You are on page 1of 60

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና
ስልጠና ቢሮ

ለአጫጭር ሰልጣኞች የተዘጋጀ


ተግባር ተኮር ስልጠና
የህንፃ ላይ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
የሰልጣኙ መምሪያ

1|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


ማዉጫ
አርእስት ገፅ
1. የስልጠና አላማ 3
2. የሰራ ቦታ ጥንቃቄ 3
3. መሰረታዊ የኤሌክትሪክ መጠኖች 6
4. የኤሌክትሪክ ምልክቶችን መለየት 7
5. ደንቦች(EBCS) 8
6. የእጅ መሳሪያዎችና ማሽኖች አጠቃቀምና አያያዝ 9
7. የኤሌክትሪክ ሽቦ አስተሳሰር 11
8. የኤሌክትሪክ ሽቦ አይነቶች 11
9. የማሰር ጥቅም 11
10. የገመድ ዉፍረት 11
11. የሽቦ ጫፍማዘጋጀት 11
12. የሽቦ አስተሳሰር ዘዴዎች 13
13. የኮንዲዩት መስመር ዝርጋታ 15
14. የኮንዲዩት ስረዎች 15
15. የኮንዲዩት አይነቶች 15
16. ኬብል ትራኪንግ 16
17. ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሚያስፈልጉ አቃዎች 16
18. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ 17
19. የሃይል/የሶኬት መስመር ዝርጋታ 24
20. የደወል መስመር ዝርጋታ 25
21. ሰርኪውቶችን የያዘ መስመር ዝርጋታ 28
22. የካይዘን ፍልስፍና ምንነትና አስፈላጊነት 37
23. የካይዘንባህርያት 38

24. 7ቱ ብክነቶች 39

ካይዘን ለመተገበር የሚጠቅሙ ቴክኒኮች 43


25
26 እንተርፕሪነርሽፕ

2|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


የብቃት አሀድ አንድ
EISBEI 01 2020v1- የ ኤሌክትሪክ መጠኖችን መለካትና ቀላል ሂሳቦችን መስራት

1.1 የስልጠናዉ አጠቃላይ አላማ


ከዚህ ስልጠና በኋላ ሰልጣኞች ቀላል ንድፎችን (Layout, wiring and architectural diagram) መሳል፣ ማንበብ
እንደሁም በወረቀት ላይ የተሰሩ የኤሌክትሪካል ንድፎችን ተረድተዉና አንብበዉ በህንጻ ላይ የሚዘረጉ መስመሮችን
በተግባር መዘርጋት ይችላሉ፡፡

1.2 የስራ ቦታ ጥንቃቄ

በስራና በተግባር መለማመጃ ቦታዎች በሰልጣኝም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን ለመከላከል ጥሩ የስራ ፀባይ
ሊኖረን ይገባል፡፡
አጠቃላይ የጥንቃቄ መመሪዎች
1. በተግባር መለማመጃ ቦታ
2. በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ላይ
3. በተዘረጋዉ መስመር ላይ ኤሌክትሪክ ሀይል ከመስጠታችን በፊት

I. በተግባር መለማመጃ ቦታ ሊደረጉ የሚገባቸዉ ጥንቃቄዎች


1. የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን መጠቀም
2. የምንሰራበትንና የምንቀሳቀስበትን ቦታ የተመቻቸ ማደረግ
3. በኤሌክትሪክ ወርክሾፕ ዉስጥ አለመጫዎት
4. በተግባር መለማመጃ ቦታ ዉስጥ የተገለጹ የስራ ቅደም ተከተሎችን በአግባቡ መከተል
5. የስራ ቦታን ከአደጋ ነፃ ማድረግ
6. ኤሌትሪክ ይዘዉ የሚቆዩ እቃወችን በተገቢዉ ቦታ ማስቀመጥ

II. የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ላይ ሊደረጉ የሚገባቸዉ ጥንቃቄዎች


1. ትክክለኛዉን የስራ ቅደም ተከተል መከተል
2. የተበላሹ መሳሪያዎችንና ማሽኖችን አለመጠቀም
3. አሰልጣኙ ሳይፈቅድ የሀይል መስመርን አለማገናኘት
4. ሁሉንም መሳሪያዎች ለተገቢዉ ስራ ብቻ መጠቀም
5. ስለትና ሹል ጫፍ ያላቸዉን መሳርያዎች በጥንቃቄ መያዝና ማቀበል
6. የኤሌክትሪክ እቃዎችን ኤሌክትሪክ አስተላላፊ በሆነ ብረት ነክ አጠገብ አለመጠቀም

3|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


7. መሰላልን ስንጠቀም አለመበላሸቱን አረጋግጠን መጠቀም
III. መስመር ላይ ኤሌክትሪክ ሀይል ከመስጠታችን በፊት መተግበር ያለባቸዉ አምስት
መመሪያዎች
1. ከዋናዉ መስመር ማቋረጥ ወይም ማላቀቅ
2. ሶኬት ላይ አለመሰካት
3. የኤሌክትሪክ ሀይል አለመኖሩን ማረጋገጥ
4. ወደ መሬት መቅበር (Earthing)
5. የተላጠ ሽቦ አለመኖሩን ማረጋገጥ
የመለኪያ አሃዶች መጠንና ስሌት

የመለኪያ አሀዶችን መጠንና የስሌት መሳሪያዎች በምንጠቀምበት ጊዜ የምናነባችውን መጠኖች


ለመግለጽ ያገለግላሉ፡፡እነዚህም ከከፍተኛ እስከ አነስተኛ መጠን ባልው አሃዶች ሊገለጹ ወይም
ሊነበቡ ይችላሉ፡፡እነዚህም አሃዶች እንደሚከተለው ይሆናል ፡፡

አሃዶች ልዩ የመጠን ቁጥር

ፒኮ P 10-12
ናኖ N 10-9
ማይክሮ Mic 10-6
ሚሊ M 10-3
ሴንቲ C 10-2
ዴሲ D 10-1
ዴካ De 10
ሔከቶ H 102
ኪሎ K 103
ሜጋ M 106
ጅጋ G 109
ቴራ T 1012
እነዚህ አሃዶች በተለያዩ መለኪያ መጠን ስም ላይ እየተደገፉ ብዛትን ወይም ልክን ይገልጣሉ፡፡

የኤሌክትሪክ ከረንት

የኤሌክትሮን ሽሽት የኤሌክትሪክ ከረንት ነዉ ፡፡ስለዚህ ኤሌክትሪክ ምንድነዉ የሚለዉን ጥያቄ


በመጠኑም ቢሆን ለመመለስ ችለናል ፡፡ ቢሆንም ስለ ኤሌክተሮኖች ፈጥሮ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ
ባለመኖሩ ምክንያት ያለን እዉቀት ዉስን ነዉ፡፡በባትሪዉ ፖስቲቭ ፕሌት በኩል የሚገቡት ኤሌክትሮኖች
ወደ ቁስ ይገፈተራሉ በዚህም ኤሌክትሮኖች ይዟዟራሉ ፡፡ነገር ግን ተከታታይ ማስተላለፊያ መንግድ
ወይም ዝግ ሰርኪዩት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ የኤሌክትሪክ ሃይል የተቋረጠ ከሆነ የኤሌክትሮኖች ሽሽት
ከመቅጽበት ይቆማል፡፡

4|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


የኤሌክትሪክ መጠንና የከረንት አሃድ

የቱቦ ርዝመቱ መለካት ቢያስፈልግ ዉስን አሃዶች ምልክት በተደረገበት ማስመሪያ መጠቀም ይቻላል ፡፡
ኤሌክትሪክ ከረንት የማይታይ በመሆኑ ለመለካት የተለየ መሳሪያ መጠቀም ያሻል ፡፡አብዛኛው እነዚህ
መሳሪያዎች ተግባራቸዉ የሚወሰነዉ በማስተላለፊያዉ ቁስ ዉስጥ የሚያልፍው ከረንት በሚሰርጸዉ
የማግኔቲክ ዉርሰት አማከኝነት ነዉ፡፡የመጀመሪያዉ አሀድ አድርገን የምንወስደዉ የኤሌክትሪክ ሙሌት
አሀድ ወይም የኤሌክትሪክ መጠን አሃድን ነዉ፡፡ይህ የምንጠቀምበት አሃድ ኮሎምብ ይባላል ምልክቱም
የእንግሊዘኛ ፊደል ሲ( C) ነዉ፡፡ይህም ከኤሌክትሪክ በኃይል የበለጠ ሲሆን የ 6*1018ኤሌክትሮኒክ
ሙሌት ከአንድ ኮሎምብ ይባላል፡፡ብሎም የኤሌክትሮኖች እጥረት ካለዉ ፖስቲቭ ሙሌት ይባላል፡፡
ሁለቱም መጠኖች መለካት የሚቻለዉ በኮለምብ ነዉ፡፡

አብዛኞቹ የኤሌክትሪክ አሃዶች የሚሰየሙት በታላላቅ ሳይንቲስቶች ሲሆን ለምሳሌ የኤሌክትሪክ


ሙሌት አሓድ ኮሎምብ የተሰየመዉ በፈንሰዊዉ ፈዚስት ቻርልሰ ኮሎምብ ነዉ፡፡/1736-1806/

የኤሌክትሪክ ዝግምታዊ ሽሽት በአስተላላፊው ቁስ ዉስጥ አንድ ኮለምብ በሰኮንድ ሲሆን የዉጤቱ
ከረንት አንድ አምፒር ከረንት/ ዉክል A ይባላል፡፡ይህም የአንድ አምፒር ከረንት የሚያመለክተዉ
በአስተላላፊ ቁስ ዉስጥ የሙሌት ጉዞ መጠን ኮለምብ በሴኮንድ ነዉ፡፡

ስለዚህ

Q=It

Q=የሙሌት መጠን በኮሎምብ(C)

I=ኮረንቲ በአምፒር(A)

T=ጊዜ የኮረንቲ ማለፍ በሴኮንድ(S)

ምሳሌ1 የአጠቃላይ የሙሌት መጠን 500Q በ20S ለማጓጓዝ ምን ያህል ከረንት ማለፍ አለበት

Q=It

I=Q/t

I=500/20=25 A

2.የከረንት12 አምፒር መጠን ለ 2 ደቂቃ ቢያልፍ ምን ያህል የኤሌክትሪክ ሙሌት መጠን ይጓዛል?

Q=It

=(12 x 2 x 60)

=1440C

5|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


1.3 መሰረታዊ የአሌክትሪክ መጠኖች

መሰረታዊ የኤሌክትሪክ መጠኖች የሚባሉት የሚከተሉት ናቸዉ

 ቮልቴጅ፡ በሁለት የተለያዩ ግፊታዊ ሀይሎች ያለ የሀይል (Force) ልዩነት ሲሆን የኤሌክትሪክ ቅንጣቶችን
በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች ዉስጥ የሚገፋ ሀይል ነዉ፡፡
 ከረንት፡ በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች ዉስጥ የኤሌክትሮኖች ፍሰት ወይም እንቅስቃሴ ነዉ
 ረዚስታንስ፡ በኤሌክትሪክ አስተላላፊ ቁሶች ዉስጥ የኤሌክትሮኖችን እንቅስቃሴ የሚያግድ ነዉ
 ኤሌክትሪካል ፓዎር፡ ቮልቴጅና ከረንት አንድ ላይ ተጣምረዉ የሚፈጥሩት የኤሌክትሪክ ጉልበት ነዉ
 የኤሌክትሪክ ሐይል፡ ምን ያህል የኤሌክትሪካል ጉልበት በተወሰነ ሰአት እንደተጠቀምን የሚገልጽ የኤሌክትሪክ
መመጠኛ ነዉ

ከላይ የተዘረዘሩትን የኤሌክትሪክ መጠኖች ለመለካት የሚያስፈልጉን የመለኪያ መሳሪያዎች የሚከተሉት ናቸዉ

1. ቮልት ሜትር፡ ቮልቴጅን ለመለካት የሚያገለግል የመለኪያ መሳሪያ ነዉ፡፡


2. ከረንት ሜትር፡ ከረንትን (የኤሌክትሮን ፍሰትን) ለመለካት የሚያገለግል የመለኪያ መሳሪያ ነዉ፡፡
3. ረዚስታንስ ሜትር፡ የረዚስታንስን መጠን ለመለካት የሚያገለግል የመለኪያ መሳሪያ ነዉ፡፡
4. ዋት ሜትር፡ የኤሌክትሪክ ጉልበትን (power)ለመለካት የሚያገለግል የመለኪያ መሳሪያ ነዉ፡፡
5. ኪሎዋት አዎር ሜትር፡ የኤሌኬትሪክ ሐይልን (Energy)ለመለካት የሚያገለግል የመለኪያ መሳሪያ ነዉ፡፡

1.4 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ምልክቶችን መለየትና ቀላል ንድፎችን ማንበብ

በህንጻ ላይ የኤሌትሪክ መስመርን ለመዘርጋት ሰልጣኞች ምልክቶችንና ቀላል ንድፎችን ማንበብና መሳል አለባቸዉ፡፡

በአብዛኛዉ ከምንጠቀምባቸዉ የኤሌክትሪካል ምልክቶች ዉስጥ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸዉ

የእቃዉ ስም ምልክቱ

ድቡልቡል አምፖል……………………………………………………………………………………………………………….........................

የሸንበቆ አምፖል…………………………………………………………………………………………………………………..............….......
ነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ……………………………………………………………………………………………………......................………

ባለሁለት/ባለሶስት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ………………………………………………………………………...................

ባለ አራት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ……………………………………………………………………………..................…….......


መንታ/ድርብ ማብሪያ ማጥፊያ……………………………………………………………………………………………...........................

6|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


ባለ ሁለት ቀዳዳ ሶኬት………………………………………………………………………………………………………............................

ባለ ሶስት ቀዳዳ ሶኬት……………………………………………………………………………………………………………......................

ደወል…………………………………………………………………………………………………………………………………………….............…

የደዎል ማብሪያ ማጥፊያ..................................................................................................................................

የኤሌክትሪክ ሀይል ማከፋፈያ.........................................................................................................................

ከፊል የኤሌክትሪክ ሐይል ማከፋፈያ..............................................................................................................


የዉሀ ማሞቂያ..................................................................................................................................................

የኤሌክትሪክ ምድጃ.............................................................................................................................

የኢትዮጵያ የህንጻ ኮድ ደንቦች (EBCS)

1. የኤሌክትሪክ ገመዶች ቀለም በተለያዩ መስመሮች ላይ

ነጠላ ፌዝ (single phase)፡- በነጠላ ፌዝ ጊዜ የምንጠቀማቸዉ ገመዶች ሶስት ሲሆኑ አንደኛዉ ፌዝ ይባላል ይህም
የኤሌክትሪክ እሳት ያለዉ ሆኖ አረንጓዴ ነዉ፡፡ ሁለተኛዉ ደግሞ ኒዉትራል ይባላል ይህም እሳት የሌለዉ ሆኖ ጥቁር ነዉ፡፡
ሶስተኛዉ ከመሬት ጋር የሚያያዝ (ground/ Earthing) ሲሆን ቀለሙ ነጭ ነዉ፡፡

ሶስት ፌዝ (three phase)፡- በሶስት ፌዝ ጊዜ የምንጠቀማቸዉ ገመዶች አራት ሲሆኑ ሶስቱ እሳት ያላቸዉ ሆነዉ
ቀለማቸዉ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ናቸዉ፡፡ አራተኛዉ ገመድ ደግሞ ግራዉንድ ሆኖ ቀለሙ ያረንጓዴና የቢጫ መስመር
ያለዉ ሆኖ እሳት የሌለዉ ነዉ እና ኒዉትራል ጥቁር ነዉ፡፡
2. የማብሪያ ማጥፊያ፣ ሶኬትና ሀይል ማከፋፈያ ከመሬት ያላቸዉ ከፍታ እንዲሁም የገመዶች ዉፍረት
በተለያዩ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ
በአንድ ባለ 10 አምፒር የኤሌክትሪክ ማቋረጫና መከላከያ መሳሪያ ከ8-12 አምፖሎችን ብቻ መሸከምይችላል፣ ማብሪያ
ማጥፊያ ደግሞ ከ 1.10 - 1.20 ሜትር ከመሬት ርቆ ግድግዳ ላይ ይቀመጣል፡፡
ሌሎች ደግሞ መጠናቸዉ እንደሚከተለዉ ተዘርዝሮአል፡፡
አንድ ባለ 16 አምፒር የኤሌክትሪክ ማቋረጫና መከላከያ መሳሪያ ከ6-8 ሶኬቶችን ብቻ ይይዛል፡፡ ሶኬት 30-40 ሴንቲ
ሜትር ከመሬት ርቆ ይቀመጣል፡፡
የኤሌክትሪክ ሐይል ማከፋፈያ (distrubtion board) ከመሬት 1.70 ሜትር ከፍ ብሎ ይቀመጣል፡፡

7|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


ተ.ቁ የመስመሩ አይነት የምንጠቀመዉ የኤሌክትሪክ ማቋረጫና
ገመድ ዉፍረት መከላከያ መጠን
በሚ.ሜ2. (circuit breaker rating)
በአምፔር
1 ለመብራት 1.5 10A
2 ለሶኬት 2.5 16A
3 ለዉሀ ማሞቂያ 4 20-25A
4 ለምጣድ 4-6 25A
5 ለደወል፣ በዘር፣ እና 1 6A
ለሰኪዊሪቲ/የጥንቃቄ
ደዎሎች

1.5 የእጅ መሳሪያዎች እና ማሽኖች አጠቃቀምና አያያዝ

ሰልጣኞች ማወቅ የሚጠበቅባቸዉ እዉቀቶች

ሀ. የእጅ መሳሪያዎችን መለየት

ለ. አጠቃቀማቸዉን ማወቅ

ሐ. በአግባቡ መጠቀም

8|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


የብቃት አሀድ ሁለት

EISBEI 02 2020v1 በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ዉስጥ የምንጠቀምባቸዉ የእጅ


መሳሪያዎች

1. መፍቻ / ካቻ ቢቴ (screw driver)፡- ጠፍጣፋና ፕሊፕስ ሲሆኑ ቡሎኖችን ለመፍታትና ለማሰር ይጠቅማሉ፡፡

2. ኤሌክትሪሽያን ቢለዋ (Electrical knife)፡- ከኤሌክትሪክ ሽቦ ላይ ፕላስቲክን ለማስዎገድ ይጠቅማል፡፡

3. ፒንሳ (plier)፡- የኤሌክትሪክ ሽቦዎችን ለመቁረጥ፣ በቱቦዎች ዉስጥ ገመዶችን ለመሳብ አና ሽቦዎችን ለመጠምጠም
ይጠቅመናል፡፡ የተለያየ ጥቅም ያላቸዉ የፒንሳ አይነቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-

9|Page ጥቅምት2011 ዓ.ም


ኮምቢኔሽን መቁረጫ ፒንሳ ዲያጎናል መቁረጫ ፒንሳ ረጅም ጫፍ መቁረጫ ፒንሳ

4. የእጅ መጋዝ (Hack saw)፡- የኤሌክትሪክ ቱቦዎችን/ ኮንዱዩቶችን ለመቁረጥ ያገለግላል፡፡

5. መዶሻ (hammer)፡- በኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጊዜ የኤሌክትሪክ ገመዶችን ከግድግዳ ጋር የሚያያዙ


ምስማሮች(ክሊፖች) ለመምታት ይጠቅማል፡፡

6. መሮ(chisel)፡ ኮንድዩትን ከግድግዳ ስናያይዝ ግድግዳ ለመቦርቦር ይጠቅመናል፡፡

7. የዉሀ ልክ(level gauge)፡- ኮንድዩቶች/ የኤሌክትሪክ መስመሮች ሳይዛነፉ ቀጥ ያሉ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ


የምንጠቀምበት መሳሪያ ነዉ፡፡

10 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
8. ሜትር(tape rule)፡- ኮንድዩትን ወይም የአሌክትሪክ ገመድ ርዝመት ለመለካት ይጠቅመናል፡፡

2. የኤሌክትሪክ ሽቦ አስተሳሰር
2.1 የኤሌክትሪክ ሽቦ (አስተላላፊ) አይነቶች

በብዛት የምንጠቀምባቸዉ የኤሌክትሪክ አስተላላፊ ሽቦዎች በሁለት ይከፈላሉ፡፡


- ከመዳብ የተሰሩ ሽቦዎች
- ከአልሙኒየም የተሰሩ ሽቦዎች
2.2 የማሰር ጥቅም፡- ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ገመዶችን ለማያያዝ ይጠቅማል፡፡
2.3 የኤሌክትሪክ ገመድ ውፍረት መጠን እና አቅም፡- የኤሌክትሪክ ገመድ የዉፍረት መጠንን አቅም እንደሚሸከመዉ
ኤሌክትሪክ ቮልቴጅና ከረንት መጠን ይወሰናል፡፡
ለምሳሌ፡- ለ220 ቮልት፣ እና ከ0-10 አምፒር ለሆነ መስመር ባለ 1.5 ሚ.ሜ2 ኤሌክትሪክ ገመድ ያስፈልጋል፡፡

2.4 የኤክትሪክ ሽቦ ጫፍን ማዘጋጀት (termination)፡- ለማሰር እንድመች የኤሌክትሪክን ሽቦ ጫፍ ማዘጋጀት ማለት
ነዉ፡፡
የተለያዩ የኤሌክትሪክ ገመዶች ጫፍ አዘገጃጀቶች ሲኖሩ እነሱም ፡-
-ስታብ ኢነድ
-ቀለበት መሳይ
-ላግ ኢነድ ናቸዉ፡፡
ሀ. ስታብ ኢንድ፡- ማለት የገመዱን ጫፍ በመላጥ ከተለያዩ እቃዎች (ሶኬት፣ ማብሪያማጥፊያ ...) ጋር ለማገናኘት
ማዘጋጀት ማለት ነዉ፡፡
የአዘገጃጀት ቅደም ተከተል
1. እንዳስፈላጊነቱ የገመዱን ጫፍ ከ10-15 ሚ.ሜ ይለኩ
2. የተለካዉን ጫፍ ይላጡ
3. የተላጠዉን ጫፍ ያጽዱ
4. የተላጠዉንና የጸዳዉን ጫፍ ከሚፈለገዉ እቃ ላይ በደንብ አጠብቀዉ በቡለን ይሰሩ

11 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የተሳሳተ ስታብ ኢንድ

ትክክለኛ ስታብ ኢንድ

ለ. ቀለበት መሳይ የገመድ ጫፍ አዘገጃጀት፡- ይህ የገመድ ጫፍ አዘገጃጀት ጫፉ ቀለበት ይመስላል


የአዘገጃጀት ቅደም ተከተል
1. እንዳስፈላጊነቱ የገመዱን ጫፍ ይለኩ
2. የተለካዉን ጫፍ ይላጡ
3. የተላጠዉን ጫፍ ያጽዱ
4. የተላጠዉንና የጸዳዉን ጫፍ በሚፈለገዉ መጠን ቀለበት አስመስለዉ ያዘጋጁ

ሐ. ላግ ኢነድ፡- ማለት የገመዱ ጫፍ መንሽ የሚመስል አዘገጃጀት ነዉ፡፡ ይህም አይነት የገመድ ጫፍ አዘገጃጀት ብዙ
ሽቦዎች /ገመዶች በአንድ ላይ ሲሆኑ ነዉ፡፡
የአዘገጃጀት ቅደም ተከተል
1. እንዳስፈላጊነቱ የገመዱን ጫፍ ይለኩ
2. የተለካዉን ጫፍ ይላጡ
3. የተላጠዉን ጫፍ ያጽዱ
4. የተላጠዉንና የጸዳዉን ጫፍ ለሁለት እኩል ቦታ ይክፈሉ
5. የተከፈለዉን ጫፍ ለየብቻ ይጠምጥሙ
6. የጠመጠሙትን ጫፎች መንሽ በማስመሰል ስእሉ ላይ እንደሚታየዉ ያዘጋጁ፡፡

12 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
2.5 የኤሌክትሪክ ሽቦ አስተሳሰር ዘዴዎች
በኤሌትሪክ መስመር ዝርጋታ ወቅት ሽቦዎችን ስናያይዝ የተለያዩ የሽቦ አስተሳሰር ዘዴዎችን እንከተላለን፡፡ እነሱም

ሀ. የአይጥ ጅራት መሰል አስተሳሰር (pig tail) -ይህ አይነት አስተሳሰር ሁለት ጠንካራ ሽቦዎችን ብቻ ለማያያዝ ይጠቅማል፡
፡ ይህ የስተሳሰር ዘዴ ፈጣንና ቀላል ሲሆን በብዛት በኤሌከክትሪክ መስመር ዝርጋታ ጊዜ እንጠቀማዋለን፡፡

የአስተሳሰር ቅደም ተከተሎች

1. እንዳስፈላጊነቱ የገመዱን ጫፍ ይለኩና ይላጡ

2. በስእሉ መሰረት 6 ጊዜ ይጠምጥሙ

ለ. ስብስባዊ አስተሳሰር (bunch splice)-የአይጥ ጅራት መሰል አስተሳሰር ሆኖ ሶስት እና ከዛ በላይ ገመዶችን

የምናያይዝበት ዘዴ ነዉ

ሐ.ዌስተርን ዩኒየን አስተሳሰር - በብዛት በቤቶች ዉሰጥ ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል ገመዶችን ለማራዘም እና ጥንካሬ
ለሚያስፈልጋቸዉ አስተሳሰሮች እንጠቀምበታለን፡፡

የአስተሳሰር ቅደም ተከተሎች

1. በመጀመሪያ የገመዶችን ጫፎች ይላጡ


2. ከሁለቱ ገመዶች መካከል በአይጥ ጅራት መሰል አስተሳሰር ዘዴ ቢያንስ 5 ጊዜ ይጠምጥሙ
3. ከዛም በስእሉ መሰረት ቢያንስ አንዱን ሽቦ በሌላዉ ላይ 6 ጊዜ ይጠምጥሙ፣ሌላኛዉንም በመጀመሪያዉ ላይ እንዲሁ 6
ጊዜ ይጠምጥሙ
4.የተረፈዉን ሽቦ ይቁረጡ

13 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
መ. ስታገሪንግ የአስተሳሰር ዘዴ
ይህ የአስተሳሰር ዘዴ በአንድ ወፍራም ሽቦ ዉስጥ ሁለትና ከዛ በላይ ገመዶችን ለየብቻቸዉ የምናያይዝበት ዘዴ ነዉ

የአስተሳሰር ቅደም ተከተሎች

1. በመጀመሪያ የገመዶችን ጫፎች ይላጡ

2. በዌስተርን ዩኒየን የአጠማጠም ዘዴ እያንዳንዳቸዉን ያያይዙ

ሠ. ፐ- የሚመስል (T-tap splice) የአስተሳሰር ዘዴ


አንድና ከዚያ በላይ ቅርንጫፍ ከዋናዉ መስመር ላይ መቀጠል ስንፈልግ የምንጠቀምበት የአስተሳሰር ዘዴ ነዉ፡፡
የአስተሳሰር ቅደም ተከተሎች

14 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
1. በመጀመሪያ ቅርንጫፍ የሚሆነዉን ገመድ ጫፍ ይላጡ

2. ዋናዉን መሰመር ቅርንጫፉ የሚያያዝበት ቦታ ላይ ይላጡ

3. የተላጠዉን ጫፍ ከተላጠዉ ዋና መስመር ላይ ይጠምጥሙ

15 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የብቃት አሀድ ሦስት
EISBEI 03 2020v1 የኮንዲዩት መስመር ዝርጋታ
3.1 የኮንዲዩት/ የኤልክትሪካል ቱቦ፡- ማለት የኤሌክትሪክ ገመዶችን ከአደጋ ለመከላከል የምንጠቀምበት ቱቦ ነዉ፡፡
3.2 የኮንዲዩት ዓይነቶች፡-የኮንድዩት አይነቶች በሁለት ይከፈላሉ አነሱም
ሀ.ፒቪሲ (ከፕላስቲክ የተሰራ) ኮንድዩት ፡- ተጣጣፊ እና የማይተጣጠፍ ተብሎ ይከፈላል፡፡
ለ. ከብረት የተሰራ ኮንድዩት ናቸዉ፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት የኮንድዩት አይነቶች በብዛት በህንጻ መስመር ዝርጋታ ጊዜ የሚዉለዉ ፒቪሲ ኮንድዩትን ነዉ፡፡
3.3 የፒቪሲ ኮንድት መጠን፡- ብዙዉን ጊዜ ከ13-18ሚ.ሜ ስፋት ያላቸዉ ኮንድዩቶች ለኤሌክትሪክ መስመር
ዝርጋታ እንጠቀምበታለን፡፡ የፒቪሲ ኮንድዩት መጠን የሚወሰነዉ በዉስጡ በሚያለፉት የኤሌክትሪክ ገመዶች
ዉፍረትና ብዛት ነዉ፡፡
ለምሳሌ፡- ባለ 16 ሚ.ሜ መጠን ባለዉ ኮንድዩት ዉሰጥ ከ6-7 የሚሆኑ ባለ 2.5ሚ.ሜ 2 ገመዶች ያልፋሉ፡፡

3.4. በኮንዲዩት ላይ የሚሰሩ ስራዎች


 አቆራረጥ(Cutting)፡- የምንፈልገዉን ኮንድዩት በሜትር ከለካን በኋላ በእጅ መጋዝ መቁረጥ፡፡
 ማጉበጥ(bending)፡- በምንፈልገዉ ርዝመት የተቆረጠዉን ኮንድዩት በእሳት በማሞቅ እንደ አስፈላጊነቱ በተለያየ
የአንግል መጠን (ለምሳሌ 90፣60፣45፣30 ድግሪና በመሳሰሉት) ማጉበጥ ይቻላል፡፡
 ኮንድዩትን የምናጎብጠዉ የኤሌክትሪክ መስመሩን አቅጣጫ ለመቀየር ስንፈልግ ነወ፡፡

ኮንድዩትን ለማጉበጥ የምንጠቀምባቸዉ መሰረታዊ መመሪያዎች


ሀ. የምንፈልገዉን የኮንድዩት ርዝመት መለካት

ለ. አላስፈላጊዉን ኮንድዩት መቁረጥ

ሐ. እንድጎብጥ የሚፈለገዉን ርዝመት መለካት

መ. የተለካዉን ሳይለበለብ በእሳት ማሞቅ

ሠ. በእሳት የሞቀከዉን ሳይጨማደድ ማጉበጥ


 ኮንዲውቶችን ለማራዘም የኮንድዩትን ጫፍ በእሳት በማሞቅ ጁንታ በመስራት ከሌላ ኮንደዩት ጋር
በማያያዝ ማስረዘም ይቻላል፡፡

3.5 የኮንዲውት አክሰሰሪዎች


-ስካቶላ ፡ (junction box)፡- ማለት ሁለትና ከዚያ በላይ ኮንዲዩቶች የሚገናኙበት ማእከላዊ የሆነ እቃ ነዉ፡፡
ስካቶላ 65ሚ.ሜ፣ 85 ሚ.ሜ እና የመሳሰሉት መጠኖች ይኖሩታል፡፡
-ማጋጣሚያ (coupler)፡- በአብዛኛዉ ሁለት የብረት ኮንድዩቶችን ለማያያዝ እንጠቀምበታለን፡፡

16 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
-ክሊፕ (clip)፡- የኤሌክትሪክ ገመዶችን ወይም ኮንድዩቶችን ከገድግዳ ጋር ለማያያዝ የምንጠቀምበት ምስማር
መሳይ እቃ ነዉ፡፡
3.6 ኬብል ትራንኪንግ፡- የኤሌክትሪክ ገመዶችን በግድግዳ ላይ ለመዘርጋት የምንጠቀምበት አራት መእዘን
የሆነ ፕላስቲክ ቱቦ ነዉ፡፡

17 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የብቃት አሀድ አራት
CON ICW 04 2020v1 ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሚያስፈልጉ እቃዎችን ማወቅ
የኤሌክትሪክ መስመር ሲዘረጋ የሚያስፈልጉ እቃዎች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
 የሀይል ማከፋፈያ (Distribution
Board)፣
 ስካቶላ (Junction Box)
 የተለያየ መጠን ያላቸዉ ሰርኪውት ብሬከሮች (Circuit Breaker)
 አምፖሎች እና ማቀፊያዎች
 የተለያዩ ማብሪያ ማጥፊያወች፣ ሶኬቶችና ደወል
 ቫልቮላ (energy meter)
 የተለያየ መጠን ያላቸዉ የኤሌክትሪክ ሽቦ /ገመድ
 መዶሻ
 ማያያዣ (clip)
 ፒንሳ
 መፍቻ (ካቻቢቴ)
 የእጅ መጋዝ
 ኮንዲዩት
 የተለያዩ ኤለክትሪክ መጠን መለኪያ መሳሪያዎች

4.1 የኤሌክትሪክ መብራት መስመር ዝርጋታ (Lighting Installation)

የተለያዩ የኤሌክትሪክ መብራት መስመር ዝርጋታዎች ሲኖሩ፣ ከነዚህም የሚከተሉት ይገኛሉ


ፕሮጀክት 1. አንድን አምፖል ከአንድ ቦታ በነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጣር፡

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ተጠቅመዉ ቦርድ ላይ ይስሩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩት ስራ
ተክክለኘት ያረጋግጡ፡፡

እስኬማትክ ድያግራም ዋይሪንግ ድያግራም ሌይአዉት ድያግራም

አምፖል
አምፖል

ማብሪያ ማጥፊያ
ነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ

18 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 2. ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ አምፖሎችን ከአንድ ቦታ በነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጣር

ስካቶላ 1

አምፖል -1 አምፖል -2

ስካቶላ 2

ነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ተጠቅመዉ የሚከተለዉን ዋይሪንግ ስእል
ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

19 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 3. በመንታ ማብሪያ ማጥፊያ አራት አምፖሎችን መቆጣጣር

አምፖል -1 አምፖል -2

አምፖል -3 አምፖል -4

መንታ ማብሪያ ና ማጥፊያ

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት (ነጠላ መስመር) ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራሙን ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

. ፕሮጀክት 4. ሁለት አምፖልን ከሁለት ቦታ በባለ ሁለት/ በባለሶስት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ተጠቅመዉ የሚከተለዉን ዋየሪንግ ስእል
ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

20 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 5. ሁለት አምፖሎችን ከሶስት ቦታ በባለ ሁለት/ በባለሶስት አቅጣጫ እና በባለ አራት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊ
መቆጣጠር
የተግባር ስራ ቅደም ተከተል
 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ስእል ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

21 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 6. ሁለት አምፖሎችን ከአራት ቦታ በባለ ሁለት/ በባለሶስት አቅጣጫ እና በባለ አራት አቅጣጫ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ስእል ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞከሩ፡፡

ፕሮጀክት 7. ስስት አምፖሎችን ከተለያየ አቅጣጫ መቆጣጠር፡- አንድ አምፖል በነጠላ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር እና
ቀሪዎቹን አምፖሎች ከሶስት ቦታ በባለ ሁለት/ በባለሶስት አቅጣጫ እና በባለ አራት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር

22 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የተግባር ስራ ቅደም ተከተል
 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራም ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨለሱ በኃላ ለስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

ፕሮጀክት 8. ባለሸንበቆ አምፖልን ከሁለት ቦታ በባለ ሁለት/ በባለሶስት አቅጣጫ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያገራም ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞከሩ፡፡

23 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 9. ሁለት አምፖሎችን ከአንድ ቦታ በዲመር ስዊች /ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያገራም ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የስሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

4.2 የሀይል ወይም የሶኬት መስመር ዝርጋታ


ፕሮጀክት 1. የነጠላ ፌዝ ሶኬቶችን (ባለሁለት ቀዳዳ) በመስመር መዘርጋትና የተዘረጋውን መስመር በመሳሪያ መፈተሽ

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረት ስካቱላዎችን፤ በስካቶላና ሶኬት መካከል የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራም ወረቀት ላይ ይሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ድያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ድያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመር ይዘረጉ

24 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

ፕሮጀክት 2. የነጠላ ፌዝ ሶኬቶችን (ባለሶስት ቀዳዳ) መስመር መዘርጋትና የተዘረጋውን መስመር በመሳሪያ መፈተሽ

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በድያግራሙ መሰረት ያስቀምጡ
 በድያግራሙ መሰረት ስካቶላዎች፤ በስካቶላና ሶኬት መካከል የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራም ወረቀት ላይ ይሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ድያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ድያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመር ይዘረጉ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

4.3 የደወል መስመር ዝርጋታ


ፕሮጀክት 1. አንድን ደወል ከአንድ ቦታ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረት በስካቶላና በደወል እንዴሁም በደዎል ማብሪያ ማጥፊያ መካከል የሚፈልጉትን ርቀት
ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያገራም ወረቀት ላይ ይሳሉ

25 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 የሳሉትን ዋየሪንግ ድያገራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩትን ዋየሪንግ ድያገራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መሰመሩን ይዘረጉ፡፡
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡
ትራንስፎርመር

220፡12 ቮልት

1.
ፕሮጀክት 2. አንድን ደወል ከሁለት ቦታ እና ከዚያ በላይ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረት በስካቱላና በደወል እንዴሁም በስካቱላና የደዎል ማብሪያ ማጥፊያ መካከል
የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራም ወረቀት ላይ ይሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ድያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ድያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመር ይዘረጉ፡
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩት ስራ
ይሞክሩ፡፡

ትራንስፎርመር

ፕሮጀክት 3. የቢሮ መጥሪያ ደወል (Announcetor) መስመር መዘርጋት


የተግባር ስራ ቅደም ተከተል
 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረት በስካቶላና በቢሮ መጥሪያ ደወል እንዴሁም በስካቶላና በደዎል ማብሪያ ማጥፊያ
መካከል የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ

26 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ድያግራም ቦርድ ላይ ይስሩ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩት ስራ
ይሞክሩ፡፡

ለይ አዉት ዲያግራም

ዋየሪንግ ዲያግራም

ቁልፍ/ማብራሪያ
/ማመልከቻ ቁጥሮች
/የማመልከቻ ቁጥሮች መደምሻ

/የፑሽበተን መደምሰሻ
/መጥሪያ
/ከመሬት ጋር የሚያያዝ ገመድ/

/ደወል
/የኤሌክትሪክ ኃይል

27 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
4.4 የተለያዩ ሰርኪውቶችን ያጣመረ የህንጻ መስመር ዝርጋታ (Install different electrical circuit)

- የመብራት፣የሀይልና የደወል ሰርኪውቶችን ያጣመረ መስመር ዝርጋታን ማሳየት


ፕሮጀክት 1. ሁለት አምፖሎችን ከአንድ ቦታ መቆጣጠርና ለጠቅላላ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ሶኬቶችን መዘርጋት

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ዲያግራም ወረቀት ላይ የሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ዲያግራም ላስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ዲያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመር ይዘርጉ፡
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩን ስራ
ይሞክሩ፡፡

ፕሮጀክት 2. ሁለት አምፖሎችን ከሶስት ቦታ መቆጣጣር ፤ አንድ አምፖልን ከአንድ ቦታ መቆጣጣር እና በተጨማሪም
የሁለት ሶኬቶችን መስመር መዘርጋት

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ዲያግራም ወረቀት ላይ የሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ዲያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ስእል አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመር ይዘረጉ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩትን ስራ
ይሞክሩ፡፡

28 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ፕሮጀክት 3. አራት አምፖሎችን በመንታ ማብሪያ ማጥፊያ መቆጣጠር ፤ ለአጠቃላይ አገልግሎትና ለተለያዬ አገልግሎት
የሚውል የሶኬት መስመር ዝርጋታ እና በተጨማሪም ደወልን ከሁለት ቦታ መቆጣጣር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል


 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ
 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ዲያግራም ወረቀት ላይ የሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ዲያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ዲያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመሩን ይዘርጉ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩን ስራ
ይሞክሩ፡፡

29 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
4.5 የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ንድፎችን ተረድተዉና አንብበዉ በህንጻ ላይ የሚዘረጉ መስመሮችን በተግባር
ማስቀመጥ
ፕሮጀክት 1. በመመገቢያ አዳራሽና በመኖሪያ ቤትአንድ አንድ ድቡልቡል አምፖሎችን ከተለያየ ቦታ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል

 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ


 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ዲያግራም ወረቀት ላይ የሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ዲያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ዲያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመሩን ይዘርጉ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩን ስራ
ይሞክሩ፡፡

30 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
15 m
1 2

3
0

Dinning room
Living Room

W
W 6

ፕሮጀክት 2. በመኖሪያ ቤት አንድ ድቡልቡል አምፖልና ሶኬት ከተለያየ ቦታ መቆጣጠር እንዲሁም በመመገቢያ አዳራሽ
አንድ ድቡልቡል አምፖል፣ አንድ ሶኬት ና አየር መቅዘፊያ መቆጣጠር

የተግባር ስራ ቅደም ተከተል

 ትክክለኛ ምልክቶችን በተገቢዉ ቦታ በስእሉ መሰረት ያስቀምጡ


 በስእሉ መሰረትበእቃዎች መካከል እራስዎ የሚፈልጉትን ርቀት ይጠቀሙ
 በሌይ አዉት ዲያግራም መሰረት ዋየሪንግ ዲያግራም ወረቀት ላይ የሳሉ
 የሳሉትን ዋየሪንግ ዲያግራም ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የስሩት ዋየሪንግ ዲያግራም አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ ቦርድ ላይ መስመሩን ይዘርጉ
 ቦርድ ላይ ሰርተዉ ከጨረሱ በኃላ ለአስተማሪዎ ያሳዩ
 የሰሩት ስራ ትክክል መሆኑን አስተማሪዎ ካረጋገጠለዎት በኃላ የኤሌክትሪክ ኃይል ሰጥተዉ የሰሩን ስራ
ይሞክሩ፡፡

31 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
1 2

3
3
0

Dinning room
Living Room

6m
W
W

15 m

32 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የብቃት አሀድ አምስት
EISBEI 05 2020v1 በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መሣሪያዎች ብልሽት እና
ጥገና
5.1 የብልሽት አይነቶች

ብልሽት ስንል በኤሌክትሪክ ዕቃዎች ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ቸግሮች ናቸው። እነዚህም


ችግሮች ቀጥሎ የተዘረዘሩት ናቸው

1. ክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit)


2. የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit)
3. የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር መገናኘት(grounding)

1.ክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit)

የክፍት የኤሌክትሪክ መስመር(open circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ


ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም
 የጭነት መብዛት
 የፊዉዝ መቃጠል
 የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መበጠስ
 በደንብ አለመገናኘት ወይም አለመርገጥ
 መዛግ
 መላላት

2.የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit)


የተገናኘ የኤሌክትሪክ መስመር(short circuit) ብልሽት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ብዙ
ምክንያቶች አሉ፣እነርሱም
 የመቃጠል
 የሙቀት መብዛት
 የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ
 እርጥበት

3.የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር መገናኘት(grounding)

የኤሌክትሪክ መስመር ከአካሉ ጋር እዲገናኙ የሚያደርጉ መንስኤዎች

 የኤሌክትሪክ መስመር(ሽቦ) መሸፈኛ መልቀቅ ወይም መቅለጥ

33 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 እርጥበት
 የመቃጠል
 የመላላት

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ብልሽቶች ይሁኑ እንጂ እያንዳንዱ ብልሽት አንዱ ሌላዉን
እንደሚያመጣ ይታወቃል።ለምሳል የኤሌክትሪክ ሥርጭት በአቐራጭ መገናኘት ከአካሉ ጋር
መገናኘትን መበጠስን ያመጣል።

ብልሽቶች በመብራት፣በሞተር፣በትራንስፎርመር ላይ ተመሣሣይ ቢሆም ምልክታቸዉና የጥገና


ሥራቸዉ ይለያያል።ለምሳል መብራትን የወሰድን እንደሆነ አምፖሉ ከተቃጠለ ያለዉ አማራጭ
መጣል ነዉ።የሞተርን ወይም የትራንስፎርመር ሽቦ(winding) ከተቃጠለ ተጠግኖ በሥራ ላይ
ይዉላል።

5.2ብልሽትን የመለየት ዘዴ

ብልሽቶች በተለያዩ መንገዶች ይታወቃል።መረጃን የማወቅና የመለየት ዘዴ አጠቃቀም አንደሰዉ


ልምድ ቢለያይም ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ።

 በማየት
 በመስማት
 በመመርመሪያ መሣሪያ በመጠቀም

 በማየት

የኤልክትሪክ ዕቃዎች ብልሽት( ለምሳል ምጣድ,ምድጃ ) የተበጠሰ ወይም የተቃጠለ ከሆነ


በመፍታተ ውስጡን በመመልከት ብልሽቱ ማወቅ ይቻላል።

 በመስማት

በመስማት ዕቃዎቹ ብልሽቱ ሲያጋጥማቸዉ ሙሉ በሙሉ ሥራቸዉን በማቐማቸዉ ብቻ


ሳይሆን እየሰሩ በሚፈጥሩት ድምፅ ሊደርስ የሚችለውን ብልሽት አስቀድሞ ማስተካከል
ይቻላል።

 በመመርመሪያ መሣሪያ በመጠቀም

ማንኛዉም የኤሌክትሪክ ዕቃ ብልሽት ሲገጥመዉ በቀላሉ የመመርመሪያ መሣሪያዎችን


በመጠቀም የብልሽቱ ዓይነት ለይቶ ለማወቅና ለጥገና አመቺ መሆኑንና አለመሆኑን መለየት
ይቻላል።

የመፈተሻ መሣሪያዎች፡ መልቲ ሜትር ፤ሜገር ፤ቴሰተር

5.3 የኤልክትሪክ ምጣድ አሰራር

34 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ሸክላ ምጣዱን ከኃላ በኩል በዝግታ መቦርቦር ይህም ሲሆን በተቦርቦረበት ጉድጓዶች መኃል
የሚገኘው ርቀት ሁልጊዜ የተመጣጠነ መሆን አለበት፡ይህም የተመጣጠነ ሙቀት ማገኘት
እንዲቻል ነው፡፡አቦራቦሩም ከ ምጣዱ መሃል ተነስቶለየሁለቱ ሪዚሰተሮች መቀበሪያ መሆን
አለበት፡፡የሁለቱን ሪዚስተር ጫፍ በማያያዝ ሪዝስተሮችን በፓራለል እንዲገናኙ ማድረግ፡፡
የሪዝስተርሮች አንዱ ጫፍ ከመሃል ሲሆን ላይኛው ከምጣዱ ጠርዝ ከ አንድ ቦታ ይሆናል፡፡

35 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ከላይ እንደተመለከተው ሲሆን ከመሃል የሚገኘው ሪዝሰተሮች ጫፎች ተመጣጣኝ በሆነ
የመዳብ ሽቦ ቀጥሎ ወድ ሌላ ሽቦ ጫፍ ማለትም ወደ ምጣዱ ጠርዝ በማምጣትሁለቱንም
በፕለግ ማያያዝ(ማሰር)፡፡ በምጠድ የሪዝስተሮችን ጫፎች በምጣድ ማቀፊያአካል ውሰጥ
በተዘጋጀላቸው ቦዮች ውስጥ በዝግታ ማሳለፍ ና የሪዝሰተሮችን ውጥረት ማስተካክል፡፡
ሪዝስተሮቹ በተመጣጠነ ደረጃ ማዞር ከተረጋገጠ(እንጅ ከተለጠጠ ሙቀት ሊሰጥ አይችልም፡፡
)ለሙከራ የሪዝስተሮችን ጨፍ 220ቮልት የኤሌክተሪክ ኃየል በ መስጠት መስራት
አለመስራቱን መመለከት መስራቱ ትክክለኛ ሙቀት መስጠቱ ከተረጋገጠ በኃላ ጀሦውን በዉኃ
በማዋሐድ መሉ በሙሉ ሪዝስተር የተቀበረበትንወራጅ የሚወጣበተን ብቻ በማስቀረት
መለሰን ፡፡

ጀሦ እንዲደርቅ ከተደረገ በኃላ ከምጠድ አቃፊ ጋር በመግጠም ወራጁን በሸክላ ማገነኛ


የኤሌክትሪክ ኃይል ከሚያመጣው ሸቦ በማገናኘት ኃይል በመስጠት ሸክላውን በማሙሸት
እንጅራ መጋገር ይቻላል፡፡

36 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የብቃት አሀድ ስድስት
EISBEI 06 2020v1 በቡድን ስራ መስራት (Work with Others)

ዋናው ዓላማ
በዚህኮርስስልጠናላይሰልጣኞች ከሰለጠኑ በኋላ ማወቅ የሚገባቸው ነጥቦች፡-

- የተሰጡን ስራዎች በተፋጠናና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለመስራት የቡድን ስራ መመስረት


አስፈላጊ መሆኑን፣

- ስራዎች ለየብቻና በጋራ(በቡድን) ሆነን በምንሰራበት ወቅት በሁነቶች ላይ ያለውን ልዩነት


ማወቅ፣

- የቡድን ስራን በመስራት በተሰጠውና፣ በተፈለገው ቦታ እና ጊዜ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ


ለማከናወን እንደሚቻል፡፡
ማውጫ
ክፍል አንድ
1. የቡድን ስራን መመስረት ሚና እና ዓላማው ምንድን ነው?
1.1. የቡድን ስራ ሚና
1.2. የቡድን ስራ ዓላማ
ክፍል ሁለት
2. በግለሰብና በቡድን ስራ ላይ ያላቸው ኃላፊነትና ሚና
2.1. በግል(ለብቻ) ስራን መስራት
2.2. በቡድን ስራን መስራት
2.3. ቡድኖች በራሳቸውጋርእናከሌሎችጋርያላቸውግንነት
2.3.1 ቡድኖችከራሳቸውጋር ያላቸውግንነት
2.3.2 ቡድኖችከሌሎች ጋር ያላቸውግንነት
ክፍል ሶስት
3. የቡድን አባል ሆኖ መሳተፍ

37 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ክፍል አንድ
1. የቡድን ስራ መመስረት ሚና እና ዓላማ ምንድን ነው?
1.1. የቡድን ስራ መመስረት ሚናዎች፡-
ግለሰቦች በተደራጁበት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎችም ሆነ በተለያዩ ድርጅቶች
የቡድን ስራ መመስረታቸው በሰለጠኑት የሙያ ዘርፍ ስራዎችን ከመስራትና ከማከናወን
በተጨማሪ እርስ በርሳቸው የተለያዩ ስራ ፈጣሪዎችን እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል፡፡ በመሆኑም
በቡድን ወይም ተደራጅተው በሚሰሩበት ወቅት በማህበረሰቡ ወይም በተጠቃሚዎች (users) ላይ
ተቀባይነት እንዲያገኙና ለሚሰሯቸው ተግባሮች ላይ ችግር በሆኑት ጉዳዮች አባላቶች እርስ
በርሳቸው በመነጋገርና ሀሳቦችን ለችግሮች ማፈላለግ፣ መፍትሄዎቻቸውን በማግኘት የተሻለ
ውጤት እንዲያስመዘግቡ ይረዳቸዋል፡፡
ሌላው የቡድን ስራ ላይ የተለያዩ ሰዎች የሚሳተፉበት በመሆኑ እነዚህም የተለያዩ ሰዎችም
የተለያየ የስራ ፈጣሪ ክህሎት ሊኖራቸው ስለሚችልና አዲስ ነገርም ከፈጠሩ በገበያ ላይ
በማውጣት ለማህበረሰቡ በማሰራጨት የድርጅታቸውን ስም በማስጠራትና የድርጅታቸው ኢኮኖሚ
እንዲበለፅግ ለማድረግ ወይም ለማስቻል ይረዳቸዋል፡፡
በተጨማሪም የቡድን ስራ በተነደፈው የመንግስት እስትራቴጂ ላይ በሀገሪቱ ያለውን ስራ
አጥነት ቁጥር በመቀነስ የተለያዩ ስራዎች በጋራ በመሆን በአንድ ሰው ብቻ መሰራት የማይችልን
ስራዎች በተደራጀ ወይም የቡድን ምስረታ በማካሄድ በኢኮኖሚ አነስተኛ የሆኑ ሰዎች ወደ ተሻለ
ስራ እንዲሰማሩ ያግዛቸዋል፡፡
1.2 የቡድን ስራ መመስረት ዓላማዎች፡-
እየተካሄደ ያለው የቡድን ምስረታ ሂደት ዓላማ በቡድኑ ውስጥ የተቀናጀ፣ የተዋሃደ፣ወጥነት
ያለውና ያልተማከለ ሁሉን አቀፍ ሆኖ ለሚሰሩት ስራዎች የገበያን ፍላጎትን መሰረት አድርጎ
ለቡድኑ(ለድርጅቱ) በውጤት ላይ የተመሰረተ ምርቶችን ለመስራትና ለመፍጠር ጥሩ የሆኑ
ተግባሮችን ማከናወን ነው፡፡
ሁሉን አቀፍ ማለት በምንሰራቸው ስራዎች ላይ በአንድ የስራ ዘርፍ ሳይወሰኑ በተለያዩ የስራ
ዘርፎች በሁሉም የኢኮኖሚ ሴክተር ለሚፈልጉት የምርት ውጤት መሰረት አድርጎ እኩል ማዳረስ
ማለት ነው፡፡
የተዋሃደ ስንል በቡድን ተደራጅተው ስራው በሚሰራበት ወቅት እርስበርሳቸው ሳይለያዩ ጥሩ
የሆነ አመለካከትና ፀባዮችን ማሳየት ነው፡፡

38 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ያልተማከለ መሆን አለበት ስንል በቡድን ምስረታው ላይ ትልቁና ትንሽ፣ ጠንካራና ደካማ፣
እውቀት ያለው እና የሌለው፣ ሴትና ወንድ ብለው ሳይለያዩ አላማዎቻቸውን ግብ ግብ ማድረስ
ነው፡፡ በመሆኑም ከእነዚህ ከላይ ከተዘረዘሩት ገንቢ አስተሳሰቦች በተጨማሪ ዋና ዋናዎቹ የቡድን
ዓላማዎች፡-

- የቡድኑን ሀሳብና አስተያየት መሰረት አድርጎ የተለያዩ ስራዎች መፍጠር፣


- ስራዎችን በተፋጠነ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን፣
- የስራ አጥነት ቁጥርን ለመቀነስና የስራ ፈጠራን ቡድኖች ውስጥ እንዲያመነጩ፣
- በጠቅላላ ስራዎች ሁሉ በተፈለገው ደረጃ ተሰርተው ዓላማውን ግብ እንዲመታ ማድረግ
ነው፡፡
ክፍል ሁለት
1. በግለሰብና በቡድን ስራ ላይ ያላቸው ኃላፊነትና ሚና
አንድ ግለሰብ በሚሰራበት ድርጅት ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦችንና መረጃዎችን መግለፅና
ማንፀባረቅ የሚቻለው በተሰጠው የስራ ኃላፊነት ብቻ ነው፡፡በመሆኑም በድርጅቱ ውስጥ የሚሰሩ
የተለያዩ ተግባሮች ላይ ሀሳብ የመስጠትም ሆነ የመግለፅ ሀይል ወይም ስልጣን የለውም፡፡ ስለዚህ
ያለውን ብቃት/ችሎታ/ጥሩ ወይም መጥፎ ነው ብሎ ሳይል ከሚያገኘው ጥቅም ውጭ ሌላ
ነገሮችን መስራት አይችልም፡፡ በግለሰቡ ላይ ያለው ስራ የመስራት ችሎታ ከሚያገኘው የገቢ
ምንጭ ጋር ሲወዳደር በጣም በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡
በአጠቃላይ አንድ ግለሰብ በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተገብቶ ለብቻው በአንድ ስራ
ሃላፊነት በሚሰራበት ወቅት የሚከተሉትን ነገሮች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

- የተለያዩ ስራዎች በሚሰሩበት ወቅት ስራውን ለብቻው የሚወጣቸው ይሆናል፡፡


- በአምባገነንነትና ስልጣን በተዋረድ ላይ የተመሰረቱ ስራዎች ይከናወናሉ፡፡
- መጠነኛ የሆነ ነፃነት የሚንፀባረቅበት ነው፡፡
- የተለያዩ ስራዎች ላይ የበላይ እን የበታች በመሆን ይንፀባረቅባቸዋል፡፡
- በስራዎች ላይ ችግሮች ቢፈጠሩ ለችግሮች (risks) በስራው ኃላፊነት ላይ ለሚሰራው
ግለሰበ ብቻ ይሆናል፡፡

- በሰልጣኞች ላይ ያላቸው ሚና እርስ በርሳቸው የተለያዩ ችግሮችን በጋራ በመሆን መፍታት


አይችሉም፡፡

39 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
- በስራው ላይ የተለያዩ ውድድሮች የሚካሄዱት በግል በሆነው ድርጅት ውስጥ ብቻ ይሆናል፡

- በስራቸው የሚያከናውኗቸውን ተግባሮች የሚገመግሙት በሌሎች ስልጣን ባላቸው


አካላትና ወይም የቅርብ ተጠሪ በሌላቸው እና በሌላ በሆነ ግለሰብ ነው፡፡

- ለስራዎች ሁሉ ግባቸው የት ቦታ ላይ መደረተስ እንዳለበት አያውቁም፡፡


- የተለያዩ ሀሳቦችንና አስተያየቶችን በግለሰቡ ድርጅት ውስጥ ካሉ አካላት ጋር ሊሳተፉ
ላይሳተፉም ይችላሉ፡፡
2.2 የቡድን ስራ እና ኃላፊነት ምንድን ነው?
የቡድን ስራ የተለያዩ ግለሰቦች ወይም ከሁለተኛ ከዚያም በላይ የሆኑ ቡድኖች
እርስበርሳቸው አባሎች ከፈለጉበት ደረጃ (common goal) ድረስ በመተባበር የሚደርሱበት ስራ
ነው፡፡ ስለዚህ ሁሉም አባላት ግባቸውን ማሳካት እስከሆነ ድረስ የስራ ሃላፊነታቸው በጣም
የተገደበ እና የተወሰነ አይደለም፡፡ በመሆኑም በቡድኑ ውስጥ ባሉ አባሎች በሚሰሩት ወይም
በሚከናወኑት የስራ ዘርፎች ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን በነፃነትና ያለፍርሐት የመግለፅ እና
የማንፀባረቅ መብታቸው በእጅግ የበዛ ነው፡፡ ከዚህ ሌላም እያንዳንዱ አባላት የሚያገኙት የገቢ
ምንጭ (ደመወዛቸው) የሚወሰነው በሚሰሩት የስራው አይነት ላይ የተመሰረተ አድርጎ ነው፡፡
በመጨረሻም ሁሉም የቡድን አባላት እርስ በርሳቸው በመተማመን፣በመከባበርና በመፈቃቀር
ችሎታቸውን ሙሉ በሙሉ ተጠቅመው እስከ ስራው ፍፃሜ ድረስ ስራቸውን የሚያከናውኑ
ናቸው፡፡
በአጠቃላይ በቡድን ሆነው በሚሰሩበት ወቅትና በስራዎች ላይ ያላቸው ሃላፊነት
የሚከተሉትን ነጥቦች ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

- ለተሰጡት ሥራዎች ሁሉ በተወያዩባቸው ሀሳቦችና አስተያየቶች ግባቸውን ለማሳካት እርስ


በርሳቸው ሥራውን የሚያከናወኑ ይሆናል፡፡

- በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ጥሩ የሆነ ግንኙነትና ተሳትፎ የሚታበት ነው፡፡ በማንኛውም


የሥራ ክንውን ወቅት ሁሉም አባላት ጥሩ የሆነ ነፃነት አላቸው፡፡

- በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ ልዩነቶች በጉልህ ማየትና ማስተያየት አይንፀባረቅበትም፡፡


- በሚሰሩበት ወቅት የተለያዩ ችግሮች ቢከሰቱ ስለችግሮቹ ሁሉም የቡድኑ አባላት
መፍትሄዎችን የሚፈልጉበት ይሆናል፡፡
በሥራው ላይ ሥልጣን ያላቸው አካላት(ተወካዮች) ለቡድኑ የተለያዩ ሀሳቦችን ያካፍላሉ፡፡

40 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
- የተለያዩ ውድድሮች የሚከናውኑት በራሳቸው ድርጅት ብቻ ሳይሆን ከሌላ ድርጅት ጋርም
ይሆናል፡፡

- የሚያከናውኗቸውን ተግባሮች በሥራቸው ላይ የሚገመገሙት በቡድን አባሎች ባለው


የመገምገሚያ መስፈርት አድርጎ ይሆናል፡፡

- በሥራዎች ላይ አባላቶች የትቦታ መድረስ እንዳለበት በደንብ አድርገው ያውቃሉ


- በስራዎች መጨረሻ ጊዜያቶች ላይ ጥሩ ለሰሩ የቡድን አባላት የማበረታቻ ሽልማቶች
ያካሄዳሉ፡፡

- ሀሳቦችን ፣ አስተያየቶችን በማንኛውም ጊዜና ሰዓት እያንዳንዱ የቡድን አባል በነፃነት


የመግለፅ መብቱ በእጅጉ የሰፋ ነው፡፡
2.3. ቡድኖች ከራሳቸው ጋር እና ከሌሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት
ቡድኖች ከራሳቸው
2.3.1. ቡድኖች ከራሳቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት፡-
ቡድኖች ከራሳቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ስንመለከት በስራቸው ላይ ያለው እንቅስቃሴ
የተለያየ ሳይን በተመሳሰለና ወጥነት ባለው መልኩ ነው፡፡ ይህም ስንል የቡድኑ ግንኙነት፡-

- የቡድኑ አባላቶች ጥሩ የሆነ መግባባት ሲያሳዩ ይታያል፡፡


- የቡድኑ አባላቶች የተለያዩ እውቀትና ችሎታ የሚያሳዩ ናቸው፡፡
- ሁሉም ቡድኖች በስራዎች ላይ ራዕይ እንዳላቸው እርስ በርስ ይነጋገራሉ፡፡
- ግባቸውን ለመምታት አባላቶች በአነድ ላይ ለስራ ይተጋሉ፡፡
- በስራዎች ላይ ከባድ ችግር በከፈጠረ እርስ በርስ በመወያየት መፍትሔዎችን ይፈልጋሉ፡፡
- ሁሉም የእርስ በርስ የሀሳብ መለዋወጥ ይኖራቸዋል፡፡
- ለቡድኑ የስራ ውጤት እንዲጨምር ቀላልና ግልፅ መንገዶችን ይቀይሳሉ፡፡
2.3.2. ቡድኖች ከሌሎች ጋር ያላቸው ግንኙነት፡-
የቡድን ስራ የተለያዩ ሰዎች በአንድ ላይ በመሆን ወደፈለጉበት ግብ (goal) የሚያደርሱበት
ሒደት ነው፡፡ በመሆኑም የተለያዩ የቡድን አባሎች እያንዳንዱ አባል በቡድኑ ላይ ያለውን
ባህሪያቶችና ፀባዮች አውቀው ጥቅማቸው ጥሩ በሆነ መልኩ እንዲጠበቅና እንዲያሳድጉ እርስ
በርሳቸው መጠናናት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም የተለያዩ የቡድን መስተጋብር ለውጥ የሚኖረው
በራሳቸው ላይ በሚያከናውኑበት ወቅት በተለያዩ የቡድን ምስረታዎች መጥፎ የሆኑን ነገሮች
የቡድኑን እድገት ወደኋላ ስለሚያደርግ የተለያዩ መልሶችን በማዘጋጀት ወደ ጥሩ ነገሮች ማምጣት

41 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ተገቢ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከአንዱ ቡድን ውስጥ ሳይፈልጉ በግድ ከቡድኑ አባልነታቸው
ይፈናቀላሉ፡፡ በተጨማሪም በምትኩ ሌላ አዲስ ወደ ቡድኑ የሚገቡ አባላቶች በስራው ላይ ያለውን
ልምድ ስለማያውቁ ለወደፊቱ የሚከናወኑ ስራዎችን ስለሚያዳግታቸው የቡድኑን ስራ ወደኋላ
ሊጎትት ይችላል፡፡ ስለዚህ በሁለት እና ከዚያ በላይ ባለ የቡድን ግንኙነት መካከል ስራን
እየተናበቡና ቅደም ተከተልን ጠብቆ መንቀሳቀስ የተለያዩ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ሲጠቅም፤
በተጨማሪም ደግሞ የተለያዩ ቡድኖች እድገታቸው አንድ ላይ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ክፍል ሶስት
3.የቡድን አባል ሆኖ መሳተፍ
አንድ ግለሰብ የቡድን አባል ሆኖ በሚሳተፍበት ወቅት በቡድን ውስጥ የተለያዩ ችሎታ
ያለቻው ግለሰቦች ስለሚኖሩ ግለሰቡ ከራሱ ሙያ ውጭ ሌሎች በቡድኑ ውስጥ ሉ የሚሰሩትን
ሙያዎች ሁሉ ሊያውቅ ስለሚችል ግለሰብን የተለያየ የሙያ ባለቤት በማድረግ ሲጠቅም፤
በተጨማሪም ደግሞ ግለሰቡ በራሱ ብቻውን ሊደርስባቸው ከማይችላቸው ስኬቶች ላይ በአጭር
ጊዜ በማድረስ ሊጠቅም ይችላል፡፡ ግለሰቡ በቡድን በሚደራጅበት ወቅት የሚከተሉትን ነጥቦች
ማወቅ ይጠበቅበታል፡፡

- በመጀመሪያ ደረጃ የቡድኖች አባላት የሚደርሱበትን (goal) ማወቅ ይኖርበታል፡፡


- በስራው ላይ ያሉትን ህጎች በደንብ አድርጎ ማጥናትና መወቅ አለበት፡፡
- በስራ መጀመሪያ ወቅት መደናገር (confusion) ሊኖር ስለሚችል በተረጋጋ አካሄድ
ነገሮችን ማስኬድ ያስፈልጋል፡፡

- ከቡድን አባላቶች ጋር መወያየትና ለተለያዩ ችግሮች መፍትሔዎችን መፈለግ እያንዳንዱ


የቡድን አባላት ሃላፊነት መሆኑን ጠንቅቆ ማወቅ አለበት፡፡

- ግለሰቡ የቡድን አባል ሆኖ ሲሳተፍ ግልፅነት፣ ተጠያቂነት፣ ቅንነትና ጥሩ አመለካከት


ያለው ሊሆን ይገባል፡፡

- በአጠቃላይ ግለሰቡ ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦችና ሌላም ነገሮች አውቆ ስራዎችን


ሲያከናውን ግለሰቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የራሱን ግብ ከመምታቱም ባሻገር የቡድኑም
ግብ በታሰበው ጊዜ ውስጥ እንዲመታ ሲያደርግ ቡድኑን ወደ ተሻለ የእድገትና ለውጥ
ሊያደርሰው ይችላል፡፡

42 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የብቃት አሀድ ሰባት
CON ICW 07 2020v1 በስራ ቦታ ላይ መግባባትና ምላሽ በመስጠት
መልካም የስራ ግንኙነት መፍጠር
(Receive and Respond to Workplace Communication)

ዋና ዓላማዎች
ይህን ኮርስ ከሰለጠኑ በኋላ ሰልጣኞች የሚከተሉትን ነገሮች ሊችሉ ይችላሉ፡፡
 አስቸጋሪ የሆኑ ሥራዎችን በንግግርና በጽሀፍ ማስታወሻ በመያዝ መስራትን ይችላሉ
 በስራ ቦታ ስብሰባ ላይ ሃብ ሰጣሉ፣ ይወያያሉ
 የስራን መጠን ይገምታሉ፣ ይመዘግባሉ፣ ያስቀምጣሉ
 ተግባቢነታቸውን ይጨምራሉ
ማውጫ
1. ስለመግባባት መግለፅ
1.1. መረጃ ማግኘትና ለሌሎች ማሰራጨት
2. በስብሰባ ላይ መሳተፍና መወያየት
2.1. የግሩፕ ስብሰባ (Team)
2.2. የስብሰባው ዋና ይዘት
2.3. ሥብሰባውን ማካሄድ
2.4. የስብሰባውን ሀሳብ መተርጎምና መተግበር
3. ተጨባጭ የሆነ ዶክመንትን ማዘጋጀት
3.1 ሪፖርት ማዘጋጀት

43 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
1. ስለ መግባባት መግለጽ/Introduction/
በአንድ አካባቢ ወይም ስፍራ ውስጥ ሰዎች ጥሩ የሆነ ግንኙነት ለማድረግ የመግባባት
ችሎታ(skill) ለተለያዩ ጥቅሞች በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ለምሳሌ በክፍል ውስጥ መምህራንና
ተማሪዎች በማስተማርና በመማር ሂደት ላይ ጥሩ የሆነ መግባባት ሊኖር ይገባል፣ አንድን ስራ
በምንሰራበት ጊዜ በጋራ (groups) ጥሩ የሆነ (effectively) እንዲኖረው መግባቢያ ነገሮች
በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ መግባቢያ በማንኛውም የኑሮ ህይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ
ነገር ነው፡፡ ስለዚህ አንተ በመግባባት ( by persuade) ጥሩ የሆነ ግንኙነት፣ ተመሳሳይነት
(inform) ፣ የሀሳብ መለዋወጥ(share) ከሌላ ሰው ጋር ለማድረግ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ ብዙ
ሰዎች ጥሩ በሆነ መግባባት አንድን ስራ በተሳካ መልኩ ሲተገብሩ ጥሩ የሆነ ግንኙነት ያሳያሉ፡፡
በመሆኑም መግባባት ስንል ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በህይወታቸው ጊዚያቶች ውስጥ
አንድን ስራ ለመስራትም ሆነ የተለያዩ ተግባሮችን ለመስራት የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው፡፡
የመግባቢያ ክፍሎች (Elements of communication)
መግባቢያ ማለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ሀሳባቸውን ለመለዋወጥ፣ ፍላጎታቸውን
ለማካፈል የሚጠቀሙበት ስልት ነው፡፡ ሰዎች በሚግባቡበት ወቅት በመነጋገር ብቻ
ሳይሆን በጽሁፍ፣ በእንቅስቃሴ፣ በፀባያቸው (mannerisms)፣ በሁኔታዎች ሁሉ
መልስ መስጠት (message) ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ለመግባባት የግድ
አስፈላጊ የሆኑ ክፍሎች ከሚባሉት ውስጥ፡-
1. ላኪ (sender)
2. ተቀባይ (receivers)
3. መልዕክት ነጋሪዎች የሚባሉ(message)
4. መልዕክት (channels)
5. እረብሻ (noise) (ጫጫታ)
6. መልስ (feedback)
7. setting (እንቅፋት ነገሮች) ዋና ዋናዎች የተባሉት እነዚህ ናቸው፡፡
ሀ) ላኪ (sender)
ይህ ክፍል በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ የተለያዩ ሀሳቦችንና ፍላጎቶች በመፍጠር በማድረግና
ሀሳቦችም ግብ እንዲመቱ የሚመቻችበት ስፍራ ወይም የመጀመሪያው ክፍል ነው፡፡ ስለዚህ ሰዎች
ሀሳባቸውን በስልክ፣ በደብዳቤ (በፖስታ) ፣በኢሜኤል ወ.ዘ.ተ ነገሮችን በመጠቀም መልዕክት
በትክክል ወደ ተቀባይ አካል (receiver) እንዲደርስ የሚያደርግ ክፍል ነው፡፡

44 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ለ) መልዕክት (message)
በዚህኛው ደረጃ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችንና ፍላጎቶችን በመያዝ ላኪውና ተቀባዩ እንዲግባቡ
የሚያመቻች ክፍል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ክፍል ውስጥ ሀሳባችን በመግለፅ፣ በመልክት፣ ቋንቋ
በመጠቀም፣ ግልፅ በሆነ በአጠቃላይ (verbal) በመጠቀምና በፊታችን የተለያዩ ነገሮችን በማሳየት፣
በአቋቋም፣ በድምፅ፣ በቅርፅ (nonverbal) ስልት በመፍጠር ላኪው ያለችግር ወደ ተቀባዩ
እንዲደርስ የማመቻቸት ስራ የሚሰራበት ክፍል ነው፡፡
ሐ) አስተላላፊ ነገሮች (channels)
ይህ ደግሞ በመያዝ አቀባይ በሆነው ክፍል (message) አድርጎ የላኪውን መልዕክት ለተቀባዩ
ለማድረስ የሚጠቅም ክፍል ነው፡፡ በዚህኛው ክፍል ላኪውና ተቀባዩ በመተያየት እርስ በርሳቸው
በመነጋገር፣ ሳይተያዩ በድምፅ፣ በማዳመጥ፣ መልዕክቱን እንዲቀባበሉ ሁኔታዎችን የሚፈጥር
ነው፡፡
መ) መልዕክት ቀባይ (receiver)
በዚህ ክፍል ውስጥ ላኪው (sender) የላኪውን ሀሳቦችና ፍላጎቶች መልዕክቱን በትክክል
የሚቀበል ክፍል ነው፡፡
ሠ) መልስ መስጠት (feedback)
ይህ ክፍል ላኪውና ተቀባዩ ያለምን ችግር ሀሳቦችንና ፍላጎቶችን በመግባባት ሁኔታዎችን
በተግባር ሲገልፁ ነው፡፡
ረ) እረብሻ (Noise)
ይህን በሌላ አባባል ጫጫታ ተብሎ ይጠራል፡፡ በመሆኑም መልዕክት በአቀባዩ (message)
አድርጎ በሚጓዝበት ወቅት ከመጠን ባለፈ የድምፅ መጠን በትክክል መልዕክቱ በአስተላላፊው
አካል ላይ (channel) ውስጥ ሳይሔድ ቀርቶ ለተቀባዩ ሳይተላለፍ ሲቀር ረብሻ አካል ብለን
እንጠራዋለን፡፡ እረብሻን በሶስት ከፍለን እናየዋለን፡፡
ሀ) በውስጣዊ
ለ) በውጫዊ
ሐ) ድንገት (semantic)
ሀ. ውስጣዊ/Internal/ ስንል፡- ሰዎች ላይ በሚፈጠረው የአዕምሮ አለመቀበል/ዝግጁ
አለመሆን ነው፡፡
ለ. ውጫዊ/External/፡- በአካባቢው በሚፈጠረው ከፍተኛ ድምፅ መኖር ምክንያት
መልዕክቱን በትክክል አድርጎ ሳይገናዘቡ መቅረት ነው፡፡

45 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ሐ. ድንገት/semantic/፡- በአጋጣሚ መልዕክቶችን በተሳሳተ አባባል ለተቀባዩ እንዲደርስ
ማድረግ ነው ምሳሌ፡- ቃሎችንም ሆነ አረፍተነገሮችን በመቆራረጥ ለተቀባዩ ማድረስ
ነው፡፡
ሸ) እንቅፋት ነገሮች/setting/
ሰዎች በአካባቢው ባህል፣ ልማድን በመያዝ የተለያዩ አመለካከት/ሀሳብ የሚያራምዱበት ስልት
ነው፡፡ ይህ ምሳሌ በአንድ አዳራሽ (auditorium) ውስጥ በሚሰባሰቡበት ወቅት የተለያየ አመለካከት
በመኖሩ ምክንያት በአንድ ሀሳብ ላይ የተቃረነ ነገር በመያዝ/በመናገር ጥሩ የሆነው መልዕክት
መጥፎ በማስመሰል በመናገር ተናጋሪውን ለተሰብሳቢዎች እንደተሳሳተ አድርጎ የሚያሳይ ሁኔታ
ነው፡፡
1.2 የመግባባት ጥቅሞች
የመግባባት ጥቅሞች ከሚባሉት ውስጥ ጥቂቶቹ፡-
ሀ) ዓላማን ከግብ ለማድረስ
ለ) እቅዶችን በፍጥነት ለመጨረስ(ለመፈፀም)
ሐ) ሰዎች እንዲደራጁና ባላቸው ጥሬ ሀብት በመጠቀም ተጠቃሚ ለማድረግ ነው
መ) ብቃት/ክህሎትን ለመለካትና ለመቆጣር
ሠ) ችግሮችን ተወያይቶ በጋራ ለመፍታት ወ.ዘ.ተ ናቸው
2.በስብሰባ ላይ መሳተፍና መወያየት
2.1. የመግባባት ችሎታ፡-
የመግባባት ችሎታ የምንለው ሰዎች ያላቸውን እውቀት በተግባር መግለፅ/ማንፀባረቅ ሲችሉ ነው፡

የሰዎችን ችሎታ በሶስት ከፍለን ማየት እንችላን፡- እነሱም
ሀ) በስልት/በሙያዊ (technical skill)
ለ) የሰዎች ፍላጎት (human skill)
ሐ) ፅንሰ ሐሳቡን መረዳት (conceptual skill)
ሙያዊ ስንል ፡- ሰዎች ባለቸው ችሎታ/ብቃት ስልቶችን በመጠቀም እን ደየሁኔታዎች
በቅደም ተከተል መስራት ሲችሉ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ስራውን ሙያ ወይም ፈጠራ
በመመልከት ሌላኛው ሰው የተመለከተውን ስራ ደግሞ መስራት ሲችል ነው፡፡
የሰዎችፍላጎትእናእውቀት፡- አንድስራለመስራትአንደኛውከሌላኛውጋርጥሩየግንኙነት
የሚኖረው እውቀት እና ፍላጎት ሲኖረው ብቻ ነው፡፡ እውቀት ያለው ሰው በራሱ የሚተማመን፣

46 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ነገሮችን በቀላሉ አይቶ መረዳት የሚችልና ምቾቱንና ፍላጎቱን ለሰዎች የሚሰጥና የሚያካፍል
ነው፡፡
ፅንሰ ሀሳቡን መረዳት፡- አንድን ሀሳብ ወይም ስራ ከመስራታችን በፊት፣ ወደሚፈለገው
ቦታ ወይም ወደ ሰዎች ለማድረስ የተሰጠው ሀሳብ ምን ዓይነት ትርጉም የያዘ መሆኑንና
በትክክለኛው አካሄድ ለማስኬድ በጥሩ ሁኔታ ፅንሰ ሀሳቡን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡
2.2 የመግባባት እንቅፋቶች (caution in communication)
ለመግባባት መሰናክል ናቸው ብለን የምንላቸውን ዘርዝረን ማየት እንችላለን፡-
ሀ) መጥፎ በሆነ መንገድ መግለፅ (Badly expressed message)
ለ) ስህተት በሆነ መል መተርጎም
ሐ) ተመሳሳይ ያልሆነ (የተለየ ቋንቋ መነጋገር)
መ) ፍላጎታዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ የሚንፀባረቅ ከሆነ ወ.ዘ.ተ
በስብሰባ ላይ መሳተፍና መወያየት
በስብሰባ ላይ አንድ ሰው ተሰብስቦ መወያየት እንዲችል ተሳታፊው የመግባባት ስልቶችን
ማወቅ ይኖርበታል፡፡ የመግባባት ስልቶች የምንላቸው እንደ፡-
ሀ) ከአእምሮ ወይ ከራስ ጋር መግባባት/Intrapersonal communication/
ለ) አንድ ሰው ከብዙ ሰዎች ጋር ሲግባባ/Intrapersonal communication/
ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ሲግባቡ /small group communication/
መ) ከብዙ ሰዎች ጋር መግባባት /public communication/

ሀ) ከራስ ጋር መግባባት ስንል ለአንድ ሰው ከሆነ አካል መልዕክት ይላክለታል፡፡ ይህ


መልዕክት የተላከለት አካል ለራሱ መልስ ሲሰጥ ይህ የመንግስት ዓይነት ከራስ ጋር ወይም
ከአእምሮ ጋር መግባባት ይባላል፡፡
ለምሣሌ፡- ዝናቡ ሰውዬው ላየ ሲዘንብ ሰውየው ጥላ ከፈተ
ለሰውዬው ተላፈው መልዕክ፡- ት ዝናብ ሲሆን
ሰውዬው የሰጠው መልስ ጥላ መክፈት ነው፡፡
ለ) ለአንድ ሰው ከብዙ ሰዎች ጋር ሲግባባ
ይህ ደግሞ አንድ ሰው ለሁለትና ከዚያ በላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር የሚያካሂደው የመግባባት ዓይነት
ይህንን የመግባባት ዓይነት አስበነውና ፕሮግራም (program) ይዘንለት የምናካሂደው የመግባባት
ዓይነት አይደለም፡፡ ባጠቃላይ ፎርማል አይደለም፡፡

47 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
ሐ) ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች ሲግባቡ (small group communication)
ቁጥራቸው ትንሽ የሆኑ ሰዎች በአንድ ላይ በመሰብሰብ አስበውትና ግዝ ቆርጠውለት
ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚካሂዱት የመግባባት ዘዴ ነው፡፡
ከብዙ ሰዎች ጋር መግባባት (Public Communication)
ብዙ ሰዎች በአንድ ላይ በመሰብሰብ ወይም ብዙ ሰዎች በየቦታው ቴሌቪዥን በመመልከት ሬዲዮ
በመስማት ጋዜጣ በማንበብ ወ.ዘ.ተ ነገሮችን በመጠቀም ብዛት ያላቸውን ሰዎችን የማግባባት
ሂደት/ዘዴ ነው፡፡
2.1. የግሩፕ ስብሰባ (Team)
የግሩፕ ስብሰባ ለማካሄድ ስብሰባው ውስጥ የሚካፈሉ ቡድኖች ስብሰባውን የሚመራ
ሊቀመንበር፣ ጸሃፊ፣ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ተሟልተው ሲገኙ ስብሰባውን ማካሄድና መወያየት
ይቻላል፡፡ እነዚህ ባልተሟሉበት ቦታ የምናከናውነው ውይይት የግሩፕ ስብሰባ ሊባል አይችልም፡
፡ ስለዚህ የግሩፕ ስብሰባ ለማካሄድ ለስብሰባ አስፈላጊ የሆኑት ሙላተ ጉባኤው መሟላት
እንዳለባቸው ከወዲሁ ማወቁ አስፈላጊ ነው፡፡
2.2. የስብሰባው ዋና ይዘት
አንድ ስብሰባ እንደሚታወቀው ዋና ይዘት ይኖረዋል፡፡ ይህ ዋና ይዘት የምንለው በተለምዶ
አጀንዳ የምንለው ሲሆን ይህ አጀንዳ ለተሰብሳቢው ከስብሰባ መሪ/ከሊቀመንበሩ የሚነገር ሲሆን
ከተሰብሳቢ ውስጥ ደግሞ ሰዎች ተወያይተውበት መፍትሄ የሚያስገኝ ሀሳብ ያለው ተሰብሳቢ ካለ
አጀንዳውን ማስያዝ ይችላል፡፡ ባጠቃላይ የስብሰባ ይዘት የምንለው ሰዎች እንዲወያዩባቸው ከስብሰባ
መሪው ከተሰብሳቢው የሚወጡ የአጀንዳ ብዛቶች ናቸው፡፡
2.3. ስብሰባውን ማካሄድ
ስብሰባውን ለማካሄድ ከመጀመራችን በፊት የስብሰባው መሪዎች ለተሰብሳቢው እራሳቸውን
ያስተዋውቃሉ፡፡ በተጨማሪም ደግሞ ለያንዳንዱ አጀንዳ ምን ያህል ጊዜ እንደሚፈልግ ሰዓት
ያስያዛሉ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በእያንዳንዱ አጀንዳ ላይ በተያዘለት ሰዓት መሰረት ውይይት ማካሄድ
ይጀመራል ይህ በሚሆንበት ሰዓት ፀሐፊው የውይይቱን ቃለ ጉባኤ ይፅፋል፡፡ ይህ ሂደት ስብሰባ
ማካሄድ ይባላል፡፡

2.4. የስብሰባውን ሀሳብ መተርጎምና መተግበር


ከስብሰባው ላይ ከተገኙ ወይም ከተላለፉ መፍትሄዎች ውሳኔዎች በመነሳት ተሰብሳቢዎች
በእነዚህ ውሳኔዎች መሰረት መተርጎምና መተግበር ያለባቸው እንቅስቃሴ ነው፡፡

48 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
3. ተጨባጭ የሆነ ዶክመንትን ማዘጋጀት
ሪፖርት ማለት ስለ አንድ እቅስቃሴ ጠንካራ ጎን፣ ደካማ ጎን እና እንቅስቃሴውን ስናካሂድ
የገጠሙንን ችግሮች በፅሁፍ ወይም በንግግር የምናቀርብበት ሂደት ነው፡፡ ይህንን ሪፖርት በፅሁፍ
ስናቀርብ መሥሪያ ቤቶቹ ባዘጋጁት የራሳቸው የሆነ (standard) ደረጃውን የጠበቀ ቅፅ ላይ ቢሆን
ለሪፖርቱ ጥራትና አመችነትን ሊጨምር ይችላል፡፡ ሪፖርት ሲዘጋጅ የሪፖርቱ ይዘት ትክክለኛና
ግልፅ መሆን አለበት፡፡
6. የካይዘን ፍልስፍና ምንነትና አስፈላጊነት

 የካይዘን ምንነት

(ካይ) ለውጥ፣መሻሻል

(ዘን) የተሻለ፣መልካም፣ጥሩ

ካይዘን - “የተሻለለውጥ

ካይዘንማለትየጃፓንየአሰራርፍልስፍናሆኖየአሰራርልምዶችን፣
ብቃትንወዘተበቀጣይነትለማሻሻልየሚያስችልየአሰራርፍልስፍናነው

• ካይዘንበምርትሂደትውስጥየሚታዩብክነቶችንበማስወገድወይምበመቀነስያለንንሀብትበቁጠባና
እናአዋጭበሆነመንገድለመጠቀምበሚያስችልቀጣይናየማያቋርጥየምርትጥራትናምርታማነ
ትንለማሳደግየሚያስችልአሰራርነው፡፡

• ካይዘንብክነትንበማስወገድጥራት፣
ወጪናየማስረከቢያጊዜያችንንበማሻሻልቁልፍአስተዋጽኦያደርጋል፡፡

የካይዘንአስፈላጊነት

49 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የኩባንያ ትርፍ ይሻሻላል

ተወዳዳሪነት ይጨምራል

ሥራይፈጠራል የሚከፈልግብርይጨምራል→የአገርገቢይሻሻላል

 የካይዘን ባህርያት
1. ቀጣይናየማያቋርጥ

2. ሁሉንም የሚያሳትፍ

3. ብዙ ወጪ የማይጠይቅ

4. በሁሉም የዘርፍ ዓይነቶች የሚተገበር (በፋብሪካዎች፣አገልግሎትሰጪድርጅቶች፣ወዘተ)

 የካይዘን ችግር አፈታት ዘዴ

መገንዘብ-----›ችግር መምረጥ------›ነባራዊ ሁኔታ ማጥናት------›ግብ ማስቀመጥ-----›ዕቅድ


ማውጣት-----›መንስኤዎች መዘርዘር------›መፍቴሔዎችን ማሰብና መተግበር-----›የተገኘውን
ውጤት ማረጋገጥ------›ደረጃ አዘጋጅቶ መቀጠል

 ካይዘንን ለመተግበር ምን ያስፈልጋል?


 የካይዘን ዕውቀት /Knowledge of KAIZEN / -
 ቀና አስተሳሰብ /Attitude /
 የሁሉም ተሳትፎ /involvement/
 ፍላጎትና ድጋፍ / zealous/-
 ስለካይዘን ማስተማርና መማር /education /
 ካይዘን በቀጣይነት መተግበር /never ending /

 ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች

1. ጥራት- የደንበኞችን ቅሬታ፣የተበላሸ ምርትመጠን፣የጥራትቁጥጥርዘዴ

2. ወጪ- የግብዓት አጠቃቀም፣የወጪ ቁጥጥር ዘዴ፣የጊዜ አጠቃቀም፣የምርት ወጪ

3. የምርት መጠን - የማሽኖችሁኔታ፣የሀብትአጠቃቀም

50 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
4. የማቅረቢያ ጊዜ- የሥራ ጊዜ አጠቃቀም፣የንብረት ክምችት ሁኔታ

5. የሥራ ቦታ ደህንነት- የሥራ ጫና፣የሥራ ቦታሁኔታ፣የአደጋ ሁኔታ

6. የሥራ ተነሳሽነት-በካይዘን ስራዎች የተሳትፎ ሁኔታ

7. አካባቢያችን - የውሃ አጠቃቀም፣የአየርመበከል፣የድምጽሁኔታ

 7ቱ ብክነቶች

ብክነትማለትለምንሰራውወይምለምናመርተውምርትምንምዓይነትእሴትየማይጨምሩወጪ
ንግንየሚጨምሩአሠራሮችናቸው፡፡

1. ከሚፈለገው በላይ ማምረት

2. የንብረት ክምችት

3. መጠበቅ

4. ማጓጓዝ

5. እንከን ያለው ምርት ማምረት

6. አላስፈላጊ እንቅስቃሴ

7. የአሰራር ብክነት

1. ከሚፈለገው በላይ ማምረት

በዓይነት፣በመጠንበወቅቱከሚፈለገውበላይ

መንስኤ
COS
የሰራተኞችና የማሽኖች መብዛት T

የሰራተኞችና የማሽኖች አቅም አለመመጣጠን

ያልተደላደለ የአመራረት ዘዴ

የሚያስከትላቸው ችግሮች

51 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
የምርት ክምችት

የማምረት ዕቅድ መዛባት

ግብዓትና መለዋወጫበብዛትመያዝ

ኪሳራ

የምርት መበላሸት

2. የንብረት ክምችት

መንስኤ

 ለሚከሰቱ ችግሮች ያለን ዝቅተኛ ግንዛቤ


 ጥሩ ያልሆነ አቀማመጥ
 በምርት ሂደት ውስጥ ያሉ ማነቆዎች
 ከሚፈለገው በላይ ማምረት
 ግምታዊ ትንበያ መሰረት በማድረግ ማመረት

የሚያስከትላቸው ችግሮች

 ረጅም የማስረከቢያ ጊዜ
 የቦታ ብክነት
 የማጓጓዝና የፍተሻ ሥራዎች መብዛት
 የለውጥ ሥራዎችን ማዳከም
 ካፒታል ይይዛል
 የማሽኖችና የሰዎች አቅም ለመገመት ያዳግታል

3. መጠበቅ

መንስኤ

• ጥሩ ያለሆኑ የማሽኖች አቀማመጥ

• ማነቆዎች መኖር

• በብዛት ማምረት

• የአቅም አለመመጣጠን

የሚያስከትላቸው ችግሮች

52 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
• የሰውኃይል፣የጊዜና የማሽኖች ብክነት

• በምርት ሂደት ውስጥ የክምችት መብዛት

4. ማጓጓዝ
መንስኤ
• ጥሩ ያልሆነ አቀማመጥ
• በብዛት ማምረት
• አንድ ዓይነት ሙያ ብቻ ያለው ሠራተኛ

የሚያስከትላቸውችግሮች

• የቦታ ብክነት

• ምርታማነት መቀነስ

• የጊዜ ብክነት

• ማጓጓዣ ዕቃዎች መፈለግ

5. እንከን ያለው ምርት ማምረት


o መንስኤ
o ያልተሟላ የጥራት ፍተሻና ደረጃዎች
 ደረጃ ያልወጣለት አሰራር
 ፍተሻ መጨረሻ ላይ ማካሄድ
 ከሚፈለገው ጥራት በላይ ማምረት

የሚያስከትላቸውችግሮች

• ምርታማነት መቀነስ

• ግድፈቶች መብዛት

• ቅሬታዎች መብዛት

• የፍተሸ ሂደት መዛባትና ፈታሾች መብዛት

6. አላስፈላጊ እንቅስቃሴ

53 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
መንስኤ
• ጥሩ ያልሆነ የማሽኖች አቀማመጥ
• ትምህርት/ስልጠና አለመኖር
• የተለየ ኦፕሬሽን መኖር
• ያለተደላደለ የማምረት ሂደት

የሚያስከትላቸው ችግሮች
• የሰው ኃይልና የሥራ ሰዓት መጨመር
• የሰራተኛ ክሕሎት መቀነስ
• ያለተረጋጋ ኦፕሬሽን

7. የአሰራር ብክነት

መንስኤ

• የሂደት ቅደም ተከተሎች ተንትኖ ያለማወቅ

• የሂደቶች ይዘትን ተንትኖ አለማወቅ

• ትክክለኛ ያልሆኑ ዕቃዎችና ትክክለኛ ያልሆነአጠቃቀም

የሚያስከትላቸውችግሮች

• ውጤታማአለመሆን

• ግድፈቶችንማብዛት

• የሰውኃይልንማብዛትናየሥራጊዜንማራዘም

ካይዘን ለመተገበር የሚጠቅሙ ቴክኒኮች

1. 5ቱማዎች (5S)

2. የጥራት ቁጥጥር ብዱኖች (QCC)

3. ሓሳብ መስጫ ዘዴ (Suggestion system)

4. 7ቱ የጥራት ቁጥጥር ቴክኒኮች (7 QC Tools)

5. ጂዶካ (JIDOKA)

6. ልክ በሰዓቱ (Just-in-time)

7. ካንባን (Kanban)

8. ፖካዮኬ (Pokayoke)

9. ደረጃውን የጠበቀአሰራር

54 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
10. ታክትታይነትን የተከተለ አመራረት(Takt time)

11. የተደላደለ አመራረት(Leveled Production)

 “5ቱማዎች (5S)”

1ኛማማጣራት

2ኛማስቀመጥ

3ኛማጽዳት

4ኛማላመድ

5ኛማዝለቅ

 “ የጥራት ቁጥጥር ብዱኖች (QCC) ”

• ጥቂት (ከ3-10) አንድ ዓይነት ሥራ የሚሰሩ ሰራተኞች አባል የሚሆኑበት ቡድን ነው።

• አባላቶቹ በሥራ ቦታቸው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የሚማሩበት ቡድን


ነው፡፡

• የጋራ መንፈስና በራስ መተማመንን የሚያዳብሩበት ቡድን ነው

 “ሓሳብ መስጫዘዴ (Suggestion system)”

• ሰራተኞች በቡድንም ሆነ በግል ሆነው የማሻሻያ ሓሳቦች የሚያቀርቡበት ሲሆን


ኩባንያውም የተሰጡ ሓሳቦች በመገምገምና በማወዳደር ጥሩ ሓሳብ ላቀረቡ ሰራተኞች
ሽልማት የሚሰጥበት ዘዴ ነው፡፡

• ይህቴክኒክ የሰራተኞችን ተነሳሽነትና ተሳታፊነት እንዲዳብር ያደርጋል፡፡

 7ቱ የጥራት ቁጥጥር ቴክኒኮች (7 QC Tools)

1. Check sheets- ለትንተና በሚያመች ሁኔታ መረጃ ለመሰብሰብ

2. Pareto diagram- በቅድሚያ መፈታት ያለባቸው ችግሮች ለመለየት

3. Cause and Effect diagram- የአንድ ችግር ዋናዋና መንስኤዎች ለመለየት

4. Histogram- ብዛት ያላቸው መረጃዎች በሥዕል በማስቀመጥ በቀላሉ ያልተለመደ ሁኔታ


ለመለየት

5. Scatter Diagram- የሁለት ዓይነት መረጃዎች ግንኙነት ለማወቅ

6. Control Chart - ሂደቶች ከተዘጋጀው ደረጃ ውስጥ መሆናቸውን ለመቆጣጠር

55 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
7. (Stratification) - የተሰበሰበ መረጃ በቡድን በማድረግና ለማወዳደር

56 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 ጂዶካ (JIDOKA)

ማሽኑ በራሱ ወይም በሰራተኛው እንዲቆም በማድረግ ግድፈት እንዳያልፍ መቆጣጠሪያ ዘዴ


ነው፡፡

 ልክ በሰዓቱ (Just-in-time)

• ማንኛውንም አስፈላጊ ነገር በተፈለገበት ሰዓት፣መጠንና ጥራት ማቅረብ መቻል ነው፡፡

• ይህ የአሰራር ዘዴ ቅልጥፍና የተሞላበት አሰራር አንዲኖርና የደንበኞችን ፍላጎት


ለማርካት ያስችላል፡፡

 ካንባን (Kanban)

57 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
• የመረጃ መለዋወጫ ካርድ(Kanban) በመጠቀም ስለመመረት ያለበ ትምርት መጠንን፣
ስንት መጓጓዝ እንዳለበት ወዘተ መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ቴክኒክ ነው፡፡
ከሚፈለገው በላይ ማምረት ለመከላከልና መዘግየትን ለማየት ያስችላል።የደንበኛን
ፍላጎት መሠረት በማድረግ የሚቀጥለው ሂደት ካለፈው ሂደት የሚፈልገውን ያህል
ይወስዳል።

የሚመረት ሁሉ ይሸጣል በሚል የደንበኛ ፍላጎት መሠረት ያደረገ ግምት በግፊት ማምረት

 ፖካዮኬ (Pokayoke)

የተለያዩ ምልክቶች፣መብራቶችና ሌሎች ስልቶች በመጠቀም ስህተቶች ወይም ግድፈቶች


በሰራተኞች ግድየለሽነት ወይም ትኩረት ባለመስጠት አንዳይፈጠሩ፣እንዳያለፉ በማድረግ
ጥራትን በየሂደቶች እንዲኖር የሚያደርግ ቴክኒክ ነው፡፡

• ብክነትን በማስወገድ የአሰራር ቅደም ተከተል የሚያሳይ የማምረት ሥልት ነው።


የምርት ዘዴ መመሪያዎች ግልጽ እነዲሆኑ ያደርጋል።

• ደረጃውን የጠበቀ አሰራር ሶስት ክፍሎች አሉት

– ታክት ታይም

– የሥራ ሂደቶች ቅደም ተከተል ከሚወስዱት ጊዜ ጋር

– በምርት ሂደት ውስጥ የሚያስፈልግ የክምችት መጠን

ታክት ታይምን የተከተለ አመራረት

• የደነበኞችን ትእዛዝ ለማድረስ ባለን የማምረት ጊዜና የማሽናችን ፍጥነት ምን ያህል


ማምረት አለብን የሚለውን ይመልስልናል፡፡

 የተደላደለአመራረት(Leveled Production)

58 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
 ቀጣይነት ያለው የአመራረት ሂደት
(Continuous Flow Processing)

ምርትን ከጥሬ ዕቃ እስከ መጨረሻ ሳይቋረጥ እና ሳይደናቀፍ በተከታታይ/ በቅብብሎሽ ማምረት


መቻል ማለት ነው።

59 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም
60 | P a g e ጥቅምት2011 ዓ.ም

You might also like