Professional Documents
Culture Documents
Yekatit 2016 Report
Yekatit 2016 Report
ንግድ ቢሮ
የንግድ ኢንፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት
በመከላከል
o ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣትና
o የንግዱንና የሸማቹን ማህበረሰብ ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እቅድ
በተለይ፡-
ክፍል ሁለት
የተቋሙ ራዕይ (Vision)
የአዲስ አበባ ከተማ በ2022 ዓ.ም ዘመናዊ፣ ፍትሃዊ እና ተወዳዳሪ የንግድ ሥርዓት
ከሰፈነባቸው የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደም እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡
የዳይሬክቶሬቱ ተልዕኮ (Mission)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ህብረተሰብ ተሳትፎ በማጠናከር፣
በዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጅ በመታገዝ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰራር ማዘመን
ደረጃቸውን የጠበቁ የግብይት ማዕከላትን በማስፋፋት እና ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር
ስርዓት በመዘርጋት ፍትሃዊ ግብይትን በማስፈን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
ነው፡፡
የተቋሙ ዕሴቶች (Values)
ቅንነት
ግልፀኝነት
ተጠያቂነት
የላቀ አገልግሎት መስጠት
5 አቃቂ ቃሊቲ
6,150 6,150 100 224,195 266,350 119
7 ኮልፌ ቀራንዮ
32,542 9,200 28.27 139,224 143,050 103
ተግባር 1. አንድ ጊዜ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ ከዘርፍ፣ ከክፍለ ከተማ እና በቢሮ ቡድኖች ጋር ዕቅድ ማናበብና ለማጣጣም ታቅዶ
አንድ ጊዜ በማናበብ 100% ማሳካት ተችሏል፣
ተግባር 2. 1 ጊዜ የዳይሬክቶሬቱን የስራ አፈፃፀም ከዘርፍ፣ ከክፍለ ከተሞችና ቡድኖች ክንውን ጋር ማናበብና ለማጣጣም በወሩ
1 ታቅዶ 1 ጊዜ በማናበብ 100% ማሳካት ተችሏል፣ እስከዚህ ወር 8 ታቅዶ 8 (100%) ተከናውኗል፣
ዓላማ 7. የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና (የብልሹ አሰራር) የክትትል ሥራዎችን ማሻሻል፣
ተግባር 1. 1 ጊዜ በተለዩ የሌብነትና ብልሹ አሰራር ምንጮችን የማክስሚያ ሰነድ ማዘጋጀትና መተግበር ታቅዶ ተከናውኗል፣
ተግባር 2. 100% በብልሹ አሰራር ዙሪያ ጥቆማ ከተደረገባቸው ውስጥ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ታቅዶ 100%
ተከናውኗል፣
ተግባር 3. በሌብነትና ብልሹ አሰራር ተግባር የተሳተፉ አካላት ላይ 100% እርምጃ መውሰድ ታቅዶ ተግባር ውስጥ ገብተው የተገኘ በዚህ ወር
የለም፤
የቀጠለ….
ዓላማ 8. የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ተሳታፊነትንና ተጠቃሚነትን ማሻሻል፣
ተግባር 1. አንድ የህፃናት ማቆያ አገልግሎት ተጠቃሚ ሴት ሠራተኞችን ለማሳደግ ታቅዶ የአንድ ሰራተኛ
ልጅ በህፃናት ማቆያ እንድትጠቀም ማድረግ ተችሏል፣
ተግባር 2. የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን 50% ማረጋገጥ ሲባል በተሰጡ ሥልጠናዎች 50% ለማሳተፍ
ታቅዶ በዚህ ወር አልተከናወነም፤
ተግባር 3. የወጣቶች ተጠቃሚነትን 60% ማድረስ አልተከናወነም፣
ተግባር 4. 100% ለአካል ጉዳተኛ ሠራተኞችና ተገልጋዮች ምቹ (ነብሰ ጡሮችንና አካል ጉዳተኞችን
ቅድሚያ በመስጠት) መፍጠር ተችሏል፣
ዓላማ 9. የበጎ አድራጎት እና የማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎችን ማሻሻል፣
ተግባር 1. እስከዚህ ወር ድረስ 1,000 የአረንጓዴ አሻራ ተግባራትን ማካሄድ /ችግኞችን መትከል/ በዚህ ወር
በዕቅድ ተይዞ ተከናውኗል /የነዳጅ ማደያ ማህበራትን በማስተባበር በ2 ዙር ችግኝ መትከል ተችሏል፤
ተግባር 2. 3 ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን መደገፍ 100% ተከናውኗል፤
ተግባር 3. በኤች.አይ.ቪ.ኤድስ ሜይንስትሪም ማድረግና ግንዛቤ መፍጠር አልተከናወነም፤
ተግባር 4. 100% በተቋሙ እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቅድመ መከላከል (መብራት፣ ኮምፑተር እና የመሳሰሉ
መሣሪያዎች በማጥፋት) 100% ማከናወን ተችሏል፣
የቀጠለ….
ዓላማ 10. ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት፣ በመቀመርና በማስፋፋት 100% የአሰራር ስርዓትን ማሻሻል፣
ተግባር 1. እስከዚህ ወር ውጤታማ የሆኑ የተግባር ተሞክሮዎች መለየት 2 የታቀዶ 2 ተለይቷል፤ እነዚህም
የቅሬታ አፈታት ስርዓት በኦላይን ማድረግ
የመረጃ በሶፍት ኮፒ ማደራጀት
ተግባር 2. የተሻለ አሰራር /ተሞክሮ/ ካላቸው ተቋማት የልምድ ልውውጦችን ማካሄድ አልታቀደም
አልተከናወነም፣
ተግባር 3. ከተለዩት ውስጥ ምርጥ ተሞክሮዎች መቀመር አልታቀደም አልተከናወነም፣
ተግባር 4. ተሞክሮ ማስፋት አልታቀደም አልተከናወነም፣
ዓላማ 11. የተቋሙን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየት 100% መፍታት፣
ተግባር 1. 1 ጊዜ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየትና እቅድ ለማዘጋጀት ታቅዶ 1 በማዘጋጀት 100% ማሳካት
ተችሏል፣
ተግባር 2. የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን 100% መፍታት ዕቅድ የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል፣
የተፈቱ የውስጥ መልካም አስተዳደር
የቁጥጥር ባለሙያዎች የቅዳሜና እሁድ የትርፍ ሰዓት ክፍያ ጥያቄ እንዲፈታ በቀረበው መሰረት ምላሽ በማግኘት ወደ ስራ
ተገብቷል፤
የቀጠለ….
ዓላማ 12. የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን 100% ማሳደግ፣
ተግባር 1. የተቋሙን የህግ ማዕቀፎች ማሻሻል /መከለስ በዚህ ወር አልተከናወነም፣ እስከዚህ ወር 2 የማስተቸት ስራ
ተሰርቷል፣ (የኢንሽፔክሽን የቁጥጥር ማንዋል እና የገበያ ፋብሪካ ቁጥጥር ማንዋል) ስለሆነም 100% ማሳካት
ተችሏል፣
ተግባር 2. በየደረጃዉ 2 ንዑስ አገልግሎት በስታንዳርድ ታቅዶ 2 በማከናወን 100% ማሳካት ተችሏል፣
ተግባር 3. በየሩብ ዓመቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ንፅፅር መስራት በዚህ ወር 1 ጊዜ ታቅዶ 1 ተከናውኗል፤
እስከዚህ ወር 2 ታቅዶ 2 በማከናወን 100% ማሳካት ተችሏል፣
በህጋዊ ስነ-ልክ ቡድን የነዳጅ ማደያዎች ዲስፔንሰር ምርመራ ማድረግ ስቲከር መለጠፍ በተቀመጠለት ስታንዳርድ 1፡20 ሲሆን
ስራው በስታንዳርዱ መሰረት እየተፈፀመ ይገኛል፤ እንዲሁም በቢፒር ያልተጠና የነዳጅ ይፈቀድልኝ ጥያቄ ተገልጋይ ማሟላት
ያለበትን መስፈርት በመለጠፍ በዕለት ስራ መመዝገቢያ ቅፅ ላይ በመመዝገብ ደብዳቤ ለማዘጋጀት በ10 ደቂቃ አገልግሎቱ እየተሰጠ
ይገኛል፡፡
ተግባር 4. የተቋሙን የዜጎች የስምምነት ሰነድ (Citizen Charter) ማዘጋጀት ተችሏል፤
ተግባር 5. የለውጥ ስራዎችን (BPR, BSC and Citizen Charter) 100% መተግበር ተችሏል፤
የቀጠለ….
ዓላማ 13. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎች 100% ምላሽ መስጠት፤
ተግባር 1. 3 የቅሬታና አቤቱታ ማስተናገጃ ስርዓት ለመዘርጋት ታቅዶ 3 (መዝገብ፣ አስተያየት መስጫ
ሳጥንና የጥቆማ ስልክ) 100% ማዘጋጀት ተችሏል፤
ተግባር 2. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል 100% ምላሽ መስጠት በዚህ
ወር 100% ተከናውኗል፤
ተግባር 3. መሰረታዊ አገልግሎትን በቅልጥፍና በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ጥናት በዚህ ወር
አልተከናወነም፡፡ የተገልጋይ እርካታ ጥናት እስከዚህ ወር 1 ጥናት ለማድረግ ታቅዶ 1 በማከናወን 100%
ተፈጽሟል፤ በዚህ መሰረት ዕርካታው 79.82% መሆኑ ከጥናቱ ትንተና ተረጋግጧል፡፡
ዓላማ 14. ከንግዱ ማህበረሰብ የሚቀርቡ ቅሬታዎች 100% ምላሽ መስጠት፣
የቀረበ ቅሬታ ብዛት የተፈታ ቅሬታ ያልተፈታ ቅሬታ
ተግባር 1. በዚህ ወር 100% ከንግዱ ማህበረሰብ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመቀበልና ምላሽ ለመስጠት
ብዛት
ብዛት
አግባብነት አግባብነት የሌለው
ያለው 16 ታቅዶ 16 ምላሽ በመስጠት 100% ማሳካት
በዚህ ወር የቀረበ የለም፤ እስከዚህ ወር ምላሽ ለመስጠት
ተችሏል፣
በወሩ
እስከዚህ ወር የለም
ድረስ፡- 0 0
እስከዚህ ወር 16 16 15 1 0
የቀጠለ….
ድምር
29,929 48,882 100% 300,894 299,766 99%
የቀጠለ
ተግባር 2. በ44,000 ኑሮ ውድነት መነሻ የሚሆኑ ንግድ ድርጅቶች በድግግሞሽ የበር ለበር
ክትትል ቁጥጥር ለማድረግ የንግድ ህገ-ወጥነትን መከላከል ታቅዶ 51,577 በመፈፀም የእቅዱን
ከ100% በላይ ማከናወን ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ 387,855 ታቅዶ 339,282 አፈጻጸም
87% ለማከናወን ተችሏል፡፡
በ4,900 ምግብ ምርቶች ጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ በወሩ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ታቅዶ 6,497 በማከናወን እቅዱን
ከ+100% በላይ ማከናወን ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ 42,393 ታቅዶ 32,806 አፈጻጸም 81% ለማከናወን ተችሏል፡፡
በ 5,300 የፍራፍሬና አትክልት ጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ በወሩ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ታቅዶ 4,597 በማከናወን እቅዱን
100% በላይ ማከናወን ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ 40,393 ታቅዶ 32,806 አፈጻጸም 81% ለማከናወን ተችሏል፡፡
በ3,300 መጋዘኖችን ለመፈተሸ ታቅዶ 4,597 በማከናወን እቅዱን 100% በላይ ማከናወን ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ
24,920 ታቅዶ 25,165 አፈጻጸም 100% በላይ ለማከናወን ተችሏል፡፡
በ2,900 የግንባታ ዕቃዎች የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ለመቆጣጠር ታቅዶ 3,372 በማከናወን እቅዱን ከ+100% በላይ ማከናወን
ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ 25,916 ታቅዶ 25,924 የተከናወነ ሲሆን አፈጻጸም 100% በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡
በቁም እንስሳት የገበያ ማዕከላት በወሩ 4 ታቅዶ 25 (+100%) ተከናውኗል፡ እስከዚህ ወር በድግግሞሽ ዕቅድ 39 ክንውን
177 አፈፃፀም ከ100% በላይ ለማከናወን ተችሏል፡፡
በወሩ ዳቦ ቤቶች ዕቅድ 2,100 ክንውን 1,522(72%) ማከናወን ተችሏል፤ እስከዚህ ወር ዕቅድ 12,020 ክንውን 7,085
(59%) ማከናወን ተችሏል፣
በወሩ 760 የነዳጅ ማደያ ቤቶች ለመከታተል ታቅዶ 520 (68%) ማከናወን ተችሏል፣ እስከዚህ ወር 4,575 ታቅዶ 2,970
በማከናወን (65%) ማከናወን ተችሏል፡፡
የ11ዱ ክፍለ ከተማ የካቲት ወር የድግግሞሽ ወርሃዊ እና የተጠቃለለ ሪፖርት
የካቲት ወር እስከዚህ ወር ዕቅድ ክንውን
ተ.ቁ ክፍለ ከተማ ምርመራ
ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም ዕቅድ ክንውን አፈፃፀም
3 ባልታደሰ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ ቁጥር 3111 2588 83 4045 3367 83
4 ንግድ ፈቃድ ሳይሰቅሉ ሲነግዱ የተገኙ ቁጥር 750 631 84 5284 4603 87
6 የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ ሲነግዱ የተገኙ ቁጥር 1323 1195 90 7797 6991 90
8 ካስመዘገቡት ዘርፍ ወይም መሥክ ውጪ ሲነግዱ የተገኙ ቁጥር 306 228 75 1708 1448 85
11 ትክክለኛ ባልሆነ የልኬት መሳሪያ ሲጠቀሙ የተገኙ ቁጥር 67 67 100 416 407 98
ድምር
8,157 32,921
መሰረታዊ ሸቀጥ ኦዲት ስራ የተገኘ ግኝት
በዚህ የካቲት ወር ከተተመነ ዋጋ በላይ ሲሸጥ የተገኘ የለም፡፡ እስከዚህ ወር ድረስ በአቃቂ ቃሊቲ 1
ማለትም (ወረዳ 10 ሸማቾች ህ/ሥራ/ማህበር) ስኳር በኪሎ 2.38 ብር ጭማሪ ከተተመነ ዋጋ በላይ
ሲሸጡ መገኘታቸው በማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፤ እስከዚህ ወር 6 ድርጅቶች ከተተመነ ዋጋ
በላይ ሲሸጡ መገኘታቸው አስተዳደራዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው 5 ወደ ህጋዊነት በመመለስ 85.7%
ለማከናወን ተችሏል፡፡
በዚህ የካቲት ወር በቦሌ ክ/ከተማ 2 ኩንታል በወረዳ አንድ በህገ ወጥ መንገድ አየር በየር ሲሸጡ
ተይዘው በሸማች ህብረት ስራ ማህበር በኩል በብር 12,524(አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ አራት
ብር) በደረሰኝ ቁጥር TT24024646611 በዝግ አካውንት ገቢ ተደርጓል፡፡
እስከዚህ ወር ድረስ በልደታ ክ/ከተማ 1.4 ኩ/ል ስኳር፣ የካ ክ/ከተማ 1 ኩ/ል ስኳር እና በለሚ ኩራ
ክፍለ ከተማ 1.5 ኩ/ል ስኳር በድምሩ 3.9 ኩ/ል ስኳር አጠቃላይ 38.2ኩ/ል ስኳር እና ዘይት በልደታ
1,735 ሊትር ዘይት እስከዚህ ወር 3,757 ሊትር ዘይት ድርጅቶች አየር በየር ሲሸጡ መገኘታቸው
አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ምርቱ እንዲወረስ ተደርጓል፡፡ እስከዚህ ወር አየር በየር ሲሸጡ የተገኙ
ነጋዴዎች 19 ነጋዴዎች ሲሆን 18 ቱም አስተዳደራዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው በኃላ ወደ ህጋዊነት
እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
የቀጠለ
በአምስት አከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ በድጎማ የቀረበ የሸሙ እና የጊፊቲ ዘይት ምርት የ2015 በጀት ዓመት ኦዲት
የተደረገ ሲሆን እነዚህም፡-
ፒዩር ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተሰራጨበት ክ/ከተማ ልደታ፣ቂርቆስ፣ላይ ያሰራጨበት የግዢ እና የሽያጭ ደረሰኝ
ባለማቅረቡ በአከፋፋዩ ቢሮ ላይ የማሸግ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
ናትናኤል አለማየሁ ለለሚ ኩራ፣ጉለሌ እና ኮልፌ ላይ ካሰራጫቸው ውስጥ በጉድለት 7320 ሊትር ከፋብሪካ
አልወሰድኩም በማለት መረጃ ያላቀረበ በመሆኑ ከፋብሪካው መረጃ ለማጣራት በቀጠሮ የሚገኝ መሆኑ፤
መሲ አካሉ የጊፊቲ ዘይት አከፋፋይ ካሰራጩት 153,010 ሊትር ዘይት ውስጥ 7,145 ዘይት ያሰራጩበት
አግባብ ህጋዊ ማህተም በሌለው ደብዳቤ ስለሆነ በመመሪያ መሰረት የመጨረሻ የጽ/ማስጠንቀቂያ እርምጃ
ለመውሰድ ተወስኗል፡፡
ሚልኪ አካሉ የጊፊቲ ዘይት አከፋፋይ ከሰራጩት 193,005 ሊትር ዘይት ውስጥ ለቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 8
ለካሳንቺስ ሸማች ማህበር ማህተም በሌለው ደብዳቤ 6,000 ሊትር ዘይት ያሰራጩ መሆኑ ታይቷል፡፡
በተገኘው የአሰራር ጉድለት በመመሪያ መሰረት የመጨረሻ የጽ/ማስጠንቀቂያ እርምጃ ለመውሰድ ተወስኗል ፡፡
ጎሌ ትሬዲንግ ከ2015 በጀት ዓመት ጀምረው ኦዲት ለማድረግ በተደረገው ጥረት መሰረት በበጀት ዓመቱ
ለ11ዱም ክ/ከተማ ምርት ያሰራጨበት ሰነድ ኦዲት 445,240 ሊትር ዘይት የተሰራጨ ሲሆን ከነበረው ኮታ
1,100,000. ውስጥ የተሟላ መረጃ ለማግኘት የ2014 በጀት ዓመት ተሰራጭቷል ቢሉም 654,760 ሊትር
ሰነድ ያላቀረበ ሲሆን እንደ ምክንያት የገቢዎች ኦዲተር የቀረበ ቢሆንም መረጃ ባለመቅረቡ የማሸግ እርምጃ
እንዲወሰድ ተወስኗል፡፡
የቀጠለ
ሊትር
o በዚህ ወር የተፈቀላቸው መጠን በሊትር = 173,860 እስከዚህ ወር 2,190,795
የተለያዩ የህጻናት ወተት፤ ዮዮ ጁስ፣ ኢንዶሚ፤ ኮንዲሽነሮች፣ ሎሽን፣ ኮርንፍሌክስ፣ ቼኮሌት፣ ሰንችፕሰ፣ ከረሜላ፣
መኮሮኒና የሰላጣ ማጠቢያ ምርቶች ናቸው
እስከዚህ ወር 73 የንግድ ድርጅቶች ለመለየት ታቅዶ 73 በማከናወን የእቅዱን 100% መፈጸም ተችሏል፡፡
ተግባር 3. በወሩ 160 ንግድ ድርጅቶች ላይ የገበያ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ
ታቅዶ 285 በማከናወን የእቅዱን 93% መፈጸም ተችሏል፡፡
ግኝት
4 ሳሙና፣1 ለውዝ እና 2 ጨው አምራች ድርጅቶች በሚመርቱት ምርት ሲያሽጉ የአስገዳጅ የጥራት መስፈርት
መግለጫዎች በተሟላ ሁኔታ ሳይጠቀሱ ለሽያጭ እያቀረቡ ሲሆን፡-
የቀጠለ……
የትላልቅ ፕሮጀክቶች
3 ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ 12,000.00 161,012.67
ግንባታ ጽህፈት ቤት
ከእቅድ ውጭ የተከናወኑ
የለም
5.2 ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራት
o 100% በተቋሙ ወረቀት አልባ (ኦቶሜሽን) አሰራርን መተግበር አልተከናወነም፣
6. ያጋጠሙ ችግሮች
o የግብዓት ችግር (የሰው ሀይል፣ ኮምፒውተር፣ ስቴሽነሪ፣ የማነፃጸሪያ….)
በወረዳና በተለይ የፋይል ኦዲቲንግ ባለሙያዎች፣
o በየወቅቱ ሪፖርት አለመላክ እንዲሁም የጥራትና ተናባቢነት ችግር
ያለባቸው መሆኑ፤
o በክፍሉ የሚታየው ከፍተኛ የተሽከርካሪ እጥረት የታችኛውን መዋቅር
ለመደገፍ የማይቻልበት ሁኔታ መፍጠሩ፣
o የዳቦ ግራም መለኪያ ድጅታል ሚዛን እና የልኬት መሳሪያዎችን ማረጋገጫ
ማነፃፀሪያዎች /ስታንዳርድ/ አለመኖር፤
o ልኬት መሳሪያዎችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የስቲከር ህትመት ግዥ
አለመፈጸሙ፣
የቀጠለ
የተወሰደ የመፍትሔ አቅጣጫዎች
ባለው ግብዓት እየተሰራ ሌሎች እንዲሟሉ ማድረግ፣
ሪፖርቶችን በየወሩ ከተዘጋጀው ላይ በመልቀም መጠመር ተችሏል፡፡
የሪፖርቶች ጥራትና ተዓማኒነትን ለማረጋገጥ በተመረጡ ተግባራት ዙሪያ ኦዲት በማድረግ የማሻሻያ
ሀሳቦችን ማዘጋጀትና መስጠት፤
7. የሰው ሀይልና የበጀት አጠቃቀም
o የሰው ሀይል በወረዳ ላይ ከፍተኛ እጥረት እንደለ የተገመገመ ሲሆን በአንፃራዊነት በማዕከልና በክፍለ
ከተማ የተሟላ የሰው ሀይል በመኖሩ ባለው የሰው ሀይል ስራውን ማሳለጥ ተችሏል፣
የቀጣይ አቅጣጫዎች
o ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው የቅንጅት ሥራውን በማጠናከር የክትትልና ቁጥጥር ስራን አጠናክሮ መስራት፤
o በህገወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ ወጥ እና አስተማሪ እንዲሆን ማድረግ፤
o ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን ተግባራት በልዩ ትኩረት መፈፀም እንዲሁም በዝግጅት ምዕራፍ ፈጻሚን የማዘጋጀት
በተለይም ስልጠናዎች እና የአሰራር መመሪና ማንዋል የሚፈልጉትን ለይቶ እርብርብ ማድረግ፤
o ከብልሹ አሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተጀመረውን ቴክኖሎጂ መጠቀም፤
ማጠቃለያ