Professional Documents
Culture Documents
Ministry of Urban & Infrastructure
Ministry of Urban & Infrastructure
የከተሞች መስፋፋት ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እያደገ በመምጣቱና የህዝብ ቁጥሩም በዛው ልክ እያሻቀበ በመምጣቱ
ከከተማ ነዋሪው ህዝብ የሚመነጨው የቆሻሻ መጠንም ከሚገመተው በላይ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ይህን ተጽዕኖ ለመቋቋም
ቆሻሻን በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ በማዋልና የከተማ አረንጓዴ ቦታዎችን በማልማት ጎጂ ተጽኖዎችን መቋቋም
ይቻላል፡፡
የከተማ አረንጓዴ ቦታዎች ለሥነ-ምህዳር አገልግሎት አቅርቦት አስፈላጊ በመሆናቸው የከተማ ውበትን፣ የህብረተሰብ
ጤና እና ደህንነትን ለማሻሻል ትልቅ ሚና አላቸው፡፡
የከተማ መናፈሻዎችም ለነዋሪዎች ቅርበት ባላቸው አካባቢዎች ለምተው ለብዙዎች ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ
በሰው ልጅ ጤና እና ደህንነት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ከፍተኛ ጥቅም አላቸው፡፡
ከመኖሪያ ቤቶች አጠገብ ወይም በዙሪያው ያሉ የግል ቦታዎች በተለያዩ የሣር ሜዳዎች፣ የጌጣጌጥ እና የአትክልት
ቦታዎች ቢሸፈኑ ለነዋሪዎች እፎይታን ከመስጠታቸው ባለፈ የአካባቢን ስነ-ምህዳር ለመቀየር ትልቅ አስተዋጽኦ
አላቸው፡፡
የከተማ ጓሮዎች የተለያዩ የባህልና የአካባቢ አገልግሎቶች እንዳሏቸው ይታወቃል። የአካባቢ አየር ማቀዝቀዣን
ያሻሽላሉ፤ ጎርፍን ለመቀነስ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግና ከጭንቀት እረፍትን ለማግኘት የሚያስችል አቅምን
ይፈጥራሉ፡፡ ስለሆነም በከተሞች አካባቢ ያለውን የብዝሃ ህይወት ለመጠበቅ የግል ጓሮዎች እና የከተማ መናፈሻዎች
ንጽህናቸው ተጠብቆ እና ለምተው ለብዙ ሰዎች ትልቅ ስሜታዊና ስነ-ልቦናዊ ፈውስ እንዲያመጡ ማድረግ የሁሉም
የከተማ ነዋሪ ተግባር ሊሆን ይገባል የሚለውን መልዕክታችንን እያስተላለፍን መረጃ ለመስጠት በሚኒስቴር መ /ቤታችን
በከተማ አመራር፣ ፋይናንስና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ፣ የከተሞች ጽዳትና የአረንጓዴ ልማት ማኔጅመንት ዴስክ
የተዘጋጀውን መረጃ ሰጪ ጽሁፍ እንድታነቡና ተግባራዊ ምላሽ እንድትሰጡ ጋብዘናችኋል፡፡
መልካም ንባብ!
ክፍል አንድ
መነሻ ሀሳብ
ክፍል ሁለት
የ 20/50 ሜትር ራዲየስ የፅዳት ስራ ማለት በከተሞች በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ውስጥ
የሚካተት ተግባር ሆኖ ሁሉም መኖሪያ ቤቶች ግቢያቸውንና አካባቢያቸውን እስከ 20 ሜትር ራዲየስ ድረስ፣
ተቋማት ደግሞ ግቢያቸውንና አካባቢያቸውን እስከ 50 ሜትር ራዲየስ ድረስ ፅዱና ውብ የሚያደርጉበት
የአሰራር ስልት ነው፡፡
ስራው በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ በከተሞቻችን ያለውን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ችግር
ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ የተፈጠረ የስትራቴጂክ እቅዶች ማስፈፀሚያ ስልት ሲሆን ሁሉም ነዋሪዎች እና
ተቋማት ግቢያቸውንና አካባቢያቸውን ፅዱና ውብ ካደረጉ ከተሞች በሙሉ ከቆሻሻ የፀዱ፣ ውብ ገፅታ
ያላቸው፣ ለሥራ፣ ለኑሮ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቭስትመንት ምቹ ያደርጋቸዋል ከሚል እሳቤ የተነሳ ሀሳብ ነው፡፡
መግቢያ መልሶ ዑደት የሚደረግ ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ ሳይለይ በሚወገድ ደረቅ ቆሻሻ የሚፈጠረውን ጉዳት
ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡
አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በማስተዳደር፣ በመያዝ እና እንደ ጥሬ እቃ በመጠቀም
ለመልሶ ዑደት በተቀናጀ ሁኔታ እየሰሩ አይደለም፡፡
መልሶ-ዑደት ማድረግ የደረቅ ቆሻሻ መጠን የመቀነስ አቅም አማራጭ በመሆኑ ከ 80-90 በመቶ ከጠቅላላው
የቆሻሻ ይዞታ ይቀንሳል፡፡ መልሰው ዑደት የማይሆኑት ቆሻሻዎች ብቻ ወደ ማስወገጃ ቦታ ይወገዳሉ፡፡
ደረቅ ቆሻሻን መልሶ ዑደት ማድረግ ማለት የአገልግሎት ጊዜውን ጨርሶ አይጠቅመንም ብለን
የምናስወግደውን ቆሻሻ መልሶ በማደስ ወደ ሌላ አዲስ ምርት የመቀየር እና የማምረት ሂደት ነው፡፡
መልሶ ዑደት ማድረግ የሚለቀቅ የግሪን ሀውስ ጋዝ መጠንን በመቀነስ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመከላከል
መልሶ ዑደት ማድረግ የስራ እድል ከመፍጠሩም በላይ ጠቀሜታ አለው፡፡ በአሜሪካ ያገለገሉ፣ የማይፈለጉ እና
ጊዜ ያለፈባቸው ወይም ያረጁ እቃዎችን በመጠቀም እያንዳንዱን ለመልሶ ዑደት ማድረግ የቀልዝ ስራን
ጨምሮ ይሰራሉ፡፡
የምግብ ትርፍራፊ፣ ልብስ፣ ወረቀት፣ ብርጭቆ፣ ፕላስቲክ፣ ቦርሳ እና ሻንጣ፣ ብረታ ብረት፤ ወረቀት፣ የታሸጉ
እቃዎች፣ ቆርቆሮ፣ ጠርሙስ ወዘተ.
መሰብሰብ
መለየት
ወደ አዲስ ምርት
መቀየር
የዕቃውን መለያ ማስወገድ፣
በውኃ ለቅለቅ በማድረግ ማጠብና መቆራረጥ
ማድረቅ
በማንሳፈፍ መለየት