You are on page 1of 47

ETHIOPIAN ELECTRIC POWER CORPORATION

UNIVERSAL ELECTRICITY ACCESS PROGRAM

አገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም

የዲስትሪቢው ሽን ኔትዎርክ ግንባታ ሱፐርቪዥንና ኮሚሽኒንግ መምሪያ

SUPERVISION AND COMMISIONING MANUAL


FOR DISTRIBUTION NETWORK

መስከረም 2004

16
ማውጫ

መግቢያ

1. ¾Ÿ}V‹ `¡¡w

2. p¾d“ Ç=³Ã” Y^

3. የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኪ.ቮ መስመር መጠበቅ ስለሚገባቸው ርቀቶች /Clearance/

4. የምሰሶ ጉድጓድ ቀፋሮና የኮንክሪት ምሰሶ በአርማታ ሙሌት አሰራር

5. የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኪ.ቮ መስመር የግንባታ ስራ

6. የትራንስፎርመር ተከላ

7. SWER /ባለ አንድ ሽቦ በመሬት ውስጥ ተመላሽ የኤሌክትሪክ መስመር/

8. ሱፐርቪዥንና ኮሚሽኒንግ

9. የሪፖርት አቀራረብና የቅፆች አጠቃቀም

10. የግንባታ ድሮዊንግ

16
መግቢያ

በአገር አቀፍ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም (አ/አ/ኤ/አ/ፕ) እቅድ መሰረት በየአመቱ የኤሌክትሪክ
መስመር ለሚዘረጋላቸው የገጠር ከተሞች በራስ ሀይል ፤በሪጅን ፤ በሀገር በቀል ኮንትራክተሮችና
በቲቪቲ ማህበራት አማካኝነት የሚሰራ ሲሆን ዋና ዋና ስራዎቹም ከታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

 የመካከለኛ ና የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ


 የትራንስፎርመር ተከላ
 የማቋረጫ/ሴክሽን ስዊች ተከላ

ይህም ስራ በመንግስት በጀት የሚሰራ ሲሆን ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ለስራው የሚያገለግሉ


እቃዎች ተገዝተው በተለያዩ የእቃ ግምጃ ቤቶች ቀርበዋል፡፡ በገንዘብ፤በጊዜና በንብረት ላይ ብክነት
እንዳይፈጠር በተጨማሪም በሱፐርቪዥን ጥብቅ የሆነና ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ይህ ግልፅ
የሆነ የሱፐርቪዥን መምሪያ ተዘጋጅቶአል፡፡

ባጠቃላይ የዚህ መምሪያ ዋና ዋና አላማዎች-

 ወጥ የሆነና ጥራት ያለው የሱፐርቪዥን አሰራር እንዲኖር


 በሁሉም ሱፐርቫይዘሮች ዘንድ ወጥ የሆነ የእውቀት /ክህሎት ወይም የመረጃ ደረጃ
እንዲኖር
 ሱፐርቫይዘሮች በሳይት ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንዲችሉ
 ሱፐርቫይዘሮች ሀላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት እንዲችሉ
 ስራዎችን በታቀደላቸው ጊዜ ፤በጀትና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በማሰራት
ለህብረተሰቡ
የመብራት ተጠቃሚ ማድረግ
1.1. መምሪያው የሚያካትታቸው ዋና ዋና ሀሳቦች
 ሳይት ርክክብን በተመለከተ
 የቅየሳ ስራ ማጣሪያና የፋውንዴሽን ስራ
 የመካከለኛ ና የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ፤ የትራንስፎርመር ተከላ እና
የማቋረጫ/ሴክሽን ስዊች ተከላ ስራዎች ሱፐርቪዥን
 የኮሚሽኒንግ ና የስራ ማጠቃለያ መረጃ አሰባሰብ

16
 SWER

መምሪያው ውስጥ ያልተካተቱ ነገር ግን ከሱፐርቫየዘሩ የሚጠበቁ ዋና ዋና ነገሮች

1.1.1. መሰረታዊ እውቀት


 መሰረታዊ የኤሌክትሪሲቲ እውቀት/ለኤሌክትሪካልና ሲቪል ሱፐርቫይዘር/
 መሰረታዊ የሲቪል ግንባታ እውቀት/ለሲቪል ሱፐርቫይዘር/
 የኤሌክትሪካል ዲዛይን ና የተለያዩ የኮንስትራክሽን ድሮዊንግ የመረዳት ክህሎት
 ጥሩ የመግባባት ብቃት/Good communication skills
 መልካም/ቀና አስተሳሰብ/Positive attitude/
1.1.2. ሌሎች ሱፐርቫይዘሩ ከተገቢው ክፍል ጋር በመነጋገር ማወቅና ወደ ትግበራ
እንዲቀይራቸው የሚጠበቁ ነገሮች
 መምሪያው ከተሰራጨ በኋላ የተደረጉ ወቅታዊ የሆኑ የተለያዩ የኮንስትራክሽን
አሰራር ለውጦች
 የቅጾች ለውጥ እና የመሳሰሉት /Updated changes /
በ 1.2.2 የተጠቀሱት በዚህ መምሪያ ውስጥ ያልተካተቱ ሲሆን በተለይም የአሰራር ለውጦችን
ለማስተባበሪያ ቢሮ በሚላኩ ማስታወሻና ከኢንጅነሪንግ በተለያየ ጊዜ በሚላኩ
ሱፐርቫይዘሮች አማካኝነት መረጃ ልውውጥ ማድረግ ይቻላል፡፡
1.2. ሱፐርቫይዘሮች በሳይት ላይ ማሟላት ያለባቸው ትጥቆች
 በማንኛውም ጊዜ ሱፐርቫይዘሩ የቀበሌና የመስሪያ ቤት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት
 Sleeping bag, bags ,shoe እና ሌሎችም መስሪያ ቤቱ የሚያቀርባቸው ትጥቆች
 GPS መሳሪያ
 Clamp on meter/Meger
 Operating rod (for commissioning)
 በተጨማሪም ይህ መምሪያ ለስራ እንዲያመች በሱፐርቫይዘሩ እጅ መገኘት አለበት

በዚህ መምሪያ ላይ መሻሻል ያለበትን የስራውን ጥራት ለማሻሻል ፤እና ለማቀላጠፍ መካተት

ያለባቸውን ሃሳቦችን በግልጽ በመነጋገር ሃሳቦችን ለኢንጅነሪንግ ክፍል አስተያየት መስጠት

16
እንደሚገባና ይህ መምሪያ የተለያየ የአሰራር ለውጦችን አካቶ ተሻሽሎ የሚቀርብ መሆኑን

እናሳውቃለን፡፡

 በስራ ላይ ያሉ ኮንትራክተሮች ኣስራር በነበረ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ መምሪያ ውስጥ የተገለጹት ነጥቦች ኣዲስ
ለሚጀመሩ ስራዎች በተግባር የሚውል ሲሆን ባጠቃላይ ግን ነባር ኣሰራሮች ተካትተው የተዘጋጀ ስለሆነ እንደ ኣጠቃላይ
ማጣቀሻ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

ምዕራፍ አንድ
የከተሞች ርክክብ
የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራምን በመወከል መብራት የሚገባላቸው ከተሞች ርክክብ በሚከናወንበት
ወቅት ርክክቡን የሚከናወነው ሱፐርቫይዘር ወይም መሃንዲስ አፅንኦት ሊሰጣቸው የሚገባቸው ጉዳዩች ፡-

1. uŸ}V‹ `¡¡w ¨pƒ ¾T>ÁeðMÑ< c’Ê‹


 ÃI ¾c<ø`y=»” T’<ªM (KT×kh’ƒ)፣
 K¢”ƒ^¡}ሩ `¡¡w ¾T>ðìUL†¨< ¾Ÿ}V‹ ´`´`፣
 ¾Ÿ}V‹ Te[Ÿu=Á pî/ö`Tƒ/፣
 `¡¡w KT>ፈፀምለት Ÿ}T ¾T>ÖKõuƒ ¾ መካከለ— SeS` SÖÑ” "Kuƒ ¾T>VLuƒ pî፣
2. ¾|M ቴ Ï SÖ”” uƒ¡¡M TekSØ

 የመካከለኛው መስመር ¨Ü ¾J’uƒ ሰብስቴሽን በትክክል ታውቆ መመዝገብ አለበት፣


 uk؁ Ÿcwe ቴሽን ወጪ የሚደረጉ መካከለኛ መስመሮች የ ቮልቴጅ መጠንን በትክክል ታውቆ መመዝገብ
አለበት፣
 አስቀድሞ Ÿcwe ቴሽን ወጪ ከሆነ መስመር ተጠልፎ የሚወሰድ የመካከለኛ መስመር ከሆነ ደግም ወጪ
የተደረገዉ መስመር ቮልቴጅ መጠን በትክክል መመዝገብ አለበት፣
 የመካከለኛው መስመር uT>ጠለፍበት ¨pƒ Ÿ 15 kv ¨ÃU Ÿ 33 Kv ¾SØKõ ›T^ß uT>•`uƒ ¨pƒ 33 Kv
}S^ß ÃJ“M ::
 መካከለኛው መስመር ከሰብስቴሽን ምን ÁIM Ÿ=.T@ }Ñ<µ ”ÅH@Å SS´Ñw ›Kuƒ
 ¾T>ÖKõuƒ ¾S"ŸK—¨< SeS` ሰብስቴሽን ከ 15 ኪቮ ወ Å 33Ÿ=| ¾T>hhM ŸJ’ ¾|M ቴጅ መጠኑ 33 ኪቮ
እንደሆነ ተወስዶ በ 33 ኪቮ ዕቃ ይሰራል፡፡ (ይህም በከተሞች ርክክብ ቅፅ ላይ በግልፅ ይሰፍራል፣
በ 19 ኪቮ ከተሞችን ለመስራት መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
 የሚጠለፍበት መስመር 33 ኬቪ መሆን አለበት፣
 የከተማው ከፍተኛ ጭነት በ 15 ዓመት ውስጥ ከ 25A ካልበለጠ /በምዕራፍ 7 ዝርዝሩን ይመልከቱ፣
 ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ብዛት /ከሦስት የበለጠ/
 የመካከለኛ መስመር የሚጠለፍበት ርቀት (ከ 5 ኪ.ሜትር በላይ)
 ከተማዋ ከሰብስቴሽን ያላት ርቀት (ከ 80 ኪ.ሜትር በላይ)

16
3. ¾›?K?¡ƒ]¡ }ÖnT> ¾T>J’< S”Åa‹ን eKT ካለል

 ወደ ከተማው ሲገባ የወረዳውን ›e}ÇÅ` uTÓ–ƒ ትክክለኛ አድራሻ ከታወቀ በኃላ ከመንደሩ ¾kuK?
›e}ÇÅ` Ò` uSJ” ¾Ÿ}T¨< ¨c” Ÿ ¨k uL ¾ku ሌው አስተዳደር ስም ፊርማና ማህተም በርክክብ
ሰነዱ ላይ መስፈር አለበት፣
 አብዛኛው ተጠቃሚ የሚገኝበት ማለትም እንደ ጤና ኬላ፣ የገበሬዎች ማሰልጠኛ (FTC)፣
ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚገኙበት የተለየ ከባድ ጭነት ያላቸው
ማዕከላት መሆኑ ታውቆ በርክክብ ወቅት እንደማዕካላዊ ቦታ ሆነው ያገለግላሉ (ማለትም
ትራንስፎርመሩ የሚተከልበት ቦታ)፣
 በእያንዳንዱ ቤት ኤሌክትሪክ ማዳረስ አዋጭ አለመሆኑን የቀበሌውን መስተዳደር ለወከሉት
ሰዎች ገለጻ በማድረግ TŸL© }wKA Ÿ}ÑKç¨< x የዝቅተኛዉ መሥመር ሊሳብ የሚችልበት
ርቀት ”ÅT>Ÿ}K¨< ÃJ“M፡፡
¾´p}— SeS` Sdw ¾T>‹K¬ ŸTŸL© x uT”—¨<U ›p×Ý Ÿ750 T@.ƒ SwKØ ¾KuƒU፣

 J•U Ó” u 750T@ ²<]Á ¾´p}— SeS\ ŸT>Ÿ}K<ƒ ¾Å”u™‹ lØ` በታች Sdw ¾KuƒU::

 80 ሜ ከ 1-4 ለሚደርሱ Å”u™‹

 160 ሜ ከ 4 - 6 ለሚደርሱ Å”u™‹

 320 ሜ ከ 7 - 10 ለሚደርሱ Å”u™‹


ŸLà Ÿ}Ökc<ƒ u}ÚT] u`¡¡w c’Æ Là ¾}kSÖ<ƒ uS<L ¨k¨< SS´Ñw Õ`v†ªM:: eK²=IU ¾›Ñ` ›kõ ›?K?¡ƒ]¡ ýace”
uS¨ŸM `¡¡u<” ¾T>ÁŸ“¨<’<ƒ ÓKcx‹ ŸLà ¾}Ökc<ƒ”“ u`¡¡w c’Æ Là ¾}kSÖ<ƒ uS<K< uƒ¡¡M SS´Ñw Lò’†¨<“
Óȁ†¨< ßU` eKJ’ u`¡¡u< ¨pƒ KT>ðÖ\ eI}„‹ }ÖÁm SJ“†¨<” K=Á¨<lƒ ÃÑvM::

4. የምሰሶ ዓይነት መረጣ (Selection Of Pole Type)

ከተሞቹ ሊሰሩባቸው የታሰቡት የምሰሶ ዓይነቶች በከተማ ርክክብ ወቅት ሊቀየር የሚችለው
በሚከተሉት መስፈርቶች ነው፡፡

የመንገዱ ዓይነት፡- የመንገዱ ሁኔታ ለክሬንና ለምሰሶ ማጓጓዝ ምቹ መሆኑን ከግምት ውስጥ
ማስገባትና ማረጋገጥ
የመንገድ ዓይነቶች፡-
 በሁሉም ወቅት ምቹ የሆነ መንገድ (All Weather Road)
 ለተወሰነ ወቅት ምቹ የሆነ መንገድ (Seasonal Weather Road)
 በጣም ውስን ለሆነ ወቅት ምቹ የሆነ መንገድ (Very Seasonal Road)

16
የመሬቱ አቀማመጥ፡- የመሬቱ መልካ ምድራዊ አቀማመጥ ለምሰሶ ዓይነት መረጣ ከግምት ውስጥ
መግባት አለበት
የአፈር ዓይነት፡- የአፈሩ ዓይነት ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ሊሆን ስለሚችል ይህም የምሰሶ
ዓይነትን ለመምረጥ አንዱ መስፈርት ነው
 መደብ አንድ፡- አለታማ /ድንጋያማ/ የሆነ የአፈር ዓይነት

 መደብ ሁለት፡- ጠንካራ ቀይ አፈር/መካከለኛ የአፈር ዓይነት/


 መደብ ሦስት፡- ጥቁር/መረሬ/፣ደለል እና ረግረጋማ የሆነ የአፈር ዓይነት
ሠደድ እሳት፡- ሠደድ እሳት ባለባቸው አካባቢ ችግሩን ሊቋቋሙ የሚችሉ የምሰሶ አይነቶች መሆን
አለባቸው፡፡
ንፋስ፡- በጣም ንፋሳማ ለሆኑ አካባቢዎች ጠንካራ ምሰሶ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በሙሉ በተገቢው ቅፅ ተሞልተው የምሰሶው ዓይነት እንዲቀየር


ሐሳብ መቅረብ አለበት፡፡ (ለተጨማሪ መረጃ የከፍተኛ መስመር ግንባታ ክፍልን ያንብቡ)

የምሰሶ ዓይነት ለመወሠን የሚረዱ ጠቃሚ ነጥቦች


ከዚህ ቀደም በእንጨት ምሰሶ የተሠሩ የመካከለኛ መስመር ስራዎች ጥራታቸው በጣም አነስተኛ ስለሆኑ
UEAP በኮንክሪትና በብረት ምሰሶ በመገንባት ላይ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ከሚቀርቡት የምሰሶ ቅያሬ ጥያቄዎች የተነሣ
ሱፐርቫይዘሮች ለማጣራትና ለውሣኔ የሚያመች ግልፅ መረጃ እንዲሰጡ የሚከተሉት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የኮንክሪት ምሰሶ፡- በሁሉም ወቅት ምቹ የሆነ መንገድ All Wather Road (AWR) ለማጓጓዝና ለማቆም ምቹ
የሆነ መልካምድራዊ አቀማመጥ ካለ መስመሩን ለመዘርጋት የኮንክሪት ምሰሶ የመጀመሪያ ተመራጭ ነው፡፡
የኮንክሪት ምሰሶ በምስጥ የማይበላ፣ ንፋስና እሳትን እንዲሁም የትኛውንም የአየር ፀባይ መቋቋም ይችላል፡፡
በነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች የተነሣ የኮንክሪት ምሰሶ ቀዳሚ ተመራጭ ነው፡፡
የብረት ምሰሶ፡- እንደ ኮንክሪት ምሰሶ ሁሉ የብረት ምሰሶም በምስጥ የማይበላ፣ ንፋስና እሳትን መቋቋም
የሚችል ሲሆን የትኛውንም የአየር ፀባይ መቋቋም ይችላል፡፡ በተጨማሪም የከፍተኛ አንግል ላይ
የምንጠቀማቸው የኮንክሪት ምሰሶዎች እጥረት ካለ የደቡብ አፍሪካ(SA) እንጨት ምሰሶ መጠቀም ይቻላል፡፡
ሆኖም ግን የብረት ምሰሶ እንደ ኮንክሪት በሀገር ውስጥ በቀላሉ ማምረት የሚቻል ስላልሆነ በተቻለ መጠን
አግባብ ባለው ቦታ ብቻ መጠቀም እንዲቻል ረጅም ኪ.ሜትር ላለበትና ኮንክሪት ምሰሶ ለማጓጓዝ
በማይቻልበት ሁኔታ የብረት ምሰሶ እንጠቀማለን፡፡ባለ 8 ሜትር የብረት ምሰሶ ስለሌለ የዝቅተኛ መስመሩን
ግንባታ በኮንክሪት ወይም በእንጨት ምሰሶ ይሰራል፡፡
የደቡብ አፍሪካ (SA) የእንጨት ምሰሶ:- የእንጨት ምሰሶ በመስመር ዝርጋታ ጊዜ የመጨረሻ ተመራጭ
በመሆኑና እንዲሁም በአሁኑ ሰዓት የእንጨት ምሰሶ እጥረት ስላለ ኮንክሪት ምሰሶም ሆነ የብረት ምሰሶ
ለማጓጓዝ በጣም አስቸጋሪ በሆነበት ቦታ ላይ ብቻ በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡት ጠንካራና ከፍተኛ ጥራት
ያላቸው የደቡብ አፍሪካ ምሰሶዎች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡

16
የእንጨት ምሰሶ፡-በሀገር ውስጥ የሚመረቱት የእንጨት ምሰሶዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት ከላይ
የተጠቀሱትን ሦሥቱን አማራጮች መተግበር ሳይቻል ሲቀር ነው፡፡

5. የሪሃብሊቴሽን ሥራ /ጥገና/ መልሶ የማብራት ሥራ/


በከተሞች ርክክብ ወቅት ለከተማው የሚጠለፍበት የመካከለኛ መስመር የወደቀ ወይም ሊወድቅ የደረሰ
መስመር ካለ ሱፐርቫይዘሩ ለይቶ መጠገን ያለባቸውን ሪፖርት ማድረግ አለበት፡፡ ለዚህ ስራ በተዘጋጁ
ቅፆች ላይ መስመሩን ለመጠገን የሚያስፈልጉ መረጃዎች በሙሉ ተሞልተው ሪፖርት መደረግ አለበት፡፡

Tdcu=Á:- uŸ}V‹ `¡¡w ]þ`ƒ SW[ƒ ¾T>¨cƃ ¨<X’@‹ ¾¢”ƒ^ƒ c’Æ” K=K¨<Ø eKT>‹M uŸ}V‹
ርክክብ ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎች በሙሉ በርክክብ ወቅት በተሳተፉ አካላት መረጋገጥ አለባቸው
(መፈረምና ማህተም መደረግ አለበት)፡፡ እነዚህም፡-

የወረዳው አስተዳደር ና የቀበሌው አስተዳደር


የኮንትራክተሩ ተወካይ
ሱፐርቫይዘሩ
መሐንዲሱና
ኮርዲኔተሩ

16
U°^õ G<Kƒ
p¾d“ Ç=³Ã” Y^

1. p¾d
¾S ካከለ— SeS` c=k¾e ማሙላ ƒ የሚገባቸው ነገሮች:-

¾T>k¾c¨< SeS` ›s^ß S”ÑÊ‹” ¾}Ÿ}K TÉ[Ó/›ß` `kƒ/


¾Ó”v Y^¨<” KTóÖ”“ KØÑ“ ›Sˆ ÃJ” ²”É u}‰K ›pU ŸS”ÑÉ S^p ¾KuƒU ፣
uSeS\ Là ›”ÓKA‹ ”ÇÕ\/”ÇÃu²</ Ø[ƒ TÉ[Ó፣

በተጨማሪም በ Check Survey ጊዜ መታየት ያለባቸው ነገሮች በተዘጋጀው ፎርማት ላይ ሪፖርት ማድረግ
ይቻላል
2. Ç=³Ã”
uŸ}V‹ `¡¡w SW[ƒ ¢”ƒ^¡}\ ¾Á”Ç ን Æ” Ÿ}T Ç=³Ã” c`„ K¿›?›ý ýaË¡„‹ ›=”Í=’]”Ó Ç=eƒ]u=¿i”
Ç=³Ã” u=a KTìÅp ÁeÑvM:: Ç=³Ã’< e’Ç`Æ” ¾Öuk SJ’ Ÿ¾ uL Ã[ÒÑØ“ u¾]Ï’< Ãu}“M::

¾ìÅk¨<” የመካከለኛ መስመር ፕሮፋይልና ¾´p}— SeS` Ç=³Ã” c<ø`zò\ ŸÅ[c¨< uL c<ø`zò\
¾T>Ñ’u<ƒ SeSa‹ uÇ=³Ã’< Sc[ƒ SJ“†¨<” ߁}LM፣ ÁeðîTM::

¾´p}— SeS` pÁe/Route/ ደንበኞች የኃይል አገልግሎት እነዲያገኙ ባማከለ መልኩ የሆነና ቀጥ ያለ
መስመር መሆን አለበት፡፡ ቀጥ ያለ ቅያስ/Route/ መጠቀማችን ለግንባታ የሚወስደውን ጊዜና ወጪ
መቀነስ ይቻላል፡፡

ከፀደቀው ዲዛይን ውጪ ሌላ የግንባታ ሥራ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ከ 5% በላይ ከሆነ በቅድሚያ ለሪጅን መሃንዲሱ
ማሳወቅ ያስፈልጋል፡፡ሪጅን መሃንዲሱም ሳይት ላይ ለመገኘት ካረጋገጠ በኋላ ለኮንትራክተሩ በአዲሱ ቅየሳ መሰረት
እንዲሰራ በማስተባበሪያ ቢሮ ሃላፊው በኩል በፅሁፍ ያሳውቃል፡፡ በግልባጭ ለኮንትራት አስተዳደር እንዲያውቅ ተደርጎ
በጽሁፍ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- አካባቢው ነፋሻማ ወይም ተራራማ ሆኖ በተለያዩ ምክንያቶች በምሰሶዎች መሀል ያለውን ርቀት መቀነስነ
አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሥራው ከመሰርቱ በፊት ከኢንጂነሪንግ ቢሮ መሐንዲስ ፍቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡

16
ምእራፍ ሶስት
የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኪ.ቮ መስመር መጠበቅ ስለሚገባቸው ርቀቶች

1. የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ኪ.ቮ መስመር ኔትዎርክ መጠበቅ ስለሚገባቸው ርቀቶች /ክሊራንስ/


ክሊራንስ ማለት በሚገነባው መስመር እና በዙርያው ባሉ ቁስ አካሎች (በሽቦዎቹ እና በመሬት፣ በመንገዶች፣ በዛፎች፣
በሕንጻዎችና በመሳሰሉት) ያለውን ክፍተት መካከል የሚኖረው ዝቅተኛ ርቀት መወሰን ማለት ነው።
1.1. ከምድር በላይ በሽቦዎችና በመሬት መሀከል ያለ ዝቅተኛ ርቀት /ክሊራንስ /(ከዋና መንገድ ውጪ)
በመሬትና በኤሌክትሪክ አስተላለፍ ሽቦዎች መካከል መኖር የሚገባው ከምድር በላይ የኤሌክትሪክ መስመሮች መጠበቅ
የሚገባቸው ርቀቶች ዝቅተኛ ርቅት እንደሚከተለው መሆን ይኖርበታል
 ከ 400 ቮልት ዝቅተኛ መስመር ገላጣ ከሆነ ወይም ሽፍን (ABC ) ሽቦ 4.6 ሜትር
 ከባለ 15 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 5.2 ሜትር
 ከባለ 33 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 5.2 ሜትር
 ከባለ 19 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 5.2 ሜትር
1.2. በኤሌክትሪክ መስመሮች እና በተክሎች መሀከል ያለ ክሊራንስ (ከዋና መንገድ ውጪ)
በተክሎችና እና በኤሌክትሪክ መስመር ሽቦዎች መካከል መኖር የሚገባው ዝቅተኛ (ርቀት) እንደሚከተለው መሆን
ይኖርበታል
 0.4 ኪ.ቮ ከሆነ ገላጣ ወይም (ABC) ሽቦ 2 ሜትር
 ከባለ 15 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 2.5 ሜትር
 ከባለ 33 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 3 ሜትር
 ከባለ 19 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 3 ሜትር
2. በሽቦዎችና ሕንጻዎች መሀከል ያለ ክሊራንስ
2.1. በማንኛውም ጊዜ ቢሆን አንድ የዝቅተኛ ቮልት ሽፍን ሽቦ ቀጥሎ ከተገለጹት ዝቅተኛ ርቀቶች
የበለጠ ወደ ህንፃ ወይም ግንባታ አካላት መቅረብ የለበትም፡፡
 ከመሬት በላይ በቀጥታ …………………………… 2.5 ሜትር
 ከመስኮቶችና በሮች በላይ ………………………… 0.3 ሜትር
 ከመስኮቶችና በስተጐንና በታች …………………..0.5 ሜትር
 ከበሮችና ባልኮኒዎች በስተጐን …………………… 1.0 ሜትር
2.2. በማንኛውም ጊዜ ቢሆን እንደየሚከተለው የመስመሩ ቮልቴጅ መጠን አንድ የምድር በላይ
የኤሌክትሪክ መስመር ቀጥሎ ከተገለጹት ዝቅተኛ ርቀቶች የበለጠ ወደ ህንጻ ወይም ግንባታ አካላት
መቅረብ የለበትም፡፡
 ሰው በተለምዶ ከሚደርስባቸው የህንጻ ወይም የግንባታ አካላት ቀጥታ ወደላይ ባለው አቅጣጫ በሚሆንበት ጊዜ
የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 4.6 ሜትር

16
 ሰው በተለምዶ ከማይደርስባቸው የህንጻ ወይም የግንባታ አካላት ቀጥታ ወደላይ ባለው አቅጣጫ በሚሆንበት ጊዜ
የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ባ. ካልበለጠ 2.7 ሜትር እንዲሁም የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. በላይ ሆኖ ግን
ከ 33 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 3.7 ሜትር
 ሰው በተለምዶ ከማይደርስባቸው የህንጻ ወይም የግንባታ አካላት በማንኛውም ሌላ አቅጣጫ በሚሆንበት ጊዜ
የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 0.6 ሜትር እንዲሁም የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. በላይ ሆኖ ግን
ከ 33 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 2.7 ሜትር
 ከመስኮቶች ክፍተቶች እና ባልኮኒዎች እንዲሁም ሰው በተለምዶ ከሚደርስባቸው የህንጻ ወይም የግንባታ አካላት
በማንኛውም ሌላ አቅጣጫ በሚሆንበት ጊዜ የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 1.5 ሜትር እንዲሁም የመስመሩ
ቮልቴጅ ከ 1 ሺ.ቮ. በላይ ሆኖ ግን ከ 33 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 2.7 ሜትር
 ከእግር ድልድይ በማንኛውም አቅጣጫ በሚሆንበት ጊዜ የመስመሩ ቮልቴጅ ከ 33 ሺ.ቮ. ካልበለጠ 4.6 ሜትር
3. በሽቦዎችና በመንገዶች መሀከል ከመሬት በላይ ያለ ክሊራንስ
3.1. ዋናመንገድ
 0.4 ኪ. ቮ ከሆነ ገላጣ ወይም ሽፍን(ABC) ሽቦ 5.2 ሜትር
 ከባለ 15/33 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 6.7 ሜትር
3.2. ባቡር መንገድ
 0.4 ኪ. ቮ ከሆነ ገላጣ ወይም ሽፍን (ABC) ሽቦ 5.5 ሜትር
 ከባለ 15/33 ኪ.ቮ ሽቦ መስመር 8.5 ሜትር
4. ከመንገድ ዳር ጠርዝ
የሚገነባው መስመር (ቴራንቲን ጨምሮ) ከመሐል መንገዱ ቢያንስ 15 ሜ መራቅ ይኖርበታል፡፡ ከመንገድ ጠርዝ ላይ ቢያንስ 2
ሜትር መራቅ አለበት።
5. የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ኪ.ቮ የሚኖረውን የስፋት ልኬት መጠን(span)
 የሚከተለው ሰንጠረዥ በእንጨት፣ በብረትና በኮንክሪት ምሰሶዎች መሐከል የሚኖረውን የስፋት ልኬት
መጠን(span) በከተማ ውስጥና ከከተማ ውጪ ለ 33 ኪ.ቮ፣15 ኪ.ቮእና 19 ኪ.ቮ በመከፋፈል ያሳያል።
 በከተማ ውስጥ የሚተከለው የመካከለኛ መስመር ምሰሶ ቁመት በቂ አቅርቦት ካለ 11 ሜትር ቢሆን ይመረጣል።
 የሁለት የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች የማቋረጫ ቦታ ላይ በመሀላቸው ወደላይ /ወደታች/ ያለው ርቀት
ቢያንስ 1.2 ሜትር ልዩነት መኖር አለበት፣
 የሁለት የመካከለኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ ሽቦዎች የማቋረጫ ቦታ ላይ በምሰሶዎች መካከል መኖር ያለበት ርቀት
40 ሜትር መሆን አለበት፤
አዲስ የሚገነባው ምሰሶ ርዝመት መሆን ያለበት ቀድሞ የተገነባው
 ምሰሶ ሁለት የተለያዩ
የመካከለኛ ቮለቴጅ
11 ወይም 12 ሜትር 9 ሜትር
መስመሮች
12 ሜትር 10 ሜትር በተመሳሳይ ቦታ ላይ
በሚኖሩበት ጊዜ
በምሰሶዎች መካከል ያለው ርቀት ቢያንስ 3 ሜትር መሆን አለበት የምሰሶዎቹ ርዝመትም ከዚህ በታች ካለው
ሰንጠረዥ ላይ ሰፍሯል።

16
5.1. በሁለት ምሰሶዎች መካከል ያለው ርቀት ለእንጨት እና ለብረት ምሰሶ/ Span/

የቮልቴጅ መጠን በከተማና ከከተማ የቮልቴጅ መጠንና ስፋት በሜትር


የምሰሶ ዓይነት
ውጭ 33KV 15KV 19KV

የመካከለኛ ቮልቴጅ ከከተማ ውጭ 70 ሜትር 100 ሜትር 150 ሜትር


የእንጨት ምሰሶ የመካከለኛ ቮልቴጅ በከተማ ውስጥ 50 ሜትር 80 ሜትር 80 ሜትር
የዝቅተኛ መስመር 40 ሜትር 40 ሜትር 40 ሜትር

የመካከለኛ ቮልቴጅ ከከተማ ውጭ 100 ሜትር 100 ሜትር 150 ሜትር

የብረት ምሰሶ የመካከለኛ ቮልቴጅ በከተማ ውስጥ 80 ሜትር 80 ሜትር 80 ሜትር

የዝቅተኛ መስመር በእንጨት ምሰሶ 40 ሜትር 40 ሜትር 40ሜትር

 በኣንዳንድ አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ እንዳስፈላጊነቱ ስፓን ማስተካከል በተለይም ከባድ አንግል ያለበትና ሸለቆአማ
ወይም ተራራማ ቦታዎች ላይ በመቀነስ ተገቢውን ክሊራንስ መጠበቅ ይገባል።
 በተጨማሪም ቦታው ንፋስ የበዛበት ከሆነ እንዳስፈላጊነቱ ስፓን ማስተካከል ይገባል።
 ለብረት ምሰሶ በአንግል ይቀንሳል ፡፡

16
የብረት ምሰሶ አጠቃቀም

የመዋቅር ዓይነት የምሰሶ አይነት


/Assembly Type/ አንግል

ቀጥተኛ 0 ≤-አ ≤ 2 ዲግሪ Normal Steel Pole

ቀላል አንግል 1 2< አ ≤15 ዲግሪ Normal Steel pole በጋይ ዋየር

ቀላል አንግል 2 15<አ ≤30 ዲግሪ Strong Steel pole በጋይ ዋየር

ከባድ አንግል 30<-አ≤60 ዲግሪ 2x Strong Steel pole በጋይ ዋየር

ተገንጣይ/ T-Off 90 ዲግሪ Strong Steel pole በጋይ ዋየር

የመጨረሻ /Dead end/ 0 ዲግሪ Strong Steel pole በጋይ ዋየር

ማርገቢያ መስመር
0 ዲግሪ 2x Normal Steel Pole
/Tension tower/

ትራንስፎርመር 0 ዲግሪ 2x Normal Steel Pole

10mt Normal Steel Pole ውፍረት ከላይ 120 ሚ.ሜ ከታች 204 ሚ.ሜ
11mt Normal steel pole ውፍረት ከላይ 120 ሚ.ሜ ከታች 216 ሚ.ሜ
10mt Strong Steel pole ውፍረት ከላይ 135 ሚ.ሜከታች 309 ሚ.ሜ
11mt Strong Steel pole ውፍረት ከላይ 135 ሚ.ሜ ከታች 328 ሚ.ሜ

16
5.2. የመካከለኛ ቮልቴጅ በሁለት ምሰሶዎች መካከል ያለው ርቀት ለኮንክሪት ምሰሶ/ Span/

አማራጭ 3
አማራጭ 1 አማራጭ 2

የምሰሶ የድጋፍ የስፋት የድጋፍ የስፋት የምሰሶ የስፋት


የመዋቅር ዓይነት አንግል ዓይነት ዓይነት መጠን የምሰሶ ዓይነት ዓይነት መጠን ዓይነት የድጋፍ ዓይነት መጠን

1x300
ቀጥተኛ 0 ≤-አ ≤ 2 ዲግሪ 100 ሜ
ዳን

በጋይ ዋየር የደቡብ


1x300 በጋይ የደቡብ አፍሪካ ወይም አፍሪካ 100
ቀላል አንግል 1 2< አ ≤15 ዲግሪ 100 ሜ 100 ሜ _
ዳን ዋየር እንጨት ምሰሶ እንጨት እንጨት ሜ
ምሰሶ ምሰሶ
የደቡብ
1x500 በጋይ አፍሪካ በጋይ ዋየር
ቀላል አንግል 2 15<አ ≤30 ዲግሪ 90 ሜ 650 ዳን   አያስፈልጊም 90 ሜ 90 ሜ
ዳን ዋየር እንጨት ወይም እንጨት
ምሰሶ ምሰሶ
ሁለት
የደቡብ
1x800 በጋይ
ከባድ አንግል 30<-አ≤60 ዲግሪ 80 ሜ 2x650/500 ዳን በጋይ ዋየር 80 ሜ አፍሪካ በጋይ ዋየር 80 ሜ
ዳን ዋየር
እንጨት ወይም እንጨት
ምሰሶ ምሰሶ
የደቡብ
1x800 በጋይ አፍሪካ በጋይ ዋየር
ተገንጣይ/T-Off 90 ዲግሪ 70 ሜ 1x650 ዳን በጋይ ዋየር 70 ሜ 70 ሜ
ዳን ዋየር እንጨት ወይም እንጨት
ምሰሶ ምሰሶ
የደቡብ
የመጨረሻ 1x800 በጋይ አፍሪካ በጋይ ዋየር
0 ዲግሪ 70 ሜ 1x650 ዳን በጋይ ዋየር 70 ሜ 70 ሜ
/Dead end/ ዳን ዋየር እንጨት ወይም እንጨት
ምሰሶ ምሰሶ
የደቡብ
2x300 አፍሪካ 100
ቴንሽን ታወር 0 ዲግሪ 100 ሜ
ዳን እንጨት ሜ
    ምሰሶ  

2x300
ትራንስፎርመር 0 ዲግሪ   ሁለት የደቡብ አፍሪካ እንጨት ምሰሶ
ዳን

 በመደበኛ ደረጃ የምንጠቀመው አማራጭ አንድን ነው


 የአማራጭ አንድ አቅርቦት ከሌለ ያለው አቅርቦት ታይቶ አማራጭ ሁለትና ሶስትን እንጠቀማለን

16
5.3. የዝቅተኛ መስመር በሁለት ምሰሶዎች መካከል ያለው ርቀት ለኮንክሪት ምሰሶ/ Span/

አማራጭ 1 አማራጭ 2
የድጋ የስፋ
ፍ ት
የመዋቅር የምሰሶ ዓይነ መጠ የድጋፍ
ዓይነት አንግል ዓይነት ት ን የምሰሶ ዓይነት ዓይነት
50
0≤ አ ≤-15 ዲግሪ 1x300 ሜት
ቀጥተኛ ዳን _ ር
50
ቀላል 15<- አ ≤30 ዲግሪ 1x300 በጋይ ሜት
አንግል ዳን ዋየር ር

30< አ <90 ዲግሪ 50


ከባድ 1x500 በጋይ ሜት 1x300 ዳን በ 25 ሜ በጋይ
አንግል ዳን ዋየር ር ስፓን ዋየር

50
1x500 በጋይ ሜት 1x300 ዳን በ 25 ሜ በጋይ
ተገንጣይ 90 ዲግሪ ዳን ዋየር ር ስፓን ዋየር

50
1x500 በጋይ ሜት 1x300 ዳን በ 25 ሜ በጋይ
ዴድ ኢንድ   ዳን ዋየር ር ስፓን ዋየር

 በመደበኛ ደረጃ የምንጠቀመው አማራጭ አንድን ነውቀጥተኛ


 የአማራጭ አንድ አቅርቦት ከሌለ ያለው አቅርቦት ታይቶ አማራጭ ሁለትና ሶስትን እንጠቀማለን

16
ምእራፍ አራት
የምሰሶ ጉድጓድ ቁፋሮ እና የኮንክሪት ምሰሶ በአርማታ ሙሌት
(Cast-in-Place Concrete) መሠረት የማቆም አሰራር ዘዴ
1. አጠቃላይ
የኮንክሪት ምሰሶ ለማቆም አሞላል ሂደት ለመካከለኛ (mv) መስመር የጉድጓድ ቁፋሮ፣
መሬት ላይ ድንጋይ ማንጠፍ (Hard Core)፣ ጉድጓድ ውስጥ ምሰሶ ማስገባት እና 1፣2፣4 የሆነ
አርማታ ከድንጋይ ጋር ቀላቅሎ መሙላት ነው፡፡ የምሰሶ አይነት አጠቃቀም ለመካከለኛ
መስመር /ከከተማ ውጪ/ 10 ሜትር፣ 11 ሜትር እና የተለየ ሁኔታ ሲኖር 12 ሜትር፣
ለዝቅተኛ መስመር /ከተማ ውስጥ/ 8 ሜትር ልንጠቀም እንችላለን፡፡

ባለ 8 ሜትር ምሰሶ የምንጠቀመው ለዝቅተኛ መስመር LV ሲሆን ለመካከለኛ መሰመር mv 10


ሜትር፣ 11 ሜትር፣ እና 12 ሜትር እንጠቀማለን፡፡ በተጨማሪ የምሰሶ አይነት በጥንካሬአቸው
ተለይተው ለተለያየ አንግል የምንጠቀማቸው ሲሆን እነዚህም 300 dan, 500 dan, 800 dan, እና
1250 dan ናቸው፡፡ በተመሳሳይ 10 ሜትር፣ 11 ሜትር፣ እና 12 ሜትር የብረት ምሰሶዎች
ለመካከለኛ መስመር ዝርጋታ የምንጠቀም ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀመው አካባቢው
ለእሳት ቃጠሎ የተጋለጠ ሲሆን እና የመሬቱ አቀማመጥ የኮንክሪት ምሰሶ ለመስራት አመቺ
ባልሆነ ጊዜ ነው፡፡ ሁለት ዓይነት የብረት ዓይነቶች አሉ እነሱም መደበኛ እና ጠንካራ
የብረት ምሰሶዎች ናቸው፡፡

በአጠቃላይ የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር ለዝቅተኛ መስመር 8 ሜትር ምሰሶ ተከላ
አፈር በመመለስ በመጠቅጠቅ ነው፡፡ ይህም ማለት ለዝቅተኛ መስመር የኮንክሪት መሠረት
አይኖርም በሌላ በኩል ሁሉም መካከለኛ መስመር mv ኮንክሪት በአርማታ መሠረት Cast in
Place መሰራት አለባቸው፡፡
የፋውንዴሽን ጥልቀት እና ስፋት ስታንዳርድ በምሰሶ ዓይነት፣ በምሰሶ ርዝመት፣ በምሰሶ
ጥንካሬ እና የአካባቢውን የአፈር አይነት መሠረት ባደረገ ነው፡፡ የመሠረት ሥራ ሂደት
ሳይት ማዘጋጀት፣ የመሬት አቀማመጥ ማስተካከል (Leveling)፣ ቁፋሮ፣ ድንጋይ ማንጠፍ

16
(Hard Coring)፣ ምሰሶ ጉድጓድ ውሰጥ ማስገባት /ማስተካከል/፣ አርማታ በመጠቅጠቅ
መሙላት እና አካባቢውን ማፅዳትን ያጠቃልላል፡፡

2. የኮንክሪት እና የብረት ምሰሶ ፋውንዴሽን እና ተከላ አሰራር


ኮንትራክትሩ በፀደቀለት ዲዛይን (GPS) መሠረት በማድረግ ቦታው የመስመሩ ቀጥተኝነት
የመንገድ ድንበር መጠበቅ አለበት የምንጠቀመው የኮንክሪት ወይም የብረት ምሰሶዎች
ዓይነት የኮንክሪት ምሰሶ ጥንካሬ እና ርዝመት በፀደቀው ዲዛይን መሠረት ነው፡፡
በማንኛውም ሁኔታ ከፀደቀው ዲዛይን ውጪ ለውጥ ሲኖር ኮንትራክትሩ ያለውን ሁኔታ
ለኢንጂነሪንግ የሥራ ሂደት በማሳውቅ ስራውን ለመቀጠል ለውጡ ተቀባይነት ማግኘት
አለበት፡፡

የአፈር አይነት /መደብ/ አመዳደብ


የአፈር ፀባይ በሁሉም የምሰሶ ተከላ ወቅት መለየት ያለበት በጥንካሬ እና በወጪ ቆጣቢ
በሆነ የመሠረት መጠን መሆን አለበት፡፡ የአፈር አይነት መደብ ለመለየት ከላይ በመመልከት
ቢሆንም 1 ሜትርም ጥልቀት ቆፍሮ በማየት የአፈሩን አይነት በትክትል መመደብ ይቻላል፡፡
ለኮንክሪት ምሰሶ የመሠረት ስራ የአፈሩ ፀባይ በሦስት ክፍሎች ተመድቧል፡፡

መደብ 1 የአፈር አይነት /ጥሩ የአፈር አይነት/


የአፈሩ የመሸከም አቅም ከ 350 ኪሎ ፓስካል (Kpa) የበለጠ እና አለታማ /ድንጋያማ/ የሆነ
ጥሩ የአፈር አይነት ነው፡፡

መደብ 2 የአፈር አይነት /መካከለኛ የአፈር አይነት/


የአፈሩ የመሸከም አቅም ከ 200 ኪሎ ፓስካል (Kpa) - 350 Kpa የሆነ ጠንካራ ቀይ አፈር
ሲሆን ተቀባይነት ያገኘ መካከለኛ የአፈር አይነት ነው፡፡

መደብ 3 የአፈር አይነት /ዝቅትኛ ጥሩ ያልሆነ የአፈር አይነት

16
የአፈሩ የመሸከም አቅም ከ 200 ኪሎ ፓስካል በታች ሆኖ ጥቁር /መረሬ/ ደለል እና ረግረግ
የሆነ የአፈር አይነት ዝቅተኛ ነው፡፡

የግንባታ መሠረት ምርጫ


የአፈሩ አይነት መደብ ከተረጋገጠ በኋላ በሱፐር ቫይዘሩ መፅደቅ አለበት የቁፋሮ ጥልቀቱና
ስፋቱ ከምሰሶው ጥንካሬ እና ከአፈሩ አይነት ጋር ተመጣጣኝ መሆኑን ከሥራ ዝርዝር
ከግንባታ መምሪያው መመልከት እና ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ኮንትራክተሩ ወጪን ያገናዘበ
የፋውንዴሽን አይነት እና ለስራው ምቹ የሆነ ትክክለኛ ምርጫ የመምረጥ ሙሉ ኃላፊነት
አለበት፡፡ የአፈሩ አይነት መደብ በሚሰጥበት ጊዜ በጥንቃቄ መሆን አለበት፡፡ በአጋጣሚ
የተመረጠው የመሠረት መደብ ከአፈሩ ፀባይ ጋር የማይጣጣም ቢሆን ኮንትራክተሩ ለችግሩ
ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል፡፡ ከሚፈለገው ዲዛይን በላይ የሆነ መጠን ያለው የመሠረት
ግንባታ ቢሰራ ተቀባይነት የሚያገኘው እና የሚከፈለው የግንባታ መምሪያው ላይ
በተቀመጠው መሠረት ነው፡፡ ከተቀመጠው መጠን በታች የሆነ የመሠረት ግንባታ ቢሰራ
ኮንትራክተሩ በተሰጠው ዲዛይን መሠረት የማስተካከል ግዴታ አለበት፡፡

ቁፋሮ
ቁፋሮ ከመጀመሩ በፊት አካባቢው ከማንኛውም ቆሻሻ ነክ የሆኑ ነገሮች መፅዳት አለበት፡፡
ቁፋሮ የችካሉን ሴንተር የጠበቀ የምሰሶ አይነት እና የመስመሩን ቀጥተኝነት ያገናዘበ መሆን
አለበት፡፡
የሚቆፈረው ወደታች ቀጥ ብሎ እና ክብ ሆኖ ሲሆን የቁፋሮውን መጠን በግንባታ
መምሪያው መሠረት መሆን አለበት፡፡ ቁፋሮው በዲዛይኑ መሠረት ሆኖ ከላይ እስከ ታች
ተመሳሳይ መሆን አለበት ከቁፋሮ በኋላ ሱፐርቫይዘሩ የአፈሩ አይነት እና በግንባታ ዝርዝሩ
ከሚያዘው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ማፅደቅ አለበት፡፡ የፋውንዴሽን ቁፋሮ ጥልቀት እና
ስፋት በምሰሶው ቁመት የመስመሩ አይነት የአፈሩ ፀባይ በግንባታ ዝርዝር እና ዲዛይን
መሠረት መሆን አለበት፡፡ የተቆፈረው ከሚፈለገው መጠን በላይ ቢሆንም ተጨማሪ
ማቴሪያል በኮንትራክተሩ ኪሳራ ተጨምሮ ይሰራል፡፡

የድንጋይ ንጣፍ (Hard Core)

16
በግንባታ መምሪያው መሠረት ቁፋሮ ካለቀ በኋላ 100 ሚ.ሜ መጠን ያለው ድንጋይ 10 ሴ.ሜ
ለመደብ ሁለት የአፈር አይነት እና 150 ሚ.ሜ መጠን ያለው በ 15 ሴ.ሜ ለመደብ ሦስት
የአፈር አይነት መነጠፍ አለበት፡፡ ለመደብ አንድ የአፈር አይነት የድንጋይ ንጣፍ (Hard Core)
አያስፈልግም፡፡ ለመደብ ሁለት እና ለመደብ ሦስት ድንጋዩ ውሃ ልክ ተጠብቆ ከተነጠፈ
በኋላ ትንንሽ መጠን ያላቸው ጠጠር በየ 20 ሳሜ እየተረበረበ ተበትኖ በቢጆ መጠቅጠቅ
አለበት፡፡

የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ


የኮንክሪት ምሰሶ ለማጓጓዝ እና በተከላ ወቅት ከመሠበር እና ከመሠንጠቅ ለመጠበቅ አመቺ
በሆነ ማሽነሪ /ክሬን/ጂንፓል/ እና ብቁና ልምድ ባለው የሰው ኃይል መሆን አለበት፡፡
ለማንኛውም በጥንቃቄ ጉድለት ለሚሰበር እና ከአገልግሎት ውጭ ለሚሆን ምሰሶ
ኮንትራክትሩ ሙሉ ኃላፊነት አለበት፡፡

የአርማታ አሞላል
ምሰሶ ጉድጓድ ውስጥ ከቆመ በኋላ በደንብ እየተጠቀጠቀ የመሬቱ የላይኛው ክፍል ድረስ
አርማታ ይሞላል፡፡ ትንንሽ መጠን የላቸው ድንጋዮች /መጠናቸው ከ 10 ሴ.ሜ - 15 ሴ.ሜ/
ከአርማታው ጋር ይሞላል፡፡ ድንጋዩ ከአጠቃላይ የጉድጓድ መጠን 20% ድንጋይ በደረጃ
ሳይሆን ከአርማታው ጋር እንዲቀላቀል ተደርጐ ይጨመራል፡፡ በመሠረት ግንባታው
የላይኛው ክፍል ወደ ውጪ ስሎኘ ተሰጥቶት ማለቅ አለበት፡፡

የመሠረት ግንባታው ተሰርቶ ካለቀ በኋላ አክሰሰሪው ከመገጠሙ በፊት በቀን ሁለት ጊዜ ለ
7 ተከታታይ ቀናት ውሃ መጠጣት አለበት፡፡

3. የኮንክሪት ፋውንዴሽን የሚሰራባቸው ዕቃዎች የጥራት ሁኔታ

3.1 ለኮንክሪት ፖል የመሰረት ግንባታ ሥራ የምነጠቀምባቸው ማቴሪያሎች ደረጃቸውን


የጠበቁና ጥራት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ለመሰረት ግንባታ የሚመጡ ማንኛውንም
ማቴሪያሎች በሳይቱ ላይ የሚገኙት ኢንጂነር ወይንም ሱፐርቫይዘር የጥራታቸውን
ሁኔታ ሳያረጋግጡ መጠቀም አይቻልም፡፡

16
ለመሰረት ግንባታ የሚመጡ ማቴሪያሎች በአግባቡ እና ደረጀውን በጠበቀ ሁኔታ
መቀመጥ አለበት እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ከሚደርስባቸው ጉዳት በአግባቡ
መጠበቅ አለባቸው፡፡

3.2 ሲሚንቶ
ሲሚንቶን በተመለከተ ለመሠረት ግንባታ የምንጠቀምበት ሲሚንቶ ትኩስ መሆን
አለበት የሲሚንቶ አይነት በሁለት ይከፈላሉ እነሱም፡- ኦርድናሪ ፓርት ላንድ ሲሚንቶ
/ኦ.ፓ.ሲ/ እና ፓዞ ላና ፓርት ላነድ ሲሚንቶ /ፓ.ፓ.ሲ/ ናቸው፡፡

የሲሚንቶ አቀማመጥ እና አያያዝን በተመለከተ የሲሚንቶ ስቶር በጭቃም ሆነ


በቦሎኬት ከተሰራ የተሰራው ስቶር በውስጡ የያዘው እርጥበት የወጣለት መሆን
አለበት የሲሚንቶ አቀማመጥን በተመለከተ ሲሚንቶው ሲደረደር ከወለሉ 15 ሴ.ሜ ከፍ
በማለት እርብራብ በመሥራት እና ወደግድግዳው ሳያስጠጉ መደረደር አለበት ነገር ግን
አንድ ሲሚንቶ ያለሥራ ስድስት ወር ከተቀመጠ ሥለሚበላሽ ስቶር የገባውን ሲሚንቶ
ከሥድስት ወር በፊት ባለው ጊዜ ጨርሶ አዲስ /ትኩስ/ ሲሚንቶ መተካት አለበት ግን
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ኮንትራክተሩ ሳይጠቀምበት ስድስት ወር ካለፈው ያንን ሲሚንቶ
ከሳይት ውስጥ ማውጣት አለበት፡፡

3.3 አሸዋ
ለመሰረት ግንባታ የምንጠቀመው አሸዋ መሆን ያለበት የወንዝ አሸዋ ነው፡፡ ነገር ግን
የወንዝ አሸዋ የማይገኝበት ቦታ ላይ የማዕድን አሸዋ መጠቀም ይቻላል፡፡ ነገር ግን
የማዕድን አሸዋ አፈር ሊኖርበት ሥለሚችል መጠነኛ ገንዳ በማዘጋጀት አሸዋውን አጥቦ
መጠቀም ይቻላል፡፡

የአሸዋውን ጥራት በተመለከተ አሸዋው ከማንኛውም አይነት ኢንኦርጋኒክ እና ኦርጋኒክ


ከሆኑ ቁሶች የፀዳ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ማለት ከጭቃ፣ ከአፈር፣ ከቅጠላ ቅጠል ከሰው
እና ከከብት እዳሪ የፀዳ መሆን አለበት፡፡ የጭቃው መጠን በጃር ቴሥት ቴሥት ሲደረግ
ከ 4% መበለጥ የለበትም፡፡

16
3.4 ጠጠር
ለመሰረት ግንባታ የምንጠቀምበት የጠጠር አይነት በአግባቡ በማሽን ደረጃውን ጠብቆ
የተፈጨ መሆን አለበት፡፡ የጠጠር መጠን ከ 40 ሚ.ሜ መብለጥ የለበትም ጠጠሩም
እንደ አሸዋው ሁሉ ኢንኦርጋኒክ እና ኦርጋኒክ ከሆኑ ቁሶች የፀዳ መሆን አለበት፡፡
ሌላው ደግሞ

ጠጠረ የሚዘጋጅበት ድንጋይ ጠንካራ ጥቁር ድንጋድ (Basaltic Stone) መሆን አለበት
እሱም ቀዳዳ (Porous) ያልሆነ መሆን አለበት ጠጠሩ ጠርዝ ያለው መሆን አለበት ክብ
ወይንም ዝም ብሎ ጠፍጣፋ አይነት መሆን የለበትም የትሪያንግል ቅርፅ ቢይዝ
ይመረጣል፡፡

4. ለመሰረት ግንባታ የሚሆኑ ማቴሪያሎችን የማዋሐድና የማምረት ሂደት

የመሥፈርና የማቀላቀል ሂደት


ለኮንክሪት ሥራ የሚያስፈልጉን ማቴሪያሎች አሸዋ፣ ጠጠር፣ ሲሚንቶ እና ውሃ
መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የማቴሪያል መለኪያ መጠን በተመለከተ 1፣ 2፣ 4 ነው ለሁሉም
አይነት የመሰረት ግንባታ ማለት ሲሆን ሲሚንቶ የሚሰፈረው በከረጢት መሆኑ
ይታወቃል፡፡ እሱም 50 ኪ.ግ ነው፡፡ ሌሎቹ ግን የመስፈሪያ መንገዳቸው በሳጥን ሲሆን
እሱም የሚዘጋጀው ከጣውላ ወይንም ከላሜራ ይሆናል፡፡ መጠኑን በተመለከተ
የጠጠሩም ሆነ የአሸዋው ሣጥን 50cm x 40cm x 20cm ይሆናል፡፡ የዚህም ውጤት 0.4m3
ይሆናል፡፡ ይህ ልኬታ የሳጥኑን ውስጥ ለውስጥ ነው ማለትም ሳጥኑ የተሰራበትን
እንጨት ውፍረት አይጨምርም፡፡

ለመሰረት ግንባታው የሚውለው የጠጠር፣ የአሸዋና የሲሚንቶ መጠን ምሰሶው


መሸከም በሚችለው መጠን እና በመሰረት አይነቱ በሰንጠረዥ ተቀምጦ ይገኛል፡፡
የመስፈር ሂደቱ ማለትም አሸዋና ጠጠሩ በሳጥን ሲሰፍር ሳጥኑን እስከ አፍ በደንብ
ሞልቶ ከአፍ በላይ የተረፈውን በሪጋ ወይም በአካፋ እጀታ ማስወገድ ነው፡፡
ኮንትራክተሩ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ልኬታ መሰረት /የሥፍር መጠን/ በምሰሶው

16
የመሸከም መጠን እና በመሰረት ግንባታው አይነት ሥራውን በአግባቡ ማከናወን
አለበት፡፡

ኮንትራትክተሩ ለመሰረት ግንባታ ያመጣው አሸዋ እርጥበት ያለው ከሆነ ግንባታው


ሲካሄድ እርጥበቱን ካለቀቀ በጠንጠረዥ ላይ ከተገለፀው የአሸዋ መጠን ላይ አንድ
ሳጥን አሸዋ መጨመር እንችላለን ነገር ግን አሸዋው ደረቅ ከሆነ በሰንጠረዥ ላይ
ከተገለፀው ውጭ ምንም አሸዋ አይጨመርም፡፡

4.1 ድንጋይ
ለመሰረት ድንጋይ ግንባታ የምንጠቀምበት ከአርማታ ጋር አብሮ የምንደባልቅው
ድንጋይ መጠን ከ 100 ሚ.ሜ - 150 ሚ.ሜ መሆን አለበት፡፡ ይሄ ድንጋይ ጠንካራ ንፁህ
መሆን አለበት፡፡

የድንጋዩ አይነትም ባልጩት (Basaltic) ለግንብ የምንጠቀምበት ድንጋይ እና ተመሳሳይ


የድንጋይ አይነት በጣም ጠንካራና ብዙ ጊዜ ሊቆይ የሚችል እና በቀላሉ ከኮንክሪቱ ጋር
መጣበቅ የሚችል መሆን አለበት፡፡ ንፅህናውን በተመለከተ ለመሰረት ግንባታው
የምንጠቀምበት ድንጋይ ከጭቃና ከአፈር እንዲሁም ከሰው እና ከከብት እዳሪ የፀዳ
መሆን አለበት፡፡

4.2 የመቀላቀል እና ውሃ የማጠጣት ሂደት


ለኮንክሪት ምሰሶ የመሰረት ግንባታ ኮንክሪት ሥራ የምንጠቀምበት ውሃ ለመጠጥ
የሚውል ንፁህ መሆን አለበት፡፡ እንደሌሎች የኮንክሪት ውህዶች ሁሉ ውሃውም
ከጭቃ፣ ከላሥቲክ፣ ከእንጨት፣ እንዲሁም ከከብት፤ ከሰው እዳሪ እና ከሌሎች
ማለትም በግንባታው ጥንካሬ ላይ እና በቆይታው ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶች
መኖር የለባቸውም፡፡

4.3 የኮንክሪት ውህደት እና የማጓጓዝ ሂደት


ለኮንክሪት ምሰሶ መሰረት ግንባታ የአሸዋ የሲሚንቶ እና ውሃ ውህድ /ሞርታር/ እና
የኮንክሪት ሥራውን ቢቻል በማሽን /ሚክሰር/ ካልተቻለ ግን በእጅ ማቡካት ይቻላል፡፡
የአዘገጃጀት ሁኔታው ኮንትራክተሩ ሥራውን የሚሰራው በእጅ እያቦካ ከሆነ የኮንክሪት

16
ውህዶቹ እንዳይባክኑ እና እንዳይቆሽሹ በሚያቦኩበት ጊዜ 2 /ሁለት/ ወይንም ከዚያ
በላይ (1m x 2m) የሆነ ጠፍጣፋ ዝርግ ብረት (Sheet Metal) መጠቀም አለበት ኮንክሪቱን
ወይንም የሲሚንቶ እና የአሸዋ ውህድ የሆነውን /ሞርታር/ ሲጠቀሙ ከታች
የተዘረዘሩንት የሥራ ሂደቶች መከተል አለባቸው፡፡
 አስቀድሞ የተሰፈረው አሸዋና ጠጠር በሚገባ ሁለት ጊዜ በተዘጋጀው ጠፍጣፋ
ስስ ብረት ላይ ማገላበጥ፡፡
 ተቀላቅሎ በተዘጋጀው አሸዋና ጠጠር ላይ በሰንጠረዥ ላይ የተጠቀሰውን
የሲሚንቶ መጠን በማድረግ እንደገና በአግባቡ ማገላበጥ /በደረቁ ሁለት ጊዜ
ማገላበጥ/፡፡
 በደንብ የተዋሃደውን ሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር ንፁህ ውሃን በመጠቀም
ለሥራ ቀላል በሆነ መልኩ የተቀላቀለውን ደረቅ የኮንክሪት ውህድ እየቆነጠሩ
ትክክለኛውን ቀለም /ግሪን/ አይነት እስኪያመጣ ድረስ ማዋሃድ ከዚያ በኋላ
የመድረቂያ ሰአቱን /ትኩስነቱን/ ሳያጠናቅቅ ባለው 25 ደቂቃ ውስጥ ሥራ ላይ
መዋል አለበት፡፡

4.4 ኮንክሪት የመሙላት እና የመጠቅጠቅ ሂደት


የተዘጋጀውን የኮንክሪት ምሰሶ የመሰረት ጉድጓድ ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት በውሃ
ማርጠብ ከዚያ በኋላ ኮንክሪቱን ለመጠቅጠቅ እንዲያመች ደረጃ በደረጃ እየሞሉ
በብረት ወይንም ሾል ባለ እንጨት መሸቅሸቅ ነው፡፡

5. ክትትል እና የጥራት ቁጥጥር


በግንባታው ላይ የግንዛቤ እጥረት እና አለመግባባትን ለማጥፋት የመጀመሪያውን አንድ ወይም
ሁለት የመሠረት ግንባታዎችን የግንባታ መምሪያው በሚያዘው መሠረት በጋራ ሆኖ በተግባር
ሰርቶ ማሳየት ይገባል፡፡

በሳይት የመሠረት ግንባታ ሰርቶ ማሳየት ላይ ከሲቪል ዲዛይን ቡድን ተወካይ፣ ከኮንትራክት
አስተዳደር ተወካይ እና በሳይቱ ተመድበው ባሉ ሱፐርቫይዘሮች ጋር በጋራ በመሆን ነው፡፡
ግንባታው በተግባር ተሰርቶ ካለቀ በኋላ ኮንትራክተሩ ወይም የኮንትራክተሩ ተወካይ አገነባቡ
ሙሉ በሙሉ እንደገባው እና በቀጣይ ለሚሰራው ስራ ሙሉ ኃላፊነት እንዳለበት መፈረም

16
አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ኮንትራክተሩ በደብዳቤ ሱፐርቫይዘር እንዲመደብለት መጠየቅ እና
ለግንባታው አሰፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ አለበት፡፡

ሳይት ሱፐርቫይዘር
ኮንትራክተሩ ማንኛውንም የመሠረት ግንባታ ሲሰራ ሳይት ሱፐርቫይዘር በቦታው መገኘት
አለበት፡፡ የሳይት ሱፐርቫይዘሩ በጥንቃቄ የጥራት ቁጥጥር እና ማንኛውንም ሂደት በስራ
ትዕዛዙ እና በግንባታ ዝርዝሩ እያንዳንዱን ምሰሶ የቁጥጥር ፎርም ላይ መሙላት አለበት፡፡

የመሠረት ግንባታ እና የምሰሶ ተከላ ስራ መለኪያ


ለክፍያ የደረሱ ስራዎች መለኪያ የኮንክሪት /ብረት/ ምሰሶ አይነት /የምሰሶ ጥንካሬና ርዝመት/
እና የመሰረት ግንባታው መደብ ነው፡፡

ክፍያ የሚከፈልባቸው የመሰረት ግንባታ የአርማታ ሙሌት (Casting) የተተከሉ ምሰሶዎች


ምንም አይነት ችግር የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡

የሚያገለግሉ መረጃዎችና ሰነዶች


በኮንክሪት ምሰሶ ለሚሰሩ የመሠረት ግንባታ እና የምሰሶ ተከላ ስራ የኮንትራት የስራ ዝርዝር
እና የመሠረት ግንባታው ዲዛይን የተዘጋጀ ሲሆን የስራ ዝርዝር የመሠረት ዲዛይን ከማቴሪያል
ጥራት ጋር እና የአገነባብ /የአሰራር/ ሁኔታ የሌላ ኮንትራትን መነሻ /መረጃ/ አድርጐ መጠቀም
አይቻልም፡፡

 10 ሜትር ኮንክሪት ምሰሶ የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን ሠንጠረዝ 1


 11 ሜትር ኮንክሪት ምሰሶ የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን ሠንጠረዝ 2
 የእንጨት ምሰሶ የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን ሠንጠረዝ 3
 የብረት ምሰሶ የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን ሠንጠረዝ 4
 8 ሜትር ኮንክሪት ምሰሶ የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን ሠንጠረዝ 5

የብረትና የእንጨት ምሰሶዎችን የማቆም ስራ ዘዴ


1. አጠቃላይ

16
በአጠቃላይ የተለየ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር ለሁሉም የእንጨትና የብረት ምሰሶዎች የማቆም
ስራ በተፈጥሮ አፈር ይሆናል።
ምሰሶ ለማቆም የሚከተለውን መንገድ መከተል ይኖርብናል፦
 በቅድሚያ ጉድጓድ መቆፈር
 ምሰሶውን ወደተቆፈረው ጉድጓድ መክትተ
 አፈር በመመለስ በመጠቅጠቂያ በመጠቅጠቅ ይሆናል
የሚመለሰው አፈር ለምሰሶ ማቆሚያ ተቆፍሮ የወጣውን አፈር፥ኮረት በመቀላቀል ወይም ከሌላ ቦታ
የመጣ ኮረት ያለው አፈር መሆን ይችላል። የምሰሶ ማቆሚያ መሰረት ጥንካሬ በሚሞላው
የተመረጠው የአፈር አይነትና በአሞላል(አጠቃጠቅ) ይወሰናል። የመሰረት ዲዛይን ስታንዳርድ
በምሰሶው ላይ በሚኖረው የነፋስ ግፊት፥የሽቦ ውጥረት፥ በምሰሶው ላይ በሚሰቀሉ ማቴሪያሎች
ክብደትና በመስኩ ላይ ባለው የአፈር አይነት ነው።

2. የአፈር አይነት አመዳደብ

የአፈር አይነት አመዳደብ ከኮንክሪት ምሰሶ ጋር ተመሳሰሳይ ነው።

3. ቁፋሮ ፡- ቁፋሮ ከመጀመሩ በፊት አካባቢው ከማንኛውም ቆሻሻ ነክ ከሆኑ ነገሮች መጽዳት
አለበት።ቁፋሮው የመሰረቱን(የችካሉን) ሴንተር፥ የምሰሶውን አይነትና የመስመሩን ቀጥተኛነት
ያገናዘበ መሆን አለበት። የሚቆፈረው ወደታች ቀጥ ብሎና ክብ ሆኖ ሲሆን የቁፋሮውም መጠን
በግንባታ መመሪያው መሰረት መሆን አለበት። ቁፋሮው በዲዛይኑ መሰረት ሆኖ ከላይ እስከ
ታች ተመሳሳይ መሆን አለበት። በቁፋሮ ወቅት ሱፐርቫይዘሩ የአፈሩ አይነትመደብ የግንባታ
ዝርዝሩ ከሚየዘው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ማፅደቅ አለበት። የመሰረት ቁፋሮው ጥልቀትና
ስፋት፥ የምሰሶው ቁመት፥ የመስመሩ አይነት፥ የአፈሩ ፀባይ በግንባታ መመሪያው መሰረት
መሆን አለበት።
4. ለእንጨትና ለብረት ምሰሶው ማቆሚያ የሚሞላው ማቴሪያል የተፈጥሮ አፈርን መሰረት ያደረገ
ነው።
ለመደብ 1 እና ለመደብ 2 የአፈር አይነት የተቆፈረውን አፈር መጠቀምና መሙላት ይቻላል።
ለመደብ 3 የአፈር አይነት የተቆፈረውን አፈር በማስወገድ ከሌላ ቦታ የመጣ የተመረጠ ኮረት
ያለው አፈር መጠቀም ይቻላል።ለመደብ 2 ና 3 የአፈር አይነት ምሰሶ ከማስገባታችን በፊት
ለመደብ 2 እና 3 አስር ሳንቲ ሜትር ኮረትመሬት ላይ በማንጠፍ መሞላትና በደንብ መጠቅጠቅ

16
አለበት፡፡ የተመረጠው አፈር በሚሞላበት ጊዜ በየሀያ ሳንቲ ሜትሩ በደንብ በመጠቅጠቂያ
መጠቅጠቅ አለበት።

ምእራፍ አምስት
የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ቮልቴጅ ኪ.ቮ መስመር የግንባታ ስራ

16
1. የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር የግንባታ ስራ
1.1. ጉድጓድ ቁፋሮ እና ምሰሶ ተከላ

የጉድጓድ ጥልቀት እንደ ምሰሶው ኣይነት፣ቁመት እና የአፈር አይነት በዚህ መምሪያ ምእራፍ 4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን
ኣለበት::
1.2. የምሰሶ አተካከል
 ሁሉም ምሰሶዎች መተከል ያለባቸው የሚታጠፉ ካልሆነ በስተቀር ወጣ ገባ ሳይል ቀጥ ብለው
ቀጥተኛ መስመሩን ተከትለው መሆን ኣለበት፣
 ምሰሶዎች ከውሃ መውረጃ ቦይ ርቀው መተከል አለባቸው፣
 በምሶሶዎች መካከል ያለው ርቀት ሌላየለውጥ መምሪያ እስካልተሰጠ ድረስ በፀደቀው ዲዛይን
መሠረት ወይም በዚህ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፣
 የመስመሩ ግራ እና ቀኝ ርቀት ስታንዳርዱን የጠበቀ መሆን አለበት፣ (ምእራፍ 4 መመልከት
ይቻላል)
 የአንገል ቦታዎች ወይም የመስመር ማብቂያ (dead end) ላይ ደጋፊ ምሰሶዎች በትክክል
መገጠም አለባቸው፣
 Guy Wire በትክክል አንግሉን ጠብቀው በአንግሉ ቀጥታ ተቃራኒ መገጠም ሲኖርባቸው
ኢንሱሌተርም(stay insulator) በትክክል መግጠም ያስፈልጋል፡፡ ወደ መሬት የሚቀበረውም
መወጠሪያ በትክክል የሚፈለገው ጥልቀት ላይ Guy plate ላይ በማሰር ወይም የድንጋይ ጥቅልል
በመስራት ጋደል ተደርጎ መቀበር አለበት፣
1.3. የምሰሶ ተጓዳኝ ዕቃዎች /Accessories/

የምሰሶ አክሰሰሪዎች ግንባታ የሚከተሉትን ያጠቃልላል

 ሁሉም የምሰሶ ተጓዳኝ ዕቃዎች ክሮስ አርም፣ ፒን፣ ሁክ፣ ኢንሱሌተር፣ የክሮስ አርም ድጋፍ /Tie
Strap/ በትክክል ጠብቀው መገጠም አለባቸው፣
 ከሮስ ኣርሞች ሲገጠሙ ውሃ ልክ የጠበቁ መሆን ኣለባቸው

 የሚገጠሙት ኢንሱሌተሮች(የፒንና የዲስክ) ያልተሠበሩና ያልተሰነጠቁ መሆን አለባቸው፣

1.4. የሽቦ መዘርጋት


ሀ) ለመካከለኛና ዝቅተኛ ቮልቴጅ የመስመር ግንባታ የሚሆኑ የሽቦ ዓይነቶች የሚከተሉት ናቸው

16
 AAAC 95 mm2/ AAAC 50 mm2 ለ 33 ኪ.ቮ: ለ 15 ኪ.ቮ እና ለ 19 ኪ.ቮ የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር
የምንጠቀምበት የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የሽቦ ዓይነቶች ናቸው።
 የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦ ዓይነት ለመምረጥ ዋናው መስፈርት መስመሩ ያለው ርቀት ሲሆን
እንዳስፈላጊነቱ በጸደቀው ዲዛይን መሰረት የሚከተለውን እንጠቀማለን።
o AAAC 95 mm2 ለዋና መጋቢ መስመሮች(main feeder) ፤ርቀት ላላቸው ና ከፍተኛ ጭነት
ላላቸው መስመሮች
o AAAC 50mm2 ለተገንጣይ መስመሮች(branching lines) ና ቅርብ ርቀት ላላቸው መጠቀም
ይቻላል፡፡

በተጨማሪም በዚህ መምሪያ መሰረት እንዳስፈላጊነቱ ታይቶ ትክክለኛውን ሽቦ በኣግባቡ ቦታ ላይ እንዲውል


ሪፖርት መደረግ ኣለበት::

ለ) ሽቦ በሚዘረጋበት ወቅት የሚከተሉትን ነጥቦች መገንዘብ ያስፈልጋል፤

 የሽቦ መጠቅለያ ድራሞች ከቦታ ቦታ በሚጓጓዙበት ጊዜ እንዲሁም ለዝርጋታ በሚተረተሩበት ወቅት


/እንዳይጦዝ/ እንዳይበተኑ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
 ሽቦዎች ሲዘረጉ ከአላስፈላጊ መጋጋጥ ለማዳንና የዝርጋታ ስራውን ለማፋጠን ለቀጥታ መስመር
እንዲሁም ለአንግል ፑሊዎች ያስፈልጋሉ። በፑሊ ሽቦ በሚጎተትበት ወቅት ሌላ አክሰሰሪዎችን አብረው
እንዳይጎተቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል።
 የመካከለኛና ዝቅተኛ ቮልቴጅ የመስመር ሽቦዎችን በእጅና እንዲሁም በማሽን መጎተት ይቻላል
 የጦዙ (የተቆረጡ) ሽቦዎችን ለመቀጠል ወይም /ቀሰም/ Mid span joint /ፋሻን መጠቀም ከተቀጠለ
በኃላ የሚከሰትን መላቀቅ እና መላላት ያስቀራል።
 የሽቦ ገመዶች ከመጠን ያለፈና ያነሰ ሐይልን ለመቆጣጠር ዊንችና ዋየር ግሪፕን መጠቀም ያስፈልጋል።
 ኢንሱሌተሮች (ሲኒዎች) ና ሌሎች አክሰሰሪዎች በክሮስ አርም ላይ በለጋቱራ/tie wire/ በሚገባ
መታሰራቸውን ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ለ AAAC50 እና AAAC 95 የሽቦ ገመዶች ባለ 16 ና ባለ 25 ሚሊ
ሜትር ስኬር ለጋቱራ (እንደየ ቅደም ተከተላቸው) መጠቀም ያስፈልጋል።
 የሽቦ ገመዶች ለማገናኘት ሲፈለግ
o AL/AL PG Clamp -aluminuim ሽቦን ከ aluminium ሽቦ ጋር ለማገናኘት ይጠቅማል
o AL/CU PG Clamp -aluminium ከ copper ሽቦ ጋር ለማገናኘት ይጠቅማል

2. የዝቅተኛ መስመር ግንባታ

16
2.1. ጉድጓድ ቁፋሮ እና ምሰሶ ተከላ
 የጉድጓድ ጥልቀት እንደ ምሰሶው ኣይነት እና ቁመት በዚህ መምሪያ ምእራፍ 4 በተጠቀሰው መሰረት መሆን
ኣለበት::
 ሁሉም ምሰሶዎች መተከል ያለባቸው የሚታጠፉ ካልሆነ በስተቀር ወጣ ገባ ሳይል ቀጥ ብለው ቀጥተኛ
መስመሩን ተከትለው መሆን ኣለበት፣
 ምሰሶዎች ከውሃ መውረጃ ቦይ ርቀው መተከል አለባቸው፣
 በምሶሶዎች መካከል ያለው ርቀት ሌላ የለውጥ መምሪያ እስካልተሰጠ ድረስ በፀደቀው ዲዛይን መሠረት ወይም
በዚህ መምሪያ ላይ በተጠቀሰው መሰረት መሆን አለበት፣
 የመስመሩ ግራ እና ቀኝ ርቀት ስታንዳርዱን የጠበቀ መሆን አለበት፣ (ምእራፍ 4 መመልከት ይቻላል)
 የአንገል ቦታዎች ወይም የመስመር ማብቂያ (dead end) ላይ ደጋፊ ምሰሶዎች በትክክል መገጠም አለባቸው፣
 Gay Wire በትክክል አንግሉን ጠብቀው መገጠም ሲኖርባቸው ኢንሱሌተርም(stay insulator) በትክክል
መግጠም ያስፈልጋል፡፡ ወደ መሬት የሚቀበረውም መወጠሪያ በትክክል መቀበር አለበት፣
2.2. የአክሰሰሪዎች ተከላ
 ሁሉም የዝቅተኛ መስመር የአክሰሰሪዎች ሁክ /የሰስፔንሽንና ዴድ ኢንድ/; ክላምኘ /የሰስፔንሸንና ዴድ ኢንድ/
በትክክል መግጠም ያስፈልጋል፡፡
 ኣስፈላጊ የሆኑ Connectors በትክክለኛው ቦታ ከታች በተዘረዘረው መሰረት መጠቀም
o AL/AL Piercing clamp_ በኬብል የተሸፈነን aluminuim ሽቦን በኬብል ከተሸፈነ aluminium ሽቦ ጋር
ለማገናኘት ይጠቅማል
o AL/Cu Piercing clamp_በኬብል የተሸፈነን aluminuim ሽቦን ከ copper ጋር ለማገናኘት ይጠቅማል
ይህም በተለይ ለ earthing እና ለ service connection ይጠቅማል፡፡
 በየ 250 ሜ ኒውትራል መስመር ከግራውንድ ተቀባሪ ሮድ ጋር በትክክል መገጠማቸውን በማረጋገጥ ወደ መሬት
በአግባቡ ስታንዳርዱን ጠብቆ መቀበር አለበት፣

2.3. የ LV Cable ዓይነቶች

የተለያየ አይነት የ 3 ፌዝ፣ 2 ፌዝና ባለ አንድ ፌዝ ኬብል ያለ ስለሆነ እንደ አስፈላጊነቱ በተገቢው ቦታ ለመጠቀም ካለው አቅርቦት
አንፃር ታሳቢ በማድረግ

 70% 3 ፌዝ
 25 % 2 ፌዝ
 5% 1 ፌዝ

ለመጠቀም የታሰበ ሲሆን በተቻለ መጠን አግባብ ባለው ቦታ 3 ፌዝና ቀሪውን በ 2 ፌዝ ና አንድ ፌዝ ኬብል እንዲሠራ መደረግ
ይኖርበታል፡፡

16
የኬብል የኬብል
መደብ ኣይነት ኣጠቃቀም ማብራሪያ

- 3 ባለ 50 ሚሚ 2 መጠን ስፋት ያላቸው


3 ፌዝ ሆኖ ከፍተኛ ጭነት ላለበት ቦታ ና ሶስቱንም ፌዝ መስመር ለማገናኘት
የሚያገለግሉ ሽቦዎች ፡
በተጨማሪም የመንገድ መብራት
- 16 ሚሚ 2 ለመንገድ መብራት
3x50+25+16
ባለ ሶስት ለሚያስፈልግበት ቦታ * - 25 ሚሚ 2 ለ Earthing
ፌዝ
3x50+25 3 ፌዝ ሆኖ ከፍተኛ ጭነት ላለበት ቦታ* - 3 ባለ 50 ሚሚ 2/ 35 ሚሚ 2 መጠን
ስፋት ያላቸው ሶስቱንም ፌዝ መስመር
3x35+16 3 ፌዝ ሆኖ መካከለኛ ጭነት ላለበት ቦታ* ለማገናኘት የሚያገለግሉ ሽቦዎች ፡
- 25 ሚሚ/16 ሚሚ ለመንገድ መብራት/
3x25+16 3 ፌዝ ሆኖ ዝቅተኛ ጭነት ላለበት ቦታ* ለ Earthing

2X35+16 2 ፌዝብቻ የሚያስፈልግበት ሆ ኖ - 2 ባለ 35 እና 25 ሚሚ 2 መጠን ስፋት


መካከለኛ ጭነት ላለበት ቦታ* ያላቸው ሁለት ፌዝ መስመር ለማገናኘት
ባለ ሁለት 2 ፌዝ ብቻ የሚያስፈልግበት ሆ ኖ ዝቅተኛ የሚያገለግሉ ሽቦዎች ፡
2x25+16
ፌዝ ጭነት ላለበት ቦታ - 16 ሚሚ 2 ለ Earthing

ባለ ኣንድ በጣም አነስተኛ ጭነት ያለበትና ረጅም ርቀት ያለ ጭነት - 1 ባለ 16 ሚሚ 2 ለ ነጠላ ፌዝ


2X16
ፌዝ የሚጓዝ መስመር - 16 ሚሚ 2 ለ Earthing

* ዲዛይን በጸደቀው መሰረትና ለመንደሩ ቅርብ ባለው የዕቃ ግምጃ ቤት ባለው የኬብል ኣይነት
ታሳቢ ባደረገ መልኩ ተመጣጣኝ የሆኑትን በመጠቀም ከላይ የተዘረዘረው ተግባራዊ
ይሆናል፡፡

16
ምእራፍ ስድስት
የትራንስፎርመር ተከላ (TRANSFORMER INSTALLATION)

1. የትራንስፎርመሩ አቀማመጥ
 የትራንስፎርመር አቀማመጥ በቀላሉ ከ MV መስመር ጋር ሊገናኝ የሚያስችል መሆን አለበት፤
 የትራንስፎርመር አቀማመጥ በጥገና ወቅት በቀላሉ ሊደረስበት የሚያስችል ቦታ መሆን አለበት፤
 ከትራንስፎርመሩ የመጨረሻው ተጠቃሚ ግለሰብ ያለው ርቀት ከ 650 ሜ መብለጥ የለበትም። ይህ
ቢሆንም እንደኣ ስፈላጊነቱ በጸደቀው ዲዛይን መሰረት እስከ 750 ሜ መጠቀም ይችላል።
 ሁሉም የትራንስፎርመር Fixtures የተቀመጠላቸውን ስታንዳርድ ጠብቀው በትክክል ሳይንሻፈፍ መግጠም
አለባቸው፣
 የመብረቅ መከላከያ፣ የመስመር ማቋረጫ እና ፊዩዝ በተገቢው መንገድ መግጠም አለባቸው፣
 ትራንስፎርመሩ ዘይቱ ሙሉ ያለ ምንም ፍሰት /እንጥብጣቤ/ መሆኑን ማረጋገጥ ፣
 የትራንስፎርመሩ ገቢ እና ወጪ ኢንሱሌተሮች ጤናማ እና በትክክል መገጠማቸውን ማረጋገጥ፣
 የትራንስፎርመር ግራውንድ ሮድ በአግባቡ ስታንዳርዱን ጠብቆ መቀበር አለበት፣
 የመብረቅ መከላከያው የትራንስፎርመር አካል እና ኒውትራል መስመር ከግራውንድ ተቀባሪ ሮድ ጋር በትክክል
መገጠማቸውን ማረጋገጥ፡፡ የማገናኛውም መደብ ሽቦ ከ 35mm2 ማነስ የለበትም፣

ዲስትሪቢዩሽን ፊዩዝ ቦክስ

 ሳጥኑ ከመሬት ያለው ከፍታ ስታንዳርዱን ጠብቆ መገጠሙን ማረጋገጥ፣


 ወጪ እና ገቢ ኬብሎች ስታንዳርዱን የጠበቁ እና በፀደቀው ዲዛይን መሠረት መሆን አለበት Loss እንዳይኖረው
በደንብ መጥበቁን ማረጋገጥ፣
 የሚገጠመው ፊዩዝ በትራንስፎርመሩ መጠን መሆኑን ማረጋገጥ፣

Hrc fuse rating


የትራንስፎርመር መጠን (KVA)
(A)
25 KVA 63 A
50 KVA 63 A

100 KVA 100 A

200 KVA 160 A

16
2. ፕሮቴክሽን፤ መስመር ማቋረጫ ስዊች እና መነሻ ነጥብ (protection, load break switch and Tapping Point)

መስመር ማቋረጫ /LBS/ ስዊች አቀማመጥ መምሪያ


 ከማንኛውም ሰብስቴሽን ለሚወጣ መጋቢ መስመር ከመነሻው ሊገጠምለት ያስፈልጋል።
 በተጨማሪ በቀጣዩ መስመር ላይ በየ 20 ኪ.ሜ ስዊች ሊካተት ያስፈልጋል። (ይህ ከሰብስቴሽ
ሰብስቴሽን ሊለያይ ይችላል)
ድሮፕ አውት ፊውዝ እንደ ዲስኮኔክተር አቀማመጥ መምሪያ
በከተማዋ መሐል የሚያልፍ ካልሆነ በቀር በእያንዳንዱ መነሻ ነጥብ (tapping point) MV መስመር መነሻ
ላይ ድሮፕ አውት ፊውዝ እንደ ዲስኮኔክተር እንጠቀማለን፤ መካከለኛ መስመሩ (MV) መስመሩ በቀጥታ ወደ
ትራንስፎርመሩ የሚገባ (Online) ከሆነ በዚህ ወቅት ድሮፕ አውት ፊውዙ የትራንስፎርመሩ አካል ይሆናል
እናም ምንም አይነት ዲስኮኔክተር አያስፈልግም። በምንም አይነት መልኩ ዲስኮኔክተር የሌለው መስመር
ኮሚሽን መደረግ የለበትም።
ከድሮፕ አውት ፊውዝ ጋር ሊካተት የሚያስፈልገው ፊውዝ ሊንክ በሚከተለው ሰንጠረዝ ተካቷል።
ከተገለፀው መጠን ማንኛውም አይነት ለውጥ ትራንስፎርመሩ ላይ አደጋ ስለሚያደርስ ትክክለኛውን ዝርዝር
መምረጥ አስፈላጊ ነው።

ፊውዝ ኤለመንት/ሊንክ
ትራንስፎርመር
(KVA)
33KV 15KV
25 1A 1A
50 1A 2A
100 2A 5A
200 5A 10 A

16
ምእራፍ ሰባት

SWER /ባለ አንድ ሽቦ በመሬት ውስጥ ተመላሽ የኤሌክትሪክ መስመር/


SWER በዋናነት አንድ ሽቦንና መሬትን እንደ ተመላሽ ማስተላለፊያ ኮንዳክተር በመጠቀም የሚሠራ ወጪ ቆጣቢ የመካከለኛ
መስመር ነው፡፡ ይህም ሁለት ዓይነት የአሰራር ዘዴ አለው፡፡
1. Direct Tapping /Shield Wire Scheme: ይህ ሰብስቴሽን ያለው የትራንስፎርመር ኮኔክሽን Y-Y ከሆነ ከሰብስቴሽን
አስፈላጊውን ተጨማሪ Earthing በማድረግ መጠቀም ወይም በ Shield Wire /አራት ኮንዳክተር በመሳብ ሦስት ፌዝና አንድ
የመብረቅ መከላከያ (Shield Wire) መጠቀም የሚያስችለን ወጪ ቆጣቢ የመካከለኛ መስመር ነው፡፡ በዚህ መስመር ላይ
ለትናንሽ ከተሞች ማለትም አጠቃላይ እስከ 25A ጭነት ድረስ በ 19 ኬቪ በቀጥታ በአንድ ገመድ መቀጠል የሚያስችል ዘዴ
ነው፡፡
Grounding system of HV/MV Substation(star-star connection)

16
2. SWER Using Isolating Transformer: ይህ አይነት የመስመር ዝርጋታ በተለይ አገልግሎት በመስጠት ላይ ካሉ ማከፋፈያ
ጣቢያዎች ከሚወጡ መጋቢ መስመሮች ላይ ለማገናኘት ለማድረግ የምንጠየቀምበት ዘዴ ነው፡፡ በአብዛኛው በኢትዮጵያ
ሰብስቴሽን ያሉ ፓወር ትራንስፎርመሮችን ኮኔክሽን Y-Δ ስለሆነ ባለ ሶስት ማስተላለፊያ መስመር ስለምንጠቀም ለዚህ አመቺ

የሆነ አሠራር ነው፡፡ ይህም ከ 33 ኬቪ ሶስተ መስመሮች ላይ ሁለቱን በመውሰድ በ Isolating /insulating
Transformer በመጠቀም ከ 33 ኬቪ ወደ 19 ኬቪ የሚቀይርና በተጨማሪም የ 33 ኬቪ ኔትዎርክ ሲስተምን ከ 19 ኬቪ
(SWER) ለመለየት (Isolate/Insulate) በማድረግ ወደ ባለ አንድ ኮንዳክተር የመካከለኛ መስመር ለመዘርጋት
የምንጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ ለዚህም አላማ የተዘጋጀ 33/19 ኬቪ፣ ባለ 100፣200 እና 315 KVA Isolating Transformer
እንጠቀማለን፡፡ በአሁኑ ሠዓት በአብዛኛው እየተጠቀምን ያለነው ይህን የ SWER አሠራር ነው፡፡
Grounding system of HV/MV Substation(star-delta connection)

16
Tapping by using Isolating /insulating Transformer

SWER በዋናነንት የምንጠቀመው ለገጠር መስመሮች ሲሆን፤ መጋቢ የ SWER መስመር ትልቁ መሸከም ያለበት ጭነት ከ 25AMP
መብለጥ የለበትም ይህም ከወጪ አንፃር፤ ከፌዞች አለመመጣጠን /Phase Unbalance/፤ እንዲሁም Protection device አንፃር
ታይቶ የቀረበ ወሠን ነው፡፡

3. የ SWER ጥቅሞች
 ከሦስት ፌዝ ከመዘርጋት አንፃር ጊዜ ቆጣቢ ነው፣

 ከሦስት ፌዝ ስራ አንፃር ወጪና የተለያዩ ግብአቶችን (Resource) ይቆጥባል፣

 የመንደሮቹ እድገት ታይቶ ወደ ሦስት ፌዝ ለመቀየር ከታሠበ በቀላሉ ማሳደግ ይቻላል ማለትም ተጨማሪ ምሰሶ
መትከልና ሁለት ፌዝ ኮንዳክተር መዘርጋት ይቻላል፣
 አንድ ኮንዳክተር ስለሆነ በምሰሶዎች መካከል ያለውን ርቀት ከፍ በማድረግ ከ 150 እስከ 300mt መጠቀም
ስለሚያስችል በተለይም አስቸጋሪ ለሆኑ ቦታዎች አመቺ ነው፣
 ለጥገና ቀላል ነው /ከጊዜና ከ Resource አንፃር፣

 በሦስት ኮንዳክተሮች መካከል የሚፈጠረውን የመነካካት ሁኔታ ና እሳት በመፍጠር ከፍተኛ የሆነ የደን ቃጠሎ
እንዳይከሰት ይረዳል፣
 በተጨማሪም በሶስት ኮንዳክተር ጊዜ የነበረውን የኮንዳክተርና ከዛፎች ጋር ያለው ግጭት ይቀንሳል፡፡

4. SWER ለመዘርጋት መጠናት ያለባቸው መስፈርቶች (SWER Feasibility Criteria)

የገጠር መንደሮች በ SWER ኢንርጃይዝ ለማድግ ከታች የተዘረዘሩት መረጃዎች መሰብሰብና መሟላት አለባቸው፡፡

1. ከተማው ከሰብስቴሽን ያለው ርቀት፤ ይህም በ Isolating Transformer የምንጠቀም ከሆነ ከ 70 ኪሜ በላይ ቢሆን
ይመረጣል፡፡ በ Shield wire (direct tapping) የምንጠቀም ከሆነ ግን በማንኛውም ርቀት ላይ ያሉ መንደሮች
ሊሆኑ ይችላሉ፣

16
2. ከታፒንግ ያለው ርቀተ በ km፤ ይህም በትንሹ 5km እና ከዛ በላይ መሆን አለበት፣
3. የ SWER መስመር ለሚዘረጋለት መንደር ቀጥሎ ያሉ መንደሮች ወይም ከዋናው የ 19 ኬቪ መስመር በሚይልፍበት
አካባቢ ያሉ ከተሞች ወይም ታኘ ተደርጐ ሊዘረጋላቸው ከሚችሉ እና ሌላ መስመር ሊደረስባቸው የማይችሉ
እንዲሁም ብዙ ጭነት የሌላቸው መንደሮች ካሉ በደንብ ተጠንቶ ታሳቢ መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም የሁሉም
ከተሞች አጠቃላይ ጭነት ከ 25A መብለጥ የለበትም፡፡ ከበለጠ ግን የ Phase unbalance ሊፈጥር ስለሚችል
መጠንቀቅና ማጣራት ያስፈልጋል፡፡
4. በመንደሩ ውስጥ ያሉ የቤቶች ብዛት /ኤሌክትሪክ ሊያገኙ የሚችሉ ቤቶች/ እና የአገልግለሎት መስጫ ማዕከላት ብዛት
መታወቅ አለበት፣
5. የልዩ ጭነቶች ማለትም ወፍጮ፣ ውሃ ፓምኘ፣ መፈልፈያ እና የመሳሰለት ብዛትና የኤሌክትሪክ ፍጆታ (kw) መታወቅ
አለበት፣

6. ከላይ በቁጥር 4 እና 5 በተጠቀሱት መሰረት ከተማው አመቺ እንደሆነ ለመለየት የሚከተለውን ግምት መጠቀም
ይቻላል፡፡
 ለመኖሪያ ቤቶች ………………………. 0.2 KW
 ለአገልግሎት መስጫ ማዕከላት………… 3 KW
 የልዩ ጭነቶች………………………….. 15 KW
7. ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ የአካባቢው የወደፊት ሁኔታ ማለትም ፋብሪካዎች /ኢንዱስትሪዎች ሊገኙበት የታቀደ
መሆን የለበትም ይህንንም ከወረዳው ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር ማጣራት ይገባል፡፡

5. የ SWER 19 ኬቪ መስመር ዝርጋታ /ኮንስትራክሽን

የምሰሶ ዓይነት፡- ወጪን ከመቆጠብ አነፃር በእንጨት/ በብረት ምሰሶ ቢሰራ ይመረጣል ሆኖም ግን አስፈላጊ በሆነበት ቦታ
እና ረጅም ስፓን ለመጠቀም ኮንክሪት ምሰሶ መጠቀም ይቻላል፡፡ ትክክለኛውን የስፓን አጠቃቀም
በሰርቬይና ዲዛይን ክፍል ውስጥ ያለውን ሰንጠረዥ መመልከት ይቻላል፡፡

የኮንዳክተር አይነት፡- የኮንዳክተር አይነት 19 ኬቪ የተለያዩ መጠቀም ይቻላል ወደፊት በቀላሉ ወደ 33 ኬቪ ለመቀየር
እንዲያመቸን AAAC 95mm2 መጠቀም ይቻላል ሆኖም ግን አስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥ ላለበት
ረጅም ርቀት ስፓን 150 ሜትር እስከ 300 ሜትር መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ AAAC 50mm2
መጠቀም ይቻላል፡፡

16
የ 19 ኬቪ አሴምብሊ፡-ለነጠላ ፌዝ ኮንዳክተርን ለመሸከም የተለያዩ አክሰሰሪዎች የተዘጋጁ ስለሆነ የኮንስትራክሽን ድሮዊንግ
በመከተል ትክክለኛውን አክሰሰሪ በመጠቀም መስራት ይቻላል፡፡

6. የ SWER 19 ኬቪ ትራንስፎርመር
በ SWER ስንጠቀም ሁለት አይነት ትራንስፎርመሮች አሉ፡፡
1. Isolating Transformer (IT) 33/19 ኬቪ፡- ይህ ትራንስፍርመር ከላየ ለመግለፅ እንደተሞከረው የ SWER
መካከለኛ መስመር ለመዘርጋት ወደ ታቀደለት ከተማ የሚሄደው የ 19 ኬቪ ታኘ የሚደረግበተ ባታ ላይ የሚቀመጥ
ሲሆን 33 ኬቪን ወደ 19 ኬቪ ለመየቀር እና በተጨማሪም በሰስስቴሽን ላይ ምንም አይነተ ተጨማሪ earthing
ሳያስፈልግ IT በሚተከልበት ቦታ ላየ ትክክለኛ earthing መጠቀም የሚያስችለን የትራንስፍረመር አይነት ነው፡፡
2. Distribution Transformer 19/0.4 ኬቪ፡- ይህ ትራንስፎርመር ከ 19 ኬቪ ወደ 400 ቮ ወይም ወደ ዝቅተኛ
መስመር መቀየር የሚያስችል ሲሆን ከሌሎች የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ በሦስት
ፌዝ ቦታ አንድ ፌዝ ዝቅተኛ መስመር መቀየሩ ነው፡፡

ሀ) Isolating Transformer አሰራር/ኢንስቴሌሽን


ከታች በስዕሉ ላይ እንደተመለከተው IT የሚቀመጥበት ቦታ ከ 33 ኬቪ ታኘ የሚደረግበት ቦታ ላይ ነው፡ ይህም ሁለት ፌዝ
የ 33 ኬቪ መስመር ታኘ በማድረግ ከ 33 ኬቪ Surge Arrestor እና Drop out fuse (as section) ለመጠቀም እንዲያመች
ገቢው ላይ ተገናኝቶ ሁለቱም ፌዝ ኮንዳክተሮች ከትራንስፎርመሩ ገቢ ቡሺንግ ላይ ይታሰራል፡፡ የትራንስፎርመሩ ገቢ ሁለት
ቡሺንግ ብቻ ስላለው በቀላሉ መለየት ይቻላል፡፡ በወጪው በኩል ተመሳሳይ ሁለት ቡሺንግ መጠናቸው አነስ ያለ የሚገኙ ሲሆን
አንዱ የ Grounding /Earthing ( ) ምልክት ያለበት ሲሆን ሌላው የ 19 ኬቪ ወጪ ነጣላ ፌዝ የሚታሰርበት ነው፡፡
በተጨማሪም ወጪው የ 19 ኬቪ መስመር ከ 19 ኬቪ Surge Arrestor Drop Out Fuse በኩል በማገናኘት /እንደ ሴክሽን
እንዲያገለግል/ በማድረግ መስመሩ ወደ መንደሩ እንዲሄድ ያደረጋል፡፡
ለ) የ Isolating Transformer Earthing
ለ IT ሁለት አይነት የተነጣጠሉ earthing ገመዶች ይኖሩታል፤ እነዚህም፡-
1. ከትራንስፎርመር (IT) secondary bushing /19kv በኩል የEarthing ምልክት ያለበት ቡሺንግ ጋር የሚገናኘው
የኮፐር ኮንዳክት ከሌላ ነገር ጋር ሳይገናኝ በቀጥታ ወደ መሬት ውስጥ ሄዶ ትራንስፎርመሩ በሚተከልበት ምሰሶዎች ዙሪያ
ዕኩል 4 ሜትር ርቀት ያላቸው ቢያንስ 60ሴሜ ወደ መሬት ገብቶ ሶስት Earthing rod በመቅበር ሶስቱንም በኮፐር
ኮንዳክተር አገናኝቶ ከትራንስፎርመሩ ከሚመጣው ኮፐር ኮንዳክተር ጋር ማገናኘት፡፡ የዚህ Earthing ዋና ጥቅም የነጠላ
ፌዝ በመጠቀማችን የሚፈጠረውን ፌዝ አለመመጣጠንን /phase unbalance/ በመሬት ውስጥ እንዲሄድ በማድረግ
ወደ ሰብስቴሽን Earthing transformer እንዳይሄድ ቀላል የሆነ ወይም low ohmic earth return path በመፍጠር

16
ከሰብስቴሽን እይታ አንፃር ትኩረት የማይሰጠው fault or insignificant fault እንዲሆን ያስችለዋል፡፡

2. ይህ ለዲስትሪቢዩሽን ከምንጠቀመው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ለ Earthing የምንጠቀመውን ኮፐር ኮንዳክተር ከSurge


Arrestor, Drop out fuse, Transformer body እንዲሁም ከCross arm ጋር በማያያዝ ትራንስፎርመሩ ካለበት
ቢያንስ 20 ሜትር በአየር ላይ በመሳብ በቅርብ ወደ ሚገኝ ምሰሶ ላይ በማሰር ወደ መሬት ውስጥ መቅበር የዚህ
Earthing ዋና ጥቅም በ19ኬቪ መስመር ላይ በሚፈጠሩ ብልሽቶች ምክንያት የሚፈጠሩ over current እና over
voltage ለመከላከል ነው፡፡

ሐ) የ Distribution Transformer Earthing

1. ለጥንቃቄ 33 ኬቪ ለዲስትሪቢዩሽን ከምንጠቀመው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ለ Earthing የምንጠቀምበት ኮፐር ኮንዳክተር


ከ Surge Arrestor, Dropout fuse, Transformer body እንዲሁም ከ Cross arm ጋር በማያያዝ ወደ መሬት
ውስጥ መቅበር፡፡ የዚህ Earthing ዋና ጥቅም በ 19 ኬቪ መስመር ላይ በሚፈጠሩ ብልሽቶች ምክንያት የሚፈጠሩ Over
current እና Over voltage ለመከላከል ነው፡፡
2. በተጨማሪም የ earth return current ለብቻው የተነጠለ /Separate/ እንዲሆን የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሩን
ኘርይሜሪ ቡሺንግ Earthing ምልክት ያለበትን ለብቻ በኮፐር ኮንዳክተር እንዲቀበር መደረግ አለበት፡፡

16
ምእራፍ ስምንት
ሱፐርቪዥንና ኮሚሽኒንግ

1. ሱፐርቪዥን /ቁጥጥር/

የሱፐርቪዥኑ ስራ በቂ የሰው ሀይልና ማቴሪያሎች መኖራቸውን የሚያረጋግጥ መሆን አለበት። መሀንዲሱ የምሰሶ
አተካከልን፤ በምሰሶ መሀል ያለን ርቀት፤ የምሰሶ ወጥነት፤ የትክክለኛ መስመር መምረጡ የአክሰሰሪዎች አቀማመጥ እና
የኮንዳክተሩን የአወጣጠር መጠን እንዲከታተል እድል ሊሰጠው ይገባል።

የሱፐርቪዥኑ ግሩፕ ሲቪል፤ ኤሌክትሪካል እና ሜካኒካል ሱፐርቫይዘሮች ከዩኤአፐ ኮኦርዲኔሽን ግሩፕ እና የኮንትራክተሩ
ተወካዮች ስብስብን ያካተተ መሆን አለበት። ከኮንትራቱም ሆነ ከቴክኒካል መስፈርቶች ውጪ ምንም አይነት ለውጥ
ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም።

ሱፐርቫይዘሩ በሚከተሉት ዝርዝሮች ላይ አስተያየት አድርጎ ኮንትራክተሩ ለማስተካከል ፍቃደኛ ካልሆነ ለሪጅን መሀንዲሱ
ሪፖርት ሊያደርግ ይገባዋል።

1.1. አስፈላጊ መረጃዎች(ዶክመንቶች)


 የሱፐርቪዝን መምሪያ
 የፀደቀ LV ዲዛይን እና MV ፐሮፋይል
 የሱፐርቪዝን ሪፖርት ቅፅ
1.2. የኮንትራክተሩ ተወካይ

16
የኮንትራክተሩ ተወካይ (ማለትም ሱፐርቫይዘር ወይም ፎርማን እና ላይን ማን በኮንትራቱ ላይ
እንደተገለፀው) በግንባታ ወቅት ሳይቱ ላይ ሊገኙ ይገባል።

1.3. የበቂ የግንባታ መሳሪያዎች መኖር

ትክክለኛ የግንባታ መሳሪያዎች (በኮንትራት ዶኩመንቱ ላይ እንደተዘረዘረው) በስራው ስፍራ ሊገኙ


ይገባል።

1.4. ፋውንዴሽን
 ራይት ኦፍ ወይ (Right - of – way)
 ወጥነት (Alignment)
 የግንባታ እቃዎች እና የሰው ሀይል
 ቁፋሮ
 የሲሚንቶ ጥራት፣ ለግንባታ ተገቢው ቅይጥ ማቴሪያል መኖር (ለኮንክሪት ምሰሶ)
 በተገቢው መልኩ መሞላቱና መስፈርቱን የጠበቀ መሆኑ ፣ እንዲሁም አጠቃላይ የምሰሶው
አካባቢ ጥራትና ፅዳት መጠበቁ ጠቅላላ የምሰሶው አከባቢ ጥራት እና ጽዳት
1.5. የምሰሶ አተካከል
 ቀጥ ያለ መሆኑ
 ትክክለኛው አክሰሰሪ አይነት እና ቁመት የጉድጓድ ጥልቀትና የማቴሪያል መጠን
 ምሰሶ ጫፍ የሚገጠሙት አክሰሰሪዎች ትከክል መገጠሙ

1.6. የኬብል እርግበት እና ውጥረት /የመስመር ዝርጋታ/


 የኢንሱሌተሮች መተከል
 እርግበት እና ከመሬት ከፍታ
 የመገጣጠሚያዎችን ትከክለኛነት
 LV የኤርዚግን ትክክል መተከል
 ለ 3phase ,2 phase, and single phase ትክክለኛውን ኬብል መጠን መጠቀማቸውን
1.7. Overhead አከሰሰሪዎች አተካከል
 ክሮስ እርም፤ ታይ ስትራፕ፤ ፒን ኢንሱሌተር፤ ወዘተ… በተክክል መቀመጥ
1.8. የትራንስፎርመር አተካከል
 የትራንስፎርመር ትክክል መተከል
 የኮኔክሽኖች ትክክል መሆን
 ድሮፕ ኣውት ፊውዝና ኣሬስተር በትክክል መገጠሙ
 ኤርዚንግ

16
ማሳሰቢያ:- ለ 33/19kv isolating transformer ኤርዚንግ ሲሰራ ሱፐርቫይዘሩ በሳይት ተገኝቶ በዚህ የአሰራር መምሪያ
በተቀመጠው መለኩ መሰራቱን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።

1.9. መስመር ማቋረጫ ስዊች/ ድሮፕ አውት ፊውዝ አተካከል


 መነሻ ነጥብ እስዊች እና ዲስኮኔክተር በትክክል መተከላቸውን፤
 መስመር ማቋረጫ ስዊች በትክክል መተከሉን፤
 Autoreclosure በትክክል መተከሉን።
2. ኮሚሺኒንግ /ርክክብ

ኮሚሺኒግ ማለት በኮንትራክተር ወይ በራስ ሀይለ የተሰራን ስራ መረከብ ማለት ነወ። ጠቅላላ አላማው ከአደጋ
የነጻ በቂ ግልጋሎት የሚሰጥ፤ የዲዛይን መስፈርቶችን የሚያሙላ እና የግልጋሎት ዋስትና ያለውን የኤሌክትሪክ
መስመርን መገንባት ነው።

2.1. የኮሚሺኒግ ስብስብ ቡድን አወቃቀር/


 ኤሌክትሮሜካኒካል ቴክኒሺያኖች ከዲስትሪቢዩሽን ኮንስራክሽን ፐሮሰስ እና በአከባቢው ከሚገኝ
EEPCo ሪጅን ቅርንጫፍ ጽ/ት ዲስትሪክት፤
 የኮንትራክተሩ ተወካይ
 የሪጅን መሀንዲስ
 ሱፕርቫይዘር
2.2. አስፈላጊ መረጃዎች
 ሱፐርቪዝንና ኮሚሺኒግ ማኑአል፤
 ዲዛይን ዶክመንቶችና ፐሮፋይሎች፤
 የሱፐርቪዝን ሪፖርቶችና አስተያየቶች፤
 ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችና ከግንባታ በኋላ ያለ ኘሮፋይል (እንደአስፈላጊው)።
2.3. አስፈላጊ መሳሪያዎች
 GPS ለምሰሶ መትከያ ቦታ ማረጋገጫ፤
 Clip on meter (multimeter) ትከክለኛውን output ለመለካት እና ትራንስፎርመር ቼክ
ለማድረግ።
 Operating rod/ፌሮቲ/
2.4. በኮሚሺኒግ ስራ ወቅት መሰረታዊ ቅደም ተከተሎች
 በአይን መከታተል የሚቻሉ
 ምሰሶ፤
 ኢንሱሌተር፤
 ኮንዳክተረ፤
 የምሰሶ የላይኛው ጫፍ አካባቢ ያሉ ስራዎች፤
 የምሰሶ ማረፊይ ወለል (ለኮንክሪት ምሰሶ)፤

16
 ራይት ኦፍ ዌይ (Right - of – way)።
 የሚከተሉትን በቦታው ተገኝቶ ቼክ ማድረግ
 የምሰሶ ጫፍ አክሰሰሪዎች በትክከል መቀመጣቸውን፤
 እርግበት እና ከመሬት ያለ ከፍታ፤
 ትራንስፎርመር በትክክል መያያዙን።
 መረጃ መሰብሰብ /ለምሳሌ- ጂፒኤስ፣ መለያ ቁጥር ወዘተ/

3. የሀይልን ሙከራ ስርጭት


 መስመሩ ከዛፎች ነጻ መሆኑን ማጣራት/ምንጣሮ/
 የተላቀቀ /poor connection/ እንዳይኖር ማጣራት
 ማንኛውም የታዩ እንከኖቸ በኮሚሺኒግ ወቅት ተጣርተው መስተካከል አለባቸው።
 መስመሩ የሚወጣበት ሰብሰቴሽን ማሳወቅ
 ለአከባቢው መንግሰት አካላት የኃይል ሙከራ ስርጭት እንደሚለቀቅ ማስታወቅ
 ትራንስፎርመሩ ዘይት እንዳለው ና በቡሺንጎች መካከል የ Continiuity checking
 በመጨረሻም የኮሚሺኒጉ ግሩፕ የኃይል ሙከራ ስርጭት ሊያደርግ ይችላል።
 መሰመሩ ካልያዘ በማቋረጥ እንደገና ሙሉ ፍተሻ በማድረግ በድጋሜ መሞከር
4. የማጣሪያ ስራ
 የትራንስፎርመሩ ወጪ ቮልቴጅ በፌዞች መካከል 400 ቮ መሆኑን ማረጋገጥ
 በሁሉም ፌዝና ኒውትራል መሃል 230 ቮ መሆኑን ማረጋገጥ ና
 frequencey 50Hz መሆኑን ማጣራት
5. የስራ ማጠናቀቅ
 ሁሉም የመጨረሻ ዲዛይን እና አስ ቢዩልት ዶክመንቶች ለአከባቢው ዲሰትሪቡሽን ኮንስትራክሸ ፕሮሰስና
ሪጅናለ ኦፕሬሽን ክፍል ሊሰጥ ይገባል።
6. ምንጭ

16
 ኮንትራት ዶክመንት
 ኤግዚስቲንግ ዎርክንግ ዶክመንት /እየተስራበት ካለው የስራ መምሪያ ዶክመንት/
 የ EEPCo እስታንዳርዶች

ምዕራፍ ዘጠኝ

የሪፖርት አቀራረብና የቅፃች አጠቃቀም

ሳይት ላይ የሚሰራ ማንኛውም ነገር በዶክመንት መልክ ማስፈር በየጊዜው ያለውን የስራ ሂደት ፍጥነት ከማሳየቱ በተጨማሪ
ለሚሰራው ኮንትራክተር የሰራውን ያሳየዋል፣ ለስራው ባለቤትም የስራውን ሂደት በርቀት እንዲያውቅ ያደርገዋል፡፡ ለተቆጣጣሪው
መሀንዲስም በጥራት የተሰራው ስራ ብዛት ከማሳየቱ በተጨማሪ ስራው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እየሄደ መሆን አለመሆኑን እንዲያውቅ
ያስችለዋል፡፡

በአጭሩ አንድ የስራ ሪፖርት በአግባቡና በወቅቱ ሲቀርብ

i) ስራዎች በጥራት መሠራታቸው ያረጋግጣል፣

ii) ስራዎች በእቅዱ መሠረት እየተሰሩ መሆን አለመሆናቸው ያሳያል፣

iii) ተገቢውን ሪፖርት ለሚፈለግ ክፍል ለማቅረብ እገዛ ያደርጋል፣

iv)ኮንትራክተሩ ለሰራው ስራ በወቅቱና በአጭር ጊዜ በውሉ መሰረት ክፍያ እንዲያገኝ ያስችለዋል፡፡

ስለዚህ በዚህ የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር የገጠር ቀበሌዎች ግንባታን ላይ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የተቀረፀ የሪፖርት ማቅረቢያ ቅፆች
የሚከተሉት አይነት ሲሆኑ በአግባቡ መሞላት ይገባቸዋል፡፡

16
1) የሳይት ርክክብ ቅፆች (Site Hand overing)

2) የሱፐርቪዥን ቅፆች

I. ለእንጨት ምሰሶ ማጠቃለያ

II. ለኮንክሪት ምሰሶ ማጠቃለያ

III. ለስቲል ምሰሶ ማጠቃለያ

IV. የዝቅተኛ መስመር መሳያ

V. የ GPS መሰብሰቢያ

VI. የሱፐርቪዥን ስራ አስተያየት መስጫ ቅፅ

3) የኮሚሽኒንግ ቅፆች

i) ለእንጨት ምሰሶ ማጠቃለያ

ii) ለኮንክሪት ምሰሶ ማጠቃለያ

iii) ለብረት ምሰሶ ማጠቃለያ

iv) የዝቅተኛ መስመር መሳያ

v) የስራ ማጠቃለያ(Job Completion) መረጃ መሰብሰቢያ ፎርም

vi)የ GPS መሰብሰቢያ

vii) የትራንስፎረመር check list

4) የጆይንት ሰርቲፊኬት

ስለነዚህ ቅፆች ምንነትና አሞላል እንዴት እንደሆነ አንድ በአንድ ከታች ተዘርዝሮአል፡፡

1. የሳይት ርክክብ ቅፆች

ይህ ቅፅ የሚሞላው ኮንትራት ተፈርሞ ካለቀ በኋላ ለኮንትራክተሩ የሚሰራውን ሳይት ሳይቱን በሚያስተዳድረው የወረዳ መስተዳድር
እና /ወይም ቀበሌ ተወካዮች በተገኙበት ሱፐርቫይዘሮች/መሀንዲሶች ሳይቱ /ቀበሌው ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና ተቋማት፣ የቀበሌ ፣
ክሊኒክ ፣ት/ቤት፣ ወፍጮ ቤት ፣የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከልን(FTC) ፣የመንገድ አካሄዶችን ፣ዋና ዋና መገንጠያ መንገዶችን ወዘተ እና
የቀበሌው ድንበር አካባቢ ያሉ ማጣቀሻዎችን ስም (References) ጥርት ባለ መንገድ በማስፈርና በመሳል የሚመለከትበት ቅፅ ነው ፡፡

እዚህ ፎርም ላይ ያሉ መረጃዎች በሙሉ በአግባቡ እንዲነበቡ በሚያስችል መልኩ መሞላት ይገባቸዋል፡፡ከዚህ በኋላ የወረዳ
መስተዳድር እና /ወይም ቀበሌ ተወካይ ፊርማ፣ስም እና ማህተም መደረግ ይገባዋል፡፡ሱፐርቫይዘሩና/መሀንዲሱ፣የኮንትራክተሩ
ተወካይና በመጨረሻ ኮኦርዲኔተሩ መፈረምም ይጠበቅባቸዎል፡፡

16
በዚህ የሳይት ርክክብ ሂደት ላይ የሚረከቡት ሳይቶች የሚገኙበት ቦታ የሚያሳይ የመንገድ ካርታ አብሮ መሠረት አለበት፡፡ ይህ
በሚሰራበት ጊዜ የሚከተሉትን መረጃዎችን እንዲይዝ ተደርጎ ነው፡፡

1/ ወደሚረከቡ ሳይቶች መሄጃ ላይ የሚገኙ ቀድሞ መብራት ያገኙ ዋና ከተሞችን/ቀበሌዎችን፣

2/ በቀበሌዎች/ከተሞች መካከል የሚገኘው ርቀት በኪ.ሜ ይያዛል፡፡

3/ በተራ ቁጥር 1 ለተጠቀሱት ከተሞች አንዳንድ ጂፒስ መረጃ ይያዛል፡፡

4/ ከትልልቅ ከተሞች እስመገንጠያ ያለው ርቀት ይያዛል፡፡በተጨማሪም የመገንጠያው ጂፒኤሲ ይያዛል፡፡

5/ በተራ ቁጥር 1 የሚጠቀሱት ከተሞች/ቀበሌዎች አዲስ ርክክብ ከሚደረግለት ሳይት በተለየ ምልክት (Symbol) ይቀመጣሉ፡፡

2. የሱፐርቪዥን ቅፆች

አንድ ሳይት ርክክብ ከተፈፀመለት በኋላ ኮንትራክተር በርክክብ ሰነዱና ውሉ ላይ ባለው ቴክኒካዊ መስፈርት መሰረት የቅየሳ፣መረጃ
ስብሰባና ዲዛይን ስራ ይሰራል፡፡

ዲዛይኑ ፀድቆ የስራ ትዕዛዝ ይዘጋጃል፡፡በዚህ መሰረት ኮንትራክተሩ ለስራ የሚያስፈለጉ ዕቃዎችን ከግምጃ ቤት እያወጣ ስራውን በውሉ
መሰረት ማከናወን ይጀምራል፡፡

እዚህ ላይ ኮንትራከተሩ ስራውን ለጀምር ሲል አጠቃላይ የቅየሳ ስራው ምን ይመስላል፣መካከለኛ መስመሩ ከዲዛይኑ አንጻር ከየት
ተነስቶ በየት አድርጎ እንደሚሄድ ይታያል፣የዝቅተኛ መስመር ዲዛይኑም ሳይቱን ከርክክቡ አንጻር በትክክል የሚወክል መሆኑም
ይታያል፡፡ እነዚህ ነገሮች በ Survey Check list Form መሰረት ይከናወናሉ፡፡

ከዚህ በኋላ ተቋራጩ ሞደል የሚሆን የምሰሶ አተካከል ሂደት ምን እነደሚመስል በተግባር እንዲያይ ይደረጋል፡፡ይህ እንደተደረገ
ሳይቱ ላይ ፎርማቶቹ ይሞላሉ፣ሁሉም ተወካዮች ይፈርሙበታል፡፡

በዚህ መንገድ ስራ እንዲጀመር ከተደረገ በኃላ ለምሳሌ በኮንክሪት ምሰሶ የሚሰራ መካከለኛ መስመር ከሆነ የሚሰራው የአ/አ/ኤ/አ
ሱፐርቫይዘሮች ባሉበት ስራው ይቀጥላል፡፡መረጃዎችም በየጊዜው መሞላት ይገባቸዋል፡፡ሱፐርቫይዘሮች በሚለወጡበት ጊዜ
በየምሰሶው ላይ ቁጥር በመስጠት አስፈላጊውን ርክክብ በጥንቃቄ መደረግ አለበት ::

በእንጨት የሚሰራ ሳይትንም ሱፐርቫይዝ ማድረግ ማለት የተሰራው ስራ በውሉ ቴክኒካዊ መስፈርት መሰረት መሰራቱን አረጋግጦና
የተሰራውን ስራ መጠን በቅፆቹ መሰረት መልቀም ማለት መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

በአብዛኞቹ ቅፆች ላይ የሚከተሉት ክፍት ቦታዎች ይገኛሉ፡፡እያንዳንዱ ክፍት ቦታ በትክክልና በአግባቡ መሞላት ይገባዋል፡፡

16
16
3. የኮሚሽኒንግ ቅፆች

ሳይት በየጊዜው በሚደረገው የሱፐርቪዥን ስራ አጠቃላይ ግንባታው መጠናቀቁ ከታወቀ በኋላ ቀጣዩ ስራ ቀበሌው የመብራት
አገልግሎት እንዲያገኙ ለዲስትሪቡሽን ሲስተም ወይም ማርኬቲና ሴልስ አገልግሎት ክፍል የማስተላለፍ/የማስረከብ ስራ
ይሰራል፡፡ይህ በሚደረግበት ሂደት ሁሉም መረጃዎች በኮሚሽኒንግ ቅጾች ላይ በጥራት ይሞላሉ፣የኮንትራክተሩ
ተወካይ፣ሱፐርቫይዘሩ/መሀንዲሱ ይፈርማሉ፡፡ የዲስትሪቡሽን ወይም ዲስትሪክት ተወካይ ፊርማ ና ማህተምም መደረግ ይገባዋል፡፡
በመጨረሻ ኮኦርዲነተሩ ሁሉም መረጃ በትክክል መሞላቱንና መያዙን አረጋግጦ ይፈርማል፡፡

4. የጆይንት ሰርቲፊኬት፡
ኮንትራክተሩ በትክክል ሱፐርቫይዘሩ ባለበት ተሰርቶ ያጠናቀቀውን ማንኛውንም ስራ ኮንትራክተሩና ሱፐርቫይዘሩ
በጋራ የተስማሙበት ለክፍያ እንዲመች ተሞልቶና ሱፐርቫይዘሩና ኮንትራክተሩ ፈርመው የሚቀርብ ነው፡፡
ይህንንም ኮንትራክተሩ ለክፍያ የሚፈልገውን ሞልቶ ለሱፐርቫይዘሩ በማቅረብ ሱፐርቫይዘሩ ከሱፐርቪዝን ሪፖርት
ጋር በማመሳከር የሚያፀድቀው ሲሆን፡ኮንትራክተሩ ይህንን ከክፍያ መጠየቂያ ጋር አያይዞ ያቀርባል፡፡

16

You might also like