You are on page 1of 17

/ /

በየካ ክ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ ቤት የመንገድ ቦዮች፣ ወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ጽዳት

የተቀናጀ የ 2 ወር ንቅናቄ ዕ ቅድን በላቀ ሁኔታ ለማስፈፀም የተዘጋጀ


ስምምነት

ግንቦት 2013 ዓ.ም

በየካ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የመንገድ ቦዮች፣ ወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ጽዳት

የተቀናጀ የ2 ወር ንቅናቄ ዕ ቅድን በላቀ ሁኔታ ለማስፈፀም የተዘጋጀ

የስምምነት ሰነድ

በ2 ወሩ ንቅናቄ ዕቅዱን በላቀ ሁኔታ ለማስፈፀም ዝግጁ መሆኔን በመግለፅ በፊርማዬ አረጋግጣለሁ

አስረካቢ
ክ/ ሙሉ ስም ኃላፊነት ስልክ ቁጥር ፊርማ
ከተማ
የካ ጫሊ ቤኛ ዋና ስራ አስኩያጅ 0913968415

ተረካቢ
ወረዳ ሙሉ ስም ኃላፊነት ስልክ ቁጥር ፊርማ
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12

/ /
በየካ ክ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ ቤት

የመንገድ ቦዮች፣ ወንዞችና ወንዝ ዳርቻዎች ጽዳት የተቀናጀ የንቅናቄ ዕቅድ


ግንቦት 2013 . ዓ ም

“የክ/ከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፍያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!!“

መግቢያ
o የካ ክ/ከተማ በከተማችን ከሚገኙ 11 ክ ከተሞች አንዱ ሲሆን

o የመኖሪያ አካባቢዎች ፣ የተለያየየ የንግድ ተቋማትና የተለያዩ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ

ተቋማት የሚገኙበት ነው፣


o የክ/ከተማዋ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመነጨው ቆሻሻ በአይነትም

በመጠንም እየጨመረ መምጣቱ የደረቅ ቆሻሻ ስርአቱን ፈታኝ እና ውስብስብ አድርጎታል፡፡


o ይህም የጽዳቱ ጉዳይ የሁሉንም ዜጐች ተሳትፎ እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የሚጠይቅ ነዉ፡፡

o ክ/ከተማወን ጽዱና ዉብ በማድረግ ረገድ ውጤታማና ስኬታማ መሆን እንደሚቻል የሁለት

ወራት የጽዳት ንቅናቄው በቂ ትምህርት የሰጠና ማረጋገጫ ነዉ፡፡


o ክ/ከተማችንን እዲሁም ከተማችን እንደ ስሟ አዲስ እና አበባ እንድትሆን በቀጣይነትና ዘላቂ

በሆነ መንገድ ለማስቻል “የክ/ከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፍያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ
የቆሻሻ መጣያ አይደሉም” በሚል መሪ ቃል የክ/ከተማው ስራ አስኪየጅ ጽ/ቤት፤ የክ/ከተማው

ተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ጽ/ቤት ፤ የምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ፤


የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበርያ ጽ/ቤት በጋራ ሊያሳትፍ የሚችል የክ/ከተማ ጽዳት ንቅናቄ
ማስፈጸሚያ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
1.2.ዓላማ፣ መሪ ቃል፣ ግብ፣ አስፈላጊነት፣ ወሰን
1.2.1.ዓላማ
የክ/ከተማችን ነዋሪዎችን ፣ ተቋማት እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የውኃ መውረጃ ቦዮችንና

ክፍት ቱቦዎችን፣ ክፍት የሆኑ ማንሆሎችን ማጽዳትና መጠገን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ

ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ የመንገድ ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን፣ የድልድይ ስርና ዙሪያዎችን፣

የባቡር ሀዲድ መስመሮችን፣ ተርሚናሎችን፣ ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ በሕገ ወጥ የሚወገዱ ቆሻሻዎችን፣

ብሎኮችን በማጽዳት ከቆሻሻ፣ ከመጥፎ ሽታና በቆሻሻ ምክንያት ከሚከሰት ጎርፍ በመጠበቅ ጽዱ፣ ውብና

ማራኪ በማድረግ ጤናማ አካባቢን መፍጠር እንዲሁም መንገዶች ለተገነቡበት ዓላማ ብቻ እንዲውሉ

ከብልሽትና ጉዳት መጠበቅ ነው፡፡

1.2.2. መሪ ቃል
“ የክ/ከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፍያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም!! ”
1.2.3. ግብ
በየመንደሩ እና በዋና ዋና መንገዶች ያሉ መንገዶች እንዲሁም የወንዝ ዳርቻዎችና ወንዞችን ከፍተኛ የህዝብ
ንቅናቄ በመፍጠር ከተማችን ከቆሻሻ ማጽዳት፣ ከመጥፎ ሽታ እና በቆሻሻ ምክንያት ከሚከሰት ጎርፍ መከላከል
ተችሏል፡፡
የንቅናቄ ዕቅዱ ዝርዝር ግቦች
 ቦዮችና ወንዞች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አለመሆናቸው ላይ ለ 70,703 የህብረተሰብ
ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፤
 በንቅናቄው ከተቋማት 2,400 ከነዋሪና አደረጃጀቶች 24,400 ባጠቃላይ 26,800 በየ 15 ቀኑ
የህብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማት በ 2 ወር ንቅናቄው 134,000 ተሳታፊ ሆነዋል፤
 በንቅናቄው 12 ኪ.ሜ የመንገድ ቦዮች፣ ወንዞቻና ዳርቻዎች እንዲሁም የቆሸሹ መንገዶች ጽዱ
ተደርገዋል፤
 11 ለቆሻሻ ተጋላጭ የነበሩ (ክዳን ያልነበራቸው) ማንሆሎች ክዳን ተገጥሞላቸዋል፡፡
 በአስራሁለቱም ወረዳዎች ባሉ በዮች፣ ክፍት ቱቦዎችና ጥርጊያ ቦዮች ያሉ ቆሻሻዎችን በማጽዳት
ሊከሰት የሚችል ጎርፍ መከላከል ተችሏል፡፡
1.2.4 አስፈላጊነት
የሁሉን አቀፍ የክ/ከተማ ጽዳት ንቅናቄ የተፈጠረዉን የአመራር፣የነዋሪና የተቋማት መነቃቃትና ግለት

በማስቀጠል በደረቅ ቆሻሻ የተዘጉና የተሸፈኑ የውኃ መውረጃ ቦዮችንና ቱቦዎችን፣ ክፍት የሆኑ ማንሆሎችን

ማጽዳትና መጠገን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ የመንገድ

ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን፣ የድልድይ ስርና ዙሪያዎችን፣ የባቡር ሀዲድ መስመሮችን፣ ተርሚናሎችን፣ ክፍት

በሆኑ ቦታዎች ላይ በሕገ ወጥ የሚወገዱ ቆሻሻዎችን፣ ብሎኮችን በማጽዳት ተመልሰው እንዳይቆሽሹ፣

የመጥፎ ሽታና የጎርፍ መንስኤ እንዳይሆኑ ግንዛቤ በማስረጽ፤ በአረንጓዴ ልማት ውብ በማድረግ

የመንገዶቻችን ደህንነትና ንጽህናን መጠበቅ በማስፈለጉ ነው፡፡

1.2.5.የሚጠበቅ ውጤት ውጤቶች

በነዋሪዎችና በባለድርሻ አካላት ባለቤትነት በዘላቂነት የፀዱ ለክ/ከተማው ሁለንተናዊ ውበትን ያጎናፀፉ 3

ኪ.ሜትር የውሃ መውረጃ እና የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች፣ 4 ኪ.ሜትር ክፍት ቱቦዎች ፣ 11 የተጠገኑ ክፍት

የሆኑ ማንሆሎች እና ጥርጊያ ቦዮች፣ 7 ኪ.ሜትር የወንዝ ዳርቻዎችና የወንዝ ዳርቻ ግንባታ ቦታዎች

፣5 ኪ.ሜትር የመንገድ ዳርቻዎች፣ የመንገድ አካፋዮች እና አደባባዮች፤ ድልድዮች ስርና ዙሪያቸው ፣የባቡር

ሀዲድ መስመሮች እና ተርሚናሎች እንዲሁም የመንገድ ማሳለጫዎች ከሕገ ወጥ የቆሻሻ አወጋገድ የተጠበቁ

ክፍት የሆኑ ቦታዎች እና 485 ብሎኮች ናቸው፡፡

1.2.6. የእቅዱ ወሰን


ንቅናቄው የሚከናወነዉ በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ ሲሆን በሁለት ወራት የክ/ከተማ ነዋሪዎችና
ባለድርሻ አካላት በሁሉም ወረዳዎች በመገኘት የውኃ መውረጃ ቦዮችንና ቱቦዎችን፣ ክፍት የሆኑ
ማኑዋሎችን ማጽዳትና መጠገን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ
አካፋዮችን፣ የመንገድ ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን፣ የድልድይ ስርና ዙሪያዎችን፣ የባቡር ሀዲድ መስመሮችን፣
ተርሚናሎችን፣ ክፍት በሆኑ ቦታዎች ላይ በሕገ ወጥ የሚወገዱ ቆሻሻዎችን፣ ብሎኮችን ከግንቦት 14 እስከ
ሀምሌ 14/2013 ዓ.ም የሚጸዱበት የትግበራ እቅድ ነው፡፡

ክፍል ሁለት
2.ያለፉት ሁለት ወራት ሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳት ንቅናቄ አፈጻጸም እንደ ነባራዊ መነሻ
2.1.ሁሉን አቀፍ የጽዳት ንቅናቄው አጠቃላይ ሁኔታ
ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በትስስር የሚሰራ ቢሆንም በዘርፉ ትልቁ ባላድርሻ

አካላት የደረቅ ቆሻሻው አመንጪ ነዋሪ ማህበረሰብ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ነዋሪውን ፣ የክ/ከተማ እና የወረዳ

ከፍተኛ አመራሮችን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን/ ታዋቂ ግለሰቦችን፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣

የፅዳት አምባሳደሮችን፣ የተለያዩ አደረጃጀቶችን፣ ማሳተፍ ለደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራ ወሳኝ በመሆኑ

ከየካቲት 27 - ሚያዝያ 30/ 2013 ዓ.ም ለሁለት ወራት ለ 2 ወራት ቆይታ ያደረገ የጽዳት ንቅናቄ

ተከናውነዋል፡፡

በ 9 ሣምንታት በየሳምንቱ የተሳተፈው ብዛት የተሰበሰበና የተጓጓዘ ምርመራ


የተሳታፊዎች ብዛት በአማካይ ቆሻሻ በሜኪዩብ

580,184 64,466 5,102.6

2.2. የጽዳት ንቅናቄው የአመራር ሁኔታ


 ያለፉት ሁለት ወራት የሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳት ንቅናቄ ከእቅድ ጀምሮ እስከ ትግበራ የክ/ከተማ

ዋና ስራ አስፈጻሚ ፣ የክ/ከተማ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ ፣የክ/ከተማ አጠቃላይ አመራሮች እና

የክ/ከተማ የፓርቲ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች በጽዳት ንቅናቄዉ

በመሳተፍና አመራር በመስጠት ሚናቸዉን ተጫዉተዋል፡፡

 ሁሉን አቀፍ የከተማ የጽዳት ንቅናቄው ተዘጋጅቶ በታቀደው እቅድ ላይ ክ/ከተማ እና ወረዳዎች

በመግባቢያ ሰነድነት በመፈራረም ወደ ትግበራ የገቡ መሆናቸው

 ü ወረዳዎች ከብሎክ አደረጃጀቶች ጋር በታቀደው እቅድ ላይ የመግባቢያ ü ክ/ከተማው ባለሙያዎች

ቡድን በማደራጀት ለወረዳዎች እና ለብሎኮች ተመድበው የክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረመልስ

በመስጠት በትጋት እና በታታሪነት እየተከናወነ የእቅዱ አፈፃፀም በቋሚነት በየሳምንቱ እየተገመገመ

መቷል፡፡

 የጽዳት ንቅናቄው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ትግበራ ምእራፍ በከፍተኛ ሀላፊነት እየተመራ

መምጣቱ
 ü በየሳምንቱ የተከናወኑትን ተግባራት በመገምገም ደረጃ እየወጣ ጥንካሬዎች እየተለዩ የበለጠ

እንዲጐለብቱ እና ድክመቶች እንዲታረሙ አቅጣጫ በመስጠት አፈፃፀሙ በየዙሩ እየተሻሻለ እንዲሄድ

ከፍተኛ ጥረት ተደርጐበታል፡፡

 ሰነድ በመፈራረም ወደ ትግበራ መግባታቸው

2.3. የማህበረሰቡ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ

 የተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስራ በመንግስት ብቻ የሚከናወን ተደርጐ የሚታየውን አመለካከት

ለመለወጥ የሚያስችል የሁለት ወራት የጽዳት ንቅናቄው ሂደት አመላክቷል፡፡

 የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣አርቲስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦችን የክ/ከተማው የጽዳትና ዉበት አምባሳደር

አድርጎ በመሰየም የጽዳቱ ዋነኛ ተዋናይ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

 በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣የጤና ባለሙያዎች፣የጸጥታ

አካላት(መከላከያ፣ፖሊስና ደምብ ማስከበር)፣ ባለሀብቶች ፣በጎ ፍቃድ ወጣቶች፣ ተማሪዎች፣ሴቶች

እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ለክ/ከተማችን ጽዳትና ውበት አካባቢያዊ ስነምሕዳር ጥበቃ የግልና የጋራ

ተሳትፎአቸው አስፈላጊነት የተገነዘቡበት ነው፡፡

 በመኖሪያ አካባቢያቸው /ብሎኮችን/ እና በመስሪያ ቤታቸዉ እንዲሁም በክ/ከተማቸው የጽዳት

ባለቤትነት ሆነው ሚናቸውን እንዲጫወቱ ልዩ ትኩረት የሚጠይቅ ከተማ አቀፍ ጉዳይ መሆኑን

ግንዛቤ የተገኘበት ንቅናቄ ነበር

 የክ/ከተማችን ጽዳት የሁሉም ደረቅ ቆሻሻ አመንጭዎች የጋራ የሆነ ማሕበረሰባዊ እሴት

የሚፈጠርበት ዘርፍ መሆኑንም አሳይተዋል፡፡

2.4. የሚድያና የህዝብ ግንኙነት ተሳትፎ


 የጽዳት ንቅነቄዉ በዘጠኙም ዙር ሰፊ የሚባል የሚድያ ሽፋን ያገኘና ዋነኛ የክ/ከተማ አጀንዳ መሆን
የቻለ ነበር፡፡
 ከቴሌቪዥን በኦ ቢ ኤን፣ዋልታ እና ሁሉም ሚድየዎች በሚባል የተሸፈነ ሲሆን በተለይ አዲስ ቲቪ
በቋሚነት የዜና እና የፕሮግራም ሽፋን ሰጥቷል፡፡
 በማህበራዊ ሚድያ (በተለይ በቴሌግራምና በፌስቡክ)፣በህትመት ሚድያዎችም ሽፋን ያገኘ ሲሆን
በሞንታርቦ ቅስቀሳ በስፋት ተሰርቷል፡፡
ክፍል ሦስት

3. በንቅናቄው የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች


3.1.የነበሩ ጠንካራ ጎኖች
 ተቋማት በፅዳት ተግባር ላይ ትኩረት ሰጥተው መሳተፍ መቻላቸው

 ብሎክ አደረጃጀቶች የብሎካቸውን ጽዳት ለማስጠበቅ በተሻለ ሁኔታ እየሰሩ መሆኑ

 በዘርፉ ያሉ ሰራተኞች በሙሉ ለንቅናቄው ትኩረት በመስጠት ለአፈፃፀሙ የላቀ ሚና መወጣታቸው

 የጽዳት አምባሳደሮች እና የብሎክ አደረጃጀቶች በጋራና በመናበብ ንቅናቄውን ማሳካታቸው

3.2.የነበሩ ደካማ ጎኖች


• ለፅዳት ንቅናቄው በተመረጡ አከባቢዎች ነዋሪ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ አቅም መጠቀም

ላይ አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩ፣

• የጽዳት ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ክፍተት መኖሩ በተለይም በዚህ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ

በስራ አስኪያጅ እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ እንዲሁም በሌሎች ሴክተሮች መካከል መኖሩ፣

• በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለብሎክ ተጠሪዎች አቅም በመፍጠር የጽዳት ንቅናቀውን በራሳቸው አቅም

እንዲመሩ ያለማድረግ ውስንነት

• በሁሉን አቀፍ የጽዳት ንቅናቄ የታየው የአመራር ተሳትፎ መልካም ቢሆንም አሁንም ትኩረት የመስጠት

ውስንነት መኖሩ፣

• በጽዳት ንቅናቄው የተቋማት ተሳትፎ ወስንነት ያለው መሆን እና በሙሉ አቅም የማሳተፍ ክፍተት፣

• ዘላቂ ለውጥ ለሚያመጣ የንቅናቄ ሥራችን ላይ ትኩረት ከማድረግ ይልቅ በአፈፃም ምዘና ላይ ትኩረት

የማድረግ ዝንባሌዎች አልፎ አልፎ የሚታዩ መሆናቸው፤


ክፍል አራት
በንቅናቄው የሚሳተፉ አካላት ተግባርና ኃላፊነት
4.1 የክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት
ተግባር 1፡- በክ/ከተማ ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላትና ከወረዳዎች የዘርፉ አመራሮች ጋር በተለዩት ተግባራት
ላይ በመወያየት የጋራ ማድረግና እንደ መግባቢያ ሰነድ መፈራረም እና እቅዱን እንደ መመሪያ መጠቀም
ተግባር 2፡- ከሁሉም አደረጃጀት ተወካዮች (ከብሎክ ነዋሪ ፣ ከህብረት ሽርክና ጽዳት ማህበራት፣ ከሰፊቲ ኔት ፣
ከእድሮች ፣ ወጣትና ሴቶች ፣ የጸጥታ አካለት ፣ የኪነ ጥበብ ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ፣ የአርቲስት ፣ የስፖርት
ቤተሰቦች) በተለዩት ተግባራት በመወያየት የጋራ መግባባት መፍጠር፡፡
ተግባር 3፡- በየ 15 ቀናት ለሚካሄደው የሁሉን አቀፍ የከተማ ጽዳት ንቅናቄ ስራዎች የተመረጡትን ቦታዎች
በመለየትና በመያዝ ቅድመ እና ድህረ መረጃዎች በፎቶግራፍ እና በቪዲዮ አደራጅቶ መያዝ

ተግባር 4፡- በየ 15 ቀናቱ ሁሉም ወረዳዎች፣ ሦስት ወይም አራት ወረዳዎች እንደነባራዊ ሁኔታቸው

በተቀመጠላቸው ፕሮግራም መሰረት በክፍለ ከተማ ደረጃ የአንድ ማዕከሉን ንቅናቄ ያካሂዳሉ፤

ተግባር 5፡- በባለድርሻ አካላትና በህዝብ ተሳትፎ የተከናወኑ የንቅናቄ ስራዎችን በክ/ከተማ ደረጃ ከባለድርሻ
አካላትና በወረዳ ላይ ከሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ጋር መገምገምና አቅጣጫዎችን መስጠት

ተግባር 6፡- የጽዳት ንቅናቄ የተደረገባቸው ቦታዎች ተመልሰው እንዳይቆሽሹና ጽዳታቸው በዘላቂነት
እንዲጠበቁ ባለቤትነት እንዲፈጠርላቸው ከባለድርሻ አካላት ጋር ስምምነት መፍጠርና መረጃቸውን መያዝ፤

ተግባር 7፡- የአንድ ማዕከል ቦታ በማዘጋጀት የፌደራል እና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣
ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ የጸጥታ አከላት፣ የብሎክ
ነዋሪዎች፣ የጽዳት አምባሳደሮች፣ የሕብረት ሽርክና ማህበራት፣ የሴፍትኔት ተጠቃሚወች አንዲሳተፉ
ማድረግ፤

ተግባር 8፡- በየ 15 ቀናቱ ክፍለ ከተሞች በተቀመጠላቸው ፕሮግራም መሰረት ንቅናቄውን ሲያካሂዱ

አስፈላጊውን ከግብዓት ጭምር ሙሉ ዝግጅት ያደርጋሉ፤

4.2 የወረዳ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት


ተግባር 1፡- በወረዳ ደረጃ ከሚገኙ ባለድርሻ አካላትና ከብሎክ ተጠሪዎች የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በተለዩት

ተግባራት ላይ በመወያየት የጋራ ማድረግና እንደ መግባቢያ ሰነድ በመፈራረም እቅዱን እንደ መመሪያ

መጠቀም፤
ተግባር 2፡- የመንገድ ጽዳት ፈጻሚዎች፣ የህብረት ሽርክና ጽዳት ማህበራት አባላት፣ የሴፊቲኔት አባላት ጋር

በንቅናቄው ሂደትና ተግባራት ላይ በመወያየት ለንቅናቄው ዝግጁ ማድረግ፤

ተግባር 3፡- በደረቅ ቆሻሻና በአፈር የተሸፈኑ እና የተዘጉ የውኃ መውረጃ ቦዮችንና ቱቦዎችን፣ የቆሸሹ ክፍት

የሆኑ ማኑዋሎችን፣ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ የመንገድ

ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን፣ የድልድይ ስርና ዙሪያዎችን፣ የባቡር ሀዲድ መስመሮችን፣ ተርሚናሎችን፣ ክፍት

በሆኑ ቦታዎች ላይ በሕገ ወጥ የሚወገዱ ቆሻሻዎችን፣ ብሎኮችን በመለየትና በመምረጥ ለጽዳት ንቅናቄው

ዝግጁ በማድረግ የማህበረሰቡን ክፍል በማሳተፍ ማጸዳት፣ እንዲሁም የቦታውን ልዩ ስምና ከንቅናቄው በፊት

እና በኋላ ገፅታቸውን በፎቶግራፍ መረጃ መያዝ፤

ተግባር 4፡- የተጸዱ የውኃ መውረጃ ቦዮችንና ቱቦዎችን፣ የተጠገኑ ማኑዋሎችን፣ ብሎኮችን ወዘተ..ተመልሰው

እንዳይቆሽሹ ለብሎክ ተጠሪዎች ማስረከብ፤

ተግባር 5፡- በየ 15 ቀናቱ ወረዳዎች በተቀመጠላቸው ፕሮግራም መሰረት ንቅናቄው ሲያካሂዱ አስፈላጊውን

ሙሉ ዝግጅት ያደርጋሉ፤

ተግባር 6፡- በየ 15 ቀናቱ ሁሉም ብሎኮች እና መንግስታዊና መስንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተቀመጠላቸው

ፕሮግራም መሰረት ንቅናቄውን ያካሂዳሉ፤

4.3 የየካ ክ/ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቅርንጫፍ

ተግባር 1፡- በደረቅ ቆሻሻ እና በአፈር የተሸፈኑና የተዘጉ የውሃ መውረጃ ቦዮችና ትቦዎች፣ክፍት የሆኑ የቆሸሹ

ማንሆሎች መጽዳትና መጠገን እንዲቻል ይለያሉና ያጸዳሉ፡፡

ተግባር 2፡- የዋና መንገዶች እና በመለስተኛ ዋና መንገዶች ግራ እና ቀኝ ዳርቻዎች፣ አካፋዮችና አደባባዮች

ላይ አፈር፣ ጠጠር እና ድንጋዮች በመለየት ያነሳሉ፤

ተግባር 3፡- በፍሳሽ ማስወገጃ ውሰጥ የተጣሉና የተጠራቀሙ ቆሻሻ ከመጸዳቱ በፊት ግብዓቶችን (ለምሳሌ

ኤክስካቫተር፣ ገልባጭ መኪና እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶች) ያቀርባሉ፤

ተግባር 4፡- የተለዩ ቦታዎች በንቅናቄ ከጸዱ በኃላ ዳግም ቆሻሻ እንዳይጣልባቸው በዘላቂነት በሚጠበቅባቸውት

ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ይሰራሉ፡፡


4.4.የየካ ክ/ከተማ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት
ተግባር 1፡- በክፍለከተማው የሚገኙ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ

አካፋዮችን፣ የመንገድ ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን የተከማቹ ቆሻሻዎችን ይለያሉና ያጸዳሉ


ተግባር 2፡- በዋና መንገዶች እና በመለስተኛ ዋና መንገዶች ግራና ቀኝ ዳርቻዎች፣ የመንገድ አካፋዮች እና

አደባባዮች ከጸዱ በኃላ ተመልሰው እንዳይቆሽሹ በአረንጓዴ ልማት ማስዋብ

ተግባር 3. የወንዝ ዳርቻ መጠበቂያ ክልል(buffer zone) እንዲከበር ክትትል በማድረግ ጽዳቱም በዘላቂነት

እንዲጠበቅና ባለቤትነት እንዲፈጠርለት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መሥራት

ተግባር 4፡- የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ የመንገድ
ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን የፈረሱ አጥሮችን መልሶ እንዲጠገን ማድረግ

4.5. የየካ ክ/ከተማ ምግብ ዋስትና እና ልማታዊ ሴፍቲኔት ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

ተግባር 1፡- በአካባቢ ጽዳት የሚሳተፉ በሴፊቲኔት የተደራጁ ዜጎችን አስፈላጊውን መረጃ ይሰጣሉ እና
በጽዳት ንቅናቄው እንዲሳተፉ ያደርጋሉ፤

ተግባር 2፡- በጽዳት ንቅናቄዎች እንዲሳተፉ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን በባለቤትነት የሚያጸዱትን የመደበኛ
የጽዳት ቦታቸውን መረጃ ይይዛሉ፤

ተግባር 3፡- በተቀናጀና በእቅድ በመምራት ለከተማው ጽዳት ጉልህ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ በንቅናቄ ዋዜማ፣
ትግበራ እና በድህረ ንቅናቄ በባለቤትነትና በኃላፊነት የተሰጣቸውን ቦታዎች መጽዳታቸውን በማረጋገጥ
ከባለድርሻ አካላት በአጋርነት ይሰራሉ፤

4.6 የየካ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

ተግባር 1፡- በብሎክ ደረጃ የተደራጁትን የማ/ሰብ ክፍሎች በአከባቢ ልማት በተለይም በጽዳቱ ዘርፍ
በባለቤትነት እንዲሳተፉና ተገቢውን ሚናቸውን እንዲጫወቱ ያስተባብራሉ፣

ተግባር 2፡- ህብረተሰቡ የመኖሪያ አከባቢውን ጽዳት በባለቤትነት በመያዝ ዘላቂ የሆነ ማህበረሰባዊ ለውጥ
እንዲያመጡ ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር ይሰራሉ፣

ተግባር 3፡- የብሎክ ተጠሪዎች ማህበረሰቡን በማስተባበር መኖሪያ አከባቢን ጽዳት በባለቤትነት፣
በዘላቂነትና በቋሚነት እንዲጠብቁ ማህበረሰባዊ ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋሉ፤

ተግባር 4፡- በክ/ከተማችን ያሉ እድሮችን በማስተባበር በጽዳት ንቅናቄው ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፤
ተግባር 5፡- የተበላሹ የኮብልስቶን እና የጠጠር መንገዶች የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮችንና ቱቦዎችን ማህበረሰቡን
በማስተባበር እንዲጠገኑ ያደርጋሉ፤

4.7.የየካ ክ/ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት


ተግባር 1፡- በክፍለከተማው የሚገኙ የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ

አካፋዮችን፣ የመንገድ ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን የተከማቹ ቆሻሻዎችን ከሌሎች ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን


ያፀዳሉ

ተግባር 2፡- በዋና መንገዶች እና በመለስተኛ ዋና መንገዶች ግራና ቀኝ ዳርቻዎች፣ የመንገድ አካፋዮች እና

አደባባዮች ከጸዱ በኃላ ተመልሰው እንዳይበከሉ ከባለድርሻ ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን ይከላከላሉ

ተግባር 3፡- የወንዝ ዳርቻዎችን፣ የመንገድና የመንገድ ዳርቻዎችን፣ የመንገድ አካፋዮችን፣ የመንገድ
ማሳለጫዎችን፣ አደባባዮችን በአካባቢ ብክለት እንዳይበከሉ መቆጣጠር እንዲሁም በነከለው ላይ እርምጃ
መውሰድ

4.8. የየካ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

ተግባር 1፡- በአካባቢ ጽዳት የሚሳተፉ በደንብ ማስከበር ባለሙያዎች መረጃ ይሰጣሉ እና በጽዳት ንቅናቄው
እንዲሳተፉ ያደርጋሉ፤

ተግባር 2፡- በመንገድ ወይም በከመፀዳጃ ቤት ውጪ ሽንት መሽናት ወይም መፀዳዳጽ ይቆጣጠራሉ ይቀጣሉ

ተግባር 3፡- ለግንባታ ሆነ ለሌላ ጉዳይ የሚሆኑ ድንጋይ፤አሸዋ፤አፈር ወዘተ…መንገድ ላይ ማራገፍ


ይቆጣጠራሉ ይቀጣሉ

ተግባር 4፡-ሆን ብሎ በመፀዳጃ ቤት ፍሳሽን ከመንገድ ጋር ማገኛኘትና መልቀቅ ይቆጣጠራሉ ይቀጣሉ

ተግባር 5፡- አውቆም ሆነ በድንገተኛ ሁኔታ በድልድዮች፤በእግረኛ መከላከያዎች፤በማንሆሎች ፤ ወይም


በክዳኖቻቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ይቆጣጠራሉ እንዲሁም ይቀጣሉ

ክፍል አምስት

5.የንቅናቄ እቅዱ የሚመራበት አደረጃጀት


5.1. በክፍለከተማ
5.1.1.የአብይ ኮሚቴ አባላት
1. የክ/ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ጸ/ቤት ………ሰብሳቢ

2. የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስኪያጅ -------------------- ም/ሰብሳቢ

3. የመንገዶች ባለስልጣን የካ ክ/ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አሲኪያጅ ------------ጸሃፊ

4. የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ------አባል

5. የምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት ጽ/ቤት ሀላፊ ……………………………….አባል

6. የህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሀላፊ …………………………..አባል

7.አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ…………………………………………………………አባል

8. ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ………………………………………………………..አባል

5.1.2.የአብይ ኮሚቴው ተግባር እና ሃላፍነት


ተግባር 1፡- የንቅናቄውን አጠቃላይ ሂደት ይመራሉ፣ ይቆጣጠራሉ፣ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ፣

ተግባር 2፡- በቋሚ የግንኙነት ጊዜ በማስቀመጥ የንቅናቄውን አፈፃፀም ይገመግማሉ፣ አቅጣጫ ያስቀምጣሉ፤

ተግባር 3፡- ለንቅናቄው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ግብዓቶችን እየተከታተሉ እንዲሟሉ ያደርጋሉ፣

ተግባር 4፡- በንቅናቄው ሂደት የሚታዩና የሚያገጥሙ ችግሮችን በወቅቱ እንዲፈቱ ያደርጋሉ፣

ተግባር 5፡- አጠቃላይ የተደራጁ ኮሚቴዎችን አፈጻጸማቸውን እየተከታተሉ አቅጣጫ እና መመሪያ ይሰጣሉ፣

5.1.3.የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት


1.የየካ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የሚመደብ ተወካይ----------------------------ሰብሳቢ

2.የየካ ክ/ከተማ የግንዛቤ ስርጸትና ሕብረተሰብ ተሳትፎ ቡድን መሪ………………. ም/ሰብሳቢ

3.የአዲስ አባባ መንገዶች ባለስልጣን የካ ክ/ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተወካይ ……..….ፀሃፊ

4.የየካ ክ/ከተማ የተፋሰስና አረንጓዴ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ተወካይ………………አባል

5. የየካ ክ/ከተማ የመልሶ መጠቀምና ኡደት/ማ ቡድን መሪ……………………………አባል


6. የየካ ክ/ከተማ የደረቅ ቆሻሻ አገልግሎት ቡድን መሪ……………………….…..……አባል

7. የየካ ክ/ከተማ ምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍትኔት ጽ/ቤት ተወካይ …………….….አባል

8. የየካ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተወካይ ……………..……..አባል

9. አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ተወካይ…………………………………………………………አባል

10. ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ተወካይ………………………………………………………..አባል

5.1.4. የቴክኒክ ኮሚቴ ተግባር እና ኃላፍነት


ተግባር 1፡- የሁሉንም ወረዳዎች የንቅናቄውን አፈጻጸም ሂደት ይከታተላሉ፣ ይቆጣጠራሉ፣

ተግባር 2፡- የንቅናቄውን የመመዘኛ መስፈርቶችን ያዘጋጃሉ፣ መስፈርቶቹ የሚኖራቸውን ክብደት/ነጥብ

ያስቀምጣሉ፣ በየደረጃው ለሚገኙ መዛኝ አካላት በመስፈርቶቹ ላይ ኦረንቴሽን በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ

ያደርጋሉ፣

ተግባር 3፡- በምዘና የአፈጻጸም ሂደት የተገኘ ወይም የተገኙ ተሞክሮዎችን በመለየት መረጃዎችን

ያደራጃሉ/ይቀምራሉ፣

ተግባር 4፡- የተቀመጡትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን በመገምገም ለደካማ ጎኖቹ መስተካከላቸው

ይከታተላሉ፣ ይቆጣጠራሉ፤
ክፍል ስድስት

 6. ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረ-መልስ አግባብ


  በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር ክልለ ውስጥ የሚካሄደው የንቅናቀውን ሂደት ሶስቱን የክትትልና ድጋፍ

አግባቦች በመጠቀም በሚከተለው መልኩ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

6.1 ሪፖርት
  በንቅናቄው ሂደት የሚያጋጥሙትን ችግሮች ይለያሉ፣ ለሚመለከተው ሪፖርት በጹሑፍ ያቀርባሉ፣
 የንቅናቄ ስራዎችን አፈጻጸም ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማ ያደርጋሉ፣ ግብረ-መልስ በቃልና በፅሑፍ

ይሰጣሉ፡፡

 ንቅናቄው ከተጠናቀቀ በኋላ አጠቃላይ ሂደቱን ለምዘና ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባሉ፣ በግልባጭ ለቴክኒክ

ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባሉ፣

 የክፍለ ከተማ የምዘና ኮሚቴ ንቅናቄው ከተጠናቀቀ በኋላ አጠቃላይ ሂደቱን ለክፍለ ከተማው ቴክኒክ

ኮሚቴ እና በግልባጭ በወረዳ ደረጃ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ሪፖርቱን ያቀርባሉ፣

6.2. ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው


6.2.1 ተግዳሮቶች

 የንቅናቄው የጊዜ ሰሌዳ ከምርጫ ጋር አብሮ ማስኬድ አመራሮቹን በሚፈለገው ደረጃ ማሳተፍ አስቸጋሪ
ሊሆን ይችላል
 የግብዓት እጥረት ሊያጋጥም ይችላል፡፡
 የሚመለከታቸዉ አካላት በሚጠበቀዉ መልኩ ያለመቀናጀት ችግር ሊኖር ይችላል
 ዝናብ የጽዳት ስራዉን ሊያስተጓጉል ይችላል

6.3.ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሄ እርምጃዎች


 ንቅናቄውን ከምርጫ ተግባራት ጋር አስተሳሰስሮ ማስኬድ

 የግበዓት ችግርን ለመፍታት የተዋቀረው ኮሚቴ እንዲፈታ ማድረግ

 ስራዎችን በወቅቱ በመገምገም የቅንጅት ችግሮችን እየፈቱ መሄድ

6.4. የአፈጻጸም አቅጣጫዎች


o የባለድርሻ አካላት መዋቅር ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኘውን አመራሮች ባለሙያ እና የተለያዩ

አደረጃጀቶች ለንቅናቄው አወንታዊ ድርሻቸውን እና የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ በቅድሚያ


በቂ የሆነ ኦረንቴሽን መስጠት
o ለንቅናቄው ስኬታማነት ለወረዳዎች እና ለብሎኮች ንቅናቄውን የሚያስተባብሩ እና ክትትል፣ ድጋፍ፣

ግምገማና ግብረመልስ የሚሰጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ይመደባሉ


o በየደረጃው በተመደቡት አመራሮችና ባለሙያዎች መጽዳት ያለባቸው ቦታዎች በተቀናጀ፣ በተናበበ

በመለየት በየ 15 ቀናት እንዲፀዱ ይደረጋሉ፡፡


o በየደረጃው የተመደቡት አመራር እና ባለሙያዎች በየ 15 ቀናት የተከናወኑ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት

በየደረጃው ለተዋቀረው ቴክኒክ ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባሉ


o በየደረጃው የተመደቡት አመራሮች እና ባለሙያዎች ለንቅናቄው እቅድ አፈፃፀም በየ 15 ቀናት

ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማ እና ግብረመልስ በመስጠት በጉድለት የታዩ ችግሮች እንዲስተካከሉ


ይደረጋል፡፡
• ለወረዳዎች ክትትልና ድጋፍ የተመደቡ የክ/ከተማው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተግባራዊ

የሆኑ የንቅናቄ ሥራዎች በየሳምንቱ ንቅናቄውን እንዲመራ ለተቋቋመው የክ/ከተማው መዛኝ ኮሚቴ

ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

• የንቅናቄ እቅዱን አፈፃፀም በመከታተል፣ በመደገፍ፣ በመገምገምና ግብረ መልስ በመስጠት

ወዲያውኑ የእርምት እርምጃዎችን በመውሰድ ተልእኮውን ማሳካት

• የንቅናቄ እቅዱ ከታቀደ በኃላ ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ከአመራሩ እስከ ባለሙያው እንዲሁም

የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች ግልፅ የሆነ ኦሬንቴሽን እና መግባባት መፈጠር

• መፅዳት አለባቸው የሚባሉ ቦታዎች በተቀናጀ፣ በተናበበ የመለየት ስራ እንዲሰራ በየደረጃው እቅድ

በማዘጋጀት ወደ ተግባር መግባት

• አፈፃፀሙ ግንኙነት ግዜ ከማእከላት እንዲሁም ከታችኛው መዋቅር በመገምገም ለውጦቹ በማጎልበት

ጉድለቶቹን በማሻሻል ስራው ውጤታማ ማድርግ

• ወቅቱ የምርጫ ወቅት በመሆኑ ስራውን አስተሳሰስሮ መተግበር፡፡


የሁለት ወራት (ከግንቦት 14 እስከ ሐምሌ 14/201ዓ.ም) የሚከናወን የህዝብ ንቅናቄ የድርጊት መርሃ-ግብር

የነቅናቄ በየ 15 ቀን ንቅናቄውን ንቅናቄዉ የሚጸዱ ቦታዎች


ዙሮች በማዕከል ደረጃ የሚከናወንበት ከፍት ቦዮች ቱቦዎችበከ.ሜ የጥርጊያ መንገድ ብሎኮች የወንዝ ዳርቻ የመንገድ
የሚያከናውኑ ወረዳዎች ቀን በከ.ሜ ክፍት ቦዮች ጽዳት በከ.ሜ አካፋይ
በከ.ሜ
1ኛ 9 21/09/2013
10
2ኛ 3
28/9/213
4
3ኛ 5
6
12/10/2013
7
8
4ኛ 11
26/10/2013
12
5ኛ 1
10/112013
2
ድምር

You might also like