You are on page 1of 7

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 /

ስራ አስኪያጅ ጽ ቤት መልሶ መጠቀም እና ኡደት ማድረግ ቡድን

የዓመቱ ማጠቃለያ ሪፖርት

ሰኔ 2013
አዲስ አበባ
መግቢያ
በወረዳችን የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመለየት ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል የማድረግ
መልካም ጅማሬዎች ሲኖሩ ለማሳያነትም የሀይላንድና የቁራሌው ደረቅ ቆሻሻዎችን በተሻለ ሁኔታ የገበያ ትስስር
በመፍጠር የጽዳት ማህበራት እየለዩ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት የማዋል ተግባር እየተከናዎነ ይገኛል፡፡
ነገር ግን በወረዳው ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ አብዛኛውን ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት ማዋል የሚቻል
ቢሆንም አሁንም በወረዳው የሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ በሚፈለገው ደረጃ እየተለየ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት
አገልግሎት ማዋል ባለመቻሉ አብዛኛው ደረቅ ቆሻሻ ወደ ማስወገጃ ቦታ እየተጓጓዘ እንዲወገድ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በተለይ በወረዳው በርካታ መጠን ያለው ስብርባሪ ጠርሙስ፤ መስታዎትና የብርጭቆ፤ አሮጌ ማዳበሪያ ከረጢት፤ አሮጌ
ወረቀትና ካርቶን፤ ጀሪካን ቁርጥራጭ፤ ውድቅዳቂ ብረታ ብረት፤ አሮጌ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ወዘተ በአግባቡ ተለይቶ
ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት ስራዎች ለማዋል የተጀመሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ ነዉ፡፡እነዚህን
ከላይ የተዘረዘሩትን ደረቅ ቆሻሻዎች በአግባቡ በመለየትና በመሰብሰብ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውሉ
በማድረግ በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪም ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት
በመለወጥ ለሀገር የሚያበረክተውን ሀገራዊ ፋይዳ ማሳደግ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ደረቅ ቆሻሻን በስፋት ለመልሶ መጠቀምና
ኡደት አገልግሎት ለማዋል ያስችል ዘንድ በመልሶ መጠቀምና ኡደት ዘርፍ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 2 ስራ
አስኪያጅ ጽ/ቤት የመልሶ መጠቀም እና ኡደት ማድረግ ቡድን በ 2013 በጀት ዓመት እቅድ ተይዞ ወደስራ መገባቱ
ይታወቃል በመሆኑም በዚህ ወር ሊያከናውናቸውና ሊተገብራቸው ያሠባቸውን ዕቅዶች በአራቱ የዕይታ መስክ ተብለው
በተቀመጡ ከተገልጋይ፣ከፋይናንስ፣ከውስጥ አሰራር እንዲሁም ከማስፈፀም አቅም ግንባታ እይታ መስክ አንፃርና
ከወረዳው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ግልጽ በሆነ መልኩ እቅድ በማቀድና እቅዱን በጋራ በመሆን በመገምገም የጋራ እውቅና
በመፍጠር ወደ ትግበራ የተገባበት ሁኔታ ይገኛል፡፡በዚህ መሠረት የ 2012 ነባራዊ መነሻ መሰረት በማድረግ ዓመታዊ
እቅድ በማዘጋጀትና ከዚያም በመነሣት የተከናወኑ ሥራዎች እንዲሁም ሲያጋጥሙ የነበሩ ችግሮች በማካተት በዝርዝር
እንደሚከተለው በማቅረብ የዓመት ሪፖርት ተዘጋጅቷል፡፡

የሪፖርቱ ወሰን/የሚሸፍነው ጊዜ/

ይህ ሪፖርት የሚሸፍነው ጊዜ ከሰኔ 22/10/2012 እስከ ሰኔ 10/10/2013 ዓ.ም ያለውን ጊዜ ነው፡፡

የሪፖርቱ ዓላማ

የወረዳ 2 ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት መልሶ መጠቀም እና ኡደት ማድረግ የስራ ሂደት ማጠናከር በተጨማሪም የባለድርሻ
አካላትን ተሳትፎ መሰረት በማድረግ ስራን በመከታተልና በመቆጣጠር ያከናወናቸውን ተግባራት የእቅድ አፈጻጸሙን
ማመላከት ነው፡፡

ራዕይ/vision/፡-

አዲስ አበባ ከተማን በ 2017 ዓ.ም ከደረቅ ቆሻሻዋ ተጠቃሚ የሆነችና ጽዱና የአፍሪካ ሞዴል ከተማ ማድረግ

ተልዕኮ/mission/

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካትን ተሳትፎ መሰረት
በማድረግ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አሰባሰብ ስራን በመከታተልና በመቆጣጠር፣በማጓጓዝ የህብረተሰብ ግንዛቤ በማሳደግ
ዘመናዊና ቀልጣፋነት ባለው መንገድ የጽዳት አገልግሎት በመስጠት ወረዳዋን ጽዱ ማድረግ

እሴት/values/
 ተጠያቂነት

 ግልጸኝነት

 የላቀ አገልግሎት መስጠት

 ለለውጥ ዝግጁነት

 የሰው ሀይል ቀዳሚ ሀይላችን ነው

 ስራዎቻችን በጋ አመለካትና ግንዛቤ መፍጠር ይጀምራል

 የቡድን ስራ ለስኬታማነታችን መሰረት ነው

 ከተማን ማጽዳት ተቀዳሚ ተግባራችን ነው

ከስታንዳርድ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት

ግብ 1 የመረጃ ተደራሽነት ማሳደግ

ተግባር 1፡- የተለየያዩ ዓይነት መረጃዎችን በአይነት መለየትና በሃርድ ኮፒ ለማደራጀት ታቅዶ 12 በማደራጀት
የእቅዱ 100℅ ማከናወን ተችሎዋል፡፡

ተግባር 2፡-የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ሪፖርቶችን 12 ጊዜ ኤጀንሲው ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ፣ጥራትና ቅጽ
መሰረት ለማዘጋጀትና ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ ታቅዶ 12 ጊዜ በማዘጋጀት የእቅዱ 100 ℅ ማሳካት
ተችሎዋል፡፡

ተግባር 3፡-በወረዳ የተሰሩ ዋና ዋና የእለት ስራዎችን መረጃ በማደራጀትና ለሌላው ተሞክሮ ሊሆን የሚችለውን
መምረጥ በየሳምንቱ በቴሌግራም 48 ጊዜ ለማሰራጨት በታቀደው መሰረት በማከናወን የእቅዱ 100 ℅ ለማከናወን
ተችሎዋል፡፡

ተግባር 4፡-በየሳምንቱ በቴሌግራም የተሰራጩ መረጃዎችን የመረጃው ዓይነት በፎቶም ጭምር፤የያዘው መልዕክትና
መረጃው የተገኘበት ቀበሌ/ቀጠና በቅጽ በሃርድ ኮፒ መመዝገብና በየሳምንቱ ተሞክሮ ሊሆኑ በሚችል መንገድ በቃለ
ጉባኤ ጽፎ ለመገምገም ታቅዶ በእቅዱ በዚህ ወር 48 ማከናወን ተችሏል፡፡

ተግባር 5፡-የመልሶ መጠቀምና ኡደት መረጃዎችን በብሮሸሮች ለማሳተምና ለማሰራጨት 1 ጊዜ በማሳካት የእቅዱ
100 ℅ ማሳካት ተችሎዋል፡፡

ግብ 2 የተቋሙን አሰራርና አደረጃጀት ውጤታማነትን ማሳደግ


ተግባር ፡-በዳይሬክቶሬቱ የካይዘን ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ የስራ አከባቢውን ለስራና ለተገልጋይ ምቹ ማድረግ
100% ማሳካት ተችሏል

ተግባር 2፡-በዳይሬክቶሬቱ የካይዘንን ፍልስፍናን ተግባረዊ በማድረግ የተለያዩ ንብረቶችን ከጉዳት በመከላከል
በዳይሬክቶሬቱ የገንዘብ ብክነትን እንዲቀንስ ማድረግ 100% አሳክተናል

ተግባር 3፡-በዳይሬክቶሬቱ አምስቱን “ማ”ዎች ተግባራዊ በማድረግ ስራዎችን ውጤታማ ማድረግ 100% አሳክተናል

ግብ 3፡-የደረቅ ቆሻሻ መጠነ መልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ማሳደግ

ተግባር 1፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት የፕላስክ ጠርሙስና ፌስታል
ደረቅ ቆሻሻ በተገቢው መንገድ ተለይቶ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል ማድረግ እቅድ 25 ክንዉን 33
አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 2፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት ጀሪካን፤ ባልዲ፤ ማዳበሪያ፤
የሻምፖና ሌሎችንም (HDP) እቃዎችን በተገቢው መንገድ ሰብስቦ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል
ማድረግ እቅድ 13 ክንዉን 24 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡ ፡፡

ተግባር 3፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት ብረታ ብረትን ለይቶ ለመልሶ
መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል ማድረግ እቅድ 6 ክንዉን 18 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡::

ተግባር 4፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት ወረቀትንና ካርቶን በተገቢው
መንገድ ሰብስቦ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል ማድረግ እቅድ 30 ክንዉን 47 አፈጻጸም በመቶኛ
100%፡፡::

ተግባር 5፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት ጠርሙስና ብርጭቆን
በተገቢው መንገድ ሰብስቦ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል ማድረግ እቅድ 2.0 ክንዉን 2 አፈጻጸም
በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 6፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት ጨርቃ ጨርቅና ኤሌክትሮኒክ
ደረቅ ቆሻሻ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ እቅድ 30 ክንዉን 37.2 አፈጻጸም በመቶኛ
100%፡፡

ተግባር 7፡-በኮምፖስት በተደራጁ ማህበራት፤ በነዋሪው ህብረተሰብና ሴፍትኔትን በመጠቀም ከደረቅ ቆሻሻ ኮምፖስት
በማምረት ቆሻሻን ወደ ሀብትነት እንዲለወጥ ማድረግ እቅድ 0.2 ክንዉን 6 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 8፡-ከማህበራት ውጪ በኢ-መደበኞች፤ በግል ጽዳት ድርጅትና የሚሰበሰቡ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት
የሚውል ደረቅ ቆሻሻ መረጃዎች በየወሩ በማደራጀት የሪፖርት አካል ማድረግ እቅድ 1,050 ክንዉን 750 አፈጻጸም
በመቶኛ 74.3%፡፡

ተግባር 9፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በዘርፉ ተደራጅተው ለሚሰሩ ማህበራት አስተማማኝ የገበያ ትስስር
በመፍጠር ገቢ እንዲያገኙ ይደረጋል እቅድ 125,000 ክንዉን 142, 350 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡
ተግባር 10፡-በከተማው ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ በ 6.3% ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል
ማድረግ እቅድ 0.1 ክንዉን 5.3 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 11፡-በማህበራትም ይሁን በግለሰቦች የተመረተ ኮምፖስት በወቅቱ እንዲሸጥ ማድረግ እቅድ 0 ክንዉን 8
አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 12፡-የህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት ለሚለዩት 6 ዓይነት የመልሶ መጠቀምና ኡደት ደረቅ ቆሻሻ በህጋዊ
ውል የተፈረመ አስተማማኝ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ማድረግ እቅድ 6 ክንዉን 1 አፈጻጸም በመቶኛ 16.6%፡፡

ተግባር 13፡-የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት አሰራርን የሚያሳይ በከተማና ክፍለ ከተማ ደረጀ የጎዳና ኤግዚቢሽን
ማዘጋጀትና ስራዎችን ለህብረተሰቡ በማስተዋወቅ ግንዛቤ መፍጠር እቅድ 0 ክንዉን 0 አፈጻጸም በመቶኛ 0%፡፡

ተግባር 14፡-በመልሶ መጠቀምና ኡደት ለተደራጁ ሁሉም ማህበራት አስተማማኝ እና በህጋዊ ውል የተፈረመ የገበያ
ትስስር እንዲፈጠር ማድረግ እቅድ 100 ክንዉን 50 አፈጻጸም በመቶኛ 50%፡፡፡፡

ተግባር 15፡-ኢ-መደበኛ የመልሶ መጠቀም ክምችት ቦታዎችን ጽዱ ማድረግ እቅድ 100 ክንዉን 100 አፈጻጸም
በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 16፡-የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት አፈጻጸምንና ክትትል ድጋፍን መሰረት በማድረግ በየሩብ አመቱ
ለሁሉም ወረዳ ግብረ መልስ በጽሁፍ መስጠት እቅድ 4 ክንዉን 4 አፈጻጸም በመቶኛ 100 %፡፡

ግብ 4 የስራ እድል ፈጠራንና የባለድርሻ አካላትነንና ተሳትፎ ማጎልበት

ተግባር 1፡-በመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ የስራ እድል መፍጠር እቅድ 32 ክንዉን 34 አፈጻጸም በመቶኛ
100%፡፡፣፡

ተግባር 2፡-በመልሶ መጠቀምና ዑደት ማድረግ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ዜጎች በተደራጁበት መስክ ስራ እንዲጀምሩ
ማድረግ እቅድ 15 ክንዉን 10 አፈጻጸም በመቶኛ 67%፡፡፣

ተግባር 3፡-በህብረት ሽርክና የጽዳት ማህበራት እና በመልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት 3 ቶን ብረታ ብረትን ለይቶ
ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል ለማድረግ ታቅዶ 15 ቶን ለይቶ በመሰብሰብ የእቅዱ 100℅ ማሳካት
ተችሎዋል::

ግብ 5፡-ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎች አፈጻጻም ማረጋገጥ

ተግባር 1፡-የዜጎች ቻርተር ሰነድና የአገልግሎት ስታንዳርድ ለተገልጋይ ተደራሽ ማድረግና መተግበር እቅድ
100% ክንዉን 100%አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 2፡-የኤ.ቢ.ሲ ሥራዎችን በተሟላ ሁኔታ መተግበር እቅድ 100% ክንዉን 100% አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 3፡-በተቋሙ አገልግሎቶች የሚነሱና በአሰራር ሥርዓት የሚለዩ የሌብነት ምንጮችንና ብልሹ አሰራሮችን አቅዶ
መተግበርና መፍታት እቅድ - ክንዉን - አፈጻጸም በመቶኛ 0%፡፡

ግብ 6 ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት አሰራርን ማሻሻል


ተግባር 1፡-በዘርፉ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር በተግባር ተሞክሮ ውጤታማ የሆኑ ምርጥ ተሞክሮ መቀመር
እቅድ 0 ክንዉን 0 አፈጻጸም በመቶኛ 0%፡፡

ተግባር 2፡-በዘርፉ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር በተግባር ተሞክሮ ውጤታማ የሆኑነና የተቀመረ ምርጥ ተሞክሮ
ማስፋት እቅድ 1 ክንዉን 1 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 3፡-በክፍለ ከተማው በየወሩ መልካም ተሞክሮ ያላቸውን ወረዳዎች በመምረጥ የሁሉም የወረዳ ቡድን
መሪዎችን የክፍለ ከተማ ባለሙያ ያካተተ የመስክ ጉብኝት ማድረግ እቅድ 4 ክንዉን 4 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

ተግባር 4፡-በየሩብ ዓመቱ መልካም ተሞክሮ ያላቸውን ወረዳዎች በመምረጥ አመራሩን ያካተተ የመስክ ጉብኝት ማድረግ
4 የክትትል፣የግምገማና የግብረ-መልስ ስርዓት እቅድ 4 ክንዉን 4 አፈጻጸም በመቶኛ 100%፡፡

4.1.የክትትል ስርዓት
በበጀት ዓመቱ ለተዘጋጀው እቅድ ስኬት የክትትልና ድጋፍ ስርዓታችን ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው ያለ ፈጻሚ አካል
ተግባራትን በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ጥራትና መጠን መከናወናቸውን መከታተልና መደገፍ ወደ ተሻለ አፈፃፀም የማድረስ
ተግባር ቁልፍ ስራችን ይሆናል፡፡በዚህም የክትትልና ድጋፍ እቅድ በማዘጋጀትና ለክትትልና ድጋፍ ቼክ ሊስት በማዘጋጀት
ተግባራት በእቅዳቸው መሰረት እንዲከናወኑ ይደረጋል፡፡

4.2.የግምገማና የግብረ-መልስ ስርዓት


በ 2013 በጀት ዓመት የሚከናወኑ የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ቡድን እቅድ ተግባራት በትግበራ ሂደት ከክፍለ
ከተማ ጋር በመሆን አፈፃፀማቸውን ተከታታይነት ባለው መልኩ በመከታተል፣ በመደገፍና በመገምገም ግብረ መልስ
እየሰጡ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት የመልሶ መጠቀምና ኡደት ማድረግ ቡድን በየወሩ የባለሙያ ሪፖርት እንዲሁም ክትትልና ግምገማ
በማካሄድ ግብረ-መልስ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡ በየወሩ ሪፖርት ቀርቦ እየተገመገመና ግብረ-መልስ
እየተሰጠባቸው የሄዱ ጉዳዮችን በማጠናቀር በየወሩ የጽሁፍ ግብረ-መልስ በመስጠት ችግር ፈቺ የሆኑ የማስተካከያ
እርምጃዎች እየተወሰዱ የተግባራት አፈፃፀም በተቀመጠላቸው ጊዜ፣ጥራትና እንዲሁም በጀት እንዲጠናቀቁ የማድረግ
ስራ ተሰርቷል፡፡

ያጋጠሙ ችግሮች

-አዲስ በመልሶ መጠቀም ዘርፍ ማህበራት ለማደራጀት የቦታ ችግር ቢፈታም ወደስራ ለመግባት የበጀት ችግር፡፡
-የሀይላንድ ለይቶ ማስረከብ ከዋጋ ጋር በተያያዝ ዝቅተኛ መሆን
-የኮምፖስት ዝግጅት ቦታ ችግር መኖሩ ህጋዊ ሆኑ ለመስራት ፍቃድ ለማዉጣት ዉል እና ማስረጃ ክፍያ ከፍተኛ መሆኑ
-በመልሶ መጠቀም ለተደራጁ ማህበራት ስልጠና ለመስጠት የበጀት ዉስንነት መሆሩ
-ኃይላንድ በወቅቱ ያለመነሳት ችግር

-ኃይላንድ የገበያ ትስስር ቢደረግም በዉል መሰረት ኃይላንድ ያለማንሳት ዉል ሳያቋርጡ መጥፋት እና ተጠያቂ
ያለማድረግ

-ኮምፖስት ዝግጅት ያደራጀናቸዉ ወጣቶች ወደስራ ለማስገባት የአከባቢዉ ማህበረሰብ ሽታ ያመጣብናል ለጤናችን
አደጋ አለዉ በማለት ስራዉን እንዳንሰራ እንቅፋት መሆን

የተወሰዱየመፍትሄእርምጃዎች

-በሀይላንድ አዲስ የገበያ ትስስር በማፈላለግ በዝቅተኛ ገንዘብ ቢሆንም መሸጥ መቻሉን
-በመንግስት ተቋማት በደብዳቤ በመጻጻፍ በጊዚያዊነት ለኮንፖስት ዝግጅት የሚዉል ቦታ ማግኘት ተችሎዋል
-የበጀት ችግር ለባለሀብት ፕሌጅ በማሰጋጀት እስፖንሰር ለማፈላለግ ጥረት እየተደረገ መመሆኑ

-የነበረዉን ገበያ መጠቀም

-የአከባቢዉን ማህበረሰብ በየደረጃዉ ላማወያየት ተችሏል ዉጤታማ ባይሆንም

--በወረቀት እናኮምፖስት ያደራጀናቸዉ ወጣቶችን በጀት በማፈላለግ ስልጠና ለመስጠት ተችሏል


በጤና ጣቢያ የተወሰነ ቦታ ፍቃድ በማፈላለግ ኮምፖስት ለማዘጋጀት ተችሏል

የሪፖርቱ ማጠቃለያ
የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ በቀጣይ ዓመት እቅድ አቅደን ሳናከናውናቸው የቀሩና የሪፎርም ስራዎችን በአጠቃላይ
በአፈጻጸም ሂደት የገጠሙንን የማስተካከልና የማሳካት ስራ መስራት እንዲሁም የተጀመረው የተሞክሮ ስራዎች ላይ
ጠንክረን መስራት እንዳለብን የጋራ መግባባት በመፍጠር በቀጣይ ወር በልዩ ትኩረት የምንፈጽም መሆኑን ተገንዝበን እና
እቅዳችንን ፈትሸን የምንተገበር ይሆናል፡፡

You might also like