You are on page 1of 7

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በክላስተር-4 ኦ/ሜ ስር የሚገኘው የአዳማ 2ኛ ንፋስ ኃይል ማመንጫ


ጣ ብ ያ የ 2 0 1 5 በ ጀ ት ዓ መ ት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት

ሚያዝያ /2015 ዓ.ም

1
4. በ 2015 በጀት ዓመት የሚያዝያ ወር የአዳማ 2 ን/ኃ/ማ የአስተዳደር ስራዎች ክንውን
 በጣቢያው የውሃ ችግርን ለመቅረፍ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የቀረውን ቱቦ ለማውጣት በባለሞያዎች በተሠጠን አቅጣጫ
መሰረት 40 ጋልቫናይዝድ ቱቦ እንደሚያስፈልግ በተነገረን መሰረት ይህንኑ ከማዕከል ገንዘብ እንዲለቀቅልን ጠይቀን በመፈቀዱና
ገንዘቡ በመለቀቁ የግዢ ስራዓቱን በጠበቀ መልኩ የመግዛት ስራ ተከናውኗል፡፡

 በተሸከርካሪ ኮድ 4-27557 በተመለከተ ከአይሻ ን/ኃ/ማ/ጣቢያ በጣቢያችን በኩል እንዲጠገን ከክላስትር 4 ኦፕና ሜንቶ መምሪያ
ቢሮ ደብዳቤ በተፃፈልን መሰረት ጥገናውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ በርካታ መለዋወጫ በመኖራቸው መለዋወጫዎችን
ከክፍላችን ሰው ተመድቦ ከባለሞያዎች ጋር አብሮ በመሆን ዝርዝሩን በማዘጋጀትና መለዋወጫዎች ለመገግዛት ፕሮፎርማ
በማሰባሰብ ከማዕከል ገንዘብ ተለቆ መለዋወጫዎቹን በመግዛት ተሸከርካሪው በጥሩ ሁኔታ እንዲጠገን ከፍተኛ ርብርብ
እንደተደረገ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ተሸከርካሪው ጥገናውን ጨርሶ ወደ ሳይት በሚመለስበት ወቅት መተሃራ ከተማ ሳይደርስ
አውራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በትራፊክ ምርመራ መሰረት አደጋው የደረሰው ከጥንቃቄ ጉድለት የተነሳ በመሆኑ
በተሸከርካሪው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ ለመከታተል ጣቢያው ከአስተዳደር ክፍል አንድ ሰው እንዲሁም የአይሻ
ን/ኃ/ማ/ጣቢያ ስራ አስኪያጅ ጉዳዩን እንዲከታተሉት የተደረገ ሲሆን መተሃራ ከተማ ከሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመሄድ
ስለጉዳዩ ከፖሶች ጋር በመነጋገር ቶሎ መፍትሄ የሚያገኝበት ሁኔታ እንዲኖር በማድረግና ከመድን ኢንሹራንስ ድርጅት ጋር
በመነጋገር ተሸከርካሪው ጉዳት ከደረሰበት ስፍራ የማምጣት ስራና ለመረጃ የሚሆኑ የትራፊክ የምርመራ ውጤት እና ሌሎች
መረጃዎችን የመያዝ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በእስቶር በኩል እንደ ነዳጅ ሪፖርት፤ ወጪ ገቢ ዕቃዎችን በተገቢው ሁኔታ ቁጥጥር የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በጣቢያው የሚገኙ ተሸከርካሪዎችን በተገቢው ሁኔታ ጥገናዎችን የማድረግና ለሚመለከቱ ክፍሎች ብቁ የሆኑ ተሸከርካሪዎች
እንዲያገኙ የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ የዕድገትና ዝውውር ማስታወቂያዎች በሚኖሩበት ጊዜ ለሰራተኞች በሚታይበት ቦታ በመለጠፍ
እንዲሁም በየስራ ክፍሉ በተከፈቱ የቴሌግራም ቻናሎችን በመጠቀም እንዲደርሳቸው ማድረግና ሰራተኞች በሚያሟሉበት እና
ህብረት ስምምነቱ በሚፈቅደው መሰረት እንዲመዘገቡ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

 በጣቢያችን ሌላው በዚህም ወር ከተሰሩ ስራዎች ውስጥ እነደ አስተዳደር በስዊች ያርድ አካባቢ የበቀሉ ሳርና ሌሎች አላስፈላጊ
ተክሎችን ለቀን ሰራተኞች ኮንትራት በመስጠጥና ለዚሁ ስራ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን በማዘጋጀትና በመከታተል እንዲፀዳ
የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡

 ሠራተኞች የጤና መታወክ ሲገጥማቸው የህክምና ደብዳቤ በመሥጠት ውል ከተያዘባቸው ሆስፒታሎች እንዲታከሙ የማድረግ
ስራ ተከናውኗል፡፡

 በተሰጠው የታይም ማኔጅመንት ስልጠና መሰረት ትርፍ ሰዓት በሲስተም ያለምንም ችግር እንዲገባ የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በተለያዩ ጊዜያት ከሰራተኞች ለሚመጡ ቅሬታዎች ተገቢውን መልስ/ምላሽ የመስጠት ስራ ተከናውኗል፡፡

 ሰራተኛው ከስራው ጎን ለጎን ማህበራዊ ህይወቱንም ሊጠቅም የሚችልበትን እንቅስቃሴ ማድረግና እርስ በእርሱ ሊያቀራርብ
የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ቀጣይነት ያለው ተግባር በመሆኑ በዚህም ወር ይህንኑ ተግባር የማስቀጠል ስራ ተከናውኗል፡፡

 የጣቢው ግቢ ንፁህና ፅዱ በማድረግ ለሰራተኛም ሆነ ለጉብኝት ለሚመጣው ሰው ጥሩ የሆነና ለዐይን የሚስብ የማድረግ ስራ
ተከናውኗል፡፡

 ተሸከርካሪዎች ለጥገና በሚሄዱበት ወቅት ከፋይናንስና ከአስተዳደር ክፍል ሰው ተመድቦ እንዲጠገን የማድረግ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በጣቢያው የሾፌር እጥረት በመኖሩ ከሌላ ክፍል በመጠየቅ የሰው ኃይሉ እስኪሟላልን ድረስ በአበል የማሰራት ስራ በዚህም ወር
ተከናውኗል፡፡

4.1 የ 2015 ዓ.ም የሚያዝያ ወር የአዳማ 2 ኛ ን/ኃ/ማ/ጣቢያ የተከናወኑ ዋና ዋና የአስተዳደር ሥራዎች


 አጠቃላይ የድርጅቱን/የጣቢያውን ንብረት በአግባቡ እንዲያዝ ማድረግና መቆጣጠር ፡፡

 አጠቃላይ የድርጅቱን/የጣቢያውን ተሸከርካሪዎች ጥገና እንዲሁም የተሻለ የተሸርካሪ ስምሪት እንዲኖር ማድረግ፡፡

 በ 2015 በጀት ዓመት የ 4 ኛ ሩብ ዓመት ለጣቢያው የሚያስፈልገውን በቂ የሰው ኃይል ፍላጎት መጠየቅና እንዲሟላ ክትትል
ማድረግ፡፡

2
 ወራዊ ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፤ እንዲሁም ወቅታቸውን ጠብቀው ሪፖርት ለሚፈልጉ የተለያዩ ክፍሎች ለምሳሌ ፤-ለፍሊት
አስተዳደር ቢሮ፤ለንብረት አስተዳደር ቢሮ ፤ለአይ.ኤፍ.አር. ኤስ እና ለመሳሰሉት ክፍሎች በወቅቱ ሪፖርት የማድረግ ስራም በዚህ
ወር ተከናውኗል፡፡

 የተለያዩ ሕክምና ፤የጋራዥ እንዲሁም የቀን ሰራተኞች ክፍያ ማዘጋጀት እንዲሁም ክፍያው እንዲፈፀም ክትትል ማድረግ፡፡

 አጠቃላይ የሰራተኞችን ትርፍ ሰዓትን በጥንቃቄ መሙላት እና የጣቢያው ሐላፊ እንዲያረጋግጥ በማድረግ ወደ ፔይሮል እንዲሄድ
ማድረግ እና ለመረጃ ይረዳ ዘንድ የተሞላው ትርፍ ሰዓት ዳታ ፕሪንት በማድረግ በተገቢው መልኩ ማስቀመጥ፡፡

 የጣቢያው ግቢ ንፅህና እና ፅዳት በተገቢው ሁኔታ መከታተልና የተተከሉ ችግኞችም በየወቅቱ በቂ እንክብካቤ እንዲያገኙ
ማድረግ፡፡

 የአስተዳደር ሰራተኞችን መግቢያና መውጫ ሰዓትን በአግባቡ መቆጣጠር፡፡

 በጣቢውያው የእርስ በእርስ ግንጉነቶች እንዲጠናከሩ ማስድረግ፡፡

 በጣቢያው ግቢ ውስጥ የገባውን ነዳጅ ልዩ ትኩረት በመስጠት ቁጥጥር ማድረግ እና አላስፈላጊ ምልልሶችን በመቀነስ
የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመቆጣጠር ወጪን በቀነሰ መልኩ ስራን መስራት ማስቻል፡፡

 የተለያዩ በጣቢያችን ለሰራተኞች ህክምናም ሆነ ለተሸከርካሪ ጥገና እንዲሁም ሌሎችን ዉሎች መያዝ አስፈላጊ በሚሆንባቸው
ጊዜዎች ውሎችን ማዘጋጀትና ተገቢውን አካሄድ በመከተል ውል እንዲያዝ ማድረግና መከታተል፡፡

 ሌላው ወቅቱን ጠብቀው የሚታደሱ ከተሸከርካሪዎች ጋር በተገናኘ እንደ ተሽከርካሪን ማስመርመር፤ ቦሎ መለጠፍ፤ሶስተኛ ወገን
መለጠፍ እንዲሁም ከይዞታ ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ ጊዜውን ጠብቆ የመሬት ግብር እንዲከፈል ማድረግና መከታተል፡፡

 ከማእከል በተሰን አቅጣጫ መሰረት ለተሸከርካሪዎች ጥገና የሚሆን አራት በርሜል 40 ቁጥር የሞተር ዘይት አዲስ አበባ
ከሚገኘው ዋናው እስቶር የመረከብ ስራ ተከናውኗል፡፡

 በ 2015 በጀት ዓመት የ 4 ኛ ሩብ ዓመት ለጣቢያው የሚያስፈልገውን በቂ ሶፍት እና ሳሙና ጠይቀን የማምጣት ስራ እና
በጣቢያችን ስቶር የማስገባት ሰስራ ተከናብኗል፡፡

2 በ 2015 በጀት ዓመት የሚያዝያ ወር በአዳማ 2 ኛ ንፋስ ኃ/ማ/ጣቢያ የተከናወኑ የአስተዳደር ስራ አፈፃፀም

የአስተዳደር ስራዎች አመላካች ዝርዝር ዕቅድ(በቁጥር) ክንውን(በቁጥር) አፈጻጸም (%)


የአስተዳደርና ንብረት አገልግሎት የተከናወኑ ስራዎች

1 12 13 108.33%

የተለያዩ ስልጠናዎች

3 የሰው ኃይል ፍላጎት ማሟላት

3
6.የአዳማ 2 ኛ ንፋስ ኃይል ማመንጫ አስተዳደር ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች

8 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣብያ ሠራተኞች የስራ ላይ ስልጠና እና በመዓከል የተሰጡ ስልጠናዎችን በተመለከተ
የኃይል ማመንጫው የተሰጠ የስራ ላይ ስልጠና ስልጠናው የሚወስደው ሥልጠና የወስዱ
ስም ጌዜ በቀን (በሰዓት) ሰራተኞች ቁጥር

አዳማ 2 ኛ
ን/ኃ/ማ/ጣ

9.የአዳማ 2 ንፋስ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣብያ የሰው ኃይል ሥራዎች አፈፃፀም
13. በአዳማ 2 ኛ ን/ኃ/ማ/ጣብያ በ 2015 በጀት የሚያዝያ ወር የተመዘገቡ ስኬቶች

 በጣቢያው የውሃ ችግርን ለመቅረፍ በውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ የቀረውን ቱቦ ለማውጣት በባለሞያዎች በተሠጠን አቅጣጫ
መሰረት 40 ጋልቫናይዝድ ቱቦ እንዲገዛ መደረጉ እንደትልቅ ስኬት የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ቀጣይ ስራውን ለመስራ በእጅጉ
ይረዳል፡፡

14.በአዳማ 2 ኛ ን/ፋ/ኃ/ማ/ጣብያ የ 2015 በጀት የሚያዝያ ወር በእቅድና በአፈፃፀም ያጋጠሙ ችግሮች


 የውሃ እጥረት ትልቁ ችግር ነው
 በጣቢያው ለጥበቃ አገልግሎት የሚሆን መሳሪያ አለመኖር ነው፡፡

15.የተወሰዱ የመፍትሄ/የማሻሻያ እርምጃዎች


 አልፎ አልፎ የሚመጣውን ውሃ በታንከር ውስጥ በማጠራቀም ለጊዜውም ቢሆን ሰራተኞች ውሃ እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል፡፡

16. በቀጣይ ግንቦት ወር 2015 በጀት አመት በአዳማ 2 ኛ ን/ኃ/ማ/ጣብያ አፈፃፀም ለማፋጠን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

 የውሃውን ጉዳይ በተመለከተ ከማዕከል በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት

 የጥበቃ የጦር መሳሪያ ጉዳይ ሌላው ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡

 በጣቢያው የተሸከርካሪ ጥገና በለሞያዎች እንዲኖሩ ማድረግና ለዚህም የሚሆን ዎርክ ሾፕ ማደራጀት

 በጣቢያው የቅድመ ህክምና ማግኛ ማዕከል የሚኖርበት ሁኔታ ቢመቻች

4
ለኦፕሬሽን
አስቸጋሪ
የሆኑ ችግሮቹ ሊፈቱበት የሚችሉበት
ሲስተሞችን አግባብ (ምክረ ሃሳብ)
በማጥናት
የተሻለና ፈታኝ የሆኑ የችግሮቹ መንስኤ የሚፈቱበት
ውጤታማ ችግሮች ደረጃ
አሰራር
ማዳበር
ተቁ
የውሃ ችግር 1. ውሃው የሚመጣው ከ በመዓከል 1. እንደ መፍተሄ የታየው
1 አንድ አቅጣጫ ብቻ የመጀመሪያው አማራጭ
በመሆኑ ውሃው ከሌላ አቅጣጫ
2. የውሃውመስመር የሚመጣበትን ሁኔታ
የተዘረጋው በገበሬ ማመቻቸት፡፡
መሳ ውስጥ ከመሆኑ 2. የነበረውን አሮጌ የውሃ
ጋር ተያይዞ ገበሬው መስመር በአዲስ መልኩ
መሬቱን በሚያርስበት በመዘርጋትናከገበሬው
ወቅት የውሃ ማሳ ውጪ
መስመሩን በማፈንዳት የሚመጣበትን መንገድ
ለሌላወጪእየዳረገ እንደ ሁለተኛ መፍትሄ
ይገኛል፡፡ ሊቀመጥ ይችላል
3. የ መ ስ መ ሩ ማ ር ጀ ት 3. ኘባሩን የውሃ ጉድጓድ
ተገቢውን ጥገና
ማከናወን፡፡
4. አዲስ የውሃ
ጉድጓድ ማስቆፈር

2 የተሸከርካሪ በመዓከል 1. ለችግሩ ትኩረት


እጥረት ጉዳይ በመስጠት መፍትሄ
ከሚመለከተው ክፍል
ቢሰጥ
የጥበቃ መሳሪያ በመዓከል 1. በስራ አስፈፃሚ በኩል
ያለመኖር 1. በተደጋጋሚ ተጠይቆ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት
3 ችግር መህትሄ ቢበጅለት ጥሩ
ያልተፈታ/ያልተመለሰ
ነው፡፡
ጉዳይ ነው

17. ማጠቃለያ

ባሳለፍነው የሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም በጣቢያችን እንደ አስተዳደር ክፍል የተሠሩ በርካታ ስራዎች እና በየዕለቱ የማይቋረጡ
ስራዎች ከመኖራቸውም ጋር ተያይዞ ለክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን በመስጠት በቂ ተሸከርካሪ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ
እንዲሁም ከላይ በተከናወኑ ስራዎች ስር በተገለፀው መሰረት ከእቅዶቻችንን በመነሳት የተለያዩ ስራዎችን ለማከናወን ተችሏል፡፡

ስለሆነም በቀጣይም ወራት ይህንኑ ስራ ትኩረት በመስጠት ሳይንሳዊና ሲስተማቲካሊ በሆነ መንገድ ስራዎችን ለመስራ ጥሩ
የሚባል ተነሳሽነት ያለን መሆኑና ጣቢያችን ብሎም ክፍላችን ባስቀመጠው እቅድ መሰረት እንደ አስተዳደር ትኩረት ሰጥተን
የምንሰራ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

5
6
1

You might also like