና ሙያ ተማሪዎች የኢንተርኔት አገልግሎት በነፃ በመስጠት

9
 ሰሜን ወሎ በዞን ደረጃ የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ስለሌለ CDMA 3G በመጠቀም የኢንተርኔት
አገልግሎት በጋራ መጠቀም እንዲቻል በማድረግ እና ኖኪያ ሞባይሎችን ለኢንተርኔት አገልግሎት ለመጠቀም
ኮምፒዩተር ላይ ፒሲ ስዊት የሚባለውን ሶፍትዌር በመጫንና በማገናኘት
 የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፌዴራል በተገኘ የበጀት ድጋፍ CDMA በማስገዛት ለእያንዳንዱ ዳኛ በማደል
የኢንተርኔት ተጠቃሚ በማድረግ
ውጤት
 ቴክኒክና ሙያ ተማሪዎችን የኢኮቴ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።
 ከስራ ሰዓት ውጭ ለፍርድ ሂደቱ አጋዥ የሆኑ የተለያዩ መረጃወችን ከኢንተርኔት ማግኘት አስችሏል ።
 የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማስፋፋት ተችሏል።

14. ሰልጥኖ ማሰልጠን


በተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ ስልጠናወች ይሰጣሉ፤ ሆኖም የሰለጠኑትን መልሶ ማሰልጠን የተለመደ ተግባር አይደለም፡፡ ይህን
ልማድ በመስበር በደ/
በደ/ጎንደር ዞንና በሰ/
በሰ/ወሎ ዞን ሰልጥኖ የማሰልጠን ሥራ ተሰርቷል፡፡
ስልት
የዞንና የወረዳ ባለሙያዎችን ወደ አንድ ማዕከል በማሰባሰብ ስልጠና በወሰዱ ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት
ውጤት
 ስልጠናወችን በዞኑ ለሚገኙ ባለሙያወች ማዳረስ ተችሏል።
 ስልጠናው በሌላ አካል ቢሰጥ ሊወጣ የነበረውን ወጭ አድኗል።

15. የቅድመ መከላከልና የኮምፒዩተር አጠቃቀም ሥልጠና መስጠት


የኢኮቴ ዕቃዎችን ማሟላት ብቻውን ውጤታማ አያደርግም። ስለዚህ ዕቃዎች በንጽህናና በጥንቃቄ ተይዘው ለረዥም ጊዜ
አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ይህን በመረዳት በሰ/
በሰ/ወሎ ዞን ላስታ ወረዳና አዊ ብ/ዞን የቅድመ መከላከል ስልጠናና የኮምፒዩተር አጠቃቀም ሥልጠና
ተሰጥቷል::
ተሰጥቷል::
ስልት
የሚመለከታቸውን ሰልጣኞች በመመልመል፣ ማንዋል በማዘጋጀትና በማሰልጠን
ውጤት
የኢኮቴ ዕቃዎች ከመበላሸታቸው በፊት የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት አላስፈላጊ ጊዜና ወጪ ማስቀረት ተችሎአል

16. የኢኮቴ ዕቃዎችን በንፅህና መጠበቅ

10
የኢኮቴ ዕቃወች በንጽህና ካልተያዙ በቀላሉ ሊበላሹ ይችላሉ ይህን በመገንዘብ አዊ ብሄረሰብ ባንጃ ሽኩዳድ ወረዳ፤ ደ/ወሎ
አልብኮ ወረዳና በሰ/
በሰ/ወሎ ቆቦ ወረዳ የኢኮቴ ዕቃዎችን ንፅህና ጠብቀው በመያዛቸው የአገልግሎት ጊዜያቸውን ማራዘም
ችለዋል፡፡
ስልት
 አቧራን ለመከላከል ለያንዳንዱ ዕቃ መሸፈኛ በማዘጋጀት
 የኢኮቴ ዕቃዎችን በንጽህና በመያዝ

ውጤት
የኢኮቴ ዕቃዎችን የአገልግሎት ጊዜን ማራዘም በመቻሉ ጊዜና ወጭን መቆጠብ ተችሏል።

17. መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠናመስጠት


መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ለመንግስት ሰራተኞች መስጠት የተለመደ ተግባር ሲሆን በሰ/ በሰ/ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፤
ዋግኽምራ ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ፤ በደ/
በደ/ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ፤ በደሴ ከተማ አስተዳደር፤ በምስ/
በምስ/ጎጃም እነማይ ወረዳና
በኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ በተለየ መልኩ መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልት
 ለቀበሌ ሥራ አስኪያጆችና የ10ኛ
10ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠና በመስጠት
 የሰለጠኑ ሰልጣኞች ማህበረሰቡን እንዲያሰለጥኑ በማድረግ
 ለመሰናዶ ተማሪወች መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና በመስጠት
 ለመምህራን፣ ስራ አስኪያጅና ለቀበሌ ሽቦ አልባ ስልክ ኦፕሬተሮች ቀበሌው ድረስ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን
በመውሰድና ሰልጠናውን በት/
በት/ቤት በመስጠት
 ኤች አይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸው 10 ሰወችን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ሆኖ በመመልመል
መሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና በመስጠት
 ስልጠናው ለስራቸው ምን ያህል አጋዥ እንደሆነ በማጥናት
 የመሰረታዊ ኮምፒዩተር ስልጠና ለ3319 የ 9 ኛና የ10 ክፍል ተማሪወችን ለ 10 ተከታታይ ቀናት ስልጠና
በመስጠት
 ከ TVET ጋር የጋራ እቅድ በመያዝ የትብብር ስልጠና በመስጠት
 መምህራንን በክረምት ወራት ለስራቸው አጋዥ የሆነ ስልጠና እንዲያገኙ ዞኖችንና ወረዳዎችን በማስተባበር
 የስልጠና ማኑዋል አዘጋጅቶ ለዞኖችና ለወረዳዎች በሶፍት ኮፒ በማሰራጨት
ውጤት
 የቴክኒክና ሙያ ተማሪወችን የተግባር ተኮር ስልጠና መስጠት ተችሏል።
 ኢኮቴን ወደ ማህበረሰቡ ማዳረስ ተችሏል።
 መምህራን ከቴክኖሎጂው ጋር እንዲተዋወቁ በመደረጉ ስራቸውን በተደራጀና በተቀላጠፈ መልኩ እንዲሰሩ
እረድቷቸዋል።

11
18. የሶፍትዌር ክምችት
የሶፍትዌር ክምችት መኖሩ ስራን በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን ያስችላል። በመሆኑም በሰ/
በሰ/ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ፤ ሰ/ጎንደር
ዞን፣ ዋግምራ ብ/አ/ዞን፤ ደ/ወሎ ዞን፤ ሰ/ሸዋ ዞን፤ ምስ/
ምስ/ጎጃም ዞን፤ ምዕ/
ምዕ/ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ፤ አዊ ብ/አ/ዞንና ኢኮቴ ልማት
ኤጀንሲ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በማከማቸት ጥቅም ላይ አውለዋል።
ስልት
 የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በመግዛት፣ከኢንተርኔት በማውረድና ከስራ ባልደረባ በመዋስ
 በክልሉ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ የታመነባቸውን ከ50 በላይ የሚሆኑ ሶፍትዌሮች
በሁለት መልክ ማለትም በጣም ትላልቅ ዳታ መጠን ያላቸውን በድረ ገጽ አድራሻቸውን በመያዝ፣ ሜታ ዳታ
በማዘጋጅትና መጠነኛ ዳታ መጠን ያላቸውን ሙሉውን ሶፍትዌር በማውረድ
ውጤት
 ለሀርድዌርና ሶፍትዌር ጥገና፤ለተለያዩ አፕሊኬሽኖች የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮችን በማሰባሰብ አስፈላጊ በሆኑበት
ሰዓት መጠቀም አስችሎአል።
 በክልሉ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ የታመነባቸውን ሶፍትዌሮች በማሰባሰብና
አደራጅቶ በማስቀመጥ አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ ተችሏል

19.ዶክመንታሪ
19.ዶክመንታሪ ፊልም ማዘጋጀት
ጠቃሚ መረጃወችን በዶክመንታሪ ፊልም አዘጋጅቶ ማስቀመጥና መረጃው አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ መጠቀም ተገቢ ነው።
ይህን በማሰብ በሰ/
በሰ/ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ እና በሰ/
በሰ/ሸዋ ዞን በረኸት ወረዳ ዶክመንታሪ ፊልም አዘጋጅተዋል።
ስልት
ቪዲዮ ካፕቸር ካርድ፣ ሶፍትዌርና ቪዲዮ ካሜራ በመጠቀም ዶክመንታሪ ፊልም ማዘጋጀት
ውጤት
በድምጽና በምስል የተቀናበሩ የፓናል ውይይቶችን፣ የችሎት ፍርዶችንና ሌሎች መረጃወችን በመያዝ አስፈላጊ በሚሆኑበት
ጊዜ መጠቀም ተችሏል

20. ዳታቤዝ ማልማት


የሰው ኃይል መረጃን በዳታቤዝ መያዝ የሚፈለግ መረጃን በተቀላጠፈ፤ በቀላሉና በተደራጀ ሁኔታ ማስቀመጥና ማግኘት
ያስችላል። በመሆኑም ሰቆጣ ወረዳ፣ ሰ/ወሎ ዞን፤ ላስታ ወረዳ፤ ቆቦ ወረዳ፣ ደ/ወሎ ዞን፣ በላስታ ወረዳ ብልባላ ቀበሌ፣
ተሁለድሬ፣ አልብኮ ወረዳ፣ በአልብኮ ወረዳ ጀማ ንጉስ ቀበሌ፣ ምስ/
ምስ/ጎጃም ዞን፣ እነማይ ወረዳ እና ምዕ/
ምዕ/ጎጃም ዞን ዳታቤዝ
አልምተው ስራ ላይ አውለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በኢትዮጵያን ካልቸራል ኸሪቴጅ የቅርሳቅርስ
መመዝገቢያ ዳታቤዝ ተለምቶ በክልል በሚገኙ ዞንና ወረዳወች ዳታቤዙን በመጫን ቅርሳቅርሶችን መመዝገብ ተችሏል።

12
ስልት
 የሰው ኃይል መረጃ ለመያዝ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከተጠቃሚዎች በማሰባሰብ በማይክሮሶፍት አክሰስ ዳታቤዝ
በማልማትና ስለአጠቃቀሙ ለተጠቃሚዎች ስልጠና በመስጠት
 በኢትዮጵያ ካልቸራል ኸሪቴጅ የቅርሳቅርስ መመዝገቢያ ዳታቤዝ ተለምቶ በክልል በሚገኙ ዞንና ወረዳወች
ዳታቤዙን በመጫን
ውጤት
 የሚፈለግ መረጃን በተቀላጠፈ፣ በቀላሉና በተደራጀ ሁኔታ ማስቀመጥና ማግኘት ተችሎአል፡፡
 የመረጃ ማጭበርበር እንዳይኖር አግዟል፡፡
 ቀጣይነት ያለው አሰራር እንዲኖር አስችሏል፡፡
 ቅርሳቅርሶችን በተገቢው ጊዜ ማሳየት፣ ከምዝበራና ስርቆት ማዳን ተችሏል።

21. ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍትን መጠቀም


መጽሐፍትን /Hard copy/ ማግኘት አመቺ በማይሆንበት ጊዜ ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍትን መጠቀም አስፈላጊ ነው። ግዳን
ወረዳና ሰ/ጎንደር ዞን ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍትን ከመጠቀም አንፃር እንደ አብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ስልት
ኤሌክትሮኒክ መጽሐፍትን ከኢንተርኔት በማውረድ
ውጤት
 የሚፈለጉ የኤሌክትሮኒክ መረጃን በቀላሉ ማግኘት ተችሏል፡፡
 ጊዜና ወጭን በተገቢው ሁኔታ መቆጠብ አሰችሏል።

22. ኢንካርታ መጠቀም


ኢንካርታ በርካታ ነገሮችን አካቶ የያዘ የማይክሮሶፍት ውጤት የሆነ ኢንሳይክሎፒዲያ በመሆኑ ኮምፒዩተር ላይ ጭኖ
እንደአስፈላጊነቱ መጠቀም ይቻላል። ይህን በመገንዘብ ላስታ ወረዳ፣ ደ/ወሎ ዞንና ሰ/ሸዋ ዞን ኢንካርታን ኮምፒዩተር ላይ
በመጫን ለተጠቃሚዎች አገልግሎት ሰጥተዋል።
ስልት
ኢንካርታ ሶፍትዌርን ኮምፒዩተር ላይ በመጫን
ውጤት
የመንግስት ሰራተኞች፣መምህራንና ተማሪዎችን የዕውቀት አድማሳቸውን ያለምንም ወጭ ለማስፋት እረድቷቸዋል።

23. ወረዳ ኔትን ለተለያዩ አገልግሎቶች ማዋል


ኮንፈረንስና ችሎት የወረዳኔት ቪዲዮ ኮንፈረንስን ተጠቅሞ ከሚሰጡ አገልግሎቶች በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው። ሆኖም
የቪዲዮ ኮንፈረንስ ለተለያዩ አገልግሎቶች ማዋል ይቻላል። በመሆኑም ላስታ፣ እነማይና ደሀና ወረዳዎች የቪድዮ ኮንፈረንስ

13
በመጠቀም ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥና የቀለም ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር የተደረገ ሲሆን
ቆቦና አልብኮ ወረዳዎች የጥገናና የተለያዩ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
ስልት
የቪድዮ ኮንፈረንስ በመጠቀም ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር የጥገናና የተለያዩ የልምድ ልውውጦች በማድረግ፣
ከትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን ጋር በመወያየት የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት የቀለም ትምህርት ጥያቄና መልስ ውድድር
በማድረግ፣
ውጤት
 ጊዜንና ወጭን በመቆጠብ ችግርን በቀላሉ መፍታት ተችሏል፡፡
 የተማሪዎችን ክህሎትና እውቀት ማዳበር ተችሏል፡፡

24. የኢኮቴ ፎካል ፐርሰን መመደብ


በኢኮቴ ዙሪያ የሚከናወኑ ሰራዎችን በባለሙያዎች ብቻ ማከናወን አስቸጋሪ ነው። ወደፊት ባደረጃጀት የሚመለስ ቢሆንም
ይህን ችግር ለመፍታት ሰ/ወሎ ዞን፣ ቆቦ ወረዳና አልብኮ ወረዳ ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች አንድ አንድ ፎካል ፐርሰን
በማስመረጥ አጋዥ ኃይል ማደራጀት ችለዋል።
ስልት
በየሴከተር መስሪያ ቤቶች የኢኮቴ ባለሙያ እስኪሟላ ድረስ ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች አንድ አንድ ፎካል ፐርሰን በማሰመረጥ
ስልጠና በመስጠትና የስራ ድርሻቸውን በማሳወቅ
ውጤት
ለኢኮቴ ትኩረት እንዲሰጠው በማድረግ ቴክኖሎጂውን በማስፋፋት ችግር መፍታትና መረጃ ከየሴክተር መስሪያ ቤቶች
በቀላሉ ማግኘት ተችሏል፡፡

25. ቴክኖሎጂውን ወደ ቀበሌ ማዳረስ


ቴክኖሎጅውን በማሰፋፋት ህብረተሰቡን ማሳወቅና ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል። ለዚህም ነው ምስ/
ምስ/ጎጃም ዞን፣ ሰ/ወሎ
ዞንና ሌሎችም ቴክኖሎጅውን ቀበሌ ድረስ ያወረዱት።
ስልት
ኮምፒዩተሮችን ቀበሌ ድረስ በማወረድ ከቀበሌ አስተዳደራዊ ስራዎች በተጨማሪ ኢንተርኔትን ቀበሌ ድረስ ተደራሽ
በማድረግ
ውጤት
 የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ማስፋፋት ተችሏል።
 ህብረተሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት ችሏል።

14
26. የኢኮቴ ክበብ ማቋቋም
የኢኮቴ ክበብ በየተቋማት መቋቋሙ ያለውን ጠቀሜታ በመረዳት ሰ/ወሎ ዞን ላይና ቆቦ ወረዳ በቴክኒክና ሙያ እና 2ኛ ደረጃ
ት/ቤቶች፣ እነማይ ወረዳ በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና በአልብኮ ወረዳ በደጅ አዝማች መንገሻ አቡዬ 2ኛ ደረጀና መሰናዶ
ት/ቤት የኢኮቴ ክበብ ተቋቁሟል።

ስልት
 ከት/
ከት/ቤቱ ር/መምህርና ከኢኮቴ መምህራን ጋር በመነጋገር በቴክኒክና ሙያ ፣ በሁለተኛ ደረጃና በአንደኛ ደረጃ
ት/ቤቶች የኢኮቴ ክበብ በማቋቋም ለአባላት የመሠረታዊ ኮምፒዩተር ስልጠና በመስጠት፣
 የመማሪያ መጽሐፍትን መሰረት በማድረግ ያገኙትን ንድፈ ሀሳብ የተግባር ልምምድ እንዲዳብር በማድረግ፣
ውጤት
 የመሠረታዊ ኮምፒዩተር ስልጠና ማግኘታቸው የክበብ አባላትን የቴክኖሎጅው ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።
 በክፍል የሚማሩትን ንድፈ ሀሳብ መሰረት በማድረግ የተግባር ልምምድ ማድረግ አስችሏቸዋል።
 ኢንተርኔት ስለሚቆራረጥ ኢንሳይክሎፒዲያ/
ኢንሳይክሎፒዲያ/ኢንካርታ በመጠቀም መረጃ እንዲያገኙ ተደርጓል፣
 ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለሚገቡ ተማሪወች የቴክኖሎጂው ፍቅር እንዲያድርባቸው እረድቷል፡፡

27. የኤሌክተሮኒክ ዕቃዎች ጥገና


የተለያዩ የኤሌክተሮኒክ ዕቃዎች ማለትም ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ፣ ዩፒየስ፣ እስካነር፣ ፕላዝማ፣ ሞኒተር፣ አዳፕተርና ፋከስ መጠገን
መቻሉ ጊዜንና ወጭን ይቆጥባል። በዚህ ረገድ ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ፣ ዩፒየስ፣ እስካነር፣
ፕላዝማ፣ ሞኒተር፣ አዳፕተርና ፋከስ ቆቦ ወረዳ ደግሞ ፕሪንተር፣ ፎቶኮፒ፣ ዩፒየስና እስካነር በመጠገን የተሻለ እንቅስቃሴ
አድርገዋል።
ስልት
 አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን በመጠገን፣
 የዲቪዲ ፓወር ሳፕላይ ለአዳፕተሮች በመቀያየር መጠገን፣
ውጤት
 የመንግስትን ወጪና ጊዜ መቆጠብ አስችሏል።
 የኤሌትሮኒክ ዕቃዎች ለረዥም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡ አስችሏል።

28. ሽቦ አልባ ስልክ ጥገና


የሽቦ አልባ ስልኮች ለህብረተሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት ከፍተኛ ነው። እነዚህ ስልኮች ሲበላሹ መጠገን መቻሉ ደግሞ
እየተሰጠ ያለውን አገለግሎት ቀጣይ ከማድረግ አኳያ ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነወ። ድላንታ፣ ደንቢያ፣ ጭልጋ፣ ጎንደር
ዙሪያ፣ ቡሬ እና ባንጃ ወረዳዎች ሽቦ አልባ ስልኮችን በመጠገን አበረታች ስራ ሰርተዋል።

15
ስልት
ከኢትዮቴሌኮም ባለሙያዎች ልምድ በመቅሰም
ውጤት
 የመንግስትን ወጪና ጊዜ መቆጠብ አስችሏል፡፡
 ህብረተሰቡ ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ማግኘት ችሏል።

29.የቢሮ
29.የቢሮ አደረጃጀትን የተሟላ ማድረግ
ውጤታማና ቀልጣፋ ስራ ለመስራት ከሚያሰፈልጉት ነገሮች ውስጥ አንዱ ምቹ የቢሮ አደረጃጀት መኖር ነው።
ይህን በመገንዘብ አልብኮ ወረዳ ራሱን የቻለ የኢኮቴ አዳራሽ፣ የማሰልጠኛ ማዕከልና ኢንተርኔት ካፌ፣ ንብረት ክፍልና
የኔትወርክ ክፍል ተከፋፍሎ እንዲሰራ አድርጓል።
ስልት
ስለ ኢኮቴ ጠቀሜታ ለአመራሮች ግንዛቤ በመፍጠር ለህንፃ ማሰሪያ በጀት እንዲመደብ በማድረግ
ውጤት
 ስልጠና በአግባቡ ለመስጠት አስችሏል።
 መሳሪያዎች በንፅህናና በአግባቡ እንዲያዙ አስችሏል።
 ሁሉንም ሴክተር መ/ቤቶች ያማከለ መሆኑ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል።
 አዳራሹ የራሱ የኢኮቴ በመሆኑ የቪ/
የቪ/ኮንፈረንስ አገልግሎት በተፈለገው ጊዜ መስጠት አስችሏል።

30.የፀሐይ
30.የፀሐይ ኃይል/Solar
ኃይል/Solar Energy/ መጠቀም
የኤሌክትሪክ ኃይል በሌለበት ሁኔታ አማራጭ የኤሌከትሪክ ኃይል መጠቀም ስራዎች ቀጣይነት አንዲኖራቸው ያደረጋል።
በአልብኮ ወረዳና በሌሎች ወረዳዎች ይህ ተግባራዊ ሆኗል።
ስልት
ከኢትዮቴሌኮም ጋር በመነጋገር የፀሐይ ኃይል /Solar Energy/ ፓናል በመዘርጋትና የባትሪ አሲድ በመሙላት አማራጭ
የኤሌከትሪክ ኃይል መጠቀም ተችሏል።
ውጤት
አማራጭ የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ሰራ እንዳይቆም አስችሏል።

31. የስልጠና ማዕከል ማደራጀት


መሰረታዊ ኮምፒዩተር ስልጠናና ሌሎች አጫጭር ሰልጠናዎችን ለመስጠት ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ አንዱ ምቹ
የስልጠና ማዕከል መኖር ነው። ይህን በመገንዘብ አዊ/
አዊ/ብ/አስተዳደር ዞን፤ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም
በሰሜን ጎንደር ዞን ፎገራ፣ ደራና ሊቦከምከም ወራዳዎችና ሌሎች ዞኖችም የስልጠና ማዕከላትን አደራጅተው መሰረታዊ
የኮምፒዩተር ስልጠና ሰጥተዋል፣ በመስጠት ላይም ይገኛሉ።
ስልት

16
 በተለያየ ሁኔታ ዞኖች ካገኟቸው ኮምፒዩተሮች ውስጥ በየወረዳው ኮምፒዩተሮች ለስልጠና አገልግሎት እንዲውሉ
በማድረግ፣
 የተበላሹ ኮምፒዩተሮችን በመጠገን አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ፣
 የማሰልጠኛ ማኑዋል በማዘጋጀት፣
 የመብራት አገልግሎት ለሌላቸው ቀበሌዎች ሊሰጡ የነበሩትን ኮምፒዩተሮች በማሰባሰብና ተገቢ/
ተገቢ/ምቹ ክፍል
በመፈለግ ፣
ውጤት
ስልጠና በስፋት መስጠት በመቻሉ የኮምፒዩተር ዕውቀት ያላቸው የመንግስት ሰራተኞች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ
ኮምፒዩተርን ተጠቅሞ ስራን በተደራጀ መልኩ መስራት አስችሏል።

32. የቤተ መጽሐፍት ዳታቤዝ


ቤተ መጽሐፍትን አደራጅቶ በመያዝ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልገሎት ለተጠቃሚዎች መስጠት ያስችላል። በመሆኑም ኢኮቴ
ልማት ኤጀንሲ እንደ አንድ የመረጃ ምንጭ የሚያገለግለው ቤተ መፃህፍት ክላሲፊኬሽን፣ ካታሎግ ካርድና ሌሎች
የማደራጀት ስራዎችን በቴክኖሎጂው የታገዘ ከማድረግ አንፃር አንድ ዳታቤዝ ተሰርቶ ስራ ላይ ውሏል፡፡እንዲሁም ገንዘብና
ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመ/
የመ/ቤቱን ቤተመጽሐፍት በ ቪዥዋል ቤዚክ በማደራጀት አጠቃቀሙን ቀላልና ቀልጣፋ ማድረግ
ችሏል።
ስልት
 መረጃወችን በማሰባሰብ በማይክሮሶፍት አክሰስ የቤተ መፅሐፍቱን ዳታቤዝ በማዘጋጀት በኤጀንሲው የሚገኘውን
ቤተመፃሕፍት ማደራጀትና በዞኖችና ወረዳወች በማሰራጨት
 በትግበራው ሂደትም የቤተ መፃህፍቱ ሰራተኛ ስለ ዳታ ቤዙ አጠቃቀም በቂ ገለፃ በማድረግና በየጊዜው ለሚቀርቡ
ጥያቄዎች ሙያዊ ምላሽ በመስጠት፣
 በ ቪዥዋል ቤዚክ በቢሮው የሚገኘውን ቤተመፅሀፍት አውቶሜት በማድረግ /ገ/ኢ/ል/፣
ውጤት
ለተጠቃሚወች ቀልጣፋ የቤተ መጽሐፍት አገልግሎት መስጠት ተችሏል።

33.ውጤት
33.ውጤት ተኮር ስርዓት /Balanced Score Card (BSC) Automation/
ከአዲስ አበባ አስተዳደር በተደረገው የልምድ ልውውጥ የፌደራል ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኤጀንሲ
የውጤት ተኮር ስርዓት በኤክሴል ሰርተው በክፍለ ከተማዎች ውስጥ ያደረጉትን የሙከራ ትግበራ ተሞክሮ በማምጣት
የኤጀንሲውን BSC አውቶሜሽን በመስራት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ስልት
የኤጀንሲውን ሂደቶች ግብና መለኪያወች ከBSC ዶክመንት በማውጣት በማይክሮሶፍት ኤክስ ኤል የኤጀንሲውን BSC
አውቶሜት በማድረግ
ውጤት

17
እቅድ በተሳካ መልኩ መዳሰስ መቻሉና የሰራተኛውንም ውጤት መለካት የሚያስችል መሆኑ

34. NVDA & JAWS


ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ አካል ጉዳተኞችን የሚያግዙ ሶፍትዌሮችን በማልማት ማየት ለተሳናቸው በኮምፒዩተር አጠቃቀም ዙሪያ
በድምፅ ሊያግዙ የሚችሉ ሁለት አፕሊኬሽኖች /NVDA and JAWS / በመምረጥ ሶፍትዌሮቹ አገልግሎት እንዲሰጡ
አድርጓል፡፡

ስልት
ማየት ለተሳናቸው NVDA & JAWS ከኢንተርኔት በማውረድና የአጠቃቀም ማንዋል በማዘጋጀት ከክልል እስከ ወረዳ
በማዳረስ፣
ውጤት
ማየት የተሳናቸው የኮምፒዩተር ተጠቃሚ መሆናቸው ለስራቸው አጋዥ የሆኑ መረጃዎቸን እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

35. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ የሚሰጥ ሶፍትዌር ማልማት


በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ የሚሰጥ ሶፍትዌር በማልማት መረጃወችን
ለተጠቃሚወች የማዳረስ ስራ ተሰርቷል።
ስልት
የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ የሚሰጥ ሶፍትዌር በማልማትና www.amharabofed.gov.et በሚል አድራሻ
መረጃወችን ለተጠቃሚወች በማዳረስ
ውጤት
የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃ ማስተላለፍ ተችሏል።

36. የቱሪስት መስህቦች ክምችት /Image Gallery/


ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተለያዩ ምስሎችን በማሰባሰብ የክልሉን ቅርሳቅርስና ሌሎች ምስሎችን ለሚፈልጉ ተጠቃሚወች መረጃ
መስጠትና ማስተዋወቅ ችሏል።
ስልት
የተለያዩ ምስሎችን በማሰባሰብ የምስሎች ክምችት በማዘጋጀት
ውጤት
በሚፈለጉበት ጊዜ ምስሎችን ለሚጠይቀው አካል መስጠትና ማስተዋወቅ በመቻሉ ጎብኝዎች ወደ ክልሉ እንዲመጡ
አድርጓል።

37. CCMS/Court Case Management System/ ሶፍትዌር መጠቀም


ጠቅላይ ፍ/ቤቱ CCMS የተባለ ሶፍትዌር በማስለማት የፍርድ ሂደቱን በተሳለጠ ሁኔታ እንዲያካሂድ ረድቶታል፡፡
ስልት

18
CCMS የተባለ ሶፍትዌር ቢሶፍት በተባለ አገር በቀል ድርጅት በማስለማት፣
ውጤት
የፋይል መጥፋትና የፍርድ ሂደት መጓተትን ቀንሷል።

38.የመድሀኒት
38.የመድሀኒት ማጣቀሻ /Drug Reference/ ሶፍትዌር

በሐብሩ ወረዳ የመድሀኒቶችን ዝርዝር የያዘ /Drug reference/ ሶፍትዌር ማዘጋጀት ተችሏል።
ስልት
መረጃወችን ከኦፕን ሶርስ በማሰባሰብ
ውጤት
 ስለመድሀኒቶች አይነትና በህሪ ለማወቅ የሚስችል ዋቢ ፅሁፎችን ማግኘት አስችሏል።
 የመድሀኒቶችን ባህሪ ለማወቅና ለማዘዝ አስችሏል።

39. የወባ ትንኝ መከላከያ ሶፍትዌር


በሐብሩ ወረዳ በወባ ትንኝ መነደፍን መከላከል የሚያስችል ሶፍትዌር ለምቷል።
ስልት
ሴቷ የወባ ትንኝ የማትፈልገውን ድምፅ ስትሰማ ከአካባቢው የምትሰወር ሲሆን ይህን ድምጽ የሚፈጥር ሶፍትዌር
ከኢንተርኔት በማውረድና ሞባይል ላይ በመጫን
ውጤት
ከወባ በሽታ መከላከል ያስችላል።

40. ማስመሰያ /Simulation/ ሶፍትዌር መጠቀም


በሀብሩ ወረዳ ለሳይንስ ቤተ ሙከራ የሚያግዙ ማስመሰያ /Simulation/ ሶፍትዌሮችን መጠቀም ተችሏል፡፡
ስልት
ሶፍትዌሮችን ከኢንተርኔት በማውረድ
ውጤት
 ለቤተ ሙከራ እቃ ግዥ የሚወጣ ወጪን ቀንሷል።
 ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቀት በመተግባር እንዲያዩት ያስችላል።

41.ቀበሌ
41.ቀበሌ አውቶሜሽን ሲስተም
ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 9 ቀበሌዎች የአውቶሜሽን ስራ ተከናውኗል።
ስልት
በ ቪዧል በዚክሽና በአክሰስ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር በመጠቀም መታወቂያ ማተም የሚችል ሶፍትዌር በማስለማት፣
ውጤት
 ስራን ለማቀላጠፍ በመርዳቱ መልካም አስተዳደርን አስፍኗል

19
 የህብረተሰቡን እርካታ አስገኝቷል
 ማጭበርበርን ቀንሷል።

42. መሬት አስተዳደር ሶፍትዌር


በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የመሬት አስተዳደር ሶፍትዌር በማስለማት በ 9 ቀበሌዎች ተስፋፍተው ጥቅም
ላይ እንዲውል ተደርጓል።
ስልት
የመሬት አስተዳደር ሶፍትዌር በማስለማት
ውጤት
 የመሬት አስተዳደር ሶፍትዌር በመጠቀም ከመሬት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃወች በማደራጀት ደንበኞችን
በተቀላጠፈ መልኩ ማስተናገድ ተችሏል።
 መሬት ነክ ግጭቶችን መቀነስ ያስችላል።
 መሬትን በአግባቡ መጠቀም ያስችላል።
 የመሬት ማጭበርበርን መቀነስ ያስችላል።

7.1.2. ከማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች

1. ኢኮቴ ን ማስፋፋት
የማሕበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት ማሕበረሰቡን የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ከማድረግ አንፃር እነማይ ወረዳ በተሻለ ሁኔታ
አከናውነዋል፡፡
ስልት
ማህበረሰቡ ከፀረወባ ማህበር ጋር ፍሎጎቱን በመግለፅ

ውጤት
ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ተችሏል።

2. የተጠናከረ አመራር
በላይ ጋይንት ወረዳ የቦርድ አመራሩ በተጠናከረ መልክ ማዕከሉን መምራት ችሏል።
ስልት
የጋራ ግንዛቤና አቋም መያዝ
ውጤት
 የማዕከሉ ገቢ ማደግ
 አገልግሎቶች የተጠናከረ መሆን

20
3. መረጃ መስጠት
የበህር ዳር ከተማ ወጣቶች ማዕከል አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመፃፍ እስከሚታተም ድረሰ ለተማሪዎች በሶፍት ኮፒ
እንዲደርሳቸው አድርገዋል
ስልት
ስርዓተ ትምህርቱን ኮምፑተር ላይ በመጫን
ውጤት
ተማሪዎች ሊገጥማቸው የሚችለውን የመፅሀፍ እጥረትን መቀነስ ችለዋል።

7.1.3 ከማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች

1. መረጃን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ


የማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት መረጃን ለማህበረሰቡ ተደራሽ በማድረግ በርካታ ስራወችን ሰርተዋል፡፡
ስልት
የዋግ ኽምራ ማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከል
 የአካባቢውን ባህላዊ እሴቶችና የተፈጥሮ ሀብቶችን የያዘ የአካባቢውን ገፅታ የሚያሳይ መለስተኛ ሙዚየም
በማዘጋጀት
 ለበጎ ፍቃደኞች የጋዜጠኝነት ስልጠና በመስጠት የጋዜጠኝነት ስራ እንዲሰሩ በማደረግ፣

ኮምቦልቻ ከተማ ማህበረሰብ ሬዲዮ


ለማህበረሰብ ሬዲዮ ሳወንድ ፕሩፍ 50 ሳንቲ ሜትር ክፍተት ባለው ግርግዳ ጭድና ሶጋቶራ በመሙላት ድምፅ የማያስተላልፍ
ስቲዲዮ በመስራት፣
በጎፍቃደኞችን በማሳተፍ የጋዜጠኝነት ስልጠና በመስጠትና ስራውን እንዲጋሩ በማድረግ፣
ውጤት
 ወቅታዊ መረጃን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
 በጎ ፈቃደኝነትን ማበረታታት ተችሏል፡፡

7.1. 4 ከባህር ዳር ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


በ2003 ዓ.ም ከኢንኩቤሽን ማዕከሉ የተወሰደ ምርጥ ተሞክሮ የለም፡፡

21
7.2 ከ 2004 ዓ.ም እስከ 30/04/2005 ዓ.ም የተሰሩ አዲስ ምርጥ ተሞክሮዎች

7.2.1 ከክልል እስከ ወረዳ በኢኮቴ ዙሪያ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


43. FTP Server
File Transfer Protocol/FTP/ በመጠቀም የተለያዩ ፋይሎችን በቀላሉ ማግኘት እንዲሚቻል በመገንዘብ ኢኮቴ ልማት
ኤጀንሲ FTPን መጠቀም የመያስችል ዘዴ ቀይሷል።
ስልት
ሰርቨር ላይ ኮንፊገር በማድገርግና አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ ሶፍትዌሮችና ዶክሜንቶች አደራጅቶ ኮምፒዩተር ላይ በማስቀመጥ
ሌሎች የኮምፒየተራቸውን ብራውዘር በመጠቀም ፋይሎችን መጠቀም እንዲችሉ በማድረግ
ውጤት
 ሶፍትዌሮችንና የተለያዩ ፋይሎችን በፍጥነት ለማግኘት አስችሏል።
 ሲዲና ፍላሽ ዲስክ ሳያስፈልግ ኔትወርኩ ባለበት ቦታ ሁሉ ትላልቅ መጠን ያላቸውን ፋይሎችን ማግኘትና ማዘዋወር
አስችሏል።

44. ሶፍትዌር ተናባቢነት ሰነድ

22
የኮምፒየተር ተጠቃሚዎች ከሚያጋጥማቸው ችግሮች ውስጥ አንዱ የሶፍትዌሮች እርስ በርስ መናበብ አለመቻል ነው።ኢኮቴ
ልማት ኤጀንሲ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን ሰነድ ካስተማይዝ በማድረግ ይህን ችግር
የሚፈታ ሰነድ አዘጋጅቷል።
ስልት
በተደጋጋሚ ጊዜ ከተከሰቱ የተናባቢነት ችግሮች (ማክሮሶፍት ኦፊስ፣ግዕዝ እና የተለያዩ ኦፐሬቲንግ ሲስተምስ አጠቃቀም )
በመነሳት መፍትሄ በመፈለግ
ውጤት
ዕለት ከዕለት የሚያጋጥሙ የተናባቢነት ችግሮች ተፈትተው ስራን በቅልጥፍና መስራት አስችሏል።

45. ኢኮቴን
ኢኮቴን ማስፋፋት
የኢኮቴን ተደራሽነት ለማስፋት በየዓመቱ የአፍሪካ ሳምንት በክልላችን ይከበራል።በዚህ ዓመትም ሰሜን ሸዋ ዞን በረኸት
ወረዳ እና ኢኮቴ ልማት ኤጄንሲ የአፍሪካ ሳምንትን በተሻለ ሁኔታ አክብረዋል።
ስልት
 ከወረዳ አመራሩ ጋር በመመካከር ሳምንቱ በወረዳና በተመረጠ ቀበሌ በስዕላዊ መግለጫና በጥያቄና መልስ ውድድር
በማክበር ለተሳተፉ ተወዳዳሪዎች ሽልማት በመስጠት፣/ በረኸት ወረዳ/
 የአፍሪካ ኢኮቴ ሳምንት አከባበር ላይ ዝግጅት የሚያደርግ ኮሚቴ በማቋቋም በዓሉ በፓናል ውይይት፣በአማራ ሬደዮ
ጣቢያ የቀጥታ ጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ ለአሸናፊዎች ሽልማት በመስጠት /ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ/
ውጤት
በረኸት ወረዳ
 ከ410 ያላነሱ ተሳታፊዎች ሰለኢኮቴ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።
 በቀበሌ ደረጃ መከበሩ የተደራሽነት ሽፋንን ጨምሯል።
 የተወዳዳሪነትን መንፈስ ፈጥሯል።
ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ
 ሕብረተሰቡ ሰለኢኮቴ ያለው ግንዜቤ ጨምሯል።
 የተወዳዳሪነትን መንፈስ ፈጥሯል።

46. ዲጅታል ላይበራሪ


ዲጅታል ላይበራሪ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በመረዳት የአማራ ክልል ሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት ጽ/ቤት ከኢኮቴ ልማት
ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ዲጅታል ላይበራሪ አልምቷል።
ስልት

23
ከኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ ስራውን የሚያከናውኑ ባለሙያዎች በመመደብ፣ለዲጅታል ላይበራሪ ዝግጅት የሚያገለግሉ
መረጃወችን በማሰባሰብ እና ኦፐን ሶርስ ሶፍትዌር በመጠቀም
ውጤት
በሚለዮን ለሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት አስችሏል።

47. የኢኮቴ ኮሚቴ በቀበሌ ደረጃ ማቋቋ


ማቋቋም
ኢኮቴ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በመረዳት በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ 01 ቀበሌ የኢኮቴ ኮሚቴ ተቋቋሟል።
ስልት
ለቀበሌው ስራ አስኪያጅና ለልማት ኮሚቴው የኢኮቴን ጠቀሜታ በማስገንዘብ
ውጤት
የቀበሌው ህብረተሰብ የቴክኖሎጅ ተጠቃሚ ሆኗል።

48. Team Viewer


Team Viewer ን ተጠቅሞ የተለያዩ ስራወችን ማከናወን ይቻላል
በመሆኑም ሰሜን ጎንደር ዞን 17 ወረዳዎች፣ዋግኽምራ ብ/አ/ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች እንዲሁም ክልል ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ
Team Viewer ን በመጠቀም የተለያዩ ችግሮችን ፈተዋል።
ስልት
የወረዳኔትን በሩቅ /Remotely/ ኮንፊገር በማድረግ
 በቅድሚያ ዞን ላይ ከተሞከረ በኋላ ወረዳዎች የሚከተለውን ቅደም ተከተል እንዲጠቀሙ በማድረግ
 Team Viewer ሶፍትዌርን ዳውን ሎድ ከተደረገ በኋላ ኢንስቶል ሲደረግ ፐርሰናል የሚለውን መምረጥ 
 በመጨረሻ ራሱ ሴፍትዌሩ የሚሰጠውን ዩዘር አይዲና ፓሰወርድ መዝግቦ መያዝና ለዞን ኢሜል ማድረግ/ሰሜን
ጎንደር ዞን/
 Team Viewer እና Skype ተጠቅሞ ከክልል ባለሙያዎችና ከሌሎች ዞኖች ጋር በመገናኘት የድጋፍና የትብብር
ስራ አብሮ በመስራት /ዋግኽምራ ብ/አ ዞን/
ውጤት
 በአካል መሄድ ሳያስፈልግ በአሉበት ቦታ ሆኖ መስተካከል ያለባቸውን ችግሮች ማስተካከል፣ ዶክመንትና ሶፍትዌር
መቀባበል አስችሏል።/ሰሜን ጎንደር ዞን/
 በሩቅ ሆኖ ሙያና ልምድ መጋራት አስችሏል።/ ዋግኽምራ ብ/አ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች/

49. Virtual Memory


አልፎ አልፎ የኮምፒዩተራችን ፍጥነት ይቀንሳል።ይህም ሊከሰት ከሚችልባቸው መንገዶች አንዱ የኮምፒተራችን ራም አቅም
ማነስ ነው።ይህን ችግር ለመፍታት Virtual Memory መጠቀም እንደሚቻል በሰሜን ጎንደር ዞን ተመላክቷል።
ስልት

24
በቅድሚያ ዞን ላይ ከተሞከረ በኋላ እንዴት እንደሚተገበር ለሁሉም ወረዳ ባለሙያዎች በስልጠና ወቅት ገለፃ በማድረግና
ጥገናዎች በሚሰሩበት ወቅት በመተግበር
ውጤት
የሜን ሚሞሪ(ራም) ግዥ ሊወጣ የነበረውን ወጪ አድኗል፤እንዲሁም የኮምፒዩተሮችን መንቀራፈፍ ቀርፏል፡፡

50. የጥገና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ዝግጅት


የጥገና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ማዘጋጀት አላስፈላጊ ወጭ ከማውጣት ያድናል። ለዚም ነው ሰሜን ጎንደር ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ
ልማት መምሪያ የጥገና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ያዘጋጀው።
ስልት
የጥገና ጨረታ ከመውጣቱ በፊት በመንግስት መ/ቤቶች ደረጃ ብልሽት የሚደርስባቸውን ዕቃዎች ዓይነት በመለየት (ሊጠገኑ
የሚችሉ የውስጥ ዕቃዎችን፣ የሚተኩ፣እንዲሁም ሶፍትዌር የሚጫኑትን ፣ሰርቪስ መድረግ የሚገባቸውን)
ውጤት
የጥገና ስራ ከመሰራቱ በፊት በተሰጠው ስፔክ መሰረት ጥገና እንዲደረግ ከመምሪያው ጋር በመስማማት

51. Interactive- Word 2003 to Word 2007


Microsoft Word 2003 ሲጠቀም የቆዮ ሰው Microsoft Word 2007 ለመጠቀም ለጊዜው ግር ሊለው
ይችላል።ሆኖም Interactive- Word 2003 to Word 2007 በመጠቀም ግርታውን ሊያስወግድ እንደሚችል ሰሜን
ጎንደር ዞን ጠቁሟል።
ስልት
ኢንተራክቲቭ ሶፍትዌር በመጫንና የሚፈለገውን double click በማድረግ የሚፈልጉትን በማየት
ውጤት
የማይክሮሶፍት ወርድ 2003 እና 2007 ያላቸውን ልዮነትና አንድነት ስለሚያሳይ የ skill ልዮነቶችን አጥብቧል፡፡

52. File and folder Un hide


አንዳንድ ጊዜ ኮምፒዩተራችን ላይ ያሉት ፋይሎችና ፎልደሮች ይሰወሩብናል።ይህን ችግር ለመፍታት File and folder Un
hide ሶፍትዌርን መጠቀም እንደሚቻል ሰሜን ጎንደር ዞን አመላክቷል።
ስልት
ችግሩ ለገጠማቸው የሰሜን ጎንደር ዞን መ/ቤቶች ሶፍት ኮፒውን በማደልና መረጃውን ከደበቀው ፎልደር ከፍቶ ፔስት
በማድረግ ሶፍትዌሩ ሚያዘውን ማድረግ
ውጤት
የተደበቁ መረጃዎችን ማውጣት ተችሏል።

53. Folder Lock

25
አንዳንድ ፋይሎችን በሚስጥር መያዝ ያስፈልጋል።ይህን ለማድረግ ፋየሎችን የያዘውን ፎልደር ሎክ ማድረግ የሚችል .
ሶፍትዌር መጠቀም የሚቻል መሆኑን ከሰሜን ጎንደር ልምድ መውሰድ ይቻላል።
ስልት
ሶፍትዌሩን ከኢንተርኔት በማውረድና ኮምፒዩተሮቻችን ላይ በመጫን
ውጤት
ፋይሎችና ዶክመንቶችን በሚስጥር እንዲጠበቁ አድርጓል፡፡

54.የሞባይል
54.የሞባይል ኢንተርኔት በላፕቶፕ መጠቀም
ኢንተርኔትን በሞባይል መጠቀም የሚቻል ቢሆንም አጠቃቀሙ አመች አይደለም።ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ ይህን ችግር ሊፈታ
የሚችል ሶፍትዌር መኖሩን አመላክቷል።
ስልት
Mobile Office Software ላፕቶፕ ላይ በመጫንና በኬብል ሞባይሉን ከላፕቶፕ በማገናኘት
ውጤት
በማንኛውም ቦታ ሞባይልን በመጠቀም ኢንተርኔት ማግኘት ይቻላል።

55. የሰዓት መቆጣጠሪያ ዳታቤዝ


የሰዓት አጠቃቀምን በተሻለ አሰራር የሚተካ ዳታቤዝ በኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ ተለምቷል።
ስልት
ዳታቤዙን ከኢንተርኔት በማውረድና ካስተማይዝ በማድረግ
ውጤት
ዳታቤዙ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ከማገዙም በሻገር ሰራተኞች በስብሰባ ላይም ሆነ ከስብሰባ ዉጭ ያሉበትን ሁኔታ
መልክት ለማስተላለፍ ይረዳል፡፡

56. BPR አውቶሜሽን


አብዛኞቹ የአማራ ክልል መ/ቤቶች መሠረታዊ የአሠራር ሥርዓት ለውጥ ጥናት / BPR / አካሂደው ወደ ትግበራ ገብተዋል።
ነገር ግን በክልሉ እየተካሄደ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የመስሪያ ቤቶችን አሰራር በቴክኖሎጂዉ
የታገዘ እንዲሆን BPR ን አውቶሜት ማድረግ ያስፈልጋል። ይህን በመረዳት የክልሉ ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ 4 የክልል
ቢሮዎችን (ትምህርት፣ ጤና፣ግብርና እና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ) እስከ ወረዳ ድረስ የሚያገናኝ ሲስተም አስለምቷል።
ስልት
 22 ሲስተሞችን ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በሚያገናኝ መልኩ በኢንፎርሚሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /INSA/
በማስለማት፣
 የሲስተሙን ልማት የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም፣/ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ
ውጤት
ከቴክኖሎጂዉ ጋር እኩል የሚያራምድ ዘመናዊና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠትና መልካም አስተዳደርን ማስፈን ያስችላል።

26
57. LAN Tool ሶፍትዌር መጠቀም
በአንድ ማሰልጠኛ ማዕከል ኔትወርክድ የሆኑ ብዙ ኮምፒዩተሮችን ለመዝጋት አሰልች ከመሆኑም በላይ ጊዜን ይሻማል።ሰሜን
ወሎ ዞን LAN Tool ሶፍትዌርን በመጠቀም ችግሩን ፈቷል።
ስልት
በሁሉም ኮምፒዩተሮች LAN Tool ሶፍትዌር መጫን
ውጤት
 በአንድ ኮምፒዩተር ላይ ሆኖ ሁሉንም ኮምፒዩተሮች መዝጋት ተችሏል
 ኮምፒዩተሮችን በመዝጋት የሚጠፋውን ጊዜ አስቀርቷል።

58. Deep Freeze ሶፍትዌርን መጠቀም


ኮምፒዩተር በቫይረስ ሲጠቃና ኤሌክትሪክ በሚጠፋበት ጊዜ ብልሽት ይደርስበታል።ብልሽቱን መካላል የሚችል ሶፍትዌር
ሰሜን ወሎ ዞን አግኝቷል።
ስልት
የኮምፒዩተሩን ሃርድ ዲስክ ፓርቲሽን መፍጠርና ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተጫነበትን ፓርቲሽን (ለምሳሌ ድራይቭ C :)
Freeze በማድረግ
ውጤት
ጠቃሚ የሆኑ ፋይሎች እንዳይጠፉ ማድረግ ተችሏል።

59.ኖርተን ጎስት ሶፍትዌር መጠቀም


ኦፔሬቲንግ ሲስተምን ከሚያበላሹ መንስኤዎች አንዱ የሀርድ ዲስክ ዲራይቭ ፓርቲሽን በኖርተን ጎስት ኢሜጅ መያዝ ነው።
(ለምሳሌ C: ኢሜጅ)
ከአምስት ደቂቃ በማይበልጥ ጊዜ ብልሽቱን ማስወገድ እንደሚቻል ሰሜን ወሎ ዞን አመላክቷል።
ስልት
ኖርተን ጎስት ሶፍትዌር ተጠቅሞ መልሶ ከኢሜጅ ሪስቶር በማደረግ
ውጤት
የኮምፒዩተርን ደህንነት መጠበቅ አስችሏል።

60.በቸክሊስት የታገዘ ድጋፍና ክትትል ማድረግ


የድጋፍና ክትትል ሰራ ማካሄድ ደካማ ጎኖች በወቅቱ እንዲታረሙ ጠንካራ ጎኖች ደግሞ እንዲበረታቱና እንዲስፋፉ ለማድረግ
ይጠቅማል።ይህን በመረዳት ሰሜን ወሎ ዞን በቸክሊስት የታገዘ ድጋፍና ክትትል አድርጓል።

ስልት
 የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊው ጋር በመወያየት በጀት እንዲፈቅድ በማድረግ፣

27
 ለ13ቱም ወረዳዎችና ለ3ቱም ማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት ቼክሊስት በማዘገዘጀት፣
 ከድጋፍና ክትትል በኋላም ለወረዳዎች ግብረ መልስ አዘጋጅቶ በመላክ
 ክልል ኢኮቴ ልማት ኤጄንሲም እንዲያውቀው በማድረግ
ውጤት
በኢኮቴ ዙሪያ የዞኑን እንቅስቃሴ ለማወቅ ተችሏል።

61.የፖርታል
61.የፖርታል ልማት
ፖርታል ድረ ገጽን፣ኢንትራኔትንና አክስትራኔትን አካቶ የያዘ መግቢያ ነው።ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ 26 የክልል መ/ቤቶችን
ያገናኘ ፖርታል አስለምቷል።
ስልት
 26 የክልል ሴክተር መ/ቤቶችን የያዘ ሲስተም በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /INSA/ በመስለማት
 የፖርታል ልማቱን የሚከታተል የቴክኒክ ኮሚቴ በማቋቋም፣/ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ
ውጤት
መረጃዎችን ዓለም አቀፋዊ ይዘት ባለው መልኩ ተደራሽ ማድረግ ያሰችላል

7.2.2 ከማህበረሰብ ሁለገብ መረጃ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


በ2005 ዓ.ም የተገኘ ምርጥ ተሞክሮ የለም፡፡

7.2.3 ከማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከላት የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


በ2005 ዓ.ም የተገኘ ምርጥ ተሞክሮ የለም፡፡

7.2.4 ከባህር ዳር ቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማዕከል የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎች


1.ወጣቶችን
1.ወጣቶችን ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት ማሸጋገር
የባህር ዳር ኢንኩቤሽን ማዕከል ዋና ዓለማው ወጣቶችን ከአንስተኛና ጥቃቅን ባለሀብትነት ወደ መካከለኛ ባለሃብትነት
ማሸጋገር ነው።በመሆኑም ማዕከሉ ውስጥ ገብተው የነበሩ 5 ካምፓኒዎችን ያስመረቀ ሲሆን አሁን እነዚህ ካምፓኒዎች
መካከለኛ ባለሀብት ሆነዋል።
ስልት
 የካምፓኒዎች የገበያ ትስስር በመፍጠር፣
 ብሮሸሮችንና ፖስተሮችን በማዘጋጀት የፕሮሞሽን ስራ በመስራት፣
 በዞን ከተሞች በመገኘት ስለማዕከሉ ዓላማና ስለካምፓኒዎች ለአመራር አካላት በማስተዋወቅ፣
 ካምፓኒዎች በእግዚቢሽንና ባዛሮች ላይ በመገኘት ምርቶቻቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ በማድረግ፣
 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው ውድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ በማድረግ ተሸላሚ እንዲሆኑ በማስቻል፣

28
 በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በመገኘት ለተመራቂ ተማሪዎች ስለኢኮቴ ቢዝነስ ዓላማ በማስተዋወቅ ቅድመ
ዝግጅት እንዲያደርጉ በማስገንዘብ፣
ውጤት
 የፈጠራ ስራን አበረታቷል።
 ከስራ ፈላጊነት ወደ መካከለኛ ባለሃብትነት መሻጋገር ተችሏል።

29
8. ማጠቃለያ
በቅመራ ሰነዱ የምርጥ ተሞክሮ ዓይነቶች ተካተዋል። ሆኖም በሰነዱ የተካተቱ ተሞክሮዎች ለአንዳንድ ተቋማት አንዳንዶቹ
ተሞክሮዎች አዲስ አሰራር ሊሆኑ የሚችሉ ቢሆንም ለአንዳንዶቹ በአቻ ወይም በተሻለ ሰርተዋቸው የሚገኙ ሊሆኑ
እንደሚችሉ በመረዳት በክልሉ የሚገኙ ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ የኢኮቴ ተቋማት ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ
እንደሚፈጽሙ ይጠበቃል:: ምርጥ ተሞከሮዎች ባልተሰሩበት ቦታ ከአካባቢው ሁኔታ ጋር በማዛመድ መተግበርን የሚጠይቅ
ሲሆን በተሰሩበት ቦታ ደግሞ ይበልጥ እንዲሻሻሉ ማድረግ ያስፈልጋል።

ምርጥ ተሞክሮዎችን በኤጀንሲው ድረ ገጽ ላይ በመጫን፤ በሲዲ አራብቶ ለዞኖች በመላክና ዞኖች በተዋረድ ለወረዳዎችና
ቀበሌዎች በሚያመቻቸው መንገድ እንዲያሰራጩ በማድረግ ማስፋፋት ይቻላል። በተጨማሪም ተቀምረው የተላኩት ምርጥ
ተሞክሮዎች ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆኑ የመከታተልና የመደገፍ ተግባር፣ የተስፋፉ ምርጥ ተሞክሮዎችን መረጃ
መያዝና ወረዳ ለዞን፣ዞን ለክልል በሪፖርት መልክ አካቶ ማቅረብ ይጠበቃል፡፡

የ ICT ዕድገት ፈጣንና ቀጣይ በመሆኑ ምርጥ ተሞክሮዎችም ወቅታዊ መሆን ይኖርባቸዋል። በመሆኑም ስራን የሚያቀላጥፉ
አሰራሮችን በየጊዜው በመቀመር ኢኮቴ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ እንዲሳካ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በየደረጃው
የሚገኙ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡

አባሪ
በ 2003 ዓ.ም የመጀመሪው ሰነድ ዝግጅት ላይ በመስክ በመገኘት መረጃ የተሰበሰበባቸው መ/ቤቶች

የክልል/ዞን /ከተማ አስተዳደር ስም የመስክ ጉብኝት የተካሄደባቸው መ/ቤቶች ምርመራ


ሰሜን ጎንደር ዞን ICT የስራ ሂደት  
ጎንደር ከተማ አስተዳደር ጎንደር ከተማ አስተዳደር ICT የስራ ሂደት  
ደቡብ ጎንደር ዞን ICT የስራ ሂደት  
ፋርጣ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  

30
ነፋስ መውጫ ማህበረሰብ ሁለገብ የኢንፎርሜሽን ማዕከል  
ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ICT የስራ ሂደት  
ሰቆጣ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ዋግኽምራ ማህበረሰብ ሬዲዮ ማዕከል  
ሰሜን ወሎ ላስታ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ብልባላ ቀበሌ ጽ/ቤት  
ዞን ICT የስራ ሂደት  
ቆቦ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ደቡብ ወሎ ዞን ICT የስራ ሂደት  
አልብኮ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ኮምቦልቻ የማሕበረብ ሬዲዮ ማዕከል  
ደሴ ከተማ አስተዳደር ደሴ ከተማ አስተዳደር ICT የስራ ሂደት  
ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ICT የስራ ሂደት  
ወጣቶች ICT ማዕከል  
ደዋጨፋ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ሰሜን ሸዋ ዞን ICT የስራ ሂደት  
ደብረብርሃን ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ምስራቅ ጎጃም  
እነማይ ወረዳ ICT የስራ ሂደት
እነማይ ፀረ-ወባ ማህበር  
ዞን ICT የስራ ሂደት  
ምዕራብ ጎጃም ዞን ICT የስራ ሂደት  
 
ቡሬ ወረዳ ICT የስራ ሂደት

የክልል/ዞን /ከተማ አስተዳደር ስም የመስክ ጉብኝት የተካሄደባቸው መ/ቤቶች ምርመራ


ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ICT የስራ ሂደት  
በላይ ዘለቀ ቀበሌ  
ከንቲባ ጽ/ቤት  
አዊ ብሔረሰብ አሰተዳደር ዞን ICT የስራ ሂደት  
ባንጃ ሽኩዳድ ወረዳ ICT የስራ ሂደት  
ክልል መ/ቤቶች ኢኮቴ ልማት ኤጀንሲ  

31
ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ  
ባህልና ቱሪዝም ቢሮ  
ጠቅላይ ፍርድ ቤት  

በ 2003 ዓ.ም የምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ቡድን አባላት፡-


1. አቶ በረደድ አግማሴ
2. ዶክተር ጌታቸው መለሰ
3. አቶ መላኩ ጥላሁን
4. አቶ ዑመር አደም

32

You might also like