You are on page 1of 2

ክ/ከተማ ------------------------------------ ቦሌ ከ/ክተማ

ወረዳ ------------------------------------ 17

ቀበሌ ------------------------------------- 24

ጥናቱ የሚያካትታቸው ቤቶች ---የፍሳሽ መስመራቸው ከቤት ቁጥር 1324 እስከ ቤት ቁጥር 1419

የሚደርስ (ባጠቃላይ 48 መኖሪያ ቤቶች)

መግቢያ
ከላይ የተጠቀሱት ከቤት ቁጥር 1324 ጀምሮ እስከ ቤት ቁጥር 1419 ያሉ የኮርፖሬሽናችን ይዞታ የሆኑ ቤቶች የፍሳሽ
መስመር ቀድሞ ተገናኝቶባት የነበረው የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ሴፕቲክ ታነከር በማለያየት ከመሬቱ አቀማመጥ አንጻር
አመቺ በሚሆነው ከቤት ቁጥር 1324 እስከ ቤት ቁጥር 1331 ባሉ የፊት ለፊት ቦታዎች ላይ ለ የ 12 ቤቶች ተመጣጣኝ
የሆነ አንድ ሴፕቲክ ታንከር ባጠቃላይ ለ የ 12 ቤቶች አንድ ሴፕቲክ ታንከር በጥቅሉ ለ 48 ቤቶች 4 ሴፕቲክ ታንከር
ማዘጋጀት፡፡

ነባራዊ ሁኔታ
ከላይ የተገለጹት መኖሪያ ቤቶች የፍሳሽ መስመር አሁን ባለው እና ቤቶቹ ካሉበት የመሬት አቀማመጥ የተነሳ
ያጋጠማቸው ችግር የሌለ ቢሆንም ከነሱ የሚመነጨው የፍሳሽ ቆሻሻ ከበታች ላሉ ቤቶች ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር
ከመሆኑም በላይ ሁለት ሴፕቲክ ታንከሮች ከአገልግሎት ብዛት በመፍረሳቸው እና አገልግሎት መስጠት ከማይችሉበት
ደረጃ በመድረሳቸው ምክንያት ለነዚህ ለተጠቀሱት 48 ለሚደርሱ ቤቶች ሌላ አዲስ የሚያመነጩትን ፍሳሽ ቆሻሻ
ሊይዝ የሚችል እና በተወሰነ ወቅት ሲሞላ በጋራ ፍሳሹን የሚያስነሱት ሴፕቲክ ታንከር መገንባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡
በዚህ ስራ ላይ የተካተቱ መኖሪ ቤቶች ዝርዝር (የቤት ቁጥር)
1. ለቤት ቁጥር 1324,1325,1354,1355,1356,1357,1386,1387,1388,1389,1418 እና 1419 1 ሴፕቲክ
ታንከር
2. ለቤት ቁጥር 1326,1327,1352,1353,1358,1359,1384,1385,1390,1391,1416 እና 1417 1 ሴፕቲክ
ታንከር
3. ለቤት ቁጥር 1328,1329,1350,1351,1360,1361,1382,1383,1392,1393,1414 እና 1415 1 ሴፕቲክ
ታንከር
4. ለቤት ቁጥር 1330,1331,1348,1349,1362,1363,1380,1381,1394,1395,1412 እና 1413 1 ሴፕቲክ
ታንከር

በአጠቃላይ ከ 48 ቤቶች ለሚመነጭ ከፍተኛ የፍሳሽ ቆሻሻ አራት ተመጣጣኝ ይዘት ያላቸው አዳዲስ ሴፕቲክ ታንከሮች
የሚገነቡ ይሆናል፡፡

የቀረቡ ምፍትሄዎች
መፍትሄዎቹን በሁለት ከፍለን ማለትም የአጭር ግዜና እና ዘላቂ መፍትሄ ብለን ከፋፍለን እናያለን፡፡
1. የአጭር ግዜ ከል እንደተገለጸው በዚህ ደብዳቤ ላይ የተጠቀሱት ቤቶች ካሉበት መሬት አቀማመት የተነሳ በዚህ
ወቅት የገጠማቸው ግልጽ ችግር ባይኖርም ከቤቶቹ የሚመነጭ የፍሳሽ ቆሻሻ ከመንገድ በታች ባሉ ቤቶች ላይ
ከፍተኛ ጫና ፍጥሯል በዚህም መሰረት እንደጊዚያዊ መፍትሄ ከቦታው አቀማመት አንጻር በተመረጡ አራት
ቦታዎች ላይ ለየ 12 ቤቶች በቂ የሆነ አንድ ሴፕቲክ ታንከር ባጠቃላይ ለ 48 ቤቶች በጠቅላላው 12 ሴፕቲክ
ታንከሮች የሚገነቡ ይሆናል ፡፡
2. ዘላቂ መፍትሄ፡- ከጊዜያዊው መፍትሄ ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር
የአካባቢውን ቤቶች የፍሳሽ መስመር ለአካባቢው በቅርበት ከሚገኝ የከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር

1
ማገናኘት፡፡ የዚህንም ጉዳይ ተፈጻሚነት ባለው አሰራር መሰረት የቅ/ጽቤታችን በሃላፊነት ክትትል ማድረግ
ይኖርበታል፡፡

ማጠቃለያ፡-
 ከጽቤታችን የሚጠበቅ
 ከላይ ለተገለጹት ስራዎች የሚያስፈልገውን ዲዛይን ፣ሰራ ዝርዝር እና የበጀት ግምት በተጨማሪም
የስራ እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ ከላይ በዝርዝር የተገለጹት የኮርፖሬሽናችን ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ
እንዲሆኑ ማስተባበር፡፡
 ከወረዳ 05 ጋር በመሆን የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እና ሴፕቲክ ታነክ ግንባታ ስራ ላይ
በወጪ መጋራት አሰራር ላይ የወረዳ 05 አስተዳደር እና የአካባቢው ነዋሪ ተሳተፊ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
 በዘላቂነት የአካባቢው አጠቃላይ የፍሳሽ ችግር ሊፈታ የሚችለው የየቤቶቹን ፍሳሽ መስመር
ከከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር እንዲገናኝ ክፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት፡፡
 ከወረዳ 05 አስተዳደር የሚጠበቀው
 የቅ/ ጽቤታችንን ጥረት በበጎ በመረዳት በራስ አቅምም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብን በማስተባበር
የመፍትሄው አካል መሆን፡፡
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ የሚመለከታቸው ካላይ የተጠቀሱት ነዋሪዎች በወጪ መጋራቱ
አነዲሳተፉ ማስተባበር
 የተከራይ ደንበኞቻችን ድርሻ ፡-
 አሁን በቅ/ጽቤታችን የታቀደው በዋናነት ደንበኞቻችንን በተገቢው ለማገልገል እና አካባቢያቸውንም
የበለጠ ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ ከመሆኑ እንጻር ከማንም በላይ በሃላፊነት በመነሳት ሌሎች
የአካባቢዎቻቸው መሰል ተከራየች እንደሚያደርጉት ለስራው የሚያስፈልገውን በጀት በማዋጣት
መደገፍ ይኖርባቸውል፡፡
 ተያያዥ መረጃዎች
-በዝርዝረ የተገለጹት ቤቶች ጂ.አይ.ኤስ ማፕ
-ለስራው የሚያስፈልግ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን
የስራ ዝርዝሩየሚጠቃልላቸው ስራዎች፡-

 የሳይት ክሊሪንግ ስራዎች


 አራት ባለ 10 *5 ሴፕቲክ ታንከሮች መገንባት
 የማንሆል ስራዎች
 የባለ 40 ቱቦ ቀበራ

You might also like