You are on page 1of 15

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ጽዳት

አስተዳደር ጽ/ቤት

የግንዛቤ ስርፀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የአካባቢ ንፅህና


ክትትል ቡድን

የ 2015 በጀት ዓመት የ 1 ኛ ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ሪፖርት

መስከረም/2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ክፍል አንድ

1
1.1 መግቢያ

አዲስ አበባ ከተማ የአገሪቱ እና የአፍሪካ መዲና ናት፣ የተለያዩ እህጉራዊና አለማቀፋዊ ተቋማት መቀመጫ እና
ተወዳዳሪ ከሚያደርጉት ጉዳዮች የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዋነኛው ነው፡፡ የከተማዋ አገራዊ ብሎም
አለማቀፋዊ ፋይዳ እያደገ በመምጣቱና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ማሕበራዊ ሚናዋ ከመጨመሩ ጋር ተበያያዘ የደረቅ
ቆሻሻ መጠን ማመንጨትም በፍጥነት እና በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ይገኛል፡፡ ከተማው አስተዳደሩም ለዘርፉ ልዩ
ትኩረት ሰጥቶ በተለያዩ ስትራቴጂዎች ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በ 2 ዐ 14 በጀት ዓመት እቅድ በማቀድ በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት የሕብረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማሳደግ
ከዋና ዋና ተግባራት የተከናወኑት የቤት ለቤት ግንዛቤ በመስጠት፣ እግዚቢሽን በማዘጋጀት፣ የስልጠና ግንዛቤ በመስጠት፣
የደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ በዓይነት በመለየት፣ በተለያዩ የሚዲያ የግንዛቤ ማስተላለፊያ መልዕክቶችን በማስተላለፍ እና
በወርሃዊ የፅዳት ንቅናቄ ሕብረተሰቡን በባለቤትነት እንዲሳተፍ በማድረግ በወረዳ ባሉት መዋቅር ከተማዋ ፅዱ፣ ውብ
ለኑሮ ምቹ ለመፍጠር በጀት ዓመቱ ከፍተኛ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

የወረዳዋን ፅዳት መንግስት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ብቻ እና ወር ጠብቆ ወርሃዊ የፅዳት ንቅናቄ የሚያደረገው
የሕብረተሰብ ተሳትፎ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይቻል በገንዘብ በዘርፉ ሁሉም ዜጐች በባለቤትነት
የሚያሳተፍ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ፅዳት ማርሽ ቀያሪ የንቅናቄ
እቅድ ማዘጋጀት “እኔ አካባቢዬን በማፅዳት የወረዳው ውበት አምባሳደር ነኝ” እና “የወረዳችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ
መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም” በሚሉ መሪ ቃሎች ሕዝባዊ ንቅናቄ ተካሂደዋል፡፡

በሁለት ምዕራፍ የተከፈለ የፅዳት ንቅናቄ በዘርፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካል የሆነው የደረቅ ቆሻሻ አመንጪ ነዋሪ
ማሕበረሰብ፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት፣ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ/ ተዋቂ
ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣ የፅዳት አምባሳደሮች እና የተለያዩ ተቋማት በፅዳቱ ቁልፍ ሚና
በመጫወታቸው የፅዳት ስራ የትኩረት ማዕከል እየሆነ መጥቷል ፡፡

በመሆኑም በግንዛቤ፣ፅርፀት ፣የሕብረተሰብ ተሳትፎና የአካባቢ ንፅህና ክትትል ቡድን የተጀመሩትን ተግባራት
ውጤታማነቱን ጠብቆ በ 2015 በጀት ዓመት በተጠናከረ መልኩ እየቀጠለ የሚገኝ ሲሆን የ 2015 በጀት ዓመት የ 1 ኛ
ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ሪፖርት እንደሚከተለው ተዘጋጅተው ቀርቧል፡

1.2ዓላማ
በግንዛቤ ማስጨበጫ እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የመጡ የባህሪ ለውጥ እና በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር
ዘርፍ ያደጉ የማህበረሰቡ ተሳትፎ እንዲሁም በባለቤትነት እንደሚሳተፉና አጠቃላይ በ 2015 በጀት ዓመት በ 1 ኛ ሩብ
ዓመት የተከናወኑ የክንውኖች ሪፖርት ለማቅረብ ነው፡፡
የሪፖርቱ አስፈላጊነት
 የታቀዱ እቅዶች መከናወናቸውን እና አለመከናወናቸውን በመግለጽ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡

2
 እቅዶች በሚከናወኑበት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለቀጣይ መፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ
ይጠቅማል፡፡
 የህብረተሰቡ ግንዛቤ አድጎ ከዘርፉ አንፃር የባህሪ ለውጥ በማምጣት ሁሉም ዜጋ በባለቤትነት እዲሳተፉ
በማድረግ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የእቅዱ አፈጻጸም ለሚመለከተው መላክ ወሳኝ በመሆኑ፣
 የህበረተሰቡን ግንዛቤና ተሳትፎ በማሳደግ ዘላቂ የሆነ የተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓቱን እንዲዘምን
የደረቅ ቆሻሻ አመንጪዎች፣ ነዋሪ ሕብረተሰብ፣ ባለድርሻ አካላትና አጋሮች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት
በተቀናጀ ሁኔታ ተሳትፎአቸውን አጎልብተው የሚጠበቅባቸውን የዜግነት ሚናቸውን እንዲጫወቱ ማድረግ
አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡
1.3 የሪፖርቱ ወሰን

በወረዳ 9 በጽ/ቤቱ በግንዛቤ ፅርፀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የአካባቢ ንፅህና ክትትል ቡድን፣ ባሉት በመዋቅራዊ
አደረጃጀቱ ቡድን በ 2014 በጀት ዓመት በ 1 ኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሆኑና ሪፖርት ከተደረገው የተጠመረ ነው፡፡

1.4 የሚጠበቁ ውጤቶች

በወረዳችን ያሉ ሁሉም የደረቅ ቆሻሻ አመንጪዎች ነዋሪ ማህበረሰብ፣ አጋሮችና ባለድርሻ አካላት በመተባበርና
በመግባባት ሁሉም በባለቤትነት በቅንጅት በመሳተፍ በዘርፉ ሁለንተናዊና ዘላቂ ለውጥ የሚያመጡትን ሚና በማወቅ
ለዘላቂ ለውጥ ሁኔታዎች ይመቻቻሉ፡፡

1.5 ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች


1.5.1 ራዕይ
በ 2017 አዲስ አበባ ፅዱ፣ ከደረቅ ቆሻሻ ሀብቷ ተጠቃሚና ለኑሮ ተመራጭ ከተማ ሆና ማየት፡፡
1.5.2 ተልዕኮ
የህብረተሰቡንና የአጋር አካላትን ተሳትፎ መሰረት በማድረግ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አሰባሰብ ስራን በመከታተልና
በመቆጣጠር በመሰብሰብ በማጓጓዝና የከተማዋን ነዋሪ ግንዛቤ እና ተሳትፎ በማሳደግ ዘመናዊና ዘላቂነት ባለው
መልኩ አገልግሎት በመስጠት ከተማዋን ጽዱ ማድረግ ነው ፡፡
1.5.3 እሴቶች /Values
 ዲሞክራሲያዊነት /ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ አሳታፊነትና ፍትሃዊነት/
 የላቀ አገልግሎት መስጠት
 ለለውጥ ዝግጁ መሆን
 በእውቀትና በእምነት መምራትና መስራት
 ስኬታማ ቲም
 ደረቅ ቆሻሻ ሀብታችን ነው
 ጽዱና ዘመናዊነት

3
 የሰው ኃይል ቀዳሚ ሀብታችን ነው
 የከተማ ጽዳት ቀዳሚ ተግባራችን ነው
1.6 የግንዛቤና የህብረተሰብ ተሳትፎ የነበሩ የትኩረት መስኮች
1.6.1 የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ
 የዘርፉ ሠራተኞች /የአቅም ግንባታ ስራዎች/
 የቤት ለቤት አባወራዎች /እማወራዎች/
 ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች
 መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት
 የንግድ ተቋማት
 የኃይማኖት ተቋማት
 ትምህርት ቤቶች እና
 የሠራተኞች የስራ ላይ ጥንቃቄና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ተዋረዳዊ
ስርዓት ትግበራ ላይ ትኩረት በማድረግ የግንዛቤ ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡
1.6.2 የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ
 ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ መቀነስ
 ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ መለየት
 በደረቅ ቆሻሻ ኡደት
 በደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም
 ሊበሰብስ ከሚችል ኦርጋኒክ ደረቅ ቆሻሻ የቀልዝና የባዮጋዝ ዝግጅት
 በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር የጎላ ተሳትፎ ማድረግ /በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በዓይነት እንዲሁም በጋራ
ጽዳት ላይ መሳተፍ እና መደገፍ/
 ከህገወጥ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ አንፃር የባህሪ ለውጥ በህብረተሰቡ ማምጣት
1.7 ስትራቴጂካዊ ውጤት
 የህብረተሰቡን ግንዛቤ እና ተሳትፎ በማሳደግ ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ የሚያስተዳድር እና ፅዳትን ባህል ያደረገ
ማሕበረሰብ በመፍጠር ዘላቂና የተቀናጀ በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ላይ ትውልድ ተሻጋሪ የሆነ የአስተሳሰብ፣
የባሕል ለውጥ ይመጣል፡፡

ክፍል ሁለት
2. የነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ ትንተና
2.1 የ 2015 በጀት ዓመት የ 1 ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም
በ 2015 የበጀት ዓመት በ 1 ኛ ሩብ ዓመት ተስፋ ሰጪ የሆኑ የፅዳት ስራዎችን ተሰርቷል፡፡ እነዚህ ስራዎችን አጠናክሮ
በማስቀጠል በተሻለ መልኩ ፅዱና ውብ ወረዳ እንድትሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጥረት የተደረገ ሲሆን በተለይም
የ 2015 በጀት ዓመት እቅድን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መግባባት ላይ በመድረስ ለበጀት ዓመቱ ተግባር ትኩረት
ተሰጥቶት ተሰርቷል፡፡ የወረዳው ነዋሪ በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ላይ ያለው ግንዛቤ እና ተሳትፎው አነስተኛ መሆኑ
በዘርፉ በፍጥነት መዘመን እና ወጥ የሆነ ለውጥ አለመታየት አንዱ እና ዋነኛ ችግር ነው፡፡ በመሆኑም በበጀት ዓመቱ
ውስጥ ወረዳው በተቀናጀ ሁኔታ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር በተለያዩ መንገዶች ግንዛቤ በመፍጠር እና ማህበረሰቡን
በቀጥታ ተሳታፊ በማድረግ ፅዱና ውብ ወረዳ እንድትሆን የግንዛቤና የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎችን ለማስፋፋት
ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የተሻለ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በወረዳችን ውስጥ ከሚኖሩት የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም በየቀኑ
መንግዶችን በማፅዳት ከሚሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ ለመልሶ መጠቀም የሚውለውን ከምንጩ በመለየት ቆሻሻን
በመቀነስና ወደ ሃብትነት በመቀየር፣ ለበርካታ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር ሰርተው እንዲጠቀሙ ከማድረጉም አልፎ

4
ወረዳዋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኝዎቿ ምቹና ጽዱ እንድትሆን በግንዛቤ እና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት
በርካታ ስራዎችን በበጀት ዓመቱ ለማከናወን ተሞክሯል ፡፡

በወረዳችን ፅዳት መንግስት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ብቻ እና ወር ጠብቆ ወርሃዊ የፅዳት ንቅናቄ በሚደረገው
የሕብረተሰብ ተሳትፎ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ እንደማይቻል በመገናዘብ ለዘርፉ ሁሉም ዜጎች በባለቤትነት
የሚሳተፍ ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከክፍለ ከተማ በጸደቀው እቅድ መሠረት
የወረዳው የንቅናቄ እቅድ በማዘጋጀት፣ “አካባቢዬን በማፅዳት የወረዳዬ ውበት አምባሳደር ነኝ” እና “የወረዳችን የፍሳሽ
ማስተላለፊያ መስመሮች የውሃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም” በሚሉ መሪ ቃሎች ሕዝባዊ ንቅናቄ
ስካሄድ እንደነበረ ሁሉ በ 2015 በጀት ዓመት በ 1 ኛ ሩብ ዓመት የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄው በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡
በሁለት ምዕራፍ የተከፋፈለ የፅዳት ንቅናቄ በዘርፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካል የሆነው የደረቅ ቆሻሻ አመንጪ ነዋሪ
ማሕበረሰብ፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት፣ የከተማ፣የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ/ ተዋቂ ግለሰቦች፣
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አርቲስቶች፣ የፅዳት አምባሳደሮች እና የተለያዩ ተቋማት ለፅዳቱ ቁልፍ ሚና
በመጫወታቸው በ 2015 በጀት ዓመት በነበሩን የተግባር አፈፃፀም የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራችን የትኩረት ማዕከል
እየሆነ መጥቷል ፡፡

2.2 በእቅድ አፈፃፀም ወቅት የነበሩ ጠንካራ ጎኖች


 የ 2015 በጀት ዓመት የ 1 ኛ ሩብ ዓመት እቅድ መታቀዱ
 የ 2014 በጀት ዓመት የ 1 ኛ ሩብ ዓመት የታቀደ እቅድ ከወረዳ ቡድን መሪዎች፣ ሰራተኞች እና ከሌሎች ባለድርሻ
አካል የጋራ የማድረግ ስራ መሰራቱ፣
 ሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄ በታቀደው እቅድ መሰረት ወደ ተግባር መግባቱ፣
 ክትትልና ድጋፍ ቼክሊስት በማዘጋጀት የወረዳ ባለሙያዎች በ 9 ኙም ቀጠናዎች የቅርብ ክትትልና ድጋፍ
ማድረጋቸው
 ለባለሙያዎች በተከፋፈለላቸው ብሎክ መሰረት ክትትልና ድጋፍ ማድረጋቸው፣
 የግንዛቤ ስራ እለት ተእለት ስራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በመዋቅሩ የሚገኙ ባለሙያዎች በተቀመጠው የቤት ለቤት
የግንዛቤ አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት በመስጠት ነዋሪው የሚያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ እንዲይዝ እና
አካባቢውን በየሳምንቱ እንዲፀዳ በማድረጋቸው፣
 ማህበረሰቡ ለአካባቢው ፅዳት የራሱን ሚና እንዲወጣ በገንዘብ፣ በዓይነት እና በጉልበት በዘርፈ እንዲሳተፍ
በማድረጋቸው፣
 በጀት ዓመቱ የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ መቻሉ
 በሕትመት ሚዲያ በመጠቀም 12 መልዕከት ማስተላለፍ ተችሏል፡፡

5
 ደረቅ ቆሻሻን በዓይነት በመለት፣ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ ለአጠቃላይ አባወራዎችን /እማወራዎችን
የቤት ለቤት ግንዛቤ ማስጨበጫ ማከናወን ተችሏል፡፡
 በወረዳችን ለተለያዩ አካላት በተቀናጀ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ሰርዓት ዙሪያ ለ--አባወራና እማወራዎች በተለያዩ
መደረኮች የግንዛቤ መሰጠቱ ፣
 ለነዋሪው የቤት ለቤት የግንዛቤ ትምህረት በመስጠት --ነዋሪዎች ኮምፖስት ስራ ማስጀመራቸው፡፡
 የወረዳችን ነዋሪ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሳምንታዊ ፅዳት ዘመቻ ላይ --ነዋሪዎች ማሳተፍ መቻሉ፡፡
 በወረዳ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ለወረዳ ፅዳት የሚውል ጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ከ - ብር በድጋፍ መገኘቱ
 በጀት ዓመቱ ትምህርት ተቋማት ተሳትፎ በማሳደግ በፅዳታቸው ሞዴልነታቸውን ማስቀጠል ተችሏል፡፡

2.3 በእቅድ አፈፃፀም ወቅት የነበሩ ደካማ ጎኖች

2.3.1 ከአመራሩ አንፃር

ሀ. ከአመለካከት አንፃር

 በሳምንታዊ የፅዳት ንቅናቄው ነዋሪው ሕብረተሰብ በሁሉም ቀጠና ሁሉም ነዋሪ ህብረተሰብ በነቂስ
በተመሳሳይ ወጥቶ ያለመሳትፍ፣

ለ. ከክህሎት አንፃር ያሉ ክፍተቶች

 ምርጥ ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ የተሰሩ ስራዎች በመለየት አለመቀመርና አለማስፋት

ሐ. ከግብዓት አንፃር የነበሩ ክፍተቶች

 በወረዳው ነባራዊ ሁኔታ ድጋፍ ሊያረጉ የሚችሉ ውስን ተቋማት መኖሩ

2.3.2 ከፈፃሚ አንፃር

ሀ. ከአመለካከት አንፃር የነበሩ

ለ. ከክህሎት አንፃር የነበሩ ክፍተቶች

 ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ አዳዲስ ዜዴዎችን ያለመጠቀም ውስንነቶች ይታየሉ፣

6
ክፍል ሦስት
3. የተከናወኑ የቁልፍ ተግባራት ግቦችና ዋና ዋና ተግባራት
3.1. የተከናወኑ የቁልፍ ግቦችና ተግባራት

በግንዛቤ ስርፀትና ህብረተሰብ ተሳትፎ ስራ ሂደት/ቡድን/ የግንዛቤ አሰጣጥ ለማሻሻልና የህብረተሰብ ተሳትፎ ለማጐልበት የሪፎርም
ሥራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ሠራተኞችን በተቀናጀ ሁኔታ በመምራት እና የተደራጀ አቅም በመፍጠር ተልዕኮን ስኬታማ ሆኖ
በተጠናከረ ሁኔታ በማስቀጠል ላይ ይገኛል፡፡ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ህብረተሰቡ በባለቤትነት እንዲሳተፍ ለማድረግ ከፍተኛ
ጥረት እያደረገ ነው፡፡
በ 2015 በጀት ዓመት የህብረተሰብ ግንዛቤንና የተሳትፎ ግቦችና ተግባራትን በተቀመጠላቸው ስታንዳርድና ከዚያም በላይ መሄድ
የሚያስችሉ የለውጥና የሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ግንዛቤን በማሳደግ በዘርፉ ላይ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ
ሁለንተናዊና ዘላቂ የሆነ ለውጥ ማምጣት ዋናው የስረ ሂደቱ/ቡዱኑ/ ትኩረት ሆኗል፡፡ የማህበረሰቡን ግንዛቤ የሚያገለብቱና በዘርፉ
ተሳትፎኣቸውን የሚያሳድጉ ተግባራትን የሚያከናውኑ ተልዕኮን የሚቀበሉ በጋራ ተግባብተውና ተባብረው ከሚጠበቀው በላይ
የሚፈፅሙ ቲሞች ተደራጅተው በተጠናከረ ደረጃ ስር-ነቀል ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልክ በኤጀንሲው በሁለት ቲሞች
ተደራጅተዋል፡፡ የግልና የቲም አቅም ግንባታም በቲም በመሥራት የሚታዩ የአስተሳሰብ፤ የዕውቀትና የክህሎት ችግሮችን በመፍታት
የስረ ሂደቱ ብሎም የጽ/ቤቱ አፈፃፀም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ተግባራት ለማከናወን የራሰን አቅም መገንባት ፤እርስ በርስ
በመማርና የልምድ ልውውጥ በማድረግ እንዲሁም አጫጭር ሥልጠናዎችን ለሠራተኞች በመስጠት በዘርፉ ሁለንተናዊና ዘላቂ
ለውጥ በማምጣት የግልና የቲም እንዲሁም የጽ/ቤቱ ብቃት ማጐልበት የሚያስችል ልዩ ትኩረት ተሰቷል፡፡
ማህበረሰቡን ግንዛቤ እና ተሳትፎ አሁን ካለበት 93% ወደ 95% በማሳደግ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ የሚያስተዳድርና
ጽዳትን ባሕል ያደረገ ማህበረሰብ ለመፍጠር በርካታ እንቅስቃሴዎች አሉ

7
የ 2 ዐ 14 በጀት ዓመት እቅድ ኦረንቴሽን አሰጣጥን በተመለከተ

3.2 በእቅድ ኦረንቴሽን መገኘት ያለበት የሰው ኃይል ብዛት /አመራር፣ ባለሙያ ፣ባለድርሻ አካላት

ተ.ቁ ተሳታፊዎች መገኘት ያለበት ተሳታፊ ብዛት የተገኙ ተሳታፊ ብዛት


ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ንጽጽር በመቶኛ
1 የወረዳ አመራር
2 የወረዳው ባለሙያ
3 የመንገድ ጽዳት ፈፃሚ
4 ባለድርሻ አካላት
5 ህዝብ ክንፍ
6 ተገልጋይና የብሎክ አደረጃጀቶች
ድምር
በእቅድ ኦረንቴሽኑ የተነሱ ጥያቄዎች፣ ሀሳቦችና የተደረሰባቸው መደምደሚያዎች ተተንትኖ እቅዱ ይከለሳል
3.3 የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አፈፃፀም ሁኔታ በሰንጠረዥ
3.3.1 የለውጥ ቡድንና የ 1 ለ 5 /ሞርኒንግ ብሪፊንግ/ አደረጃጀትን ከማጠናከር አኳያ የተከናወኑ ተግባራት

ተ.ቁ መደራጀት ያለበት የለውጥ ቡድን የተደራጀ የለው ቡድን ብዛት መደራጀት ያለበት የ 1 ለ 5 የተደራጀ የ 1 ለ 5
ብዛት አደረጃጀት ብዛት አደረጃጀት ብዛት
1 ወ ሴ ድ
10 6 16 1 1 3 3

3.4 . የተቋሙን ሰራተኞች የመፈፀም አቅም ለማሳደግ የተሰጡ ስልጠናዎችን በተመለከተ


3.41. ስልጠና ያገኙ አመራርና ባለሙያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በ 2015 በጀት ዓመት የስልጠና እቅድ
በስልጠናው በስልጠናው

ንጽጽር በመጾኛ
የሚሳተፈው የሚሳተፈው
ተ. የሚካሄድበት የቀን ድግግ
ስልጠናው ተሳታፊ አካላት የሚሰጠው የስልጠና አይነት ሰው ብዛት ሰው ብዛት
ቁ ጊዜ ብዛት ሞሽ
እቅድ እቅድ ክንውን

የጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ የጽዳት የ 2014 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም፣ መስከረም/


1 ሽርክና ማህበር፣ ባለድርሻ አካላት፣ የ 2015 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት እና ጽ/ቤቱ 1 1 200
2015 በጀት ዓመት
ህዝብ ክንፎቻችን፣ተገልጋዮች የሚሰጣቸው አገልግሎቶችን የተዘጋጀው ቲም ቻርተር
ለህዝብ ክንፍ ይፋ በማድረግ ስምምነት መፍጠር

3 መሰረታዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አስተዳደር ዙሪያ ጥቅምት/ 2 1 75


የጽ/ቤቱ ሰራተኞች 2015 በጀት ዓመት
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ የጽዳት መሰረታዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ አስተዳደር እና ጽዱ
4 ሽርክና ማህበር፣ ባለድርሻ አካላት፣ ማራኪ የሆነ ሞደል ብሎክ እና ተቋማት መፍጠሪያ ህዳር/2015 1 1 100
ህዝብ ክንፍ እና ተገልጋዮች ዘዴዎችን በተመለከተ በጀት ዓመት

ህብረተሰብ ተሳትፎ ጋር ተያይዞ የነዋሪዎች ፣


5 የብሎኮች አስተባባሪዎች፣ የተቋማት 1 1 150
የተቋማት ተወካዮች እና ሚናን እና ሃላፊነታቸውን ከህግ ማዕቀፎች ጋር ታህሳስ/2014
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች በማነጻጸር በጀት ዓመት
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እና የደረቅ
6 ቆሻሻ መሰብሰብ ህብረት ሽርክና 2 1 35
የተሻሉ ክ/ከተማ እና ወረዳ በመለየት ታህሳስ/2015
ማህበር
ልምድ ልውውጥ ማድረግ በጀት ዓመት
በወረዳው ውስጥ ያሉ የት/ቤቶች በት/ቤቶች አካባበቢ የአካባቢ ጥበቃ እና ክብካቤ ክበባት
7 ክበባት አባላት እና የት/ቤቱ 1 1 150
በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አካባቢ ጽዳት እና ማራኪ እና ጥር/2015
ማህበረሰብ ውብ ከማድረግ ዙሪያ ሚናቸወን በተመለከተ በጀት ዓመት

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣የጽዳት
8 ሽርክና ማህበር፣ ባለድርሻ አካላት፣ የ 2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት 1 1 150
ህዝብ ክንፎቻችን፣ተገልጋዮች እቅድ አፈጻጸም ውይይት እና ስልጠናዊ ግምገማ ጥር/2015 በጀት
ማካሄድ ዓመት

9 የጽ/ቤቱ ሰራተኞች መሰረታዊ ኮምፕተር ፣ የመረጃ አያያዝ እና የካቲት/2015 5 1 35


አደረጃጀት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ በጀት ዓመት

የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እና የደረቅ


10 ቆሻሻ መሰብሰብ ህብረት ሽርክና የተሻሉ ክ/ከተማ እና ወረዳ በመለየት 2 1 35
ማህበር ልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ ተሞክሮ ቅመራ እና መጋቢት/2015
ማስፋት ሰነድ ዘግጅት በጀት ዓመት
የጽ/ቤቱ ሰራተኞች፣ ባለድርሻ
11 አካላት፣ በጽ/ቤቱ ስር ስለሚከናወኑ የተለያዩ መመሪያዎች እና ሚያዚያ/2015 2 1 150
ህዝብ ክንፎቻችን፣ተገልጋዮች ደንቦች በጀት ዓመት  

ድምር 14   26 14 1222

3.5 መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ


3.6 ግንባር ቀደም ሰራተኞችን ከማፍራት አኳያ የተከናወኑ ተግባራት

ግንባር ቀደም ሆነው የተለዩ ሰራተኞች ብዛት ግንባር ቀደሞችን ለመለየት ጥቅም ላይ የዋለ መስፈርት

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
እቅድ ክንውን
በወረዳ በወረዳ ስራዎችን ከጠባቂነት በመውጣት በሀላፊነት ከመስራት አኳያ
ተ.ቁ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ
10 6 16 10 6 16
3.7 የኪራይ ሰብሳቢነትን ከመታገል አኳያ የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ
ተ. የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባራት ፈጽመው የተገኙ ሰራተኞች ብዛት የተወሰደ እርምጃ ተፈጽሞ የገኘው የስነ
ቁ ምግባር ጉድለት ቢገለጽ
ማስጠንቀቂያ ከኃላፊነት የወረደ ከስራ የተሰናበተ
ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ ወ ሴ ድ
1

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
ክፍል አረት
4.2 የአበይት ተግባራት ግቦችና ዝርዝር ተግባራት

ከተገልጋይ/ህዝብ እይታ መስከ አንጻር


3.1. የአበይት ተግባራት ግቦች፤አላማዎች እና ዝርዝር ተግባራት
ግብ 1 የማህበረሰቡን ግንዛቤ እና ተሳትፎ አሁን ካለበት 70% ወደ 75% በማሳደግ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ
የሚያስተዳድርና ጽዳትን ባሕል ያደረገ ማህበረሰብ መፍጠር
አላማ 1 ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዙርያ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ከ 70%ወደ 75% ማሳደግ
ዋና ዋና እና ዝርዝር ተግባራት
ተግባር 1. በዓመት 4936 ህብረተሰብን በጽዳት ንቅናቄ በየሳምንቱ 1250 ማሳተፍ፣ እቅድ 4936 ክውን 16013 ንፅፅር
100%
ተግባር 2 ሁሉንም ተቋማትን በሳምንታዊ የዓርብ ጽዳት ንቅናቄ 22 ማሳተፍ እቅድ 22 ክውን 22 ንፅፅር 100%
ተግባር 3. 14 ብሎኮችን በጽዳታቸው ሞዴል እንዲሆኑ ማድረግእቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 4. 2 ትምህርት ቤቶችን በጽዳታቸው ሞዴል ማድረግ እቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 5. 1 የወረዳ ጽ/ቤቶችን በጽዳታቸው ሞዴል ማድረግና ሞዴልነታቸውን ማስቀጠል እቅድ ክውን ንፅፅር
ተግባር 6. 1 የሃይማኖት ተቋማትን በጽዳታቸው ሞዴል ማድረግ እቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 7. 101412 በወረዳ ደረጃ ከህብረተሰቡ ተሳትፎ በአይነት ወይም በገንዘብ የሀብት ማሰባሰብ እቅድ 10000 ክውን
9960 ንፅፅር 100%
አላማ 2 በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ላይ የማህበረሰብን ግንዛቤ ከ 70 ወደ 75 ማሳደግ
ተግባር 1. በደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣አጠቃቀምና አወጋገድ ላይ ለ 4936 አባወራዎች /እማወራዎች የቤት ለቤት ግንዛቤ
መፍጠር፤ እቅድ 1233 ክውን 1778 ንፅፅር 100%
ተግባር 2. የቤት ለቤት ግንዛቤ የሚሰጣቸው አባወራና እማወራ መረጃ በጾታ፤ በእድሜ መቶ ፐርሰንት ማደራጀት እቅድ
1233 ክውን 1778 ንፅፅር 100%
ተግባር 3. 1826 አባወራዎች /እማወራዎች/ ደረቅ ቆሻሻን ከምንጩ በስታንዳርድ መሠረት እንዲለዩ ማድረግ እቅድ 456
ክውን 1238 ንፅፅር 100%
ተግባር 4. 271 አባወራዎች /እማወራዎች/ የቤት ለቤት ቀልዝ እንዲያመርቱ ማድረግ እቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 5. ግንዛቤ የሚያጐልብቱ የተለያዩ 1 ኩነት (ቶክሾው፣ ፓናል ውይይት) ማዘጋጀት እቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 6. በደረቅ ቆሻሻ ዙሪያ ባለድርሻ አካላትንና የተለያዩ አደረጃጀቶችን በማስተባበር 1 ጊዜ ትምህርታዊ ጉብኝት
ማዘጋጀትና ተግባራዊ ማድረግ እቅድ ክውን ንፅፅር %

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
ተግባር 7. በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ወይም በማህበራዊ ሚዲያ 52 የግንዛቤ ማስጨበጫ
መልዕክቶችች ማስተላላፍ እቅድ 4 ክውን 4 ንፅፅር 100%
ተግባር 8. በህትመት ሚዲያዎች 13 የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን ማስተላለፍ እቅድ 9 ክውን 9 ንፅፅር 100%
ተግባር 9. በወረዳ አቅም 200 ለሚሆኑ ለተለያዩ አካላት በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ስርዓት ዙሪያ የግንዛቤና
ስልጠና መስጠት እቅድ 100% ክውን 100% ንፅፅር 100%
ተግባር 10. ለተለያዩ አካላት የተሰጡ ስልጠናዎችን መቶ ፐርሰንት መረጃ በጾታ፣ በስልጠናው ዓይነትና ርዕስ ማደራጀት
እቅድ 100% ክውን 100%ንፅፅር 100%
አላማ 3 የለውጥና ሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ማሳደግ
ተግባር 1. በዘርፉ ያለ የክህሎት፣ የዕውቀትና የአመለካከት ክፍተት መለየት እቅድ 100% ክውን 100% ንፅፅር 100%
ተግባር 2. የአመለካከት ለውጥ፣ ክህሎትን ለማሳደግና የግብኣት አጠቃቀምን ለማሻሻል 2 ጊዜ አጫጭር ስልጠናዎችን
በመስጠት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን እቅድ 1 ክውን 1 ንፅፅር 100%
ተግባር 3. በስርዓተ ጾታና ኤች.አይ.ቪ ሚኒስትሪንግ ላይ 2 ጊዜ ስልጠና መስጠት እቅድ ክውን ንፅፅር %
ተግባር 4. በአቻ ለአቻ ፎረም አደረጃጀት በየሳምንቱ ውይይት ማካሄድ እቅድ 100 ክውን 100 ንፅፅር 100%
ተግባር 5. 2 ምርጥ ተሞክሮዎችን መቀመርና ማስፋት እቅድ ክውን ንፅፅር %
አላማ 4 የሙስናና ብልሹ አሰራሮችን 100 %መከላከል
ተግባር 1 የሙስናና የብልሹ አሰራር ምንጮችን 100% መለየት እቅድ 100 ክውን 100 ንፅፅር 100%
ተግባር 2 የሙስናና ብልሹ አሰራር ምንጮች ማክሰሚያ 1 ሰነድ ማዘጋጀት እቅድ 1 ክውን 1 ንፅፅር 100%
ተግባር 3 በብልሹ አሰራር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ 100% ተግባራዊ ማድረግ እቅድ ክውን
ንፅፅር %
አላማ 5 የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ስርዓትን ማጠናከር
ተግባር 1 በቼክሊስት የተደገፈ በሳምንት 2 ጊዜ የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ማካሄድ እቅድ 1 ክውን 1 ንፅፅር 100%
ተግባር 2 የክትትልና ድጋፍ ግብረ መልስ በጽሑፍ 12 ጊዜ መስጠት/በወር አንድ ጊዜ/ እቅድ 100 ክውን 1 ንፅፅር 100%
ተግባር 3 የክትትልና ድጋፍ ፋይዳ ግምገማ ሰነድ እናየሱፐርቪሽን ግብረ መልስ 4 ጊዜ መስጠት እቅድ 1 ክውን 1 ንፅፅር
100%
ተግባር 4 በዓመት ሁለት ጊዜ በ 6 ወር 1 ጊዜ ምዘና ማካሄድ እቅድ ክውን ንፅፅር %

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
ክፍል አምስት
5.ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮችና (Challenges) እና የተወሰዱ መፍትሄዎቻቸው
5.1 ያጋጥሙን ችግሮች
 ሁሉም ነዋሪዎችና ተቋማት በየቀጠናውና በየመንደሩ በተመሳሳይ የጽዳት ዘመቻ ላይ እኩል ያለመሳተፍ
ችግሮች
 በጽዳት ዘመቻ የጸዳት በግዜው ማንሳት ላይ የመኪና ስምሪት ችግር
 የብሎክ አደረጃጀት መሪዎች በተለያዩ ስራዎች ምክንያት የማስተባበር ክፍተት
 ነዋሪው አልፎ አልፎ ለብሎክ መሪዎች አለመታዘዝ ችግሮች
 ለባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች የተለያዩ ስልጠናዎችና ንቅናቄዎችን ለመፍጠር የበጀት እጥረት 5.2
ችግሮቹን ለመፍታት የሚወሰዱ መፍትሄዎች
 ሁሉም ነዋሪዎችና ተቋማት በየቀጠናውና በየመንደሩ በተመሳሳይ የጽዳት ዘመቻ ላይ ያለመሳተፍ ችግር
ለመቅረፍ ባለሙያዎች ቅንጅታዊ አሰራሮችን አጠናክሮ በተመደቡበት ቀጠና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም
ማሳካት ተችሏል፡፡
 በጽዳት ዘመቻ የጸዳት በግዜው ማንሳት ላይ የመኪና ስምሪት ችግር እንዳይከሰት ከሚመለከተው አካ ጋ
በቅርበት በመናበብ ላይ እንገኛለን፡፡
 የብሎክ አደረጃጀት መሪዎች በተለያዩ ስራዎች ምክንያት የማስተባበር ክፍተት እንዳያጋጥመን ሁኔታዎችን
የጊዜው ማቻቻል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
 ነዋሪው አልፎ አልፎ ለብሎክ መሪዎች አለመታዘዝ እንዳይከሰት በቡና ጠጡና በተለያዩ ዘዴዎች ግንዛቤ
እየተፈጠረና እየተፈታ ይገኛል፡፡
 ለባለድርሻ አካላት የተለያዩ ስልጠናዎችና ንቅናቄዎችን ለመፍጠር የበጀት እጥረትን ለመቅረፍ
ከክ/ከተማ፣ከወረዳውና ከጽ/ቤቱ ጋር በመነጋገር ስልጠናው በሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በሂደት ላይ ነን፡፡

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት
5.3 በቃልና በፅሁፍ የተሰጡ ግብረ መልሶች
በየ ሩብ ዓመቱ ቼክሊስቶችን በማውረድ በዓመት 4 ጊዜ ግብረመልሶችን የመስጠት ስራ ይሰራል፡፡
5.4 በቃልና በፅሁፍ ግብረ መልሶች ከተሠጡ በኃላ የተሻሻሉ ጉዳዮች መልሶ ማየት
ለቀጣይ መስተካከልና ማሻሻል የሚገባቸው ደግሞ በማየት የማሻሻል ስራ ተሰርቷል፡፡

ምዕራፍ ስድስት

6. ማጠቃለያ፡- ባለፉት ዓመታት እና ወራት ውስት የተጀመረውን የህዝብ ንቅናቄ መድረኮችን እየተካሄደ ቆይተዋል፡፡ ይሄም
አጠናክሮ ለማስቀጠልና የማሳካት ዙርያ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር በመዋቅራችን የህዝባችን የልማት ፍላጎት ጋር አስተሳስሮ
የማስከድ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በተለይም ግንዛቤ ስራዎችን አስመልክቶ የቤት ለቤት በቡና ጠጡ እና በየቀጠናዎች በተዘጋጁት በህዝብ ውይይት መደረኮች ላይ ሰፊ
ግንዛቤ መፍጠር ስራ እየተሰራ ነው፡፡ ነዋሪው አካባቢውን ፅዱ ውብ ለኑሮ ምቹ በማድረግ የራሱን ሚና እንዲወጣ በኔነት ስሜት
ባለው አቅም ሁሉ በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸውና በሃብታቸው እንዲሳተፉ ሰፊ መግባባት እንዲፈጠር ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

በትምህርት ቤቶችም ላይ ክበባትን በማቋቋም በግንዛቤና በተሳትፎ ሰፊ ስራ ተሰርተዋል፡፡ በፅዳት ስራ ላይ በእስትራቴጅክ ዘመኑ
በመደበኛ ሳምንታዊ እና በልዩ የጽዳት ዘመቻ ስራ ህብረተሰቡ ተሳትፎ እየተሻሻለ ይገኛል፡፡

በስትራቴጅው ዘመን የተያዘውን የደረቅ ቆሻሻ ከምንጩ የመለየት፣ ለመልሶ መጠቀም ስራዎች የተለዩ ደረቅ ቆሻሻዎችን ወይም
እቃዎችን የሚወስድ ድርጅቶች ጋር በማቀናጀት የመልሶ መጠቀም ስራዎቻችንን ደረጃቸው እንዲያድግ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 9 ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት የግንዛቤና ህብረተሰብ ተሳትፎ ዋና የስራ ሂደትሪፖርት

You might also like